Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

መኢአድና ኢራፓ የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ

$
0
0

aeupየመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) እና የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) ግንቦት 16 ቀን 2007 ዓ.ም. የተካሄደውን ጠቅላላ ምርጫ ውጤት እንደማይቀበሉት፣ ግንቦት 25 ቀን 2007 ዓ.ም. በየጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አስታወቁ፡፡

መኢአድ ቴዎድሮስ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው ዋና ጽሕፈት ቤቱ ምርጫውን አስመልክቶ በፕሬዚዳንቱ አቶ አበባው መሐሪና በሌሎች የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች መግለጫ ሲሰጥ፣ በምርጫው ወቅት ገጠመኝ ያላቸውን ችግሮችና ጫናዎች ዘርዝሮ አቅርቧል፡፡

‹‹ባለፉት አራት ምርጫዎች በተከሰቱ ችግሮች ዙሪያ መፍትሔ አስቀምጦ ሙሉ በሙሉ ተሻሽሎ ይካሄዳል የሚል ዕምነት ቢኖረንም፣ ራሱን ሙሉ በሙሉ ወደ አምባገነንነት በቀየረው ገዥ ፓርቲ አፈና፣ ወከባ፣ እስራትና ግድያ የተነሳ ምርጫው ሳይሳካ ቀርቷል፤›› በማለት መኢአድ አስታውቋል፡፡

መኢአድ በምርጫው ዕለትና ከዚያ ቀደም ብሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ደረሰብኝ ያላቸውን ችግሮች ዘርዝሯል፡፡ ከአዲስ አበባ በስተቀር ኦሮሚያ፣ አማራና ደቡብ ክልሎችን ጨምሮ አባላቱ መታሰራቸውንና ታዛቢዎቹ ከምርጫ ጣቢያ መባረራቸውን ገልጿል፡፡

‹‹ምርጫው ነፃ፣ ፍትሐዊና፣ ሰላማዊ እንደሆነ ይገለጽ እንጂ በተግባር የታየው ግን የዚህ ተቃራኒ ነው፤›› ብሏል፡፡ ‹‹ሰው እየደበደቡ፣ እያሰሩ፣ እያንገላቱ፣ ከመኖሪያ እያፈናቀሉና የግድ ንብን ምረጡ ብለው ለማስፈራራታቸው ተጨባጭ መረጃ ባለበት ሁኔታ እንዴት ብሎ ነፃ፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ ምርጫ እንደተካሄደ የሚያውቀው አፋኙ ሥርዓት ብቻ ነው፤›› በማለት መኢአድ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

በምርጫው ምክንያት የታሰሩ የፓርቲ አባላትና ሌሎች የፖለቲካ እስረኞች በአስቸኳይ እንዲፈቱ ጠይቋል፡፡ ‹‹ምርጫው ታዋቂ የሆኑ ዓለም አቀፍ ታዛቢዎችና ከፖለቲካ ገለልተኛ የሆኑ የሲቪክ ማኅበራት ባልተገኙበት ኢሕአዴግ ባደራጃቸው የሲቪክ ማኅበራትና አባብሎ ወደ ታዛቢነት ያሰማራቸው የምርጫ ታዛቢዎች በተገኙበት የተካሄደ በመሆኑ፣ ይህንን የፖለቲካ ድራማ የተከናወነበት ምርጫ የማንቀበለው መሆኑን እናስታውቃለን፤›› በማለት መኢአድ መግለጫውን አጠቃሏል፡፡

የፓርቲውን የወደፊት አቅጣጫ በተመለከተ የፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ አበባው ሲገልጹም፣ ‹‹ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር መክረን ዘክረን ወደፊት የምናሳውቀው ይሆናል፤›› ብለዋል፡፡

በተመሳሳይም በዋና ጽሕፈት ቤቱ መግለጫ የሰጠው የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ)፣ የዘንድሮው ምርጫ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መካሄዱን ያስረዱልኛል ያላቸውን የተለያዩ ክስተቶች በማንሳት አስረድቷል፡፡ በፓርቲው ፕሬዚዳንት አቶ ተሻለ ሰብሮና በሌሎች ኃላፊዎች በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተገለጸው፣ ለምርጫ ቦርድ ፓርቲው ያቀረባቸው ዕጩዎች ቁጥራቸው ያለምንም አሳማኝ ምክንያት ተቀንሶ ፓርቲው በተወሰኑለት ዕጩዎች ብቻ እንዲወዳደር መደረጉ ከፍተኛ ጫና ፈጥሮበታል፡፡

እንዲሁም በአማራ፣ በደቡብና በኦሮሚያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በዕጩ ምዝገባ ወቅት፣ በቅስቀሳና በምርጫው ዕለት አጋጠሙኝ ያሏቸውን ችግሮች በባለ 6 ገጽ መግለጫው አስታውቋል፡፡ አብዛኛዎቹ ችግሮችም ከዕጩዎች አለመመዝገብ፣ ከአባላት መዋከብና መታሰር እንዲሁም የታዛቢዎች በሥፍራው ተገኝተው መታዘብ ከመከልከላቸው ጋር የሚያያዙ ናቸው፡፡

‹‹ጠጣር ግድፈቶች በተንፀባረቁበትና በተስተዋሉበት ሁኔታ የሕግ የበላይነት ተሟልቷል ተብሎ ከነጉድፉ መቀበል የፖለቲካ ቃር የሚያስይዝ ከመሆኑም በላይ፣ ከቀደምቶቹ ምርጫዎች 2002 እና 2005 (ማሟያና አካባቢያዊ) ባልተለየ መልኩ በአንድ ቅርጫት የተቀመጠ የቅድመ ምርጫ ሒደትና ውጤት በመሆኑ ፓርቲው አልተቀበለውም፤›› በማለት አስታውቋል፡፡

ቀጣይ አቅጣጫቸውን በተመለከተ ከሪፖርተር ለቀረበላቸውም ጥያቄ፣ ‹‹በትግል ደክመን ሳይሆን በመንግሥት ጫና ምክንያት መፈናፈን ባለመቻላችን ምንም እንኳን ዛሬ በዝረራ ብንወጣም፤ ዝረራው ግን ለነገው ቁጭት ጭሮብናል፤›› በማለት መልሰዋል፡፡

ፓርቲው ለወደፊቱ ሁለት አቅጣጫዎች ማዘጋጀቱን ገልጿል፡፡ አንደኛው ብሔራዊ መግባባትን ማስገኘት የሚል ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር አብሮ መሥራት የሚሉ ናቸው፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post መኢአድና ኢራፓ የምርጫውን ውጤት አንቀበልም አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስድስት ሠራተኞች በጥይት ተገደሉ

$
0
0

–ግድያውን ፈጽሟል የተባለው ተጠርጣሪ እጁን ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በመቀሌ ዲስትሪክት የማይፀብሪ ቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጅን ጨምሮ፣ ስድስት የባንኩ ሠራተኞች ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተገደሉ፡፡

national bank of ethiopiaግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. የተለመደ ሥራቸውን በማከናወን ላይ እያሉ፣ በባንኩ የጥበቃ ሠራተኛ በጥይት ተደብድበው የሞቱት የቅርንጫፉ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ወልዳይ ገብሩ፣ የባንኩ ኮንትሮለር አቶ አትንኩት ደምሴና የደንበኞች አገልግሎት ኦፊሰሮች የነበሩት ወ/ሮ ለምለም ግደይና አቶ አስማማው ገብረ ማርያም መሆናቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ኤፍሬም መኩሪያ አረጋግጠዋል፡፡ አቶ ንጉሤ ግርማና አቶ ጌትነት ባዩ የተባሉ በኮሜርሻል ኖሚኒስ አማካይነት የተቀጠሩ የባንኩ ሠራተኞችም መገደላቸውን አቶ ኤፍሬም አክለዋል፡፡

የባንኩ ሠራተኞችን በመግደል የተጠረጠረው የጥበቃ ሠራተኛ በፖሊስ ቁጥጥር ሥር ሆኖ፣ ግድያውን ሊፈጽም የቻለበት ምክንያት እየተጣራ መሆኑን የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ግድያውን የፈጸመው ግለሰብ የሥራ አፈጻጸሙን በሚመለከት ምክር፣ ተግሳጽና ማስጠንቀቂያ ከተሰጠው ከደቂቃዎች በኋላ መሆኑን መረዳታቸውን ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የጥበቃና የፅዳት ሠራተኞችን የመቅጠርና የመቆጣጠር ሥራን ለኮሜርሻል ኖሚኒስ መስጠቱን የጠቆሙት አቶ ኤፍሬም፣ የባንኩን ሠራተኞች በመግደል የተጠረጠረው ግለሰብም የተቀጠረው ከዚያው መሆኑን ጠቁመዋል፡፡ ተጠርጣሪው በሥራው ላይ ተገቢ ያልሆነ ባህሪያትን በማሳየቱ በባንኩ ኃላፊዎች ቢመከርም ሊስተካከል ባለመቻሉ፣ የቅርንጫፍ ዋና ሥራ አስኪያጁ መቐለ ለሚገኘው የኮሜርሻል ኖሚኒስ ጽሕፈት ቤት ደብዳቤ በመጻፍ፣ የጥበቃ ሠራተኛውን በሌላ እንዲተካላቸው ጠይቀው እንደነበር ገልጸዋል፡፡

