Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

በሚኒሶታ የዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል በአስገዳጅ ሁኔታ እንዳይከበር ተሰረዘ!

$
0
0

ውድ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች! ጁን 20 የዘ-ሐበሻን 7ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል በሚኒሶታ ለማክበር ዝግጅታችንን አጠናቀን ነበር:: ሆኖም ግን በአስገዳጅ ምክንያት የዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል እንደማይካሄድ ከይቅርታ ጋር እየገለጽን ዘ-ሐበሻን ለመርዳት የምትፈልጉ በድረገጻችን በመግባት በፔይፓል መጠቀም እንደምትችሉ ለመጠቆም እንወዳለን:: እውነት ያሸንፋል! የሚለው መርህዋን ተከትላ የምትቀሳቀሰው ዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመቷን ወደፊት የትና መቼ እንደምታደርግ በቅርቡ እንደምታሳውቅም በዚሁ አጋጣሚ እየጠቆምን ለተፈጠረው ችግር ይቅርታ እንጠይቃለን::

በዚሁ አጋጣሚም ለዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል በክብር እንድነት ለመገኘት ፈቃደኛነታቸውን ገልጸውልን ለነበሩት ለኤርሚያስ ለገሰ (የመለስ ትሩፋቶች መጽሐፍ ደራሲ) እና ለጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ያለንን ክብርና ፍቅር ለመግለጽ እንወዳለን::

የምንወዳት ሃገራችንን ፈጣሪ ይጠብቅልን

የዘ-ሐበሻ ቡድን
Zehabesha

The post በሚኒሶታ የዘ-ሐበሻ 7ኛ ዓመት በዓል በአስገዳጅ ሁኔታ እንዳይከበር ተሰረዘ! appeared first on Zehabesha Amharic.


በፓትርያርኩ መቀመጫ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅርሶች እና ንዋያተ ቅድሳት ጉዳይ ምርመራ እንዲካሔድ ተጠየቀ

$
0
0

ታሪካዊው የቅዱስ እንጦንስ ጽሌ በአርተፊሻል ተቀይረዋል ከተባሉት አንዱ ነው
የስእለት እና የስጦታ ወርቆች እና የብር ጌጣጌጦች በየመሸታ ቤቱ እየተሸጡ ነው
የውጭ ኦዲት እንዲካሔድ በፓትርያርኩ የተሰጠው መመሪያ ተግባራዊ አልተደረገም
በየመሸታው አስነዋሪ ሥራ የሚያዘወትሩ ካህናት ለምእመናን መራቅ ምክንያት ኾነዋል
የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ለችግሩ መባባስ ተጠያቂ ተደርገዋል

(ኢትዮ-ምኅዳር፤ ቅጽ 03 ቁጥር 107፤ ቅዳሜ ግንቦት 22 ቀን 2007 ዓ.ም.)

በምሥረታ ታሪኳ እና በሕገ ቤተ ክርስቲያኒቱ ድንጋጌ የፓትርያርኩ መንበር በሚገኝባት ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም፣ በቅርስነት የሚታዩ ጥንታውያን የቤተ ክርስቲያን ንዋያተ ቅድሳት፣ አልባሳት፣ መጻሕፍት እና ልዩ ልዩ ንብረቶች እየተለወጡ እና እየተሸጡ በመጥፋት ላይ ናቸው ያሉ የገዳሟ አገልጋዮች እና ምእመናን ምርመራ እንዲካሔድ ጠየቁ፡፡
ባለፈው ሚያዝያ ወር መጨረሻ የገዳሙ አገልጋዮች እና ምእመናን ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ የጻፉት ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ገዳሟ የበርካታ ንዋያተ ቅድሳትና ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ስትኾን ከተለያዩ አብያተ ክርስቲያን ተሰርቀው በእግዚአብሔር ኃይል የተገኙና ወደ ስፍራቸው እስኪመለሱ ድረስ በአደራ የተቀመጡ ብዙ ንዋያተ ቅድሳትም ያሉባት ነች፡፡
ከታቦተ ሕጉ ጀምሮ የገዳሟ ንዋያተ ቅድሳትና ታሪካዊ ቅርሳ ቅርሶች ተመርጦ በተመደበው ካህን በየዓመቱ እየተቆጠሩ በጥንቃቄ ተመዝግበው መጠበቅ ሲገባቸው፣ ‹‹የመልካም ሥነ ምግባር አብነት መኾን በተሳናቸው›› አንዳንድ የገዳሟ ሠራተኞች በአምሳላቸው እየተለወጡና እየተሸጡ የመጥፋት አደጋ እንደተጋረጠባቸው ተገልጧል፡፡
Ethiopian_Orthodox_Church_Siege_Addis_Abeba_2
ካለፈው ዓመት ጀምሮ እየተባባሰ መምጣቱ በተነገረው በዚኽ ዓይነቱ ዘረፋ፣ ጥንታውያን ጽሌዎች በአርተፊሻል እንደተቀየሩ፣ ጥንታውያን የብራና መጻሕፍት እና የወርቅ ጽንሐሕ እንደ ወጡ በጥያቄው ተጠቁሟል፡፡ ‹‹እኔ የማውቃቸው ብዙ ንብረቶች ጠፍተዋል›› ሲል ለኢትዮ-ምኅዳር የተናገረ አንድ የገዳሙ አገልጋይ፣ ድርጊቱ የሚፈጸመው ጥንታውያኑን ንዋያተ ቅድሳት እና ቅርሶች በአሳቻ ጊዜ በማውጣት፣ በዕቃ ማጣርያ እና ሽያጭ ሰበብ እንዲኹም ሰነዶችን በመደለዝ እና በማጥፋት እንደኾነ አስረድቷል፡፡ ጥገና እየተደረገላቸው በቅርስነት ተከብረው ለአጠባበቅ ምቹ በኾነ ዕቃ ቤት ተቀምጠው መጎብኘት የሚገባቸው የመጀመሪያውን ኢትዮጵያዊ ፓትርያርክ ጨምሮ ቀደምት ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የለበሷቸው ካባዎች፣ ቀጸላዎች፣ አክሊሎች፣ መጎናጸፊያዎች፣ መጋረጃዎችና ጽዋዎችበግምጃ ቤቱ ስለመኖራቸው በንብረት ዓመታዊ ምዝገባ እና ቁጥጥር ማጣራት እንደሚያስፈልግ አገልጋዩ በሐዘን ጠይቋል፡፡
የድርጊቱ ዋነኛ ፈጻሚዎች እንደኾኑና የማጣራቱ ርምጃ እንዲካሔድባቸው የተጠየቀው÷ በገዳሙ የቁጥጥር ክፍል ሓላፊ፣ በንብረት ክፍል ሓላፊ እና በቄሰ ገበዙ ላይ ነው፡፡ የሦስቱን ሓላፊዎች ድርጊት የሚያውቁ አንዳንድ የገዳሟ መነኰሳትም ‹‹የድርሻችን›› በማለት ሲጠይቁ እንደሚስተዋሉ የጠቀሱት አመልካቾቹ፣ ‹‹የቢሮ ሥራ እንሰጣቸኋለን፤ የሙዳይ ምጽዋት ቆጠራውን ወደነበረበት እንመልሰዋለን›› በሚል ሕገ ወጥ አካሔድ እና ጥቅም በማማለል ማባበያ እየተደረገለቸው እንዳለ ገልጸዋል፡፡
በሚልዮኖች የሚቆጠር የገዳሟ ገንዘብ እና ንብረት በአስተዳደር ሓላፊዎች እና ሠራተኞች መመዝበሩን ተከትሎ በኅዳር ወር አጋማሽ የተቋቋመው የሙዳየ ምጽዋት ቆጠራ ኮሚቴ፣ የስድስት ወራት የሥራ ጊዜው ቢጠናቀቅም በእጁ ያለውን ንብረት አስረክቦ ለመቀየር ዝግጁ ካለመኾኑም በላይ በኮሚቴው የሰበካ ጉባኤው ምክትል ሊቀ መንበር እና ቄሰ ገበዙ ተካተውበት ቆጠራው በካሽ ካውንተር አጋዥነት በባንክ ባለሞያዎች ድጋፍ እንዳይቆጠር አባላቱ መቃወማቸው ተመልክቷል፡፡
ኮሚቴው ከምእመናን በስእለት የተሰጡ ንብረቶች በአግባቡ እየተመዘገቡ ግምታቸው ታውቆ በሕጋዊ መንገድ ገቢ እንዲኾኑ በማድረግ በኩል ከፍተኛ ድክመት ማሳየቱ የአመልካቾቹ ሌላው ትኩረት ነው፡፡ በተለይም ካለፈው ሚያዝያ ወር ወዲኽ እየተባባሰ በመጣው የንብረት ምዝበራ፣ ከበጎ አድራጊዎች ለገዳሙ የተለገሠ ላፕቶፕ ኮምፒዩተር እና ጸሎተ ቅዳሴውን ለብዙኃን ለማስተላለፍ ያገለግላል የተባለ ፕሮጀክተር ተመዝግቦ ገቢ ሳይደረግ በግለሰቦች ወጥቶ መሸጡ ተገልጧል፡፡
በደብዳቤው እንደሰፈረው÷ ከመቶ ኻያ ግራም በላይ የአንገት እና የጣት ወርቆች፣ መጠናቸው የማይታወቅ የብር ጌጣጌጦች በደንቡ እና በመመሪያው መሠረት በሕጋዊ ሰነድ ለንብረት ክፍሉ ገቢ ሳይደረጉ መልአከ ብሥራት አባ ወልደ ትንሣኤ አዳሙ በተባሉ የቆጠራ ኮሚቴው አባል በተለያዩ መሸታ ቤቶች መሸጣቸው በዓይን እማኞች ተረጋግጧል፡፡
ከሰማኒያ በላይ ካህናት ባሉበት ገዳም የቃለ ዐዋዲ ደንቡን የሥራ ሓላፊዎች ምርጫ እና የአገልግሎት ዘመን ድንጋጌ በመቃረን ተመሳሳይ ያልኾኑ ሓላፊነቶችን ደራርበው ይዘዋል የተባሉት መልአከ ብሥራት አባ ገብረ ሥላሴ፣ የልማት ኮሚቴው ለሚያሠራው ኹለ ገብ እና የአገልግሎት ሕንፃ ያለፕሮፎርማ በተፈጸመ ጥራቱን ያልተጠበቀ የብረት ግዥ ተገቢ ያልኾነ ጥቅም (ቢያንስ ከብር 200,000 በላይ) ማግኘታቸው ተጠቁሟል፡፡ የገዳሟ የሥራ ማስኬጃ ገንዘብ ያዥ፣ የልማት ገንዘብ ተቀባይ፣ ዕቃ ግዥ እና ንብረት ቁጥጥር ሓላፊየኾኑት የመልአከ ብሥራት አባ ወልደ ሥላሴ ስም ከቄሰ ገበዙ አባ ሳሙኤል ቀለመ ወርቅ እና ሌላ ካህንን ጨምሮ ለምንኩስና ሥርዐት በማይስማማ ተግባር በአልባሌ ቦታ ከመገኘት ጋር ተያይዞም ተነሥቷል፡፡
መነኰሳቱ፥ ‹‹ልናጠምቃቸው ነው›› በሚል እና በምግብ አብሳይነት ሰበብ በገዳሙ ቅጽር በሚገኘው ማረፊያ ቤታቸው የሚገቡ ሴቶችን እስከ መንፈቀ ሌሊት እያቆዩ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ነውር በመፈጸም፤ በየግሮሰሪው ዓምባጓሮ እየፈጠሩ ከአስተናጋጆች ጋራ ለድብድብ በመጋበዝ፤ በስካር ወደ ገዳሙ ተመልሰው እየገቡ ከምእመናን ጋራ በክፉ አንደበት በመመላለስ፤ በዘር አንዳንዴም በመንደር እየተከፋፈሉ ቅጽሩን የአሉባልታ እና የአድማ መናኸርያ በማድረግ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን ነቅፈው አስነቅፈዋል፤ ክብረ ቤተ ክርስቲያንን ደፍረው አስደፍረዋል ተብሏል፡፡ አዲሱ የገዳሟ ሰበካ ጉባኤ ይህን ለመከላከል የጊዜ ወሰንን ጨምሮ ያወጣው ዝርዝር የመተዳደርያ ደንብ ‹‹ሕጉ እኛን ለመገደብ ነው፤ እስከ ከዛሬ እንደኖርነው እንኖራለን እንጂ ሕግ አያስፈልግንም፤›› ባሉት በሦስቱ መነኰሳት ግንባር ቀደምነት ተግባራዊነቱ መስተጓጎሉ ተዘግቧል፡፡
ከሰማኒያ ዓመታት በላይ መንፈሳዊ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ስትሰጥ የቆየችው ገዳሟ አኹን ያለችበት የቤተ መቅደስ የውስጥ አገልግሎት ‹‹መንፈሳዊ ሕይወት በማይታይባቸው እና ሞያዊነት በሚያንሳቸው ካህናት የተነሣ ደረጃዋን የማይመጥን ነው፤›› ይላሉ አመልካቾቹ፡፡ የውስጥ አገልግሎቱ እና የክህነቱ ተግባር በቂም በቀል፣ በጥላቻ ለደመወዝ ሲባል ብቻ እንጂ መንፈሳዊነቱ ተጠብቆ እና ሥነ ሥርዐቱ ተሟልቶ እየተፈጸመ አይደለም፤ ከጥምቀት እስከ ጸሎተ ፍትሐት አስፈላጊውን መንፈሳዊ አገልግሎት ለምእመናን መስጠት የካህናቱ ኹሉ ሓላፊነት እንደመኾኑ የተመደቡበትን ተልእኮ በሙሉ ኃይላቸው እና ችሎታቸው ለበላይ ሓላፊ በመታዘዝ ከማከናወን ይልቅ ደጀ ጠኚዎችን እየተኩ በውክልና የሚያስፈጽሙ፤ ‹‹ተረኛው የለም፤ ጊዜው አልፏል›› በሚል ግልጋሎት ፈላጊ ምእመናንን ግብረ ገብነት እና ቅንነት በጎደለው ቃል እየተናገሩ የሚያስመርሩ ካህናት ጥቂቶች አይደሉም፡፡ አመልካቾቹ፣ ‹‹በአገልግሎት ከአረጀንባት ቅድስት ስፍራ የሰበካዋ ምእመናን እንዲርቋትና ወደ ሌሎች አድባራት እንዲሔዱ ምክንያት ኾነዋል፤›› በማለት ካህናቱን ይወቅሳሉ – በደብዳቤአቸው፡፡
ምእመናንን በሃይማኖት የመጠበቅ ግዴታቸውን የዘነጉት ካህናት፣ ከተጠያቂነት ለመዳን የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊን ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃን ጨምሮ ቅርበት አላቸው የሚባሉ ሓላፊዎችን መከታ እንደሚያደርጉም ተገልጧል፡፡ የገዳሙን ሀብት እና ንብረት ከመጠበቅ ጀምሮ ለገዳሙ አስተዳደር እና አገልግሎት የበላይ ሓላፊና ተጠሪ የኾኑት አስተዳዳሪው በተጠቀሱት ካህናት እና መነኰሳት ዘንድ ሥልጣን አልባ መደረጋቸው ተነግሯል፡፡
St Marry Bulding comp.
የገዳሟ ያለፉት ስድስት ዓመታት የሒሳብ አያያዝና የንብረት አጠባበቅ በውጭ ኦዲተር እንዲመረመር የልማት ኮሚቴው የበላይ ጠባቂ በኾኑት በፓትርያርኩ ባለፈው ኅዳር ወር የተሰጠው መመሪያ እስከ አኹን ተግባራዊ አለመኾኑ የአስተዳዳሪው ሥልጣን ውሱንነት እና የተጠቀሱት ዋልጌ መነኰሳት የበላይነት መገለጫ ተደርጎ ታይቷል፡፡ በታኅሣሥ ወር አጋማሽ በተመረጠው አዲሱ ሰበካ ጉባኤ ገዳሟ፣ የኻያ በመቶ የሀገረ ስብከት ፈሰስ ውዝፏን በመክፈልና ተቀማጯን ወደ 1 ነጥብ 8 ሚልዮን በማሳደግ የተጓተተው የባለስድስት ፎቅ ሕንፃ ግንባታ እየተፋጠነ ቢኾንም ለውጭ ኦዲቱ ‹‹እየተዘጋጀን ነው›› ከማለት ያለፈ በተግባር ለማስፈጸም አለመቻሉ ታውቋል፡፡
የንብረት እና የቁጥጥር ክፍሎች ሓላፊዎች ከቄሰ ገበዙ ጋራ በመኾን ‹‹አዲሱ ሰበካ ጉባኤ ኦዲት አስደርጎ እኛን ሊያባርረን ነው፤ አንገታችንን እንሰጣለን እንጂ ኦዲቱ አይካሔድም›› በሚል የውጭ ኦዲት ምርመራው እንዳይፈጸም በተለያዩ ስልቶች እየተከላከሉ እንዳሉ ነው የተገለጸው፡፡ ፈቃድ እየጠየቁ ዕረፍት በመውጣት በሥራ ገበታ አለመገኘት አንዱ ስልት መኾኑ ተጠቁሟል፡፡
መንበረ ፓትርያርክ በኾነችው በገዳሟ በውስጥ አገልግሎቷ ከሚታይባት በቂ ሞያ እና ቁጥር ያላቸው ካህናት ጉድለት ባሻገር በቢሮ ሠራተኞች ዘንድም ከፍተኛ የዕውቀት ማነስ እና የአቅም ውስንነት እንዳለ ተጠቅሷል፡፡ ለአብነት ያኽል፣ ለኦዲቱ ሥራ የሚያስፈልገውን የሒሳብ ሪፖርት በጥራት እንዲያቀርቡ የሚጠበቁት የሒሳብ ሹሙ የትምህርት ደረጃ ከዐሥረኛ ክፍል ያለፈ አይደለም፡፡ ሰበካ ጉባኤው ለቦታው በዕውቀት የሚመጥን ባለሞያ እንዲላክ ከአንድ ወር በፊት በጉባኤ ወስኖ ሀገረ ስብከቱን የጠየቀ ቢኾንም ክፍተቱ እንዳይደፈንና ‹‹ከእኛ በላይ ሰው የለም›› በሚል ከቢሮ ሠራተኞች ጋር በጥቅም በተቆራኙት ሦስት ካህናት ክፋት እንዳይፈጸም መደረጉ ነው የተገለጸው፡፡
‹‹ሰበካ ጉባኤው አይጠቅመንም፤ ይውረድልን›› በሚሉ አድማዎች ሳቢያ ሰበካ ጉባኤው አርቅቆ ያቀረባቸው የሰው ኃይል፣ የፋይናንስ፣ የንብረት እና የግዥ ዝርዝር መመሪያዎቹ÷ ‹‹መተዳደርያ ደንብ፣ ማኑዋል የሚባል ነገር አያስፈልገንም፤ እንዲያስቀሩልንም ለሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ነግረናቸዋል›› በሚሉት ሦስቱ ግንባር ቀደም መነኰሳት የተነሣ ሊሠራባቸው እንዳልቻሉና ተጨባጭ ለውጥ ለማሳየት የሚያደርገው ጥረት ዕንቅፋት እንደገጠመው ተመልክቷል፡፡ ይኸውም የአድኅሮት አቋማቸው ‹‹ሕገ ቤተ ክርስቲያን፣ ቃለ ዐዋዲ እና የሠራተኛ መተዳደርያ ደንብ አለን፤ ሌላ ምንም አያስፈልገንም›› የሚሉት ዋና ሥራ አስኪያጁ ሳይተባበሩበት እንዳልቀረ ተጠቁሟል፡፡
በገዳሟ ‹‹ሃይማኖት ጎድሏል፤ ግብረ ገብነት ጠፍቷል፤ ምዝበራ ተንሰራፍቷል›› የሚሉት አመልካቾቹ፣ በመጋቢት ወር ለብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ ጥያቄአቸውን ለማቅረብ ሞክረው እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ ይኹንና የፓትርያርኩ ልዩ ጸሐፊ ንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ‹‹ጾም ሲፈታ እንጂ አኹን አይቻልም›› ብለው በማለታቸው ችግሩ እየተባባሰ እንዲሔድ ምክንያት መኾናቸውን በመጥቀስ ጉዳዩ ፖሊስን ጨምሮ በሚመለከታቸው አካላት እንዲጣራ ያደርጉላቸው ዘንድ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስን መጠየቃቸው ታውቋል፡፡
የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው በበኩሉ ባለፈው ሳምንት ኀሙስ ወደ ፓትርያርኩ ቀርቦ ከተመረጠበት ታኅሣሥ ወር ወዲኽ በአስተዳደር እና በልማት ያከናወናቸውን ተግባራት በሪፖርት ማቅረቡ ዘግይቶ ተሰምቷል፡፡ በተለይም በአሠራር መመሪያዎቹ ዝግጅት ‹‹ከጠበቅኹት በላይ ነው የሠራችኹት›› የሚል ማበረታቻ ከፓትርያርኩ ማግኘቱ ተገልጧል፤ ለተግባራዊነቱ ስለገጠመው ዕንቅፋትም ‹‹በቃለ ዐዋዲው መሠረት ሕግ እና ሥርዐት ተከትላችኹ ርምጃ ከመውሰድ የሚያግዳችኹ ነገር የለም›› የሚል መመሪያ መቀበሉ ተነግሯል፡፡
St Marry Church
የመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ስያሜዋን ያገኘችው በ፲፱፻፳፪ ዓ.ም. ስትመሠረት የቅዱሳን ፓትርያርኮች መንበር ስለሚገኝባትና በመንበረ ፓትርያርክ ግቢ ስለምትገኝ መኾኑን ታሪኳ ይገልጻል፡፡ ስፍራው ቀደም ሲል የሥርዐተ ምንኵስና መሥራቾቹ የቅዱስ አባ እንጦንስ እና አባ መቃርስ ቤተ ክርስቲያን ተሠርቶበት የግብጻውያኑ ሊቃነ ጳጳሳት ማረፊያ እና ዕጨጌው እንዲኹም ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጸሎት የሚያደርሱበት በመኾኑ አቡን ቤት እየተባለ ይጠራ ነበር፡፡ በግብጻዊው ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ከኢየሩሳሌም መጥቶ በመናገሻ ማርቆስ ተቀምጦ የቆየው የቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ጽላት እስከገባበት ድረስም ምእመናን አምልኮታቸውን ይገልጹበት ነበር፡፡
ጥር ፳፩ ቀን ፲፱፻፳፪ ዓ.ም በብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ትእዛዝ መሠረቱ የተጣለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ሥራው የተጠናቀቀው መስከረም ፲፱፻፳፰ ዓ.ም ነው፡፡ በወቅቱ በፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ምክንያት ሌሎች በርካታ ታቦታትም በቤተ መቅደሱ ተቀምጠው እንደነበር ይነገራል፡፡ ገዳሟ የግብጽ ኦርቶዶክስ ካህናት እና የሕንድ ኦርቶዶክስ ካህናት በየራሳቸው ቤተ መቅደስ መንፈሳዊ አገልግሎት የሚፈጽሙባት ብቸኛዋ ቤተ ክርስቲያን ነበረች፡፡ ግብጻውያን ኦርቶዶክሳውያን ዛሬም በገዳሙ ደቡባዊ አንቀጽ ከክርስትናው ቤት ፎቅ ላይ በመገኘት መንፈሳዊ አገልግሎታቸውን ሲፈጽሙ ይታያሉ፡፡
በሚያዝያ ወር መጨረሻ ለፓትርያርኩ በተጻፈው የገዳሟ ካህናት ደብዳቤ ‹‹በአርተፊሻል ተቀይረዋል›› ከተባሉትና ምርመራ እንዲካሔድ ከተጠየቀባቸው ጥንታውያን ጽላት አንዱ ታዲያ የአበ መነኰሳት ቅዱስ እንጦንስ መኾኑ ነው እየተነገረ የሚገኘው፡፡
Source:: haratewahido

