Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

“የምርጫውን ካርድ ቀዳችሁ ጣሉት”–ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ

$
0
0

nega birhanu zehabesha Ginbot 7
May 22, 2015

የተከበራችሁ እናቶቼና አባቶቼ፤ እህቶቼና ወንድሞቼ እንዲሁም ልጆቼ የምትሆኑ ወጣቶች!! አገራችን የምትገኝበትን አስጨናቂ ሁኔታ ሁላችንም እንረዳለን። የህወሓት/ኢሕአዴግ ፋሽስቶች ቡድን እየገረፈ፣ እያሰረና እየገደለ በካርዳችሁ መርጣችሁ የምርጫ ድግሴን ካላሞቃችሁልኝ እያለ ነው። እንኳንስ ዛሬ ታዛቢ በሌለበት፤ ታዛቢ እያለም እንኳን ወያኔ የሕዝብን ድምጽ በትክክል ቆጥሮ አያውቅም። ወያኔ ለህዝብ ድምጽ ምንም ደንታ የሌለው የኋላቀር ወሮበሎች ቡድን ነው::

ለስንት አስርት ዓመታት ለወያኔ ባርነት እንገብራለን? ለሀያ አስምስት ዓመታት ተገዛን፣ ተገደልን፣ ተቀጠቀጥን፣ ታሰርን፣ ተሰቃየን፣ ልጆቻችን በአገራቸው ተስፋ ቆርጠው ሲሰደዱ በበረሀ ንዳድ አለቁ፤ በባህር ሰጥመው ቀሩ፤ በባዕዳን አረመኔዎች እንደከብት ታረዱ፤ ቤንዚን ተርከፍክፎባቸው ተቃጠሉ። ሀይማኖታችን ተዋረደ፤ ባህላችን ረከሰ፤ ታሪካችን ተናቀ። በልማት ስም ወልደን ከከበድንበት ተፈናቀልን፤ አገራችን አደገች እያለ ሕዝብ በኑሮ ውድነት ተሰቃየ። በልቶ ማደር ብርቅ ነው። እንደሙጫ የሚያጣብቀንን ማህበረሰባዊ ትስስር በስልጣን ለመቆየትና ህብረተሰቡን ለመዝረፍ ሲል ሆን ብሎ እያፈራረሰው ነው:: ይኽ ሁሉ አይበቃንምን? ይኸ ሁሉ አይመረንምን?

ወላጆቼ፣ እህት ወንድሞቼ!ውርደት ይብቃን። የተረገጥንና የተገደልን አንሶን ፍጹም ማንንም ሊያሞኝ በማይችል የለበጣ ምርጫ ወደን የተረገጥን፤ ፈልገን የተገዛን ለማስመሰል ወያኔ የሚያደርገውን ሩጫ እናክሽፈው:: ከፊታችን ያለውን ምርጫ ባለመሳተፍ ምሬታችንን እንግለጽ።

ዛሬ በግሌ እና በአርበኞች ግንቦት 7፡ የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ስም ጥሪዬን አቀርባለሁ። በዚህ ምርጫ አትሳተፉ። የምርጫ ካርዳችሁን ቀዳችሁ ጣሉት። እናምርር። ካላመረርን ለውጥ ሊመጣ አይችልም። ይልቅስ ለማይቀረው የመጨረሻው ትግል ራሳችንን እናዘጋጅ::

አርበኞች ግንቦት 7፣ ከትግራይ፣ ከኦሮሞ፣ ከአፋር፣ ከኦጋዴን፣ ከጋምቤላ፣ ከቤሻንጉል ድርጅቶች ጋር ትብብር በመፍጠር የአገር አድን ኃይል በመገንባት ላይ ነው። እኛ ልጆችህ በብሔርም ሆነ በሀይማኖት አንከፋፈልም። ከትግራይ እስከ ኦጋዴን፤ ከአፋር እስከ ጋምቤላ ሁሉንም የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ያካተተ ስብስብ ፈጥረን በኅብረት አገዛዙን እየታገልን ነው። ይህ ትግል ግን የኢትዮጵያ ሕዝብ ሁሉ ትግል ነው። የትግሉም ባለቤት የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ ነው። ክርስቲያን ሙስሊም፤ ወንድ ሴት፤ ወጣት አረጋዊ ሳንል፤ በብሔርም ሆና በቋንቋ ሳንከፋፈል ሁላችንም ይህን አስከፊ ሥርዓት በቃህ እንበለው።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! ይህንን የውሸት ምርጫ ባለመሳተፍ ለለውጥ ያለህን ዝግጁነት አሳይ! ደግሜ እለዋለሁ – የምርጫ ካርድህን ቅደድ!!!

የጦርና የፓሊስ ሠራዊት አባላት ሆይ!

እናንተ የሕዝብ አካላት ናችሁ። በወገኖቻችሁ ላይ አትተኩሱ። ይልቁንስ አፈሙዛችሁን አገራችንን ለውርደት በዳረገውና በሙስና በተጨማለቀው ዘራፊው የህወሓት አገዛዝ ላይ አዙሩት። ታሪካችሁን ከምታበላሹ፤ ታሪክ ሥሩ። ለራሳችሁ፣ ለቤተሰቦቻችሁ፣ ለልጆቻችሁ እና ለሕዝብ የሚጠቅም አገርና መንግሥት እንዲኖረን የእናንተ የግልም ሆነ የጋራ ተነሳሽነት ወሳኝ ነው። ወያኔ ህዝቡን የሚዘርፈው በእናንተ ትከሻ ላይ ቆሞ እንደሆነ ላንዳፍታም አትርሱት:: እንደመላው ህብረተሰብ እናንተም በነጻነትና በኩራት የምትኖሩበት ሀገር እንደምትሹ አልጠራጠርም:: ስለዚህም ይህን የህወሓት የውሸት ምርጫ ተቃወሙ። ዛሬውኑ ነፃነትና ፍትህ ከጠማው ወገናችሁ ጎን ቁሙ።

የኢትዮጵያ ወጣቶች፤ ትግላችን እስከ ነፃነት ድረስ ይቀጥላል። ነፃነታችንን በእርግጠኝነት በትግላችን እንቀዳጃለን። የምትወዷት፣ የምትኮሩባት አገር – ኢትዮጵያ – ትኖረናለች። ለዚህ ግን ዛሬ ተደራጅተን፣ ፀንተን መታገል የሁላችንም ኃላፊነት ነው። ዛሬ ሁላችንም በፍላጎትና በመንፈስ የተገናኘን ነንና ሁሉም በያለበት ትግሉን ያጧጡፍ። ውጤቱ ቀድሞ በታወቀው በዚህ ምርጫ አለመሳተፍ ለትግሉ ያለንን ቁርጠኝነት ማሳያ ነውና ለውሸት ምርጫ ያለን የመረረ ተቃውሞ በምርጫው ባለመሳተፍ እናሳይ።

ነፃ እንወጣለን!

የኢትዮጵያ ሕዝብ የነፃነቱ ባለቤት ይሆናል! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

The post “የምርጫውን ካርድ ቀዳችሁ ጣሉት” – ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ appeared first on Zehabesha Amharic.


በሚኒሶታ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘው ኢትዮጵያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል

$
0
0

Abiyuአብዩ ተከሥተብርሃን ይባላል:: ኤፕሪል 16 (ሚያዝያ 20 ቀን 2007 ዓ.ም) ከሥራ ውሎ ከተመለሰ በኋላ ከቤት እንደወጣ ሳይመለስ ስለቀረ ምን እንደደረሰበት ሳይታወቅ ሲፈለግ ሰንብቶ ከሁለት ሳምንታት በኋላ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ እንደተገኘ ቤተሰቦቹ ለቀብር ካዘጋጁት በራሪ ወረቀት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል:: መረጃው እንደሚለው ይህ ወጣት ኢትዮጵያዊ በሚኒሶታ እንዴት እንደሞተ ፖሊስ እያጣራ ያለበት ሁኔታ ሲሆን የቀብር ስነስርዓቱም የፊታችን ሜይ 22 (ግንቦት 20 ቀን 2007) ይፈጸማል::

በሚኒሶታና አካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በአሳዛኝ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘውን ወጣት ወንድማችን ቀብር ስነሥርዓት ላይ እንድትገኙ ጥሪ ቀርቦላችኋል::

ሜይ 22 በሚኒሶታው ቅዱስ ዑራኤል ቤተክርስቲያን ከቀኑ 12:15 ጀምሮ የፍትሃት ስነስር ዓት የሚደረግ ሲሆን 2:45 ላይ ደግሞ በሜንዶታ ሃይትስ የመቃብር ሥፍራ ሥር ዓተ ቀብሩ ይፈጸማል::

አድራሻውም

2101 Lexington Ave South

Mendota Heights

MN 55120. ነው::

 

 

abyu tekestebirhan

The post በሚኒሶታ ለጊዜው ባልተረጋገጠ ሁኔታ ተገድሎ የተገኘው ኢትዮጵያዊ የቀብር ሥነሥርዓት ዛሬ ይፈጸማል appeared first on Zehabesha Amharic.

መነሻውን ከህውሃት ጉያ ውስጥ ያደረገው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ መፅሃፍና አነጋጋሪው ክህደት

$
0
0

በሰሜን አሜሪካና በተቀረው ዓለም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህብረትethiopian airforce

የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል በሃሰት ውንጀላ በጅምላ ወደ ህውሃት ማጐሪያ እንዲጋዝ ከተደረገና በኋላም በጨፍጫፊነት ተፈርጆ በአዋጅ ከስራ ውጪ እንዲሆን የፈረደበትን ግንቦት 1983 ዓ/ምን እሳቤ በማድረግ ከምስረታው እስከ አሳዛኝ ብተናው ድረስ የነበረውን ታሪክ በመፅሃፍ መልክ ለማዘጋጀት የተደረገው ጥረት አስርተ ዓመታትን አስቆጥሯል።

በቅብብሎሽ አንዱ በፃፈው ላይ ሌላኛውም እያከለ የተቋሙን ታሪክ ወደ ሙሉዕነት ለመቀየር ከፍተኛ ድካም ተደክሞበታል ። መፅሃፉን አንድ ሰው ያሳተመው ይምሰል እንጂ ባለቤትነቱ በህብረት ነው ።

ከእዚህ ወደ እዚያ ሲንከባለል የቆየው የመፅሃፍ ዝግጅት መነሻ አየር ኃይሉ በደረሰበት ዕጣ ፈንታ በእጅጉ በመቆጨት –

1. የአገር አንድነትን ለማስከበር የተሰዋበትን
2. በአኩሪ ታጋድሎውም በህዝብ ዘንድ ብቻ ሳይሆን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ አክብሮት የተቸረበትን ፣
3. በአሳዛኝ መልኩ ስመጥር ታሪኩን በሬት በመለወስ በትውልድ እንደ ጨፍጫፊና ወንጀለኛ እንዲቆጠር የተደረገበት ሁኔታ ሌት ተቀን እንቅልፍ የነሳቸው የሰራዊቱ አዛውንት አባላት ተሰባስበውና ተማክረው እውነተኛውን ገፅታ ለማቅረብ ጊዜአቸውንና ሃብታቸውን መስዋዕት አድርገዋል ።

