Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

አይሲኤስ ሕይወታቸውን የቀጠፈው ኢያሱና ባልቻ ማን ናቸው?

$
0
0

በሊቢያ የአሸባሪው ቡድን ‘አይኤስአይኤስ’ ታጣቂዎች፣ ’28balcha-and-eyasu ኢትዮጵያዊያን ክርስትያኖችን ገድለናል’ ብለው በቪዲዮ የተቀረፀ አሰቃቂ የጭካኔ ግድያ ያሰራጩት በሳምንቱ መጨረሻ ላይ ነው። በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ በደረሰው ዘረኛ ጥቃት ማግስት፣ በሊቢያ ሲቪል ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ላይ የተፈፀመው የአሸባሪ ቡድን ዘግናኝ ግድያ፤ የኢትዮጵያውያን ሐዘንና ቁጭት አክብዶታል።
በኢንተርኔት የተሰራጨው ቪዲዮና ፎቶ፣ የሟቾቹን ማንነት ወዲያውኑ ለማወቅና ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ለማረጋገጥ ለብዙዎች አስቸጋሪ ቢሆንም፣ ለቤተሰቦች ግን አጠራጣሪ አልነበረም። ወላጆችና ቤተሰብ፣ ወንድምና እህት፣ ጎረቤትና ወዳጆች ሁሉ ውስጥን በሚያደማ ቅፅበታዊ ሐዘን ነው የተመቱት።

በአዲስ አበባ የኢያሱ ይኩኖአምላክ እና የባልቻ በለጠ ቤተሰቦች ድንገተኛ መርዶ የደረሳቸው እሁድ እለት ነው። በሰላሳዎቹ ዕድሜ ላይ የነበሩት ኢያሱና ባልቻ በአንድ ሰፈር ውስጥ ያደጉ ጎረቤታሞች ናቸው – በቀድሞው ወረዳ 21 ቀበሌ 25፤ በአሁኑ ወረዳ 10። የሟቾቹ ቤተሰቦች መኖሪያ ቤት አጠገብ ለአጠገብ ስለሆነ ለቅሶውም አንድ ላይ ነው፡፡

ኢያሱና ባልቻ የዛሬ ሁለት ወር ገደማ ወደ ሊቢያ የሄዱት አንድ ላይ እንደሆነ የገለፀልን የኢያሱ ወንድም፤ የሊቢያውን የግድያ ወሬ የሰማው እሁድ ዕለት ነው – ስልክ ተደውሎ። የደወለለት ሰው፣ “የናንተ ሰፈር ልጆች ሊታረዱ ሲሉ የሚያሳይ ፎቶ በፌስቡክ ተለጥፏል” ብሎ ሲነግረው፤ በደንጋጤ “እነማን ናቸው?” ብሎ ጠየቀ። “የወንድሜን ስም ጨምሮ ነገረኝ፤ የወንድሜን ስም አያውቅም ነበር” ይላል የኢያሱ ወንድም።
“የኔ ፌስቡክ ስለማይሰራ ጓደኛዬ ጋር ሄጄ አየሁ። በደንብ ስላልታየኝ እንደገና ከምሽቱ አራት ሰአት ስንከፍት ወንድሜን ተንበርክኮ አየሁት። ባልቻን ደግሞ ቀይ ቱታ ካደረጉት መሀል ለየሁት፡፡ ለእናቴ ከመንገሬ በፊት ለሩቅ ዘመዶች ለመናገር እያሰብኩ እያለ እነሱ ቀድመው ሰምተው ለቅሶ ላይ አገኘኋቸው” ብሏል የኢያሱ ወንድም።
ኢያሱ ኳታር ሰርቶ የተወሰነ ገንዘብ ይዞ ስለመጣ የባልቻንም ወጪ ሸፍኖለት ነው አብረው የሄዱት። ከኢትዮጵያ ወጥተው በሱዳን ጉዞ የጀመሩት ከሁለት ወር በፊት ነው። “ሱዳን እያሉ በስልክ እንገናኝ ነበር። ገንዘብ ሲያስፈልጋቸው እልክላቸው ነበር” የሚለው የኢያሱ ወንድም፤ “ወደ ሊቢያ ከተሻገሩ በኋላ ግን ስልክ ቁጥር እሰጥሃለሁ ቢለኝም አንገናኝም ነበር” ብሏል።

ምንጭ፦ አዲስ አድማስ

The post አይሲኤስ ሕይወታቸውን የቀጠፈው ኢያሱና ባልቻ ማን ናቸው? appeared first on Zehabesha Amharic.


ድምጻችን ይሰማ አይሲኤስ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የፈጸመውን ግድያ በማውገዝ መግለጫ አወጣ

$
0
0

ይህ መግለጫ በርግጥም ኢትዪጲያዊኖች ሽብር አጥብቀው የሚዋጉና ሰላም ወዳድነታቸውን አመላካች ነው የመግለጫው ሙሉ ቃል እነሆ
=================================
ኢ–ሰብአዊነትንና ሽብርን ደግመን እናውግዝ! ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን እንታደግ!
ሰኞ ሚያዝያ 12/2007

በአለማችን የተለያዩ ክፍሎች የሰው ፍጡር ክቡርነቱ ረክሶ ፍጡር በፍጡር ላይ ግፍና ጭካኔ የተመላን እኩይ ስራ ሲሰራ ማየት የእለት ተእለት ዜና እየሆነ መጥቷል፡፡ በተለያዩ አካላት፣ መንግስታትም ይሁን ቡድኖች ንፁሀን እንደቅጠል እየረገፉ እናያለን፤ እንሰማለን፡፡ ሰሞኑን እየተሰሙ ያሉት ዜናዎች ደግሞ መላውን ኢትዮጵያዊ እያሳዘኑና አንገት እያስደፉ ይገኛል፡፡
ethiopian killed by isil 1
በተለያዩ ምክንያቶች ዜጎች የተሻለ ህይወት ፍለጋ ሀገራቸውን እየለቀቁ ሲሰደዱ ለከፍተኛ አደጋ ይጋለጣሉ። በመንገድ ላይ ዘራፊና ሽፍታ፣ ረሀብና ጥማት፣ እንግልትና እስር ይፈራረቁባቸዋል፡፡ ወደተሻለ ቦታ ለመሻገር ባህር ሲሻገር ሰጥሞ የሚሞተውም ተበራክቷል።

በደቡብ አፍሪካ ኢትዮጵያውያን እና ሌሎችም አፍሪካውያን ዜጎች ላይ አሰቃቂ የግድያ ወንጀል እየተፈጸመባቸው ይገኛል። ሰቅጣጩ የጭካኔ ምግባር አፍሪካዊያን ላይ በአፍሪካዊያን የሚፈፀም መሆኑ ደግሞ ይበልጥ አሳዛኝ ያደርገዋል፡፡ ከአስርት ዓመታት በፊት ምእራባዊያን ደቡብ አፍሪካዊያን የሚያደርጉትን የፀረ-አፓርታይድ ትግልና መሪያቸውን ኔልሰን ማንዴላን በ«ሽብርተኝነት» ፈርጀው ሳለም እንኳን ኢትዮጵያና ሌሎች አፍሪካዊያን ትግላቸውን ደግፈዋል፡፡ ይህ ታላቅ ውለታ ተዘንግቶ የተፈፀመው እና ሰሞኑን እያየነው ያለውን የጥላቻና የግፍ ግድያ ሰብአዊ ፍጡር ሁሉ ሊያወግዘው ይገባል። ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ይህንን ተግባር በአንድ ድምፅ እናወግዛለን፤ እንቃወማለንም፡፡

በሊቢያም በክርስትያን ወገኖቻችን ላይ አይሲስ በተባለው የሽብር ቡድን የተፈፀመው አሰቃቂ ተግባር ሌላው አሳዛኝ ክስተት ነው፡፡ ይህ ስብስብ የሚሰራውን አሰቃቂ የግፍና የሽብር ተግባር «እስላማዊ» ካባ ሊያላብስ ቢሞክርም በዓለም ዙሪያ ያሉ ሙስሊሞች በአንድ ድምፅ አውግዘውታል፡፡ ጌታችን አላህ በቅዱስ ቁርአን ሱረቱል ማኢዳህ 5፡32 አንድን ነፍስ ያለአግባብ መግደል ሁሉንም ሰብአዊ ፍጡር መግደል እንደሆነ፣ በአንፃሩም አንድን ነፍስ ህያው ማድረግ (መታደግ) ሁሉንም ሰው ህያው እንደማድረግ መሆኑን በማያሻማ ሁኔታ ገልፆዋል። ይህ የሰብአዊ ፍጡርን ሕይወት ዋጋ ትልቅነት የሚያሳይ መሆኑን በርካታ የእስልምና ዑለሞች (ሊቃውንት) ያስረዳሉ፡፡

አይሲስ የተባለው የሽብር ቡድንና «የእሱን ፈለግ እንከተላለን» የሚሉ ሌሎች ቡድኖች ሙስሊሙንም ክርስትያኑንም በግፍ ሲገድሉ ቆይተዋል፡፡ ከህጻናት እስከ ዩኒቨርሲቲ ያሉ ተማሪዎችን በማደሪያ ቦታቸውና በትምህርት ቦታቸው ባሉበት ገድለዋል። ለአምልኮ የተሰባሰቡ ሰዎችን በመስጊድም በቤተ ክርስቲያንም ጨፍጭፈዋል፤ በስደትም ይሁን «በበጎ አድራጎት ተግባር ላይ እንሰማራለን» ብለው ወደሌላ አገር የተጓዙ የሌላ አገር ዜጎችንም ሳይቀር እንደዋዛ በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋል፡፡ ይኸው ትናንት በተሰማ ዜና ደግሞ 28 ኢትዮጵያውያን የክርስትና ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቻችን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ በሽብር ቡድኑ ተገድለዋል። እንደዚህ አይነቱን የሽብር ተግባር በእርግጥም ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ከማውገዝም ባሻገር እንደሙስሊምነቱም እንደዜግነቱም አላህ በሰጠው ችሎታ ለመከላከል የበኩሉን ስራ መስራት አለበት፡፡ በተለያዩ ሀገራት በስደት ላይ ሆነው ህይወታቸው ከፍተኛ ችግር ላይ ለወደቁ ዜጎች በተገኘው ቀዳዳ ድጋፍ የመስጠት ስራ ላይ መሳተፍ አስፈላጊ ነው። በግለሰብ፣ መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶችና ተቋማትም እንዲሁ የሚችሉትን ማድረግ ያስፈልጋል።

በመንግስት በኩልም አፋጣኝ ምላሽ ያሻል። መንግስትም ይሁን ሌሎች አካላት ጊዜው የፖለቲካ ትርፍና ኪሳራ የሚሰላበት፣ አልያም የወቀሳና ክርክር መድረክ የሚፈጠርበት አለመሆኑን ተገንዝበው ዜጎችን የማዳኑ ተግባር ላይ ትርጉም ያለውና ውጤት የሚያመጣ ስራ ላይ መጠመድ ዋነኛ ተግባራቸው ሊሆን ይገባል፡፡ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞችም ይህንን ተግባር በይፋ ከማውገዝም ባለፈ በቻልነው ሁሉ ዜጎችን ከአደጋ የመታደግ ስራ ልንሰራ ይገባል። ቤተሰቦቻቸው ለሞቱባቸው ሁሉ መፅናናትን እንመኛለን!!!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post ድምጻችን ይሰማ አይሲኤስ በኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ላይ የፈጸመውን ግድያ በማውገዝ መግለጫ አወጣ appeared first on Zehabesha Amharic.

(ሊያደምጡት የሚገባ) አለምነህ ዋሴ የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን “የሊብያ ሰማዕታት”ጽሁፍ እንደሚከተለው አንብቦታል

$
0
0


ethiopian killed by isil 3

“ሁለተኛው የሚጎድለው ነገር ደግሞ ፍጥነት ነው፡፡ አትሌቶቻችን በኦሎምፒክ ሲያሸንፉ የባለሥልጣናቱ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልእክት ሯጮቹ ቆርጠውት ካለፉት ሪቫን ቀጥሎ የሚመጣ ዜና ነበር፡፡ አትሌቶቹ ደክሟቸው ከመሬት ሳይነሡ የባለሥልጣናቱ መልእክት ለሚዲያ ይደርስ ነበር፡፡ በዚህ የሁላችንም ኀዘን በሆነው ጉዳይ ግን ለምን መዘግየት እንደተመረጠ ግልጽ አይደለም፡፡ ማጣረቱ፣ መረጃ መሰብሰቡ፣ ተጨማሪ የዲፕሎማሲ ሂደቶችን መሄዱ ጊዜ ይወስዳል፡፡ ማዘን ግን ጊዜ አይወስድም፡፡ ቪዲዮው ተለቅቋል፡፡ ሲሞቱ እያየን ነው፡፡ መልካቸው የኛው ነው፡፡ አይሲስ የገደላቸው ‹ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች› ብሎ ነው፡፡ የዓለም ሚዲያዎች ያንኑ እያስተጋቡ ነው፡፡ ይኄ ለኀዘን ያንሳል? አፈፍ ብሎ ተነሥቶ ‹በሆነው ነገር እናዝናለን፤ ልባችን ተነክቷል፤ ለቤተሰቦቻቸው መጽናናትን እንመኛለን፤ ዝርዝሩን በየጊዜው እንነግራችኋለን› ለማለት ስንት ሰዓት ይወስዳል? የደቡብ አፍሪካው ችግር ደረሰ እንደተባለ ሙጋቤን ለውግዘት የቀደማቸው የለም፡፡ የኛዎቹስ የት ሄዱ?”

