Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

ጀርመን አሻፍንቡርግ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሰላማዊ ፡ ሰልፍ ፡ ጥሪና ፡ የሀዘን ፡ ጉዞ

$
0
0

Saudicryሁላችሁም ፡ እንደምታውቁት ፡ ሚያዝያ ፡ 20 ቀን ፡ 2015 ዓ.ም ፡ 28 ኢትዮጵያውያን ፡ ወንድሞቻችን ፡ በእስልምና ፡ ስም ፡ በሚነግደው ፡ ኣሽባሪ ቡድን ፡ ISIS (የእስልምና ፡ መንግስት ፡ በኢራቅና ፡ ሲሪያ) በኣሰቃቂና ፡ በዘግናኝ ፡ ሁኔታ ፡ መሰዋታቸውን ፤

በደቡብ ፡ ኣፍሪካ ፡ በሕይወታቸው ፡ የተቃጠሉና ፡ ንብረታቸውን ፡ የተዘረፉትን ፤

በየመን ፡ በተቀሰቀሰው ፡ የሀገር ፡ ውስጥ ፡ የእርስ ፡ በእርስ ፡ ጦርነት ፡ መጠጊያ ፡ ኣጥተው ፡ የተገደሉ ፤ የቆሰሉ ፤ አሁንም ፡ በርሀብና ፡ በጥማት ፡ የሚሰቃዩትን ፡

በተለያየ ፡ ምክንያት ፡ ከኣገራቸው ፡ ኢትዮጵያ ፡ ወጥተው ፡ በየበረሐው ፡ የኣውሬ ፡ እራት ፡ በየባሕሩ ፡ የሰመጡትን ፡ እህቶችችንና ፡ወንድሞቻችንን ፡ ታስታውሳላችሁ!!

በተከታታይ ፡ እየደረሰብን ፡ ያለውን ፡ መከራ ፡ በጋራ ፡ ለማዘንና ፡ ችግራችንንም ፡ ለየምንኖርበት ፡ ኣካባቢ ፡ ለማሳወቅ ፡ በአሻፈንቦርግና ፡ ኣካባቢ ፡ የኢትዮጵያን ፡ ማህበር ፡ e.V. ለግንቦት(MAY) 21 2015 . 1400 ሰዓት እስከ 1700 ሰዓት ፡ በኣሻፈንቦርግ ፡ ከተማ ፡ ሰላማዊ ፡ ሰልፍ ፡ የጠራ ፡ ስለሆነ ፡ እርስዎም ፡ የሰላማዊ ፡ ሰልፉ ፡ ተካፋይ ፡ እንዲሆኑ ፡ በኣክብርት ፡ ጥሪ ፡ ቀርቦልዎታል ።

ወደ ፡ ቦታው ፡ ለመምጣት ፡ የሚከተሉትን ፡ ኣማራጮች ፡ መጠቀም ፡ ይችላሉ ።

በባቡር ለምትመጡ፤

ከደቡብ (ሙኒክ ፤ ኑርንበርግ ፤ ቩርዝቦርግ …) የምትመጡ ፡ ከባቡር ፡ እንደወረዳችሁ ፡ ወደ ፡ ግራ ፡ በመታጠፍ ፡ ወደ ፡ ከተማው ፡ ይውጡ ፤

 

ከሰሜንና ፡ ከምዕራብ ፡ ከዳርምስታት ፤ ከፍራንክፎርት ፡ ኣቅጣጫ ፡ የምትመጡ ፡ ከባቡር ፡ እንደወረዳችሁ ፡ ወደ ፡ ቀኝ ፡ በመታጠፍ ፡ ወደ ፡ ከተማው ፡ ይውጡ ፤

 

በመኪና ፡ ለምትመጡ፤

 

ከደቡብ (ሙኒክ ፤ ኑርንበርግ ፤ ቩርዝቦርግ …) የምትመጡ ፡ A3 – Ausfahrt Aschaffenburg Ost – Schönbornstraße –  Auhofstraße -Glattbacher Überfahrt – Elisenstraße

ከምዕራብ ፡ ከዳርምስታት ፡ ኣቅጣጫ ፡ የምትመጡ ፡ B26 – Darmstädter Straße – Westring – Friedrich Ebertsbrücke – B 26  Hanauerstraße – Kolpingstraße – Ludwigstraße

ከሰሜን ፡ ፤ ከፍራንክፎርት ፡ ኣቅጣጫ ፡ የምትመጡ ፡ A3 – Ausfahrt Aschaffenburg West – B 8 – Hanauerstraße – Kolpingstraße – Ludwigstraße

የኣሻፈንቦርግና ፡ ኣካባቢ ፡ የኢትዮጵያን ፡ ማህበር  e.V.

The post ጀርመን አሻፍንቡርግ ከተማ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን የሰላማዊ ፡ ሰልፍ ፡ ጥሪና ፡ የሀዘን ፡ ጉዞ appeared first on Zehabesha Amharic.


በስቶክሆልም በሊቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን በደመቀ ሁኔታ ታስበው ዋሉ

$
0
0

ethiopians in sweden

ethiopians in sweden 2

ethiopians in sweden 3

ዳንኤል ሐረር ለዘ-ሐበሻ ከስዊድን እንደዘገበው:-

ትላንት ሐሙስ ግንቦት 6/2007 በምስራቅ አፍሪካ እና አውሮፓ አህጉረ ስብከት የመንበረ ፀባዖት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ እስቶኮልም ሆተርየት ባዘጋጀው የ21ኛው ክፍለ ዘመን ድንቅ የእግዚአብሔር ምስክሮች ለሆኑት 30 (ሰላሳ ) የኦርቶዶክስ ልጆች መታሰቢያ ፕሮግራም በዕለቱ ከተገኙ የግብፅ የሶርያ ብጹአን አባቶች ጋር በደማቅ ሁኔታ ታሥቦ ውሏል፡፡ በዕለቱ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስትያን ካህንና የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስትያን ካህናት ተገኝተዋል።

እንዲሁም በስቶኮልም ባሉ አብያተ ክርስቲያናት ስንበት ት/ቤት ተማሪዎች የህብረት መዝሙረና በወቅቱ የነበረውን የሰማዕታቱን ጽናት የሚያሳይ ትዕይንት ፤የአበባ ማስቀመጥ እና የጧፍ ማብራት ፕሮግራሞ ተካሂዷል።

The post በስቶክሆልም በሊቢያ ሕይወታቸውን ያጡ ኢትዮጵያውያን በደመቀ ሁኔታ ታስበው ዋሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

5 በሃይል አማራጭ የሚያምኑ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ውይይት ጀመሩ

$
0
0

Ethsatበስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በማንኛውም አማራጭ ለማስወገድ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ የተቃዋሚ ሃይሎች በጋራ ለመታገል የሚያስችላቸውን ውይይት መጀመራቸውን ለኢሳት በላኩት መግለጫ አስታውቀዋል።

ውይይቱን የጀመሩት የትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ ( ትህዴን)፣ የጋምቤላ ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የቤንሻንጉል ህዝብ ነጻነት ንቅናቄ፣ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄና አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ ናቸው።

ድርጅቶቹ ” በሂደት ወደ አንድ የምንመጣበትን ሁኔታ እያመቻቸን፣ አሁን ግን አገርና ህዝብን የማዳኑን ስራ እንጀምር በሚል ውይይት እያደረግን መሆናችንን ለኢትዮጵያ ህዝብ መግለጽ እንወዳለን” ብለዋል።

የኢህአዴግን አገዛዝ በሃይል እናስወግዳለን በማለት የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ድርጅቶች ከጊዜ ወደ ጊዜ በሰው ሃይልና በሎጂስቲክ እየተጠናከሩ መምጣታቸውን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።

ስርዓቱ በአገር ውስጥ በሚገኙ ዜጎች ላይ እያደረሰ ያለው አፈና ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር፣ ወጣቶች የትጥቅ ትግል አማራጭን የሚደግፉ ሃይሎችን እንዲቀላቀሉ እያደረጋቸው ነው።

Source:: Ethsat

The post 5 በሃይል አማራጭ የሚያምኑ ድርጅቶች በጋራ ለመታገል ውይይት ጀመሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት ተካሄደ

$
0
0

ethiopiaበአሜሪካ ዋሺንግተን ዲሲ ከተማ እና አካባቢዋ ያሉ አብያተ ክርስቲያንናት እንዲሁም የተለያዩ የሲቪል ድርጅቶች በቅርቡ በየመን፥ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን ለመዘከር እሁድ እለት በዚህ በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ የመታሰቢያ ዝግጅቶችን አካሄዱ።

ነዋሪነታቸው በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካባቢዋ በርካታ ኢትዮጵያዊን በታደሙበት በዚህ ዝግጅት፥ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ባራክ ኦባማ ሟች ኢትዮጵያዊያንን አስመልክቶ ያስተላለፉት የሀዘን መልክት ተነቧል። ልዪ የጸሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት በተከናወነበት በዚሁ ዝግጅት፥ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፥ ከኢትዮጲያ የሙስሊም እምነት ተወካዮች፥ ከመካነ-እየሱስ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን፥ እንዲሁም ከአለምአቀፍ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን የተወከሉ የሀይማኖት አባቶች የሃዘን መግለጫ መልክት ማስተላለፋቸውን ከስፍራው የደረስን መረጃ አመልክቷል ።

ለግማሽ ቀን ያህል በተከናወነው በዚሁ የመታሰቢያ ዝግጅት ወቅት ከዋልድባ ገዳም ማህበር ፤ ከዲሲ ሜትሮ ግብረ-ሀይል እንዲሁም ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በሊቢያ በአሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉ ኢትዮጵያዊንን በማስመልከት የተሰማቸውን ሀዘን እንደገለጹ ታዉቋል።

በእለቱም ለሟች ቤተሰቦች ድጋፍ የሚውል የገንዘብ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ተካሂዶ ከ ፬ ሺህ ዶላር በላይ መሰብሰቡ ታውቋል።

በቅርቡ በሊቢያ፥ የመንና፥ ደቡብ አፍሪካ የተገደሉ ኢትዮጵያዊያንን በማስመልከት ነዋሪነታቸው በዚሁ በአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶችና የተለያዩ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ዝግጅቶችን ሲያከናውኑ መቆየታቸው ይታወሳል።

Source:: Ethsat

The post በሊቢያ በግፍ ለተገደሉ ኢትዮጵያዉያን የፀሎትና የሻማ ማብራት ስነስርዓት ተካሄደ appeared first on Zehabesha Amharic.

