Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

በሊቢያ ከተሰውት መካከል አያልቅበት ስንታየሁ –“እናቴን አደራ”

Next: Hiber Radio: ቻይና ለኢትዮጵያው አገዛዝ የጦር መሳሪያ ማስታጠቋን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ደርሼበታለሁ አለ *የመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ዜጎችን ከመመለስ ይልቅ የውስጥ የቪዛ ንግድ ላይ አተኩሯል ይላሉ * የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ተቃዋሚዎቻቸውን ላለማስታጠቅ ለመስማማት ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ተዘገበ * የኢትዮጵያ መንግስት በእስራኤል መብታቸው የተነካ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች ጉዳይ ያሳስበኛል ማለቱን ብዙዎች አጣጣሉት * ኢትዮጵያዊው የታሪክ ተራኪ ኤድዋርዶ ባይሮኖ የሰጠው ቃለምምልስ እና ሌሎችም..
$
0
0

shumete

(ያሬድ ሹመቴ)

አያልቅበት ስንታየሁ ሱዳን ውስጥ ለ3 ዓመት ያህል የኖረ የብርሀኑ ጌታነህ ወዳጅ ነው። የሚናፍቃቸውን እና ያላባት ብቻቸውን ያሳደጉትን፤ ለስደቱ ምክንያት የሆኑትን እናቱን ለማየት የዛሬ ዓመት ገደማ ወደ ሀገሩ ተመለሰ።

ሱዳን በነበረበት ወቅት ከራሱ ተርፎ እናቱን ለመርዳት የሚልካት ጥቂት ገንዘብ በስተርጅናቸው ሰው ቤት ተቀጥረው የጉልበት ስራ ከመስራት አላዳናቸውም።

ወይዘሮ አለሚቱ በላይነህ ልጃቸው ሱዳን ሳለ የሚልክላቸው ገንዘብ ከቤት ክራይ ክፍያ ውጪ የማይሸፍንላቸው ቢሆንም፤ ችግራቸውን ለልጃቸው ነግረው ከማሳቀቅ፤ በስተርጅናቸው የጉልበት ስራ ውስጥ ገብተው ኑሮዋቸውን በመከራ ተያይዘው ቆዪ።

የእናቱ ነገር የማይሆንለት አያልቅበት፤ በናፍቆቱ ምክንያት ወደ ሀገሩ ሲመለስ ግን ሱዳን እያለ ይልክ የነበረው ገንዘብ ምን ያህል የእናቱን ህይወት ፈቅ ማድረግ እንደተሳነው ተረዳ።

የዚያን ጊዜ ታድያ ከሱዳን አድማስ ማዶ፤ እናቱን ለመጦር ይችልበት ዘንድ ተስፋ የጣለበትን የባህር ላይ ጉዞ ህልም ሰነቀ።

ለልጆቹ ህይወት በእጅጉ ከሚጨነቀው የረዥም ጊዜ ወዳጁ ብርሀኑ ጌታሁን ጋርም ሀሳባቸው ገጠመ። ወደ ሊቢያም በጋራ ሊሻገሩ ተቃጠሩ። ልጆችን ለማሳደግና እናትን ለመጦር።

አያልቅበት በሀምሌ 5፣ 2006 ዓ.ም ወደ ሱዳን ለመመለስ በሚሸኝበት ጊዜ፤ ከዚህ ቀደም በሰላም ደርሶ የተመለሰው ልጃቸው ተመልሶ የሚመጣው መርዶው መሆኑን ፈፅሞውኑ ባይገቱም ካይናቸው ልጃቸው ከሚርቅ በርሀብ ቀድመውት ቢሞቱ መርጠው ነበር።

የብርሀኑ እና አያልቅበት ቀጠሮ ቀን ሲደርስ፤ ብርሀኑ ሚስቱን “ድሬዳዋ ለስራ መሄዴ ነው፤ ስልኬ ግን አይሰራም” ብሎ ሀገሩን ለቆ ወደ ሱዳን አመራ።

በተቀጣጠሩ በስድስት ወራቸው ሱዳን ላይ የተገናኙት እኒህ የልብ ወዳጆች፤ አንዳቸው ስለ ልጅ አንዳቸው ስለ እናት ፍቅር ምስክር ሆነው። ልጆቹን ለናታቸው አደራ ሰጥቶ የተሰደደው፤ ለእናት የሚሰጥ ፍቅር ሀያልነት በአያልቅበት ሲማር፤ ለልጆቹ ሲል የተሰደደው ብርሀኑ ደግሞ በተራው የአባት ፍቅር ምሳሌው ነበር።
yared shumete

ወይዘሮ አለሚቱ፤ አያልቅበት ከሄደ በጝላም ቢሆን የዘወትር ፀሎታቸው የሚወዱት ልጃቸው መንከራተት በቅቶት ከእቅፋቸው ዳግም እንዲገባ ነበር።

የሀገራችን ሰማይ ጠቁሮ፤ ኢትዮጵያም አምርራ በልጆችዎ የግፍ ሞት ስታለቅስ፤ እንደ ብርሀኑ ባለቤት ብርቱካን እና መላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ የአያልቅበት እናትም እንባቸውን ይዘረግፉት ነበር። ሊቢያ የማን ሀገር ጎረቤት እንደሆነች እንክዋን የማያውቁት እናት እንዲሁ በደፈናው ልጆቼ ለሚልዋቸው የኢትዮጵያ ሰማዕታት ሁሉ ያነቡ ነበር።

ከሚወደው ወዳጁ ብርሀኑ ጎን በሊቢያ በርሀ አንገቱን ለሰይፍ የሰጠው አያልቅበት ሰማዕትነቱ የተሰማው ዘግይቶ የሁሉም ቤት ሀዘን በመብረድ ላይ ሳለ ነበር።

የእኒህን እናት አይን ለማየት በውነቱ ማን ይደፍር ይሆን? የሀዘናቸውንስ ጥልቀት ምን ይገልፀው ይሆን? በምንስ አይነት መንገድ….?

ዛሬም ቢሆን ስሜቴ ክፉኛ ተጎድቶአል። ገርጂ ከጊዮርጊስ ቤ.ክርስቲያን ጀርባ በምትገኘው ሰማዕቱ ልጃቸው በተከራየላቸው ጠባብ ቤት ውስጥ፤ በብቸኝነት ተኮራምተው፤ አንድያ ልጃቸው ተመልሶ እንደማያዪት ከተረዱ ሳምንት ሳይሞላቸው ያለ አስተዛዛኝ ብቻቸውን የተቀመጡት እናት፤ የሚያነጋግራቸው ዘመድ፣ ሲቦርቁ እያዪ የሚፅናኑባቸው ህፃናት የሌሉበት ጠባብ ቤት ያለመጠን ሰፍቶ ፍርሀት ሲያነግስባቸው፤ ቤታቸው የተሰቀለው ልጃቸውን ከነገዳዩ የሚያሳይ ምስል እያባነነ እንቅልፍ ሲከለክላቸው፤ ይህንን ሁሉ እየሰማን እና ይህን ሁሉ እያየን ዝም የምንል መሆናችን ያሳፍራል። (በእርግጥ ለህዝቡ ማን ነገረው? የመንግስት ሚድያዎች በሌሎች ጉዳዮች ተጠምደዋል። ሀላፊነታቸውን በብርቱ ይወጡ የነበሩ ጋዜጦች እና መጵሄቶች ዛሬ በስራ ላይ የሉም) ዛሬስ እኔም እፍረት በዝቶብኝ አንቆ ሊደፋኝ ደርሶዋል።

አያልቅበት እኮ “የሞተው ሁላችንንም ተክቶ ነው። እሱ እኮ አንገቱን የደፋው የናቱን አንገት ቀና ሊያደርግ ነው።”

በኢትዮጵያ አምላክ እለምናለው አዛውንት እናትና ህፃናት ልጆች አንድ ናቸው። ስደቱም የመጣው ለማሳደግና ለመጦር ነው። እኚህን እናት አጠገባቸው ሄደን እናጽናናቸው። ቀሪ ህይወታቸውንም ወድቀው እንዳይቀሩ እንደግፋቸው።

የሰማዕቱ አያልቅበት ድምጽ ግን ይሰማል። ብቸኛዋን “እናቴን አደራ”።

ለሰማዕቱ አያልቅበት ነፍስ ይማርልን!! እንፀድቅባቸው ዘንድ እናቱንም ትቶልን ከሱ ሰማዕትነት በረከት እንድንሳተፍ እነሆ “እናቴን አደራ” ይለናል።

ከቻሉ በአካል ተገኝተው እናታችንን ያፅናኑ፤ ካልቻሉ ይህን መልዕክት share በማድረግ የሰማዕታቱ ቤተሰቦች መሆናችንን (እንግለጥ።)

አሁንም በድጋሚ እናገራለው። ከብዙ ቃል መግባት ጥቂት ቃልን መፈፀም ዋጋው የላቀ ነው። እግዚአብሔር ይርዳን!!

፨፨፨
በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቦሌ ቅርንጫፍ ሂሳብ ቁጥር፦
0173045290500 ለወ.ሮ አለሚቱ በላይነህ
ስ.ቁጥር 0911811070

The post በሊቢያ ከተሰውት መካከል አያልቅበት ስንታየሁ – “እናቴን አደራ” appeared first on Zehabesha Amharic.


Hiber Radio: ቻይና ለኢትዮጵያው አገዛዝ የጦር መሳሪያ ማስታጠቋን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ደርሼበታለሁ አለ *የመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ዜጎችን ከመመለስ ይልቅ የውስጥ የቪዛ ንግድ ላይ አተኩሯል ይላሉ * የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ተቃዋሚዎቻቸውን ላለማስታጠቅ ለመስማማት ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ተዘገበ * የኢትዮጵያ መንግስት በእስራኤል መብታቸው የተነካ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች ጉዳይ ያሳስበኛል ማለቱን ብዙዎች አጣጣሉት * ኢትዮጵያዊው የታሪክ ተራኪ ኤድዋርዶ ባይሮኖ የሰጠው ቃለምምልስ እና ሌሎችም..

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የግንቦት 2 ቀን 2007 ፕሮግራም

እንኳን ለእናቶች ቀን አደረሳችሁ!

< …የትናንት ታሪካችን የምንማርበት እንጂ ዛሬ ላይ ሆነን የምንጨቃጨቅበትና የምንጣላበት ሊሆን አይገባም ታሪክን ዛሬ ላይ እንደፀብ መነሻ የሚያዩት ግን… >

ኢትዮጵያዊው የታሪክ ተራኪ ኤድዋርዶ ባይሮኖ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በጉባኤው ላይ የሰላማዊ ትግልና የትጥቅ ትግል እንዴት ተመጋግበው ለውጡን እንደሚያግዙ፣ የኢትዮጵያ ሴቶች ለለውጥ ያላቸው ፖለቲካዊ ተሳትፎ፣ ስለብሄራዊ እርቅ ፣ኢትዮጵያ ውስጥ በምርጫ ለውጥ ሊመጣ ይችላል ወይ የሚሉና ሌሎች አብይ ጉዳዮችም ኢትዮጵያንና የአካባቢ አገራትን ወቅታዊ እና የወደፊቱን የዳሰሱ በኢትዮጵያና በኤርትራዊያን ምሁራን ጭምር ሰፊ ጥናቶች የቀረቡበት ስኬታማ ጉባኤ ነው….>

አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የመለስ ቱርፋቶች መፅሀፍ ደራሲ በኢሳት የተዘጋጀ ግንቦት 1 እና 2 በኢትዮጵያና በአፍሪካ ቀንድ የዲሞክራሲ የልማት የወደፊት እድል እና መረጋጋት ላይ ስለተካሄደው ስብሰባ አዘጋጆቹን በመወከል ከሰጡን ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…እናቶች ለልጆቻቸውና ለቤተሰባቸው ከሚያደርጉት ላቅ ያለ አስተዋፅኦ በተጨማሪ እራሳቸውንም መጠበቅ አለባቸው ማህበረሰቡም ሊያግዛቸውና ሊያበረታታቸው ይገባል…>

ወ/ሮ ፌበን ፋንቱ የህብር ሬዲዮ የእናቶች ቀን እንግዳ ከሎስ አንጀለስ ከሰጠችው ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

በቬጋስ የታክሲ ተቆጣጣሪ ባለስልጣን ኦፊሰር ድብደባ የተፈጸመበት ኢትዮጵአዊ የሊሞ አሽከርካሪ በሕግ ለመፋረድ ለወገኖቹ ያቀረበው ጥሪ

የግብጽ ሰራዊት ኢትዮጵያውያንን ማስለቀቅና የፕሬዝዳንቱ አልሲሲ የዓለምን መገናኛ ብዙሃን የሳበ አየር ማረፊያ ወርደው ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን መቀበላቸው የፈጠረው ስሜትና የፖለቲካው አንደምታ(ልዩ ጥንቅር)

ኢትዮጵያዊው አርበኛ ደጃዝማች ብርሃነመስቀል ደስታ ዜና እረፍትና የአስከሬናቸው ሽኝት በሎስ አንጀለስ(ልዩ ዘገባ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ቻይና ለኢትዮጵያው አገዛዝ የጦር መሳሪያ ማስታጠቋን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ፔንታጎን ደርሼበታለሁ አለ

የኢትዮጵያ መንግስት በእስራኤል መብታቸው የተነካ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች ጉዳይ ያሳስበኛል ማለቱን ብዙዎች አጣጣሉት

የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ተቃዋሚዎቻቸውን ላለማስታጠቅ ለመስማማት ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ተዘገበ

የመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ዜጎችን ከመመለስ ይልቅ የውስጥ የቪዛ ንግድ ላይ አተኩሯል ይላሉ

በአገር ቤት በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ማሳደድና የአገዛዙ የጥላቻ ቅስቀሳ ቀጥሏል

ፓርቲው በመጭው ቅዳሜ በመስቀል አደባባይ የጠራው የምርጫ ቅስቀሳ ታላቅ ስብሰባ አይቀርም ብሏል

ሀይሌ ገ/ስላሴ ራሴን ከውድድር አርቄያለሁ ማለቱ ተዘገበ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: ቻይና ለኢትዮጵያው አገዛዝ የጦር መሳሪያ ማስታጠቋን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ደርሼበታለሁ አለ *የመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ዜጎችን ከመመለስ ይልቅ የውስጥ የቪዛ ንግድ ላይ አተኩሯል ይላሉ * የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ተቃዋሚዎቻቸውን ላለማስታጠቅ ለመስማማት ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ተዘገበ * የኢትዮጵያ መንግስት በእስራኤል መብታቸው የተነካ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች ጉዳይ ያሳስበኛል ማለቱን ብዙዎች አጣጣሉት * ኢትዮጵያዊው የታሪክ ተራኪ ኤድዋርዶ ባይሮኖ የሰጠው ቃለምምልስ እና ሌሎችም.. appeared first on Zehabesha Amharic.

አርበኞች ግንቦት7 – የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!!

Previous: Hiber Radio: ቻይና ለኢትዮጵያው አገዛዝ የጦር መሳሪያ ማስታጠቋን የአሜሪካ መከላከያ ሚኒስቴር ደርሼበታለሁ አለ *የመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አገዛዙ ዜጎችን ከመመለስ ይልቅ የውስጥ የቪዛ ንግድ ላይ አተኩሯል ይላሉ * የኢትዮጵያና የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ተቃዋሚዎቻቸውን ላለማስታጠቅ ለመስማማት ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ተዘገበ * የኢትዮጵያ መንግስት በእስራኤል መብታቸው የተነካ ኢትዮጵያውያን ቤተ እስራኤሎች ጉዳይ ያሳስበኛል ማለቱን ብዙዎች አጣጣሉት * ኢትዮጵያዊው የታሪክ ተራኪ ኤድዋርዶ ባይሮኖ የሰጠው ቃለምምልስ እና ሌሎችም..
$
0
0

የህወሓት አገዛዝ ፋሽስታዊ ባህርያት እያደር መረን እያጣ፤ ነውረኛ እየሆነ መጥቷል። በአሳለፍነው ሣምንት ብቻ እንኳን አስነዋሪ ይዘት ያላቸው ሁለት ፋሽስታዊ ክስተቶችን አስተውለናል።

ginbot 7አንዱ በምርመራ ስም በታሳሪዎች ላይ የሚደረገው አሳፋሪ ሰቆቃ ነው። በገላቸው በሚያፌዙና በሚሳለቁ ተቃራኒ ፆታ መርማሪዎች ፊት ለሰዓታት ተመርማሪዎች ራቁታቸውን እንዲሆኑ የሚደረግበት እና እየተፌዘባቸው የሚደበደቡበት ሥርዓት መኖሩ የጉዳቱ ሰለባዎች ይፋ ሲያወጡ እፍረቱ ለመርማሪዎቹ ብቻ ሳይሆን ይህንን ጉድ ተሸክመን ለኖርነው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ነው። በተለይም ደግሞ እንዲህ ዓይነት ክብረነክ ሰቆቃ በሴቶች ላይ እየተፈፀመ መሆኑን ስንሰማ አገራዊ ውርደቱ ያሸማቅቀናል። እንዲህ ዓይነቶችን በሰው ስቃይና እፍረት የሚዝናኑ ጉዶችን ተሸክመን የምኖር መሆናችን ሁላችንን ያዋርደናል። ይህንን አስነዋሪ “የምርመራ ዘዴ” ያጋለጡት የዞን 9 ብሎገሮች፣ ጋዜጠኞችና ፓለቲከኞች ክብርና ሞገስ የሚገባቸው ጀግኖች ሲሆኑ የተዋረዱት እነሱ ሳይሆኑ እኛ ኢትዮጵያዊያን መሆናችን ሊሰማንና “ውርደት በቃ” ልንል ይገባናል።

ሁለተኛው አሳፋሪ ድርጊት ደግሞ ወገኖቻችንን በግፍ ባረደው አይሲስ በተሰኘው አሸባሪ ድርጅት ላይ የህወሓት አገዛዝ የተለሳለሰ አቋም ወስዷል ብለው ራሱ ህወሓት በጠራው ሰልፍ ላይ ተቃውሞዓቸውን ባሰሙ ወጣቶች ላይ አገዛዙ የወሰደው የኃይል እርምጃና ከዚያም ወዲህ እየተደረገ ያለው ነገር ነው። አገዛዙ ለፕሮፖጋንዳው ይጠቅመኛል ብሎ በጠራው ሰልፍ ወጥተው ተቃውሞዓቸውን የገለፁ ወጣቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ተደብድበዋል፤ በጅምላ ወደ እስር ቤቶች ተግዘዋል። የአገዛዙ ካድሬዎች ወገኖቻችንን የፈጀውን አይሲስን በመቃወም ፋንታ የራሱ የህወሓትን ውል አልባ ህግ አክብረው በመንቀሳቀስ ላይ ያሉትን ሰማያዊ ፓርቲ፣ ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞችን እና አረና ፓርቲን እየወነጀሉ መሆኑ አጅግ አሳፋሪ ነገር ነው። የአይሲስን አረመኔአዊ ድርጊት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር ለማገናኘት በህወሓት የደህንነት ቢሮ አማካይነት እንቅስቃሴ መጀመሩ እየተሰማ ነው። ለወጣቱ በብዛት መሰደድ በምክንያትነት የሚያቀርቡት ደላሎችን መሆኑ አላዋቂነት ሳይሆን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ቅራኔው በኢትዮጵያዊያን መካከል እርስ በርስ እንዲሆን ያለመ መሠሪነት ነው። ከዚህም አልፎ የትግራይ ወጣቶችን ነጥሎ በመሰብሰብ “ትምክህተኞች ሊበሉህ ነውና ታጥቀህ ሳይቀድሙህ ቅደም” እያሉ መቀስቀስ በመንግሥት ደረጃ የእርስ በርስ እልቂትን ከማደራጀት ተለይቶ አይታይም። የሥርዓቱ ይሉኝታ ቢስነት የደረሰበት ዝቅጠት ገላጭ ከሆኑ ነገሮች አንዱ “እስከምርጫ መጨረሻ ድረስ ልጆቻችሁን አስረን እናቆይላችሁ” እያሉ ወላጆችን እስከመጠየቅ መድፈራቸው ነው።

ከላይ በአጭሩ የተዘረዘሩት ኩነቶች የሚያረጋግጡት ህወሓት የተማከለ አመራር አጥተው መንገድ የጠፋቸው፤ ሆኖም ግን እጃቸው ውስጥ የገባው ስልጣንና ሀብት ላለማጣት ምንም ነገር ከማድረግ የማይመለሱ አውሬዎች ስብስብ መሆኑ ነው። እንዲህ ዓይነቱን የአውሬዎች ስብስብ የሚገዛው የህግም ሆነ የሥነ-ምግባር ገደብ የለም። ህወሓት እስር በርሳችንን አባልቶ አገራችንንና ሕዝቧን ወደ ማንወጣው አዘቅት ከመክተቱ በፊት ራሱ ህወሓትን ማስወገድ እና በምትኩት ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን መገንባት የዚህ ትውልድ ኃላፊነት ነው። ይህ ካላደረግን አሁን በወህኒ ቤቶች የሚደረገው ዜጎችን ልብስን አስወልቆ የማዋረድ አስነዋሪ ተግባር ነገ በአደባባዮች የማይደረግ ስለመሆኑ ምንም ማረጋገጫ የለንም። ይህ ትውልድ ኃላፊነቱ ካልተወጣ ህግን አክብረው ከአገዛዙ የተለየ ሀሳብ እናራምዳለን የሚሉ ወገኖቻችን በሙሉ አደጋ ውስጥ ናቸው። በህወሓት መሠሪ ተግባራት ሳቢያ በክርስትናና እስልምና እምነት ተከታይ ኢትዮጵያዊያን መካከል ያለው መግባባት እንዲሻክር እየተደረገ ነው። ዜጎችን በማዋረድ የሚደሰት አገዛዝና ለመዋረድ የፈቀደ ሕዝብ እስካለ ድረስ የቁልቁለቱ ጉዞ መጨረሻ የለውም። ይህንን ማስቆም ያለብን እኛ ሁላንችንም ነን። በአደባባይ መደራጀት ሲከለከል በምስጢር መደራጀትን መልመድ የኛ ኃላፊነት ነው። የኢትዮጵያ አርበኞች ድል መታሰቢያ በዓልን ስናከብር ከቀደምቶቻችን ልንወርስ ከሚገቡን እሴቶች አንዱ ለክብራችን ዋጋ መክፈል ያለብን መሆኑን ጭምር ነው። የኢትዮጵያዊያን ክብር በወያኔ ሲዋረድ እያየን ዝምታን ከመረጥን ከዚህም የባሰ እንዲመጣ መፍቀዳችንን እንወቀው።

አርበኞች ግንቦት 7:የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የዜጎችና የአገር ውርደት ይብቃ! በተባበረ ክንድ ህወሓት ይወገድ፤ በምትኩም ፍትህ፣ ነፃነት፣ ዲሞክራሲና እኩልነት የሰፈነባት ኢትዮጵያን ለመመሥረት መሠረት እንጣል፤ ይህንን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በኅብረት እንነሳ ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post አርበኞች ግንቦት7 – የቁልቁለቱን ጉዞ እናስቁም፤ ውርደት ይብቃን!!! appeared first on Zehabesha Amharic.

