Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

በትግራይ የፖለቲከኞች የሃይማኖት ጣልቃ ገብነት ምእመናኑን ከቤ/ክ እያራቀው ነው፤ ቤ/ክ ሊሳለሙ ሄደው ‘ወይን’ጋዜጣን በግድ ግዙ ይባላሉ

$
0
0

የትግራይን እናድን ትዝብታዊ ትንታኔ

በትግራይ የፖለቲከኞች ጣልቃ ገብነት በሃይማኖቶች ላይ፤

በትግራይ በተለይም በገጠሩ አካባቢዎች ያለው የፖለቲከኞችና ካድሬዎች ጣልቃ ገብነት ብዙ አማኞችን ከሀይማኖታቸው በተለይም ከቤተ-ክርስትያኒቱ እያሸሸ ነው፡፡
ተዘዋውሬ ባየኃቸው አብያተ-ክርስትያናት ያለው ነገር በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡

1. በብዙ ወረዳዎች በገጠሩ አብያተ-ክርስትያናት በካድሬዎች ቁጥጥር ውስጥ የገቡ ናቸው፡፡ በየአብያተ-ክርስትያናት ፈጣሪን ለማምለክ የመጡትን ምእመናን ከአጭር ፀሎት በኃላ ቀጥታ ህዝቡን ከቤተክርስትያኑ የሚወጣውን ምእመን በመሰብሰብ የ”ወይን” የተባለ የፓርቲው ጋዜጣ አስተምህሮትና ውይይት በካድሬዎች ይከተላል፤ ምእመናኑም ለጋዜጣውን መግዣ ተብሎ በየወሩ መዋጮ እንዲያዋጡ ግዴታ ተጥሎባቸዋል፡፡ የሚመጣው ጋዜጣ አንድ ፤ህዝቡ የሚያዋጣው ብር ደግሞ የት-የለሌ፡፡ ያሳፍራል እኮ ወገኖች፡፡ በዚህ የተማረረ ምእመንን ይሀንን ለመሸሽ ቤተ-ክርስትያን መሄዱን እያቆመ ነው፡፡
tigrai church
2. በሀይማኖታዊ ታላላቅ በዐላቶች የሀይማኖታዊ ቀኖና፣ ስርዓትና መርሐ-ግብር ባዛነፈ መልኩ ያልተገቡ የፖለቲካ ቅስቀሳዎች፣ ከበዓላቱ ጋር ተያያዥነት የሌላቸው ዲስኩሮች አማኙ በሀይማኖታዊ በዐላት ሊያገኝ የሚገባውን ሀይማኖታዊ አስተምህሮዎች እንዳያገኝ፣ ከበዐል አከባርና ስነ-ስርዐት ሊያገኝ የነበረውን የመንፈስ እርካታ የሚያውክና ብሎም በተራዘመ ሂደት አማኙ ከሀይማኖታዊ በዐላት እንዲሁም ከሀይማኖቱ የሚያሸሽ ነው፡፡ ለምሳሌ፡ በትላንቱ የጥምቀት በዐል ላይ ያየነው ከቀኑ ጋር ምንም ያልተገናኘ እቺ እኛ የማናውቃት የ11% እድገት፣ የህዳሴ ዲስኩር፣ የግለ-ሰቦች ራእይ እና መሰል የተለመዱ የፈጠራ ወሬዎችና ዲስኩሮች የበዐሉን ታዳሚ ፍፁም ያስከፋና የበዐሉን ድባብ ያበላሹ ናቸው፡፡

3. ለአብያተ-ክርስትያናትና ቅርሶቻቸው የሚደረግ ምንም ጥበቃ አለመኖር፣ የቅርሶች ዝርፊያ መበራከት ወ.ዘ.ተ አንዱና ዋና ምክንያት ለሀይማኖቱ የማይቆረቆሩ ካድሬዎች በየስርቻው መሰግሰጋቸው ነው፡፡

ምናልባት አማኙ ከሀይማቱና ከትውፊቱ በማራቅ ማንነቱና ኩራቱ በማሳጣት ውዝግብግቡ የወጣ፣ የተወናበደና እምነቱ፣ ባህሉ፣ ማንነቱ ያጣና ግራ የተጋባ ማሕበረሰብ ለመፍጠር የሚደረግ ማርክስ-ሌኒናዊ አስተምህሮት ውጤት ነው ወይስ ሌላ፤ ቤተ-ክርስትያኒቱ ልታየው፣ ልትመረምረውና ልትታገለው የሚገባ ነገር ነው፡፡ እኔ እራሴን እንደሀይማኖተኛ ባልቆጥርም የማንነታችንና የታሪካችን መገለጫ ትውፊቶች፣ አባቶቼ የተውልኝ አሻራዎች ግን እንዲህ እየወደሙ ሳይ ያመኛል፡፡


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>