ይህንን በጐ ዓላማ ይዞ የተነሳው የታሪክ መፅሃፍ ታትሞ አደባባይ ከመውጣቱና በዚያ ታላቅ የሃገር ሃብት የሆነ የመከላከያ ተቋም ላይ የተወሰደው ፖለቲካዊ ብያኔ የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ ስሜትና ቀልብ እንደሚስብ ፣ ሃላፊነት የጐደለውም ፍርደ ገምድላዊ ብያኔ ምን ያክል አገር የማፍረሱ አካል መሆኑን ቁልጭ አድርጐ በማሳየት በስልጣን ላይ ያለውን ዘረኛ ስርዓት ከማሳጣቱ በፊት ፖለቲካዊ ማድበስበስ ተደርጐ ለዳግም ክህደት ተዳርጓል ።

የተቃውሞው መነሻ –

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ሙሉዕ ታሪክ ተፅፎ ለትውልድ ቢተላለፍ የሚጠላ አንድም ኢትዮጵያዊ እንደማይኖር ሁሉ ታሪኩ ጐዶሎና በፖለቲካዊ ደባ የተንሸዋረረ እንዲሆን ሲፈረድበት ዝም ብሎ መመልከት ደግሞ ለአገራቸው መስዋዕት የሆኑ ዛሬ ግን እራሳቸውን ሊከላከሉ የማይችሉትን ሰማዕታትንም አገርንም መክዳት ነው ።
የአየር ኃይል ታሪክ በቀዳማዊ ኃ/ስላሴ ዘመነ መንግስት መመስረቱ ብቻ ሳይሆን በዘመነ ህውሃት/ኢህአደግ ዘመን በውርደት መፍረሱን ፣ በአባላቱም ላይ የደረሰው ወደር የለሽ ሰቆቃና እንግልት ፣ እስርና ረሃብን የማይገልፅ የታሪክ መፅሃፍ ሙሉዕነቱ የተጓደለ ብቻ ሳይሆን እውነትን ፈፅሞ ለመጋፈጥ የሸሸ አሳዛኝ አድርባይነት ይሆናል ።

የአየር ኃይሉን አመሰራረትና የስልጠና ታሪክ ማሳየት ብቻ ሳይሆን አኩሪ ታሪክ የፈፀሙ ጀግኖች እኩሌታው በአሳዛኝ ሁኔታ ከአገር እንዲሰደዱ ተደርጐ ፣ ቁጥሩ ቀላል ያልሆነው ደግሞ በፍርደ ገምድልነት የሞትና የእድሜ ይፍታህ ፍርደኛ ሆነው በመካከላችን ቆመው በሉበት ሁኔታ ፤ ከሁሉም በላይ ድሃዋ ኢትዮጵያ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የደከመችበትንና የሃገር ሃብት የፈሰሰበትን ፣ ሃላፊነት በጐደለው ስርዓት ገደል እንዲገባ የተደረገበትን እንዳላየና እንዳልሰማ በዳሰሳ ብቻ ማለፍ ታሪክ ይቅር የማይለው ወንጀል ነው ።

ለመሆኑ በወንጀለኝነትና በጨፍጫፊነት ተወንጅሎ ለነጋሪ እንዳይተርፍ ሆኖ በጅምላ ታስሮ ፣ በሞትና በእድሜ ልክ እስረኝነት ፍርድ የተፈረደበት የአየር ኃይል ታሪክ መነሻውን ከህውሃት ቤተመንግስት እንዴት አደረገ ?

እንዲህ የሚከበርና ለአገርም አለኝታ እንደነበረ የሚተረክለት አየር ኃይል ስለምንስ ዛሬ ድረስ በጅምላ ወንጀለኛ የሚለውን ስም እንዲሸከም ተደረገ ? እንዴትስ አባላቱ የሞትና የእድሜ ልክ ፍርደኛ ሆነው ሊቀሩ ቻሉ ? በምንስ መመዘኛ አየር ኃይሉ በጅምላ ይህንን ያክል ፍዳና መከራ ሲሸከምና ሲከፍል ከዳር ሆነው የተመለከቱት የህውሃት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት መፅሃፉ ሲመረቅ በክብር እንግድነት ተስተናገዱ ? ጥቂት ከዘረኛው ስርዓት ጋር የደም ትስስርና ዝምድ ካላቸው የቀድሞው ሰራዊት አባላት በስተቀረ ብዙሃኑ ተወንጃይ የአየር ኃይል አባላትስ የታሉ ? እንዴትስ የዚህ የተወነጀለው አየር ኃይል አባላትና የቀድሞው ስርዓት ጀነራል መኰንኖች የቤተ መንግስት ደጃፍ ያለከልካይ ክፍት ሆነላቸው ?

እነዚህን የመሳሰሉትን ሁሉ ያላገናዘበና ምላሽ ያልሰጠ ፣ ይልቁንም ዘረኛው ስርዓት በጐ እንደሚሰራ ለማስመሰል የሚደርግ ርካሽ የልወደድ ባይነት የተንፀባረቀበት ሆኖ አግኝተነዋል ።

አሁንም ታሪኩ ለትውልድ እንዲተላለፍ የሚደረገውን ጥረት እያደነቅን ነገር ግን ምስረታውንና እድገቱን ለመዘከር የደፈርነውን ያክል በአሳዛኝና ኃላፊነት በጐደለው መልኩም እንዲፈርስና እንዲወድም መደረጉንም ለመግለፅ ድፍረቱ ያስፈልገናል እያልን የህውሃትን ቡራኬ ለማግኘት ሲባል ብቻ ይህንን ታላቅ ዓላማና ስራ ወስዶ ህውሃት ጫማ ስር ማዝረክረኩን አጥብቀን እየተቃወምን ይህ የማይሆን ከሆነ ግን የቀድሞውን የኢትዮጵያ አየር ኃይል አባላት ያላማከረና ያልወከለ ተግባር በመሆኑ አጥብቀን እናውግዛለን ።

በሰሜን አሜሪካና በተቀረው ዓለም የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ህብረት

The post መነሻውን ከህውሃት ጉያ ውስጥ ያደረገው የቀድሞው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ታሪክ መፅሃፍና አነጋጋሪው ክህደት appeared first on Zehabesha Amharic.

የዞን 9 ማስታወሻ

$
0
0

zoneeጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ምርጫውን አስመልክቶ ከአልጀዚራ ቴሌቭዥን ጋር ቆይታ ባደረጉበት ወቅት በተደጋጋሚ ስለዞን9 ጦማርያን አና ሶስቱ ጋዜጠኞች ተጠይቀው በጥቅሉ የሚከተሉትን ምላሾች ሰጥተዋል፡፡
1. ከሽብርተኛ ድርጅቶች ጋር አንደሚሰሩ እርግጠኞች ነን ብሎገርነት ስም ሽፋን ነው
2. ፓርላማ በሽብር ከመደባቸው ድርጅቶች ጋር እንደሚሰሩ ማስረጃ አለኝ የድርጅቱን ስም ግን አሁን አልናገርም ምክንያቱም የፍትህ ሂደቱ ላይ ተጽእኖ ላመጣ እችላለሁ
3. ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር ላለመስራታቸው (ለፍርድ ቤቱ) ማስረዳት አለባቸው
4. አንድ ዓመት እስር ለሽብር ህግ ምንም ማለት አይደለም

የጠቅላይ ሚኒስትሩን ንግግር አስመልክቶ ከዚህ በፊት በእስር ላይ ከሚገኙት ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ግልጽ ደብዳቤ የጻፍን ቢሆንም ጠቅላይ ሚንስትሩ በዛሬውን ንግግራቸው የተለመደውን የአመክንዮ፣ የሃቅ እና የህግ ስህተቶች ፈጽመዋል

1. የዞን9 ጦማርያን የሽብርተኛ ድርጅት አባል ለመሆናቸው የቀረበባቸው ምንም የአባልነት ማስረጃ የለም ፡፡ ፍርድ ቤት ላይ የቀረቡ ማስረጃዎችም ይህንን አያስረዱም ፡፡
2. በፍርድ ቤት የተከሰስነው የግንቦት ሰባት እና የኦነግ አባልነት መሆኑ በግልጽ ተቀምጦ ሳለ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሚስጥር ማስመሰላቸው ጉዳዩ ላይ እውቀት አንደሌላቸው ያስረዳል፡፡
3. በመሰረታዊ የህግ መርሆ መሰረት ከሽብርተኛ ድርጅት ጋር አለመስራታችንን ማስረዳት ሳይሆን መንግስት በአቃቤህግ በኩል ወንጀል መስራታችንን ነው ማስረዳት ያለበት ፡፡ የማስረዳት ሸክሙን እኛ ላይ በመጣል መሰረታዊ የህግ ጥሰት ከመፈጸማቸውም ውጪ መንግሰታቸው የሚሰራበትን “ሁሉም ሰው ወንጀለኛ ነው ወንጀለኛ አለመሆኑን ማስረዳት አለበት” የሚል ትችት የሚሰነዝሩ ዜጎችን አንደወንጀለኛ የማየት አቅጣጫ ፍንትው አድርጎ ያሳያል ፡፡ በዚህም ወጣት የህግ ባለሞያዎች እንዳሉበት ስብስብ አፍረናል፡፡
4. መሰረታዊ የሆነው አፋጣኝ ፍትህ የማግኘት መብት በተራዘመ ምርመራ እና የፍርድ ቤት ቀጠሮ መጉላላት መጣሱ መንግስትን አንደማያሳስበው ማየታችን አሁንም አሳፍሮናል፡፡ አገራችን በፈረመቻቸው አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ህጎች መሰረት አፋጣኝ ፍትህ ማግኘት የዜጎች መብት ሲሆን የመንግሰት ከፍተና አመራረር ያለምንም ማፈር የመብት ጥሰቱን መከላከላቸው አስገራሚ ነው ፡፡

በመሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ ሌሎች ከፍተኛ የመንግሰት ባለስልጣናት ያልተፈረደባቸውን ተከሳሾች ሽብርተኛ በማለት መፈረጃቸው አንዲያቆሙ ፣ መሰረታዊ የወንጀል ህጎቸን አንዲያከብሩና አንዲያስከብሩ ልናሳስብ አንወዳለን፡፡

የዞን9 ጦማርያንም ሆነ ወዳጅ ጋዜጠኞች በምንም አይነት ወንጀል ተሳትፈው የማያውቁ ሲሆን ክሳቸውም ፓለቲካዊ ነው ፡፡ ተከሳሾቹን በነጻ ማሰናበት ለመንግሰት በጣም ቀላሉ ችግሩን የመፍቻ መንገድ ነው ፡፡

