በጣም አስቸኳይ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ
በባየርን ክልል ለምትገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በሙሉ
ወንድማችን አቶ አበራ ሽፈራውን በማስገደድ ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ የሚደረገውን ጥረት ለማስቆም በባየር ከሚገኙ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች ጋር በመሆን አንድ ታላቅ የሰላማዊ ስልፍ እናደርጋለን በመሆኑም ማንኛውም በባየር አካባቢ የምትገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ከታች በተጠቀሰው ቀንና ሰአት ከስፍራው እንድትገኙ በጥብቅ እያሳሰብን ጉዳዩ የጋራ ጉዳይ መሆኑን ተረድታቹ ከማንኛውም በፊት ቅድሚያ በመስጠት እንድትገኙ አደራ እያልን ከዚህም በተጨማሪ በኢንተርኔት የተለቀቀውን የፊርማ ማሰባሰቢያ ሰነድ ላይ ፊርማችሁን በማስቀመጥ ተባበሩ::
የሰልፉ ቀን፥ 29/01/2014 ቦታ፥ Bundesamt for Migration and Refugees (BAMF) Frankenstr. 210 90461Nürnberg
ሰአት፥ 12°° (ምሳ ሰአት)
ማሳሰቢያ፥ ሰአት ይከበር የተለያዩ መፈክሮች ከተቻለ
EPCOU-GERMANY
015211790603
www.epcou-bayern.de