The post (ሊያደምጡት የሚገባ) አለምነህ ዋሴ የዲ/ን ዳንኤል ክብረትን “የሊብያ ሰማዕታት” ጽሁፍ እንደሚከተለው አንብቦታል appeared first on Zehabesha Amharic.

“የኢትዮጵያ ሕዝብ ስደትን አቁሞ እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ ወይም በሕዝባዊ እምቢተኝነት ሃገሩን ሳይለቅ ይሳተፍ”–አርበኞች ግንቦት 7

$
0
0

ሀያ ስምንት ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ዛሬ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓ.ም. ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደርሷል። ይህ አሰቃቂ መርዶ ልብን የሚሰብር ነው። አይ ሲስ በጥንት በጭለማ ዘመን እንኳን ባልነበረ ጭካኔ ራሳቸውን መከላከል የማይችሉ ሰዎችን በማረድ የሚደሰት፤ በሰው ዘር ሁሉ ላይ የመጣ አውሬ መሆኑን ነብዩ መሐመድ አትድረሱባቸው ያሏቸውንም ኢትዮጵያዊያንን ጭምር በማረድ አረጋገጧል። ይህ አሰቃቂ ተግባር ምንም ዓይነት አመክኖ ሊቀርብለት የማይችል አረመኔዓዊ የሽብር ጥቃት ነው።

ginbot 7አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ በወገኖቻችን ላይ በደረሰው አሰቃቂ ግድያ የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን ይገልፃል፤ ለሟች ቤተሰቦችና ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ መጽናናትን ይመኛል። ኢትዮጵያዊያን ሁሉ አይ ሲስን በጥብቅ እንዲያወግዙ፤ በአመቻቸው መንገዶች ሁሉ እንዲታገሉት አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።

በዚህ አጋጣሚ የአይሲስን የሽብር ተግባራት ከእስልምና እምነት ጋር ማያያዝ ፈጽሞ ትክክል እንዳልሆነ፤ ብዙሃን ሙስሊሞች የአይሲስና መሰል ቡድኖችን አካሄድ የሚቃመው መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ማስገንዘብ ይሻል። ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች ከክርስቲያን ወገኖቻቸው ጋር ተዋደውና ተፋቅረው የኖሩና እየኖሩ ያሉ ሲሆን የሁለቱ ሀይማኖቶች ተከታዮች ተደጋግፎ መኖር ለሀገራችን ህልውና ወሳኝ ጉዳይ መሆኑ የአርበኞች ግንቦት 7 እምነት ነው።

በያዝነው ሣምንት በወገኖቻችን ላይ እልቂት ሲደርስ የሊቢያ ብቸኛ ክስተት አይደለም። በደቡብ አፍሪቃ ወገኖታችን ከነሕይወታቸው በእሳት ተቃጥለው ተገድለዋል፤ በስለት ተዘልዝለዋል፤ ንብረታቸውን ተዘርፈዋል። በዛሬው ዕለት 700 ዜጎች የሜዲተራኒያን ባህር በጀልባዎች ሲሻገሩ መስመጣቸው ተሰምቷል። በየመን ደግሞ በርካታ ወገኖታችን በጦርነት እሳት ውስጥ እየተማገዱ ናቸው።

ኢትዮጵያዊያን በአገራችን የሰፈነውን የነፃነት እጦት፣ የፍትህ መጓደልና የኑሮ መክበድ ሸሽተን በሄድነት አገር ሁሉ የሚጠብቀን አሰቃቂ ሞትና ውርደት ሆኗል። ኢትዮጵያ ለኑሮ ያልተመቸችን በህወሓት አገዛዝ ብሉሽነት መሆኑ ጥርጥር የለውም። ይህንን ብልሹ አገዛዝ አስወግደን በምንወዳት አገራችን ተከብረን መኖር እንችላለን። ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለ አገር የለም።

አርበኖች ግንቦት 7: የኢትዮጵያዊያን መከራ እንዲያበቃ ስደት ይብቃ ይላል። እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባሌውና እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ አሊያም የሥራ ቦታውና መኖርያው ሳይለቅ በሕዝባዊ እምቢተኝነት በተደራጀ መንገድ የህወሓትን አገዛዝን ይታገል። በሕዝባዊ አመጽና በሕዝባዊ እምቢተኝነት የህወሓት ፋሽስቶችን አስወግደን በአገራችን በነፃነትና በክብር እንድንኖር ሀይማኖትም ሆነ የዘር ሀረግ ሳይለየን በጋራ እንታገል የሚል ጥሪ ያቀርባል።

ዘላለማዊ ክብርና እረፍት ለግፍ ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን

The post “የኢትዮጵያ ሕዝብ ስደትን አቁሞ እንደችሎታው በሕዝባዊ አመጽ ወይም በሕዝባዊ እምቢተኝነት ሃገሩን ሳይለቅ ይሳተፍ” – አርበኞች ግንቦት 7 appeared first on Zehabesha Amharic.

(ሰበር ዜና) የሊቢያውን ግድያ በመቃወም በአ.አ. ድንገተኛ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው * ወደ ቤተመንግስት ያመራው ሕዝብን ፖሊስ ቢመልሰውም መስቀል አደባባይ እየተሰበሰበ ነው

$
0
0

cherkos addis ababa

* ፌደራል ፖሊስ ለሐዘን የወጣውን ሕዝብ መደብደብ እና ማሰር ጀመረ
* ሐዘናቸውን የመኪና ጡሩምባ የሚያሰሙ ሹፌሮችን እያዋከበ ነው
* ሕዝቡን ከመስቀል አደባባይ ለመበተን ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሠራዊት ሰፍሯል

(ዘ-ሐበሻ) በሊቢያ አይሲኤል 28 ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ከገደለ በኋላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጣውን በተለያየ መንገድ እየገለጸ ይገኛል:: በስልጣን ላይ ያለው ይህ ሁሉ ሕዝብ በአሰቃቂ ሁኔታ ሕይወቱን አጥቶ ለጉዳዩ ትኩረት አለመስጠቱ ያንገሸገሸው ሕዝብ በአዲስ አበባ በራሱ አነሳሽነት ከቤቱ ተነስቶ ወደ ቤተመንግስት ያመራ ሲሆን የመንግስት ወታደሮች እየመለሷቸው ይገኛሉ:: ሰልፈኛው “ከቤተመንግስት የምታስመልሱን ከሆነ መስቀል አደባባይ ሆነን እናለቅሳለን… መንግስት የለንም” በሚል ተቃውሞውን እያሰማ ይገኛል::

ፖሊስ ለሐዘን የወጣውን ሕዝብ ወደ ቤቱ እንዲመለስ እያሰገደደ እንደሆነ የገለጹት የዘ-ሐበሻ ምንጮች
ተከብረሽ የኖርሽ በአባቶቻችን ደም፣
እናት ኢትዮጵያ የደፈረሽ ይውደም
እያለ መዝሙር እንደሚያሰማም አስታውቀዋል:: ፌደራል ፖሊሶቹ መንግስት ሐሙስ የራሱን ሰልፍ ስለሚጠራ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ እያሉ ቢያግባቡም “እንዴት እስከ ሐሙስ ጠብቁ ትሉናላችሁ?” የሚል ጥያቄ እያነሳም እንደሆነ ታውቕል::
‹‹መንግስት የሌለው ኢትዮጵያ ብቻ ነው!››
‹‹መንግስት የሌለን እኛ ብቻ ነን!››
እያለ መፈከር እያሰማ ወደ መስቀል አደባባይ የሚተመው ሕዝብ ቁጥር እየጨመረ ነው::

ጉዳዩን ተከታትለን እንዘግባለን::

The post (ሰበር ዜና) የሊቢያውን ግድያ በመቃወም በአ.አ. ድንገተኛ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ ነው * ወደ ቤተመንግስት ያመራው ሕዝብን ፖሊስ ቢመልሰውም መስቀል አደባባይ እየተሰበሰበ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በአ. አ. አይሲኤል እና ቸልተኛው የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም ድንገት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቭዲዮ (Video + Text)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) አይሲኤል የተባለው አሸባሪ ቡድን 28 ኢትዮጵያውያንን በሊቢያ ሕይወታቸውን ካጠፋ በኋላ ዛሬ በአዲስ አበባ እየተደረገ ባለው ድንገተኛ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ሐዘኑን ሊገልጽ ክወጣው ሕዝብ መካከል ወጣቶች እየተመረጡ በቆመጥ ተደበደቡ:: ሕገወጥ ሰልፍ አድርጋችኋል በሚልም ሕወሓት የሚመራው መንግስት ወጣቶችን እያሰረ ይገኛል::

28 ኢትዮጵያውያን ነብሳቸውን በአይሲኤል ሲነጠቁ ዜጎቼ መሆናችውን አላጣራሁም ሲል በሟቾቹ ጉዳይ ግድም እንደሌለው ያሳየው ሕወሓት የሚመራው መንግስት ወታደሮቹን በማሰማራት በመስቀል አደባባይ በመሰብሰብ ላይ የነበረውን ሕዝብ መደብደቡ የሃገር ፍቅርና የወገን ፍቅር ከሌለው መንግስት የሚጠበቅ ተግባር ነው ሲሉ የፖለቲካ ተንታኞች አስተያየታቸውን ይሰጣሉ::
addis ababa cherkos
ወደ መስቀል አደባባይ በአይሲኤል እና በዜጎቹ ላይ ቸልተኛ በመሆነው የኢትዮጵያ መንግስት ላይ ተቃውሞውን ለማሰማትና ለሞቱት ወንድሞች ሐዘኑን ለመግለጽ የወጣው የአዲስ አበባ ሕዝብን በመስቀል አደባባይ በብዛት እንዳይሰበሰብ የመንግስት ወታደሮች ወደ መስቀል አደባባይ በተቃውሞ የሚተመውን ሕዝብ ከየመጋቢ መንገዶች እየቆረጡ ሕዝቡን ለማስቅቅረት እየሞከሩ ነው ተብሏል::

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እንመለሳለን

The post በአ. አ. አይሲኤል እና ቸልተኛው የኢትዮጵያ መንግስትን በመቃወም ድንገት የተደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ቭዲዮ (Video + Text) appeared first on Zehabesha Amharic.

በአይሲኤል ሕይወታቸውን ከተቀጠፉት መካከል አንዱ አወቀ ገመቹ

$
0
0

በሊቢያ በአይሲኤል ሕይወታቸውን ካጡት ኢትዮጵያውያን መካከል የሁሉንም ኢትዮጵያውያን ማንነት ማረጋገጡ ቀጥሏል:: የተወሰኑትን ማንነት ዘ-ሐበሻ ባለፉት ቀናት ስታስተዋውቅ ቆይታለች:: የሁሉም በደረሰን ጊዜ ለማቅረብ እንሞክራለን:: በዚህም መሠረት ሕይወታቸውን ካጡት ውስጥ አወቀ ገመቹ ቡባ ይገኝበታል:: ከምስራቅ ወለጋ ሆሮጉድሩ ወደ ሊቢያ የተጓዘው አወቀ ሕይወቱ በ እንዲህ ያለው ሁኔታ ማለፉ በጣም ያሳዝናል::

እስካሁን ያወቅናቸው፦
1. ኢያሱ ይኵኖአምላክ
2. ባልቻ በለጠ
3. ዳንኤል ሐዱሽ
4. ቡሩክ ካሳሁን
5. ኤልያስ ተጫኔ
6. በቀለ ታጠቅ
7. በቀለ አርሰማ
8. ዳዊት ሐድጉ
9. መንግሥቱ ጋሼ
10. ጀማል ራህማን
11. አወቀ ገመቹ
ለቤተሰቦቹ መጽናናትን እንመኛለን::
aweke

aweke horo gudru

The post በአይሲኤል ሕይወታቸውን ከተቀጠፉት መካከል አንዱ አወቀ ገመቹ appeared first on Zehabesha Amharic.