እስራኤልን እንዳሰብክ ኢትዮንም አስባት (አዳነ መኮነን)

$
0
0

eth cry

ግፍና መከራው ሲፈራረቁባት

እያየህ ዝም አትበል ተሎ ድረስላት
እስራኤልን እንዳሰብክ ኢትዮንም አስባት።
በዓለም ተበትነው ሲገቡ ከእስር ቤት
አንገታቸው ሲቀላ በሌላቸው እምነት
የፊጥኚም ታስረው ሲቃጠሉ በእሳት
ከፎቅ ተወርውረው ሲጣሉ ከመሬት
ይህነን እያየህ ምነው ጨከንክባት
እስራኤልን እንዳሰብክ እሷን አስባት
በተናገርከው፤ በቃልህ መሰረት።
እንጀራ ፍለጋ ከተሰደዱበት
ልጆቿን ሰብስበህ መልሰህ አምጣላት
ከሞት የተረፉትን የአሉትን በሕይወት።
እንደ በግ መታረድ ለክርስቲያን ሰው
ዛሬ አዲስ አይደለም ድሮም የነበር ነው
አባቶች አልፈዋል ሰማእ-ት ተቀብለው።
የውጭ ጠላትማ ጥንትም የነበር ነው
አሁን እያረደን ያለ የውስጥ አይሲስ ነው
ቆዳው እኛን መስሎ ልቡ ግን ሌላ ነው።
በአለፈው ዓመት መምህሩን ስትወስድ ተማሮች ትተሃል
እስከ መጨረሻው መቼም አይማሩ ደጋግመው ወድቀዋል
የንጉሦች ንጉሥ የኃያላን ኃያል
እነሱን አንስተህ አሳየን ዘንድሮ ክፍል አጣበዋል።
ቦታውም ይለቀቅ ለቆጠረ ፊደል
ለተማረ ሰው እውቀት ለሚያካፍል።
ተማሩ ተማሩ እያለ ህዝቡ ቢነግራቸው
ከማንስ ያዩትን ትምህርቱ ይግባቸው
ሃያ አራት ዓመት ተደፍኖ ልብና አንጎላቸው።
እጃቸውን ይዞ ሰው ሲያስተምራቸው
ትምህርቱን የሚያቁት ያኔ ነው ያኔ ነው
ከነሱም ሲደርስ ከሰው የደረሰው።
ጠላት አሰፍስፎ ዙሪያውን ቢከበን
የቅዱሳን አምላክ የአባቶቻችን
እኛን ይጠብቃል ሆኖ በጎናችን
የሚያስፈራን የለም እግዚአብሔር አለልን።
እኛ አንጠብቅም ከሰዎች እርዳታ
አለልን ፈጣሪ ችግር የሚፈታ
እልል በይ ኢትዮጵያ በትንሣኤ ለታ
አንችን ለመቀደስ ሊመጣነው ጌታ።
ከትቢያው አንስቶ ዙፋን ላይ ሊያስቀምጥሽ
መላእኩ ይመጣል ምስራች ሊያበስርሽ
ጥቁሩን አውልቂና ነጩን ልብስ ልበሽ
ከፍ ብለሽ ተቀመጭ ዓለምም እንዲያይሽ።
ኢትዮጵያ ሀገራችን ወድቀሽ ትነሻለሽ፤
ልክ እንደ እስራኤል አችንም አይረሳሽ፤
ጠላትሽን አጥፍቶ አንችን ይባርካል፤
የፈጠረሽ አምላክ የኃያላን ኃያል።
ግንቦት፤፯ቀን፡ ፪ሺ፯ ዓ/ም (15/05/2015)

The post እስራኤልን እንዳሰብክ ኢትዮንም አስባት (አዳነ መኮነን) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሥርዓቱን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ 4 ወታደሮች ወደ ሱዳን ተሰደዱ

$
0
0

Zehabesha News
የደህሚት ድምጽ እንደዘገበው በርካታ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ ነባር የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ወታደሮች ስርዓቱን በመቃወም ወደ ሱዳን ሃገር እየሄዱ መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል።

በምንጮቻችን መረጃ መሰረት ለረዥም አመታት በውትድርና ሲያገለግሉ ቆይተው ከሃዲው ስርዓት የተለያዩ ምክንያቶችን በመፍጠር እያባረራቸው እንደሆነ የገለጸው መረጃው ከእነዚህም መካከል አወል አሊና ገብረማሪያም ታከለ የተባሉ የደቡብ ወሎ ተወላጆች እንዲሁም ምንዋጋው ቸኮልና አሸናፊ የተባሉ የጎንደር ተወላጆች የሚገኙባቸው 4 ነባር ወታደሮች ስርዓቱን በመቃወም ወደ ሱዳን ሃገር ሲሄዱ መያዛቸውን ታውቋል።

እነዚህ በስርዓቱ ታስረው የሚገኙ ወገኖቻችን ለበርካታ አመታት ስርዓቱን ሲያገለግሉ ቆይተው ያለምንም መቋቋሚያ ከተባረሩ በኋላ መሬት ጠይቀው የሚሰጣቸው አካል ባለማግኘታቸው ኑሮ መሯቸው ወደ ሱዳን ሃገር እንዲሰደዱ መገደዳቸውን ለማወቅ ተችሏል።

The post ሥርዓቱን ለረጅም ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ 4 ወታደሮች ወደ ሱዳን ተሰደዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

በትግራይ ምክትል 10 አለቃ አሊ አራጌ ተገድሎ ተገኘ

$
0
0

Zehabesha News
በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ምድረ ፈላሲና አካባቢዋ ከሚገኙ የኢ.ህ..አ.ዴ.ግ ወታደሮች የምክትል አስር አለቃ ማእርግ ያለው ወታደር ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች እንደተገደለ የደህሚት ድምጽ ዘገበ::
እንደ ዘገባው ከሆነ በትግራይ ክልል ሰሜናዊ ምዕራብ ዞን ላዕላይ አድያቦ ወረዳ ልዩ ስሙ ምድረ ፈላሲና አካባቢው ከሚገኙት የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ. ስርዓት ወታደሮች መካከል አሊ አራጌ የተባለ ምክትል አስር አለቃ ሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ/ም በፈቃድ ወደ አዲ ነብሪ ኢድ በሄደበት ጊዜ ማንነቱ ባልታወቀ ገዳይ ሚያዝያ 23 ቀን 2007 ዓ/ም በአከባቢው በሚገኘው ካምፕ ሞቶ እንደተገኘ ታውቋል።
ይህ የተገደለው ወታደር በማን እንደተገደለ በሃላፊዎች ምንም ዓይነት የተደረገ ምርምራ ሳይኖር መቀበሩን የገለፀው መረጃው የአካባቢውን ህብረተሰብ ከሰራዊቱ ለመነጠል የዚህ አካባቢ ህዝብ የትህዴን አባል ነው የሚል ወሬ ከሰራዊቱ አዛዦች መናፈሱን የደረሰን መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።

The post በትግራይ ምክትል 10 አለቃ አሊ አራጌ ተገድሎ ተገኘ appeared first on Zehabesha Amharic.

