Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአየር ሃይል የበረራ አስተማሪዎች ታሰሩ

$
0
0

ሚያዝያ ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ሰሞኑን ከፍተኛ የደህንነት ሃላፊዎች  ያስተላለፉትን ድንገተኛ ትእዛዝ ተከትሎ በፌደራል ፖሊስ አባላት የእጅ ስልኮችና የኢሜል አካውንቶች ላይ በተደረገ ፍተሻ፣ የተቃዋሚ መሪ ፎቶዎችን፣ አገራዊ ሙዚቃዎችንና ማንኛውም ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸውን ጽሁፎች ከኢንተርኔት አውርደው በስልካቸው ላይ ያስቀመጡ ፖሊሶች ተይዘው የተወሰኑት ማእከላዊ ሲገቡ፣ የተወሰኑት ደግሞ ጃንሜዳ አካባቢ በሚገኝ እስር ቤት መታሰራቸውን የፖሊስ ምንጮች ገልጸዋል።

ethiopian airforceበድንገት የተደረገውን ፍተሻ ተከትሎ በአጠቃላይ ከ120 ያላነሱ ፌደራል ፖሊስ አባላት ሲታሰሩ፣ በፍተሻው በቀጥታ የተቃዋሚ መሪዎች ፎቶዎች ወይም ፖለቲካ ነክ የያዙ ጽሁፎች የተገኙባቸው 37 የሚሆኑ ፖሊሶች ማእከላዊ ተወስደው ታስረዋል።

ከ80 በላይ የሚሆኑት ደግሞ አጠራጣሪ የሆኑ ጉዳዮች አሉ በሚል ለተጨማሪ ምርመራ ጃን ሜዳ አካባቢ በሚገኝ ማቆያ እንዲታሰሩ ተደርጓል።

የፌደራል ፖሊስ አዛዦች የሚሰጡትን ትእዛዝ ላለመቀበል ያንገራግራሉ ተብለው አስቀድመው በተለዩ ፖሊሶች ላይ ደግሞ ክትትሉ መጨመሩን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በዚህም መሰረት በአርማጭሆና ሰሜን ጎንደር የጸረ ሽብር ግብረሃይል ሃላፊዎች የሆኑት ኢንስፔክተር ስንታየሁ፣ ሳጅን አበበ እና ም/ል ሳጅን ብርሃኑ ተይዘው ወደ ማእከላዊ ተወስደዋል።

በእስር ላይ የሚገኙት የግንቦት7 ዋና ጻሃፊ የአቶ አንዳርጋቸውን ፎቶ ግራፍ በብዙ ወታደሮች ሞባይል ስልኮች ላይ መገኘቱን ምንጮች አክለው ገልጸዋል።

ከድምጻውያን ደግሞ የቴዲ አፍሮ፣ የብርሃኑ ተዘራና የፋሲል ደሞዝ ሙዚቃዎችን ከኢንተርኔት አውርዶ ማዳመጥ ኢህአዴግን እንደመክዳት እያስቆጠረ ነው ተብሏል።

በተመሳሳይ ዜና  ድሬዳዋ ውስጥ በበረራ አስተማሪነት ይሰሩ የነበሩ ሁለት መኮንኖች ሰሞኑን ተይዘው ማእከላዊ መታሰራቸውን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል። ስማቸውን እስካሁን ለማወቅ ባይቻልም፣ አብራሪዎቹ ቀድም ብሎ ከታሰሩት 4 አብራሪዎች ጋር ግንኙነት ነበራችሁ ተብለው መታሰራቸው ታውቋል።

የኤም 35 ተዋጊ ሄሊኮፕተር የበረራ አስተማሪ የነበረው የሻለቃ አክሊሉ መዘነ ወንድም ሰይፉ መዘነም ማእከላዊ ታስሮ በመሰቃየት ላይ ነው። የቀድሞው አንድነት ፓርቲ የአመራር አባል የነበረው መሳይ ትኩም ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት ነው።

ገዢው ፓርቲ በደህንት ተቋማት ላይ ያለው ጥርጣሬ ከመቼውም ጊዜ በላይ ከፍ እያለ መምጣቱን የሚናገሩት ምንጮች፣ ተጨማሪ ፍተሻዎች፣ ድንገተኛ ግምገማዎችና እስሮች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገልጻሉ።

የጥርጣሬው መነሻ ምን እንደሆነ በውል ለማወቅ አልተቻለም። ይሁን እንጅ ስራቸውን እየለቀቁ የሚጠፉ የፌደራል ፖሊሶች ቁጥር መጨመር ስርአቱን ስጋት ላይ ሳይጥለው እንደማይቀር ምንጮች  ይገልጻሉ።

The post በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላት እና የአየር ሃይል የበረራ አስተማሪዎች ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


በአማራ ክልል ሊመደብ የነበረው የኮማንዶ ጦር እቅድ ተሰረዘ * አለመተማመኑ በርትቷል

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ) – የመጭው ምርጫ ጋር በተያያዘ ስጋቱ እያየለበት የመጣው የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ አምባገነን ቡድን በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር እና በጎጃም ክፍለሃገራት ሊመድበው የነበረው የኮማንዶ ጦር እቅድ በጦሩ ውስጥ ያለውን ጉምጉምታ እና አለመተማመን ስላሳሰበው መሰረዙን እና ጦሩ ወደ ካምፕ እንዲመለስ መደረጉን ለጄኔራል ሰአረ መኮንን ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

(ፎቶ ከፋይል)

(ፎቶ ከፋይል)


ሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በጦሩ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እና ሕዝቡ በጦሩ ላይ ጫና እንደፈጠረ እንዲሁም የከተማ ፖሊሶች የሕዝብ ወገንተኝነት ማሳየታቸው የፌዴራል ፖሊሶች ግምገማ የፈጠረው ችግር የደህንነቶች መክዳት የህዝቡ ለውጥ መሻት ተደማምሮ አለመተማመኖች በስርአቱ ውስጥ እየሰፋ እንዲሄድ አድርጎታል::በሰራዊቱ ውስጥ የተከሰተው አለመተማመን እየሰፋ እና እርስ በእርስ በጥርጣሬ መተያየት እየነገሰ መምጣቱ ሰራዊቱን በሕዝቡ መሃል ብናሰፍረው መሳሪያውን በመንግስት ባለስልጣናት ላይ ሊያዞር ስለሚችል በካምፕ እንዲቆይ እና በታትኖ ከአጋዚ ጦር ጋር መቀላቀል እና በተለያዩ አከባቢዎች ላይ እንዲመደብ የሚል ሃሳብ ቀርቧል::

የሕዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ በከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቶ እየዳከረ በጠበንጃ ሃይል ሕዝብን ፈጅቶ ስልጣኑን ለማስረዘም እየሰራ መሆኑን ይታወቃል::ሰሞኑን የደረሱ መረጃዎች አዲስ አበባ በአጋዚ ጦር እና በፌዴራል ፖሊሶች እየተሸበረች መሆኗን መግለጹ ይታወሳል::

The post በአማራ ክልል ሊመደብ የነበረው የኮማንዶ ጦር እቅድ ተሰረዘ * አለመተማመኑ በርትቷል appeared first on Zehabesha Amharic.

በሞያሌ ሕወሓት የሚመራው መንግስትን ይደግፋሉ የተባሉ ንግድ ድርጅቶች ውድመት ደረሰባቸው

$
0
0

በሞያሌ በተነሳው ተቃውሞ ከገዢው ፓርቲ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉ ሆቴሎች ከፍተኛ ውድመት ደረሰባቸው
ኢሳት ዜና :- የከተማ ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት በከተማዋ ከሚታወቁት ሆቴሎች መካከል ፈቃዱ ሆቴል ፣ ኢትዮ ኬኒያ ሆቴል ፣ ሃጎስ ሆቴልና ማሕሌት ሆቴል ጉዳት ድርሶባቸዋል።

Moyale Main Street (Photo file)

Moyale Main Street (Photo file)


የሆቴሉ ባለቤቶች የገዢው ፓርቲ ደጋፊዎች ናቸው በሚል ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ነዋሪዎች ተናግረዋል። በተለይ ኢህአዴግን በመደገፍ እና ቅስቀሳ በማድረግ የሚታወቁት የማህሌት ሆቴል ባለቤት ንብረት ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል። የአካባቢው ሽማግሌዎችና የጎሳ መሪዎች የተጎዱ ሆቴሎችን የጎበኙ ሲሆን ፣መረጋጋት እንዲፈጠር ነዋሪዎች ለማሳመን እየጣሩ ነው።

ከሞያሌ ወጣብላ በምትገኘው ኩሌንሳ መንደር የተኩስ ድምጽ መሰማቱን የገለጹት ምንጮች፣ ውጥረቱ አሁንም ድረስ እንዳለ ተናግረዋል። በመከላከያ ሰራዊት አባላትን በሶማሊ ክልል ታጣቂዎች መካከል የተነሳው ግጭት በፌደራል ፖሊሶች ጣልቃ ገብነት ቢበርድም፣ በማንኛውም ጊዜ ሊነሳ ይችላል በሚል ነዋሪዎች ስጋታቸውን ገልጸዋል። ትምህርት ቤቶች፣ የመንግስት መስሪያ ቤቶችና አንዳንድ ድርጅቶች ዛሬ መከፈታቸውን ለማወቅ ተችሎአል።

The post በሞያሌ ሕወሓት የሚመራው መንግስትን ይደግፋሉ የተባሉ ንግድ ድርጅቶች ውድመት ደረሰባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

ደርባን ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ VOA

$
0
0

south africa

በደቡብ አፍሪካይቱ ደርባን ከተማ ካለፈው ሣምንት ማብቂያ ጀምሮ በውጭ ሀገር ዜጎች ላይ በደረሱ ጥቃቶች ቢያንስ አምስት ሰው መገደሉን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

ትናንት፤ ማክሰኞ – ሚያዝያ 6 / 2007 ዓ.ም ደርባን ከተማ ጎዳናዎች ላይ ሁከት ተፈጥሯል።

ኢትዮጵያዊያኑን ጨምሮ ደርባን ውስጥ የሚኖሩ አፍሪካዊያን በፍርሃት ቤታቸውን ዘግተው ተቀምጠዋል።
[jwplayer mediaid=”40550″]

The post ደርባን ደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያዊያን ተገደሉ VOA appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አመራር ምክር ቤት የተሳካ ጉባኤ አካሄደ

$
0
0

shengoበቅርቡ የሽንጎው ከፍተኛ አመራር አካል የሆነው ምክር ቤት ባካሄደው የሁለት ቀን ስብሰባ  ሀገራችን ኢትዮጵያ የምትገኝበትን ሁኔታ በሰፊው መርምሮ  ለቀጣዩም ትግል ምን መደረግ እንዳለበት መመሪያ በመሰጠት ተጠናቋል።

በተጨማሪም የሽንጎው የተለያዩ የስራ ክፍሎች የስራ አፈጻጸምን በተመለከተ የቀረቡለትን ሪፖርቶች መርምሮ ትግሉ ተጠናክሮ የሚቀጥልበትን ተጨማሪ መመሪያ በመስጠት ተጠናቋል። በተለይም ደግሞ ሽንጎው በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚያካሂደው ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ የተገኙትን መልካም ግንኙነተቶችን እና አበረታች ውጤቶች ከመረመረ በኋላ በዚህ መስክ የሚካሄደው እንቅስቃሴ እጅግ ተጠናክሮ እንዲቀጥል መመሪያ ሰጥቷል፡

የሸንጎው ምክር ቤት የኢትዮጵያን አጠቃላይ ተጨባጭ ሁኔታ የገመገመ ሲሆን፣ በሀገሪቱ ውስጥ እጅግ ተጠናከሮ የቀጠለውን ሁለንተናዊ የመብት ረገጣ ፣ በተለይም ደግሞ ባሁኑ ሰአት ዜጎች መሰረታዊ የሆነውን መሪዎቻቸውን በድምጻቸው በነጻነት የመመምረጥ መብታቸውን በትክክል እንዳይገልጹ ገዥው ሕወሀት/ኢህአዴግ እና እንደልቡ የሚያዛቸው የምርጫ የጸጥታና የፍትህ ተቋማት በህዝባችን ላይ በቀጣይነት እያሳዩት ያለውን እጅግ አሳዛኛ ግፍ ባፅጽንኦና በታላቅ ሀዘን ተገንዛቧል።

በዚህ እጅግ ፈታኝ ሁኔታ ውስጥ፣ የፖለቲካ መድረኩን ለገዥው ቡድን ባለመተው የህዝባችንን መብት ለማስከበር እጅግ ብዙ መስዋእትነት ለከፈሉ እና በመክፈል ላይ ለሚገኙ ታጋዮች ሁሉ ያለውን አድናቆት አክብሮትና የትግል አንድነት ምክር ቤቱ በድጋሜ አረጋግጧል።

ገዥው ቡድን ሕወሀት ኢህአዴግ የህዝባችንን መብት በሁሉም መልኩ መርገጡን በቀጠለ ቁጥር ህዝባችን ደግሞ በስርአቱ ላይ ያለው ብሶት ቅሬታና  ጥላቻ፣ እጅግ እየሰፋ መምጣቱን፣ የሚደርስበት ግፍ ሊሸከመው ከሚችለው በላይ እንደሆነም ብዙ መረጃወችን ምክር ቤቱ ተመልክቷል።ዛሬ ህዝባችን ከዚህ ስርአት መልካም ነገርን መጠበቅ ትቷል፡ በራሱ አነሳሽነት ስርአቱ እንዲወገድለት አምርሮ ይፈልጋል፡ አልገዛም ማለትን በየቦታው እያሳየ ነው። ለመብቱ መቆምን፣ በግልጽ ማሳየቱን ቀጥሏል፤ የፍርሀት ድባብን አፈራርሶ በመጣል ላይ ይገኛል።

ከዚህ በተጨማሪም በገዥው ሕወሀት ኢህአዴግ ውስጥ የርስበርስ አለመተማመን እና ውጥረትም እየሰፋ መምጣቱን የሽንጎው ከፍተኛ አመራር  ምክር ቤት በሰፊው ቃኝቷል።

እነዚህን ሁሉ ባንድ ላይ ስንመለከትም ሀገሪቱ ውስጥ ህዝባዊ የለውጥ አመጽ ሊነሳ የሚችልበት ሁኔታ እጅግ በፍጥነት እየተቃረበ መሆኑን ሽንጎው ተገንዝቧል።

ገዥው ሕወሀት ኢህአዴግ ከላይ  ሲታይ ሁኔታወችን የተቆጣጠረና የተረጋጋ ይምሰል እንጂ ከሁሉም ህዝብ፣ ከሁሉም ፖለቲካ ድርጅቶች፣ ሲቪክ ማህበራት የሀይማኖት ተቓሞች ጋር የገባበት ቅራኔ የራሱን ጥላ ሳይቀር ማንንም እንዳያምን ስላደረገው እነሆ ሌትም ቀንም በመደናበር ካንዱ ስህተት ወደሌላው እየተላተመ ወደ መጨረሻው መቃብሩ እንደተቃረበ እንረዳለን።

ሀላፊነት የጎደለው ሕወሀት ኢህአዴግ ጠባብ ቡድን ከራሱ ስልጣን እና አልጠግብ ባይ ዝርፊያ ባሻገር ለማገናዘብ ባለመቻሉም ሀገሪቱን ራሷን ወደ አደጋ አፋፍ አድርሷታል።

ይህን ሀገራችን የምትገኝበትን ሁኔታ የሚከታተሉ የሀገሪቱ ጠላቶችም የህዝባችንን የለውጥ እንቅስቃሴ ለአደጋና ለራሳቸው ቀጣይ አጥፊ አጀንዳ ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ሸንጎ ተገንዝቧል።

ሐገራችንና ህዝባችን ከታሰሩበት  የግፍ ሰንሰለት ነጻ ለማውጣትና በምትኩም  አንድነቷ በተጠበቀ ኢትዮጳያ ስር ህገመንግስታዊ ዴሞክራሲአዊ ስርአትን ለመገንባት የሚደረገው ትግል ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሽንጎው ምክር ቤት መመሪያ የሰጠ ሲሆን፣ ይህን ትግል ወደግብ ለማድረስም ሆነ ከላይ የጠቀስናቸውን አሳሳቢ ሁኔታወች ለማስወገድም ያንድነት ሀይሎች ከምን ጊዜውም በላይ በመተባበር በንቃት እንዲንቀሳቀሱ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርቧል።

ሐገራችን ከምትገኝበት አስከፊ ሁኔታ ሁሉም አሽናፊና ተጠቃሚ ወደሆነበት ስርአት ለመሽጋገር ብሄራዊ መግባባትና ብሄራዊ እርቅ አማራጭ የሌለው እንደሆነ ምክርቤቱ አጽንኦ ሰጥቷል።

የሸንጎው ያመራር ምክር ቤት ዛሬ በሚካሄደው ትግል ውስጥ ያማራጭ ሚዲያን አስፈልጊነት በሰፊው ከተወያየ በኋላ፤ ወደ ኢትዮጵያ የሚተላለፍ ያጭር ሞገድ ሬዲዮ ፕሮግራም ባስቸኳይ እንደሚያስፈልግና፣ ይህን እቅድ ተግባራዊ ለማድረግም በውጭ የሚገኙ እትዮጵያውያን በገንዘብ እና ጊዜያቸውን በማበርከት ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

The post የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ አመራር ምክር ቤት የተሳካ ጉባኤ አካሄደ appeared first on Zehabesha Amharic.