የኮሜርሻል ኖሚኒስ ኃላፊዎች በሠራተኞቻቸው ላይ ቅሬታ ሲደርሳቸው በቦታው በመገኘትና ሠራተኞቹንና የተቋሙን ኃላፊዎች በማነጋገር፣ ሠራተኛው ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት ሥራውን እንዲቀጥል ወይም እንዲባረር እንደሚያደርጉ የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ተጠርጣሪውም በዕለቱ ተመክሮ፣ ተገስጾና ማስጠንቀቂያ ተሰጥቶት በዕለቱ ተረኛ ስለነበር መሣሪያውን ይዞ ወደ ሥራው መሰማራቱን ተናግረዋል፡፡ ከደቂቃዎች በኋላ ግን ሁለት የፍተሻ ሠራተኞችን አቁስሎ ሌሎቹን መግደሉን አስረድተዋል፡፡

የተገደሉት የባንኩ ሠራተኞች የቀብር ሥነ ሥርዓት መፈጸሙን ያስታወቁት አቶ ኤፍሬም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ አቶ ወልዳይ ገብሩ ቤተሰቦቻቸው በሚኖሩበት በዓደዋ ልዩ ስሙ ወርኢ ዳጋብር ቀብራቸው እንደተፈጸመም አክለዋል፡፡ ኮንትሮለሩ አቶ አትንኩት ደምሴ በትውልድ ሥፍራቸው ባህር ዳር የቀብራቸው ሥርዓት ተፈጽሟል፡፡ ወ/ሮ ለምለም ግደይና የኮሜርሻል ኖሚኒስ ሁለቱ ሠራተኞች አቶ ንጉሤና አቶ ጌትነት፣ በዚያው በማይፀብሪ ቀብራቸው ሲፈጸም፣ አቶ አስማማው ከማይፀብሪ በ100 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ዲማ በሚባለው አካባቢ ቀብራቸው ተፈጽሟል፡፡

ባንኩ በሠራተኞቹ ላይ በደረሰው ያልታሰበና ድንገተኛ አደጋ ጥልቅ ሐዘን እንደተሰማው የገለጹት አቶ ኤፍሬም፣ ሠራተኞቹ መገደላቸው ከተሰማበት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ቀብራቸው እስከተፈጸመበት ዕለት ድረስ፣ የመቀሌ ዲስትሪክት ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አሻግሬ አስመላሽ በሥፍራው ተገኝተው ያደረጉት አስተዋጽኦም ከፍተኛ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ የንግድ ባንክ ጠቅላላ የጥበቃዎች ሥራ አስኪያጅም እዚያው ሆነው ጉዳዩን እየተከታተሉ መሆኑን አቶ ኤፍሬም አስታውቀዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ስድስት ሠራተኞች በጥይት ተገደሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአለም ሀገራት ባሰፈኑት የህግና ፍትህ ስርአት ምዘና ኢትዮጵያ ከ102 የአለም ሀገራት 94ተኛ ደረጃ ተሰጥቷታል

$
0
0

Justiceዎርልድ ጀስቲስ ፕሮጀክት የተባለው በአለም ላይ ፍትህና የህግ የበላይነት እንዲረጋገጥ እሰራለሁ የሚል ተቋም የ 102 የአለም ሀገራትን የፍትህና ህግ ስርአት ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡ ከተለያዩ ሀገራት ከ 100 ሺህ የማያንሱ ህዝቦችን መጠይቅ በማድረግ ጭምር የተጠናቀረው ይህ የተቋሙ ሪፖርት በዚህ ረገድ የኢትዮጵያችንንም ደረጃ ይፋ አድርጓል፡፡

የፍትህና ህግ የበላይነት ጉዳይ ብዙ ጊዜ የህግ ሰዎች ስራ ብቻ ተደርጎ ሊታይ ይችላል ነገር ግን ሁላችንንም በየእለቱ የሚያጋጥም የእለት ተእለት ጉዳይ ነው ያለው ተቋሙ የአለም መንግስታት ለዜጎቻቸው ያላቸው ግልጽነትና ተጠያቂነት የሚለካውም በዚሁ መስፈርት እንደሆነ ነው ያስቀመጠው፡፡

ሪፖርቱ በዋናነት የአለም መንግስታት ለዜጎቻቸው የቱን ያክል ግልጽነትና ተጠያቂነት አስፍነዋል የሚለውን ሲያስቀምጥም በአራት መስፈርቶች እንደመዘናቸው ነው የገለጸው፡፡ መንግስታቱ በተጻፉ ህጎችና መረጃዎች ነው ወይ ህዝባቸውን የሚያስተዳድሩት የሚለው ቀዳሚው መስፈርት ሲሆን፣ የዜጎች መረጃ የማግኘት መብት፣ የሲቪክ ማህበራት ተሳትፎ፣ እንዲሁም ቅሬታና አቤቱታ አፈታት በሚሉ አራት መመዘኛዎች ሀገራቱ መገምገማቸው ታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት ከአጠቃላይ 102 ሀገራት ውስጥ ስዊድን፣ ኒውዚላንድና ኖርዌይ እጅግ ግልጽ የሆኑ የመንግስት ስርአት የሰፈነባቸው ተብለው የህግና ፍትህ ስርአታቸው ሲወደስ እንደ ማይናማር፣ ኡዝቤኪስታንና ዚምባብዌ ያሉ ሀገራት ደግሞ መንግስታቶቻቸው ዝግ በሆነና ፍትህና ህግ ባልሰፈነበት ሁኔታ ህዝባቸውን የሚያስተዳድሩ ተብለው በመጨረሻዎቹ እርከኖች ላይ ሰፍረዋል፡፡

የኢትዮጵያችንንም ደረጃ ያስቀመጠው ይህ ሪፖርት በአራቱም መስፈርቶች መልካም የሚባል ውጤት እንዳላገነች ነው ይፋ ያደረገው፡፡

በተጻፉ ህጎችና መንግስታዊ መረጃዎች 73ተኛ፣ በመረጃ ማግኘት መብት 79ኛ፣ በዜጎች ተሳትፎ 97ተኛ፣ እንዲሁም በቅሬታ አፈታት ስርአት 89ኛ ደረጃዎችን ያገኘችው ኢትዮጵያችን ይህ ደግሞ በዚህ ሪፖርት በአጠቃላይ ውጤት ከ 102 ሀገራት በ 94ኛ ደረጃ ላይ እንድትሰለፍ እንዳደረጋት ነው የተነገረው፡፡

The post የአለም ሀገራት ባሰፈኑት የህግና ፍትህ ስርአት ምዘና ኢትዮጵያ ከ102 የአለም ሀገራት 94ተኛ ደረጃ ተሰጥቷታል appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮዽያዊው በአሜሪካ 122 አመት ተፈረደበት

$
0
0

በአሜሪካን ሀገር በሚሊየን የሚቆጠሩ ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች ይኖራሉ! እነዚህ ስደተኞች ከጥቃቅን ስራዎች አንስቶ እስከ_ታላላቅ ካምፓኒዎች በወዛቸው ያገኙዋትን ዶላር አጠራቅመው አንድ ቀን ሀገሬ እገባለው ከሚል ተስፋ ጋር ሕይወትን ይገፋሉ::Ethiopians

ህልሙ የሞላለት ጥቂቱ ጠቅልሎ ሲመጣ አብዛኛው ግን በዥዋዥዌው የአሜሪካ ህይወት ባለበት ሰምጦ ይቀራል! ስደት የእድሜ ወፍጮ ነው! በአምስት አመት ውስጥ ሀገሬን አያታለው ያለ ዲያስፖራ ሳይታሰብ ስምንት የአሜሪካ ፕሬዝዳንቶች ምርጫ መታዘቡን ሲያሰላው ስደት ከወጣም ከሰላሳ አመት መዝለሉ ትዝ ይለዋል! ነገ ያሉት እቅድ ተራራ የመግፋት ያህል ይከብድና የተስፋ ሞተርም እየቀዘቀዘ ይመጣል! ይሄ ሁሉ “ምን ይዤ ልግባ?” ከሚል ይሉኝታ የሚፈጠር ሰውኛ ጭንቀት ነው! በእርግጥ ዲያስፖራዎች ያሳዝናሉ::

ለአንድ ራሳቸው የሚሆን ቅሪት ቢፈጥሩ እንኩዋን አናት_እያከከ የሚጠብቃቸው ነብሳት ብዙ ነውና ሀገር ቤትን እንደ_ናፍቆታቸው ሊመለሱበት ይፈሩታል! እናም “ወይ_ሀገሬ” ከሚል የትዝታ ዜማ ጋር የአሜሪካ ሰፊ ከርስ ውጦዋቸው ይቀራል! እንደዚህም ሆኖ ሀገራዊ ምስላቸው ሸጋ ገፅታ ይዞ ኖሮዋል! ሰሀንም አጥበው ነገን ለፈጣሪ ይተውታል እንጂ ገንዘብ ፍለጋ አጉል መንገድ አይሞክሩም! ባለፈው ማርች ወር ግን እውነት ይሄ ሰው የአበሻን ውሃ የጠጣ ነው? ያስባለ ጋንግስተር ኢትዮዽያዊ የአሜሪካ መነጋገሪያ ሆኖ ነበር! ኢትዮዽያ ውስጥ የተወለደው የ42 አመቱ “ወሰን_አሳየ” እ.ኤ.አ ከ2013 ኦክቶበር አንስቶ 12 ባንኮችን መዝረፉ ሳያንሰው በህግ ጥላ ውስጥ ከዋለ በዋሃላም ጀብዱ መስራቱን አላቆመም! በፖሊስ ታጅቦ ከሄደበት ሆስፒታል የፖሊሱን ሽጉጥ ነጥቆ በማምለጥ በሂሊኮፕተር ሳይቀር በተደረገበት ክትትል ተይዞ ዛሬ 122 አመት ተፈርዶበታል::

The post ኢትዮዽያዊው በአሜሪካ 122 አመት ተፈረደበት appeared first on Zehabesha Amharic.