ስለሚያገባን እንጦምራለን!
ዞን 9

The post የዞን 9 ማስታወሻ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለመሆኑ፤ ይኼ ትግል የማንነው? –አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘጋጅ

$
0
0

ቅዳሜ፤ ግንቦት ፲፭ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 5/23/2015 )

electionእስኪ በመጀመሪያ አንባቢየን ልጠይቅ! ለመሆኑ ይኼ ትግል የማነው? ጥያቄው መሠረታዊ ነው። ለዚህ የምንሠጠው መልስ፤ ከዚያ በኋላ መከተል ላለባቸው ጉዳዮች በሙሉ ወሳኝ ነው። ያለጥርጥር ይህ ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግል ነው። ትግሉ ደግሞ በኢትዮጵያ ሕዝብና በሥልጣን ላይ ተቀምጦ፤ ሕዝቡን በማሰቃየትና ሀገሪቱን ወደ አዘቅት በመክተት ላይ ባለው የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ቡድን መካከል ነው። በድርጅቶች መካከል ያለ ምርጫ አይደለም። በሕዝቡ ተወከሉም ወይም ራሳቸውን ወከሉ፤ በውጭ ሀገር፤ በፖለቲካ ትግሉ ምኅዳር የተሰለፉ የትግል ድርጅቶች አሉ። እንግዲህ እዚህ ላይ፤ ኢትዮጵያዊ የሆኑትን ማለቴ ነው። በተጨማሪም፤ የዚህ ጽሑፍ መልዕክት፤ በውጪ ሀገር ያሉ ታጋይ ድርጅቶችን ብቻ ነው የሚመለከተው።

ታዲያ ትብብር ሲባል፤ በነዚህ ድርጅቶች እና ታታሪ ታጋይ ግለሰቦች መካከል ነው። ተደራጅተው በመገኘታቸው፤ ታጋይ ድርጅቶች ከፍ ያለ ሚና አላቸው። ትብብርን በሚመለከት፤ ሕዝቡ በአንድነት፤ “ተባበሩ ወይንም ተሰባበሩ!” እስኪል ድረስ ጩኸቱን አሰምቷል። በዚህ ሳምንት፤ ባልጎበኘኋቸው የኢትዮጵያዊያን ድረገጾች ስሽከረከር፤ የአቶ ዮሴፍ መርሻንና የአቶ እያሱ ዓለማየሁን ጽሑፎች አነበብኩ። በቪዲዮ ደግሞ የዶክተር ብርሃኑ ነጋን ንግግር አዳመጥኩ። ገረመኝ። እስከዛሬ ተባበሩልን የሚባሉት ጉምቱዎቹ እኒህ አልነበሩም እንዴ? ጠሪዎቹ ሆነው ሳገኛቸው፤ ደስ አለኝ።

የአቶ መርሻ ዮሴፍ ጽሑፍ ርዕስ እንዲህ ይላል፤ “በአንድነት ስንቆም ኃያል ነንና ዛሬም እንደወትሯችን እናብር!!”

በተመሳሳይ መልኩ፤ አቶ እያሱ ዓለማየሁ መተባበር የግድ አለብን የሚሉ መልዕክቶችን አስፍረዋል።

ዶክተር ብርሃኑ ነጋም በቪዲዮው፤ መተማመን፣ ትብብርና አብሮ መሥራት የግድ አንዳለብን አስምረዋል።

በግለሰብ ደረጃና በየተሰባሰቡበት ሁሉ፤ አቶ ኦባንግ ሜቶ፣ ኮሎኔል ሮቤል አባቢያ፣ ዶክተር አበባ ፈቃደ፣ ዶክተር መሳይ ከበደ፣ ዶክተር አክሎግ ቢራራ፣ ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም፣ አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው፣ አቶ አበበ በለው፤ በጽሑፍም በንግግርም ይኼኑ ሲሉ ተደምጠዋል። የግለሰቦቹን ለጊዜው ላቆየውና፤ ሸንጎና የሽግግር መንግሥት ካዉንስል በተደጋጋሚ ይኼኑ ዋና መልዕክታቸው አድርገው፤ ይሯሯጣሉ። ታዲያ ምኑ ላይ ነው ጉድለቱ። ይኼ ትግል የማነው? ጠሪው ማነው? ተጠሪው ማነው። የትኛው ድርጅት ነው ኑ ሳይባል ቀርቶ፤ ኑ እያለ ጥሪ ያላቀረበ?

እስኪ ወደ መጀመሪያዎቹ ሶስቱ ጉምቱ መሪዎች ልመለስ። አቶ መርሻ ዮሴፍ! እርስዎ ጥሪ አቅርበዋል። አቶ እያሱ ዓለማየሁ እርስዎ ጥሪ አቅርበዋል። ዶክተር ብርሃኑ ነጋ! እርስዎ ጥሪ አቅርበዋል። ይህ ትግል የናንተ ነው። የናንተ ያልኩበት ምክንያት፤ ሕዝቡን ወክላችሁ ሕዝባዊ ትግል እያካሄዳችሁ ስለሆነ ነው። ታዲያ ተጋባዥ ማነው? ጋባዥስ ማነው? ጋብዛችኋል። ተጋብዛችኋል። መቸም አልኩ ለማለት ጥሪውን አቀረባችሁ የሚል ወንጀል ፈጽሞ አይወጣኝም። ታዲያ ምንድን ነው የምትጠብቁት?

እንዲህ ይሁን። ለመሰባሰብ ፈቃደኛ ብቻ ሳትሆኑ፤ ሰብሳቢም ለመሆን ጥሪ አቅርባችኋል። በጄ! አንዳችሁ ለሌላችሁ መልስ መሥጠት አልወደዳችሁም። ፍቀዱልኝና እኔ ነኝ አልወደዳችሁም ያልኩ። ጥፋቱ ከኔ ይሁን። እናም ልክስ ዝግጁ ነኝ። አንዳችሁም ንጹህና ጉድለት የሌለው አይደላችሁም። እኔም ብዙ ጉድለት አለኝ። ተሰባስበን እንከላዋለን። እርስበርስ ተጠራርታችሁ ስላልተገናኛችሁ፤ እኔ አገናኝ ልሁን። አስፈላጊውን ወጪም እራሳችሁ የማትችሉ ከሆነ፤ ሲሆን ረዳቶችን በማግኘት፤ አለያም ከዚህ የበለጠ ያገሬ ጉዳይ የለምና፤ እኔው ወጪውን ችዬ ላገናኛችሁ። ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ የለበትም። በቀጥታና በግልጽ መልስ ሥጡኝ። ባንድነት የት እንደምንገናኝና መቼ እንደምንገናኝ፤ መልሱን ስትሠጡኝ እንወስናለን። የትግሉ ባለቤቶች፤ ሲሆን ጋባዥ አያስፈልጋቸውም። ከሆነም በኔ ይሁንና ልጋብዛችሁ። እኔን ለመርዳት የምትሹ ግለሰብ ታታሪዎች ሁሉ፤ ጉዳዩ የናንተም ስለሆነ፤ እባካችሁ ወደኋላ አትበሉ፤ እርዱኝ! መወቃቀሻና መወዳደሻ ሰዓቱ አልቋል። የተግባር ሰዓቱ ተደውሏል። ሀገር ከሁሉም ይበልጣል። በሀገር የጎደለብንን እንስተካክላለን።

የትግል ባለቤትነትን የጠየቅሁት ወድጄ አይደለም። ከኔ የከበዱ፤ ከኔ የበለጠ የትግል ልምድና የትምህርት ልቀት ያላቸው ሊያገናኟችሁ ሞክረዋል። እኔ በልጬ አይደለም። ራሳችሁ የጠራችሁትን፤ ትግላችሁ የኔ ትግል በመሆኑ፤ ደፍሬ እጄን ዘረጋሁ። እናንተው ያላችኋቸውን መልሼ ለናንተው ብተርክ ስድብ ነው። አስፈላጊነቱ፣ ወቅታዊነቱ፣ . . . አጉል ድፍረት ይሆንብኛል። እናም ባደባባይ የናንተውን ጥሪ ለናንተው አድርጌያለሁና፥ መልስ ሥጡኝ። አንባቢም በትኩረት ይከታተለው። አቶ ዮሴፍና አቶ እያሱ የግል ቁጥሬ ስላላችሁ፤ ባመቻችሁ ጊዜ ልትደውሉልኝ ትችላላችሁ። ዶክተር ብርሃኑም ቁጥሬን ማግኘት አይርቅዎትም። አስፈላጊ ከሆነም በኢሜል ለያዳንዳችሁ እልካለሁና ከዚህ ሥር ባለው የኔ ኢሜል መልስ ሥጡኝና ስልኬን እልክላችኋለሁ። ባሁኑ ሰዓት ዋናው የታጋይነት መለኪያው፤ ለትብብር የምናሳየው ፈቃደኝነት ነው። እስኪ ምሩን። ፈቃደኛ በመሆንም እኮ ይመራል። እኔ ደግሞ ሀገሬ ላለችበት ሁኔታ ማድረግ የምችለውን ሁሉ ለማድረግ ወደኋላ አልልም።

ይህ ትግል የሚቀጥለው ትውልድ ትግል አይደለም። ይህ ትግል ያለፈው ትውልድ ትግል አይደለም። ይህ ትግል የኛ ነው። ባላቤትነቱና ኃላፊነቱን በድፍረት እንውሰድ። እንቆጠር። ዛሬ ነው ትግሉ። ዛሬ ነው ኃላፊነታችን። ዛሬ ከታጋዩ ሕዝባችን ጎን እንሰለፍ። ሕዝቡ እየታገለ ነው።

 

ከታላቅ አክብሮት ጋር

ምንጊዜም ኢትዮጵያዊ

አንዱዓለም ተፈራ   eske.meche@yahoo.com

Directly emailed to:

አቶ መርሻ ዮሴፍ  ms38498@yahoo.com

አቶ እያሱ ዓለማየሁ  iyasou19@aol.com

ዶክተር ብርሃኑ ነጋ  org@ginbot7.org   followup@ginbot7.org

Copies sent to:

ኢትዮሸንጎ                  የሽግግር መንግሥት ካውንስል

አቶ ኦባንግ ሜቶ፣           ኮሎኔል ሮቤል አባቢያ፣              ዶክተር አበባ ፈቃደ፣        ዶክተር አክሎግ ቢራራ፣ ዶክተር መሳይ ከበደ፣           ፕሮፌሰር ዓለማየሁ ገብረማርያም፣   አቶ አክሊሉ ወንድአፈረው፣          አቶ አበበ በለው፤

አቶ አብረሃ በላይ፣                   አቶ ግርማ በቀለ፣                     ዶክተር እምሩ አሰፋ

ከዚህ በተረፈ፤ በድረገጻቸው ያወጡት ዘንድ፤ ለኢትዮጵያዊ ድረገጽ አርታዒዎች እልከዋለሁ።

The post ለመሆኑ፤ ይኼ ትግል የማንነው? – አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ ውጤታማ የሚሆነው አስፈፃሚዎቹ ከወገንተኝነት ሲፀዱ ነው –ትዝታ በላቸው