የጋምቤላ ነዋሪዎች መንግስት በታጠቁ አካላት እያስጨፈጨፈን ነው አሉ

$
0
0

fig_1በጋምቤላ ክልል፣ መጃንግ ዞን፣ ጎደሬ ወረዳ የሚኖሩ ዜጎች በመንግስት በተቀነባበረ ሴራ ጭፍጨፋ እየደረሰባቸው እንደሆነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በተለይ ከግንቦት 2006 ዓ.ም ጀምሮ 400 ያህል ነዋሪዎች እንደተገደሉ የገለጹት ነዋሪዎች መንግስት የእርስ በእርስ ግጭት ለማስመሰል ቢሞክርም ችግሩ በመንግስት የተቀነባበረ እንደሆነ እንደሚያምኑ ገልጸዋል፡፡ ‹‹የአብዛኛዎቹ ነዋሪዎች እርሻ ለገዥው ፓርቲው ካድሬዎች በመስጠት እኛ ከቦታችን እንድንፈናቀል ጥረዋል፡፡ አንወጣም ስንል ግን በግድ እንድንወጣ የተላከብን ጨፍጫፉ ነው፡፡›› ሲሉ የአካባቢው ነዋዎች በስልክ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ዕለት በግልጽ ባልታወቁ ነገር ግን እነሱ ሚሊሻዎች እንደሆኑ በሚገምቷቸው 10 ያህል ሰዎች እንደተደገደሉ ነገር ግን ከስድስቱ በስተቀር የሌሎቹን ሰዎች አስከሬን ማንሳት እንዳልቻሉ ነዋሪዎቹ ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ አክለውም ‹‹መንግስት በጭፍጨፋው ላይ እጄ የለበትም ቢልም ህዝቡ ሲማረር ይወጣል በሚል እያስጨፈጨፈን ይገኛል፡፡ በርካታ ወታደርና ፖሊስ ቢኖርም ጭፍጨፋውን ለማስቆም ጥረት አለማድረጉ መንግስት ከበስተጀርባው እንዳለ እንድናምን አድርጎናል፡፡›› ብለዋል፡፡

The post የጋምቤላ ነዋሪዎች መንግስት በታጠቁ አካላት እያስጨፈጨፈን ነው አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ደርግን ያስናፈቀ አገዛዝ! –ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

Amsaluእኔ ለደርግ ሥርዓት ጥሩ ስሜት የለኝም፡፡ በእርግጥ ደርግ ያደረገውን የቀይ ሽብር ፍጅት በወቅቱ ገና መወለዴ ስለነበር በዐይኔ ዐላየሁም፡፡ ይሁንና የሆነውን ሁሉ ግን አባቴም በኢሕአፓነቱ የደርግ ጥቃት ሰለባ ስለነበር እሱ ከነገረኝም ሆነ እኛ ዜጎች የደርግንም ሆነ የሌላውን ማንነት ከመረዳት አንጻር ከታሪክ ብዙ የምንረዳው ነገር አለና ለደርግ ጥሩ ስሜት የለኝም፡፡ ከፈጸማቸው የግድያ እርምጃዎች ጋር በተያያዘ አሁን ሀገራችን ላለችበት ዘንቀ ብዙ ችግሮች ተጠያቂ እንደሆነም አስባለሁ፡፡ በተለይም እነዚያ ብዙ የተማሩ ብዙ የሚያውቁ ብዙ የውጪ ግንኙነት ልምድ የነበራቸው የ62ቱ የቀዳማዊ ዐፄ ኃይሌ ሥላሴ መንግሥት ሚንስትሮችን ጉዳይ ሳስብ ዘወትር ይከነክነኛል፡፡ ኢትዮጵያ ከስር የተነቀለችው ዐይኖቿ የጠፋው ያኔ ነው፡፡ እነ ጠቅላይ ሚንስትር አክሊሉ ሀብተ ወልድን የሚያህል እጅግ አስተዋይ፣ አርቆ አሳቢ፣ ደከመኝ ሰለቸኝን የማያውቅ ትጉ፣ ተናግሮ ሊያሳምነው የማይችለው ሰው የሌለው ብልህ፤ በእነዚህ ብቃቱም በመንግሥታቱ ድርጅት ታሪክ ኮከብና አንጸባራቂ ዲፕሎማት (አቅናኤ ግንኙነት) የነበረን ታላቅ ሰው የመሳሰሉ ብርቅየ የሀገራችን ፖለቲካ (እምነተ አሥተዳደር) ቁልፍና መዝገቦች ያለ አግባብነት ያለው ፍርድ በግፍ መግደሉ ነው ሀገሪቱ መስመር ስታ ወዳልሆነ አቅጣጫ መንጎድ የጀመረችው፡፡

ሰሞኑን የፕሬስ (የጥፈት) ነጻነት ቀን ሚያዚያ 25 (May 3) በዓለም ዓቀፍ ደረጃ ታስቦ ነበር:: ታዲያላቹህ በሀገራችንም ይሄንን የጥፈት ነጻነትን ቀን በዓል ለማክበር ለማሰብ እነማን ተሰባሰቡላቹህ መሰላቹህ? ጥፈትን (ፕሬስን) የገባችበት እየገቡ የሚያሳድዷት ጭፍሮች ተሰባስበው ታደሙና “ይሄው በዓልሽን እያከበርንልሽ ነው” ብለው ጥፈትን (ፕሬስን) ሲያፌዙባት ሲቀልዱባት ሲሳለቁባት ሲያበግኗት ዋሉ፡፡ ጥፈት (ፕሬስ) በጣም አሳዘነችኝ እንደምን ታር! እንዴት ትበግን! እንዴት ትደብን! ብየም አሰብኩላት፡፡ ጨጓራዋ ተልጦ ቆሽቷ ደብኖ እየጨሰች ታየችኝ፡፡ መድረኩ ላይ ተሠይመው እየተንጎባለሉ በመደስኮር ሲያቃጥሏት ከነበሩት የጥፈት ጠላት የወያኔ ጭፍሮች አንዱና በሀገሪቱ የጥፈት (የፕሬስ) ነጻነት እንዳለ ተደርጎ እንዲታሰብ ብቻ ተቋቁመው ከሚሠሩ የኅትመት የብዙኃን መገናኛዎች ባለቤቶች አንዱ የሆነው ሰው ምን አለ መሰላቹህ? እኔ ማንን ለማለት እንደፈለገ ቢገባኝም እንዴት ሆኖ እንደሆነ ግን ሊገባኝ አልቻለም፡፡ እንዲህ ነበር ያለው “አትመጣም ወይ መንጌ አትመጣም ወይ? እያለ የደርግን መልሶ መምጣት በመናፈቅ የሚጨፍር የፖለቲካ ፓርቲ ስለ ፕሬስ ነጻነት ተሟጋች እንዴት ሊሆን ይችላል?” ነበር ያለው፡፡ ሌላኛው ደግሞ አሁን በዚህ ወቅት “ነጻ ጥፈት (ፕሬስ) አለ በሚገባም እየሠራ ነው…..” በማለት ሌሎችን አለመኖሩን በማስረጃ አስደግፈው የሚሟገቱትን እንደ ሲ.ፒ.ጀ. ያሉ የዓለም አቀፍ ድርጅቶችን አቋምና ክስ ለማጣጣል ጥረት አደረገ፡፡ የሚገርማቹህ ይህ ሰው አንድ ወቅት ላይ የዚህ ዓለም አቀፍ ድርጅት ተሸላሚ የነበር ሰው ነው፡፡ እነዚህ ግለሰቦች ቀድሞውንም ቢሆን ሥውር ተልእኮ ስለነበራቸው በነጻው ጥፈት ተሰማሩ እንጅ አንጻራዊ በሆነ መልኩ ነጻው ጥፈት የተሻለ ይሠራ በነበረበት ወቅት አገዛዙ በነጻው ጥፈት (ፕሬስ) ላይ ያለውን አያያዝና አቋም ቀንደኛ ተችና ተቃዋሚ ሆነው ኖረው አሁን ላይ ጭራሽ አገዛዙ ነጻውን ጥፈት (ፕሬስ) ደብዛውን ባጠፋበትና የለየለት አንባገነን በሆነበት ወቅት ከወትሮው ይበልጥ መቃወምና መታገል ሲኖርባቸው ሲጠበቅባቸው እነኝህ የነጻው ጥፈት ውጤት ጋዜጣ ባለቤት ነኝ ባይና ነጻ ጋዜጠኛ ነኝ ባይ ግለሰቦች የአገዛዙ ደጋፊ ሆነው ከአገዛዙ ጋር ሊሠሩ ሊሰለፉ የሚችሉበት አንዳችም ምክንያት የለም፡፡ የስለላ ተልእኮ ነበራቸው ለመመሳሰል ተቃዋሚ ሆነው በሚገባ ተወኑ አንደኛው እንዲያውም እስከመሸለም ድረስ ደረሰ ወዲያው ግን ተነቃባቸው ስለተነቃባቸውና ስለተገለሉም “ከተነቃ አይገደድም” ብለው ወደ ቤታቸው ተመለሱ፡፡ ያለው ነገር ይሄ ነው ሌላ ምንም ምሥጢር የለውም፡፡

አገዛዙ የፈጸመውን ግፍና ወንጀል ከዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዐይን ለመሠወር ሲል የውጭ ዜጎች ድርሽ እንዳይሉ ወደ ተከለከሉበት አገዛዙ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብት ረገጣና የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን በፈጸመባቸው የሀገራችን አካባቢዎች የተፈጸሙትን ኢሰብአዊ ድርጊቶቹን ለማጣራትና መረጃ ለመሰብሰብ ባለመቻላቸው ምክንያት የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ሠራተኞች በተለያየ ዘዴና መንገድ መረጃ ለመሰብሰብ መሞከራቸውን ይሄ ጋዜጠኛ ነኝ ባዩ ወያኔ በዚህ በዓል ዝግጅት ላይ ሲናገር እንደሰማቹህት ነጻ ጋዜጠኛ መስሎ ይሰልል በነበረበት ወቅት ካየውና ካጋጠመው ተነሥቶ በመኮነንና እንደ ወንጀል በመቁጠር በወቅቱ ሲሠራው ከነበረው የስለላ ሥራው እየጠቀሰ ይናገር ነበር፡፡ ይሄ ሰው ከመሰሎቹ ጋር ሆኖ ባለፈው የሕወሀት 40ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሚከበርበት ወቅት ወደ ስፍራው ተጉዘው ጉብኝት ካደረጉት ጋዜጠኞችና ከያኔያን ነን ባዮች ጋር በመሆን በጉብኝታቸው መጨረሻ ላይ ባለ 6 ነጥብ የአቋም መግለጫ በማውጣት በማንኛውም እረገድ ከሕወሀት ጎን እንደሚሰለፉ ለሕዝብ በብዙኃን መገናኛ ካረጋገጡ ምንደኞች አድርባዮች ባንዶች አንዱ ሆኖ እያለ ነው እንግዲህ ዛሬም ሳያፍር አጻ ጋዜጠኛ ነኝ ሊለን የሚሞክረው፡፡

እንደምታስታውሱት ሚያዝያ 14,2007ዓ.ም. ቀን ሊቢያ ውስጥ በአረማዊያን ለተሠው ወገኖቻችን የተሰማንን ሐዘን ለመግለጽና ለአረመኔው አይ.ኤስ ቡድን ደግሞ ያለንን ተቃዉሞ ለማሰማት በወጣንበት ቀን በብልሹ አሥተዳደሩና በግፍ አገዛዙ ወገኖቻችንን ለስደት እየዳረገ ለእርድ፣ ለስጥመተ ባሕርና ተቆጥሮ ለማያልቅ መከራ ያበቃቸው ይህ የአገዛዝ ሥርዓት እንደመሆኑ መጠን ምክንያቱም አገዛዙ ዜጎች በዜግነታቸው የዜግነት ኃላፊነታቸውን ግዴታቸውንና መብታቸውን ለመወጣት ጥረት በሚያደርጉበት ወቅት ለሱ ስላለተመቸው በኃይል ይዞ አልለቅም ላለው ሥልጣኑ ሥጋት ስለሆኑ “እኔ የምላቹህን ብቻ ተቀብላቹህ ሳትወዱ በግድ እየተገዛቹህ መኖር አንችልም ካላቹህ ተሰደዱ” ብሎ ዜጎችን ከገዛ ሀገራቸው እንዲሰደዱ መሰደድን ብቸኛ አማራጭ አድርጎ የሰጠ ካልሆነ ግን አስራለሁ እገላለሁ ብሎ በብዙኃን መገናኛ አስፈራርቶ የሚያውጅ አገዛዝ (በምርጫ 97ዓ.ም. ወቅት አቶ መለስ ለቅንጅት አመራሮችና ተከታዮቻቸው የተናገሩትን ያስታውሷል)፣ ተቃዋሚ እንዲሰደድ እንጅ በሀገር እንዳይኖርና ሚናውን እንዲጫወት ባለመፍቀድ አቋም የያዘና አሳዳጅ አገዛዝ እንደመሆኑ ለዜጎች ስደት በቀጥታ ተጠያቂ ነውና በዚህ ምክንያት በሰልፉ ላይ ሕዝቡ በተለያየ መንገድ ለዚህ የአገዛዝ ሥርዓት ያለውን ተቃዉሞ ያሳይ ይገልጽ ነበር፡፡ ከእነኝህ የሕዝቡ ተቃዉሞ መገለጫዎች ከነበሩት ነገሮች አንዱ የነበረው ከላይ የነጻ ጋዜጣ ባለቤት ነኝ ባዩ ሰው የጠቀሰው “አትመጣም ወይ መንጌ አትመጣም ወይ?” የምትለዋ ዜማ ነበረች፡፡ አገዛዙ በዕለቱ ለተነሡት ተቃዉሞዎች ሁሉ ተጠያቂ ያደረገው ሰማያዊ ፓርቲን ነው፡፡

እናም እነዚህ የውሸት የጥፈት (የፕሬስ) ሰዎች ነን ባዮች የወያኔ ጭፍሮች ታዲያ እንደ ወያኔነታቸው ይሄንን የወያኔን ሐሰተኛ ክስ ትክክለኛ እንደሆነ አድርገው በማውራት ለማሳመንም በማሰብ በዚህ የጥፈት ነጻነትን በዓል ቀን ለማክበር በተሰበሰቡበትም ቀን ጉዳዩን በማንሣት የወያኔነት ሥራቸውን ለመከወን ሙከራ አደረጉና ከላይ የጠቀስኩትን ንግግራቸውን ተናገሩ፡፡

እኔ ወያኔዎች ከሚገርሙኝ ነገራቸው አንዱ ምናልባትም ዋነኛው እራሳቸውን ከደርግ የተሻሉ እንደሆኑ አድርገው በማሰብ ደርግን እያነሡ “የጥፈት (የፕሬስ) ነጻነት ያልነበረበት፣ ወጣቱን ትውልድ እየረሸነ የፈጀ እንዲህ ዓይነት አረመኔ መንግሥት እኮ ነበር የነበረው!” በማለት ሕዝቡ እነሱን የተሸሉ እንደሆኑ አስቦ አሜን ብሎ እንዲቀበላቸው የሚያደርጉት ጥረት ነው፡፡ አንባቢያን እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቃቹህ? የጥፈት ነጻነት አለ ሰጥቻለሁ በሕገ መንግሥት አረጋግጫለሁ ብሎ ሲያበቃ ሰው ሲናገር ሲጽፍ የሚናገሩትን የሚጽፉትን እየለቀመ በማፈን ከሚያጠፋው ከሚያስረው ከሚገለው እና ስለማጠፋህ አትናገር አትጻፍ ብሎ አስቀድሞ አስጠንቅቆ መጻፍ መናገርን ከከለከለው ማንኛው ይሻላል? እኩይነት መርዘኛነት ሸረኝነት አጥፊነትስ የትኛው ላይ ነው ያለው? እንዲያው ነገሩን አልኩ እንጅ ወያኔስ ቢሆን ለማስመሰል ምዕራባዊያኑን ለመደለል ወረቀት ላይ አሠፈረው እንጅ የትኛው የሰጠው ያረጋገጠው ያሰፈነው ነጻ ፕሬስ (ጥፈት) ነው አደረኩ ብሎ ሊያወራው የሚችለው? ለማስመሰልም ቢሆን በትንሽ በትንሹ እንዲጻፍ ማድረጉ እኮ ያለፈ ድሮ የቀረ ታሪክ ሆነ፡፡ አሁንማ እኮ ጋዜጠኝነት በአሸባሪነት የሚያስከስስና የሚያስቀጣ ሞያ እኮ ሆነ፡፡ አሁንማ እኮ ነጻ ጥፈት (ፕሬስ) ሕገ መንግሥታቸውን በቀጥታ በሚጻረሩ በሚሽሩ እንደ ፀረ ሽብርተኝነት በመሳሰሉ ፀረ ሕገ መንግሥት ፀረ ሰብአዊ መብት ሕግጋት እግር ከወርች ታስሮ እንዳይሠራ እንዳይንቀሳቀስ ከተደረገ ቆየ አይደል እንዴ? ቅድመ ምርመራው (ሴንሰር ሽፑ) ተመልሶ መጥቶ ጋዜጠኖችንና ጸሐፍትን ውስብስብ ችግርና ሥጋት ውስጥ በመክተት በራሳቸው ላይ ግለ ቅድመ ምርመራ (self censor) እያደረጉ እንዲጽፉ በማስገደድ ከዚህ ያለፈውን ደግሞ ማተሚያ ቤቶቹ አገዛዙን የሚተቹ ጽሑፎች ሲኖሩ እንዲህ ዓይነት ጽሑፍ አናትምም እያሉ ኅትመቶች እንዳይታተሙ መደረግ ከተጀመረ ዓመታት ተቆጠሩ አይደለም አይደል እንዴ? ሌላው ቀርቶ ወያኔ አሁን ደግሞ የማኅበራዊ የብዙኃን መገናኛውን (social media) ማለትም እንደ ፌስ ቡክ (መጽሐፈ ግጽ) ያሉትን የብዙኃን መገናኛ መንገዶችን ሊዘጋብን ሊያግድብን ወስኖ ቁልፍ መጫን ብቻ እንደቀረው ሰማን አይደለም አይደል እንዴ? እንግዲህ የወያኔ የአንባገነንነትና የፀረ ነጻ ፕሬስ (ጥፈት) ማንነት አፋኝነት እዚህ ድረስ ነው፡፡ ይሄ ማንነቱም ከአሜሪካ መንግሥት እስከ የመብት ተሟጋች ድርጅቶች ድረስ በሚገባ ታውቆ ቀንደኛ ፀረ ነጻ ጥፈትነቱና አፋኝነቱ ካሰራቸው ካሳደዳቸው ከሶ ከሚያንገላታቸው ጋዜጠኞች ቁጥር ጋር እየተጠቀሰ በየጊዜው እየተመሰከረበት ይገኛል፡፡ አሁን በዚህ ወቅት ወያኔ በዓለማችን ውስጥ ካሉ 10 አፋኝና ፀረ ነጻ ጥፈት አገዛዞች ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ከሚጠቀሱት አንዱ ነው፡፡ ታዲያ ወያኔና ደጋፊዎቹ አሰፈንን ብለው የሚያወሩት የትኛውን ነጻ ፕሬስ (ጥፈት) መብት ነው? ሀቁ ይሄ ከሆነስ ከደርግ እንሻላለን የሚሉት እኮ እንዴት ሆኖ ነው?

ቀይ ሽብር ቀይ ሽብር የሚሉትስ ወያኔስ ቢሆን የገደለበትን ዘመቻ ስም አውጥቶ አይንገረን እንጅ አደባባይ ላይ ብዙዎችን አልገደለም አልረሸነም ወይ? የደርግና የወያኔ የገዳይነት ተግባር በአንድ ቀን በተፈጁት ዜጎች ቁጥር የግድ ተሰልቶ መነጻጸር አለበት ወይ? ዋናው ጉዳይ ዜጎች ተቃወሙ መብታቸውን ጠየቁ ተብሎ ለጥያቄያቸው ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት ባለመፍቀድ ባለመፈለግ ከአንባገነናዊ ባሕርይ የተነሣ መሣሪያ አንሥቶ ለመግደል ፈልጎና አስቦ ሰላማዊ ዜጎችን ግንባር ግንባራቸውንና ደረት ደረታቸውን እያሉ ለመግደል ታስቦ መፈጸሙ ነው እንጅ ብዛቱ ነው ወይ መታየት መነጻጸር ያለበት? በብዛቱስ ቢሆን በምርጫ 97ዓ.ም. የተነጠቀውን ድምፁን ለማስመለስ ለማስከበር በተቃዉሞ የወጣው ወጣት የወያኔን ጭካኔ ዐይቶ መለስ ባይልና እንደ ደርግ ዘመን ወጣት የጨከነ የቆረጠ የማይመለስ ቢሆን ኖሮ ወያኔስ ቢሆን ወጣቱን በሙሉ ጨፍጭፎ በመጨረስ ጎዳናውን ሁሉ የደም ጎርፍ ሳያጎርፍበት ይመለስ ነበር ወይ? እንኳንና ወጣቱ ሁሉ ተነሥቶ ያችን ታክል ለተወጣው እንኳ የታዘዙት የአየር ኃይል አባላት “በሰላማዊ ወገናችን ላይ አንተኩስም” በማለት አብራሪዎቹ ከድተው ወደ ጅቡቲ ሸሹ እንጅ ወያኔማ ሰላማዊ ሕዝብ እንዲጨፈጨፍ ሄሊኮፕተር ያዘዘ አረመኔ አገዛዝ አይደለም ወይ? ጉዳዩ በተጠያቂነት መንፈስ ሕዝብ የጠየቀውን መብቱን የማክበርና ያለማክበር ጉዳይ ነበረ እንጅ አላግባብ የተቃጣን ሕዝባዊ ጥቃትን ወይም ዐመፅን የመከላከል ጉዳይ ነበረ ወይ? ጉዳዩ ይሄ ባልሆነበት ሁኔታ ያ የተፈጸመ ግድያ ሕጋዊ ወይም አግባብነት ያለው የሚሆነው እንዴት ሆኖ ነው?

