Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

የመንግስት ሠራተኞች የደሞዝ ጭማሪ ለሐምሌ ወር አልደረሰም

$
0
0

“ከተፈቀደበት ጊዜ አንስቶ ጭማሪው ተሠልቶ ይከፈላል”

    birr-cover  ለመንግስት ሠራተኞች ከሃምሌ ወር ጀምሮ የደሞዝ ጭማሪ ይደረጋል ቢባልም ጭማሪው ከሐምሌ ወር ደሞዝ ጋር ባለመሰጠቱ ሠራተኞች ቅር የተሰኙ ሲሆን የሲቪል ሠርቪስ ሚኒስቴር በበኩሉ፤ የደሞዝ ጭማሪው እየተሰራ መሆኑን ጠቁሞ፣ የሃምሌ ወሩ ጭማሪ ቃል በተገባው መሠረት ተሰርቶ ባለቀ ጊዜ ተሰልቶ ይከፈላል ብሏል፡፡ ከሐምሌ 1 ጀምሮ ጭማሪው ተግባራዊ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ፣ በጉጉት ሲጠብቁት እንደነበር የተናገሩ የመንግስት ሠራተኞች፤ ደሞዝ ሲቀበሉ የተባለው ጭማሪ አለመታከሉ በኑሮአቸው ላይ ጫና እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡ በአንድ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በግዥ ኦፊሠሪነት የሚሰራ አንድ ወጣት የደሞዝ ጭማሪውን አስመልክቶ በሰጠው አስተያየት፤ “መንግስት አስቀድሞ ደሞዝ ሊጨምር መሆኑን በማወጅ በመንግስት ሠራተኛውም ሆነ በሌላው ህብረተሰብ ላይ ከቤት ኪራይ ዋጋ ጭማሪ አንስቶ የኑሮ ውድነት እንዲፈጠር የቅስቀሳ ስራ መስራቱ አግባብ አልነበረም” ብሏል፡፡ አብዛኛው ሠራተኛ ጭማሪውን በወሩ መጨረሻ ላይ ጠብቆት እንደነበረ የገለፀው ሌላው አስተያየት ሰጪ፤ ጭማሪው ከወዲሁ ተግባራዊ ቢደረግ ኖሮ፣ ነጋዴው በሸቀጦች ላይ ያደረገውን የዋጋ ጭማሪ ለመቋቋም ያስችል ነበር ብሏል፡፡

ነጋዴዎች ያደረጉትን የዋጋ ጭማሪ ወደነበረበት እንዲመልሱ መንግስት እርምጃዎችን እየወሰደ ቢሆንም ውጤታማ አልሆነም፤ ይህ ደግሞ የመንግስት ሠራተኛውን ይበልጥ ተጐጂ ያደርገዋል ሲል ተናግሯል፡፡ የሲቪል ሠርቪስ ሚኒስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ አቶ መሐመድ ሰይድ፤መንግስት ለሠራተኛው ከሃምሌ 1 ቀን 2006 ዓ.ም ጀምሮ ደሞዝ እንዲጨመር መፍቀዱን አስታውሰው፣ ቀን ባይቆረጥለትም ዝርዝር ሁኔታው ተሰርቶ እንደተጠናቀቀ ከተፈቀደበት ጊዜ አንስቶ ጭማሪው ተሠልቶ ተግባራዊ ይደረጋል ብለዋል፡፡

ምንጭ፥ -አዲስ አድማስ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>