ከኢሳት ጋር የሰጡትን ቃለ መጠይቅ አዳመጥኩ። ከዚህ ሁሉ ዓመት አስራት በኋላ አንዲህ አይነት ብሄርተኝነት የተሞላበት አቋም ይዘው ብቅ አንደማይሉ ትንሽም ብትሆን ተስፋ ነበርረኝ። አስር ቤት ሆነው አብረዋቸው የነበሩት ከተለያዩ ብሄር የተውጣጡ አስረኞች ጋር ከርመው አንዴት ሰው ይህን ያክል ግፍ ቀምሶ ሲወጣ ከዘር ባልወረደ ሃሳብ ተመልሶ ብቅ ይላል??? አስር ቤት አንደ ሰው አንዲያስቡ የሚያረግ ተስፈ ነበረኝ። ይች ሃገር የማናት በለው ራሳቸውን ጠይቀው ለየት ያለ መልስና አቋም ይዘው ቢወጡ ምን በኮራንባቸው ነበር። መልሰው አዛው ነክረውናል።
አማራውን ሕዝብ ሳይሆን የምንወነጅለውን ከዛ ክፍለ ብሄር ወተው በኦሮሞ ህዝብ ላይ ግፍ ያወረዱበት ብለው አስምረውበታል። በተጨማሪም የኦሮሞ ህዝብ በአንድብሄር ስር ተጽኖ ተደርጎብን፤ ተገደን ነበር አማራው ይቅርታ ሊጠይቅ ይገባል አሉ። በሌላው በኩል ውበታችን ልዩነታችን ስለሆነ ግን አንድነት አየተባለ አንድ ቋንቁ ብቻ አናውራ የሚለው አንደማይመቻቸው አስረድተዋል።
አኝህ ሰው ለፖለቲካ ፍጆት ካልሆነ አንዲህ ዓይነት ውንጅልና በጣም ደካማነታቸውንና ከማሳየቱም በላይ የፖለቲካል ፍጆታውን ለመቀጠል ቆርጠው የተነሱ የመስላል ። ለምን?? አንድ ሃገር ከነታሪኩ ከነጉድፉ ይዘን መኖር ካልቻልን አንዴት ልንኖር ነው?? አማራውን ወክሎ የሚቀርበው ማነው ? ማነው ይቅርታስ የሚጠይቀው?? ሰጪውስ ማን ነው?? አማራ ማለት አራሱ ውስጡ ህብረ ብሄር ነው በሃይማኖትም የተለያዩ አምነቶች አሉት። አንዴት ሆኖ ነው አንድ የአማራ መሪ መቶ [ማንን ወክሎ??ይህንን አንኳን አንዴት አቶ በቀለ መረዳት አልቻሉትምን ወይስ አንደው ድብቅብቆሽ ፓለቲካ ? ] አማራ ለማንስ ነው ይቅርታ ሚለው አንደው ጥፈት ተሰራ ተብሎ አንኳን ቢታመንበት?? ሌላው ደግሞ አማራውስ ተሰራብኝ ያለውን ወንጀል ለኦሮሞ የተባለው ክፍለ ብሄር መቅረብስ የለበትም ? ያ በማስረጃ ከመጣ ኦሮሞን አንወክላለን የምትሉት ለአማራው ሕዝብስ ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ናችሁ ወይ??
የሚገርም ነገር ነው በአውነት ! በጣም አዘንኩኝ ። አያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ አኩል ከሁሉ ብሄር አሉን አቶ በቀለ ዞር ይሉና ወደ መጨረሻው ! አንዴት? በወቀሳና በማስፈራራት?? ማ ሸሽቶ ማ ልፈራ?? ይህ የሚያመጣው አዙሪት የጥላቻ አካሄድ ነው ። አንዱን ወንጆሎ፤ በኦሮሞ ክፍለ ብሄር የተሰራውን ወንጀል[አማራውም የራሱ ናሬሽን አለውና ] ሳያነሱ መዝለሉ ያሳዝናል።
ታሪክ የሰራውን ጥፈት ከይተም ይምጣ በሳይንቲፊክ መልኩ ታይቶ ይታረማል አንጂ አርሶ ስላሉት አውነት አያረገውም!! አማራውም ወንጀል ተሰርቶብኛል ካላ ማስረጃውን ካላቀረብ የሱም ውድቅ ይሆናል። ለዛም ትክክለኛ ፍትሃዊ የሆነ ፓድየም ይስፈልጋል። አንዱን ብሄር መቶ ወንጅሎ ከዛ ቀስ ብሎ ደሞ ሰው ሳይሆን ከነሱ የወጣው ብሄር ስርዓት ነው ማለት ምን ማለት ነው?? ማንን ነው ?? የትኛውን መንግስት.ስርዓት ነው ተጥያቂ ለአርሶ ?? ያ ስርዓት አማራን ወክያለው ብሎ ሃገርን በድሏል ወይ? መውንጀል ተገቢ ነው ግን ከማስረጃ ጋር ሲሆን ነው ።፡ ይቅርታ ይገባናል ብሎ ማስፈራራት የትም አያደርስም። ሁሉም የራሱ የሆነ የታሪክ ዓይን የሚያነብበት አለው አና ማነው ፈራጁ አስፈራጁ!!
በተጨማሪም ኢሳቶች ለነ አኦሮሞ ኮንፌዴርሽን በር ከፍተው ኢንተርቪው ካደረርጉ ፤ ይህ አድል አኩል ለአማራውም መሰጠት አለበትና አማራውን አውክላለው የሚለው ድርጅት ተጋብዞ ይሄንን ያቀረቡትን የወቀሳ ጥያቄ የመከላከል መብት መስጠት አለበት !!!!
አውነት ይነገር ከተባለ አንግዲህ ሁሉም የራሱን የታሪክ አይታ ያቅርብ ማለት ነው ።
አሳዛኝ ዘመን ! አኔ ተምራችሁ ጭቃ ብያለው!! ትውልድ በታትናችሁ ከማለፍ ምን ልታመጡ አንደሆነ አይገባኝም!! ለዚህ ለዚህ ሁላችንም አንገነጣለና ተለያይተን አንኑር!!! ይች ደሞ ሁልሽም አንደማታዋጣ ታውቅያለሽ! አና ማንን ገለህ ማንን ልታኖር ነው??? አቶ በቀለ ገርባ ከይቅርታ ጋር በጣም ወርደዋል!!! ኤፍ!!