$
0
0

29B7870E-08AB-41FB-B990-96E2A689EBC0_w640_r1_s_cx0_cy31_cw0“ምርጫ ዓለምአቀፍ ተቀባይነት ያለው የዴሞክራሲያዊ ሥርዓት መገለጫ ነው። አንድ ሃገር ነፃ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ የሥልጣን ዝውውር ካላደረገ ዴሞክራሲያዊ ተብሎ ሊገለፅ አይችልም” ዶክተር ዓለምአንተ ገብረሥላሴ ስለ ምርጫ ምንነትና መገለጫዎቹ በሰጡትን ትንተና ነው ይህንን ያሉት።

“ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማለትም አንድ ሕዝብ በሥልጣን ላይ ያለውን መንግሥት የሥራ ክንውኖች ጥሩውን ከመጥፎው ለይቶ የሚገመግምበት፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሥልጣን ይገባናል የሚሉ አዳዲስ ተወዳዳሪዎችን የፖለቲካ ፕሮግራም መርምሮ ለራሱ የሚበጀውን በማመዛዘን ውሣኔ የሚሰጥበት ሥርዓት ነው” ብለዋል ዶ/ር ዓለምአንተ።

“አንድ ምርጫ ውጤታማ የሚሆነውም የምርጫ አስፈፃሚ አካላት ከወገንተኝነት የፀዱና የዴሞክራሲያዊ ምርጫ መሥፈርቶችን ሁሉ በማሟላት ሕዝቡን ወክለው ሲሠሩና የምርጫ ውጤት ምንም ይሁን ምን ተወዳዳሪዎች የሕዝቡን ውሣኔ ሲቀበሉ ነው” ብለዋል።

ዶክተር ዓለምአንተ ገብረሥላሴ ለሃያ ዓመታት ያህል ዩናይትድ ስቴትስ ቨርጂንያ ግዛት በሚገኘው ዊልያም ኤንድ ሜሪ ኮሌጅ ሕግና ሕገ መንግሥትን አስተምረዋል፡፡ አሁን ጡረታ ላይ ናቸው።

ዕሁድ፤ ግንቦት 16 ኢትዮጵያ ከምታካሄደው ጠቅላላ ምርጫ ዋዜማ ትዝታ በላቸው ሰለ ነፃ ምርጫ ፋይዳና መገለጫዎቹም አነጋግራቸዋለች።

ለሙሉው ውይይት የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

Source:: voanews

The post ምርጫ ውጤታማ የሚሆነው አስፈፃሚዎቹ ከወገንተኝነት ሲፀዱ ነው – ትዝታ በላቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

ዓለምነህ ዋሴ የኃይለማርያም ደሳለኝን የአልጀዚራ ቃለምልልስ ይተነትነዋል (ያድምጡ)

$
0
0


ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ከአልጀዚራ ቴሌቭዥን ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ አለምነህ ዋሴ እንደሚከተለው ተንትኖታል:: ክፍል አንድ ከላይ ክፍል ሁለት ደግሞ ከታች ቀርቧል:: አድምጣችሁ አስተያየት ሰጡበት::

ክፍል ሁለት

du_pm_haile_mar_des

The post ዓለምነህ ዋሴ የኃይለማርያም ደሳለኝን የአልጀዚራ ቃለምልልስ ይተነትነዋል (ያድምጡ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የቻለ ፓርላማ ያልቻለ ፓልቶክ ይግባ (ሄኖክ የሺጥላ)

$
0
0

Birhanu Nega
የሆነው ይህ ነው
ወያኔ-ትግሬ ( የትግራይ ሰው የሆኑ የሀገረ ኢትዮጵያ ብሔር ሽፍቶች ) ፣ ስልጣን ላይ ወጡ ፣ ህዝቡ አጨበጨበ ፣ ሙህራኖች ከሚኖሩበት ሃገረ አማሪካን ፣ እንግሊዝ ፣ ጀርመን ወዘተ፣ ወዘ-ተርፈ ተጏዙ ፣ የተማሩት ሀገራቸውን ሊያገለግሉ ፣ እውቀታቸውን ሊያካፍሉ በየ ትምህርት ተቋማቱ ገቡ ፣ የቻሉት ቤተ- መንግስት ድረስ ዘለቁ ፣ ከያኔው ጠቅላይ ሚንስትር ጋ ተጨባበጡ ፣ ብርጭቆ አጋጩ ፣ አብረው ለመስራት ተስማሙ ፣ እንደውም አንዳንዶች እንደ ቀብድ አማራን የሚኮንን መጽሐፍ ጻፉ ።
ጊዜው ነጎደ ፣ ህውሃት ከተማ ሲገባ ፣ በሰላምና መረጋጋት ስም ሌባ በአደባባይ በመረሸን ፣ በአንቀጽ 39 ስር ፣ በሽግግር መንግስት እና ወዘተ ስር ደብቆት የነበረው ቀንዱ ወጣ ። ከሀገረ አማሪካ ከህውሃት ጋ ለመስራት የሄዱትን ሙህራኖች አሰረ ፣ ውዳሴ ህውሃት ወይም እርግማነ አማራ መጽሐፍ እንደበረከት ያቀረቡለትን አባረረ ፣ ከዚያ ድብድቡ ተጀመረ ።

ቀጠለ ። ታላላቅ የዩንቨርስቲ መምህራንን አባረረ ፣ እነ ዶክተር ታዬ ወ/ሰማ’ትን እና እነ ፕሮፌስር አስራት አሰረ ፣ በላዩ ላይ እኔ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋንና እነ ፕ/ር መስፍን ወልደማርያምን ጨመረበት ። ጥሉ ከረረ ። አሁንም ቀጠለ ። እነ አንዳርጋቸው ጽጌን ተፋታ ፣ እነ ብርሃነ መዋ እና እነ ክቡር ገናን አብጠለጠለ ። በዚህ ውሃ ውስጥ ሌሎች የኢሰመጉ አመራር አካሎች ፣ የመኢአድ ባለስልጣናት ፣ የሃይማኖት ሰዎች ተበሉ ። ሁኔታው ቀጠለ ፣ ሌባ በአደባባይ ከግንቦት 22 1983 እስከ ዛሬ እየገደለ ያለው ስርዓት ፣ ራሱ የወጣለት ሌባ ሆነ ።

ሲጀመር አብረው ለመስራት ከዚህ ከአማሪካ ተሳፍረው የሄዱት እነ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ማርሽ ቀየሩ ፣ ፊታቸውን እስከ ምርጫ 97 በከፊል አዙረው የምርጫ 97 ለት ጎራ ለዩ ። ባንድ ወቅት እጁን የጨበጡትን ጠቅላይ ሚንስቴር ስልጣኑን እንዲለቅ ሞገቱት ፣ ሞግተውትም አልቀረም ዘረሩት ። የዘረሩት ህውሃት ግን ከካርቶን ፌንቱ ተነስቶ የቅንጅት አመራሮችን አሰረ ። እነሱም ባጋጣሚ ባገኙት ድል እንደ ባቢሎን ሰዎች ልሳናቸው ተዘበራርቆ ስለነበር ተቦጫጨቁ ። ኃይሉ ነው ፣ ብርቱካን ናት ፣ ብርሃኑ ነው ፣ ወዘተ ወዘተ ተባባሉ ። ( በነገራችን ላይ ስለዚህ ሁኔታ ሳስብ ዛሬም ድረስ ያሳፍሩኛል ፣ ሀፍረቴ የሚመጣው ደሞ በጥቅምት 22እና 23 1998 በአደባባይ የተገደሉት ልጆች ሰልስት ሳይወጣ እነሱ ንትርክ በመጀመራቸው ነው ) ። በነገራችን ላይ ቀኑን ጠብቀን ” ቅንጅትን ማን አፈረሰው !” የሚል ጽሑፍ እናወጣለን ። በይበልጥ የኔ ብርሃነ መዋ እና የሌሎች የዛሬ ጀግኖቻችን አስተዋጾ ምን እንደነበር እናትታለን ። ምክንያቱም የስራ ልምድ () ማንነትን በደንብ ስለሚገልጥ ። አሁን አላማችን እሱ ስላልሆነ ወደ ዋናው ሃሳብ እንገስግስ ።
ከፈርሱት የቅንጅት አመራሮች ውስጥ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ ወደ አማሪካን በመምጣት ፣ በሃሳብ፣ በራእይ፣ ርዮት እና በወዳጅነት አብረው ከዘለቋቸው ሰዎች ጋ በመሆን ግንቦት ሰባትን መሰረቱ ። የግንቦት ሰባት እውቅና በሚድህበት ሰሞናት ፣ ህውሃት ግንቦት ሰባትን ማስተዋወቅ ጀመረ ። አሸባሪ ብሎ ሰየመው። ሊቀመንበሩን እና ሌሎች የማዕከላዊ ኮሚቴ አባሎቹን በአሸባሪነት ከሰሰ ። አሁን ላይ ሆኘ ሳስበው ህውሃት ይህንን ያደረገው የሚመስለኝ ለአንድ ነገር ሲል ነበር ። እንደምናቀው “አሸባሪ እዚህ አገር ታየ!” ብለው ያለ ምንም እውነት የሰው ሀገር እንደሚደበድቡት ምዕራባውያን ፣ ወያኔም ግንቦት ሰባትን የሚፈልገውን ለማሰር እና ለማጥፋት ማሳበቢያ ለማድረግ ነበር ። በዚህም የተንሳ ብዙ የብሔረ አማራ የጦር አዛዦች ከስልጣን ተባረዋል ፣ በየ መአከላዊው ታስረዋል ፣ ተገለዋል ። ብዙ ነጻ ጋዜጠኞች ( ምሳሌ እስክንድር ነጋና እና አንዷለም አራጌ ) ፣ እንደ ዞን 9 ያሉ የድህረገጽ ሞገደኞች ፣ እና ወዘተን ። ( በነገራችን ላይ ህውሃት አሸባሪነትን የማይፈልገውን ትግሬ ያልሆነ ብሔር ከስልጣን ማባረሪያ ምክንያት አድርጎ ሲጠቀም ግንቦት ሰባት የመጀመሪያው ድርጅት አይደለም ፣ እንደውም ከግንቦት ሰባት ቀደም ብሎ ብዙ የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ ባለስልጣናትን በኦነግ ስምነት አስሯል ፣ ገሏል ፣ ወዘተ )።

