Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

ኢትዮጵያውያንን የገደለው አይሲኤስን ለማውገዝ ስልፍ በመውጣቱ የታሰረው አቶ ዳዊት አስራደ ለሶስተኛ ጊዜ የዋስትና ገንዘብ ከፍሎ ታሰረ

$
0
0

• እስካሁን 36 ሺህ ብር ከፍሏል

የቀድመው አንድነት አመራር አቶ ዳዊት አስራደ ትናንት ግንቦት 3/2007 ዓ.ም አራዳ ፍርድ ቤት 1ኛ ወንጀል ችሎት ቀርቦ በ5000 ብር ዋስ እንዲፈታ ዋስትና የተፈቀደለት ቢሆንም ገንዘቡን ካስያዘ በኋላ ዋስትናው እንደተነሳ ተነግሮት በእስር ላይ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ በትናንትናው ችሎት ፖሊስ ተከሳሾቹ ምስክሮችን ያባብሉብኛል በሚል ምስክሮችና መረጃዎችን አሰባስቦ እስኪያቀርብ ጊዜ ድረስ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቆ የነበር ቢሆንም አቶ ዳዊት አስራደ፣ አቶ አለነ ማህፀንቱና ወይዘሪት ሜሮን አለማየሁ የ5000 ብር ደሞዝ ያለው የሰው ዋስ ወይንም ገንዘብ አስይዘው ከእስር እንዲወጡ ፈቅዶ ነበር፡፡
dawit asrade
ይሁንና የአቶ ዳዊት አስራደ ቤተሰቦች መፍቻ ይዘው ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ሲሄዱ የአዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ፖሊስ አቶ ዳዊትን ለቄራ ፖሊስ ጣቢያ ማስረከቡን እንደገለጸላቸው ጠበቃው አቶ ገበየሁ ይርዳው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የቄራ ፖሊስ ጣቢያም ከአሁን ቀደም አቶ ዳዊት አስራደ በተመሳሳይ ክስ ተፈቅዶለት የነበረውን ዋስትና ማንሳቱን በመግለጽ እንዳሰረው ለማወቅ ተችሏል፡፡

በተመሳሳይ በተፈቀደለት ዋስትና መሰረት 5000 ብር ያስያዘውን አቶ አለነ ማህፀንቱን ፖሊስ መጀመሪያ ወደ ማታ እፈታዋለሁ፣ እንዲሁም ከቆይታ በኋላ ይግባኝ እጠይቃለሁ ብሎ እስር ላይ ቢያቆየውም አሁንም ድረስ ይግባኝ ሳይጠይቅ በእስር ላይ እንደሚገኝ ጠበቃው ገልፀዋል፡፡

መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰረው አቶ ዳዊት አስራዳ በተመሳሳይ ክስ ለሶስተኛ ጊዜ የዋስትና ገንዘብ እያስያዘ እንደገና በእስር ላይ የቆየ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ 25 ሺህ፣ በቀጣይነትም 6 ሺህ፣ እንዲሁም በትናንትናው ዕለት 5 ሺህ ብር በአጠቃላይ 36 ሺህ ብር ዋስትና አስይዞ እንደገና ታስሯል፡፡ አቶ ዳዊት አስራደና ወይዘሪት ሜሮን አለማየሁ ሚያዝያ 14 መንግስት ላይ በተነሳው ተቃውሞ ሰበብ በአንድ ጉዳይ ሁለት ክስ ተመስርቶባቸው በሁለት ፍርድ ቤቶች ጉዳያቸውን ሲከታተሉ ቆይተዋል፡፡ በቄራና ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያም በፈረቃ ሲታሰሩ ቆይተዋል፡፡

The post ኢትዮጵያውያንን የገደለው አይሲኤስን ለማውገዝ ስልፍ በመውጣቱ የታሰረው አቶ ዳዊት አስራደ ለሶስተኛ ጊዜ የዋስትና ገንዘብ ከፍሎ ታሰረ appeared first on Zehabesha Amharic.


በሚኒሶታ የተደረገው ኮንሰርት ትርፍ ባይገኝበትም አዘጋጆቹ ከኪሳቸው ያዋጡት ገንዘብ ለመ/ር ዘመድኩን በቀለ ተላከ * ወለጋ ለሚገኙት የአይሲኤስ ሰለባ ቤተሰቦች ይሰጣል

$
0
0

Temesgen
(ዘ-ሐበሻ) “አንድነት” በሚል በሊቢያ በአይሲኤስ የተሰውቱን ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች በገንዘብ ለማገዝ ሜይ 23 2015 የተጠራው ኮንሰርት ትርፍ ባይገኝበትም አዘጋጆቹ ከኪሳቸው አዋጥተው ገንዘቡን ለመ/ር ዘመድኩን በቀለ ላኩ:: የሟች ቤተሰቦችን በየከተማው እየዞረ ከውጭ የተላኩትን ገንዘቦች እያደረሰ የሚገኘው መ/ር ዘመድኩን ገንዘቡን መረከቡን እና ወለጋ ውስጥ ለሚገኙ የአይሲኤል ሰለባው መንግስቱ ጋሼ ቤተሰቦች እንደሚያደርስ አስታውቋል::
ethiopians isis
መንግስቱ ጋሼ የተባለው የአይሲኤል ሰለባ ቤተሰቦቹ እስካሁን እርዳታ አለማግታቸው ሲታወቅ መምህር ዘመድኩንም በሁለት ቀናት ውስጥ ከሚኒሶታ የተዋጣውን ገንዘቡን ይዞ ወደ ወለጋ እንደሚሄድና ቤተሰቦቻቸውን እንደሚያጽናና ለዘ-ሐበሻ ገልጾአል::

የአንድነት የሙዚቃ ኮንሰርት አዘጋጆችች መካከል ዲጂ ሶሎ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጸው 100% ትርፉ በሊቢያ ለተሰዉት ወገኖች መርጃ ይውላል ተብሎ በተዘጋጀው አንድነት ኮንሰርት ከትኬት $21, 876.00 ገቢ ተገኝቷል:: ሆኖም ግን ወጪው $22,709.30 በመሆኑ ኮንሰርቱ ላይ ምንም ትርፍ አልተገኘም:: ወጪውም ለአርቲስት ተመስገን ደሳለኝ; ለምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት; ለአብዱ ኪያር, ለንጉሱ ታምራት እና ለሃፍቶም የተከፈለ $10.500; ለራስ ባንድ $2,500; ለ11 ሰዎች ዓየር ትኬት ወጪ $3,884.40; ለሆቴል $636.90; ኮንሰርቱ ለተዘጋጀበት አዳራሽ ኪራይ $3,500; ለኮንሰርት ኢንሹራንስ $413; ለሳውንድ ቴክኒሻን $945 በአጠቃላይ $22,709.30 ወጪ መውጣቱን ዲጄ ሶሎ ለዘ-ሐበሻ ገልጿል::

ይህን ኮንሰርት ያስተባበሩት ሶሎ ኤቨንትስ $500; አርቲስት ደሳለኝ ተሻለ $500; አቶ ማሙሽ አማረ $500; ፋሲል ዱባለ $500 እንዲሁም ከማስታወቂያ በተገኘ $450 በአጠቃላይ $2,400 ወለጋ ለሚገኙት የመንግስቱ ጋሼ ቤተሰቦች እንዲደርስ ለመ/ር ዘመድኩን ገንዘቡ ተልኳል:: ይህን ኮንሰርት በማስተዋወቅም ዘ-ሐበሻ ሰፊ ድርሻ ነበራት::

አቶ ሰለሞን በኮንሰርቱ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችንና መልካም ነገሮችን ሲገልጹ “አርቲስት ተመስገን ገብረ እግዚአብሄር (ተሙ) እኩለ ለሊት ላይ ገንዘቤን ካልሰጣችሁኝ መድረክ ላይ አልወጣም በማለቱና በድቅድቅ ጨለማ ካሽ ገንዘብ ለመፈለግ ሲሯሯጡ ዘፋኙ ዘይግቶ ሥራውን እንዲጀምርና ተመልካቹም ተመስገን ወደ መድረክ እስኪወጣ አላስፈላጊ መቆየት ውስጥ እንደገባ” ጠቅሰዋል:: “ከዚህ በፊት በርካታ ዘፋኞችን አምጥተናል – ሁሉም ሥራ ካለቀ በኋላ በፖስታ ገንዘባቸውን ሰጥተን አመስግነን ነው የምንልካቸው” ያሉት አቶ ሰለሞን ተመስገን በፈጠረው የገንዘቤን ካልሰጣችሁኝ መድረክ ላይ አልወጣም ግብግብ ሕዝቡ የሚገባውን ያህል በዘፋኙ ሊዝናና ባይችልም አብዱ ኪያር; ንጉሱ ታምራትና ሃብቶም መድረኩን ይዘው ቆይተዋል::

አቶ ስለሞን መልካሙን ነገር ሲገልጽ “ይህ ኮንሰርት ኪሳራው ከ$6 ሺህ ዶላር በላይ ይሆን ነበር:: በሚኒሶታ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲን ፈቃድ (ላይሰንስ) በመጠቀማችን ከትርፍ ነፃ የሆነ ኮንሰርት በመሆኑ ታክስ ከመክፈል ድነናል:: ለኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ምስጋናችንን እናቀርባለን:: ብሏል::

The post በሚኒሶታ የተደረገው ኮንሰርት ትርፍ ባይገኝበትም አዘጋጆቹ ከኪሳቸው ያዋጡት ገንዘብ ለመ/ር ዘመድኩን በቀለ ተላከ * ወለጋ ለሚገኙት የአይሲኤስ ሰለባ ቤተሰቦች ይሰጣል appeared first on Zehabesha Amharic.

ይድረስ ስለ አንዳርጋቸው –አብዩ በለው ጌታሁን

$
0
0

መቅድም

andargachew Tisgeእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተጠርጥረው በህወሃት የማሰቃያ ጉድጓድ ከተጣሉ እነሆ የዳግሚያ ስቅለት 6ኛ አመታቸው አለፈ ፡፡ ታዲያ በዚያን ሰሞን ነበር፡-

1ኛ. ጀነራሎቹ እንዴት በህወሃት የስለላ ወጥመድ ውስጥ ሊወድቁ ቻሉ?

2ኛ. ስህተቱ በማንና ምን ላይ ተሰራ? ከመካከላቸው ለህወሃት ያደረ ይኖር ይሆን? ወዘተ የመሳሰሉ ጥያቄዎችን ያለማቋረጥ አስተናግድ የነበረው፡፡

እነሆ ዛሬ እነዚህን መሰል ወሳኝና ፈታኝ ጥያቄዎች ለድርጅታዊ ወይም ለግልፅ ህዝባዊ ውይይት ቀርበው ምላሽ ሳያገኙና የእርምት እርምጃ ሳይወሰድባቸው ስድስት የድብት አመታት አለፉና ዛሬም ሌላ ዙር ክሽፈት፣ ሌላ ዙር አስጨናቂ ጥያቄና፣ ሌላ ዙር መራር መርዶ ለማስተናገድ የተገደድን ይመስለኛል፡፡

በአንፃሩ ደግሞ ዛሬ በህወሃት የማሰቃያ ጉድጓድ ውስጥ የተጣለው የግንቦት 7ቱ አቶ አንዳርጋቸው ባይሆን ኖሮ ከላይ የገለፅኳቸውን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ከስድስት አመታት በኃላ ወደ ማን ይዥጎደጉዳቸው ነበር? ብዬ መጠየቄ አልቀረም፡፡ ለምን ቢሉ እነሆ ያ! ብርቱ ጠያቂዬ ዛሬ ሊጠየቅለት ተረኛ ሆኗልና ተጠያቂነቱን ለባለተራዎቹ እነሆ በረከት እላለሁ፡፡

ዛሬ ድረስ በህወሃት አረመኔያዊ የማሰቃያ ዘዴዎች ለሚሰቃዩት ለእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ እና ጓዶቹ  መታሰቢያ ትሁንልኝ፡፡

መልካም ንባብ

ለነፃነታችን፣ ለፍትህና፣ ለዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ መገንባት ከህወሃት በተፃፃሪ ተሰልፈን ለምንታገል ሁሉ፤ መቼም ቢሆን ፀፀቱ ለማይለቀን ስህተትና ውድቀት ስንዳረግ፣ ህወሃትንና የስለላ ቡድኑን ምትሃታዊ አድርጎ ማቅረብና ውንጀላውንም ሆነ ተጠያቂነቱን ወደ አንድ ጥግ መግፋት የሚያዋጣና ከተጠያቂነት የሚያድን የብልሆች መንገድ አልመስልህ ካለኝና የ“ቀስት” መንገድ ከተኮላሸ እነሆ አስርት አመታት፤ የእነ ጀ/ል አሳምረው ፅጌ ጉዞ ከከሸፈ ደግሞ ድፍን ስድስት አመታት እንደዋዛ ነጎዱ፡፡

ፈላስፋው “ታሪክ እራሱን ደገመ፣ መጀመሪያ አሳዛኝ ቀጥሎ ቧልት በሚመስል መንገድ” እንዳለው ሁሉ የእነ ጀነራል ተፈራ ማሞ በህወሃት ወጥመድ ውስጥ የወደቁበትን አሳዛኝ እውነታ ለማወቅና የጥፋቱን ቋጠሮ ለመፍታት እንዲያ በእልህና በቁጭት ተውጦ የጥያቄ ናዳ ሲያወርድብኝ የነበረው አይታክቴው የፅጌ ልጅ ዛሬ ለህወሃት ቧልት በሚመስል መልኩ በዚያው ወጥመድ ተጠልፎ ሲሰቃይ ማየት በእጅጉ ያማል፡፡

ይህ ብርቱ ፀፀትና ህመም የሚጠግገውና የህወሃትን የጠለፋ ቡድን ከአስማተኛነት ወደ ወጀድ ጠባቂነት ማውረድ የሚቻለው፣ ከአቶ አንዳርጋቸው መጠለፍ ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ውስጣዊና ውጫዊ ጉዳዮች ግልጽነትና ተጠያቂነት ባለው ሁኔታ በመመርመር፣ የተፈፀሙትን ስህተቶች ነቅሶ በማውጣት የማያዳግም የእርምት እርምጃ መውሰድ ሲቻል ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ለዚህም ይረዳ ዘንድ በተለይም፡-

1ኛ. ድርጅታቸው ግንቦት 7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ (የአሁኑ አርበኞች ግንቦት 7) ፣

2ኛ. የህዝብ አይንና ጆሮ የሆናችሁት የእኔው ኢሳት፣ አዲስ ድምፅ ሬዲዮና፣ ሁላችሁም ነፃና የህዝብ ሚዲያዎቻችን በሙሉ፣

3ኛ. የህወሃትን ሸፍጥ በማጋለጥ የምትተጉና ለእውነት ዘብ የቆማችሁ ጋዜጠኞችና አክቲቪስቶች፣ በተለይም ጓዴ አበበ ገላው፣

እናንተ ሁላችሁ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን አያጣችሁምና ቅድሚያውን በመውሰድ የየበኩላችሁን ጥረትና ምርመራ በማድረግ የደረሳችሁበትን እውነት ወገኖቹን ከወያኔ መንጋጋ ነፃ ለማውጣት ሌት ከቀን ለሚባዝነው ወገናችሁ የማሳወቅና መጭውንም አደጋ ከወዲሁ የመከላከል ታላቅ ኃላፊነትና አደራ አለባችሁ የሚል ፅኑ እምነት ስለአለኝ፤

ይልቁንም አበው “ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ” እንዲሉ፡-

እግረ-መንገዳችንም ህወሃት መራሹን ዘራፊ ቡድንና የሚዲያ ተቋማቱን ከምንወቅስበት የግልፅነትና የተጠያቂነት በሽታ ይልቁንም “ከልማታዊ ጋዜጠኝነት” እራሳችንን እያፀዳንና ለዚህ ክስረት አስተዋፅኦ ያደረጉና ኃላፊነታቸውን በአግባቡ ያልተወጡ አካላት የድርሻቸውን በማንሳት ለህዝባቸው ያላቸውን ታማኝነትና ተጠያቂነት ማረጋገጥ ቢችሉ እሰዬው ነው፡፡

1ኛ. አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በህወሃት የስለላ ወጥመድ ውስጥ እንዴት ሊወድቁ ቻሉ?

