Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

በኦሮሚያ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች ተገደሉ * “ምርጫ ሳይሆን ዘረፋ ነው የተካሄደው”–ዶ/ር መረራ ጉዲና

$
0
0

Gudina
(ዘ-ሐበሻ) ትናንት እሁድ የተካሄደው ምርጫ በመሳሪያ የተደገፈ ዘረፋ እንጂ ምርጫ አልነበረም ሲሉ ዶ/ር መረራ ጉዲና አስታወቁ:: የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም የምርጫውን ሂደት አወገዙ::

ምርጫው በፌደራል ፖሊስ እና በልዩ ሃይሎች የሕዝብ ድምጽ እንዲሰረቅ መድረጉን ያጋለጡት ዶ/ር መረራ ጉዲና በአምቦ አካባቢ የተቃዋሚ ፓርቲ 2 የምርጫ ታዛቢዎች መገደላቸውንም ለኢሳት ገልጸዋል:: ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስም በደቡብ ክልል በተለያዩ ቦታዎች በመንግስት ታጣቂዎች የምርጫ ኮሮጆ ከመሰረቁም በላይ በርካታ የምርጫ ታዛቢዎች መደብደባቸውና ማስፈራሪያ እንደደረሰባቸው አስታውቀዋል::

በአሪሲ ኮፈሌ እንዲሁም አምቦ ሚደጋን ቶላ ላይ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች መገደላቸውንና በሌሎች ላይም ጥቃት መፈጸሙን ዶ/ር መረራ ገልጸዋል:: ዶ/ር መረራ ጉዲና ሕዝቡ በሰላማዊ መንገድ የተሰረቀውን ድምጹን ለማስመለስ እንዲታገልም ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

The post በኦሮሚያ ሁለት የምርጫ ታዛቢዎች ተገደሉ * “ምርጫ ሳይሆን ዘረፋ ነው የተካሄደው” – ዶ/ር መረራ ጉዲና appeared first on Zehabesha Amharic.


ምርጫ 2007: የአለም አቀፍ የመገናኛ ብዙሗን ዘገባና መሬት ላይ ያለዉ እዉነታ (ሊያደምጡት የሚገባ የሳዲቅ አህመድ ትንታኔ)

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የተሰጠ መግለጫ –“በምርጫ ተሸንፎ በስልጣን መቆየት አያዋጣም”

$
0
0

ወያኔ/ኢሕአዴግ በምርጫ ተሸንፎ እያለ አጭበርብሮ በሥልጣን ለመቀጠል በሚያደርገዉ መፍጨርጨር ለሚከተለዉ ማንኛዉም ሕዝባዊ ተቃዉሞ ተጠያቂ ነዉ።
የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን
Guji 2
በ 2007 ብሄራዊ ሀገር አቀፍ ምርጫ የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ከምርጫው ቅስቀሳ ጊዜ ጀምሮ ያለው ሁኔታ ነፃና ፍትሃዊ አለመሆኑን ባወጡት ሪፖርት አረጋግጠዋል::ወያኔ በምርጫው ቅስቀሳ ሂደት ድብደባ፣ አፈና ፣እስራት ፣ግድያ እና እንግልት በግልጽ ፈጽሟል:: (በምዕራብ ሸዋ ዞን ሚዳቀኝ እና በአርሲ ኮፈሌ የተፈጸመው ግድያ ፤ በእነ በቀለ ገርባ ላይ በበደሌ፣ ጅማ እና በነቀምቴ የተፈጸመውን ድብደባ ልብ ይሏል)::

ተቃዋሚዎች ወያኔ ኢሕአዴግን በምርጫ ክርክር አዋረዷት:: ህዝቡ ለመድረክ የሰጠው ድጋፍ ስላስደነገጠው ሃይልን በመጠቀም ጫና ቢያደርግም አልተሳካላትም:: ተስፋ ስቆርጡ ለምርጫው ሁለት ቀናት ሲቀሩት ጠ/ሚኒስትሩ ፓርላማው በማይጠራበት ወቅት ስብሰባ በመጥራት ማስፈራሪያ እና ዛቻ በተቃዋሚዎች ላይ ሰንዝረዋል:: ይህም አስቀድሞ የምርጫውን ውጤት ለመቀልበስ በሃይል ምርጫውን ለማጭበርበር ቅድመ ዝግጅት እያደረጉ እንደነበር የሚያስይ ነበር :: የኢሕዴግ ካድሬዎች የምርጫው ዋዜማ ሌሊት ከአለቆቻቸው የተላለፈውን ትእዛዝ ለመፈጸም አስቀድመው ኮሮጆ በመሙላት በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የፌዴራል ፖሊስ: ሚሊሺያዎች: ፈጥኖ ደራሽ ፖሊስ እና አድማ በታኝ ፖሊሶችን በማዝመት የምርጫ ቦርድ ተወካዮችን እና የተቃዋሚ (የመድረክ) የምርጫ ታዛቢዎችን መታወቂያቸውን በመቀማት እያስፈራሩ እየደበደቡ በርካቶችን (90%) ሙሉበሙሉ ማለት ይቻላል ከምርጫ ጣቢያ በሀይል አባረዋል።በርካታ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የምርጫ ካርድ ተከልክለዋል። የመምረጥ መብታቸዉን ተነፍገዋል።

ስለሆነም: ፀረ ሠላም እና ፀረ ዴሞክራሲ የዘረፋ ቡድን የፈጸመው ምርጫን ማጭበርበር ፣ የህዝብ ድምፅ መዝረፍ፣ ንጹሃን ዜጎችን መግደል እና የማሰር ድርጊት አጥብቀን እያወገዝን የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን ይህን መግለጫ አውጥቷል።

1. ኦፌኮ/ መድረክ በኦሮሚያ ክልል ምርጫዉን ሙሉ ለሙሉ አሸንፏል።
2. የተፈፀመው ድርጊት በማንኛውም አለም አቀፍ የምርጫ መስፈርት ተቀባይነት የሌለው እና ህገ ወጥ መሆኑን እንገልጻለን:: በጽኑ እናወግዛለን::
3. ይህንን የህዝብ ድምፅ ዝርፊያ እና የምርጫ ማጭበርበር ተከትሎ ለሚነሳው የህዝብ ተቃውሞም ሆነ መንግሥት ለወሰደው እና ለሚወስደው እርምጃ ተጠያቂው እራሱ ኢሓዴግ ነው።
4. የህዝቦች ህገመንግስታዊ መብቶች በተጣሰበት፣ በማፈንና በማስፈራራት ምርጫ አስፈፃሚዎች እና የምርጫ ታዛቢዎች ተባረው ምርጫ ተካሂዷል ለማለት አንችልም።
5. ህዝባችን የመረጠው ድርጅት ኦ.ፌ.ኮ /መድረክ/ የሚያደርገውን ቀጣይ የትግል ጥሪ ዝግጁ በመሆን እንዲጠብቁ እናሳስባለን ።
6. የወያኔን አፋኝ ስርአት እድሜ ለማሳጠር በትግል ላይ የምትገኙ ሃይሎች: ወያኔ ይህን ያህል ረጅም ዓመታት በስልጣን ላይ ሊቆይ የቻለው በራሱ ድርጅታዊ ጥንካሬ ሳይሆን የተቃዋሚ ሃይሎች ትግሉን በተቀናጀ ሁኔታ ያለመምራት በመሆኑ በቀጣይ ለሚደረገው ትግል የፖለቲካውን ክፍተት በመዝጋት ትግሉን ወደ ቀጣይ ምዕራፍ ለማሸጋገር በመተባበር እና ልዩነቶችን በማጥበብ እንድንታገል ጥሪ እናቀርባለን።

ትግሉ ይቀጥላል !!!!!!!!

የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን

The post የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድን የተሰጠ መግለጫ – “በምርጫ ተሸንፎ በስልጣን መቆየት አያዋጣም” appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል በ 70 ከመቶ ድምጽ እየመራ መሆኑ ተነገረ

$
0
0

election 2015 ethiopiaየቱርኩ የዜና ወኪል ትናንት ዘግይቶ ይፋ እንዳደረገው ከሆነ በአዲስ አበባ ከሚገኙ 23 ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ በ 16ቱ የድምጽ ቆጠራው ተጠናቆ ይፋ መደረጉን ተናግሯል፡፡ የምርጫ ቦርድ ምንጮቼ ነገሩኝ ያለው መረጃው በዚህ ቆጠራ ሂደትም ገዢው ፓርቲ ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል በ 70 ከመቶ እየመራ እንደሚገኝ ነው ይፋ ያደረገው፡፡ በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ካሉ ምርጫ ጣቢያዎችም እንደሚሰማው ከሆነ ገዢው ፓርቲ ኢህአዲግ በሚቀጥሉት አምስት አመታት ሀገሪቱን መምራቱ የተረጋገጠ ይመስላል ሲል ነው የዜና ምንጩ የተናገረው፡፡

The post ኢህአዴግ በአዲስ አበባ ምርጫ ክልል በ 70 ከመቶ ድምጽ እየመራ መሆኑ ተነገረ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዲስ ድምጽ ሬድዮ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አበበ በለው የወያኔ ማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊትን አጋለጠ

$
0
0
Abebe Belew

አበበ በለው

በስደት ላይ የሚገኘው ህጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በባልቲሞር ሜሪላንድ 41ኛው ጉባኤውን በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ሲኖዶሱ ያወጣው መገለጫ ይጠቁማል።በዚሁ መገለጫ ላይ ሲኖዶሱ ራሱን አይሲስ ብሎ በሚጠራው ቡድን የተሰዉትን ወጣቶች የኢትዮጵያውያን ሰማዕታት በሊቢያ ምድር መሰየማቸው እንደዚሁም ቤተሰቦቻችው እርዳታ የሚያሰባስብ በሊቀ ጳጳስ የሚመራ ግብረ ኃይል መቋቋሙን ያስረዳል። በተጨማሪም በዚህ የፈተና ወቅት መለያየቱ እንደማይበጅ አስረድቶ ራሳቸውን በገለልተኛነት መድበው የሚንቀሳቀሱ አብያተ ክርስቲያናትን ከህጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር አብረው እንዲሰሩ ጥሪ ያቀርባል።