ታዲያ በዚህ ሁናቴ ላይ እያለ ነው ህውሃትን የማይመጥን ስህተት የተሰራው ። ግንቦት ሰባትን ከመንግስት ግልበጣ ጋ ያያያዘ ዜና አፈትልኮ ወጣ ። ያቺ ቀን ለግንቦት ሰባት ከፍተኛ የፕሮፖጋንዳ ሥራ ሰርታ አለፈች ። በዛ ውለታው ውስጥ ግን ብዙ የጦር መኮንኖችን መአከላዊ አስገብታ ማሰቃየት ጀመረች ። እንግዲህ በዚህ ሁኔታ ሰሞን ላይ ነው ኢሳት የተመሰረተው ። ( ምን ያህል እውነት እንደሆነ ባላውቅም ፣ ይህንን ኢሳት የሚባለውን ነገር በሃሳብነት ካፈለቁት ሰዎች መሃከል አንዱ አቶ ክንፉ አሰፋ ( የኢትዮጵያ ሚዲያ ፎረም ድህረ ገጽ ዋና አዘጋጅ ) እንደሆነ ሰምቻለሁ ። ምስጋና ሃሳቡን ላፈለቁት ። ሌላ ምስጋና ያንን ሃሳብ ላላባከኑት ! ( ለሰረቁት አላልኩም !) የግንቦት ሰባት ምናባዊ ጥንካሬ ወደ ቁሳዊ ህልውና ቀስ እያለ መቀየር ጀመረ ። በተለይም ትኩስ ሁኔታዎችን ለማብራራት በኢሳት መስኮት ላይ በተደጋጋሚ ብቅ እያሉ አስተያየታቸውን የሚሰጡት ዶ/ ር ብርሃኑ ነጋ ፣ ስለ አስመራ ጉዟቸው እና ቆይታቸው የነገሩን አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ፣ የራሱ የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ መታሰር ፣ የነ-መሳይ መኮንንና ፋሲል የኔ ዓለም የአስመራ ቆይታ ፣ ጦሩ ፣ ሳንጃው ፣ የግራር ክላሹ እና ወዘተ ነገሩን አሟሟቀው ። ግንቦት ሰባት ከአርበኞች ጋ ተዋሐደ ፣ ኢሳት እያንዳንዷን ነገር አስተላለፈ ። ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣቶች ይህንን መጀመሪያ መስማት ከዚያ ማዳመጥ ጀመሩ ። አንዳንድ ወዳጆቼ (የማቃቸው እና የማላውቃቸው ሰዎች ) ፣ በየት በኩል ጫካ ልግባ የሚል ጥያቄ ያጎርፉልኝ ጀመር ። ታዲያ በዚህ ሁኔታ ላይ እያለን ፣ ከዚህም ሁኔታ ቀደም ብሎ ፣ ምርጫ 2007 ድሆ ድሆ ከተፍ አለ ፣ ወያኔ-ትግሬ የለመደውን ውንብድና ጀመረ ። በቀን ጆሯቸው ምርጫውን በግራ ጆሯቸው ኢሳትን ሲያዳምጡ የከረሙት የአንድነት እና መኢአድ አባሎች ፍትህን ሲነፈጉ ፣ ፍትህ ልናገኝበት እንችላለን ወዳሉት ወደ ኤርትራ ጫካ ገቡ ። እንደኔ እምነት ( ከሚደርሰኝ መልእክት እና መረጃ ኢሳት ከፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቄ ጋ ያደረገውን ቃለ ምልልስ ጥበብ በተሞላበት መንገድ አድርጎት ቢሆን ምናልባት ዛሬ አሁን ካየነው በተሻለ “የሰው ጎርፍ ” አርበኞች ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል በሄደ ነበር )። አሁንም ቢሆን የምወደው እና የማከብረው ኢሳት እዚህ ጉዳይ ላይ በጥንቃቄ ይሄድ ዘንድ እንመክራለን ።

ምርጫው ቀጠለ ፣ መድረክ እንደለመደው ዛሬም ፓርላማ ገብቶ መሰዳደቡ እንደናፈቀው እገምታለሁ ( መድረክ ስል በተከታዮቹ እና መሪዎቹ መሃል ያለ የነጻነት አስተሳሰብ ልዩነት እንዳለ እጅግ ስለሚገባኝ ነው )። አንቦ ላይ መድረክን ደግፎ የወጣውን ሕዝብ አዲስ አበባ ላይ ቅንጅትን ደግፎ ከወጣው የ 1997 ሕዝብ በምንም ለይቼ አላየውም ። ሁለቱም ስርዓቱን ከመጥላት እና በስርዓቱ ተስፋ ከመቁረጥ የታየ እና አጋጣሚውን በመግለጽ ንዴቱን ለመግለጽ የወጣ ሕዝብ ስለመሆኑ ዶ/ር መራራ ጉድና በደንብ ያወቀዋል ። ብልጥ ፖለቲከኛ ስለሆነ እንደለመደው ያንን ኃይል ወደ ወንበር ለመቀየር እየትጋ ነው እንጂ !

ሰማያውዊም እስሩን ፣ እንግልቱን ፣ ስቃዩን እና መከራውን ተቋሙሞ ዛሬ ላይ ደረሰ ። ምርጫው ደረሰ ሰማያዊ ም አለሁ አለ ። እስከሚገባኝ ታዲያ የሰማያዊ ሃሳብ ኢፍትሃዊ በሆነ ምርጫ ተሳትፎ የተሰጠውን ድምጽ ይዞ ፓላማ መግባት እና የመንግስት ደሞዝተኛ መሆን ፣ ከዚያም በቴሌቪዥን በሳምንት ወይም በወር አንዴ እየቀረቡ ወያኔ ወስኖ ለጨረሰው ጉዳዮች ድምጽ አለመስጠት አይመስለኝም ። እሱ ከሆነ እኔም እንደ ብርሃኑ ነጋ የምርጫ ካርዳቹን ቅደዱት በሚለው ሃሳብ ላይ እስማማለሁ ። እኔ እማስበው ሰማያዊ ከዚያ የተለየ ማንነት አለው ብዬ ነው ። ጫካ መግባት አማራጩ የማይሆን የሚሆነው ፓርላማ ለምግባት ሰለወሰ ነው ብዬ እስከ አሁኗ ሰዓት ድረስ አላስብም ። ምክንያቱ ግን ያ ከሆነ አሁንም የምርጫ ካርዱን ቅደዱት በሚለው ሃሳብ እስማማለሁ ። ባንጻሩ ግን በአሁኑ ሰዓት እንደ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲ በጭንቅላታችሁ የያዛችሁት ሃሳብ ” የሆነለት ፓርላማ ፣ ያልሆነለት ፓልቶክ ይግባ ” የሚል እንዳልሆነ ስለማምን የምርጫ ካርዱን ቅደዱት በሚለው ሃሳብ ብዙም አልስማማም ።

እስከ መጨረሻው መጀመሪያ ድረስ በመታገል አምናለሁ ። የናንተ መንገድ ዛሬ የናንተ ብቻ ነው ፣ ነገ በምትወሱነት አካሄድ ወይ የናንተ ብቻ ሆኖ ይቀራል ወይም ደሞ ወደ ሕዝብ የኛነት ይቀየራል ።

ሄኖክ የሺጥላ

The post የቻለ ፓርላማ ያልቻለ ፓልቶክ ይግባ (ሄኖክ የሺጥላ) appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢትዮጵያ –የምርጫ ቀጣና ሳይሆን የጦርነት ቀጠና እየመሰለች ነው

$
0
0

Bahrdar

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዉጥ ይፈልጋል። የነገዉን ምርጫ እንደ መሳሪያ በመጠቀም፣ ለዚህ ግፈኛ መንግስት ተቃዉሞዉን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል። ህወሃት/ኢህአዴግ ህዝብ እንደተፋው ያውቃል። ከዚህም የተነሳ በብዙ ቦታዎች ፣ የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ተዘግተዋል። እንደ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር ያሉ ከተሞች የጦርነት ቀጠናዎች ይምስሉ። ቁጥሩ እጅግ በጣም ብዙ የሆነው የታጠቃ ኃይል ተሰማርቷል። ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆነ ኢትዮጵያዉይን እየታፈሱ ነው።

bahrdar 1
በአገር ቤት ያለው ሁኔታ እንዲህ እንዳለ ህወሃት/ኢሕአዴግ ከፍተኛ የአለም አቀፍ ተቃዉሞ ገጥሞታል። በርካታ የዉጭ ጋዜጦች ምርጫው የዉሸት እንደሆነ እየዘገቡ ነው። የአቶ ኃይለማሪያም የአልጃዚራም ቃል ምልልስ በአገዛዙ ላይ እጅግ ከፍተኛ የሆነ ዉርደትን አከናንቧል። አቶ ኃይይለማሪያ የአንድ አገር መሪ ሳይሆኑ ሃሺሻ ሳያገኝ ሲቀር የሻሺሽ ሱሰኛ እንደሚሆው ፣ የሚቀጠቀጡ ዱርዬ ነበር የሚመስሉት።

ሕወሃት/ኢሕአዴግ በራዲዮና ቲቪ በመዛት፣ የወታደር ብዛት በማከማቸት፣ ታንኮች በማሰማራት በ1997 እንዳደርገው የሕዝቡን ጥያቄ አፈቤ እገዛለሁ የሚል እምነት ይኖረዋል። ሆኖም 2007 እንደ 1997 አይደለም።

ይሄ በአገዛዙ ላይ የደረሰው ዉጥረትና ውርደት ፣ የሕዝብ ትግል ያመጣው ነው። ይሄ የሕዝብ የትግል መነሳሳት ደግሞ በአገራችን የነጻነት ጮራ የሚፈነጥቅበት ጊዜ ቅርብ መሆኑ የሚያሳይ ነው። በርግጥም የሕዝብ ጉልበት ያሸንፋለ። እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እነርሱ እስከ አሁንም የኖሩት እየከፋፈሉ ነው። እኛ ግን ሚሊዮኖች ነን። እኛ ግን ዘር፣ ኃይይማኖት ሳንለይ አንድ ሆነናል።

The post ኢትዮጵያ – የምርጫ ቀጣና ሳይሆን የጦርነት ቀጠና እየመሰለች ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የ”ምርጫው”ውሎ ምን ይመስላል? –ከተለያዩ ከተሞች የተጠናቀረ

$
0
0

election
-‹‹እየተከተሉ እስከ ድምጽ መስጫው በመግባት ጫና ያደርጋሉ፡፡ ታዛቢ የሚባል ነገርም አላየሁም፡፡›› ሰሜን ወሎ ራያቆቦ

-‹‹በጣም ያሳዝናል፡፡ ራሳቸው ናቸው የሚመርጡት፡፡ ምልክት የሚያደርጉት እነሱው ናቸው፡፡ እንደ አጠቃላይ ፍትሃዊ አይደለም፡፡›› ደቡብ ወሎ ወግዲ ወረዳ
-ደብረማርቆስ ከተማ ላይ መንበረ ዘውዴ የሚባል የብአዴን ፀኃፊ ተዘዋዋሪ ታዛቢዎችን የሚጓጓበትን መኪና በማስቆም እንዳይታዘቡ አድርጓል፡፡ ታዛቢዎች ምዕርባ ጎጃም ፈረስ ቤት የሰማያዊ ፓርቲ ምልክት እንዳይኖር ተደርጓል፡፡