የተግባር ሳምንት –ኤርሚያስ ለገሰ

$
0
0

11255736_10206693848489925_7593816954121445331_nውጤቱ የታወቀው ምርጫ ሊካሄድ የመጨረሻው ሳምንት ላይ እንገኛለን። የኢትዬጲያ ህዝብ የምርጫውን ውጤት አስቀድሞ የገመተው በመሆኑ ለሂደቱ ትኩረት ሳይሰጠው በመጠናቀቅ ላይ ይገኛል። በዚህ የመጨረሻ ሳምንት ላይ ተቀምጠን ሂደቱ እንዴት አለፈ ብሎ ለመመርመር ጊዜው ገና ይመስላል። ከዛ ይልቅ በምርጫው እለት ምን ሊሰራ ይችላል የሚለው ላይ አተኩሮ መንቀሳቀሱ የተሻለ ይሆናል። ለጊዜው ሁለት አማራጮች ይታዩኛል።
አማራጭ አንድ: ድምጵ ያለመስጠት፣
ከሚቀርቡት አማራጮች በግለሰብ ደረጃ ከፍተኛ ዋጋ ሊያስከፍል የሚችለው በምርጫው እለት ወደ ጣቢያ ባለመሄድ ድምጵ አለመስጠት ነው። ምንም እንኳን ዋጋው ከባድ ቢሆንም የሚያስተላልፈው መልእክት ከየትኛውም አማራጭ የላቀ ነው። መሰረታዊ የዲሞክራሲና ሰብአዊ መብት በተገፈፈበት፣… የሲቪል ማህበረሰብ ተቋማት በተሽመደመዱበት፣… የገዥው መደብን ፕሮፐጋንዳ ብቻ የሚያስተጋቡ ፕሬሶች የፓለቲካ ምህዳሩን በሞሉበት፣ …የብእር አርበኞችና የሀይማኖት ነጳነት ታጋዬች በአሸባሪው የፀረ ሽብር አዋጅ በተከሰሱበት፣ …ገዥውን መደብ በተወሰነ መልኩ ሊገዳደሩ የሚችሉ የፓለቲካ ፓርቲዎች በፓለቲካ ውሳኔ ተላልፈው በተሰጡበት… ወዘተ ሁኔታ የምርጫ ካርድ ተሸክሞ ወደ ምርጫ ጣቢያ መሄድ የሞራል ጥያቄ ማስነሳቱ የማይቀር ሀቅ ነው።
ስለዚህ ድምጵ የምሰጠው ምን ፈልጌ ነው? ምን ለማትረፍ ነው? ከላይ የተጠቀሱት መሰረታዊ ችግሮች በእኔ ድምጵ ሊሻሻሉ ይችላሉ ወይ? የሚሉ ቁምነገሮችን በማንሳት ምላሽ መስጠት የዚህ ሳምንት ቁልፍ ጥያቄ ይሆናል።
በመጀመሪያ ምርጫ ተመዝግቦ ድምጵ ያለመስጠት ልምድ ከዚህ በፊት በነበሩት ምርጫዎች ተከስቶ እንደሆነ መመልከቱ አስፈላጊ ይሆናል። ሩቅ ሳንሄድ የዛሬ አምስት አመት (2002 አም) በተካሄደው ምርጫ መቼም ልቡን ለኢህአዴግ ሰጥቶ የማያውቀው የአዲሳአባ ህዝብ ተግብሮታል። ለዚህ ማስረጃ የሚሆን አንጋፋው ፓለቲከኛ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ ማርያም በ2003 አም ” ሥልጣን ፣ባህልና አገዛዝ ፣ ፓለቲካና ምርጫ” በሚለው መጵሀፋቸው በግልጵ አመላክተዋል። ፕሮፌሰሩ የምርጫ 2002 ዋና ተዋንያኖች በሚተርኩበት ክፍል በገጵ 156 ላይ የክልሎቹን ህዝብ ብዛት፣ ለምርጫው የተመዘገቡና የመረጡትን በሰንጠረዥ አሳይተዋል። በዚህም መሰረት በአዲሳአባ እመርጣለው ብለው ከተመዘገቡት ውስጥ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ የመረጡት 43•8% ብቻ ናቸው። በሌላ አነጋገር ለምርጫ ከተመዘገቡት 100 ሰዎች ውስጥ 56 ያህሉ አውራ ጣታቸው ላይ ቀለም አላረፈም። ወይም ምርጫ ካርዳቸውን ቀዳደው ጥለዋል።
በማስከተል ድምጵ ያለመስጠት ውጤታማ የሚሆነው በየትኛው አካባቢ ነው? የሚለውን ጥያቄ እንመልከት። ከልምድ በመነሳት የተቃዋሚ ፓርቲ እውነተኛ ታዛቢ በሌለባቸው፣ ገጠራማ አካባቢዎችና እንደ አፋር፣ ሱማሊያ፣ ጋምቤላ፣ ቤኔሻንጉል፣ ትግራይ የመሳሰሉ ክልሎች ድምጵ ያለመስጠት ብዙም ትርጉም የለውም። በእነዚህ “ተው ባይ” በሌለባቸው አካባቢዎች ምርጫው ከመካሄዱ በፊት ተለዋጭ ኮሮጆ የመዘጋጀት እድሉ ሰፊ ነው። የማቅለሙም ስራ አስቀድሞ ይጠናቀቃል። የገዥው ፓርቲ ተወዳዳሪዎች የአካባቢው ህዝብ ባጠቃላይ በአስር እጥፍ ተባዝቶ የሚያክለውን ያህል ድምጵ ያገኛሉ። ለዚህ ማሳያ የሚሆነው አሁንም የፕሮፌሰር መስፍን መጵሀፍ ይሆናል። ሁሉም እንደሚያውቀው በምርጫ ህጉ መሰረት አንድ የምርጫ ወረዳ የሚዋቀረው በምርጫ ወረዳው እስከ መቶ ሺህ ህዝብ ( ህጳናት፣ ወጣቶች፣ አዋቂ በሙሉ) ሲኖር ነው። በማእከላዊ ስታስቲክስ መረጃ መሰረት በኢትዬጲያ ከ15 አመት በታች የሚሆነው ሕዝብ ቁጥር 45•2% ያህል ይሆናል። ይህ ማለት በአንድ ምርጫ ክልል ለመምረጥ እድሜው የደረሰ በሙሉ ተመዝግቧል ቢባል ብዛቱ ከ50 ሺህ በታች ይሆናል። ይህን ታሳቢ አድርገን ጋሽ መስፍን በገጵ 157 ላይ ” አስገራሚ የምርጫ ውጤት” በሚል ርእስ የ25 ሰዎች ከመቶ ሺህ በላይ ድምጵ ማግኘታቸውን በሰንጠረዥ አሳይተዋል። ከዚህ ውስጥ ፊልቱ ወረዳ የተወዳደሩት አቶ ኡስማን አለ መላ 368, 211 ፣ ጂጂጋ ምርጫ ክልል አቶ አሊ ኡመር አለሌ 213,288፣ አሁንም ጅጅጋ አቶ አብዱልፈታህ አብድላሂ 246,782 የሚያህል ድምጵ አግኝተዋል። በመሆኑም እንደዚህ አይነት ቦታዎች ላይ ድምጵ መስጠትም ሆነ አለመስጠት የሚያመጣው ለውጥ የለም።
( በነገራችን ላይ የእነ ኡስማንን አስገራሚ ውጤት ስመለከት በጭንቅላቴ የሚመጣው አርቲስት ታማኝ በየነ በአንድ ወቅት በአዲሳአባ ስቴዲዬም ያቀረበው ቀልድ ነው። በወቅቱ በጫካ መሽገው ኢህአዴግ ስንት የኢትዬጲያ ወታደሮች እንደገደለ በሬዲዬ የሚናገሩት ፍሬህይወት ( በአሁን ሰአት የአዲሳአባ ፓርላማ እጩ) እና ሴኮቱሬ ጌታቸው ነበሩ። በየቀኑ 50ሺህ፣ 100ሺህ ገደልን የሚለው የእነ ሴኮ ብስራት ያልተዋጠለት ታማኝ ” እነዚህ ሰዎች ከነገው ትውልድ ተበድረው ይገላሉ ወይ?” የሚል ቀልድ አንስቶ በታሪክ ተመዝግቦለታል። በንጋታው የሬዲዬ ጣቢያውን የተረከበው ሴኮቱሬ ” ታማኝ! ሂሳቡን ስንመጣ እናወራርዳለን” ብሎት ነበር።

አወራርደው ይሆን??)
አማራጭ ሁለት: የድምጵ መስጫ ወረቀቱን የተቃውሞ መግለጫ ማድረግ ይህ አማራጭ ከግለሰብ ደህንነት አንጳር አስተማማኝ ተደርጐ ሊወሰድ የሚችል ነው። ይህን እርምጃ ሊወስዱ የሚችሉ ሰዎች በአንድ ለአምስት መዋቅር ውስጥ ተጠርንፈው መላወሻ ያጡ ግን ደግሞ ገዥው መደብንም ሆነ ተቃዋሚዎችን ለመምረጥ ፍላጐት የሌላቸው መሆናቸው አይቀርም። ከዚህ በተጨማሪም አንዳንድ የአንድነት፣ መኢአድና የትጥቅ ትግል አማራጭን የሚደግፋ ግለሰቦች በዚህ ማእቀፍ ውስጥ ሊካተቱ ይችላሉ ( በኢህአዴግ ኔትወርክ “C” እና ” D” ደረጃ የተሰጣቸው)። በተለይ ባለመምረጣቸው የስራ ዋስትና የማጣት እጣ ፋንታ የሚያጋጥማቸው ነዋሪዎች ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ወረቀቱን የተቃዉሞ መግለጫቸው ቢያደርጉት ይመረጣል።
ቀጥሎ የሚመጣው ጥያቄ ወረቀቱ ላይ የሚሰፍረው የተቃውሞ መልእክት ምን ይሁን የሚለው ይሆናል። በመጀመሪያ ደረጃ በተቻለ መጠን መልእክቱ ወጥ እንዲሆን ማድረግ ነው። በተለይም የቡድን ጥያቄ ያላቸው ማህበረሰቦች የጋራ ፍላጐታቸውን የሚያሳይ የተቃውሞ መልእክት ( ምስልን ጨምሮ) ሊነድፋ ይችላሉ። ለምሳሌ የሙስሊሙን ንቅናቄ የሚመሩ አመራሮች ከዚህ ቀደም እንዳደረጉት ” ፍትህ” ፣ አሊያም ” የጨረቃ ምስል” የሚያሳይ እንዲሆን ማድረግ። የኦርቶዶክስ ተከታዬች ሰሞኑን የታረዱ ወንድሞቻችንን ለመዘከርና መንግስት በቤተክርስቲያኗ ላይ የሚያደርሰውን ጣልቃ ገብነት ለመቃወም ” የመስቀል ምልክት” አሊያም ተዛማች ነገሮችን ማድረግ። ለውጥ የሚመጣው በትጥቅ ትግል እንደሆነ የሚደግፋ ነዋሪዎችም በተመሳሳይ መንገድ ወጥ መልእክት ወይም ምልክት የሰፈረበት ወረቀት ወደ ኮሮጆ እንዲጨምሩ ማድረግ ያስፈልጋል። ይቻላልም።
ተቃዋሚ ፓርቲዎች፣
በምርጫው የሚሳተፋ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በሁሉም ጣቢያዎች ታዛቢዎቻቸው እንዲገኙ ማድረግን መናገር ለቀባሪው ማርዳት ይሆናል። ሆኖም ግን በቂ ኦረንቴሽን ሰጥቶ ማሰማራት መታለፍ የሌለበት ነው። በ2002 የነበረው አንድ ችግር የተበላሹ ወረቀቶች ጣቢያው ላይ በሚገኙ ታዛቢዎች ስምምነት እንዲቆጠሩና ድምጵ አልባ እንዳይሆኑ ተደርጐ ነበር። ይህ የሚጠቅመው ገዥው መደብን ብቻ ነው። በመሆኑም የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች ለፓርቲያቸው ድምጵ ከመቆጣጠር ተሻግረው የተበላሹትንም መቁጠርና በፈርጅ በፈርጁ ማስቀመጥ እንደ ዋና ስራቸው መውሰድ ይኖርባቸዋል። ይህንንም ለፓርቲያቸው በፍጥነት ሪፓርት ማድረግ ይኖርባቸዋል። ጭማቂውን መሰረት አድርገው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች በምርጫው ማግስት ሰላማዊ ሰልፍ ቢጠሩ ደግሞ ትግሉን ወደ ሌላ ምእራፍ ያሸጋግሩታል። ውሳኔው የራሳቸውና የራሳቸው ብቻ ቢሆንም!!

 

The post የተግባር ሳምንት – ኤርሚያስ ለገሰ appeared first on Zehabesha Amharic.


በ30 ዓመት የትዳር አጋሩ የተነሳ በዋሽግንተን ዲሲ የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን የበቃው ኢትዮጵያዊ

$
0
0

washington DC
ከአረአያ ተስፋማርያም

“አትቀስቅሱኝ!”
በምዕራብ ዲሲ አቅጣጫ ማለዳ ላይ ስናልፍ ከወደጥግ አንድ ኩርምት ብሎ የተኛ ሰው አይናችን ገባ። በ50ዎቹ አጋማሽ የሚገመት ሃባሻ ወገን ነው። አቶ አምሳሉ ይባላል። የውስጡን ጉዳት ገፅታው ያሳብቃል።

..አንድ ልጅ ካፈራችለት የ30 አመት ፍቅረኛው ወይም የትዳር አጋሩ ያላሳበው በደል እንደተፈፀመበትና ለጐዳና ህይወት እንደዳረገው ይናገራል። ብዙም ማውራት የማይፈለገውና ተስፋ የመቁረጥ ሁኔታ የሚታይበት አቶ አምሳሉ ከባለቤቱ ጋር ያለያያቸው ድንገት በአደጋ የተገኘ ጠቀም ያለ የኢንሹራንስ ገንዘብ እንደሆነ ይናገራል። አሜሪካ ያስመጣቸው የባለቤቱ እህትና ወንድም እንዲሁም አንዲት ዘመዷ አባሪና ተባባሪ በመሆን እንዲሁም «ሊገድላትና ሊደፍራት ሲል አይተናል» ብለው በሃሰት በመመስከር ትዳሩን እንደበተኑትና በቁም እንደገደሉት ይገልፃል። የ21 አመት ልጁ በአባቱ በተፈፀመው በደል ተበሳጭቶ ሌላ ከተማ ሄዶ እንደሚኖርና የት እንዳለ እንደማያውቅ አምሳሉ ይጠቁማል።

« የ30 አመት ፍቅሬ ሊደፍረኝ…አለችኝ። ይገርማል! ጭራሽ ሊገድለኝ አለች!..በ30 አመት አንድ ቀን እጄን አንስቼባት አላውቅም! አንድ ቀን ሌላ ሴት ጋር ሄጄ አላውቅም! አሳሰረችኝ። አስፈረደችብኝ። ህይወቴን አመሳቀለችው» በሃዘን ስሜት ተወጦ ..ተመልሶ ለመተኛት ያደፈች አንሶላውን ወደፊቱ ጣል እያደረገ « እባካችሁ ተውኝ! አትቀስቅሱኝ! ሞቻለሁ!..»