ይህ እውነታ እንዳለ ሆኖ “ራሴን የመከላከል ሕጋዊ እርምጃና ሰላምና መረጋጋትን ማስፈን ስላለብኝ ይሄንን ማድረግም መብትና ግዴታየ ስለሆነ ነው” ከተባለም ደርግስ ቢሆን ታዲያ “ነጭ ሽብር” ተብሎ ለተሰነዘረበት ጥቃት እራስን ለመከላከል ብሎ “ቀይ ሽብርን” ከመፈጸም የተለየ ሌላ ምን ምክንያት ነበረው? ወያኔ ሲገድል ሲያፍንና ሲያጠፋ እንደ ደርግ በብዙኃን መገናኛ እነከሌን እነከሌን ገድያለሁ ብሎ አለመናገሩ ነው እንጅ በደርግ ጊዜ ከተፈጁት ዜጎቻችን ይልቅ በወያኔ ዘመን የተፈጁት የታፈኑት ዜጎቻችን ብዙ ጊዜ እጥፍ አይበልጡም ወይ? ደርግ ሰዎችን ሲገድል የፖለቲካ (የእምነተ-አሥተዳደሩ) ተቃዋሚዎች ከሚለው በስተቀር ሌላ ምክንያት ነበረው ወይ? ወያኔ ግን ከዚህ በተጨማሪ ሌላ የመግደያ የማጥፊያ የማፈኛ ምክንያት ጨምሮ በመምጣት “ጠላቴና መጥፋት ያለበት ዘር” ብሎ በሀገራችን ታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ ደረጃ ዘርን ከመገደያ ምክንያቶች አንዱ አድርጎ አማራን በግልጽም በሥውርም ጎጆ ዘግቶ በላያቸው ላይ ከማቃጠል ጀምሮ እስከ በጥይት መደብደብ ድረስ፤ በራሱ ሕገ መንግሥት “ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል መዘዋወር መኖር ንብረት ማፍራት ይችላል” የሚል መብት ታዉጆ እያለ መብታቸውን በመንፈግ ከኖሩበት ተወልደው ካደጉበት ንብረት ካፈሩበት ሀገራቸው እያፈናቀለ እያሳደደ ግፍ እየፈጸመና መኖሪያ እያሳጣ ያለው ማን ነው? ደርግ በየትኛው ብሔረሰብ ላይ እንዲህ ዓይነት ሰይጣናዊ ሴራ አሲሮ ብሔረሰብን ለይቶ በጠላትነት ፈርጆም እንዲህ ዓይነቱን የዘር ማጥፋት ወንጀል በየትኛው ብሔረሰብ ላይ ፈጸመ? ጭራሽ እንዲያውም ያባበለ መስሎት በሁሉም እረገድ የኤርትራና የትግራይ ተወላጅ የሆኑትን ልዩ ተጠቃሚ አድርጎ አስተናገደ እንጅ በትግራይ ተወላጆች ላይ ትግሬ ስለሆኑ ብቻ መቸና የት ወያኔ እየፈጸመ ያለውን ዓይነት ግፍ ፈጸመ?

ወያኔ እየደጋገመ የሚያነሣው የሀውዜኑ የጦር አውሮፕላን ጥቃትም እኮ ወያኔ ሆን ብሎ ደርግን በዓለማቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ ለማስጠቆር በውጤቱም ርካሽና ግፈኛ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት ያስፈጸመው እንደሆነ በራሱ በወያኔ አመራሮች የተረጋገጠ እውነት ከሆነ ሰነበተ፡፡ ስለሆነም ይህች የምትጠቀስ የጦርነት አደጋ ደርግን ሳይሆን ወያኔን የሚያስኮንን አስገራሚና አሳዛኝ ድርጊት ከሆነ ቆይቷልና ይሄም የናንተ ሥራ ነው፡፡ እንደ ወያኔ ሁሉ ደርግ ዘሬ ብሔረሰቤ ነው ብሎ ከኢትዮጵያ ሕዝብ አንድን ብሔረሰብ ነጥሎ ተጠቃሚ ለማድረግ በማሰብ ሁሉንም ነገር በቅድሚያና በተለየ ሁሌታ ተጠቃሚ እንዲሆን ለማን ወይም ለየትኛው ብሔረሰብ ታጥቆ ሠራ? “ኢትዮጵያ ትቅደም” የሚል መሪ ቃል በመያዝ በነገሮች ሁሉ የኢትዮጵያን ጥቅሞች በማስቀደም ለመሥራት ከመሞከር ውጪ እንደ ወያኔ ሁሉ መቸና የትስ የሀገርን ብሔራዊና ሉዓላዊ ጥቅም ከራሱ ከግል ጥቅሙ በማሳነስ ለራሱ ጥቅም የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም አሳልፎ በመስጠት የሀገር ክህደት መቸና የትስ ፈጸመ? ደርግ መቸ ነው እናንተ ወያኔ ካልሆናቹህ በስተቀር እያላቹህ የሁለተኛ ዲግሪ ትምህርትን አንዳንዴም የመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርትን መማር አትችሉም እያላቹህ እንደምትከለክሉት ከትምህርት ገበታ እንደምታባርሩት ደርግ የዜጎችን መሠረታዊ የዜግነት መብት የከለከለው መቸ ነው? እንደናንተ ሁሉ ደርግ መቸ ነው “የፖለቲካ ፓርቲ የንግድ ድርጅትና የብዙኃን መገናኛንም ማቋቋም አይችልም” የሚል ሕግ ካወጣ በኋላ የንግድ ድርጅቶችን አቋቁሞ ኢፍትሐዊና ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ በመነገድ ሀገርንና ሕዝብን የበዘበዘው የመዘበረው የዘረፈው መቸ ነው? የፓርቲ የብዙኃን መገናኛዎችን አቋቁሞ ከሀገር ጥቅም በተጻራሪ የቡድን ጥቅሙን ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ ያጧጧፈው መቸ ነው? የእናንተ ጉድ ተዘርዝሮ አያልቅምና ወዘተረፈ ብየ ልዝጋው፡፡ ወያኔዎች ሆይ! እራሳቹህን ከደርግ ጋር ስታነጻጽሩ ስታወዳድሩ ስታፎካክሩ ትንሽም እንኳን አታፍሩም? መቸ ነው እንደሚያስብ እንደሚያገናዝብ ሰው ልካቹህን አቅማቹህን ማንነታቹህን አውቃቹህ አፋቹህን ይዛቹህ ቁጭ የምትሉት? ሐፍረት የሚሰማቹህ መቸ ነው? ጤነኞች አይደላቹህምና መቸም ታደርጉታላቹህ ብየ አልጠብቅም፡፡

እኔ ይሄንን ይሄንን የማነሣው አፍቃሬ ደርግ ሆኘ ወይም ለደርግ ጥብቅና ለመቆም ሳይሆን ይህ አገዛዝ እሻላለሁ ብሎ ከሚያስበው እጅግ የባሰና ከምኑን የማይደርስ እንደሆነ ለማሳየት ነው እንጅ ደርግንስ አልወድም እጠላዋለሁ፡፡ ደርግን ከጠላሁ ደግሞ ወያኔን ምን ያህል ልጠላ እንደምችል አስቡት? ከላይ እንዳየነው የባሰ እንደመሆኑ መጠን እጅግ እግጅ እጠላዋለሁ፡፡

እናም እነ አቶ ማንትስየም ሆናቹህ የወያኔ ባለሥልጣናት ይሄንን ያህል ናቹህና ኅሊና ካላቹህ ማሰብ ማገናዘብ የምትችሉ ጤነኞች ከሆናቹህ ደርግን እያነሣቹህ “ቢያንስ ከደርግ እንሻላለን” በማለት ማስተዛዘኛ እንዲታሰብላቹህ መሞከራቹህን ብታቆሙ መልካም ነው፡፡ እንዲህም መሆናቹህን ጠንቅቆ ስለሚያውቅ ስለሚረዳ ልካቹህ ይሄ ስለሆነም ነው ሕዝቡ ደርግን እንኳ ለመናፈቅ የበቃው፡፡ አይገባቹህም እንጅ “ደርግ ከእናንተ ተሻለ እናንተ ደግሞ ከደርግ እጅግ ባሳቹህብን” ሲል ነው “አትመጣም ወይ መንጌ አትመጣም ወይ?” እያለ ያዜመው እሽ?፡፡ እንዴ! ሰው እንዴት አስቦና አቅዶ አውቆ ጥፋት እየሠራ የሚሠራው ጥፋት እንዴት አይታወቀውም? እንዴት ይጠፋዋል? እንዴት ያጣዋል ጃል?

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

The post ደርግን ያስናፈቀ አገዛዝ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on Zehabesha Amharic.

እነ ወይንሸት ዋስትና ተከልክለው ለግንቦት 24 ተቀጠሩ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

11259613_410044559178190_2673289472491445703_nመንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳትና በማስተባበር›› ካሰራቸው ሰዎች መካከል እነ ወይንሸት ሞላ ላይ ክስ መሰረተ፡፡ በፌደራል አቃቤ ህግ ከሳሽነት ክሱ የተመሰረተባቸው አራት የሰማያዊ አባላትና አንዲት ሌላ ግለሰብ ሲሆኑ፣ ተከሳሾች ዛሬ ግንቦት 4/2007 ዓ.ም በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ቄራ ምድብ ወንጀል ችሎት ቀርበዋል፡፡

በእነ ወይንሸት ሞላ የክስ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾች ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬ፣ ኤርሚያስ ጸጋዬ፣ ማስተዋል ፈቃዱ እና ቤተልሄም አካለወርቅ ሲሆኑ፣ የክሱ ይዘትም በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 32(1)(ሀ) እና 490(3) የተመለከተውን በመተላለፍ መሆኑ በክሱ ላይ ተገልጹዋል፡፡

1ኛ ተከሳሽ መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ሲናገሩ፣ ስድብና ማንቋሸሽ እንደፈጸመችና ሌሎች ተከሳሾችን በማስተባበር ‹‹ናና ናና መንግስቱ ኃ/ማርያም ናና››፣ ‹‹ወያኔ አሳረደን፣ ወያኔ ሌባ›› እያሉ ህዝቡን ያነሳሱ እንደነበር ክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡

ሁሉም ተከሳሾች ፍርድ ቤቱ የዋስትና መብታቸውን እንዲያስጠብቅላቸው የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ ጥያቄያቸውን ባለመቀበል 20 ቀናት ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡ በዚህም ተከሳሾቹ ለግንቦት 24/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፣ ወደ ‹ማረፊያ ቤት› እንዲወርዱም ታዝዟል፡፡

አቃቤ ህግ አሉኝ ያላቸውን የሰው ምስክሮች ያሰማ ሲሆን፣ በምስክሮቹ ቃል ላይ ወጥነት የሌለውና ተደጋጋሚ መደነባበር ተስተውሎባቸዋል፡፡

(የክሱን ሙሉ ይዘትና የቀረቡ ምስክሮችን ዝርዝር ይመልከቱ!)

ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia's photo.
ነገረ ኢትዮጵያ / Negere Ethiopia's photo.

The post እነ ወይንሸት ዋስትና ተከልክለው ለግንቦት 24 ተቀጠሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔ ሁለንታዊ እኩይ ፖሊሲ የሰዋቸው ሰማዕታት -ከሮበሌ አባቢያ፣

$
0
0

ግንቦት 4 ቀን 2007 ዓ.ም
Sydney Ethiopians australiaውድ ኢትዮጵያ አገራችን እስከ አራት ሺህ ዓመታት የዘለቀ ታሪክ እንዳላት ይገመታል። እንደ እውቁ ሐዋርያ አባ ወልደ ትንሣኤ አባባል፣ የመጀመሪያ ሁለቱ ተከታታይ ፈርዖኖች ኢትዮጵያውን እንደነበሩም ይነገራል፤ በአክሱማውያን ዘመነ መንግሥት በዓለም ላይ ከነበሩት አራት ሀያላን መንግስታት ውስጥ ኢትዮጵያ አንዷ እንደ ነበረች በታሪክ ተመዝግቧል። ከዚያን ጊዜ አንስቶ አማርኛ ብሄራዊ ቋንቋ እንደበርና እሰካ ዛሬም መሆኑ አያከራክርም።
ባለመታደል፣ በዘመነ መሳፍንት በተለይ በሰሜን ኢትዮጵያ የተከሰተው የሥልጣን ሽኩቻ ትርጉም የለሽና ዓላማቢስ መከፋፈልን አስከትሎ የሀገሪቱን አንድነት ክፉኛ ተፈታትኖ ውድቀት አፋፍ አድርሶ እንደነበር አይካድም ። እግዚአብሔር ኢትዮጵያን መቼም ስለማይረሳት፣ ወደር የማይገኝለትን ሀገር ወዳድ ጀገናውን አፄ ቴዎድሮስን አስነስቶ ዘመነ መሣፍንት አበቃና የኢትጵያን አንድነትና ልማትን ያማከለ የፖለቲካ ሥርዓት ተተክቶ ደርግ ከሥልጣን እስከ ወደቀበት 1983 ዓ.ም ድረስ ሊዘልቅ ቻለ።
ለአስራ ሰባት ዓመታት በሥልጣን ላይ የቆየው ደርግ፣ ከውስጥ ከአያሌ ተቃዋሚዎች ጋር ደም ያፋሰሰ ትግል እያካሄደ፤ ከውጪ ምንጊዜም ለኢትዮጵያ ውድቀት የሚፋጠንበትን ቀን ከሚጠባበቁ አድሀርያን የአረብ መንግሥታት የሚሸርቡትን ሴራ እየመከተ መቆየቱ ሐቅ ነው። በታሪክ የሚያስጠይቅ እጅግ በጣም የሚያሳን ነገር ደግሞ፣ የማረክሲስት ሌኒኒስት ርዕዮት አረማጆች በእያረብ ሀገራት እየተዘዋወሩ ለምነው ባገኙት ግንዘብ ታጥቀው ደርግን ለመጣል ያደረጉት ርብርቦሽ ነው። ይህ አልበቃ ብሎ በነጭ ሽብርና በቀይ ሽብር ጎራ ተሰልፈው እርስበርሳቸው መገዳደላቸው ለሀገር አንድነት የተሰለፉትን ወገን ክፉኛ የጎዳ እንደነበር አያከራክርም። በዚህ ውዥንበር ውስጥ መተማመን እየከሰመ፣ የውጊያ ወኔ እየተዳከመ፣ የአሚሪካ አስተዳደር ወያኔን አፍቃሬነት እና ፀረ-ደርግ የቁጭት አቋም ተዳምረው ደርግን ለመጣል ችለዋል።
ነገር ግን ደርግን የተካው ግድ የለሹ የወያኔ አገዛዝ፣ ሕዘቡን በጎሣና፣ በሃይማኖት እየከፋፈለ ሲያሰኘውም የራሱንም ሕገ መንግሥት እንዳሸው እየጣሰ በአምባገነንነት ሥልጣን ላይ ተኮፍሶ የሀገሪቱን አንድነት በወድቀት አፋፍ ላይ አድርሷልና ይህ ሁኔታ ለሚያስከትለው የእርስ በርስ መፋጀት፣ ከጭፈራ በቀር ውጠቱ ያልታየው የ“ብሔር ብሔረሰብ” ፖለቲካ ቁንጮ አራማጆች እና እበላባይ ሆድ-አደር አጫፋሪዎቻቸው ተጠያቂዎች ናቸው።
የትግራይ ማርክሲስት ሌኒንስት ሊግ መሥራችና የወያኔ ርዕዮተ-ዓለም ፓትሪያርክ ስብሐት ነጋ፣ የአማራንና የኦርቶዶክስ ክርስቲያን ተዋህዶ ሃይማኖትን አከርካሪ ሰብረነዋል
2
ብሎ በማን አለብኝነት በአደባበይ እርካተውን ደጋግም ሲያሰምርበት ተደምጧል። ስለዚህ፣ አይሲል በሊቢያ አንገታቸውን በሠይፍ የቀላቸው፣ ግንባራቸውን በጥይት የበረቀሳቸው ወገኖቻችን፣ ለስብሐትና ለመሰሎቹ እሰይ ተገለገለናቸው የሚያሰኙ፣ ግን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዘለዓለማዊ ሰማዕታት ናቸው። የመከፋፈላችንም ሰለባዎች ኛቸው።
ISIS (አይሲስ)፣ በእርሱ እምነትና ራዕይ ለመጠመቅ የማይፈልጉትን ሁሉ በሠይፍ የሚቀላ፣ በጥይት ግምባራቸውን የሚበረቅሰ፣ በአሳት አከላታቸውን አቃጥሎ የሚገድል ጨካኝ ሠይጣናዊ ስብስብ ነው። የወያኔም አምባገነን ሥርዓት በስልት ይለይ እንጂ እኔ ብቻ ልግዛ የሚል ዓላማው ተመሳሳይ ነውና በምርጫ 2007 ድባቅ ተመትቶ ዳግም ላይመለስ ከኢትዮጵያ ፖለቲካ ሕይዎት እንዲወገድ ማድረግ ግዴታ ነው። ይህ ሲሆንና የዴሞክራሲ ሥረዓት ሲሰፍን ብቻ ነው በወያኔ የጭካኔ ደርጊት የተሰዉት ሰማዕቶቻችን በአዲስ አበባ ውስጥ የመታሰበያ ሐውልት የሚቆምላቸው፡፡ አለበለዚያ ቅጥፈት መገለጫ ባህሪያቸው የሆነው የወያኔ መሪዎች በሥልጣን ላይ ከቆዩ ለሰማዕቶቻችን መታሰቢያ ሐውልት አይኖርምና፣ በተለይ ወጣቱ ትውልድ በመጪው ምርጫ የሰማያዊ ፓርቲን ወይም የመድረክን እጩ ተወዳዳሪዎችን በመምረጥ፣ በሙስና የተዘፈቀውን ገዢውን ፓርቲ ከሥልጣን የማስወገድ ታሪካዊ ሀላፊነት አለበት።
ኢትዮጵያ ዜጎቿን የምታሰተዳድርበት የራስዋን ሕግ አውጥታ በሥራ ላይ ያዋለች በዓለም ላይ የመጀመሪያ ሆና ሳለ፣ ዛሬ በወያኔ መራሹ ሥርዓት ጋዜጠኞችን ጨምሮ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ የፖለቲካ እስረኞች ወህኒ ቤት መታጎረቸው ያሳዘናል፤ ከነዚህ እስረኞች መካከል 40 ሺህ የሚሆኑት ኦሮሞዎች መሆናቸው እየተነገረ ነው። ስለዚህ፣ ሁሉም የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱና ለወደፊቱም በፖለቲካ ምክንያት ማንም እንዳይታሰር ወጣቱ በአጽንኦት መታገል አለበት!
በአፍሪካ ቀንድ የኢትዮጵያችን እስተራቴጂካዊ አቀማመጥ፣ መልካም የአየር ንብረቷ፣ ለም መሬቷ፣ አያሌ ወንዞቿ፣ የተዋበ መልክዓ ምድሯ፣ ወዘተ ለአረብ ሀገሮችና አፍርካን ለመቀራመት ለሚክለፈለፉ ቅኝ ገዢዎች የሚያስጎመዡ እሴቶቻችን ናቸው። ወያኔ እነዚህን ውድ ብሄራዊ እሴቶቻችንን ለሌላ አሳልፎ የሚሸጥ እንጂ ተንከባክቦ የሚጠብቅልን መንግሥት አለመሆኑን በአለፉት 24 ዓመታት ውድ መስዋዕት ከፍለን ለመረዳት ችለናል።
ስለዚህ ወጣት ሆይ! ዛሬም እንደ 1966ቱ አብዮት “ተነሳ ተራመድ!” እንበል። ለማስታወስ የህል በዚያን ጊዜ የኢትዮጵያ አየር ሀይል ወጣቶች ለህዝብ ያበረከቱትን አብዮታዊ መዝሙርና ሠረዊቱ የገባውን ቃል ኪዳን የያዘ ሠንጠረዥ፣ የዛሬው የመከላከያ ሠራዊት አባላትም ተገንዝበውት ከሕዝብ ጎን እንዲቆሙ በሚቀጥለው ገጽ ላይ አቅረቤዋለሁ።
ከዚህ ቀደም በመጣጥፎቼ እንደገለጽኩት፣ እኔ የመዝሙሩን ካሴት ለደርግ ለማድረሰ ታማኝ ተላላኪ ከመሆን በስተቀር፣ በመዝሙሩ ፕሮጅክት ውስጥ ምንም ተሳትፎ አልነበረኝም።

ተነሳ ተራመድ
መዝሙር
ቃል ኪዳን
ተነሳ ተራመድ ክንድህን አበርታ፣
የሀገር የወገን የብረት አጥራችን፣
ለአገር ብልጽግና ለወገን መከታ፣
ጠላት መመከቻ ጦርና ጋሻችን፣
እንበል ሃሌ ሉያ ታላቅ የምሥራች፣
የጀግኖቹ ጀግና ነህ የአየር ሀይላችን።
ከብዙ እስር ዘመን ኢትዮጵያ ተፈታች፣
አንድነታችንን በደሙ አስከብሮ፣
ኢትዮጵያችን ተቅደም ብለን እንገሥግሥ፣
ካድማስ አድማስ ዘልቆ ባየር ተስፈንጥሮ፣
ለትውልድ እንዲደርስ የያዝነው ጥንስስ።
እንደትናተናው ዛሬም ዛሬም ድል ሊያበስር፣
አዝማች፦ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም! (ሁለት ጊዜ)
ቃልኪዳን ያድሳል ለናት ሀገሩ ክብር።
እንግዲህ ይበቃል እኔ ለኔ ማለት፣
አሸባሪ ድምፁ አንገት አስደፍቶ፣
እኛ ለኛ ብለን እንሥራ በህብረት፣
ድንገት ሳይታሰብ ምሽግ ጥሶ ገብቶ፣
መሻሻል ሥራ እንጂ አይወድም ስንፍና፣
ጠላትን አርበድባጅ ፈጥኖ ሳይሰጥ ፋታ፣
ለናት ሀገራችን አይበጃትምና።
የጭንቅ ጊዜ ደራሽ የወገን አለኝታ።
አዝማች ሙዚቃ አዝማች
ለዘላቂው ሰላም ለእድገት ብልፅግና፣
ወንዞች ይገደቡ ይዋሉ ለልማት፣
በከንቱ ፈሰዋል ለብዙ ሺ ዓመታት፣
እስኪሚታይ ድረስ ሀገር የወል ሆና፣
ቃል ኪዳን አደሰ ትጥቁን ሳያላላ፣
ይውጡ ማዕድናት ላገራችን ጥቅም፣
የዳር ድንበር አጥር ለመሆን ከለላ።
ሕዝቧም ታጥቆ ይሥራ በተቻለው አቅም፣
አዝማች፦ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም! (ሁለት ጊዜ)
አሸብርቃ ታይታ በተፈጥሮ ሀብት፣
ተብላ እንዳልነበር የአፍሪቃ እመቤት፣
ብለው እንዳልጠሯት የዳቦ ቅርጫት፣
እንዴት እናታችን ትባል እራባት።
አዝማች ሙዚቃ
ይቅር ማንቀላፋት ይበቃል መኝታ፣
ይጥፋ ካገራችን ድህነት በሽታ፣
ይነገር ይለፈፍ ይታወጅ በይፋ፣
አንድነት ሀይል ነው የርምጃችን ተስፋ።
አዝማች፦ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም! (ሁለት ጊዜ)
የናት ያገራችን ጥቃቷን አንወድም፣
ሕዘቧም ተበድሎ ማየት አንፈልግም፣
የዘር የሃይማኖት ልዩነት አንሻም፣
ይላሉ ልጆችሽ ኢትዮጵያችን ተቅደም።
አዝማች፦ሀሁ ኢትዮጵያ ትቅደም! (ሁለት ጊዜ)
ዘለዓለማዊ ክብር የወያኔ ሁለንታዊ እኩይ ፖሊሲ ለሰዋቸው ሰማዕታት ይሁን!!!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!
rababya@gmail.com

The post የወያኔ ሁለንታዊ እኩይ ፖሊሲ የሰዋቸው ሰማዕታት -ከሮበሌ አባቢያ፣ appeared first on Zehabesha Amharic.