-‹‹ከንብ ውጭ ምልክት የለም፡፡ ከዛም ካርድ ይቀዳሉ፡፡ ሶስት ቀበሌዎች ተዘዋውሬ አይቻለሁ፡፡ መምህራን ስለሚጠይቁ ችግር እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህ ምርጫ ይበላል?›› ኦሮሚያ ክልል አደሬ ጮሌ ቀበሌ

-በተለያዩ የአዲስ አበባ ክፍሎች የሚገኙ የምርጫ ጣቢያዎች ላይ የሰማያዊ ፓርቲ ምልክት የለም እየተባሉ እንደተመለሱ መራጮች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

-‹‹ምክትል ሊቀመንበሩ ከምርጫ አስፈፃሚዎች ጋር በመሆን እያጠቆረ ለመራጩ ይሰጣል፡፡ የመራጩ ስራ ኮሮጆው ውስጥ ማስገባት ብቻ ነው፡፡ የሚሰማ ሰው ካለ አድርሱልን፡፡›› ምስራቅ ጎጃም ዞን ፈለገ ብርሃን ከተማ
-ደቡብ ጎንደር ዞን ወረታ ከተማ ላይ ከፍተኛ አፈና እና ወከባ እየተፈፀመ ነው
-በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ የሆኑት አቶ መለሰ ተሸመ ትናንት ማታ በደህንነቶች ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ አልታወቀም፡፡ በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ስቴ ወረዳ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱም ታዛቢዎች እግርና እጃቸው ላይ ከፍተኛ ስብራት አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል፡፡
-ባህርዳር ላይ የድምፅ አሰጣጡ ሚስጥራዊ አይደለም ተባለ:..በአንድ ምርጫ ሳጥን ላይ አንድ ጊዜ የሚመርጡትም በካድሬዎች 1ለ5 የተጠረነፉት ነዋሪዎች መሆናቸውን ለማወቅ ተችሎአል፡፡
-አዲስ አበባ ውስጥ የወረዳ 12ና 13 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ ይድነቃቸው አዲስ መራጮች ጣት ላይ የሚቀባው ቀለም በሶፍትም እንደሚለቅ ማረጋገጡን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

-መታወቂያ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው

ወረዳ 20 ምርጫ ጣቢያ መታወቂያና የምርጫ ካርድ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው ተብሏል፡፡ ነዋሪዎች በዚህ አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ ስድስት ወር ሆኗቸዋል በሚል ያለ ቀበሌ መታወቂያ እየመረጡ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 5ና 8 ምርጫ ጣቢያ ላይ መታወቂያና የምርጫ ካርድ ያልያዙ ነዋሪዎች እየመረጡ እንደሆነ የአካባቢው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነት አቶ እስክንድር ጥላሁን ገልጾአል፡፡

-‹‹የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ካለ ንብ ሌላ የሚመረጥ ምልክት አያሳዩንም፡፡ ሌላ ምልክት አሳዩን ስንል ከፈለክ ይህን ምረጥ ከዚህ ውጭ የሚመረጥ የለም ነው የሚሉን፡፡ ይህ ምኑ ምርጫ ይባላል?›› ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ (ነገረ- ኢትዮጵያ)

The post የ”ምርጫው” ውሎ ምን ይመስላል? – ከተለያዩ ከተሞች የተጠናቀረ appeared first on Zehabesha Amharic.

ካድሬዎች መራጮችን እያስገደዱ ነው * እራሳቸው መራጮቹ ይናገራሉ * የመድረክና የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ይናገራሉ (መደመጥ መጋለጥ ያለበት የኢህአዴግ የምርጫ ሴራ)

$
0
0

ካድሬዎች መራጮችን እያስገደዱ ነው * እራሳቸው መራጮቹ ይናገራሉ * የመድረክና የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ይናገራሉ (መደመጥ መጋለጥ ያለበት የኢህአዴግ የምርጫ ሴራ)
ቢቢኤን ግንቦት 16/2007 ሰበር ልዩ የምርጫ ዘገባ
(ያዳምጡ ያጋልጡ ለሌሎችም ያስተላልፉ)
[jwplayer mediaid=”41652″]
election 2015 addis ababa

The post ካድሬዎች መራጮችን እያስገደዱ ነው * እራሳቸው መራጮቹ ይናገራሉ * የመድረክና የሰማያዊ ተወዳዳሪዎች ይናገራሉ (መደመጥ መጋለጥ ያለበት የኢህአዴግ የምርጫ ሴራ) appeared first on Zehabesha Amharic.

4 የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች ተደበደቡ * በክፍለሃገራት ኢሕአዴግ ራሱን በራሱ እየመረጠ ነው

$
0
0

election 2015 ethiopia
ሰማያዊ ፓርቲ የመደባቸው 4 የምርጫ ታዛቢዎች በገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች መደብደባቸው ተዘገበ::
ምስራቅ ስቴ የተበደቡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች
1. ታደለ ግዛው (ዳጉት ቀበሌ)
2. እሱ ያውቃል በላይ (ለዋዬ ቀበሌ)
3. ገብሬ ተፈራ (ደንጎልት ቀበሌ)
4. መልካሙ ነጋ (አበርጉት ቀበሌ)

በተጨማሪም ይስማው ወንድሙ የተባለ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ በጥይት መሳቱን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
*****
‹‹ጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ ከተማ ብርብር ምርጫ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎችን አዋክበው እንዳይታዘቡ አድርገዋል፡፡ ካቢኔ ኮሮጆው ክፍል ድረስ ገብተው ኢህአዴግ ላይ ምልክት እንዲያደርግ ጫና አድርገዋል፡፡ በተለይ ሴቶችንና ሽማግሌዎችን በግዳጅ ነው ያስመረጧቸው፡፡ በአጠቃላይ በጋሞጎፋ የህዝብ ታዛቢዎች የተመረጡት በኢህአዴግ ነው፡፡ ይህን ቀድመንም ተናግረናል፡፡›› አቶ ወንድሙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ

*****

‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ

*****
‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመራሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ/ከደጀን
*****
ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ አንድ እና ምርጫ ጣቢያ ዘጠኝ ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ምክንያት ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡
****
‹‹የኢህአዴግ አባላት ናቸው የምርጫ ወረቀቱን እየተቀበሉ ምልክት የሚያደርጉት፡፡ ታዛቢ የሚባሉት ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው፡፡›› ከዱር ቤቴ
*****
‹‹ባለስልጣናት ምርጫ ጣቢያው በር ላይ ቁጭ ብለው እጅ ይዘው እያስፈረሙ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ውጭ እንመርጣለን ያሉ ወጣቶች ከአካበቢው ተባረዋል፡፡ ችግሩን ለሌሎች ይገልጻል የተባሉ ወጣቶች ስልካቸውን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ከአካባቢው ርቀናል፡፡›› ስልጤ ዞን ላንፎሮ ወረዳ አርጢማ ቡላ ቀበሌ

(ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው)

The post 4 የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች ተደበደቡ * በክፍለሃገራት ኢሕአዴግ ራሱን በራሱ እየመረጠ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

በጉደር አምቦ ጸጥታው ደፍርሷል::ምርጫው ቆሟል::

$
0
0

Gondorበአቦ በባድዮ ጉደር አምቦ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ከቁጥጥር ውጪ ያደረጉ ችግሮች የተፈጠሩ ሲሆን በየምርጫ ጣቢያዎቹ የኢሓዴቅ የቅስቀሳ ፖስተሮች ተለጥፈዋል::ይህን ተከትሎ በጉደር ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ተፈጥሯል::በታዛቢዎች እና በምርጫ ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ አለመግባባቶች ተፈጥረው እስከ ድብድብ ተደርስል::‹‹ከንብ ውጭ ምልክት የለም፡፡ ከዛም ካርድ ይቀዳሉ፡፡ ሶስት ቀበሌዎች ተዘዋውሬ አይቻለሁ፡፡ መምህራን ስለሚጠይቁ ችግር እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህ ምርጫ ይበላል?›› ኦሮሚያ ክልል አደሬ ጮሌ ቀበሌ
‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ
ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 1 እና ምርጫ ጣቢያ 9 ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡ ከደጀን ‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ

The post በጉደር አምቦ ጸጥታው ደፍርሷል::ምርጫው ቆሟል:: appeared first on Zehabesha Amharic.

ህወሃትና ሌቦክራሲ በኢትዮጵያ ።ምርጫ ሳይሆን ግዳጅ –ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ

$
0
0

ሌቦክራሲ የሚለው የፖለቲካ ስርዓት ስያሜ የወያኔን ከ “ነጻ አውጭ ነት” ወደ ሌብነት ስርዓት መመስረት ያደረገውን ሽግግር አመልካች ነው። የሌቦች አገዛዝ ለማለት ነው። ሌቦክራሲ በስልጣን የባለጉ፤በሙስና የተዘፈቁ የሚመሩት ስርዓት ነው። በኢትዮጵያ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ከስልጣን ወጥቶ እንዲህ የህዝብ ንብረት በድፍረት የዘረፈበት ታሪክ የለም።እንዲህም አድርጎ ህዝብ ያፈነ ስርዓት አልነበረም። ይህ ምርጫ የሌቦች ስም ማደሻ ሰልፍ ማስተካከያ እንጂ ሌላ አይደም።የዚህ ስያሜ የሰጠነው ስርዓት እሰነብትበታለሁ የሚለው ትዕይንት ነው።የምናውቀው እባብ አዲስ ቆዳ የሚለብስበት።


police ethiopiaአፍ ተሸብቦ፤በግድ ምረጥ ብሎ፤ካልመረጥ ደግሞ “ይከተልሃል” ተብሎ ምን ምርጫ ይባላል? ግዳጅ እንጂ።የቀድሞ ታዛቢ ያፈረበት፤የተቸበት ምርጫ በኢትዮጵያ እየካሄድ ነው። ህወሃት መሩ መንግስት ያለሀፍረት ተመረጥኩ፤ህዝቡ እምነቱን ሰጠኝ ብሎ ለመደንፋት እየተመቻቸ ነው።