The post በ30 ዓመት የትዳር አጋሩ የተነሳ በዋሽግንተን ዲሲ የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን የበቃው ኢትዮጵያዊ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሃያአራት አመት ጊዜ ያለወጠው አዙሪት! ከአዙሪት ለመውጣት .. (ምንሊክ ሳልሳዊ)

$
0
0

tplfበሕወሓት የበላይነት የሚተዳደረው የኢሕአዴግ አምባገነናዊ አገዛዝ ላለፉት ሃያአራት አመታት እጅግ ከፍተኛ ወንጀሎችን በሕዝብ ላይ በመፈጸም ንጹሃንን በማሰር ሰርቶ አገር ሊለውጥ የሚችለውን ትውልድ በማሰደድ እምቢኝ ያሉትን በመግደል…በተከታታይ እና በተደጋጋሚ በሚፈጽማቸው አሰቃቂ ግፎች ስልጣን ላይ ለመቆየት በሚያደርገው ትንቅንቅ እጅግ ዘግናኝ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል በዜጎች ላይ ፈጽሟል እየፈጸመ ነው::ወንጀል መፈጸሙ ሳያንሳ የራሱን የደም እጆች በሌሎች ላይ ለማቀባባት በመሞከር ራሱን ነጻ ለማውጣት የሃሰት ፕሮፓጋንዳ ቢረጭም አልተሳካለትም::

እያንዳንዳችን ከበፊቱ በተሻለ መልኩ ቆም ብለን ልናስብበት የሚገባ እድሎችን በመተቀም ለዘላቂ መፍትሄ ራሳችንን በማዘጋጀት እንዲህ አይነቱን አምባገነን መንግስት ልናስወግድ ይገባል::እስከዛሬ በሰቀቀን እና በ እ ህ ህ ያሳለፍነው ዘመናችን ችግሩ ማነው ብለን ልናጤነው እና ችግሩን በዘላቂነት ልናስወግድ የዜግነት ግዴታችን ነው::የወያኔው ስርአት በፈጠረው የኢኮኖሚ ፖሊሲ ግድፈት ሕዝቦች በከፍተኛ ደረጃ በኑሮ ውድነት ከመሰቃየታቸውን አልፎ ጥቂት የባለስልጣናት እና የዘመዶቻቸው ቱጃርነት የብዙሃን ድህነት ሲንሰራፋ ሙስና የስር አቱ ዋና መገለጫ መሆኑ የአደባባይ ሃቅ ነው::የኢኮኖሚ ፖሊሲው ኑሮ ውድነትን ብቻ ሳይሆን ስራ አጥነትንም በሰፊው አንሰራፍቷል::የዚህ ስራ አጥነት የፈጠረው ችግር ትኩሱን የስራ ሃይል ወደ ሰው አገር ከመሰደዱም በላይ ከፍተኛ ብሄራዊ ውርደትን አስከትሏል::

በመላው ኢትዮጵያ መብራት፣ ውሃና ኔትወርክ የለም የለም ብቻ ሳይሆን ላለመኖሩ ሰበብ ከሚፈጥር ውጪ ችግሩን የሚፈታ መንግስት የለም::በመላው አገሪቱ በተለይ በከተሞች አከባቢ የመንግስት ሰራተኞች ተማሪዎች የግል ተቀጣሪዎች በትራንስፖርት ችግር እየተንገላቱ ነው:ለዚህም መፍትሄ የሚሆን ነገር የሚያመጣ መንግስት ስለሌለ ሕዝቡ ራሱን እያስተዳደረ መሆኑ እሙን ነው::በጉልበት የሕዝብን ስልጣት ይዞ አለቅም ያለ ፓርቲ የመልካም አስተዳደር ችግር በመፍጠሩ ሕዝብ አቤት የሚልበት እና ችግሩን የሚፈታበት ቦታ በማጣቱ ቤቱ ተቀምጧል::በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ነጻ ሚዲያዎች በነጻነት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ግማሹ ለስደት ግማሹ ለእስር ግማሹ ለሞት ግማሹ ሰርቶ እንዳይበላ ተደርጎ በአምባገነኖች ተኮላሽቷል::ተቃውዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች ይሁኑ የሲቭክ ማህበራት የበጎ አድራጎት ድርጅቶች በሚፈለገው መልኩ በነጻነት መንቀሳቀስ አልቻሉም::ይህ ሁሉ የፈጠረው የስር አቱ ፖሊሲዎች በርካቶችን ለሞት እና እስር እንዲሁም በርካታ ዜጎች ህይወታቸውን ለአደጋ በሚዳርግ መልኩ እየተሰደዱ ነው፡፡ ከዚህም በላይ ለቁጥር የሚታክቱ ምሬቶችና አቤቱታዎች ከየአቅጣጫው በየጊዜው ይሰማሉ፡፡

ያለው ስርአት በሃገር እና በሕዝብ ላይ የሚከሰቱ ችግሮችን በፍጹም እንደማይፈታ የታወቀ ነው::ከመፍታት ይልቅ በሰበብ እና በሌሎች ላይ በመላከክ ስለተጠመድ የህዝብን አቤቱታ መስማት በፍጹም ፍቃደኛ ባለመሆኑ ባለፉት 24 አመታት ባለበት ዛቢያ እየዞረ ምንም ነገር ስላለወጠ ካለ አዙሪት ለመውጣት የወያኔን የሰከረ ፖለቲካዊ ስርአት በሰበብ እና በሌሎች ላይ የሚላከኩ ጉዳቸውን አሸክሞ ከኢትዮጵያ ማስወገድ ችላ ሊባል የማይገባ ወሳኝ ወቅት ላይ ስለሆንን አፋጣኝ እርምጃዎችን በመውሰድ በሕዝባዊ አመጽ በአንድነት ስርአቱን ታግለን ልናስወግድ ግዴታ አለብን::

The post ሃያአራት አመት ጊዜ ያለወጠው አዙሪት! ከአዙሪት ለመውጣት .. (ምንሊክ ሳልሳዊ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በዓረና መድረክ የተደናገጠው ሕወሓት በትግራይ የተቃዋሚዎችን የምርጫ ፖስተሮች መቅደድ ጀምሯል

$
0
0

amdom s

amdom2

amdom
አምዶም ገብረስላሴ ከትግራይ እንደገለጸው:-

የዓረና መድረክ የእጩ ተወዳዳሪዎች ምስል የያዙ ፖስተሮች በህወሓት የወረዳ ካቢኔ ኣባላት፣ ካድሬዎች፣ ፖሊሶችና የኮብልስቶን በመስራት ላይ ያሉ ወጣቶችና በህፃናት ኣማካኝነት እየተቀደደ ነው። የምርጫ ህጉ የተወዳዳሪዎች ፖስተር መቅደድ በህግ የሚያስጠይቅና የሚያስቀጣ ቢሆንም ህወሓት ግን በህጉ ተገዢ ለመሆን ፍቃደኛ ልጦን ኣልቻለችም።

ህወሓት በተግባርዋ የህዝብ መሳቅያ ሁና ፍርሃትዋ ምን ያክልል እንደሆነ በት ዝብት ላይ ወድቃለች። ይህ የህወሓት የፖስተር ቀደዳ ተግባር ለኮረጆ ቀደዳ እንደ የኣቋም መፈተኛ ልምምድ ሊታስብ ይችላል። እነሱ የፈለጉት ህገወጥ ተግባር ሲሰሩ እኛ ደግሞ የህዝባችን ልብ ፣ ድጋፍና ማገር እያገኘን እንጎመራለን።

ዓረና መድረክ እምዲህ ያስደነገጣቸው ምክንያት በመላ ትግራይ የምርጫ ታዛቢዎች መልምሎ ኣዘጋጅቶ በማቅረቡ ነው። ለታዛቢዎቻችን የእስራት፣ የማስፈራራትና ዛቻ በኣስተዳዳሪዎች እየደረሰባቸው ነው።

የፖሊስ ስራውና ሃላፊነቱ በኣግባቡ ኣለመወጣት ምርጫው ወዳልሆነ ኣቅጣጫ እየወሰደው ይገኛል።
ነፃነታችን በእጃችን ነው

The post በዓረና መድረክ የተደናገጠው ሕወሓት በትግራይ የተቃዋሚዎችን የምርጫ ፖስተሮች መቅደድ ጀምሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪ በኤርትራ በነፃነት እየተንቀሳቀስን ነው አሉ * ተክሌ የሻው በፕሮፌሰር አስራት ስም ፋውንዴሽን ለማቋቋም ሃሳብ እንዳለ ገለጹ * አሜሪካ ዜጎቿ ምርጫውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበች * በሊቢያ ለሞቱት ሐዘን የወጣውን ሕዝብ አሳምጸዋል ተብለው የተከሰሱት ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ * አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ የሰጡት ቃለምልልስ እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የግንቦት 9 ቀን 2007 ፕሮግራም

< …በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን ያለውን ውጥረት ለማርገብና ለአገሪቱና ለሕዝቡ መፍትሄ ለመፈለግ ቢያንስ እነዚህ ስልጣን ላይ ያሉ ሰዎች በአገርና በሕዝብ ላይ የበለጠ ጉዳት ሳያመጡ የያዙትን ይዘው… አብዮት በማንኛውም ሰዓት ይነሳል የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን አሁን ሆ ብሎ አስቀድሞ ያለቀውን ምርጫ ተከትሎ … >

አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በኤርትራ ውስጥ በነጻነት ትንቀሳቀሳላችሁ ወይ ላልከው በነጻነትማ ስለምንቀሳቀስ ነው ይሄው ወጣቶች ትግሉን የሚቀላቀሉበትን ሁኔታ እያመቻቸን ያለነው….አምስት ዓመት ሙሉ ምን ስትሰሩ ነበር የተባለው ወያኔን የመሰለ ጠላት በአንድ ጊዚ ተነስቶ ሳይሆን በቂ ዝግጅት አድርጎ ነው …>

