Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

ሰበር ዜና –አልበሽር “ተለቀው”ወደ ሱዳን በረሩ

Previous: Hiber Radio: በሰሜን ጎንደር በታጣቂዎች በተወሰደው እርምጃ አምስት ንጹሃን ሲገደሉ ስድስት መቁሰላቸው ተነገረ፣ በእንግሊዝ ሁለት የጥበቃ ሰራተኞች ትገል ነበር ተብሎ ኢትዮጵያዊው ከሰባት ዓመት በላይ ተፈረደበት፣የአፍሪካ ህብረት የጦር ቃል አቀባይ በአልሸባብና በኢትዮጵያ ወታደሮቹ መካከል የደፈጣ ውጊያ መኖሩን ማመኑ፣ ደቡብ አፍሪካዊው በስጦታ ያገኘው ብልት ለእጮኛው ተርፎ ማስረገዙ መዘገቡ፣ በሆንግ ኮንግ የሚገኘው ቆንስላ በህግ ወጥ ንግድ መሰማራቱ መጋለጡ የሚሉና ሌሎችም አሉን
$
0
0

alebeshir
በደቡብ አፍሪካዋ ፕሪቶሪያ ግዛት ውስጥ በቁም እስር ላይ የነበሩት የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው ሳይሰጡ ከደቂቃዎች በፊት ወደ ሱዳን መብረራቸውን የተለያዩ የዜና ምንጮች ዘግበዋል:: በቅርብ ሰዓት ውስጥ ካርቱም ይደርሳሉ የተባሉት እኚሁ ፕሬዚዳንት እዚያም እንደገቡ ለጋዜጠኞች መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ ይጠበቃል::

The post ሰበር ዜና – አልበሽር “ተለቀው” ወደ ሱዳን በረሩ appeared first on Zehabesha Amharic.


በደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል: ሰበካ ጉባኤውን በማዳከም በካህናት እና ምእመናን ላይ ግፍ የፈጸሙት አለቃ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ

$
0
0

bisrate-gabriel-church00የደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን: በልማት ስም ከጥቅመኛ ግለሰቦች ጋር በመመሳጠር የቤተ ክርስቲያንን ሀብት እና ንብረት ለግሉ በማካበት በሚታወቀው የቀድሞው አለቃ ኃይሌ ኣብርሃ፥ በግንባታ እንዲኹም የባለቤትነት እና የተጠቃሚነት መብቱን አሳልፈው በሚሰጡ የኪራይ ውሎች ከመመዝበሩም በላይየሚልዮኖች የባንክ ባለዕዳ አድርጎት ያለተጠያቂነት ለመሰል ዘረፋ ወደ ሌላ ደብር ተዘዋውሯል፡፡

በእግሩ የተተኩት ግብታዊው እና ዐምባገነኑ መልአከ ብርሃን ዘመንፈስ ቅዱስ (የሀገረ ስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሊቀ ማእምራን የማነ አባት)፥ በቃለ ዐዋዲው ደንቡ መሠረት በሰበካ ጉባኤው ሙሉ ተሳታፊ የኾኑትን እና የወሳኝነት ድርሻ ያላቸውን የማኅበረ ካህናት፣ የማኅበረ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት ተወካዮችን በማሳደድ እና ከልጃቸው ጋር ተማክረው ሥልጣን በሌለው የክፍለ ከተማው የሰው ኃይል አስተዳደር ሓላፊ በኩል ወደ ሌላ አድባራት በማዘዋወር ሀብቱንና ይዞታውን ከሚነጥቁ ቀማኞች ጋር እየሠሩ ነው፡፡

* * *

  • በአለቃው ከሰበካ ጉባኤው የተባረረው የማኅበረ ምእመናን ተወካዩ እና የሰንበት ት/ቤቱ አባሉ ዲ/ን ሰሎሞን የኋላሸት ‹‹ወረቀት በትኗል፤ አድማ አነሣስቷል›› በሚል በአለቃው ጥያቄ ከቅዳሜ ምሽት ጀምሮ በእስር ላይ ነው
  • በጥፋታቸው ስለሚቃወሟቸው፣ በዋና ሥራ አስኪያጁ ልጃቸው ተመክተው በግፍ ያዘዋወሯቸው ካህናት በሳምንት ጊዜ ውስጥ እንዲመለሱ፤ ሰበካ ጉባኤውም እንደ ቃለ ዐዋዲ ደንቡ በተሟሉ ተወካዮች እንዲጠናከር ምእመናኑ ማሳሰቢያ ሰጥተዋል
  • በደብሩ የጠበልተኞች ማደርያ የኾነው ቦታ እንዲከበር የሚጠይቁትን የጠበል ዕድርተኞች ፊት በመንሳት ለግለሰብተላልፎ እንዲሰጥ እየተባበሩ ነው
  • በሰበካ ጉባኤው የሰንበት ት/ቤቱ ተወካይ በመልቀቁ በሌላ እንዲተካ ሰንበት ት/ቤቱ ለወራት ላቀረበው ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ አይደሉም
  • ምክትል አስተዳዳሪ በሚል ተቀምጦ ቀድሞ ደብሩን ለመዘበረው ኃይሌ ኣብርሃ መረጃ የሚያቀብለው ግለሰብ ተጨማሪ ምእመናንን በጥቆማ ለማሳሰር እየሠራ ነው

Source:: haratewahido

The post በደ/ብሥራት ቅ/ገብርኤል: ሰበካ ጉባኤውን በማዳከም በካህናት እና ምእመናን ላይ ግፍ የፈጸሙት አለቃ ከሓላፊነታቸው እንዲነሡ ተጠየቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ ራሱን አጠፋ

$
0
0

ትህዴን ባሰራጨው ዘገባ ለሃምሌ ወር 2007 ዓ/ም የቆይታ ጊዜአቸውን ጨርሰው በሚገኙ የሰራዊት አባላት ላይ እየተካሄደ ባለው የከፋ የዘረኝነት ምልመላ ምክንያት አንድ የኦሮሞ ተወላጅ የሆነ የአስር አለቃ ማዓረግ አይገባህም በመባሉ የተነስ እራሱን እንዳጠፋ ተገለፀ።

newsለትህዴን በደረሰው መረጃ መሰረት- የ23ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሬጅመንት በ3ኛ ሃይል ውስጥ የቲም ምክትል አዛዥ የነበረ አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ የተባለው ወታደር በተለያዩ መድረኮች ላይ ተቃራኒ የሆነ ሃሳቦችን ያቀርባል ለህገ መንግስቱ ታማኝ አይደለም መንግስትን ያማርራል የሚሉ ነጥቦችን አስቀምጠው ማዕረግ አይገባህም ተብሎ ከሃይል አመራር በላይ ያሉ አዛዦች ውሳኔውን በማስተላለፋቸው ምክንያት ስሜቱ የተጎዳው ይህ ወታደር ስብሰባው እንዳለቀ ዋርዲያ ነኝ በሎ በመውጣት እራሱን እንዳጠፋ ከእዙ የደረሰን መረጃ አመለከተ።

በአሁኑ ጊዜ በኢህአዴግ የሰራዊት አባላት ውስጥ ያለው የከፋ የዘረኝነት አድሎዎ ለማዕረግ እድገትና ለተለያዩ ጥቅማጥቅሞች ሲባል በሚደረጉ ምልመላዎች ላይ የሰራዊቱ ከፍተኛ አመራሮች በሰራዊት ውስጥ ኢ- ፍትሃዊ የሆነ አሰራር እየሰሩ መሆናቸውን በተለያዩ የሰራዊት እዞች ውስጥ የሚገኙ ምንጮቻችን የላኩልን መረጃ ያስረዳል ሲል ትህዴን መረጃውን ቋጭቷል::

The post አስር አለቃ ጫላ ጋዲሳ ራሱን አጠፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ * ብርሃኑ “እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ”ተብሎ ወረቀቱን ተነጥቋል

$
0
0

birhanu tekle
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት የኢትዮ-ኤርትራ ድንበርን ተሻግረው ኤርትራ የሚገኘውንና በተወካዮች ም/ቤት በሽበርተኝነት የተፈረጀውን የግንቦት ሰባት ወታደራዊ ክንፍ ሊቀላቀሉ ሲሉ በጸጥታ ኃይሎች ማይካድራ ላይ በቁጥጥር ስር አውያቸዋለሁ ያላቸው እነ ብርሃኑ ተክለያሬድ አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ መቃወሚያቸውን አስገቡ፡፡

ዛሬ ሰኔ 9/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ የቀረቡት በእነ ብርሃኑ ተክለያሬድ የክስ መዝገብ የተካተቱት አራት ተከሳሾች ማለትም፣ ብርሃኑ ተ/ያሬድ፣ እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፍቅረማርያም አስማማውና ደሴ ካህሳይ በጋራ ያዘጋጁትን የክስ መቃወሚያ አስገብተዋል፡፡ አራቱ ተከሳሾች ጠበቃ ማቆም አንፈልግም በማለታቸው ያለጠበቃ የቀረቡ ሲሆን፣ ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ ሁለት አብይት ነጥቦችን በመጥቀስ ክሱ ውድቅ ተደርጎ በነጻ እንዲሰናበቱ ጠይቀዋል፡፡