መጀመሪያ ዲሞክራሲን ምርጫ፤መመረጥ፤በየአራት፡ አምስት ዓመት፡ የሚመጣ፤ የሚሄድ አድርገን እንዳናይ በኛው ታሪክ እንኳን ቢያንስ የሁለት ዓሰርት ዓመታት ልምዳችን በቂ ትምህርት ሰጥቶናል።ከወያኔ ስርዓት ሌላ የነበረውን ትተን ማለት ነው።በምርጫ መሪዎች ማውጣት፤በምርጫው ጊዜ በሙሉ ፍላጎትና ስሜት መካፈልን አስመስክረናል።ኢትዮጵያውያን የዲሞክራሲ ስርዓት ናፍቆታቸውን የሁለት መቶ ዓመታት ልምድ አለን ከሚሉት ለምሳሌ አሜሪካ እንደማናንስ አሳይተናል።ኢትዮጵያዊው መራጭ ማለዳ የወጣ ጀምበር እስክትጠልቅ ድምጹን ለመስጠት ተራውን በመጠበቅ ጽናቱን አሳይቷል።

election 2015 addis ababaዲሞክራሲ የሚገነባ ስርዓት ነው።ሸፍጠኞችም የሚያንጹት አይደለም።ላገር ለህዝብ የሚሉ ከዝቡ ጋር ሆነው የሚያቆሙት ያገር መውደድ ፍሬ እንጂ ለወሬ ፍጆታ የሚቀርብም አይደለም።ዲሞክራሲ የባህል ለውጥ ማዕከል ነው።መከባበርን ወግ የሚያደርግ ነው።ለአገር እድገት መሰረት ነው።በህግ መገዛትን መሰረት ያደረገ ነው።የሰው አክብሮት፤ፈሪሃ እግዚአብሄርም አጥሩ ነው። እውን ጠባብ ብሄርተኞች፤ክፋትና ጥላቻ አስፋፊዎች ዲሞክራሲን ያበስራሉ ? ህወሃት መሩ መንግስትና ዲሞክራሲ ተቃራኒዎች ናቸው።

ዛሬ ኢትዮጵያ  የሚካሄደው ትእይንት የምርጫ አቸናፊው ቀድሞ የታወቀበት ነው።እግር ተወርች የታሰረ ተወዳዳሪ ጡንቻውን ሊያሳይ ሁሉን ከሚያደርግ የመንግስት ፓርቲ ጋር ይወዳደራል። ይህ መሆኑን በግልጥ እያወቁ በኢትዮጵያ ፍትሃዊ ምርጫ ይደረጋል ብለው ሲመሰክሩም ታዝበናል።ምርጫማ አፍሪካ ሁሉ ያደርገው የለ? በአሜሪካ መንግስት አስተያየት በኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት እያደገ፤እየጎለበተ ነው። ይህን ያለ አምባገነን ሁሉ የሚያካሂደው “ውድድር” መልካም ነው እንደማለት ነው። እንኳን አሁን ፋሺሽት ኢጣሊያም ስትወረን ማን ከማን ጋር እንደቆመ የሚሳየው ታሪክ የሩቅ ጊዜ አይደለም።ኢትዮጵያ በውጭ ወዳጅ የታለች ሆና አታውቅም።ወዳጅ አለኝ ብለው ካልተማመኑት አባቶቻችን ለመማር ጊዜ የሚወስድ አይደለም። ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት ወዲህ ያለው ታሪካችን ብቻ በቂ ትምህርት ይሰጣል።

ሰሞኑን በቡሩንዲ ሶስተኛ ጊዜ ለመወዳደር ህጉን የቀየረውን መሪ ህዝቡ ለመቋቋም ሲታገል ተመልክተናል። “አታረጋትም !” ብሎ ሆ ብሎ ወጥቷል።ይህ እምቢታ ዛሬ ተሳካ አልተሳካ የጊዜ ጉዳይ ነው።የቡሩንዲ ህዝብ መልክቱን አስተላልፏል።በሚካሄደው የህወሃት የምርጫ ቲያትርም  የኢትዮጵያ ህዝብ የሚለውን እየጠበቅን ነው።የጠላውን፤ያንገሸገሸው፤ያስመረረው የህወሃት መንግስት “ከነምርጫ ቲያትርህ ጥርግ በል” ሊለው ይችላል። ከዚህ ከውጭ ያለነው የምንታዘበው የኢትዮጵያ ህዝብ በትዕስግቱ፤እየደማ፤ እየታሰረ፤ሰብዕናው እንዲደፈር ቢደረግም ህወሃት መሩ መንግስትን ዛሬ አዳከሟል:: የውጭ ሀይሎችን የሙጥኝ እንዲል አድርጎታል። ህወሃት መሩን መንግስት በስርቆት ፋፍቶ መንቀሳቀስ የማይችል ዝሆን አድርጎ አዝሎታል።ገፍትሮ የሚጥለው ጊዜ መቃረቡን አመልካች ምክንያቶች ብዙ ናቸው።

ይህ ምርጫ ወትሮ ከሚደረጉት ልዩ የሚሆንበት ካጀቡት ሁኔታዎች አንጻር ሲታይ ነው።ወያኔ ሙሉበሙሉ የዲፕሎማሲ ክስረት እያናጋው አይደለም።የስለላ መዋቅሩ በትላልቅ ከተሞች አስልቷል።ተቃዋሚዎች በአድጎራ መቆም እየጀመሩ እንጂ ገና በህብረት በጥንካሬ አልቆሙም። ይህም ቢሆን ግን ያለው ነባራዊ ሁኔታ ህዝባዊ አመጽን የሚጭር ሁኔታ ቢከሰት ቶሎ የሚቀየር፤ መንግስቱን የሚያርድ ሁኔታ አይፈጠርም ማለት አይደለም።የንጉሳዊ ስርዓትና ደርግን የሸኗቸው ምክንያቶች በጣም ጨምረው ዛሬ በአገራችን ይገኛሉ። የኑሮ ውድነቱ ለከት የለውም::ወጣቱም ሆነ ሌላው ተስፋ ቆርጧል። የህዝቡ እሮሮ አንገሽግሿቸው ወያኔ በሚያውቀው መንገድ ሊገጥሙት የቆረጡ ህዝቡን አይዞህ የሚሉት ሀይሎች መኖር ዋናው ነው። ይህን ህወሃት መሩ መንግስት አታንሱብኝ ብሏል።በውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ልጆች በቁጭት ለተግባር መነሳታቸው አንዱ ትልቅ ክስት ነው።በኢትዮጵያ ህዝቡ በሚችለው ሁሉ በከተማ በገጠር ይህን የክፋት ስርዓት እየተቋቋመ ነው።የሌቦክራሲው ስርዓትን የሚሰናብቱ እኒሁ ሶስት ረድፎች ናቸው።የህዝብ ትግል በከተማ በገጠር፤በውጭ ያለነው እርዳታ፤ህወሃት መሩን መንግስት በሀይል እያጫነቁት ያሉት ወንድሞቻችን ጽናት አይነተኛ ነው።ከነዚህ ሀይሎች ማንም  ደገፍኩህ ቢለው የህወሃትን መንግስት ሊያሰነብተው አይችልም።

በመጨረሻ ይህ ምርጫ ሲያልፍ ያው የተለምዶው ይቀጥላል እንጂ ወዲያው የሚቀየር ነገር ይኖራል ማለት ዛሬ አይቻል ይሆናል።አንድ ትልቅ ትምህርት ግን ትቶ ያልፋል። ህወሃት መሩ መንግስት በሰላም፤በምርጫ ይቀየራል የሚሉትን ግንዛቤአቸው ቀይሮ ያልፋል። ይህ ደግሞ ለወሳኙ ፍልሚያ ጠቃሚ ነው። ወያኔን አንበረካኪ ሁኔታ ሳይኖር የሰላም ሽግግር የማይሆን መሆኑን አስገንዝቦ ማለፉ ለዲሞክራሲ ትግላችን ያቀረበው ትምህርት ይሆናል።

ምርጫን ለህዝብ ቅንጣትም ደንታ የሌላቸው መንግስታትም ያደርጋሉ። ወጉ ምርጫ መካሄዱ ሳይሆን እንዴት ባለ ስርዓት ተካሄደ ነው።ምርጫ ሲደረግ ህዝብ የወደደውን ያሰነብታል።የጠላውን ያሰናብታል።ሁሉም በስልጣን ያለ “ተመርጨ ነው” ማለትን ይወዳል።ተመረጠ ተወደደን አመልካች በመሆኑ።ለዚህ ገና አልታደልንም።የተቀናጀ ትግል ይጠይቃል።

 

የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ!ምርጫ ከመካፈል በፊት ይህ ይቀድማል።

ኢትዮጵያ በክብር፤በአንድነት፤ተረጋግታ በነጻነት ትኖራለች።የጃዙር ቅኝ ግዛት አትሆንም!!!

 

 

 

 

 

The post ህወሃትና ሌቦክራሲ በኢትዮጵያ ።ምርጫ ሳይሆን ግዳጅ – ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአ.አ. አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የተቃጠለው የአረቄ ፋብሪካ የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ ንብረት መሆኑ ታወቀ

$
0
0

በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የአረቄ ፋብሪካ የኢህአዴግ ባለስልጣኖች መሆኑን ያወቁ ሰዎች እንዳቃጠሉት ታወቀ።በአዲስ አበባ አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው አረቄ ፋብሪካ ንብረትነቱ የከፍተኞች የኢህአዴግ አመራሮች የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ መሆኑን የተገነዘቡ ወገኖች ይህ ፋብሪካ በሃገርና በህዝብ ገንዘብ ተሰርቶ ለባለስልጣኖች ጥቅም ብቻ መዋል የለበትም በማለት ግንቦት 11/2007 ዓ.ም እንዳቃጠሉት የሚስጥሩ አዋቂ ምንጮቻችን ከከተማዋ ገለፁ።
fire
ፋብሪካው እየተቃጠለ በነበረበት ወቅት ሲመለከት የነበረው ነዋሪው ማህበረስብ፣ እሳቱን ለማጥፋት ምንም አይነት እገዛ ማድረግ ያለመቻሉን የተመለከቱት የስርዓቱ ካድሬዎች ወሮበላ ተከታዮቻቸውን በማሰባሰብ ነዋሪውን ህዝብ ማን አቃጠለው ከእናንተ አልፎ ሌላ የሚያውቅ የለም ተናገሩ እያሉ ላይና ታች ቢሉም እንኳን ነዋሪው ህዝብ ግን እኛ የምናወቀው የለንም የምታውቁት ካለ ደግሞ እናንተ ንገሩን በማለት ለጥያቄአቸው በጥያቄ መልክ በመመለስ ምንም አይነት መረጃ ከመስጠት እንደተቆጠበ ለማወቅ ተችሏል።

The post በአ.አ. አቃቂ ክፍለ ከተማ የሚገኘው የተቃጠለው የአረቄ ፋብሪካ የኩማ ደመቅሳና አዲሱ ለገሰ ንብረት መሆኑ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.