ታጋይ ተፈሪ ካሳሁን በኤርትራ የሚገኘው የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪ

የቀድሞ የመኢአድ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊን ተስፋሁን አለምነህን ጨምሮ ኤርትራ ከገቡ ሶስት ወጣት ታጋዮች ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅና ያስተላለፉት ጥሪ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ የኢትዮጵያውያን ድጋፍ የነበራቸው እውቅ የህክምና ሰው ፣የህዝብ ተቆርቋሪ አባታቸውን ግራያኒ ገሎባቸው እሳቸው በወያኔ እስር ቤት ተሰቃይተው በወቅቱ ህክምና ተከልክለው ለሞት የበቁ እንደ አቡነ ጴጥሮስ ለአገራቸው ሲሉ የተሰው ኢትዮጵያዊ ሰማዕት ናቸው …16ተኛ የሙት ዓመታቸውን ስንዘክር በስማቸው ወደፊት ፋውንዴሽን እንዲቋቋምና…>

አቶ ተክሌ የሻው የሞረሽ ወገኔ ሊቀመንበር የፕ/ር አስራት ወልደየስን 16ተኛ የሙት ዓመት መታሰቢያ ዝግጅት ያካሄዱበትን ምክንአት ለህብር በሰጡት ቃል ከገለጹት የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

የከሸፈው የብሩንዲ መፈንቅለ መንግስት እና በለውጡ አራማጆች ላይ ያመጣው ጣጣ( ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ደቡብ አፍሪካ የኢትዮጵያውያን ሱቅ ሰሞኑን በዘረኞች ጥቃት ደረሰባቸው በበኬኒያ በስደት ላይ የሚገኙ የኢትዮጵያ ነፃ ፕሬስ ጋዜጠኞች ህይወታቸው አደጋ ላይ መሆኑን ገለጹ

አሜሪካ ዜጎቿ ምርጫውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበች

ከመንገድ የታፈኑት አቶ ማሙሸት አማረ ነገ በድጋሚ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

በሊቢያ ለሞቱት ሐዘን የወጣውን ሕዝብ አሳምጸዋል ተብለው ተከሰዋል

በስልጣን ላይ ያለውን አገዛዝ በአገር ቤትም ሆነ በውጭ በጠመንጃ ብቻ ነው ማንበርከክ የሚቻለው ሲሉ ኤርትራ ለመሳሪያ ትግል የገቡ ወጣቶች ገለጹ

የብሩንዲ ፕሬዝዳንት ህዝቡ ወይ እኔን ወይ አልሸባብን ይምረጥ ሲሉ አስፈራሩ

የኢትዮጵያ በርካታ ወጣቶች ልባቸው መሸፈቱን ሮይተርስ ዘገበ

ናይጄሪያዊው አገረ ገዢ ኢትዮጵያዊት አገቡ መባላቸውን አስተባበሉ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: የአማራ ዲሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ መሪ በኤርትራ በነፃነት እየተንቀሳቀስን ነው አሉ * ተክሌ የሻው በፕሮፌሰር አስራት ስም ፋውንዴሽን ለማቋቋም ሃሳብ እንዳለ ገለጹ * አሜሪካ ዜጎቿ ምርጫውን ተከትሎ በኢትዮጵያ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ጥንቃቄ እንዲያደርጉ አሳሰበች * በሊቢያ ለሞቱት ሐዘን የወጣውን ሕዝብ አሳምጸዋል ተብለው የተከሰሱት ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ * አቶ ፈቃደ ሸዋቀና ስለወቅቱ የኢትዮጵያ ሁኔታ የሰጡት ቃለምልልስ እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

[አሳዛኝ ዜና] ዛሬም አሳዛኝ ዜና ከወደሊቢያ ተሰማ * ሁለት እናቶች ጨርቆስ አካባቢ የልጆቻቸውን የሊቢያ ሞት ተረዱ

$
0
0

cherqos
ባለፈው ጊዜ በISIS ብዙ የጨርቆስ አካባቢ ወጣቶች መስዋዕት የሆኑ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን አካባቢው ነዋሪ ከሃዘኑ ሳያገግም ሌሎች ወጣቶቻቸውን አጥተዋል።

በቅርቡ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ በሰጠመችው ጀልባ ላይ ከነበሩት ውስጥ ወደ ሰባት የሚሆኑ ወጣቶች የጨርቆስ ወጣቶች ሲሆኑ የሁለቱ 1/ አቤል ሽብሩ 2/ ቴድሮስ የተባሉ ወጣቶች ቤተሰቦች በትላንትናው ዕለት ተረድተው ቤተሰቦቻቸውና የአካባቢው ነዋሪዎች ሃዘን ተቀምጠዋል

The post [አሳዛኝ ዜና] ዛሬም አሳዛኝ ዜና ከወደሊቢያ ተሰማ * ሁለት እናቶች ጨርቆስ አካባቢ የልጆቻቸውን የሊቢያ ሞት ተረዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ነጻነት፥ ሰብአዊ መብትና፥ ዲሞክራሲ ወሳኝ ግብዓቶች ናቸዉ።

$
0
0

ግንቦት 10 ፤ 2007

Ethiopia-and-the-Horn-628x319የኢትዮጵያ ሳተላይትና ሬዲዮ ድርጅት (ኢሳት) ከምሁራንና ከሌሎች ወሳኝ አካላት ጋር በመተባበር ከግንቦት 1-2 2007 ዓ.ም. ኢትዮጵያና ምስራቅ አፍሪካ: ለዲሞክራሲ ለሰላምና ለብልጽግና የወደፊት አቅጣጫ” በሚል ርዕስ ያዘጋጀዉን የሁለት ቀን ሲምፖዝየም እጅግ በተሳካ ሁኔታ አጠናቋል። ስብሰባዉ የተለያዩ የማህበረሰብ አካላት፥ ባህሎችና፥ አመለካከቶች የተስተናገዱበት ከመሆኑን በላይ የአፍሪካ ቀንድ አሁን ያለበትን ጆግራፊያዊ፥ ሃይማኖታዊ፥ ባህላዊ፥ ኢኮኖሚያዊ ግንኙነቶችና ፍልሰቶችን ትክክለኛ ገፅታ ግንዛቤ ዉስጥ በማስገባት እጅግ የተሳሰረ መሆኑን አሳይቷል። ታሪካችን አብሮነትን ያንጸባርቃል።

ይህ በትክክለኛ ወቅት ላይ የተካሄደዉ ሲምፖዝየም ያተኮረባቸዉ ዋና ዋና ነጥቦች

  1. በሰብአዊ መብት፥ በአስተዳደር፥ በሲቢል ማህበረሰብ፥ በዘዉግ አስተሳሰብ፥ በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮች፥ በጅምላ ስደት፥ በሙስና፥ በህገወጥ የገንዘብ ሸሽት እና ዝዉዉር
  2. በ2007 የኢትዮጵያ ፓርላማ ምርጫ ገፅታ
  3. በአዲስ ፖሊሲ ቀረፃና የወደፊት አቅጣጫ የአመለካከት ለዉጥ
  4. በወደፊት እቅድና አቅጣጫ ላይ አጠቃላይ መግለጫ

የስብሰባዉ ተሳታፊዎች በመፈራረስ ላይ ያሉ ወይም የመፈራረስ አደጋ የተጋረጠባቸዉ አገሮች ላይ የሚታዩ፥ ሆን ተብለዉ ህዝባዊ አመጽ ሊፈጥሩ በሚችሉ፥ የመገንጠል አደጋ በሚያመጡ፥ አለመረጋጋትን እና አሸባሪነትን በሚያስፋፉ የግጭት ምክንያቶችንና መንስኤዎችን ላይ በዝርዝር ትንተናና ክርክር አድርገዉባቸዋል። ኢትዮጵያ በመልካም ጎኗ ለአጠቃላይ አፍሪካ ቀንድ ብሎም ለምስራቅ አፍሪካ በፖለቲካና በስትራቴጂ እጅግ ጠቃሚ አገር መሆኗን የስብሰባዉ ተሳታፊዎች ተስማምተዋል። እምቅ የተፈጥሮ ሃይሏ፥ ከሰዉ ሃብቷና እ.ኤ.አ. በ2014 ካገኘችዉ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ የዉጭ እርዳታ ጋር ተዳምሮ አካባቢዉን በማረጋጋት እና መስመር በማስያዝ በኩል ክፍተኛ ጠቅሜታ ቢኖራትም፥ በአንድ ፓርቲ የበላይነት የምትተዳደር፥ ሃይማኖታዊና የዘዉግ ቁርቋሶ የሚስተናገዱባት፥ ሃብቶቿ በሙስና የሚባክኑባት፥ የፖአቲካና ማህበራዊ መጫወቻ ሜዳዎቿ ተጠርቅሞ የዘጋባት፤ መሰረታዊ የነጻነትና ሰብአዊ መብቶቿ ያልተከበረባት፥ የህግ የበላይነት የሚጣስባት፥ እዉነተኛ መድበለ ፖለቲካ የተከለከለባት አገር በመሆኗ፥ የነበራት አቅም፥ ተሰሚነትና ሃይሏ ቀስ በቀስ እያሽቆለቆለና እየተሸረሸረ መጥቷል።

 

የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ከ1983 ዓ.ም. በፊት ጀምሮ በጉልበት ስልጣን ላይ የተቆናጠጠዉ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢህአዴግ) ህዝቡን ለማስተዳደር ብቃት እንደሌለዉና ተአማኒነትና እንዳጣ በሙሉ ድምፅ ተስማምተዋል። ኢህአዴግ ህዝቦችን የሚያቃቅሩ ማለትም ፍርሃት፥ ግብታዊነት፥ ሽብርተኝነት፥ የእርስ በእርስ ሽኩቻ የመሳሰሉ እኩይ ሁኔታዎችን በመፍጠር አገሪቷን አደጋ ላይ ከመጣሉም ባሻገር፤ ለሉአላዊነቷም ከፍተኛ አደጋ ሆኖ ተጋርጧል። እነዚህም ችግሮች አብዛኞቹ ወጣቶች በሚሆኑ በመቶ ሚሊዮን ኢትዮጵያዉያን ህይወት ላይ አስነዋሪ ጥላ ሊጥሉ የሚችሉ ናቸዉ። የሰብአዊ መብቶች ድርጅት (Human Rights Watch) በርዕሰ-አንቀጹ “ምርጫዎች፤ የኢትዮጵያ ተምሳሌትነት” በሚል ርዕስ እንዳሰፈረዉ “ካለፈዉ ምርጫ ጀምሮ ገዢዉ ፓርቲ የመሰብሰብና የንግግር መብቶች ላይ ከፍተኛ ቁጥጥር እና አፈና አድርጓል።” ገዢዉ ፓርቲ ተቃዋሚዎችንና ተፎካካሪዎችን በተፈበረከ ዉሸት በሽብርተኝነት ይከሳል፥ ይደበደባል፥ ያስራል፥ ወይም አገር ጥለዉ እንዲሰደዱ ያደርጋል። ኢህአዴግ እ.ኤ.አ. በ2014 ብቻ ከሰላሳ በላይ ጋዜጠኞች አገር ጥለዉ እንዲወጡ አድርጓል፤ በቁጥር ያልተገለጹ ተቃዋሚዎችን በማሰር ያለፍትህ እንዲማቅቁ አድርጓል። የፍትህ ስርዓቱ የፖለቲካ ወገንተኝነት ሌላዉ እራስ ምታት ነዉ። እ.ኤ.አ. በ2009 የወጣዉ ፀረአክራሪነት ህግና የመያዶ ድርጅቶችን አዋጅ የሲቢል ማህበራት በመንግስት ላይ ተቃዉሞ ሊያሰሙ በሚችሉ ድርጅቶች ላይ የተቃጣ ስለት ሆኗል።