The post በፓትርያርኩ መቀመጫ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅርሶች እና ንዋያተ ቅድሳት ጉዳይ ምርመራ እንዲካሔድ ተጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል

$
0
0

በሀገራችን ኢትዮጵያ ስላለው ሁለንተናዊ ቀውስ በመወያየት ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል የሚቋቋምበትን ሂደት ለመምከር ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል

የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ፤ የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄና
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ኅብረት ጋር በተደረጉ ተከታታይ የሁለትዮሽ ውይይቶችና
ስምምነቶች፡ ህዝባችን ላለፉት 24 ዓመታት ያለነፃነት በህወሓት የግፍ አገዛዝ ሥር ፍዳውን የሚያይበት ዋና ምክንያት፤
ሕዝብን መሠረት ያደረገና ብሄራዊ ጥቅምን ያስቀደመ፤ በአንድ ማዕከል የሚንቀሳቀስ ሁሉን አቀፍ የአማራጭ አካል
በማቋቋም ሥርዓቱን ለማስወገድ አስፈላጊውን ትግል የማድረግ ቁርጠኝነቱ በተቃዋሚው ጎራ ያለመኖሩ ዋና ጉዳይ
መሆኑን የጋራ ግንዛቤ ላይ ደርሰናል። ይህን አዙሪት በመስበርና ሁኔታዎችን በጋራ በማመቻቸት የአማራጭ ኃይሉ
በአስቸኳይ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ መድረሳችንንም በተከታታይ ባወጣናቸው የሁለትዮሽ መግለጫዎች ይፋ
መሆናቸው የሚታወስ ነው።
shengoENTC
ሥርዓቱ ባሳለፍነው ሳምንት ውጤቱ ምን ሊሆን እንደሚችል አስቀድሞ የታወቀውን የህወሓት/ኢህአዴግ የምርጫ
ድራማ በማካሄድ፤ ሕዝብን ተስፋ በማስቆረጥና ግፉን አሜን ብሎ በመቀበል፤ ቀደም ሲል ሲያደረግ የነበረውን ሀገር
የማፈራረስ ሂደትና የሕዝብን ስቃይ የሚያበዛ አገር በቀል የአፓርታይድ አገዛዝ ለቀጣይ አምስት አመታት ለማስቀጠል
የሚያስችለውን ህጋዊ ሽፋን በማመቻቸት ላይ በሚገኝበት በዚህ ወሳኝ ወቅት፤ አገር አድን የምክክር ጉባዔ በማድረግ
በሕዝብ ተቀባይነትና ታማኝነት ያለው ሁሉን አቀፍ የአማራጭ ኃይል በማቋቋም ትግሉን በተጠናከረ ሁኔታ መቀጠል
ወቅታዊና አስቸኳይ ነው።
EYNM New Logo
ከላይ በመግቢያው ላይ የተዘረዘሩት ድርጅቶች፤ ከተለያዩ አክቲቪስቶችና ታወቂ ግለሰቦች ጋር በመሆን ከጁላይ 2-3
የምክከር ጉባዔ በጋራ ያዘጋጃሉ። የጉባዔውን ውጤት ለማሳወቅ ሕዝባዊ ስብሰባም ይዘጋጃል። የመሰብሰቢያ ቦታ፤
ዝርዝር ፕሮግራሞችና ተያያዥ እንቅስቃሴዎችን በተከታታይ እንደምናሳወቅ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን።
ስለዚህ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ የፓለቲካ ድርጅቶችና የሲቪክ መኅበራት፣ የነገ ሀገር ተረካቢ የሆናችሁ ወጣቶች፤
በሀገራችን ነፃነት ሠላም እኩልነትና ፍትኅ ይሰፍን ዘንድ የምትተጉ የቴሌቪዥንና የሬዲዮ አዘጋጆች፣ የፓልቶክ ክፍሎች፣
ጋዜጠኞች፣ አክቲቪስቶች፣ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች፣ የእምነት አባቶች፤ እንዲሁም ለሀገር ደህንነት ተቆርቋሪ
የሆናችሁ ዜጐች በሙሉ፤ የሚገነባው የተባበረ አማራጭ ኃይል ባለቤት እንደመሆናችሁ መጠን የሂደቱ ቀጥተኛ ተሳታፊ
በመሆን፤ በሀገራችን ነፃነት እውን እንዲሆን በሚደረገው ወሳኝ ሕዝባዊ ትግል ውስጥ የበኩላችሁን አስተዋፅዖ ታበረክቱ
ዘንድ፤ እንዲሁም በሕዝባዊ ስብሰባው ላይ ንቁ ተሳትፎ እንድታደርጉ አደራ እያልን በአክብሮት ሀገራዊ ጥሪያችንን
እናቀርባለን።

ይህ አደገኛ የቁልቁለት ጉዞ እንዲገታ በጋራ እንቁም!
የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (SHENGO)
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC)
የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ንቅናቄ ደጋፊዎች ህብረት (UEM-PMSG)
የኢትዮጵያ ወጣቶች ብሄራዊ ንቅናቄ (EYNM)
ግንቦት 22፤ 2007 (May 30, 2015)


The post ከጁላይ 2-3 በዋሽንግተን ዲሲ የሀገር አድን ጉባዔ በጋራ ይዘጋጃል appeared first on Zehabesha Amharic.

ጋዜጠኛውን የደበደበው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ በፍርድ ቤት ተቀጣ

$
0
0

ከአንዲት ግለሰብ ጋር ፊልም እስራልሻለሁ በሚል ገንዘብ ተቀብሎ ገንዘቡን ክዷል የሚል ክስ ቀርቦበት ፍርድ ቤት እየተመላለሰ የሚገኘው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ ለምን ይህን ጉዳይ ዘገባችሁ በሚል የኢትዮፒካ ሊንክ ጋዜጠኞች ላይ ጥቃት ለማድረስ አስቦ በአንዱ አዘጋጅ ላይ ድብደባ በመፈጸሙ በከሰሰበት ክስ ጥፋተኛ ተብሎ 2 ቀን ከታሰረ በኋላ ተፈረደበት:: ዝርዝሩን ያድምጡ::


Daniel tegegne

The post ጋዜጠኛውን የደበደበው አርቲስት ዳንኤል ተገኝ በፍርድ ቤት ተቀጣ appeared first on Zehabesha Amharic.

የወያኔ የመከላከያ ከፍተኛ በጀት

$
0
0

ginbot 7የወያኔ የመከላከያን ከፍተኛ በጀት ለትግራይ ክልል እንደ ተጨማሪ ልዩ በጀት አድርጎ ይጠቀማል፡፡ በሰራዊቱ ውስጥ ዘረኛ መድሎን ይፈጽማል፡፡ የትግራይ ሪፑብሊክ ምስረታ ህልሙንም አልረሳም፡፡

በአሁኑ ጊዜ 85% የሚሆነው የመከላከያ ሠራዊት ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ በትግራይ ክልል ሠፍሮ ይገኛል፣ ይህንንም አጋጣሚ
በመጠቀም ፦