  መውደቂያ ያጣ እንባ

$
0
0

ውሀ በጠማው በረሀ በደረቀ የምድር ሀሩር
የሠማይ ዝናብ ይመሥል የወንድሜ ደም ሲገበር
ኑሮ ለገፋው ወገኔ ሰይፍ ካፎቱ ሲመዘዝ
የሰው ልጅ ልክ እንደስሳ አንገቱ አንዲህ ሲገዘገዝ
ሀዘኑ ሆዴን ቢያምሠው ስቀት አንጀቴ ቢገባ
ቁስለቴ ሽቅብ አንስቼ የውስጤን ህመም ላሠማ
አንድባይ ገላገይ ሽቼ ወጣሁኝ ከአገሬ ማማ
ግን ጩኸቴ  እንደመናኛ እንኳንስ ሊሠጠው ስፍራ
እንዳጠፍ ወንጀለኛ ልባቸው ጥቂት ሳይራራ
ማልቀሻ ነሱኝ በአገሬ ሀዘኔም እንዳያባራ
ያብሡልኛል ያልኳቸው ለአይኖቼ ውሀ ግደባ
ወታደር ልከው አሠሩኝ ቁስሌ ልባቸው ሳይገባ
እንኳን ከፊቴ ሊታበስ መውደቂያ ያጣው የእኔ እንባ
ቁልቁል ደረቴን ሰንጥቆ ደም ከሞላው ልቤ ገባ ፡፡

ይርጋለም ዘለቀ

KONICA MINOLTA DIGITAL CAMERA

 

The post   መውደቂያ ያጣ እንባ appeared first on Zehabesha Amharic.

ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት- በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

$
0
0

11257577_718473044945023_8620623119912413467_nሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በመንግስት ተጠርቶ ከነበረው ሰልፍ ጋር በተያያዘ በምርጫ ማግስት ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ለእስር የተዳረገችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት፡፡
ዛሬ ግንቦት 26/2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቂርቆስ ምድብ ችሎት የቀረበችው ወ/ሮ ንግስት፣ በፌደራል አቃቤ ህግ ከሳሽነት በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 32/1/ሀ እና 490/3/ የተመለከተውን በመተላለፍ የሚል ክስ ቀርቦባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም በነበረው ሰልፍ ላይ ‹‹ወያኔ ሌባ፣ መንግስት አሸባሪ፣ ታርዷል ወገኔ፣ ይለያል ዘንድሮ የወያኔ ኑሮ፣ ወያኔ አሳረደን፣ ናና መንግስቱ ናና፣ ወያኔ አሸባሪ…በማለት እጅን አጣምሮ ወደላይ በማድረግ ታስረናል›› በማለት ሰላማዊ ሰልፉ እንዲታወክ አድርጋለች በሚል ተከሳለች፡፡ በተጨማሪም በሚያዝያ 13/2007 ዓ.ም ቂርቆስ አካባቢ ‹‹ስብሰባን ወይም ጉባኤን›› በማወክ እንደተከሰሰች የክስ ቻርጁ ያሳያል፡፡
ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት በቀረበችበት ወቅት ፍርድ ቤቱ ለግንቦት 28/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ‹‹በምስክሮች ላይ ማስፈራራት እየተፈጸመ ስለሆነና ምርመራየንም ስለጨረስኩ›› በሚል ፖሊስ ዛሬ ቤተሰቦቿ እንኳ ሳይሰሙ ወ/ሮ ንግስትን ፍርድ ቤት አቅርቦ ክስ መስርቶባታል፡፡
ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው በቀጣይ አርብ ግንቦት 28/2007 ዓ.ም ለሶስተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ትቀርባለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

The post ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ክስ ተመሰረተባት- በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር appeared first on Zehabesha Amharic.

በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል * በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) 2ኛ ሳምንቱን የያዘውና በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር ባሉ መንደሮች አካባቢ በተነሳ ጦርነት ትናንት ረቡዕ እና ዛሬ ሐሙስ በተደረጉ ውጊያዎች የ19 ሰዎች ሕይወት ማለፉን እና ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ ዜጎች ቁስለኛ መሆናቸውን ዘ-ሐበሻ ከስፍራው ያገኘችው መረጃ አመለከተ::

boarder

በድንበሩ አካባቢ ትናንትና ዛሬ በ3 መንደሮች አካባቢ 2 ውጊያዎች መደረጋቸውን ያስታወቁት የአካባቢው የዜና ምንጮች በዚህ ውጊያ ሳቢያ የአካባቢው ነዋሪዎች ንብረታቸውን እና ቤታቸውን ጥለው ለመሰደድ በቅተዋል::

በሶማሊያና በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ ባሉት መንደሮች አካባቢ የተነሳው ጦርነት እስካሁን ግልጽ አለመሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮች በደፈናው የዘር ግጭት ነው ሲሉት ይገልጹታል:: በዚህ ጦርነት ዙሪያ የሶማሊያም ሆነ የኢትዮጵያ መንግስት ጉዳዩን ለማርገብ ምንም አይነት ንግግር አለማድረጋቸውም ተዘግቧል::

በኢትዮጵያና በሶማሊያ ድንበር ባሉ መንደሮች ላለፉት ዓመታት በዘር ግጭት የተለያዩ ጦርነቶች ሲደረጉ የቆዩ መሆናቸውን የሚጠቁሙት የዜና ምንጮቹ የኢትዮጵያም ሆነ የሱማሊያ መንግስታት ዜጎቻቸው እየተላለቁባቸው ጉዳዩን በዝምታ ማለፋቸው በጣም አሳፋሪ ነው ብለውታል::በተለይም የኢትዮጵያ መንግስት ጦሩን ወደዚያ ከማስጠጋት ውጪ ጉዳዩን ለማረጋጋት ያደረገው ይኸ ነው የሚባል ሥራ አለመስራቱ እየተተቸ ነው::

The post በኢትዮጵያና ሱማሊያ ድንበር ውጥረቱ አይሏል * በትናንትና ዛሬ ጠዋት ጦርነት 19 ሰዎች ሞቱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ

$
0
0

semayawi 2

semayawi
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ ምርጫው ልምድ ያላቸው የውጭ ታዛቢዎች ያልተገኙበትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ‹‹ነፃና ፍትሓዊ›› ነበር ለማለት ያልደፈረበት፣ ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጭበረበረ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በደብዳቤው አስታውሷል፡፡

ምርጫው ገዥው ፓርቲ 100% አሸነፍኩ ያለበት፣ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫናና እስር ከዚህም ሲያልፍ ለሞት የተዳረጉበት ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን ገልጾአል፡፡ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና ፖለቲከኞችን ለማጥቃት በወጣው የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካ እስረኞች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ መሆኗን ፓርቲው አስታውሳል፡፡

የጉባኤው አባላት ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው የንግድ ግንኙነትና በሚያበረክቱት እርዳታ ምክንያት በሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም የኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ የሚመራው መንግስት ለሰብአዊ መብት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየገደበና ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

ጉባኤው ሰብአዊ መብትና ዴሞክራዊያዊ መብትን ለልማትና የኢኮኖሚ ግንኙነት በቅድመ ሁኔታነት በመውሰድ ጫና ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባታን እንደሚጎዳም ሰማያዊ ፓርቲ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ጉባኤው የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ማሰርና እንቅስቃሴያቸውን ከመገደብ እንዲቆጠብ እና አፋኝ አዋጆች ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡

The post ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰበር ዜና መርካቶ ሸራ ተራ እየተቃጠለ ነው

$
0
0

ለዘሃበሻ የደረሰው ሰበር መረጃ እንዳመለከተው መርካቶ የሚገኘው ሸራ ተራ እየተቃጠለ ይገኛል። የእሳቱ መነሻ ባይታወቅም እሳቱን ለመቆጣጠር እንዳልተቻለ ይህ ዜና እስከ ተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ የደረሰን መረጃ ኣመልክቱአል።
shera tera 2

shera tera 4

shera tera merkato

shera tera

merkato addis

merekato 2

markato 43

The post ሰበር ዜና መርካቶ ሸራ ተራ እየተቃጠለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢሳት ዜና ሰበር ዜና –በደቡብ ክልል እና ጋምቤላ አዋሳኝ ቴፒ ከተማ ታጣቂዎች ጥቃት ፈፀሙ 