ሲምፖዚያሙ በቅርቡ የሚደረገዉ ምርጫ ካለፉት ምርጫዎች የተለየ እንዳልሆነና፤ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት (Human Rights Watch) እንዳለዉ በግንቦት 2007 ዓ.ም. ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲዎች በነጻነትና በአግባቡ መንቀሳቀስ እጅግ ከባድ ፈተና ሆኖባቸዋል። አንድ ኢትዮጵያዊ አክቲቪስት፥ በኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉን አስፈሪ ድባብ እና ጭቆናን አስመልክቶ ለሰብአዊ መብቶች ድርጅት “ባደባባይ ሰልፍ ብንወጣ እንታሰራለን፤ ስለፖሊሲ መቀየር ቢሮያቸዉ ሄደን ብንጠይቅ “አሸባሪ” እንባላለን፥ በፍርድ ቤት ብንከስ ነጻነት የለንም፤ ዘብጥያ እንወርዳለን። ስለዚህ ምን ማድረግ ይሻለናል?” ሲል ምሬቱን ገልጿል። ዘጋርዲያን የተባለዉ ጋዜጣ “ኦርዌሊያን” ብሎ በሰየመዉ አይነት ኢትዮጵያ በአንድ ፓርቲ ቁጥጥር በጭካኔ የምትመራ አገር ሆናለች። የኢትዮጵያ መንግስት በየአመቱ በመቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ አንድ ለአምስት (1፡5) ለተባለ የአፈና አደረጃጀትና ለስለላ መዋቅሩ ያባክናል። አንድ ለአምስት የተባለዉ የአፈና አደረጃጀት፥ አንድ ሰዉ የሌሎችን 5 ሰዎች ውሎ (ሰዎቹ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያላቸዉን ግንኙነት፤ ህብረትና፥ እንቅስቃሴ) ቀን በቀን እየተከታተለ ለበላይ ሃላፊዎች ሪፖርት የሚያደርግበት መዋቅር ነዉ። የገዢዉ ፓርቲ ጠላት ተብሎ የተፈረጀ ወይም የተጠረጠረ ግለሰብ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ ይታሰራል፥ ይደበደባል፥ ይንገላታል። ስልክ ኢንተርኔት ማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ቁጥጥር ይደረግባቸዋል፤ ከኢትዮጵያ ዉጭ የየትኛዉም ሚዲያ በአገር ዉስጥ እንዲሰራጭ አይፈቀድም። አፈናዉ መበርታት ለአመጽና ለሽብርተኝነት በር ይከፍታል።

ሲምፖዚየሙ ሂዉማን ራይትስ ዎች በቅርቡ በኢትዮጵያ ፓርላሜንታዊ ምርጫ ላይ ያቀረበዉን ግምገማ እጅጉን ያደንቃል። በቅርቡ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር የፖለቲካ ጉዳዮች የበታች ሃላፊ የሆኑት ዊንዲ ሸርማን “ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አገር ናት። የሚቀጥለዉ ምርጫ ነጻ፥ ፍትሃዊ፥ ታማኝ፥ ግልፅና፥ አሳታፊ ይሆናል” የሚል የተሳሳተ አስተያየት ሰጥተዉ ነበር። ሂዉማን ራይትስ ዎች ከዋሽንግተን ፖስት ጋር ተቀራራቢ የሆነ ርዕሰ አንቀጽ እ.ኤ.አ. በግንቦት 1 2015 “ማስመሰል እንደኢትዮጵያ” በሚለዉ ሓተታዉ “በኢትዮጵያ ዉስጥ የሚደረገዉ ጭቆና ዋሽንግተ ማዉገዝ እንጂ ማድነቅ አይገባትም” በማለት የሃላፊዋን አስተያየት ኮንኗል። ፍሪደም ሃዉስ፥ ሂዉማን ራይትስ ዎች፥ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፥ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ፕሮጄክት፥ የጋዜጠኞች ተከላካይ ድርጅት፥ ኢንተርናሽናል ሪቨርስ እና ኢትዮጵያዉያን ዊንዲ ሸርማን ንግግራቸዉን እንዲያስተባብሉ ለአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ የተቃዉሞ ደብዳቤ ፅፈዋል። የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ከላይ ከተገለጸዉ ርዕሰ አንቀጽ ጋር በመስማማት ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ አገር ለመሆኗ ምንም በመረጃ የተደገፈ ነገር አለመኖሩን አስምረዉበታል። በተቃራኒዉ የኢትዮጵያ መንግስት ተስፋ የሚያስቆርጥና ፍርሃት የነገሰበት አፋኝ ስርዓትን በመፍጠር በቋፍ ላይ ያለችዉን አገር ወደባሰ አዘቅት ዉስጥ እየገፋት ይገኛል። በኢትዮጵያ ዉስጥ ሰፍኗል የተባለዉ የዉሸት ሰላምና መረጋጋት በጉልበትና በአፈና ላይ የተመሰረተ ነዉ።

ይሁን እንጂ የአንድ አገር አለመረጋጋት ወደመበታተን ሊመራ እንደሚችል የሲምፖዚየሙ ተሳታፊዎች ያምናሉ። ጭቆናዉና አፈናዉም ወደማያባራ የእርስ በእርስ ህዝባዊ አመጽና ጦርነት ሊሸጋገር ይችላል። ይህ ድርጊት ሊቆም የሚችለዉም የምራባዊያን ዲሞክራሲያዊ አገራት በተለይም አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የዲሞክራሲ እሴቶችንና፥ የህግ የበላይነትን እንዲያከብር የተፅእኖ ሃይላቸዉን ማሳረፍ ሲችሉ ብቻ ነዉ። ኢትዮጵያ እና ኢትዮጵያዉን ከገጠማቸዉ አስከፊ ሁኔታዎች አንጻር ሲምፖዚየሙ የሚቀጥሉትን ዉሳኔዎች በማስተላልፍ የመትሄ ሃሳቦችን አስቀምጧል።

  • ክርስቲያ ወንድሞቻችን በአይኤስ በግፍ መታረዳቸዉን፥ ህግ አክባሪ ኢትዮጵያዉያን በደቡብ አፍሪካ መገደላቸዉን፥ በየመን ኢትዮጵያዉናንና ሌሎች በአየር የመደብደባቸዉን ድርጊት እናወግዛለን፤ የኢትዮጵያን መንግስትም ህዝብን ያማከለ አሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርግ የስራ ፈጠራ እድገት መርሃ ግብር እንዲያወጣ እንጠይቃለን።
  • በኢትዮጵያ ያሉ ሁሉም ተቃዋሚዎች፥ የሲቪል፥ ፕሮፌሽናልና የሃይማኖት ድርጅቶች፥ የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ቡድኖች፥ አክቲቪስቶችና ምሁራን አንድነትን በብዘሃነት መነጽር እንዲያዩትና እንዲደግፉ፥ ለአንድ አላማ አብሮ ለመስራት ቆርጠዉ እንዲነሱና አማራጭ ሃሳቦች የሚንሸራሸሩባት፥ ዲሞክራሲያዊነት የጎለበተባት፥ ሁሉን አቀፍ የሆነች ኢትዮጵያን ለመፍጠር እንዲረባረቡ እንጠይቃለን።
  • ሁላችንም የተገነዘብነዉ ነገር የኢትዮጵያ ህዝብ፥ አፍሪካ ቀንድና የምራባዉያን አገሮች በዘላቂነት የሰብአዊ መብት እንዲከበር፥ ነጻነት እንዲኖር፥ ተጠያቂነትና አሳታፊነት እንዲጎለብት ይፈልጋሉ፤ ለዚህም ይታገላሉ። በመሆኑም የአሜሪካ መንግስት ትርጉም ያለዉ ለዉጥ ለማምጣት በኢትዮጵያ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ በማሳደር የፖለቲካ ምህዳር እንዲሰፋ፥ ብሄራዊ እርቅ እንዲደረግና፥ ሁሉም አካላት የስልጣን ተካፋይ እንዲሆኑ በማመቻቸት ችግሮቹ ከመባባሳቸዉ በፊት አወያይቶ ሊፈታ ይገባል።
  • የአሜሪካ መንግስትን በኢትዮጵያ መንግስት ላይ የሚያወጣቸው የማስመሰል መግለጫዎችና የተለሳለሱ አቋሞች ወይም አቀራረቦች እንደማይሰሩ እንዲረዳልን እንፈልጋለን። አሜሪካ ሚዲያን፥ ፖለቲካ ፓርቲዎችንና ተቃዋሚዎችን ለሚያፍነዉ መንግስት ትርጉም ያለዉ ለዉጥ እስካልመጣ ድረስ ድጋፏን እንድታቆም እንጠይቃለን።
  • አለም አቀፍ ማህበረሰብ አባላት በተለይም ምዕራባውያን ለጋሽ አገራት፥ መንግስታትና የዉጭ ኢንቨስተሮች ኢትዮጵያ ሚሊዮኖችን ከስራ ዉጭ ያደረገች፥ ኢፍትሃዊነት እንዲነግስባት የተደረገች፥ ሁሉንም ቡድኖች ያላማከለ የአስተዳደር ችግር ያለባት አገር መሆኗን እንዲገነዘቡ እንፈልጋለን። በቅርቡ በአይስ (ISIS) የተደረገዉ የጅምላ ግድያ ኢትዮጵያ ዉስጥ አለ የተባለዉ እድገት የተጣመመ ለመሆኑ አመላካች ነዉ። ኢትዮጵያዉያን ወጣቶች በዉጭ አገር ስራ ለማግኘት ሲሉ ህይወታቸዉን ለአደጋ በመስጠት ለህገወጥ የሰዉ አዘዋዋሪዎች ገንዘብ ይከፍላሉ። የኢትዮጵያ መንግስት ወደ 400 ገደማ የሚጠጉ በሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ የሚያጋብሱ የህገወጥ ሰዉ አዘዋዋሪ ደላሎችንና ድርጅቶችን እንዲዘጋና የወጣቶች የስራ ፈጠራ ፕሮግራሞችን በአስቸኳይ እንዲነድፍ እንጠይቃለን።
  • የኢትዮጵያ መንግስት ሁሉንም የፖለቲካ እስረኞች ያለምንም ቅድመሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈታ፤ የፀረሽብርተኝነትና የመያዶ ህጎችን እንዲሽራቸዉ እንጠይቃለን።
  • የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ከፍተኛ ኮሚሽነር፥ የቀይ መስቀልና የቀይ ጨረቃ ማህበራት ወደኢትዮጵያ ቢመለሱ ችግር ለሚደርስባቸው በሊቢያና በየመን ዉስጥ በችግር ለሚሰቃዩ የኢትዮጵያ ስደተኛ ወገኖች ከለላ እንዲሰጣቸዉ በአሜሪካና በሌሎች አገሮች ጥገኝነት እንዲያገኙ እንዲያመቻችላቸዉ ስንል እንጠይቃለን። የምራባዉያን መንግስታት፥ ጃፓን እና ሃብታም አገሮች ለኢንተርናሽናል ኦርጋናይዜሽን ፎር ማይግሬሽንና (IOM) ለሌሎች ድርጅቶች ለስደተኞች ግልጋሎት የሚዉል ገንዘብ እንዲለግሱ እንጠይቃለን።
  • የአሜሪካ የኮንግሬስ አባላት የሰብአዊ መብት ጥበቃ፥ የህግ የበላይነትና ዲሞክራሲን ያግዛል የተባለለትን የ2007 የዲሞክራሲና ተጠያቂነት ረቂቅ ህግ እንደገና እንዲያንሸራሽር በጥብቅ እንጠይቃለን። ኢትዮጵያዉያን ነጻነት፥ ክብር፥ የሰብአዊ መብት ከለላ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ከመቼዉም ጊዜ በላይ እንደሚያስፈልጋቸዉ እናምናለን።