  1. ለሠራዊቱ ቀለብ አቅርቦት ያለ ጨራታ ከአዛዧች ጋር በመመሳጣር፣ የትግራይ ሰዎች ብቻ እንዲያቀርቡ ተደርጓል። አቅራቢ ከሆኑትም መሀል አቶ ጉዕሺ፣ ወ/ሮ ዘውዴ ፣ አቶ ስብሀት ፣ ወ/ሮ አዲስ፣ አቶ ገብረስላሴ፣ አቶ ሃጎስ በመባል የታወቁ ሰዎች ይገኙበታል፡፡ ለሰራዊቱ የሚያቀርቡትም አትክልት ፣ በርበሬ፣ የወጥ እህሎችና ሥጋ፣ ዱቄት ፣ ዘይት ወዘተ. መሆኑ ታውቋል። አቅራቢዎቹ የትግራይ ሰዎች አቅርቦቱም ከትግራይ ክልል እንዲገዛ ተደርጓል።
  2. ሰራዊቱ በከፍተኛ ቁጥር ትግራይ ላይ በመስፈሩ ብቻ ምን ያህል የክልሉን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንደጠቀመ አንድ ምሳሌ እንስጥ፡፡ የወያኔ አንድ ወታደር በቀን 8 ዳቦ ይበላል፡፡ ይህም ማለት ወደ መቶ ሽህና ከእዛም በላይ የሚቆጠረው በትግራይ ውስጥ የሰፈረው ሰራዊት በአማካይ በትንሹ በቀን 800000 ዳቦ ያስፈልገዋል ማለት ነው፡፡ በቀን ይህን ያህል ዳቦ የማቅረብ ስራ ብቻ ምን ያህል ኢንቨስትመንት የሚያስፈልገው እንደሆነ መገመት ይቻላል፡፡ ወያኔ ሰራዊቱ በሆዱ እንዳይከፋበት ካለው ፍላጎት ለምግብ ከፍተኛ ወጪ ያደርጋል፡፡ ካዳቦ ውጭም በእዚሁ በትግራይ ክልል ውስጥ ሰራዊቱን መሰረት በማድረግ የሚመረተው የተለያየ የምግብ ውጤትና ሽያጭ በገንዝብ ሲለካ በብዙ መቶ ሚሊዮኖች ብር የሚቆጠር ይሆናል፡፡
  3. ሌሎች ከቀለብ ውጭ በመደበኛ በጀት የሚገዙ አላቂና ቋሚ እቃዎች፣ የኤሌትሪክ ማሽነሪዎች ፣ የጽህፈት ዕቃዎች፣ ማንኛውም የቢሮና የመኖሪያ ቤት መገልገያ ዕቃዎችና የስልጠና መገልገያ ዕቃዎች፣ በሙሉ ከትግራይ ክልል ብቻ እንዲገዙ በመመሪያ ታዟል። ሌላው ቀርቶ ጠቅላላ የመከላከያ ወታደራዊ አገልግሎትና ሌሎች ጨርቃ ጨርቆች በሙሉ፣ ያለ ጨረታ አድዋ ከሚገኘው ከአልሜዳ ጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ብቻ እንዲገዛ ተወስኖ፣ ተግባራዊ ከሆነ ብዙ አመታት አስቆጥሯል። ይህ ሰራዊት በአመት ሁለት ግዜ የደንብ ልብሱን እንዲቀይር ከወጣው መመሪያ ጋር ተደምሮ እነአልሜዳ ምን ያህል ገንዝብ ከመከላከያ ሚኒስቴር እንደሚዘርፉ ማየት ይቻላል፡፡
  4. በኢትዮ – ኤርትራ ጦርነት ጊዜ የጦርነቱን አጋጣሚ በመጠቀም 50000 (ሃምሳ ሽህ ) የትግራይ ሚሊሻ በጦርነቱ ትሳትፏል፣ ጦርነቱ ከቀጠለም ይዋጋሉ፣ በሚል ምክንያት ሥራ ላይ ሣይገኙ በየቤታቸው ተቀምጠው፣ በመከላከያ የደሞዝ መክፈያ ሰነድ፣ ከሰኔ 1991 ጀምሮ እስከ ሰኔ 1993 ዓ.ም ድረስ በተራ በወታደር ማዕረግ በወር 500.00 (አምስት መቶ ) ብር ተክፍሏቸዋል። ይህ አሰራር መቋረጡን ማወቅ የቻልንበት ማስረጃ የለም፡፡
  5. በግንባር አካባቢ ወታደራዊ ልምምድ ሲደረግ ልምምዱ የገበሬዎች ሰብል አውድሟል፣ የግጦሽ ሳራቸውን ጎድቷል፣ አትክልታቸውን ሰባብሯል፣ በሚል ሰበብ የልተመጣጠነ ከፍተኛ ዋጋ ይከፈላል። ለምሳሌ አዲግራት ደንጎል አካባቢ፣ በሁለት ሄክታር መሬት ላይ የተዘራ ገብስ ላይ ‹‹የተወሰነ የእግረኛ ልምምድ ተደርጎበት ወደመ›› ተብሎ የግብርና ባለሙያዎች መጥተው ‹‹ከ30-40% ምርት ሊቀንስ ይችላል›› ብለው ሄዱ። ለሰዎቹ ግን የተሰጠው የካሳ ክፍያ 780000 (ሰባት መቶ ሰማኒይ ሺ) ብር ነበር። ይህ ገንዝብ ግን በሙሉ በተራው ገበሬ እጅ የገባ ሳይሆን ሰራዊቱን በዋንኛነት የሚቆጣጠሩትን የትግራይ ተወላጅ የሆኑ ከፍተኛ መኮንኖች ኪስ እንዳደለበ ይታወቃል፡፡
  6. ሠራዊቱ በትግራይ ከተሞችና ገጠሮች በብዛት ሰፍሯል። በሠፈረባቸው አካባቢዎች ሁሉ ለመኖሪያ፣ ለቢሮና ለመጋዘኖች፣ ቤቶችን በውድ ዋጋ ተከራይቶ ይጠቀማል። ሰራዊቱ በሚኖርባቸው ቤቶች፣ ካምፖች፣ በሚገለገልባቸው ቢሮዎች ውስጥ ለቤት ሰራተኛነት፣ ለጽዳት ሰራተኛነትና ለሌሎችም ስራዎች የሚቀጠረው የአካባቢው ተወላጅ ቁጥር በትግራይ የስራ አጡን ቁጥር በመቀነስ ትልቅ ሚና አለው፡፡ ሰፊ የስራ መስክ ሆኗል፡፡
  7. ሰራዊቱ በየወሩ ደሞዙን ተቀብሎ መልሶ የሚያወድመው በእዚሁ ክልል ውስጥ ስለሆነ ከሰራዊቱ የመዝናኛ ፍላጎቶች ጋር የተያያዙ ኢንዱስትሪዎች ከፍተኛ ተጠቃሚዎች የሆኑበት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ እነዚህ ደግሞ በዋንኛነት በወያኔ ወይም በወያኔ አባላት የተያዙ ናቸው፡፡
  8. ወያኔዎች የወታደሩን ነፃ ጉልበት ተጠቅመው ሠራዊቱን በአፈርን ውሃ ዕቀባ፣ በእርሻና በእርከን ሥራ በአረምና በአጨዳ ሥራ ይጠቀሙበታል።
  9. የመከላከያን የኮንስትራክሽን ማሽነሪዎችና ባለሙያዎች ክልሉ እንደፈለገ በነፃ ይጠቀምባቸዋል። ይህንን በመጠቀም በርካታ መንገዳች ተሰርተዋል። ግድቦች ተገንብተዋል።
  10. ዘረኛነትንና አድሎን በተመለከተ ደግሞ የሚከተለው በደል ይፈጸማል። ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያት የሚቀነሱ፣ በአካል መጉደል ወይም በሌሎች ምክንያቶች ሊሆን ይችላል፣ የሰራዊቱ አባላት መሃከል በዘር ላይ የተመሰረተ አድሎ ይፈጸማል፡፡

ከሌሎች ብሄረሰቦች የመጡ የሰራዊቱ አባላት የሚሰጣቸው ገንዝብ ከሚሰናበቱበት ግንባር ተነስተው ከሚኖሩበት ክልል የማያደርስ ነው፡፡ ለትግራይ ተወላጆች የሰራዊቱ ተቀናሾች ከመከላከያ ሚኒሰቴር በጀት ወጪ እየተደረገ የሚሰጠው ካሳ በአስር ሽዎች ብር የሚቆጠር ብቻ ሳይሆን፣ እነዚህ የሰራዊቱ አባላት በተለያዩ ስራዎች መቀጠል እንዲችሉ የስልጠና የብድር ሌሎችም አስፈላጊ ግብአቶች ይሟሉላቸዋል፡፡ በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ማብቂያ ከሰራዊቱ በተለያዩ ምክንያቶች የተቀነሱ የሌሎች ብሄረሰብ አባላት የተሰጣቸው ገንዝብ በግለሰብ ደረጃ ከ2000 እስከ 3000 ብር የሚደርስ ብቻ ነበር፡፡ ለትግራይ ተወላጆች ግን ከ30 እስከ 40 ሽህ ብር ነበር፡፡ ሌሎቹ ከሰራዊቱ ከተበተኑ በኋላ ምንም አይነት የመቋቋሚ ድጋፍ ያልተደረገላቸው ሲሆን የትግራይ ብሄረሰብ ለሆኑ የሰራዊቱ አባላት ግን የሚደረገው አጠቃላይ የማቋቋሚ ድጋፍ በብዙ ሚሊዮን ብሮች በሚሰላ ሃብት የተደገፈ ነው፡፡ ይህን አሳዛኝ ዘረኛ አድሎ ወያኔ የሚፈጸመው ወያኔ እንደሚለው 70 ሽህ ዜጎች ሳይሆን 98ሽ ዜጎች ትግራይ ምድር ድረስ ተጉዘው መለስ ዜናዊ ‹‹ለወላይታው ምኑ ነው›› ያለውን የአክሱም ሃውልት ምድር ለመከላከል በረገፉበት ዘግናኝ ጦርነት ማግስት ነበር፡፡ እግረ መንገዳችንን በኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት ከሞቱት መሃል አብዛኛው አማሮች ሲሆኑ ከስምንት ሽህ በላይ የሚሆኑ የአፋር ተወላጆች በእዚህ ጦርነት ውድ ህይወታቸውን መክፈላቸውን ማወቅ ችለናል፡፡ አጅግ በርካታ የሆኑ የአካል ጉዳተኞችም ያለምንም ድጋፍ በየክልሎቹ ተበትነው፤ በጦርነት የተቆረጠ እግራቸውንና እጃቸውን መለመኛ አድርገው የመከራ ኑሮአቸውን ይገፋሉ፡፡ በሰዎች መታወቂያ ላይ ሳይቀር የዜጎችን ዘር ለመጻፍ ድፍረቱ ያለው አገዛዝና በሆነ ባለሆነ ስለብሄራዊ ተዋጽኦ ዲስኩር መስጠት የሚቀናቸው የወያኔ ባለስልጣናት ለምን በየጦርነቱ አውድማ የሚማግዱተን የህዝብ ቁጥርና የሟቾቹንና የተጎጂዎችን ብሄራዊ ተዋጽኦ ሊነግሩን
እንደማይፈቅዱ ከእዚህ መረጃ መገንዘብ ይቻላል ፡፡

ለማጠቃለል፡ ወያኔ የኢትዮ – ኤርትራ ፍጥቻ እንዲቀጥል የሚያደርገው፣ አብዛኛውን የሃገሪቱን የመከላከያ ሃይል በቀላሉ ሊቆጣጠረው ከሚችልበት አካባቢ ለማስቀመጥ እድል እንደሚሰጠው ስለሚያውቅ ነው፡፡ የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ እስከቀጠለ ድረስ የሃገሪቱ መከላከያ ሃይል ቁጥሩም በጀቱም አይቀንስም፡፡ የሚሰፍረውም በትግራይ ውስጥ ይሆናል፡፡ ይሀ ማለት ከአመት አመት የመከላከያ በጀት በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ከላይ በጠቀስናቸው መንገዶች በትግራይ ክልል የሚደረገውን የልማት ስራ አጋዥ ሆኖ ይቀጥላል፡፡ ይህንን ጠባብ፣ ዘረኛና ዘራፊ የሆነ የወያኔ ቡድን ፍላጎት እስካሟላ ድረስ፣ ኢትዮጵያ ከድህነቷ ጋር የማይመጣጠን ትልቅ የመከላከያ ሃይል ተሸክማ ኖረች አልኖረች ወያኔን አያሳስበውም፡፡ ወያኔ ሌላው የኢትዮ-ኤርትራ ፍጥጫ እንዲቀጥል የሚፈልግበት ምክንያት፣ ወደፊት ወያኔ በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ሊፈጽም ላሰበው ወንጀል የመከላከያ ሃይሉን የጦር መሳሪያዎች በቀላሉ መጠቀሚያ ለማድርግ በሚያመች ቦታ ማከማቸት ስላስቻለው ነው፡፡ ዛሬ የሃገሪቱ የመከላከያ ሃይል፣ አየር ሃይሉ በሙሉ፣ ሜካናይዝድ ብርጌዱ ከነዘመናዊ ታንኮቹና መድፎቹ፣ በሰራዊት ውስጥ አለ የተባለው ሌላ ዘመናዊ መሳሪያ በሙሉ የሚገኘው በትግራይ ክልል ነው፡፡

በወያኔ የፖለቲካ ስሌት ውስጥ የኢትዮጵያ ህዝብ በወያኔ ዘረኛነትና ዘራፊነት ላይ ተንገፍግፎ ከተነሳ ትግራይን ከነሙሉ የሃይል ማመንጫዎቿ፣ በኤፈርት ዘረፋ ከተሰባሰበው ታላቅ የገንዝብ ካፒታል ጋር፣ በኤርትራ ፍጥጫ ስም በክልሏ ወያኔ እንዲከማች ካደረገው የሃገሪቱ ወታደራዊ ድርጅትና ዘመናዊ የተሟላ የጦር መሳሪያ ጋር፣ በዘር አድሎ ላይ በተመሰረተ የሃገር ውስጥና የውጭ ትምህርትና የሙያ ስልጠና ሲሰጣቸው ከኖሩት የጦርና የሲቪል ሙያተኞች ጋር ከኢትዮጵያ ገንጥሎ፣ እነመለስ ዜናዊ የነገሱባት ነጻ የትግራይ ሪፑብሊክ ለማወጅ ይቻላል የሚል ስሌት ጨምሮ እንደሆነ መረዳት ይገባል፡፡ ወያኔ ከሌሎች ብሄርና ብሄረሰብ የመጡትን የሰራዊት አባላት ከትግራይ አባሮ የሃገሪቱን መከላከያ ሃይል ሙሉ በሙሉ ይዞ ያለምንም መከላከያ ሃይልና መሳሪያ ባዶውን የቀረውን የኢትዮጵያ ህዝብ እንዳሻው እያስፈራራና እያሸበረ በነጻይቱ ትግራይ ላይ ተረገጋቶ የመኖር ተለዋጭ እቅድ ያለው ዘረኛ አገዛዝ መሆኑን መላ የኢትዮጵያ ህዝብ በግዜ ማወቅ የሚገባው ጉዳይ ነው፡፡

The post የወያኔ የመከላከያ ከፍተኛ በጀት appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ 2007 እና የእስቴት ዲፓርትመንት የፖሊሲ ዉዝዋዜ –የሳዲቅ አህመድ ምርጥ ትንታኔ

ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት በገዢው መንግስት እንዲቃጠል ተደረገ

$
0
0

የኢህአዴግ ባለስልጣኖች ቦንጋ አካባቢ የነበረ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት እንዲቃጠል ማድረጋቸውን የትህዴን ድምጽ ዘገበ::
Zehabesha News
የትህዴን ምንጭ የዜና ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው በደቡብ ክልል ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ ሰፊ የተፈጥሮ ጫካ በአካባቢው ህዝብ ለዘመናት ጠብቆት የኖረ ሃብት ሲሆን የገዢውን ስርአት በመቃወም እየታገሉ ያሉት ተቃዋሚዎች የሚንቀሳቀሱበት አካባቢ ነው ብለው ስጋት ላይ የወደቁት የስርአቱ ካድሬዎች እሳት ለኩሰው እንዲቃጠል ማድረጋቸውና ይህን እኩይ ተግባር የታዘበው የአካካባቢው ህዝብም በስርአቱ ላይ ጠንካራ ተቃውሞ እንዳስነሳ ለማወቅ ተችሏል።

የአካባቢው ህዝብ እየተቃዎመ በነበረበት ሰዓት እንደገለፀው በአፋችሁ ልማት አልሙ፤ ድህነት አጥፉ እያላችሁ በተግባር ግን መተኪያ የሌላቸውን የተፈጥሮ ሃብቶችን እያቃጠላችሁ ነው በማለት ሃይለኛ ተቃውሞ ማንሳታቸውን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

The post ቦንጋ አካባቢ የሚገኝ የተፈጥሮ ጫካ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየተንቀሳቀሱበት ነው በሚል ምክንያት በገዢው መንግስት እንዲቃጠል ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

(የሳዑዲ ጉዳይ) ስራቸውን እየሰሩ ነው፣ እኛ ተዘናግተናል ! * በሳውዲ እስር ቤት የኢትዮጵያውያን መልዕክት

Next: Hiber Radio: የኦጋዴን ነጻ አውጭ ስድስት የአገዛዙን ልዩ ሀይል አባላት መማረኩ፣ጠፍቷል የተባለው የአሜሪካ አየር ሀይል ባልደረባ የሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከአገር ቤት ሲመጣ እጁን ለፖሊስ ሰጠ፣ ዶ/ር መረራ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ፣ ሳውዲ አረቢያ የሐጂ ተጓዦችን አዲስ የመቆጣጠሪያ ብራስሌት እንዲያደርጉ ልታስገድድ ነው፣ አቶ ማሙሸት መስቀል አደባባይ አመጽ አስነስተዋል በተባሉበት ዕለት ፍ/ቤት እንደነበሩ አስመሰከሩ፣የምርጫ ታዛቢዎች ላይ የተጀመረው እስር ቀጥሏል፣ የሼህ ካሊድ፣የብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ እና የአክቲቪስት ታማኝ በየነ ንግግር እና ሌሎችም
$
0
0

ነቢዩ ሲራክ

በሳውዲ ጅዳ ሪያድና በተለያዩ ከተሞች ህገ ወጥ የተባሉትን የውጭ ዜጎች የማጥራቱ ዘመቻ ደመቅ ብሎ ባይሰማም በሂደት ላይ ነው ። በያዝነው ሳምንት ጅዳ ውስጥ በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው በተለያዩ የከተማዋ ክፍሎች በተደረገ ፍተሻ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ህጋዊ መኖርያ ፍቃድ ያላቸው እህቶችና ወንድሞች ቤት ለቤት በሚደረገው አሰሳ ተይዘዋል ።
nebyu sirak
በአሰሳ ፍተሻው ተይዘው በወህኒ የሚገኙት እንዳደረ ሱኝ መረጃ ከሆነ አያያዛቸው መኖርያ ፈቃድ ከሌላቸው ጋር በመገኘታቸውን ጨምሮ በአንድ ህንጻ ውስጥ ህገወጦች ተገኙ ተብሎና ሌላም ሌላ ምክንያቶች የተሰጣቸውን መሆኑን መረጃ አድርሰውኛል። በተለይም ህጋዎ መኖርያ ፍቃድ እያላቸው ከነ ልጅ ቤተሰቦቻቸው የተያዙት ወገኖች ቢቻል የመንግስት ተወካዮች ጉዳዩን ከአሰሪዎቻቸውና ከሳውዲ መንግስት ሃላፊዎች ጋር ተነጋግረው በዋስ እንዲዎጡ እንዲረዷቸው ተማጽነዋል !

