(ዘ-ሐበሻ) በዳላስ የተጀመረው የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር በዋሽንተን ዲሲ እና በሲያትል ከቀጠለ በኋላ ዛሬ በላስቬጋስ ከተማ እንደሚደረግ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::
በትልቁ ጎልድ ኮስት ካዚኖ ውስጥ በሚደረገው በዚሁ የአርበኞች ግንቦት 7 የገቢ ማሰባሰብ ላይ የድርጅቱ ከፍተኛ አመራር የሆኑት አቶ ሙሉነህ እዩኤል እንዲሁም አቶ ጋሻው ገብሬ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::
እስካሁን በ3 ከተሞች ብቻ በተደረገ የአርበኞች ግንቦት 7 ገቢ ማሰባሰቢያ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ ($200 ሺህ) ዶላር መገኘቱን ዘ-ሐበሻ መዘገቧ ይታወሳል::