Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

የህገ ወጡ የፌደራል መጅሊስ አመራሮች የመንግስት ባለስልጣናትን በመዞር እያናገሩ መሆናቸው ታወቀ

$
0
0

mejlis

አቡ ዳውድ ኡስማን

የህገ ወጡ የኢትዬጲያ እስልምና ጉዳዬች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ሼኽ ኪያር መሃመድ አማን እና ዋና ጸሃፊው መሃመድ አሊ የመንግስት ባለስልጣናትን በመዞር እያናገሩ መሆናቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡

በፌደራሉ መጅሊስ የስራ አስፈፃሚ አባላት እና በስሩ ባሉ የመጅሊሱ መዋቅር ውስጥ በመንግስት የተሾሙት አመራሮች ለሁለት ቡድን ተከፍለው ከፍተኛ የስልጣን ሹክቻ ውስጥ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

በመንግስት ሾሚነት በቀበሌ በተመርጡት ካድሬዎች እንዲመራ የተደረገው ህገ ወጡ መጅሊስ የመንግስትን እቅድ ከማስፈፀም ይልቅ እርስ በእርስ በሚያደርጉት የስልጣን ሽኩቻ ጊዜያቸውን እየፈጁ በመሆናቸው መንግስት ጣልቃ በጉዳዩ ላይ ገብቶ ሁሉንም የስራ አስፈፃሚ አባላት በመቀየር ሌላ አዲስ የስራ አስፈፃሚ ማስመረጥ አለበት የሚል ሃሳቦች እየተነሱ በመምጣታቸው በሼኽ ኪያር የሚመራው ቡድን በየመንግስት ባለስልጣናት ቢሮ በመዞር ጉዳዩን በማስረዳት ተማፅኖ እያቀረበ መሆኑ ታውቋል፡

በመንግስት ሾሚነት በቀበሌ በተመርጡት ካድሬዎች እንዲመራ የተደረገው ህገ ወጡ መጅሊስ የመንግስትን እቅድ ከማስፈፀም ይልቅ እርስ በእርስ በሚያደርጉት የስልጣን ሽኩቻ ጊዜያቸውን እየፈጁ በመሆናቸው በሼኽ ኪያር የሚመራው ቡድን በየመንግስት ባለስልጣናት ቢሮ በመዞር ችግሩን እያስረዳ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡

በሼህ ኪያር የሚመራው ቡድን የአህባሽን የግዳጅ ጠመቃ መካሄድ የለበትም ፣ ሙስሊሙን በቀጥታ የሚያስቆጣ ተግባር በመጅሊሱ መሰራት የለበትም፣ሙስሊሙን አንድ አድርገን በማቻቻል ለኡማው የሚጠቅም ስራዎች እንስራ የሚል አቋም ያላቸው ሲሆን በዶ/ር ሽፈራው በሚደገፈው የአህባሽ አቀንቃኞቹ የታጋይ ሼህ ከድር እና የአዲስ አበባው መጅሊስ ፕሬዝደንት የዶ/ር አህመድ ቡድን ደግሞ የዶ/ር ሸፈራውን እቅድ ሙሉ በሙሉ ማስቀጠል አለብን በሚል ከፍተኛ ፀብ ውስጥ መግባታቸው የሚታወስ ነው፡፡

ይህንንም ሹክቻ ተከትሎ በዶ/ር ሽፈራው የሚደገፈው የአህባሾቹ ቡድን ሼኽ ኪያር እና መሃመድ አሊ ዋሃቢያ ናቸው፣መንግስት እየታገለ የሚገኘውን የአክራሪዎች እንቅስቃሴ ይደግፋሉ በሚል መፈንቅለ ስልጣን በሼኽ ኪያር ላይ ለማካሄድ ሙከራ አድርገው የነበረ ሲሆን የስራ አስፈፃሚው አባላት ለሁለት በመከፈላቸው መፈንቅሉ ሳይሳካ በሼኽ ኪያር ቡድን አሸናፊነት ውዝግቡ ተጠናቆ ነበር፡፡

ሼኽ ኪያር መፈንቅለ ስልጣን ለማካሄድ የሞከሩበትን ምክትል ፕሬዝደንቱን ታጋይ ሼኽ ከድርን ጨምሮ ዶ/ር አህመድን እና 2 ተጨማሪ የስራ አስፈፃሚ አባላትን ከጠቅላላ ጉባኤው እና ከስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው አግዷቸው እንደነበር የሚታወስ ነው፡፡

በሁለቱ ቡድኖች የነበረውን ሽኩቻ ተከትሎ ሼህ ኪያር ለተለያዩ የመንግስት ሚኒስተር መስሪያ ቤቶች እና የደህንነት ቢሮዎች በዶ/ር ሽፈራው የሚደገፈው አህባሻዊው የሼህ ከድር ቡድን ጸረ ሰላም የሆነ አጀንዳ ይዞ በመንቀሳቀስ ረገብ እያለ ያለውን የሙስሊም ማህበረሰብ ወደ ልማት ፊቱን እንዳያዞር እንቅፋት በመሆን ሙስሊሙ ማህበረሰብን ዳግም ወደ ቁጣ እና ተቃውሞ በማስገባት የሃገሪቷን ሰላም አደጋ ውስጥ እየጣሉ ናቸው ብሎ በመወንጀል ደብዳቤ መፃፉ የሚታወስ ነው፡፡

