Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

አይሲኤስ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ጭካኔያዊ ግድያ ለመቃወም ሰልፍ የወጣው ናትናኤል 3 ዓመት ከ 3 ወር ተፈረደበት

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው የኢትዮጵያ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን የጭካኔ እርምጃ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የታሰረው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደበት፡፡ ዛሬ 25/2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውን ያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩን ገልጾአል፡፡
nat
በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት…›› የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል፡፡

በተመሳሳይ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንጋይ በመወርወር ሰልፉን አውካችኋል›› የተባሉ ሌሎች አምስት ወጣቶች ለሰኔ 4 የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ተቀጥረዋል፡፡ በሰልፉ ሰበብ ተይዘው የታሰሩት ወጣቶች በቤተሰብ እንዳይጠየቁ መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

The post አይሲኤስ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ጭካኔያዊ ግድያ ለመቃወም ሰልፍ የወጣው ናትናኤል 3 ዓመት ከ 3 ወር ተፈረደበት appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>