የኢትዮጵያ እግር ኳስ ብሄራዊ ቡድን አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ ቀጣይ ላለባቸው የዓለም ዋንጫና የቻን ማጣሪያ ጨዋታ የ19 ተጫዋቾችን ስም ዝርዝር ይፋ አደረጉ።
የተመረጡት ተጨዋቾች መስከረም 19 ቀን 2008 ዓ.ም ከቦትስዋና ጋር በሚያደርገው የአቋም መለኪያ ጨዋታ ይሳተፋሉ ሲሉ መንግስታዊ ሚዲያዎች ዘግበዋል::
ለ2018ቱ የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ እንዲሁም ለ2016ቱ የአፍሪካ አገሮች እግር ኳስ ዋንጫ /ቻን/ ከቡሩንዲ ጋር ለሚደርገው ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋሉ።
ሁሉም ተጫዋቾች መስከረም 10 ቀን 2008 ዓ.ም በፌዴሬሽኑ ጽህፈት ቤት ተገኝተው ሪፖርት በማድረግ ወደ ሆቴል የሚሰባሰቡ ሲሆን፥ ልምምዳቸውንም የሚጀምሩ ይሆናል።
ተጨማሪ ተጨዋቾች ከ2007 ዓ.ም የኢትዮጵያ ጥሎ ማለፍ የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በኋላ እንደሚለዩ የኢትዮጵያ ብሄራዊ እግር ኳስ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ መግለፃቸውን ፌዴሬሽኑ የላከው መግለጫ ያመለክታል።
በአሰልጣኙ የተመረጡት ተጨዋቾችም ከዚህ በታች የተዘረዘሩት ናችው።
ግብ ጠባቂዎች፦
1. ታሪክ ጌትነት
2. ለዓለም ብርሃኑ
3. አቤል ማሞ
ተከላካዮች፦
1. ስዩም ተስፋዬ
2. ተካልኝ ደጀኔ
3. አሰቻለው ታመነ
4. አንተነህ ተስፋዬ
5. ሙጂብ ቃሲም
6. ዘካርያስ ቱጂ
አማካዮች፦
1. ኤፍሬም አሻሞ
2. ጋቶች ፓኖም
3. ሙሉ ዓለም መስፍን
4. ብሩክ ቃልቦሬ
5. ቢኒያም በላይ
6. በረከት ይስሃቅ
7. አሰቻለው ግርማ
አጥቂዎች፦
1. ባዬ ገዛሀኝ
2. ዳዊት ፈቃዱ
3. ራምኬል ሎክ