ይህ ልዩነታቸው እየተካረረ መጥቶ እስካሁን ምንም መፍትሄ ያልተበጀለት ሲሆን ሼህ ኪያር እና ዋና ጸሃፊው መሃመድ አሊ በተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች በመዞር ጉዳዩን በማስረዳት መንግስት እርምጃ እንዲወስድባቸው ተማፅኖ እያቀረቡ መሆናቸው ተሰምቷል፡፡

ከ5 ቀናት በፊት የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝደንት ወደ ሆነው አቶ ሙክታር ከድር ጋር ሼኽ ኪያር እና መሃመድ አሊ በመሄድ እየተመላለሱ ያናገሩት ሲሆን ከሳምንት በፊት ደግሞ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወደ ሆኑት አቶ ተገኔ ጌታነህ ጋር መሄዳቸው ታውቋል፡፡ የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ወደሆኑት አቶ ተገኔ ጌታነህ ጋር ሲመላለሱ የነበረበት ምክንያት እስካሁን በግልፅ አልታወቀም፡፡

በተመሳሳይም ከሳምንት በፊት ወደ አዲስ አበባ ከንቲባ ወደሆኑት አቶ ድሪባ ኩማ ጋር በመሄድ እየተነጋገሩ ሲመላለሱ የቆዩ ሲሆን በትላንትናው ዕለት ዕለተ ረቡዕ ጥር 6 ከረፋዱ 5 ሰአት አካባቢ ደግሞ ጠ/ሚኒስተር ኃ/ማርያም ደሳለኝን ለማነጋገር አራት ኪሎ ወደሚገኘው የጠቅላይ ሚኒስተሩ ቢሮ መሄዳቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ከጠ/ሚኒስተር ኃ/ማርያም ደሳለኝ ጋርም በበርካታ ጉዳዬች ላይ ውይይት ማካሄዳቸው የተገለፀ ሲሆን በዋነኝነትም በሼኽ ኪያር የታገዱት የስራ አስፈፃሚ አባላት በተለይም የአዲስ አበባው ህገ ወጥ መጅሊስ ሰብሳቡቢ ዶ/ር አህመድ እጅግ አስቸጋሪ መሆናቸውን እና በሙስና የተዘፈቁ መሆናቸውን ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ማስረዳታቸው ታውቋል፡፡

በተለይም በአንዋር መስጂድ ዙሪያ የተሰሩ ሱቆችን በህገ ወጥ መንገድ ሽጠዋል በማለት መንግስት ይህን እያወቀ አስቸኳይ እርምጃ ሊወስድባቸው ይገባል ሲሉ መጠየቃቸው ታውቋል፡፡

በተጨማሪም የኡለማ ምክር ቤት አመራሮች ከተሰጣቸው ሃላፊነት ውጪ በመውጣት በፌደራሉ መጅሊስ ውስጣዊ ጉዳዬች ላይ እየገቡ መሆናቸውን ለጠቅላይ ሚኒስተሩ ማስረዳታቸውን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

የህገ ወጡ ኡለማ ምክር ቤት አመራር ናቸው ተብለው በመንግስት የተሾሙት ግለሰቦችም ሰሞኑን በሸገር ኤፍ ኤም ሚዲያ ላይ በመቅረብ የመጅሊሱ አመራሮችን እና ስራ አስፈፃሚ አካላቱ ምንም ስራ እየሰሩ አለመሆናቸውን በአደባባይ ያብጠለጠሏቸው ሲሆን ህዝብ የመረጣቸውን አላማ በመዘንጋት እርስ በእርስ የስልጣን ሽኩቻ ውስጥ በመግባት ለሙስሊሙ፣ ለመንግስት እና ለሃገር ሰላም አደጋ ከመሆናቸው በፊት የመጨረሻ የእርቅ ሙከራ ለማደረግ እንደሚንቀሳቀሱ መግለፃቸው ይታወሳል፡፡

ሼኽ ኪያር እና ዋና ፀሃፊው መሃመድ አሊ ከጠ/ሚኒስተሩ ጋር በነበራቸው ውይይት ወቅት በዋነኝነት ህገ ወጡ መጅሊስ በግንቦት ወር ስለሚካሄደው ሃገራዊ ምርጫ ከጠ/ሚኒስተሩ በኩል ሙስሊሙን እንዴት መቀስቀስ እንዳለባቸው የስራ መመሪያ የተቀበሉ ሲሆን እነ ሼኽ ኪያርም የምርጫ ታዛቢዎችን በማስመረጡ ሂደት ላይ ለመሳተፍ ፍላጎቱ እንዳላቸው መግለፃቸው ተሰምቷል፡፡ ይህንንም ተከትሎ የምርጫ ታዛቢዎችን እንዲመርጡ የተነገራቸው ሲሆን ህገ ወጡ መጅሊስም የምርጫ ታዛቢዎችን ለማስመረጥ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በሼኽ ኪያር የሚመራው ቡድን ከተለያዩ የመንግስት ባለስልጣናት ጋር ያካሄደው ውይይት ውጤታማ እንደነበር ሼኽ ኪያር መናገሩን የውስጥ ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በመንግስት በግዳጅ በቀበሌ የተመረጡት አመራሮች ከፌደራሉ መዋቅር ጀምሮ እስከታች ድረስ ባለው መዋቅር አመራሮቹ በሙሉ በጥቅም እና በስልጣን እየተፋጁ እርስ በእርስ ሲካሰሱ እና አንዱ አንዱን ሲያግድ መክረማቸው የሚታወስ ነው፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>