ይህ በእንደዚህ እንዳለ ራሱን ለህጋዊ ሲኖዶስ ተቆርቋሪ በማስመሰል ግን ህጋዊውን ሲኖዶስ ላይ ማህበራዊ ሚዲያ መርዝ የሚረጭ ወጣት አሉባልተኛ ከወደ ላስቬጋስ ብቅ ብሏል።በሳውዝ አፍሪካ የወያኔ ኤምባሲ ተላላኪና ጉዳይ አስፈጻሚ የነበረው ጉደኛ ወደ ላስቬጋዝ ብቅ ብሎ ጃኬቱን ገልብጦ የወያኔ ተቋዋሚ የሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ ደጋፊ ሆኖ ተገኝቷል። ህጋዊ ሲኖዶስ ደግሞ የሚደግፈው በሲኖዶሱ ጥላ ስር ሆነው በመላው ሰሜን አሜሪካ፣በአውሮፓ፣በአውስትራልያና በአፍሪካ እየተዘዋወሩ የተሰደደው ኢትዮጵያውያንን እንደዚሁም ህጋዊውን ሲኖዶስ በትጋት የሚያገለግሉትን የወንጌል ገበሬዎችን በመሳደብና በማዋረድ እንደዚሁም ህጋዊ ሲኖዶስ ያልወሰነውን ውሳኔ በማንበብ ነው።በተጨማሪም ሕጋዊው ሲኖዶስ የገንዘብ አያያዝን አስመልክቶ ብክነት እንዳለ የሀሰት ወሬዎችን በማሰራጨት ነው። ዓይናችሁን ጨፍኑ እናሞኛችሁ ነው ነገሩ።

ወያኔ በዘመናችን የኛ የምንለው ነገር እንዳይኖረን የቤት ስራውን ጨርሷል። የኛ የምንላቸውን ተቋሟት ሰርጎ በመግባት ከፋፍሏል፣ የኛ የምንለውን ሲኖዶሱንም እየተጋለ ይገኛል፣ የሲኖዶስን ዓይን የሆኑትን የስደተኛውን አባቶች እያሳደደ ይገኛል። በዚህ ወቅት ነው አክቲቪስትና ጋዜጠኛ አበበ በለው መሰረቱን ዋሽንግተን ዲሲ ባደረገው የሬዲዮ አገልግሎት ይህንን ነገር ተከታትሎ ያጋለጠው። የመለስ ትሩፋት ጸሃፊ አቶ ኤርሚያስ እንዳሳሳበን ወያኔ ወጣቶችን በማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊት አሰልጥኖ የሃሰት መረጃ በማቅረብ የአንድነት የኢትዮጵያ ሃይሎችን መከፋፈል ዓይነተኛ ምግባራቸው ነው። በመሆኑም የበግ ለምድ ለብሰው የመጡትን የወያኔ ጀሌዎች እንደ አበበ በለው በየማእዘኑ እናጋልጣችው። ለማንኛውም ጋዜጠኛ አበበ በለው ከሁለት የኃይማኖት አባቶች ጋር ያዘጋጀው ፕርግራም እነሆ ተከታተሉት።

[jwplayer mediaid=”41734″]

The post የአዲስ ድምጽ ሬድዮ አዘጋጅ ጋዜጠኛ አበበ በለው የወያኔ ማህበራዊ ሚዲያ ሰራዊትን አጋለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

የጥረቱ ሂደት ዕድገት፤ # ፬ –አንዱዓለም ተፈራ

$
0
0
ቀን፤     ማክሰኞ፤ ግንቦት ፲፰ ቀን፤ ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 5/26/2015 ) 11፡00 ጠዋት፤ ፓሲፊክ የሰዓት አቆጣጠር
eskemecheአንድ ነገር ጥሩ እየተካሄደ ያለው፤ የመሰባሰቡ አስፈላጊነት በየቦታው ዋና መነጋገሪያ ጉዳይ መሆኑ ነው። ከዚህ አንጻር፤
  • የኢሕአፓ ዴሞክራሲያዊ ጊዜያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ ሁለት አባላት መድቦ፤ በቅድመ ዝግጅቱ ላይ ለውውይት ለመሳተፍ ወስነው አሳውቀውኛል።
  • የሸንጎ አባላት በሙሉ ልባቸው ተካፋይ እንደሚሆኑ አሳውቀውኛል።
  • የሽግግር መንግሥት አመራር አባላት ፈቃደኛነታቸውን ከማበረታቻ ቃላት ጋር ልከውልኛል።
  • አብረውኝ እንዲያስተባብሩ ከጠየቅኋቸው መካከል አራቱ ፈቃደኛ ሆነዋል። በአንድነት የሕዝባዊ መገናኛ እስክናበጅ ድረስ፤ ይኼንኑ የኔን የኢሜል አድራሻ ለጊዜው ልንጠቀም ተስማምተናል።
በተጨማሪ፤ ይሄ የመሰባሰብ ጉዳይ የማንም ግለሰብ ሆነ ድርጅት የግል ጉዳይ ስላልሆነ፤
  • ካሁን በኋላ ከማንኛውም ግለሰብም ሆነ የድርጅት ተወካይ ጋር እኔም ሆነ ሌሎች አስተባባሪ አባላት የምናደርገው የስልክም ሆነ ማናኛውም ዓይነት የግንኙነት ልውውጥ፤ ሕዝባዊና ታሪካዊ አስፈላጊነትና ተጠያቂነት ስላለበት፤ የሚቀዳ ነው። የግል ዘመቻ አልያዝንም።
  • የኔን ሆነ የሌሎችን አባላት ማንነት፣ የትምህርት ደረጃ፣ የትግል ተመክሮ፣ የማስተባበር ልምድ ማንም ማወቅ የለበትም። እያንዳንዱ ግለሰብም ሆነ የድርጅት ተወካይ፤ ማወቅ ያለበት፤ ራሱ የሚታገልለትን የግልም ሆነ የድርጅት ዓላማና ግብ፤ ጊዜያዊውን የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሀቅና የትግል አሰላለፍ፣ አሁን የሚያስፈልገውን ግንዛቤና አጣዳፊ ተግባር ነው። ከዚያ ተነስቶ ነው ማንም ግለሰብ ሆነ ድርጅት፤ ከሌሎች ጋር ሊያደርገው የሚፈልገውን ግንኙነት የሚወስነው። እኛ እንደ አበረታታች እንጂ እንደእንቅፋት መታየት የለብንም።
  • አሁንም ብዙ ግለሰቦች ለኔ ኢሜል እየላካችሁልኝ ነው። አመሰግናለሁ። በያላችሁበትም በመሰባሰብም ሆነ በግል ይሔኑ የመሰባሰብ ጉዳይ ልታራምዱ ይገባል። ሰዓቱ አሁን ነው። መበርታት አሁን ነው።
  • ከግንቦት ሰባት በድርጅት የተሠጠኝ መልስ የለም።
  • ለኢሕአፓ አመራር፤ ተሳታፊ እንዲመድቡ፤ እስካሁን በነበረው ግንኙነት በኩል፤ ጥሪ በዛሬው ቀን እንልካለን።
አሁን፤ የመጀመሪያውን የመግባቢያ ስብሰባ ማድረጊያ ሰዓቱ ነው። መጀመር የግድ ያለበት ጉዳይ፤ “ይጀመራል!” እየተባለ ውሎ ማደር የለበትም። መጀመር አለበት። የምንጀምረው በሚከተሉት ሰዎች ነው። ቀኑ በቅርብ ይወሰናል።
፩ኛ.      አሰባሳቢ ለመሆን ፈቃደኛ የሆኑ አምስት ግለሰቦች፤
፪ኛ.      በግለሰብ ለመገናኘትና ለመሰባሰቡ ፈቃደኛ ሆነ የተገኙ ስድስት አባላት፤
፫ኛ.      ከጊዜያዊው የኢሕአፓ ዴሞክራሲያ አስተባባሪ ኮሚቴ የተወከሉ ሁለት አባላት፤
፬ኛ.      ከሸንጎ አባላት የተወሰኑ ( ቁጥሩ አልተገለጸልኝም )፤
፭ኛ.      ከሽግግር ( ዝርዝሩን ገና አልወሰንም )፤
( ፈቃደኛ ከሆኑ፤ ከማንኛውም ኢትዮጵያዊ የውይይት መድረክም ሆነ የፖለቲካ ስብስብ፤ [EEDN, etc ] ቀርበውና ማንነታቸውን አረጋግጠው ሲገኙ፤ እናስተናግዳለን። )
መመዘኛ ነጥቦቹ፤ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተቀበሉ ናቸው።
፩.  የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና ጠላት ነው ብሎ የሚያምንና ለማስወገድ የሚታገል፤
፪.  ኢትዮጵያዊያን በሀገራችን የፖለቲካ ሂደት መሳተፍ ያለብን፤ በግለሰብ ደረጃ በኢትዮጵያዊነታችን ተሰባሰቦ ነው፤
፫.  ይህ ትግል ሀገራዊ ስለሆነ፤ ሁላችንም የተካተትንበት አንድ ኢትዮጵያዊ የትግል ማዕከል ያስፈልጋልና እንፍጠር፤
፬.  የኛ ጥረት፤ የሕዝቡን በሀገር ቤት መነሳሳት ለመርዳትና ከጎኑ ተሰልፎ ለድል እንዲበቃና አስተማማኝ እንዲሆን ነው፤
ESKEMECHE

The post የጥረቱ ሂደት ዕድገት፤ # ፬ – አንዱዓለም ተፈራ appeared first on Zehabesha Amharic.

አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ… (ክንፉ አሰፋ)

$
0
0

የ”ምርጫው” ድራማ እየተተወነ ሳለ፤ የቦርዱ ሊቀመንበር ዶ/ር መርጋ በቃና እና ምክትል ሊቀመንበሩ ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ለአቦይ ስብሃት ስልክ ደወሉ።

“ሃሎ?”

“ሃሎ፣ አቦይ ስብሃት ኖት?”

“ነኝ፣ ምን ፈለግክ?”

“ዶ/ር መርጋ በቃና እና ዶ/ር አዲሱ ገብረእግዚአብሔር ነን።”

“ችግር መስማት አልፈልግም። የታዘዛችሁትን አደረጋችሁ?”