እኒህ ወገኖች እያለቀሱ ባስተላለፉት መልዕክት እንዲህ የሚል ይገኝበታል …” … የረባ ልብስ ሳንለብስ ቤተ ተሰብሮ ተይዘን ፣ በባዷችን ወደ ሀገር ግቡ እየተባልን ነው ! ለአመ ታት የሰበሰብነውን ቁሳቁስ ፣ ሀብት ንብረት ሳንሰበስብ ቤተሰቦቻችን በትነን ወደ ሀገር መሸኘት የለብንም ፣ የኢትዮ ጵያ መንግስት ተወካዮች ከአሰሪዎቻችንና ከመንግስት ጋር ተነጋግረው ያስፈቱን ፣ ማስፈታት ካልቻሉ ንብረታችን ሰብስበን የምንሄድበት መንገድ መንግስታችን ያመቻችልን ዘንድ ድምጻችን አሰማልን !” ብለውኛል ! መልዕክቱ ለሚመለከታችሁ ሁሉ ይድረስ !
እነሱ ስራቸውን እየሰሩ ነው ፣ አቁሙ አይባሉም ፣ እነማን እንደሆኑ እያወቅን ፍን ደጋግመን ተዘናጋን ! … ደጋግመን አበሳን ለመክፈል ተገደድን ፣ እንጠንቀቅ ፣ ከመጭው አደጋ ለመዳን !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ግንቦት 23 ቀን 2007 ዓም

The post (የሳዑዲ ጉዳይ) ስራቸውን እየሰሩ ነው፣ እኛ ተዘናግተናል ! * በሳውዲ እስር ቤት የኢትዮጵያውያን መልዕክት appeared first on Zehabesha Amharic.


Hiber Radio: የኦጋዴን ነጻ አውጭ ስድስት የአገዛዙን ልዩ ሀይል አባላት መማረኩ፣ጠፍቷል የተባለው የአሜሪካ አየር ሀይል ባልደረባ የሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከአገር ቤት ሲመጣ እጁን ለፖሊስ ሰጠ፣ ዶ/ር መረራ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ፣ ሳውዲ አረቢያ የሐጂ ተጓዦችን አዲስ የመቆጣጠሪያ ብራስሌት እንዲያደርጉ ልታስገድድ ነው፣ አቶ ማሙሸት መስቀል አደባባይ አመጽ አስነስተዋል በተባሉበት ዕለት ፍ/ቤት እንደነበሩ አስመሰከሩ፣የምርጫ ታዛቢዎች ላይ የተጀመረው እስር ቀጥሏል፣ የሼህ ካሊድ፣የብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ እና የአክቲቪስት ታማኝ በየነ ንግግር እና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የግንቦት 23 ቀን 2007 ፕሮግራም

< …የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ከሃያና ሰላሳመት በሁዋላ በሚኖር አጀንዳ አሁን ከሚለያዩ መጀመሪያ ዲሞክራሲያዊ ለውጥ ለማምጣት በጋራ ይቁሙ ሌላው በጊዜው…አንተ ሰሜን አሜሪካ ተቀምጠህ የትጥቅ ትግል ካልሆነ አያዋጣም ብትለኝ …ሁሉም የሚችለውን ይስራ … >

ዶ/ር መረራ ጉዲና የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የኦፌዲን ሊቀመንበር ተቃዋሚዎች ከተዘረፈው ምርጫ ማግስት ስለሚኖራቸው ሚና ከህብር ሬዲዮ ጋር ያደረጉት ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…እዚህ የተቀመጡትን ሼህ ካሊድንና አቡነ መቃሪዮስን አንድ ላይ ቢያይ ኢቲቪ ሽብር ሊፈጥሩ ተሰበሰቡ ይል ነበር …>

አክቲቪስት ታማኝ በየነ በቬጋስ ካደረገው ንግግር የተወሰደ( ያዳምጡት)

<…ሚዲያ የአንድ ፖለቲካ ፓርቲ ልሳን ከሆነ የሕዝብን ጉዳይ ይረሳል ። ሚዲያ ገለልተኛ መሆን ነው ያለበት…>

ሼህ ካሊድ የፈርሰት ሒጅራ ኢማም በቬጋስ ለኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ተገኝተው ከተናገሩት

<…እነዚህ ሰው የሚያርዱት በሙስሊሞች ስም የሚጠሩ እንጂ ሙስሊም እንደዚህ አያደርግም። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ናቸው …የአገራችን አይ.ሲ.ስ ወያኔ ራሱ ነው…> ብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ በቬጋስ ተገኝተው ከተናገሩት (ሙሉውን ያዳምጡት)

የፊፋ ባለስልጣናት የሙስና ቅሌት ፣ የአሜሪካና የአውሮፓ በፊፋ ጉዳይ ጣልጋ ማስገባት ለምን ፈለጉ ?(ልዩ ጥንቅር)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

ትውደ ኢትዮጵያዊው የአሜሪካ አየር ሀይል ባልደረባ ጠፍቶ ሲመጣ ለጸጥታ ሰዎች እጁን ሰጠ

ዶ/ር መራራ ጉዲና ትግላችን ይቀጥላል አሉ

ተቃዋሚዎች የዛሬ 30 እና 40 ዓመት አጀንዳቸውን ወደ ጎን አድርገው ተባብረው መታገል አለባቸው ብለዋል

የአፍሪካ ህብረት ታዛቢዎችን አጣጣሉ

የሕዝብ ድምፅ ይከበር ያሉ ከ6 መቶ በላይ የመድረክ ጠንካራ አባሎችና ታዛቢዎች ታስረዋል

በኢትዮ ሶማሊያ ድንበር ኦብነግ 6 ታጣቂዎችን ማረኩ አለ

አቶ ማሙሸት መስቀል አደባባይ ሕዝብ አሳመጹ በተባለው እለት ምርጫ ቦርድን ከሰው ፍ/ቤት እንደነበሩ አስመሰከሩ

የሳውዲ መንግስት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ለሐጂ ወደ አገሪቱ የሚገቡ አዲስ የኤሌክትሮኒክስ ብራስሌት እንዲያጠልቁ ለማስገደድ በዝግጅት ላይ መሆኑ ተነገረ

ሁበር በቬጋስ ከወር በኋላ ሥራ እጀምራለሁ አለ

በኢትዮ ሶማሊያ ድንበር አገዛዙ ሠራዊትና በአካባቢው ተወላጆች መካከል በተፈጠረው ግጭት በርካቶች ጉዳት ደረሰባቸው

የአገዛዙ ወታደሮች ጉዳት የደረሰባቸውን ወጣቶች ህክምና እንዲያገኙ ከለከሉ

የሚሉና ሌሎችም ዜናዎች አሉን

The post Hiber Radio: የኦጋዴን ነጻ አውጭ ስድስት የአገዛዙን ልዩ ሀይል አባላት መማረኩ፣ጠፍቷል የተባለው የአሜሪካ አየር ሀይል ባልደረባ የሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከአገር ቤት ሲመጣ እጁን ለፖሊስ ሰጠ፣ ዶ/ር መረራ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ፣ ሳውዲ አረቢያ የሐጂ ተጓዦችን አዲስ የመቆጣጠሪያ ብራስሌት እንዲያደርጉ ልታስገድድ ነው፣ አቶ ማሙሸት መስቀል አደባባይ አመጽ አስነስተዋል በተባሉበት ዕለት ፍ/ቤት እንደነበሩ አስመሰከሩ፣የምርጫ ታዛቢዎች ላይ የተጀመረው እስር ቀጥሏል፣ የሼህ ካሊድ፣የብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ እና የአክቲቪስት ታማኝ በየነ ንግግር እና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የጋራ አቋም መግለጫ

Previous: Hiber Radio: የኦጋዴን ነጻ አውጭ ስድስት የአገዛዙን ልዩ ሀይል አባላት መማረኩ፣ጠፍቷል የተባለው የአሜሪካ አየር ሀይል ባልደረባ የሆነው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ከአገር ቤት ሲመጣ እጁን ለፖሊስ ሰጠ፣ ዶ/ር መረራ ትግላችንን እንቀጥላለን አሉ፣ ሳውዲ አረቢያ የሐጂ ተጓዦችን አዲስ የመቆጣጠሪያ ብራስሌት እንዲያደርጉ ልታስገድድ ነው፣ አቶ ማሙሸት መስቀል አደባባይ አመጽ አስነስተዋል በተባሉበት ዕለት ፍ/ቤት እንደነበሩ አስመሰከሩ፣የምርጫ ታዛቢዎች ላይ የተጀመረው እስር ቀጥሏል፣ የሼህ ካሊድ፣የብጹዕ አቡነ መቃሪዮስ እና የአክቲቪስት ታማኝ በየነ ንግግር እና ሌሎችም
$
0
0

eotc-ssd-4th-gen-assembly-participantsበሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እና ብሔራዊት ቤተ ክርስቲያናችን ህልውና እና ዕድገት ፊት ከተጋረጡትና አፋጣኝ እልባት ከሚሹት የዘመናችን የውስጥ ችግሮች እና የውጭ ተግዳሮቶች ውስጥ ሙስና እና ኑፋቄ ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡ አንዱ የሌላው መተላለፊያ፣ መንሥኤ እና ውጤት እየኾኑ ለቤተ ክርስቲያን ተቋማዊ ለውጥ የተደረጉ ጥረቶችን ሲያመክኑ፤ የመዋቅር እና የአደረጃጀት አቅሟን ሲያዳክሙ ቆይተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት የሚያዝያ ፳፯ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. መግለጫ እንደተመለከተው፣ በቅዱስ ሲኖዶስ ተወግዘው ከተለዩ በኋላ በቅጥር ወደ አስተዳደራዊ እና የአገልግሎት መዋቅሯ የገቡ የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን መኖራቸው ሙስና እና ኑፋቄ የተሳሰሩ እና የሚመጋገቡ ለመኾናቸው ግልጽ አስረጅ ነው፡፡

ከግንቦት ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. በጠቅላይ ቤተ ክህነት የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሔድ ቆይቶ ለጽርሐ መንበረ ፓትርያርኩ አርዕድ አንቀጥቅጥ በኾኑ፤ መልካም አስተዳደር እና ፍትሐዊ ፍርድ በሚጠይቁ መዝሙሮች ትላንት ማምሻውን የተጠናቀቀው ፬ኛው ዓመታዊ ሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ፣ በጋራ አቋም መግለጫዎቹ በቀጥታ ይኹን በአማራጭ ያረጋገጠውም ይህንኑ እውነታ ነው፡፡

* * *


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት

ብፁዕ አቡነ ሉቃስ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ እና የሰቲት ሑመራ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ እና የወላይታ ኮንታ እና ዳውሮ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዕ አቡነ ቀሌምንጦስ የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ የበላይ ሓላፊ ሊቀ ጳጳስ፣ በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የፓትርያርኩ እንደራሴ ሊቀ ጳጳስ፣ የጉራጌ ስልጤ ከምባታ እና ሐዲያ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት
የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች
ከተለያዩ አካላት ጥሪ የተደረገላችኹ የክብር እንግዶች፤

እኛ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤያትን ወክለን በ፬ኛው የሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት አጠቃላይ ጉባኤ ላይ የተሳተፍን የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ አባላት ከግንቦት ፳፩ – ፳፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ላለፉት ሦስት ቀናት÷ የማደራጃ መምሪያው ዓመታዊ የአገልግሎት ዘገባ፤ ከ37 አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት እና የሰንበት ት/ቤቶች ዋና ክፍሎች ሪፖርቶች፤ የሰንበት ት/ቤቶች አባላት በኾኑ ባለሞያዎች በቀረቡ ጥናታዊ ጽሑፎች ላይ ሰፊ ውይይት አድርገናል፡፡

በመምሪያው ዘገባም ኾነ ከ37 አህጉረ ስብከት የመጡ ተወካዮች ያቀረቡት ሪፖርት ሰንበት ት/ቤቶች እጅግ በርካታ ተግባራት እያከናወኑና የቤተ ክርስቲያንን ተልእኮ ለማፋጠን እየተጉ መኾኑን አስገንዝቧል፡፡ ኾኖም ግን በየአህጉረ ስብከቱ የሚታዩ፡-

  • የመናፍቃን እና የአፅራረ ቤተ ክርስቲያን ተጽዕኖ፤
  • በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን እየደረሱ ያሉ የአስተዳደር በደሎች፤
  • የበጀት እና የመምህራን እጥረት፣ የአዳራሽ እጥረት፤
  • የአንዳንድ አህጉረ ስብከት ስፋት ለትራንስፖርት አመቺ አለመኾን፤

አገልግሎቱን እየተገዳደሩ ያሉ ዋና ዋና ችግሮች ኾነው ተዘግበዋል፡፡

‹‹የሰው ኃይል አያያዝ በሰንበት ት/ቤት›› በሚለው ጥናታዊ ጽሑፍ መነሻነት በተደረገው ውይይትም ለቤተ ክርስቲያን ኹለንተናዊ ዕድገት ወሳኝ የኾነው የሰው ኃይል መኾኑን በማመን የቤተ ክርስቲያን አካላት በሙሉ በተለይም ሰንበት ት/ቤቶች ትኩረት ሰጥተን ልንሠራበት እንደሚገባ ተገንዝበናል፡፡ በማያያዝም ‹‹የኢኮኖሚ ግንባታ ለቤተ ክርስቲያን›› በሚለውም ጥናት፣ የኢኮኖሚ አቅም ማነስ÷ የመጠቀምን፣ የመደመጥን፣ የመወሰንን፣ የመተግበርን አቅም ያሳጣል፤ በሌላ በኩል እምነትን ይፈትናል፤ ሥጋዊውን ጥቅም ለማሳካት ሲባል ከቤተ ክርስቲያን መለየትን ያመጣል፤ ብዙ ተባዙ ምድርንም ምሏት ያለውን የእግዚአብሔር ቃል ያስጥሳል፤ ወጣቱንም ለስደት እና ለመከራ እየዳረገ ይገኛል፤ የቤተ ክርስቲያን ተልእኮም እንዳይፋጠን ያደርጋል፡፡

ስለዚኽ ቤተ ክርስቲያን ያላትን ሀብት በአግባቡ በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ አቅሟን ልታጠናክር፤ ተሰሚነቷን ልታስከበር ይገባታል፤ ሰንበት ት/ቤቶችም የኢኮኖሚ አቅማቸውን ለማጠናከር የሚያስችሉ ተግባራት ሊሠሩ፤ የቤተ ክርስቲያን መምሪያዎችም ሊያግዟቸው እንደሚገባ ውይይቱ ትኩረት ሰጥቶበታል፡፡

በመጨረሻም በሪፖርቱም ኾነ በጥናታዊ ጽሑፎች የተጠቀሱትን ዋና ዋና ችግሮች በመለየት በተደረገ የቡድን ውይይት ሰንበት ት/ቤት በቀጣይነት በጋራ የምንሠራቸውን እና የምንስማማባቸውን የአቋም መግለጫዎች አውጥተናል፡፡