የቀድሞ የመኢአድ የሕዝብ የህዝብ ግኑኙነት ሀላፊን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ኤርትራ ለትጥቅ ትግል መግባታቸውን ገለጹ

$
0
0

“ወያኔን በሰላማዊ ትግል አይወድቅም ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በትጥቅ ትግል መታገል ነው” ወጣት ተስፋሁን አለምነህ

Tesefahun-Alemeneh_001 (1)

ወጣት ተስፋሁን አለምነህ

የቀድሞ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የነበረው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ በአገር ቤት የወያኔን አገዛዝ በሰላማዊ ትግል ታግሎ መጣል አይቻልም ብሎ በመወሰን እሱና ሌላው የመኢአድ አባል ደሳለኝ ሲሳይ ከበርካታ ወጣቶች ጋር ኤርትራ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ሰሞኑን መግባታቸውን ለህብር ሬዲዮ ከስፍራው በሰጠው አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ገለጸ።

<<በአስቸጋሪ ሁኔታ አልፈን የቀድሞው መኢአድ ግማሹ ክንፍ ኤርትራ ገብተናል>> በሚል አርዕስት ለህብር የላከውን ማስታወሻ እውነተኛነት ለማጣራት ባቀረብነው ጥያቄ የኤርትራ ስልኩን ልኮልን እሱም ሆነ ሌሎቹ በትጥቅ ትግል ስርዓቱን ለመጣል ኤርትራ የገቡ ወጣቶች መኖራቸውንና  ገልጿል ።

በአገር ቤት በሰላማዊ ትግዩ አምንን በተደጋጋሚ ስንታሰርና መከራ ሲደርስብን ነበር ያለው ተስፋሁን ሰላማዊ ትግሉ መሪያችን ፕሮፌሰር አስራትን ጨምሮ ብዙዎችን ከማስበላት ያለፈ ስርዓቱን ለማዳከም ባለመቻሉ የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ኤርትራ መግባታቸውን አረጋግጦልናል ።

<<ወያኔን በሰላማዊ ትግል አይወድቅም ከውጭም ሆነ ከአገር ውስጥ በትጥቅ ትግል መታገል ነው>> ያለው ወጣት ተስፋሁን አለምነህ ስርኣቱን በሰላማዊ መንገድ ብቻ ታግሎ መጣል አለመቻሉን ጠቅሷል።

ከወጣት ተስፋሁን አለምንህ ጋር ያደረግነውን አጠር ያለ ቃለ ምልልስ ዘግይተን እናቀርባለን።

(ህብር ሬዲዮን ከድህረ ገጻችንና ከዘ-ሐበሻ በተጨማሪ ዘወትር በ7124328451 ማዳመጥ ይቻላል)

ምንጭ – ህብር ሬዲዮ

The post የቀድሞ የመኢአድ የሕዝብ የህዝብ ግኑኙነት ሀላፊን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች ኤርትራ ለትጥቅ ትግል መግባታቸውን ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.


ኃይለማርያም ደሳለኝ እምባ እስኪተናነቃቸው ድረስ በአርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ ተተቹ

$
0
0

ኢሳት ዜና :- ጠ/ሚኒስትሩ ሚኒስትሮችንና የኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናትን በሙሉ ሲያስገመግሙ ከከረሙ በሁዋላ በመጨረሻ ራሳቸው 15 ሰአታት በፈጀ ግምገማ ተገምግመዋል። አብዛኞቹ በአቶ ሃይለማርያም የስራ ችሎታና አመራር ላይ ዘለፋ ቀረሽ ሂስ አቅርበውባቸዋል። አቶ ሃይለማሪያም የቀረበባቸውን ሂስ ለመቀበል ዝግጁ አለመሆናቸው ግምገማው ረጅም ጊዜ እንዲወስድ አድርጓል። ግምገማው ከምርጫው በሁዋላ የሚቀጥሉና የማይቀጥሉ ባለስልጣናትን ለመለየት እና ግድፈታቸውን አርመው ሰርተው እንዲጠብቁ ለማድረግ ያለመ መሆኑ ተነግሯል።
HaileMariam
አቶ ሃይለማርያም ከህወሃቶቹ ከአቶ አርከበ እቁባይ፣ አቶ ስብሃት ነጋና አስመላሽ ወልደስላሴ የሰላ ትችት ሲቀርብባቸው፣ ከራሳቸው የደህዴን አባላት ከሆኑት ከአቶ ሬድዋን ሁሴንና ሙፈሪያት ከሚልም ዘለፋ ቀረሽ ትችት አስተናግደዋል። አብዛኞቹ ብአዴኖች፣ አቶ በረከት ሳይቀሩ የአቶ ሃይለማርያምን ቁርጠኝነት ጥያቄ ውስጥ አስገብተዋል። በመጠኑም ቢሆን የራሩላቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ብቻ ናቸው።

አቶ ሃይለማርያም እንቅስቃሴያቸውንና የሌሎችን ሰዎች እንቅስቃሴዎች የሚቆጣጠሩ የስለላ ካሜራዎች እንዳይተከሉ፣ በጽህፈት ቤታቸው ያለውም እንዲነሳ ማድረጋቸው ከደህንነት ሃይሉ ጋር አጋጭቷቸው እንደቆየና ውዝግቡ አሁንም ድረስ እንደቀጠለ መሆኑ ተወስቷል።

አቶ ሃይለማርያም አንዳንድ መልሶችን ሲሰጡ እንባ ይተናናቃቸው ነበር። በተወሰኑ ቦታዎች ላይ ደግሞ በእልህና በወኔ ተሟግተዋል። አቶ ስብሃት ነጋ በአቶ ሃይለማርያም ላይ ለሰነዘሩት ትችት፣ አቶ ሃይለማርያም ” ስብሃት በጣም ይጮሃል፣ እንዳሞራ ሁሉ ይዞረኛል፣ እዚህ ሳወያይም ይጮሃል፣ አለቃ መሆን ችግር ነው ብየ ዝም አልኩ። ንግግር ከመልክ ያምራል ይባላልና ያሳሳትኩት ነገር ካለ አርማለሁ። በአባባል ክፍተት ካለ ይቅርታ” በማለት መልሰዋል።

የግምገማውን ዝርዝር ሪፖርት በነገው ዘገባ የምናቀርብ መሆኑን ለመግለጽ እናወዳለን።

The post ኃይለማርያም ደሳለኝ እምባ እስኪተናነቃቸው ድረስ በአርከበ እቁባይና ስብሃት ነጋ ተተቹ appeared first on Zehabesha Amharic.

አርበኞች ግንቦት 7 አዳዲስ ታጋዮችን አስመረቀ

$
0
0

ginbot 7 2

ginbot 7
አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ ውህደት አድርጎ አንድ ከሆነ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በርካታ አርበኛ ታጋዮችን ማስመረቁ ተሰማ::

አርበኞች ግንቦት 7 ታጋዮቹን በኤርትራ ያስመረቀው ያለፈው እሁድ ግንቦት 2 ነው:: ከኤርትራ ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በርካታ ኢትዮጵያውያን ከተለያዩ ቦታዎች ወደ ኤርትራ በመግባት አርበኞች ግንቦት 7ን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ:: የምርቃቱን ፎቶዎች ይመልከቱ::

The post አርበኞች ግንቦት 7 አዳዲስ ታጋዮችን አስመረቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ሴቶች የታሰሩት ኮሚቴዎች ነጻ መሆናቸውን መሰከሩ “ሙስሊሙን ጨካኝ ለማስመሰል የሚደረገው ሴራ አይሰራም”

$
0
0

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሴት ሙስሊሞች ባደረጉት ኮንፈረንስ የታሰሩት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ነፃ መሆናቸውን መሰከሩ:: ሙስሊሞችን ጨካኝ ለማስመስል የሚደረገው ሴራም በቅዱስ ቁርአን የማይፈቅደውና የማይገባ ነው ብለዋል:: ሙሉ ቭዲዮውን ይመልከቱ::
ይህን ታላቅ የሴቶች ኮንፈረንስ ያዘጋጀው ሪሳላ ኢንተርናሽናል ነው::

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ሴቶች የታሰሩት ኮሚቴዎች ነጻ መሆናቸውን መሰከሩ “ሙስሊሙን ጨካኝ ለማስመሰል የሚደረገው ሴራ አይሰራም”

The post በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ሙስሊም ሴቶች የታሰሩት ኮሚቴዎች ነጻ መሆናቸውን መሰከሩ “ሙስሊሙን ጨካኝ ለማስመሰል የሚደረገው ሴራ አይሰራም” appeared first on Zehabesha Amharic.

ሳሞራ የኑስ በዋሽንግተን ዲሲ እጅግ ተዋረዱ * ተቃውሞው ቀጥሏል

$
0
0

samora and azeb
በዋሽንግተን ዲሲ ማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ድንገት የተገኙት የወያኔው መንግስት መከላከያ ሚኒስተር ጄነራል ሳሞራ የኑስ በኢትዮጵያዊያኑ ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶባቸው ውርደትን መከናነባቸውን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::

በአንድ ለሊት አዳር 12 ሺህ 700 ብር በሚከፈልበት በማንደሪን ኦሪየንታል ሆቴል ያረፉት ጀነራል ሳሞራ የኑስ ከዋሽንግተን ዲሲ ግብረሃይል ወጣቶች ጋር ፍጥጫ ገጥመው ከፍተኛ የሆነ ግብግብ ተፈጥሯል:: አካባቢው በዲሲ ፖሊሶች የታጠረ ሲሆን ሳሞራም ካረፈበት ከዚህ ሆቴል ሊወጣ እንዳልቻለ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል::

ኢትዮጵያውያኑ “ኢትዮጵያውያንን የሚያሰቃይ ወንጀለኛ ለፍርድ ይቅረብ” በሚል ሳሞራ ላይ ተቃውሟቸውን በማሰማት ላይ ናቸው::

በሽንግተን ዲሲ መጥተው በኢትዮጵያውያኑ ውርደትን ከተናነቡ የወያኔ ተላላኪ ባለስልጣናት ውስጥ ስብሃት ነጋ; ሬድዋን ሁሴን; ሶፊያን አህመድና ሌሎችም ይገኙበታል::

ግብግቡ አሁንም የቀጠለ ሲሆን የደረስንበትን መረጃ እናሳውቃችኋለን::

The post ሳሞራ የኑስ በዋሽንግተን ዲሲ እጅግ ተዋረዱ * ተቃውሞው ቀጥሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

ትናኤል ያለምዘውድ ለብይን ተቀጠረ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር


መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም መስቀል አደባባይ ህዝቡን ከጠራው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በትናንትናው ዕለት ለእስር የተዳረገው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ ግንቦት 5/2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ቀርቦ ክስ የተሰማበት ሲሆን ለግንቦት 11/2007 ዓ.ም ለብይን ተቀጥሯል፡፡
በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ወንጀል ችሎት የቀረበው ናትናኤል ቀደም ብለው ክስ እንደተመሰረተባቸው የፓርቲው አባላት በተመሳሳይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ህግ አንቀጽ 490(3) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲረበሽ አድርጓል የሚል ክስ ቀርቦበታል፡፡
በዕለቱ ተከሳሹ ‹‹ከሌሎች ግብረ አበሮቹ ጋር›› በመሆን ወያኔ አሳረደን፣ ኢቲቪ ሌባ፣ መንግስቱ ናና እያሉ በመናገር ፖሊስ ላይ ድንጋይ በመወርወር ሁከት እንዲፈጠር አድርገዋል መባሉ በክሱ ላይ ተጠቅሷል፡፡ አቃቤ ህግ አሉኝ ካላቸው 5 የሰው ምስክሮች መካከል ሁለቱን ያሰማ ሲሆን ቀሪዎቹን የተለየ አያስረዱልኝም በሚል ሳያሰማ ቀርቷል፤ ናትናኤል በበኩሉ ምንም መከላከል አልፈልግም ብሏል፡፡ ምስክሮቹ ተከሳሹ ‹‹ወያኔ አሳረደን፣ እናት ኢትዮጵያ ያስደፈረሽ ይውደም፣ እኛን ከምትደበድብ አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ደብድብ…›› በማለት ሰልፉን ረብሹዋል ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል፡፡
በመሆኑም ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 11/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሌላ ዜና ናትናኤል ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት በስፍራው ከተገኙት ጓደኞቹ መካከል ዮናስ መኮነን የተባለ ወጣት ፎቶ አንስተሃል በሚል መታሰሩ ታውቋል፡፡
(ሙሉ የክሱን ይዘት ይመልከቱ)

11265050_708951002563894_6433793283434369431_n

The post ትናኤል ያለምዘውድ ለብይን ተቀጠረ appeared first on Zehabesha Amharic.

  የሀገር ሀብት ዘረፋ፤ስደት፤እሥራትና ግድያው እንዲቆም ህወሃትን ከሥልጣኑ አውርደን መጣል ግዴታችን ነው።

$
0
0

   ገብርየ በለው።  

ካልገደሉ አያቆሙንም ነው ያለው ሐብታሙ አያሌው?( ወጣቱ የፖለቲካ መሪ)ሟች ማን ገዳይ ማን?ታጋይ ይሞታል እንጅ ትግል አይሞትም።

    EPRDFፋሽስቱና አረመኔው የህወሃት ቡድን ፀረ-ሕዝብነቱን ፀረ-ኢትዮጵያዊነቱን አጠናክሮ ለ24 ዓመታት ያህል ሲዘልቅ ከባድና ከፍተኛ የሆኑ ጠባሳ የታሪክ አሸራዎችን እያስመዘገበ ማለፉ በግልጽ የሚታወቅ የሚጨበጥና የሚዳሰስ ታሪካዊ ክህደት ነው።በተለይ ከ1997 ምርጫ በኋላ በቀቢጠ ተስፋ የሚሠራውን አሳጥቶት ይገኛል ከ2007 ምርጫ በፊት በምርጫ መስናዶ ያሳያቸው የአውሬነት ባህርያትም በውል ሊስተዋሉ የሚገባቸው ናቸው።

     በአንፃሩ ደግሞ ይህን የህወሃት ታሪካዊ ክህደትና የቅጥረኝነት አስነዋሪ ተግባር ለመመከት በኢትዮጵያዊነታችን የምናምን ዜጎች የሄድንበት ርቀት ወንዝ የሚያሻግር ሆኖ አላገኘሁትም። ጉዳዩ ህወሃት የሰጠን የቤት ሥራ ብቻውን አቅም እንድናጣ አድርጎናል ብየም አልገምትም። የራሳችን ችግርም አስተዋፅኦ አድርጓል።እንደኔ አመለካከት ቁልፉ ጉዳይ እዚህ ላይ ነው ያለው ብየ አምናለሁ። ለምን ቢባል ሕዝቡ ለአመጽ ዝግጁ አይደለም ብለው ምክንያት ሲፈጥሩ የነበሩ የተቃዋሚ ድርጅቶች ሕዝቡ ጥሏቸው ሄዶ እነሱን ጭራ አድርጓቸው ይገኛል። የተቃዋሚ ኃይሎች በራሳቸው መካከል ያለውን ግንኙነት ስንመለከት ተስፋ ሰጭ አይደለም።

     የተቃዋሚ ኃይሎች መጀመርያ ራሳቸውን ሊፈትሹ ይገባል በተለመደው ስሌት እንደ ከዚህ ቀደሙ ሕዝብ ያገኘውን ድል ለመንጠቅና ሥልጣን ላይ ቁጢጥ ለማለት ከሆነ አድፍጣችሁ ያላችሁት የናንተ መደራጀት ገደል ይግባ እንድንል ይገፋናል።ምክንያቱም ሕዝቡ አሁን የሚፈልገው-፦ የድርጅት ብዛት ሳይሆን ጠንካራ የሕዝቡን ትግል በመምራት ወደ ፊት የሚያራምድ ሁሉም ጎሳዎችና ነገዶች በእኩልነት፤በአንድነትና በጋራ ተከባብረውና ተባብረው የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን የሚገነባ፤የሕግ የበላይነትና ፍትሕ የሰፈነባት፤ሉዓላዊነቷ የተከበረና የታፈረ ሥርዓት የሚያመጣ ለሕዝብ ተአማኒነት ያለውን ድርጅት ነው።

    ዛሬ በቅርብም ይሁን በሩቅ የሚገኙ የኢትዮጵያ ወዳጅ አገሮች ፊታቸውን ዞረውብናል እንዲያውም በአገር ውስጥና በውጭ አገር ኢትዮጵያውያን እየታደኑ እንዲታሰሩ፤ለሰው በላው ህወሃት ተላልፈው እንዲሰጡና እንዲገደሉ እያደረጉ ነው።ኢትዮጵያውያን አገር ጥለው እንዲሰደዱ የሚያደርገውን አንኳር ጉዳይ እንመልከት ካልን፦ተወልደው ባደጉበት አያት ቅድመ አያቶቻቸው ደማቸውን አፍስሠው፤አጥንታቸውን ከስክሰው አስከብረው ባቆዩአት አገራቸው እንዳይኖሩ ያደረገው ህወሃት ነው።ህወሃት ሀብታቸውን ዘርፎ በድህነትና በችግር እንዲማቅቁ አድርጓል፤ያስራቸዋል፤ይገድላቸዋል፤አስሮ ክብርን በሚነካና በእጅጉ በየትኛውም አገር ታይቶና ተሰምቶ በማያውቅ ሁኔታ እርቃናቸውን ሆነው የሚመረመሩባትና ራሳቸውን ወደታች ዘቅዝቆ ወፌ ይላላ የመገረፉባት፤በፈላ ዘይት የሚጠበሱባት፤በቀዝቃዛ ውሃ የሚሰቃዩባት የባርያ ሽያጭ በቀረበት በዚህ በ21ኛው ክፍለ ዘመን ወጣት ሴቶችንና ወንዶችን ወደ የተለያዩ አገሮች በኩንትራት ለዘመናዊ ባርነት አሳልፎ የሰጠ ከሃዲና ወሮበላ ቡድን በሥልጣን ላይ ያለባት አገር ናት ኢትዮጵያ ።ታዲያ ይህ ያላሰደደ የቱ ነው የሚያሰድደው?ከስደቱ ባሻገር ሌላ የተሻለ አማራጭ የለም ወይ?ለሚለው አማራጭ አለው።ራስን ነፃ ለማውጣት መታገል።ዳሩ ግን ትግሉን ከማን ጋር?የሚል ጥያቄ ሲነሳ የተቃዋሚ ኃይሎች የሚመልሱት ጥያቄ ይሆናል።

        አንድ በቅርቡ ኢትዮጵያ ደርሶ የተመለሰ ሰው እንዳወራኝ ኢትዮጵያ ውስጥ ከሆቴል ሰዎች በልተው ያተረፉትን ምግብ(ቡላ) ከመደፋቱ በፊት ከሆቴሉ ሠራተኞች በመረከብ ከሰባት መቶ እስከ ስምንት መቶ ደመወዝ የሚከፈላቸው ቤተሰብ ማስተዳደር የሚያስችል አቅምና ተመጣጣኝ ክፍያ ስለማያገኙና የኑሮ ሁኔታው ጣራ ላይ በመወጣቱ የተመለሰ ምግብ ገዝተው ቤተሰብ እየመገቡ እንደሚገኙ ገልጾልኛል። በአንጻሩ ደግሞ እግረ-ደረቁ የህወሃት ቡድን ኢትዮጵያ በኢኮኖሚ አደገች ተመነደገች እያለ የተለመደ የውሸት ቱልቱላውን ሲያናፍስ ይስተዋላል።

     ከሩቅ ሆኖ መተንበይ አዳጋች ቢሆንም በሕብረተሰቡ ላይ እየደረሱ ያሉት የደረሱት በውጭም በሀገር ቤትም የተፈጠሩት ሁኔታዎች እንደሚያመለክቱት በወርሃ ሚያዝያ የመን፤ደቡብ አፍሪካና ሊቢያ ላይ ብቻ በክርስቲያን ኢትዮጵያውያን ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የተሠነዘረብን ወርሃ ሚያዝያ የኢትዮጵያ ጥቁር ቀን የሆነበት የካቲት 12 እንድናስብ ያደረገን የህወሃት ሥርአት አላኖር አላስኬድና አላስቀምጥ ብሏቸው ዳቦ ፍለጋ ሲንከራተቱ ሕሊናን በሚሰቀጥጥ ዘግናኝ ሁኔታ እንደ በግ ሲታረዱና በጥይት ሲቆሉ ተመልክተናል።ይህ በእውነቱ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ ለሚያምን ሁሉ እንቅልፍን የሚነሳ፤ብሔራዊ ሞራልን የሚሰብር ሁኔታ ተከስቷል፤ደርሶብናል።ይህን ሁሉ ችግር ያመጣብን የጠባቦችና የጎጠኞች የህወሃት ድናቁርቶች ስርአት ነው።በመግደል በማሰርና በማሰደድ የሀገር ሀብት በመዝረፍ የስርአት አልበኝነት ስርአትን በማራመድ የሥልጣንን እድሜ ለማራዘም በከንቱ መንደፋደፍ ይህንም እንኳን ለማድረግ አቅም ይጠይቃል። ህወሃትን፦ ሕገ-አራዊቱ ሕግ አያስጥለውም።

ይህ በአገር በቀል ጣሊያኖች እየተካሄደ ያለው ፋሽስታዊ ሥርዓት እንዲያከትምና እንዳይደገም እኛ ኢትዮጵያውያን ምን ልናደርግ ይገባል?

