Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

በሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ በመብራት እጦት የግል ድርጅቶች ለኪሳራ እየተዳረጉ ነው * ለ4 ቀናት መብራት የጠፋባቸው ቦታዎች አሉ

$
0
0

Zehabesha News
በሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ በተከሰተ የመብራት መቋረጥ ምክንያት በመብራት የሚሰሩ የግል ድርጂቶች ለኪሳራ መዳረጋቸውን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቹን ጠቅሶ የደህሚት ድምጽ ዘገበ::

በራዲዮው ዘገባ መሰረት በጂግጂጋ ከተማ  የሚገኙ ከ12 ቀበሌ በላይ ህዝቦች ከዚህ በፊት መቆራረጡን ለመቀነስ እንደመፍትሄ በፈረቃ ይጠቀሙ የነበሩ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ከቀበሌ 1 እስከ ቀበሌ 5 ያሉት ነዋሪዎች  ለ6 ሰዓታት በአንድ ቡድን ከቀበሌ 5 እስከ ቀበሌ 9 የሚገኙት ደግሞ በተመሳሳይ በሌላ ፈረቃ እንዲሁም 3 ቀበሌዎች የመብራት ተጠቃሚ አይደሉም::

ይህ በእንዲህ እንዳለም በፈረቃ ይጠቀሙ የነበረው መብራት ከነጭራሹ ከጠፋ 4 ቀናት ያስቆጠረ መሆኑንና በዚህ ሳቢያም በግል ወኪልነት የሚንቀሳቀሱ ድርጂቶች ለኪሳራ መጋለጣቸውን በምሬት ተናግረዋል።

በሌላ በኩል በሶማሌ ክልል የሶማል ተወላጅ ወጣቶችና ሃበሻ በሚል የሚጠሯቸው በርካታ ነዋሪዎች ለምርጫ ከተመዘገቡ በኋላ ተወዳዳሪ በሌለበት አንመርጥም ብለው በግልፅ በመናገራቸው እየታሰሩ መሆናቸውን ያይን እማኞች ከስፍራው ገልፀዋል።

The post በሶማሌ ክልል ጂጂጋ ከተማ በመብራት እጦት የግል ድርጅቶች ለኪሳራ እየተዳረጉ ነው * ለ4 ቀናት መብራት የጠፋባቸው ቦታዎች አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>