 

የስብሰባዉ አዘጋጅ ኮሚቴ የተሰብሳቢዎቹን ቀልብ የሳቡ ርዕሶችን በጊዜ እጥረት ምክንያት በበቂ ሁኔታ ሳያወያይባቸዉና ሳይሸፍናቸዉ ቀርቷል። ለወደፊቱ ግን በእነዚህ ርእሶች ላይ በጥልቀት እንድወያይ መድረኮችን ያመቻቻል።  ከርዕሶቹ በጥቂቱ

  1. የኢትዮ ኤርትራ ግንኙነት
  2. ዕርቅና ሰላም በአፍሪካ ቀንድ
  3. አዲሱ ሚዲያ (ፌስቡክ፥ ትዊተር፥ ዩቲዩብ፥ ወዘተ) በመንግስት፥ በዲሞክራሲ፥ እና በሰብአዊ መብት ግንዛቤ ዙሪያ ላይ ላይ ያለዉ ሚና
  4. ተቀራራቢነት ያላቸዉ ሌሎች ሃሳቦችም ይስተናገዳሉ።

 

Contact information:

 

ጥያቄ ካለዎት  ኢሜይል ethio-horn@ethsat.com ሊያገኙን ይችላሉ። በስልክም እንዲሁ በ571- 335-4964 ይደዉሉልን።

 

The post ለኢትዮጵያና ለአፍሪካ ቀንድ ነጻነት፥ ሰብአዊ መብትና፥ ዲሞክራሲ ወሳኝ ግብዓቶች ናቸዉ። appeared first on Zehabesha Amharic.

አንድ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ተገደለ

$
0
0

Zehabesha News
ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖረው የ25 ዓመቱ ሲሳይ ተሾመ በቅጽል ስሙ ገብሬ ያለፉትን 8 ዓመታት በቃሊቲና በዝዋይ እስር ቤቶች እየተመላለሰ አሳልፏል።
በተለይ ወደ ዝዋይ እስር ቤት ከተላለፈ በሁዋላ ፣ ሃጎስ የተባለው የእስር ቤቱ ሃላፊ ” አንተ የነፍጠኛ ልጅ እንበቀለሃለን፣ በእኔ እጅ ነው የምትሞተው” እያሉ ይደበድቡትና ይዝቱበት ነበር። ባለፈው ቅዳሜ እናቱ ሊጠይቁት ሲሄዱ፣ ታሞ ሚኒሊክ መወሰዱን ይነግሩዋቸዋል። ወደ ሚኒሊክ ሲሄዱ፣ በአንድ አምቡላንስ ውስጥ ጎንና ጎኑ በኤሌክትሪክ ተጠብሶ፣ ኩላሊቱ አካባቢ ተረጋግጦና በልዞ፣ አናቱ አካባቢ ያረፈበት ድብደባ ፊቱን ለማየት በማይቻል ሁኔታ በደም እንዲሸፈን
አድርጎታል።
የደረሰበትን ጉዳት ለመግለጽ ይዘገንናል የሚሉት ቤተሰቦቹ፣ ፖሊሶች አንዴ ታሟል፣ ሌላ ጊዜ ጉዳዩ በአቃቢህግ ተይዟል በማለት ለመደናገር እየሞከሩ ነው። የ22 አካባቢ ወጣቶች የሟቹ ቲሸርት ያለበትን ፎቶ እያሳተሙ ነው። ፖሊሶችና ደህንነቶች በድንካኑ አካባቢ እየተዘዋወሩ በመቆጣጠር ላይ ናቸው። የሟች የቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደን እያሉ ነው ።

The post አንድ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ተገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.


ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ላይ ንብን እየለጠፉ ለመራጩ እያደሉ ነው

$
0
0


EPRDF
በጋሞጎፋ ዞን ቁጫና ቦርዳ ወረዳዎች የደኢህዴን/ኢህአዴግ ካድሬዎች የህዝቡን ካርድ እየተቀበሉ የምርጫ ካርዱ ላይ የንብን ምልክት በስቴፕለር በማያያዝ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሚገኙ በጋጎፋ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪ አቶ ወንድሙ መኩሪያ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ካድሬዎቹ ህዝቡን 1ለ5 በማደራጀት የንብ ምልክት የተለጠፈበት ካርድ በማደል ‹‹የምትመርጡት ኢህአዴግን ነው›› እያሉ እያስገደዱ እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

የዞኑ፣ የወረዳውና የየ ምርጫ ክልሉ ምርጫ አስፈጻሚዎች ካድሬዎቹ የንብ ምክትን የምርጫ ካርዱ ላይ እያያያዙ ኢህአዴግን እንዲመርጡ እያስገደዱ መሆኑን ቢያውቁም ምንም እርምጃ እየወሰዱ አይደለም ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በጋሞጎፋ ዞን ቦረዳ ወረዳ ሰማያዊ ፓርቲ እሁድና ቅዳሜን ‹‹የገበያ ቀን ስለሆነ›› በሚል ቅስቀሳ እንዳያደርግ መከልከሉን አስተባባሪው ገልጸዋል፡፡ ‹‹የምርጫ ህጉ የሚለው ቅስቀሳ መደረግ ያለበት ከገበያ 500 ሜትር ርቆ ነው እንጅ በገበያ ቀን ቅስቀሳ አይደረግም አይልም፡፡ እኛን ግን ገበያ በሌለባቸው ቦታዎች ሁሉ እሁድና ቅዳሜ ቅስቀሳ እንዳናደርግ ከልክለውናል›› ብለዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ቅስቀሳ እንዳያደርግ እየከለከሉ የሚገኙት የቦረዳ ወረዳ የፀጥታ አስተዳደር ኃላፊ አቶ ማርካ ማዶ እና የወረዳው ፖሊስ አዛዥ መቶ አለቃ ታምራት ናቸው ብለዋል፡፡

The post ካድሬዎች የምርጫ ካርድ ላይ ንብን እየለጠፉ ለመራጩ እያደሉ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ጆሲ ኢንዘሓውስ ሾው ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ጻፈ “ከግንቦት 30 ጀምሮ በእናንተ አስገዳጅነት ፕሮግራማችንን እናቋርጣለን”

$
0
0

jose in ze house1
ጆሲ እንዘሓውስ ሾው ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን በላከው ግልጽ ደብዳቤ በቴሌቪዥን ጣቢያው አስገዳጅነት ፕሮግራሙን ከግንቦት 30 ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ:: ሙሉ ደብዳቤውን ያንብቡት::

ጉዳዩ፡ፕሮግራም ስለማቋረጥ

ድርጅታችን ከጣቢያችሁ የአንድ ሰዓት የስርጭት ጊዜ በመውሰድ በ ኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላለፉት ሁለት ዓመታት “ጆሲ ኢን ዘ ሃውስ ሾው ” የተሰኘ ፕሮግራም እያቀረበ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡ ፕሮግራሞቻችን ሀገራዊ ፋይዳ ያላቸው፤ ትውልድን የሚያንጹና የሚያስተምሩ በመሆናቸው በአጭር ጊዜ ውስጥ በተመልካች ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነት ለማግኘት የቻሉ እንደሆነ አያጠራጥርም፡፡ቀደም ባለው ጊዜ በተፈቀደልን የአየር ሰዓት የሠራናቸውን ፕሮግራሞች ለማቅረብ የነበሩት ሁኔታዎች የተመቻቹ ቢሆንም ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን አየር ላይ እንዲውሉ ከላክናቸው ፕሮግራሞች አንዳንዶቹ በተፈቀደልን የአየር ሰዓትና ጊዜ እንዳይተላለፉ ተደርገዋል፡፡

ጆሲ መልቲሚዲያ የሚያዘጋጃቸው ፕሮግራሞች የአየር ሰዓት ለመሸፈን ብቻ ተብለው የሚዘጋጁ ሳይሆን እያዝናኑ የሚያስተምሩ ኢትዮጽያዊ አንድነትን የሚያጠነክሩ ፤የትላንትን ታሪክ የሚያውሱና ትውልድ የሚቀርጹ፤ መረዳዳትንና መተጋገዝን የሚሰብኩ ናቸው ፡፡