በደቡብ አፍሪካ እየተፈጸመ ያለውን ስደተኞችን የማጥቃትና ማሳድድ ወንጀል በመቃወም ሰልፈኞች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ

$
0
0

south africa
ኢሳት ዜና :- በደቡብ አፍሪካ የውጪ ሀገር ዜጎች ላይ የተፈጸመው ጥቃት ያስቆጣቸው በርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ደርጊቱን ለማውገዝ በደርባን ታላቅ ሰልፍ ማድረጋቸውን የአገሪቱ የመገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

በ10 ሺዎች የሚቆጠሩ ደቡብ አፍሪካውያን እና የውጭ አገር ዜጎች በሰልፉ ላይ ተገኝተዋል። “የውጪ ሀገር ዜጎችን ማጥቃትና ማሳድድ ይቁም!” የሚል መፈክር ያነገቡት የደርባን ነዋሪዎች፤ በጥቃት ፈጻሚዎቹ ላይ ተቃውሟቸውንና ቁጣቸውን ገልጸዋል።

ሰልፈኞቹ ትናንት በደርባን የተፈጸመውን ድርጊት ከማውገዝ ባሻገር ለውጪ ሀገር ዜጎች ያላቸውን አጋርነት በይፋ አረጋግጠዋል።.
ሰሞኑን በደርባን በተፈጸመው ጥቃት በትንሹ 5 ሰዎች መገደላቸውንና የበርካታ ሰዎች ሱቆች መዘረፋቸውን ቢቢሲ አመልክቷል። ከሟቾቹ ውስጥ ሶስቱ ኢትዮጵያውያን ናቸው።

በደርባን የሚገኙ ኢትዮጵያኖች ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል አስፈላጊውን እርምጃ እየወሰዱ ነው። በደቡብ አፍሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲ ወኪል ወደ ደርባን በማቅናት ኢትዮጵያውያኑን ማነጋገሩን የደሰረን መረጃ ያመለክታል። ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ የደረሰውን ጥቃት የማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም እያወገዙት ነው።

በደርባን የተፈጸመው እርምጃ በጆሃንስበርግም ይደገማል የሚል የስልክ መልእክት ተላልፎአል በሚል፣ በከተማዋ የሚገኙ የውጭ አገር ነዋሪዎች ሱቆች ተዘግተው አርፍደዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2008 ዓመተ ምህረት በውጪ ሀገር ዜጎች ላይ በተፈጸመ ተመሳሳይ ጥቃት 62 ሰዎች እንደተገደሉ መዘገብቡ አይዘነጋም።

የዙሉ ንጉስ የውጪ ሀገር ሰዎች ሻንጣቸውን ሸክፈው ወደሀገራቸው መሄድ አለባቸው በማለት ያደረጉት ንግግር ለጥቃቱ መጀመርና መባባስ ዋነኛ ምክንያት መሆኑ ተመልክቷል። እርሳቸው ግን ለችግሩ ተጠያቂ አይደለሁም በማለት አስተባብለዋል።
ጥቃቱ መፈጸሙን ተከትሎ ማላዊ ዜጎቿን ከደቡብ አፍሪካ በማውጣት ቀዳሚዋ ሀገር ስትሆን፤ ዚምባቡዌም ድርጊቱን በይፋ በማውገዝ በውጪ ዜጎች ላይ የሚፈጸመው ጥቃት እንዲቆም ጠይቃለች።

The post በደቡብ አፍሪካ እየተፈጸመ ያለውን ስደተኞችን የማጥቃትና ማሳድድ ወንጀል በመቃወም ሰልፈኞች ድምጻቸውን ሲያሰሙ ዋሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአረብ ሀገር እስከ ደቡብ አፍሪካ * የስደተኛው ሮሮና የመንግስት ቸልተኝነት ! (ይድረስ ለክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም …)

$
0
0

ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

የማለዳ ወግ …ከአረብ ሀገር እስከ ደቡብ አፍሪካ
የስደተኛው ሮሮና የመንግስት ቸልተኝነት !

* ይድረስ ለክቡር ዶር ቴዎድሮስ አድሃኖም …
* ኢህአዴግን እንዴት እንምረጥ ?

ትናንት በሁከት ፣ ዛሬ በመፈራረስ በሚመስል አደገኛ የለውጥ ሂደት ውስጥ ባለችው የመን የኢትዮጵያውያን የድረሱልኝ ድምጽ ከነኡኡታው ሰላም ይነሳል ። በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያን ስደተኛ ወገኖቻችን ላይ ከኢራቅና ሶርያ አይ ኤስ አይ ኤስ ISIS ጽንፈኞች ባላነሰ ከፍ ሲል በሰብአዊው ዜጋ ፣ ዝቅ ሲል ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ በተለያዩ የውጭ ዜጎች ላይ የተጀመረው ጥቃት ሊያዩት ሊሰሙት ይከብዳል ። በሰላ ገጀራ ፣ ሰንጢ የሰው ፍጡር የመቆራረጥና ፣ በእሳት የማቃጠልን የአውሬ ተግባርን መመልከት ዘልቆ ልብን ይሰብራል ። ይህ ሁሉ ሲሆን ” መንግስ አለን !” ባዮች ኢትዮጵያውያን ፈጥኖ ደራሽ ቀርቶ ጉዳቱን አጥብቆ የተቃወመ መንግስት ባለማየታችን አዝነናል !
Saudicry
በአንድ ወቅት ብቻ ሳይሆን በተደጋጋሚ ” ኢህአዴግን ምረጡ !” በሚል በማህበራዊ መገናኛ የፊስ ቡክ ቅስቀሳ ዘመቻዎ ባስተላለፉት መልዕክት የፈረደበት መንገድ ፣ ህንጻውንና ግድቡን በፎቶ አሸብርቀው ” እነሆ ሰርተን አሳይተናል ፣ ስራ ላይ ነን !” በማለት “የወሬ የለው ፍሬ ” በሚልና “ስራ እንጅ ወሬ አናውቅም ” የሚል አንድምታ ያለው መልዕክት አስተላልፈው ተመልክቻለሁ ። ለድርጅትዎ ቀናኤ መሆንዎን አልቃወምም ። ዳሩ ግን በስደት ህይዎቴ በድርጅትዎ የሚወከሉ ባለስልጣኖችም ሆኑ ተራ የድርጅትዎ ካድሬዎች የመንገድ ህንጻውንና ግድቡ ከእነ ተሳላጠው የሃገር እድገት እያነሱ በመጣል ከመደስኮር ፣ ለድጋፍ ገንዘብ ለመሰብሰብ ከሚደረገው ድግስና የስብሰባ ጥሪ ባሻገር ለዜጋው መብት ማስከበር ቆመው አይቸ ፣ ሰምቸ አላውቅም ። እናም ሀገር የማለት ትርጉሙ ቅጥ አንባሩ ይጠፋብኛል !

በማዲባ ምድር በደቡብ አፍሪካ በዜጎች ላይ እየተፈመ ያለውን አሰቃቂ ግፍ እንደ ዜጋ አሞኛል ። ድርጊቱን በአደባባይ የሚያወግዝልን መንግስት ማጣታችን አውጥቸ አውርጀ ለዜጎች መብት ማስጠበቅ ተግቶ የማላውቀው ኢህአዴግን ብመርጥ ሀገሬ ህዝቤ ምን እንደሚሆኑ ማሰቡ አልተሳነኝም ። …አናም መንግስትዎ እንደ ዜጋ የስደተኛ መብታችን ካስጠበቀልን እንጅ ግዑዙን መንገድ ስለሰራ ፣ ህንጻውን ስላቆመና ግድቡ ስለገደበልኝ ፣ በአንጻሩ መሆን አለበትን ? ስል ከራሴ የወጣ ፈታኝ ጥያቄ አንገላታኝ… እናም ትናንትም ሆነ ዛሬ ኢህአዴግ ለዜጎች መብት እስካልተጋ ድረስ እንዴት ኢህአዴግን እንምረጠው ? አልኩ ቢቸግረኝ …

የሆነው እና እየሆነ ያለው ቢያከፋኝና ፣ ቢያስጨንቅ ፣ ቢያስጠብበኝ ወቀሳ ቢጢ ልልክልዎ ነሸጠኝ … ! ብዕሩን በቀለም ነከሬና ወረቀቱን አቅርቤ የታወከው ውስጤ እርሙን ያወጣ ዘንድ እንደለመድኩት በማለዳ ወጌ ብሶቴን መተንፈሱን መረጥኩ … ንዴት ብስጭቴ አይሏልና ክብርዎን እንዳልነካ በመጠንቀቅ እራሴን አረጋግቸ ስሞታ ፣ ቅያሞቴን አሳምሬ በማውቀው የአረብ ሀገሩ ስደት በጨረፍታ ልጀምረው ፈቀድኩ … !

ከሁሉ በማስቀደም ከ20 ዓመታት ወዲህ ዘንድሮ ወግ ደርሶን ባለሙያ ወደ አካባቢው መላኩን ባልክድም ፣ ከዚህ ቀደም በአረብ ሃገራት በዜጎች መብት ጥበቃ የገጠመን የባለሙያ ተወካይና የመንግስት ትኩረት እጦት ፈተና ግን እንዲህ በአጭሩ የሚገለጽ አለመሆኑን ከጅመሩ አስረግጨ ልነግርዎ ደስ ይለኛል ! …ግን በአጭሩ ልሞክረው …

እርስዎ የጤና ጥበቃ ሃላፊ ከመሆንዎ በፊት ጀምሮ እስከዚህች ሰዓት ላለፉት 20 አመታት በአረብ ሀገር የመ ብት አስጠባቂ ተቆርቋሪ አጥተን ስለመናቅ መዋረዳችን ፣ ስለመገፋት መገደላችን ፣ ስለ ስደቱ አስከፊነት የሚደ ርሰውን በደል በከፊልም ቢሆን በማቀርባቸው መጣጥፎች ባለፈ በአንጋፋው የጀርመን ራዲዮ የዜጎችን ይዞታ ላልሰሜ ለማሰማት ሞክሬያለሁና ” ሁሉን ቢባገሩት ሆድ ባዶ ይቀራ ል ” የምል ዜጋ አይደለሁም ! እኔን ሆንኩ መሰሎቸ የዜጎች መብት ይከበር ፣ የመብት ጥበቃ ይደረግልን እያልን ድምጻ ችን ያሰማን ቢሆንም ሰሚ በማጣታችን ግፉ ከጠበቅነው በላይ ሆኖ አሁን ድረስ ቀጥሏል …

የእኛ እውነት የእናንተ ስህተት …
====================

ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
እርስዎ የተኳቸው የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የአሁኑ የተከበሩ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ወደ ሳውዲ አረቢያ ለጉብኝት መጥተው የኮንትራት ስራ ኢትዮጵያውያንን ለመቀበል ሳውዲዎች ፍላጎት ማሳየታቸ ውን ለሳውዲ ታዋቂ ጋዜጦች መግለጫ ሰጥተው እንደ ሄዱ ያለምንም ቅድመ ዝግጅትና ጥናት የኮንትራት ስራውን ሲጀመር ከቀሩት ወገኖቸ ጋር በመሆን ህጋዊ የኮንትራት የሁለትዮሽ ውል ሳይደረግ ዜጎችን መላኩ አደጋ አለው በሚል የተቃውሞ ድምጻችን ስናሰማ የስምምነት ህጋዊ ውሉን መፈራረምና አማራጩ ቅድመ ዝግጅት ማድረግ ነው ብንልም ሰሚ አላገኘንም ። በአጭር ጊዜ ህጋዊ ውል በሌለው ስምምነት በኮንትራት ስራ ስም ዜጎች ይላኩ ጀመር ። ከጅምሩ እስከ አሁን ያለውን አሰቃቂ የእህቶቻችን የመከራ ዋይታ መስማት ጀመርን ። እርስዎ ወደ ስልጣን በመጡ ማግስት ያለምንም ጥናትና ቅድመ ዝግጅት የተጀመረውን በድርጊቱ ሁሉ ከታመሙት መካከል የምወዳት ሃገሬ እጓለማውታ ስደተኛ አንዱ እኔ ነኝ !
Tedros-Adhanom-
ምንም እንኳን ዛሬ መንግስትዎ ዜጎችን ያለ ሁለትዮሽ ውል ወደ አረብ ሀገራት ለስራ መላኩ ስህተት እንደነበር ማመኑን ሳስበው እታመማለሁ። ዛሬ እውነቱ በሂደት ፍን ትው ብሎ ወጥቶ እኛ የሰጠነው መረጃ ትክክል እናንተ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ዜጎችን በኮንትራት ስራ ስም ያለ ውል መላካ ችሁ ስህተት መሆኑን ብታምኑም የዜጎች ህይዎት የተገበረበት የአካሄድ ስህተት አንኳ ይቅርታ አልጠየቃችሁም። ይባስ ብላችሁ አሁንም ባለ ድርሻ አካላት በግልጽ ያልመከሩበት አዲስ ህግ ተረቆ ለትግበራ ጥድፊያ ላይ መሆናችሁ ለዜጎች ታስቦ ነው አልልም ። ያኔ እንደ ዜጋ አግብቶን ስንናገር ባለመሰማታችን እናንተ ተሳሳታችሁ እነደነበር ዛሬ በአደባባይ አመናችሁ ፣ ዛሬም እንደ ዜጋ አግብቶን ረቂቅ ህጉን ባለድርሻ ዜጎች ይወያ ዩበት ስንል ሰሚ አጥተን ” ግመሏ ትሄዳለች ውሻዎች ይጮሃሉ! ” አይነት የተለመዴ አካሄድ የተያዘ ለመሆኑ የሚያሳብቁ ኩነቶች ታጅበን እየተጓዝን እንገኛለን ! ከአንድ አመት በፊት ” ስደት ይብቃ !” በሚል መሪ ቃል በሚሊኒየ ም አዳራሽ ከአፍ እስከ ደገፉ የሞሉ ታዋቂ ሰዎችና ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ልብ አሸብሮ ያስለቀሰው ግፍ እንዲፈጸም ምክንያቱ ስህተታችሁ አልነበረምን? ዛሬስ እንዴት ያ ሁኔታ ባለበት እንዲቀጥል ትፈቅዳላችሁ ? ለምንስ አትሰሙም ?

በደቡብ አፍሪካስ ለኢትዮጵያውያን የት አላችሁ?
==============================
ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ…

ወገን በደቡብ አፍሪካ ለሳምንት በአጣብቂኝ ውስጥ ወድቆ ከአይሲኤስ በማይተናነሱ የደቡብ አፍሪካ አውሬዎ ች በኢትዮጵያውያን ላይ ግፍ ሲፈጽሙ የት አላችሁ ? ኢት ዮጵያውያን ስደተኞች ሃብት ንብረታቸውን እየተቀሙ ፣ እየተ ዘረፉ ሲሳደዱ ፣ ሲወገሩ ፣ በእሳት ሲነዱንና ጨፈጨፉ ሲፈጸምባቸው ማትረፍ ባትችሉም እንዴት ድርጊቱን ማውገ ዝ ተሳናችሁ ? ዜጎች መደፈር የአገር ህመም አልሆን ብሎ ፣ የሀገራቱ ሁለትዮሽ ዲፕሎማሲያዊው ግንኙነት እንዳይ ናጋ ይሆን ? እውነት እልዎታለሁ … እርስዎ በከፍተኛ ኃላ ፊነት ያስቀመጠዎ መንግስት ፣ እርስዎም እንደ ውጭ ጉዳይ ኃላፊነትዎና እንደ ዜጋ የዜጎችን መብት ለማስከበር ተቃውሞ ድመወጻችሁን ለአለም አላሰማችሁም ። ይህም ስታደርጉ ትልቁን ሃላፊነት አልተወጣችሁምና አዝኛለሁ !
south africa
ከአፖርታይድ የነጻነት እለህ አስጨራሽ ትግል በደ ገፍናት ፣ ለመሪዋ ለማንዴካ መሸሸጊያ ፣ ለታጋይ ፋኖዎቿ መጠጊያና ስንቅ ትጥቅ ያቀበለችው ሃገር ዜጎች በደቡብ አፍሪካ ዘረኛ ወሮበሎች ተደፍረናል ። በህግና በስርአት በምትመራ በምትባለው ስልጡን አፍሪካዊት ሀገር በደቡብ አፍሪካ ፣ በአለማችን የነጻነት ታጋይ በክቡር ኔልሰን ማን ዴላ ምድር ፣ ነጻነቷን ከወራሪ አስከብራ የኖረችው ሀገር የኢትዮጵያ ልጆች ግፍ ተፈጽሞብናል ። በዘር ጥላቻ የወገን ደም ረክሶ በሰላ ገጀራ አካላቸው ሲጎመድ ፣ ሲቃጠሉን ሲገደሉ እያያችሁ ዝምታን መምረጣችሁ እኔ በግል በመን ግስት ላይ ተስፋ እንድንቆርጥ አድርጎኛል ። አፋጣኝ የወ ገን አለኝታነትን አለማሳየታችሁ እኔን ብቻ ሳይሆን ሀገር ወዳዱን ደጋፊዎችዎን ሁሉ ማስቆጣቱን ማምሻውን በለቀ ቁት ብጣሽ መረጃ ስር የተጻፈውን የሰላ ሂስ ማንበቡ ብቻ በቂ ይመስለኛል ።