$
0
0

news ”በደቡብ ክልል እና ጋምቤላ አዋሳኝ ኢትዮጵያ ቴፒ ለፍትህ እና ለነፃነት የቆምንነን ያሉ ታጣቂዎች ዛሬ ማለዳ ላይ ጥቃት ፈፀሙ”
ኢሳት ቴሌቭዥን የዛሬ ሰበር ዜና።በሰበር ዜናው ውስጥ የሚከተሉት ነጥቦች ተነስተዋል –
– ታጣቂዎቹ ከአንድ መቶ እስከ አንድ መቶ ሃምሳ ናቸው፣
– ትናንት ጥቃት እንደሚፈፅሙ ቀድመው አሳውቀው ነበር፣
– በሶስት ክፍል ውስጥ ያሉ ከአንድ መቶ በላይ እስረኞችን እና በከተማው የሚገኝ
የፖሊስ ጣቢያ ሰነድ እና በርካታ የጦር መሳርያ ይዘው ሄደዋል።
– የቴፒ ከተማ ነዋሪ በታጣቂዎቹ ጥቃት ደስታውን ሲገልፅ ታይቷል።
– ታጣቂዎቹ ከፍተኛ የህዝብ ድጋፍ አላቸው።”

The post ኢሳት ዜና ሰበር ዜና – በደቡብ ክልል እና ጋምቤላ አዋሳኝ ቴፒ ከተማ ታጣቂዎች ጥቃት ፈፀሙ  appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ ምርጫው ልምድ ያላቸው የውጭ ታዛቢዎች ያልተገኙበትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ‹‹ነፃና ፍትሓዊ›› ነበር ለማለት ያልደፈረበት፣ ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጭበረበረ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በደብዳቤው አስታውሷል፡፡

ምርጫው ገዥው ፓርቲ 100% አሸነፍኩ ያለበት፣ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫናና እስር ከዚህም ሲያልፍ ለሞት የተዳረጉበት ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን ገልጾአል፡፡ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና ፖለቲከኞችን ለማጥቃት በወጣው የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካ እስረኞች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ መሆኗን ፓርቲው አስታውሳል፡፡

የጉባኤው አባላት ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው የንግድ ግንኙነትና በሚያበረክቱት እርዳታ ምክንያት በሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም የኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ የሚመራው መንግስት ለሰብአዊ መብት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየገደበና ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

ጉባኤው ሰብአዊ መብትና ዴሞክራዊያዊ መብትን ለልማትና የኢኮኖሚ ግንኙነት በቅድመ ሁኔታነት በመውሰድ ጫና ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባታን እንደሚጎዳም ሰማያዊ ፓርቲ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ጉባኤው የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ማሰርና እንቅስቃሴያቸውን ከመገደብ እንዲቆጠብ እና አፋኝ አዋጆች ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡

ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ሰማያዊ ፓርቲ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ነገ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በሚካሄደው የG-7 ስብሰባ መጋበዛቸውን ተከትሎ የወቅቱ የጉባኤው መሪ ለሆኑት የጀርመን ቻንስለር ለአንጌላ ሜርክል በፃፈው ደብዳቤ መሪዎቹ በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ በስብሰባው ላይ መጋበዛቸው ቅር እንዳሰኘው የገለፀው ፓርቲው 24 አመት በስልጣን ላይ የቆየው የጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ፓርቲ አፋኝ ለመሆኑ የ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫን በምሳሌነት ጠቅሷል፡፡ ምርጫው ልምድ ያላቸው የውጭ ታዛቢዎች ያልተገኙበትና የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም ‹‹ነፃና ፍትሓዊ›› ነበር ለማለት ያልደፈረበት፣ ሰማያዊን ጨምሮ ሌሎች ተቃዋሚ ፓርቲዎች የተጭበረበረ መሆኑን ማረጋገጣቸውን በደብዳቤው አስታውሷል፡፡

ምርጫው ገዥው ፓርቲ 100% አሸነፍኩ ያለበት፣ ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ ጫናና እስር ከዚህም ሲያልፍ ለሞት የተዳረጉበት ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ገለልተኛ ሲቪክ ማህበራት እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን ገልጾአል፡፡ ጋዜጠኞችን፣ ጦማሪያንን፣ የሀይማኖት አባቶችንና ፖለቲከኞችን ለማጥቃት በወጣው የፀረ ሽብር ህግ ምክንያት ኢትዮጵያ በፖለቲካ እስረኞች ብዛት ከአፍሪካ ቀዳሚዋ መሆኗን ፓርቲው አስታውሳል፡፡

የጉባኤው አባላት ከኢትዮጵያ ጋር ባላቸው የንግድ ግንኙነትና በሚያበረክቱት እርዳታ ምክንያት በሰብአዊ መብት፣ ዴሞክራሲና ልማት ላይ አዎንታዊ አስተዋጽኦ ማድረግ የሚችሉ ቢሆንም የኃይለማርያም ደሳለኝ ፓርቲ የሚመራው መንግስት ለሰብአዊ መብት፣ ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት እየገደበና ተቃዋሚዎች ላይ ከፍተኛ በደል እያደረሰ ይገኛል ብሏል፡፡

ጉባኤው ሰብአዊ መብትና ዴሞክራዊያዊ መብትን ለልማትና የኢኮኖሚ ግንኙነት በቅድመ ሁኔታነት በመውሰድ ጫና ማድረግ ካልቻለ የኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ግንባታን እንደሚጎዳም ሰማያዊ ፓርቲ አሳስቧል፡፡ በመሆኑም ጉባኤው የፖለቲካ እስረኞች ያለ ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ፣ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን ማሰርና እንቅስቃሴያቸውን ከመገደብ እንዲቆጠብ እና አፋኝ አዋጆች ላይ ማሻሻያዎች እንዲደረግባቸው በኢህአዴግ መንግስት ላይ ጫና እንዲያደርግና ተገቢውን እርምጃ እንዲወስድ አሳስቧል፡፡

 

11407238_719529988172662_9201368755983019763_n

11416333_719529974839330_3281869570455127392_o

The post ሰማያዊ የG-7 መሪዎች በኢህአዴግ ላይ ጫና እንዲያደርጉ አሳሰበ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!”–ድምጻችን ይሰማ!

$
0
0

የተፈረደው እኛው ላይ ነው!
ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!
አርብ ግንቦት 28/2007

ሶስት መሰረታዊ የመብት ጥያቄዎችን አንስተን ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› ማለት ከጀመርን 175 ሳምንታት አለፉ። እነዚህ ጥያቄዎች እንኳንስ ግድያ፣ እስራት፣ ማሰቃየት፣ ማንገላታት፣ ስደት፣ ሃብት ዘረፋ፣ ወሲባዊ ትንኮሳ፣ ሃይማኖትን ማራከስ፣ የእምነት እሴቶቻችንን ማብጠልጠል፣ በአደባባይ ስምን ማጥፋት አና ሌሎች በደሎችንም ሊያስከትሉ ይቅርና መጀመሪያውኑ ሳይጠየቁ መከበር የነበረባቸው ናቸው። ሆኖም ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደ ቀደምት አባቶቹ ዛሬም ቢሆን በሃገሩ ላይ እንደ ዜጋ ሳይቆጠር እጅግ ያነሱና አሻሚ ያልሆኑ፣ቢከበሩ ማንንም የማይጎዱ ጥያቄዎችን በማንሳቱ ብቻ ላለፉት 3 ዓመታት በጅምላ በተለያየ ደረጃ የመከራ ገፈት እየቀመሰ ይገኛል።
Muslim in ethiopia
በመንግስታት ደረጃ እንኳን ሊታሰቡና ሊጠበቁ ያልቻሉ የስነ-ስርአት መርሃ-ግብሮችን ለሃገር ሰላምና ለህብረተሰብ ደህንነት ባሰበና ባከበረ መልኩ ስንተገብር ቆይተናል። ይህንን ሁሉ ስናደርግ አማራጭ በማጣት፣ አልያም የመንግስትን እርምጃ በመፍራት ሳይሆን ለአገራችን ካለን ጥልቅ ፍቅርና
የሰላምን ዋጋ ካለፈው ታሪካችን እጥብቀን በመረዳታችን ብቻ ነበር፡፡

ባለፉት ቀናት በወንድም ዓሊ መኪ እና በወንድም ዓብዱልዓዚዝ ጀማል ላይ የተላለፈው የፖለቲካ ውሳኔ በመላው ሙስሊም ህብረተሰብ ላይ የተላለፈ ቅጣት ነው። ሰደቃ ማዘጋጀት እና ‹‹ንጹሃን እስረኖች ይፈቱ›› ማለት 15 ዓመታት የሚያስፈርድ ወንጀል ከሆነ በእርግጥም የተፈረደው በእኛው ላይ ነው… በፍትህ ፈላጊዎች ሁሉ ላይ! የ‹‹ድምጻችን ይሰማ!›› እንቅስቃሴ የግለሰብ እና የቡድን ጥያቄ ሳይሆን የመላው ሙስሊም ህብረተሰብ እና የፍትህ ወዳዶች በሙሉ ጥያቄ ነው። በሃሰት ክስ ወንድሞቻችን ላይ የተፈረደው የፖለቲካ ፍርድ ሙስሊሙ ህብረተሰብ ላይ የተወረወረ የንቀት መልእክት ነው። ሕዝብን መናቅ እና ህዝብን ማስቆጣት ደግሞ መጨረሻው ምን እንደሆነ ከታሪክም ባለፈ መንግስት የተቀመጠበትን የስልጣን ወንበር ማየት ብቻውን በቂ ምስክርነት ነው።በመሆኑም በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ አገራት የሚኖሩ ሰላም ወዳዶችና ፍትህ ፈላጊዎች በሙሉ ይህንን ህዝብን የመናቅ ተግባር አጥብቀው ሊያወግዙት እና ሊታገሉት ይገባል። ሁላችንም ‹‹የተፈረደው እኛው ላይ ነው! የተናቅነው እኛው ነን! ሕዝብን መናቅ ደግሞ ዋጋን ያስከፍላል!›› ልንል ይገባል!