  1. የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ከ2006 – 2010 ዓ.ም. የታቀደውን የአምስት ዓመት መሪ ዕቅድ በቀሩት ጊዜያት ለመፈጸም እና ለማስፈጸም ቃል እንገባለን፤
  2. የሰንበት ት/ቤቶች አጠቃላይ መሪ ዕቅድ የኹሉም የአጥቢያ ሰበካ መንፈሳውን ጉባኤያት ዕቅድ አካል እንዲኾን እና የጠቅላይ ቤተ ክህነት መምሪያዎችም ኹሉ መሪ ዕቅዱን ከዕቅዳቸው ጋራ በማገናዘብ እንዲያካትቱ ይደረግ ዘንድ እንጠይቃለን፤
  3. መልክአ ምድርን መሠረት ያደረገ የሰንበት ት/ቤቶች ትስስር በማጠናከር ሰንበት ት/ቤቶች ባልተቋቋሙባቸው አጥቢያዎች እንዲቋቋሙ፣ በተቋቋሙባቸው ደግሞ የተጠናከረ አገልግሎት እንዲሰጥባቸው ለማድረግ እንሠራለን፤
  4. የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ ኑፋቄ ችግሮችን ለማጋለጥ ያስችል ዘንድ ከሀገር አቀፍ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጀምሮ እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ሰንበት ት/ቤት የሚደርስ መረጃ የማሰባሰብ ሥርዐት በመዘርጋት የመረጃ ማሰባሰቡን አጠናክረን እንሠራለን፤
  5. በአኹኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያን ተልእኮ አፈጻጸም ላይ ተጽዕኖ እየፈጠረ ያለው የፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃንን እንቅሰቃሴ ለማስቆም ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ በየደረጃው ያሉ የቤተ ክርስቲያን አካላት አፋጣኝ ርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፤
  6. ቀደም ሲል በአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ስለ ፕሮቴስታንታዊ ተሐድሶ መናፍቃን የቀረበው ማስረጃ ውሳኔ እንዲሰጠው፤ ውሳኔውም ተግባራዊ ይኾን ዘንድ ከቅዱስ ሲኖዶስ ጀምሮ ያሉ የቤተ ክርስቲያን አካላት አስፈላጊውን ርምጃ እንዲወስዱ እንጠይቃለን፤
  7. በአኹኑ ጊዜ አንዳንድ የቤተ ክርስቲያን ሓላፊዎች በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች እና አባላት ላይ በተሳሳተ አመክንዮ እያደረሱት ያለው እስር፣ እንግልት እና ወከባ እንዲቆምልን በአጽንዖት እንጠይቃለን፤
  8. ከዚኽ ጋር ተያይዞ የመንግሥት የፍትሕ አካላትም ከአጥፊዎች ጋር በመተባበር የሰንበት ት/ቤት አባላትን ከማሰር እና ከማንገላታት እንዲታቀቡ ይደረግ ዘንድ እንጠይቃለን፤
  9. በቃለ ዐዋዲው እና በ1986 ዓ.ም. ሕገ ደንቡ ላይ የተጠቀሰው የሰንበት ት/ቤቶች የዕድሜ ገደብ እንዲነሣልን በድጋሜ እንጠይቃለን፤
  10. ከሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ አንሥቶ እስከ አጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች የሚደርስ የፋይናንስ ትስስር እና አያያዝ ሥርዐት በመምሪያው በኩል ተጠንቶ እንዲጸድቅልን እንጠይቃለን፤
  11. የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግል ጥቅማቸው በማዋል የቤተ ክርስቲያንን አቅም የሚያዳክሙ አማሳኞች ማስረጃ ተጠናቅሮ በአገሪቱ ሕግ መሠረት እንዲጠየቁልን እንጠይቃለን፤
  12. የቤተ ክርስቲያን የፋይናንስ አሠራር ማእከላዊ እንዲኾን እና በባለሞያዎች የሚታገዝ የክትትል እና የቁጥጥር ሥርዐት እንዲኖረው እንጠይቃለን፤
  13. በዘመናችን ሚዲያ በወጣቱ እና በሕፃናት አስተዳደግ ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እየፈጠረ ስለሚገኝ የቤተ ክርስቲያንን አስተምህሮ በስፋት ለምእመናን ለማዳረስ እንዲቻል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሚመራ እና የሚተዳደር፤ ቤተ ክርስቲያኒቷንም የሚወክል የቴሌቪዥን መርሐ ግብር እንዲጀመር በአጽንዖት እንጠይቃለን፤
  14. በአኹኑ ሰዓት በቤተ ክርስቲያን ስም ቤተ ክርስቲያንን የማይወክል ትምህርት እና መልእክት የሚያስተላልፉ የቴሌቪዥን መርሐ ግብሮች በተቻለ ፍጥነት እንዲዘጉ አልያም በቤተ ክርስቲያን ስም ከመጠራት እና ከመጠቀም እንዲከለከሉ እንጠይቃለን፤
  15. ለጠቅላላ ጉባኤው ተወካዮቻቸውን ያልላኩ አህጉረ ስብከት ተለይተው በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የማያዳግም ርምጃ እንዲወሰድባቸው እንጠይቃለን፤
  16. በቤተ ክርስቲያናችን መንፈሳዊ እና ልማታዊ ጉዳዮች ከአባቶቻችን ጋር በመኾን ያለንን አቅም አሟጠን በመጠቀም ለቤተ ክርስቲያን ዕድገት እና ልዕልና የበኩላችንን ድርሻ እንወጣለን፤
  17. የቤተ ክርስቲያናችንን ኹለንተናዊ ችግር ለመፍታት ከመንፈሳዊ ኰሌጅ ምሩቃን(ቴዎሎጅያን) ጋር ተባብረን የምንሠራ መኾናችንን እንገልጻለን፤
  18. የአዲስ አበባ ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ያቀረበው ጥያቄ የኹላችንም አቋም ስለኾነ አፋጣኝ መልስ እንዲሰጠው እንጠይቃለን፡፡

ግንቦት ፳፫ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም.

Source:: haratewahido

The post ፬ኛው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ሰንበት ት/ቤቶች አንድነት ጠቅላላ ጉባኤ የጋራ አቋም መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፈጣን ሩጫ አይሉት ማራቶን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ –የተርጓሚው ማስታወሻ

$
0
0

ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ

ይህ ጽሁፍ ዘኢኮኖሚስት ከሚያወጣቸው ኁሉ ብናየውና ብንወያይበት ይጠቅማል በሚል አሳብ ተተርጉሞ ቀርቧል።እራሱን ሳንሱር እያደረገ እንደጻፈው ማየት አያስቸግርም። ከዚህ ትርጉም እንደምታዩት ምዕራብ፡ ምስራቁ ህወሀት መሩ መንግስት ተብዬ ላይ ሁሉም ተስፋ መቁረጡን በግልጥ ያሳያል። የቻይና አምባሳዶር  እቅጩን ይናገራል።ያፈርጠዋል። እዲያው አበዛችሁት ዓይነት ነው።በቻይና የምጣኔ ሃብት ግንባታው ሊሰራ የቻለው የቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ የህዝቡን ድጋፍ  ይዞ ነው።ዛሬ ወያኔ ከህዝብ ተገልሎ ፈርቶ አደር  ሆኖ እያነከሰ ነው።ህወሀቶች ቻይና መልሳ ካፒታሊዝምን ተማሩ የምትላቸው ከጊዜው ጋር መራመድ የማይችሉ፤መለስ ከሞተ ወዲያ እንኳን የሰራውን ጥፋት ማየት ያልቻሉ ትቷቸው እንደሄደ ተገትረው የቀሩ ጉዶች ናቸው።ዘኢኮኖሚስት ከመለስ ሞት በኋላ በሰላም በመንግስትነት ተሸጋገሩ ይላል ሌላ ሊሆን እንደሚችል ሁሉ።ዛሬ እየሆነ ያለውን፤የምርጫውን ቧልት፤በሰሜን ኢትዮጵያ ወያኔን ስለሚያጫንቀው ሁኔታ አይተነፍስም።ወያኔ ላይ ያንጃበበው ዳመናም አይታየውም ወይም አይቶት አይናገርም።ለኛ ገሀድ የሆነውን።

የውጭ ተንታኝ ይሳሳታል።እኛ ወያኔ ይወድቃል ህዝብ ተመሯል አይሰነብትም ስንል።በኢትዮጵያ ወያኔን ቀጣይ አድርጎ ያያል። ወያኔዎች ዙሪያው ገደል ሆኖባቸው፤እርስ በርስ እየተወነጃጀሉ ለመሆናቸው ምልክቶች እየታዩ ነው። ወያኔ ዳሩ እየላላበት ነው። መሃሉም ረመጥ እሳት ይሆንበታል። በመጣበት ዘዴ ሊሸኝ። ትርጉሙ እነሆ።

ከቢላል አበጋዝ፡ ዋሽግቶን ዲ፡ሲ

 

ፈጣን ሩጫ አይሉት ማራቶን_ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ

ይህ ጽሁፍ ዘ ኢኮኖሚስት May 30th 2015 ያወጣው ጽሁፍ ትርጉም ነው።

ከመላው አፍሪካ በሙሉ እንደ ኢትዮጵያ አድርጎ ቻይና እንደ መራሄ ኮከብ፤ዋና ምሳሌ ተደርጋ የምትወሰድበት የለም።ይሄው ኢትዮጵያ በሜይ 24 እዚህ ግባ የማይባል ውጤቱ ቀድሞ የታወቀ፤ምርጫ አካሂዳለች።ያው ለነባሩ ፓርቲ አዲስ አገዛዝ ዘመን የሚለግስ።ከአሃጉሩ በህዝብ ብዛት ሁለተኛ፤በፍጥነት ታዳጊ ኢኮኖሚ ያላት  ኢትዮጵያ ከኮሚኒስት ቻይና ጋር የጠበቀ የአስተሳሰብ ዝምድና አላት።የኢትዮጵያም ባለስልጣናቶችዋን  ወደ ቻይና የፓርቲ ትምርት ቤት ትልካለች።ኢትዮጵያኑ በቻይና ኢንዱስትሪ የማስፋፋትን ወንጌልን፤እንዲዋሀዱና ጠንካራ ማከላዊ የማያላውስ ጨቌኝ መንግስትን ባለብዙ ዘውጎች ያውም ያለመስማማትም ታሪክ ያላቸላቸው ህዝቦችን ስለመግዛት፡ያጠናሉ።

234

ዛሬ ከቻይና ጋር ሁሉም አልጋባልጋ አይደለም። አዲሱ የቻይና አምባሳዶር ያለፈው ፌብሩአሪ አዲስ አበባ ሲደርሱ ለወዳጆቻቸው ያልታሰበ አጉል መልዕክት አድርሰዋል። አምባሳደር ሊ ፋን በዝግ ችሎት የወያኔን ባለስልጣናትን ያለፈው ብቸኝነትን ትታችሁ፤ኢኮኖሚያችሁን ለውድድር ክፈቱት ብለዋል።ንዋይም ዜናም በማዕቀብ መያዙን እያመልከቱ።ባንክና ቴሌ አሰራራቸው የዘመነ ሎጥ ነው።ነጋዴዎች ተመረዋል።ንግድ ወደ ኋላ ቀርቷል።ላመታት ወያኔን ሲያመሰግኑ የኖሩት ቻይኖች ዛሬ ልክ እንደምእራብያውያን ተችዎች ሁሉ ያማርራሉ።

  [ሰንጠረጁ የሚያሳየው የኢትዮጵያን በኢንተርኔትና ቴሌ እጅግ ኋላ መቅረትን ነው።]እአአ 2013 የተቀናበረ ሪፖርት የተወሰደ ከመቶ ሰዎች ምን ያህሉ ግለጋሎት ያገኛሉ በሚል የተጠና።

___________________

የችግሩ መሰረት ድፍረት የለም።በኢትዮጵያ መንግስት ውስጥ ያሉ፤የገዥው ፓርቲ አባላት የጸጥታ ተቋሙን የሚቆጣጠሩትም መሻሻሎችን ማድረግ ብቻ የኢኮኖሚ እድገትና የፖለቲካ መረጋጋትን እንደሚያመጡ ያምናሉ። ሊተገብሩአቸው ግን  ቀርፋፎች ናቸው።

የመንግስቱ ቀዳማይ ፍላጎት ኢንዱስትሪን ማስፋፋት ነው።ነገር ግን ነጋዴዎች በቢሮክራሲ ተተብትበው ከንዋይም ማንቀሳቀስ ታግተዋል።ባለስልጣናት ሁዋጅያንን ያመለክታሉ።ሁዋጅያንን የቻይና በኢትዮጵያ የጫማ ፋብሪካ ነው።በጥቂት አመታት የሰራተኛን  ቁጥርን ከ600 መቶ ወደ 3 ሺ 600 ያደረሰ ነው።ኢትዮጵያ ታዲያ መቶዎች ሁዋጅያንን ትፈልጋለች። ኢንዱስትሪ ሳይስፋፋ 80 % ግብርናን ከማሻሻል በኋላ የሚተርፈውን የሰው ሀይል የምታደርስበት መኖር አለበት።

መንግስት ኢንዱስትሪ መስፋፋትን ለመርዳት መንገጎች ይሰራል፤ባቡር ሃዲዶች ይዘረጋል፤የሀይል ማመንጭያ ጣቢያዎችን፤ግድቦችን ልክ ቻይና እዳረገችው ቅጅውን ይተገብራል።እኒህ ተግባሮች በኦፊሴል የሚታወቀውን የአስር እጅ የኢኮኖሚ ዕድገት አስከትለዋል።ምንም እንኳ ዕድገቱ ሰባትና ስምንት እጅ ነው ተብሎ በውጭ ጠበብት ቢነገርም።የዋጋ ግሽበት ወደ አንድ አሃዝ ወርዷል።ሆኖም ባለፉት ሶስት ዓመታት የዓለም  የንግድ ድርጅቶችን ለመቀላቀል የሚደረግ ጥረት የለም።ስራ የሚያንቀሳቅስ የውጭ ካፒታል መገኘቱ አስተማማኝ አይደለም።

ያለው መንግስት ቁንጮዎች መንግስታችን ይገለበጣል የሚል ስጋት ለውጦችን ከመግፋት ችላ እንዲሉ አድርጓል።በአንድ በኩል ሲያስቡት የመልካም ውጤታቸው ሰለባ የሆኑ ይመስላል።ዲሲፕሊንና አስተዳደራዊ ረቂቅነት ላለው መንግስት ቁንጮዎች መጨቆኛ መሳሪያዎችን በጃቸው እንዲሆኑ አድርጓል።ይህ ደግሞ በአሃጉሪቱ ያሉ መሰል ጨቋኞቸ ሊመኙት ብቻ የሚችሉት ነወ። አሁን ያለው መንግስት ቁንጮዎች ካልዘረጉት የጭቆና መረብ ተለይተው ለመኖር አይታሰባቸውም።

ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከ1974 እስከ 1991 እአአ ከነበረው የስበስ ጦርነት በኋላ አገሪቱን ያደሳት መሃንዲስ በ2012 እአአ ከሞተ ወዲህ ሁኔታው እየባሰ መጣ እንጄ የተሻለ ነገር አልሆነም።መለስ በባህሪው ብርታት፤የአእምሮ ችሎታውና በጦርነት ጊዜ ባፈራቸው ጥብቅ ወዳጅነቶች መሰረት የመንግስቱን ወደፊት እንዲሄድ ያደርገው ነበር።እርግጥ ነው የንግዱ ክፍልና ህዝባዊ ድርጅቶችን ይጠላ ነበር።ቢያስ ግን ጋሬጣ የሆኑ ጉዳዮችን ያስወግድ ነበር።ከሞቱ በኋላ መንግስቱ በሰላም ሽግግር አድርጓል።ረዳትጠ/ሚኒስትሩ እንደታቀደው ስልጣን ይዟል።

አሁን ያለው አመራር የስብስብ ነው።አዲሱ ረዳትጠ/ሚኒስትር መለስ አይደለም።መለስ አንዱ መታሰቢያው የተከፋፈለውን ድርጅት መከፋፈሉን መደበቅ ነበር። ዛሬ ሚኒስትሮች ውሳኔ ከማድረግ በፊት የነባር አመራርን ፈቃድ ማግኘት አለባቸው።የትግራይ ተወላጆች መለስ ወገናቸው የሆኑት ጦሩን፤ጸጥታውን፤ ቴሌን፤የውጭ ጉዳይን ይቆጣጠራሉ።እነርሱ ጡረታ እስቲወጡ ወይ እስቲሞቱ ቢያንስ ሌላ አስር ዓመት ይፈጅ ይሆናል።

አዲሱ ጠ/ሚኒስቴር ለውጥ የሚሻ፤ምክንያታዊ ሰው ነው።በአንጻሩ ደካማ ነው።በመጭው ሴፕቴምበር በኢህአዴግ ጉባኤ የፓርቲው መሪነት እንደገና ይጸድቅለት ይሆናል።ግን መሰንበቱ የተረጋገጠ አይደለም።መለስ ለምን እንዳጨው የረሱት ጥቂቶ ናቸው።ከተበታተነው ደቡብ የአገሪቱ ክፍል በመሆኑ ዋናዎቹን ቡድኖች የማይቀናቀን በመሆኑ ነው።

በኢትዮጵያ የሚገኘው የቻይና ህብረተ ሰብ ከፍተኛ አባል ተስፋ በመቁረጥ የአገሪቱ[ኢትዮጵያ] ትልቁ ችግር በቻይና ማእከላዊው መንግስት የክልሎች የበላይ ነው።በኢትዮጵያ ግን ሁሉም ነገር ፌዴራል ነው። የንግድ ቀዬዎች የሚገነቡት በጥናት በተመረጡ ቦታዎች ሳይሆን በኮታ ነው።ከዚህም በላይ እንደ ማኦ መርህ “ፓርቲው ጠመንጃውን ይቆጣጠራል” የሚለው ተረስቷል።ጸጥታ ጠባቂዎቹ ህጉን ራሱን ሆነዋል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ከፍተኛ መሪዎች ችሎታ ቢኖራቸውም እንደቻይና ችሎታ ያላቸው የመካከለኛ ደረጃ አስተዳዳሪዎች የላቸውም።ባጠቃላይ ብዙ ቻይኖች ኢትዮጵያ በብዙ በየቦታው ባሉ ጉልበተኞች  እደተያዘች ያያሉ።