ክቡር ሚኒስትር ዶር ቴዎድሮስ በደቡብ አፍሪካ ዜጎ ቻችን ላይ አፋጣኝ እርምጃ አለመውሰዳችሁ በመስሪያ ቤትዎም ሆነ በመንግስት ተስፋ ያልቆራጥን የነበርንን ጥቂት ገለልተኛ ነን የምንል ወገኖችን ሞራል አልጠበቀል ንም ። ከእኛ አልፎ ሲደግፉ ያው ግዑዙን መንገድ ህን ጻውን ፣ ግድቡን ፣ “ተንፈላሰሳችሁበት ” የሚሉንን ሞክ ራሲና እድገቱን ከመጥቀስ ፈቀቅ የማይሉ ፣ የሚሰደደውን ህልቀ መሳፍርት ዜጋ ድህነት ፣ የኑሮ ውድነትና የአውራ ፖርቲ ፖለቲካ ትንኮሳ ምክንያት አስረግጠው ለማስረዳት በቂ ምክንያት የሚያጥራቸውን ከነፍሳቸው ጋር የታረቁ ደጋፊዎቻችሁን ተቀይመዋችኋል። እነሱን ለማጽናናት ሲባል ቢያንስ
” … የኢህድሬ መንግስት ና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዜጎቹ የሚፈጸመውን አሰቃ ቂ በደል በመቃዎም የደቡብ አፍሪካን አንባሳደር በአስቸኳ ይ ጠርቶ አፋጣኝ እርምጃ እንዲዎስድ ማስጠንቀቂያ ሰጠ ! ይህ ካልሆነ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ግንኙነት እስከመቋረጥ የሚያደርስ እርም እንደሚወስድ መንግስት ያወጣው መግለጫ አስታወቅ !”
ተብሎ በቴሌቪዥንና በራሳችሁ ራዲዮ መስማቱን ናፍ ቀነው የውሃ ሽታ ሆኖ ሳንሰማው ቀረን … እርስዎም ቢሆን መረጃው እንደ ደረሰዎ በትኩሱ በለመድነው ዘመነኛ መረ ጃ ቅበላዎ የረባ መረጃ ስላልሰጡን የለውጥ ተስፋ ያለን ሁሉ ምኞት ከንቱ መሆኑን አሳይቶ የማይጨበጠውን ተስፋ አጨናግፎታል !

እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው …በጥሞና ይስሙኝ !
==========================

ክቡር የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር …
ክቡርነትዎም ሆኑ የሚመለከታችሁ እንዲህ እንደ ተዋረድን ፣ እንደ ከሸፍን እንዳንቀር ፣ በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመብንን ግፍ የሚመለከት ከእርስዎና ከኢትዮጵያ መንግስት የምንጠብቀው ከብዙ በጥቂቱ ሃሳቤ የሚከተለው ነውና በጥሞና ስሙኝ !

1ኛ / የኢትዮጵያ መንግስት በደቡብ አፍሪካ እየተፈጸመባቸው ላለው ግፍና በደል ለድርድር እንደማይቀርብ በማስገንዘብ ለአለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን በአደባባይ ከዚያም አልፎ ለአለም አቀፉ ማህበረሰብ ጠንከር ያለ መግለጫ መስጠት አለበት ።

2ኛ / ለነጻነት ትግሉ ከፍተኛ ተጋድሎ ያደረገችው ሃገር የኢትዮጵያ ዜጎች በደቡብ አፍሪካ የተፈጸመባ ቸውን ግፍ ህዝብን ያስከፋ ያስቆጣ ድርጊት መሆኑን በሀገር ቤት መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር በግልጽ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፎች እንዲደረጉ መፍቀድ ።

3ኛ / ተቀማጭነታቸው አዲስ አበባ ያደረጉትን የደቡብ አፍሪካ ፣ የአፍሪካ ህብረት ፣ የተባበሩት መንግስታትን ከፍተኛ ኃላፊዎች በመጥራት በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው በደል የሁለቱን ሃገር ግንኙነት እስከ ማቋረጥ የሚደርስ እርምጃ እንደሚያስከትል ከበድ ማስጠንቀቂያ መስጠት ።

4ኛ / በህግና ስርአት የፕሬ ጃኮብ ዙማ ትተዳደራለች በምትባለው የደቡብ አፍሪካ መንግስት ግፍ በዜጎቻችን መፈጸሙን በአጽንኦት ለማስረዳት በጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በእርስዎ የሚመራ ቡድን በአስቸኳይ ወደ ደቡብ አፍሪካ ሊሄድ ይገባል ።

5ኛ / ወደ ሀገር ቤት ለመመለስ የሚፈልጉ ዜጎች ለጉዳታቸወና ለተዘረፉት ንብረት ካሳ መጠየቅ ።

6ኛ / ወደ ሀገር መመለስ ለሚፈልጉ ተመላሽ ዜጎች አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረግ ፣ ወደ ሶስተኛ ሀገር መሔድ ለሚፈልጉ መብታቸውን ማክበር ይገባል ።

በደቡብ አፍሪካ ያላችሁ ዜጎች ብርታቱነን ይሰጣችሁ !
የሞቱትን ነፍስ ይማር ከማለት ባለፈ መሄድም ሆነ ክብራች ን መመለስ ባይቻልም ፣ ሀገርና መንግስት አለን ለማለት አፋጣኝ እርምጃ ከመንግስትዎና ከመስሪያ ቤትዎ እንጠብቃለን !

ሀገር ማለት ህዝቡ ነው !

ከሰላምታ ጋር !

አክባሪዎ

ነቢዩ ሲራክ
ሚያዝያ 9 ቀን 2007 ዓም

The post ከአረብ ሀገር እስከ ደቡብ አፍሪካ * የስደተኛው ሮሮና የመንግስት ቸልተኝነት ! (ይድረስ ለክቡር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም …) appeared first on Zehabesha Amharic.

(የደቡብ አፍሪካና የየመን ጉዳይ) “ከራሳችን ውጪ ለችግራችን ደራሽ መንግስት የለንም!”የሰማያዊ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ

$
0
0

የኢትዮጵያውያን የውርደት ዘመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሰሞኑን ከተከሰተው እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ አድርሶናል፡፡ የመን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ተጎጂ የሆኑትን የውጭ ዜጎች መንግስታቶቻቸው ቀድመው ሲያስወጡ ለኢትዮጵያውያን ግን የሚደርስላቸው አልተገኘም፡፡ ይህንን ውርደትም ወገኖቻችን ‹‹የመን ውስጥ የቀረነው እኛና ውሻ ብቻ ነን፡፡›› ሲሉ እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ገልጸውታል፡፡ ኢትዮጵያውያን ላይ የመድፍ፣ የሞርታርና የአውሮፕላን ድብደባ ሲዘንብባቸው በመከራ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ስልክ እንዲደውሉ በፌስ ቡክ ላይ በመለጠፍ ከማላገጥ ውጭ ምንም ያላደረገው የህዝብ ስልጣንን በሀይል የተቆጣጠርው ገዥው ፓርቲ ለራሱ ስልጣን ይጠቅሙኛል ያላቸውን የጦርነቱ ተሳታፊዎች ደግፎ መግለጫ ሲሰጥ የኢትዮጵያውያንን ስቃይ እጥፍ ድርብ አድርጎታል፡፡ በአጭሩ ኢህአዴግ ለራሱ ጥቅም ሲል ብቻ በማያገባውና በማይወጣው ዓለም አቀፍ ጦርነት ውስጥ ሀገራችንን ሲዘፍቅ ጦርነቱን ያወጀው የሚደርስላቸው ባጡ ምስኪን ኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡ ይህም የሀገራችን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከመቸውም ጊዜ በላይ የወደቀና ለዜጎች እንደማይቆም በድጋሚ ገሃድ የወጣበት ነው፡፡
south africa ethiopians
በየመን የተከሰተውን መርዶ ሰምተን ሳንውል ሳናድር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ ሌላ አስደንጋጭ አደጋና እና ሰቆቃ ልንሰማ ተገደናል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሀብትና ንብረታቸው መዘረፉ ሳያንስ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ሲያልፍ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተከታትለናል፡፡ የዚህ አሰቃቂ አደጋ ሰለባ የሆኑ የሌሎች ሀገራት ዜጎች በቶሎ ከደቡብ አፍሪካ ሲወጡ፣ እንዲሁም ሀገራቱ ዜጎቻቸውን መታደግ ያስችላል ያሉትን መፍትሄዎች ሲያስቀምጡ እና ሲያስጠነቅቁ ቢደመጥም ኢህአዴግ ግን እንደተለመደው የኢትዮጵያውያንን ሰቆቃና ስቃይ ከምንም እንዳልቆጠረው በግልፅ እየታየ ነው፡፡

በእርግጥ ላለፉት 24 ዓመታት ኢህአዴግ ሀገር ውስጥ የሚኖሩትን ዜጎች ሲያሰቃይ፣ በውጭ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንም የሆነ ያልሆነ ስም እየለጠፈ በጠላትነት ሲፈርጃቸው እንደቆየ አይተናል፡፡ ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የራሱን የግል ጥቅም ሲያሳድድም ቆይቷል፡፡ በቅርቡ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ወገኖቻችን ከፍተኛ በደል ሲደርስባቸው ይህ ነው የሚባል እገዛ ያላደረገው ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን በደል በማውገዝ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የሳውዲ ኤምባሲ ላይ ተገኝቶ ሲቃወም የሳውዲ ፖሊሶች ሀገራቸው ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፈፀሙት በደል ያልተናነሰ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰልፍ በወጡት ኢትዮጵያውያን ላይ በጭካኔ ድብደባ ፈፅሟል፡፡ ይህም ኢህአዴግ ለኢትዮጵያውያን የቆመ ሳይሆን በበእድ አገራት በኢትዮጵያውያን ላይ በደል ከሚፈፅሙት ያልተናነሰ ጨካኝ ስርዓት መሆኑን ያሳየበት ነው፡፡

ኢህአዴግ ለስሙ ‹‹የዳያስፖራ ፎረም›› በሚል የራሱን ደጋፊዎች አደራጅቶ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለልማት የበኩላቸውን እንዲያደርጉ እየሰራ እንደሚገኝ በስሩ በያዛቸው ሚዲያዎች ሲያሰራጭ ከርሟል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያውያኑ ለእነሱና ለሀገራቸው እንደማያስብ በመረዳታቸው ምክንያት ፊታቸውን ስላዞሩበት ውጤታማ አልሆነም እንጅ በተለያዩ አገራት እየተዘዋወረ ለአባይ ግድብ የበኩላቸውን እንዲያዋጡ ሲወተውት ታይቷል፡፡ ሳንቲም ለመልቀም በተለያዩ የዓለም ከተሞች እየዞረ ኢትዮጵያውያንን የሚሰበስበው ገዥው ፓርቲ በችግራቸው ወቅት ግን ምንም አይነት እርዳታ ሲያደርግ አይስተዋልም፡፡ ይብሱንም ችግር ላይ ባሉት ኢትዮጵያውያን ላይ ሌላ በደል ሲፈጽምና በስቃያቸው ላይ የማላገጥ ያህል ፕሮፖጋንዳ ሲሰራባቸው እያየን ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው ገዥው ፓርቲ ኢትዮጵያውያንን አባብሎ ገንዘብ ከመቀበል ያለፈ ለውድ ህይወታቸው ደንታ እንደሌለው ነው፡፡

በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ባሉት ተደጋጋሚ ግፎች ተሸፈነ እንጅ ሰሞኑን ሌላ ኢህአዴግ ለዜጎች እንደማይጨነቅ የታየበት ክስተት እየተፈፀመ እንደሆነ በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ ለመከታተል ችለናል፡፡ ኢህአዴግ ለራሱ ጥቅም ሲል ለሱዳን መንግስት አሳልፎ በሰጠው ሰፊና ለም የሀገራችን ሉዓላዊ መሬት አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ሌላ አሳፋሪ እና አሰቃቂ ወንጀል እንደተፈፀመ ተዘግቧል፡፡ የሱዳን መንግስት ወታደሮች ድንበሩን ጥሰው የሱዳን አዋሳኝ በሆነው የሰሜን ጎንደር ዞን ጠረፋማ ቦታዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ሊታደጋቸው አልቻለም፡፡

ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ሰቆቃ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ውስጥ ቢሆኑም ቢሰደዱም ከመከራው ሊላቀቁ እንዳልቻሉ አመላካች ነው፡፡ በውጭም ሆነ በሀገር ቤት የሚኖሩ የአንድ ሀገር ዜገች መብታቸውና ክብራቸው ሊጠበቅ የሚችለው ሀገር ውስጥ ለሀገርና ዜጎች የሚያስብና የሚቆረቆር መንግስት ሲኖር ነው፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያውያን የሚገዙት ኢህአዴግን በመሰለ ለሀገርና ለህዝቡ ደንታ በሌለው ስርዓት በመሆኑ የሰሞኑ ሰቆቃ የሚገርም አይደለም፡፡ መቼውንም ኢህአዴግ የሀገርና የዜጎቹን መብትና ክብር ያስጠብቃል ብሎ መጠበቅም ዘበት ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን የሀገራችንና የራሳችን ክብር እና ደህንነት ማስጠበቅ ካለብን መጀመሪያ ሀገራችን ላይ የሚገኘውን ስርዓት በፅኑ መታገል የግድ ይለናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ምቹ አስተዳደር፣ ዴሞክራሲያዊና ለዜጎች የሚያስብ ስርዓት ቢኖር መጀመሪያውኑም ወገኖቻችን በገፍ ለአደጋ ወደሚጋለጡባቸው አካባቢዎች ባልተሰደዱ ነበር፡፡ በመሆኑም በቅድሚያ ክብራችንን ለማስመለስ የነፃነት ትግሉን አጠናክረን በመቀጠል፣ እንዲሁም በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ለጊዜውም ቢሆን ራሳችን ከአደጋ ለማዳን በተለያዩ ማህበራት ተደረጃቶ በመንቀሳቀስ ብሎም ስርዓቱ እስካለ ድረስ ችግሮቻችን እየተባባሱ እንጂ እየተቀረፉ እንደማይመጡ በመገንዘብ በሀገር ቤት ስርዓቱን ለመቀየር የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል በማገዝ የችግራችንን ሁሉ መሰረት የሆነውን አምባገነናዊ አገዛዝ ለመለወጥ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ ክብራችንን ልናስመልስ የምንችለው ሀገራችን ውስጥ እንዳንኖር ያደረገንን ስርዓት ቀይረን አንድም በገዛ አገራችን መኖር ስንችል፣ አንድም በአደጋ ወቅት ሊደርስልን የሚችል ተቆርቋሪና ለዜጎች የሚያስብ መንግስት መመስረት ስንችል ብቻ መሆኑን ልንገነዘበው ይገባል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በደቡብ አፍሪካ ሰቆቃ እየደረሰባቸው ያሉ ወገኖቻችንን ለመታደግ በዓለም ላይ ተበትናችሁ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በችግር ውስጥ ለወደቁት ወገኖቻችን አጋርነታችሁን በማሳየት ዓለማቀፍ የተቃውሞ ድምፃችሁን እንድታሰሙም ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ እልባት እንዲያገኝ ፓርቲያችን የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል ለማስቆም አዲስ አበባ በሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ በኩል የራሱን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የመን ውስጥና በሱዳን አዋሳኝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ስርዓቱ ከባዕዳን ጋር ተባብሮ የሚፈፅመውን በደልም ለህዝብና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ በማጋለጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ መረጃዎችን እያሰባሰበ ይገኛል፡፡
በትግላችን የሀገራችንና የራሳችን ክብርና መብት እናስጠብቅ!
ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!
ሚያዝያ 9/2007 ዓ.ም

The post (የደቡብ አፍሪካና የየመን ጉዳይ) “ከራሳችን ውጪ ለችግራችን ደራሽ መንግስት የለንም!” የሰማያዊ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.