የፖለቲካ ፍርድ አንቀበልም!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post “ሙስሊሙን ህብረተሰብ መናቅ ከባድ ዋጋን ያስከፍላል!” – ድምጻችን ይሰማ! appeared first on Zehabesha Amharic.

በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዋና ዋና ዝግጅቶች ይፋ ሆኑ

$
0
0

ከፊታችን ጁን 28 እስከ ጁላይ 4 ድረስ በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ዝግጅት ላይ ከሚቀርቡ ዋና ዋና ዝግጅቶች መካከል የተወሰኑትን ፌደሬሽኑ ለዘ-ሐበሻ ልኳል:: ወደዚያው ጉዞ ለሚያደርጉ ወገኖች ይጠቅማልና በራሪ ወረቀቶቹን ተመልከቱ::
Opening Day

Beharawi Theater

Teddy and Gossaye

Golf Final

Ethiopian Day Final flyer

Jacky Final

The post በዋሽንግተን ዲሲ የሚደረገው 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል ዋና ዋና ዝግጅቶች ይፋ ሆኑ appeared first on Zehabesha Amharic.

በደራሸ ወረዳ 15 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ (ዝርዝራቸውን ይዘናል)

$
0
0

Zehabesha News
(ነገረ ኢትዮጵያ) በደቡብ ክልል ደራሸ ወረዳ አርጎባጠና ቀበሌ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት አቶ ከተማ ካሳን ጨምሮ በርካታ ወጣቶች መታሰራቸውን የወረዳው አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን እያደነ እያሰረ መሆኑን የገለጹት አስተባባሪዎቹ ከ27 በላይ ወጣቶች የደረሱበት እንዳልታወቀ ገልጸዋል፡፡ ዛሬ ግንቦት 29/2007 ዓ.ም በደራሸ ወረዳ አርጎባጠና ቀበሌ በፖሊስ ተይዘው በደራሸ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከሚገኙት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሚከተሉት ናቸው፡፡
1. አቶ ከተማ ካሳ (ዕጩ ተወዳዳሪ)
2. ወጣት ሙሉጌታ ሙንጣዮ
3. ወጣት ይበልጣል አቡሽ
4. ወጣት ኢሳሞ ሽብሩ
5. ወጣት ጨንቄ ሻንቆ
6. ተማሪ ገብሬ ኩሴ
7. ተማሪ ደረቡ ካሳ
8. ወጣት ደግነት ደነቀ
9. ወጣት የኋላሸት
10. ወጣት ሙሉጌታ ጢኖ
11. ወጣት አርቢኖ ታየ
12. ወጣት ታሪካ ጭንጌ
13. ወጣት ጥጋቢ ጭልጌ
14. አቶ ጭንቃዮ ካሳሁን
15. አቶ ሙሉቃ በርበሶ ናቸው
በደራሸ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከሚገኙት በተጨማሪ በሌሎች የወረዳው አካባቢዎችም በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት እየታደኑ እየታሰሩ እንደሚገኙ አስተባባሪዎቹ ገልጸዋል፡፡

The post በደራሸ ወረዳ 15 የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ታሰሩ (ዝርዝራቸውን ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

አባቱን እንደናፈቀ ሳያገኘው ያለፈው ሰማዕት (ዳንኤል ሐዱሽ) “በዐይኔ አይቼ በጆሮዬም ሰምቼ ከሥፍራው በመገኘት ጻፍኩላችሁ”

$
0
0

ዘመድኩን በቀለ

ቅድስቲቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች ከተማ ፣ ጥንታዊቷ የታላቋ ሐገር ኢትዮጵያችን የቀድሞ ዘመን ዋና መናገሻ ከተማ ፣ የታቦተ ጽዮን የዘለዓለም ማረፊያ ፣ የስልጣኔአችን ምንጭ ፣ የሥነ ዜማ ፣ የሥነ ፊደል ፣ የሥነ ጥበብ ፣ የሥነ ሕንፃ መገኛ ፣ የሊቃውንተ ቤተክርስቲያን መፍለቂያ ዋነኛዋ ምንጭ በዘመነ ኦሪትም ኋላም በዘመነ ሐዲስ የአምልኮተ እግዚአብሔር መፈጸሚያ ማዕከል ወደ ሆነችው አክሱም ጽዮን ከተማ በትናንትናው ዕለት በሰላም መግባቴን ፣ በዚያም እንደደረስኩ እኔ ባልጠበኩት ሆኔታ የከተማዋ ከንቲባ አቶ ካህሳይ እና አማካሪያቸው አቶ ሐጎስ አውሮፕላን ጣቢያ ድረስ በመምጣት ተቀብለውኝ ፣ የማረፊያ ሆቴልንና የምግብ አገልግሎትም ጭምር እንዲሰጠኝ አድርገውልኝ እንደነበር ነግሬያችሁ ነበር ለዛሬ ቀጠሮ ይዘን የተለያየነው ።
የዛሬ ውሎዬን ደግሞ እነሆ ብያለሁ ።

hadush

hadush daniel
እንደ እኔ ሐሳብ ዛሬ ከአክሱም ከተማ 60 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ወደ ምትገኘው ኢንቲጮ ከተማ በትራንስፖርት በመሄድ ከዚያም ጾረና ግንባር ወደሚገኘው ሰማዕት ቤትም ከዚያው ከኢንቲጮ ከተማ ትራንስፖርት ይዤ ለመሄድ ነበር እቅዴ ። እኔ እንዳሰብኩት መች ሆነና ብላችሁ እኔ ያላሰብኩት ሆነ እንጂ ።

የአክሱሙ ሲደንቀኝ የኢንቲጮው ከንቲባ አቶ ሰሎሞን በጠዋት መኪና እንደሚልኩልኝ ነግረውኝ ስለነበር በቃላቸው መሰረት ሾፌር ከነ መኪናው በጠዋት ልከውልኝ ረጅም ቀናት ይፈጅብኝ የነበረውን ጉዞዬን በአንድ ቀን እንዳጠናቅቅ ረድተውኛልና እባካችሁ ጓደኞቼ በሰማዕታቱ ስም አመስግኑልኝ ።

አሁን ሹፌሬ ክብሮም ቶዮታ ፒካፕ መኪናውን ይዞ ከአክሱም ወደ ምስራቅ አቅጣጫ በሚወስደው መንገድ ወደ ኢንቲጮ ከተማ ይዞኝ እየተጓዘ ነው ። በመንገዳችን ላይም ኢትዮጵያ ሃገራችን ነጻ ሆና እንድትኖር እነሱ አጥንታቸውን ከስክሰው ደማቸውን አፍስሰው የህይወት ዋጋ ከፍለው ነፃነት አግኝተን እንድንኖር ያደረጉበትን የአድዋን የጦርነት ሥፍራና እኒያን ሰማይ ጠቀስ የአደዋ ተራሮች እያየሁ ሥለ ቀደሙት ሰማዕታት እያሰብኩ በእኔ ዘመን ደግሞ አንገታቸውን ከነ ማዕተባቸው በመስጠት ለኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ እምነታቸው ያላቸውን ታማኝነት ወደገለፁት ብርቅዬ የዘመኑ ሰማዕታት ወንድሞቻችን ወላጆች ቤት ጉዞዬን ቀጥያለሁ ።

በኢንቲጮ ከተማ መግቢያ ላይ ቆመው ይጠብቁኝ የነበሩትን የከቲማዋን ከንቲባ ክቡር አቶ ሰሎሞንን በመያዝ ወደ ሰማዕቱ ዳንኤል ሐዱሽ ቤት አመራን ።
በቤቷ ውስጥ ቀድሞ እኔ እንደምመጣ ታላቅ ወንድሙ ያውቅ ነበርና ጥቂት እንግዶችም ተገኝተው ነበር ። የእመቤታችን ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪ ፣ የአቡነ አረጋዊ ቤተክርስቲያን አስተዳዳሪና የወረዳዋ ሰባኬ ወንጌልም በቦታው ነበሩ ።