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን ማራካሱን ቀጥሎበታል

$
0
0

kirkos

ማምሻውን ፖሊሶችና ፌድራል ፖሊሶች ጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ መፈጸማቸውን ጉዳት የደረሰባቸው ለቢቢኤን ገለጹ::

ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን በማርከስ ከዚህ ቀደም በገዳማት በመስጅዶች ውስጥ በመግባት በምእምናን ላይ ድብደባ ሲፈጸም መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን በዛሬው እለት በጨርቆስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ድረስ በመዝለቅ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸማቸውን በቦታው ላይ ድብደባ የተፈጸመባቸው ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡

በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከሚስቱ ጋር እንደነበር የገለጸው ወጣቱ ፖሊሶቹ ሴት ወንድ ሳይሉ ከሁለት መቶ በላይ በሚሆኑት ምእምናን ላይ ድብደባ እንደፈጸሙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በቤተክርስቲያኑ የነበሩትን አማኞች በከደበደቡ በሁላ በየክፍለ ከተማቸው በመለየት በመኪና ጭነው እንደወሰዷቸው በድጋሚ እንደደቧቸው ተናግረዋል;፡

በመጨረሻም ፎቶ አንስተው አሻራ ተቀብለው ከምሽቱ 5፤45 እንደለቀቋቸው ለቢቢኤን ገልጸዋል፡፡ መንግስት የሃይማኖት ነጻነት አክብሪያለሁ እያለ የእምነት ተቋማትን ክብር ጭምር በመዳፈር የዚህ አይነት አስነዋሪ ድርጊት በመፈጸማቸው ማዘናቸውን ምእምናኑ ገልጸዋል፡፡

The post ህወሃት መራሹ ኢህአዴግ የእምነት ቦታዎችን ማራካሱን ቀጥሎበታል appeared first on Zehabesha Amharic.


በሲድኒ አውስትራሊያ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ እና የሻማ ማብራት ምሽት

$
0
0

በሲዲኒ አውስትራሊያ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሊቢያ በአይሲኤል አማካኝነት ሕይወታቸውን ለተቀጠፉ; እንዲሁም በየመን እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ሕይወታቸውን ላጡት ኢትዮጵያውያን መታሰቢያ የሚሆን የተቃውሞ እና የሻማ ምሽት የፊታችን እሁድ ጠርተዋል:: ፍላየሩን በመጫን አሳድገው ይመልከቱት::
Sydney Ethiopians australia

The post በሲድኒ አውስትራሊያ ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ እና የሻማ ማብራት ምሽት appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸው ታወቀ • 500 በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታስረዋል

$
0
0

self
(ነገረ ኢትዮጵያ) መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰልፈኛው ‹‹መንግስት በዜጎቻችን ላይ ለተፈፀመው አረመኔያዊ እርምጃ በቂ ምላሽ እየሰጠ አይደለም›› በሚል ባሰሙት ተቃውሞ በርካቶች ተደብደበው ከተሳሩና ሰልፉ ካበቃ በኋላ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትና የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል በርካቶች እየታደኑ መታሰራቸውን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

ሰልፉ ካበቃ በኋላ ታድነው ከታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል ብሩክ የኔነህ ማታ 12 ሰዓር ላይ የተያዘ ሲሆን በአሁኑ ወቅት አራዳ መምሪያ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡ በተመሳሳይ ዜና ከሰልፉ በኋላ ከ500 በላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተይዘው አራት ኪሎ አካባቢ በሚገኘው 2ኛ ፖሊስ ጣቢያ ላይ ታስረው እንደሚገኙ ተማሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ጠና ይታየው፣ ይድነቃቸው አዲስና እስክንድር ጥላሁን የተባሉት የሰማያዊ ፓርቲው ዕጩዎች ሌሊት 6 ሰዓት ላይ ከአባላት ተለይተው መፈታታቸውን አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታድነው መታሰራቸው ታወቀ • 500 በላይ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ታስረዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

”ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው”–ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

$
0
0

Birhanu Nega PHD
የአርበኞች ግንቦት 7 የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያቀረቡት አስቸኳይ ጥሪ

የተከበራችሁ ወገኖቼ፤ ከሰላሳ በላይ የሆኑ ወገኖቻችን አይ ሲስ በተሰኘ ህሊና ቢስ፣ ፀረ-ሰው እና ፀረ-ስልጣኔ ቡድን በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የመገደላቸው መርዶ ከትናንት ወዲያ ሚያዝያ 11 ቀን 2007 ዓም ደርሶን ኢትዮጵያዊያን በያለንበት በመሪር ሀዘን ውስጥ ነን። ዛሬ “እግዜር ያጥናህ” ወይም “እግዜር ያጥናሽ” የሚባል ሰው የለም። ሁላችንም ሀዘንተኞች ነን። ካጣናቸው ቁጥራቸው በብዙ እጥፍ የሚበልጥ ወገኖቻችን አሁንም በአራዶች መዳፍ ውስጥ መሆናቸው ሀዘናችን እጅግ የበረታ ያደረገዋል። ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ ሆኖም በሺህ የሚገመቱ ኢትዮጵያዊያን ዛሬም ሊቢያ ውስጥ ናቸው። በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያን አሁንም ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ ናቸው። ሌሎች በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችን ደግሞ በየመን ከሰማይም ከምድርም በቦንብና በጥይት እየተማገዱ ነው።

ለምንድነው ኢትዮጵያዊያን እንዲህ እሳት ውስጥ ለመማገድ የምንደፍረው? መልሱ ግልጽ ነው። አገር ውስጥ ተስፋ የለም፤ ወያኔዎች ተስፋችንን አጨለሙት። ከሳዉዲ በመከራ የተመለሱ ወንድሞቻችን ናቸው በሊቢያ በኩል ለመሰደድ ሲሞክሩ በአይ ሲስ ተይዘው የታረዱት። ወያኔዎች አገራችንና ክብራችን ዘረፉን። ወያኔዎች ስብዕናችንን ገፈፉን።

የዘመኑ ጥቂት የህወሓት ቱጃሮች ፎቆችን እየገነቡ በነሱ መጥገብ እኛ እንድናገሳላቸው ይፈልጋሉ። የኢትዮጵያ ሕዝብ መራቡ፣ መታረዙ፣ መደህየቱ እውነት ነው፤ ሆኖም ግን “ተራብኩ”፣ “ታረዝኩ”፣ “ደኸየሁ” ብሎ መናገር አይችልም። እውነት መናገር ያስቀጣል፣ ያስወነጅላል። በፍርደ ገምድል ችሎት እውነት መናገር “ሽብርተኛ” ያስብላል። እስር ቤቶችን የተሞሉት ለእውነት፣ ለፍትህ፣ ለነፃናትና ለእኩልነት በቆሙ ሰዎች አይደለምን?

በአይ ሲስ ያሳረደን ማነው? መልሱ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው። እንደ አገርና እንደ ሕዝብ የደረሰብን ውርደት የትም ብንሄድ የምናመልጠው አልሆነም። በአገር ውስጥ የደረሰብንን ውርደት ለማምለጥ ስንሰደድ ውርደት ተከትሎን ይመጣል።

ወገኖቼ፤ ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ሊኖረን አይችልም። ዛሬ የመሸሻ ጊዜ አይደለም። አገራችንን ከወያኔ ነጥቀን፤ በአገራችን ኮርተን በሰላም መኖር እንሻለን። ይህ መብታችን ነው። አገራችን የኛ ነች። አገራችን የጥቂት ወያኔዎች መፈንጫ አይደለችም።

ወገኔ፤ ዛሬ ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም በአርበኖች ግንቦት 7 ስም የማደርግልህ ጥሪ አድምጠኝ። በሀይማኖት፣ በብሔር፣ በጾታ ልዩነት ሳታደርግ ዛሬ በአንድነት እንደተሳህ አንድነትህን እንደጠበቅህ ቀጥል። አንድነትህን ለመሸርሸር ወያኔ የማይፈነቅለው ድንጋይ አይኖርም፤ ለወያኔ ዱለታ ጆሮህን አትስጥ። የወያኔ አገዛዝ እንዲያበቃ በአንድነት ተነስ። ዛሬ የጀመርከው ትግል እዳር ሳይደርስ እረፍት የለንም።

አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሚያ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር በመጣመር የአገር አድን ኃይል የመገንባት ሥራውን እያጠናቀቀ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት ሳንከፋፈል፤ ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ባካተተ ስብስብ ውስጥ አብረን ህወሓትን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የአንተ የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ነው። የትግሉም የአገሪቷም ባለቤት አንተ ነህ። ስለሆነም ተነስ! “እንቢኝ” በል። ዘርፈ ብዙ የትግል ስልቶችን በመጠቀም ወያኔን አዳክም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በትግልህ ፍሬ የአገርህ ባለቤት ሁን።

የመከላከያና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። የደረሰብንን ብሔራዊ ውርደት እያያችሁ፤ እሮሮዓችን እየሰማችሁ በሕዝብ ላይ መተኮስ በራሳችሁ ጭንቅላት ላይ መተኮስ ማለት መሆኑን ለደቂቃ እንኳን አትዘንጉ። ይልቁኑ ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ የወጣትነት የፈጠራ ችሎቻችሁ መፈተኛው አሁን ነው። ለእያንዳንዱ ጥቃቅን ጉዳይ መመሪያ እስኪሰጣችሁ አትጠብቁ። እያሰላችሁ፣ እያጠናችሁ፣ እያደባችሁ፣ ወያኔን ታገሉ።

የታፈረች፣ የተከበረችና የበለፀገች ኢትዮጵያን እውን እናደርጋለን።

ብርሀኑ ነጋ

የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ሊቀመንበር

ሚያዝያ 13 ቀን 2007 ዓም

The post ” ያዋረደን፣ በአይ ሲስ ቢላዋ ያሳረደን ህወሓት ነው” – ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከ መሬት ለባለሀብቱ ጀርባ ? –ኤድመን ተስፋዬ

$
0
0

comment picእ.ኤ.አ በ2007/08 በነዳጅ ሀብቱ እና በሀገሩ ያሉትን እህቶቻችንን እና ወንድሞቻችንን በማሰቃየት የሚታወቀው ሳውዲ አረቢያ መንግስት በንጉሱ ንጉስ አብዱላህ አነሳሽነት የሀገሩን ዜጎች ለመመገብ በሚል አዲስ መርሀ ግብር የነደፈ ሲሆን፣ በንጉሱ የተነደፈው የግብርና መርሀ ግብር አላማው መሬት በሚሸጡ ደሀ ሀገራት መንግስታት ላይ ትኩረት በማድረግ በነዚህ ሀገራት የሚገኙትን ለም መሬቶች በሳውዲ መንግስት ስም በሽያጭ እና ወለድ አግድ የመሬት ይዞታ(ንብረትን በግዥ፣በኮንትራት፣በሊዝ) ባለቤትነት በመያዝ አስፈላጊውን የመዋእለ ነዋይ ፍሰት በማድረግ በነዚህ ሀገራት የሚመረተውን የግብርና ምርት ወደ ሳውዲ በመላክ የሳውዲን ህዝብ መመገብ ነው፡፡ ይህ በአለማችን ላይ የሚገኙትን የዘመናችንን እውቅ ኢኮኖሚስቶች በሳተፈ መልኩ የተጠናው የሳውዲ አረቢያ የግብርና መርሀ ግብር ትኩረት የሚያደርገው በተለያዬ የውጪ ሀገራት ማለትም በኢትዮጲያ፣ሱዳን፣ዩክሬን፣ፊሊፒንስ እና ብራዚል በመሳሰሉት ሀገሮች ላይ ሰፋፊ መሬቶችን በመግዛት አልያም በመኮናተር ምርት አምርቶ ሳውዲ አረቢያን በእህል ምርት እራሷን ማስቻልን ላይ ነው፡፡ ይህንንም የሀገሪቷን አላማ የሳውዲ የንግድ እና ኢንደስትሪ ሚኒስትር በወቅቱ የመጀመሪያ አላማችን በውጪ ሀገራት የመሬት ይዞታ ንብረትን ማግኘት ሲሆን ቀጥሎም ዘመናዊ ግብርና ማስፋፋት በተያያዝም የመዋእለለ ንዋይ ፍሰት በማድረግ የመሠረተ ልማት መዋቅር በማስፋፋት የግብርና ምርቱን ወደ የሳውዲ ዓረቢያ መላክ እንደሆነ ዓላማቸውን በማስረገጥ ገልፀዋል፡፡ ከላይ በጠቀስኩት የሳውዲ መንግሰት አላማ መነሻነት በዋነኛነት የሳውዲ መንግስት ስም በተያዙ ትላልቅ የሀገራችን እርሻ መሬቶች ላይ የተመረተው ሩዝ እ.ኤ.አ ከ 2008 እስከ 2012 ወደ ሳውዲ የተጫነ ሲሆን በተጨማሪም ሀብቱ በሳውዲ ዜጋነት የተመዘገበው የቢሊየነሩ ሼህ መሀመድ አላሙዲን ድርጅት የሆነው የሳውዲ ስታር አግሪካልቸራል ዲቨሎፕመንት እና የህንዱ ካራቱሬ በሀገራችን ሰፋፊ የግብርና መሬቶችን በመውሰድደ የግብርና እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡

እንደ ዓለም ዓቀፍ የምግብና የእርሻ ድርጅት( Food and Agriculture Organisation (FAO) ጥናት ከሆነ ከኢትዬጵያ 145.6 ሚሊዬን ሄክታር ብዝሃ መሬት ውስጥ 100 ሚሊዬን ሄክታር ለእርሻ የሚሆን መሬት ሲሆን ይህም መሬት የሚታረሰው በአመዛኙ በአነስተኛ መሬት ባላቸው ገበሬዎችና ከእጅ ወደ አፍ በሆነ ገቢ በሚተዳደሩ ደሃ አርሶ አደሮች ሲሆን በጣም ትልልቅ የንግድ እርሻዎች ድርሻም 400,000 ሽህ ሄክታር መሬት ነው፡፡ እ.ኤ.አ በ2011 ኦክሰፋም ያወጣው ሪፖርት እንደሚያመለክተው የመካከለኛው ምስራቅና የሩቅ ምስራቅ ኢንቨስተሮች በታዳጊ ሀገራት ኢትዮጲያንም ጨምሮ ለያዙት የግብርና መሬት በሄክታር በአመት አንድ የአሜሪካ ዶላር (በአመት አስራ ዘጠኝ ብር አካባቢ መሆኑ ነው) ብቻ ነው የሚከፍሉት፡፡ በሀገራችንም ሆነ በሌሎች የአለማችን ሀገራት በውጪ ሀገራት መንግስታት ለግብርና ምርት በሚል የተያዘውን መሬት እንደ የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሁማን ራይትስ ዎች እና ኦክስፋም ያሉ ተቋማት ከሀገሬው አርሶ አደር የመሬት ባለቤትነት እና መፈናቀል ወዘተ ጋር በተገናኘ ጉዳዩን በሀያ አንደኛው ዘመን የሚደረግ የመሬት መቀራመት መሆኑን በመግለፅ ክፉኛ ቢቃወሙትም የሀገራችንን መንግስት ጨምሮ መሬት ሻጭ የሆኑት መንግስታት መሬት መቸብቸባቸውን ቀጥለውበታል፡፡

የእውቁ ኢኮኖሚስት አዳም እስሚዝ የአለማቀፋዊነት ንድፈ ሀሳብ እንደሚያትተው በሀብት (በሰዋዊም ሆነ በቁሳዊ) ረገድ ሙሉ የሆነ የአለማችን ሀገር ባለመኖሩ ሀገራት በጎደለ ሙላ በሚለው መሰረት አንዱ ባለው ሀብት የሰውን ሀገር ቀዳዳ በመሙላት ቀዳዳውን ከሞላለት ሀገርም ሆነ ከሌሎች ሀገራት በሚያገኘው ሀብት (የገቢ እን የወጪ ንግድ ትርፍ) የራሱን ቀዳዳ በመሙላት የራሱን ሀገር ኢኮኖሚ ከማሻ|ሻል ባለፈ ለአለማቀፋዊ የኢኮኖሚ ትስስር መንስኤ ይሆናል፡፡ የወቅቱን በስግብግቦቹ ካፒታሊስቶች በሳፋ ተቀብሎ በማንኪያ መመለስ በሚል መርህ የሚዘወረውን አለማቀፋዊነት ወደ ጎን ትተን ይህን የአዳም ንድፈ ሀሳብ ከተመለከትነው የሚያመላክተን ፍትሀዊ ሆነ የኢኮኖሚ ሰጥቶ መቀበል መርህ የሚደረግ የሀገራት የኢኮኖሚ ሽርክና ከሀገራት ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባለፈ ለአለም ሀገራት የኢኮኖሚ ትስስር መንስኤ የመሆኑን ሁነት ነው፡፡ የውጪ ሀገር መንግስታትም ሆነ ኩባንያዎች በሀገራችን መሬት ላይ ለዛውም የኢኮኖሚያችን የጀርባ አጥንት በሆነው ግብርና ላይ መሳተፋቸው በሀገራችን የግብርና ዘርፍ ላይ የሚፈጥረውን አሉታዊ እና አዎንታዊ ተፅእኖ የግብርናው እንቅስቃሴ በሚደረግባት ሀገራችን ያሉትን አርሶ አደሮች እና በሀገራችን የግብርና እንቅስቃሴ የሚያደርጉትን ሀገራት መነሻ በማድረግ ማየቱ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

በዚህ መነሻነትም የውጪ ባለሀብቶች በሀገራችን መሬት ላይ የሀገራቸውን ህዝብ ለመቀለብ በሚል የሚያከናውኑት የግብርና እንቅስቃሴ በሀገራችን ግብርና ምርት እና አርሶ አደር ላይ ካለው ተፅእኖ አንፃር እና በውጪ ባለሀብቶች እየተከናወነ ያለው የግብርና እንቅስቃሴ በሀገራችን መንግስት ቢከናወን በሀገራችን ከሚያስገኘው ግብርናዊ ጥቅም አንፃር መመዘን ያስፈልጋል፡፡ በሌላ በኩል የምንገኝበት የሀያ አንደኛው ክፍለ ዘመን በሀገራት መሀል የሚደረግ ኢኮኖሚያዊ ሽርክና በሀገራቱ መሀል ካለው የኢኮኖሚ ሽርክና ባለፈ በሀገራቱ መሀል ባለ የፖለቲካ ሁነት እና ሀገራቱ ከሌላ ሶስተኛ ሀገራት ጋር ካላቸው ጤናማም ሆነ ጤናማ ካልሆነው የፖለቲካል ኢኮኖሚ ግንኙነት ተፅእኖ ስር የወደቀበት ዘመን መሆኑን የውጪ ሀገር መንግስታት በሰው ሀገር እያከናወኑት ያለው የግብርና እንቅስቃሴ ምክንያቱ ለሰው ልጅ የመኖር መንስኤ ለሆነው ምግብ ከመሆኑ ጋር ስንገምደው በሀገራችን የግብርና ምርት እያመረቱ ያሉትን የውጪ ሀገር መንግስታት በተለይ የመካከለኛው ምስራቅ ሀገራትን የወቅቱን የቀጠናውን የፖለቲካ ትኩሳት ማእከል ባደረገ መልኩ ሀገራቱ በሀገራችን የግብርና ምርት በማምረታቸው የተነሳ የወቅቱ የቀጠናው የፖለቲካ ትኩሳት ሀገራችን ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የሚያመጣውን አሉታዊ ተፅእኖ ሀገራቱ በሀገራችን የግብርና ምርት በማምረታቸው የተነሳ ለሀገራችን በቀጠናው ከሚፈጥርላት እና ከፈጠረላት ሀይል አንፃር በመመዘን ማየቱ ተገቢ ይመስለኛል፡፡

በሀገራችን መሬት ምግብ የሚሰራው የሳውዲ መንግስት እና የሀገራችን መንግስት

የሳውዲ መንግስት እንደ መንግስት በሀገራችን መሬት ላይ የራሱን ህዝቡ ለመቀለብ የግብርና ምርት ማምረቱ በራሱ ስህተት ያለው ይመስለኛል፣ እንደ እኔ እምነት ስህተቱ ያለው የሳውዲ መንግስት ይህን ያህል እርቀት ባህር አቋርጦ በሀገራችን መሬት የሚያመርትበት ምክንያት መንግስት ህዝቡን ለመቀለብ ምን ያህል ዋጋ እንደሚከፍል አሳይ መሆኑን እና የአለማችንን የዘመኑን የግብርና አመለካከት ያልተረዳው እና በውጪ ያሉትንም ሆነ የሀገር ውስጥ አቅሙ ያላቸውን ባለሀብቶች በማስተባበር እና ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፣ በመንግስታዊ በጀት በሀገራችን የሳውዲ የሚያደርገው አይነት የግብርና እንቅስቃሴ (በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በሰፋፋ እርሻዎች ላይ) በማድግ የግብርና ምርቱን ለሀገር ውስጥ ገበያ በማቅረብ በሀገራችን የሚታየውን የግብርና ምርት የዋጋ ንረት ማስወገድን ያልቻለው የሀገራችን መንግስት ላይ ይመስለኛል፡፡

በአዲስ አበባ ከሚተላለፉ የኤፍ ኤም ፕሮግራሞች በአንዱ ላይ የአየር ሰአት በነበረው የሰይፉ ፋንታሁን ፕሮግራም ላይ ሀብታቸው በሳውዲ ዜግነት የተመዘገበው ቢሊየነሩ ሼህ መሀመድ አላሙዲ ከሰይፉ ፋንታሁን ጋር ባደረጉት አጠር ያለ የስልክ ቃለ ምልልስ ሰይፉ ፋንታሁን እዚህ ብዙ የአርሰናል ደጋፊዎች ስላለን ለምን የአርሰናልን ክለብ አይገዙልንም ብሎ ለጠየቃቸው ጥያቄ ሲመልሱ የአርሰናልን ክለብ መግዛት ይቆየኝና አሁን (በጊዜው) ድርጅታቸው ግብርና ላይ ለመሳተፍ ዝግጅቱን ማጠናቀቁን በመጥቀስ የግብርና ምርትን በሀገራችን ለማሳደግ እንደሚሰሩ መጥቀሳቸውን አስታውሳለው፡፡ በግብርና ላይ የተሰማራው የሼኩ ኩባንያ ሳውዲ ስታር አግሪከልቸራል ዲቨሎፕመንት በሊዝ ከወሰደው 24700 ሄክታር መሬት ውስጥ 860 ሄክታር መሬት ላይ ሩዝ በመዝራት ያገኘውን ጠቅላላ ምርት በተደጋጋሚ ወደ ሳውዲ መላኩን የኦክስፋም ሪፖርትን እና ዘ ሂንዱ በ ጁን 1/2013 የዘገበውን ዘገባ መነሻ ስናደርግ ሼኩ ቃላቸውን ጠብቀው የሀገራችንን ህዝብ በበቂ ሁኔታ የግብርና ምርት በገበያው እንዲያገኝ ሳይሆን ያደረጉት በሀገራችን መሬት ያመረቱትን ምርት ሀብታቸው ወደ ተመዘገበበት ሀገር ስለ መላካቸው የምንረዳ ይመስለኛል፡፡

የፖለቲካ አመለካከትን እንደ ቅድመ ሁኔታ የሚወሰድበትን ያልተፃፈ አሰራር ወደ ጎን በመተው በሀገር ውስጥም ሆነ በውጪ ያሉ አቅሙ ያላቸውን በተለይ በፖለቲካ የተነሳ ያላቸውን ሀብት በሰው ሀገር እያፈሰሱ ያሉትን የሀገራችን ዜጎች የሳውዲ መንግስትን ጨምሮ ሌሎች የውጪ ሀገር መንግስታት በሀገራችን መሬት እያመረቱ እንዳለው የሀገራችንን የግብርና ምርታማነትን በሚያሳድግ እና ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ለሚውል የግብርና እንቅስቃሴ ላይ ተሳታፊ የሚሆኑበት አሰራር ቢኖር ኖሮ እና ቢዘረጋ በገዛ ሀገራቸው የሚኖሩትን ዜጎች በማፈናቀል እና ደን በመጨፍጨፍ የያዘውን መሬት የግብርና ምርት ሊያመርትበት ባለመቻሉ ለውጪ ሀገር ባለሀብቶች የሚሰጠውን የግብርና መሬት መጠን የሚጠቅሰው ፖሊሲ እንዲከለስ ምክንያት እንደሆነው እና ከሀገራችን ባንኮች የተበደረውን መመለስ እንኳ እንዳቃተው የህንዱ ካራቱሬ አይነት ድርጅቶች በሀገራችን መሬት ባልፈነጩ ነበር፡፡ ከሁሉም በላይ ደግሞ ኢኮኖሚያዊ አዋጭነታቸው እንደሀገር ምንም ባልሆኑ ነገር ግን ለሙስና ካላቸው ተመቻችነት አኩአያ ከፍተኛ በሆኑ እንቅስቃሴዎች ላይ ልማት በሚል የዳቦ ስም የሀገሪተዋን ሀብት የሚያፈሰው መንግስት የውጪ ሀገራት መንግስታት በሀገራችን ለህዝቦቻቸው ምግብ ዋስትና በሚል እንደሚያደርጉት በገዛ ሀገሩ መሬት ላይ እንደ እነሱ አይነት የግብርና እንቅስቃሴ በመንግስታዊ በጀቱ ለማድረግ አለመንቀሳቀሱ በአንድ በኩል የውጪ ሀገራት መንግስታት በሀገራችን መሬት ላይ የሚያደርጉት የግብርና እንቅስቃሴ ወደፊት ሀገራችን እያመረተች ወደ ውጪ የምትልከውን የግብርና ምርት በሀገራችን መሬት እያመረቱ በአለም ገበያ ተፎካካሪ የመሆናቸው አይቀሬነት ሲታይ በሌላ በኩል የመሬት ፖሊሲው፣የግብርና ግብአት (ማዳበሪያ በዋነኛነት) ብድር የግብርና እንቅስቃሴውን ሲኦል ያደረገበት የሀገሬ አርሶ አደር የራሱን የግብርና እንቅስቃሴ በመተው በውጪ ሀገራት መንግስታት እና ግለሰቦች ባለቤትነት ወደ ተያዙት እርሻዎች ተቀጣሪ ሆኖ የመስራቱ (እየሰራም ይገኛል) እድል ከፍተኛ የመሆኑ ሁነት ኢህአዴግ የስልጣኔ ምንጭም ሆነ የሀገራዊው ፖሊሲዬ ማእከል አርሶ አደሩ ነው ከሚለው ጋር ስንገምደው ኢህአዴግ እንደ መንግስት ግብርናው ላይ የሚከተለው ፖሊሲ ያስገኘውን ውጤት የዜሮ ብዜት የሚያደርገው ይመስለኛል፡፡