  • አንድ ላለመሆን በጋራ ጽናት እንዳይኖረን መደማመጥ፤መከባበር፤መተማመን እንዳንችል የተስማማንና ለህወሃት ለም አፈር ሆነን በግል ባኅርያችን አገርን በጠራራ ፀሐይ የሚሸጥ፤ሕዝብን የሚፈጅና የሚያስፈጅ ከባእዳን ወግኖ የሚሞግተንና የሚወጋንን ህወሃትን የስልጣን ዘመኑ እንዲራዘምለት በማድረግ እኛው ራሳችን ነዳጅ ሆነን እያገለገልነው ስለምንገኝ መጀመርያ ከዚህ አደጋ ራሳችን ማውጣት አለብን።
  • አሁን እንደምንመለከተው በተቃዋሚ ኃይሎች አካባቢ (እየተፈፀሙ)እየተሠሩ ያሉት ሁኔታዎች ችግሮችን ተባብሰው እንዲቀጥሉ የሚያደርጉ በመሆናቸው በድርጅቶች ዙርያ ያለው ችግር ሳይቀረፍ እታገላለሁ ማለት በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ ስለሚሆን ይህን የማጋለጥና ሕዝብ እንዲያውቀው ማድረግ ይህ ሲሆን ተገደው ለሕዝብ ፍላጎት ተገዥ መሆናቸውን ማረጋገጥ።(ለአብነትም የቅንጅት፤መኢአድና የአንድነት ወርሾች ህወሃት ያደራጃቸው የህወሃት ጉጅሌዎች ናቸው)፤በውጭም ኢህአፓን ብቻውን ብንጠቅስ በአሁኑ ሰአት ከሶስት የተከፈለበት ሁኔታ ይገኛል፤የአርበኞች ግንባር ከሁለት ከተከፈለ ቆይቷል።በሌሎች ዙርያም ቱጃሩ እጀ ረጅሙ ህወሃት ላለመኖሩ ማስተማመኛ የለንም።በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ ሰርጎ መግባትና ማደናቀፍ የህወሃት ተግባር ስለሆነ ራስን ማጥራት ያሻል።
  • ተጨባጩን የህወሃት ሁኔታ ስንመለከት በሕዝብ ዘንድ አመኔታን ያጣ ወይም ከሕዝቡ መነጠሉን አምኖ ሁሉንም ነገር በኃይል ለማስቀጠል እየጣረ ያለበትና አባላቱም እየጣሉ መጥፋትና ማጉረምረም መጀመራቸው አንድ በመጨረሻዋ ሰአት ላይ የሚገኝን ስርዓት የሚያመላክቱ መሆናቸውን ያሳየናል።እዚህ ላይ ትኩረት አድርጎ በመሄድም ብዙ ድክመቶች ይታያሉ፡ህወሃት የሕዝቡን የትግል ስሜት ለመስለብ አቅጣጫ ሲቀይር ህወሃት የሚያናፍሰውን መከተል ሳይሆን በተፃራሪው የመቀስቀሻ ነጥቦችን አውጥቶ ማጋለጥ ያስፈልጋል።ህወሃት ልማታዊ መንግሥት ሊሆን አይችልም ምናልባትም ፎቆች፤መንገዶችና ቤቶች ተገንብተው ሊሆን ይችላል እነዚያ ግን ሀብትነታቸው የማን ነው? ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል።ህወሃትን ራሱን ሊጠቅም የሚችል ነገር ካልሆነ በስተቀር በፍጹም ለሕዝብ ጥቅም የሚሰጥ ልማት እንደማይሞክረው የተረጋገጠ ነው።
  • ጅብ እንደ አገሩ ይጮሃል እንዲሉ አንዳንዶች ህወሃትን በሰላማዊ መንገድ ታግለን እናስወግዳለን ብለው የተነሱ ሲሆን አንዳንዶቹ ደግሞ ህወሃት የሰላማዊ ትግል ምንነት የሚገባው ድርጅት ስለአልሆነ እሱ በመጣበት መንገድ በመሄድ የጫካ ሕጉንና ሰው በላውን የህወሃትን ስርዓት እናስወግዳለን ብለው ራሳቸውን በተቃዋሚ ኃይል የመደቡና የተሰለፉ ይገኙበታል።ይህ ሰልፍ ህወሃት በራሱ አምሳል የለጠፋቸውን አይጨምርም።ከዚህች ነጥብ ላይ አንድ መጨመር የምፈልገው ነገር ቢኖር ህወሃት በመሃላችን እየገባ አንድነታችን አብሮነታችን ሲንደው እኛስ ለምን እሱ በሄደበት ሄደን አንከፋፍለውም?እርስ በርሳቸው እንዲባሉ አናደርጋቸውም?ለምሳሌ ህወሃት ብአዴን ብሎ የሚጠራውን ድርጅት ወስደን አማራ የሆኑትን አማራ ያልሆነው ድርጅት እንደ በግ ሲነዳቸውና እጃቸውን ቆልምሞ ሲያስር ሲያሳድድ፤ሲገድል፤ሲዘርፍ በቃ እጅህን ሰብስብ እንዲሉት ማድረግ አይቻልም ወይ?ነበረብን አሁንም ማድረግ አለብን።
  • ከሁለቱም ሰልፎች አንዳንድ ወስደን ብንጠናከር ህወሃት የማይወድቅበት አንድም ምክንያት የለም። ነፍጥ ካነሱት አንዱን ከሰላማዊ ተሰላፊዎች አንዱን ብንመርጥና የመምራት ኃላፊነቱን እንዲወስዱ ብናደርግ በሰው ኃይል በገንዘብና በተለያዩ ቁሳቁሶች አቅም መፍጠር ይቻላል። ሁልጊዜ በአንድ አይነት መንገድ እየሄዱ መታገል ስልትን ማስበላትና ትግሉን ከምንኮላሸት አያድነውም። የትግል ስልቶች እንደየ ወቅቱ የፖለቲካ ትኩሳት መቀያየር ይኖርባቸዋል።በግሌ እንደተመለከትኩት ሁለቱም አሰላለፍ በብዛኛው እያስቀጨ ያለው የአማራውን ነገድ ሕዝብ ነው ለምን? ያልን እንደሆነ፦

       1/ ህወሃት ሰበበ-አስባብ ፈልጎ ማጥፋት የሚፈልገው ገና ድርጅቱ ሲመሰረት ዓላማየ ብሎ የተነሳበትም የአማራውን ሕዝብ  በመሆኑ፡ 2/ አሁን ላሉት የተቃዋሚ ኃይሎች የመታገያ ነጥብ መነሻ የሚሆኑ ብዙ ምንያቶች ያሉት በመሆኑና የአማራ ነገድ ሕዝብ የሚኖርበት አካባቢ ለትግል ጥሩ የተፈጥሮ አቀማመጥ ስለአለውና ከጎረቤት አገር የሚያዋስን በመሆኑ እንዲሁም በኢትዮጵያ የሉዓላዊነት ጉዳይ የጎላ ታሪክ ያስመዘገበ ኃላፊነትና ግዴታውን የሚያውቅ ሕዝብ በመሆኑ አካባቢው ሊመረጥ ይችል ይሆናል። 3/ ከአንድ ጹሑፍ ያገኘሁት መረጃ እንደሚገልጸው በድሮ ጊዜ የወሎ የመሬት ቆዳ ስፋት 94.400 ኪ/ሜትር የጎንደር መሬት ቆዳ ስፋት 74.200 ኪ/ሜትር፤ የትግራይ 65.900 ኪ/ሜትር ሲሆን በአሁኑ ሰአት የትግራይ መሬት የቆዳ ስፋት 102.000 ሆኖ ይገኛል።ይህ ማለት ህወሃት ከሁመራ፤ወልቃይት፤ጠገዴ፤ጠለምት፤ዳንሻን ከጎንደር ራያና ሰቆጣ አበርገሌን ከወሎ በመውሰድ ያደረገውን ትግራይን የማስፋፋት ሊሎች አጎራባች ክፍለ ሀገሮችን የማሳነስና ሕዝቡን የማፈናቀል አብይ ዓላማ መሆኑን የሚገልጽ አንድ የመታገያ አጀንዳም ስለሚሆን የትግሉ ማዕከል ሊሆን ይችላል ዳሩ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱን የሚያመዝን እዳይሆን በጥናት የተደገፈ የትግል ስልት መቀየስን ይጠይቃል ይህ የተሟላበት አካሄድ አይመስልም።

  • በሀገር ቤትና በውጭ የሚገኘውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ማቀናጀትን በሚመለከት 1/ ዲያስፖራው ሊያበረክት የሚችለው አስተውጾ ምንድን ነው?ብሎ መለየት 2/ በሀገር ቤት ያለው ሕዝባዊ አመጽ ሊደረስበትና አመራር ሊያገኝ መቻል አለበት እንዴት ብሎ ለሚለው ጥያቄ፦1/ በሰላማዊ ትግል ላይ የሚገኙትን መጠቀም 2/ የህቡእ አደረጃጀትን ስልት መከተልና ቴክኖሎጅውን በመጠቀም መረጃ መለዋወጥ አስፈላጊ ናቸው ብየ አምናለሁ።በተለይ ለዚህ እኩይና ፀረ-ሕዝብ የሆነ የህወሃት የጀርባ አጥንት በሆኑት የደህንነት፤የመከላከያ፤የፌደራልና የየክልል ፖሊስ፤የክልል ፈጥኖ ደራሽ፤የአጋዚ ሠራዊት እየተባለ በሚጠራውና በካድሬው አካባቢ የሚደረጉትን እንቅስቃሴዎች በሰላ ሁኔታ መከታተል።

    አገርን ለመገንባትና ለማበልፀግ ጤናማ ሕብረትሰብ ፤የተማረና በሙያ የሰለጠነ ኃይል እንዲኖረን ለማድረግ ከድኻው ሕዝብ የሚሰበሰበውን ግብር ለትምህርት በመበጀት ሁኔታው በሚፈቅደው መጠን በሀገር ቤትም ሆነ በውጭ በቁጥሩ የማይናቅ ምሁር ኢትዮጵያ እንዳላት ይታወቃል። ይሁን እንጅ ይህ አስተሳሰበ ኩድኩድ የህወሃት ቡድን የኢትዮጵያ ምሁራንን ኮቴ ኮቴያቸውን እያለ አገር ጥለው እንዲሄዱ አድርጓል፤የቀሩት ዱላውንም ችለን በሀገራችን ያሉትን ደግሞ የህወሃት አባል አይደላችሁም በማለት ከሥራ ገበታቸው እንዲፈናቀሉና ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን እንዳያስተዳድሩ አድርጓል።በውጭ ያለው ምሁርም እባብ ያየ በልጥ ይሸሻል እንዲሉ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ሕዝቡንና አገሩን እንዳያገለግል በመደረጉ የባእዳን አገልጋይ ሆኖ ይገኛል።

   እኛ ኢትዮጵያውያን በውጭው ዓለም የምንታወቀው ድህነትና በርሃብተኛነት ብቻ እንዲሆን ሆነ ተብሎ የተሸረበብን ተንኮል ፍጥነቱንና እድገቱን ጨምሮ ስደተኛ የሚለው ታክሎበት ወገኖቻችን በሀገር ውስጥ ከመዋረድና ሶስተኛ ዜጋ ሆኖ ከመገኘት ሞትን ለመጋፈጥ ወይም ለጊዜው ሞትን አምልጦ ዳቦ በልቶ ለማደር የሰሐራን በርሃ ሲያቋርጡ ርሃብ፤አውሬና የውሃ ጥማት የፈጃቸው፤ባህር አቋርጠው ሊወጡ ሲሉ ያለቁት፤በየመን፤በደቡብ አፍሪካ፤በሳኡዲ ዐርብያ በግፍ ያለቁት፤ሊብያ በጥይት የተቆሉትና በቢላ እንደ በግ የታረዱት በውስጣችን እንደ እሳት እያንገበገበን ባለበት ወቅት ህወሃትና የህወሃት ግብረ በላዎች መሳለቂያ ሲያደርጉን ተመለከትን ከዚህ ወዲያ ውርደትና ሞት የለም።ብሔራዊ ሞራላችንን ነክተውታል፤ከወላጆቻችን የወረስነውን አኩሪ ታሪክ አርክሰዋል፤ድንበራችን አስደፍረዋል፤ሉዓላዊነታችንን አስደፍረዋል፤አንገታችን ደፍተን እንድንሄድና አደባባይ እንዳንወጣ አድረገውናል። ጎበዝ!! ለትግልና ህወሃትን ለማስወገድ እነዚህ በቂ አይደሉም?ጥያቄየ አንድ እንሁን አንዲት አገርና አንድ ሕዝብ ነው ያለን የሚለው ነው።

     ድርጅቶች በበዙ ቁጥር የሕዝብ ኃይልና የገንዘብም ይሁን የቁሳቁስ(ማቴርያል) አቅማችን ያንኑ ያህል ነው የሚያንሰውና በውስን አቅም የጥቃት ሰለባ እንድንሆን የሚያደርገን።ለምን ለህወሃት የሚመች ለም መሬት ሆነን እንገኛለን? ሕዝባችን ሲጨርሱት፤ተራ በተራ ነጣጥለው፤ከፋፍለው ሲፈጁት ምን እየጠበቅን ነው?መካካዱ፤አለመተማመኑና በጥርጣሬ የመተያየቱ አባዜ ያብቃ !! ተራውን ለህወሃት እንስጠውና እኛ በአንድነት በጋራ ቆመን የጋራ ጠላታችን የሆነውን የህወሃትን ግባተ መሬት እናፋጥንለት።በምርጫው ዋዜማ እያሰማ ያለውና በምን መሰናዶ ላይ እንዳለ ይታወቃል ዛሬም እንደ ምርጫ 1997ቱ ወገኖቻችን የሞት ሰለባ እንዳይሆኑ እንታደጋቸው በግንባር ቀደምትነት የተደራጁ የተቃዋሚ ኃይሎች ኃላፊነት ቢኖርባቸውም እያንዳንዱ ሕዝቡን አገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በዚህ ጉዳይ ላይ ሊረባረብበት ይገባል።

               እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከጥፋት ይጠብቃት!!

    በባእድ አገር በአሰቃቂ ሁኔታ የሞቱ ወገኖቻችን ነብስ ይማር ቢተሰባቸውን ጽናት ይስጥልን!!

                          ሕዝባዊ እንብኝተኝነቱ ይጠንክር!!!

                                       ገብርየ በለው።                                                                            

The post   የሀገር ሀብት ዘረፋ፤ስደት፤እሥራትና ግድያው እንዲቆም ህወሃትን ከሥልጣኑ አውርደን መጣል ግዴታችን ነው። appeared first on Zehabesha Amharic.

የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ በደህንነቶች ታፍነው ተወሰዱ

$
0
0

(ህብር ሬዲዮ) መኢአድን ለመምራት በሕጋዊ መንገድ ተመርጠው አመራሩን በያዙ በጥቂት ቀናት በምርጫ ቦርድ ሕገ ወጥ ውሳኔ በፌዴራል ፖሊስ ከቢሮ ተባረውየነበሩት ህጋዊው የመኢአድ ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ ረቡዕ ማለዳ አዲስ አበባ ቦሌ ሚካኤል አካባቢ ቴዲ ባር አቅራቢያ ከቤታቸው እንደወጡ በደህንነቶች ታፍነው መወሰዳቸውን አንድ የፓርቲው የቀድሞ አመራር ለህብር ሬዲዮ ገለጹ።
mamushet
አቶ ማሙሸት አማረ ዛሬ ማለዳ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ቦሌ ሚካኤል ቴዲ ባር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከቤታቸው እንደወጡ ሲጠብቋቸው በነበሩ የደህንነት አባላት ታፍነው የተወሰዱ ሲሁን ከቆይታ በሁዋላ ሲ.ኤም.ሲ አካባቢ ከሚገኝ ፍርድ ቤት ወስደው መልሰው ፖሊሶችና የደህንነት አባላት ቤታቸውን መበርበራቸውን ያገኘነው መረጃ አስረዳል።

አቶ ለገሰ ወልደሃና የቀድሞው በምርጫ ቦርድ እንዲፈርስ የተደረገው መኢአድ ም/የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ የአቶ ማሙሸት ከቤት ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ማታ ለሚከታተሉት የፖለቲካል ሳይንስ ትምህርት ፈተና ስላለባቸው ላይብረሪ ለመግባት በወጡበት ወቅት በቤታቸው አካባቢ ሲጠብቋቸው በነበሩ የደህንነት አባላት በያዙት መኪና አፍነው እንደወሰዷቸው ለህብር ሬድዮ ገልጸዋል።

አቶ ማሙሸት አማረ በሁለት ጊዜ በቀናት ልዩነት በተደረገ ጉባዔ መኢአድን ለመምራት ከመላው አገሪቱ በመጡ የፓርቲው የማዕከላዊ ም/ቤት አመራሮች ቢመረጡም ምርጫ ቦርድ ምርጫውን ባለመቀበል ስልጣኔን በፈቃዴ ለቅቄያለሁ ያሉትን የፓርቲውን የቀድሞ ፕሬዝዳንት አቶ አበባው መሐሪን ከቤታቸው አምጥቶ ስልጣን ላይ ማስቀመጡን ተከትሎ ውሳኔውን በመቃወም በፍርድ ቤት በቦርዱ ላይ ክስ መመስረታቸው ይታወሳል። ክሱ በሂደት ላይ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የፓርቲውን ሕጋዊነት ለማረጋገጥ ከመንቀሳቀስ ውጭ የፖለቲካ እንቅስቃሴ እያደረጉ እንዳልነበር አቶ ለገሰ ጠቅሰዋል።

አቶ ማሙሸት በተለይ የመኢአድን አመራር ቦርዱ አልቀበልም ባለው ከጥቅምት 28-30 በተደረገ ጉባዔ መኢአድን ለመምራት በተመረጡበት ሕጋዊ ምርጫ ስልጣን ከመያዛቸው በፊትና በሁዋላ ማስፈራሪያና ዛቻ ብቻ ሳይሆን ሰፊ ክትትል ይደረግባቸው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ማሙሸት አማረ አገዛዙን በሰላማዊ መንገድ ታግሎ መጣል ይቻላል ብለው በማመን በምርጫ ቦርድ የተወሰደውን ውሳኔ በመቃወም ወደ ፍርድ ቤት ሄደው የፓርቲውን ሕጋዊ ስልጣን ለማስመለስና ትግሉን ለማስቀጠል ሲንቀሳቀሱ ነበር።

The post የመኢአድ ሕጋዊው ፕሬዝዳንት አቶ ማሙሸት አማረ በደህንነቶች ታፍነው ተወሰዱ appeared first on Zehabesha Amharic.