ተከሳሾቹ በክስ መቃወሚያቸው ላይ እንደጠቀሱት አቃቤ ህግ ያቀረበባቸው ክስ ከህገ መንግስቱ ጋር የሚጣረስና (ጸረ-ሽብር አዋጁ ከህገ መንግስቱ ጋር እንደሚጣረስ በመጥቀስ) በወ/መ/ሥ/ሥ/ህጉ መሰረት ያልቀረበ በመሆኑ ፍርድ ቤቱ እንደ ህጉ ያልቀረበን ክስ ውድቅ በማድረግ በነጻ ያሰናብተን ብለዋል፡፡

ፍርድ ቤቱ በተከሳሾች የቀረበው አቤቱታ ላይ አቃቤ ህግ መልስ እንዲሰጥ በሚል ለሰኔ 19/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡ በሌላ በኩል አንደኛ ተከሳሽ ብርሃኑ ተ/ያሬድ በተደጋጋሚ በእስር ቤት በሚደርስበት በደል ላይ አቤቱታ ማሰማቱን ቀጥሏል፡፡ በዚህም ፍርድ ቤቱ አቶ ብርሃኑ አለኝ የሚለውን አቤቱታ በጽሑፍ እንዲያቀርብ አዝዞ የነበር ቢሆንም አቶ ብርሃኑ የማዘጋጀውን አቤቱታ ‹‹እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ›› በሚል ጽሑፉን እየተነጠቀ እንደሆነ በመግለጽ አቤቱታውን በጽሑፍ ማቅረብ እንዳልቻለ አስረድቷል፡፡

ይህን የአቶ ብርሃኑን አቤቱታ በተመለከተ የማረሚያ ቤቱ ተወካይ ችሎት ፊት እንዲቀርቡ ተደርገው ‹‹ፍርድ ቤቱ ተከሳሹ ያለውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አዝዘናል፤ ስለዚህ እናንተ መልስ ካላችሁ መልሳችሁን እንቀበላለን፣ አሁን ግን ተከሳሹ የሚያዘጋጀውን አቤቱታ እንዲያቀርብ አድርጉ›› በማለት በፍርድ ቤቱ ተነግሯቸዋል፡፡ በመሆኑም አቶ ብርሃኑ በቀጣዩ ቀጠሮ በእስር ቤት አያያዝ ላይ ያለውን አቤቱታ በጽሑፍ ይዞ ይቀርባል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

The post እነ ብርሃኑ ተ/ያሬድ የክስ መቃወሚያ አቀረቡ * ብርሃኑ “እንዴት ማረሚያ ቤቱን ትከሳለህ” ተብሎ ወረቀቱን ተነጥቋል appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ ሳሙኤል አወቀ ተገደለ

$
0
0

Samuel Aweke

"በመጨረሻም ተገደለ በቅርብ ከማውቃቸው ቆፍጣና: ሀገሩን ከምንም በላይ በማስቀደም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሊታገልላት ቆርጦ በመነሳት ምስክርነቴን ከምሰጣቸው ወጣት ታጋዮች አንዱ ነበር:: ለቃለመጠይቅም ሆነ መረጃ ፍለጋ በደወልኩለት ጊዜ ሁሉ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት ትብብር በማድረግ የስርዓቱን ግፍና ጭካኔ በማጋለጥ ግዴታውን በሚገባ እየተወጣ የነበረ ብረት የሆነ ወጣት:: ደበደቡት: አሰሩት: በአካሉ ላይ የሚችሉትንና የሚፈልጉትን ሁሉ ጉዳት አደረሱበት:: ሳሙኤል ካመነበት ንቅንቅ የሚል አልነበረም:: በመጨረሻም የወጣትነት ህይወቱን አጠፉት:: ታጋይ ይሞታል:: ትግል ግን........ሳሙኤል ነፍስ ይማር!" - ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

“በመጨረሻም ተገደለ
በቅርብ ከማውቃቸው ቆፍጣና: ሀገሩን ከምንም በላይ በማስቀደም የህይወት መስዋዕትነት በመክፈል ሊታገልላት ቆርጦ በመነሳት ምስክርነቴን ከምሰጣቸው ወጣት ታጋዮች አንዱ ነበር:: ለቃለመጠይቅም ሆነ መረጃ ፍለጋ በደወልኩለት ጊዜ ሁሉ በልዩ የሀገር ፍቅር ስሜት ትብብር በማድረግ የስርዓቱን ግፍና ጭካኔ በማጋለጥ ግዴታውን በሚገባ እየተወጣ የነበረ ብረት የሆነ ወጣት:: ደበደቡት: አሰሩት: በአካሉ ላይ የሚችሉትንና የሚፈልጉትን ሁሉ ጉዳት አደረሱበት:: ሳሙኤል ካመነበት ንቅንቅ የሚል አልነበረም:: በመጨረሻም የወጣትነት ህይወቱን አጠፉት:: ታጋይ ይሞታል:: ትግል ግን……..ሳሙኤል ነፍስ ይማር!” – ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን

ነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ እንደዘገበው የሰማያዊ ፓርቲ የምስራቅ ጎጃም ዞን ፀኃፊና በ2007 ዓ.ም ምርጫ የፓርቲው ዕጩ ተወዳዳሪ የነበረው ወጣት ሳሙኤል አወቀ ተገደለ፡፡ ወጣት ሳሙኤል አወቀ ትናንት ሰኔ 8/2007 ዓ.ም ምሽት ላይ ወደ ቤቱ እየገባ በነበረበት ወቅት በሁለት ግለሰቦች ከፍተኛ ድብዳባ ከተፈፀመበት በኋላ ሆስፒታል ውስጥ ነፍሱ አልፋለች፡፡

ወጣት ሳሙኤል ከቀድሞው አንድነት ጀምሮ ሲታገል የቆየ ሲሆን የሰማያዊ ፓርቲ መስራች አባል ነው፡፡ በአካባቢው የሚፈፀሙ በደሎችን ለሚዲያ በማጋለጥ ሲያበርክተው ከነበረው ሚና ባሻገር በፓርቲው በነበረው ጠንካራ እንቅስቃሴ ምክንያት በተደጋጋሚ እስርና ድብደባ ተፈፅሞበታል፡፡

የወጣቱን ግድያ ተከትሎ የነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ አዘጋጅ ጌታቸው ሽፈራው በፌስቡክ ገጹ የሚከተለውን አስፍሯል:: እንደወረደ ይኸው:-

ሳሙኤል ይህ አረመኔያዊ እርምጃ እንደሚወሰድበት ያውቅ ነበር፡፡ ግን ትግል ነውና ወደኋላ አላለም፡፡ ከሳምንታት በፊት እግሩን ሰብረውታል፡፡ ከዛ በፊት በተደጋጋሚ ታስሯል፡፡ ህዝብ በዳኞች ላይ ተማርሮ የጻፈውን የህዝብ አስተያየት አንተ ነህ የጻፍከው ተብሎ ታስሯል፡፡ እንደሚገድሉት ዝተውበታል፡፡ ይህ ሁሉ አልሆንላቸው ሲል ከሀገር እንዲወጣ ወትውተውታል፡፡ እሱ ግን እስከ ትናንትናዋ ማታ ድረስ ፀንቶ ቆይቷል!

ከሁለት ሳምንት በፊት ደግሞ በፌስቡክ ገጹ እኔን ቢገድሉኝም እናነተ ግን ፅኑ ብሎ አደራውን አስተላልፎ ነበር፡፡
samuel aweke lem

ውድ የደብረማርቆስ ከተማ ኗሪዎች!

ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ከ25’0000 በላይ መራጮች(ኮረጆውን) እርሱት እና በተጨማሪም በ31 ዩኒቨርስቲ የምትገኙ ከ14,000 በላይ ሰማያዊ ፓርቲን የመረጣችሁ ሌሎች ደጋፊዎች እና የኢሕአዴግ አባላትም የማያፍረው ብአዴን / ኢሕአዴግ ድምፅ መቀማቱ ሳያንስ በ21/08/2007 ዓም አፍነው ደብድበው ከሞት መትረፌ ቆጭቷቸው እሰር ቤት ለመወርወር ያለመከሰስ መብቴን እንኳን ተዳፍረው የሀሰት ክሰ እየፈጠሩ ነው!

በስልኬ እደተደወለም ያለፍላጎቴ ደሕንነት እያስገደደኝ ይገኛል፡፡

ተገደልሁም፣ ታሠርሁም፣ ታፈንኩም ነፃነት አይቀርም እና ለማሰረጃነት የደሕንነቶችን ስም፤ ፎቶግራፍ ፤ እና አድራሻ እንዲሁም በሐሠት ምሰክርነት እና ከሳሽነት የተደራጁ አካላት እና ዋና ተወካዮች የደብረማርቆስ ከተማ 04 ቀበሌ አመራሮች እና ፖሊስ ለታሪክ አሰመዘግባለሁ፡፡ ማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለሀገሬ እና ለነፃነት ነው፡፡ ከታሠርሁም ሕሊናዬ አይታሰርም ከገደሉኝም ትግሌን አደራ በተለይ የኔ ትውልድ አደራ! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትም! ትግላችን የነፃነት ጉዟችን ጎርባጣ መድረሻችን ነፃነት ታሪካችን ዘላለማዊ ነው!