የሀገራችንን ኢኮኖሚ ከግብርና ወደ ኢንደስትሪ ለማሸጋገር በገዢው ፖርቲ የተነደፈው የአምስት አመቱ የእድገት እና የትራንስፎርሜሽን እቅድ አንድ አመት በቀረበት በያዝነው አመት ኦክስፋም በአለም ላይ ከሚገኙ ሀገራት በቂ የሆነ ምግብ የማይበሉ ህዝቦች ያሉባት ሀገር በሚል ከአለም ሀገራት በሁለተኛ ደረጃ ባስቀመጣት እንዲሁም የተባበሩት መንግስታት ለምግብ እጥረት የተጋለጡ ስድስት ነጥብ አምስት ሚሊዮን ህዝቦች በዚህ አመት መኖራቸውን በገለጠባት ሀገራችን በግለሰብም ሆነ በመንግስት ደረጃ ሳውዲዎቹ በሀገራችን መሬት የራሳቸውን ህዝብ ለመቀለብ የሚያደርጉትን የግብርና እንቅስቃሴ ከኪራይ ከሚያገኘው አስቂኙ ገቢ በስተቀር በሁለትዮሽ ግንኙነትም ሆነ በተለዋጭ ጥቅም ሀገራችንን ተጠቃሚ ማድረግ ያቃተው እንዲሁም የሳውዲ መንግስት ከግብርናው እንቅስቃሴ ጋር በተገናኘ በሀገራችን ህዝቦች ላይ የሚደርሰውን የሰብአዊ መብት ጥሰት እና መፈናቀል በማስረጃ በማስደገፍ የሚያቀርቡትን አቤቱታ እንደ ለመደው የኒዮ ሊበራሊዝም አስተሳሰብ ውጤቶች በማለት ለሚያልፍው እና ሌላው ቢቀር እንደ መንግስት በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ ሙከራ ያላደረገው ኢህአዴግ ለውጪ መንግስታት ለግብርና በሚል የሰጠውን መሬት በተመለከተ የሚከተለው አካሄድ እንደ እኔ እምነት የራሷ አሮባት የሰው ቤት የምታማስለዋን ሴትዮ የሚያስታውስ ይመስለኛል፡:

ሳውዲዎቹ ለሀገራችን የሚያመጡት ትሩፋት ወይስ እዳ ?

ስለ ምድራችን የ ተፈጥሮ ሀብት እና ስነምህዳር የኢኮኖሚክስ አስተምህሮት ንድፈ ሀሳብ እንደ የሚነግረን እንደ የፀሀይ ብርሀን እና ዝናብ የመሳሰሉትን ተፈጥሮአዊ ሀብቶች ገንዘብ ሊገዛቸው አንደማይቻለው ነው፡፡ አሁን ላይ ምድራችን ያጋጠማትን የውሃ እጥረት፣የበረሀ መስፋፋትን ተከትሎ በአለም አቀፍ ደረጃ ያጋጠመው የምግብ እጥረት እና የምግብ ፍጆታዎች የዋጋ መናር መልካምድራዊ በሆኑ ምክንያቶች የተነሳ ለምግብ ፍጆታ የሚሆኑትን የግብርና ምርቶች በሀገሯቸው በበቂ ሁኔታ ለማያመርቱ እና ፍጆታዎቻቸው ከውጪ ሀገር ለሚያስገቡ ሀገራት ሁኔታው አስደንጋጭ ሲሆን፣ ይህ አስደንጋጭ አደጋ ከተጋረጠባቸው ሀገራትም ውስጥ አንዷ በነዳጅ ሀብቷ የምትታወቀው ሳውዲ አንዳ ስትሆን፡፡ ሀገሪቷ ይህን አደጋ ለመወጣት በነደፈችው የግብርና እቅድ መነሻነት እ.ኤ.አ በ2009 በሳውዲ አረቢያ ንጉስ አብዱላህ መሪነት በ መቶ ሚሊዮን ዩኤስ ዶላር የመዋእለ ነዋይ ፍሰት በሀገራችን መሬት የግብርና ምርት ማምረት የጀመረው የሳውዲ መንግስት በጋምቤላ ክልል በስሙ በተያዙ ሰፋፊ መሬቶች ያመረተውን የሩዝ ምርት እ.ኤ.አ ከ 2008 እስከ 2012 ወደ ሳውዲ የጫነ ሲሆን፣ ይህ በሀገራችን የተመረተው የሩዝ ምርት የሀገሪቱን የምግብ ክፍተት ከማጥበቡም በላይ ለሀገሪቱ የምግብ ፍጆታ ዋስትና በሚል በንጉሱ ለተነደፈው እቅድ እንደ ስኬት ተወስዳል፡፡

ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚ ግብአት ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነውን የነዳጅ ሀብት የተጎናፀፈችው ሳውዲ በሀገራችን ለምግብ ፍጆታዋ የግብርና ምርት ማምረቷ ከሁለትዮሹ ሀራዊ ግንኙነት አኩአያ ከሚያስገኘው ጥቅም አንፃር ሲታይ በአጭር ጊዜም ይሁን በረዥም ጊዜ ለሀገራችን የነዳጅ ፍጆታ ፍላጎት ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ ባይሆን እንኳ ከበፊቱ በተሸለ ሁኔታ ዋስትና እንዲኖራት፣ለሀገራችን ዜጎች ምቹ ያልሆነውን የመሀከላው ምስራቅ ከበፊቱ በተሸለ ሁኔታ ለስራ ወደ አካባቢው በሚሄዱት ዜጎቻችን ላይ በተለይ በእህቶቻችን ላይ የነበረውን መጎሳቆል እንዲቀር መንስኤ ሊሆን በተቻለው ነበር፣ ነገር ግን ከሳውዲ መንግስት ጋር የሀገገራችንን መሬት በተመለከተ ውል የፈፀመውን የኢህአዴግ መንግስት ለትችት በዳረገው በቅርቡ በሳውዲ ሀገር በእህቶቻችን ላይ የተፈፀመው አረመኔአዊ ተግባር ባጎረስኩኝ እጄን ተነከስኩኝ አይነት መሆኑ ውሉ ከሁለቱ ሀገራት የሁለትዮሽ ግንኙነት ላይ ያለውን ሀገራዊ ጠቄሜታ ጥያቄ ውስጥ የሚከተው ይመስለኛል፣ በሌላ በኩልም በመሀከለኛወ ምስራቅ ቀጠና አሁን ላይ ለሚታየው የሶሪያ እና የኢራቅ ትኩሳት መንስኤ ለሆነው እና አላማው ቀጠናውን በፅንፈኛ አስተሳሰቡ አንድ አርጎ መምራት ለሆነው አይሲሲ የሎጀስቲክ እና የገንዘብ ምንጭ ነው በማለት በኢራን እና በሶሪያ የሚከሰሰው የ ሳውዲ መንግስት ህዝቡን ለመቀለብ በሀገራችን መሬት ላይ በሚያመርተው ምርት የተነሳ በፅንፈኛው አይሲሲ ሀገራቸው እየተመሰቃቀለ ያሉት ሀገራት እና ጉዳዩ ያሳሰባቸው ከቀጠናው ውጪ ያሉ ሀገራት ሀገራችን ላይ በቀጥታም ይሁን ቀጠተኛ ባልሆነ መንገድ ተፅእኖ ማድረጉ ቢኖር እንኳ በዲፕሎማሳዊውም ሆነ በሌሎች መንገዶች ረገድ እንደ መንግስት ተፅእኖውን ለመቋቋም ያለውን አቅም እና ተነሳሽነት በሳውዲ መንግስት በራሱ ዜጎች ላይ ለተፈፀመው ኢሰበአዊ መከራ ኢህአዴግ መራሹ የሀገራችን መንግስት ያከራየውን መሬት (ከሳውዲ ጋር ያለን የሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ግንኙነት ወደ ሳውዲ ያደላ እና የሳውዲ መንግስት ኢኮኖሚያዊው ድጋፍ ከፈተኛ ቢሆንም አሁን ላይ ካለው የሳውዲ አንገብጋቢ የምግብ ፍጆታ ፍላጎት አኩአያ ያከራየናቸው መሬት ከፍተኛ አቅም ለሀገራችን መፍጠር ይችላል) ለተፅእኖ ያለመጠቀሙን እውነትነት ሲታይ ለሀገራችን አደጋ መፍጠሩ አይቀሬነት ማመላከቻ ይመስለኛል፣ ከሁሉም በላይ ደግሞ በአሁን ዘመን በአለማችን እየተስፋፋ ያለውን የሀይማኖት አክራሪነት ባልተለመደ መልኩ እንስሳዊ በሆነ መንገድ ሰይጣናዊ አላማውን ለማሳካት ከሶሪያ እስከ ኢራቅ ከኢራቅ እስከ ሊቢያ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው እና የቀጠናውን ሀገራት በአንድ መንግስት የማስተዳደር አላማ ያለውን አይሲሲ በመርዳት የሚከሰሰው የሳውዲ መንግስት በሀገራችን መሬት በሚያመርተው ምርት የተነሳ የፅንፈኛው ተቃዋሚ የሆኑ ሌሎች አክራሪ ሀይሎችም ይሁን አይሲስ ላይ ጦርነት ያወጁ ሀገራት ሀገራችን ላይ ጥርስ ስለ አለመንከሳቸው መተማመኛ እንዳናገኝ በሀገራችን መሬት የግብርና ምርቶች እያመረተ የሚገኘው የሳውዲ መንግስት መንስኤ የሚሆን ይመስለኛል፡፡

The post ከ መሬት ለባለሀብቱ ጀርባ ? – ኤድመን ተስፋዬ appeared first on Zehabesha Amharic.

“በጆሮ እንደሰማን በአይን አየን”–አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ

$
0
0

“በጆሮ እንደሰማን በአይን አየን”
በሐዲስ ሃዋርያ አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ
በሊብያ በሰማዕትነት ላረፉትና በስቃይ ላይ ላሉ ወገኖቻችን የፀሎት ምሽት
በደብረ ፅዮን ድንግል ማርያም ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካቴድራል Los Angles, CA

 

 

The post “በጆሮ እንደሰማን በአይን አየን” – አባ ወልደ ትንሣኤ አያልነህ appeared first on Zehabesha Amharic.

የማለዳ ወግ ቅምሻ ልዩ ዘገባ …”የISIS ሽብር እርምጃ አንድ አደረገን እንጅ አልለያየንም! “

$
0
0
(Photo File)

(Photo File)

* በሳውዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የአሸባሪው የ ISIS የእጭካኔ እርምጃ አዎገዙ !