ከራሳችን ውጪ ለችግራችን ደራሽ መንግስት የለንም! (በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ)

$
0
0

blue_party_ethiopia101370869814 (1)የኢትዮጵያውያን የውርደት ዘመን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ሰሞኑን ከተከሰተው እጅግ አስከፊ ሁኔታ ላይ አድርሶናል፡፡ የመን ውስጥ በተከሰተው ጦርነት ተጎጂ የሆኑትን የውጭ ዜጎች መንግስታቶቻቸው ቀድመው ሲያስወጡ ለኢትዮጵያውያን ግን የሚደርስላቸው አልተገኘም፡፡ ይህንን ውርደትም ወገኖቻችን ‹‹የመን ውስጥ የቀረነው እኛና ውሻ ብቻ ነን፡፡›› ሲሉ እጅግ በሚያሳዝን መልኩ ገልጸውታል፡፡ ኢትዮጵያውያን ላይ የመድፍ፣ የሞርታርና የአውሮፕላን ድብደባ ሲዘንብባቸው በመከራ ላይ ያሉት ኢትዮጵያውያን ስልክ እንዲደውሉ በፌስ ቡክ ላይ በመለጠፍ ከማላገጥ ውጭ ምንም ያላደረገው የህዝብ ስልጣንን በሀይል የተቆጣጠርው ገዥው ፓርቲ ለራሱ ስልጣን ይጠቅሙኛል ያላቸውን የጦርነቱ ተሳታፊዎች ደግፎ መግለጫ ሲሰጥ የኢትዮጵያውያንን ስቃይ እጥፍ ድርብ አድርጎታል፡፡ በአጭሩ ኢህአዴግ ለራሱ ጥቅም ሲል ብቻ በማያገባውና በማይወጣው ዓለም አቀፍ ጦርነት ውስጥ ሀገራችንን ሲዘፍቅ ጦርነቱን ያወጀው የሚደርስላቸው ባጡ ምስኪን ኢትዮጵያውያንና በኢትዮጵያ ላይ ነው፡፡ ይህም የሀገራችን የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ ከመቸውም ጊዜ በላይ የወደቀና ለዜጎች እንደማይቆም በድጋሚ ገሃድ የወጣበት ነው፡፡

በየመን የተከሰተውን መርዶ ሰምተን ሳንውል ሳናድር ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በኢትዮጵያውያን ላይ ሌላ አስደንጋጭ አደጋና እና ሰቆቃ ልንሰማ ተገደናል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሀብትና ንብረታቸው መዘረፉ ሳያንስ በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸው ሲያልፍ በዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ተከታትለናል፡፡ የዚህ አሰቃቂ አደጋ ሰለባ የሆኑ የሌሎች ሀገራት ዜጎች በቶሎ ከደቡብ አፍሪካ ሲወጡ፣ እንዲሁም ሀገራቱ ዜጎቻቸውን መታደግ ያስችላል ያሉትን መፍትሄዎች ሲያስቀምጡ እና ሲያስጠነቅቁ ቢደመጥም ኢህአዴግ ግን እንደተለመደው የኢትዮጵያውያንን ሰቆቃና ስቃይ ከምንም እንዳልቆጠረው በግልፅ እየታየ ነው፡፡

በእርግጥ ላለፉት 24 ዓመታት ኢህአዴግ ሀገር ውስጥ የሚኖሩትን ዜጎች ሲያሰቃይ፣ በውጭ የሚኖሩትን ኢትዮጵያውያንም የሆነ ያልሆነ ስም እየለጠፈ በጠላትነት ሲፈርጃቸው እንደቆየ አይተናል፡፡ ከኢትዮጵያውያን ይልቅ የራሱን የግል ጥቅም ሲያሳድድም ቆይቷል፡፡ በቅርቡ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ ወገኖቻችን ከፍተኛ በደል ሲደርስባቸው ይህ ነው የሚባል እገዛ ያላደረገው ኢህአዴግ ሰማያዊ ፓርቲ በወገኖቻችን ላይ የደረሰውን በደል በማውገዝ አዲስ አበባ ውስጥ የሚገኘው የሳውዲ ኤምባሲ ላይ ተገኝቶ ሲቃወም የሳውዲ ፖሊሶች ሀገራቸው ውስጥ ኢትዮጵያውያን ላይ ከፈፀሙት በደል ያልተናነሰ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ሰልፍ በወጡት ኢትዮጵያውያን ላይ በጭካኔ ድብደባ ፈፅሟል፡፡ ይህም ኢህአዴግ ለኢትዮጵያውያን የቆመ ሳይሆን በበእድ አገራት በኢትዮጵያውያን ላይ በደል ከሚፈፅሙት ያልተናነሰ ጨካኝ ስርዓት መሆኑን ያሳየበት ነው፡፡

ኢህአዴግ ለስሙ ‹‹የዳያስፖራ ፎረም›› በሚል የራሱን ደጋፊዎች አደራጅቶ በውጭ የሚገኙ ኢትዮጵያውያንን ለልማት የበኩላቸውን እንዲያደርጉ እየሰራ እንደሚገኝ በስሩ በያዛቸው ሚዲያዎች ሲያሰራጭ ከርሟል፡፡ ከዚህም ባሻገር ኢትዮጵያውያኑ ለእነሱና ለሀገራቸው እንደማያስብ በመረዳታቸው ምክንያት ፊታቸውን ስላዞሩበት ውጤታማ አልሆነም እንጅ በተለያዩ አገራት እየተዘዋወረ ለአባይ ግድብ የበኩላቸውን እንዲያዋጡ ሲወተውት ታይቷል፡፡ ሳንቲም ለመልቀም በተለያዩ የዓለም ከተሞች እየዞረ ኢትዮጵያውያንን የሚሰበስበው ገዥው ፓርቲ በችግራቸው ወቅት ግን ምንም አይነት እርዳታ ሲያደርግ አይስተዋልም፡፡ ይብሱንም ችግር ላይ ባሉት ኢትዮጵያውያን ላይ ሌላ በደል ሲፈጽምና በስቃያቸው ላይ የማላገጥ ያህል ፕሮፖጋንዳ ሲሰራባቸው እያየን ነው፡፡ ይህም የሚያሳየው ገዥው ፓርቲ ኢትዮጵያውያንን አባብሎ ገንዘብ ከመቀበል ያለፈ ለውድ ህይወታቸው ደንታ እንደሌለው ነው፡፡

በኢትዮጵያውያን ላይ እየደረሱ ባሉት ተደጋጋሚ ግፎች ተሸፈነ እንጅ ሰሞኑን ሌላ ኢህአዴግ ለዜጎች እንደማይጨነቅ የታየበት ክስተት እየተፈፀመ እንደሆነ በተለያዩ ድህረ ገጾች ላይ ለመከታተል ችለናል፡፡ ኢህአዴግ ለራሱ ጥቅም ሲል ለሱዳን መንግስት አሳልፎ በሰጠው ሰፊና ለም የሀገራችን ሉዓላዊ መሬት አካባቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ሌላ አሳፋሪ እና አሰቃቂ ወንጀል እንደተፈፀመ ተዘግቧል፡፡ የሱዳን መንግስት ወታደሮች ድንበሩን ጥሰው የሱዳን አዋሳኝ በሆነው የሰሜን ጎንደር ዞን ጠረፋማ ቦታዎች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት ሲፈፅሙ የኢትዮጵያ የመከላከያ ሰራዊት ሊታደጋቸው አልቻለም፡፡

ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰው ሰቆቃ ኢትዮጵያውያን አገራቸው ውስጥ ቢሆኑም ቢሰደዱም ከመከራው ሊላቀቁ እንዳልቻሉ አመላካች ነው፡፡ በውጭም ሆነ በሀገር ቤት የሚኖሩ የአንድ ሀገር ዜገች መብታቸውና ክብራቸው ሊጠበቅ የሚችለው ሀገር ውስጥ ለሀገርና ዜጎች የሚያስብና የሚቆረቆር መንግስት ሲኖር ነው፡፡ ሆኖም ኢትዮጵያውያን የሚገዙት ኢህአዴግን በመሰለ ለሀገርና ለህዝቡ ደንታ በሌለው ስርዓት በመሆኑ የሰሞኑ ሰቆቃ የሚገርም አይደለም፡፡ መቼውንም ኢህአዴግ የሀገርና የዜጎቹን መብትና ክብር ያስጠብቃል ብሎ መጠበቅም ዘበት ነው፡፡

ኢትዮጵያውያን የሀገራችንና የራሳችን ክብር እና ደህንነት ማስጠበቅ ካለብን መጀመሪያ ሀገራችን ላይ የሚገኘውን ስርዓት በፅኑ መታገል የግድ ይለናል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ምቹ አስተዳደር፣ ዴሞክራሲያዊና ለዜጎች የሚያስብ ስርዓት ቢኖር መጀመሪያውኑም ወገኖቻችን በገፍ ለአደጋ ወደሚጋለጡባቸው አካባቢዎች ባልተሰደዱ ነበር፡፡ በመሆኑም በቅድሚያ ክብራችንን ለማስመለስ የነፃነት ትግሉን አጠናክረን በመቀጠል፣ እንዲሁም በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ለጊዜውም ቢሆን ራሳችን ከአደጋ ለማዳን በተለያዩ ማህበራት ተደረጃቶ በመንቀሳቀስ ብሎም ስርዓቱ እስካለ ድረስ ችግሮቻችን እየተባባሱ እንጂ እየተቀረፉ እንደማይመጡ በመገንዘብ በሀገር ቤት ስርዓቱን ለመቀየር የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል በማገዝ የችግራችንን ሁሉ መሰረት የሆነውን አምባገነናዊ አገዛዝ ለመለወጥ የበኩላችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ ክብራችንን ልናስመልስ የምንችለው ሀገራችን ውስጥ እንዳንኖር ያደረገንን ስርዓት ቀይረን አንድም በገዛ አገራችን መኖር ስንችል፣ አንድም በአደጋ ወቅት ሊደርስልን የሚችል ተቆርቋሪና ለዜጎች የሚያስብ መንግስት መመስረት ስንችል ብቻ መሆኑን ልንገነዘበው ይገባል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በደቡብ አፍሪካ ሰቆቃ እየደረሰባቸው ያሉ ወገኖቻችንን ለመታደግ በዓለም ላይ ተበትናችሁ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን በሙሉ በችግር ውስጥ ለወደቁት ወገኖቻችን አጋርነታችሁን በማሳየት ዓለማቀፍ የተቃውሞ ድምፃችሁን እንድታሰሙም ሰማያዊ ፓርቲ ጥሪውን ያስተላልፋል፡፡ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን ሰቆቃ እልባት እንዲያገኝ ፓርቲያችን የበኩሉን ጥረት እያደረገ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የሚደርሰውን በደል ለማስቆም አዲስ አበባ በሚገኘው የደቡብ አፍሪካ ኤምባሲ በኩል የራሱን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በሌላ በኩል የመን ውስጥና በሱዳን አዋሳኝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ላይ ስርዓቱ ከባዕዳን ጋር ተባብሮ የሚፈፅመውን በደልም ለህዝብና ለዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ በማጋለጥ የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማድረግ መረጃዎችን እያሰባሰበ ይገኛል፡፡

በትግላችን የሀገራችንና የራሳችን ክብርና መብት እናስጠብቅ!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!!

ሚያዝያ 9/2007 ዓ.ም

The post ከራሳችን ውጪ ለችግራችን ደራሽ መንግስት የለንም! (በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ወያኔ እና የቅድመ-ምርጫ ግምገማው- ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት

$
0
0
  • ወያኔ የአምስት ዓመቱ «የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ» እንዲሁም የዐባይ ግድብ ግንባታ እንዳልተሳካለት አመነ፣
  • በመጭው ምርጫም የሚያሰጋኝ የድርጅትም ሆነ የግለሰብም ተወዳዳዳሪ የለኝም አለ።

Moreshየትግሬ-ወያኔ መራሹ ዘረኛ አገር እና ትውልድ አጥፊ ቡድን፣ መጭው የይስሙላ ምርጫ ሊያስከትል የሚችለውን ሕዝባዊ ቁጣ እና  እምቢተኝነት በከፍተኛ ደረጃ በመፍራት፣ ሊነሣ የሚችለውን ሕዝባዊ አመፅ በወያኔ ፍላጎት ሥር ለማዋል እንዲቻል፣ አባላቱን በመከፋፈል፣ ሰሞኑን በከፍተኛ ደረጃ የተያዘ ጥብቅ ሚሥጢራዊ ግምገማ እና ውይይት ማድረጉን የታመኑ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት ውስጥ-ዐወቅ የመረጃ ምንጮች አረጋግጠዋል። የሕወሓት/ኢሕአዴግ አባል በሆኑ እና ለወያኔ ታማኝ የሆኑ የየድርጅቶቹ አባሎች ተሣታፊ የሆኑበት ለበርካታ ቀኖች በተከታታይ ግምገማ እና ውይይት የተደረገባቸው ጉዳዮች፦

አንደኛ ፦አቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ በኃላፊነቱ ይቀጥል ወይስ ይነሣ?

ሁለተኛ፦የትግሬ የበላይነት አለ? ወይስ የለም?

ሦሥተኛ፦የአምስት ዓመቱ «የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ»፣ እንዲሁም የዐባይ ግድብ ግንባታ በታቀደው መልኩ ያለመከናወናቸው መሠረታዊ ችግሮች ምንድን ናቸው?

አራተኛ፦ በ2007 ዓ.ም. ምርጫ ጠንካራ ተቃዋሚዎች አሉ ወይ? ካሉስ እነማን ናቸው?

የሚሉት እንደሆኑ ታማኝ እና ሁነኛ የሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት የውስጥ-አዋቂ ምንጮች አረጋግጠዋል።

በርዕሰ ጉዳዮቹ ላይ በተደረገው ግምገማ እና ውይይት ከሚከተሉት ውሣኔዎችና ድምዳሜዎች ላይ መደረሱን ምንጮች አስረድተዋል። አቶ ኃይለማርያም በያዘው የጠቅላይ ሚኒስቴርነት ኃላፊነት ይቀጥል? ወይስ አይቀጥል፣ በሚለው ጉዳይ ላይ የወያኔ ቡድን አንድ ቁርጥ ያለ አቋም ላይ ለመድረስ እንዳልቻለ ታውቋል። ከሕወሓት ውጭ ያሉት እና «የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች» የሚባሉት አባሎች፣ «ኃይለማርያም ወያኔ ከሚሰጠው መመሪያ ውጭ የማይንቀሳቀስ በመሆኑ በያዘው ቦታ ቢቀጥል የሚያመጣው ችግር የሌለ ስለሆነ ይቀጥል» ሲሉ፣ የወያኔ አባላት ከሆኑት የተወሰኑ ትግሬዎችም «እስካሁን እኛ ያልነውን ብቻ ሣይሆን፣ ያሰብነውን እና ልንሠራ የምንፈልገውን ቀድሞ የሚናገርልን ስለሆነ በያዘው ቦታ መቀጠሉ ለወያኔ ዓላማ መሳካት ያግዛል እንጂ አይጎዳም» ሲሉ መደመጣቸው ታውቋል።

በሌላ በኩል «አክራሪ» እና «ለምን ከወሣኝ የሥልጣን ቦታ ላይ ትግሬ ይጠፋል? እኛ ሞተን እና ቆስለን ባስገኘነው ሥልጣን የሌላ ነገድ አባል የሆነ እና በትግሉም ወቅት ምንም ዓይነት አስተዋጽዖ ያላደረገ ሰው፣ በመለስ ዜናዊ ብቸኛ ውሣኔ ለዚህ ቦታ የበቃ ሰው፣ ለተከታዮቹ አምስት ዓመታት በሥልጣን ላይ መቆየት የለበትም» በማለት ኃለማርያም በሌላ ትግሬ እንዲተካ የከረረ አቋም መያዛቸው መስተዋሉን የሞረሽ ምንጮች አስረድተዋል። «ኃይለማርያም መነሣት አለበት» የሚሉት የወያኔ አባሎች የሚያቀርቡት የመከራከሪያ ነጥብ፣ «ኃይለማርያም ከወያኔ ፍላጎት ያፈነገጠ ጠባይ ባይታይበትም፣ የመጀመሪያ ደረጃ መረጃ ለእርሱ የሚደርስ በመሆኑ፣ መረጃዎች ለወያኔ የሚደርሱት በሁለተኛ ደረጃ ስለሆነ፣ ፈጣን ውሣኔዎችን ለመስጠት ተቸግረናል። ለዓላማችን መሣካትና በፈለግነው አቅጣጫ ለመጓዝ የጠቅላይ ሚኒስቴርነቱ ቦታ በትግሬ መያዝ አለበት» የሚል መሆኑ ታውቋል። ኃይለማርያም ደሣለኝ መነሳት አለበት የሚለው ቡድን በተጨማሪ መከራከሪያነት የሚያነሳው ጭብጥ አለ። ይኸውም፦ «ለአምስት ዓመቱ የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እና ለዐባይ ግድብ ግንባታ መክሸፍ ዋነኛ ምክንያቱ የአመራር ድክመት፣ የውጭ ፖሊሲያችን ውድቀት» መሆኑ መወሳቱ እና «መለስ ቢሆን ወይም ሌላ ትግሬ አመራሩን ቢይዝ ኖሮ ይህ ውድቀት አይከተልም ነበር። ኃይለማርያም ፈጥኖ የመወሰን ብቻ ሣይሆን፣ በራስ የመተማመን ችግር ስላለበት በእርሱ አመራር ወደ ግባችን መድረስ አንችልም።» ከሚል ድምዳሜ መድረሳቸውን ያስረዳሉ። ይህ የተከፋፈለ አመለካከት «ኃይለማርያም ይቀጥል? ወይስ በሌላ ይተካ?» ለሚለው ጥያቄ ቁርጥ ያለ መልስ ላይ አለመደረሱን ምንጮቻችን አስታውቀዋል።

በዚህም ይመስላል፣ ወያኔ የመጭውን ምርጫ ውጤት ተከትሎ ሊቀሰቀስ ለሚችል ሕዝባዊ አመፅ፣ ቀጥቅጦ እና ጨፍልቆ የወያኔን የበላይነት ለማረጋገጥ፣ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ በ«ሕገመንግሥቱ የተሰጡትን ሥልጣኖች» በመሻር፣ ጊዜያዊ አዋጅ ከማወጅ አንስቶ፣ የአገሪቱን የመከላከያ፣ የደህንነት እና የፖሊስ ኃይል በበላይነት የሚመራ እና የሚቆጣጠር ኮሚቴ ፈጥሯል። የኮሚቴው ሰብሳቢም ጨካኙ እና ፈሪው ዐባይ ፀሐዬ እንዲሆን ተደርጓል። ይህን ውሣኔ ከላይ «ኃይለማርያም ይነሳ? ወይስ ይቀጥል?» ለሚለው ጥያቄ መነሳት አለበት የሚሉት ወገኖች አቋም ከወዲሁ አንድ እርምጃ ወደፊት የተራመደ እና ኃይለማርያም በዐባይ ፀሐዬ የተተካ መሆኑን ያሳያል። ምክንያቱም ኃይለማርያም ለይስሙላም ቢሆን በወረቀት ላይ የተሰጡትን ወሣኝ የሆኑትን ሥልጣኖቹን አጥቷልና!