ቻይኖች የማይተነፍሱት  መእራባውያን ግን የሚናገሩት የፖለቲካ ስርዓቱ የሚያደርሰው ጭቆና እንዳዳከመው ነው። ወጣቶች ተቆጥተዋል።ስራ አላገኙም።የብሶት መወጫቸው፤መተንፈሻቸው ቶሎ ተዘግቷል። አስተዋይ የተቃዋሚ መሪዎች ለስደት፡ለእስራት ይዳረላሉ።ይህ ደግሞ ለአክራሪዎች ቦታውን ክፍት ያደርጋል። የዩኒቨርሲቲ ቁጥሮች በርከቷል ግን ለብሩሃኑ ተመራቂዎች የተዘጋጀ ስራ የለም።

ፈርቶ አደርሮች ምክንያት ኢትዮጵያ አጣብቂኝ ውስጥ ትገኛለች።ባላት አስደናቂ እድገት የተነሳ ለጥቂት ጊዜ አንከስ እያለችትሄድ ይሆናል።የሀይል ማመንጫዎችዋም ተጨማሪ ድጋፍ ይሰጥዋት ይሆናል። ኢትዮጵያ ቀርቶባታል መሆን ትችል የነበረውን አስደናቂ  መሆን አልሆነችም።

http://www.economist.com/news/middle-east-and-africa/21652307-africas-most-impressive-economic-managers-suffer-excessive-caution-neither

 

The post ፈጣን ሩጫ አይሉት ማራቶን የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ – የተርጓሚው ማስታወሻ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሃመር ወረዳ ከፍተኛ እልቂት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ

$
0
0

ግንቦት ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን በሃመር ወረዳ በዲመካ ከተማ እና አካባቢዋ የሚኖሩ አርብቶአደሮች ” እኛ ድምጽ ሳንሰጥ” እንዴት ኢህአዴግ አሸነፈ ይባላል በሚል ካለፈው ሰኞ ጀምሮ ከጸጥታ ሃይሎች ጋር ሲታኮሱ መቆየታቸውን የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ አንድ ሻለቃ ጦር እና የፌደራል አባላት ወደ አካባቢው በመንቀሳቀስ በወሰዱት እርምጃ ከፍተኛ ጉዳት ደርሷል። አንዳንድ የአካባቢው ነዋሪዎች አደጋ የደረሰባቸውን ሰዎች ቁጥር በመቶዎች ያደርሱታል።
የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት አርብቶ አደሮች 5 የመከላከያ ሰራዊት አባላትን ያቆሰሉ ሲሆን፣ ቁስለኞችም በሄሊኮፕተር ተወስደዋል። በአርብቶ አደሮች በኩል የተገደሉትን ሰዎች በትክክል ለማወቅ እንደማይቻል የሚናገሩት የአካባቢው ነዋሪዎች አስከሬን በየቦታው ወደቆ እንደሚታይ እየገለጹ ነው።
news
በዞኑ የሚኖሩ አንድ ታዋቂ ግለሰብ እንደተናገሩት ደግሞ ትናንት አርብቶ አደሮች ዲመካን በሌሊት ለመያዝ ጥቃት በፈጸሙበት ወቅት የመንግስት ወታደሮች ከባድ መሳሪያ በመተኮስ በወሰዱት የአጸፋ እርምጃ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎችእንደተገደሉ መረጃው እንደደረሳቸው ገልጸዋል። በሶስት ፒካፕ መኪኖች የተጫኑ ቁስለኛ ወታደሮች ጂንካ ሆስፒታል መግባታቸውንም አክለው ገልጸዋል። ሁለቱም ወገኖች ለወራት የጦርነት ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸውን የሚናገሩት ግለሰቡ፣ የችግሩ ምንጭ ከምርጫ ጋር ብቻ ሳይሆን ከመሬት ጋር የተያያዘ መሆኑም ይገልጻሉ።

ሌላ የአካባቢው ነዋሪም እንዲሁ በተወሰደው እርምጃ ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን መረጃ እንደደረሳቸው ተናግረዋል ። የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በርጤ ዢላ መግለጫ ለመስጠት ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተናግረዋል።
ኢሳት በሁለቱም ወገን የሞቱትን ሰዎች ከገለልተኛ ወገን ለማጣራት ያደረገው መኩራ አልተሳካለትም። ኢሳት ከሶስት ቀናት በፊት አርብቶአደሮች 3 ፖሊሶች ማቁሳለቸውን ዘግቦ የነበረ ሲሆን፣ ሆቴል ቤቶችና ሌሎች አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አሁንም ድረስ እንደተዘጉ ነው።
ለወራት የዘለቀው ውጥረት ምርጫውን ሰበብ አድርጎ መጀመሩን ነዋሪዎች ይገልጻሉ። ሰመጉ ከሁለት ሳምንት በፊት ባወጣው ልዩ መግለጫ ከጥር 7 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተ ግጭት 7 ሰዎች መገደላቸውንና 9 ሰዎች መቁሳለቸውን በጥናት አረጋግጦ ይፋ አድርጓል።

ሰመጉ በሪፖርቱ ህዳር 7 ቀን 2007 ዓም አቶ ዑልዴ ሃይሳ በሐመር ወረዳ ሸንቆ ወልፎ ቀበሌ ውስጥ ነዋሪ የነበረ አርብቶ አደር ሲሆን፣ በድንገት በተነሣ አለመግባባት ምክንያት ባሌ ኢልዴ በተባለ የፖሊስ አባል ኩላሊቱ ላይ በከባድ እርግጫ በመመታቱ የአቶ ዑልዴ ህይወት በእለቱ ህዳር 7 አልፏል። የሐመር ብሔረሰብ አባላት አቶ ዑልዴን የገደለው የፖሊስ አባል ሕግ ፊት ቀርቦ ባለመጠየቁ ከፍተኛ ቅሬታ አድሮባቸውና የመበደል ስሜት ውስጥ ገብተው እንደነበር የሰብአዊ መብት ድርጅቱ አስታውቃል።

ማንጐ ተብሎ በሚጠራው ፓርክ ጎሽ የገደሉ የሐመር ብሔረሰብ አባላትን ለመያዝ ከደቡብ ኦሞ ዞን ፓሊስና ልዩ ኃይል የተውጣጡ አባላት ጥር 7/ 2007 ሥፍራው ሲደርሱ ለሽምግልና የተቀመጡ የአካባቢውን ሽማግሌዎች ጎሽ ገዳዮችን እንዲያወጡ በጠየቁዋቸው ጊዜ “በቅርቡ የተፈጸመውን የአቶ ዑልዴን ግድያ ሳታጣሩና ገዳዩን ይዛችሁ ለፍርድ ሳታቀርቡ፣ ከረዥም ጊዜ በፊት ጎሽ ገደለ የምትሉትን ሰው ለመያዝ እንዴት መጣችሁ?” የሚል ጥያቄ ማቅረባቸውን ይሁን እንጅ ” የፖሊስና ልዩ ኃይል አባላቱ በወቅቱ የተሰጣቸው ግዳጅ ጎሽ የገደለን ሰው መያዝ ብቻ መሆኑን በመግለጽ፣ ፖሊስ የተላክሁበትን ግዳጅ እፈጽማለሁ በማለቱ የሐመር ሽማግሌዎችና የማኅበረሰቡ አባላት ደግሞ የአቶ ዑልዴ ሃይሳን ገዳይ ሳትይዙ የጎሽ ገዳይ ልትይዙ አትችሉም በሚል አለመግባባት መፈጠሩን ሪፖርቱ ያስረዳል።

አለመግባባቱ እየተካረረ ሄዶ በዚያው ቀን ጥር 7 ቀን 2007 በሐመር ማኅበረሰብ አባላትና በፖሊሶች መካከል ተኩስ ተጀምሮ፣ ሰፋ ወዳለ ግጭት ያመራ ሲሆን በግጭቱም 7 ሰዎች ሲሞቱ 9 ሰዎች መቁሰላቸውን ማረጋገጡን የሰመጉ 134ኛ ሪፖርት ያስረዳል።

ሰመጉ ባወጣው የሟቾች ስም ዝርዝር አብዛኞቹ የሞቱትና የቆሰሉት የደቡብ ኦሞ ዞን ፖሊስና የልዩ ሃይል አባላት ናቸው።

ሰመጉ በግጭቱ ተሳታፊ ከነበሩት የሐመር ብሔረሰብ አባላት በኩል ምን ያህል ሰዎች ጉዳት እንደደረሰ ለማወቅ አለመቻሉን በመግለጫው አስታውቋል።
በሃመር ወረዳ ከ45 ሺ በላይ ነዋሪዎች ይኖራሉ። ዲመካ የወረዳው ዋና ከተማ ናት።

The post በሃመር ወረዳ ከፍተኛ እልቂት መድረሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከመስፍን ወልደማርያም (ፕሮፍ) ምን እንማር? (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና)

$
0
0
ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

ሚያዚያ 16 ቀን 2007 ዓ.ም 85 ዓመት ለሆናቸው መስፍን ወልደማሪያም (ፕሮፌሰር)፣ ደጋግሞ ታላቅ ክብር መስጠት ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡ በዚህ ዕድሜ ስለሀገር እና ህዝብ የሚያምኑበትን፣ የሚታዘቡትን፣ የሚያዝኑበትን፣ የሚደሰቱበትን፣ …ሀሳብ መሰረት በማድረግ ብዕርን ከወረቀት ወይም ጣቶችን ከኮምፒውተር ኪቦርድ ጋር አገናኝቶ ለህትመት እና ለማኅበራዊ ድረ-ገጽ አንባቢያን ማቅረብ መቻል የሚያስመሰገን ተግባር ነው፡፡

ሀገራችን በተለያዩ የሙያ እና የዕውቀት ዘርፎች ያፈራቻቸው እጅግ በርካታ ምሁራኖች እንዳሏት ይታወቃል፡፡ ነገር ግን አብዛኞቹ፣ ሀገር እና ህዝብ (ከሚያውቁት አኳያ) ብዙ ሲጠብቅባቸው የጋን ውስጥ መብራት ሆነው፣ አይተው እንደላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ፣ ታዝበው እንዳልታዘቡ፣ አውቀው እንዳላወቁ በመሆን አንድም በፍርሃት አሊያም የሥርዓቱ አሸብሻቢ መሆንን መርጠው አድርባይነት መገለጫቸው ሆኗል፡፡ ይህ የሚያሳዝን አካሄድ ፕሮፍን አይመለከትም፡፡ ሥርዓቱ ተከፋ አልተከፋ፣ ተቆጣ አልተቆጣ፣ አሰረ አላሰረ፣ አስፈራራ አላስፈራራ ፕሮፍ ያመኑበትን በድፍረት ሲነገሩ እና ሲጽፉ ኖረዋል፡፡ ፈጣሪ ጤናና ዕድሜ ይስጣቸው፣ በዚህ መንገድ ዛሬም ነገም ይኖሩታል፡፡ ፕሮፍን ብዙ በጽሑፋቸው፣ ጥቂት በአካል ከማውቃቸው አኳያ፣ እንደዛሬ ትውልድ አባልነቴ ‹‹ከእሳቸው ብንማር ይጠቅሙናል›› ብዬ ከማስባቸው ነገሮች መካከል የተወሰኑትን ከዚህ በታች ልጥቀስ፡-

ተፈጥሮን መኖር
——
በዓለማችን ላሙኑበት ዓላማ፣ እስከመጨረሻው ድረስ ከመንገዳቸው ሳይዛነፉ የሚኖሩ ሰዎች ቁጥር አነስተኛ ይመስሉኛል [ጥናት ላይ የተመረኮዘ ጽሑፍ ስላልሆነ ነው]፡፡ ላመኑበት እውነት የሚኖሩ ሰዎች፣ በውስጣቸው የሚለዋወጥ ፍላጎት ሳይሆን ረግቶ የሚኖር መሻት አላቸው፡፡ ይህም ነው፣ በዋነኝነት ጽኑ የሚያደርጋቸው፡፡ በሁኔታዎች እና በጊዜያቶች የሚዋልል ፈላጎት ያላቸው ሰዎች ቆምንለት ላሉት ሀሳብ ሩቡን ወይም ገሚሱን እንኳን ሳይጓዙ ማሊያቸውን ለውጠው የመገለባበጥ ጅምናስቲክ ሲሰሩ ይገኛሉ፡፡ በሀገራችንም ቢሆን ይሄን ትናንት አይተናል፤ ዛሬም ሆነ ነገ እናይ ይሆናል፡፡ ከዚህ ረገድ፣ ፕሮፍ ካሏቸው ጽኑ መሻቶች መካከል አንዱ፤ በሀገራችን የሰብዓዊ መብት ተከብሮ ማየት መሆኑን ከተግባራዊ እንቅስቃሴዎቻቸው በቀላሉ ማየት ይቻላል፡፡ ሰመጉ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ ፕሮፍ፣ ስለፍትህ መጓደል፣ ስለ ዴሞክራሲ ንፍገት፣ ስለነጻነት ዕጦት፣ ስለችጋር፣ ስለትውልዱ ችግር፣ …ወዘተ ያለመታከት ጽፈዋል፡፡ ይሄ እንግዲህ በሀገራችን የሚታዩ ወሳኝ ችግሮችን ለማጋለጥ ጠንክሮ መቆምን ያሳያል፡፡

እኔ እና አቤል አለማየሁ በ2005 ዓ.ም መጨረሻ ላይ በጋራ አዘጋጅተነው በነበረው ‹‹ኢትዮጵያን ማን ይታደጋት?›› መጽሐፍ ላይ እንዲህ ገልጸው ነበር፡- ‹‹የተፈጠርኩለትን ዓላማ ምን እንደሆነ በእውነት አላውቅም፡፡ [ፈገግታ ያጀበው ሳቅ] በአዕምሮህ ‹ይህ ተፈጥሮዬ ነው› ልትል ትችላለህ፡፡ አዕምሮህን ስለህ፣ እያሰብኩ ‹ይሄ ትክክለኛ መንገድ ነው፤ በአስተሳሰብ፣ በሕግ ሀልዮት ደረጃ ይሄ ትክክል ነው› ብለህ የምትሄድበት መንገድ አንዱ ነው፡፡ ሁለተኛ ደግሞ በልብህ፣ በህሊናህና በስሜትህ መጥፎ፣ ክፉ ነገር ስታይ ያን መጥላትህ፣ ‹‹እንደዚህ ዓይነት ነገር በሰው ላይ መፈጸም የለበትም›› ብለህ ራስህን አጋልጠህ መኖርህ፣ ሐሳብ እና ስሜትህ በተገናኙበት መንገድ ለመሄድ መቻልህ ተፈጥሮዬ ነው ልትል ትችላለህ፡፡ እምነትም እዚህ ውስጥ ሊገባ ይችላል፡፡ ራስህን ብቻ አውጥተህ፣ ጥቅም ብቻ እያሳደድክ የምትኖረው ኑሮ ለእኔ በፍጹም ሕይወት አይደለም፡፡ በአከባቢዬ ያለው፣ በመስኮት ስመለከት የማየው ነገር ሁሉ እንዲነካኝ፤ የሌላው ችግር እንዲቸግረኝ፣ የሌላው ሰቆቃ እና ጭቆና እንዲሰማኝ እፈልጋለሁ፡፡ የሰውየውን ያህል ችግሩ ላይሰማኝ ቢችልም ትንሽም ቢሆን እንዲነካኝ ካላደረኩኝ ለእኔ ሕይወት ምንም ትርጉም የለውም፡፡›› በዚህ ገለጻ ውስጥ፣ በተፈጥሮ መንገዳቸው መሄዳቸውን እና ለሰብዓዊነት ተቆርቋሪነታቸውን በግልጽ መረዳት ይቻላል፡፡

ድፍረት
—–
በሕይወት፣ የሚያምኑበትን ነገር መለየት እና ለተግባራዊነቱ መወሰን፣ መንቀሳቀስ መጀመርና ላመኑበት ነገር መኖር ድፍረትን ይጠይቃል፡፡ በአጭሩ ፕሮፍን ድፍረት ይገልጻቸዋል፡፡ ያመኑበትን በግልጽ አማርኛ ይናገራሉ፡፡ ይሄንን ለመረዳት እና ለማረጋጋጥ የጻፏቸውን መጽሐፎች፣ ግጥሞች፣ ግለ-ሀሳቦች መለስ ብሎ ማየት ነው፡፡ ከላይ በተጠቀሰው መጽሐፍ ውስጥ፣ በፍርሀት ቆፈን ውስጥ ስላሉ ሰዎች ሀሳብ እንዲሰጡን ለፕሮፍ ጥያቄ እንስቼላቸው፣ እንዲህ ብለዋል፡- ‹‹ፍርሃቱን ልትነግረው ‹‹ተው አትፍራ›› ብትለው አትችልም፤ የማይቻል ነው፡፡ ፍርሃት በጣም የግል (Subjective) ነው፡፡