እርግጠኛ መሆን አይቻል እንደሆን እንጂ ይህ ጥያቄ የሁሉንም ነፃነት ናፋቂና ታጋይ ኢትዮጵያዊ ህሊና በእጅጉ የሚሞግት ይመስለኛል፡፡ በተለይም ለቀጣዩ የትግል ጉዞ ትምህርት ሊሆኑ የሚችሉ፣ የህወሃትን አስማተኛነት የሚያረክስ፣ ሁሉም በህወሃትና አጋሮቹ የስለላ መረቦች ላይ በሩን አጥብቆ እንዲዘጋ የሚረዱ ቅርቃሮች ለማግኘት በሚያግዙ ተጠየቆች ላይ ትኩረት ይሰጣል የሚል ፅኑ እምነት አለኝ፡፡

የአቶ አንዳርጋቸው የየመን ጉዞ የስህተቶች ሁሉ ድምር ውጤት መቋጫ/መዳረሻ ሊሆን ይችል እንደሆን እንጂ ዋናው ስህተትና የመጀመሪያው መጨረሻ ቀደም ብሎ እንደተሰራ መገመት አያዳግትም፡፡ ከዚህም በመነሳት የፅጌን ልጅ ለክፉው አሳልፎ ሊሰጣቸው የቻለው ስህተት የትኛው/ኞቹ ነበር/ሩ?  ብሎ መጠየቅ ተገቢና ወቅታዊ ይመስለኛል፡፡

ይልቁንም አቶ አንዳርጋቸው ከማንም በተሻለ ሁኔታ የህወሃትና የአጋሮቹን የስለላ መዋቅርና አሰራር ጠንቅቀው የሚያውቁና በተለይም የየመንን መንግስትና በወቅቱ የነበረውን የአካባቢውን ተጨባጭ ሁኔታ ተንትነው የሚያስረዱ እንደሆኑ ለማመሳከር ወደ ኢሳት ማህደር ጎራ ማለቱ ከበቂ በላይ ይመስለኛል፡፡ በተለይም ይህን የህውሃት አፋኝ ቡድን ተግባራት ጠንቅቆ የሚያውቀው የግንቦት 7 “የስለላ ክንፍ” የመሪውን እንቅስቃሴና ደህንነት እንዴት ነበር የሚከታተለው? የድርጅቱ መሪ በባላንጣው የአፈና ወጥመድ እንዴት ሊታፈኑ ቻሉ? ተቀዳሚ ጥያቄዎቼ ናቸው፡፡

2ኛ. ለመታፈናቸው እነማን አስተዋፅኦ አደረጉ? ተጠያቂዎቹስ? (የወደቀችውን የመን አንድ ብያለሁ)

ሁሌም እንደሚባለውና እንደሚታመነው፣ ለህወሃት መራሹ ዘራፊ ቡድን ጡንቻ መፈርጠምና እድሜ መራዘም ከእራሱ ከህወሃትና ከግብረ-አበሮቹ ጥንካሬ ይልቅ ለነፃነት፣ ለአንድነትና፣ ለዲሞክራሲ መከበር የምንታገል ግለሰቦችና ሃይላት ድክመት ትልቁንና ዋናውን ድርሻ እንደሚይዝ ተብሎ ተብሎ ያለቀለት ጉዳይ ነው፡፡

በተለይም ተጠያቂነትንና ግልፅነትንም በተመለከተ ህወሃት ከበርሃ ጀምሮ ለሚፈፅማቸው መራር ግፍና ወንጀሎች እነሆ ዛሬም ይከሰሳል፡፡ ይወቀሳል፡፡ በሌላ በኩል ደግሞ ባለፉት 24 ዓመታት ብቻ ለተለያዩ ድርጅቶች፣ ጥምረቶች፣ ህብረቶችና፣ ቅንጅቶች መፍረስ፣ ለታጋዩ መበታተንና፣ ለነፃነት ናፋቂ ወገናችን ቅስም መሰበር አስተዋፅኦ ያደረጉና ሂደቱንም የመሩ ሁሉ ግልፅ በሆነ መንገድ ሂሳባቸውን ሳያወራርዱና ይመሩት ለነበረው ድርጅትና ህዝብ ያላቸውን ተጠያቂነት ሳያረጋግጡ ከአንዱ ወደ ሌላኛው መገለባበጣቸው ምን ያህል ትግሉን እንደጎዳውና ህወሃትን እንዳፈረጠመው በተግባር አሳይቶናል፡፡

ዛሬ ዛሬ በነፃነት ታጋዩ በኩል ለሚፈፀሙ ተመሳሳይ ክህደቶች፣ ወንጀሎችና፣ ጥፋቶች እንደ አይነታቸውና መጠናቸው ተጠያቂው አካል ተለይቶ ሊታወቅ፣ ተገቢውን የእርምት እርምጃም በወቅቱ ሊወሰድና፣ ውጤቱ እንደ አስፈላጊነቱ ለታጋዩና ለሰፊው ህዝብ ሊገለጥ ይገባል የሚለው አስተሳሰብና እምነት ገዥ ሃሳብ እየሆነ የመጣ ይመስለኛል፡፡ የመሻላችን አንዱና ዋነኛው መገለጫ ግልፅነትና ተጠያቂነት ካልሆነ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል? ደርግ ክፍል ሶስትን በላያችን ላይ ለማንገስ?

ይልቁንም በሃገርቤት በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የቆረጡትን ንፁሃን ታጋዮች በማን አለብኝነት እያፈነ፣ በውስጡ ሆነው የተቃወሙትንና ለህሊናቸው ለመቆም የተውተረተሩትን መዋጥ ስላልበቃው፤ ይኃው የሞተው እባብ እኛው ባፈረጠምናቸው ክንዶቹ ባህር ተሻግሮና ድንበሮችን አቆራርጦ በሱደንና በኬንያ ስንገረም የመን ደርሷል፡፡

ህወሃት የመን ድረስ ተጉዞ አቶ አንዳርጋቸውን ሲያፍን በወቅቱ የነበረው የየመን ብልሹና የተፍረከረከ አስተዳደር ያደረጉት አስተዋፅኦ የሚታወቅና ግልፅ ነው፡፡ ነገር ግን ሌሎች አካላት አስተዋፅኦ አላደረጉም ብሎ ማሰብ ግን ለእኔ አልተቻለኝም፡፡ ጥፋቱንም ሁሉ ህወሃትና የመን ላይ የሚጠፈጥፍ ግለሰብም ሆነ ተቋም ካለ፣ እርሱ በቀደመውና ህወሃት በመጣበት ሁሉንም ጥፋት “አማራ”ና “ደርግ” ላይ የመለጠፍ የሸፍጥና የማንአለብኝነት ጎዳና መሄድን የመረጠ ብቻ ይመስለኛል፡፡

ስለዚህም፡-

ለአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በህወሃት የአፈና ቡድን መጠለፍ አስተዋፅኦ ያደረጉ ሁኔታዎች ምንና ምን ናቸው? ተጠያቂ አካላትስ እነማን ናቸው? ድርጅታቸው ግንቦት 7 እና አመራሩስ ምን ያህሉን ድርሻ ይወስዳሉ? የኤርትራው ሰውዬስ አይመለከታቸው ይሆን? ወዘተ  . . . በማለት አቶ አንዳርጋቸውን አክዬ ስለ አቶ አንዳርጋቸው ድምፄን ከፍ አድርጌ ለመጠየቅ እገደዳለሁ፡፡

 

በመጨረሻም

ከላይ ለማንሳት የሞከርኳቸው መሰረታዊ ጉዳዮች በሚመለከታቸውና ያገባናል በሚሉ አካላት ዘንድ ተገቢውን አትኩሮትና መፍትሄ የማግኘታቸው ነገር አንድምታው የትየለሌ ይመስለኛል፡፡ ትላንተ በሌሎች የነፃነት ታጋዮች፣ ዛሬ ደግሞ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የደረሰው አፈና በፀፀት ያንገበገበን ወገኖቻቸው እሳቸውን ከወያኔ መንጋጋ ለማውጣት ከዳር እስከዳር እየታገልን ባለንበት በዚህ ሰአት በሌሎች ጀግኖቻችን ላይ ተመሳሳይ ጥፋት ሲደገም ማየትም ሆነ መስማት ፈፅሞ ልንሸከመውም ሆነ ልንወጣው ወደማንችለው አደገኛ ሁኔታ ሊከተን ይችላል የሚል ከፍተኛ ስጋት አድሮብኛል፡፡

በተለይም ለእናት ሃገራቸውና ለሚወዱት ህዝባቸው ሲሉ በኤርትራ በርሃዎች ለመሸጉት የሃገሬ እንቁዎች ቆራጥነትና ጀግንነት ለመመስከር የሚያበቃ እውቂያ አለኝና ህልማቸውን ሳያሳኩ በተለይም ተጠያቂነትና ግልፅነት በሌላው ዝርክርክ አሰራር ምክንያት አንዲሁ መንገድ ላይ የህወሃትና የግብረ-አበሮቹ የአፈና ወጥመድ ሲሳይ ሆነው እንዳይቀሩ አብዝቼ መጨነቄ አልቀረልኝም፡፡ (እነዚያን ጀግኖች ባላውቃቸው ምንኛ ደግ በሆነልኝ ነበር)

ይልቁንም በዚህ ሰሞን ከግንቦት 7 አመራሮች ጋር ጥብቅ ግንኙነት አላቸው በሚል በሱዳን መንግስት የደህንነት ኃይሎች ታፍነው ለህወሃት መራሹ መንግስት ተላልፈው የተሰጡ ወገኖቻችንና ከወደ ኬንያ ለተመሳሳይ አደጋ በመጋለጣቸው ምክንያት የምንሰማቸው የድረሱልን ጥሪዎች ስጋቴን በእጅጉ የሚያባብሱ እና ከላይ ያነሳኃቸውን ተጠይቆች የሚያጠናክሩ ሆኖ አግኝቻቸዋልሁ፡፡

እንግዲህ በተናጠልም ሆነ በተቀናጀ መልኩ የአቶ አንዳርጋቸውን ጉዳይ የሚያጣራና ከላይ ላነሳኃቸውና ሌሎች ወገኖች ለሚያነሷቸው ተመሳሳይ ጥያቄዎች ትክክለኛውን ምላሽ በመስጠት ተገቢውን የእርምት እርምጃ ለመውሰድ የሚያበረታታ፣ ግልፅነትና ተጠያቂነት የተሞላበት አስተማሪ የምርመራ ሂደት በሁሉም አካላት ዘንድ ይልቁንም በድርጅታቸው በግንቦት 7 በኩል ይወሰዳል፤ ውጤቱም ለህዝብ ይፋ ይደረጋል የሚል ታላቅ ተስፋ አለኝ፡፡ ካልሆነ ግን የተረፉና የምንሳሳላቸው ጀግኖቻችንን ለማዳን ሲባል ወደ እየራሳችን መላምታዊ የትንተና መንገድና የእርምት እርምጃ እንዳይወስደን እሰጋለሁ፡፡

ክብር ለኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች

አብዩ በለው ጌታሁን

ሰኔ 2007

 

 

 

The post ይድረስ ስለ አንዳርጋቸው – አብዩ በለው ጌታሁን appeared first on Zehabesha Amharic.

የማለዳ ወግ …በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ ! (ነቢዩ ሲራክ)

$
0
0
* የእናት 9 ዓመት ሰሚ ያጣ ጩኸት
* እናት አንጀቷን አስራ የፍትህ ያለህ ስትል ዛሬም ታነባለች
* ፍትህ ዘግይቶ ጎድቷታል …አለፋ ስቅተቷ በዝቷል
* ፍትህ የሚያስገኛት ፣ ግፉን የሚያስቆመው ጠፍቷልMinilikየ4 ዓመት ደልዳላ እያለ ድክ ድክ እያለ ሮጦ ለቀላል ህክምና ከጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት አፍንጫ ስር በሚገኝ አንድ ሆስፒታል ገባ ። ብዙም ሳይቆይ ከሰመመን መንቃት አልችል አለ ፣ ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ከሰመመን አልነቃም ፣ በሃኪሞች ስህተት ብላቴናው መሀመድ ህይዎቱ ተሰናክሎ ላለፉት 9 ዓመታት የአልጋ ቁራኛ ሆነል።   ትናንትም ሆነ ከትናንት በስቲያም መሀመድና ቤተሰቦቹ ፍትህ ርትዕ ያገኙ ዘንድ ደጋግሜ ጠይቄያለሁ  ፣ ዛሬም እጠይቃለሁ ! ላለፉት በዘጠኝ አመታይ ከጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች ጀምሮ ሳይኖር ” አለሁ ” እስከሚለን  የሴቶች ማህበር ተወካዮች ፍትህን ለመሀመድ ያስገኙ ዘንድ ተደጋጋሚ ጥያቄ ቀርቦ ፍትህ ማስገኘት ገዷቸዋል ፣ ተበዳዮች ፍትህ  ርቋቸዋል  … !

ክልትሙ ተንከባሎ ዛሬ ላይ ሲደርስ …
========================

ታሪኩን ከመሀመድ እናት ቃል በቃል ስሙት ፣ እኔ መግቢያየን አጠር ላድርገው … ከዚህ ሁሉ አመት በኋላ የብላቴናው መሀመድ አብድልአዚዝ ቤተሰቦች ደጋግመው ያደረጉት ውትወታ በቀደም የጅዳ ቆንስል ኃላፊዎች ተቀባይነት አግኝቶ አያውቅም ።  ለአዲሱ አንባሳደር የቀረበው አቤቱታ ተቀባይነት አገኘና በጉዳዩ ላይ ክትትል መጀመሩን ተመለከትን ።  ቆንስል መስሪያ ቤቱ ጉዳዩን በያዘው ማግስት ደግሞ ለ9 ዓመት የዋለለው የፍትህ ጥያቄ መልስ አገኘ  ! አዎ …  በአሳር በመከራ ለመሃመድ ቤተሰቦች ያለማሰለስ ባደረጉት ጉትጎታ 2.5 ሚሊዮን የሳውዲ ሪያል ካሳ እንደሚሰጥ በሳውዲ ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አንድ አጣሪ ኮሚቴ ውሳኔ ተላለፈ ። ውሳኔው ባይከፋም ለሰዓታት ከመተንፈሻ መሳሪያ ውጭ መንቀሳቀስ የማይችለው ብላቴ ቤተሰቦች የተወሰነውን ካሳ ተቀብለው ከሀኪም ቤቱ እንዲለቁ የተላለፈውን ፍርደ ገምድል የወላጅ ቤተሰቦች ተቃወሙት! በሰጠናቸው መረጃ መሰረት በውሳኔ አሰጣጡ ሂደት የተገኙት የጅዳ ቆንስል ተወካይም የወላጆችን ውሳኔ በመደገፍ የውሳኔውን ፍትሃዊ አለመሆን ሳይቀበሉ ቀረ   ! ውሳኔ ያሳለፈው ኮሚቴ በህክምና ስህተት መሀመድ በደል የደረሰበት መሆኑን የሚያረጋግጠው ሰነድና ሙሉ ውሳኔ በአስር ቀናት ውስጥ ለወላጅና ለቆንስል መስሪያ ቤቱ እንደሚሰጥ ፣ አስፈላጊ ነው ካሉ  ወደ ፍርድ ቤት መውሰድ እንደሚቻል  ተገልጾ ጉዳዩ በተያዘው ቀጠሮ ተዘጋ … ይህ የሆነው ከወራት በፊት ነበር  !

ህግ አስከባሪ የማጣት እንቆቅልሽ  !
======================

ዛሬስ  ?  ዛሬ የተገባው ቃል የማይጨበጥ ፣ የማይዳሰስ ጉም ሆኗል ፣ ቆንስል መስሪያ ቤቱ በውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኩል አቀርብኩት ያለው አቤቱታ መልስ አላገኘም ፣  ወላጆች ላፍታ ከመድሃኒትና ከህክምና ውጭ መቆየት የማይችለውን መሀመድን ይዘው እንዲዎጡ እየተወተወቱ ነው!  እናት ልጇቸውን በቅርብ እንዲያስታምሙ ከተሰጣቸው ማደሪያ በኃይል እንዲለቁ ተገደዋል ፣ መጠለያውን በጸጥታ አስከባሪዎች እንዲለቁ ሲደረግ ለቆንስል መስሪያ ቤቱ  ቢያመለክቱም መጠለያውን ከመልቀቅ አልታደጓቸውም ! የሳውዲ መንግስት የጤና ጥበቃ መስሪያ ቤት አጣሪ ቡድን  ያረጋገጡት ግፍ ተፈጽሞ የመሀመድ ቤተሰቦች በተለይም ብርቱዋ እናት  ዛሬም ድረሱልኝ እያሉ ነው  !  ቆንስል መስሪያ ቤቱም ፣ የተላለፈውን የውሳኔ ሰነድ ተረክቦ ጉዳዩን ወደ ፍትህ አካላት ማቅረብ ተስኖታል  ! የጎደለባቸው ፍትህ እንዲሰፍን ዛሬም ተገፊዋ ይጮሃሉ … “ቄሱም ዝም መጽሐፉም ዝም !”  የሆነበት እንቆቅልሽ ግን አልገባን ብሏል  !