“99.8% ህዝብ አልመረጠንም። ግን በታዘዝነው መሰረት ውጤቱን ገልብጠነዋል!”

“0.2% ብቻ ነው የመረጠን ማለት ነው?”

“አዎን ጌታዬ። ሌላ ምን እንታዘዝ?”

“99.8% ህዝብ የስም ዝርዝሩን አንብብልኝ።” አሉ አቦይ ስብሃት እየተባለ ይወራል።

election 2015 addis ababaአንድ ወዳጄ ስለ አቦይ ስብሃት የነገረኝ ታወሰኝ። ሰውዬው ከግመል እንኳን የማይሻል እንስሳ ብጤ ነው። ግመል ሳትጠጣ ለቀናት ትሰራለች አቦይ ስብሃት ደግሞ ሳይሰራ ቀኑን ሙሉ ይጠጣል። አብዛኞቹ የህወሃት አባላት እድሜያቸው እንደ አስተሳሰባቸው ስላረጀ ጨዋታቸው ከውሃ ጋር ነው። ከውድ ውሃ ጋር! ድንጋይን ውሀ ያስጮኸዋል!

ሜዳው የኢህአዴግ፣ ዳኛው ኢህአዴግ፣ ታዛቢው ኢህአዴግ፣ ድምጽ ቆጣሪው ኢህአዴግ እንዲሆን ተደርጎ የተዘጋጀው “ምርጫ” እነሆ ተጠናቀቀ። በአፈና የታጀበው ምርጫ ጸጥ-እረጭ ባለ ድባብ ተጠናቅቋል። ልክ አስገድደው እንደሚደፍሩ ወሮበሎች፤ በሃይል ጠልፈው ያላቻ ትዳር እንደሚመሰርቱ ጉልበተኞች፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ያለፍቃዱ እንደገና የአምስት አመት የትዳር ቁርኝት ውስጥ ገብቷል። ሌላ አምስት አመት። ሌላ የህወሀት ዘመን። ሌላ የጥርነፋ ዘመን! ሌላ የቁምራ ዘመን! ሌላ የመፈናቀል ዘመን! ሌላ የመሬት ነጠቃ ዘመን! ሌላ የስደት ዘመን!…

የህወሃት ሰዎች አሁን የጭንቀቱ ምእራፍ ሁለት ላይ ናቸው። በዛሬው እና በትላንቱ እለት የህወሃት ባለስልጣናት ተሰባስበው በፐርሰንቱ ምደባ ላይ ውይይት ይዘዋል። ዘረፋው ላይ ሁሉም በ 100% ይስማማሉ። ምደባው ላይ ግን ችግር አለ። አንዳንዶቹ ይህ ጉዳይ ተአማኝነት እንዲኖረው ለተቃዋሚዎቹ ትንሽ መልቀቅ ይኖርብናል ሲሉ ለሎች ደግሞ ይህንን ሃሳብ ይቃወማሉ። ጥቂት ተቃዋሚዎችን ፓርላማ እንዲገቡ መፍቀድ አለብን የሚሉ ተከራካሪዎች “ሌባ ከሰረቀው ጥቂቱን ቢሰጥ” እንደማይጎዳው ይናገራሉ። ይህንን የማይቀበሉት ግን የተቃዋሚዎች በፓርላማ መግባት ራስ ምታት እንደሚሆንባቸው በስፋት መክረዋል። 547 መቀመጫ የነበረው የቀድሞው ፓርላማ ውስጥ እውነትን የያዘ አንድ ተቃዋሚ ብቻ ጭንቅላታቸውን በጥብጦት እንደነበር ሁሉም አይዘነጉትም። ይህንን በድጋሚ መፍቀድ አልያም ውግዘቱን በመቀበል መሃል ባለ አጣብቂኝ ውስጥ ከርመዋል። ውጤቱን ከሰሞኑ ይፋ ያደርገዋል ዶ/ር መርጋ።

የዘንድሮው ዝርፍያ ጤናማ አይደለም። ልክ እንደ ቦራት ዘ-ዲክታተር ፊልም ተወዳዳሪዎችን እግር እግራቸውን እየመቱ ለብቻ ሮጦ፤ በራስ ዳኛ የድል ዋንጫ መረከብ? ይህ በእውነት በዚህ በ21ኛው ዘመን እጅግ የሚያሳፍር ተግባር ነው። ተቃዋሚ ሃይሎች በምርጫው ክርክር እና በትውልድ ስፍራቸው ላይ የነበራቸው የሕዝብ ድጋፍ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ በታየበት ሁኔታ ህወሃቶች 100% አሸንፈናል ሲሉ ከሌብነታቸው ይልቅ ንቀታቸው ጥርስ የሚያስነክስ መሆኑን ለአፍታ እንኳ አላስተዋሉትም። እጅግ ትንሽ ጭል ብላ የነበረችውን ዲሞክራሲ በምድረ ኢትዮጵያ ገድለው፣ ከፍነው ቀበሩት። አዲዮስ ዲሞክራሲ…

ፈረንጆች የሚሉት አባባል አለ። “ለነብሰ-ገዳዮች ትክክለኛ ዲሞክራሲ ማለት ፍጹም አንባገነን መሆን ነው።”

“በ100% ድምጽ ተመርጠናል!” አሉ። የመረጣቸው ህዝብ የቱ ይሆን? በአዲስ አበባ በነቂስ ወጥቶ “ወያኔ በቃን! መንግስቱ ይግደለን” ያለው ህዝብ ነው ወይንስ ለም መሬቱን ተነጥቆ ለባእድ የተሰጠበት የገጠር ህዝብ? በጋምቤላ፣ በቤንሻንጉል፣ በሁመራ…ወዘተ የተፈናቀለው ህዝብ ነው የመረጣቸው? ወይንስ አምቦ – ጉደርን እንደ ሱናሚ ያጥለቀለቀው ህዝብ ? የቱ ነው ወያኔን የመረጠው? ከስርአቱ ጋር ሆድና ጀርባ የሆነው ሙስሊሙ እምነት ተከታይ ነው ወይንስ በእምነቱ ጣልቃ እየገቡ ካድሬ ጳጳስ የሚሾሙለት ክርስቲያኑ ህብረተሰብ? ማን ነው ህወሃትን የመረጠው? እንደ ምጽዓት ለስደት እያኮበኮበ ያለው ስራ-አጥ ወጣት ነው ወይንስ በአነስተኛና ጥቃቅን ተደራጅቶ ድንጋይ የሚፈልጠው ወጣት ምሁር? መብራት እና ውሃ በፈረቃ ያደረጉበት ህዝብ ነው የመረጣቸው?… ለመሆኑ ስንት አመት ነው ህዝቡ ላይ እንዲህ የሚቀልዱት?

እነሱ ልባቸው በትእቢት ስለተወጠረ፤ ሌላው ህዝብ የማይመለከትና የማይሰማ ይመስላቸው ይሆናል። ትእቢት ደግሞ የውድቀት ምልክት ናት። በመጀመርያ የውጭ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ተደረገ። ዝም! በምርጫው ወቅት ደግሞ የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎችን አሰሯቸው። አሁንም ዝም ተባለ። ከዚያ ኮሮጆ እየተሞላ ቀረበና በቁም ያሰሯቸው ታዛቢዎችን ምሽት ላይ ፈትተው እንዲፈርሙ አዘዝዋቸው። የተያያዙት አስገድዶ መድፈር ነውና አንዳንዱን አስገድደው በተሰረቀ የድምጽ ሳጥን ላይ አስፈረሟቸው። ምርጫ 2007 በዚህ ሁኔታ “ሰላማዊ፣ ፍትሃዊ፤ ዲሞክራሲያዊና የህዝብ ተዓማኒነትን አግኝቶ” ተጠናቅቋል ሲሉ ፕ/ር መርጋ በቃና አበሰሩ። እኚህ ፕሮፌሰር ግን ህሊና ይኖራቸው ይሆን? ካላቸው በምን ለወጡት? በገንዘብ? ህሊና ስንት ያወጣል?

አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ከምርጫው በኋላ ስላለው ነገር ብዙም አላሉም። ማን እንደሚያሸንፍ እና በምን ያህል ድምጽ እንደሚያሸንፍ አስቀድመው ዘግበው ስለነበር ውጤቱን መድገም የፈለጉ አይመስልም። አስቀድሞ ውጤቱ የታወቀበት ምርጫ መሆኑን አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ብቻ ሳይሆኑ፣ ራሱ የምርጫው ቦርድ በድረ-ገጹ ላይ በግልጽ አስቀምጦት ነበር። የምርጫው ቦርድ በድረ-ገጹ እንዳስቀመጠው የኢሕአዴግ 501 ተወዳዳሪዎች የተመዘገበለት ሲሆን መድረክ 270፣ የሰማያዊ ፓርቲ 139 እጩዎች ብቻ እንዲኖራቸው ተደረገ። የሰማያዊ ፓርቲ 200 እጩዎች በምርጫ ቦርዱ ተሰርዘውበታል። 108 እጩዎች አስመዝግቦ የነበረው አንድነት ፓርቲም ስልታዊ በሆነ ዘዴ በቦርዱ እንዳይሳተፍ ታግዷል። ይህ እንግዲህ በሎተሪ ሰበብ የተገለሉትን ሳይጨምር ነው።

መቼም ይታገሉታል እንጂ አይታደሉትምና ቀኑ እስኪደርስ የኢትዮጵያ ሕዝብ ባልፈለገው ሊገዛ፤ ባላመነበት ሊዳኝ፣ ባልመረጠው ሊተዳደር ነው። አሁንም ዝምታን መርጧል። ዝምታ ራሱን የቻለ መልስ ነው። በዝምታ የተዋጠች እያንዳንድዋ ሰከንድ ቁርሾ ይዛ ማለፍዋም ግልጽ ነው። ማሰብ ላልተሳነው ሁሉ ዝምታ ያስፈራል። ምጥና ውሃ ሙላት በድንገት እንዲሉ ዝም ያለ ወራጅ ሲወስድ አይታወቅም። ጽዋም ሲሞላ ይፈስሳል…