የሰማዕቱ እናት ወሮ ዛፉ ገብረየሱስ ሐጎስም በሚያሳዝን ሁኔታ ከሁለት እናቶች መሐል ኩርምት ብለው ተቀምጠዋል ። ጥቂት አረፍ እንዳልን እናት ማልቀስ በመጀመራቸው ታላቅ ልጃቸው አቶ ጌታቸውም ፣ እንግዶቹም መገሰፅ መጀመራቸው እኔ ጥቂት ለመናገር በር ስለከፈተልኝ የሰማዕትነትን ጥቅም ፣ ልጃቸው ከቀደሙት ሰማዕታት ከነ ቅዱስ እስጢፋኖስ ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስና ፣ ቅዱስ ቂርቆስ ጋር ያለውን ክብር በመጠኑ በመግለጽ ከእንግዲህ ማልቀስስ ለእኛ ነው እንጂ ፣ በምን እንደምንሞት ለማናውቀው ምስኪኖች ፤ በማለት ጥቂት ካጽናናሁ በኋላ ስለ ሰማዕቱ ዳንኤል ሐዱሽ እንዲነግሩኝ አግባባሁዋቸው ። እናት አማርኛ መስማት እንጂ ብዙም መናገር ባለመቻላቸው ልጃቸው ጌታቸው ሐዱሽ ስለ ሰማዕቱ ዳንኤል የነገረኝን እነሆ እናንተም ስሙት ብዬ በእንዲህ አይነት መልኩ አቅርቤላችኋለሁ እና ተከታተሉት ።

ጥቅምት 7 1982 ዓም ከምሽቱ ሦስት ሰአት ሲሆን የዛሬው ሰማዕት ዳንኤል ሐዱሽ አስመራ ከተማ እዳጋ አርቢ በተባለ ስፍራ ነው የተወለደው ። በ40ኛው ቀኑ ህዳር 12 ቀን በቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ስርዓት መሠረት እዚያው አስመራ ከተማ እንዳ ገብርኤል ቤተክርስቲያን ውስጥ ስርዓተ ጥምቀትን በመፈጸም የክርስትና ስሙም ተስፋ ሚካኤል ተባለ ።

ይህ ኦርቶዶክሳዊ ህጻን ብዙም ሳይቆይ የመንግሥት ለወጥ በኤርትራ በመከሰቱ እንዳሊቁ በመባል ከሚታወቁ አባት ዘንድ የጀመረውን የቄስ ትምህርት በማቋረጥ በ1985 ዓም ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው ይውጡ ሲባል ከቤተሰቦቹ ጋር ወደ ኢንትጮ ተመለሰ ።

የዳንኤል አባት ግን እንዴት በእድሜዬ ሁሉ የለፋሁበትን ሃብትና ንብረት እንዲሁ ከሜዳ ላይ በትኜው እቀራለሁ በማለት ተመልሰው ብቻቸውን ወደ አስመራ ያቀናሉ ። በዚያም በንብረታቸው ላይ ይገባኛል የሚል አካል ተነስቶባቸው ስለነበር በአስመራ ፍርድቤት እንደዋዛ የጀመሩት ክርክር መቋጫ በማጣቱ ከአስመራ ሳይወጡ የኢትዮ— ኤርትራው ጦርነት በመጀመሩ ይባስ ብለው ከቤተሰባቸው ተቆራርጠው ቀሩ ።

ዳንኤል ግን ምንም አባቱ ከአጠገቡ ባይኖሩም ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ኛ ክፍል በዚሁ ባደገባት ኢንቲጮ በእናቱ አጋዥነት ተምሮ ባመጣው ከፍተኛ ነጥብ ወደ ጅማ ዩኒቨርስቲ በማምራት 4 ዓመት ሙሉ በትጋት ትምህርቱን በመከታተል በ2006 ዓም በኮምፒዩተር ሳይንስ ተመርቆ ትምህርቱን አጠናቅቋል ።

ዳንኤል ተመርቆ ሥራ ያለማግኘቱ ቢያስከፋውም እሱ ግን እንዲሁ ዝም ብሎም አልተቀመጠም ። መሆኒ ከተማ የምትገኘው እህቱ ዘንድም በመሄድ የእህቱ ባል እንዲያው ከፍ ወዳለ ሥራ እስክትሸጋገር ፎቶ ቤትም ቢሆን ልክፈትልህ ብሎትም እንደነበር ወንድሙ ጌታቸው ይናገራል ።

በመሃል ላይ ጆርጅ ከተባለ ስትሬት A ያመጣ ጎበዝ ተማሪ ጓደኛው ጋር ጠበቅ ያለ ጓደኝነት ከመመስረታቸውም በላይ መቐለ ላይ በማኅበር ተደራጅተው ሥራ ሊጀምሩ እንደሆነ እና ለዚህም እያንዳንዳቸው ከ10 ሺህ እስከ 12 ሺህ ብር እንደሚያስፈልጋቸው በመወሰኑ ለእርሱም ሠርቶ የሚከፍለው ብር እንዲያበድረው ታላቅ ወንድሙን ጌታቸውን ያግባባውና ያሳምነዋል ።

ለመጀመሪያ ጊዜ 2ሺህ ብር ይቀበለውና ወደ መቐለ ያመራል ። መቐለ እንደገባም ቀሪውን 10ሺ ብር ይልክለታል ። በቃ እፎይ ሥራ ጀመረ ብሎ ቤተሰቡም ተረጋግቶ ሳለ በመሃል ዳንኤል ሁመራ ነው ያለሁት ሥራው ሰፋ እያለ ስለመጣ ተጨማሪ 5 ሺህ ብር ያስፈልገኛል ብሎ ወንድሙን ይጠይቀውና ብሩን ወንድሙ ይልክለታል ።

በመሃል የዳንኤል ስልክ ዝም ጭጭ ይላል ። 2 ሳምንት ሙሉ በኔትወርክም እየተሳበበ ትንሽ ጊዜ ከቆዩ በኋላ ድንገት ለጌታቸው ይደውልና ሱዳን ካርቱም መግባቱን ፣ ለእናቱ እንዳይነግር ፣ እሱም በቅርቡ አውሮፓ በመግባት የተበደረውን ገንዘብ ጭምር እጥፍ አድርጎ እንደሚከፍለው በመንገር በሰላም ካሰበበት እንዲገባ ጭምር እንዲጸልይለት ለወንድሙ በመንገር ተሰነባበቱ ። ወንድሙ ጌታቸው ምንም በሁኔታው ቢያዝንም ምንም ማድረግ የማይችለው ነገር በመሆኑ ዝም ከማለት ውጪ ምንም አማራጭ ስለሌለው ደንግጦ ይቀራል ።
ከቤት እናት ወሮ ዛፉ ገብረየሱስ ደግሞ ይህን ሁሉ የታላቅና የታናሽን ምስጢር ባይሰሙም ውስጣቸው እየተረበሸ ተቸግረዋል ። “ልጄ ምነው ድምፁ ጠፋ ” መቐለ ሆኖ ነው እንዲህ የጠፋው? ብለው ይጠይቃሉ እውነታውን የሚነግራቸው የለም እንጂ ። የእናት አንጀት አይደል የሚባል ። ወደ ኋላ ላይማ በግልፅ ” ህልም አይቻለሁ ። ልጄ ታስሯል ። አደጋም ደርሶበታል እያሉ ቢናገሩም ማን አድምጧቸው ።

በመጨረሻም የዳንኤል የመጨረሻ ወንድሙ ሃኒ ኢንተርኔት ሲጎረጉር የወንድሙን የግፍ አገዳደል አይቶ ደነገጠ ። ለማን እንደሚነግር ቢጨንቀው ወንድሙ ጌታቸውን በመጥራት ዳንኤል ታርዷል ብሎ ምስሉን ያሳየዋል ። ከዚያ በኋላ የሆነውን ጌታቸው ማስታወስ አይፈልግም ። እስካሁን ድረስ ምነው ያን ገንዘብ ባልሰጠሁት እያለ ይንገበገባል ። የእናቱን ፊት እንኳን በሙሉ አይኑ ለማየት አይደፍርም ። ጥቁር ልብሱን እንኳን ዛሬ ነው እንዲያወልቅ በካህናቱ አስመክሬ እሺ ያሰኘሁት።

ምናልባት ተሳስቼ ወይም ተመሳስሎብኝ እንደሆነ ብሎ ደብረዘይት በኢንጅነሪንግ ተመርቆ በማስተማር ላይ ወዳለው ታናሽ ወንድሙ ጋር ቢደውል ወንድሙ ጣዕመ ሐዱሽ ለካ ቀድሞ በኢንተርኔት አይቶ ኑሮ ትኬት እንደቆረጠና በበነጋው እንደሚመጣ ፣ እናታቸውንም እንደሚያረዱ ተነጋግረው በማግሥቱ እናት በህልማቸው ያዩትን የልጃቸውን አደጋ በገሐድ አረጋገጡላቸው ።

አባት አቶ ሐዱሽ ገብረ ኪዳን አሁንም አስመራ ናቸው በቅርብ ርቀት ድንበር የሚሉት ጣጣ አይሻገሩት ነገር ችግር ሆኖባቸው የወለዱትን ልጅ አድጎ ዩኒቨርስቲ ገብቶ ተመርቆ እስኪወጣ እንደናፈቃቸው ዓይኑን ለማየት እንደጓጉ በሊብያ በረሃ በጨካኞች እጅ ወድቆ ሰማዕትነትን ተቀበለ ። ባለፈው ዓመት ጅማ ዩኒቨርስቲ ዳንኤል ሲመረቅ በባህርም በየብስም ብዬ እንደምንም ብዬ መጥቼ የልጄ የምርቃት ፕሮግራሙ ላይ እገኛለሁ ቢሉም አልተቻለም ።