«የትግራይ የበላይነት አለ? ወይስ የለም?» ለሚለው የመገማገሚያ ነጥብ፣ እጅግ በርካታ ሰዎች «የትግራይ የበላይነት አለ። በሁሉም የፖለቲካ፣ የማኅበራዊ እና የኢኮኖሚ ዘርፎች፣ ከትንሽ እስከ ትልቅ በትግሬዎች የተያዙ ናቸው» ሲሉ፣ የተወሰኑት ደግሞ፦ «የትግሬ የበላይነት የለም» እንዳሉ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። በየትኛውም ደረጃ የየውይይቱ መሪዎች ትግሬ ካልጠፋ በስተቀር ሁሉም ትግሬዎች ናቸው። እነዚህ አገማጋሚዎች «የትግሬ የበላይነት አለ» ሲሉ ኃሣባቸውን የገለጹትን፥ «የትግሬ የበላይነት አለ ስትሉ የበላይነቱ በምን፣ በምን እንደሚገለፅ አስረዱ» በማለት ተገምጋሚዎችን አፋጥጠው መያዛቸው ታውቋል። ተገምጋሚዎቹም ለተጠየቁት ጥያቄ ሲመልሱ፦ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በማኅበራዊ መስኮች ወሣኝ ቦታዎች ብቻ ሳይሆኑ ጥቃቅን ቦታዎች ሳይቀሩ በትግሬዎች መያዙ፤ ትግራይ ከሌሎች ክልሎች ተነጥላ እንድትበለጽግ መደረጉ፤ ከፍተኛ የሆነ የትምህርት፤ የጤና፣ የመገናኛ፣ እና የኢንዱስትሪ ግንባታዎች በትግራይ መሠራታቸው፤ የቀረው ቀርቶ ትግርኛ መናገር የማያስፈትሽ እና የማያስጠይቅ እንደሆነ ተጨማጭ ማስረጃዎችን በማቅረብ መልስ እንደሰጡ ታውቋል። ለተሰጡት መልሶች አወያዮቹ «ይህማ የግንቦት 7 እና የኢሣት ፕሮፓጋንዳ ነው። ትግሬን የሚጠሉ ሰዎች አቋም ነው። ጥቅማቸው የተነካባቸው የቀድሞው ሥርዓት ናፋቂዎች የሚያራግቡት ፖለቲካ ነው» በማለት እንዳጣጣሉት ለማወቅ ተችሏል። በሚያስገርም ሁኔታ «የትግሬ የበላይነት የለም» ያሉትን ደግሞ «እናንተ አድርባዮች ናችሁ! ወላዋዮች እና አስመሳዮች ናችሁ። ግምገማው ተገቢውን ውጤት እንዳያስገኝ ያሰባችሁ ናችሁ» በማለት የዘለፉዋቸው እንደሆነ ሲታወቅ፣ በዚህ የመገማገሚያ ርዕስ አንድ ዓይነት አቋም ላይ ሳይደረስ፣ አወያዮቹ እንደተለመደው የተሰጡትን ኃሣቦች በማጣጣል ውይይቱ መደምደሙ ታውቋል።

በሦሥተኛ ደረጃ የመገማገሚያ ርዕስ በነበረው በተደረገው ግምገማ እና ምዘና፥ «የአምስት ዓመቱ የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ እንዲሁም የዐባይ ግድብ በታሰበው መልኩ አለመከናወኑ ብቻ ሳይሆን፣ አጠቃላይ ውድቀት እንደሆነ» በሙሉ ድምፅ መስማማታቸውን ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። ለዕቅዶቹ አለመፈጸም መሠረታዊ ምክንያቶች ሆነው የተጠቀሱት፦ «ከአበዳሪ እና ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች ይገኙ የነበሩት ዕርዳታዎች እና ብድሮች መቋረጥ፣ ለዕቅዶቹ ተፈጻሚነት የሚያስፈልጉት ግብዓቶች አብዛኛዎቹ ከውጭ መሆን እና ይህን ማግኘት አለመቻሉ» እንደነበረ ሲጠቀሱ፣ «ይህ ደግሞ የውጭ ፖሊሲያችን ውድቀት መሆኑ፣ የፖሊሲው ውድቀት ደግሞ ብቃት ያለው እንደመለስ ያለ መሪ አለመኖሩ» እንደሆነ በስፋት መገለጹን የውስጥ-ዐወቅ የመረጃ ምንጮቻችን አረጋግጠዋል። በመሠረቱ መለስ ዜናዊ ይህንን የቅዠት ዕቅድ ሲያወጣ፣ ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት የሚያስፈልጉት አግባብ ያላቸውን ፖሊሲዎች እንዳልቀረፀ ይታወቃል። ከዚያም በላይ የአንድ አገር የኢኮኖሚ ዕድገት በውጭ ዕርዳታ እና ብድር በሚገኝ መዋዕለ-ንዋይ ብቻ ይከናወናል ብለው የሚያስቡ ገዢዎች፣ ከመነሻውም ያለባቸውን የአመራር ድክመት የሚያሣይ ነው። ስለዚህ ብዙ የተደሰኮረለት «የአምስት ዓመቱ የዕድገት እና የትራንስፎርሜሽን ዕቅድ» ውጤቱ ዜሮ ቢሆን ቀድሞውንም የሚጠበቅ ነው።

የ2007 ዓ.ም. ምርጫን በተመለከተ በተደረጉ ግምገማዎች እና ምዘናዎች፣ ሕወሓት/ኢሕአዴግን የሚያሰጉ፣  በሕዝቡ ተቀባይነት ያላቸው ድርጅቶችም ሆኑ ግለሰቦች እንደሌሉ በገምጋሚዎቹ እይታ ሙሉ እምነትና ስምምነት መደረሱ ታውቋል። በሌላ በኩል «ብቻቸውን ለምርጫ ቀርበው ለምን ምርጫ ይላሉ?» ለሚሉ ወገኖች አፍ ማዘጊያ፣ እንዲሁም  እንዳለፈው ምርጫ «በ99ነጥብ6 አሸነፍን» ላለማለት፣ «በዓላማ ከእኛ ጋር የሚስማሙትን፣ በአፈጻጸም የሚለዩትን በመድረክ ሥር ከተሰባሰቡት ሰዎች በድርጅት ስም ሳይሆን፣ በግለሰብ ደረጃ ተመርጠው የፓርላማ ወንበር የሚያገኙበት ሥልት እንዲመቻች» በማለት መስማማታቸው ተረጋግጧል።  ይህም ለታማኝ ተቃዋሚዎቻቸው ለእነ ፕሮፌሠር በየነ ጴጥሮስ፣ ለዶክተር መረራ ጉዲና፣ ለአቶ ገብሩ አሥራት ዓይነቶች በር የተከፈተላቸው እንደሆነ ይጠቁማል። «ይህን ሁላ አድርገንም ምርጫውን እኛ አሸነፍን ብንል ሕዝቡ ሊቀበለን ስለማይችል፣ ይህን ተከትሎ ለሚፈጠር አመፅ አስፈላጊውን የኃይል ርምጃ የሚወስድ በቂ ዝግጅት እንዲደረግ» የሚል ውሣኔ አሣልፈዋል። ይህም ቀደም ሲል ጀምሮ የታሰበበት እንደሆነ ታውቋል። ስለሆነም ከይስሙላው ጠቅላይ ሚኒስትር ከአቶ ኃይለማርያም ደሣለኝ ሥልጣን የተረከበው በዐባይ ፀሐዬ የሚመራው ኮሚቴ ዐቢይ ተግባር፣ ሕዝባዊ አመጽን መስበር እንደሆነ የኮሚቴው ዓላማና የግምገማው ውጤት ያሳያል። ለዚሁ ተግባር ሲባልም በከተሞች የተጠናከረ የስለላ እና የመቺ ኃይል ቡድኖች ተደራጅተው በመንቀሳቀስ ላይ እንደሆኑ ታውቋል። በገጠር የገበሬ ማኅበራት በእያንዳንዱ ምርጫው እስከሚጠናቀቅበት ጊዜ ድረስ ከፍተኛ ገንዘብ የሚከፈላቸው ከአንድ መቶ እስከ መቶ ስልሳ የሚሆኑ አፋኝ ቡድኖች አባሎች መመደባቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። የትግሬ-ወያኔ አገዛዝ በየአምሥት ዓመቱ የይስሙላ የምርጫ ድራማ እንደሚያዘጋጅ እና ውጤቱም ሁልጊዜ በትራጄዲ እንደሚደመደም ይታወቃል።

The post ወያኔ እና የቅድመ-ምርጫ ግምገማው- ሞረሽ ወገኔ የዐማራ ድርጅት appeared first on Zehabesha Amharic.

በደቡብ አፍሪካም እንዲህ ሆነ – (ሄኖክ የሺጥላ)

$
0
0

ethiopia south africa
ከ 17ኛው ክፍለ ዘመን እስከ በቀደም በነጮች ( በመጀመሪያ በ-ቡሮች ወይም ደቾች ቀጥሎም በ 19ኛው ክፍለ ዘመን የአልማዝ መገኘትን ተከትሎ በእንግሊዞች ) የባርነት ቀንበር ስር ስትማቅቅ የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ በብረት እሾህ ታጥራ ልጆቿን በስልጡን የጀርመን ውሻዎች (Geremen Shippered) ስታዘነጥል የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ ነጭ ባለፈበት እንዳታልፍ ፣ እንዳትማር ፣ እርስ በእርስ እንዳትነጋገር ፣ ህዝቦቿ በገዛ ሀገራቸው አራተኛ ወይም የመጨረሻ ዜጋ ተደረገው ( ከ እንግሊዝ ፣ ከደች ፣ ከ ሕንድና ኤስያ ቀጥሎ ) ለመቶ አመታቶች ነጻነት ምን እንደሆነ ሳታውቅ የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ ነጻነትን ከትናንት ወዲያ ያገኘች ው ደቡብ አፍሪካ ፣ ቦጠሊቃዊ ፣ ሰላማዊ ፣ ሰዋዊ ስብሰባዎችም ሆነ ማንኛውም የሰለጠነ እና እንደሰው የሚኖር ሰው የሚያደርጋቸው ተፈጥሯውዊ ክንውኖች ተነፍጏት የኖረችው ደቡብ አፍሪካ ( ለምሳሌ እኔ ደቡብ አፍሪካ በነበርኩበት ግዜ ሴቶቹ ደቡብ አፍሪካውያን ሲሰክሩ በአብዛኛው በቁማቸው እንደሚሸኑ አይቻለሁ )፣ አዎ ያቺ የባርነት ተምሳሌት ፣ የመረገጥ እና የውርደት ቤት የነበረችው ደቡብ አፍሪካ ፣ ከመሬቷ ሲሶ ያህሉ እንኩዋ የሷ ያልሆነው (ያልነበረው ) ፣ የምድሯን በረከት ፣ የልጆቿን ደም ፣ አንጡራ ሀብት በሉት ፣ እምቅ ሀብት ፣ ወርቁን እና ፣ አልማዙን ቆፍረው እና አጥለው ፣ ኖራውን እና የድንጋይ ከሰሉን በድማሚት አፍርሰው ፣ ረስተንበርግን እንደ ኩይሳ ከላይ ያፈር ክምር ፣ ከስር የምስጥ ቤት አስመስለው ፣ ጆሃንስበርግን ( ወይም ኢጎሊን ) የወርቅ ምድር እያሉ እያሞካሹ ህዝቦቿን እያሹ ኑረው ፣ ኑረው የተትረፈረፉባትን ጌታዎቿን ፣ ደምና ውስኪ እኩል ያፈሰሱባትን ገዳዮቿን ይቅርታ ያለችው ያቺ ሳውዝ አፍሪካ ፣ የዘመን በደሏን ረስታ ፣ የባርነት ቀንበር ህሊናዋ ላይ ክርክር ቢሰራም ፣ በፍቅር ተረታሁ ፣ ሰውነት ከበደል እና ከክፉ ታሪክ በለጠብኝ ብላ ፣ በ ጁሃን ስበርግ ( በሱዌቶግዛት ወይም ከተማ )፣ በ-ደርባን ፣ በ ፖርት ዔልዛቤት ፣ በ ኬፕታወን ፣ በዋና ከተማው በፕሪቶሪያ ፣ በራንጉሌ ፣ በጃካራንዳ፣ በሮቢን ደሴት ፣ እና በወዘተ፣ እነ ሜምቄጺ፣ እኔ ሲቦንጊሌ ፣ እነ ታቱ ፣ እነ ዙማ ፣ እነ ማዲባ ፣ እነ ወዘተ በባቡር መሳፈርያው ሆነ ፣ በአሳንሱር ላይ ፣ በመንገድ ላይ ሲጏዙም ሆነ አምጠው ሲወልዱ ፣ በዚህ በኩል እንዳትሄዱ ፣ በዚህ በኩል ሂዱ ( NET NIE BLANKES ( None white person only blacks ) ) እየተባሉ የኖሩት ደቡብ አፍሪካውያን ፣ በአንድ ምህረት ፣ ሁለት ገጽ የይቅርታ ደብዳቤ ተቻችለው መኖር የለመዱት ደቡብ አፍሪካውያን ፣ ሲቸገሩ ድንበር አቋርጠው ያስጠጏቸውን ሞዛምቢኮች ፣ መሳሪያ ደብቀው ያሸገሩላቸውን ዚምቡዋቤዎች ፣ መሪዎቻቸውን ወስደው ያሰለጠኑላቸውን ኢትዮጵያውያኖች ዛሬ በእሳት አቃጠሉ ፣ በድንጋይ እንደ ዘማይ በአደባባይ ወገሩ ፣ እንደ ጌቶቻቸው እነሱም የባርነት ግፋቸውን ፣ ያደፈ ልባቸውን ፣ ያቄመ ልቦናቸውን በወንድሞቻቸው ላይ አነሱ ።

እንደ እንሰሳ ለዘመናት የገዟቸውን ፣ እንደ ትል የረገጧቸውን ፣ እንደ ትቢያ ያረከሷቸውን ፣ አጥንታቸውን የከሰከሱትን ፣ ደማቸውን የመጠጡትን ፣ እምቅ ሀብታቸውን የዘረፉትን ይቅርታ ማድረግ ያልከበዳቸው ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ ዛሬ ግን በደም እና በቀለም የሚመስሏቸውን ፣ በችግር የደረሱላቸውን ፣ በ ጨለማ መብራት የሆኑላቸውን ፣ አብረዋቸው የመከራ ጽዋ ( ገፈት ) የቀመሱ አፍሪካዊ ወንድሞቻቸውን አይን ማየት አስጠላቸው ፣ ህጻናትን የፈጁትን የአፓርታይድ መሪዎች ፣ ወታደሮች ፣ እና ወዘተ ይቅርታ ማድረግ ያልከበዳቸው ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ በቢሊዮን ምናልባትም በትርሊዮን ዶላሮች የሚቆጠር ገንዘብ ለመቶ አመታት የዘረፏቸውን ፣ የወረፏቸውን እንደ እንስሳ ያዩዋቸውን ቀኝ ገዢዎች ይቅርታ ማለት ግድ ያላላቸው ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ ዛሬ ጨርቅ ነግዶ ፣ በየ ቅያሱ ( ሎኬሽን ) ብርድ-ልብስ አዙሮ ፣ ነጠላ ጫማ በየ መንገዱ አንጥፎ ፣ ቻፓቲ ሸጦ ህይወቱን ለማሸነፍ የሚውተረተረው ጥቁር ንብረት አስቆጣቸው ፣ በሱዌቶ የህጻን ልጅ ደም በ መትረየስ ( አውቶማቲክ ጠብ መንጃ ) የቀጠፈውን አፓርታይድ ይቅርታ ማድረግ ያልከበዳቸው ደቡብ አፍሪካውያን ፣ we are passionate about South Africa የሚል ጽሑፍ ሽንጡ ላይ ለጥፎ በጎዳናዋ ላይ የሚሽከረከረው የመአድን መጫና ባቡር ሳይሆን በብሪ ፣ ዴሊቨር እና ጂፒ ጎዳናዎች ላይ የተከፈቱት ጥቃቅን ሱቆች ደማቸውን አፈላው።

የሚከተሉትን ሕጎች የተቀበሉት (Population Registration Act, 1950 – This Act demanded that people be registered according to their racial group. This meant that the Department of Home Affairs would have a record of people according to whether they were White, Coloured, Black, Indian or Asian. People would then be treated differently according to their population group, and so this law formed the basis of apartheid. It was however not always that easy to decide what racial group a person was part of, and this caused some problems.

Group Areas Act, 1950 – This was the Act that started physical separation between races, especially in urban areas. The Act also called for the removal of some groups of people into areas set aside for their racial group. Well known removals were those in District Six, Sophiatown and Lady Selborne (also see Cato Manor, Fietas and Curries Fountain (Grey Street area)). People from these areas were then placed in townships outside of the town. They could not own property here, only rent it, as land could only be white owned.

Promotion of Bantu Self-Government Act, 1959 – This Act forced different racial groups to live in different areas. Only a small percentage of South Africa was left for black people (who comprised the vast majority) to form their ‘homelands’. Like the Group Areas Act, this act also got rid of ‘black spots’ inside white areas, by moving all black people out of the city. This Act caused much hardship and resentment. People lost their homes, were moved off land they had owned for many years and were moved to undeveloped areas far away from their place of work.

Bantu Education Act, 1953 – established an inferior education system for Africans based upon a curriculum intended to produce manual laborers and obedient subjects. Similar discriminatory education laws were also imposed on Coloureds, who had lost the right to vote in 1956, and Indians. The government denied funding to mission schools that rejected Bantu Education, leading to the closure of many of the best schools for Africans. In the higher education sector, the Extension of University Education Act of 1959 prevented black students from attending “white” universities (except with government permission) and created separate and unequal institutions for Africans, Coloureds, and Indians respectively. The apartheid government also undermined intellectual and cultural life through intense censorship of books, movies, and radio and television programs.

The Suppression of Communism Act, 1950 (originally introduced as the Unlawful Organisations Bill) – The Act was introduced in an attempt to curb the influence of the CPSA and other formations that opposed the government’s apartheid policy. It sanctioned the banning/punishment of the CPSA or any group or individual intending to bring about political, economic, industrial and social change through the promotion of disorder or disturbance, using unlawful acts or encouraging feelings of hostility between the European and non-European races of the Union of South Africa. The Act was progressively tightened up in 1951, 1954, and yearly from 1962-1968.
) እና ለነዚህም ይቅርታ ያደረጉት ደቡብ አፍሪቃውያን ፣ የጥቁር ወንድሞቻቸው ገላ ላይ እሳት ጫሩ ።

መደምደሚያ

ጥንትስ ቢሆን ሰው ወገኑን ካዋረደ ለግፍ ጥሎ
ባለቤት ያቀለለውን ባለ ዕዳ መች ተቀብሎ ! ይላል አባት ዓለም ጸጋዬ ገ/መድህን ። እኛም

ባገራችን በአድ ሆነን በመአዳችን ቀላዋጭ
በሰው ሀገር የሰው ዝቃጭ !

ሀገር የሌለው ክብር ፣ ዘር ፣ ሕይወት እና ተስፋ የለውም ! የትም የኛ አይደለም ! የኛ ኢትዮጵያ ብቻ ነች !
ለነጻነታችን ካልተጋን ፣ ካልተዋጋን ፣ በየመን የሰማይ እሳት ፣ በቀይባይ ባህር የመአበል እሳት ፣ በሳውዲ አረቢያ የሹርጣ እሳት ፣ በ ሳውዝ አፍሪካ የቆራጣ ባርያ እሳት ይበላናል ። ሀገር ይኑረን ! ነጻነታችንን እናስመልስ !

ሄኖክ የሺጥላ

The post በደቡብ አፍሪካም እንዲህ ሆነ – (ሄኖክ የሺጥላ) appeared first on Zehabesha Amharic.

“አምባሳደሩ ወዳገራቸው መመለስ አለባቸው” የናይጄሪያ እንደራሴዎች “አሁን የተፈጠረው ጊዜያዊ ክስተት ነው” ሃይለማርያም

$
0
0

* “ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉት ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን” ቴድሮስ አድሃኖም

በደቡብ አፍሪካ በሚገኙ አፍሪካውያን ላይ የተጀመረው ጥቃት ያስቆጣቸው የናይጄሪያ እንደራሴዎች በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት አምባሳደር ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ውሳኔ አስተላለፉ፡፡ የሩዋንዳውን ፕሬዚዳንት በማስተናገድ የተጠመዱት ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያም ደሳለኝ በደቡብ አፍሪካ “የተፈጠረው ጊዜያዊ ችግር ነው ብለን እናምናለን” በማለት አስተያየት ሰጡ፡፡ ውጭ ጉዳይ ሚ/ር ቴድሮስ ከየቦታው ሃሳብ እየሰበሰብኩ ነው፤ “ወደ አገራቸው መመለስ ለሚፈልጉ ድጋፍ እናደርጋለን” አሉ፡፡ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግን የመመለስ ፍላጎት እንደሌላቸው ይናገራሉ፡፡
south africa news
ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ የተነሳው አሰቃቂ ግድያና ዘረፋ ብዙዎችን እኤአ በ2008 የተከሰተውን እንዲያስታውሱ አድርጓቸዋል፡፡ በወቅቱ ከስድሳ በላይ አፍሪካውያን የተገደሉና የበርካታዎች ንብረት የተዘረፈ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ሰሞኑን በተነሳው ሁከት ሶስት ኢትዮጵያውያን መሞታቸውንና አስከሬናቸውን ወደ ኢትዮጵያ መላኩን ከዚያው የወጡ መረጃዎች ቢጠቁሙም የኢህአዴግ ባለሥልጣናት ግን የሞተው አንድ ብቻ ነው ማለታቸውን ኢቲቪ ዘግቧል፡፡

ከኢትዮጵያውያኑ ሌላ ዜጎቿ እንደሞቱባት የምትጠቀሰው ናይጄሪያ በድርጊቱ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅቶች እያደረገች መሆኑ ተሰምቷል፡፡ የናይጄሪያ እንደራሴዎች በደቡብ አፍሪካ ላይ የከረረ እርምጃ እንዲወሰድ እየሞገቱ ነው፡፡ የናይጄሪያ ተወካዮች ምክርቤት በጉዳዩ ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ካደረገ በኋላ በደቡብ አፍሪካ የሚገኙት የናይጄሪያ አምባሳደር ወደ አገራቸው እንዲመጡ አጽድቋል፡፡

sa2sa4በተለያዩ ድረገጾች ላይ የተነበበው ይህ ዜና እንደሚያስረዳው የተከበሩት እንደራሴዎች እጅግ በጋለና አገር ፍቅር ስሜት በወገኖቻቸው እንዲሁም በአፍሪካውያን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አውግዘዋል፤ ኮንነዋል፡፡ የኤዶ ግዛት እንደራሴ ረቂቅ ሕጉ ላይ የናይጄሪያ መንግሥት ከደቡብ አፍሪካ ጋር ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲያቋርጥ የማሻሻያ ሃሳብ አቅርበው ነበር፡፡ ሃሳቡን የዴልታው እንደራሴ በአጽንዖት የደገፉ ቢሆንም ውሳኔ ድምጽ ላይ ሲደርስ አምባሳደሩ ወደ አገራቸው በአስቸኳይ እንዲጠሩ የሚለው ሲያልፍ ማሻሻያው ግን በቂ ድምጽ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡ ማሻሻያውን የደገፉ እንደራሴዎች በጉዳዩ ላይ እንደሚሰሩ የተሰማ ቢሆንም አምባሳደሩን ወዳገራቸው ማስመጣቱ በፍጥነት እንዲፈጸም ፕሬዚዳንት ጉድላክ ዮናታን የጉዳዩን አስቸኳይነት ለፕሬዚዳንት ያዕቆብ ዙማ እንዲገልጹ ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

በኢትዮጵያ ጉብኝት የሚያደርጉትን የሩዋንዳ ፕሬዚዳንት እያስተናገዱ ያሉት ሃይለማርያም ደሳለኝ በደቡብ አፍሪካ የደረሰውን በተመለከተ በእንግሊዝኛ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ ጠ/ሚ/ሩ ታሪክን የዘነጋ በሚመስል ለስላሳ አነጋገር “ደቡብ አፍሪካ ከቅኝ አገዛዝም ሆነ ከአፓርታይድ አገዛዝ ነጻ እንድትወጣ ድጋፍ መስጠታችን ይሰማናል” በማለት አጭሩን ንግግራቸውን አሰምተዋል፡፡ ሲቀጥሉም “አፍሪካውያን በፈለጉበት መኖር” እንደሚችሉ ከገለጹ በኋላ “አሁን የተፈጠረው ጊዜያዊ ክስተት ነው ብለን እናምናለን፤ የደቡብ አፍሪካ መንግሥትና ፓርቲ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ እንጠብቃለን” በማለት ወደ ግብዣቸው ተመልሰዋል፡፡

በአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መ/ቤት አራተኛዋ ባለሥልጣን የሆኑትን የበታች ጸሃፊ ዌንዲ ሸርማንን በማስተናገድ የተጠመዱት ቴድሮስ አድሃኖም በፌስቡክ በለቀቁት አጭር መልዕክት “በደቡብ አፍሪቃ ከሚገኙ አንዳንድ ወገኖች” ጋር በስልክ እየተነጋገሩ መሆናቸውን እና ምን መደረግ እንዳለበት ከየቦታው እስካሁን ሃሳብ በመሰብሰብ ሥራ ላይ መጠመዳቸውንsouth-africa-foreigners የሚገልጽ እንደምታ ያለው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ “ወደ አገራቸው መመለስ የሚፈልጉትን” ለመደገፍ መዘጋጀታቸውን በዚሁ መልዕክት ገልጸዋል፡፡
ነዋሪዎችን ከየመኖሪያቸው በማፈናቀል፤ መኖሪያ በማሳጣት እና በግዳጅ ባልፈለጉበት ቦታ በማስፈር የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙ በተለያዩ ዘገባዎች በማስረጃ የሚነገርለት ኢህአዴግ ወደ አገር ለመመለስ ለሚፈልጉ ዝግጅቱ ማድረጉን ቢገልጽም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ግን ሁኔታው አስፈሪ ቢሆንም ወደ አገራቸው መመለስ እንደማይፈልጉ ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ አንዳንዶችም “ከአገራችን የወጣነው የኢኮኖሚ ጥገኝነት አስገድዶን ብቻ አይደለም፤ የመኖር ኅልውናችን አደጋ ላይ በመውደቁም ጭምር ነው” ሲሉ ተሰምተዋል፡፡
ለጎልጉል አስተያየታቸውን የሰጡ እንዳሉት “ደቡብ አፍሪካውያን ኢትዮጵያዊ ስለተባልን አገር ያለን መስሏቸው ከአገራቸው እንድንወጣ ይነግሩናል፤ በህይወት እያለን ወደ ኢትዮጵያ ሄደን በደኅንነት መኖር ስለማንችል እኮ ነው ስንሞት አስከሬን የምንልከው፤ ይህንን ግን የተረዱት አይመስለኝም” በማለት ሃሳባቸውን ተናግረዋል፡፡

sa9እኤአ በ2000 መጀመሪያዎች አካባቢ በአገራቸው የሚኖሩ ነጭ ሰፋሪዎችን ያባረሩት የዚምባብዌው ፕሬዚዳንት ሮበርት ሙጋቤ በዚሁ የደቡብ አፍሪካ ጉዳይ ላይ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ ከሁለት ሚሊዮን በላይ ዜጎቿ ደቡብ አፍሪካ እንደሚኖሩ የሚነገርላት ዚምባብዌ የዜጎቿን ጉዳይ ቀዳሚው ስፍራ የሰጠችው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በተለይ ግን ሙጋቤ ጉዳዩን አስመልክቶ በላኩት መልዕክት እንዲህ በማለት በደቡብ አፍሪካውያን ላይ ተሳልቀዋል፤ ዘልፈዋቸውማል፡፡

“ደቡብ አፍሪካውያን አንድ ነጭ በህይወት እያለ በጥፊ ለመምታት ሙከራ እንኳን ስለማያደርጉ (ስለሚፈሩ) ነጭ ሲሞት ሃውልቱን ይደበድባሉ፤ ነገር ግን አንድ ጥቁር የሌላ አገር ዜጋ በመሆኑ ብቻ በድንጋይ ወግረው ይገድላሉ፡፡”

Source: googlgule.com

The post “አምባሳደሩ ወዳገራቸው መመለስ አለባቸው” የናይጄሪያ እንደራሴዎች “አሁን የተፈጠረው ጊዜያዊ ክስተት ነው” ሃይለማርያም appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በሚኒሶታ እያደረጉት ያለውን ሕዝባዊ ስብሰባ በቀጥታ ይከታተሉ (Live)

ኢትዮጵያዊያኑ የመን ውስጥ በጭንቅ እያነቡ ነው ያሉት

$
0
0

በግሩም ተ/ሀይማኖት

የመን ምጥ በቁና መሆኑን ትታ ምድራዊ ሲዖል እየሆነች ነው፡፡ ባስነጠሳት ቁጥር ግዙፍ ግዙፍ ሚሳኢሎቿን የሚያወድም ሚሳኤል ከአየር እየተወረወረላት ነው፡፡ ያኔ ማስነጠሱ ቀርቶ ይነስራታል፡፡ በዜጎቿ ደም ነስሯን ታንቦለቡላልች፡፡ ሰሞኑን ሰነዓ ከተማ ውስጥ ፈጂ አጣን የሚባለው ቦታ ላይ ያለ የመሳሪያ ክምችት በተከታታይ ተመታ፡፡ ፓለስቲክ ሚሳይሉ ያለው እዛ ውስጥ እንደሆነ ነው የሳዑዲ ባለስልጣኖች የሚናገሩት፡፡ በእርግጥ ትክክልም ይመስላል፡፡ በፍንዳታው አካባቢው በመጥፎ ኬሚካል ተበከለ፡፡ ከ1 ኪሎ ሜትር ራዲየስ አካባቢ ያሉ ነዋሪዎች ሳል፣ ቋቅታ፣ ወደላይ ወደታች አናወጣቸው፡፡ በሳዑዲ የሚመራው ህብረ ሀይል አንድ መላ ቀየሱ….
yemen
ቦታውን ታርጌት አድርገው ከባህር ያስወነጨፉት ሚሳይል እየተመዘገዘገ ከተማውን አቋርጦ ሲያልፍ ጀት መስሏቸው ሲተኩሱበት እንደነበር የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ሚሳይሉ ግን ታርጌት የተደረገበትን ቦታ በሀይለኛው ድባቅ በታና ወደታች ይዞጥ ጦለመ፡፡ ከፍ ብሎ በቀጥታ ወደታች ቁልቁል ይዞት ሲወርድ ከላዩ አፈር አለበሰው የሚበነው ኬሚካል ተቀበረ፡፡ ለአካባቢው ሰላም ሰጠ፡፡

የመን ሰሞኑን ጫን በርታ ያለ ድብደባ እየደረሰባት ቤቶቻችንም አረገደች ምድር እያሉ እንቅጥቅጥ ድንከራቸውን ተያይዘውታል፡፡ በተመታ ቁጥር ቤቶቹ ያረግዳሉ፤ መስኮት ይከፈታል፣ ህጻናት በድንጋጤ ከተኙበት ተሳቀው ይነሳሉ፡፡ የልብ ምታችን በመቶ እጥፍ ይጨምራል፡፡ የሰነዓ ከተማና መብራት ከተገናኙ ዛሬ ስድስተኛ ቀናቸው ነው፡፡ ውሃ ዋጋው የወርቅ ሆኗል፡፡ ቆሻሻ በየቦታው ተከምሮ ይታያል፡፡ ነዳጅ ከወትሮው ዋጋ በ5 እጥፍ ጨምሯል፡፡ 3000 ሪያል የነበረው በአንዴ 15.000 እና 20.000 ሪያል ገብቷል፡፡ በዚህ ምክንያት ቆሻሻ የሚያነሱት ሰራተኞች መስራት አልቻሉም፡፡ የግማቱ ነገር የፈነዳ ሽንት ቤት ውስጥ የተቆረቆረች ከተማ ሊያስመስላት ነው፡፡

ርሃብም ብዙዎችን ለማጨድ አቆብቁቦ የሸመቀ ይመስላል፡፡ መንገዱ ላይ ውርውር የሚሉት መኪናዎች በጣት የሚቆር ነው፡፡ ሰዉም ቢሆን ከረመዳን ጊዜው የባሰ ጥፍት ብሎ ከተማዋ በጭርታ የተኩስ ድምጽዋን እያዳመጠች ነው፡፡ የሁቲይ ሚኒሻዎች ጄቶቹን ለመከላከል ተኩሱን ከየአቅጣጫው ያዳምቁታል፡፡ ግን ጀቶቹ ጋር የመድረስ አቅም የለውም፡፡

ኢትዮጵያዊያኑ በዚህች አይነቷ የመን ውስጥ ነው በጭንቅ እያነቡ ያሉት፡፡ በእስር የነበሩት 680 ኢትዮጵያዊያን ከሚግሬሽን እስር ቤት ከተፈቱ በተኩል ሰዓት ውስጥ አካባቢው በተኩስ ተናውጦ በአየር ተደበደበ ምንም እንኳን የእስር ቤቱ ባይመታም ዙሪያውን ያሉት ተቋሞች ተደበደቡ፡፡ የሚያሳዝነው ግን ከእስር የተፈቱትን 680 ኢትዮጵያዊያን 30 የሞላውን እንኳን ማግኘቱ ከባድ ሆነ በእውነት ልባችን እንደፈራው ሆኖም መሰለኝ፡፡

በድሮው ፕሬዘዳንት አብደላ ሳላህ ጊዜ ደቡብ የመን እና ሰሜን የመን ሲዋጉ ኢትዮጵያዊያኑን በጦርነት አሰልፎ የነበረው የሰሜን የመን ከጦርነት በኋላ ዜግነት የሰጣቸው ዘሬም ስንት ኢትዮጵያዊያን አሉ፡፡ ታሪክ ራሱን ይደግማል ይባላል፡፡ እኛ ላይ ግን መድገም ብቻ ሳይሆን መደጋገም ሆኖ ጢቢጢቢ እየተጫወተብን ነው፡

The post ኢትዮጵያዊያኑ የመን ውስጥ በጭንቅ እያነቡ ነው ያሉት appeared first on Zehabesha Amharic.

በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር

$
0
0

senakriem1
ክንፉ አሰፋ

“አሜሪካ ይዞን ከሄደ በኋላ በዋሽንግተን ዲሲ አንድ የገበያ አዳራሽ (ሞል) ውስጥ ጥሎን ጠፋ…ፖሊስ ሁለት ግዜ ይዞን ነበር… በርሃብ ተቀጣን፣ ርሃብ ጸንቶበት ሆስፒታል የገባም ልጅ አለ። … በየሬስቶራንቱ እየዞርን ለምነናል።” ይላል አንድ የ 11 አመት ሕጻን ሳይንቲስት። ሂውስተን ቴክሳስ ያሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ለመጎብኘት ከአዲስ አበባ ሄደው ነው አስሩ ሕጻናት ዲሲ ላይ የሚሰቃዩት።

አስሩን ህጻናት በአንድ መኪና(ትራክ) ውጽጥ አጭቆ ነበር ወደ ሞሉ የወሰዳቸው። የያዘው መኪና ከአራት ሰው በላይ መጫን አይችልም። እመንገድ ላይ ፖሊስ እንዳያያቸው “ሁላችሁም ጎንበስ በሉ።” ይላቸው እንደነበርም ህጻናቱ አጫውተውኛል።

እነዚህ ሕጻናት ሀገሪቱ የምትመካባቸው የነገ ሳይንቲስቶችዋ ናቸው። ከአጠቃላይ ትምህርት ቤቶች ተወዳድረው ከፍተኛ፤ እጅግ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ ታዳጊዎች። በነዚህ ታዳጊዎች እና በወላጆቻቸው ላይ የደረሰው በደል እጅግ ብዙ ነው። ታሪኩ አንድ አሳዛኝ ፊልም ይወጣዋል። ወላጆቹ አሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ደውለው ይህ በደል ለህዝብ ይፋ እንዲሆንላቸው ቢጠይቁም የራዲዮ ጣብያው ጉዳዩን ባልታወቀ ምክንያት አፍኖታል። ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ለጻፉት የአቤቱታ ደብዳቤም ምላሽ ተነፍገዋል። ጉዳዩ ለሚመለከተው ክፍል ሁሉ አቤት ብለዋል። ሰሚ ግን አላገኙም።
senakriem-mekonnen

ይህንን በደል የፈጸመው ግለሰብ ከአዲስ አበባ እንዲሸሽ ተደርጎ በዚያው በዋሽንግተን ዲሲ በአንድ የፕሮቴስታንት ፓስተር ቤት መሽጓል። በአሜሪካ የመኖርያ ፈቃድ የለውም። የባንክ ሂሳብ ግን አውጥቶ ገንዘቡን እዚያው አከማችቷል።

የትንግርታዊው “ዶክተር” ሳሙኤል ዘሚካኤልን የሽወዳ ስልት ገና ከአእምሯችን ሳናወጣ፤ ሌሎች የእሱ ደቀ መዝሙሮች ብቅ እያሉ ነው። ስልታቸውን ይቀይሩ እንጂ የሁሉም ቁጭ በሉዎች አላማ አንድ ነው – ህዝብን ማታለል። አንዳንዶቹ ለሽወዳቸው ረቀቅ ያለ ዘዴ ሲጠቀሙ ሌሎች ደግሞ ዘርካካ በመሆን የዋሁን ህዝብ በዘረፋ ተያይዘውታል።

ዛሬ ይዤላችሁ የቀረብኩት አጭበርባሪ የረቀቀ ስልት ባይጠቀምም ለሌብነቱ የተለየ መንገድ ይዞ ነው ብቅ ያለው። ሰናክሪም መኮንን ይባላል። ይህ ሰው የገዥው ፓርቲ አባል በመሆኑ ለዝርፊያው ምቹ መንገድ እንደፈጠረለት ይነገራል።

የሰናክሬም መኮንን አንድ አዲስ ፕሮጀክት ነደፈ። ከመላው ትምህርት ቤቶች በትምህርታቸው ከፍተኛ ውጤት ያመጡትን አወዳድሮ ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ታዳጊዎችን አሜሪካ በመውሰድ ሂውስተን ቴክሳስ የሚገኘውን ናሳ የጠፈር ምርምር ተቋም ማስጎብኘት። ከዚህም ሌላ የላቀ ውጤት ላመጡ ህጻናት የላፕቶፕ እና የአይፓድ ልዩ ሽልማት እሰጣለሁ ብሎ ቃል ይገባል። በየትምህርት ቤቱ እየዞረ የትምህርት ቤቶቹን እና ልዩ ልዩ መገናኛ ብዙሃንን በመጠቀም አላማውን አስፈጸመ። ወጪውን ሁሉ የሚሸፍኑ ስፖንሰሮች አገኘ። አዲካ ትራቭል፣ ኦሮሚያ ባንክ እና ኢትዮጵያ አየር መንገድ የህጻናቱን ወጪ በሙሉ የሚሸፍን በቂ የሆነ ስፖንሰር ተገኘ።
macdonalds
ሰናክሬም የስፖንሰሩን ድጋፍ እና የአስሩን ህጻናት ፓስፖርት ይዞ አሜሪካ ኤምባሲ ለቪዛ ሄደ። በቂ የስፖንሰር ድጋፍ ስለነበረው ያለምንም ችግር የልጆቹን ቪዛ አገኘ።

ጫወታው እዚህ ላይ ነው የሚጀምረው። ስፖንሰሩን እና ቪዛውን በእጁ ካስገባ በኋላ የህጻናቱን ቤተሰቦች በተናጥል እየጠራ እያንዳንዳቸው የህጻናቱን የትራንስፖርት እና የመስተንግዶ ወጪ እንዲሸፍኑ ጠየቃቸው። ሰውየው በቂ በጀት ከስፖንሰሮች እንዳገኘ በወላጆቹ ይታወቃል። በመጀመርያ የገባውን ቃል አጥፎ ወላጆቹ የልጆቻቸውን ወጪ እንዲሸፍኑ መጠየቁ ለሁሉም እንግዳ ሆነባቸው። ሁሉም አንከፍልም ሲሉ መለሱለት።

ሰናክሬም ግን አጭር መልስ ሰጣቸው። “ወጪውን የማትሸፍኑ ከሆነ እድሉል ሌሎች ልጆች እሰጠዋለሁ።” ሲል የባሰ መርዶ አመጣባቸው።
ወላጆች አጣብቂኝ ውስጥ ገቡ። በአንድ በኩል ልጆቻቸው ወደ ሂውስተን ለመሄድ ተነሳስተዋል። የልጆቻቸውን ስሜት መጠበቅ ግድ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ይህ ሰው እያጭበረበራቸው መሆኑን አውቀውታል። ከብዙ ማንገራገር በኋላ ግን ገሚሱ ወላጅ የአውሮፕላን ትኬት፣ የአምስት ኮከብ ሆቴል፣ የመስተንግዶ እና የኮቴ ከፍሎ ልጆቹን ወደ አሜሪካ ላከ። ሰናክሬም ከውጭ ሃገር ከተቀበለው ዶላር ውጭ ወላጆቹ የከፈሉት ገንዘብ በድምሩ አንድ ሚሊዮን ብር ይጠጋል።

ይህንን ወጪ መክፈል ያየልቻሉ ህጻናትን ተሰረዙ። የነሱ እድል ሌሎች ጥሩ ውጤት የሌላቸው ግን ገንዘብ ላላቸው ወላጆች ተሸጠ። ዘረፋው በዚህ መልኩ ተፈጸመ። አስሩ ህጻናትም ወደ አሜሪካ ተጓዙ።

ወደ ዋና ድራማው ደግሞ ልውሰዳችሁ። አሜሪካ ዋሽንግተን እንደገቡ ለአንድ ቀን ብቻ በማሪዮት ሆቴል ቆይታ ያደርጋሉ። በነጋታው ሁሉም በአንድ ትራክ ተጭነው እዚህ ግባ የማይባል ማረፍያ ውስጥ በቡድን በቡድን ታጎሩ።

የጉዞው ዋና አላማ በሂውስተን የሚገኘውን የናሳ ጠፈር ምርምር ተቋም መጎብኘት ነበር። እሱን እርሱት ብሏቸዋል ሰናክሬም። ለግዜው ወላጆችን ማታለያ አስሩንም በቡድን ፎቶ አነሳቸው። የናሳን ማስክ በፎቶሾፕ እያስገባ አለበሳቸው። ናሳ የሄዱም አስመሰላቸው። ፎቶውንም በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ለጠፈው።

አሁን ልጆቹም ስለናሳው ጉዳይ አያስቡም። ከወላጆቻቸው ተነጥለው ወጥተው በአንድ ሃላፊነት በጎደለው ሰው እጅ ላይ ወድቀዋል። በአንድ ክፍል ወስጥ ተቆልፎባቸው ይውሉና ለተወሰነ ሰዓት በገበያ አዳራሽ ውስጥ ይለቀቃሉ። በአሜሪካን ሃገር በርሃብና ጥማት እየተሰቃዩ ነው። ረሃብ ጸንቶባቸው ሆስፒታልም የገቡ አሉ።

ወላጆቹ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በጻፉት ደብዳቤ*፣ “ሰናክሬም ከእያንዳንዱ ወላጅ የአምስት ኮከብ ሆቴል ሂሳብ ተቀብሎ ሳለ ህጻናቱ ግን ተገቢውን የሆቴል አገልግሎት አላገኙም። ሴቶቹ የማይታወቁ ሰዎች ቤት እንዲያርፉ መደረጉ እና ወንዶቹ ደግሞ በቡድን በአንድ ክፍል ውስጥ እንዲያድሩ አድርጓል።” ብለዋል።

ምግብን በተመለከተ ተገቢውን ምግብ ሳይመገቡ ለረሃብና ለህመም መዳረጋቸውና ከዚህም የተነሳ በምግብ ማጣት ጉዳት ሆስፒታል መግባታቸው፤ የተወሰኑት ከአቶ ሰናክሬም ተወስደው ወደ ዘመድ ቤት እንዳረፉ በደብዳቤው ላይ ተገልጿል። በመጀመርያዎቹ ቀናት ማክዶናልድ እየወሰደ ይመግባቸው እንደነበር ልጆቹ ተናግረዋል። ከዚያ በኋላ ነው የረሳቸው።

ከሁሉም በላይ የሚያሳዝነው ነገር ደግሞ ደግሞ እነዚህን በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በዋሽንግተን ዲሲ ለልመና መጠቀሙ ነው። “ከሄዱበት አላማ ውጪ በአደራ የተቀበላቸውን ህጻናት በየቤተክርስትያኑ እያዞረ ‘ለችግረኛ የሚሆን’ በማለት ኩፖን በማሸጥ አሰማርቷቸውም ነበር።” ይላል ደብዳቤው። ልጆቹን በዚህ መልኩ በልመና በማሰማራት በሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ እንደሰበሰበ ህጻናቱ ይናገራሉ። በተለይ ዋሽንግተን ዲሲ ያለው ወንጌላዊ ቤተ-ክርስትያን ህጻናቱ በጉባኤው ፊት ቆመው የልመናውን ኩፖን እንዲያሳዩና እንዲሸጡ አድርጓቸዋል። ይህ የሆነው የቤተ-ክርስቲያኗን ፓስተር ሃንፍሬይን በማታለል ነው።

ሕጻናቱ በዚህ መልኩ ተንገላትተው ግን ለመጡበት አላማ ምንም ነገር ሳያደርጉ ሊመለሱ ነው። በአካባቢው ያሉ የቤተሰብ አባላት አንድ ሃሳብ አመጡ። ኢትዮጵያዊው ጠረፍ ሳይንቲስት የሆኑትን ዶ/ር ብሩክ ላቀውን በጉዳዩ አማከሩዋቸው። ዶ/ር ብሩክም ፈቃደኛ ሆኑ። በወላጆች ትውውቅ የመጡት እኚህ ኢትዮጵያዊ ሳይንቲስት ህጻናቱ ካረፉበት ስፍራ ድረስ በምሄድ ስለ ናሳ አስረዷቸው።

ህጻናቱም ይህችን እውቀት ይዘው፤ ናሳን በቴለቭዥን እንኳን ሳይመለከቱ ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ። የሰናክሬም የናሳ ጉዞ ፕሮጀክትም በዚህ ላይ ተጠናቀቀ። ገቢው አጓጊ ነውና ሰናክሬም አሁንም ሌላ ዙር ሊሰራ ማሰቡ አልቀረም።
የህጻናቱ ቤተሰቦች ግን በመሰባሰብ የጋራ አቋም ላይ ደርሰዋል። ያላግባብ የተወሰደባቸው ገንዘብም እንዲመለስ ጠይቀዋል። ሰናክሬም ግን ሸሽቶ አሜሪካ መሽጓል።

ይህ መረጃ እንደደረሰኝ ሰናክሬም መኮንን በኢሜል አግኝቼው ነበር። ጉዳዩን እልባት እንዲሰጥ፤ የሰዎቹንም ገንዘብ እንዲመልስ በተደጋጋሚ ጠየቅኩት። ይህ ከልሆነ ታሪኩን ለህዝብ ይፋ እንደማደርገውም ነግሬው ነበር። ይህ ጉዳይ ሜድያ ላይ ከወጣ ታዋቂ እንደሚያደርገው ተናግሮ አሾፈብኝ።

ይህንን የማደርገው ለሌሎች ወላጆች ትምህርት እንዲሆን ነው። ጉዳዩን ለበርካታ የሜዲያ አካላት ማሳወቄም ግድ ነው። ለጥንቱ ወዳጄ ሰይፉ ፋንታሁንም የህጻናቱን በደል ነግሬው ነበር። ህጻናቱን አነጋግሯቸዋል። ጉዳዩን በቅርቡ እንደሚያቀርበው ነግሮኛል።
ወላጆች በጋራ በመሆን ለሚመለከተው አካል የጻፉትን አቤቱታ ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ።*
*

The post በአሜሪካ የመሸገው የሳሙኤል ዘሚካኤል ደቀ-መዝሙር appeared first on Zehabesha Amharic.


ISIL በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በማረድ እና በጥይት ገደለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ISIL ወይም ISIS በሚል የሚታወቀው ቡድን በሊቢያ 30 ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን ግማሹን በማረድ ግማሹን በጥይት መግደሉን በለቀቀ ቪዲዮ አስታወቀ::
ethiopian killed

Ethiopian killed by ISIL

ethiopian killed by isil 1

ethiopian killed by isil 3
ISIL በለቀቀው የ29 ደቂቃ ቪዲዮ በሊቢያ ሁለት ግዛቶች ውስጥ ማለትም ባርካ እና ፋዛን ከተሞች ውስጥ እነዚህን ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች በጥይት እንዲሁም ሌሎቹን ሲያርዷቸው አሳይቷል::

ማስክ ያጠለቁት እነዚሁ የISIL አባለት ኢትዮጵያውያኑን የያዟቸውና ከላይ በተጠቀሱት ከተሞች ሕይወታቸውን ያጠፉት ከምስራቅ እና ደቡብ ሊቢያ እንደተያዙ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ይጠቁማል:: ክርስቲያኖቹ ሃይማኖታቸውን እንዲቀይሩ አልያም የተለየ ታክስ እንዲከፍሉ ከመታረዳቸውና ከመገደላቸው በፊት እንደተጠየቁ የዘገበው አሶሺየትድ ፕሬስ ኢትዮጵያዊያኑ በባህር ዳርቻ አካባቢ ሕይወታቸው ተቀጥፏል ብሏል::

በርካታ ኢትዮጵያውያን ወደ አውሮፓ ለመሻገር የሰሃራ በረሃን በማቋረጥ ሊቢያ በሚገቡበት ወቅት ለበርካታ ችግሮች በተለይም ለተገዶ መደፈር; ለኩላሊት መሰረቅ እንዲሁም ለመገደልና ለመታሰር ሲበቁ ቆይተዋል::

ISIL የወሰደውን እርምጃ ተከትሎ በርካታ አስተያየቶች እየተሰጡ ሲሆን ጋዜጠኛና አክቲቭስት አበበ ገላው በፌስቡክ እጹ የሚከተለውን አስፍሯል::

ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው!
በየመንና በደቡብ አፍሪካ የተከሰተው ሰቆቃ ሳያንሰን ዛሬ ደግሞ በሊቢያ ISIS ኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖችን ሰብስቦ ማረዱን አረዳን። ኢትዮጵያዊው በአገሩ ክብርና መብት ተነፍጎ፣ በአስከፊ ድህነት ይሰቃያል፣ ከመሬቱ፣ ከቤቱ ከቀዬው ይፈናቀላል፣ ታፍኖ በየእስር ቤቱ ይታጎራል፣ ይገደላል፣ በሃሰት ይከሰሳል፣ ሰቆቃ ይፈጸምበታል። የተሰማኝ ሃዘን ጥልቅ ነው። ቸሩ አምላክ የነዚህን ምስኪን ሰማእታት ነፍስ ይታደግልን፣ ለቤተሰቦቻቸውም መጽናናትን ይስጥልን።
በስደትና በሽሽት ምድር ተዋርዶ መኖር ሳይበቃው በቁሙ ይቃጠላል፣ እንደ በግ ይታረዳል። የዚህ ሁሉ ችግር ዋነኛ መንስኤ ወያኔዎች ኢትዮጵያን ለጥቂቶች ምድራዊ ገነት ለብዙሃኑ ደግሞ ምድራዊ ሲኦል በማድረጋቸው ምክንያት መሆኑ ህሊና ላለው ሁሉ ግልጽ ነው። ለአንድ ህዝብ ከዚህ የከፋ የቁም ሞት የለም። ኢትዮጵያዊ ሁሉ በያለበት በቃ ብሎ የሚነሳበት ግዜ አሁን ነው። አገሩን ያላስከበረ ትውልድ ከዚህም የከፋ ይገጥመዋል። ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ ነው። በቃ ብለን በአንድነት የምንነሳበት ግዜ አሁን ነው። ሊነጋ ሲል ይጨልማል!

The post ISIL በሊቢያ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖችን በማረድ እና በጥይት ገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በዋሽንግተን ዲሲ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ አጠገብ ነገ ሰኞ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን በደቡብ አፍሪካ በስደተኞች ላይ የተፈጸመውን ግድያና ማዋከብን በመቃወም የደቡብ አፍሪካ መንግስት ይህን ጉዳይ በቶሎ እንዲያስቆም የሚጠይቅ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በዋሽንግተን ዲሲ እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ለዘ-ሐበሻ ገልጸዋል::
south africa ethiopians
በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያኑ እና በሌሎች የአፍሪካውያን ስደተኞች ላይ የተፈጸመውን አሳፋሪ ድርጊት በመቃወም የተለያዩ ሃገር ወዳድ አርቲስቶች በተለያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ሃዘናቸውን ሲገልጹ ነበር:: ከነዚህም መካከል በቅርቡ ‘ወገኔ’ የሚል ትልቅ መልዕክት ያለው ሙዚቃ የለቀቀው አርቲስት ብርሃኑ ተዘራ ይጠቀሳል:: ብርሃኑ በደቡብ አፍሪካ በኢትዮጵያውያኑ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት አውግዞ ከወገኖቹ ጋር እንደሚቆምና እስካሁንም ጉዳት ያልደረሰባቸው ወገኖች ሁኔታው እስኪረጋጋ ድረስ ራሳቸውን እንዲጠብቁ ጠይቋል:: ብርሃኑ “ከዚህ በፊትም በአረብ ሃገር አሁንም በደቡብ አፍሪካ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ስቃይ ያሳዝናል” ብሏል::

ታዋቂው ተወዛዋዥ አብዮት (ካሳነሽም) እንዲሁ በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸውን ላጡ ኢትዮጵያውያን ፈጣሪ በገነት ነብሳቸውን እንዲያኖር ጠይቆ በጉዳዩ በጣም ማዘኑን ገልጿል:: ወጣቱ ተወዛዋዥ አብዮት በደቡብ አፍሪካ በስቃይ ላይ ለሚገኙት ወገኖቹ በሙያው አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም ገልጿል:: በተጨማሪም ሁሉም ኢትዮጵያዊ በያለበት ሃገር የደቡብ አፍሪካ ኢንባሲ ደጃፍ በመገኘት ለወገኖቹ ድምጹን እንዲያሰማ ጥሪም አቅርቧል::

እንቆቅልሽ የተሰኘ ተወዳጅ አልበም በቅርቡ የለቀቀው ድምፃዊ ፋሲል ደመወዝም እንዲሁ በደቡብ አፍሪካ የደረሰውን ሲመለከት እንዳመመው ገልጾ ሁሉም ጸሎት እንዲያደርግ ጠይቋል:: በዋሽንግተን ዲሲ በነገው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ በሚደረገው ሰልፍ ላይም ሕዝቡ በነቂስ ወጥቶ ድምጹን እንዲያሰማም ጥሪ አቅርቧል::

ሰኞ ኤፕሪል 20 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በ9 ሰዓት በሚደረገው በዚህ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ታዋቂውን የሰብ አዊ መብት ተሟጋች እና አርቲስት ታማኝ በየነን ጨምሮ በርከት ያሉ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል::

Monday …April 20th @ 9:am
South African Embassy
3051 Mass Ave NW, Wash, DC

The post በዋሽንግተን ዲሲ የደቡብ አፍሪካ ኢምባሲ አጠገብ ነገ ሰኞ ጠዋት ሰላማዊ ሰልፍ ይደረጋል appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአይሲኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ካደ * “የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም”አለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሁሌም በዜጎቹ ጉዳይ ከበዳይ ወገን ጋር አብሮ በመሰለፍ ዜጎቹን የሚያዋርደው የሕወሓት የሚያስተዳድረው የኢሕ አዴግ መንግስት በሊቢያ አይሲኤስ የገደላቸውን 28 ኢትዮጵያውያንን ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ማረጋገጫ አላገኘሁም አለ::
ethiopian killed by isil 1

Ethiopian killed by ISIL
ሕወሓት የሚመራው መንግስት ባወጣው መግለጫው “አይሲኤስ የተባለው አለም ዓቀፍ አሸባሪ ቡድን በሊቢያ በሚኖሩ ስደተኞች ላይ ፈፅሜያዋለሁ በሚል በቪዲዮ ያሰራጨው ዘግናኝ የግድያ ተግባር የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚያወግዝ ሲገልጽ” ስደተኛ እንጂ ኢትዮጵያውያን ማለት አልፈቀደም::

ሕወሓት የሚመራው መንግስት ዜጎቹን በመካድ በአቶ ሬድዋን ሁሴን በኩል የሰጠው መግለጫ ላይ እንዲህ ይላል:-

“በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ዓመተ ምህረት የተለያዩ አለም ዓቀፍ ሚዲያዎች ባሰራጩት ዘገባ አይ ኤስ የተባለው አሸባሪ ቡድን ግድያ የፈፀመባቸው ስደተኞች ኢትዮጵያውያን እንደሆኑ ቢገልፁም በግብፅ ካይሮ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ግን ስደተኞቹ ኢትዮጵያውያን ስለመሆናቸው ማረጋገጫ እንዳልሰጠም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡
አሸባሪው ቡድኑ ለህልፈት የዳረጋቸው ዜጎች ኢትዮጵያውያን ቢሆኑም ባይሆኑም መንግስት በንፁሃን ላይ የሚፈፀም ይህን መሰል አፀያፊና ዘግናኝ የሽብር ድርጊት አጥብቆ ይኮንናል ብለዋል፡፡”

በግልጽ ኢትዮጵያውያንን የመሰሉ ሰዎች ታርደውና ተገድለው ባህር ላይ ተጥለው መንግስት ገና ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን አላረጋገጥኩም ማለቱ ዜጎቹን በመካድ የታወቀው የሕወሓት መንግስት ዳግም እርቃኑን ቀርቷል:: በቅርቡ እሳዑዲ አረቢያ በየመን እና በደቡብ አፍሪካ በዜጎቹ ላይ ክህደት የፈጸመው ይኸው አምባገነን መንግስት በሊቢያ የሚገኙ ዜጎቹን መካዱ ብዙዎችን አሳዝኗል::

The post ሕወሓት የሚመራው መንግስት በአይሲኤስ የተገደሉ ኢትዮጵያውያንን ካደ * “የተገደሉት ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላረጋገጥኩም” አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል…በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ…በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ…“በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው”–ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ…ጋዜጠኛ አበበ ገላው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጠው ማብራሪያና ሌሎችም

$
0
0

Habitamu
የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 11 ቀን 2007 ፕሮግራም

ለኢትዮጵያውያን በሙሉ በሊቢያ ፣በደቡብ አፍሪካና በየመን ለሞቱ ወገኖቻችን ነፍስ ይማር ! መጽናናትን እንመኛለን !

< ...በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪካና በየመን በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያውያን ማዘን ማልቀስ ብቻ በቂ አይደለም። በአገር ቤትም በውጭም በንጹሃን ላይ የሚደርሰውን ጥቃት ማስቆም የሚቻለው ተባብረን ይሄን ስርዓት ማስወገድ ስንችል ብቻ ነው…የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ በኢትዮጵያ ጉዳይ አልተቀየረም የሴትዮዋ ንግግር መሰረተ ቢስ ነው ራሳቸው ማብራሪያ ይሰጡበታል…>

ጋዜጠኛ አበበ ገላው በሊቢያ ፣በደቡብ አፍሪካና በየመን ስለሞቱ ወገኖቻችንና የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ባለስልጣንን መግለጫ አስመልክቶ ከሰጠን ማብራሪያ የተወሰደ

<… በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው…መፍትሄው በሀይማኖት ፣በጎሳ ሳንከፈል መከራ ሲደርስብን አብሮን የሚቆም መንግስት የሌለን በመሆኑ ለራሳችን ራሳችን እንነሳ…> ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ ስለ የሊቢአው የአይ.ሲ.ስ የአሸባሪዎች ድርጊትና ተያያዥ ጉዳዮች ጠይቀነው ከመለሰው (ሙሉውን ያዳምጡት)

በሊቢያ በአይ.ሲ.ስ አሸባሪዎች የተገደሉት ኢትዮጵያውያን ፣ የስርዓቱ ግዴለሽነትና የግብጽ ከአሸባሪው ጋር መፋለም (ልዩ ጥንቅር)

<...ሁለት ወንድሞቼ ደቡብ አፍሪካ ናቸው እነሱ ያሉት እኛ ቢያንስ እየታገልን የምንሞት ነን በሊቢያ የታረዱ፣በጥይት በአሸባሪዎች የተገደሉ ወገኖቻችን ጉዳይ አስለቅሶናል ።የመንግስት ተብዬው ክህደት አሳዝኖናል እባካችሁ በመላው ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን ጸልዩ እያሉ ነው …>

አስተያየት ሰጪ ለህብር ከገለጹት

<…ኢትዮጵያውያንን በቁም ያቃጠሉትን ለፍርድ ለማቅረብ እየተንቀሳቀስን ነው…ችግር ላይ ያሉትን ለመርዳት ሩጫ ላይ ነን…>

አቶ ደረጄ መኮንን በደቡብ አፍሪካ ጆሐንስበርግ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ዋና ጸሐፊ ለህብር ከሰጡት

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር በሚገኙበት በቬጋስ የተጠራው ስብሰባ ( ከስብሰባው አዘጋጆች አንዱ አቶ አሸብር ጋር የተደረገ ቆይታ)

<…በደቡብ አፍሪካ አሁንም ሕይወታችን አደጋ ላይ ነው ዙሉዎቹ ቀድሞም አጋጣሚ ነው የሚፈልጉት ወገኖቻችን ይጩህልን…> አቶ ታሪኩ ጀማል ከደርባን ደቡብ አፍሪካ አቅራቢያ ለህብር እንደተናገሩት(ሙሉውን ያዳምጡ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በሊቢያ ተጨማሪ ኢትዮጵያውያን አደጋ ውስጥ ናቸው

በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል

በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በወገኖቻቸው ላይ እሳት በቁማቸው የለኮሱትን በህግ ለመፍረድ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ገለፁ

በደርባን በድርጊቱ የተጠረጠሩ 19 የዙሉ ጎሳ አባላት ተይዘዋል

በአሸባሪው አይ.ሲ.ስ ሊቢያ ላይ አንገታቸው ተቀልቶና በጥይት ተደብድበው በሞቱት 30 ወገኖቻችን ጉዳይ ቁጣቸውንና ሐዘናቸውን እየገለፁ ነው

አገዛዙ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን አላጣራሁም ማለቱ የተለመደ የስርዓቱ ጭካኔ ነው ተብሏል

በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ

በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: በየመን ያሉም ኢትዮጵያውያን የአይሲስ በሊቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደው የግፍ ግድያ ይፈጸምብናል የሚል ስጋት ፈጥሮባቸዋል… በደቡብ አፍሪካ ያሉ ኢትዮጵያውያን ጥሪ አስተላለፉ… በኬኒያ እስር ቤት ያሉ 62 ኢትዮጵያውያን የረሀባ አድማ መቱ… “በሊቢያ ወገኖቻችንን ያረዱት፣ በጥይት የገደሉት እነዚህ በየትኛውም የእስልምና አስተምህሮ የተወገዙ ሰይጣኖች ናቸው” – ጋዜጠኛ ሳዲቅ አህመድ… ጋዜጠኛ አበበ ገላው በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ የሰጠው ማብራሪያና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

“በሊቢያ የተፈጸመው የጭካኔ ተግባር የማንኛውም ሃይማኖት ተቋምና እምነት የማይወክል የአሸባሪዎች ተግባር ነው”ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ

$
0
0

H_E_Abune_Matiyas_Archbishop_of_Jerusalem_Misa
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን

ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ/ም ከእኩለ ቀን ጀምሮ በመላው ዓለም ያሉ የዜና ማሰራጫዎች በሰሜን አፍሪካ በሊቢያ የሜዲትራንያን ባህር ዳርቻ አካባቢ አይኤስ በተባለ አሸባሪ ቡድን በንጹሐን ወገኖች አሰቃቂ ግድያ እንደተፈጸመባቸው ዘግበዋል፡፡
ዘገባው ከምኑም ከምኑ የሌሉበት ንጹሐን ክርስቲያን ወጣቶች በታጠቁና ፍጹም ሰብኣዊነት በሌላቸው አሸባሪዎች ሲገደሉ የሚያሳየው ምስልም በመላው ዓለም እየታየ ይገኛል፡፡

አሰቃቂው ግድያ ስለተፈጸመባቸው ንጹሐን ወጣቶች ዜግነትና ማንነት ግልጽና አስተማማኝ የሆነ መረጃ ለማግኘት ጥረት እየተደረገ ቢሆንም እስካሁን ድረስ በበርካታ የዓለም ዜና ማሰራጫዎች ሲነገር እንደሚሰማው የዚህ የግፍ ወንጀል ሰለባዎች ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አማኞች መሆናቸውን የዜና ማሰራጫዎቹ አክለው እየገለጹ ነው፡፡

የኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በፈጣሪ የተሰጠች የማንኛውም የሰው ልጅ ሕይወት ኃላፊነት በማይሰማቸውና በእነሱ ላይ ሊደረግ በማይፈቅዱ ምንም ዓይነት ሰብአዊ ርኅራኄ በሌላቸው እንድትቀጠፍ ስለማትፈቅድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ይህንን አሰቃቂ ድርጊት በጽኑ ትቃወማለች፣ አጥብቃም ታወግዘዋለች፡፡

ስለዚህ የዚህ ግፍ ሰለባ የሆኑት ወገኖቻችን ማንነት ተረድተን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ትውፊት መሠረት አስፈላጊውን ሁሉ የምናደርግ መሆኑን ሕዝበ ክርስቲያኑና መላው ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ተገንዝበው ሁኔታውን በትዕግሥት እንዲጠብቁ፤
እንደዚሁም የተፈጸመው የጭካኔ ተግባር የማንኛውም ሃይማኖት ተቋምና እምነት የማይወክል የአሸባሪዎች ተግባር መሆኑን ተገንዝበው ኢትዮጵያውያን የሆኑ ሁሉ እንደቀድሞው በአንድነት በማውገዝ የዚህ ድርጊት ፈጻሚዎች ኪሣራ እንጂ ምንም ዓይነት ትርፍ የማያገኙ መሆናቸውን በተግባር እንዲያሳዩዋቸው እናሳስባለን ፡፡

እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦቿን ይባርክ
አሜን
አባ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ
ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት
አዲስ አበባ

The post “በሊቢያ የተፈጸመው የጭካኔ ተግባር የማንኛውም ሃይማኖት ተቋምና እምነት የማይወክል የአሸባሪዎች ተግባር ነው” ፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live