(ከሳሙኤል አወቀ ዓለም –
የሰማያዊ ፓርቲ የደብረ ማርቆስ የሕዝብ ተወካዮች እጩ ተወዳዳሪ)

The post የሰማያዊ ፓርቲ የፓርላማ እጩ ተወዳዳሪ ሳሙኤል አወቀ ተገደለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰበር ዜና –የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ» ትላንት ምሸት በድብቅ ጅዳ ገቡ

$
0
0

የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ»

የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ»

ሰኔ 8 ቀን 2007 ምሸት ሳውዲ አረቢያ የገቡት የኢትዮጵያው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስተር ጉብኘት ያለተጠበቀና እንግዳ መሆኑን የሚናገሩ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ምንጮች በዲፕሎማቱ ዘንድ ከፍተኛ መደናገጥ መፈጠሩን  ገልጸዋል፡፤ ሚንስትሩ ከሳውዲ ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ለመገናኘት  ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ቢሄዱም   የኢ.ህ.አ.ዴ.ጉ ከፍተኛ  ባለስልጣን ጉብኝት ኦፊሴላዊ ይሁን በድብቅ እስካሁን የሚታወቅ ነገር እንደሌለ   ጅዳና ሪያድ ያሉት የመንግስት ዲፕሎማቶች ምንም አይነት ነገር  እንደማያውቁ   ከቆንስላው ጽ/ቤትና ከሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

13የሚንስትሩን ድንገተኛ ጉብኝት ተከትሎ   ማምሻውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ጋር ለመወያየት ሽርጉድ ይሉ የነበሩ የጅዳና አካባቢው ካድሬዎች ፡ የልማት ማህበራት ተወካዮች ለደጋፊዎቻቸው በሚስጠር ጥሪ ማስተላለፋቸውን የሚቃወሙ  ኢትዮጵያውያን  ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣኑ በዚህ መልክ ወደ ጃዳ  መግባታቸው  ዲፕሎማት ብለው ለሾሞቸው አገልጋዮቻቸው ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ብቻ ሳይሆን በዲፕሎማቱ  ላይ እምነት እንደሌላቸው  አመላካች መሆኑን ይናገራሉ። ከቀርብ ግዜ ወዲህ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ከፍተኛ ባለ ስልጣናት ለስራ ጉብኘትም ይሁን ለህክምና ወደ ሳወዲ አረቢያ ሲገቡ የኤንባሲው ዲፕሎማቶች  መረጃ የሚያገኙት ከተለያዩ  ድህረ ገጾች መሆኑን የሚናገሩ ውስጥ አዋቂዎች ከአንድ አመት በፊት አቶ በረከት ስመኦን በሚስጠር ለህክምና ሲገቡ ዲፕሎማቱ በተመሳሳይ ሁኔታ መረጃ እንዳልነበራቸው   ያስታውሳሉ ፡፤
12በሳውዲያዊው ቱጃር ሼክ አላሙዲን የግል አውሮፕላን ተጭንው  እኩለ ለሊት ሳውዲ  የገቡት አቶ  በረከት ስመኦን  ጅዳ ከተማ  የሚገኝ አንድ ሆስፒታል ውስጥ በህክምና ላይ መሆናቸውን የቆንሳላ ጽ/ቤቱም ይሁን  በሪያድ የኢትዮጵያ ኤንባሲ  ያወቁት  ጎልጉል እና ዘሃበሻ ሚዲያ ላይ በተለቀቀው መረጃ  መሆኑን  የሚገልጹ እነዚህ ወገኖች  በዲፕሎማቱና በመንግስት መሃከል ከፍተኛ የሆነ የመረጃ ክፍተት መኖሩን በማውሳት  የመረጃ ክፍተቱን ለማሞላት ዲፕሎማቱ ሚስጥራዊ  መረጃዎችን  ለማግኘት የተጠቀሱትን ሚዲያዎች  መከታተል አማራጭ የሌለው መፍትሄ እንደሆነባቸው  ይነገራል። ዛሬ በጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተደረገው ስብሰባ ላይ የታዩት ሚንስቲር ገብረክርስቶስ በሙስና ስለ ሚታመሰው በጅዳ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤትና ህልውናው ስላከተመው በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር ንብረት መባከን  ምንም መረጃ እንደሌላቸው ለማወቅ ተችሏል ።
አንድ የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መ/ቤት ሰራተኛ አስከትለው ትላንት ጅዳ ሳውዲ አረቢያ ስለገቡት ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚንስቲር ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ ጉብኘት  በሳውዲም ይሁን በኢትዮጵያ መንግስት መገናኛ ብዙሃን እስካሁን  ምንም የተባለ ነገር እንደሌለ ለማወቅ ተችሎሏ፡፤ አሁን ዘግይቶ በድረሰን ዜና ሚንስትሩ ወደ ሪያድ ከተማ ያቀናሉ ተብሎ ይጠበቃል

Ethiopian Hagere Jed

The post ሰበር ዜና – የወያኔው ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር «ብርሃነ ገብረ ክርስቶስ» ትላንት ምሸት በድብቅ ጅዳ ገቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ናቸው ተብሎ በኢሕ አዴግ ባለስልጣናት ተፈረጀ

$
0
0

የትህዴን ድምጽ እንደዘገበው ባህርዳር ከተማ ውስጥ የሚገኙ የአቢሲኒያ ባንክ ቅርጫፍ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ ተብሎው በኢህአዴግ ባለስልጣናት መነገራቸው ተገለጸ።
bank of abissinya
ለዜና ምንጩ በደረሰው መረጃ መሰረት በባህር ዳር ከተማ የኢህአዴግ ባለስልጣን በሆነው በአዲሱ ለገሰ በተደረገው የስብሰባ መሪነት አብዛኛው የአቢሲያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊዎች ናችሁ፤ ከመንግስት ጋር ያላችሁን ችግር በውይይት እንፋታው ብሎ በከፈተው ስብሰባ ላይ የባንኩ ሰራተኞች እኛን የቀጠረን ባንክ የግል ተቋም ነው። ስለዚህ ላንተ የምንሰጠው መልስ የለንም ብንናገርም የሚመጣ ለውጥ የለም በማለት ያለምንም ፍሬ ነገር ሳይግባቡ ከስብሰባው እንደተበተኑ ለማወቅ ተችሏል።

በአሁኑ ሰዓት አብዛኛው የመንግስት ሰራተኛ ምንም ዓይነት ወንጀልና ጥፋት ሳይኖረው ስርዓቱ በውስጡ ካለው ያለመተማመንና መጠራጠር ሁኔታ በመነሳት ንፁሃን ዜጎችን እያንገላታና በቂ ማስረጃ ሳያገኝ እያሰቃያቸው እንደሚገኝ የተገኘው መረጃ ጨምሮ አስረድቷል።

ለዘ-ሐበሻ በደረሰው መረጃ መሰረት ደግሞ አቢሲኒያ ባንክ የአማሮች ባንክ ተብሎ በሕወሓቶች ተፈርጇል:: ሕወሓቶች በአሁኑ ወቅት ወጋገን ባንክን እንደራሳቸው ባንክ የሚቆጥሩ ሲሆን አቢሲኒያ ባንክን ለማክሰም የአማሮች ባንክ በሚል ስያሜ እየሰጡ ሰዎችን እንደሚያሸማቅቁ ታውቋል::

The post የአቢሲኒያ ባንክ ሰራተኞች የተቃዋሚ ድርጅት ደጋፊ ናቸው ተብሎ በኢሕ አዴግ ባለስልጣናት ተፈረጀ appeared first on Zehabesha Amharic.