አለም-አቀፉ ህብረተሰብም ዝርፊያውን ስለለመደው ችላ ብሎታል። የእንግሊዙ “ዘ ጋርዲያን” ጋዜጣ “ምርጫውን ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ እንደ አንድ ክስተትም አይቆጥረውም።” ሲል፣ ሂዉማን ራይትስ ዎች፤ አምነስቲ ኢንተርናሽናል፣ ፍሪደም ሃውስ፣ ሲፒጄ፣ የመሳሰሉት አለም አቀፍ የመብት ተከራካሪ ተቋማት አፈና የሰፈነበት እና ነጻ ሜድያ በሌለበት ሁኔታ የሚካሄደው ይህ ምርጫው ፍሱም ኢ-ፍትሃዊ እንደነ ገልጸዋል። አልጃዚራ፣ ዋሽንግተን ፖስት፣ ኒውዮርክ ታይምስ የመሳሰሉ ታላላቅ ሜድያ ውጤቱ አስቀድሞ የታወቀ ምርጫ ሲሉ ሂደቱን በክፉ ኮንነውል።

ነገሩ ግልጽ ነው። ነጻ ሜድያ በሌለበት፣ ገለልተኛ ታዛቢዎች ባልተፈቀዱበት፣ ነጻ ዳኛ በልተመደበበት ነጻ ምርጫ አይታሰብ። የዘንድሮው ክስተት ህወሃት የዘረፋ ደረጃውን ያወረደበት ምርጫ ነው። ከረቀቀ የዘረፋ ስልት ወደ ግልጽ የውንብድና ተግባር።

የጀርመን ድምጽ እንግሊዝኛው ክፍል ከምርጫው በኋላ ምንጮችን ጠቅሶ ሲዘግብ “ታዛቢዎ የቁም እስር ላይ ስለነበሩ ወደ ውጭ ወጥተው ምርጫውን መታዘብ አልቻሉም” ብሏል። የሰራዊት እና የሚሊሽያ አባላት በየምርጫ ጣብያው እየተገኙ መራጮችን እያስፈራሩ የተካሄደ ምርጫ በአለም ላይ ይህ ብቻ ነው። የምርጫ ዘመቻም በታጠቁ ሃይሎች ወታደራዊ ትእይንት የተካሄደው በኢትዮጵያ ብቻ ነው።

30 አመት ሙሉ ያል ህዝብ ፍቃድ በስልጣን መቆየት ይሰለቻል። እነዚህ ሰዎች የምእተ አመቱን አንድ አራተኛ የሃገሪትዋን ሃብት ብቻ ሳይሆን የህዝብን ድምጽም እየዘረፉ ተቀመጡ። ባለፉት 24 አመታት በአሜሪካ አምስት ግዜ መንግስት ተቀይሯል። በሆላንድ 7 ግዜ መንግስት ወርዶ በህዝብ ድምጽ ሲቀየር አይተናል። አፍሪካዊቷ ጋና አምስት ግዜ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ፣ ሶስት ግዜ ፓርላሜንታዊ ምርጫ አድርጋለች።… ያልታደልን ወይንም ያልታገልን እኛ ግን ለ30 አመታት በአንድ አንባገነን ተይዘናል።

ህወሃቶች በሩን ሁሉ ዘግተው ህዝቡን ወደማይፈለገው አመጽ እየገፉት ነው። ያልተረዱት ቢኖር አንደኛው በር ሲዘጋ ሌላኛው በር መከፈት መቻሉን ነው። የ90 ሚሊዮን ህዝብን ድምጽ ሰርቀው፣ አንደበቱን ለጉመው ምን ያህል እንደሚዘልቁ የምናየው ይሆናል። መቶ አመት የዘለቀ አንባገነን በታሪክ አልተከሰተም።

ከዚህ ቀደም ባስነበብኳችሁ ቀልድ ጽሁፌን ልቋጭ። አንድ የህንድ ኢንቨስተር አዲስ አበባ ዮሴፍ ቤተ ክርስቲያንን የቀብር ስፍራ አይቶ በሊዝ ሊገዛ ፈለገ። የአዲስ አበባ ባለስልጣናትን ጠርቶ እንዲሸጡለት ጠየቀ። ባለስልጣናቱም መልሰው ሌሎች ቦታዎች ሳያልቁ የቀብር ስፍራ ለግዜው እንደማይሸጡለት ነገሩት። ህንዱ መለሰና መከራቸው። “እኛ አገር ሰው ሲሞት እናቃጥላለን እንጂ አንቀብርም። ለምን ይህን ለም ቦታ ታባክናላችሁ?” አላቸው። ባለስልጣናቱም መለሱ፣ “እኛ አገር ደግሞ ሰውን በቁሙ እንጂ ሲሞት አናቃጥልም!”

 

The post አምስተኛው ዙር የድምጽ ዘረፋ… (ክንፉ አሰፋ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ተቃዋሚዎች የህዝብ ድምጽ ተሰርቋል የሚል ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠሩ ነው

$
0
0

11180611_976488465717327_5626230407392496810_n
– ምእራባውያን ዲፕሎማቶች ወያኔን እና ተቃዋሚዎችን ለማስማማት ደፋ ቀና እያሉ ነው::
– ወያኔ እና የምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት አሸናፊነታቸውን ለማወጅ እየመከሩ ነው::
– አለማቀፍ ሚዲያዎች እፍረት ያሌለበት ምርጫ ብለው የመሰከሩለት ወያኔ ፍርሃት ለቆበታል::
– ምርጫው ጋር በተያያዘ የተገደሉ ዜጎች አራት ደርሰዋል::
– ታዛቢዎችን እና እጮዎችን ጨምሮ በምርጫው ቀን በተደረገ አፈሳ በመላው ሃገሪቱ ከ500 በላይ ዜጎች ታስረዋል::
– የአፍሪቃ ሕብረት የታዛቢዎች ቡድን የድምፅ መስጪያ ኮሮጆዎች ድምፅ ከመሰጠቱ በፊት ባዶ መሆናቸዉን ለማረጋገጥ ቢጠይቁ እንዳልተፈቀደላቸዉ፤ ኮሮጆዎቹ የቅደም ተከተል መለያ ቁጥር እንዳልተሰጣቸዉ እና የሐገር ዉስጥ ታዛቢዎች ተሳትፎ እጅግ ደከማ እንደነበር አስታዉቋል። Minilik Salsawi (ምንሊክ ሳልሳዊ)

The post ተቃዋሚዎች የህዝብ ድምጽ ተሰርቋል የሚል ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ ሊጠሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


ፊታችንን ከምርጫ ፓለቲካ ወደ ሁለገብ ትግል እናዙር!- የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

$
0
0
ግንቦት 18 2007 ዓ.ም
ginbot 7ምርጫ 2007 ተጠናቆ ተወዳዳሪም አወዳዳሪም የሆነው ህወሓት ይፋ ውጤት እስኪገልጽ እየተጠበቀ ነው። ሁሉ በእጁ ነውና ባለሥልጣኖቹ ምን ዓይነት ውጤት እንደሚስማማቸው እስከሚነግሩን ጥቂት ቀናት ይወስዱ ይሆናል። ከፈለጉ ሁሉን የፓርላማ ወንበሮች ሊወስዷቸው ይችላሉ፤ ካሻቸው ደግሞ ጥቂቱን ለተቃዋሚዎች ሊሰጡ ይችላሉ። ወሳኞቹ እነሱ ናቸው። በዚህ የፓርላማ ወንበሮች እደላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ድምጽ አንዳችንም ሚና የለውም።
ምርጫ የሕዝብ የሥልጣን ባላቤትነት ማረጋገጫ ከሆኑ አቢይ ዲሞክራሲያዊ ተቋማት አንዱ መሆኑ የታወቀ ነው። ሆኖም ግን ነፃ ተቋማት በሌሉበት፤ በአምባገነኖች አስፈፃሚነት የሚደረግ ምርጫ የመራጮች ነፃ ፍላጎት መግለጫ በመሆን ፋንታ የገዢዎች ሥልጣን ማረጋገጫ መሣሪያ ይሆናል፤ ከአገራችን እየሆነ ያለውም ይህ ነው።
የዘንድሮው ምርጫ 2007 ከዚህ በፊት ከነበሩ በባሰ ለአፈና የተጋለጠ የነበረ መሆኑ ከጅምሩ በግልጽ የታየ ጉዳይ ነበር። በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲዎች ላይ አገዛዙ የወሰደው የግፍ እርምጃ የዚሁ የምርጫ ዘረፋ ስትራቴጂ አካል ነበር። ከዚያ በተጨማሪም መራጮች እውነተኛ ፍላጎታቸውን በነፃነት መግለጽ እንይችሉ ዘርፈ ብዙ ጫናዎች ሲደረግባቸው ቆይቷል። የተወዳዳሪ ፓርቲዎች አባላት እንደተፎካካሪ ሳይሆን እንደጠላት ሲሳደዱ፣ ሲታሰሩ፣ ሲደበደቡና ሲገደሉ ሰንብቷል። በምርጫው ሰሞንና በዕለቱ በተለይ ከተሞች በባዕድ ጦር የተወረሩ መስለው ነበር። ይህ ሁሉ ስነልቦናዊና አካላዊ ተጽዕኖ ታልፎ የተሰጠው ድምጽ ቆጣሪው ራሱ “ተወዳዳሪ ነኝ” ባዩ ህወሓት ነው።
በእንዲህ ዓይነት ምርጫ መሳተፍ ትርፉ “በሕዝብ ድምጽ ተመረጥኩ የማለትን እድል ለአምባገኑ ህወሓት መስጠት ነው”፤ “ለዓለም ዓቀፍ ማኅበረሰብም የተምታታ መልዕክት ማስተላለፍ ነው”፤ ”ለህወሓት ተጨማሪ ገንዘብ ማግኛና የኢትዮጵያን ሕዝብ መከራ ማራዘሚያ ነው“ በሚል በዚህ ምርጫ ላይ ማዕቀብ እንዲደረግ አርበኞች ግንቦት 7 ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል። በርካታ ወገኖቻችን የምርጫ ካርድ ቢያወጡም የደረሰባቸውን ጫና ተቋቁመው በምርጫው ባለመሳተፍ ላሳዩት ጽናት አርበኞች ግንቦት 7 አድናቆቱን ይገልፃል።
ህወሓት በስልጣን ላይ እስካለ ድረስ የምርጫ ጉዳይ እና የምርጫ ፓለቲካ ግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የተጠናቀቀ ቢሆንም እንኳን ተጨማሪ ማስረጃ ለሚፈልጉ ግንቦት 16 ቀን 2007 መጥቶላቸዋል። አሁን ከፊታችን የተደቀነው ጥያቄ የሚከተለው ነው – አገራችን ከህወሓት አፈና ነፃ ለማውጣት ያለን አማራጭ መንገድ ምንድነው?
አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ህወሓት ከኢትዮጵያዊያን ጫንቃ የሚወርደው ሕዝባዊ እምቢተኝነትና ሕዝባዊ አመጽን ባቀናጀ ሁሉገብ ትግል ነው ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት ለሁለቱም የትግል ዘርፎች ተስማሚ የሆኑ አደረጃጀቶችን አዘጋጅቷል።
ሕዝባዊ እምቢተኝነት፣ ታጋዩ ከመኖርያ ወይም ከሥራ ቦታው ሳይለቅ በህቡዕ የሚከናወን ትግል ነው። ሕዝባዊ አመጽ ደግሞ ከመኖሪያና ሥራ ቦታ ለቆ መንቀሳቀስን ይጠይቃል። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች የህወሓትን ህጎች በመቃወም የሚደረጉ ናቸው። ሁለቱም የትግል ዘዴዎች ድርጅት፣ ዲሲሊንና ጽናትን ይጠይቃሉ። ለድላችን ሁለቱም የትግል ዘርፎች እኩል ዋጋ አላቸው። እናም ከዛሬ ጀምሮ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ እንደዝንባለውና አቅሙ በሚመቸው የትግል ዘርፍ ይሳተፍ። ሕዝባዊ ኃይልን መቀላቀል የቻለ ይቀላቀል፤ ያልቻለው በያለበት ተደራጅቶ በሕዝባዊ እምቢተኝነት ይታገል።
በየመኖሪያ ሠፈሩና በሥራ ቦታዎች የሚቋቋሙ የአርበኞች ግንቦት 7 ማኅበራት በርካታ ሥራዎች አሏቸው። ከሁሉ አስቀድሞ ድርጅትን ማጠናከር የሁላችንም ድርሻ መሆኑ ሊዘነጋ አይገባም፤ እናም ትኩረታችን እዚያ ላይ እናድርግ። እያንዳንዳችን ከሚመስሉንና ከምናምናቸው ጋር ተነጋግረን እንደራጅ፤ ወያኔ የሸረሸረብንን በራስ መተማመን እና የእርስ በርስ መተማመንን መልሰን እንገንባ። ውስጥ ውስጡን ጠንካራ አገራዊ ኅብረት እንፍጠር፤ የዕለት ተዕለት ተግባሮቻችን ደግሞ አካባቢያዊ ይሁኑ። ድርጅታችንን እያጠናከርን ወያኔን ከሁሉም አቅጣጫ እንሸርሽረው እንገዝግዘው። በዚህ መንገድ በሚደረግ ሕዝባዊ ትግል የሚገኝ ድል ፈጣን ከመሆኑን በላይ የድሉ ሕዝባዊነት ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ይሆናል።
ስለሆነም እያንዳንዱ ለውጥ ፈላጊ ኢትዮጵያዊ ታጥቆ እንዲነሳ፤ ወደ ተግባራዊ ትግል ፊቱን እንዲያዞር አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ያቀርባል።
ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!!!
የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ

The post ፊታችንን ከምርጫ ፓለቲካ ወደ ሁለገብ ትግል እናዙር!- የአርበኞች ግንቦት 7 መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

መድረክ የእሁዱን ምርጫ ውጤት አልቀበልም አለ ‪

$
0
0

ምርጫ ቦርድ በዛሬው እለት ያወጣው ጊዜያዊ ውጤት ተቀባይነት የለውም ሲሉ የመድረክ ፓርቲ አመራር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ለቢቢኤን ገለጹ::
beyene_petros
የመድረክ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በምርጫው ሂደት ላይ ችግሮች የነበሩ በመሆኑ ውጤቱን አንቀበልም ብለዋል። አፍንጮ በር አከባቢ በሚገኘው የመድረክ ዋና ፅህፈት ቤት መግለጫ የሰጡት የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ ፣ ዶ/ር መረራ ጉዲና እና ሌሎች የመድረኩ አመራሮች ናቸው።

ምርጫ ቦርዱ በዛሬው እለት ይፋ ባደረገው ጊዜያዊ የምርጫ ውጤት መግለጫ ኢህአዴግ 100 ፐርሰንት በደረሱ ጊዜያዊ ውጤቶች ማሸነፉን ገልጽዋል፡፡ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ ያለው መድረክ በበኩሉ በዛሬው እለት በሰጠው አስቸኳይ መግለጫ ይህንን እንደማይቀበለውና በምርጫው ጊዜ የደረሱትን ችግሮች በመዘርዘር ለሁለት ሰአታት መግለጫ ሰጥቷል፡፡

The post መድረክ የእሁዱን ምርጫ ውጤት አልቀበልም አለ ‪ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአሜሪካ መንግስት ምርጫውን አሽሟጠጠው

$
0
0


ወያኔን በጓንትነት የሚተቀመው የአሜሪካ መንግስት በተቃዋሚ የለውጥ ሃይሎች ላይ በሲቭል ሶሳይቲ በነጻ ሚዲያዎች እና በነጻነት ድምጾች ላይ የሚደረገው ወከባ እንደሚያሳስበው በመግለጽ የአሜሪካ መንግስት ዲፕሎማቶች ምርጫውን እንዳይታዘቡ መከልከሉንና መደረጉን በለሆሳስ አንስቶ ከአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች ያገኘውን መረጃ ዋቢ በማድረግ የተቃአሚ ሃይሎች ታዛቢዎች በምርጫው ላይ እንዳይታዘቡ መደረጉ እንዳሳዘነው በመግለጽ በምርጫው ወቅት የነበረው የአፍሪካ ሕብረት ታዛብ ቡድን እንኳን የወከባዎች ተጋሪ እንደነበር ተናግሯል መግለጫው::
election
ለፍትሃዊ እና ነጻ ምርጫ አስፈላጊ የሆኑ ነጻ እና ለቅስቀሳ የሚሆን የመረጃ ማሰራጫ ሚዲያ የዲሞክራሲ እና የሰብአዊ መብቶች ሲቭክ ማህበራት እንዲሁም የተላያዩ አለም አቀፍ እና ሃገር አቀፍ ሕብረተሰቦች በታዛቢነት ባልተወከሉበት ምርጫ ማካሄድ አያስኬድም ሲል መግለጫው አሽሟጧል::ጋዜጠኞችን በማሰር እና በማሳደድ የበጎ አድራጎት ድርጅቶችን ገደብ በመስጠት የፖለቲካ ድርጅቶች ውስጥ ጣልቃ በመግባት የፖለቲካ ምህዳሮችን በማጥበብ ምርጫ ማካሄድ አይሞከርም ሲል መግለጫው ተናግሯል::

የአሜሪካ መንግስት ከኢትዮጵያ እና ከሕዝቧጋር ጠንካራ ግንኙነት አለው ያለው መግለጫው ዲሞክራቲክ ተቋማት ዕንዲጠናከሩ የፕሬስ ነጻነተ እንዲያብብ በሃገሪቱ የታፈነው የፖለቲካ ምህዳር ሁሉ ክፍት እንዲሆኑ ኢትዮጵያ የፈረመችውን የአለም አቀፍ ሰባዊ መብቶች ድንጋጌ ግዴታዎች እንድታከብር አብረን እንሰራለን ብሏል::

The post የአሜሪካ መንግስት ምርጫውን አሽሟጠጠው appeared first on Zehabesha Amharic.

“ምርጫው ተብዬውን ቧልት ላለመታዘብ ወሰንን”–አና ጎምሽ

$
0
0

የዘንድሮው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ተካሄደ፡፡ የምርጫውን ሂደት የታዘበው ብቸኛ ዓለምአቀፍ ተቋም የአፍሪካ ኅብረት ነው፡፡
The Honorable Ana Gomes blasts EU over human rights violations in Ethiopia (video)
ለወትሮ የኢትዮጵያን ምርጫዎች ይታዘቡ የነበሩትና አሁንም በዓለም ዙሪያ እየተንቀሣቀሱ የሚታዘቡት የአውሮፓ ሕብረትና የአሜሪካው የካርተር ማዕከል ግን አልተገኙም፡፡ ለምን?

የአውሮፓ ፓርላማ አባል የሆኑትና የ1997ቱ ምርጫ የኅብረቱ የታዛቢዎች መሪ የነበሩት አና ጎምሽ የአውሮፓ ኅብረት ያልታዘበው ምርጫው “ቧልት ስለሆነ ነው” ብለዋል፡፡

“የአውሮፓ ኅብረት የታዛቢዎችን ቡድን በመላክ ለገዥው ፓርቲ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ያካሄደ የማስመሰያ ማኅተም መስጠት ስላልፈለግን የደረስንበት የፖለቲካ ውሣኔ ነው” ብለዋል፡፡

ለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥት አሁን ባለው አቋሙ ዴሞክራሲያዊ፤ ፍትሐዊና ነፃ ምርጫ ለማካሄድ ብቁ ነው?