“አይሲስን ስንቃወም ህወሓትን አለመርሳት”–አርበኞች ግንቦት 7

$
0
0

በአይሲስ በግፍ በታረዱብን ወገኖቻችን የተሰማን ሀዘንና ቁጭት ከፍተኛ ቢሆንም እንኳን ከአዕምሮዓችን መውጣት የሌለበት ሀቅ አለ። ይህ ሀቅ “ያስጠቃን፣ ያሳረደን ወያኔ ነው” ከሚለውም ያለፈ ነው። መረሳት የሌለበት ሀቅ፣ ከአይሲስ የከፋ ጨካኝ በአገራችን የመንግሥት ሥልጣን የተቆጣጠረ መሆኑ ነው።

የህወሓት ፋሽስት ጦር በበደኖ፣ በአዋሳ፣ በሀረር፣ በጋምቤላ፣ በጎንደር፣ በኦጋዴን፣ በአዲስ አበባ፣ በሸካና መዠንገር፤ እንዲሁም በሚታወቁም በማይታወቁም የማሰቃያ እስር ቤቶች አይሲስ እየፈፀመ ካለው የባሱ ወንጀሎች በወገኖቻችን ላይ ፈጽሟል፤ አሁንም እየፈፀመ ነው። ባሳለፍነው ሣምንት እንኳን በሁመራ ወገኖቻችን የራሳቸውን መቀበሪያ ጉድጓድ ቆፍረው በጅምላ ተገድለዋል። በአይሲስና በህወሓት መካከል ያለው ልዩነት አይሲስ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሩን በቪዲዮ እየቀረፀ ለዓለም ሲበትን ህወሓት ግን እነዚሁኑ ነውረኛና አረመኔዓዊ ተግባሮችን እየፈፀመ መረጃዎች አፍኖ መያዙ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ ግን ህወሓት ሰዎችን ከነሕይወታቸው ጉድጓድ ውስጥ የቀበረ አረመኔ፣ እኩይ ድርጅት ነው።
ስለሆነም ለዓለም ሰላም ስጋት የሆነውን አይሲስን ስንቃወም የራሳችንን አይሲስ – ህወሓትን – አለመርሳት እጅግ አስፈላጊ ነገር ነው።
ginbot 7
በሌላ በኩል ደግሞ ህወሓት፣ የአይሲስን እኩይ ተግባራት ከኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች የመብት ጥያቄ ጋር እና ከዲሞክራሲያዊያዊ ፓለቲካ ፓርቲዎች እንቅስቃሴ ጋር ለማገናኘት እያደረገ ያለው ጥረት ምን ያህል አደገኛ ተግባር እንደሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲረዳው ያስፈልጋል። ዓይን አውጣ ሌባ ንፁሁን ሰው “ሌባ” እንደሚለው ሁሉ የኛው አይሲስ ራሱን ንፁህ አስመስሎ ሌሎችን “አይሲስ” ማለቱ ሊነቃበት ይገባል።

ሌላው ተያያዥ ጉዳይ ደግሞ ስለስደተኝነት የሚሰጠው ገለፃ ነው። ህወሓት ለስደተኝነት ምክንያቱ ደላሎች እንደሆኑ ይናገራል። ይህ የጉዳዩን ግንድ ትቶ ቅርንጫፎች ላይ ማትኮር ነው። ህገወጥ ደላሎች ራሳቸው ሊኖሩ የቻሉት ገንዘብ ከፍለውና የሕይወት ሪስክ ወስደው ለመሰደድ የሚፈልጉ ዜጎች በመኖራቸው ነው። ችግሩን በቅንነት ለመመርመር የሚፈልግ “ይህን ያህል ሰው የሕይወት ሪስክ እየወሰደ ከአገር ለመሰደድ ምን አነሳሳው?” ብሎ መጠየቅ እና ምላሽ ማግኘት ይኖርበታል። በሀገር ውስጥ በነፃነት ተረጋግቶ መኖር፣ ሠርቶ የማደግ ተስፋ ቢኖር ኖሮ ይኸን ያህል ሰው የአደጋውን ከፍተኛነት እያየ ለመሰደድ ይነሳሳ ነበርን? ኢትዮጵያዊው ከስደት ሊያገኝ የሚሻው ምንድነው? እንደ ወያኔ ካድሬዎች ገለፃ ከሆነ ከስደት ሊያገኝ የሚችለው አገሩ ውስጥ እያለለት ነው ኢትዮጵያዊ የሚሰደደው። ይህ ምን ዓይነት አመክኖ ነው? ከዚህ የባሰው ደግሞ ስደትንም የእድገት ውጤት አድርጎ የማቅረብ በሽታ ነው። ይህ እውነት ከሆነ፤ ህወሓት ለኢትዮጵያ አመጣሁላት የሚለው እድገት ውጤት ረሀብ፣ ስደት፣ መርዶ፣ እስር፣ ስቃይ፣ ሞት ከሆነ እንዴት “እድገት” ብለን እንጠራዋለን። ለስደተኝነት መብዛት ህገወጥ ደላሎችን ብቻ ተጠያቂ ማድረግ፤ “እኔ ከደሙ ንፁህ ነኝ” የማለት ያህል ነው። በህጋዊዎቹም በህገወጦቹም ደላሎች ውስጥ የወያኔ ሰዎች በቀጥታም በተዘዋዋሪም እንዳሉበት መረጃዎች ያመለክታሉ። ገንዘብ ባላበት ሁሉ የወያኔ እጅ መኖሩ ፀሐይ የሞቀው ሀቅ ነው። የሰዎች ዝውውር የህወሓት አንዱ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ መሆኑ የማይታበል፤ በቀላሉ ማረጋገጥ የሚቻል ሀቅ ነው።

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ በዓለም አቀፉ አይሲስ አረመኔያዊ ተግባሮች በደረሰብን የመጠቃት ስሜት ተውጠን የራሳችንን አይሲስ – አረመኔውን ህወሓት – እንዳንረሳ ያሳስባል። መቆሚያው ለማይታየው የዜጎቻችን መሰደድ መንስኤዎች የነፃነት እጦት እና የኑሮ እድሎች መጥበብ መሆናቸው እንዳንዘነጋ ይጠይቃል። ንቅናቂያችን እነዚህ ተያያዥ ችግሮች ሁሉ የሚቃለሉት ህወሓትን አስወግደን በምትኩ ፍትህ፣ ነፃነት፣ እኩልነትና ዲሞክራሲ የሰፈኑባት ኢትዮጵያን ስንመሰረት ብቻ ነው ይላል። ለዚህም ደግሞ ሁላችንም በያለንበት የበኩላችንን ተሳትፎ ማድረግ ይገባናል። ሁለገብ ትግል ማለት፤ እያንዳንዱ ከሚመስለው ጋር እየተደራጀ በያለበት ወያኔ ማስጨነቅ፣ ማዋከብና ማዳከም፤ በመጨረሻም በጋራ ትግል ማስወገድ ማለት እንደሆነ ልብ እንበል። በሁለገብ ትግል ለውጥ የሚመጣው ሁሉም እንደ አቅሙ በሚያደርገው ተሳትፎ በመሆኑ፣ የሚቻለንን በማድረግ የለውጥ ጠባቂ ሳንሆን፣ የለውጥ አምጭ አካል እንሁን ይላል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post “አይሲስን ስንቃወም ህወሓትን አለመርሳት” – አርበኞች ግንቦት 7 appeared first on Zehabesha Amharic.

የዓረና_መድረክ የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶች በውቅሮ ተዘረፈ

$
0
0

Zehabesha News
አምዶም ገብረሥላሴ እንደዘገበው

የዓረና_መድረክ ኣማራጭ ፖሊሲዎች የታተመበት የውቅሮ ክልተ ኣውላዕሎ, ኣፅቢ ወንበርታ, ሓወዜን, ሳዕሲዕ ፃዕዳ እምባ ምርጫ ክልሎች ለህዝብ የሚታደል ከ12 ሺ በራሪ ወረቀቶች ባልታወቁ ሰዎች የኣቶ ቴድሮስ ሞገስ የኪራይ ቤት ቁልፍ በመስበር በጠራራ ፀሃይ ሊዘርፉት ችለዋል::

ዘረፋው የተፈፀመው በ04/ 09/ 2007 ዓ/ም ከቀኑ 9: 30 ሰዓት ሲሆን ኣቶ ቴድሮስ ከቤቱ ሲወጣ ወድያውኑ ነው:: የኣቶ ቴድሮስ የፓርቲ ኣባልነት መታወቅያ ሳይቀርና የተለያዩ የመድረክ ሰነዶችም ተዘርፈዋል::

የከተማዋ ካድሩዎች ለኣካራዩ ኣቶ ቴድሮስን ከቤቱ እንድያስወጣው በተደጋጋሚ ግዜ ከፍተኛ ማስፈራርያ ዛቻዎች ሲደርሱባቸው ነበር::
የከተማው ፖሊስ ስለ ወንጀሉ ኣብዮቱታ በቀረበበት ወቅት ጉዳዩ ለመመዝገብና ለማጣራት ከፍተኛ ዳተኝነት በማሳየት ጉዳዩ ተድበስብሶ እንዲቀር ያለው ፍላጎት ኣመላክተዋል::
ዝርፍያው የፖሊስ ወይም ድህንነት እጅ እንዳለው የሚያመላክቱ ነገሮች ለፖሊስ ኣሳውቀናል::

ጎበዝ ህወሓት የመድረክ በራሪ ወረቀት መዝረፍ ያልተወች የምርጫ ካርድ ትተዋለች ብላቹ ትጠብቃላቹ? ለነገሩ መስረቅ የለመደ ኣምባሻ ይልሳል ነው የሚባለው::
በተያያዘ ዜና በውቅሮ ክልተ ኣውላዕሎ ምርጫ ክልል የክልል ምክር ቤት እጩ ተወዳዳሪ የሆነው ኣቶ ሃይለኪሮስ ታፈረ በኣይናለም ቀበሌ ዓዲ ወረማ በተባለ የነበረ ገለባ በእሳት እንዲያያዝ በመደረጉ ሙሉ በሙሉ እንደወደመና ገለባው የተቀመጠበት ቤቶችም ወደ ኣመድ እንደተቀየሩ ታውቀዋል:: የእሳት መያያዝ ወንጀሉ በህወሓት ኣመራሮች የታዘዘና የተቀነባበረ ሴራ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው::

ህወሓት በዓረና_መድረክ ፓርቲና ኣባላቱ እያደረሰች ያለው ዓፈናዎች ለማመን የሚዳግቱ ናቸው::

The post የዓረና_መድረክ የቅስቀሳ በራሪ ወረቀቶች በውቅሮ ተዘረፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

መድረክ በጃንሜዳ የፊታችን ግንቦት 8 ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ (የፈቃዱን ወረቀት ይዘናል)

$
0
0

ከመድረክ የተላለፈ ጥሪ:-
መድረክ በአዲስ አበባ ከተማ ለግንቦት 8 ህጋዊ እውቅና ያገኘ ህዝባዊ ስብሰባ ጠራ፡፡ የውይይቱ ዓላማ የ2007 ምርጫ አስመልክቶ ከአዲስ አበባ ህዝብ ጋር ለመወያየት ነው፡፡ ህዝባዊ ውይይቲ ከጥዋቱ 3፡00 ጀምሮ እስከ ከቀኑ 8፡00 ይካሄዳል፡፡ ስለሆነም መልእክቱ ለመላው ህብረተሰብ እንዲዳረስ እናድርግ…ውይይቱ የተሳካ እንዲሆን የበኩላችንን ሚና እንጫወት፡፡
mederek

The post መድረክ በጃንሜዳ የፊታችን ግንቦት 8 ሕዝባዊ ስብሰባ ጠራ (የፈቃዱን ወረቀት ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ ለይስሙላ –አክሎግ ቢራራ (ዶር)

$
0
0

አክሎግ ቢራራ (ዶር)

electionበቅርቡ ኢትዮጵያዊያንን ብቻ ሳይሆን የዓለምን ሕዝብ በሚዘገንን ሁኔታ የቀሰቀሰው፤ ያስለቀሰውና ያስቆጣው የኢትዮጵያዊያን ክርስቲያኖች በሊቢያ በሚገኙ የአይሲስ ሽብርተኞች መታረድና በጥይት መርገፍ፤ ወደ አውሮፓ ሲጓዙ በጀልባ መሞት፤ በደቡብ አፍሪካ በሰላም ሲኖሩ በቤንዚን ተቃጥለው መሞት፤ በየመን የርስ በርስ ጦርነት በሳውዶዎች አየር ኃይል ተባራሪ ጥይት መሞት ወዘተ ብቻ አይደለም። በአወንታዊውም፤ የግብፅ መንግሥት ለሞት አደጋ የተዳረጉ ወገኖቻችን ከአደጋ ማትረፉ ሌላው ያልተጠበቀና የሚያበረታታ ዜና ነው። ኢትዮጵያዊያን በያሉበት ጎሳና ኃይማኖት፤ ሃብትና ሞያ፤ ጾታና እድሜ ሳይለዩ በሰብእነታቸውና በኢትዮጵያዊነታቸው ተባብረው ድምጻቸውን ማሰማታቸውም የሚያበረታታ ክስተት ነው። አሁንም ተባብረን ከጩኸት ወደ ድርጊት እንድንራመድ አሳስባለሁ።

የኢትዮጵያዊያን የስደት ኑሮ አስከፊ ገፅታ ዲሞክራሳዊ በሆነችው ኢስራኤልም ሲካሄድ ቆይቶ ሰላማዊ ሰልፍና ግጭት አስከትሏል። የኢስራኤል መንግሥት ለሌሎች ኢስራኤላዊያን የሚያደርገውን እንክብካቤና የዜግነት መብት ለኢትዮ-ኢስራኤላዊያንም በማያሻማ ደረጃ መስጠትና ሰብአዊ መብታቸውን ማስከበር አለበት። ኢትዮጵያዊያን ጥቁሮች በመሆናቸው ራሱ ጋብዞና አባብሎ ካመጣ በኋላ ልክ እንደ አፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ዜጋ ሊያደርጋቸው አይገባም። በሃገር ቤትም እንኑር በውጭ ተቃውሟችን በየቦታው ማሰማት ግዴታችን ነው። ይኼን በሚመለከት እኔንና ሌሎችን ተመልካቾች ያስገረመን የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር በኢስራኤል የሚገኙ፤ የሃገሪቱ ዜግነት ያላቸውን ትውልዳቸው ኢትዮጵያ፤ ዜግነታቸው ኢስራኤሊ የሆኑ ወገኖቻችን አስመልክቶ ለኢስራኤል መንግሥት ያቅረበው “አቤቱታ” ነው። ለመሆኑ፤ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶችን ያፈነውና ለስደተኛነት ዋና ተጠያቂ የሆነው ገዢው ፓርቲ ከመቸ ወዲህ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ሰብአዊ መብት ጠበቃ ሆነ?

ኢትዮጵያዊያን በገፍ ከሃገራቸው የሚሰደዱበት ምክንያቶች ሶስት ናቸው። አንድ፤ ሰብአዊ፤ ማህበራዊና ፖለቲካዊ መብቶቻቸው ሙሉ በሙሉ ስለታፈኑና መፈናፈኛና አቤቱታ የሚያቀርቡለት፤ ፍትህ የሚሰጥ፤ ከፖለቲካ ቁጥጥር ነጻ የሆነ የሚዳኝና ፍርድ የሚሰጥ ተቋም ስለሌላቸው ነው። ሁለት፤ የተማረ ሆነ ያልተማረ፤ የስራ ልምድ ያለው ሆነ ገና ልምድ የሌለው የስራ እድልና የግል ተቋም ለመመስረት ሁኔታው ጨለማ ስለሆነበት ነው። ሶስት፤ በአንዳንድ ክልሎች የርስ በርስ ግጭት፤ በዜግነት መብት ተማምኖ ለመኖርና ለመስራት አለመቻልና ሌሎች እርጋታ የሌለባቸው ሁኔታዎች እየተስፋፉ በመሄዳቸው ነው። ኢትዮጵያዊያን በገፍ ከሃገር ሲበረግጉ ምን አይነት የኢኮኖሚ መርህ አስበረገጋቸው ብሎ መመራመር አግባብ አለው። ሑሉን አሳታፊ፤ ሕዝብን ማእከል ያደረግና ለሕዝብ አገልጋይ የሆነ የእድገት መርህ ለአብዛኛው ሕዝብ እድል እንደሚከፍት የሌሎች ሃገሮች የእድገት ታሪክ ያስተምረናል።

ዛሬ ወጣት ሴትና ወንድ፤ ገጠሬና ከተሜ፤ መሃንዲስ፤ አውሮፕላን ነጅ፤ ሃኪም፤ መሃንዲስ፤ አስተማሪ፤ ኃብታም፤ ድሃ፤ የተለያዩ የኃይማንት መሪዎችና ተከታዮች፤ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ትግሬ፤ ጉራጌ፤ ሶማሌ፤ ወላይታ፤ አኟክ ወዘተ ሳይለዩ በገፍ ይሰደዳሉ። ገዢው ፓርቲ ራሱ “የሰው ነጋዴ ነው”፤ የስራ እድል አለመኖርንና የፖለቲካ ተቃውሞን ችግሮች የሚፈታው በስደት ነው የሚሉ ታዛቢዎች ብዙ ናቸው። ከአራት መቶ በላይ ፈቃድ ተሰጥቷቸው ወገኖቻቸውን ለትርፍ የሚያስተናግዱ የሰው ነጋዴዎች (Human Traffickers) አሉ። ፈቃዱን የሰጠው መንግሥት መሆኑ ሊካድ አይችልም። ሊያቆመውም የሚችል መንግሥት ነው። አግባብ ያለው ጥያቄ ይኼን እንደ ዓባይ ወንዝ ጎርፍ የሆነ የሰው አስበርጋጊ ሁኔታ ምን አይነት የኢኮኖሚና የፖለቲካ ስርዓት ፈጠረው? የሚለው ነው። “የሃገር አንበሳ” የሆነው አገዛዝ ለዚህ ግዙፍ መበርገግ (Exodus) መልስ የለውም። የኢትዮጵያ ችግሮች ሊቀረፉ የሚችሉት በሁሉም የፖለቲካ፤ የማህበረሰብና የኃይማኖት ተከታዮች ተባባሪነትና ተሳታፊነት ብቻ ነው። መበርገጉን ያመጡት ተቃዋሚ ፓርቲዎች አይደሉም። እርጋታ እንዳይኖር ያደረጉት “በሕገ መንግሥቱ መሰረት እንወዳደር” የሚሉት፤ ወይንም በእስር ቤት የታጎሩት፤ ወይንም ከሃገር የተሰደዱት ኢትዮጵያዊያን አይደሉም። ተቃዋሚው ኃይል የሚታገለው ለፍትህ፤ ለእኩልነት፤ አግባብ ላለው የእድል ክፍተት፤ ለዲሞክራሳዊ አገዛዝና ለሕግ የበላይነት ነው።

ነጻ፤ ፍትሃዊ፤ ክፍትና አግባብ ያለው ምርጫ አብሮና ተባብሮ ብሄራዊ ችግሮችን ለመፍታት ያስችል ነበር። የዚህ ትንተና ዋና መከራከሪያ ነጥብ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት እንደሆነው አሁንም መንግሥትን በሕዝብ ድምጽ የመለወጥ እድሉ አይሳካም የሚል ነው። ምክንያቱም፤ ህወሓት/ኢህአዴግ እውነተኛ የሆነ፤ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የሚሳተፉበት የፖለቲካ ምህዳር ከልክሏል። ለሕዝብ አገልጋይና ጠበቃ የሆኑ የመገናኛ ብዙሃንንና የማህበረሰብ ድርጅቶችን አውድሟል። አግባብ ያላቸው የአገርና የውጭ ታዛቢዎች የሚሳተፉበት ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ እንዲካሄድ አልፈቀደም። የአውሮፓ የጋራ ማህበር በምርጫው አልሳተፍም ያለበት ዋና ምክንያት ገዢው ፓርቲ በተከታታይ ያሳየው ማጭበርበርና አፈና የሚደገም መሆኑን ስላመነበት ነው። ገዢው ፓርቲ በተደጋጋሚ ያሳየው ልምድ፤ ምንም አፈና ለሌለበት የፖለቲካ ውድድርና የመንግሥት ለውጥ ተገዢ እንደማይሆን ነው። ይኼን ያልኩበትን ምክንያቶች ባጭሩ ላስቀምጥ።

በ1995 ዓም የጸደቀው ሕገ መንግሥት መግቢያ ዜግነትን መሰረት ያደረገ፤ ለመላው ሕዝብ ተጠሪነትና ሃላፊነት ያለው ሁኖ አልተቀረፀም። አገልጋይነቱ ለጎሳ ልሂቃንና ለአንድ ፓርቲ ስብስብ በሚሆን ብልሃት የተዋቀረ ነው። መግቢያውና አንቀፅ ስምንት “እኛ የኢትዮጵያ ብሔሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉዓላዊ ሥልጣን ባለቤቶች” ነን ይላል። የትግራይ፤ የኦሮሞ፤ የጉራጌ፤ የአማራ ወዘተ ሰፊ ሕዝብ ቀጥታ የሆነ “ሉዓላዊ ሥልጣን” ያለው ኃይል ነው የሚል፤ ወይንም ሕዝብ የሥልጣን መነሻና መድረሻ መሆኑን ህጋዊ መልክ ለመስጠት ነው። ሕዝብ የፖለቲካ ሥልጣን ባለቤት ለመሆን አልቻለም። ቢሆን ኑሮ ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰብአዊ መብቶች ይከበራሉ፤ ቀጥተኛ የሆነ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ተሳትፎና ውድድር ይኖራል። ሕገ መንግሥቱ ያጠናከረው የአንድ ፓርቲን ፍፁም የሆነ ተከታታይነትና የጎሳ ልሂቃንን የበላይነት መሆኑን በጥቂት ምሳሌዎች ለማሳየት ይቻላል። አንቀጽ አስር (i) “ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች ከሰው ልጅ ተፈጥሮ የሚመነጩ የማይሰጡና የማይገፈፉ ናቸው” ይላል። በስራ ሲተረጎም፤ ማንኛውም ግለሰብ ወይንም ስብስብ መብቱን ተጠቅሞ ገዢውን ፓርቲ ለመተቸት፤ አማራጮችን ለማቅረብና ሰላማዊ ሰልፎችን ለማካሄድ መብቶቹ የተከበሩ ናቸው ማለት ነው። ይኼ በኢትዮጵያ አይታሰብም። Washington Post Editorial Comment, “In Ethiopia, a Chilling Message,” እንዲህ ሲል ደምድሟል። “Over the past decade, the Ethiopian government, which controls the country’s main media outlets, has displayed varying degrees of appetite for free political discourse” and mentions the 2005 contested election at which Ethiopians were massacred and that the ruling party annulled when it saw ominous signs of losing. ከአስር ዓመታት በኋላ የኢትዮጵያ የፖለቲካ፤ የኃይማኖትና የማህበረሰብ ሁኔታዎች ተባብሰዋል። የጋዜጠኞችንና የብሎገሮቹን አሰቃቂ ሁኔታ አስመልክቶ የፖስቱ ትችት እንዲህ ይላል። “The Ethiopian government has rejected criticism from Western governments and human rights groups about its handling of the case. It asserts the bloggers are on trial for attempting to sabotage the state.” ገዢው ፓርቲ ለሰብአዊ መብቶችና ለነጻነቶች መገፈፍ የሚሰጠው ምክንያት ተመሳሳይ ነው፤ “አመፀኛ፤ ሽብርተኛ፤ ፀረ-እርጋታ፤ ጸረ-ሰላምና ፀረ ልማት” የሚሉ።

የሰብአዊ ድርጅቶች የሚሉት ገዢው ፓርቲ ከሚለው የተለየ ነው። ለምሳሌ፤ ፍሪደም ሃውስ “ኢትዮጵያ ነጻ ካልሆኑ ሃገሮች መካከል አንዷ ናት” ይላል። The Committee to Protect Journalists (CPJ) በተደጋጋሚ ያወጣው ዘገባ “ኢትዮጵያና ኤርትራ በአፍሪካ ጋዜጠኞችን ከሚያስሩና ከሚያሳድዱ መንግሥታት መካከል አንደኛና ሁለተኛ” መሆናቸውን አስምሮበታል። Human Rights Watch የኢትዮጵያ መንግሥት እርዳታን ለጎሳና ለፖለቲካ አድልወ፤ ለአፈናና ለሙስና እንደሚጠቀምና በፖሊሲ ደረጃ የኢትዮጵያ ልማት በማህበረሰብ አገልግሎት በዜጎች የኑሮ መሻሻል ያልተመሰረተ መሆኑን በማስረጃ አቅርቧል። The World Economic Forum ኢትዮጵያ በሕግ የበላይነት እንደማትተዳደር፤ የሕጉ አካል የገዢው ፓርቲ መቆጣጠሪይ በትር መሆኑን አመልክቷል “The independence of the judicial system was rated 2.9 out of a possible score of 7 in a recent report by the World Economic Forum.” በእነዚህና በሌሎች መስፈርቶች ሲገመገም፤ የኢትዮጵያ መንግሥት የሚታወቀው በክህደቷን በስ ብአዊ መብቶች ገፈፋው እንጅ በሃቀኛነቱ፤ በግልፅነቱ፤ በፍትሃዊነቱና በሃላፊነቱ አይደለም።