እርዱን ፍረዱልን አንልም፤ በነፃነት ተጋድሎአችን አይግቡብን! –ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ

$
0
0


Wendy-Sherman-Ethiopian-Election-628x329በመካከለኛዉ ምስራቅ ዝነኛ የሆነዉ ጋዜጠኛ ድንቅ የስነጹሁፍ ሰዉም ነዉ። በኮሎኔል ጋማል አብዱልናስር የቅርብ ሰዉነትነትና አማካሪነትም ይታወቃል። ሖስኒ ሙሃመድ ሃይከል እንደዳቦ የሚገመጡ መጻሕፍትን በመጻፉ፥ ከመካከለኛዉ ምስራቅ ባሻገር የእንግሊዝ አንባቢዎቹ የጹሁፎቹ እስረኞች ናቸዉ። አሁንም በጋርዲያን ጋዜጣና በስፔክቴተር መጽሄት የሚወጡ መጣጥፎቹ እንደጆን ላካሬ ልብወለድ መጻሕፍት የሚያማልሉ ናቸው። በእኛ በኩል ከዚህ ደራሲ-ጋዜጠኛ The Sphinx and the Commissar መጽሃፉ በቀልድም በቁም ነገርም የተጠቀሰ አንድ አጭር ‘ኤፒሶድ’ ለመዋስ እንወዳለን።

ሐይከል እንደጻፈው ከሰባቱ ቀን የአረቦችና የእስራኤል (1967) ጦርነት ማብቂያ አካባቢ የግብፁ መከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ፋዉዚ ሰፋ ያለ የጦር መሳሪያ ሸመታ ሊስት ይዘዉ ወደ ሞስኮ ይሄዳሉ። በክሬምሊን የተቀበሉአቸው የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር ማርሻል ግሬችኮ ነበሩ። በሰባቱ ቀን የሞስኮ ቆይታቸዉ ወቅት እስራኤል ስላወደመችባቸዉ ታንኮች፥ ኤፒሲዎች፥ አውሮፕላኖች – ስለማረከችባቸዉ ስፍር ቁጥር የሌለው የጦር መሳሪያዎች አንስተው እነዚያን እንዴት መተካት እንደሚቻል ሲነጋገሩ ሰንብተዋል።

በዉይይቱ ፍጻሜ ላይ ሁለቱ ማርሻሎች ብቻ ሳይሆኑ በሁለቱም ልዑካን ቡድኖች ዉስጥ አባላት የነበሩ የሁለቱም አገሮች ሹማምንት መለኪያ በማጋጨት “ናዝድራቬ ናዝድራቬ” ሲባባሉ ቆይተዉ የሶቪየቱ የመከላከያ ሚኒስትር የማሳረጊያ ንግግር ያደርጋሉ። የፖለቲካ ባህል ስለሆነ የሶቪየት ኅብረት ቀይ ሰራዊት የጀርመን ናዚዎችን እንዴት እንዳሸነፈ፤ አገሩን ብቻ ሳይሆን መላውን ምስራቅ አዉሮፓን ለድል እንዳበቃና ፒፕልስ ዲሞክራሲዎችን እንዴት እንዳቋቋሙ ደሰኮሩ። ከዚያም ማርሻሉ “አሁንም ከግብፅ ሰራዊት ጎን ተሰልፈን ጽዮናውያንን “እንደመስሳለን! እናሸንፋለን!” ብለው መለኪያ አጋጩ። መፈክር ቀረበ፤ ተፎከረ። (የልዑካን ቡድን አባላት ሆናችሁ ወደሞስኮ የሄዳችሁ ሁሉ የተከታተላችሁት ስነ-ስርዓት ሁሉ ተከናወነ። እንደምታዉቁት በስራ ሰአት በቢሮዎች የሚሾመው ቮድካ፥ ኮኛክ፥ ቪኖ ወዘተ ልክ የለዉም። ትንሽ የአካል ጥንካሬ ከሌለዎ የመጠጡ መጠን አለመኖር ሳይታሰብ ጉድ ያፈላል። ለማንኛዉም ፉከራዋም አለች።)

ትርዒቱ አላለቀም። የሶቪየቱ ማርሻል የግብጹን ማርሻል አውሮፕላን ማረፊያ ድረስ አጅበው በመሄድ በመጨረሻ ሞቅ ያለ ሰላምታ ተሰጣጡ። የግብፁ መከላከያ ሚኒስትር ለጊዜው መሳሪያ ጭነው ባይመለሱም፤ መስፈሪያ ሚዛን የሌለው ተስፋ ተሸክመው ሊሄዱ ነዉ። ያንን ተስፋ ከመሳፈራቸው በፊት እንደገና ለመስማት ፈለጉና፤ “ዛሬ ጠዋት የገቡልን ቃል ልቤን አሙቆታል” ይላሉ። በዚህ ጊዜ የሶቪየቱ አቻቸዉ “የቱ ነው ልብዎን ያሞቀው?” ሲሉአቸዉ ፋውዚ “ከእናንተ ጎን ተሰልፈን ፅዮናውያንን እንወጋለን፥ ያሉትን መጥቀሴ ነዉ” ይሏቸዋል። የሶቪየቱም ማርሻል እዚህ ላይ ሲደርሱ “ያንንኮ የጠቀስኩት ‘አንድ ለመንገድ’ ይሆንዎታል ብዬ ነዉ። “One for the Road አያዉቁም?” አሉአቸዉ ይባላል። ማሾፍ ወይም እንደፈረንጆቹ “bluff” ማድረጋቸዉ ኖሯል።

ባለፈው ወር ላይ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (ስቴት ዲፓርትመንት) ረዳት ሚኒስትር ወደ አዲስ አበባ የሚወስድ ተልዕኮ ነበራቸውና ወደዚያው ዘልቀው ተመልሰዋል። ለምን ነበር የሄዱት? ተብሎ የሚጠየቅ አይመስለኝም። በዚያ አካባቢ ትልቅ የጦርነት ቋያ አለ። በአረቢያን ፔኒንሱላ ያለውን አልቃይዳ እንዲከላከል ተመድቦ የነበረዉ የየመኑ ፕሬዚዳንት አብደላ ሳለህ፥ በአረብ ስፕሪንግ ባይበላም በህይወት ወጥቶ የመለስ ዜናዊ እንግዳ ሆኖ ነበር። አሁንም በዚያው አካባቢ ብቅ ጥልቅ ይላል። የመንን በተለይ ሆዴይደንና ሳንዓን ከአሰብ ድንጋይ ወርውረህ አንድ ሰው ልታቆስል ትችላለህ። አሜሪካ ደግሞ የእኛ ቤተኛ ስለሆነች ጋሞ ጎፋ (አርባ ምንጭ) በርከት ያሉ ሰው አልባ አዉሮፕላኖች (drones) አሰማርታ እነዚያ እንደዳክዬ ጉብ ጉብ ብለው ተቀምጠዋል። ስድስት ሺህ የአሜሪካ ሰራዊት ጅቡቲ ላይ መሽጓል። ባራክ ኦባማ ደግሞ የተመረጡበት አንድ ዓቢይ ቃል ኪዳን (ፕላትፎርም) በአመራራቸዉ ዘመን አንድ አሜሪካዊ በየትም አገር የጦር ሜዳ ላለማስገባት ስለሆነ ምንደኞችን በበጎ ፈቃድም ይሁን በግዥ ለማሰማራት አዘጋጅታ ያስቀመጠች የሃይለማርያም አስተዳደር አለች። እግረ-መንገዳቸዉን ወሃቢስቶችም ኤርትራን እንዲያግባቡ በዚያዉም (በነካ እጃቸው) ኢሳያስን ከርቀት ሆነው ከሚሳደቡበት አቅጣጫ እንዲመልሱ ልዩ ተልእኮ ተቀብለው ኤርትራዊውን መሪም በሪያድ አነጋግረዋል። ስንቅና ትጥቅ በማቀበል ረገድ (የመንን በኢራኖች ከሚደገፈዉ ደብረ በጥብጥ ኢስላማዊ ሃይል ለመታደግ) ዘመቻ ማስተባበር ያስፈልጋል። ምን ያስፈልጋችኋል? ምን ይሟላላችሁ? የሚል መልእክት ከማስተላለፍ ባሻገር ዌንዲ ሸርዉድ ጥቃቅን የመሰላቸዉን ራሳቸዉ ለመፈጸም ቃል ይገባሉ። ለነገሩ አዲስ አበባ ላይ ብሄራዊ ባንኩ የዉጭ ምንዛሪ የለኝም ማለት ከያዘ ሰንብቷል። አሜሪካ በዓመት የሚሰፍርልን ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የት እንደደረሰ እንግሊዝ ብቻ ለበጀት ማስተካከያ፥ ለዕዳ መክፈያና ለመሳሰሉት የምትሰጠዉ ሶስት መቶ ዘጠና ሶስት ሚሊዮን ፓዉንድ የአዲስ አበባን መንገድ አለማየቱን ሴትዮዋ እያወቁ አያውቁም። የአዉሮፓ ኅብረት አባል አገሮች በአጠቃላይ ለዚያ “ቀበኛ” እያሉ ለሚያሙት መንግስት ከቢሊዮን ዶላርስ በላይ ያፈሳሉ። እዉነትም ቀበኛ? “አየሁን” አያውቅም። ገንዘቡ የሚገባበት የበርሙዳ ትሪያንግል አለ። ለዌንዲ ያ ሁሉ ኢምንት ነዉ። ወያኔ ስለሚያስራቸዉ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ሰዎች – በአደባባይ ስለሚረሸኑ ኢትዮጵያዉያን ደንታ የላቸዉም። ያልተነሳም። አይነሳም። ጠባቸው ከአለም አቀፍ ሰብአዊ መብት ተከታታይ ሃይላት ጋር ነው። የዌንዲ ደንበኞች አይን ለአይን መተያየት የማይችሉ፥ ለምስክርነት የማይበቁና ከህሊናቸዉም ጋር የተሰነባበቱ ናቸው። ሴቲቱ ግራ የገባቸውና የሚያሳዝኑ ናቸው። ሀይለማሪያምና ጭፍሮቹ በምንም አይነት ሊደገፉ አይችሉም። ለአሜሪካኖቹ ደግሞ ስለነሱ የሚሰጡት ድጋፍ ሁሉ የሚያስገምታቸውና የሚያሸማቅቃቸው ነው። ወራዳና ባለጌ ባቆለጳጰስኸው ቁጥር ውርደቱ ሁሉ ወዳንተ ትከሻ ይዛወራል። ዌንዲ የዚህ ሰለባ ናቸው።

