Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

የነዋይ ደበበ የተበደረውን ገንዘብ አለመክፈል ክስ; የከሳሽ ማስረጃዎች እና የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ዶክመንቶችን ይዘናል

$
0
0

neway3
(ዘ-ሐበሻ) አቶ ኤፍሬም ኤርሚያስ የተባሉ ግለሰብ ለአርቲስት ነዋይ ደበበ ያበደርኩት ገንዘብ አልተመለሰልኝም ሲሉ ክስ መመስረታቸውን ዘ-ሐበሻ ከዚህ ቀደም መዘገቧ አይዘነጋም:: ዛሬ ደግሞ ይህን ዜና የሚያጠናክሩ ማስረጃዎችን አግኝተናል::

ነዋይ ደበበ ገንዘቡን የተበደረው ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ ለመግባት በወሰነበት ጊዜ እዚህ አሜሪካ ውስጥ ያለበትን ዕዳ ለመክፈል ሃገር ቤት ከሚገኘው ከሳሽ ነው:: ከታች የከሳሽን ደብዳቤ ስለምታነቡት መረጃው ብዙ ይነግራችኋል::
የፌደራሉ ፍትሐ ብሔር ችሎት በአርቲስት ነዋይ ደበበ ላይ የንብረት እግድ ያስተላለፈበት ደብዳቤ የሚከተለው ሲሆን:-

IMG_4171

IMG_4172

የፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ እንደሚያሳየውም ነዋይ ደበበ ቤቱ እንዳይሸጥ እንዳይለወጥ መታገዱን ነው:: ከሳሽ እንዳቀረበው ማስረጃ ከሆነ ወ/ሮ አምሮት ደግፌ የተባሉ ወ/ሮ ለነዋይ ደበበ 20 ሺህ ዶላር እንደተቀበሉለትና በእማኞች ፊት መፈረማቸውን ነው:: ወ/ሮ አምሮት ለነዋይ ገንዘቡን ተቀብያለሁ ብለው የፈረሙበት ማስረጃ የሚከተለው ነው::

IMG_4173

 

ቀጣዩ ማስረጃ የሚያሳየው ደግሞ አበዳሪው አቶ ኤፍሬም ኤርሚያስ ለምን ገንዘቡን ለነዋይ ደበበ እንዳበደሩትና እንዲመልስ የጠየቁበት ደብዳቤ ነው:: በደብዳቤው ላይ እንደሚለው ጉዳዩ “በብድር የወሰድከውን ገንዘብ እንድትመልስ በፍ/ብ/ሕ/ቁ 1773/1/ መሰረት ማስጠንቀቂያ ስለመስጠት” ይልናል “እኔ ኤፍሬም ኤርሚያስ ካንተ ጋር በነበረኝ መልካም ግንኙነትና ወዳጅነት ምክንያት ሚያዝያ 6 ቀን 2007 ዓ.ም አሜሪካ ሁነህ ወደ ኢትዮጵያ ለመመለስ አሜሪካን አገር ያለብኝን ዕዳ መክፈል ይኖርብኛል:: በመሆኑም ለጊዜው ገንዘብ ስለሌለኝ አበድረኝ በማለት በስልክ ከጠየቅኸኝ በኋላ አከፋፈሉንም በሚመለከት ገንዘቡን ለወ/ሮ አ እምሮት ደግፌ ስጥልኝ ለሳ እንደሰጠሃት እኔ እዚሁ አሜሪካን ሃገር ካሉ ከሷ ዘመዶች ገንዘቡን እቀበላለሁ በማለት ስትጠይቀኝ በ እምነት ከባህሬን እንደመጣው ወደ ቤቴ እንኳን ሳልገባ ወዲያውኑ በ እጄ ይዤው የነበረውን $20,000 (ሃያሺህ ዶላር) በ እማኞች ፊት ለወ/ሮ አ እምሮት ደግፌ ዲክሌር አስደርጊ ብዬ የሰጠሗት መሆኑ ይታወቃል::
” ይሁን እንጂ ከላይ በብድር የሰጠሁህን ገንዘብ አመስግነህ ልትመልስልኝ ሲገባ ለልፉት 7 ዓመታት ገንዘቡን ልትመልስልኝ አልቻልህም:: እኔም በሆደ ሰፊነት የነበረንን ወዳጅነት ላለማጣት እና በመሃላችን የነበረውን መልካም ግንኙነት ላለማሻከር በማሰብ ጉዳዩን ወደ ፍርድ ቤት ከመውሰድ ይልቅ በሽማግሌ ታይቶ ገንዘቤን እንድትመልስልኝ ሽማግሌ ብልክም እወነቱን ወደጎን በመተው እና ገንዘቡ መቀበልህን ሳትክድ ሌሎች ከጉዳዩ ጋር ፍጹም ግንኙነት የሌላቸውን መልሶች በመስጠት እስካሁን በፈቃደኝነት ልትመልስልኝ አልቻልክም::

በመሆኑም አሁንም የተበደረከውን ገንዘቤን በ5 ቀን ውስጥ እንድትመልስልኝ በጥብቅ እየጠየቅሁ ይህ የማይሆን ከሆነ ግን ፍርድ ቤት ከስሼ ለፍርድ ቤት ክፍያ; ለጠበቃ እና ለሌሎች ወጪዎች ያወጣሁትን ገንዘብ ጭምር የምቀበል መሆኑን በመግለጽ ይህን የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ በፍ/ህ/ቁ 1773/1 መሰረት ሰጥቼሃለሁ::

ከሰላምታ ጋር ኤፍሬም ኤርምያስ” ይላል::

 

 

IMG_4174

IMG_4175


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>