በአብዘኛው የአፍሪካ ሀገራት በቅኝ አገዛዝ መዳፍ ውስጥ በነበሩት ወቅት ሀገራችን ኢትዮጵያ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም የጣልያንን ወራሪ ጦር ያሸነፈችበት የአድዋ ድል 119ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በድሉ እንደሚኮራ እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ በያገባኛል ስሜት ደክመን የሠራነው የአድዋ ድል መታሰቢያ ፕሮግራም በተፈቀደልን ቀንና የአየር ሰዓት እሁድ የካቲት 29 ቀን 2007 ዓ.ም ከሁለት ሰዓት እስከ ሶስት ሰአት እንዳይተላለፍ ተደረጎብናል ፡፡ይህ ያልተለመደ ነገር ሲከሰት ብናዝንም ቀደም ሲል የነበረንን መልካም የሥራ ግኑኙነት ከግምት ውስጥ በማስገባትና ወደፊትም እንደማይደገም በማመን ነገሩን በትዕግስት አልፈን አብረን ለመስራት ሞክረን ነበር፡፡

ይህ መፈጠሩ እያሳዘነን እያለ ሌላ ነገር ተከሰተ፡፡ ድርጅታችን በጣቢያቸሁ ፕሮግራም ማስተላለፍ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ በሀይማኖታዊና በዘመን መለወጫ በዓላት ላይ በተለያየ ጊዜና ሙያ ሀገራቸውን ያገለገሉ ግን ደግሞ የተዘነጉ የሀገር ባለውለታዎችን መጠየቅና የተቻለውን ያህል ድጋፍ ማድረግ የተለመደ ነበር፡፡በእዚህም መሰረት የ2007 ዓ.ም የትንሣኤን በዓልን ምክንያት በማድረግ ያዘጋጀነው ፕሮግራም በቂና አሳማኝ ባልሆነ ምክንያት እንዳይተላለፍ ተደርጎብናል፡፡
jossy gebre
ፕሮግራማችን በተደጋጋሚ በተለመደው የአየር ሰዓት እንዳይተላለፍ መደረጉ እያሳዘነን እያለ ፤በየመን ፤በደቡብ አፍሪካ በተለይም በሊቢያ አይ.ኤስ የተባለው ፅንፈኛ ቡድን በንጹሃን ዜጎቻችን ላይ ያደረሰውን ጥቃት ተከትሎ እንደ ኢትዮጵያዊ አዝነን ፤ቤተሰቦቻቸውን እና ዘመዶቻቸውን በሞት ከተነጠቁ ሀዘንተኞች ጎን ሆነን ሀዘናችን ገልጸንና የሀዘናቸው ተካፋይ ሆነን ድጋፍም አድርገን በተጨማሪም በኢትዮጵያዊ አንድነት ፤በሀይማኖት እኩልነት ፤ተፈቃቅሮ ፤ተቻችሎና ተከባብሮ በመኖር፤ እርስ በእርስ በመረዳዳት እንዲሁም ዜጎቻችንን ለእንግልትና ለሕልፈተ ሕይወት እየዳረገ ባለው ሕገ ወጥ ስደትና ሕገ ወጥ ደላሎች ዙሪያ ደክመን የሰራነው አስተማሪ ፕሮግራም ከጣቢያው በወሰድነው የአየር ሰዓት ላይ በተደጋጋሚ እንዳይተላለፍ መደረጉ ወደፊት አብሮ የመስራታችንን ነገር በጥርጣሬ እንድንመለከተው አድርጎናል ፡፡

ፕሮግራማችን በጣቢያችሁ ላይ መቅረብ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ለነበረን መልካም ግንኙነት ከልብ እናመሰግናለን፡፡ ከላይ ከጠቀስናቸው ችግሮች በተጨማሪ ሌሎችም ምክንያቶች ቢኖሩም የስራ ግኑኝነታችን እንዲቀጥል ስምምነት ለማድረግ ብንሞክርም አልተሳካም ፡፡ በእናንተ በኩል እየተከናወነ ያለው ያልተለመደ ተግባር የስራ ግኑኝነታችን እንዲቋረጥ ከፍተኛ ፍላጎት ያለ እንደሆነ እንድናምን ስላደረገን በእኛም በኩል ይህንን በአጽንኦት እንድንመለከተው አስገድዶናል፡፡

ከእዚህ በተጨማሪ ውል ተፈራርመን መስራት ሲገባን በድርጅታቸሁ አሰራር መሰረት ያለፈውን አንድ ዓመት ያለ ውል መስራታችን ይታወቃል ፡፡ ከአሁን በኋላ ግን በእዚህ አሰራር መቀጠል አንችልም ፡፡ ስለሆነም ከስፖንሰሮቻችን ጋር እስከ ሲዝን 4 የመጨረሻ 13ኛ ክፍል ድረስ የተደረገውን ውል ከግምት ውስጥ በማስገባት እስከ ግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ ፕሮግራማችን በጣቢያቸሁ እንዲተላለፍ በእኛ በኩል አስቀድመን ዝግጅታችንን የጨረስን መሆናችንን እያሳወቅን፤ ከግንቦት 30 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በጣቢያቸሁ ሲተላለፍ የነበረው “ጆሲ ኢን ዘ ሃውስ ሾው” የተሰኘው ፕሮግራማችን በእናተው አስገዳጅነትና ተገቢ ያልሆነ አሰራር እንደምናቋርጥ አስቀድመን እናሳውቃለን ፡፡
ከሰላምታጋር

The post ጆሲ ኢንዘሓውስ ሾው ለኢቢኤስ ቴሌቪዥን ማስጠንቀቂያ ጻፈ “ከግንቦት 30 ጀምሮ በእናንተ አስገዳጅነት ፕሮግራማችንን እናቋርጣለን” appeared first on Zehabesha Amharic.

የህወሓት አየር ኃይል ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ

$
0
0

ethiopian airforce
ምኒልክ ሳልሳዊ ዘንደዘገበው

የህወሓት አየር ኃይል ለሰላም ማስከበር ተልዕኮ ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ፡፡በበረራ፣ ጥገና፣ ድጋፍ ሰጪ፣ ዘመቻና አስተዳደር ከ200 በላይ አባላቱን በከፍተኛ ወጪ ለ6 ወራት ሲያሰለጥን የባጀው አየር ኃይል የሰላም ማስከበሩ ተልዕኮ ወደሚከናወንበት ደቡብ ሱዳን ሊጓዙ የተመረጡት መንገደኞች ከየአየር ምድቦቻቸው ተነስተው ደብረ ዘይት ከከተቱ በኋላ ጉዞው ድንገት ተዘርዟል፡፡

ጉዞው የተሰረዘባቸው ምክንያቶች በአባላትና አባላት፣ በአባላትና አመራሮች እንዲሁመም በአመራሮችና አመራሮች መካከል አለመተማመን በመስፈኑ፤ ያለመጠን ስር ሰዶ የተንሰራፋው ጎሰኝነት ተባብሶ በትግርኛ ተናጋሪ የህወሓት ሰዎች መካከልም ውቅሮና አዲግራት ወደሚሉ የመንደር ቡድንተኝነት ቁልቁለቶች በመውረዱ፤ ልክ እንደከዚህ ቀደሙ አሁንም አብራሪዎች ተዋጊ ሄሊኮፕተሮችን ይዘው ሊኮበልሉ ይችላሉ ከሚል ስጋት በመነጨ፣ ከፍተኛ በሆነ የአቅም ማነስ ችግር፤ ከምርጫው ጋር በተያያዘና ብረት ያነሱ የነፃነት ኃይሎች ጦርነት ይከፍታሉ ተብሎ በመሰጋቱ የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡

በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው አየር ኃይል ከዚህ በፊት በ2005 ዓ.ም በብቃት ማነስ ምክንያት ከዳርፉር ተባሮ የሰላም ማስከበር ተልዕኮውን ሳያሳካ ጓዙን ጠቅልሎ ውርደት በመከናነብ መመለሱ አይዘነጋም፡፡

The post የህወሓት አየር ኃይል ወደ ደቡብ ሱዳን የሚያደርገው ጉዞ መሰረዙ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘው ኢትዮጵያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ሊፈጸም ነው

$
0
0

abyu tekestebirhan
አብዩ ተከሥተብርሃን ይባላል:: ኤፕሪል 16 (ሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም) ከሥራ ውሎ ከተመለሰ በኋላ ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ስለቀረ ምን እንደደረሰበት ሳይታወቅ ሲፈለግ ሰንብቶ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ እንደተገኘ ቤተሰቦቹ ለቀብር ካዘጋጁት በራሪ ወረቀት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: መረጃው እንደሚለው ይህ ወጣት ኢትዮጵያዊ በሚኒሶታ እንዴት እንደሞተ ፖሊስ እያጣራ ያለበት ሁኔታ ሲሆን የቀብር ስነስርዓቱም የፊታችን ሜይ 22 (ግንቦት 20 ቀን 2007) ይፈጸማል::

በሚኒሶታና አካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በአሳዛኝ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘውን ወጣት ወንድማችን ቀብር ስነሥርዓት ላይ እንድትገኙ ጥሪ ቀርቦላችኋል::

ሜይ 22 በሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 12:15 ጀምሮ የፍትሃት ስነስር ዓት የሚደረግ ሲሆን 2:45 ላይ ደግሞ በሜንዶታ ሃይትስ የመቃብር ሥፍራ ሥር ዓተ ቀብሩ ይፈጸማል:: አድራሻውም 2101 Lexington Ave S, Mendota Heights, MN 55120. ነው::

The post በሚኒሶታ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘው ኢትዮጵያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ሊፈጸም ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ኦፌኮ መድረክ የምርጫ ቅስቀሳ በጉጂ ዞን – (ይናገራል ፎቶ)

$
0
0

መድረክ በዘንድሮው ምርጫ የተሳካ የምርጫ ቅስቀሳዎችን በተለያዩ ከተሞች እያደረገ ነው:: ለድጋፍ የሚወጣውም ሕዝብ ቁጥርም በጣም ብዙ በመሆኑ የዶ/ር መረራን ንግግር መጥቀስ ያስፈልጋል:: “ኢህአዴግ ሁለት ምርኩዝ አሉት። ምርጫ ቦርድ እና ጠመንጃ ። ሁለቱን ምርኩዞች አስቀምጦ ተወዳድሮ ካሽነፈ 100 አመት እንዲገዛ ፈርምለታለው”

ከታች በፎቶ ግራፎች የምትመለከቱት የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ/ መድረክ በጉጂ ዞን በቡሌ ሆራ ያደረገው የምርጫ ቅስቀሳ ነው:: ይህ ደማቅ የምርጫ ቅስቀሳ የተመራው በቅርቡ በሰሜን አሜሪካ ከደጋፊዎቻቸው ጋር በተገናኙት በቀለ ነጊያ ነው::

ኦሕዴድ/ኢሕአዴግ ኮሮጆውን ሰርቆ ለመሙላት እንዲዘጋጅ ያደረገው ይህ ታላቅ ቅስቀሳን በፎቶ ይመልከቱ::
guji

Guji 2

Guji 3

guji 4

The post ኦፌኮ መድረክ የምርጫ ቅስቀሳ በጉጂ ዞን – (ይናገራል ፎቶ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>