 

መጽሃፋችን “የሚያበራየዉን ወይፈን አፍ ማሰር አይገባህም” ይላል። የመንግስታችን እምነትም ይኸዉ ነዉ። የዉጭ ምንዛሬ በዉጭ፥ ለዉጭ ይቀመጣል። በአገር ከአገር የሚገኘዉ ገንዘብ ክርስቶስ እንዳለዉ የ “ቄሳር” ነዉ። ያም ሆነ ይህ የአሜሪካ የዉጭ ጉዳይ ረዳት ሚኒስትር ይህን ለመተሳሰብ ስልጣንም ዉክልናም የላቸዉም። ቢሆንም የመንግስታችንን ቀማኛነት፥ ፍርደ-ገምድልነትና፥ ተራ ሽፍትነት ­– ወደር የሌለው ወንጀለኝነት አያውቁትም አንልም። እኛ እንኳ ማስረጃ ስንጠይቅ ዋቢያችን የዌንዲ መስሪያ ቤት ሪፖርት ነዉ። በአጭሩ በኦባማ ፍልስፍና መመሪያ መሰረት ­– በተለይ ኦባማ “America should lead the world” የሚል አቋም በሰፊው እያራመዱ እንደ መሆናቸው አለምን የሚመሩበት አንደኛው አቋም የአሜሪካንን ጦርነት ደሀ ልጆቻችን በጦርነት መሰውያዉ እሳት ላይ ማንደድ ብቻ ሊሆን ነዉ::

 

በወያኔ በኩል አሁንም በመስዋዕትነት የሚቀርብ አለ። ስራዊቱ የእሳት ራትና የመድፍ ቀለብ እየሆነ ይዋጋላቸዋል። አሁንም ይዋጋል። ይህ ሁሉ ከሆነ በኋላ የወያኔ ባለስልጣኖች ለሴቲቱ ያቀረቧቸዉ ጥያቄዎች ምን እንደነበሩ መገመት ይቻላል። ጠንቋይ በመቀለብ ወይም በጸሎት የሚገኝ አይመስለኝም። ወያኔ ለአሜሪካም ሆነ ለሌላ ሀይል የኢትዮጵያ ልጆች የሆኑትን የሰራዊቱን አባላት በምንደኝነት ለማከራየት ዝግጁ ናቸው። በእውነቱ በእነ ሐይለማሪያም ደሰለኝ በኩል ሳይቀፍፋቸው፥ ለአፍታ እንኳን መንፈሳቸውን ሳይረብሸው ከቶውንም ጮቤ እየረገጡ የሚፈጽሙበት ይህን መሳይ ወራዳ ሰራ ነው። አሜሪካኖች በፈንታቸው ሊያስነኩ የማይፈልጉት እንዲህ ያሉ ወገኖቻቸውን የሚሸጡ ብቻ ሳይሆን የራሳቸውንም ሕሊና፥ መንፍስና፥ ነፍስ ለመሸጥ የተዘጋጁ ሰዎችን ነው ። እንዲህ ያሉ መሪዎች ከየትም አናገኝም ቢሉ አይደንቀንም። የአሜሪካ ድጋፍ ምክንያት ይህ ነው ።

 

የእኛዉ መሪዎች ከጦር መሳሪያ ሸመታዉ ዝርዝር፥ በመካከለኛዉ ምስራቅ በተለይም በሶማሊያና በየመን ባህረ ሰላጤ ከአሜሪካ ጋር ለመቆም ከሚያሳዩት ስምምነት ባሻገር ለመሄድ ዝግጁ ናቸው። ዌንዲ እንደሚሰማቸዉ ዛሬ አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትፈልገዉን ሁሉ ለማቅረብ የሚችለው ወያኔ ብቻ ነው። ያ መንግስት ለኢትዮጵያ ህዝብና ለኢትዮጵያ ያልቆመ በጥቃቅን ጥቅም ሊታለል የሚችልና “ብሄራዊ ክብር” የሚባል እምነት የሌለዉ መሆኑን ያውቃሉ። በገበያ የሚፈለገው አይነት መንግስት ተገኝቷል ማለት ነው። እንዲያም ሆኖ በጊዜ ማህፀን ዉስጥ ያለ መንግስት መፈለጋቸው እዉነት ነዉ። ጨረታው ከወጣ ደግሞ ቆይቷል። የተቃዋሚ ሃይሎችን ባነጋገሩ ቁጥር “ግልፅ አማራጭነታችሁን አረጋግጡ” እንዳሉ ነዉ። በዚህ አንጻር እነሱ ከአሜሪካ የሚያገኙት ጥቅም ሁሉ ተደማምሮ የእነ ብርሃኑ ነጋ ግንቦት ሰባት የማታ ማታ ምን ሊያደርስባቸዉ እንደሚችል አይዘነጉትም። የህልዉና ጥያቄ ነው ለወይዘሮይቱ ያነሱት። አዎን በየቦታዉ ሰራዊቱን እየላኩ የመድፍ ቀለብ፥ የእሳት ራት እያደረጉት ነዉ። ለኢትዮጵያ ጦርነትና ጥቅም ሳይሆን ለትልቁ ወንድም (ቢግ ብራዘር) የመስዋዕትነት ጠቦት እየሆንን ነዉ። በነገራችን ላይ ከዚህ ቀደም ለበርካታ አመታት (ከ1945 ወዲህ) የአሜሪካ መሪዎች “ይህ የአሜሪካ ዘመን ነዉ። አሜሪካ ዓለምን መምራት አለባት የሚለዉ የፖለቲካ ፈሊጥ በኦባማ የግዛት ዘመንም የበለጠ እየተራገበ መሆኑ ይደንቀናል። በ21ኛ ምዕተ አመት ሌሎች የአሜሪካ ፕሬዚዳንቶች አሜሪካን ወታደሮችን በጦር ሜዳ እያሰማሩ ሲሆን ኦባማ ግን ለአሜሪካ የዓለም ገዥነት የሌሎችን ሕዝቦች ነፍስና ደም የሚፈልጉ መስለዋል። “አሜሪካ አለምን መምራት አለባት” “America should lead the world” ያለይሉኝታ የሚነገር፥ አለም በሙሉ ለአሜሪካ መገበር እንዳለበት በእብሪት የሚገለጥ መፈክር ሆኗል። ከቀዝቃዛዉ ጦርነት ወዲህ አሜሪካ ብቸኛዋ ልዕለ-ሃያል በመሆንዋ ዓለም በሙሉ በእስዋ ፈቃድና ትዕዛዝ መሰረት መገዛት አለበት የሚል እብሪት የተሞላዉ አቋም ተፈጥሯል። አዎን! ነፍሰ ገዳዮችና የአራዊት ልብ የገባላቸው አምባገነኖችን አሜሪካ እያደነች በሕዝቦች ላይ በመጫን አለምን የመግዛትዋን አቋም ማንም ህሊና ያለው የአለም ዜጋ አይቀበለውም። በ21ኛው ክፍለዘመን አዲሱን የባርነትና የተራቀቀ ኒዮኮሎኒያሊዝም ለመቀበል ያዳግታል።

 

ወደ ሚስ ሸርዉድ እንመለስ

 

ሴቲቱ ከወያኔ መንግስት ባለሟሎች ጋር በሰፊዉ ሲወያዩ በአጀንዳዉ ውስጥ የወያኔ ጠላቶች ጉዳይ እንደሚያዝ ሳይታለም የተፈታ ነዉ። ስለሆነም ግንቦቶችና በዚያ የገለማ ስርዓት ላይ የተነሱ ሃይሎች ሁሉ ስለነሱ የተባለና የሚባል ጉዳይ መኖሩን መገመት አለባቸው። እንዲያዉም ማንም የአሜሪካና የአዉሮፓ መንግስት ባለስልጣን ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝና የወያኔ ሹማምንት ወደ እነዚህ አገሮች ሲሄዱ ከልመናና ከግዥ ሰነዳቸዉ ሊስት ዉስጥ ይህ ጥያቄ ዋነኛዉ መሆኑን መገመት አለ።

 

