Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

በባህርዳር ከተማ በንፁሀን ዜጎች ላይ ዘግናኝ ጭፍጨፋ ያደረሱ በህግ ፊት ይቅረቡ! –ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በትናንትናው ዕለት ታህሳስ 10/ 2007 ዓም በባህርዳር ከተማ መንግስት ኃይሎች የጥምቀት ክብረ በዓል ታቦት የሚያርፍበትን ቦታ ሊፈርስ ነው በመባሉ ምክንያት ስሞታ ለማሰማት ወደ አስተዳደሩ ጽ/ቤት ያመሩ ንፁሃን ዜጎች ላይ የመንግስት ኃይሎች የወሰዱትን የግዲያና የድብደባ ህገወጥ ተግባር ያወግዛል።

ኢህአዴግ ቤተ እምነቶችን በየምክንያቱ መዳፈር የጀመረው ዛሬ አይደለም፤ መንግስተ በሃይማኖት ጉዳይ ላይ ጣልቃ አይገባም የሚለውና የሀይማኖት ነፃነት ማክበር ሲገባው፤ ስለኃይኖታቸው ጥያቄ የሚያነሱትን ዜጎች መግደል፣ ማሰርና ማሳድድ ተያይዞታል። ከአሁን በፊት በሞስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የፈፀመውን ግፍና የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ አሁን ደግሞ በባህር ዳር ከተማ የኦርተዶክስ ኃይማኖት ተከታዮች ላይ የወሰደው የኃይል እርምጃ ለሰው ህይወት መጥፋትና ለአካል መጉደል ምክንያት ሆናል፤ አንድነት በዚህ ጭፍጨፋ ህይቀታቸውን ያጡ ዜጎች ቤተሰቦች መፅናናትን እየተመኘ፤ እነዚህ ወንጀሉን የፈፀሙ፣ ያዘዙና ያስፈፀሙ አካላት በየደረጃው በህግ ፊት ቀርበው እንዲጠየቁ ለማድረግ አስፈላጊውን ትግል የምናደርግ መሆናችን ለማሳወቅ እንፈልጋለን።

ድል የህዝብ ነው!

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
ታህሣሥ 11 ቀን 2ዐዐ7 ዓም
አዲስ አበባ

UDJ


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>