ልጅ ዳንኤል ከኢትዮጵያ አባቴን እንዳለ ፣ አቶ ሐዱሽም ከአስመራ ልጄ እንዳሉ ፣ ላይገናኙ እንደተነፋፈቁ ተላለፉ አባትና ልጅ ። ወይ ነዶ አለ ያገሬ ሰው ።
አቶ ሐዱሽ እንደምንም ብለው አሁን መውጫ ቀዳዳ አግኝተው ከኤርትራ ምድር ወጥተው ጎረቤት ሐገር ገብተዋል ። እግዚአብሔር ካለ ሰሞኑን ኢትዮጵያ ይገባሉ ። ዳንኤልን በሕይወት ባያገኙትም ቀሪ ዘመናቸውን ከተቀሩት ልጆቻቸው ጋር ለማሳለፍ ሃገራቸው ለመግባት ቀናት እየቆጠሩ ይገኛሉ ።

ዳንኤል በክርስትና ህይወቱ የተመሰከረለት ፣ ለሃይማኖቱ እጅግ ልዩ ቅንአት ያለው ልጅ እንደነበረ አሁን በሕይወት የሚገኙት ጓደኞቹ ጭምር ይናገራሉ ። ISIS እጅ ከወደቀበት ጊዜ ጀምሮ በረሃብና በጥም ጭምር ብዙ የተሰቃዩ ቢሆንም እንኳ ከፊቱ ላይ ወዙ እንዳለ እንደነበር ሁላችን ያየነው ነው ። አንገቱን ከአካሉ ቆርጠው ወገቡ ላይ አስቀምጠውት እንኳ የተቆረጠው ፊቱ ላይ ፈገግታና ወዙ እንዳለ ነበር የሚታየው ።

ዳንኤል ሐዱሽ ማዕተቡን ከአንገቱ ሳይበጥስ ከነማዕተቡ አንገቱን የሰጠ ጀግና ሰማዕት ነው ። ቁም ነገር የላችሁም ለምንባል ለእኛ ፣ አዬ የ8ተኛው ሺህ ልጆች ለምንባል ለእኛ ኩራት የሆነን ። ቀና ብለን እንድንሄድ ያደረገን ምርጥና ብርቅዬ የተዋህዶ ልጅ ፣ የ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመንም ሰማዕት ነው ።

በ ስዊዘርላንድ የሚገኙት የኢትዮ ዙሪክ የእግር ኳስ ቡድን አባላት የላኩትን 8520 ብር አቶ አምሀ ከአሜሪካን እነ ህይወትም እንዲሁ ከአሜሪካን ብፁዕ አቡነ ማትያስ የካናዳ ሐገረ ስብከት ሊቀጳጳስ በሀገረ ስብከታቸው ከሚገኘው የካናዳ ቫንኮቨር ሆህተ ሰማይ ቅድስት ማርያም ምእመናን ልጆቻቸው ተቀብለው እንዳደርስ የሰጡኝን 4100 ብር በአጠቃላይ 25177. 95 ብር በኢንቲጮ ከተማ አስተዳሩ በአቶ ሰሎሞን እጅ አስረክቤላችኋለሁ ። ለሰጣችሁ ሁሉ እግዚአብሔር ይስጣችሁ ።

የሰማዕቱ ዳንኤል እናት ያቀረቡልኝን ነጭ ወተት የመሰለ ማር በአንባሻ ከተቀበልኩ በኋላ ክቡር ከንቲባው በረሃው ሳይበረታባችሁ በጊዜ ወደ ጾረና ግንባር ወደሚገኘው ሰማዕቱ ተስፎም ታረቀኝ በስመ ጥምቀቱ ተስፋማርያም ቤተሰቦች ዘንድ እንድንሄድ መኪናዋን ከነ ሹፌሩ ስለፈቀዱልኝ ከአባቶች ቡራኬ ተቀብዬ የሰማዕቱ ዳንኤል ወንድም ጌታቸውም አብሬህ ነው የምሄድ ብሎኝ ጉዞ ወደ ገርሁ ስርናይ አድርጌያለሁ ።

ኦ አምላኬ ምን አይነት ምስቅልቅሉ የወጣና የሚያሳዝን ቤተሰብ በዚያ እንደገጠመኝ ሰሞኑን አወጋችኋለሁ ። በትእግስት ጠብቁኝ ።

አሁን ከሌሊቱ 5 ሰዓት ሆኗል ። ነገ ሰንበት ስለሆነ አክሱም ጽዮን የማስቀደስ እድሉን አግኝቻለሁ ። በረራዬ ከምሽቱ 11 ሰዓት ላይ መሆኑ አክሱም እቆያለሁ ።
የሰማዕቱን ዳንኤል ሐዱሽን ቤተሰቦች ለመርዳት የምትፈልጉ በእናትየው ስም በተከፈተው የባንክ አካውንት ካላችሁበት ሆናችሁ አስገቡላቸው ።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አኒቲጮ ቅርንጫፍ
የባንክ ሂሳብ ቁጥር
Z 21 S 010007346
ሞባይል +251917872705 አቶ ጌታቸው ሐዱሽ ብላችሁ ደውላችሁ አጽናኗቸው ።

ይህን ጽሑፍ ካነበቡ በኋላ ሼር ቢያደርጉት ከበረከቱ መካፈል ለሚፈልግ ሰው እድል እንደመስጠት ይቆጠራልና ላልሰማ ሼር በማድረግ እናሰማ ።
ማንኛውንም አስተያየታችሁን እቀበላለሁ ። በዚህ ዙሪያ ለምትጠይቁኝ ሁሉ መልስ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ ። የእጅ ስልኬ +251 911608054 ነው ።

ከሁሉ የማንስ እኔ አክባሪ ወንድማችሁ
ዘመድኩን በቀለ ነኝ
ግንቦት 29/9/2007 ዓም
አክሱም — ኢትዮጵያ

The post አባቱን እንደናፈቀ ሳያገኘው ያለፈው ሰማዕት (ዳንኤል ሐዱሽ) “በዐይኔ አይቼ በጆሮዬም ሰምቼ ከሥፍራው በመገኘት ጻፍኩላችሁ” appeared first on Zehabesha Amharic.


በትናንቱ የመርካቶ ቃጠሎ 7 ሰዎች ተጎድተዋል ተባለ

$
0
0

በአዲስ አበባ መርካቶ ወረዳ 8 ሸራ ተራ ተብሎ በሚታወቀው ቦታ ላይ ትናንት የደረሰው የእሳት ቃጠሎ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት ያወደመ ሲሆን 7 ሰዎች በጭስ የመታፈን አደጋ ደርሶባቸዋል፡፡
የፕላስቲክ ጫማ ማምረቻ ጨምሮ ወደ 50 የሚጠጉ የብርድልብስና የተለያዩ የላስቲክ ውጤቶች፣ የንግድ መደብሮችና መጋዘኖች መቃጠላቸውን ጉዳቱ ከደረሰባቸው ወገኖች ያገኘነው መረጃ ያመለከተ ሲሆን የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ መቆጣጠር ባለስልጣን በበኩሉ፤ የአደጋው መንስኤና በአደጋው የወደመው የንብረት መጠን እየተጣራ መሆኑን ለአዲስ አድማስ ገልጿል፡፡
katello
እሳቱ የተነሳው ከቀኑ በ8፡50 ገደማ ላይ መሆኑን ከአካባቢው ሰዎች ያገኘነው መረጃ ሲያመለክት የእሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መቆጣጠሪያ የኮሙዩኒኬሽን ኦፊሰር አቶ ንጋቱ ማሞ፤ ለመ/ቤታቸው ጥሪ የደረሰው 8፡57 ደቂቃ መሆኑንና በ3 ደቂቃ ውስጥ የአደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎችና ሰራተኞች በስፍራው ተገኝተው እሳቱን የማጥፋት ስራ እንደጀመሩ ገልፀዋል፡፡
ከ3 ሰዓት በላይ የዘለቀውን የእሳት ቃጠሎ የእሳትና ድንገተኛ ተሽከርካሪዎች በምልልስ ለማጥፋት ርብርብ ያደረጉ ሲሆን የአየር መንገድ የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪም ትብብር ማድረጉን አቶ ንጋቱ ጠቁመዋል፡፡ በአካባቢው ተገኝተን እንደተመለከትነው የአካባቢው ህብረተሰብ አደጋውን ለመቆጣጠር እንዲሁም ከእሳት ቃጠሎብ ንብረት ለማትረፍ ከፍተኛ ርብርብ ያደረጉ ሲሆን በርካታ ሸቀጦችም በዚህ መልክ ማትረፍ መቻሉን ለማየት ችለናል፡፡
እሳቱን በፍጥነት ለመቆጣጠር የቦታው ለተሽከርካሪዎች አመቺ አለመሆንና እንደ ፕላስቲክና ጨርቃጨርቅ ያሉት ተቀጣጣይ ቁሳቁሶች በብዛት መኖር አዳጋች እንዳደረገባቸው የጠቆሙት አቶ ንጋቱ፤ የአደጋ መቆጣጠሩን ስራ ለባለሙያዎች አለመተውም አንዱ ችግር ነበር ብለዋል፡፡