በሊብያ መስዋእት የሆኑትን ወገኖቻችን በሚመለከት “ከጩኸት ባሻገር” በሚል ርእስ የሰጠሁትን ትችት እንደገና ላቅርብ። የግብጽ መንግሥት የሃገሩ ክርስቲያኖች በሊብያ አንገታቸው እንደ በግ ታርዶ ሲሞቱ ምንም ሳያመናታ በሽብርተኞች ላይ ዘምቷል። በቅርቡም ብዙ ኢትዮጵያዊያንን በጦር አውሮፕላኖች ተደግፎ ከሊቢይ መንጥቆ ከአደጋ አውጥቷቸዋል። እነዚህን ወገኖቻችን ፕሬዝደነት ሲሲ በካይሮ የአውሮፕላን ማረፊያ ሲቀበል ያየ ኢትዮጵያዊ “የእኛስ መንግሥት የት አለ” ብሎ ቢጠይቅና ለግብፅ መንግሥት አክብሮቱን ቢገልፅ አግባብ አለው። የኢትዮጵያ መንግሥት ተወካይ ነኝ ባዩ ግለሰብ የወገኖቻችን አንገት እንደ በግ ሲቆረጥና በጥይት ተደብድበው ሲሞቱ “ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገና በማጣራት ላይ ነን” ያለው ትውልድ የማይረሳው ከሃዲነት ነው። አንቀጽ ሰላሳ ሰባት ማንኛውም ኢትዮጵያዊ “ፍትህ የማግኘት መብት” አለው የሚለው ለፖለቲካ ጥቅም አገልጋይ እንጅ በሃገርም ሆነ በውጭ ለሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን መብት አስከባሪ አይደለም።

ገዢው ፓርቲና ደጋፊዎቹ ቢወዱም ባይወዱም፤ በሕገ መንግሥቱ ላይ የሰፈረው አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ የኢትዮጵያ አፍራሽ መሳሪያ ሁኗል። ዛሬ ማንም ሃገር ወዳድ መንግሥት የሚገዛውን ሃገር ለፖለቲካና ለኢኮኖሚ የበላይነት ትኩረት ሰጥቶ “የመገንጠል መብትን” አይደግፍም። ኢትዮጵያዊያንን ከሚያኮሩ እሴቶች መካከል የኢትዮጵያ ረጅም ታሪክ፤ ነጻነትና ሉዓላዊነት መከበር አንዱና ዋናው ነው። የእንግሊዙ ጋዤጠኛና ደራሲ ሪቻርድ ዳውደን እንዲህ ሲል አስቀምጦታል። “Ethiopia has one rich asset that much of Sub-Saharan has lost or never developed. It has been a state for a very long time, longer than Britain and most of Europe…Ethiopian connections to the Semitic world go back thousands of years, through migration and trade. Its Coptic Christianity and ceremonies were established in the third Century, AD.” ይኼን የማይገኝና የማይተካ ጥሪት ነው ገዢው ፓርቲ ሆነ ብሎ ያፈረሰውና የሚያፈራርሰው። ዛሬ የሚታየው ክስተት የአዲስ ታሪክ ፈጠራ፤ የጎሳዎች መለያየት፤ የክልሎች አዲስ መሳፍንት አመራርና የወጣቱ ትውልድ በጎሪጥ እየተያዩ መተላለፍ ለሃገሪቱ ህልውናና ዳይቨርስ ለሆነው ሕዝቧ ጠንቅ የፈጠረ መሆኑ ነው። አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝ (አንድ) እንዲህ ይላል። “ማንኛውም የኢትዮጵያ ብሔር፤ ብሔረሰብ፤ ሕዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን እስከ መገንጠል ያለው መብት በማናቸውም መልክ የተጠበቀ ነው።” ራሱን በራሱ ለመበታተን ፈቅዶ በሕገ መንግሥቱ ያስገባ ገዢ ፓርቲ ህወሓት/ኢህአዴግ ብቻ ነው። ከጎሳ ልሂቃን ውጭ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይኼን አንቀፅ አይቀበልም። ኢትዮጵያዊያን መስዋእት ሲሆኑ፤ የሃገሪቱ ዜጎች በገፍና በአንድ ላይ ያለቀሱትና የጮኹት፤ ገዢውን ፓርቲ የወቀሱትና የተቹት ኢትዮጵያን እንደ ሃገር፤ ኢትዮጵያዊነትን እንደ ዜግነት መታወቂያና መለያቸው አድርገው ስለመረጡ ነው።

ገዢው ፓርቲ በልማትና በእድገት የሚከተለው መርህ ከፖለቲካው አይለይም።  አንቀጽ አርባ ሶስት (አንድ ሁለትና አራት) እንዲህ ይላል። “የኢትዮጵያ ሕዝቦች፤ በአጠቃላይም ሆነ በኢትዮጵያ ያሉ ብሄሮች፤ ብሄረሰቦች፤ ሕዝቦች በተናጠል የኑሮ ሁኔታዎችን የማሻሻልና የማያቋርጥ እድገት የማግኘት እድላቸው የተጠበቀ ነው (ንኡስ አንድ)። ዜጎች በብሄራዊ ልማት የመሳተፍ በተለይ አባል የሆኑበትን ማህበረሰብ የሚመለከቱ ፖሊሲዎችና ፕሮጀክቶች ላይ ሃሳባቸውን እንዲሰጡ የመጠየቅ መብት  አላቸው” (ንኡስ ሁለት)። ጠንካራና ተጠቃሚ የሆኑ የጎሳ ፖለቲካ መሪዎች ያሏቸው ክልሎች የተሻለ እድል ይኖራቸዋል ማለት ነው። እንደ ጋምቤላ፤ አዋሽ ሸለቆ፤ አፋር ወዘተ ያሉት ማን ይሟገትላቸዋል? የተዛባ የክልል ልማት ወይንም የተዛባ ገቢና ሃብት ቢከሰት ማን ይዳኛል፤ ማን ያስተካክላል? የተፈጥሮ ኃብት ባለባቸው፤ ለምሳሌ ለም መሬት፤ ወንዝ፤ መአድን ወዘተ ኋላ ቀር ክልሎች ሕዝብ መብትና ጥቅም ማን ይከራከራል? ንኡስ አራት እንዲህ ይላል። “የልማት እንቅስቃሤ ዋና ዓላማ የዜጎችን እድገትና መሰረታዊ ፍላጎቶች ማሟላት ይሆናል።” ይኼ መርህ በስራ አልተተረጎመም። ለምሳሌ፤ የስራ እድል ከሌለ ገቢ ሊኖር አይችልም። የፍላጎት ምርት እያደገ ካልሄደ የኑሮ ውድነት የማይቀር ነው። ጉቦ፤ ጎሳዊ አድልው፤ ሙስና ተቋማዊ ከሆኑ ሃብት ከሃገር ማሸሽ የማይቀር ነው። ይኼን ሁኔታ ያባባሰው እያንዳንዱ የጎሳ አለቃ ወይንም አዲስ መሳፍንት የሚሰራው ለመላው የሃገሪቱ ሕዝብ አለመሆኑ ጭምር ነው። ሁሉም ለግሉና ለራሱ ቡድን ከሆነ ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያገለግል ኢኮኖሚ አልተመሰረተም ማለት ነው። ለልማት የሚውለው ካፒታል ለግዙፍ ስለላ ፈሰስ ከሆነ፤ ከተሰረቀና ለፖለቲካ ስልጣን ከዋለ ካፒታሉ ባከነ ማለት ነው። “የዜጎች እድገትንና መሰረታዊ ፍላጎቶች” ለማሟላት ቃል የገባና ቆርጦ የተነሳ መንግሥት የጥቂቶች አገልጋይ ሁኗል የምለው ለዚህ ነው።

ሕገ መንግሥቱ ለተዛባ ገቢ፤ ሃብትና እድገት የተቆራኙ የአገዛዝ መርሆዎችን ያስተጋባል። የተዛባውን የሚያስተካክል ከመንግሥት ቁጥጥር ነጻ የሆነ ወይንም  የመንግሥት ሁኖ በሞያው ጥራትና በነጻነት የሚሰራ አካል የለም (The Constitution does not provide an independent oversight to ensure checks and balances in governance). አንቀጽ አምሳ (አንድ) እንዲህ ይላል። “የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሳዊ ሪፐብሊክ በፌደራል መንግሥትና በክልሎች የተዋቀረ ነው።” ልክ እንደ ኮሙኒስት ፓርቲዎች አንዱ ሌላውን የሚደግፍ ማእከላዊ የሆነ የአንድ ፓርቲን የበላይነትና የሚመሩትን ግለሰቦች የሚጠቅም አገዛዝ መሆኑ ነው። ምርጫውን ስንመለከት ሂደቱ ከላይ የቀረቡትን የአንድ ፓርቲ የበላይነት የሚያጠናክር ሁኖ እናገኘዋለን። አንቀጽ አምሳ ስድስት እንዲህ ይላል። “በምክር ቤቱ አብላጫ መቀመጫ ያገኘ የፖለቲካ ድርጅት ወይንም ጣምራ ድርጅቶች የፌደራሉን መንግሥት የሕግ አስፈጻሚ አካል ያደራጃል/ያደራጃሉ/ይመጥጣል/ይመርጣሉ።” ይኼን በበለጠ የሚያጠናክረው አንቀጽ ሰባ ሁለት እንዲህ ይላል። “የኢትዮጵያ ፌደራል መንግሥት ከፍተኛ የአስፈጻሚነት ሥልጣን የተሰጠው ለጠቅላይ ሚኒስትሩና ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ነው” ይላል። ስለዚህ፤ ከዲሞክራሳዊ ባህሪው ይበልጥ ህገ መንግሥቱ የሚያደላው ጠንካራ፤ አንድ ወጥ ለሆነ፤ በመንግሥት ባጀት ለተደገፈ ፓርቲ ነው። በአሁኑ ምርጫ ከአርባ በላይ ከሆኑት “ተወዳዳሪ ፓርቲዎች መካከል ተቃዋሚ ሊባሉ የሚችሉት መድረክና ሰማያዊ” ናቸው። አብዛኛዎቹ ለህወሓት/ኢህአዴግ ታማኝ የሆኑ ተቀጥላዎች ወይንም ሕገ መንግሥቱ “ጣምራ ድርጅቶች” ናቸው። ይኼ የሆነበት ፈሊጥ “በምክር ቤቱ አብላጭ መቀመጫ” ለማግኘት ነው። ስለሆነም፤ ህወሓት/ኢህአዴግ አብላጭ መቀመጫ እንዲያገኝ ቀደም ብሎ ታስቦበት በስራ ላይ የዋለ የተለመደ ዘዴ ነው። ይኼ ሲሆን ከላይ የቀረቡትን የፖሊሲና የመዋቅር ችግሮች ለሕዝብ አቅርቦ ለመወያየት አይቻልም ማለት ነው። ምርጫው የሚካሄደው የገዢን ፓርቲ ስልጣን ለማራዘም ነው።

አደጋው ሰላምና እርጋታ እንዲኖር ሲባል ያለውን እንቀበል የሚለው ምክርና ሽምግልናም አብሮ የሚካካሄድ መሆኑ ነው። ፍትሃዊ የሆነ ለውጥ ከሌለ ችግሩ ይባባሳል፤ ወጣቱ ትውልድ ልክ አንበሳ እንዳየ የእንስሳ መንጋ እንደ ከብት እየበረገገ ከሃገሩ ይሰደዳል። “የነቃ ተሳትፎ ማድረግ” ይገባል የሚለው ምክር የሳታቸው ብዙ የፖሊሲ ጥያቄዎች አሉ፤ የኑሮ ውድነት፤ ሙስና፤ ከሃገር የሚሸሺ ሃብት፤ የወጣቱ ትውልድ ተስፋ መቁረጥ፤ የጎሳ ጥላቻ ወዘተ። “አዲስ አበባ ግንቦት 4/2007 መጪው ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ ኅብረተሰቡ የነቃ ተሳትፎ እንዲያደርግ የአገር ሽማግሌዎች ጠየቁ። የአገር ሽማግሌዎቹ ምርጫው ሠላማዊና ፍትሃዊ ሆኖ በሚጠናቀቅበት ሁኔታ ዙሪያ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ጋር ተወያይተዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ ምክትል ሰብሳቢ ፓስተር ዳንኤል ገብረስላሴ በዚሁ ጊዜ እንዳሉት ዜጎች የፈቀዱትን የፖለቲካ ፓርቲ በሠላም መርጠው እንዲገቡ ሽማግሌዎቹ የበኩላቸውን ያደርጋሉ።” ተናጋሪው “የፈቀዱትን የፖለቲካ ፓርቲ በሰላም መርጠው እንዲገቡ” ሲሉ ያልተናገሩት ከተናገሩት ይበልጣል፤ አንድነትና መኢአድ መፈራረሳቸው፤ ብዙ መቶ የዲሞክራሲና የሰብአዊ መብቶች ጠበቃዎች አሁንም አለመፈታታቸው፤ የኢትዮጵያ መንግሥት በሃገር ቤትና በውጭ ለሚደርሰው የሰብ አዊ መብቶች መገፈፍ ሃላፊነትና ተጠያቂነት እንዳለበት አለማመኑ ወዘተ። “በሕዝብ የተመረጠው አካል ሥልጣኑን እንዲይዝና የተሳካ ምርጫ እንዲሆን የድርሻቸውን እንደሚወጡም ገልጸዋል። የአገር ሽማግሌዎቹ በፖለቲካ ፓርቲዎች የውይይትና የክርክር መድረኮች ላይ በመገኘት የሠላም ኃሳባቸውን እየገለጹ መሆኑን ነው የተናገሩት።የአገር ሽማግሌዎቹ ከተለያዩ የኃይማኖት ተቋማት፣ የሲቪክ ማኅበራትና ከተለያዩ የሙያ መስኮች የተውጣጡ መሆናቸውንና ለኅብረተሰቡ ባላቸው ቅርበት ምርጫው በሠላም እንዲጠናቀቅ በማስተማር የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱ ገልጸዋል።

ከአገር ሽማግሌዎቹ መካከል ልዑል ራስ መንገሻ ስዩም በአገሪቱ በርካታ ለውጦች እየመጡ መሆኑን በመግለጽ ይህንኑ ለማስቀጠል መጪው ምርጫ በሠላም ሊጠናቀቅ ይገባል ብለዋል።

ወጣቱ ሠላምን በማረጋገጥ የአገሩን ልማት ለማስቀጠል የሚረዳውን ምርጫ በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ያለውን ሚና ተገንዝቦ በኃላፊነት ሊንቀሳቀስ እንደሚገባም አስገነዝበዋል።” ኢትዮጵያ የአባቶች ምክር እንደሚያስፈልጋት አምናለሁ። ምክር አቅራቢዎች ለህሊናቸው ብቻ የመገዛት ሃላፊነት አለባቸው። ምክሩ ጠቃሚና ሚዛናዊ የሚሆነው በገዢው ፓርቲ የሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ረገጣ እንዲቆም፤ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ፤ የሰላምና የእርቅ ድርድር በአስቸኳ እንዲካሄድና ሁሉን አሳታፊ የሆነ ብሄራዊ የሆነ የአንድነት መንግሥት ተቋቁሞ እውነተኛ ዲሞክራሳዊ ምርጭ እንዲካሄድ ቢጨመርበት የሕዝብ ተስፋን ይቀሰቅስ ነበር። በጎሳ ይሁን በጥቅም ወይንም ሌላ ምክንያት ምክሩ አድሏዊ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ይኼን ምክር ሲሰማ ለምርጫው ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ወቅት በሽምግልና ስም ገዢውን ፓርቲ ደግፈው ድምፃቸውን ለሚያሰሙ አባቶችም ያላቸው አክብሮት ዝቅ እንደሚል መገመት አያስቸግርም። ወጣቱ ትውልድ ይኼን ሰምቶ “ነገ ስራ አገኛለሁ፤ ተስፋየ የጠነከረ ይሆናል” የሚል አይመስለኝም። በሌሎች ሃገሮች ዘጠና በመቶ የሚሆነውን የስራ እድል የሚፈጥረው የግል ክፍሉ ነው። በኢትዮጵያ የመቅጠር የበላይነት የያዘው ህወሓት፤ የሚቆጣጠረው መንግሥትና የፈጠራቸው ተቋሞች ናቸው።

ነጻ፤ ፍትሃዊና አግባብ ያለው ምርጫ እንዳይካሄድ ሆነ ተብሎ የሚደረገው ተንኮለኛነት መሠረታዊ ምክንያት አለው።  የግል ጥያቄየ ህወሓት/ኢህ አዴግ ለምን ራሱን ለአደጋና ለውርደት ያጋልጣል? የሚል ነው። የምርጫ ቦርዱን ለፖለቲካ የኳስ ጨዋታው የተጠቀመበት ምክንያት ግልጽ ነው። ህወሓት/ኢህአዴግ የውጭና የውስጥ ተመልካቾችን ለመሸንገል ሲል ያመቻቸውና የፈቀደው ለራሱ አጎብዳጅና ተገዢ ለሆኑ፤ በተለይ፤ በውስጣቸው ገብቶ፤ አባብሎ ወይንም አስፈራርቶ በኢትዮጵያ ሕዝብ ባጀት “ለገዛቸው” ተለጣፊ ቡድኖች፤ ተቀናቃኝ የሆኑትን አፍርሶ ላቋቋማቸው ታማኝ ድርጅቶች፤ ለፖሊሲ ለውጥ ሳይሆን ለወንበር ለተሰለፉትና፤ በአብዛኛው ለብሄር/ብሄረሰብና ሕዝቦች ፓርቲዎችን ተሳትፎ ነው። ማስፈራሪይ ዱላው ተተኪው መንግሥት “ያጠቃሃል፤ ያሳድድሃል፤ ያስርሃል፤ የዱሮ ጠላቶችህን ይመልስብሃል” የሚል የተለመደ ፕሮፓጋንዳ ነው። በሰማያዊ ፓርቲ አመራርና አባላት ላይ የሚደረገው ማሳደድ፤ መደብደብ ማሰርና “ተራ ወንጀል” ለዚህ ዋቢ ነው። የብሄር ሆኑ የህብረ ብሄር ድርጅቶች–

በምርጫው የሚሳተፉ ፓርቲዎች–የመሳተፍ መብት እንዳላቸው አምናልሁ። በከፊልም ቢሆን፤ ቢያንስ ከገዢው ፓርቲ የሚለዩበትን መሰረታዊ ጉዳይ ለሕዝብ ለማቅረብ እየሞከሩ ነው። በቅርቡ የሚካሄደውን የቴሌቪዢን ውይይት ሳይ ልዩነቶቹ ከባድ መሆናቸውን እገነዘባለሁ። ለምሳሌ፤ አንድ ለአምሥት የሚለው የገዢው ፓርቲ የስለላ መረብ ማንን ለመቆጣጠር እንደተቋቋመ ለውይይት መቅረቡ። ምርጫው ዲሞክራሳዊ ነው አይደለም? የሚል ውይይት መካሄዱ። ይኼ እናዳለ ሁኖ፤ ውይይቱ ሕዝብ የሚፈልገውንና የሚመኘውን የፖሊሲ ለውጥ ለማምጣት አይችልም። በገፍ ለሚሰደዱ ወጣቶች አጥጋቢ እድል ከፋች መልስ አያመጣም። በኑሮ ውድነት ለሚሰቃየው ድሃና መካከለኛ ስርቶ አደር ሕዝብ በቀን ሶስት ምግብ አያቀርብም። ሙስናው እንዲቆምና በገፍ የተዘረርፈው ወደ ሃገር እንዲመለስ አያደርግም።

ፈልጎም ወይንም ተገዶ ሕዝብ ድምፁን ያሰማል። ሆኖም፤ ብሄራዊ ምርጫ አንድ ሶስተኛ፤ ወይንም ከዚያ በላይ በሆነ የሕዝብ ተሳትፎና በማስፈራራት ሊካሄድ አይችልም። አገሪቱ “ሰሜንና ደቡብ” በሚል የምርጫ ሂደት ብትጓዝ ተከታዩ በጣም አደገኛ ነው። ለመምረጥ አልፈልግም የሚለው ሕዝብ መብትስ ምን ሆነ፤ ለምን ታፈነ፤ ብለን መጠየቅ ይኖርብናል። የማይመርጡና በፍርሃት የሚመርጡ ቢኖሩም ህወሓት/ኢህአዴግ “በከፍተኛ የሕዝብ ድምፅ አሸነፍኩ” ለሚለው ስልት ይጠቅመዋል። ምን አልባት በ99.6 በመቶ ከማሸነፍ 90 በመቶ ወይንም ከዚህ በታች ቢያሸንፍ የፖሊሲ ለውጥ የማይታሰብ ነው።

ለዚህ የምርጫ ማጭበርበር ስልት የተካነበት የአደረጃጀት ዘዴ እንዳለው እናውቃለን። አስቀድሞ መገምገምና ታማኝና ታዛዢ የሆኑ ስብስቦችን ማደረጀትና አቅጣጫ ማስያዝ አገዛዙን ለማራዘም የተፈተነ ዘዴ ነው። ብዙ ማስረጃዎች የሚያመለክቱት፤ ህወሓት በውጭም ሆነ በውስጥ፤ በማንኛውም የኢትዮጵያ “ድርጅት ወይንም ስብስብ” ሰርስሮ ገብቷል። በኢትዮጵያ ሕዝብ ባጀት የፖለቲካ ደጋፊዎች በገፍ ሰብስቧል። በተለይ በወጣቶች ዙሪያ። አንድ ለአምስት ማለት ቁጥጥሩ ወደ ቤተሰብ ገብቷል ማለት ነው።፡ከምርጫ ዘጠና ሰባት በኋላ አንድ የዓለም ባንክ ጥናት ያሳየው የምርጫ ዘጠና ሰባት አይነት ጥቃትና ውርደት እንዳይከሰት፤ ህወሓት ሆነ ብሎ እቅድ አውጥቶ ብዙ ሚሊዮን ደጋፊዎችን ለኢህአዴግ አባልነት መልምሏል። በፈቃድ ሳይሆን በማባበል። በራሱ ወጭ ሳይሆን በሃገሪቱ ባጀት። ዛሬ ከክልል አንድ ውጭ የበላይነቱን የሚያካሂደው በክልሉ በተወለዱ፤ ባህሉን፤ ቋንቋውን ወዘተ በሚያውቁ፤ በተለይ ባለፉት ሃያ አምስትና ሰላሳ ዓመታት በተወለዱ፤ ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን በቅጡ በማያውቁና እንዳያውቁ በተገደዱ ወጣቶች ተባባሪነትና ደሞዝተኛነት ነው።