ፍርሃቱ እስኪተውው ድረስ ‹‹አትፍራ›› ልትለው አትችልም፡፡ አንተ ባለመፍራት አንዳንድ ነገር ስታደርግ እሱ ስለሚፈራ ‹‹ቂል›› ይልህ ይሆናል፡፡ ፈሪ ሆኖ ጥሩ ፎቅ ቤት ውስጥ ይኖራል፡፡ ጥሩ ኑሮ ይሆናል፡፡ አንተ ያልሆነ አልባሌ፣ ዓይነት ኑሮ በመኖርህ ‹‹ይሄ ቂል አርፎ ቢቀመጥ፣ እንደ እኔ እንዲህ መኖር ይችል ነበር›› ይልሃል፡፡ ይሄን መቻል አለብህ፡፡ ነገ፣ ከነገወዲያ፣ ሁልጊዜ በአንድ መስመር እንድትሄድ የሚደርግህ እንዳልኩህ ሚዛንህን መያዝህ ነው፡፡›› የዛሬ ወር ገደማ ፕሮፍ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ (በፌስ ቡካቸው) ላይ ባሰፈሩት አጭር ጽሑፋቸው ውስጥ ኑሯቸውም ሆነ ሞታቸውም በሀገራቸው መሆኑን አጽንኦት በመስጠት ሀገር ጥለው እንዲወጡ እየተነኳኮሷቸው ላሉት ካድሬዎች የሰጡት አጭር ምላሽ በድፍረት የታጀበ ነበር፡፡ በዚህ አጋጣሚ በቤታቸው የሚገኙት የገብረ-ክርስቶስ ደስታ ስዕሎች መሆናቸውን ጠቅሰው ‹‹በዚህ አጋጣሚ ሥዕሎቹን የሚገዛ…›› ያሏት አገላለጽ ደስ እና ፈገግ አስደርጋኛለች፡፡

አድናቆት እና ትችትን መቻል
——-
ለፕሮፍ የተለያዩ ሰዎች በተለያዩ ጊዜያት አድናቆትን በቃላትና በጽሑፍ ሰጥተዋቸው ያውቃሉ፡፡እንዲሁም ፕሮፍ በጋዜጦች/በመጽሔቶች/በመጽሐፎቻቸው ባነሷቸው ሀሳቦች ላይ ተንተርሰው የተለያዩ ሰዎች ትችትን በጽሑፍ አቅርበውባቸውም አንብበናል፡፡ ለተቿቸው ሁሉ ግን መልስ አይሰጡም፡፡ ምሳሌ ለማንሳት ያህል፣ ‹‹መክሸፍ እንደኢትዮጵያ ታሪክ›› ለተሰኘው አነጋጋሪ መጽሐፋቸው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ላነሳባቸው ትችት መልስ ሰጥተውታል፡፡ የኢዴፓ አመራር የነበረው አብዱራህማን መሐመድ በሰንደቅ ጋዜጣ ላይ ሰፊ ጽሑፍ ፕሮፍ ላይ ቢጽፍም አጸፋዊ መልስ ነፍገውታል፡፡ ስለዚህ ፕሮፍ መልስ የሚሰጡበትና የማይሰጡበት የትችት ዓይነት እንዲሁም ሰዎች ስለመኖራቸው የሚያሳይ ነው፡፡ እሳቸው ቢሆኑ አድናቆቱም ሆነ ትችቱ አልጣላቸውም፡፡ እዚህ ጋር፣ ‹‹አድናቆት ይጥላል ወይ?›› የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችል ይሆናል፡፡ መልሴ አዎን ነው፡፡ አድናቆትን መቆጣጠር የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ ሁሉ፤ በአድናቆት ሰክረው ከመንገዳቸው የሚንሸራተቱ ሰዎች መኖራቸውን ማወቅም ተገቢ ነው፡፡ በትችት መንፈሳቸው በቀላሉ የሚሰበሩ ሰዎች አሉ፤ አይተናልም፡፡ ፕሮፍም ቢሆኑ ለሰዎች አድናቆት ሲሰጡ እና ጠንካራ ትችትን ሲሰነዝሩም እናውቃቸዋለን፡፡ አንድ ሰው ራሱን አደባባይ ላይ በተለያየ መንገድ አውጥቶ ልተች አይገባም ሊል እንደማይችል በአንድ ወቅት ከሰጡት ቃለ-ምልልስ ተረድቻለሁ፡፡ ስለዚህ አድናቆትንም ሆነ ትችትን መቻል ትልቅ ጥበብ አድርጎ መውሰድ ይቻላል፡

ተስፋ አለመቁረጥ
—–
በሀገራችን የፖለቲካው መስክ፣ ይበልጥ የተስፋ የመቁረጥ አዝማሚያ በብዙዎች ላይ በገሃድ ይንጸባረቃል፡፡ አፍ አውጥተው ተስፋ መቁረጣቸውን የሚናገሩም አሉ፡፡ ይህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት በተለይ ወጣቶች ላይ ሲታይ ያስጨንቃል፤ ያሳዝናልም፡፡ ለሥርዓቱ የጭካኔ በትር በአንድ ጊዜ የሚንበረከኩ ሰዎች መኖራቸውንም በግል ታዝቤያለሁ፡፡ ይህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ‹‹መስመራችን ነው›› ካሉት ጎዳና አስወጥቶ እስከወዲያኛው ያርቃቸዋል፡፡ ከዚያም አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አውቀው እንዳላወቁ ወደመሆን ያመራሉ፡፡

ፕሮፍ ግን፣ ሀገሪቷ በተለያዩ አስቸጋሪ ሁነት ውስጥ እየኖረች መሆኑን ተገንዝበው፤ አይተው እንዳላዩ፣ ሰምተው እንዳልሰሙ፣ አውቀው እንዳላወቁ መሆን አልቻሉም፡፡ ባለፈው ዓመት መጨረሻ አካባቢ ‹‹ፋክት›› መጽሔት ከመዘጋቷ በፊት በየመጽሔቷ አምደኛ ሆነው በየሳምንቱ ሀሳባቸውን ይሰነዝሩ ነበር፡፡ ከዚያ በኋላም ቢሆን፣ በማኅበራዊ ድረ-ገጽ በፌስ ቡክ ገጻቸው አልፎ አልፎም ቢሆን ሃሳባቸውን እየጻፉ ማስነበባቸውን ቀጥለዋል፡ች በሀገራችን ብዙ አሳዛኝ ድርጊቶች መፈጸማቸው ቀጥለዋል፡፡ በእነዚህ አሳዛኝ ሆነቶች ፕሮፍ ተስፋ ቢቆርጡ ኖሮ ሀሳባቸውን በአንድም ይሆን በሌላ መንገድ ባላየን ነበር፡፡ ይህ፣ በሀገር ጉዳይ ተስፋ ያለመቁረጥ ስሜት አንዱ ማሳያ ነው፡፡ ተስፋ ስንቆርጥ እንቅስቃሴያችን ይገታል፡፡ ስለዚህ፣ ሰዎች በሕይወት እስካለን ድረስ ተስፈኛ መሆን ይገባናል፡፡

እንግዲህ በግሌ ከፕሮፍ ብንማራቸው ይጠቅሙናል ያልኳቸውን እራት ነጥቦች በአጭሩ ለማቅረብ ጥረት አድርጌያለሁ፡፡ ሌሎችም ፕሮፍን ከማወቅ አኳያ፣ አስተማሪ ናቸው የምትሏቸው ሀሳቦች ካሉ ሀሳባችሁን ሰንዝሩና አብረን እንማማር፡፡

(በዘንድሮው የፋሲካ ዕለት፣ ሚያዚያ 4 ቀን 2007 ዓ.ም የተጻፈ)

በዚህ አጋጣሚ፣ ፈጣሪ ዕድሜ እና ጤናን ለፕሮፍ ይስጥ ብያለሁ!

ቸር እንሰንብት!

The post ከመስፍን ወልደማርያም (ፕሮፍ) ምን እንማር? (ኤልያስ ገብሩ ጎዳና) appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢትዮጵያና ኤርትራ ለማስታረቅ ሱዳንና ኳታር እቅድ መያዛቸውን ተሰምተዋል

$
0
0

Eriteriaየሱዳኑ ፕሬዝደንት ዑማር ልበሽር የአገሪቱን ምርጫ በማሸነፋቸው በነገው ዕለት የቃለመሃላ ሥነ ሥርዓት ያካሂዳሉ።
በዚህ በዓል የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝና የኤርትራው ፕሬዝደንት አቶ ኢሳያስ አፍወርቂ ፊት
ለፊት ይገናኛሉ።
የሱዳንና የኳታር መሪዎች ይህን አጋጣሚ በመጠቀም በከረረ ጥላቻ የሚገኙት ኤርትራና ኢትዮጵያን ለማስታረቅ ሙከራ
ያደርጋሉ ተብሏል። የኢትዮጵያና የኤርትራ ጥል በአፍሪካ ቀንድ ብሎም በምሥራቅ አፍሪካ ሠላም ለማስፈን ማነቆ መሆኑን የተረዱት
መሪዎቹ ችግሩን ለመፍታት በቁርጠኝነት የማስታረቁ ሥራ እንደሚሞክሩት ይጠበቃል።
ፕሬዝደንት አልበሽር በሚያደርጉት የቃለመሃላ ሥነስርዓት ከኤርትራን ኢትዮጵያ በተጨማሪ የኳታር፣ ሳውዲ አረቢያ፣
ግብጽ፣ ቻድ፣ ደቡብ ሱዳን፣ ኡጋንዳ፣ ኬንያንና የሌሎች አገሮች በርካታ መሪዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል። የ91 ዓመት ዕድሜ አዛውንት የ ዚምባብዌንፕረዚደንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ሮበርት ሙጋቤ በሥነሥርዓቱ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል።

The post ኢትዮጵያና ኤርትራ ለማስታረቅ ሱዳንና ኳታር እቅድ መያዛቸውን ተሰምተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

አይሲኤስ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ጭካኔያዊ ግድያ ለመቃወም ሰልፍ የወጣው ናትናኤል 3 ዓመት ከ 3 ወር ተፈረደበት

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው የኢትዮጵያ መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈፀመውን የጭካኔ እርምጃ ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የታሰረው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ተፈረደበት፡፡ ዛሬ 25/2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውን ያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩን ገልጾአል፡፡
nat
በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት…›› የሚል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው ጠይቀዋል፡፡

በተመሳሳይ ‹‹ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድንጋይ በመወርወር ሰልፉን አውካችኋል›› የተባሉ ሌሎች አምስት ወጣቶች ለሰኔ 4 የመከላከያ ምስክር እንዲያቀርቡ ተቀጥረዋል፡፡ በሰልፉ ሰበብ ተይዘው የታሰሩት ወጣቶች በቤተሰብ እንዳይጠየቁ መከልከላቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድተዋል፡፡

The post አይሲኤስ በወገኖቻችን ላይ የፈጸመውን ጭካኔያዊ ግድያ ለመቃወም ሰልፍ የወጣው ናትናኤል 3 ዓመት ከ 3 ወር ተፈረደበት appeared first on Zehabesha Amharic.


የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ – -በአበራ ለማ

$
0
0

127የዛሬ አራት ዓመት በኖርዌይ ተቀስቅሶ የነበረው የ500 ጥገኝነት ጠያቂ ኢትዮጵያውያን ስደተኖች ጉዳይ በኦስሎ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት 127ኛ ችሎት በቅርቡ ሲታይ ሰንብቷል፡፡ ይህ ቀደም ሲል በዶ/ር ግሩም ዘለቀ የግል ተነሳሽነት በኖርዌይ ጠበቆች አማካኝነት በየደረጃው ላሉ የኖርዌይ ፍርድ ቤቶችና በኋላም ለአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረው ጉዳይ አሁን የታየው እ.አ.አ. ከሜይ 4 – 29 ቀን 2015 ዓ.ም. ድረስ ነው፡፡ የአውሮፓ የሰብዓዊ መብት ጥበቃ ፍርድ ቤት መቀመጫውን ለንደን ባደረገው ”ዘ አየር ሴንተር – The AIRE Center” (Advice on Individual Rights in Europe) በተሰኘው መንግሥታዊ ባልሆነው የሕግ ባለሙያዎች ድርጅት አማካኝነት የቀረበለትን ይህን ጉዳይ፣ ከሦስት ዓመታት ተኩል በላይ ለሆነ ጊዜ ሲመለከተው መቆየቱም ይታወሳል፡፡—

[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]

 

 

The post የኖርዌይና የስደተኞቻችን ፍልሚያ – -በአበራ ለማ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich G7 ኃይለማሪያም ደሳለኝ

$
0
0

ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ

ታላቅ የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich  ሰአት 13:00 

በኢትዮጵያ ውስጥ የሚካህደውን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ረገጣ፣ የዲሞክራሲ እና የነጻ ፕረስ መታፈን፣ ኢንዲሁም የምርጫ  ማጭበርበር በመቃወም ሁሉም  ለኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት እና የ ዲሞክራሲ እንዲሁም የሰላም ተቆርቋሪ የሆናችሁ ሁሉ ኑ በአንድ ላይ ድምጻችንን እናሰማ  

የሰላማዊ ሰልፍ አላማ

በጀርመን የአመቱ ፕሬዚደንትነት አዘጋጅነትና ጋባዥነት በዚህ አመት 2015 06.-07.June 2015 በ ሙኒክ ከተማ ጀርመን በሚካህደው የ G 7 ስብሰባ ላይ በአፍሪካ ዉስጥ ጋዘጠኞችን በብዛት በማሰር  እና ምርጫ ማጭበርበር እንዲሁም በከፍተኛ ሰብአዊ መብት መጣስ የሚከሰሰውን ኢንዲሁም በከፍተኛ ደረጃ ስደተኛ አመንጪ የሆነዉን የኢትዮጵያን አምባገነን ስርአት ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማሪያም ደሳለኝን መገኘት አጋጣሚ በማድረግ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተዘጋጅቶዋል

የሰላማዊ ሰልፍ አላማ

፩፣ኢትዮጵያ ውስጥ የሚደረገውን የሰብአዊ መብት ረገጣ እንዲቆም

፪፣በኢትዮጵያ ውስጥ የታሰሩት የፖሊቲካ  እስረኞች በጠቅላላ ባስቸኩዋይ  እንዲፈቱ

፫፣የጀርመን መንግስት እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና የ G7 አገሮች ሁሉንም አምባገነን በእኩል አይን እንዲይዩ ለቆሙለት በቆሙበት ለሚመሰክሩለት ደሞክራሲ እና ሰብአዊ መብት ለኢትዮጵያ ሲሆን ፊታቸውን ማዞር የሚያቆሙበት ጊዜ መሆኑን ተረድተው በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ስርአት የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲያቆሙ እና በአንጻሩ ለዴሞክራሲ ለህግ የበላይነት ለስብአዊ መብት መከበር ድጋፋቸውን እንዲሰጡ እንጠይቃለን ፦፦፦

የጀርመን እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት እና የ ጂ፯ አገሮች መራጭ ዜጎች መንግስቶቻቸው     በከፍተኛ ደረጃ ሰብአዊ መብትን ከሚረግጥ ፣የዲሞክራሲን እና የነጻ ፕረስን አፍኖ ከሚያጠፋ፣ለህግ የበላይነት ለማይገዛው በኢትዮጵያ ውስጥ በስልጣን ላይ ላለው አምባገነን ስርአት የሚሰጡትን ድጋፍ
እናጋልጣለን

 

 

 

ሰልፉ የሚጀምርበት ሰአት 13:00

ሰልፉ የሚጀምርበት ቦታ Stachus (Karlsplatz), München 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚቴ

 

Contact Tel:. +49 160 4357232
E-mail:menschenrecht-ethiopia@hotmail.de

 

220px-2379_-_München_-_Residenz

 

The post የሰላማዊ ሰልፍ 04.06.2015 Munich G7 ኃይለማሪያም ደሳለኝ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአፍሪካ አርዓያ የሆነዉ የናይጄሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫና ሰላማዊ የስልጣን ርክክብ (በሳዲቅ አህመድ) –ሊያደምጡት የሚገባ