Source: Addis Admass Newspaper

The post በትናንቱ የመርካቶ ቃጠሎ 7 ሰዎች ተጎድተዋል ተባለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴዲ አፍሮ የተለያየው ማናጀሩ የፌስቡክና የዩቲዩብ አካውንቱን ፓስወርድ እንዲመልስ ጠየቀ

$
0
0

989TeddyAfro_NYC_26
(ዘ-ሐበሻ) ዝነኛው አርቲስት ቴዲ አፍሮ ከማናጀሩ ከዘካሪያስ ጌታቸው የመለያየታቸው ዜና ከተሰማ በኋላ በየሥፍራው የተለያዩ መረጃዎች እይወጡ ይገኛሉ:: የቴዲ አፍሮ እና የማናጀሩ የመለያየት ምክንያት ራድዮ ፋና የገለጸው አይደለም እየተባለ ባለበት በዚህ ወቅት የዘ-ሐበሻ የቅርብ ምንጮች እንዳረጋገጡት ቴዲ አፍሮ ማናጀሩ የፌስቡኩን እና የዩቲዩብ ፓስወርዱን እንዲመልስ ጠይቋል::

ወደ 417 ሺህ ሰዎች ላይክ ያደረጉት የቴዲ አፍሮ ዋና የፌስቡክ ገጽን የሚያስተዳድረው ዘካሪያስ ጌታቸው የነበረ ሲሆን ቴዲ አፍሮ የዚህን ፓስወርድ እንዲመልስ ማናጀሩን በሽማግሌ ቢያስጠይቅም ዘካሪያስ ፓስፖርቱን ለመመለስ ከፍተኛ ገንዘብ መጠየቁን ምንጮች ለዘ-ሐበሻ አስታውቀዋል::

በቴዲ አፍሮ በኩል ይህን ፓስወርድ ለማስመለስ ዘካሪያስ የጠየቀውን ከፍተኛ ክፍያ ለመክፈል ፈቃደኛነት የለም:: የቴዲ አፍሮ የዩቲዩብ አካውንትም እንዲሁ በዘካሪያስ ጌታቸው እጅ የሚገኝ ሲሆን 9,529 ሰዎች ተመዝግበዋል:: ይህንንም ፓስወርድ እንዲመልስለት በሽማግሌዎች እየጠየቀ ባለበት በዚህ ሁኔታ እንደውም ዘካሪያስ ፓስወርዱን የማይመልስ ከሆነ አዲስ የፌስቡክ ላይክ ገጽ እንከፍታለን በሚል በባለቤቱ በኩል እንቅስቃሴ መጀመሩም ተሰምቷል::

ከሰሞኑ የተከፈተው አዲሱ የቴዲ አፍሮ ዋና የፌስቡክ ገጽ በርካታ ተከታዮችን እያፈራ ሲሆን እርስዎም ላይክ ማድረግ ከፈለጉ ሊንኩ የሚከተለው ነው::

Teddy Afro Offical

The post ቴዲ አፍሮ የተለያየው ማናጀሩ የፌስቡክና የዩቲዩብ አካውንቱን ፓስወርድ እንዲመልስ ጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት መንግስት ስርዓቱን የከዱትን 9 የጦር መኮንኖች እያደነ ነው * መኮንኖቹ ኦነግን ተቀላቅለዋል እየተባለ ነው

$
0
0

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ከደቡብ ምስራቅ እዝ የከዱ ዘጠኝ የባሌ ክፍለሃገር ተወላጅ የሆኑ የሰራዊቱ መኮንኖችን ለመያዝ ማደኑን አንደቀጠለ አና አስካሁን ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተቀላቅለዋል ከሚባል ውጪ ያሉበት ቦታ ምንም ፍንጭ እንደሌለ ለጦር ሃይሎች መምሪያ የደህንነት ክፍል የመጣ መረጃ መጠቆሙን የመከላከያ ምንጮች ገልጸዋል::
clash
በተለያዩ ጊዜያት ከባለፉት ሳምንት ጀምሮ ድንበር ዘለል ወረራ በኬንያ ላይ ያደረገው የወያኔ ሰራዊት ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ጦርነት ገጥሞ አንደነበር ሲታወስ የከዱ የመከላከያ ሰራዊት መኮንኖች ከኦነግ ኣማጽያን ጋር ተደባልቀው የወያኔን ሰራዊት አንደወጉ ቢገለጽም አስካሁን ድረስ የኦነግ ታጣቂ ሃይሎችን ያሉበትን ኣከባቢ ለማግኘት ኣለመቻሉን መረጃዎቹ ሲጠቁሙ ኣሉበት የተባሉ ኣከባቢዎችን በሃገር ውስጥ ደኖች ላይ ኣንደተለመደው አሳት በመልቀቅ አና ጎረቤት ሃገሮችን በመውረር በሃይል ለማዳከም ስራዎች አየተሰሩ አንደሆን ምንጮቹ ለምንሊክ ሳልሳዊ ተናግረዋል::

ሰራዊቱን ከድተው ወተዋል ከተባሉት ከፍተኛ መኮንኖች ውስጥ ሶስቱ ኮሎኔሎች የጦር መሪዎች መሆናቸው ሲታወቅ አነሱም
፤ ፩ = ኮሎነል ያሲን ሁሴን
፪ = ኮሎኔል ነገራ ኢደሳ
፫ = ኮሎኔል ኑሩ ኣስሊ ይገኙበታል::

የሰራዊቱ የዘመቻ እንቅስቃሴ መረጃዎች በጃቸው አንደሆነ የሚነገርላቸው የጦር መሪዎች መክዳት ከፍተኛ ድንጋጤ አንደፈጠረ ታውቋል፥፥ይህ በእንዲህ አንዳለ በሶማሊያ አና በኢትዮጵያ ድንበር ኣከባቢ በወያኔ ሰራዊት እና በኦብነግ ኣማጽያን መካከል ግጭቱ የቀጠለ ሲሆን በክዐንያው ድርድርም አስካሁን የተገኘ ውጤት አንዳሌለ ታውቋል:

The post የሕወሓት መንግስት ስርዓቱን የከዱትን 9 የጦር መኮንኖች እያደነ ነው * መኮንኖቹ ኦነግን ተቀላቅለዋል እየተባለ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

Sport: ዋሊያዎቹ በዛምቢያ‬ ተሸነፉ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ዛሬ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከዛምቢያ አቻቸው ጋር ባደረገው የወዳጅነት ጨዋታ 1-0 ተሸነፈ። ዛምቢያ በአላን ሙኩካ አማካኝነት 45 ኛው ደቂቃ ጎል ማስቆጠር ችለዋል። 75ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ የፍፁም ቅጣት ምት ብታገኝም ቢንያም አሰፋ ሳይጠቀምበት ቀርቶ ጨዋታው በዛምቢያ 1- 0 አሸናፊነትም ተጠናቋል::

ፎቶ ክሬዲት - ለኢትዮ-ኪክ

ፎቶ ክሬዲት – ለኢትዮ-ኪክ

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን በተለይም ጋቶች ፓኖም እና ምንተስኖት አዳነን በብሩክ ካልቦሬ እና ፍሬው ሰለሞን በመቀየር ከእረፍት መልስ የተሻለ ቢንቀሳቀስም ግብ ማስቆጠር ተስኖት ታይቷል ያሉት የስፖርት ተንታኞች ጨዋታው ሊጠናቀቅ አምስት ደቂቃ ሲቀርም ሙጂብ ቃሲም ሆን ብሎ ኳስ በእጅ በመንካቱ በቀይ ካርድ ከሜዳ መሰናበቱን ገልጸዋል::

ፌዴሬሽኑ ይህን የወዳጅነት ጨዋታ የዛምቢያ ብሄራዊ ቡድን ወጪ በመቻል ወደ ኢትዮጵያ ያመጣው ጨዋታው የተካሄደው አዲሱ አሰልጣኝ ዩሃንስ ሳህሌ የሚመሩት ዋልያዎቹ የፊታችን ሰኔ 7 ለ2017ቱ የአፍሪካ ዋንጫ ከሌሴቶ ጋር ለሚያደርጉት የምድብ ጨዋታ ቅድመ ዝግጅት እንደሚረዳቸው ታስቦ ነበር::

ፊፋ በየዓመቱ በሚያወጣው የዓለም የ እግር ኳስ ደረጃ 8 ደረጃዎችን በማሽቆልቆል 68ኛ ደረጃ ሲቀመጥ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአንጻሩ 2 ደረጃዎችን ወደ ላይ በማሻሻል 99ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል::

The post Sport: ዋሊያዎቹ በዛምቢያ‬ ተሸነፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኖርዌይና የኢትዮጵያውያን ስደተኞቻችን ፍልሚያ –በአበራ ለማ

$
0
0
Photo File

Photo File

የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኖች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ”ዘ አየር ሴንተር – The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) በተሰኘው መንግሥታዊ ባልሆነው የሕግ ባለሙያዎች ድርጅት አማካኝነት የቀረበለትን ይህን ጉዳይ፣ ከሦስት ዓመታት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲመለከተው መቆየቱም ይታወሳል፡፡

Read Full Story in PDF

The post የኖርዌይና የኢትዮጵያውያን ስደተኞቻችን ፍልሚያ – በአበራ ለማ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>