የዚህ መጣጥፍ መክፈቻ ካደረግነዉ የአልአህራም ጋዜጣ አዘጋጅ “አንድ ለመንገድ” አንጻር የሚስ ሸርዉድን መግለጫ መውሰድ እያመች ይሆናል። ይሁንና ሴቲቱ ለወያኔ አመራር ከሰጡት ተልዕኮና ሃላፊነት አንጻር የተወሰኑ የወያኔን ጠላቶች ማስፈራራት ትንሹ ውለታ ነበር። ወይም እስከ እናካቴዉ ግሬችኮ ለፋዉዚ የሰጡት የሽንገላ ቋንቋ ይሆናል። ፈረንጅ “የማሾፍ ፖለቲካ” ወይም bluff የሚለዉ ነዉ። ይህንን የፈረንጆች “የማሾፍ ፖለቲካ” ከራሳችን ታሪክ እንደሚከተለው እናቀርባለን።

 

የቪክቶር ኢማኑኤልና የቤኒቶ ሙሶሊኒ ኢጣልያ የመንግስታትን ማህበር ቃል ኪዳን ጥሳ ኢትዮጵያን ስትወረር በደፈጣ ፖለቲካ ውስጥ ገብተዉ የፋሽስቶች ረዳት ለመሆን ከአለም አቀፍ ሴራው ዋነኛ ተዋንያን መካከል የእንግሊዙ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰር ሳሙኤል ሖርና የፈረንሳዩ ጠቅላይ ሚኒስትር ፒየር ሳቫል ነበሩ። እነዚህ ሁለት ዲፕሎማቶች የሊግ ኦፍ ኔሽንስ ዋና ጸሃፊና የአንዳንድ ሌሎች መንግስታት ወኪሎች አምታተው ሴራቸውን ተያይዘውታል። በዚሁ መሰረት ፈረንሳይና እንግሊዝ የሙሶሊኒ ሰራዊትና የጦር መሳሪያ በስዊዝ ካናል በኩል ወደሞቃዲሾና ምጽዋ እንደተሸኘ ያውቃሉ። የሙሶሊኒ ሰራዊትና የጦር መሳሪያ፥ የአየር ቦምቦችና የነርቭ ጋዝ በስዊዝ ካናል ፀሃይ እየሞቀዉና 140 የእንግሊዝና የፈረንሳይ መርከቦች እያዩአቸዉ ኢትዮጵያዉያንን ለመጨረስ ተጭኖ አልቋል። በዚህ መካከል ቀና አመለካከትና ሰብዕና የነበራቸዉ በሊጉ የእንግሊዝ ቋሚ መልእክተኛ የነበሩት አንቶኒ ኢደን በሴራዉ በመብሸቅ አንጀታቸዉ ቆስሎ አልሰሩ አላስበላ አላስጠጣ ብሏቸዋል። በመካከሉ ሁሉ ነገር ለኢጣልያ ከተመቻቸና በሽሬና በአምባአላጌ እንዲሁም የጦር ሚኒስትሩ ራስ ሙሉጌታ በነበሩበት ግንባር (50ሺ ጦር) ሩቡ ያህል በቦምብና በጋዝ ሲያልቅ ላቫልና ሖር የፖለቲካ ትርኢት ማሳየት ይጀምራሉ። በዚህም መሰረት ሰር ሳሙኤል ሖር ወደ ጄኔቫ በመሄድ ወደሊጉ ስብሰባ ገብቶ “የሊጉ ቃል ኪዳን ይከበራል! አይታጠፍም! ሊጉ ለቆመለት ቁም ነገርና አላማ አገሮች ማናቸዉንም መስዋዕትነት ይከፍላሉ። እንግሊዝ ወረራውን በቀላሉ አትመለከተዉም” በማለት ጉባዔውን አንጫጫው። አዳራሹ በጭብጨባ ተቃጠለ። በዚሁ ልክ ፒየር ላቫልም ከሊጉ አዳራሽ ውጭ ሆኖ “ፈረንሳይም ከሊጉ ጋር ትቆማለች” እያለ ሲጮህ ዋለ። (በነገራችን ላይ የታሪክ ፍርድ ሲገመገም ሳቫል ማታ ላይ ፓሪስ ውስጥ የተለመደ እንቅልፉን ማለዳ ሲጨርስ ፈረንሳይ የሂትለር ግዛት ሆናለች።)

 

ሁለቱም የፖለቲካ አሻጥረኞች በጄኔቫ እንዲያ ሲናገሩ ብዙ የመንግስታት ወኪሎች ተቀብለዋቸዉ ነበር። ታዲያ ሳሙኤል ሖር በሊጉ ጉባዔ ላይ ያደረገዉን “ታሪካዊ ንግግር” በተመለከተ በትዝታ መጽሃፉ ውስጥ ማሾፌ ነበር፥ “It was all a bluff” ብሎታል። ራሱ ቤኒቶ ሙሶሊኒ ሳሙኤል ሖር ያንን ንግግር ካደረገ በኋላ በማግስቱ በእንግሊዙ Morning Star ላይ ባወጣዉ ጽሁፍ “ሰራዊታችን ያለ ችግር ምስራቅ አፍሪካ ገብቷል! ጉዳዩ የሁለት ቢሊዮን ሊሬ ጥያቄ ነበር። ያንን ሁሉ በሰማይ ከዋክብት የሚለካ ገንዘብ ያወጣነዉ ለለበጣ መሰላችሁ?” ብሎአል። በዚሁ አይነት እኒህም የአሜሪካ ዲፕሎማት የተናገሩትን ያናገራቸው የከዋክብት ግምት ያለው ጣጣ ካልሆነ እንዲሁ የፖለቲካ bluff ነው ትላላችሁ? የአዉአሎም ልጆች አካሄድኮ አይታወቅም። በመልካም ልግስና ብዙ ስራ ለመስራት እንደሚፈልጉ አንዳንድ ጊዜም በእህቶቻችንና በሚስቶቻቸዉ አማካኝነት ወፍራም አስበ ደነስ (ግዕዙን ቀሲስ አስተርይ ካልተቃወሙት) እንደሚያፍሱ ይታወቃል። ተክነዉበታልም። እንዲያም ሆኖ እንደ ሳሙኤል ሖር It was a bulff ወይም እንደ ማርሻል ግሬችኮ It was one for the road የሚሉበትም አጋጣሚ አይጠፋም። ኣድሮ ማየት ነዉ። ታዲያ ብዙዎቻችን ሚስ ዌንዲን የወቀስናቸዉንና የተቸናቸዉ፥ “እንዴት ለወያኔ እንዲህ ያለ ምስክርነት ይሰጣሉ?” በማለት ነዉ። ከፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ መግለጫዎች አንዲቱን ይዤላቸዋለሁ። አሜሪካኖች ለመስማት ሲፈልጉ ይሰማሉ፤ ለማየት ሲፈልጉ ያያሉ። ለማየት ሲፈልጉ በሳር ክምችት ዉስጥ ያለች መርፌ ያያሉ። ካልፈለጉ ደግሞ በእልፍኝ ዉስጥ የሚጎማለል ዝሆን አይታያቸዉም ብለዋል። ዌንዲ አስመሳይና የዉሸት ተለማማጅ እንጂ በደደብነት የሚታሙ አይመስለኝም። (በነገራችን ላይ ሴትዮዋ ተገፍተው ወጥተዋል። ዕድል ሌላ ጊዜ ይህን የመሰለ ስራ የምትሰጣቸው አይመስልም። የምዕራቡ የፖለቲካ አምላክ የጻፈላቸው የፈረደባቸው እንዲሁ ዘወር ማለትን ብቻ ነው።

 

እነዚህ ልምድ ያላቸዉ ምዕራባውያን ለምሳሌ አሜሪካ ከአንድ መንግስት ጋር የጠበቀ ግንኙነት አለው ተብሎ በሚገመትበት ሰአት ላይ እንኳ ዉስጥ ለዉስጥ ሌላ ስዉርና በተጠባባቂነት የተቀመጠ ሃይል እስከማደራጀት ይይዛሉ። በአለም ዙሪያ በዚህ መልክ ሲያካሄዱ የኖሩትን ለአብነት ማቅረብ ይቻላል። ለቦታና ለጊዜ፥ እንዲሁም ጹሑፍ ላለማንዛዛት ከኢትዮጵያ ሁኔታ አንድ ማስረጃ እናቀርባለን።

 

በ1950ዎቹ (እስከ 1958 ይመስለኛል) በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር የነበሩት ኮሪ ትዝ ይሉኛል። ጆን ኬኔዲ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በሆኑበት ስዓት ከመረጧቸዉ ወጣት የሐርቫርድ ምሩቃን መካከል አምባሳደር ኮሪ አንዱ ናቸዉ። ከንጉሠ ነገስቱ እልፍኝ ከአዳራሽ፥ የዙፋን ችሎትና እንዲያ ባሉ ስፍራዎች የሚሽከረክሩ ናቸዉ። ይህ ብቻም ሳይሆን በመኖሪያ ቤታቸዉ በየጊዜዉ ድግስ ያደርጋሉ። ለምሳሌ በወር አንድ ቀን የጋዜጦች አዘጋጆች ይጋብዛሉ። እሳት ግር ብሎ ይነድዳል። የፈለገ ጥሬ ስጋ ያወራርዳል። አለዚያ ቄንጠኛ ጥብስ በኮኛክ ይጠበሳል። ፍሌመኞን ነዉ የሚባለዉ? ቲቦን ወዘተ ይቀርባል። ማወራረጃዋ ኮኛክ በእድሜዋ ትመጣለች። ኦን ዘ ራክስ ተለምዷል። በአጭሩ የአምባሳደር ኮሪ ግብዣ የምትናፈቅ ናት። የፕሬዚዳንት ሩዝቬልት የኋይት ሃዉስ “ባህል” እየተባለ በሚጠቀሰዉ ስልት ከመኖሪያ ቤታቸዉ ጎምቱ ጎምቱ የሆኑ ሰዎችን እየጠሩ፥ እያበሉና እያጠጡ ለነገና ለተነገ ወዲያ ስራ የሚጠቅማቸዉን ጉዳይ መተኮሻ ኣድርገዉታል።