“አይደለም ብሎ የሚያሣምነኝ እስካልመጣ፤ አዎ ብቁ ነው” ይላሉ በደቡብ ሱዳን የፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ልዩ አማካሪ እንዲሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የላካቸው፤ በዩናይትድ ስቴትስ የተወካዮች ምክር ቤት የአፍሪካ ስፔሻሊስት ሆነው ለሃያ አራት ዓመታት ያገለገሉት አቶ ቴዎድሮስ ዳኘ፡፡

“ኢትዮጵያ ውስጥ የፖለቲካ ችግር አለ የሚባል ከሆነ ብዙውን ጊዜውን እርስ በራሣቸው በመጣላትና በውጭ ሃገሮች በመኖር ጊዜያቸውን የሚያጠፉት ተቃዋሚ ፓርቲዎችም ተጠያቂነቱን ሊወስዱ ይገባቸዋል” ብለዋል አቶ ቴዎድሮስ፡፡

ለተጨማሪ ከሁለቱም ጋር በተደረጉ ቃለምልልሶች ላይ የተዘጋጀውን ቅንብር የያዘውን የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡
[jwplayer mediaid=”41766″]

The post “ምርጫው ተብዬውን ቧልት ላለመታዘብ ወሰንን” – አና ጎምሽ appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ ቦርድ የአስቂኙን ምርጫ ውጤት ይፋ አደረገ * ኢሕአዴግ 100% አሸነፈ አለ * ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ወንበር አላገኘም

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ኢህአዴግ እና አጋር ድርጅቶቹ የዘንድሮውን አሳፋሪ ምርጫ 100% ማሸነፋቸውን ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ገለጸ:: ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ በፓርላማው ውስጥ መቀመጫ እንዳላገኘም ተገልጹዋል::
election board
የገዢው ፓርቲ መሳሪያና ገለልተኛ ያልሆነው ምርጫ ቦርድ ይፋ ባደረገው ሪፖርት ኢህአዴግ አዲስ አበባ ላይ ከ23 መቀመጫዎች ኢህአዴግ 23ቱንም መቀመጫዎች አግኝቷል።
– ከትግራይ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ31 መቀመጫዎች ውጤት ህውሃት/ኢህአዴግ 31 መቀመጫዎችን
– ከአማራ ክልል ከደረሱት የ107 መቀመጫዎች ውጤት ብአዴን/ኢህአዴግ 107 መቀመጫዎች
ከኦሮሚያ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ150 መቀመጫዎች ውጤት ኦህዴድ/ኢህአዴግ 150 መቀመጫዎችን
– በኢትዮጵያ ሶማሊ ክልል ቦርዱ ከደረሱት የ16 መቀመጫዎች ውጤት ኢሶዴፓ 16 መቀመጫዎችን
– ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከደረሱት የሰባት መቀመጫዎች ውጤት ሰባቱንም ቤጉዴፓ;
– ከደቡብ ክልል ከደረሱት የ95 መቀመጫዎች ውጤት ዴኢህዴን/ኢህአዴግ 95 መቀመጫዎች፣
– በጋምቤላ ክልል ጋህዴፓ ከሶስት መቀመጫዎች ሶስቱንም፣ በሀረሪ ክልል ሀብሊ ከ2 መቀመጫዎች አንዱን ሲያገኝ አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ፣
– በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ከሁለቱ መቀመጫዎች አንዱን ኦህዴድ/ኢህአዴግ ቀሪውን ሶህዴፓ አግኝተዋል
– ከአፋር ክልል ከደረሰው ከደረሰው የስድስት መቀመጫዎች ውጤት አብዴፓ ስድስቱንም መቀመጫ አግኝቷል።

በአሳፋሪነቱ የሚጠቀሰው የዘንድሮውን ምርጫ የአውሮፓ ሕብረት; የአሜሪካ መንግስትና ሌሎች ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ፍትሃዊ ያልሆነ ምርጫ ሲሉ አውግዘውታ:: ተቃዋሚዎችም የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበሉት አስታውቀዋል::

The post ምርጫ ቦርድ የአስቂኙን ምርጫ ውጤት ይፋ አደረገ * ኢሕአዴግ 100% አሸነፈ አለ * ምንም አይነት ተቃዋሚ ፓርቲ የፓርላማ ወንበር አላገኘም appeared first on Zehabesha Amharic.

ፍ/ቤቱ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የቀረቡ የሲ.ዲ መረጃዎችን ውድቅ አደረገ

$
0
0

zone9-bloggers6በእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ቀርቦባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሶስቱ ጋዜጠኞች ዛሬ ግንቦት 19/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ቀርበዋል፡፡ መዝገቡ የተቀጠረው አቃቤ ህግ አሉኝ ባላቸው ሲ.ዲዎች እና ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ብይን ለመስጠት ነበር፡፡
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ ብይን ሰጥቷል፡፡ ቀሪ ምስክሮቹን በተመለከተ ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ምስክሮቹን ለማቅረብ ፍርድ ቤቱ በተደጋጋሚ የሰጠውን እድል ባለመጠቀሙ እና ምስክሮቹን ላለማቅረቡ የሰጠው ምክንያትም በቂ ባለመሆኑ አቃቤ ህግ ያቀረበውን የተጨማሪ ጊዜ ባለመፍቀድ ከዚህ በኋላ ምስክሮቹን እንደማይሰማ አመልክቷል፡፡
አቃቤ ህግ በኤግዚቢትነት ይዟቸው የቆያቸውን የ12ቱን ሲ.ዲዎች ጉዳይ በተመለከተ ፍርድ ቤቱ ሲ.ዲዎቹ በማስረጃ ዝርዝሩ ውስጥ ፕሪንት ተደርገው የተያያዙ ሰነዶችን እንደያዙ ስለተገለጸ ሲ.ዲዎቹ ከማስረጃነትም ሆነ ከኤግዚቢትነት ውድቅ መደረጋቸውን ገልጹዋል፡፡
አቃቤ ህግ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የሲ.ዲ ዶክሜንተሪ ማስረጃ ማቅረቡን በመግለጽ ፍርድ ቤቱ እንዲመለከትለት የጠየቀ ሲሆን፣ ፍርድ ቤቱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ አቃቤ ህግ ሲ.ዲውን በጽ/ቤት በኩል እንዲያስገባ በማዘዝ በአንደኛ ተከሳሽ ላይ የቀረበውን ዶክሜንተሪ በቢሮ ዳኞቹና ጠበቆቹ እንዲመለከቱት ከተደረገ በኋላ ሲ.ዲው ሌሎችን ተከሳሾች ይመለከታል ወይስ አይመለከትም የሚለውን አይቶ ብይን ለመስጠት ለሰኔ 8/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል ተከሳሾች ጥያቄያቸውን ለፍርድ ቤቱ ለማስረዳት በሞከሩበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ የመናገር እድል ሲነፈጉ የተስተዋለ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ ፍርድ ቤቱ እንዲፈቅድላቸው ሲጠይቁ ‹‹ስነ-ስርዓት አድርጉ!›› ባለ ጊዜ ጦማሪ አቤል ዋበላ ‹‹እናንተ ራሳችሁ ስነ-ስርዓት አድርጉ….እንናገርበት! ይህ የመብት ጉዳይ ነው…በግልጽ ችሎት ላይ ህገ መንግስታዊ መብታችንን አክብሩ እንጂ…ጥያቄ አለን ተቀበሉን›› ሲል በመናገሩ ችሎት ደፍረሃል ተብሏል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ በአቤል ጉዳይ ላይ ብይን ለመስጠት ለግንቦት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

The post ፍ/ቤቱ በጦማርያኑ እና ጋዜጠኞች ላይ የቀረቡ የሲ.ዲ መረጃዎችን ውድቅ አደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

በምርጫ ቦርድ ውጤት የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል * ፊደል ቀመስ አባሎች ውጤቱን አልተቀበሉትም

$
0
0

ግንቦት ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ የግንቦት15ቱን ምርጫ መቶ በመቶ ማሸነፉ ከተገለጸ በሁዋላ የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል። ምንጮች እንደገለጹት በርካታ ፊደል ቀመስ አባሎቹ ኢህአዴግ አሸነፍኩ
ያለበትን የድምጽ ልዩነት አልተቀበሉትም። ውጤቱን የሚቃወሙ የግንባሩ አባላት ” ህዝቡ ከእንግዲህ በሰላም መንግስት እቀይራለሁ የሚለው እምነቱ ተሟጦ የሃይል አማራጭን ብቻ እንዲመለከት ከማድረጉም በላይ፣ የሃይል አማራጭን
የሚከተሉ ሃይሎች በህዝቡም ሆነ በአለማቀፉ ማህበረሰብም የተሻለ ተቀባይነት እንዲያገኙ ያደርጋቸዋል” በማለት ለድርጅቱ አስተያየታቸውን እየሰጡ ነው።
election 2015
በሌላ በኩል ደግሞ ተገኘ የተባለውን ውጤት ከመደገፍ አልፈው፣ ህዝቡ እንዴት ለተቃዋሚዎች ይህን ያክል ድምጽ ሊሰጥ ቻለ በማለት በቁጭት አስተያየት የሚሰጡ ደጋፊዎች መኖራቸውንም ምንጮች ገልጸዋል።

ኢህአዴግ እያሰባሰበ ባለው መረጃ ላይ እንደተገለጸው፣ አንዳንዶች ” ይህ ህዝብ ምን አይነት ልቡ የማይታወቅ ከሃዲ ህዝብ ነው! እንዴት ይሄን ሁሉ ልማት እያዬ ለተቃዋሚ ድምጹን ሊሰጥ ቻለ?” የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ ምርጫ ቦርድ ራሱ ባወጣው ሰሌዳ መሰረት የምርጫውን ውጤት መግለጽ የነበረበት ግንቦት21 ቢሆንም፣ የግንቦት20 በአልን ለማድመቅ እንዲረዳ በሚል ከእቅዱ በፊት እንዲገለጽ መደረጉን ምንጮችን ዋቢ በማድረግ
ዘጋቢያችን ገልጿል።

ኢህአዴግ በየክልሉ ከፍተኛ ወጪ የወጣበት የፌሽታ በዓላትን አዘጋጅቷል። ትናንት የገዢው ፓርቲ ደጋፊ አርቲስቶች ያዘጋጁት የኪነጥበብ ምሽት በብሔራዉ ቲያትር ተካሂዷል፡፡፡ በርካታ የፌዴራል የመንግስት መ/ቤቶች በተለያዩ ሆቴሎች
በዓሉን ለማክበር ጥሪ አስተላልፈዋል።

ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግን አሸናፊነት ቢያውጅም መድረክ የተባለው የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅቶች ስብስብ የምርጫውን ውጤት አልተቀበለውም። ድርጅቱ ምርጫው አነስተኛ የሚባሉ መስፈርቶችን እንኳ ያላሟላ በማለት አጣጥሎታል። መድረክ
በአገሪቱ ውስጥ ያሉ ገለልተኛ የሚባሉ ሰዎች ተመርጠው መምርራ እንዲያካሂዱ ጠይቋል።
ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫውን በተመለከተ ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ድረስ ያለው ነገር የለም። መንግስት የሰማያዊ ፓርቲ ደጋፊዎችን እያዋከበ በማሰር ላይ መሆኑ፣ ፓርቲውን አጣብቂኝ ውስጥ ሳይከተው አልቀረም። ሰማያዊ የምርጫውን
ውጤት ይቀበለዋል ተብሎ አይጠበቅም።

የአሜሪካ መንግስትና የአውሮፓ ህብረት ምርጫውን በተመለከተ በርካታ እጸጾችን አውጥተው ቢገልጹም፣ ከኢህአዴግ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንደማያቋርጡ አስታውቀዋል። የአሜሪካ ስቴት ዲፓርትመንት ባወጣው መግለጫ ዲፕሎማቶች
በምርጫ ታዛቢነት እንዳይሰታፉ መከልከላቸው፣ ምርጫው አሳታፊ አለመሆኑንና የተለያዩ ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች መታሰራቸውን በመግለጫቸው አመልክተዋል።

በምርጫው ሂደት ያጋጠሙ በርካታ አስገራሚ ክስተቶች ለኢሳት እየደረሱ ነው። ግንቦት12 ቀን 2007 ዓም በአዲስ አበባ ልዩ ቦታው ላንቻ ወይም ጠመንጃ ያዥ ነዋሪ የሆነ አንድ የ12 ዓመት ህፃን የኢህአዴግን የምርጫ መልዕክት ያየዘ
ፖስተር ከተለጠፈበት ግድግዳ ላይ ቀደሃል በሚል 6 ወር ተፈርዶበታል።

በአዲስ አበባ ችሎት በሚባል ቦታ አርብ ግንቦት 14 ቀን 2007 ዓ.ም ሁለት ማየት የተሳናቸው ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል። ወጣቶቹ የተያዙት አንደኛው ሙሉ ሰማያዊ ልብስ ለብሶ በመውጣቱ በተፈጠረው አተካራ ነው። የአካባቢው
ሴት ካድሬ አንደኛውን ማየት የተሳነው ወጣት “ለምን ሰማያዊ ልብስ ለበስክ የሰማያዊ ፓርቲ አባል ነሆይ?” በማለት ጥያቄ ስታቀርበለት፣ ጓደኛው “ምን አገባሽ ምንስ ብለብስ!” የሚል መልስ መስጠቱን ተከትሎ፣ ግለሰቧ በብስጪት
ለደህንነቶች ባስተላለፈችው ጥቆማ መሰረት ሁለቱም ወጣቶች በድንገት ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን እስከዛሬ ድረስ ታስረው ይገኛሉ።
መነን መሰናዶና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት እንዲሁም ፀሃይ ጮራ ት/ቤት ውስጥ የሚገኙ ቁጥራቸው 20 መምህራንና 30 ተማሪዎች የሰማያዊና የአንድነት ፓርቲ አባላት ናቸው በሚል ዝርዝራቸው ለጸጥታ አካላት ተልዕኮ በልዩ ሁኔታ ክትትል እንዲደረግባቸው ከአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከምርጫ በፊት ትዕዛዝ ተላልፎ እንደነበርም የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

The post በምርጫ ቦርድ ውጤት የኢህአዴግ ደጋፊዎች ከሁለት ተከፍለዋል * ፊደል ቀመስ አባሎች ውጤቱን አልተቀበሉትም appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ • ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል

$
0
0

‹‹በኃይል የተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስት በህዝብ ተቀባይነት የለውም››
• ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል
• ‹‹የአፍሪካ ህብረት ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል የእንጨት ድስት ነው›› አቶ ስለሽ
ሰማያዊ ፓርቲ የ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን እንደማይቀበለው አሳወቀ፡፡ ፓርቲው ዛሬ ግንቦት 21/2007 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ‹‹ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!›› በሚል ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ምርጫው ‹‹ከዚህ ቀደም ከተካሔዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ሊወዳደር የማይችል እጅግ ኢ-ፍትኃዊ፣ ወገንተኛና ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን አይቀበለውም፡፡›› ብሏል፡፡
semayawi Party
በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ፓርቲም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ እያወቀ መሆኑን የገለፀው ሰማያዊ በሂደቱ የተሳተፈው የስርዓቱን ችግሮች ለማጋለጥ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹በሂደቱ ውስጥ በመቆየታችን እጩዎቻችን በህገ ወጥ መንገድ ሲታገዱ፣ ታዛቢዎች ሲከለከሉና ሲታሰሩ አሳይተናል፡፡ በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል፡፡ ከመጀመሪያው ጀምሮም ሆነ በምርጫው ወቅት የነበረውን ማጭበርበር ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አጋልጠንበታል፡፡›› ብለዋል፡፡ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስለሽ ፈይሳ በበኩላቸው ምርጫው መትረየስ ተጠምዶ፣ ብረት ለበስ በየ መንገዱ ቆሞ፣ የአጋዚ ጦር አባላት ከተማ ውስጥ ተሰማርተው ከመካሄዱም ባሻገር ከፍተኛ የድምጽ ማጭበርበር የነበረበት ነው ብለዋል፡፡ የምርጫው ብቸኛ የውጭ ታዛቢ የሆነውን የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል ‹‹የእንጨት ድምጽ ነው!›› ሲሉ ተችተዋል፡፡
ምርጫው በህገ ወጥ አሰራሮች የታጀበ፣ በማንኛውም መመዘኛ ፍትሃዊ፣ ነፃና ተአማኒ ሊሆን እንደማይችል ሒደቱ በግልፅ አመላካች ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በውጤቱም በሐገራችን የዲሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ወደ መቃብር የከተተና ኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሐገር መሆኗን ያረጋገጠ ነው፡፡..ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የጨለማ ዘመን መምጣቱን ከማሳየቱ ባሻገር ኢህአዲግ በፍርሃት ተውጦ ሁሉንም ለመቆጣጠር ባደረገው ሩጫ ለመግለፅ እስኪያፍር ድረስ የሚያሸማቅቅ ውጤት እንዲከናነብ ሆኗል፡፡›› ብሏል፡፡ በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስትም በሕዝብ ተቀባይነት እንደሌለውም ገልጾአል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ በአፈና እና ጭቆና ውስጥ ሆነው ድምጽ ለሰጡት መራጮች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ በምርጫው ሂደት የተንገላቱ፣ የታሰሩትን፣ የተደበደቡና የተሰደዱትን አባላቱንም ፓርቲያቸው በኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ የተጣለበት እንዲሆን ለደረሰባቸው መከራና በደል ክብር ይገባቸዋል ብሏል፡፡ የዜጎች ነፃነት ሳይከበር ነጻና ፍትኃዊ ምርጫ ሊደረግ አይችልም ያለው መግለጫው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን እስከሚከበሩ ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ በሚያካሂደው የነጻነት ትግል ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጾአል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው አስታወቀ • ‹‹በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል›› ኢ/ር ይልቃል appeared first on Zehabesha Amharic.

የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ኢትዮ-እስራኤላዊው ወታደር የ100 ሺህ ዶላር ካሳ ጠየቀ

$
0
0

netanyahu

natanyahu 2
ገንዘቡን ለፍትህና እኩልነት ለሚታገሉ ድርጅቶች እሰጣለሁ ብሏል

ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ በእስራኤሏ ባት ያም ከተማ በፖሊስ የድብደባ ጥቃት የደረሰበት ኢትዮ-እስራኤላዊው ወታደር ዳማስ ፓካዳ፣ የተፈጸመብኝ ጥቃት ከዘረኝነት የመነጨ ነው ሲል በአገሪቱ ፖሊስ ላይ ክስ መመስረቱንና ለደረሰበት ጉዳት የ100 ሺህ ዶላር ካሳ እንዲሰጠው መጠየቁን “ታይምስ ኦፍ እስራኤል” ዘገበ፡፡የ19 አመት ዕድሜ ያለው ግለሰቡ ባለፈው ማክሰኞ በቴል አቪቭ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአገሪቱ ፖሊስ ላይ በመሰረተው ክስ፣ ለደረሰበት ጉዳትና ጉዳዩን በህግ ለመከታተል ላወጣው ወጪ ካሳ እንዲሰጠው የጠየቀ ሲሆን፣ ጠበቃውም በግለሰቡ ላይ የተፈጸመው ጥቃት የአገሪቱ ፖሊስ በዜጎች ላይ በተደጋጋሚ የሚፈጽመውን ስነምግባር የጎደለውና ሃይል የተቀላቀለበት ጥቃት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ግለሰቡ በፖሊሶች ጥቃት ሲፈጸምበት በካሜራ ባይቀረጽና ለማስረጃነት ባይቀርብ ኖሮ፣ ምናልባትም ፖሊስን በመድፈር ከባድ ወንጀል ተከሶ ሊቀጣ ይችል እንደነበር የገለጸው ክሱ፣ ጥቃቱ በግለሰቡ ላይ አካላዊና መንፈሳዊ ጉዳት ከማድረሱ ባሻገር የመላውን ኢትዮጵያዊ ቤተ እስራኤላዊ ልብ የሰበረ ነው ብሏል፡፡ ፓካዳ በፍርድቤት ተከራክሮ ካሸነፈና የጠየቀውን የገንዘብ ካሳ የሚያገኝ ከሆነ፣ የተወሰነ ያህሉን ገንዘብ ለፍትህና ለእኩልነት ለሚታገሉ የኢትዮጵያውያን ማህበረሰብ ድርጅቶች ለመስጠት ማሰቡን ተናግሯል፡፡

ሁለት የፖሊስ ባልደረቦች በግለሰቡ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ የሚያሳየው አጭር የቪዲዮ ምስል፣ በስፋት መሰራጨቱንና በቴል አቪቭ በሚኖሩ ቤተ እስራኤላውያን ዘንድ ከፍተኛ ቁጣና ተቃውሞ መፍጠሩን ተከትሎ፣ የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁና የፖሊስ ኮሚሽነሩ ዮሃናን ዳኒኖ ግለሰቡን በአካል አግኝተው ለተፈጸመበት ጥቃት በፖሊስ ስም ይቅርታ መጠየቃቸውና ከሁለት ሳምንታት በፊትም ጥቃቱን የፈጸመው አንደኛው ፖሊስ ከስራ መባረሩ ይታወሳል፡፡