እንኳንስ ይህም መሰል ግፍ ተሰርቶ በአደባባይ ተፈጽሞባቸው ፣ በከባድ የሳውዲ መንግስት ከፍተኛ ኃላፊዎች የተፈጸመ የህግ ጥሰት የሚሸፋፍን የህግ ስርአት ሳላለመኖሩ ብዙ መረጃ ማቅረብ ይቻላል ።  የቀደመውን ትተን ዛሬ የወጣውን የሳውዲ ጋዜጥ ብንመለከት ያን ሰሞን በሳውዲ አየር መንገድ ተጓዠ የነበሩ ሁለት ታዳጊዎችን ደፍረው የተመሰከረባቸው ሁለት የአየር መንገዱ የጸጥታ ሰራተኞች የአራት አመት እስራትና 1000 ጅራፍ ተፈርዶባቸዋል  ! የእኛ ብላቴና መሀመድ ስቃይና የወላጆቹ አቤቱታ ጉዳይ ግን ጠያቂ አጧቷልና  ህግ ፊት እንኳ የሚያቀርበው ጠፍቷል  ! ስለሆነም  የዜጎች መብት የሚያገባቸው አካላት የት አሉ  ?  ብለን እንጠይቅ ዘንድ እንገደዳለን  !

ስለ ጎደለብን ፍትህ መከበር  እንናገር  !
=========================

ለሰብዕናና ለፍትህ ቀናኢ አይደለንም ፣  በሳውዲ አረቢያ የከተመው ነዋሪ ከኮሚኒቲ አባልነት ሸሸቷል ፣ የጅዳና የሪያድ ኮሚኒቲዎች የአባላት ድርቅ የመመታታቸው ሚስጥር ተአማኒነት ማጣት እንጅ ” ቡዳ ” በልቷቸው አይደለም ፣ ባሳለፍናቸው በርካታ አመታት ተወካዬዮቻችን ማህበራት ምስረታ አድርተው ትልቁን ኮሚኒቲ  አኮላሸተውታል ፣ እናም እላችኋለሁ ፣ ለሰው መብት መቆምን ፈነጋግላችሁ የልማት ማህበራት እንደ እንጉይ የመፈልፈሉ የመጠመዳችሁን አደጋ  ዛሬም በውል ያልታያችሁ ጉዳይ ፈጻሚ የመንግስት አካልት አካሄዳችሁን ልትገመግሙ ግድ ይላል ። ከምንም በላይ ዘንድሮ በተሃድሶ ላይ ነው የምንለው ቆንስል መስሪያ ቤት መመሪያ ወርዶ እያስፈጸመ ቢሆንም መልሶ ከዳጡ ወደ ማጡ እንዳይወድቅ እሰጋለሁ  !  ለተገፊው መሀመድ ፍትህ ማግኘት ሁላችን ልንተጋ ግድ ይለናል ፣ ቢያንስ ጉዳዩን ወደ ፍትህ አካል ይቀርብ ዘንድ ሁላችንም የቻልነውን ከማድረግ ጎን ለጎን መሀመድን በጸሎት ታስቡት ዘንድ አደራየ የጠበቀ ነው !

ተወካዮቻችን የግፉአንን እንባ በመጥረጉና መብትታቸውን በማስከበሩ ሰናይ ምግባር ቆመው አለማየታችን የምስኪኗ የመሀመድ አብድልአዚዝ እናት እንባ የሚነግረን እውነታ አይጠፋም  ! ” ስለ እውነት እንመስክርና የመጣው ይምጣ ! ”  ማለትን ለደፈረ ባለፉት በርካታ አመታት በዋነኛነት የዜጎች መብት የቆሙት ተወካዮቻችንም ሆነ የሚያደራጇቸው ማህበራት  ድግስ እየደገሱ በስሙ ገንዘብ ከመሰብሰብ ያለፈ ስራ ሰሩ ቢባል ለህዳሴውን ግድብ አደረጉ የሚባለውን ድጋድ ብቻ ነው የምናገኘው  ! ለሀገር ግንባታ ፣ ለልማትና ድንበሩ ተደፈረ ሲባል ለሀገሩ ቀናኢነት የሚያሳየው ዜጋ ፍትህ እጦት ግን ዛሬም ተዘንግቷል …! ይህ በጣሙን የሚያም ፣ ሲነገሩት እንኳ መስዋዕትነትን የሚያስለፍል እውነታ ቢሆንም ነግ በኔ ነውና እኔ የምፈራው መከፈል ያለበት መስዋዕትነት የለም ፣ ከልጆቸ ፣ ከሞቀው ቤቴና ከከባቢው የተረጋጋ ኑሮየ   እሰናከል ይሆናል ፣ ይህ ሁሉ ግን እውነቱን በተጨባጭ መረጃ ከመናገር ላፍታም ያህል አይገታኝም  ! እውነቱን ተናግረን ከመሸበት እንደር …ስለ ፍትህ መከበር  እናገራለሁ  ! እናንተም ተናገሩ  !

በእሱ ስራ አንገባም ፣ የዘገየው ፍትህ ይሰፍን ዘንድ ለፈጣሪ አቤት እንላለን  ፣ መልስም እናገኛለን  !  ምድራዊ ነንና የተወካዮቻችን ጀሮ የተፊዎችን ድምጽ ይሰማ ዘንድ ከመማለዱ ጎን እንደ ፍጡር የፍትህ ማስከበር ጥሪያችን ትሰሙ ዘንድ እንማለዳችኋለን    !

የየራስ ፍርዳችሁን ስጡ ፣ እኔ እንዳገባኝ እናንተም ያገባኛል ካላችሁ  ፣ የማቀርበውን ጭብጥ መረጃ ፣ ስለ ሰነብአዊ መከበርና ስለ ፍትህ መረጃውን እየተቀባበላችሁ ጩኹት  … የተነፈግነውን ፍትህ ማግኘት እስክንችል  :(  የእናት ፍቅርን የምታውቁትም ሆነ የማታውቁ  ፣ የእናት አንጀትን መላወስ ህመም ጠልቆ የሚሰማችሁትም ሆነ ስሜቱን የማይገባችሁ ፣  የምትወዱትን ነገር በግፍ ስለመነጠቃችሁ እያሰባችሁ ስለ መሀመድና ስለ ግፉአን ቤተሰቡ ፍትህ ማግኘት አቤት ትሉ ዘንድ አደራ እላችኃለሁ . .. !

በሳውዲ መንግስት ጤና ጥበቃ ሚኒስትር አጣሪ ኮሚቴ በህክምና መሰናከሉ የተረጋገጠው የብላቴናው  ጉዳት ዛሬ ላይ ሲደርስ ፍትህ እጦቱ አንገሽግሾናል  ፣ ብላቴናውና ቤተሰቦቹ ፍትህ ይሻሉ ፣ እኛ የወገናችን ጉዳይ ያገባናልና ፍትህ ፣ እንሻለን ፣ ፍትህ ናፍቆናል   ! ጉዳዩን ወደ ፍትህ አቅርቡልን  !

ቸር ያሰማን  !

ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓም

( ሙሉ የመሀመድን እናት ቪዲዮ ከፊስ ቡክ ገጼ ማግኘት ትችላላችሁ  )

The post የማለዳ ወግ … በብላቴናው ላይ የዘገየው ፍትህ ! (ነቢዩ ሲራክ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ዶ/ር ዳኛቸዉ አሰፋ በ15 ቀናት ውስጥ የዩኒቨርሲቲውን ቤት እንዲያስረክቡ ደብዳቤ ደረሳቸው

$
0
0

Dr Dagnachew
(ዘ-ሐበሻ) ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ ከሦስት ዐሥርት ዓመታት የአሜሪካ ቆይታ በኋላ በሚሌኒየሙ መባቻ ወደ አገራቸው ተመልሰው ላለፉት ሰባት ዓመታት በማስተማር ሥራ ላይ ቆይተዋል፡፡ ምሁሩ በዋናነት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የፍልስፍና መምህር ቢኾኑም በሕግ ፋክልቲ፣ በሴንተር ፎር ሂዩማን ራይትስ፣ በኢትዮጵያ ጥናትና ምርምር ተቋም፣ በአምስት ኪሎ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፋክልቲ፣ በቴአትሪካል አርትስና በያሬድ የሙዚቃ ት/ቤትም አስተምረዋል፡፡ ለሰባት ተከታታይ ዓመታት በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች በተለያየ ጊዜ ሲያስተምሩ ቢቆዩም ከጠየቁት የዓመት ዕረፍት(sabbatical leave)ን እንደምክንያት በማድረግ ለሃገራቸውን ለወገናቸው ያላቸው ተቆርቋሪነት በስር ዓቱ አልወደድ በማለቱ ከዩኒቨርስቲው መሰናበታቸው ይታወቃል::

አሁን ደግሞ ግንቦት 29 በተጻፈ ደብዳቤ ዩኒቨርሲቲው የሰጣቸውን ቤት በ15 ቀናት ውስጥ ለቀው እንዲወጡ የሚያሳስብ ደብዳቤ ደርሷቸዋል:: (ደብዳቤውን ይመልከቱና ከታች የዶ/ር ዳኛቸውን ምላሽ ያንብቡ)
Dr. Dagnachew Asefa
ዶ/ር ዳኛቸዉ አሰፋ ለዩኒቨርሲቲው ቤቶች አስተዳደር ያስገቡት ደብዳቤ፣
ሰኔ 4 ቀን 2007 ዓ.ም
ለ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቤቶች አስተዳደር መምሪያ
አዲስ አበባ
ከ፦ ዶ/ር ዳኛቸዉ አሰፋ
ጉዳዩ፦ ቤት የማስረከብን ሁኔታ ይመለከታል፡፡

ከሁሉ አስቀድሞ “ከመስከረም 2002 ዓ.ም ጀምሮ ዩኒቨርሲቲዉ እንደማንኛዉም የዬኒቨርሲቲዉ መምህራን ቤት ሰጥተዎት” የሚለዉ ገለፃ በከፊል እዉነት ሲሆን የገባሁበት ቀንና ዓመተምህረት የናንተዉ መስሪያ ቤት ባዘጋጀዉ ሰነድ ላይ ተመዝግቦ እያለ፤ “ከ2002 ዓ.ም ጀምሮ” የዩኒቨርሲቲዉ ቤት ዉስጥ ትኖር ነበር ብላችሁ የተሳሳተ የግዜ አሃዝ ማስቀመጣችሁ ግምታዊና ሙያዉ የሚጠይቀዉን አሰራር እንደማታሟሉ ይጠቁማል፡፡

ግንቦት 28 ቀን 2007 ዓ.ም በቁጥር ቤአ/259/2007 በተጻፈ ደብዳቤ የምኖርበትን ቤት እስከ ሰኔ 15 ቀን 2007 ዓ.ም ማለትም በ15 ቀን ዉስጥ እንዳስረክብ የጠበቀ ማሳሰቢያ ደርሶኛል፡፡ ይህንንም ተግባራዊ ለማደረግ እንደምክንያት የቀረበዉ ዩኒቨርሲቲዉ በ15/01/2015 በተመራ ደብዳቤ “በጡረታ የተገለልህ” በመሆንህ በሚል ሰበብ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ ይህንን ደብዳቤ በጣም አስገራሚ እና ከእውነት የራቀ የሚያደርገዉ ከላይ በተጠቀሰዉ ቀንም ሆነ ይህንን ደብዳቤ እስካረቀቅሁበት ጊዜ ድረስ ለእኔም ሆነ ለትምህርት ክፍሉ ኃላፊ እንዲሁም ለማህበራዊ ሳይንስ ኮላጅ ዲን ጡረታ መዉጣቴን እና ኮንትራቴ እንዳማይራዘም የሚያበስር ደብዳቤ እንዳልተፃፈ እና እንዳልደረሰ በእርግጠኝነት መናገር ይቻላል፡፡ እዉነታዉ ይህ ሆኖ እያለ ተፃፈ የተባለዉ ደብዳቤ ለእኔ ለባለጉዳዩና ኮንትራቴ እንዲራዘምልኝ በአጽንኦት ለጠየቁልኝ የትምህርት ክፍልና ለማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ ሳይደርስ ለእናንተ አስተዳደር (ቤቶች አስተዳደር መምሪያ) ደርሶናል ማለታችሁ እንቆቅልሽ ነዉ፡፡ በመሆኑም ለእኔ ባልደረሰኝና በማላውቀው፣ ምንአልባትም እርስ በርሳችሁ በተጻጻፋችሁት ሰነድ ላይ ተመርኩዛችሁ በ15 ቀን ዉስጥ ቤቱንና ቁልፉን በአስቸኳይ አስረክበህ ዉጣ የሚል አስተዳደራዊ ደብዳቤ መጻፋችሁ ለህግና ለሞራል ተገዥ አለመሆናችሁን ያሳያል፡፡

በተጨማሪም በ15 ቀን ዉስጥ የተባለዉን ዉዝፍ የቤት ኪራይ (3‚300 ብር) እና መብራትና የዉሃ ፍጆታ ከፍዬ እንድወጣ ከላይ እንደጠቀስኩት ትዕዛዝ ተሰጥቶኛል፡፡ ይህንን ጉዳይ በሚመለከት ሦስት ነጥቦችን አቅርቤ ደብዳቤዬን መዝጋት እፈልጋለሁ፦

1ኛ/ እንደሚታወቀዉ ቤት አከራይ ተከራዩን ከተከራየዉ ቤት ለማስለቀቅ ቢያንስ 3 ወራት ያህል ጊዜ መስጠት ይጠበቅበታል፡፡ይሁን እንጂ ለእኔ የተሰጠኝ ጊዜ ከላይ የተጠቀሰዉን ትዕዛዝ ለመፈጸም በቂ ስላልሆነ ህግና ደንቡ በሚፈቅደዉ መሰረት ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠኝ ስል እጠይቃለሁ፡፡

2ኛ/ ከላይ አለብህ ተብሎ የተጠቀሰዉን ገንዘብ ለመክፈል ፈቃደኛ መሆኔን እየገለጽሁ ዶ/ር ሁሴን ጀማ (አካዳሚክ ስታፍ አፌርስ ዳይሬክተር) ጡረታ የወጣህበትን ወረቀት ካላመጣህ በሚል ፈሊጥ ያስተማርኩበትን ገንዘብ (14ሺህ) እና ዶ/ር ተመስገን ቡርቃ (አሶሺዬት ዲን እና የ2007 ዓ.ም የኢህአዴግ ለፓርላማ ምክር ቤት ተመራጭ) አግባብ በሌለዉ መንገድ የያዙብኝን ተጨማሪ 14ሺህ ብር ፣እንዲሁም ሁለት በድህረ-ምረቃ ፕሮግራም ያስተማርኩበትን ተጨማሪ 28ሺ ብር፤ በድምሩ 56 ሺህ ብር ዩኒቨርሲቲው ቢከፍለኝ ያለብኝን ኃላፊነት በጊዜዉ መወጣት ያስችለኝ ነበር፡፡

3ኛ/ ከላይ ያቀረብኳቸው ሁለት ነጥቦች መሠረታዊ ቢሆኑም እጅግ የሚያሳዝነው ጉዳይ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር በዜጎች መካከል የሚፈጥረው ልዩነትና እድሎ ነው፡፡ ለዚህም ማሳያ እኔ በምኖርበት ህንጻ ላይ በተለያየ ምክንያት ከዩኒቨርሲቲው ለቀው እንዲያውም የተሻለ ገቢ የሚያገኙ ሰዎች፣ ከዩኒቨርሲቲው ቤት እንዲለቁ ሳይደረግ በዩኒቨርሲቲው ድጎማ እየኖሩ፤ በተናጠል እኔ ከቤት በጥቂት ቀናት ውስጥ ለማባረር መደረጉ ነው፡፡በመሆኑም የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር የመንግሥትን ንብረት እንደራሱ በመቁጠር በፖለቲካ የሚጠላቸዉን ዜጎች ማጥቂያ ማድረጉን ማቆም እንዳለበት ይሰማኛል፡፡ ሆኖም ግን ሹመኞቹ ከኢሞራላዊ አሰራር የፀዱ እንዳይሆኑ በላያቸዉ ላይ የሰፈረዉ የትዕዛዝና የጥቅም መስተጋብር እንደሚከለክላችዉ መረዳቱ አያዳግትም፡፡በጎ ነገሮች ይመጣሉ በሚል በተስፋ ላይ ተስፋ ሰንቀን ብንጓዝም ከዩኒቨርሲቲው የአመራር ለውጥ ጋር ተያይዞ የሥርዓት ለውጥ ይመጣ እንደሁ እንጂ አሁን ባለው ሁኔታ ምንም ዓይነት ለውጥ እንደማይመጣ ልቦናችን ይነግረናል፡፡
ከሰላምታ ጋር
ግልባጭ
• ለፕሬዝዳንት ጽ/ቤት
• ለአስተዳደር እና ተማሪዎች አገልግሎት ም/ፕሬዝዳንት
• ለፋሲሊቲ ማኔጂንግ ዳይሬክተር
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