 

አንድ ቀን (1959?) ለጦር አዛዦች የሚሰጥ ግብዣ ነበር። ጄኔራል መኮንኖች በተለይ የሃይል አዛዦች በብዛት እንደነበሩ አይጠረጠርም። ለእነዚህ ደግሞ ወደ አሜሪካ የሚወስድ ስያሜዉ “ሊደርሺፕ ቱር” በተሰኘ ፕሮግራም እየመጣ ሁሉም የአሜሪካ ልጅነት እስኪሰማው ድረስ የሚቀብጥበት አጋጣሚ ነበር። ከዝርዝሩ እንመለስና በአንዱ የግብዣ ወቅት ሁሉም ከንጥረ-ነገሩ ገፋ አድርጎ ሲወስድ አምባሳደሩ ከዋናዉ ጄኔራል ጋር ድምጻቸዉን ቀንሰው ማዉራት ይጀምራሉ። “ሆድ ያባዉን ብቅል ያወጣዋል” የሚባለዉ አነጋገር በፈረንጅም አለ “In wine comes the truth” ። ታዲያ አምባሳደሩ ሌተና ጀኔራሉን ከልብ ማጫወት ይዘዋል። “ጄኔራል ዛሬ እኮ በሁሉም የአፍሪካ አገሮች ወታደራዊ መፈንቀለ-መንግስት እየተካሄደ ነው። ይህ የወታደር መንግስት መቋቋም ጉዳይ ማቆሚያ አጥቷል። ለዚህም መንግስት ሳያሰጋ አይቀርም። ያስቡበት። ያንን የመሰለ ሁኔታ እንዳይፈጠር እርስዎን ልንረዳዎት እንችላለን” በማለት አንድ ትልቅ ኳስ ከሜዳቸዉ ዉስጥ ይጥሉላቸዋል። ጄኔራሉ ግን ነጋ አልነጋ ብለዉ ወደ ንጉሰ-ነገስቱ ዘንድ ሄደዉ “አሜሪካኖች” ምንኛ የማይታመኑና ወዳጃቸዉ የሆነዉን ይህን መንግስትም እንደምንም ለመለወጥ እንደሚሹ ይገልጡላቸዋል። የፖለቲካው የጊዜ ጨዋታ አጤ ዮሃንስ ወይም አጤ ሃይለስላሴ “ለአሜሪካ ታማኝ አይደሉም” የሚል አይደለም። ዋናው ጉዳይ የሃይለስላሴ መንግስት መገልበጡ የማይቀርና ባይሆን የሚመጣዉን መንግስት አዋላጆች አሜሪካኖች ራሳቸው ይሆኑ ዘንድ የሚቀይስ ፖለቲካ ነዉ። (በነገራችን ላይ አምባሳደር ኮሪን ጃንሆይ ሲያስጠሯቸው ሰዉየዉ ጉዳዩን በመጠርጠር ወደላንጋኖ ሄደዋል አሰኙ፤ ጃንሆይ ደግሞ ለፕሬዚዳንት ጆንሰን ስልክ ደዉለዉ ዲፕሎማቱ ሳይዉል ሳያድር “እንዲጠራ” ተደረገ። ምን ሆነ መሰላችሁ? አምባሳደር ኮሪ ለጥቂት ጊዜ ዋሽንግተን አካባቢ ሲሽከረክሩ ቆይተዉ ሳልቫዶር አየንዴ በቺሌ ሶሻሊስት መንግስት እንዳቋቋሙ ያንን ለመገልበጥ ሁሉንም ሴራ ጎንጉነዉ በመጨረሻ ላይ ያለዉን ምዕራፍ ለናትናኤል ዴቪስ አስረክበዉ ወደዋሽንግተን ተመለሱ። ናትናኤል ዴቪስ ከጄኔራል ፒኖቼ ጋር ሁሉን ነገር ጨርሰዉ ከቅልበሳዉና እልቂቱ አንድ ቀን በፊት ወደ ዋሽንግተን ተመለሱ። ከዚያ አንድ ወር ሳይሞላቸዉ በአዲስ አበባ የአሜሪካ አምባሳደር እንዲሆኑ “አግሪማ” (ስምምነት) ተጠየቀ። በነካ እጃቸዉ አብዮት ይቀለብሱ ዘንድ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ ረጃጅም ጽሁፎች የሚቀርቡበት ሲሆን ምናልባትም ሊሰመርበት የሚገባዉ አንድ ሃቅ አምባሳደር ኮሪ እንዳሉትና እንደፈሩት ሁሉ “የማይታወቁና እንዲያዉም በየጦሩ ካምፕ የተናቁ” ወታደሮች ያንን የሶስት ሺህ ዘመን ታሪክ ገረሰሱት። ስዩም ሐረጎት “Serving Emperor Haile Selassie” በሚለዉ መጽሃፉ እንደገለጠዉ ደግሞ “የክብረ-ነገሥት ፍጻሜ” ሆነ።

 

ሚስ ሸርዉድ ግንቦት 7ን ሽብርተኛ አድርገዉ ሲያቀርቡ ከልባቸዉ ላይሆን ይችላል። የምለዉ ይህ እንቅስቃሴ ኣድጎና ተጠናክሮ ይህን ዛሬ የሚረዱትን መንግስት ጨምድዶ ወደታሪክ መጣያ ቅርጫት ሲወረውረው ለማየት ቢችሉ ደስ ይላቸዋል ባይ ነኝ። ከዚያም በፊት ጥንካሬውንና “ግልፅ አማራጭነቱን” በማየት “እሹሩሩ” ቢሉት አይድነቃችሁ። ብቻ ሴቲቱ የእኛ ሰዉ እንደናቃቸዉና እንዳዘነባቸዉ ሁሉ የኦባማም አስተዳደር የፈቀዳቸዉ አልመሰለኝም። በቃሽ ተብለዋል። የታላላቅ መንግስታት ፖለቲካ በመሰረቱ ይህን ይመስላል። ረቂቅ ፖለቲካና ጠለቅ ያለ የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ ከነዚህ መንግስታት ስትጠብቁ ሳታስቡ አንሰዉ ስታገኟቸዉ አለመደነቅ ነዉ። የሚስ ሸርዉድ መስሪያ ቤት ቢያንስ ባለፉት አስር አመታት ሰለወያኔዎች ፖለቲካ አሳፋሪነት፥ ስለሰብአዊ መብት ሬከርዳቸዉ አስቀያሚነትና ስለ ኢኮኖሚ ያላቸዉ ዝቅተኛ የሞራል ደረጃ የራሳቸዉ መንግስት ያወጣውን ተደጋጋሚ መግለጫ አያዉቁትም፤ አልሰሙትም ብሎ ማሰብ አያመችም። ምናልባትም በዝግጅቱ በስተጀርባም ሊኖሩ ይችላሉ። እኔ የሎርድ Parlmerston “ነፍስ አይማረዉ” የምልበት ጊዜ ሞልቷል። በ 1848 የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር የነበረዉ ይህን ግለሰብ ንግስት ቪክቶሪያ “ለመሆኑ በዛሬዉ ዕለት የእንግሊዝ ወዳጆችና ጠላቶች እነማን ናቸዉ?” ብለዉ ይጠይቃሉ። ያን ጊዜ ነዉ “እንግሊዝ የዘለቄታ ጠላትም ሆነ የዘለቄታ ወዳጅ የላትም።  የዘለቄታ ጥቅም እንጂ” በማለት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የተናገሩት።

 