48 የምርጫ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ ናቸው * 26 ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን መለሱ

$
0
0

election 2015 ethiopia addisዛሬ 12 ሰዓት የጀመረው ምርጫ በወከባ ተጀምሯል፡፡ ኢህአዴግ ካድሬዎች መራጮቹን በመጠርነፍ እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሆነ አዲስ አበባ ውስጥ ከምርጫ ጣቢያ 03 የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ታግደው በማርፈዳቸው ወረቀት ሳይቆጠር ምርጫው ተጀምሯል፡፡ በተመሳሳይ በወረዳ 15 ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ‹‹አትገቡም!›› ተብለው ወከባ እንደደረሰባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት አቶ ተገኔ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

በሌላ በኩል ወረዳ 6 ምርጫ ጣቢያ 20 መራጮች ጣት ላይ የሚደረገው መርገጫ ቀለም የሚለቅ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ቀለሙ የሚለቅ መሆኑን ገልጸው ቃለ ጉባኤ እንዲያዝላቸው ቢጠይቁም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደህንነቶች ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝና አንዳንዶቹ በወከባው ምክንያት በቦታው አለመገኘታቸውን ዕጩዎቹ ገልጸውልናል፡፡

ሲዳማ ቦርቻ ወረዳ ደግሞ 26 የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን እየመለሱ ሲለቀቁ፣ ሶስቱ መታወቂያን አልመልስም በማለታቸው አሁንም እንደታሰሩ ናቸው፡፡ በጉራጌ ዞን የም ልዩ ወረዳ ደግሞ 48 የሰማያዊ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

The post 48 የምርጫ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ ናቸው * 26 ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን መለሱ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔው ሚዲያ ኢሕአዴግ አ.አን እና ጎንደርን 100% አሸነፈ ሲል ዘገበ * ዶ/ር መራራና ዶ/ር በየነ ተሸነፉም አለ የወያኔው አይጋ

$
0
0
የማያፍረው ወያኔ ይህ ሁሉ ሕዝብ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ደግፎ አደባባይ ወጥቶላቸው ዶ/ር መረራ ተሸነፉ ሲል ከምርጫ ቦርድ በፊት በአይጋ ፎረም በኩል ይፋ አድርጓል::

የማያፍረው ወያኔ ይህ ሁሉ ሕዝብ ዶ/ር መረራ ጉዲናን ደግፎ አደባባይ ወጥቶላቸው ዶ/ር መረራ ተሸነፉ ሲል ከምርጫ ቦርድ በፊት በአይጋ ፎረም በኩል ይፋ አድርጓል::

የወያኔው ምርኩዝ ምርጫ ቦርድ የምርጫውን ውጤት ይፋ ሳያደርግ አይጋ ፎረም የተሰኘው አፍቃሪ ወያኔ ድህረ ገጽ፣ ወያኔ በአዲስ አበባ በአዲስ አበባ፣ በጎንደር ዞኖች 100% እንዳሸነፈ ገለጸ። ቁጥሩ እጅግ በጣም በርካታ ነዋሪ ድጋፉን ለመድረክ በሰጠበት፣ ዶር መራራ ጉዲና በተወዳደሩበት በአምቦ/ጉደር፣ እንዲሁም ዶ/ር በየነ በተወዳደሩበት ሃዲያ ዞን ኢሕአዴግ እንዳሸነፈም አይጋ ጠቅሷል። አዲስ አበባ፣ ሙሉ ጎንደር ዞኖችን 100% ወይኔ እንዳሸነፈ ነው የተገለጸው።

አይጋ ከህወሃት ጋር በቅኝት የሚሰራ ድህረ ገጽ እንደመሆኑ፣ ወያኔ ይፋ ሊያደርገው የሚችለው ዉጤት ምን ሊሆን እንደሚችል የሚያሳይ እንደሆነ አንድንዶች ይናገራሉ።
ሆኖም የሕዝቡን ስሜት አስቀድሞ ለመለካት ሆን ተብሎ እንደ ታክቲክ የተደረገ ዘገባ ሊሆንም ይችላል።
አይጋ የሚከተለውን ነው የዘገበው
“Although some expected Dr Merara and Dr Beyene to reclaim their lost seat in parliament preliminary count suggests EPRDF has won both seats and 100% sweep in the Capital City as well as other regions! The only region opposition has a chance to win some seats is in Amhara Kilil but that is not certain either so far Gondor is all gone to EPRDF”
ከዚህ ቀጥሎ ያለው በአምቦ/ጉደር መድረክን ደግፎ የተሰበሰበው ህዝብ ነው። እንግዲህ ይሄ ሁሉ ህዝብ እያለ ነው ወያኔ አሸነፍኩ የሚለው።

The post የወያኔው ሚዲያ ኢሕአዴግ አ.አን እና ጎንደርን 100% አሸነፈ ሲል ዘገበ * ዶ/ር መራራና ዶ/ር በየነ ተሸነፉም አለ የወያኔው አይጋ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እና የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ ልዩ ቃለምልልስ ስለምርጫው * አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል * በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል * በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸውና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የግንቦት 16 ቀን 2007 ፕሮግራም

< …የምርጫው ውጤት አስቀድሞ የተገመተ ገዢው ፓርቲ የፈለገውን ድምጽ ለራሱ የሚሰጥበት የይስሙላ ነው … በአገር ውስጥም በውጭም ያለው ለውጥ እንዲመጣ የሚሰራው ሀይል ግን በአንድነት ፈጣን ውሳኔ መውሰድ አለበት። በአገር ውስጥ አብዮት መቀስቀስ እንዲችል… >

ዶ/ር አክሎግ ቢራራ የአገር ቤቱን የይስሙላ ምርጫ አስመልክቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡት)

<…በምርጫው ድምጽ መሰረቅን አስመልክቶ ገበሬውም ተማሪውም መምህሩም በአጠቃላይ ሁሉም ተመሳሳይ ግንዛቤ አለው። ድምጼ እንዳይሰረቅ ብሎ ነበር በድፍረት ስቃይ እየደረሰበት ታዛቢ ልሁን ለው….ተቃዋሚዎች ተባብረው በጋራ የህዝቡን ድምጽ ለማስከበርና አስገድደው ወደ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ለማምጣት መታገል ለባቸው …>

የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ወጣት አምዶም ገ/ስላሴ (ከመቀሌ ምርጫውን አስመልቶ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ማብራሪያ የተወሰደ )

በየመን ያሉ ኢትዮጵያውያን አጣብቂኝ እና የተባበሩት ሀይሎች የአየር ድብደባ ያደረሱት ጉዳቶች(ልዩ ዘገባ)

የኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ በቬጋስ(ከበዓሉ አዘጋጆች አንዱ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ)

አስተያየት በአገር ቤቱ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ላይ

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የተቃዋሚ የምርጫ ታዛቢዎች ጥቃት ሲፈፀምባቸው ዋለ

አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል

ሕዝቡ በተዘረፈው ድምጹ ጉዳይ ተቃውሞ እንዳያቀርብ በሚል የሰብዓዊ ጥሰቱ ቀጥሏል

በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል

በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው

ኬኒያዊው ጠበቃ ፕሬዝዳንት ኦባማ ልጃቸውን ከዳሩልኝ ለጥሎሽ 50 ከብቶች 70 በጎችና 30 ፍየሎች እሰጣለሁ ማለቱ ተሰማ

የኤርትራ መንግስት ለአገሪቱ ወጣቶች ስድትና ሞት የሰብዓዊ ተሟጋች ድርጅቶች ጭምር ይጠየቃሉ አለ

ኢትዮጵያና ኤርትራ በኮንፊዴሬሽን እንዲዋሃዱ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ጠየቁ

የሔጉ ውሳኔ በአዲስ መልክ እንዲቀየር አንድ ታማኝ የተቃዋሚ መሪ ገልፀዋል

ሁቨር በኔቫዳ ስራ እንዲጀምር ህጉ ፀደቀ

ስራ ከመጀመሩ በፊት ለተቆጣጣሪው ኩባንያ ማመልከት አለበት ተብሏል

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: ዶ/ር አክሎግ ቢራራ እና የአረናው አምዶም ገ/ሥላሴ ልዩ ቃለምልልስ ስለምርጫው * አገዛዙ የሕዝቡን ድምጽ ወደጎን አድርጎ ለራሱ የሰጠውን የምርጫ ውጤት ይፋ ለማድረግ ተዘጋጅቷል * በኦሮሚያ አንዳንድ አካባቢዎች ተማሪዎች የሕዝብ ድምፅ እንዲከበር መጠየቅ ጀምረዋል * በአዲስ አበባ የ17 ዓመቷን ወጣት ሃና ሌላንጎን የደፈሩት ከ17 ዓመት እስከ እድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸውና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

የሻዕቢያ “የተሀድሶ” ስትራተጂ አካሄዱና አንደምታው

$
0
0

issayas afewerki
አክሊሉ ወንድአፈረው
ሜይ 22፣ 2015

በአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ የሚመራው አስመራ ላይ የተሰየመው የሻዕቢያ መንግሥት ለ 23 ዓመታት የተከተለውን አካሄድ እንዳላዋጣው በመገንዘብ ይመስላል በተወሰነ ደረጃ ለየት ያለ ገጽታን ለማሳየት እና ራሱን አለሳልሶና የሰላም አባወራ ሆኖ ለመቅረብ በመሯሯጥ ላይ ይገኛል። ይህ ምን መልክ ይዞ ነው የሚራመደው? ለሀገራችን ኢትዮጵያስ ምን እንደምታ አለው? የሚለው የዚህ ጽሑፍ ዋና Aላማው ነው።

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post የሻዕቢያ “የተሀድሶ” ስትራተጂ አካሄዱና አንደምታው appeared first on Zehabesha Amharic.

ለ50 ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ

$
0
0


(ዘ-ሐበሻ) በዘፋኝነት; በሙዚቃ አቀናባሪነትና በሙዚቃ መሳሪያ ተጫዋችነት የሚታወቁት ታዋቂው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ::

በፖሊስ ኦርኬስትራ ውስጥ የትራንፔት ሙዚቃ ተጫዋች የነበሩትና “አደሉላ (የዘማች እናት)” በሚለው ታዋቂ ዘፈናቸው የሚታወቁት ሻምበል ወደ ሙዚቃው ዓለም ከመግባታቸው በፊት የወርቅ ሰራተኛ ነበሩ:: ሻምበሉ በአንድ ወቅት ለዘ-ሐበሻ ዘጋቢ እንደገለጹት ወርቅ ሰሪነት የተቀጠሩት በወቅቱ 15 ብር ነበር::

ድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ዛሬ የተለዩት እኚሁ ባለጥምር የሙዚቃ ክህሎት ባለሙያ ሻምበል መኮንን ለሂሩት በቀለና ለተለያዩ የሙዚቃ ሰዎች ሙዚቃ አቀናብረዋል:: ለ50 ዓመታት በሙዚቃ ዓለም ቆይታቸውም በርከት ያሉ ሥራዎችን ሰርተዋል:: ሃመልማል አባተ ከሃረር መጥታ በአዲስ አበባ የሙዚቃ ሥራ እንድትሰራ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ትልቅ ሲሆን የቴዲ አፍሮ አባት አቶ ካሳሁን ገርማሞ የቴዲ አፍሮን እናት ባገባ ጊዜ ሚዜም ነበሩ::

የእኚሁ ታዋቂ አርቲስት የቀብር ስነስርዓት በኖሩበት ኮልፌ አካባቢ በሚገኝ ቤተክርስቲያን ነገ ይፈጸማል ተብሎ ይጠበቃል::

ቭዲዮውን ይመልከቱ::

shambel Mekonen Mersha

The post ለ50 ዓመታት በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ትልቅ ሥፍራ የነበራቸው አርቲስት ሻምበል መኮንን መርሻ አረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>