The post ዶ/ር ዳኛቸዉ አሰፋ በ15 ቀናት ውስጥ የዩኒቨርሲቲውን ቤት እንዲያስረክቡ ደብዳቤ ደረሳቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

በጊቢ ገብርኤል አካባቢ በተነሳ ቃጠሎ ካለቅያሪ ልብስ የቀሩ 25 ሰዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው

$
0
0

wereda 8

wereda 8 addis

wereda 8 addis ababa

wereda 8 gibi geberil

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ወረዳ ስምንት በተለምዶ ጊቢ ገብርኤል አካባቢ ተብሎ በሚጠራው ሰፈር በደረሰ የ እሳት አደጋ ቤታቸው የወደመባቸው ወገኖቻችን ለወገኖቻቸው የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ::

የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች አካባቢውን ሄደው ከጎበኙ በኋላ እንደጠቀሱት ሰኔ 3 ቀን 5 ሰዓት አካባቢ በደረሰው ቃጠሎ 25 ሰዎች ንብረታቸው እና ቤታቸው ወድሞባቸው ካለቅያሪ ልብስ ቀርተዋል::

የዚህ የ እሳት አደጋ መንስ ኤ ምን እንደሆነ ገና እየተጣራ መሆኑን የጠቀሱት የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ነዋሪዎቹ በአሁኑ ወቅት ወረዳ 8 ላይብረሪ ውስጥ ተጠልለው እንደሚገኙና የወገኖቻቸውን እርዳታና ማጽናናት እንደሚሹ ተገልጿል::

በ እሳት አደጋው ጉዳት ከደረሰባቸው መካከክል ስሜ እንዳይጠቀስ የተፈለገች እህት በቅርቡ ወደ ቻይና ለመሄድ በዝግህት ላይ የነበረች ቢሆንም ሁሉም የመጓጓዣ ዶክመንቶቿ በአደጋው ቃጠሎ እንደደረሰበት ለማወቅ ተችሏል::

The post በጊቢ ገብርኤል አካባቢ በተነሳ ቃጠሎ ካለቅያሪ ልብስ የቀሩ 25 ሰዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ በጀርመን እና በአካባቢው ለምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያ ወዳጆች

አልሸባብ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በደፈጣ ውግያ ገደልኩ አለ * የጦር መሳሪያም ማርኬያለሁ ብሏል

$
0
0

ethiopian somalia copy
(ዘ-ሐበሻ) በአሸባሪነት የተፈረጀው የሶማሊያው አልሸባብ በሞቃዲሾ አቅራቢያ 30 የሚሆኑ ወታደሮችን መግደሉን አስታወቀ::

ዘ-ሐበሻ ከአፍሪካ ሕብረት የሰላም አስከባሪ ሃይል መረጃ መረብ ባገኘችው መረጃ መሠረት የሰላም አስከባሪው ሃይል 30 ኢትዮጵያውያን ወታደሮች መሞታቸውን ያመነ ሲሆን ጉዳዮችን እየመረመርኩ ነው ብሏል::

የሶማሊያ ሸማቂ ቡድን አልሽባብ ሞቃዲሾ አቅራቢያ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በደፈጣ ጥቃት ገድሎ ከባድ የጦር መሳሪያና ተሽከርካሪ መማረኩን አስታወቀ። የአፍሪቃ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል በኢትዮጵያውያኑ ወታደሮች ላይ ጥቃት መፈፀሙን አምኖ የደረሰውን ጉዳት እያጣራሁ ነው ብሏል።

ኢትዮጵያውያን ወታደሮች ለሰላም ማስከበር ወደ ሶማሊያ ሄደው ሕይወታቸው ሲያልፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም:: ከዚህ ቀደም እነዚሁ ወታደሮች በሶማሊያ አደባባይ ላይ ሬሳቸው ሲጎተት የሚያሳየው አሳዛኝ ክስተትን ማየታችን የሚታወስ ነው::

The post አልሸባብ 30 የኢትዮጵያ ወታደሮችን በደፈጣ ውግያ ገደልኩ አለ * የጦር መሳሪያም ማርኬያለሁ ብሏል appeared first on Zehabesha Amharic.


18ኛው የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመጀመርያ ጊዜ በጀርመን ሃገር ፍራንክፈርት ከተማ (ማስታወቂያ)

$
0
0

Europe
18ኛው የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመጀመርያ ጊዜ በጀርመን ሃገር በFrankfurt am Main ከተማ ይዘጋጃል::

በዚህም ጉባኤ ላይ በአውሮፓ፤ በምሥራቅና ደቡብ አፍሪቃ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ ከልዩ ልዩ አብያተ ክርስቲያናት ከሚመጡ አባቶችና ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ጋር ይገኛሉ::

እንዲሁም ለዚህ ጉባኤ የተጋበዙት ታዋቂ መምህራን:
– የዘመኑ ሃዲስ ሃዋርያ አባ ወልደትንሣኤ አያልነህ
– መምህር ቀሲስ ጸዳሉ አለባቸው እና
– መምህር ጥበቡ ቢሰጠኝ ሲሆኑ

የተጋበዙት ዘማርያን ደግሞ:
– ሊቀ መዘምራን ዲ/ን ታዲዮስ ግርማ እና
– ሊቀ ልሳናት ቸርነት ሰናይ በተሰጣቸው ጸጋ ለማገልገል በዝግጅት ላይ ናቸው፡፡

ጉባኤውም የሚካሄደው ከሐምሌ 3 – 5 ቀን 2007 ዓ. ም (July 10 – 12, 2015) ነው፡፡

ጉባኤው የሚካሄድባቸው ቦታዎች:-

– የአርብ ጉባኤና የእሁድ ቅዳሴ:
የFrankfurt ምስካዬ ኅዙናን መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን የምንገለግልበት ቤተ ክርስቲያን:
Philipp-Fleck-Str.13,60486 Frankfurt am Main

-ቅዳሜ ሙሉ ቀን እና እሁድ ከቅዳሴ በኋላ:
Frankfurt Bonames የሚገኘው Saalbau Nidda, Harheimer Weg 18, 60437 Frankfurt am Main

ስለዚህ የዚህ ታላቅ መንፈሳዊ ጉባኤ ተሳታፊ እንዲሆኑ በእግዚአብሔር ስም ተጋብዘዋል።

The post 18ኛው የአውሮፓ መንፈሳዊ ጉባኤ ለመጀመርያ ጊዜ በጀርመን ሃገር ፍራንክፈርት ከተማ (ማስታወቂያ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ተከበረ * አላሙዲ 5 ሚሊዮን ብር ሸለሙት

$
0
0

 

(ዘ-ሐበሻ) የትዝታው ሙዚቃ ንጉሥ የሚል የክብር ስያሜን ከኢትዮጵያውያን የተጎናጸፈው ዝነኛው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ዘመኑ ተከበረ::

ማምሻውን በሸራተን አዲስ በተከናወነው በዚሁ የማህሙድ አህመድ የሙዚቃ ዘመን 50ኛ ዓመት ልደት ላይ ድምፃዊውን የሚዘክሩ የተለያዩ ፕሮግራሞች ከመቅረባቸውም በላይ ድምፃዊውም ሥራዎቹን ለሕዝቡ ማቅረቡን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ጠቆሟል::

በዚሁ ምሽትም ለ50 ዓመት የሙዚቃ አገልግሎቱ ከሼህ መሃመድ አላሙዲ የ5 ሚሊዮን ብር ስጦታ እንደተበረከተለት ለማወቅ ተችሏል::

የማህሙድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ ሕይወት በራሱ አንደበት እንደሚከተለው ዘ-ሐበሻ አሰናድታዋለች:: ይከታተሉት::
Mahamud Ahemed 2

ትውልድና ዕድገት
ቤተሰቦቼ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ነበሩ፡፡ አሁን በሕይወት የሉም፡፡ የተወለድኩት አሜሪካ ግቢ በ1933 ዓ.ም ነው፡፡ እስከ ሶስት ዓመቴ ድረስ አሜሪካ ግቢ ካደኩ በኋላ በሶስት ዓመቴ ወደ ጉለሌ አርበኞች ት/ቤት ፊትለፊት ያለው ኦሎምፒያ ኳስ የሚባል የግሪክ ክለብ ነበር እዚያ ውስጥ አባቴ ይሰሩ ነበር፡፡ በዚያ ስፖርት ክለብ ውስጥ እየሄድኩ የቅርጫት ኳስ፣ የእጅ ኳስ ሜዳ ስፖርተኞች ከተጫወቱበት በኋላ ሜዳውን ውሃ እያጠጣሁ እየደመጥኩ አስተካክል ነበር፡፡ አባቴ በሌሉበት ጊዜ የዚያ ስራ ሀላፊነት የኔ ነበር፡፡

ትምህርት ቤት

ትምህርት ቤትን በተመለከተ ብዙ ባይገባኝም መማር ጀምሬ ነበር፤ ትምህርት ቤት ስገባ ምናልባት 8 ዓመት 9 ዓመት ይሆነኝ ይሆናል፡፡ ቄስ ት/ቤትም ከጓደኞቼ ጋር ገብቼ ነበር፤ መጀመሪያ በእርግጥ ሙስሊም ት/ቤት ነበርኩ፡፡ ወደ 15 ዓመት ሲሆነኝ አባቴ የሚሰሩበት የግሪክ ክለብ ሲዘጋ ስራ ፈቱ፡፡ ከእናቴ ጋር ሆኜ የቤተሰቡን ህይወት ለማገዝ ከእናቴ ጋር ብታምኑም ባታምኑም ጉሊት ቁጭ ብዬ እንጀራ እሸጥ ነበር፡፡ ወደ ጫካ ሄጄ ጭራሮ ና ማገዶ ለቅሜ በማምጣት ለእናቴ እንጀራ መጋገሪያ አቀርብላት ነበር፡፡
በዚህ ሁኔታ ለ6 ዓመት ያህል ትምህርት ቤት እየሄድኩ ስመለስ ሊስትሮ ሆኜ ጫማ እጠርግ ነበር፡፡ ከጓደኞቼ መሀከል ሰነፉ ተማሪ እኔ ነበርኩ፡: ጥያቄ ሲቀርብ ግን የምመልሰው እኔ ነበርኩ፡፡ ግን ፈተና ላይ ስንቀመጥ ነርቨስ ስለምሆን መስራት አልችልም ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ መማር መቀጠል አልቻልኩም፡፡

ሊስትሮና ሙዚቃ

ማታ ማታ እናቴ ዘፈን ታንጎራጉር ስለነበር ስሜቴ ሁሉ ወደ ሙዚቃ ሆነ፤ በ1949 ዓ.ም የንጉሰ ነገስቱ የክብር ዘብ ግቢ ውስጥ የጠቅል ሬዲዮ የሚባል ነበረ፤ ማክሰኞና ሀሙስ ዘፈንና አንዳንድ ፕሮግራሞች ይለቀቁ ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ በሬዲዮ ቀርበው ይዘፍኑ የነበሩት እነ ካሳ ተሰማ፣ ተዘራ ሀ/ሚካኤል፣ መቶ አለቃ ኑር ወንዳፍራሽ (የብዙነሽ በቀለ የልጆቿ አባት የነበረው) ብዙነሽ በቀለ፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ አየለ ማሞ፣ እሳቱ ተሰማ ወዘተ ነበሩ፡፡ የዚያን ጊዜ እነዚህ ድምፃውያን በሳምንት ሁለት ቀናት ሙዚቃቸውን እየመጡ ያሰሙ ስለነበር እኔ ቡና ቤት በር ላይ ሊስትሮ ሳጥኔ ላይ ቁጭ ብዬ ዘፈናቸውን አዳምጥ ነበር፡፡ የሚገርማችሁ ማታ የሰማኋቸውን ዘፈኖች ጠዋት ት/ቤት ከመግባታችን በፊት ለክፍል ጓደኞቼ እዘፍንላቸው ነበር፡፡

በወቅቱ ሞዴሌ አድርጌ የምቆጥረው ትልቁ ወንድሜን በአሁኑ ወቅት በዚህ ዓለም ላይ የሌለው ጥላሁን ገሠሠ ነው፡፡ ሌላ ደግሞ በወቅቱ ከውጪ ሀገር የሚመጡ ፊልሞችን እመለከት ስለነበር በተለይ የኤልቪስ ፕሪስሊንን ዘፈን አዳምጥ ነበር፡፡ ኤልቪስ ፕሪስሊን ሲዘፍን እግሩን እንዴት ያንቀጠቅጥ እንደነበር በፊልም ላይ እመለከት ስለነበር እኔም ወደፊት መድረክ ላይ ስወጣ እግሬን አንቀጠቅጣለሁ እል ነበር፤ የኤልቪስ ፕሪስሊንን ብቻ ሳይሆን የነ ሳምኩክን፣ የነ ጀምስ ብራውንን ዘፈኖች አዳምጥ ነበር፡፡
ወደ ሙዚቃው እየተሳብኩ ስመጣ የትምህርቱ ነገር እየቀረ መጣ፤ ከ8ኛ ክፍል በላይ ማለፍ አልቻልኩም፡፡ ጎረቤታችን ወ/ሮ የሺሀረግ ለእኛ የሰጡን አራት በአራት የምትሆን አንድ ክፍል ነበረችን፡፡ ጎረቤታችን አንድ ግብፃዊ ጠበቃ ነበር፤ ያ ጠበቃ ሹፌሮች ቡና ቤት ከሚባለው ቤት ባለቤት ጋር በመሆን ራስ ሀይሉ ቤት ውስጥ ናይት ክለብ ሊጀመር ነው የሚል ወሬ ስሰማ ለእናቴ ሄጄ ሥራ እንዲያስገባኝ ለምኚልኝ አልኳት፡፡ እሷም እሺ አለችና ሄዳ ስትጠይቀው ጥሩ ይምጣና ከአናፂዎች ጋር እመድበዋለሁ አለ፡፡ እሺ አልኩና ሄድኩ፡፡ ከአናፂዎች ጋር ሰርቻለሁ፡፡ ከቀለም ቀቢዎች ጋር ሠርቻለሁ፡፡ ቡና ቤቱ ለናይት ክለብ በሚሆን መልኩ ይሰራ ስለነበር ከነሱ ጋር ሰራሁ፤ በየግድግዳው ላይ ሰዎች ሲጨፍሩ ሁሉ የሚያሳይ ስዕል ተሰርቶ ተጠናቀቀ፡፡

ምሽት ክለብ

በ1954 ዓ.ም ገደማ የሚገርማችሁ ምሽት ክበቡ ተሠርቶ ከተጠናቀቀ በኋላ ሲከፈት እኔ ወደ ወጥ ቤት ነበር የገባሁት፡፡ ወጥ ቤት ስገባም የወጥ ቤት ረዳት ተደርጌ ነበር የተመደብኩት፡፡ ረዳት ሆኜ እየሰራሁ ማታ ማታ ምሽት ክለቡ ውስጥ እየመጡ የሚዘፍኑትን እነ እሳቱ ተሰማ፣ ጥላሁን ገሠሠ፣ ተፈራ ካሳ፣ ታምራት ሞላ፣ አባይ በለጠ (ነፍሳቸውን ይማረውና) እመለከት ነበር፡፡

እነሱ ዘፍነው ለእረፍት ሲቀመጡ እኔ ሳንድዊችና ሻይ አቅራቢ ነበርኩ፡፡ እነሱን ስር ስር ጉድ ጉድ እያልኩ ዘፈናቸውን በደንብ ነበር የማደምጠው፤ ታዲያ በአንድ አጋጣሚ እነ ጥላሁን ድሬዳዋ ለስራ ታዘው ሲሄዱ ሙዚቀኞች ብቻቸውን ቀሩ፡፡

ሙዚቀኞቹ የተፈራ ካሳን አልጠላሽም ከቶ ዘፈን መጫወት ሲጀምሩ ከወጥ ቤቴ ሹልክ ብዬ ወጥቼ ‹‹ይህቺን ዘፈን እሺ ልዝፈናት›› አልኳቸው፡፡ ቀጭን ስለነበርኩ አይተውኝ ‹‹ትችያዋለሽ እንዴ›› አሉኝ፡፡ እሞክራሁ አልኳቸውና መድረክ ላይ ወጥቼ ስጫወት እንደአጋጣሚ እዚያ ቤት ከምድር ጦርም ከጦር ሰራዊትም የኮንጎ ዘማቾች ነበሩና ሰምተው ተገረሙ ስጨርስ ቢስ ብለው አስደገሙኝ፤ ስጨርስ እንደገና ለሶስተኛ ጊዜ አስደገሙኝ፤ ‹ይህም አለ ለካ› የተሰኘውን የተዘራ ኃ/ሚካኤልን ስጫወትም ይደገም ተባለ፤ ደገምኩ፤ ያንን ዘፍኜ ከመድረክ ልወርድ ስል የምሽት ክለቡ ባለቤት ፊት ለፊቴ ቆሞ ‹‹ያ አላህ፤ ለመሆኑ መዝፈን ትችላለህ እንዴ?›› አለኝ ‹‹እሞክራለሁ›› ስለው ከነገ ጀምሮ ወደ ወጥ ቤት አትመለስም እነ ጥላሁን እስከሚመጡ ድረስ እዚሁ ትዘፍናለህ›› አለኝ፡፡ በማግስቱም መርካቶ ወሰደኝና ሙሉልብስ፣ ጫማና ሸሚዝ ከነልዋጩ ገዛልኝ፡፡ እነ ጥላሁን ከድሬዳዋ ሲመለሱ መድረኩ ላይ ቄብ ብዬ ጠበኳቸው፡፡ መድረክ ላይ ቆሜ ስዘፍን ሲያዩኝ ተገረሙ፡፡ ‹‹መዝፈን ትችያለሽ እንዴ›› እያሉ ሲጠይቁኝ ‹‹እሞክራሁ›› ነበር መልሴ፤ ከዚያ ብታምኑም ባታምኑም አንድ ሙሉ ግጥም የያዘ ደብተር አመጡልኝና አጥና አሉኝ፡፡ እየመረጥኩ የጥላሁንን፣ የእሳቱን፣ የተዘራን፣ የካሳን ዘፈኖች ግጥሞች ማጥናት ጀመርኩ፡፡

Mahamud Ahemed

ምሽት ክለቡ እየተሟሟቀ ብዙ ደንበኞች እየመጡ ሳለ በ1954 ዓ.ም እቴጌ መነን ያርፋሉ፡፡ በዚሁ ሰበብ ምሽት ክለቡ ተዘጋ፡፡ ግን ከሁለት ወራት በኋላ ሀዘኑ ይበቃል ብለው ግርማዊ ቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ ‹‹ህዝቤ ሀዘኔን ከኔ ጋር ተካፍለሀልና ከዚህ በኋላ ወደ ስራህ ግባ›› ባሉት መሠረት የሙዚቃ ሥራ ዳንስ ቤቱ ሁሉ ሲከፈት የእኛም ምሽት ክለብ ተከፈተ፡፡ የዚያን ጊዜ ያው የሰው ዘፈን እያጠናሁ ስለነበር የምዘፍነው የመጀመሪያዋን የራሴ ዘፈን፡-
‹‹ካንቺ በቀር ሌላ ብሞት አልመኝም
ግን እስካሁን ድረስ አላወቅሽልኝም››

የተባለችው ዘፈን ተሰጥታኝ የጉሮሮዬ ማሟሻ ሆና ተጫወትኳት፡፡ ይህቺ ዘፈን አሁን ድረስ አብራኝ አለች፡፡

ጉዞ ወደ ክቡር ዘበኛ

ወደ ክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ከመግባቴ በፊት መጀመሪያ ፖሊስ ሠራዊት ሙዚቃ ክፍል ነበር ለመግባት የፈለግሁት፡፡ በዚህም መሠረት ለምን ሄጄ አልጠይቃቸውም ብዬ ሄጄ ስጠይቅ ‹‹የማንን ዘፈን ነው የምትዘፍነው?›› ሲሉኝ የነ ጥላሁን ገሠሠ፣ የነ እሳቱ ተሰማ ስላቸው ‹‹የሙዚቃ ትምህርት ተምረሃል ወይ›› አሉ፣ አልተማርኩም ስል ካላወቅህ አንፈልግም አሉኝና መለሱኝ፡፡ ከዚያ እንደገና ወደ ምድር ጦር ሙዚቃ ክፍል ሄድኩ፡፡ እዚያ ደግሞ ‹‹መጀመሪያ ደብረ ብርሃን ሄደህ ወታደርነት ተቀጥረህ ስትመጣ ነው ወደዚህ ክፍል የምትገባው›› አሉኝ፡፡ አይ እንግዲህ ዕድሌ አይደለም ብዬ ዝም ብዬ እዚያ ምሽት ክለብ ውስጥ ማታ ማታ ስሰራ ቆይቼ ለምን ክቡር ዘበኛ አልሄድም ብዬ ሻለቃ ግርማ ሀድጎ ስሄድ በዚያን ወቅት የፊደል ሠራዊት የሚባል ተቋቁሞ ለነሱ እርዳታ ማሰባሰቢያ የሙዚቃ ዝግጅት የክቡር ዘበኛ፣ የጦር ሠራዊት፣ የፖሊስ እና የቀዳማዊ ሀይለስላሴ የሙዚቃ ክፍሎች ባሉበት ዝግጅት ተዘጋጅቶ ነበር፡፡ የቀዳማዊ ሀይለ ስላሴ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት እነ ተሾመ ምትኩን ይዞ ተሳትፏል፡፡ በዚህ የሙዚቃ መድረክ ላይ ነው እንግዲህ ተፈትነህ ካለፍክ ትቀጠራለህ የተባልኩት፡፡ በዕለቱ ትዝ ይለኛል የመድረክ አስተዋዋቂ በዚያን ወቅት የ10 አለቃ ገዛኸኝ ደስታ ነበር፡፡ የተናገረው ነገር አሁን ድረስ አይረሳኝም፡፡ ‹‹አንድ አዲስ ልጅ ዛሬ እናቀርብላችኋለን፡፡ ልጁ ምናልባት የጥላሁን ገሠሠ ደቀመዝሙር ይሆናል ብለን እንገምታለን፡፡ ይሁን ካላችሁ ይቀጥላል›› ነበር ያለው፤ አስቦት ይሁን የተናገረው ታይቶት ይሁን አላውቅም፡፡ እንደዚህ አስተዋውቆኝ መድረክ ላይ ወጣሁ፡፡ ይዤ የነበረው የታምራት ሞላን፣ የገላን ተሰማን፣ የጥላሁን ገሠሠንና የራሴን የተሰጠችኝን ካንቺ በቀር ሌላን ተጫወትኩ፡፡ ከታምራት ዘፈን ቀጥሎ የራሴን ስዘፍን አቀባባሉ ልዩ ነበር፡፡ ስጨርስ ይደገም ተባለ፡፡ ደገምኩ፡፡ የሚገርማችሁ ሶስተኛውን ዘፈን ስጫወት ልክ ያኔ ኤልቪስ ፕሪስሊን እንደሚያደርገው እግሬን እያንቀጠቀጥኩ ነበር፡፡ ህዝቡም በልዩ አድናቆት አጀበኝ፡፡

ከመድረክ ስወርድ በክቡር ዘበኛ ውስጥ ልቀጠር እንደምችል አውቅ ነበር፡፡ ምክንያቱም የህዝቡ አቀባበል ልዩ ነበር፡፡ ታዲያ ሻለቃ ግርማ ሀድጎ ምን አሉኝ ‹‹ስማ አንተ ልጅ በወታደርነት እንቅጠርህ ቢሉ እሺ እንዳትላቸው፤ በሲቪል ግን ካሉህ እሺ በላቸው፡፡›› አሉኝ፡፡ እሺ አልኳቸውና በወታደርነት እንቅጠርህ ሲሉኝ አልፈልግም በሲቪልነት ነው የምፈልገው አልኳቸው፡፡ ከዚያ የዚያን ጊዜ ደሞዝ 60 ብር ስለነበር በሲቪልነት በ60 ብር በወታደርነት ደግሞ በ60 ብር በድምሩ በ120 ብር እንቅጠርህ አሉኝ፡፡ አልፈልግ ስል በሲቪልነት በ60 ብር ደሞዝ ታህሳስ 15 ቀን 1955 ዓ.ም ክቡር ዘበኛ ሙዚቃ ክፍል ተቀጠርኩ፡፡

ለ11 ዓመታት ያህል በክቡር ዘበኛ የሙዚቃ ክፍል ውስጥ ሳገለግል የመጀመሪያው መምህሬ የአፍ አከፋፈትና የድምፁ አወጣጥ ያስተማረኝ ወንድሜ ጥላሁን ገሠሠ ነበር፡፡ ሌሎችም ጓደኞቼ የየራሳቸውን ምክር ሰጥተውኛል፡፡ እነ እሳቱ ተሰማ፣ ተዘራ ሀ/ሚካኤል፣ ብዙነሽ በቀለ ሁሉም መክረውኛል፡፡ እስከ ዛሬ ድረስ እጠቀምበታለሁ፡፡
በ1955 ዓ.ም ለ1956 ዓ.ም አዲስ ዓመት መግቢያ የምድር ጦር የንጉሰ ነገስቱ የክብር ዘብ ሙዚቀኛ፣ ፖሊስ ሠራዊትና ኪነ ጥበባት መምሪያ የሚባል ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ያለው ልዩ ዓመታዊ የሙዚቃ ውድድር ያካሂድ ስለነበር ሁላችንም ተዘጋጅተን ነበር የምንሄደው፡፡ የዚያን ጊዜ እያንዳንዳችን አራት ወይም አምስት አዲስ ዘፈን ይዘን ነበር የምንቀርበው፡፡ በዚህ አጋጣሚ ለኔም ሌሎች አዳዲስ ዘፈኖች ተሰጡኝ፡፡ በደንብ መዝፈን ጀመርኩ፡፡ በ11 ዓመታት ቆይታዬ ብዙ ዘፈኖች ተጫውቻለሁ፡፡ ከዚያ ክቡር ዘበኛን ለቅቄ ወደ ናይት ክለብ ስራ ራስ ሆቴል ገባሁ፡፡

ወደ ናይት ክለብ ስራ ልገባ የቻልኩት ክቡር ዘበኛ የሚከፈለኝ 250 ብር እያነሰኝ መጣ፡፡ ቤታችን ውስጥም 3 ወንዶች ሶስት ሴቶች ስላለን ለማስተዳደር በቂ አልሆን አለ፡፡ አባቴም ስራ ስላቆመ እናቴም እንጀራ ጉልት ብቻ ስለነበር የምትሸጠው የኔ ደሞዝ እያነሰ ሲመጣ ለቅቄ በ1966 ዓ.ም ራስ ሆቴል አይቤክስ ጋር ናይት ክለብ ገባሁ፡፡ ከዚያ ጊዜ ወዲህ ህይወቴም እየተሻሻለ መጣ፤ አሁን ለደረስኩበት ደረጃ መሠረት የሆኑኝን ዘፈኖች ሰራሁ፡፡

በኛ ዘመን ከነበረው አንፃር እናንተ በጣም እድለኞች ናችሁ፡፡ ምክንያቱም በኛ ጊዜ እግዚአብሔር ከሰጠን ድምፅ ፀጋ በቀር ሌላ እውቀት አልነበረንም፡፡ እናንተ ግን አሁን ሙዚቃን በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ነው እየተማራችሁ ያላችሁት፡፡ በዚህም ልትኮሩ ይገባል፡፡ ሙዚቃ በዓለም ላይ ትልቅ ደረጃ ደርሷል፡፡ እዚያ ደረጃ ላይ የማድረስ ሀላፊነት እናንተ ላይ ነው የተጣለው፡፡ ለመጪው ትውልድ እናንተ መብራቶች ናችሁ ተጠቀሙበት፡፡
ስለ ፍራንሲስ ፋልሴቶ

በኔ በኩል የኢትዮጵያን ሙዚቃን ከራሴ አልፌ በዓለም እንዳስተዋውቅ ያደረገኝ አንድ ሰው አለ፡፡ ፈረንሳያዊው ፍራንሲስ ፋልሴቶ ይባላል፡፡ ይሄ ፈረንሳዊ ፕሮሞተር ነው፡፡ ፍራንሲስ ፋልሴቶ የኢትዮጵያ ሙዚቃን የሚወድ፣ ልቅም አድርጎ የሚያውቅ ሰው ነው፡፡

የኔን ዘፈን በሬዲዮ ሰምቶ ነው ከፈረንሳይ ወደ አዲስ አበባ የመጣውና ያገኘኝ፡፡ ራስ ሆቴል ድረስ መጥቶ ካንተ ጋር መስራት እፈልጋለሁ፤ አለኝ፡፡ የዚያን ጊዜ ያው እንደ ማንኛውም ሰው አይ ይሄ ፈረንጅ እውነቱን ነው ብዬ ነበር የተጠራጠርኩት፡፡ ከዚያ ከአይቤክስ ሙዚቀኞች ጋር ሆነን የመጀመሪያ ጉዟችን ወደ ፈረንሳይ ሄድን፡፡ የዚያን ጊዜ ትዝ የሚለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ፓሪስ ውስጥ እኔ ስሰራ ከኛ አዳራሽ ፊት ለፊት ባለ ሌላ መድረክ ላይ ማይክል ጃክሰን ይዘፍን ነበር፡፡ የዚያን ጊዜ እኔ ስጫወት ሙላቱ አስታጥቄ ትልቁ ሙዚቀኛ አብሮን ነበር፡፡ ሙላቱ የኢትዮጵያ ሙዚቃን በከፍተኛ ደረጃ ያስተዋወቀ ሰው ነው፡፡

ከዚያን ጊዜ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ፈረንሳይን ረግጨ ብዙ ስራዎችን አብረን ከፍራንሲስ ፋልሴቶ ጋር ሰርተናል፡፡ የኢትዮጵያ ሙዚቃ አልበምን አሳትሟል፡፡ የኔ ብቻ ሳይሆን የጥላሁን ገሠሠ፣ ሙሉቀን መለሰ፣ አለማየሁ እሸቴን የሌሎችንም በልዩ ሁኔታ አስቀርፆ አውጥቷል፡፡

በነገራችን ላይ እኔ ይህ የመጀመሪያዬ ነው፡፡ ከተማሪዎች ፊት ቁጭ ብዬ የሕይወት ልምዴን ሳካፍል፤ ለናንተ ይህንን ነገር ከተናገርኩ በኋላ እኔ ዛሬ ማታ ብሞት ቅር አይለኝም፡፡
የአንጋፋው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ ገለፃ እንዳበቃ ልዩ ልዩ ጥያቄዎች ከተማሪዎች ቀርቦለታል፡፡ ከቀረቡት ጥያቄዎች መሀከልም የመጀመሪያ አልበምህ ያሳተምከው መቼ ነው? የሚለው ይገኝበታል፡፡ ማህሙድ ሲመልስ ‹‹በካሴት ደረጃ ያወጣሁት የመጀመሪያ ካሴት በ1972 ገደማ ነው፤ ከዚያ በፊት ሸክላ ነበር፤ በዚህ ካሴት ላይ አሽቃሩ የሚለው ዘፈን ያለበት ሲሆን ደራን ጨምሮ 10 ዘፈኖችን ይዟል፡፡ የሚገርማችሁ በዚያን ወቅት ጥላሁንም ካሴት አውጥቶ ነበር፡፡ የሱ በሎ የሚለውን የኦሮሞኛ ዘፈን የያዘ ሲሆን የኔ ደግሞ አሽቃሩ የሚለው የጉራጊኛ ዘፈንን የያዘ ነበር፡፡ በዚህ የተነሳ እሱ አሽቃሩ ሲለኝ እኔ በሎ በሎ ነበር የምለው፡፡››

በትዝታ ዘፈኖችህ ላይ ልዩ ድምፅ አለህ? ይህንን ችሎታህ እንዴት አዳበርከው ለተባለው ጥያቄ ደግሞ ‹‹እኔ ከሌሎች የተሻለ ድምፅ አለኝ ለማለት አልችልም፤ ከሌሎች ተሽዬ ሳይሆን ባለኝ አቅም እግዚአብሔር በሰጠኝ ፀጋ እዚህ ደርሻሁ፡፡ የድምፅ አወጣጥ ወይም ስለ ድምፅ የተሰጠኝ ትምህርት የለም፡፡ በተፈጥሮ ያለ ነገር ነው የምንዘፍነው ካንዳችን አንዳችን የምንማረው ነገር አለ፡፡ አሁን እናንተ እድለኞች ናችሁ የምለው በኖታ ተፅፎ እያነበባችሁ ነው ሙዚቃ የምትጫወቱት፡፡ በኮንዳክተር የሚዘፍኑ ድምፃውያን አሉ፤ ከኖታ ላይ የሚዘፍኑ አሉ፤ እኛ ግን የዚህ ዕድል ተጠቃሚዎች አልነበርንም፡፡ ለዚህ ነው እኔ ችሎታ አለን ብዬ የማልናገረው፡፡ ሀይል አለኝ አልልም፤ ሀይል የእግዚአብሔር ነው››
በሙዚቃ ህይወትህ ያጋጠሙህ ፈተናዎች ምን ይመስላሉ? እንዴትስ አለፍካቸው? ለወጣቶችስ ምን ትመክራህ? ‹‹በሙዚቃ ህይወቴ ብዙ ነገሮችን አሳልፌያለሁ፡፡ በመጀመሪያ ደረጃ ስቀጠር በሙዚቀኛ ደረጃ አልነበረም የምንጠራው፤ ያንን ጊዜ በትዕግስት አልፈናል፡፡ አዝማሪ ነበር የምንባለው፤ ግን በዚያን ወቅት አዝማሪ እንደስድብ የሚቆጠር ቢሆንም በኋላ ግን ክብር መሆኑን ነው ያወቅሁት፡፡ ምክንያቱም አዝማሪ ይዘምራል የሚል ነገር ስላለ ስድብ ሳይሆን ክብር መሆኑን ነው ያወቅሁት፡፡ ያንን ዘመን አሳልፈናል፤ ግን በፀጋ ነው ተቀብለን ያሳለፍነው፤ በውጪው ዓለም አሁን የሙዚቃ ሰው ያለውን ክብር እያያችሁ ነው፤ ይህንን ይዞ ወደፊት መሄድ ያስፈልጋል፡፡ እናንተ ናችሁ ሙያችሁን የምታስከብሩ፤ ተስፋ አትቁረጡ፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ ነው የምለው፤ ችግር ቢመጣም መቻል ነው ያለባችሁ፡፡ መሠረታችሁን ሳትለቁ የኢትዮጵያ ሙዚቃን ለማሳደግ ነው መጣር ያለባችሁ፡፡ አንዳንድ ጊዜ የውጪ ሀገር ሙዚቃዎችን ስታሰሙ እንዴት አድርገው ነው የሰሩት ልትሉት ትችላላችሁ፤ ግን በትምህርት የተሰራ በመሆኑ ትምህርታችሁን ጠንክራችሁ ልትማሩ ይገባል››

በ1968 እና 1968 ገደማ በነበረው የሀገራችን ሁኔታ ውስጥ የሰራሃቸው ስራዎች መሠረታዊ ለውጥ ያመጡ እንደሆኑ ይታወቃል፤ በተለይ የዕድገት በህብረት ዘመቻ ጊዜ የወጡት ስራዎች ማለት ነው፡፡ በእርግጥ አንዳንድ ሰዎች ትችት የሰነዘሩባቸው ሥራዎች አሉ፤ ስለ እነዛ ሥራዎችና ስለወቅቱ እስኪ አንዳንድ ነገሮችን ንገረን? ተብሎም ተጠይቆ ነበር፡፡
‹‹ከ1963 ዓ.ም ጀምሮ ራስ ሆቴል ከአይቤክስ ባንድ ጋር እሰራ ነበር፤ በዚያን ወቅት እነ ኩሉን ማን ኳለሽ፣ እነአምባሰል፣ እነትዝታ፣ እነችቦ አይሞላም ወገቧ፣ አልማዝ ምንዕዳ ነው የሠራሁበት ወዘተ ነው፡፡ ክቡር ዘበኛ ሆኜ ነበር በራስ ሆቴል ማታ ማታ የምሠራው፡፡ ታዲያ በዚህ የተነሳ ምን አየሠራህ ነው ተብዬ ተጠይቄ ነበር፤ እነዛን ዘፈኖች የተቀረፀበት ብስራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያ ነበር፡፡ታዲያ እነኩሉን ማንኩሎሻል ስጫወት ከፍተኛ ዝና ነበር ያገኘሁት፡፡ ጋዜጠኛ ግን ምንአለኝ ፍራሽ አዳሻ አለኝ፡፡ ‹‹ፍራሽ አዳሽ ስልህ ከፋህ ወይ›› ሲለኝ ለምን ይከፋኛል አልከፋኝም አልኩት፤ ፍራሽ አዳሽ የተበላሸ ፍራሽ ጥጥ እንደገና አስተካክሎ ሰው እንዲተኛበት የሚያደርግ ባለሙያ ነው፡፡ ፍራሹ ከመቆርቆር ወደ ምቾት ይቀይረዋል፡፡ እኔ ደግሞ የተረሱትን ዘፈኖች በማደሴና ፍራሽ አዳሽ በመባሌ ምንም ቅር አይለኝም ነው ያልኩት፡፡

በዕድገት በህብረቱ ዘመቻ ወቅት ተማሪው በሙሉ ወደ ገጠር ዘመቻ ሲሄዱ እኔ አታውሩልኝ ሌላ፣ ነይ ደኑን ጥሰሽ፣ መላ መላን፣ አባይ ማዶን ነበር የዘፈንኩት፤ እንደውም የአባይ ማዶን ግጥም የገጠመልኝ ሰው እዚህ መሀከላችሁ ይገኛል፡፡ ሸርፈዲን ሙሳ ይባላል፡፡ አባይ ማዶን ብቻ ሳይሆን ሌላም ዘፈን ፅፎልኛል፡፡ በቅርቡ ትሰማላችሁ ‹‹አብራኝ ናት›› የተባለ ግጥም ፅፎልኛል፡፡ አብራኝ ናት የሚለው አሁን አብራኝ ላለችው ባለቤቴን ነው፡፡ ድሮም ነበረች፤ አልማዜ ብዬም ዘፍኜላት አውቃለሁ፡፡ አብራኝ ናት ያልኩት ለምንድንነው? ከልጅነት እስከ እውቀት አብራኝ ናት፣ በሞራል አብራኝ ናት፣ በስራዬ አብራኝ ናት፣ የምታማክረኝ ናት፣ የኑሮ ደረጃዬ ከፍ እንዲል እየሠራች እዚህ ደረጃ ያደረሰችኝ እሷ ናት፡፡ አልማዝ አልማዝዬ ብዬ ዘፋኜላታለሁ፡፡ አሁን ደግሞ አብራኝ ናትን እዘፍንላታለሁ፡፡ አልማዝ አልዝዬ ግጥምና ዜማ የሰጠኝ ነፍሱን ይማረውና ፍሬው ሀይሉ ነበር ዛሬ ልጁ ደግሞ ፍሬው እዚሁ ት/ቤት ተምሮ ራሱን ለትልቅ ደረጃ ያበቃ የራሱን ካሴት ያወጣ ልጅ አፍርቷል፡፡ እናንተንም ለዚህ ደረጃ ያብቃችሁ ነው የምለው ፡፡
ታዲያ እነዛን ዘፈኖች በዕድገት በህብረት ዘመን ወቅት በመዝፈኔ በፖለቲካ ጉዳይ ውስጥ ባልገባም ብሔራዊ ቴአትር የነበሩ ሠራተኞችና ሙዚቀኞች አድማ አድርገው ታፍሰው ነበር፡፡ በአድማው በታሰሩበት አንድ ካድሬ መጥቶ ሊያስፈታቸው ሲል ‹‹እኛ ትግል እየታገልን እንደገና አንዳንዱ አታውሩልኝ ሌላ ከሷ ዜና በቀር አያለ ይዘፍናል፡፡ እኛ ትግል እየታገልን ነይ ደኑን ጥሰሽን ይዘፍናል›› ብለው ወደሌላ ነገረ ቀይረው ሊያስመቱኝ ነበር፡፡ በወቅቱ ብዙ ችግሮችን አልፌያለሁ፤ ግን እግዚአብሔር ይመስገን ያንን ሁሉ አልፌ ለዚህ ደረጃ በቅቻለሁ፡፡

የት የት ሀገራት የሙዚቃ ስራዎችህን አቅርበሃል? በሚል ለተጠየቀው ጥያቄ ‹‹መጀመሪያ ጊዜ ከፍራንሲስ ፋልሴቶ ጋር ፈረንሳይ ላይ ሙዚቃዎቼን ካቀረብኩ በኋላ ያልሄድኩበት ቦታ የለም ልል እችላለሁ፤ እንግዲህ በአሁኑ ሰዓት በትክክል የማላውቃቸው ሀገሮች ጃፓንና ብራዚል ብቻ ናቸው ልል እችላለሁ፤ ከዚህ ውጪ ያሉ ሀገሮችን አይቻለሁ፡፡ በእንግሊዝ ሀገርም የቢቢሲ ሚውዚክ አዋርድ ተሸልሜያለሁ፡፡ በመላው ዓለም ዛሬ የኢትዮጵያን ባንዲራ ለብሼ ሀገሬን አስተዋውቄያለሁ ብል የዋሸሁ አይመስለኝም፡፡››
የህይወት ታሪክህን የተመለከተ መፅሐፍ እየተዘጋጀ እንደሆነም ይነገራልና መቼ ለአንባብያን የሚደርስ ይመስልሃል? በሚል ለቀረበለት የመጨረሻ ጥያቄም‹‹ታሪኩ በረድፍ በረድፉ እየተሠራ ነው፤ ግን ማነው በጥሩ ሁኔታ የሚፅፈው የሚለውን እያፈላለግሁ ነው፡፡ የራሴን ገጠመኞች እኔ ነኝ የምፅፈው ወይስ ለሌላ ሰው ተናግሬ ነው የማፅፈው የሚለው ገና ነው፡፡ ግን በህይወት እያለሁ መፅሐፌ ታትሞ ባየው ደስ ይለኛል፡፡ እኔ ላልፍ እችላለሁ፤ ግን ታሪኬን በመፅሐፍ ለቀጣዩ ትውልድ ለማስተላለፍ ምኞት አለኝ፡፡ እግዚአብሔር እንደሚያሳካው እምነት አለኝ፤ ኢትዮጵያ በነፃነት ለዘለዓለም ትኑር አመሠግናለሁ፡፡››

The post የማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ተከበረ * አላሙዲ 5 ሚሊዮን ብር ሸለሙት appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት እንደደረሳቸው ተነገረ

$
0
0

Tedros-Adhanom-
መርጋ ደጀኔ እንደዘገበው

በደቡብ አፍሪካ የሚደረገዉን የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ለመካፈል ወደዚያዉ ያመራዉ የወያነኔ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት ከወያኔ መረጃ ቢሮ በፕሪቶሪያ ለሚገኘዉ የወያኔ ኢንባሲ መተላለፉን ከዉስጥ የወጣ መረጃ አመለከተ::

ተላላኪዉ ቴድሮስ አድሐኖም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የወያኔ ደጋፊዎችን ሰብስቦ ሊያነጋግር በሞባይል ስልክ መልክት (text)እያደረገ ሳንድተን ሪክሬሽን ሴንተር ቀጠሮ እያስያዘ መሆኑን የደረሱበት በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ተቃዋሚዎች በንቃት እየተጠባበቁት ሲገኙ ተላላኪዉ ቴድሮስ በማንኛዉም ስፍራዎች ለመዟዟር እንዳይችል ተደርጓል።

በተጨማሪ ኢትዮጵያዊያን በሙሉ ሚኒስተሩን በመቃወም በተገኘበት ስፍራና ቦታ ሁሉ መረጃ ለመስጠት በተጠንቀቅ መቆማቸዉን አሳዉቀዋል። ወያኔና ወያኔይያዊያን በሙሉ በደረሱበት ሁሉ ከመዋረዳቸዉንና ከመሸማቀቃቸዉን በዘለለ መልኩ ህዝብን በመፍራት መደበቃቸዉ በራሱ አንድ ታላቅ ድል ነዉ ሲሉ ከወደ ሳንድተን አንድ ግለሰብ ተናግረዋል፤

The post ቴድሮስ አድሐኖም በጆሐንስበርግና በፕሪቶሪያ ዙሪያ እንዳይዘዋወሩ ጥብቅ መልእክት እንደደረሳቸው ተነገረ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣ ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ (ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ)

$
0
0

አንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበር

ANDENET NORTH AMERICA ASSOCIATION OF SUPPORT ORGANIZATION

     8121 Georgia Avenue, Silver Spring, MD 20910 ste 10, Tell: (301) 585-7700

ሰኔ ፲, 2007 ዓ/ም (June 12, 2015)

udjየደርግ ስርዓት ሲገረሰስ  ሕወሃት/ኢሕአዴግ የዲሞክራሲ ስርዓት እንደሚገነባ ቃል ገብቶ ነበር። ሆኖም፣ ይኸው ሃያ አራት አመታት አለፈ፤ ኢትዮጵያዉያን የግፍ ቀንበር በላያቸው ላይ ተጭኖ፣ መብታቸዉንና ነጻነታቸውን ተገፈው፣ በአገራቸው በፍርሃትና በሰቀቀን እየኖሩ ነው። ምንም እንኳን እጅግ በጣም ጥቂት የሆኑ የስርአቱ ተጠቃሚዎች ቢከብሩም፣ የመልካም አስተዳደር እጦት፣ የኑሮ ዉድነት፣ ዜጎችን ከቅያቸው የማፈናቀል ተግባራት፣ አድልዎና ዘረኝነት፣  ከጊዜ ወደ ጊዜ ኢትዮጵያን ለብዙዎች ሲኦል እያደረጋት ነው።

ምርጫ ዜጎች ልዩነቶቻቸውን በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የሚረዳ እንደመሆኑ አገር ቤት ያሉ የሰላማዊ የፖለቲካ ድርጅቶች፣ ምርጫውን ተጠቅመው ለዉጥ ለማምጣት  በርካታ እንቅስቃሴዎችን አድርገዋል። ሆኖም አገዛዙ  የፖለቲካ ምህዳሩን በማጥበብ ከፍተኛ ጫና እያደረገ አላሰራ እንዳላቸው የአደባባይ ሚስጠር ነው። ጫና ከማሳደር ባለፈም፣ የሚዘረጋበትን መሰናክል በማለፍ፣ ጠንካራ ድርጅታዊ መዋቅር የዘረጋዉንና  በሕዝቡ  ዘንድ በሁሉም ክልሎች ተቀባይነት ያገኘውን የአንድነት ፓርቲ፣ አገዛዙ ሕገ ወጥ በሆነ መንገድ እስከማገድም ደርሷል። ብቸኛ ተቀናቃኝ የሆነዉን እና ምርጫውን ሊያሸንፍ የሚችል ድርጅት በታገደበት ሁኔታ የተደረገ ምርጫ ተቀባይነት ሊኖረው አይችልም። በምርጫው ወቅትም፣  ምርጫ ሳይሆን የድምጽ ዘረፋ በይፋ እንደደተደረገ፣ የምርጫ ጣቢያዎች የጦርነት ቀጠና ይመስሉ እንደነበረ፣ ኮረጆዎች እንደተገለበጡ በስፋት ተዘግቧል።  ምርጫዉን የአዉሮፓ ሕብረትም ሆነ የካርተር ማእከል ያልታዘቡት ሲሆን፣ የአሜሪካን ኤምባሲም የምርጫውን ሂደት ለመከታተል ሰራተኞች ለመላክ ቢጠይቅም ፍቃድ አላገኝም። በብዙ ቦታዎች የተቃዋሚ ፓርቲ ታዛቢዎች አልተገኙም። በተወሰኑ የምርጫ ጣቢያዎች የታዘበው፣ የአገዛዙ አጋር ተደረጎ የሚቆጠረው የአፍሪካ ሕብረት ታዛቢዎች ሁሉ ሳይቀሩ፣  ምርጫው ሰላማዊ ነበር ቢሉም፣  ነጻና ዴሞክራሲያዊ እንዳልሆነ አረጋግጠዋል።

ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣  ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ ፣ ራሱ ፖሊስ፣ ራሱ ዳኛ  ሆኖ  ባደረገው የምርጫ ድራማ፣ መቶ በምቶ አሸነፍኩም ብሎ አውጇል። የሕወሃት ቅርንጫፍ የሆኑት የምርጫ ቦርድ ሃላፊዎችም  የምርጫው ዉጤት አለመቀበል በሕግ እንደሚያስቀጣ በመግለጽ እያስጠነቀቁ ነው።ሆኖም፣ የብዙ ድርጅቶች ግንባር የሆነው መድረክ፣ ኢዴፓ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ እና ኢራፓ ምርጫውን እንደማይቀበሉ  በይፋ አሳወቀዋል።

አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች፣ በምርጫውው ሂደት ላበረከቱት አስተዋጾና  ለከፈሉትን መስዋትነት ያለንን አክብሮት እየገለጽን፣  ምርጫውን እንደማይቀበሉ በመግልጽ የወሰዱትን አቋም እንደምንደገፍ ለመገልጽ እንወዳለን። እኛም ከዚህ ምርጫ የሚገኝ ምንም አይነት ሕጋዊነት እንደሌለ በማስረገጥ፣ ሕወሃት ያለ ህዝብ ፍቃድ በጉልበት የሚገዛ ግፈኛ አገዛዝ እንደመሆኑ  የምንታገለው መሆናችንን እናረጋግጣለን።

አለም የትናይት በደረሰበችበት፣ በቅኝ ግዛት ሥር የነበሩና እኛ ስንረዳቸው የነበሩ እንደ ጋናና ናይጄሪያ ያሉ አገራት  የዲሞክራሲና የነጻነት አየር እየተነፈሱ ባለበት ዘመን፣ ሕወሃት መቶ በመቶ አሸነፍኩ ብሎ ማወጁ፣  ምን ያህል ለኢትዮጵያና ለሕዝቧ ንቀት እንዳለው በግልጽ ያመላከተ ሲሆን፣  ይሄን ሕዝብን የሚንቅ አገዛዝ የመሸከም ትከሻ ማንም ኢትዮጵያ ሊኖረው  አይገባም ብለን እናምናለን።በመሆኑም ለዉጥ እንዲመጣ የለዉጥ እንቅስቃሴን ለማገዝ ማድርረግ ያለብንን ሁሉ ለማድረግ ቁርጠኝነት እንዳለን ልናረጋግጥ እንወዳለን።

አገር ቤት ያሉ ድርጅቶች፣  ትግሉ የርዮት አለም ሳይሆን የነጻነት መሆኑን ተረድተው፣  ኃይላቸውን በማስተባበር በጋራ እንዲንቀሳቀሱም በአጽንኦት እናሳስባለን። ተመሳሳይ ፕሮግራሞች  ያላቸው ወደ ዉህደት፣ ካልሆነም ደግሞ መስማማት በሚቻልበት ጉዳዮች ላይ የጋራ ግንባር በመፍጠር፣  መግለጫ ከማውጣትና ብሶት ከማውራት አልፎ በመሄድ፣  ስርአቱን የሚያስጨንቅ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች ወደ ማድረግ እንዲሸጋገሩ እየጠየቀን፣ በማንኛው  ጊዜ በጋራ ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ ኢትዮጵያዊ አጋርነታንን እንደማይለያቸው ቃል እናሳውቃለን።

 

ድል ለኢትዬጵያ ሕዝብ!

የአንድነት ድጋፍ ማህበሮች በሰሜን አሜሪካ አስተባባሪ ኮሚቴ

 

The post ሕወሃት አይኑን በጨው አጥቦ፣ ራሱ መራጭ፣ ራሱ ተመራጭ፣ ራሱ ታዛቢ፣ ራሱ ምርጫ ቦርድ (ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች ማህበራት የተሠጠ መግለጫ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት በዋና ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ እየታሰሩ ነው

$
0
0
  •   በጥያቄአቸው፣ በአስተዳደር ይኹን በልማት ሥራ ምንም ችግር የለም ብለዋል፤ በሌለ ልማት!
  • ምእመናኑንም ‹‹ምንም ዓይነት ድርሻ የሌላቸውና ማንነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ገልጸዋቸዋል
  • የታሰሩት ምእመናን በፖሊስ ጣቢያ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ መስቀላችኹን አውልቁ›› ተብለዋል
  • የቀድሞው የደብሩ አለቃ ዘካርያስ ሓዲስና ኃይሌ ኣብርሃ ከውዝግቡ ለማትረፍ እያሰሉ ነው

bole bulbula medየቤተ ክርስቲያን ይዞታ ከቤተ ክርስቲያን አቋም ጋር በሚስማማ እና ሀብቷን በሚያስጠብቅ አኳኋን እንዲለማ በመጠየቅ በቅንጅት የተንቀሳቀሱ የቦሌ ቡልቡላ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ደብር ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላትበሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ጥያቄ እየታሰሩ እና ለእንግልት እየተዳረጉ ነው፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ለቦሌ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ እና በክፍለ ከተማው ለወረዳ 12 ፖሊስ ጣቢያ በጻፉት ደብዳቤ፣ በምእመናኑ እና የሰንበት ት/ቤት አባላቱ ተበይዶ የታሸገው የደብሩ ቢሮዎች በፖሊስ ርምጃ እንዲከፈቱ ምእመናኑም በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ አመልክተዋል፡፡

ጥያቄአቸውን ተከትሎ ባለፉት ኹለት ቀናት ከኻያ የማያንሱ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት መታሰራቸው ታውቋል፡፡ ትላንት እና ከትላንት በስቲያ ታስረው ከተለቀቁት ውጭ እስከ አኹን በእስር የሚገኙ ስምንት ምእመናን (አራት ምእመናን እና አራት የሰንበት ት/ቤት አባላት) በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት እንደሚቀርቡ ተገልጧል፡፡ ከታሳሪዎቹ መካከል ደብሩን በስብከተ ወንጌል ሲያገልግሉ ቆይተው በጡረታ የተገለሉ የ70 ዓመት ሕመምተኛ አዛውንት ይገኙበታል፡፡ ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲገቡ በአዛዡ ‹‹ማዕተባችኹን በጥሱ፤ መስቀላችኹን አውልቁ›› መባላቸውን ከእስር የተፈቱት ምእመናን ተናግረዋል፡፡

በደብሩ የልማት እና የመካነ መቃብር ይዞታዎች የሚገኙ የንግድ ቦታዎች እና ሱቆች ከቤተ ክርስቲያን ይልቅ ግለሰቦችን በሚጠቅም አኳኋን በከፍተኛ ዋጋ እየተከራዩ ባለበት ኹኔታ የደብሩ ገቢ እና ልማት እየተዳከመ መምጣቱ በምእመናን እየተገለጸ እና ይኸውም በጠቅላይ ቤተ ክህነት የአስተዳደር ጉባኤ በተሠየመ አጥኚ ቡድን ተረጋግጦ እርምት እንዲደረግ ተደጋጋሚ ማሳሰቢያ ቢሰጥም፣ ዋና ሥራ አስኪያጁ በደብሩ የአስተዳደር ይኹን የልማት ሥራዎች ምንም ዐይነት ችግር እንደሌለ ነው በደብዳቤአቸው የጠቀሱት፡፡

በሌላ በኩል ዋና ሥራ አስኪያጁ፣ ‹‹ችግር አለ ተብሎ የሚታሰብ ከኾነ ሊፈታ የሚችለው በሀገረ ስብከቱ ነው›› ቢሉም በትላንትናው ዕለት በጽ/ቤታቸው ላነጋገሯቸው 12 የምእመናን ተወካዮች፣ ‹‹አያገባኝም፤ የጻፍኹትም ደብዳቤ የለኝም፤ ሰንበት ተማሪ አድርግ የሚባለውን ከማድረግ በቀር ሌላ ሥልጣን የለውም›› ብለው እንደመለሷቸው ምእመናኑ በከፍተኛ ሐዘን ገልጸዋል፡፡

ዋና ሥራ አስኪያጁ ሊቀ ማእምራን የማነ፣ በቤተ ክርስቲያን አስተዳደር የምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ሚና yemane zemenfes‹‹አድርጉ የተባሉትን ብቻ ከማድረግ ያለፈ አይደለም፤ ልካቸውን ሊያውቁ ይገባል››በሚለው ንቀት የተመላበት ንግግራቸው ይታወቃሉ፡፡ በዚኽም ደብዳቤአቸው ምእመናኑን ‹‹በቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ምንም ዐይነት የሥልጣን ድርሻ የሌላቸውና ማምነታቸው የማይታወቅ›› ሲሉ ነው የገለጧቸው፡፡ አካሔዱን አላርምም ባለው የደብሩ አስተዳደር ላይ የቤተ ክርስቲያንን ሀብት ለማስጠበቅ እና ተጠቃሚነቷን ለማረጋገጥ በማስገዳጃነት የወሰዱትንም ርምጃ፣ ‹‹የቤተ ክርስቲያንን መብት የሚጋፋ እና በቤተ ክርስቲያን ላይ የተፈጸመ በደል ነው››ብለውታል፡፡

በዋና ሥራ አስኪያጁ ‹‹ማንነታቸው አይታወቅም›› የሚባሉት ምእመናን ግን የደብሩ አስተዳደር በየምክንያ የሚጠይቀውን ድጋፍ ከመስጠት የማይሰስቱ እና በበጎ አድራጎታቸው የሚታወቁ ናቸው፡፡ ልማት በሚል ለሦስተኛ ወገን እየተላለፈ በአስተዳደሩ የሚሰበስበው በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠር ወርኃዊ ገቢም ሓላፊዎቹንና ግለሰቦችን ከመጥቅም በቀር በተጨባጭ የሌለ ለመኾኑ ‹‹በደብሩ አካውንት ያለው ተቀማጭ ማሳያ ነው፤ ባዶ እጁን የመጣ መኪና ገዝቶ እየወጣ ነው››ይላሉ – ምእመናኑ፡፡

ምእመናኑን በመረዳት ችግሩን በትክክለኛ ገጽታው ተመልክቶ ከመፍታት ይልቅ ‹‹ልማቱን ለማስቀጠል›› በሚል እንዲታሰሩና በወንጀል ድርጊት እንዲጠየቁ ዋና ሥራ አስኪያጁ የወሰዱት ርምጃ ከአማሳኞች ጋር በተግባር ያልተፋቱ ለመኾናቸው ማረጋገጫ ነው፡፡ ለዚኽም ነው የቤተ ክርስቲያንን መብት ለማስጠበቅ ከተንቀሳቀሱት ምእመናን ይልቅ በእንቅስቃሴው ጥቅማቸውን ካጡ ተከራዮች ጋር ዳኝነት የተቀመጡትንና በውዝግቡ አጋጣሚ እንዴት እንደሚያትርፉ የሚያሰሉትን አማሳኝ ባለሟሎቻቸውን – የቀድሞው የደብሩ አስተዳዳሪ ዘካርያስ ሐዲስን እና ቀንደኛው ሌባ ኃይሌ ኣብርሃን እየሰሙ የሚገኙት፡፡

በሀ/ስብከቱ ሥር በሚገኙ 69 ገዳማት እና አድባራት የመሬት፣ የሕንፃ፣ የመካነ መቃብር ኪራይ እና የመኪና ሽልማት ጉዳዮችን አጥንቶ የመፍትሔ ሐሳብ እንዲያቀርብ በጠቅላይ ቤተ ክህነት አስተዳደር ጉባኤ የተቋቋመው ኮሚቴ ጥር ፳፮ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. ባቀረበው ሪፖርት፣ የደብሩ አስተዳደር ሱቆችንና ሰፊ ቦታዎችን በሕገ ወጥ መንገድ በማከራየት የቤተ ክርስቲያንን ጥቅም አሳልፎ መስጠቱን አረጋግጧል፡፡ የደብሩ አስተዳደር የቀሩትን ባዶ ይዞታዎች በማከራየት ሕገ ወጥ አካሔዱን ሊቀጥል እንደሚችል የጠቆመው ሪፖርቱ፣ በሀገረ ስብከቱ በኩል ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጠው ጠይቆ ማሳሰቢያው እንደተላለፈ መዘገቡ ይታወሳል፡፡

እንደ ቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ባሉ አድባራት ሰፊ ይዞታዎች ላይ ዐይናቸውን የጣሉት የዋና ሥራ አስኪያጁ የሙስና ባለሟሎች እነኃይሌ ኣብርሃ፣ ዘካርያስ ሐዲስ እና ተስፋ ፍሥሓ በልማት ስም በሚካሔዱ ግንባታዎች በየደብራቸው ያካበቱትን የዘረፋ ልምድ የሚያስፋፉበት ስልት ሲቀይሱ፣ ዋና ሥራ አስኪያጁም በልማት ስም በየአድባራቱ ጉብኝት እያካሔዱ እንደኾነ ተጠቁሟል፡፡ የሰንበት ት/ቤቶች አንድነትን የመልካም አስተዳደር፣ የፍትሕ እና የዕቅበተ እምነት ንቅናቄ በተለያዩ ክሦች ለማዳፈን በመቶ ሺሕ ብሮች(እስከ ብር አምስት መቶ ሺሕ) መድበው የሚንቀሳቀሱትም ለዚኽ ነው፡፡

ይኹንና የአማሳኞች በደል እና የፍትሕ ዕጦት ያንገሸገሻቸው የአጥቢያው ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤቶች ግንቦት ፴ ቀን ፳፻፯ ዓ.ም. የጽ/ቤቱን ቢሮዎች በይደው በማሸግ፤ የአድባራቱን ሓላፊዎች በማባረር እና መኪኖቻቸውን በመቆጣጠር የያዙት አቋም ንቅናቄውን አንድ ርምጃ ወደፊት ያራመደ፤ ችግሩ በሚጠይቀው ልክ ለመሥዋዕትነት የተዘጋጁ፤ የታዘዙትን ብቻ የሚፈጽሙ ሳይኾኑ መልሰው እንደሚጠይቁም ያሳዩበት ኾኗል፡፡

*          *          *

The post በቦሌ ቡልቡላ መድኃኔዓለም ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት አባላት በዋና ሥራ አስኪያጅ የማነ ዘመንፈስ ቅዱስ ጥያቄ እየታሰሩ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የአላሙዲና የአርቲስት ማህደር አሰፋ ግንኙነት አደባባይ መታየት ጀምሯል (ፎቶ ይዘናል)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሼህ መሃመድ አላሙዲ ከአርቲስት ማህደር አሰፋ ጋር ግንኙነት ጀምረዋል የሚለው ወሬ ሲወራ ከቆየ ሰንበትበት ብሏል:: በተለይም ማህደር ለትዳር ከምታስበው ጓደኛዋ ጋር ከተለያየች በኋላ ብዙ ጊዜ ከሼኩ ጋር ታይታለች:: በትናንትናው ዕለት ደግሞ ይህን የሁለቱ ግንኙነት በአደባባይ ታይቷል:: የአርቲስት ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙዚቃ አገልግሎት ዘመን ሲዘከር አላሙዲና ማህደር በሕዝብ ፊት ወጥተው እየተቃቀፉ ሲደንሱ ታይተዋል:: ይህም ፎቶ ለዘ-ሐበሻ ደርሷል – በጨለማ ውስጥ የተነሳ በመሆኑ ለፎቶው ጥራት ይቅርታ::
alamudi

alamudi

alamudi and mahder

alamudi and mahder asefa

 

 
Mahder asefa

The post የአላሙዲና የአርቲስት ማህደር አሰፋ ግንኙነት አደባባይ መታየት ጀምሯል (ፎቶ ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ጭልጋ ላይ ገበያ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ገደሉ * በርካቶች ቆስለዋል

$
0
0

ሰሜን ጎንደር ጭልጋ ወረዳ በአይከል ከተማ ዛሬ የህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ የሚመራው መንግስት ወታደሮች በወሰዱት እርምጃ 3 ሰዎች መገደላቸው ታወቀ።
news
ከስፍራው የሚወጡት ዜናዎች እንደሚያረጋግጡት በአይከል ከተማ መሀል ገበያ ህዝብ ላይ ተኩስ የከፈቱት የህወሀት ወታደሮች በርካታ ሰዎችንም ማቁሰላቸው ተገልጿል።

ከሶስቱ ሟቾች የሁለቱ ስም የታወቀ ሲሆን የአስር አለቃ ውቤ እና አቶ ብርሌ በህወሀት ወታደሮች ዛሬ ተገድለዋል።

የአይከል ከተማ ነዋሪ የሆኑ አንድ ሙስሊምም መገደላቸው ከስፍራው የሚወጡ መረጃዎች አስታውቀዋልል::

እንደ ዘገባው ከሆነ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል እየተነገረ ነው። ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በአይከል ከተማ ውጥረቱ ተባብሶ ቀጥሏል።

በማንነት ጉዳይ የተነሳው የህዝብ ጥያቄ በመንግስት ምላሽ ተስጥቶታል ቢባልም አከባቢውን ወደትግራይ ክልል ለመጠቅለል በህወሀት መንግስት እየተደረገ ያለው ድብቅ ሴራ ህዝቡን እንዳስቆጣው ይነገራል።

ባለፈው ቅዳሜ የሱዳን ወታደሮች የኢትዮጵያን ድንበር አልፈው በአብደራፊ የሚገኘውን የሁለት ኢትዮጵያውያን ባለሀብቶች የእርሻ ይዞታ ሲያቃጥሉ የእኛ ድንበር የሚዋሰነው ከትግራይ ክልል እንጂ ከአማራ አይደለም ማለታቸው መዘገቡ የሚታወስ ነው።

The post የሕወሓት መንግስት ወታደሮች ጭልጋ ላይ ገበያ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ 3 ሰዎችን ገደሉ * በርካቶች ቆስለዋል appeared first on Zehabesha Amharic.


ደቡብ አፍሪካ አልበሽርን ለICC አሳልፋ ትሰጥ ይሆን? –የአለምነህ ዋሴ ትንታኔ (ያድምጡ)

የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም በረሃ ወርዶ የብረት ትግሉን ተቀላቅሏል

$
0
0

የሰላም በሮች ሲዘጉ የአመጽ በሮች ይከፈታሉ

ከዳዊት ሰለሞን

የቀድሞው አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ከዓመት በፊት ጠቅላላ ጉባኤውን በአዲስ አበባ ሲያከናውን ከየክልሉ የመጡ ተሳታፊዎችን የማግኘትና በክለላቸው ስለሚያደርጓቸው እንቅስቃሰዎች፣ስለሚደርስባቸው እስራት፣ወከባ፣ድብደባና ስለሚፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች እንዲያካፍሉን የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ባልደረቦች እንወተውታቸው ነበር፡፡
Abreham 2

Abreham
አብርሃም ልጃለም ከጎንደር አካባቢ ወደ አዲስ አበባ ለጠቅላላ ጉባኤው የራሳቸውን የትራንስፖርት ወጪ ችለው ከመጡ የክልሉ የአንድነት አመራሮች አንዱ ነው፡፡ጎንደሮች አዲስ ሲመጡ ባዶ እጃቸውን አልመጡም፡፡ገበሬውን ወላጅ አባቷን በመኖሪያ ቤቱ በጥይት ደብድበው ከገደሉት በኋላ በተኛችበት የመደብ አልጋ በተተኮሰባት ጥይት የቀኝ እጇን ለመቆረጥ የበቃችን የስምንት ዓመት ታዳጊ ወጪዋን ሸፍነው አምጥተዋት ነበር፡፡

አብርሃም ልጃለምና ጓደኞቹ በክልላቸው ስለሚፈጸም የመብት ጥሰት የሚያወሩት በቃል አይደለም፡፡ስለሚያወሩት ነገር በሙሉ መረጃዎች አጠናቅረው ዶሴ አዘጋጅተው ሌላው ቀርቶ ኢህአዴግ አካባቢውን ከተቆጣጠረበት ግዜ አንስቶ ጠቅላላ ጉባኤው እስከተደረገበት ወቅት ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የተገደሉ ሰዎችን ስም ዝርዝር እስከ አያታቸው መዝግበው ይዘዋል፡፡

የ2007 ምርጫ ለኢህአዴግ በክልላቸው የመጨረሻ እንደሚሆን በድፍረት የሚናገሩት እነ አብርሃም ምርጫው ከመድረስ አስቀድሞ ምርጫ ቦርድ የተባለ መራጭ አንድነትን ለትዕግስቱ መስጠቱን ተከትሎ ህልማቸው ተዘረፈ፡፡አፍታም ሳይቆይ የአብርሃም አካባቢ የአንድነት አባላት በገዢው ፓርቲ ፖሊሶች ታስረው ማዕከላዊ ተወሰዱ፡፡
አብርሃምና ከአፈናው የተረፉት የአርማጭሆ ልጆች ተማከሩ፡፡ከአሁን በኋላ ምን ቀረን የሚለው ጥያቄ የምክራቸው ማጠንጠኛ ነበር፡፡ፓርቲያቸው ፈርሷል፣ሰላማዊ ትግልን የቆረቡበት ያህል ጸንተው ያጸኗቸው ጓዶቻቸው ‹‹ሽብርተኛ››ተሰኝተው ደብዛቸው እንዲጠፋ ተደርጓል፡፡እናማ ቀሪዎቹን የወሰዱ እግሮች እያንዳንዳቸው ደጃፍ ከመድረሳቸው አስቀድሞ ቀደሟቸው፡፡

አብርሃምን በምስሉ እንደምትመለከቱት በረሃ ወርዶ ከሐሳቡ ውጪ የነበረውን መንገድ ተቀላቅሏል፡፡ከ15 የማያንሱ የጎንደር አካባቢ የቀድሞ የአንድነት አባላትም ዛሬ በአብርሃም መንደር ይገኛሉ፡፡

The post የአንድነቱ አብርሃም ልጃለም በረሃ ወርዶ የብረት ትግሉን ተቀላቅሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle) (በሥዩም ወርቅነህ)

$
0
0

ሼህ መሐመድ አላሙዲ-ከመንግስት ባለስልጣናት-ከልማታዊ አርቲስቶቻችን

 

unnamedቱጃሩ ‘ሼክ’ መሐመድ አል አሙዲን፤ጋጠወጦቹ የወያኔ መንግስት ሹማምንቶች፦ የሃገሪቱ ፕሬዚደንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ፣ የፌደረሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ በረከት ስምዖን፣ እንዲሁም ታላላቅ ‘የተከበሩ’ እንግዶችና የአርቲስት ቤተሰቦች በተገኙበት፤ በትላንትናው እለት የትዝታው ንጉስ ጋሽ ማህሙድ አህመድ 50ኛ ዓመት የሙያ ጉዞ በማስመልከት የተዘጋጀ ዝግጅት ሲከበር፤ ከወጣቷ አክትረስ ማህደር አሰፋ ጋር ከትዳራቸው ውጭ ሲማግጡ ታይተዋል። ይህ ከሃገራችን ባህልና ወግ በእጅጉ የሚፃረርና የወደፊት ተተኪውን ትውልድን ወደ አልባሌ ድርጊት የሚገፋፋ ነውረኛ ተግባር ነው።

 

ማህደርና ሼሁ ለብዙ ጊዜ ሲታሙ መቆየታቸው ይታወቃል። ነገር ግን ንቀት ካልሆነ በቀር እንደዚህ ጋጠወጥ የሆነን ድርጊት በአደባባይ ማድረጉ ለምን አስፈለገ? የወያኔ ሊቀመናብርት ባለስልጣናትን በመዳፋቸው በማስገባት የሃገሪቱን ሃብት የሚዘርፋት ሼክ መሃመድ አል አሙዲን በልማታዊ አርቲስቶቻችን ሰይፉ ፋንታሁን፣ ሰራዊት ፍቅሬ፣ ሙሉዓለም ታደሰ፣ ማዲንጎ አፈወርቅና በሌሎችም አማካኝነት ታዳጊ ወጣት የሃገራችን ልጃገረዶችን በሃብታቸው በማማለል ከአላማቸው በማሰናከል ንፅህናቸውን እንዲያረክሱ ያስገድዷቸዋል። ይህን ህገ-ወጥ ድርጊት የሚያውቁት የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ከማድረግ ይልቅ በተጋበዙበት ግብዣ እንኳን ከትዳራቸው ውጭ እየማገጡ እያዩ በጭብጨባ አጅበዋቸዋል።

 

ወያኔና ጀሌዎቹ ላለፉት 24 ዓመታት የኃገራችን ሃብትና ንብረትን የዘረፉት አንሷቸው፤ ታሪካችንን ሲያጠለሹ፣ ሲያጠፉ፣ የታሪክ መፅሃፍትና ቅርስ ለባዕድ ሲሸጡ፣ ሲያቃጥሉ፣ ባህልና ወጋችንን ሲያንኳስሱ፣ የእምነትና ሃይማኖት ስፍራዎችን ሲያረክሱና ሲያቃጥሉ፣ እንዲሁም አያሌ ወንጀሎችን ሲፈፅሙ መቆየታቸው ፀሃይ የሞቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው። እንደ አንድ ኢትዮጵያዊ ለእኔ በዚህ ደረጃ ተንኮታኩታ ጥበብ በአደባባይ ረክሳ፣ ሃገር ተደፍራና አንገታችንን አስደፍታ ማየት ያመኛል። ልማታዊ አርቲስቶቹና የወያኔ ቁንጮ ባለስልጣናት በሼሁ ፍርፋሪ ገንዘብ ህሊናቸው ታውሯል። ልማታዊ አርቲስቶቹም በጥቅም በመደለል የወያኔ ሎሌ ሆነዋል። በቅኝ ግዛት ተገዝታ የማታውቀው ሃገራችን ኢትዮጵያም ሼክ መሐመድ አል አሙዲን እንደፈለጉ የሚፈነጩባትና እሚያዙባት ሃገር ሆናለች።

 

ሼህ መሐመድ አል አሙዲን 28 ክርስቲያን ወንድሞቻችን ISIS በሚባለው እስላማዊው አሸባሪ ቡድን ከታረዱ ወዲህ ለብዙ አርስቲስቶች በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ብሮች በስጦታና በሽልማት መልክ አበርክተዋል። ለአብነት ያህል ለአርቲስት ማዲንጎ አፈወርቅና ለንዋይ ደበበ ሁለት ሁለት ሚሊዮን ብር፣ ለመሳፍንት 9 ሚሊዮን ብር እንዲሁም በትላንትናው ዕለት ለአርቲስት ማህሙድ አህመድ 5 ሚሊዮን ብር በሽልማት መልክ ለግሰዋል። እውን ይህን ሁሉ የሚያደርጉት ለአርቲስቶቻችን እውነተኛ አክብሮት ኖሯቸው ይሆን!? እውነተኛ ምክንያታቸው ይህ ቢሆን ኖሮ በርካታ ታላላቅ አርቲስቶቻችንና እውቅ ዜጐቻችን በሼሁ ብሮች በተጥለቀለቁ ነበር። ይልቁኑስ በዙሪያቸው የተሰባሰቡት አርቲስት ተላላኪዎቻቸውና ሎሌዎቻቸው በወንጀል ያደፈ ልባቸውን፣ በዝርፊያ የተጨማለቀ እጃቸውንና፣ ውስጠ ሚስጥራቸውን ስለሚያውቁ በውለታ መልክ ጠፍረው ለመያዝና አንዳንድ የዋህ ዜጐችን ለማምታታት ይመስላል።

 

ሼሁ በእውነት ለሃገራችን ደራሽ የሆኑ ቅን ሰው ቢሆኑ ኖሮ፤ መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ በሃዘን ቅስሙ በተሰበረበት፣ መሪር ሃዘኑ በከፋበት፣ የልጆቹ አንገት በቢላዋ ሲቀላ በአደባባይ ተመልክቶ ባዘነበት በዛ ድቅድቅ ጨለማ፣ ለኢትዮጵያ ህዝብ ሃዘናቸውን በገለፁ ነበር፤ እንደሌላውም ቅን ኢትዮጵያዊ ልጆቻቸው ለታረደባቸው ቤተሰቦች እርዳታ ባደረጉ ነበር። ዛሬ ደግሞ አይናቸውን በጨው አጥበውና የኢትዮያን ህዝብ ንቀው፤ የልጅ ልጃቸው ከምትሆነው ከወጣት ተዋናይት ማህደር አሰፋ ጋር፤ ከኢትዮጵያ ባህልና ወግን ባልተከተለ መልኩ ባደባባይ ባልባለጉ ነበር። ሼሁ በISIS ልጆቻቸው ለተጎዳባቸው ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ያልገለፁትና  ያለመርዳታቸው፣ ያለሃፍረትም እንዲህ ያስፈነጠዛቸው ምክንያት በሃዘናችን ተደስተው ይሆን!? ወይንስ ሌሎችም እንደሚታሙት ለISIS አጋርነታቸውን እየገለፁ!?~መጠርጠር አይከፋም!።

 

የኢትዮጵያ ታሪክና ወግን አስጠብቀን ለተተኪ ትውልድ ለማስተላለፍ ወያኔን ማስወገድ አማራጭ የሌለው መፍትሄ ነው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም በልጆቿ ተከብራ ትኑር!

እናቸንፋለን!

The post የፍቅር ትርያንግል አዙሪት(Lovers Triangle) (በሥዩም ወርቅነህ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል በ20 ሰው በድብቅ በሚኒሶታ አከበረ

$
0
0

Girma biru
(ዘ-ሐበሻ) የሕወሓት መንግስት የሚኒሶታን ሕዝብ እንደ ጦር ነው የሚፈራው – ለዛም ነው ሕዝባዊ ስብሰባና በዓል ሲያደርግ በድብቅ የሚያደርገው:: ከዚህ ቀደም በአደባባይ ፖስተር ለጥፎ ስብሰባ ሲጠራ ሕዝቡ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት በማወኩ ስብሰባው ሳይካሄድ ቀርቷል::

ትናንት June 13 በሚኒሶታ የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል ለማክበር በሚኒሶታ በድብቅ ስብሰባ ጠርቶ ነበር:: በሚኒሶታ 5ለ1 በሚል ጥርነፋ የተደራጁ የሕወሓት መንግስት ደጋፊዎች ያሉ ሲሆን እነዚህ ሰዎች የየራሳቸውን ኮኔክሽን ቢጠሩም በስብሰባው ላይ ከ20 የበለጠ ሰው ሳይገኝ ቀርቷል:: በረመዳ ሆቴል በተደረገው በዚሁ በከሰረው የግንቦት 20 በዓል ላይ የሕወሓቱ ተላላኪና ከደንበል ሲቲ ሴንተር ጋር በተያያዘ በሙስና የሚታሙት አቶ ግርማ ብሩ የመጡ ቢሆንም በኪሳራ ወደመጡበት ተመልሰዋል::

ከአቶ ግርማ ብሩ የቀረቡ ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሠረት በስብሰባው ላይ ከ20 ሰው በታች መገኘቱ በጣም ከመበሳጨታቸው የተነሳ በድብቅ የተጠሩት ሰዎች ሁሉ ባለመገኘታቸው “ምን አድርገናቸው ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ነው::

የሕወሓት መንግስት በዓል የሆነው የግንቦት 20 በዓል በሚኒሶታ በባዶ አዳራሽ መካሄዱ ለሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ትልቅ ድል ነው::

The post የሕወሓት መንግስት የግንቦት 20ን በዓል በ20 ሰው በድብቅ በሚኒሶታ አከበረ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ሰኔ 7 ቀን 2007 ፕሮግራም
Habitamuአቶ ወረታው ዋሴ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ጉዳይ ሀላፊ በድህረ ምርጫ የተቃዋሚዎች ዝምታን አስመልክቶ ጠይቀናቸው ከሰጡት ምላሽ የተወሰደ  (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…በቀጥታ አይከል ከተማ ከላይ አርማጭሆ የመጡ ሶስት ወጣቶች ሻይ ቤት ተቀምጠው እያለ ታጣቂዎቹና ፖሊሶች በአንድነት መጥተው ወጣቶቹ ላይ ጥቃት ሲፈጽሙ ሰው ግልብጥ ብሎ አትነኳቸውም ልጆቻችንን አለ በዚህ ጊዜ ወደ ሕዝቡ ተኮሰው አምስት ገለው ስድስት ቆስለዋል..እንዴት ሰላማዊ ሰው ላይ በመሳሪያ ጭፍጨፋ ይደረጋል?..> በሰሜን ጎንደር የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ሁበር ኤክስ ለቬጋስ አያዋጣም የሚያዋጣው ብላኩ ነው እሱ እንዲፈቀድ መታገል ጥሩ ነው ካልሆነ የቲፕ ነገር የግድ በስብሰባ መነሳት አለበት…>

አሌክስ አበራ ከሳን ፍራሲስኮ ስለ ሁበር የግል ልምዱን መሰረት አድርጎ ከሰጠው ማብራሪያ  (ውይይቱን ያዳምጡት)

ከኒዮርኩን እስር ቤት ያመለጡት መጨረሻ ያለመታወቅ የፈጠረው ጭንቀት እና ያልተሳካው በመቶዎች የሚቆጠሩ ፖሊሶች አሰሳ( ልዩ ዘገባ)

በውጭ የሚኖረው ነጻነት ናፋቂ ኢትዮጵያዊ በጭብጨባ ተገቢውን ትኩረት አግኝቷል? (ምልከታ)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ አልሸባብ ከኢትዮጵያ ወታደሮች ጋር መዋጋቱን አመነ

ኢትዮጵያዊው በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞችን በጠርሙስ ልትገድል ነበር በሚል ከሰባት ዓመት በላይ እስር ተፈረደበት

በሆንግ ሆንግ የኢትዮጵያን ቆንስላ የሚመሩት ባለስልጣን በህገ ወጥ የዝሆን ጥርስ ዝውውር እንዳሉበት ተዘገበ

በሰሜን ጎንደር የአገዛዙ ታጣቂዎች በሰላማዊ ሰዎች ላይ ተኩሰው አምስት ሲገድሉ ስድስት ማቁሰላቸው ታወቀ

የደቡብ አፍሪካው ፍርድ ቤት በአልበሽር ላይ ያስተላለፈው ውሳኔ አለመከበር ቅሬታ ፈጠረ

 የሰው ብልት በበስጦታ ያገኘው ደቡብ አፍሪካዊ ከእጮኛው ልጅ ማግኘቱ ተዘገበ

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የይስሙላውን ምርጫ የመቶ በመቶ አሸነፍኩ ማለቱ  አገዛዙ የማጭበርበር አቅም ማጣቱን ያያል ብሏል

የኢትዮጵያው ዋሊያ የሌሴቶን ቡድን 2 ለ1 አሸነፈ

የሱዳኑ ፕሬዝዳንትን የደቡብ አፍሪካ ባለስልጣናት የፍርድ ቤት ውሳኔ በመጣስ ከአገር እንዲወጡ መፍቀዳቸው ተዘገበ

 ሌሎችም ዜናዎች አሉ

(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ።  በተጨማሪ  በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢውሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት 1340 .ኤም  የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።

The post Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>