ስለዚህ በፖለቲካቸዉ ውስጥ ጥቅም እንጂ ሞራሊቲ የሚባል ቅመም የለም። ሰብአዊነት ብርቅ እሴት ነዉ። ይልቁንም ለጥቅማቸዉ መከበር ሚሊዮንና ትሪሊዮን የሆነ ነፍስ ቢጠፋ ቁብ አይሰጣቸውም። የሕዝብ የሕሊና ቁስል አይሰማቸውም። የሚዘረፍ የለም እንጂ ከዚች ደሃ የኢኮኖሚ ቋታችን ኣድፋፍተዉ ቢወስዱብን የሚሰማቸዉ እንዳች የህሊና ወቀሳ የለም። ለነገሩ ታላላቆቹ መንግስታት በፖለቲካ ቀመራቸው ዉስጥ ህሊና የለም። የህሊና ወቀሳ “ላም ባልዋለበት” ነዉ። ሚስ ሸርዉድ እንደሌሎቹ የአሜሪካ ፖለቲከኞች ሁለት ነፍስ ናቸዉ። በአደባባይ ወያኔ የሚወደዉን በመናገር ሊሸዉዱት ይወዳሉ (ይፈልጋሉ) ። በግል የተወሰኑ ሰዎች ህሊናቸዉን የሚወቅስ ጉዳይ ሲያቀርቡላቸዉ “ወንጀላቸዉን ሁሉ ከእናንተ የበለጠ አዉቃለሁ” የሚሉ ናቸዉ። አንድ ሰዉ አንድ ጭንቅላት ሁለት ምላስ! ይህን መሳይ የፖለቲካ ዘማዊነት ከታላላቆቹ መንግስታት ደጋግማችሁ ትሰማላችሁ። ማፈሪያ! እንዲህ ሲያደርጉ መንግስታቸዉን እንደሚጎዱ ለማወቅ አይፈልጉም። ወያኔዎችን “እሹሩሩ” ካላሉና bluff ካላደረጉ ወደብጫዉ መንግስትና ብጫዉ ጎዳና (ቻይና) ይሄዳሉ ብለዉ ተራ ፍርሃት ይመጣባቸዋል። የፖለቲካው ዘማዊ ባህርይም ይህ ከንቱ ስጋት ነው።

 

አዎን ትላልቆቹ አገሮች – ድሮ የምናዉቃት ሶቪየት ኅብረትና አሁንም ጣዕሟን የበለጠ እየተረዳን የመጣነዉ አሜሪካም ወሮበላ መሪዎችንና አምባገነኖችን ይወድዳሉ። ያስጠጓቸዋል። እነዚህ ግለሰቦች የሞራል ትልቅነትና የነፍስ ‘ንፅሕና’ ስለሌላቸው ለባርነትና ለአገልጋይነት የተመቹ ናቸው። ዝግጁ ናቸው። የሚዋረድ ኩራት የላቸውም። እንደምታዩት እነ ስብሐት ነጋ ከእንስሳዊ ሰብዕናቸው የት ይወርዳሉ? አንዳንድ ደማካ ነፍስ የሆኑትንም በአምባገነንነት ይቀርጿቸዋል። የእነሱን ተልዕኮ እስከፈጸሙ ድረስ ማናቸዉም ድጋፍ ይሰጧቸዋል። ህዝባዊ ወንጀሎቻቸውን የሚያዩ አይኖች የሏቸዉም። የአሜሪካ ቅምጥሎች የነበሩ እነ ሞቡቱ ሴሴ ሴኮን፥ እነ ሳሞዛን፥ እነ ባቲስታን፥ እነ ሻህ ኤንድሻህ ፓሕላቪን ይጠቅሷል።

 

ከዚህ እኩል አምባገነን በመፍጠር ሂደት የአሜሪካኖችን ሚናም እንዲሁ ማንሳት ይቻላል። ከሁለተኛ የዓለም ጦርነት በኋላ ከሚደነቁት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮቻቸው መካከል ዲን አክሰን (Dean Acheson) ይገኛሉ። እንደሚታወሰው በ1952 የግብፅ ወጣት መኮንኖች ቡድን ፋሩቅን ከስልጣን አባርሮ የብዙሃን ፓርቲ አመራርን ለማስፈን ይንደፋደፍ በነበረበት ሰዓት ከዲን አኬሰን በኩል የቀረበዉ አሳብ እኔ መልቲ-ፓርቲ በምትሉት ዉዥንብር ዉስጥ ስዳክር አልገኝም። ከሺ ሰዎች ጋር መደራደር አልፈልግም። ይልቁን ከመሃላቸዉ ጉልበት ያለዉ አንድ ሰዉ ይውጣና ልንረዳዉም ልንንከባከበዉም እንችላለን” ብሏል። የዲን አኬሰንን የትዝታ መጽሃፍና በቅርቡ ስለግብጽ ሬቮሉስዮን የተጻፈዉን Soldiers, Spies and Statesmen ይመለከቷል። ናስርን በአምባገነንነት የመፍጠሩን ሃላፊነት የወሰዱት ዲን አኬሰን ነበሩ ማለት ይቻላል።

 

ራቅ ባለ ዘመን (ምንአልባትም 47 አመት) ያነበብሁት “The Boss” የተባለዉ መጽሃፍም የአሜሪካ የስለላ ድርጅት (በመንግስት ውስጥ ያለው መንግስት) እና ዲን አኬሰን እንደሚነግሩን ለአሜሪካ ጥቅም ተቀዳሚነት የሚተማመኑበት አምባገነን እስከመፍጠርና እሱንም እስከመንከባከብ የደረሰ (የሚያደርስ) የቅብጠት አያያዝ ሊሰጡ ይገደዳሉ። በካይሮ ለናስር መንግስት በሚሰጡት ክብካቤ በመጀመሪያ ላይ ይህንን አጽንተዋል። በኢራን ህጋዊዉንና በህዝብ የተመረጠዉን ጠቅላይ ሚኒስትር ሞሃመድ ሞስዴህን በመገልበጡና ሻህ ኤንድ ሻህ ፓህላቪን በማንገሡ ሂደት (1953) የአሜሪካ ሲአይኤና የእንግሊዝ መንግስት (ኤም አይ ሲክስ) ሚና በሃፍረት የሚታወስ ነዉ። ቀደም ባለዉ ገለጻ በቺሊ በህዝብ የተመረጠዉን ሳልቫዶር አየንዴን በመግደልና መንግስቱን አስገልብጦ ጨካኝና ጨቋኝ የሆነዉን ጄነራል ኦግስቶ ፒኖቼን መጎለቱን አንስተናል።

 

እነዚህ አምባገነኖች በህዝቦች ላይ የፈጸሙት ደባ፥ ያቋቋሙአቸዉ የሽብር ሪፐብሊኮች (ግዛቶች) ታሪክ በትክክለኛ መልኩ ተዘግቦ የሚገኘዉ በሲአይኤ መስሪያ ቤት ነዉ። የአሜሪካም የፖለቲካ ነውር ማስረጃ ሁሉ የሚገኘዉ በዚያዉ ባህረ-መዝገብና የፖለቲካ ሰነድ ዉስጥ ነዉ። ሌላዉ ቀርቶ ሲአይኤ ከተመሰረተበት ክ1948 አንስቶ ከ52 የማያንሱ በህግ የተመረጡ የዓለም መሪዎች ለአሜሪካ ጥቅም ባለመመቸት ሰበብ ተገድለዋል። እነ ሉሙምባና የፓናማ ሶስት መሪዎች ከዚህ ተራ ዉስጥ ይመደባሉ። ታዲያ ፕሬዚዳንት ኒክሰን የኒካራጉዋን ህዝብ ደም እያስለቀሰና በአንዳንድ ጸሃፊዎችም አገላለጽ “ደም እየጠጣ” የገዛዉን የአናስታሲያ ሶሚዛን (ደባልዬ) አምባገነንነት ተጠይቀዉ የሰጡት መግለጫ በትምህርት ማዕድ ላይ እንኳን የሚጠቀስ ነዉ። ኒክሰንን እንጥቅሳቸዉ፤ “Yes I know Somosa is a son of a bitch፥ but he is our son of a bitch” ነበር ያሉት።

 

እኔ የወቅቱን ወንጀለኛና “ማፈሪያ” የኢትዮጵያ መሪዎች (ገዢዎች) በኒክሰን ቋንቋ ላዉቃቸዉ አልፈልግም። ለፕሬዚዳንት ኦባማና ለዌንዲ ግን የግላቸዉ sons of bitches ናቸዉ። አሽከርነታቸዉንና ነፍስና ስጋቸዉን ለእነሱ አገልግሎት ማዋላቸውን እቀበላለሁ። “የዉሻ ልጅ” የምትለዋ ቋንቋ ለአማርኛዉ አገላለጥ ስለማትስማማ ሌላ አማርኛ ልናመጣ እንችላለን (በዚያ ትክ ማለቴ ነዉ)። የዛሬ 267 ዓመት ወደ ፖለቲካዉ መዝገበ ቃላት የገባዉ “ዘላለማዊ የወዳጅነትና የጠላትነት መለኪያና የዉጭ ጉዳይ ፖሊሲ እምብርት የአሜሪካ ወይም የእንግሊዝ ጥቅም” የመሆኑ ጉዳይ ዛሬም እየተሰመረበት ነዉ። ውብ ቋንቋና ጥዑም አነጋገር ያላቸዉ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ አሜሪካ አለምን መምራት አለባት” እያሉ ደጋግመው ይነግሩናል። በሚመች ጊዜ ይህን አገላለጥ በራሱ ባሕርያትና ይዘት በሰፊው ብመለስበት ደስ ይለኛል። አገሬ በእድገትና በሰላም ገስግሳ ከአሜሪካ ብትስተካከል እጅግ እደሰታለሁ። የመጨረሻ ህልