Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

ኦ አዳም አንተ!! (አስፋ ጫቦ)

$
0
0

 

አስፋ ጫቦ Dallas Texas USA

No Man is an Island

John Donne

…………
Any man’s death diminishes me,
Because I am involved in mankind,

አምባሳደር ፍስሐ ገዳ

Fisha Gedaወንድሜና ጓደኛዬ የነበረው አምባሳደር ፍስሐ ገዳ  አሜሪካን አገርሐምሌ 8፣2007  አርፎ  Fairfax County, Virginia USA የቀብሩ ስነስረአት ተፈጽሟል።እኔ ግን አልተገኘሁም።ይኸ መታደለ ፤መረገም ፤ወይም አጋጣሚ   መሆን አለመሆኑን ገና በቅጡ ያላበራየሁት ነው።እስከዛሬ የሚቀርቡኝ ስዎችና ዘመድ አዝማድ ቀበር ላይ ተገኝቼ አላውቅም።ሁለት ትንንሽ እህቶቼ ባህር ዳር እያለሁ ነበር ያረፉት።እናቴና የባለቤቴ እናት ያረፉት ማእከላዊ እያለሁ ነበር።አባቴና ልጅ የራፉት ደግሞ እዚሁ አሜሪካ እያለሁ ነበር።

የህ ራሱ ራሱን የቻለ የሞትና የቀብር ምስል ይፈጥራል።ልኔ የፈጥርበኛል።መታደለ ያሰኜኝ እነዚህን ዘምድ ወዳጆቼን ያማስታውሳቸው፣ትዝ የሚሉኝ ልክ የመጨረሻ ቀን እንደየኋቸሁ ነው። ስለዚህም ያ ምስል ስለአለ እነሱም አሉ። መረገሙ ያሰኜኝ የሉም። የሌሉትን አሉ ብሎ የተወሰን የሒሊና ክፍሌ ማማለሉ ነው።አፈር ሲመለስ ካልታዬ ቀዳዳው  አይዘጋም። ወይም ቁስል ሁኖ ሊኖር ይሻል።

ፍስሐን ሞሞት ያነበብኩት አንድ ገጽ ላይ ነበር።ሌላው ወንድሜ፤ግርማ ይልማ፤ያባህልም የማስታወቂያም ሚንስቴር የነበረው፤በኋላም መስኮብ አምባሳደር  የነበረው ከSeattle, Washington  ስልክ ደውሎልኝ ኖሮ ጥሪውን አለስማሁትምና  መልክት ተወልኝ።ወደ ፍስሐ ቀብር ሊጓዝ ከነበርበት አየር ማረፊያ ነበር የደውለልኝ።በሁለተኛው ቀን መልእክቱን ሰማሁት። ያኔ ነገረ-አለሙ የትላትንት ዜና ሆኗል።

ግርማ ይልማ በቀብሩ ስነ ስርአት ንግግር ካደርጉት አንዱ ነበር።እኔ ባልገኝም ግርማ እኔ ልል ከምችለው የበለጠና የተሻለ ስለፍስሐ ገዳ ሊል እንደሚችል እርግጠኛ ነበርኩ። ምክንያቱም ፍስሐን ከኔ የተሻለና የበለጠ እንደሚያውቀው አውቃለሁ::የሁለተኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ትውውቁ እንደተጠበቀ ሁኖ ከአመታት በኋላ ደርግ ሲመሰረት የተገናኙ ለረዝም አመታት አብረው ደርግ ማስታወቂያ ኮሚቴ ውስጥ አብረው ሰረተዋል።

ፍስሐ፤ግርማና እኔ የተገኛነው በ1953 አዲስ አበባ፤ቀበና፤ኮከበ ጽባሕ ትምህርት ቤት ነበር::በዚያን አመት ኮከበ ጽባሕ የመምህራን ማስልጠኛ ዘርፍ ከፍቶ ስለነበር ስምንተኛ ክፍል ከነበረባቸው 12ቱም ጠቅላይ ግዛቶች በከፍተኛ ውጤት የ8ኛ ክፍል ፈተናን ያለፉ ሁለት ሁለት ተማሪዎች መጥተው ነበር።

ለአዲስ አበባ ልጆች ከጠቅላይ ግዛት የመጡትን ማየት በውቅቱ ያዩት የነበረውን የነታራዛንን ፊልም የስታወሳቸው ይመስለኛል።አማርኛችን፤እንግሊዚኛችን፤ከመምህራን ጋር የነበረን ግንኙነት፤በክፍል ውስጥ ለጥያቄ አመላለሳችን፤በአጭሩ ሁለንተናችን ቲያትር መስሎ ታይቷቸዉ በታመቀ ሳቅ  ይሞቱ ነበር።ኮከበ ጽባህ ደግሞ የአዲስ አበባ ልጆች ትምህርት ቤት ብቻ ሳይሆን  የመኳንንት፤የመሳፍንትና የሚኒስተር ልጆችም የሚማረበት ነበርና ይህ እንግዳ ደራሹ ቢገርማቸዉኘው አይገርምም።በኋላ እንዳስብኩት ለማለት ነው!

ፍስሐ ገዳንም የአዲስ አበባ ልጅ አድርጌ ነበር የወስድኩት። ለየት ያለ የአዲስ አበባ ልጅ! አለመሆኑን ያውኩት ቅይቶ፤ኖሮ ኖሮ ነበር። አላነሳሁበትም።ለየት ያለ የአዲስ አበባ ልጅ የሰኜኝ ሁለመናው ነበር።የያጋሞ ስብእና (personality)ያለው አይነት ነበር። ወይም የጋሞ ሰው አሻም የሚለው አይነት ስብእና።አሻም በነጠላው ቢተርጎም እንኳን ደህና መጣህ(ሽ) ማለት ይሆናል።አንድምታው ግን ቅባትና ወዝ ያለው ይመስለኛል። ከደርቁ እንኳን መጣህ(ሽ) ላቅ የሚልበት መንገድ ያለው ይመስለኛል። የሲዳዎችን ዳኤ የሚያውቅ የተሻለ የሚረዳኝ ይመስለናኛል። ሞቅ፤ደማቅ የማለት ቃና አላው።ሁለት እጆችን ከፍቶ እቅፍ የማድረግ ቃና። እዚህ አሜሪካኖቹ  ሀግ (Hugging) የሚሉት  አይነት።ማስመስሉ ሲቀነስ!ፍስሐ ገዳ ላይ መጀመሪያ ያስተውልኩት ይህንን አሻም ባህርይ ነበር።ይህ የጋራ ባሕርይ  ካቀራረበን ውስጥ መግቢያ በሩ ይመስለኛል። ማየት ማመን(Pereception is Reality) ነው እንዲሉ

ጓደኞቼም፤ያልሆኑትም ቅዳሜና እሁድ ለጥናት ቀበና ጫካ ውስጥ ይሔዳሉ።እኔ ደግሞ ፒያሳ ሻይ ቤት እሔዳለሁ።በኪንግ ጆርጅ ባርና በጆኖፖሎስ መጽሐፍት መሸጫ መካከል አንድ አፈ ሰፊ ሻይ ቤት ነበረ።፣ፒያሳ በሔድኩ ቁጥር ፈስሀ ገዳን አገኘዋለሁ።በቀኝ ክንዱ የሚሸጡ መጽሐፍት አቅፎ ይዞራል።ሲሸጥም ለመሸጥ ሲያግባባም አየዋለሁ።ያለጥርጥር የአዲስ አበባ ልጅ፤በተለይም ነጋዴው የሚፈልቅበት የመርካቶ ልጅ ነው የሚለውን ግምቴን ያጠናከረልኝ ይመስለኛል።የመጽሐፍቱ አይነት ባብዛኛው ያጠሩና (abridged) አጫጭር ልበወልዶችና የስለላ ታሪክ  ናቸው።ዋጋቸው በአብዛኛው በሱሙኒና በብር መካከል የነበር ይመስለኛል። አንዴ ይሁን ሁልቴ በ 50 ሳንቲም ማግዛቴ ትዝ ይለኛል።በሳምንቱ ይሁን እንዲያ ሻይ ቤቱ ገብቶ ሻዬንም ፓስቲውንም ከፈለልኝ። “እንዴት ለወንድም ይሸጣል!” የሚል ውስጠ ታዋቂነት የነበረው አድርጌ የወሰድኩት ይመስለኛል። በዚህ ሁሉ ውስጥ ያስተዋልኩት ፈስሀ ገዳ መጽሀሐፍ ሻጭ አለመምስሉ ነበረ።ተቸግሮ  የእለት ኑሮ ለማሸነፍ የሚሯሯጥ ሳይሆን አንድ የሚያስደስት ስራ (Hobby) እያሰራ ያለ የሚመስል ነገር ነበረው።

ከፍስሐ ገዳ ጋር፤ኮከበ ጽባህ ለመጨረሻ የተገናኛነው ስኔ 1954  ትምህርት ቤት ለክርምቱ ሲዘጋ ይመስለኛል።ቆይቶ እንዳውኩት ፍስሐም ለመኮንንነት ኮርስ ሆለታ እኔም ሲብል አቪየሽን ገባሁና የሁለተኛ ድረጃ ትምህርታችን እዚሁ ላይ አበቃ።ሁለታችንም ብንሆን በሌላው መልኩ ትምህርትና ስራ አጋብተን የቀጠልን ይመስለኛል።

ከአመታት በኋላ አንድ ምሽት ባልቻ ሆስፒታል ጎን የሚገኘው የጦር ሠራዊት መኮንኖች ክበብ ተገናኘን።ቦርሳዬ ከሳ ስትል የጦር ወሠራዊት ጓደኞቼን ማፈላለጌ የተለመደ የታወቀ ነበር። ከፍስሀ ጋር ተገናኘን። ትንሽ ተጯጯህንና ጓደኞቼቸን ጣጥዬ ከፍስሀ ጋር አመሸሁ። የመኮንን ልብሱን ገጭ አድርጎ ነበርና የመጣው ጦር ሠራዊትነቱ እንዳማረበት የነገርኩት ይመስለኛል። ሐረር እንዳለ የነገረኝ ያን ለት ነበር። ውስኪዬንም ብራውንም ከፋፈለው። ለመግደርደር ብሞክርም “እዚህ ለመክፈል መብት የለህም!!” ያለኝ ይመስለኛል።

ቀጥሎ የተገናኘነው አራተኛና ክፍለ ጦር የደርግ ማስታውቂያ ኮሚቴ ቢሮ ነበር። በራዲዮና ተለቨዝን በተናገርኩት እንቅስቃሴሰውን  ቅራሪ ብሏል ተበዬ ተከስሽ ነበር። ወዳጄ ተክሉ ታቦር ነበር ይዞኝ የሔደው።”አስፋን ውልደው!” ብለው አፋጠውት ኖሯል። ፍስሐገዳንና ግርማ ይልማና እዚያ አገኜኋቸው።በወቅቱ የኮምቴው ሰበሳቢ የነበረ ሻለቃ አስራት ደስታ  ቆራጭ ፈላጫ እንደሆነ ሊያስረዳኝ በፊቱም(Body Language) በቃላትም ከበቂ በላይ መልእክት ላከልኝ።”ከአንተ አይጠበቅም!” የሚለው ነገር ነበረው።ተክሉ ቴፑን ይዞ ስለመጣ እስቲ የሚጠበቅብኝን ለማውቅና ላለማውቅ መጀመሪያ ቴፑን እናዳምጥ አልኩት። ተደመጠ።አስራት ያለውም ሌላም ተፈልጎ ታጣ። ”ካፈርኩ አይመልሰኝ!” ሆኖበት መስል” ካንተ አ ..” አቋርረጨ ተነሳሁ። ሁለተኛ እኔንም ሆነ ሌላ  ሰው ባልታጣራ ነገር አትጥራ” ብዬ  ተነስቼ ወጣሁ። ፍስሀ ተክተሎኝን ወጥቶ ኖሮ” አሁንም ያው ነህ !!” ብሎ ስቆ ተመለሰ። ተክሉ ታቦር ፊቱ ላይ ምን ያክል እፎይታ ያነበብኩ መስለኝ።ለነገሩ እኔ ቅራሪ አለማለቴ ተረጋገጠ። የአብዮቱ እንግዴ ልጆች ተሰባስበው ቅራሪ ማድረጋቸው ግን እርግጥ ነው። ይኸ አሁን ሳሰበው ማለት ነው።

ፍስሐ ገዳ በኢትዮጵያ አብዮት ከልደት እስከሞቱ ተካፋይ ነበር።የሚያውቀውን፤የሚያምነውን የሚችለውን በቅን መንፈስ የሰጠ በአይነቱ ከጥቅቶቹ ውስጥ የሚደመር ነበር።አሁንም ያው ነህ!” ያለኝ አንድምታ ያለው 1954  በኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት የተካሔደዉን፣ተመሳሳይም ተቀራራቢም የማይገኝለትን የተማሪ የተሳካ አብዮት ለማስታወስ ይመስለኛል። ፍስሐገዳና ግርማ ይልማ የዚያ አብዩት አካል አምሳል ብቻ ሳይሆኑ ንቁ ቀማሪዎችና ተከፋዮች ነበሩ።

ታሪኩ እንዲህ ነበር። በውቅቱ የኮከበ ጽባህ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር ሚስተር ዉድ ትንሹ (Mr.Wood Junior)ይባላል። ሚስት አለችው። አባቱና እናቱንቱም ዉድ ትልቁ (Wood Senior) የሚባሉም ነበሩ።በዜግነታቸው ካናዳዊን ነበሩ።የክፍለ ጓደኛችን፤በደርግ ዘመን መንዝ ሸፍቶ ለብዙ ገበሬ እልቂት ሰበብ የነበረው የመሳፍንቱ ወገን መርዕድ ብሩም ኗሪነቱ ሚስተር ዉድ ቤት ነበር።የሚስተር ዉድ ቅጣት 2,3,4,5 በያንዳንዱ እጅ (2,3,4,5 On Each Hand) የሚል ነበር።ያ ማለት በጉማሬ አለንጋ የውስጥ እጅን መተለተል ማለት ነው። ገራፊው ድንገት ስቶ መሀል ለመሀል ካላሳረፈ ያ አይቆጠርም። ቆሞ ነበር የሚያስገርፈው።ሁለት ገራፊዎች ነበሩ።ብቻ ምን ጥፋት ለዚያ እንደሚያበቃ አላውቅም። የሚያውቅም ያለ አይመስለኝም። አንዱ የሚያስቀጣው  ትዝ የሚለኝ  ዉድ ትልልቆቹ(Wood Seniors) በተማሪ አጠገብ ሲያልፉ የተቀመጠው ተነስቶ እንዴናችህ ብሎ እጅ ካልነሳ ለግርፊያ ይላካል።

በኔ ግምት እነዚህ ካናዳዊያን ስለአፍሪቃ፣ስለጥቁር ፤የቅኝ ገዝዎቹ እንግሊዛዊያንና ፈርንሳይ ደራሲዎች የጻፉትን አጓጉል መጽፈሐፍት ሳያነቡ የቀሩ አይመስለኝም።ለጥቁር ፊት አለምስጠት ነው!” የሚል። ያላነበቡበት መጽሐፍ ቢኖር ከኢትዮጵያ በስተቀር የሚል መኖር ያለመኖሩን ልብ አለማለታቸው ይመስለኛል።  የዚህ የዘመኑ አውሩድልኝ ልብስ አይነት ለሁሉም የሚመን (Fits All Sizes) አይነት መሆኑ ነው።

ሲብላላ ቆየና ፈነዳ።ይበልጥ የሚገርመው ለፍንዳታው ጫሪ የሆኑት ከጠቅላይ ግዛት ትላንት የመጡት መሆናቸው ነበር። አሁን መለስ ብዬ ሳየው!! አንድ ለሊት ግርማ ይልማና እኔዉርደቱ ይብቃ!! ተነስ!! አመጽ!! ዛሬ ክፍል አትግባ!! ኳስ ሜዳ ተሰብሰብ!!” የሚል  በደብተራችን ቅዳጅ ወረቅት ጽፈን  ገና ተማሪ ዝር ሳይል በየክፍሉ  ክ1-12 ለጠፍን።ጥሪውን ተቀብሎ ኳስ ሜዳውን አጥጠለቀለቀው !ነግረነው!!አባቶቻችንን ጣሊያን ዶቅሰው እንዳላስወጡ ሁሉ…..!!”    አንዴ ከተሎኮሰ እሳቱን የሚያራግብ እጥረት  አልለነበረም።ተቀጣጠለና እሳቱን አጥፊም ሆነ እንዴትስ መጥፋት እንደሚገባው ነጋሪ አዋቂ ታጣ።ሚስተር ዉድሊማጸንም ሊያስፈራርም ቢሞክር ሜዳ ሙሉ  ተማሪ አንዴ ሲያንቧርቅበትነፍሴ አውጭኝ !”ብሎ ሸሸ። ከዚያ ከትምህርት ሚኒስቴር ተራ በተራ ባለስልጣናት ለማስፈራት፤ለማባበል ከዚያ ለመለማመጥም ተቀያየሩ።”ፍንክች ያባ ቢለዋ ልጅ !!”ሆነ።በመጨረሻም ሚስተር ውድ ከነጓዝንጉዙ ተነቅሎ ወደሚሔድበት ሔደ። ጋሼ አማረ ጉልላት አዲሱ የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ዳይረክተር ሆኖ መጣ። ይህ የመጀመሪያዉ፣ብቸኛውየተሳካ የተማሪ ንቅናቄ ይመስለኛል። አምባሳደር ፍስሐ ገዳ የዚህ ንቅናቄ አካልና አምሳል ነበር። ግርማ ይልማ ቆይቶ የተማሪዎች ማህበር ምክትል ፕሬዝዳንት ፕረዚዳንትም ሆኖ ነበር።

አንድ አራት አመት ያክል ደርግ ጽሕፈት ቤት ቢሮ ነበርኝና ፍስሐ ገዳን በየቀኑም ባይሆን ብዙ ጊዜ የማግኘት እድል ነበረኝ። ብዙም የምንነጋገረው አልነበረም። አስፈላጊ በሆኑ ነጥቦች ብቻ ካልሆነ በስተቀረ። የቀረውን ሳንነጋር የምንግባባ (Given) ይመስለኛል። የታውቀ ነው በሚሉት መልክ። ከማስታውቂያ ኮምቲ በኋላ የፕሬዚዳንቱ፤የመንግስቱ ኃይለ ማርያም፣ የፕሮቶኮል ሹም ሆነ። ይህ የሚሰማማው ስራ መሆኑን የነገርኩት ይመስለኛል። የፕሮቶኮል ሹም ስራ አሻማ ነው ብዬ ስለማምን።ከዚያ እኔ ማእከላዊ ከወርድኩ በኋላ የሆቴሊና ቱሪዝም ኮሚሽነር ሆኖ መሾሙን ሰማሁ። ዋናውን የአሻም ስራ አገኘ አልኩኝ በልቤ። በሆቴሊና ቱሪዝም ዘርፍ ከመስራቹ አቶ ኃብተ ስላሴ ታፈሰ ጋር የሚነጻጸር ምናልባትም ሊበልጥ የሚችል ለውጥ ያመጣ ፍስሽ ገዳ መሆኑን ዛሬ ወዳጅም ጠላትም አምኖ ተቀብሎ በዚያ ላይ ተንተርሶ  ወደሚቀጡለት ደርጃ ያደረሱት ይመስለኛል። ወዳጅም ጠላትም ከማለት ሁሉም ተቀብሎ ብል የሚሻል ይመስለናኛል። ፍስሀ ጠላት ያለው ሊኖረውም የሚችል ስለማይመስለኝ ነው።ስሜን ኮሪያ  አምባሳደር መሆኑን እኔ፤በግሌ፤ ግዞት እንደተላከ ነበር የቆጠርኩት። ዝግ አገር ነውና አሻም የሚላቸውም አሻም የሚሉትም ያሉ አይመስለኝም። ከስሜን ኮሪያ ጋር መንግስቱ ግኑኝነት ሊያጠናክር የፈለገው የሶቭየቱ ጋርባቾቭ “እስቲ ጦርነቱ ይብቃና ስላም መንገድ ፈልግ !” ብሎ መሳሪያም ፊትም ስለነሳው አማራጭ መፈለጉ ነበር።

የሆተልና ቱሪዝም ኮሚሽነር ሆኖ እንደተሾመ ፍስሐ ገዳ የሰራውን ፤ከምንጩ የሰማውን አያሌው ነገረኝ።እንደተሾመ  “እኔ ስለሆቴልና ቱሪዝም ምንም የማውቀው ነገር የለም!” ብሎ ለመንግስቱ ነገረው  “ታዲያ ምን ይሻላል!?” ተብሎ ሲጠየቅ “ስራውን የማያውቁ እስር ቤት ናቸውና ይፈቱልኝና ያስተምሩኝ!” አለ። በዚሁ መስረት የቱሪዝም እናት አባት የሆነው አቶ ኃብተ ስላሴ ተፈስና አቶ ዮንስ ክፍሌ ከእስር ቤት ተፈተው ወደስራቸው ወይም ፍስሐ ገዳ ወደሚመድባቸው ስራ ተመለሱ።

በማስፈታት ብቻ አልተገታም። ስራውን በተረጋጋና በተዝናና ሙሉ መንፈስ ሊያካዱ ይችሉ ዘንድ እርፍት ቦታና ጊዜ ስጣቸው። ለሚመደቡበት ስራ እውቀት ብቻ ሳይሆን ከስራው ባህርይ ጋር ተመጣጣኝ የሚሆን እይታ ይኖራቸው ዘንድ ልብስ ከጣሊያን አገር አስመጣላቸው።

ከቀበሩ ስነስርአት እንደተመለሰ ይህንኑ ለግርማ ይልማ ነገርኩት። “አሴ ልክ ነው! የአቶ ኃብተ ስላሴ ታፈሰ ልጅ የቀብሩ ስነ ስርአት ላይ ንግግር ካደርጉት አንዱ ነበር.. ይህንኑ  ተናገር” አለኝ። ለዚህም ነው ይህንን  አያሌው  በግል የነገርኝና  አደባባይ ያወጣሁት።

Fisha Geda 1
ከፍ ብሎ “ሁለታችንም ብንሆን በሌላው መልኩ ትምህርትና ስራ አጋብተን የቀጠልን ይመስለኛል” ወዳልኩት ለአፍታ መመለስ ፈለኩ። ሁለታችንም ከ10ኛ ክፍል አቋርጠን ወደየምንሔድበት ሔድን። እኔም የምሆነውን ሆንኩኝ። አሁን ዞር ብዬ ሳየው ግን ፍስሀ ገዳ እድሜ ልኩን ትምህርት ቤት ነበር ለማለት የሚያስችሉ ምልክቶች አያለሁ። የመጽሐፍት አዟሪነቱ የሕዝብ ግንኙነት ትምህርት መማሪያ  መድረክ ሆነው። ተፈጥሮ የስጠውንና የእለት-ተለት ኑሮ አስገድዶት መጽሐፍት ሲሸጥ አለበለዚያ ሊያገኛቸው የማይችላውን ግለስቦችን ድርጅቶችንም  ማገኘትና መገናኘት ቻለ። ታዋቂውን ደራሲና የረዥም ጊዜ የአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ የነበረውን ብርሐኑ ዘሪሁንን የተዋወቀው በዚህ አጋጣሚ ነበር። የልዑል ራስ እሙሩን ልጅ፤ወይዘሮ የምሥራች እምሩን፤ ተዋውቆ ቤተሰብ የመሆን ደርጃ የደረሰውም በዚሁ መጽሐፍ አዟሪነቱ  ምክንያት ነበር። ሁለት ስም ለዐይነት ጠቀስኩኝ እንጅ ያ ስራው የብዙ ሰዎች መተዋወቂያ፤የብዙ ቢሮዎች መክፈቻ ቁልፍ ሆኖት/ሆኖለት ነበር ማለት የሚቻል ይመስለኛል።

ፍስሐ ገዳ በአዟርነቱ ያገኘውን ትምህርት ወደሚቀጠለው ሕይወቱና ሙያው ከፍ ያደረገው ይመስለኛል። በመኮንንቱ ሐረር ሶስተኛ ክፍለ ጦር ሲመደብ  የክፍለ ጦሩ የሕዝብ ግንኙነት መኮንን ሆነ :: ለ11 አመታት የሠራዊቱ መጽሔት አዘጋጅ ነበር። የደረግ የመስታወቂያ ክፍል ሰራተኛ ነበር። የፕሬዚዳንቱ የፕሮቶኮል ሹም ከዚያም የሆቴልና ቱሪዝም ስራ አስኪያጅ ፤ከዚያም አምባሳደር ሆነ።በስደት አሜሪካ ከመጣም በኋላVienna,VerginiaATI Career Institute,School of International Hotel and Resautarant Mangment  ገብቶ በሙያው መስልጠን ብቻ ሳይሆን አስልጣኝም ሆነ። በዚህ ስራውም አለምን ዞረ። ይህ ሁሉ የጋዘጤኛና የህዝብ ግኑኝነት ስራ ሙያ ነው። ዩኒበርስቲ ገብተዉ የሚማሩት! ፍስሐ ለዚህ ሙያ የሰለጠነው በአዲስ አበባ የመንገድ ላይ ዩኒቨርስቲ ነበር።

አንድ ሌላ ስለፍስሐ ገዳ መነገር ያለበት አለ። ፍስሐ ከደሀ ቤተሰብ መውለድ ብቻ ሳይሆን ህይወትን በጸጋ ፊት ለፊት ተጋፍጦ ከደረሰበት የደረስ ነበር። አንድ እውቂ ባሕርዩ ማን እነደነበር፣ከየት እንደተነሳ፣ አንዴትስ እዚህ እነደደረስ መስማት ለሚፈልግ ሁሉ ሳይጠቀየም ይናገራል። ከራሱ አይሸሽም ነበር። ከራሱ ጋር ጸብ አልነበረውም። የሚናገረው በኩራት መልክ አለነበረም።በጸጸትም መልክ አልነበረም። በማፈረም አልነበረም። እኔ የኸው ነኝ፤እንዲህ ነበርኩ በሚል እውነቱን በመናገር (A matter of fact) መልኩ ብቻ ነበር።

 ለኔ ፍስሐ ገዳ ሰዉዬው የሚባል ሰው ነበር ።የKipling “IF”  የሚለውን ግጥም ያስታውሰኛል ።ይህን ግጥም አቶ ከበደ ሚካኤል ወደ አመርኛ መልሰውት ነበር።

If you can talk with crowds and keep your virtue,

Or walk with kings –not lose the common touch,

Yours is the Erath and everything that is in it

And –what is more, you will be a Man, my son

አንዳንዴ በጸጸት መልክ ወደኋላ የማያቸው አሉ። ከነዚህ አንዱ፤በደርግ አካባቢ ብዙ እቡያን መሰባሰባችን እውነት ነው።ጥቂት ብጹአንም መኖራቸው እርግጥ ነው። ፍስሐ ገዳ ከነዚህ አንዱ ነበር። በዛ ያሉ ፍስሐዎች ቢኖሩ ኖሮ  የወደአዘቅት ጉዟችንን ሊያስቀሩት ከዚያም ሊለዉጡት ይችሉ ነበር?  እላለሁ። ይህ  እንግዲህ ጸጋዬ ገብረ መድኅን:-

ትዝታ ነው የሚርበን

ላናገኘው ላያጠግበን  ወዳለው የሚደመር ይመስለኛል።

የማይሞት ሰው ሞተ!!በፍስሐ የሕይወት ታሪክ ውስጥ ደግሞ:-

ባለቤታቸው፣ ከወ/ሮ እቴነሽ ሸዋዬ ጋር፣ በ፩፱፭፱ ጋብቻ በመመስረት፣ ከ፬፰ ዓመት በላይ፣ በትዳርና ባማረ ፍቅር ኖረዋል። ከአብራካቸውም ሰርካለም ፍሰሐን፣ ብሩክታዊት ፍሰሐን፣ ደረጀ ፍሰሐን፣ በላይ ፍሰሐንና ንጋት ፍሰሐን አፍርተው አምስት የሚሆኑ የልጅ ልጆችን ለማየት በቅተዋል”  የሚል ተጽፏል።

ሰው ዘለዓለማዊ ነው!! የሚለው አንድምታም ያለው ይመስለኛል። አንድምታው ፍስሐ ማዉን የሚያነሱ ተክቷል። በዚህ ደግሞ እንጽናናለን!!

 

 

 

 


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>