* ” የሰው አራዊቶች እርምጃ ለዘመናት ተፋቅሮ ሳይለያይ የኖረው ኢትዮጵያዊ ሙስሊምና ክርስትያኑን አይለያየንም !” ከነዋሪው ድምጽ
* በሳውዲ ሰማይ የኢትዮጵያ ሀዘን ለመግለጽ ባንዴራችን ዝቅ ብሎ በመውለብለብ ላይ ነው
* የተለያዩ ሀገር ዲፕሎማቶች ሀዘናቸውን እየገለጹ ነው
* አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ትምህርት ቤት 3000 ተማሪዎች በሊብያ ለተሰውት ወገኖች የህሊና ጸሎት አድረጉ
* የውጭ ዲፕሎማቶችና ነዋሪው ጥልቅ ሀዘኑን በመግለጽ ላይ ናቸው
* መንግስት በሀገር ቤት ሀዘናቸውን ለመግለጽ በወጡ ወገኖች ላይ የወሰደው የሃይል እርምጃም ተኮንኗል

በማለዳ ወግ ሰሞነኛ የመረጃ ቅምሻ ፣ በአዲስ አቀራረብ በድምጽ የተሰናዳ ልዩ ጥንቅር … !

የሞቱትን ነፍስ ይማር !

ነቢዩ ሲራክ
በጨለመው ሚያዝያ 16o ቀን 2007 ዓም

The post የማለዳ ወግ ቅምሻ ልዩ ዘገባ …” የISIS ሽብር እርምጃ አንድ አደረገን እንጅ አልለያየንም! “ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሻማ ማብራት ምሽት አካሄዱ * ከ10 በላይ የተለያይይ የሃይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል (+Photo + Video)

$
0
0

Minnesota 1

Minnesota 2

Minnesota 3

Minnesota 4

Minnesota 5

Minnesota 6

Minnesota 7

minnesota 9

Minnesota 11

Minnesota 13

Minnesota 15

minnesota 18

Minnesota 19

Minnesota 20

Minnesota 21

Minnesota 22
(ዘ-ሐበሻ) አይሲኤል በሊቢያ 28 ኢትዮጵያውያን አርዶ እና በጥይት ከገደለ በኋላ በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያውን ከዳር እስከ ዳር ተቆጥተዋል:: ትናንት ማምሻውን ሐሙስ በመላው ዓለም ኢትዮጵያውያን በየሚኖሩበት ሃገር የሻማ ማብራት እና የጸሎት ስነ-ስርዓት አካሂደዋል::

በሚኒሶታ ስቴት ካፒቶል ደጃፍ ዘ-ሐበሻ እና የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በመተባበር የጠሩት የሻማ ማብራት የመታሰቢያ ምሽት ላይ በሊቢያ… በደቡብ አፍሪካና በየመን የተገደሉ እና እየተሰቃዩ ያሉ ታስበዋል::

ከአንድ ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ኤርትራውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች በተገኙበት በዚህ የመታሰቢያ ምሽት:-

– ከደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ መላከ ሰላም – ቀሲስ መሪጌታ ጌታሁን
– ከደብረብርሃን ቅዱስ ዑራኤል ቤ/ክ – አባ ገብረኪዳን ገብረዋሂድ
– ጠሃ ሳሚር ከሪሳላ ኢንተርናሽናል የሙስሊም ማዕከል
– ናስር ሃምዛ ከቶፊክ ሙስሊም ሴንተር
– ፓስተር መልካሙ ነገሪ ከኦሮሞ ኢቫንጀሊካል ቤተክርስቲያን
– ፓስተር ፍራንሲስ ከኢትዮጵያ መካነኢየሱስ
– ፓስተር ስለሺ ከኢግል ክርስቲያን ቤተክርስቲያን
– ፓስተር አበባየሁ አበበ ከጎስፕል አማኞች ቤተክርስቲያን
– ፓስተር ደስታዬ ክራፎርድ ከኤቨንት ትራይብ ቤተክርስቲያን
– ወንድም ዳንኤል ከኤቨንት ትራይብ ቤተክርስቲያን
– የሴናተር ኬዝ አሊሰን ተወካይ
– የሴናተር ኤሚ ክላባቸር ተወካይ
– ወጣት ዛኪር ሃሰን
– ወጣት ቃልኪዳን አለማየሁ
– የኤርትራ ኮምዩኒቲ ተወካይ
– ወ/ሪት ዘመን ታደሰ
– አቶ ተከስተብርሃን ተፈራ
– ወጣት መስፍን አየለ
– አልዩ ተበጀ ከኢትዮ-ሲሊዳሪቲ ሚኒሶታ ግሩፕ

ንግግር ያደረጉ ሲሆን በንግግራቸውም በሊቢያ የተገደሉትን ኢትዮጵያውያን አስታውሰው በአይሲስ ላይ ያላቸውን ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተዋል:: በደቡብ አፍሪካ እና በየመን እያለቁ ስላሉት ኢትዮጵያውያንም ተጸልይዋል:: ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ያሰመሩበት አንድ ነገር ቢኖር “አንድነት”ን ሲሆን ሁሉም አንድ ሆኖ ለሃገሩና ለሕዝቡ እንዲቆም ጠይቀዋል::

በሚኒሶታ ስቴት ካፒቶል በኢትዮጵያውያኑ መካከል የእምነት ልዩነት ሳይኖር በአንድ ላይ እንዲህ ያለው ትልቅ ዝግጅት መደረጉ ብዙዎችን ያስደሰተ ሲሆን ይህ መተባበርና አንድ መሆን በችግር ጊዜ ብቻ ሳይሆን በደስታውም ጊዜ አንድነቱ እንዲቀጥል ሕዝቡ ጠይቋል::

(የዚህን ዝግጅት ሙሉ ቭዲዮ እስከምንለቅላችሁ ድረስ ቀንጨብ ያለችውን የ5 ደቂቃ ቭዲዮ ይመልከቱ)

The post በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሻማ ማብራት ምሽት አካሄዱ * ከ10 በላይ የተለያይይ የሃይማኖት መሪዎች ተገኝተዋል (+Photo + Video) appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢህአዴግ የሞቱትን ወገኖች ክብር እያራከሰ ነው ሲል ሰማያዊ ወቀሰ • ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ጉዳዩን በዝምታ አያልፈውም›› አቶ ዮናታን ተስፈዬ

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) ኢህአዴግ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በሚል በሚጠራቸው ሰልፎች ሰማያዊን በማውገዝ ላይ መጠመዱንና ይህንም ሰማያዊ ፓርቲ በዝምታ እንደማያልፈው የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ ትናንት ሚያዝያ 15/2007 ዓ.ም በባህርዳር፣ ሆሳና እና ሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች መንግስት በጠራው ሰልፍ ሰልፈኞቹ አይ ኤስን ሳይሆን ሰማያዊ ፓርቲን የሚያወግዙ መፈክሮችን ይዘው እንደወጡ የታወቀ ሲሆን አብዛኛዎቹ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ደም ከማፋሰስ ተግባሩ መቆጠብ አለበት›› የሚሉ መፍክሮችን ይዘው ወጥተዋል፡፡
ethiopian killed by isil 1
ይህ የሆነው አዲስ አበባ ውስጥ መንግስት የጠራው ሰልፍ ላይ ሰልፈኞች መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ ምልሽ አልወሰደም በሚል ተቃውሞ ካሰሙ በኋላ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን ገና ፖሊስ ምርመራውን ሳይጨርስ ተቃውሞውን ያሰማው ሰማያዊ ፓርቲ ነው ብለው ከወነጀሉ በኋላ ፓርቲያቸው የያዘው አቋም እንደሆነ ኃላፊው ገልጾአል፡፡ አቶ ዮናታን ይህን የኢህአዴግ አቋምም ‹‹እጅግ አሳፋሪና አፀያፊ ነው›› ብሎታል፡፡ የባህርዳርና የሆሳና ሰልፈኞች ሰማያዊ ፓርቲን ለማውገዝ በያዟቸው መፈክሮች ፊታቸውን እንደሸፈኑ የገለፀው አቶ ዮናታን ሰልፈኞቹ በኢህአዴግ ተገድደው እንጅ አምነውበት እንዳልወጡ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

መንግስት ለችግሩ አፋጣኝ መፍትሄ መስጠት ሲያቅተው የሚነሱበትን ተቃውሞዎች ሰማያዊ ፓርቲና ድምጻችን ይሰማ የፈጠሯቸው አድርጎ መወንጀሉ ለስርዓቱም ሆነ ለሀገሪቱ አደጋ የሚፈጥር ነው ያለው አቶ ዮናታን ለአይ ኤስ አይ ኤስ ተብሎ የተጠራውን ሰልፍ ለራሱ የፕሮፖጋንዳ ፍጆታ ማዋሉ የሞቱትን ወገኖቻችን ክብር የሚያረክስ፣ ርካሽና ፀያፍ ፕሮፖጋዳ ነው ሲል ወቅሷል፡፡
ኢህአዴግ እንደ መንግስት መስራት ያለበትን ባለመስራቱ የሚነሱበትን ተቃውሞዎች ለመሸፈን እና አጀንዳ ለማስቀየስ ሲል በሰማያዊ ላይ እየፈጠራቸው ያሉትን ውንጀላዎች ፓርቲው በዝምታ እንደማያልፋቸውና ክስ እንደሚመሰርትም አቶ ዮናታን ገልጸዋል፡፡

The post ኢህአዴግ የሞቱትን ወገኖች ክብር እያራከሰ ነው ሲል ሰማያዊ ወቀሰ • ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ጉዳዩን በዝምታ አያልፈውም›› አቶ ዮናታን ተስፈዬ appeared first on Zehabesha Amharic.

ባለቤት ያጣ ትውልድ እንደ በግ ሲታረድ –በዲያስፓራ የዓረና ትግራይ ድጋፍ ከሚቴ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ

$
0
0

arenaበተወለዱባትና እትብታቸውን በተቀበረባት እናት ምድር ላይ እንደ ሰብኣዊ ፍጡር – እንደ ዜጋ በነፃነታቸው፣ በማንነታቸውና በኢት}ዮያዊነታቸው ኮርቶውና አልሞቶው በሰላም የመኖር አማራጭ ያጡና ተስፋው የጨለመባቸው ወገኖቻችን ሳይወዱ በግድ ስደት በመምረጥ መድረሻ አጥተው ሲንከራተቱና የሞት ፅዋን ሲቀበሉ የሚያሳይ በሊቢያ፣ በደቡብ አፍሪቃ፣ በሜዲተራኒያን ባህርና በየመን አካባቢ የደረሰባቸውን ዘግናኝና ልብ ሰባሪ ዜና ስንመለከት በዘመናችን ታይቶ የማይታወቅ እጅግ አስደንጋጭ በመሆኑ በጣም አዝነናል ተቆጥተናልም::

ኢትዮ}ያ ለዘመናት የነፃነት፣ የኩሩ ህዝብና የጀግና ሀገር ተምሳሌት እየተባለች በዓለም ማሕበረሰብ ዘንድ ወርቃማ ታሪክ ይዛ ተከብራና ታፍራ እንዳልቆየች ሁሉ ዛሬ ግን ገፀ ባህሪዋንና የነፃነት ድባብዋን በሀዘን ጨለማ ተቀይሮ ረሃብ፣ ስደት፣ ሞት፣ ውርደትና እልቂት የነገሠባት፣ ባለቤት ያጣች፣ የልቅሶና የዋይታ ምድር ሆና ስናያት በጣም ያሳዝነናል:: ይቆጨናልም::

ጨዋ፣ ኩሩ፣ እንግዳ አክባሪና የዋሁ ህዝባችንም ሀገርና መንግስት እንደሌለው ተቆጥሮ የውሻን ያህል እንኳን ክብር ሳይሰጠው እንደ በግ እየታረደ፣ እንደ ቆሻሻ ባህር ውስጥ እየተወረወረ፣ ከቦታ ቦታ በመንከራተትና እስር ቤት በመታጎር በአሁኑ ጊዜ በዓለም ላይ የሚያነሳው ያጣ፣ የተዋረደና የረከሰ ህዝብ ሆኖ ስናይ እጅግ የሚያሳዝን የትውልድ ሐፍረት ነው::

በቅርቡ ከሳውዲ ዓረቢያ ወደ ሩብ ሚሊዮን የሚጠጉ ዜጎቻችን ከሰብኣዊ ርህራሄ አያያዝ ውጭ በጭካኔ ተደብድበውና ተዘርፈው ባዶ እጃቸውን በተባረሩበት ወቅት የደረሰባቸው የስነ ልቦና፣ የማሕበራዊና የኢኮኖሚ ቀውስ ጠባሳው እስካሁን ድረስ አልሻረም:: ለደረሰው ጉዳትና ታሪካዊ በደልም ተመጣጣኝ መልስ የሚሰጥና ከወገኖቻችን ጎን የሚቆም የሀገርና የህዝብ ፍቅር ያለው መንግስትም አልተገኘም:: ይልቁንም ከኛ የበለጠ እውቀትና ዓቅም የሌላቸው ዓረቦች ባዶ ሀገር ስላገኟት ደማችንን ብቻ ሳይሆን አንጡራ ሀብታችንም ጭምር እየጋጡና ሕብረተሰባችንንም ከሚኖርበት መሬት እያፈናቀሉ ለስደት የሚዳርጉት መሆናቸውም ጭምር ነው:: ሰሞኑን አይሲሲ የተባለው የአውሬ መንጋ በውድ ወንድሞቻችን ላይ የፈፀመው አስደንጋጭና አስነዋሪ ድርጊት እንቅልፍ የሚነሳና ልብን የሚያደማ አረሜናዊ ተግባር ነው::

በዚሁ ፈታኝ፣ አስቸጋሪና አስደማሚ በሆነበት አጋጣሚም

  1. ኢ-ሰብኣዊ በሆነ ተግባር ሰለባ ለሆኑት ወገኖቻችን ሁሉ ጥልቅ ሀዘን እየተሰማን ለሁሉም ቤተሰቦቻቸውና ለመላ የኢትዮ}ያ ህዝብ መፅናናትን እንመኛለን:: ለሞት ፅዋ የተዳረጉት ሰማእታቱንም ታሪካቸው ህያው ሆኖ በምድር ላይ ይኖራልና ነብሳቸውን በመንገስተ ሰማይ ያኑርልን::
  1. በሀገር ውስጥና በስደት ዓለም የምትገኙ ወገኖቻችን ሁሉ በዚሁ አሳዛኝ ክስተት ምክንያት ምን ያህል ልባችሁ እንደ ተሸበረ እኛም ይሰማናል:: ይህ በወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው አስፈሪና አሰቃቂ በደል የመጀመሪያ እንጂ የመጨረሻ አይደለም:: ነገም ከዚህ በባሰ መልኩ በእያንዳንዳችን ሊደርስ የሚችል ችግር ነው:: በመሆኑም መፍትሄው አንድና አንድ ነው:: እሱም ሀዘናችንን ዋጥ አድርገን ይህ የሰማእታቱን ጥሪ ለኛ መተባበርና እብረን ስለነገ ህልውናችንን ማሰብ እንድንጀምር አዲስ ምዕራፍ ለመክፈት ንስሓ የምንገባበት ጊዜ ነው::
  1. እኛን በሀይማኖት፣ በዘር፣ በቋንቋና በቦታ ከፋፍለውና እርስ በራሳችን አናቁረው ዘላለም ለመግዛት የሚፈልጉ አምባ ገነኖችም የችግሮቻችንን መንሲኤ ናቸው እንጂ በፍፁም የመፍትሄ አካል ሊሆኑ አይችሉም:: የተፈጠረውን አሳዛኝ ሁኔታም ህዝቡን የማስፈራሪያ፣ የማናቆሪያና የማለያያ ፕሮፓጋንዳ አድርገው ለመጠቀም ወደሗላ እንደማይሉ እሙን ነው:: ስለሆነም ሳይጨልም አይነጋምና የተከሰተው መጥፎ ሁኔታ አንገታችንን የሚያስደፋንና የሚስደነግጠን ሳይሆን ቀፎው እንደተነካ ንብ ከእንቅልፋችን የሚቀሰቅሰን፣ የሚለያየን ሳይሆን የበለጠ የሚያስተሳስረን፣ የሚያናቁረን ሳይሆን የበለጠ የሚያስተቃቅፈንና የሚያፋቅረን መሆኑና በተለይም ከነሱ በፊት ቀድመንና በልጠን በመገኘት የቀውጥ ቀን ለጆች መሆናችንን በተግባር ማሳየት ይኖርብናል:: ኢትዮ}ያዊ ነኝ ማለቱ መገለጫው ይኸው ነውና::
  1. ሰሞኑን የተከሰተው አስደንጋጭ ሁኔታ አላማው ኢትዮያውያንን ለማዋረድ፣ ለማሳፈርና ማንነታችንን ለማንቋሸሽ ሲባል በህዝባችንና በሀገራችን ላይ የተቃጣ የስነ ልቦና ጦርነት መሆኑን እሙን ነው:: ይህም በሕብረተሰባችን ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ ቀላል አይደለም:: ሰለሆነም በሀገር ውስጥም ሆነ በዲያስፓራ በመንቀሳቀስ ላይ የምትገኙ የፓለቲካ ድርጅቶች፣ የሀይማኖት ተቋማትና አባቶች፣ የሲቢክ ማሕበራትና ሰብኣዊ መብት ተሟጓቾች ድርጅቶች፣ ምሁራኖች፣ አርቲስቶች፣ ወጣቶች፣ አክቲቪስቶች፣ ጋዜጠኞች፣ የሚዲያ አውታሮችና ሌሎች ዜጎች በሙሉ ጨዋነት፣ ሃላፊነትና ጥበብ በተሞላበት አኳሃን ህዝቡን ለጋራ ችግሩ በጋራ ለመቆም ይችል ዘንድ ለማስተባበር የምትፈተኑበት ጊዜው አሁን ነው::

የጋራ ችግራችንን በጋራ ለመፍታት ተባብረን እንቁም

ኢትዮ}ያ ሀገራችን በልጆችዋ ተከብራ ለዘላለም ትኑር

Bega2260@comcast.net

The post ባለቤት ያጣ ትውልድ እንደ በግ ሲታረድ – በዲያስፓራ የዓረና ትግራይ ድጋፍ ከሚቴ የተሰጠ የሀዘን መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት አጭር መግለጫ

$
0
0

ላለፉት ሃያ አራት ዓመታት ያለ ኢትዮጵያዊ መንግስት የኖረው ሕዝባችን፣ በወያኔ/ የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር ሁለንተናዊ ጥቃት፣ሞት እና ስደት ሲፈራረቁበት ኖሮአል። በአገሩ የመኖር ተስፋ በማጣቱ ፣ሰብዓዊ መብቱ ተጥሶ በውርደት እንዲኖር በመገደዱ የተነሳ ወጣቱ ትውልድ ስደትን እንደ አማራጭ እንዲወስድ በረቀቀ መንገድ ተገዷል። ሰሞኑን በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ በሳውዲ አረቢያ፣ በየመን ፤በደቡብ አፍሪካና በሊቢያ በተፈጸመው ኢሰብዓዊ ተጋባርና አሰቃቂ ግድያ ጥልቅና ከባድ ሃዘን ተሰምቶናል አስቆጥቶናልም።Ethiopian-Womens-Organization

የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት የወገኖቻችን የሰማዕታት ደም በከንቱ ፈሶ የማይቀር መሆኑን እያረጋገጥን የበለጠ ተጠናክረን ለስደትና ለሰቆቃ የዳረገንን የወያኔ ስርዓትን በቆራጥነት የምናስወግድበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል በለን እናምናለን። በኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ላይ የመከራ እጁን ያነሳ ሁሉ ተገቢውን ዋጋውን እንደሚያገኝ ጥርጥር የለንም። በቅድሚያ ግን ለዚህ አስከፊ ችግር እና ሰቆቃ የዳረገን ፀረ ኢትዮጵያ የሆነው ወያኔ የትግሬ ነፃ አውጭ ግንባር በመሆኑ የችግሩን ምንጭ ማድረቅና መንስዔውን አሁኑኑ ማስወገድ ሰብዓዊ፣ ኢትዮጵያዊና ታሪካዊ ግዴታችን ነው። ይህ ካልሆነ ግን ኢትዮጵያውያን በአገር ውስጥም ይሁን በዓለም ዙሪያ ለከፍተኛ መከራና ችግር፣ ለወራሪዎች ኢላማ፣ የእልቂትና የሞት አውድማ የመሆን አደጋ ከፊታችን የሚጠብቀን መሆኑን ከወዲሁ መገንዘብ ይኖርብናል።

ስለዚህም ዛሬ ለተሰዉት ወገኖቻችን ማዘን ብቻ ሳይሆን፣ ዘላለማዊ ሕይወታቸው በአምላካቸው ጎን በመሆኑ ተጽናንተን ፣የፈሰሰው ደማቸው ለኢትዮጵያ ትንሳኤ ኃይልና ጉልበት እንዲሆን የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ ይጠበቅብናል። ክብራችንና ነጻነታችን ያለው በእኛ በኢትዮጵያውያን እጅ ነው፤ ከሀዘንና ከውግዘት መገለጫ ባሻገር ቆርጠን በመነሳት እውን ልናደርገው ይገባል። ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት በአገርም ውስጥ ሆነ በውጭ አገር የሚደርሰው በደልና የሚፈሰው የወገኖቻችንን ደም ከንቱ ሆኖ እንዳይቀር በተባበረ ኢትዮጵያዊ የነጻነት መንፈስ እንነሳ ዘንድ፣ ዛሬ ኢትዮጵያውያን ያለንበትን ተጨባጭ ሁኔታና ስሜትን የሚገልጸው የክላውድ ማኬ ታሪካዊ ግጥምን በማስታወስ ወገናዊ ጥሪ እናቀርባለን።

If We Must Die
Claude McKay, 1889 – 1948

If we must die—let it not be like hogs
Hunted and penned in an inglorious spot,
While round us bark the mad and hungry dogs,
Making their mock at our accursed lot.
If we must die—oh, let us nobly die,
So that our precious blood may not be shed
In vain; then even the monsters we defy
Shall be constrained to honor us though dead!
Oh, Kinsmen! We must meet the common foe;
Though far outnumbered, let us show us brave,
And for their thousand blows deal one deathblow!
What though before us lies the open grave?
Like men we’ll face the murderous, cowardly pack,
Pressed to the wall, dying, but fighting back!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት
ሚያዚያ፣ 2007

The post የዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ የሴቶች ድርጅት አጭር መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

“የችግሩ መሰረታዊ ምንጭና መፍትሔው ፓለቲካዊ ነው’!! አቶ ኤርምያስ ለገሰ

$
0
0

daniel ermiasሰሞኑን በኢትዬጲያውያን ላይ የመከራ ዶፍ እየዘነበ ነው። ይህ የድቅድቅ ጨለማ ናዳ ባስከተለው አደጋ የተፈጠረው ቁጭትና መብከንከን ከቃላት በላይ ሆኗል። በኢትዬጲያውያን ዘንድ ከዚህ ውጭ የመተከዣ አጀንዳ ያለ አይመስልም። እንባ እንደ ጐርፍ እየወረደ ነው። የእናቶቻችን ደረት በእሳት የተለበለበ እስኪመስል ድረስ እየተደለቀ ነው። ወጣቶቻችን ከአረመኔዎች ጋር ግብግብ እየገጠሙ ነው። በመንገድ፣ በትራንስፓርት፣ በምግብ ቤት፣ በስራና በተለያየ አጋጣሚ የምናገኛቸው የባእድ አገር ሰዎች ሳይቀር የሀዘናችን ተካፋዬች መሆናቸውን እየነገሩን ነው። ነግረውን ብቻ አያቆሙም ። አያይዘው ፣
“ችግሩ ለምን እናንተ ኢትዬጲያውያን ላይ ባሰ?፣ ሀገራችሁን ትታችሁ ስደትን ለምን እንደ አማራጭ ወሰዳችሁ? ለምን እንደ ጨው ዘር ትበተናላችሁ?፣ ሰብሳቢ የላችሁም ወይ? ” የሚል ጥያቄ ያስከትላሉ። የሚገርመው ነገር እንደዚ አይነት ጥያቄ በግለሰብ ደረጃ ብቻ ሳይሆን እንደተቋምም እየቀረበ ነው። ለዚህ አባባል አብነት የሚሆነኝ ባለፈው አርብ አርቲስት ታማኝ በየነ ያጫወተኝ ወግ ነው። ከእሱ ጋር በፍሎሪዳ ግዛት በነበረን ቆይታ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ጉዳይ ኮሚሽን / ዩኤን ኤች ሲአር / ጋር እሱና የስራ ባልደረቦቹ በነበራቸው ስብሰባ ያነሱለትን ጥያቄ አንስቶ ነበር ውይይታችን የተጀመረው። ዩኤን ኤች ሲአሮች እንዲህ በማለት ነበር የጠየቁት፣
” እናንተ ኢትዬጲያውያን ሀገራችሁን ጥላችሁ በመሰደድ ተወዳዳሪ የሌላችሁ ሆናችኃል። ሌላው ቀርቶ በኢኮኖሚ አቅሟ ከእናንተ በምንም የማትሻለዋና የተንኮታኮተች ( የደቀቀች) ሀገር ወደ ሆነችው የመን እንዴት ትሰደዳላችሁ? ”
ይህ መሰረታዊ ጥያቄ ነው።እያንዳንዱ ኢትዬጲያዊ ከጊዜያዊ ዋይ ዋይታ ተቆጥቦ ከእኛ የማትሻለውን “የመን” አማትረን የምንመለከትበት ባይነኩላር ለምን እንዳስገጠምን መነጋገር ይኖርብናል። ከፊታችን እየመጣብን ያለው አደጋ ክብደትና አስፈሪነት በግልጵ አውጥተነው ችግሩን መነጋገር ያስፈልጋል።ይህን ማድረግ ካልቻልን ከራሳችን በላይ የምናስቀድማት ” ኢትዬጲያ ሀገራችን” የመኖርና ያለመኖር የህልውና አደጋ ይጋረጥባታል። ርግጡን እንነጋገር ከተባለ አሸዋ ላይ እንደተገነባ ቤት እየፈረስን ነው። የኢትዬጲያ ህዝቦች ላይ የተጠመደ ፈንጂ ለመፈንዳት ጊዜውን እየጠበቀ መሆኑ እየታየ ነው።
ቢያድለን ኖሮ ይህን አጀንዳ መክፈት የነበረበት መንግስት ነበር። ለጵድቅ ሳይሆን ከመንግስት ዋነኛ ሀላፊነቶች አንዱ ዜጐቹን ከውጭ ጥቃት የመከላከልና የህዝቡን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ የሚጣልበት በመሆኑ ። ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም የመንግስትን ትርጉም እንደሚከተለው ገልፀውታል፣
“መንግስት ማለት የአንድን ህዝብ መሰረታዊ አቋሞች ፣ አንድነትና ነጳነት ከውጭ ጠላት የሚከላከል፣ የሕዝቡን ደህንነት ፣ እድገትና መሻሻል የሚመራ ፣ ሕዝቡ ከውስጥ እርስ በእርሱ ያለውን ግንኙነት ፣ መብትና ግዴታ በሕግና በስርአት እየወሰነ የስልጣን ባለአደራ ሆኖ የሚያስተዳድር ድርጅት ነው” በማለት ። ” መንግስታችን!” ፕሮፌሰሩ ባስቀመጡት ሁሉም መስፈርት በዜሮ ተባዝቷል። ይህም የውርደታችን ምንጭ ሆኗል። የባእዳን ማላገጫና አፍ መፍቻ ሆነናል።
ትላንት የውጭ ዜጐችን በስብሰባ፣ በትምህርት… ወዘተ ባገኘን ቁጥር ” ሉሲን ታውቃታለህ?፣ አስራ ሶስት ወር ሙሉ የፀሀይ ብርሀን ፀጋ እንዳለን ታውቃለህ?፣ ከአፍሪካ ሀገሮች በቀኝ ግዛት ያልተያዝነው እኛ እንደሆንን ይገባሀል? ” በማለት ደረታችንን ነፍተን እንናገር ነበር። ነገርን ነገር ያነሳዋል እንዲሉ ይህን ማስታወሻ ስጵፍ አንድ ሁልጊዜም የማልረሳው ታሪክ አስታወሰኝ። ታሪኩ እንዲህ ነበር፣
በ1993 አ•ም• በአዲሳአባ ምክርቤት አዳራሽ በኢህአዴግ / ህውሀት የውጭ ጉዳይ ፓሊሲ ላይ ውይይት እያደረግን ነበር። የእለቱ ውይይት በፓሊሲው መግቢያ ላይ ባለው ” ብሔራዊ ውርደት” በሚለው ርእስ ላይ ነበር። በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት እጁን ያነሳው በወቅቱ የኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ፕሬዝዳንት የነበረው ዶክተር ዘሪሁን ነበር። በአንድ የውጭ ኮንፍረንስ ላይ ጥናታዊ ጵሁፍ ሊያቀርብ ያጋጠመውን ነበር የነገረን። ዶክተር ዘሪሁን እንደ መንደርደሪያ ” ሉሲ፣ አስራ ሶስት ወር፣ በኮለኒ ያልተያዘች…ወዘተ” እያለ ሲደሰኩር የአንድ አፍሪካዊ እጅ ይቀሰራል። አፍሪካዊው ፍቃድ ሳይጠይቅ ” ዶክተር ለምን ጨምረህ መዝገበ ቃላት “ቸነፈር” የሚለውን ሲያብራራ ኢትዬጲያን እንደ ምሳሌ ማንሳቱን አትነግረንም?፣ …ለምን ሀገራችሁ የሟሸሸ መንግስታት በመሆኗ እንደ ሀገር መቀጠል እንዳቃታችሁ አትነግረንም?፣… ለምን በዘርና በጐሳ ተከፋፍላችሁ እንደምትኖሩ አትነግረንም?…ለምን ህዳጣን ብዙሀኑን እየገዙ መሆኑን አትነግረንም… ወዘተ ” በማለት በጥያቄ ያፋጥጠዋል። ኬሚስቱ ዶክተር ዘሪሁን በወቅቱ የሚመልሰው መልስ አልነበረውም። ጥያቄው አናሊቲካል ወይም ባዬ-ኬምስትሪ አልነበረምና!!
ዛሬም ይህ ኢትዬጲያ መሬት ላይ ያለ ሀቅ አልተቀየረም። እየባሰበት ሄደ እንጂ!…
በሀገራችን ጥቂቶች የአውሮፓና የአረብ ቅምጥል የሚኖረውን ኑሮ እየኖሩ፣ ብዙሀን በችጋር እየተገረፋ ነው።… በሀገራችን ጥቂቶች ልጆቻቸውን በአሜሪካን ሀገር በሚገኙ እጅግ ውድ ዩንቨርስቲዎች በዶላር እያስተማሩ ( የአራት ጀነራል ልጆች በጆርጅ ታወን ዩንቨርስቲ ያስተምራሉ)፣ ብዙሀን ልጁን የሚያበላው አጥቶ ከትምህርት ቤት ያስቀራል።…ጥቂቶች ባል ሜጀር ጀነራል፣ ሚስት ኮረኔል፣ ልጅ ፓይለት የመሆን እድል ይመቻችለታል፣ ብዙሀኑ “ድንጋይ ማነጠፍ ” ለመስራት አሊያም ” አፍራሽ ግብረሀይል” በቀበሌ ለመቀጠር ቦታ የለንም ይባላል።…በሀገራችን ጥቂቶች የለውጥ ውቅያኖስ ገብተው የሀብት ጋራ እንዲቆናጠጡ ይደረጋል፣ ብዙሀኑ በአፍአዊ ለውጥና ከንቱ ተስፋ እንዲሞሉ ይደረጋል። …ጥቂቶች የህሊና እምብርት ሳይበጅላቸው የሀገር ሀብት ወደ ውጭ ያወጣሉ ( በዚህ አመት ከአፍሪካ ተሰርቆ ከወጣው ቢሊዬን ዶላር ውስጥ 28•5% ከኢትዬጲያ መሆኑን ልብ ይሏል)፣ ብዙሀን በአፍሪካ ጫካ የአውሬ ራት ይሆናሉ…በሰሀራ በረሀ እንደ ሎጥ ሚስት ደርቀው ይቀራሉ… በአረብ ሀገራት እንዳበደ ውሻ ይክለፈለፋሉ ( የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቃል እንደወረደ!)…ጐማ ተጠቅልሎባቸው በእሳት ይጋያሉ…እንደ ዶሮ አንገታቸው ተቀንጥሶ ይጣላሉ።
ወደድንም ጠላንም የዚህ ሁሉ አቢይ መንስኤ ፓለቲካዊ ነው። የፓለቲካው መበላሸት የፈጠረው ችግር! የውስጣዊ አድልዎ ፓሊሲ የፈጠረው ችግር !…እውነት እንነጋገር ከተባለ በአድሎዋዊው ፓሊሲ ምክንያት እኩል የመማር፣ የመስራት፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች የማግኘት እድል የለም። የፓለቲካው መበላሸት የህግ ልእልና እንዳይሰፍን አድርጓል። የህግ ልእልና ባለመስፈኑ ምክንያት ደግሞ ሀሳብን በነጳነት የመግለጵ፣ የመደራጀትና በሰላም ወጥቶ የመግባት መሰረታዊ መብት ዝግ ሆኗል። የህግ የበላይነት ባለመኖሩ ሁሉም የሀይማኖት ተቋማት በጣልቃ ገብነት እየታመሱ ይገኛሉ። በዚህም ሳይወሰን የእምነት ተቋማቱ በካድሬ ተጵእኖ በመውደቃቸው ምክንያት የእምነት ነጳነት ከስም የማያልፍ ሆኗል።
ከውስጣዊው የአድሎ ፓሊሲ ባልተናነሰ የውጭ ፓሊሲያችንም “መርህ አልባ” መሆን እና ” ጠላት ሳትፈጥር አትኑር! ” የሚለው የመለስ አስተምህሮ ለችግራችን መባባስ አስተዋጵኦ አበርክቷል። በሱማሊያ የተወሰደው የጣልቃ ገብነት እርምጃ የሳጥናኤል ጭንቅላት የተገጠመላቸው የሰው ዘር ባልሆኑት አይሲሶች ጥርስ እንዳስገባን የአደባባይ ሚስጥር ነው። በህዳር 21 ቀን 1999 አ•ም• ወደ ሱማሊያ ስንገባ አቶ መለስ ፣” ወቅታዊና ተጨባጭ የሉአላዊነት አደጋ ገጥሞናል። በኢትዬጲያ ላይ የጅሀድ ጦርነት ታውጇል ። ይህን ወቅታዊና ተጨባጭ አደጋ በአጭር ጊዜ ቀልብሰን ወደ ልማታችን እንመለሳለን” የሚል ነጋሪት በፓርላማ ጐስሞ ነበር። “ቀስ ብለን እናጢነው”፣ ” በኃላ ማጠፊያው እንዳያጥረን” ” የራሷ አሮባት የሌላውን ታማስላለች እንዳይሆንብን” እያሉ ተማጵእኖ ያሰሙትን አንጋፋ ፓለቲከኞች ( ዶክተር በየነ፣ ዶክተር መራራ፣ አቶ ቡልቻ…) ” የኢትዬጲያን ብሄራዊ ጥቅም አሳልፈው የሰጡ ከሀዲዎች፣ የሻእቢያ ተላላኪዎች” የሚል መልእክት ቀርፀን አብጠልጥለናል። ሰፋፊ መድረኮች ከፍተን ከፍ ዝቅ አድርገናል። እውነታው ግን የሱማሊያ ችግር እንኳን በአጭር ጊዜ ሊፈታ የኢትዬጲያ ወታደሮች ሱማሊያን ለቀው ሳይወጡ አስርተ አመት ሊደፍኑ አንድ አመት ብቻ ቀርቶአል። ውጤቱም ወንድሞቻችን በሰው በላ የዲያብሎስ መልእክተኛ በሆኑ አይሲሶች አንገታቸው መቀላት ሆኗል። የራሳችን አሮ የሌላውን እያማሰልን ነው!!

The post “የችግሩ መሰረታዊ ምንጭና መፍትሔው ፓለቲካዊ ነው’!! አቶ ኤርምያስ ለገሰ appeared first on Zehabesha Amharic.

የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ ድብደባ ተፈፀመበት

$
0
0

11162511_701415159984145_6213321057327874841_nየሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን አስተባባሪ የሆነው አቶ አዲሱ ጌታነህ በትናንትናው ዕለት በደህንነቶች ድብደባ እንደተፈፀመበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸ፡፡ መንግስት አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ላይ የወሰደውን እርምጃ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ የባህርዳር ከተማ አስተዳደርና ጸጥታ ኃላፊ አቶ አጃናው ‹‹በሰልፉ ጉዳይ መነጋገር አለብን›› ብለውት እንደነበር የገለጸው አቶ አዲሱ ‹‹ሰልፉ ላይ በግለሰብ ደረጃ እንጅ እንደ ፓርቲ ስለማንገኝ የምንነጋገረው ነገር የለም›› የሚል መልስ እንደሰጠ ገልጾአል፡፡

ከሰልፉ ቀደም ብሎ በጠዋት ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ሲያቀና ቢሮው በፖሊስ ተከቦ እንዳገኘው የገለጸው አቶ አዲሱ እሱና ሌሎች የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ሰልፉ ላይ በተሳተፉበት ወቅትም ደህንነቶች እየተከታተሉ ፎቶ ሲያነሷቸው እንደዋሉ ገልጾአል፡፡ ከሰልፉ መልስ ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ያመራው አቶ አዲሱ ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ከቢሮ ወጥቶ ወደ ቤት በሚሄድበት ወቅት በደህንነት ድብደባ እንደደረሰበት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡
በደህንነቶች ድብደባ የተፈፀመበት አቶ አዲሱ ‹‹ኢህአዴግ በሀሰብ መብለጥ ሲያቅተው የነፃነት ትግሉን በኃይል ለማስቆም እየጣረ ነው፡፡ ይህ እርምጃ ትግሉን ይበልጡን የሚያጠናክረው ይሆናል እንጅ ወደኋላ የምንልበት አጋጣሚ አይኖርም›› ብሏል፡፡

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia

The post የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ ድብደባ ተፈፀመበት appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>