ምንጭ አዲስ አድማስ ጋዜጣ

The post የዘረኝነት ጥቃት የደረሰበት ኢትዮ-እስራኤላዊው ወታደር የ100 ሺህ ዶላር ካሳ ጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

ግለሰቡ በትግራይ ክልል 6 ሰዎችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ገደለ

$
0
0

tigrai
(ዘ-ሐበሻ) በትግራይ ክልል ከሚሰራበት ባንክ መስሪያ ቤት የተባረረው ግለሰብ በፊት ይሰራበት ባንክ ገብቶ 6 የባንኩን ሠራተኞች መግደሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::

በትናንትናው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በምትገኘው ማይ ፀብሪ በተባለች ከተማ ይኸው ቀድሞ በዘበኝነት ባንኩን ያገለግል የነበረው ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማይፀብሪ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና የወንድ ዘበኛ ጨምሮ 6 የባንኩ ሰራተኞችን ሲገድል አንዲት የባንኩ ሴት ዘበኛም ማቁሰሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል::

እንደ ዜናው ከሆነ ይኸው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቅርንጫፍ ለተወሰኑ ሰዓታት ተቆጣጥሮት ቆይቶ በመጨረሻም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቆሟል:: ሰዎቹን የገደለው ይኸው የቀድሞ የባንክ ሠራተኛ ለምን ከሥራው እንደተባረረ የደረሰን መረጃ የለም::

The post ግለሰቡ በትግራይ ክልል 6 ሰዎችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ሁለንተናዊ ቀውስ በመወያየት ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል የሚቋቋምበትን ሂደት ለመምከር ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል

$
0
0

shengoENTCየኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት ጋር በተደረጉ ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶችና ስምምነቶች፡ ህዝባችን ላለፉት 24 ዓመታት ያለነፃነት በህወሓት የግፍ አገዛዝ ሥር ፍዳውን የሚያይበት ዋና ምክንያት፤ ሕዝብን መሠረት ያደረገና ብሄራዊ ጥቅምን ያስቀደመ፤ በአንድ ማዕከል የሚንቀሳቀስ ሁሉን አቀፍ የአማራጭ አካል በማቋቋም ሥርዓቱን ለማስወገድ አስፈላጊውን ትግል የማድረግ ቁርጠኝነቱ በተቃዋሚው ጎራ ያለመኖሩ ዋና ጉዳይ መሆኑን የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰናል። ይህን አዙሪት በመስበርና ሁኔታዎችን በጋራ በማመቻቸት የአማራጭ ኃይሉ በአስቸኳይ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳችንንም በተከታታይ ባወጣናቸው የሁለትዮሽ መግለጫዎች ይፋ መሆናቸው የሚታወስ ነው።

ሥርዓቱ ባሳለፍነው ሳምንት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የታወቀውን የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ ድራማ በማካሄድ፤ ሕዝብን ተስፋ በማስቆረጥና ግፉን አሜን ብሎ በመቀበል፤ ቀደም ሲል ሲያደረግ የነበረውን ሀገር የማፈራረስ ሂደትና የሕዝብን ስቃይ የሚያበዛ አገር በቀል የአፓርታይድ አገዛዝ ለቀጣይ አምስት አመታት ለማስቀጠል የሚያስችለውን ህጋዊ ሽፋን በማመቻቸት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ አገር አድን የምክክር ጉባዔ በማድረግ በሕዝብ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል በማቋቋም ትግሉን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል ወቅታዊና አስቸኳይ ነው።

ከላይ በመግቢያው ላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶች፤ ከተለያዩ አክቲቪስቶችና ታወቂ ግለሰቦች ጋር በመሆን ከጁላይ 2-3 የምክከር ጉባዔ በጋራ ያዘጋጃሉ። የጉባዔውን ውጤት ለማሳወቅ ሕዝባዊ ስብሰባም ይዘጋጃል። የመሰብሰቢያ ቦታ፤ ዝርዝር ፕሮግራሞችና ተያያዥ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እንደምናሳወቅ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን።

ስለዚህ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ መኅበራት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆናችሁ ወጣቶች፤ በሀገራችን ነፃነት ሠላም እኩልነትና ፍትኅ ይሰፍን ዘንድ የምትተጉ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አዘጋጆች፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣ ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት አባቶች፤ እንዲሁም ለሀገር ደህንነት ተቆርቋሪ የሆናችሁ ዜጐች በሙሉ፤ የሚገነባው የተባበረ አማራጭ ኃይል ባለቤት እንደመሆናችሁ መጠን የሂደቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ በመሆን፤ በሀገራችን ነፃነት እውን እንዲሆን በሚደረገው ወሳኝ ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ታበረክቱ ዘንድ፤ እንዲሁም በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ አደራ እያልን በአክብሮት ሀገራዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

 

ይህ አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ እንዲገታ በጋራ እንቁም!

የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (SHENGO)

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት (UEM-PMSG)

የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)

 

ግንቦት 22፤ 2007 (May 30, 2015)

The post በሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ሁለንተናዊ ቀውስ በመወያየት ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል የሚቋቋምበትን ሂደት ለመምከር ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአፍሪካ ልማት ባንክ የተወዳደሩት አቶ ሱፍያን አህመድ ሳይመረጡ ቀሩ

$
0
0

sofian_ahmedየአፍሪካን ልማት ባንክን በፕሬዚዳንትነት ለመምራት ዕጩ ሆነው የቀረቡት የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፍያን አህመድ ሳይመረጡ ቀሩ፡፡

ናይጄሪያዊ የግብርናና የገጠር ልማት ሚኒስትር የ55 ዓመቱ ኦኪንውሚ ኦዴሲና የባንኩ ፕሬዚዳንት አድርጎ የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ግንቦት 20 ቀን 2007 ዓ.ም. መርጧቸዋል፡፡

ባንኩን ላለፉት አሥር ዓመታት ሲያስተዳድሩት የቆዩትን ሩዋንዳዊውን ዶናልድ ካቤሩካን ለመተካት አቶ ሱፍያንን ጨምሮ ስምንት ዕጩዎች ቀርበው የነበረ ቢሆንም፣ በምርጫ ሥነ ሥርዓቱ አቶ ሱፍያን በሁለተኛ ዙር ከውድድር ውጪ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

አቶ ሱፍያን ቀደም ብሎ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ሆነው ባስመዘገቡት ስኬት የማሸነፍ ዕድላቸው ከፍተኛ እንደሚሆን ተጠብቆ ነበር፡፡ አቶ ሱፍያን ከ20 ዓመታት በላይ በመሩት ሚኒስቴር ካከናወኗቸው ዓበይት ተግባራት መካከል፣ በአገሪቱ ሲከሰት የነበረውን ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ወደ ነጠላ አኃዝ በማውረድ ረገድ የተጫወቱት ሚና ይነገርላቸዋል፡፡ በአገሪቱ አዲስና የቅርብ ክስተት ከሆኑት ውስጥ፣ አገሪቷ በዓለም ቦንድ ገበያ ውስጥ ተሳታፊ መሆኗም ከሚጠቀሱላቸው ተግባራት መካከል ይካተታል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ አቶ ሱፍያን የባንኩ ሁለተኛ የሥራ ቋንቋ የሆነውን ፈረንሳይኛ ቋንቋ መናገር የማይችሉ በመሆናቸው ከፍተኛ ፈተና ሊገጥማቸው እንደሚችል የገመቱም ነበሩ፡፡ በተለይ አንዳንድ የመስኩ ባለሙያዎች የፕሬዚዳንትነቱን ውድድር ለምዕራብ አፍሪካ አገሮች ተወካዮች የተሻለ ቅድመ ግምትን ሰጥተውም ነበር፡፡

በስምንተኛው የባንኩ ጉባዔ ላይ ይፋ በሆነው የምርጫ ሥነ ሥርዓት ላይ አሸናፊ በመሆን የተመረጡት ናይጄሪያዊው ኦዴሲና ‹‹ዛሬ ታላቅ ኃላፊነትን ተቀብያለሁ፤›› በማለት ደስታቸውን ከሚጠብቃቸው ኃላፊነት ጋር በማያያዝ ገልጸዋል፡፡

በቅድመ ምርጫ ወቅት ስምንቱ ዕጩዎች ለውድድሩ የየራሳቸውን ስኬትና አሸናፊ ከሆኑ ለባንኩ ይበጃል ያሉዋቸው ዕቅዶች አቅርበው ነበር፡፡ በተለይ አቶ ሱፍያን ኢትዮጵያ ላለፉት አሥር ዓመታት አስመዝግባዋለች ያሉትን የኢኮኖሚ ዕድገትና የገንዘብ ግሽበትን በመቆጣጠር ልማትን እንዴት ማፋጠን ያስችላል ያሉትን ዕቅድ ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

ተሰናባቹ ፕሬዚዳንት ካቤሩካ በበኩላቸው በጉባዔው ላይ ባደረጉት ንግግር፣ ለተተኪያቸው የእንኳን ደስ ያለህ መልዕክት በማስተላለፍ መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል፡፡ ‹‹ለተተኪዬ መልካሙን ሁሉ እመኝለታሁ፡፡ አሥር ዓመት በፍጥነት መሄዱን አይቻለሁ፡፡ እጅግ ውስብስብና ውጥረት የተሞላበት ሥራ ነበር፡፡ ቢሆንም ግን አስደሳች የሥራ ወቅት ነበር፡፡ በእርግጥ ይኼን ሥራ ብዬ ከምጠራው ተልዕኮ ብለው ይሻለኛል፤›› ሲሉ ባንኩን ለአሥር ዓመት ያስተዳደሩት ዶናልድ ካቤሩካ በባንኩ ስላሳለፉት የሥራ ዘመን ተናግረዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post ለአፍሪካ ልማት ባንክ የተወዳደሩት አቶ ሱፍያን አህመድ ሳይመረጡ ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>