የታፈነ ምርጫ ሙስናን ያንፀባርቃል

በጎሳዊ አድልዎ፤ በጉቦና በሙስና የተበከለ አገዛዝ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ሊፈቅድ አይችልም። እንዴት ራሱን ለአደጋ ያጋልጣል? የምርጫ ማጭበርበር ሙስና የተለያዩ ገጾች አሉት፤ የገንዘብ፤ የፍርሃት፤ የፖለቲካ፤ የስም ማጥፋትና ሌላ። በማባበል፤ ድጎማ በመስጠት፤ “ይኼን ካደረግህ ይኼን እስጥሃለሁ” በማለት። ለምሳሌ ብድር፤ ማዳበሪያ፤ መሬት፤ ፈቃድና ሌሎች ግብዓቶች በመስጠት አባላት መሰብሰብ የማጭበርበር ገፅታ ነው። (Fraud, deception and manipulation are forms of electoral corruption at a state level). “የመንግሥት ባጀት” ለፖለቲካ የበላይነት ውሏል። ሰርጎ ገብነት፤ ከፓርቲው ቁጥጥር ውጭ የሆኑ ህብረ ብሄር ድርጅቶችን ማፈራረስ፤ እንዲካሰሱ ማድረግ፤ የግለሰቦችን ስም ማጥፋት፤ ፈቃዳቸውን መከልከል፤ ንብረታቸውን መቀማት ሙስና ነው። በጎጃም ገበሬዎች ላይ እንደሆነው “ምርጫው እስከሚያልቅ ድረስ የመሬት ጥቅም ይዞታ ፈቃዳችሁ ለጊዜው ተከልክሏል” ብሎ የፖለቲካ ውሳኔ ማዳረግ የማይረሳ ጭካኔና የስልጣን ብልግና ነው። በህብረ ብሄር ድርጅቶች ምትክ ጥገኛና ተለጣፊ ድርጅቶችን ፈጥሮ የሕግ እውቅና መስጠት ወዘተ “የሙስና አካል” ነው። እነዚህ አይነቶቹ ጫናዎች የተለመዱ የፖለቲካ የበላይነት መሳሪያዎች ሁነዋል። ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት አገልግለዋል። በዚህ አይነቱ የፖለቲካ ሁኔታ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ይካሄዳል ብሎ ማመን ራስን ማታለል ነው። የአሜሪካ የውጭ መስሪያ ቤት የፖለቲካ ክፍል ምክትል ሃላፌ ዌንዲ ሸርማን “ነጻ፤ ፍትሃዊ፤ ክፍትና አግባብ ያለው ምርጫ ይካሄዳል፤ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ናት” ብላ የተናገረችውን ሌላው ቀርቶ ብዙ የኢህአዴግ አባላት አይቀበሉትም። የኢትዮጵያን ሕዝብ አይቀበለውም፤ አንድም ተቃዋሚ ፓርቲ አላነጋገረችም። የኢትዮጵያንና የራሷን ሃገር ዘላቂ ጥቅም ጎድታለች።

ከፍተኛ ተስፋ የሚሰጠው የኢትዮጵያ ሕዝብ የፖለቲካ ብስለት ያለው መሆኑ ነው። የፖለቲካ ጨዋታውን እየሳቀ ያልፈዋል። ማን ለምን እንደሚወዳደር ያውቃል። አንዳንድ ታዛቢዎች በምርጫው መሳተፍ የዲሞክራሲ ቀዳዳ ይከፍታል የሚል አመለካከት ይሰነዝራሉ። ይኼ አመለካከት ቢያንስ ባለፉት ሃያ አራት ዓመታት ሲነገር ቆይቷል። ጥቂት ወንበሮች መያዝ ይቻላል። ፖሊሲ ለመለወጥና ሙስናን ከስሩና ከጭንቅላቱ ነቅሎ ለመቅረፍ አይቻልም። በየትኛውም ዲሞክራሳዊ አገር የፓርላማ ውሳኔዎች የሚደረጉት በድምፅ ብልጫ ነው። ጥቂት ወንበሮች የድምፅ ብልጫ ሊያመጡ አይችሉም። ብቸኛ ተቃዋሚ የፓርላማ አባል ከመጮህ ውጭ ምንም ለማድረግ አይችልም/አትችልም። ችግሩ እንዳለ ለዓምስት አመታት፤ ለአስር አመታት ወዘተ ሊቆይ ይችላል። ገዢው ፓርቲ የሚፈልገው ይኼን ነው። የሰላሙ ትግል ዘዴዎች መቀየር አለባቸው የምለው ለዚህ ነው።

የመሳተፍ መብታቸው እንዳለ ሁኖ እውነተኛ በሆነ መንገድ ለሕዝብ መብቶች፤ ለፍትህና ለዲሞክራሳዊ ለውጥ የቆሙ ፓርቲዎች ይኼን “ምርጫ” ይካሄዳል የሚል የፖለቲካ ኪሳራ የሚያስከትል ፕሮፓጋንዳ መሸመትና መቀበል ያለባቸው አይመስለኝም። አስቀድሞ፤ “አናሸንፍም፤ ሆኖም የመሳተፍ መብታችን እንጠቀማለን” የሚል መልእክት ለሕዝብ ቢቀርብ ይጠቅም ይመሰለኛል።

ከለይ ያቀርብኩት የምከራከርብት ሃሳብ አንድ ነው። ይኼውም የፖለቲካ ለውጥ፤ ማለትም የመንግሥት አመራና የፖሊሲ ለውጥ ካስፈለገ “እምቢ፤ የገዢውን ፓርቲ ተንኮል ከአሁን በኋላ አንቀበልም” ብሎ ሕዝቡን ለመብቱ እንዲነሳ የማድረግ ግዴታ እንደሚታይ ነው። ይኼን ደጋግሜ የማመለክተው የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የታወቀ ስለሆነ ነው። ያለፉት አራት ምርጫዎች የሚያሳዩት ልምድ፤ የምርጫው አሸናፊ ሁል ጊዜ ህወሓት/ኢህአዴግ እንደሚሆን ነው። የሚያሸንፍበት ምክንያት የፖለቲካ ለውጥ እንዳይመጣና ያካበተው ጥቅም እንዳይናጋ ጭምር ነው።

ታዲያ ምን ይደረግ?

ቢያንስ፤ ተወዳዳሪዎችን ዓለም የሚያከብራቸው፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚቀበላቸው፤ ሊያቀርቧቸው የሚገባቸው ዲሞክራሳዊ ጥያቄዎች አሉ። “የህወሓት ገመና” በሚል፤ ከዚህ በፊት በድህረገጾች የቀረበ  በማስረጃ የተደገፈ ሃተታ የኢትዮጵያዊያን ሕዝብ ሰብአዊ መብቶች ፍፁም በሆነ ደረጃ እንደታፈኑ፤ ይኼ አፈና ለሃገሪቱ ህልውናና ለሁሉም ኢትዮጵያዊያን ህይወት አደጋዎችን እንደፈጠረ፤ የምእራብ ሃገሮች፤ በተለይ አሜሪካና እንግሊዝ ለህወሓት የሚሰጡት ግዙፍ እርዳታ፤ የመረጃና የዲፕሎማሲ ድጋፍ ለአደጋው መጋቢ እንደሆነና መለወጥ እንዳለበት አሳስባለሁ። ተቃዋሚ ፓርቲዎች በመተባበርና በመናበብ በጉዳዩ ሊረባረቡበት ይችላሉ፤ አዳማጭ ይኖራቸዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ፤ ተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፤ የማህበረሰብ ክፍሎች፤ ልሂቃን፤ ለጋስ ድርጅቶችና መንግሥታት ደፍረው ማስተናገድ ያለባቸው አስኳል ጉዳዮች አሉ። ለምሳሌ፤ ሰላምና እርጋታ እየደፈረሰ መሄዱና የእርቅና ሰላም ድርድር አስፈላጊ መሆኑን በግልፅ መናገር፤ ሕዝቡ በኑሮ ውድነት መሰቃየቱ አደገኛ የማህበረሰብ ቀውስ (Social Crisis) እንደሚያስከትል ማሳሰብ፤ የምእራብ ሃገሮች ዘላቂ ጥቅም ዋስትና የሚኖረው ግፍ፤ በደል፤ ሙስና ወዘተ ሲጠፉ መሆኑን ማስረዳት። ወጣቱ ትውልድ በሃገሩ አማራጮች እንዲኖሩት ያልተቆጠበ ግፊትና ድጋፍ መስጠት። ተቃዋሚ ፓርቲዎች እነዚህን በግልፅ የሚታዩ ችግሮች መፍትሄዎች ችላ ካሏቸው አስፈላጊ የሆነውን የዲሞክራሲ ስርዓት ምስረታ ለብዙ አስርት ዓመታት ይገቱታል። የአሁኑን ጨቋኝ አገዛዝ ዲሞክራሳዊ በሆነ አገዛዝ ለመተካት ካልተቻለ ከፍተኛ ቀውስ መፈጠሩ አይቀርም።

አንዳንድ ተመልካቾች የሚሉት፤ ህወሓት የኢትዮጵያ የመፈራረስ አደጋ ከታየው ጠቅልሎ ወደ ምሽጉ ወደ ትግራይ ይገባል፤ የፈለገውን “ታላቋን ትግራይ” ይመሰርታል ነው። እንዲያውም፤ በቤኒ ሻንጉል የሚገኘውን የተሃድሶ ግድብ የሚገድበው ለራሱ ለህወሓት ጥቅም እንጅ ለነዋሪዎቹና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ተቆርቁሮ አይደለም የሚሉም አሉ። አንድ፤ ቢሆንስ፤ “ታላቋ ትግራይ” ታላቅ ኢትዮጵያ አትሆንም የሚል ግምት አለኝ። ህወሓት ኢትዮጵያዊያንን አናክሶ በሰላም ለመኖር አይቻልም። ሁለት፤ የትግራይ ሕዝብ አገር ወዳድ ስለሆነ እንዴት ይኼን ውጤት ይቀበላል፤ ራሱ መልሶ አንፈልጋችሁም የሚል ድምፅ አያሰማም ብለን ለመቀበል የምንችልበት ምን መረጃ አለ? መረጃ የለም እላለሁ። የጎንደር ሕዝብ፤ በሌላው ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ተደግፎ፤ የተነጠቀውን መሬትና በአዲስ ለፖለቲካ የበላይነት የተመቻቹን ንዑስ ክልሎች ስኬታማ እንዳይሆኑ አድርጎ፤  የታወቀ ድንበሩን እስከ ተከዜ ወንዝ ሳያስመልስና ህወሓት በምስጢር ለሱዳን የሰጠውን መሬት ሳያስመልስ “ለታላቋ” የህወሓት ትግራይ ሰላም የሚሰጥ አይመስለኝም። “የተኛ” የሚመስል ሕዝብ ጉዳቱ እየበዛበት ሲሄድ መነሳቱ የማይቀር ነው። ቢያንስ ለራሱ ህልውና ይታገላል የሚል ግምት አለኝ። የጎንደርም ሆነ የሌላው ሕዝቡ ትእግስት ማለቁን የሚያሳዩ ብዙ ምልክቶች አሉ። በመከላከያ ኃይሉ ውስጥ ልዩነቶች መነሳታቸው አይቀርም። የኃይማናት አባቶች በቅርቡ ያወጧቸው መግለጫዎችና አደራዎች የኢትዮጵያ የመከላከያ ኃይል መወከል ያለበት አምባገነኑን አገዛዝ መሆን የለበትም የሚል ነው። የሕዝቡን አደራ አክብሮና ተቀብሎ ፊቱን ወደ ራሱ ሕዝብ መብትና ክብር እንዲያዞር አደራ ብለዋል። ትግል በተናጠል ስኬታማ አይሆንም። ኢትዮጵያዊያን ተባብረውና ቆርጠው በአንድ ድምጽ ከተነሱ አዲስ ታሪክ የመስራት ብቃትና አቅም አላቸው።

በውጭም ሆነ በሃገር ቤት የምንኖር አገር ወዳዶች ማጤን ያለብን በግልጽ የሚታዩ ሁለት አደጋዎች አሉ። አንድ የኢትዮጵያ ሉዐላዊነት መበረዙና ሃገሪቱ በየቦታው እየተናጋች መሆኗ፤ ሁለት ገዢው ፓርቲ ሆነ ብሎ የቀረፀው የጎሳ ልዩነት ሊቆም የማይችል የሚመስል የጎሳ ጥላቻ  መፍጠሩ። ቀውስ የማይቀር ነው የሚሉ የሃገር ውስጥ ታዛቢዎች ብዙ ናቸው። እኔ የምከራከረው ሁለቱንም አደጋዎች ለመከላከል መተባበር አስፈላጊ ሁኗል በሚል ነው። ትእቢተኛውና ጠባብ ጎሰኛው ህወሓት አላወቀበትም እንጅ፤ ቀውስ ለማንም አይበጅም። አስከፊ የሆነ የርስ በርስ ጦርነት ሊነሳ ይችላል። የቀረችው ኢትዮጵያ የመከፋፈል እድሏ የተባባሰ እንደሚሆን አስቀድሞ መገመት አስፈላጊ ነው። አንዳንድ ታዛቢዎች የሚሉት በትጥቅ ትግል ለመገንጠል የሚታገል ኃይል ለህወሓት ህልውናና የበላይነት አደገኛ ከሆነና በፖለቲካውና በዲፕሎማሲው የሚያዋጣው ከሆነ የህወሓት አመራር አንቀጽ ሰላሳ ዘጠኝን ተጠቅሞ ኤርትራን እንዳስገነጠለ ሁሉ፤ ሌላ ክልል እንዲገነጠል ቢያደርግ አያስገርምም። ኢትዮጵያን ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ወዳለው የእድገት ጎዳና ለማመቻቸት የሚቻለው ለሁሉም አሳታፊ የሆነ በሕግ የበላይነት የተመሰረተ እውነተኛ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ ሲመሰረት ብቻ ነው። ገዢው ፓርቲ በራሱ አቅምና ብርታት ዘላቂና ፍትሃዊ እድገት ለማራመድ አይችልም። እስካሁን የቆየው ተቃዋሚው ኃይልና ሌሎቻችን ተከፋፍለን ደካማና ፈሪ መሆናችንን ስለተረዳውና በውጭና በሃገር ቤት ያለው “ተቃዋሚ” ጥበበኛ አመራር ስለሌለው ነው። ይኼ ሁሉ እናዳይደጋገም ከተፈለገ አፋኙን አገዛዝ የሚተካ፤ ሁሉን የሚያስተናግድ ዲሞክራሳዊ አማራጭ አስፈላጊ ነው። ለዚህ መደራጀትና አብሮ መስራት ወሳኝ መሆኑን በተደጋጋሚ አሳስቢያለሁ።

የዲሞክራሲ መንግሥት አማራጭ እንዲሁ በምኞት አይገነባም። ሕዝቡ፤ በተለይ ወጣቱ ትውልድ ለራሱ ህይወት መሻሻል ሲል እውቀቱንና አቅሙን ማጎልመስ፤ እንደ እንሰሳ ከመበርገግ ይልቅ ሳይሰለች መታገል፤ ለፍትህ መስዋእት ለመሆን መድፈር፤ አቤቱታውን በተባበር ድምፅ ማሰማት ወዘተ ግዴታው ነው። በሊብያ አንገትን ተቆርጥና በጥይት ተደብድቦ ከመሞት፤ በየመንና በደቡብ አፊሪካ ተሰዶ ከመዋረድ በሃገር ውስጥ ሁኖ ለመብቶች መታገል ዘላቂ ፍትህ ያመጣል። ይኼን ማንም የውጭ ኃይል ሊያደርግልን አይችልም። ከሁሉም በላይ በየደረጃውና በየአካባቢው ድርጅት ማቋቋም፤ አዲስ መሪዎች እንዲወጡ ማበረታታት፤ በሰሰከነ አእምሮ ብልሃት ያለው ብሄራዊ የፖለቲካ አመራር እንዲኖር መጎትጎት፤ አብሮና ተባብሮ የመስራት የፖለቲክና የማህበረሰብ አደረጃጀት ልምድ እንዲስፋፋና ጥልቀት እንዲኖረው ጠንክሮ መስራት፤ ወጣቱ ትውልድ ከህወሓት/ኢህአዴግ የጎሳ ጥላቻ መርዝና መንጋጋ ነጻ እንዲወጣ ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ፤ በውጭ የሚኖረው ስደተኛ አፋኙን መንግሥት እንዳይደግፍ፤ ማንኛውንም ዓይነት እገባ እንዲያደርግ ጥሪ ማድረግና ለጋስ ድርጅቶች፤ መንግሥታትና ኢንቬስተሮች ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ ትኩረት እንዲሰጡ ሳይሰለቹ መጎትጎት  ይገኙበታል። ልዩ በሆነ መንገድ መደራጀትና ማደረጀት ተቀዳሚነት አለው። እኛ ካልደፈርንና አብረን ለመስራት ከፍተኛ ጥረት ካላደረግን ማንም መንግሥት አይደግፈንም። እንዲያውም እንደ ተናቅ እንቆያለን። መቃወም ብቻ አማራጭ አይደለም።

ይኼን የተቀነባበረ ትግል ለማካሄድ ለአብዛኛው ሕዝብ ህይወት አለመሻሻል ማነቆ የሆኑ ስርዓት ወለድ ማነቆዎች እንዳሉ መገንዘብና መፍትሄ መፈለግ ተገቢ ነው። የፖለቲካው ምህዳር ፍፁም በሆነ ደረጃ መዘጋቱ፤ የሰብአዊ መብቶች በሚያሰቅቅ ደረጅ መገፈፋቸው ከችግሮቹ መካከል የመጀመሪያውን ደረጃ ይዘዋል። ይኼን ችግር ነጥለን ብናየው (መነጠል ባይቻልም)፤ በሃገር ቤት የተቃዋሚ ፓርቶዎች ድርጅታዊ ህልውና ጠፍቷል። ጥሩው ነገር መሪዎቹና አባላቱ አሉ። አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ይደግፋቸዋል። ሊያንሰራሩ ይችላሉ። በውጭ ያለው ግዙፍ ኃይል በጋራ ራእይና የዓላማ አንድነት ተስማምቶ የተበታተነውን ተቃዋሚ ለማስተባበር ያልተቆጠበ ጥረት ማድረግ ግዴታው ነው። ወገኖቻችን ሲሞቱ ማልቀሱና መቅበሩ ዘላቂ መፍትሄ አያመጣም። አንዱ በሌላው ማመካኘቱ መቆም አለበት። በሃገርና በውጭ ያለው አለመግባባትና አብሮ ለመስራት አለመድፈር የሕብረተሰቡን አሰቃቂ የኑሮ ሁኔታ እንዳባባሰው ስለምናውቅ ከመወቃቀስ ባህል ወደ መተባበርና መስማማት ባህል እንሸጋገር።

ወደ ተሻሻለ ዲሞክራሳዊ አገዛዝ አማራጭ ሊይወስድ የሚያስችል፤ የተዋሃደም ባይሆን የተባበረ፤ በሃገር ውስጥና ከሃገር ውጭ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ፓርቲዎችን፤ የማህበረሰብ ክፍሎችንና ግለሰቦችን ያካተተ አማራጭ መስርቶ በእውቀትና በጥበብ የተቀናጀ፤ የማይበገርና የሃገሪቱን የሕዝብ ስርጭት የሚያንፀባርቅ ድርጅትና አመራር መፍጠር የወቅቱ ታሪካዊ ጥያቄና ግዴታ ሁኗል። ኢትዮጵያን እንደ ሃገር፤ ኢትዮጵያዊያንን እንደ ሕዝብ የምንቀበልና የምናከብር ሁሉ ደፍረንና ተባብረን ከተነሳን የሚያቆመን ኃይል አይኖርም። ለአንድ ለሚያልፍ ህይወት፤ ለሚያልፍ ዝናና ጥቅም ከመረባረብ ይልቅ ተከታታይ ትውልድ ለሚጠቅሰው ቁም ነገር የራሳችን የግል አስተዋፅኦ ብናደርግ ራሳችን አስከብረን ሃገራችንም እናስከብራለን።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር

The post ምርጫ ለይስሙላ – አክሎግ ቢራራ (ዶር) appeared first on Zehabesha Amharic.

በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ

$
0
0

የኢህአዴግ ስርአት የማእከላዊ እዝ ወታደሮች ከቦታ ወደ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መምሪያ እንዳወረዱላቸው ምንጮቻችን ገለፁ ሲል የደህሚት ድምጽ ዘገበ::
clash
በአዲ-ኮኮብ የሰፈሩት የማእከላዊ እዝ የበታች አመራር ወታደሮችና ተራ ወታደሮች ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር እንዳይገናኙና ወደ አዲ-ዳዕሮና ሸራሮ እንዳይንቀሳቀሱ ተከልክለው እንደሚገኙ የገለጸው የደህሚት ድምጽ እነዚህ የበላይ አመራሮች ሰራዊቱን በመሰብሰብ በአዲ-ዳዕሮ፤ አዲ ነብሪ ኢድ፤ አዲ-ሃገራይ፤ ሸራሮና አካባቢው በአጠቃላይ በአካባቢው የሚገኝ ህብረተሰብ የትህዴን አባል ሰለሆነ የምናጣራው ነገር አለን መንቀሳቀስ ክልክል ነው በማለት ትእዛዝ እንዳወረዱላቸው ለማወቅ ተችሏል።

በተጨምሪም- ወታደሮቹ በአካባቢው ህብረተሰብ ላይ ጥላቻ እንዲያሳድሩና ከሱ ጋር እንዳይወግኑ የሃሰት ፕሮፖጋንዳ ቅስቀሳ ሲሰጥ የሰነበተ ሲሆን ስርአቱ ከህዝብ ተነጥሎ በጠምንጃ ሃይል ብቻ የቆመ እንደሆነ በሚገባ ሰለሚያውቅ ወታደሮቹ ደግሞ ስርአቱን በመተው ከህዝባቸው ጋር እንዳይወግኑ በመስጋት የመነጨ መሆኑን ወታደሮቹ በሚገባ እንደተረዱት ለመረጃ ምንጩ የደረሰው መረጃ አስረድቷል።

The post በፍርሃት ውስጥ ያለው የኢሕአዴግ ሥርዓት የማዕከላዊ ዕዝ ወታደሮች ከቦታ ቦታ እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ መመሪያ አወረደ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live