በዘውዲቱ ሆስፒታል የ5 ልጆች እናት በህክምና ስህተት ሕይወቷ አለፈ

$
0
0

zewditu

zewditu hospital
በዘውዲቱ ሆስፒታል የመህፀን እጢ እንዳለባቸው የተነገራቸው የ 5 ልጆች እናት እጢው ወደ ካንሰር እንዳይለወጥ አስቸኳይ ቀዶ ጥገና እንዲደረጉ ይታዘዛሉ ። ለዚህም ቀዶ ጥገና ሆስፒታሉ መሳሪያ ስለሌለው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የምርመራ ውጤታቸውን አባሪ በማድረግ ይልካቸዋል። የተጠቀስው ሆስፒታል እደደረሱም እናት ለህክምና ከአቅማቸው በላይ የሆነ ክፍያ ሰለተጠየቁ «ያለአባት የሚያሳድጓቸው የ 5 ልጆች እናትና የቤተሰብ ሃላፊ መሆናቸውን ጭምር በመግለጽ ሆስፒታሉ ከሞት እንዲታደጋቸው ይማፀናሉ ። የሆስፒታሉ አስተዳደር እናት ከቀበሌ ደብዳቤ ካመጡ በነጻ ህክምና የሚያገኙበትን መላምታ እንደሚያመቻቹላቸው ቃል በመግባት ያሰናብቷቸዋል። የጤና ጉዳይ ነውና እናት የተባለውን ሁሉ አሞልተው ዳግም ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በማቅናት ለነጻው ህክምና ተራ ያሲዛሉ ። ከወራት ቆይታ በኃላ እናት የቴሌፎን ጥሪ ከሆስፒታል ይደርሳቸዋል « ተራዎ ስለደረሰ መጥትው ነጻ ህክምናውን ይውሰዱ የሚል» ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል በቁሙ የገባ ታካሚ እንደዋዛ በሬሳ ሳጥን ታሽጎ በአስከሬን በር የሚወጣበት ፤ የመኪና ግጨትን ጨምሮ በተለያያ ድንገተኛ አደጋዎች እግርጥሎት ወደ ሆስፒታሉ ያቀና «ዘመድ አዝማድ የሌለው የኔ ቢጤ » የሰውነት ክፍሉ ተበልቷ ለሃብታሞች ጫራታ የሚቀርብበት ፡ በአጠቃላይ ሆስፒታሉ ወደ ሰው ቄራነት የተለወጠ ፤ የህክምና መሳሪያን ጨምሮ በ መደሃኒትና በባለሙያ እጠረት ያለበት መሆኑን ቀደም ብለው የተረዱ እናት ሁኔታው ደስ ስላላቸው « እሱ እንደፈጠረኝ እሱ ይግደለኝ » ብለው ምንም አይነት የህመም እንደማይሰማቸው ገልጸው የቀዶ ጥገና ሃሳባቸውን መለወጣቸውን ለሆስፒታሉ ያስረዳሉ። የኚህን እናት ሙሉ መረጃ የያዙ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ዶ/ሮች በተደጋጋሚ ስልክ በመደውል እጢው ቀላል እንደሆነና በዛው ልክ ቀዶ ጥገና እንደሚያደርጉላቸው ያግባቦቸዋል።

እናት ያለአባት የቀሩ ልጆቼን ላሳድግ ኽረ ! ጉድ ታደርጉኛላችሁ ! ቢሉ ማን ሊሰማ ። በዶ/ክተሮች ተማጽኖ ሆስፒታል የገቡት እናት ግን የፈሩት አልቀረላቸውም። ዕለቱ ማክሰኞ ረፋዱ ላይ ነው ። ከሶስት ቀን በፊት ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል አልጋ ተይዞላቸው የቀዶጥገና ቀናቸውን የሚጠብቁት የ 5 ልጆች እናት ስጋታቸው ጨምሯል። እናት ፍረሃት ፍረሃት እንዳልቸው ለገኙት ሁሉ ቢገልጹም ደሃ ታሞ በማይድንባት ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም እንደሆነ የሚነገርለትን የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ባዶ ህንጻና ነጫጭ ገዋን በለበሱ የጤና ባለሙያዎች በተማረኩ ወገኖች አበረታችነት እናት በተጠቀሰው ቀን ከቀኑ 8 ሰዓት ልጆቻቸውን ተሰናብተው ወትሮም ወደ አላመኑበት ቀዶ ጥገና ክፍል ገቡ ። ልጆቻቸውን ጨምሮ ሁሉም ቤተሰብ ቀዶ ጥገና ክፍል በሩ ላይ በጭንቀት ተውጦ ፈጣሪውን ይማፀናል ። የቀዶ ጥገና ክፍሉ መግቢያ ላይ ዶ/ሮቹ ቀዶ ጠገናውን መጀመራቸውን የሚያመላክተው ቀይ መብራት በርቷል ።ሶስት ሰዓት ይፈጃል ይተባለለት ቀዶ ጥገና ሳይጥናቀቅ ከቀዶ ጥገና ክፍሉ አንድ በወጣትነት እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኝ የህክምና ባለሙያ እይተቻኮለ ወጣ ፤ በጭንቀት ተመስጥው በር ላይ ለታደሙት ቤተሰቦች በተርበተበተ አንደበት « ሴትየዎ ብዙ ደም ስለፈሰሳቸው ደም ስለሚያስፈልግ ፈልጋችሁ አምጡ » የሚል ትዕዛዝ ቢጤ አስተላልፎ እየተቻኮለ ወደ መጣበት ክፍል ተመለስ ።ሁሉም ቤተሰብ በየአቅጣጫው ደም ፍለጋ ከተማ ውስጥ ያሉትን ሆስፒታሎች ማካለል ጀመር ወትሮስ ምክንያት እንጂ ችግሩ የደም አልነበረም ። የናታቸው ህይወት አደጋ ውስጥ መውደቅ የተነገራቸው ልጆች እሪታቸውን አቀለጡት የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህንጻ እንደዚህ አይነት ጩህቶችን በየግዜው መስተናገድ የተለመደ ቢሆንም የልጆቹ ጩኽት ግን ከወትሮው ለየት ያለ ነበር ፤ በአካባቢ የነበረውን ሁሉ ደረት በማስደቃት የሆስፒታሉን ድባብ ለወጠው ።በሁኔታው የተደናገጡት ዶ/ር ተብዬዎች ከአካባቢው ተሰወሩ ችግሩ ወደ ተፈጠረበት የቀዶ ትገና ክፍል የመጡ የሆስፒታሉ ህላፊዎች በቀዶ ጥገና ወቅት በደም ስር ላይ ጉዳት ሳይደርስ እንዳልቀረና ሴትየዋ የማይተርፉ መሆናቸውን ቢረዱም የዜጎች ህይወት በተደጋጋሚ በቀዶ ጥገና ስህተት መጥፋት የተለመደ ነውና በአካባቢ የነበረውን ቤተሰብ ከማስተዛዘን ውጭ ዴታም አልነበራቸውም ፤ በተለይ ልጆቻቸውን ለማረጋጋት በእድሜ የገፋውን ልጅ ቀዶ ጥገና ክፍል ውስጥ ይዘውት በመግባት ከማደነዘዣ የነቁትን እናት እንዲያይ ፈቀዱለታል ።

የአባት ፍቀር እንደተራበ እናቱን ለማየት ወደ ቀዶ ጠገና ክፍል የዘለቀው ልጅ ከእናቱ አንደበት « ብርድ ብርድ አለኝ ፤ ተጫወቱብኝ የሚለውን ቃል ከመስማት ባሻገር »እናት ጤና እያሉ ይለግሱት የነበረውን የእናትነት ፍቅር ዳግም መስማት አለታደለም ። የማህጸን እጢ አለባቸው ተብለው ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ተለምነው የገቡት እናት ይህይወት ፍጻሜ በቀዶ ጠገና ስህተት ሁሉም ነገር አበቃ ። በዛው ቅጽፈት የቀዶ ጠገና ክፍሉ ዘግናኝ የደውል ድምጽ አቃጨለ ተጠያቂነትና የህግ የበላይነት በሌለበት ሃገር ተተኪ የሌላት የ 5 ልጆች እናት ላትመለስ እስከ ወዲያኛው አሸለበች ። በፖለቲካ አመመለካከታቸው አያሌ የሃገሪቷን እውቅ ዶክተሮች ከሃገር እንዲሰደዱ ያደረገው « የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት » በጤና ፖሊሲው የፖለቲካ ቱሩፋት ለማግበስበስ ያለ በቂ ባለሙያ ፤ የህክምና መሳሪያና መደሃኒት በየክልሉ ለይስሙላ ባስገነባቸው ባዶ ህንጻዎች ውስጥ ህይወታቸው እንደዋዛ ያጡትን ዜጎቻችንን ቤት ይቁጠራቸው::

The post በዘውዲቱ ሆስፒታል የ5 ልጆች እናት በህክምና ስህተት ሕይወቷ አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

ዳኛ ብርቱካን አቶ ማሙሸት አማረን ክሱ ተቋርጦ ይፈቱ ስትል ፖሊስ አለቅም አለ

$
0
0

Zehabesha News
* የአይ.ሲ.ስን ግድያ ለማውገዝ ሰልፍ የወጣው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ከሶስት ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት

(ሕብር ሬዲዮ-ላስ ቬጋስ ) የመኢአድ ሕጋዊው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ ሚአዚአ 14 ቀን 2007 በመስቀል አደባባይ በተጠራው ሰልፍ ላይ ብጥብጥ አስነስተዋል በሚል ለተከሰሱበት የፈጠራ ክሱንና የሀሰት ምስክርነቱን ዋጋ የሚያሳጣ በዕለቱ በሌላ ፍርድ ቤት ምርቻ ቦርድን ከሰው ሙግት ላይ መሆናቸውን የሚአስረዳ የሰውና የሰነድ መከላከያ ምስክር ባለፈው አርብ ያቀረቡለት ቦሌ ምድብ የመጀመሪአ ፍርድ ቤት ሶስተና ችሎት ዛሬ በሰጠው ትዕዛዝ አቶ ማሙሸትን ያሰረው ቦሌ ፖሊስ መምሪያ ክሱ በመቋረጡ እንዲፈታቸው ትዕዛዝ ቢሰጥም ፖሊስ ሳይፈታ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳዛወራቸው ያገኘነው መረጃ ይገልጻል።

አቶ ለገሰ ወ/ሃና የዛሬውን የአቶ ማሙሸት የፍርድ ቤት ውሎ ተከታትለው በላኩልን መረጃ መሰረት ባለፈው አርብ በዋለው ችሎት የአቶ ማሙሸት አማረን የመከላከያ ምስክር የሰማው የፌዴራል መጀመሪአ ደረጋ ቦሌ ምድብ ሶስተኛ ችሎት ለዛሬ ለውሳኔ ቀጥሮ የነበረ ሲሆን ክሱን ሲያዩ የቆዩት ዳኛ ብርቱካን ገላው በሰጡት የፍርድ ቤቱ ውሳኔ መሰረት አቶ ማሙሸት አማረ ድልነሴ በተከሰሱበት ስብሰባን ወይም ጉባዔን ማወክ ክስ ተከሳሹ የተከሰሰበት መዝገቡ የተቋረጠ ስለሆነ ይፈታ ሲል ማክሰኞ ጠዋት በሶስት ሰኣት ሲል ያዛል።

የፍርድ ቤቱን ውሳኔ ማክበር የነበረበት ፖሊስ ውሳኔውን ወደ ጎን በማድረግ የቦሌ ፖሊስ መምሪአ ቤተሰብና የአቶ ማሙሰት አማረን የትግል አጋሮች ጠብቁ ሲል ቆይቶ ሌላ ክስ ሳይቀርብ ፣የፍርድ ቤቱም ውሳኔ ሳይከበር ከሰኣታት ጥበቃ በሁዋላ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ተዛውሯል መባላቸውን የደረሰን መረጃ ያስረዳል።

የመኢአድ ሕጋዊው ፕ/ት አቶ ማሙሸት አማረ ግንቦት 5 ቀን 2007 ከመኖሪያ ቤታቸው አቅራቢያ በደህነቶች ታፍነው ተወስደው በዚሁ ፍርድ ቤት በሊቢያ ለሞቱት ወገኖች ሐዘን ለመግለጽ ሚአዚአ 14 ቀን 2007 መስቀል አደባባይ የወጣውን ሕዝብ አሳምጸዋል ብትብት አስነስተዋል በሚል የፈጠራ ክስ ተከሰው አገዛዙ የሀሰት ምስክሮች አቅርቦ አስመስክሮ የነበረ ቢሆንም ባለፈው አርብ አቶ ማሙሰት አማረ ባቀረቡት የመከላኬአ የሰነድና የሰው ማስረጃ በዕለቱ መስቀል አደባባይ እንዳልነበሩ ይልቁንም ምርጫ ቦርድ በመኢአድ ላይ የወሰደውን አመራሩን በሕገ ወጥ የማባረር እርምጃ በመቃወም በቦርዱ ላይ ያቀረቡትን ክስ ለመከታተል ልደታ ምድብ የፌዴራሉ አንደና ደረጃ ፍርድ ቤት እንደነበሩ ፍርድ ቤቱ በሰነድ ያረጋገጠውንና በዕለቱ አብረዋቸው የነበሩትን አስመስክረዋል። ይሄን የአርብ ምስክርነት የሳው ፍርድ ቤት በዛሬው ቀጠሮ ክሱን አቋርጦ ይፈቱ ቢልም ፖሊስ ሳይፈታ ቀርቷል።

አገዛዙ ፍርድ ቤት የሚፈልገውን ካልወሰነ ቱንም ትዕዛዝ የማያከብር ሲሆንየዛሬዋ ዳኛ ብርቱካን ገላው የሰቱትን ውሳኔ አለመከበር ከዚህ ቀደም በስፋት የሚታወቀውን የዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳን ውሳኔ የሚአስታውስ ሆኗል። ዳና ብርቱካን ሚደቅሳ የቀድሞው የአገዛዙ ባለስልጣን አቶ ስዬ አብርሃን የቀረበውን የሙስና ክስ መዝገብ በመመልከት በጊዜ ቀጠሮ ፖሊስ አለ በቂ ምክንያት የምርመራ ጊዜ እየጠየቀ ተገቢውን ባለመስራቱ የመሀል ዳኛ በሆነችበት አራዳ ምድብ በችሎት ፖሊስ በዋስ ይፈቱ የተባለውን ውሳኔ ባለማክበሩ በነጻ ማሰናበቷ ይታወሳል። ይሁንና ፖሊስ ውሳኔውን ተግባራዊ ላለማድረግ የፍርድ ቤቱን ግቢ በር ለጊዜው ዘግቶ መልሶ ከአለቆቹ ትዕዛዝ ሲደርሰው ከፍርድ ቤቱ እንደወጡ ጥቂት በእግራቸው እንደተጓዙ ሁኔታውን ለመከታተል ካጀባቸው ሕዝብ፣ቤተሰቦችና ጠበቃቸው ነጥሎ መልሶ ማሰሩ ይታወሳል። ዛሬ አቶ ማሙሸት በፍርድ ቤቱ ትዕዛዝ ሳይፈቱ ከእስር ቤት ወደ እስር ቤት ተዛውረዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ወጣት በሚያዚያ 14/2007 በሊቢያ በአይ.ሲስ አሸባሪ ቡድን በሊቢአ በግፍ የተገደሉ ወገኖች ላይ ተወሰደውን በመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ አደባባይ በመገኘቱ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ›› ፈጥረሃል በሚል ተይዞ የቆው ናትናኤል የዓለም ዘውድ የ3 አመት ከ3 ወር እስራት ዛሬ የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ የመናገሻ ፍርድ ቤት እንደተፈረደበት ፓርቲው ይፋ አድርጓል።

ከፓርቲው የተገኘው መረጃ እንደሚገልጸው ናትናኤል የኣለም ዘውድ ዛሬ ግንቦት 25ቀን 2007 ዓ.ም የፌደራል መጀመሪያ ፍርድ ቤት መናገሻ ምድብ ችሎት የቀረበው ወጣት ናትናኤል የዓለም ዘውድ ላይ የቀረበው ክስ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ መፍጠር›› የሚል ሲሆን አቃቤ ህግ ከፍርዱ በፊት ‹‹ሁከትና ብጥብጡን የፈጠረው ኢትዮጵያውያን ላይ ግድያ የፈፀመውን አይ ኤስ አይ ኤስ ለማውገዝ የተጠራው ሰልፍ ላይ በመሆኑ፣ በተፈጠረው ረብሻ በርካታ ሰዎች የተጎዱ በመሆኑ እና ረብሻውን የፈፀመው አምስተኛው አገራዊ ምርጫ እየተቃረበ ባለበት ወቅት በመሆኑና ይህም አደጋውን ያባብስ የነበር መሆኑን በማገናዘብ›› የሚል የቅጣት ማክበጃ መጨመሩንም ይሄው መረጃ ገልጿል።

በሌላ በኩል በተመሳሳይ ክስ ተከሰው በዚሁ ፍርድ ቤት የቀረቡት ማቲያስ መኩሪያ፣ ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤና መሳይ የተባለ ሌላ ወጣት መከላከያ ምስክር ለማቅረብ ለሰኔ 4 ተቀጥረዋል፡፡ እነ ማቲያስ ‹‹ሰልፉ ላይ ሀሰተኛ ወሬ በማውራት፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እየተናገሩ በነበረበት ወቅት ወደ ፖሊስ ድንጋይ በመወርወር፣ ህዝቡን አትነሳም ወይ በማለት…›› የሚል ክስ እንደቀረበባቸው ያስታወሰው ይሄው ፓርቲው መረጃ በጉዳዩ ላይ ዛሬ ይቀርባል ተብሎ የነበረው የቪዲዮ ማስረጃ ባለመቅረቡ በሚቀጥለው ቀጠሮ እንዲቀርብላቸው መጠየቃቸው ታውቋል።

The post ዳኛ ብርቱካን አቶ ማሙሸት አማረን ክሱ ተቋርጦ ይፈቱ ስትል ፖሊስ አለቅም አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>