(ዘሐበሻ) በሕዝብ ብዛት የዓለማችን ሦስተኛ ሃገር የሆነችው አሜሪካ ከ322 መቶ ሚሊዮን ሕዝቦቿ ውስጥ 38% የሚሆኑት ፓስፖርት የላቸውም:: ታዲያ ሰሞኑን ትራቭል ኤንድ ሌዠር የተሰኘው ድረገጽ ያወጣው መረጃ ለነዚህ 38% ለሚሆኑት አሜሪካውያን ዱብ እዳ ነው::
ድረገጹ እንደሚለው ከሆነ አሜሪካ ካሏት ስቴቶች ውስጥ 5ቱ ስቴቶች የመኪና መንጃ ፈቃዳቸውን እንደ መታወቂያ የሚጠቀሙ ሰዎች በዚህ መታወቂያ ከዚህ ቀደም የትኛውም ስቴት በአውሮፕላን ሲበሩ ቆይተዋል:: ከ2016 ጀምሮ ግን ይህ የማይታሰብ ነው ይለናል – ድረ ገጹ::
“Driver’s licenses from New York, Louisiana, Minnesota, American Samoa, and New Hampshire will no longer be enough to get on a domestic commercial flight” ሲል ያስነበበን ድረገጹ የኒውዮርክ; የሉሲያና; የሚኒሶታ የአሜሪካን ሳሞአ እና የኒውሃምፕሻየር መንጃ ፈቃድ ያላቸው ሰዎች በአውሮፕላን ለመሳፈር አስቸጋሪ የሚሆኑት መታወቂያዎቹ የሆምላንድ ሴክዩሪቲን “REAL ID Act” ደረጃ አያሟሉም::
ይህ ሕግ በ2016 ሲጸድቅ ከላይ የተጠቀሱት ስቴቶች ውስጥ የሚኖሩት ወገኖች በአውሮፕላን ከስቴት ወደ ስቴት ለመዘዋወር ከመንጃፈቃድ የዘለለ መታወቂያ ያስፈልጋቸዋል:: ቀኑ አይወሰን እንጂ የስቴት መታወቂያ ይዞ አውሮፕላን ማረፊያ ለመሳፈር የሚሄድ ሰው ከመታወቂያ የዘለለ ፓስፖርት ወይም እንደ ግሪን ካርድ ያሉ መታወቂያዎችን ካልያዘ ለመጀመሪያ ጊዜ እንዳይሳፈር አይከለከልም ሆኖም ግን የ3 ወር የይቅርታ ጊዜ ይሰጠውና በነዚህ ጊዜያቶች ውስጥ የሚጠየቀውን መታወቂያ ካላሟላ በአውሮፕላን መሳፈር አይችልም::
በነዚህ 5 ስቴቶች ውስጥ የምትኖሩ ወገኖች ሕጉ በ2016 ተግባራዊ ይሆናል ይባል እንጂ ቀኑ አልተገለጸም:: በመሆኑም ካሁኑ ተዘጋጁ::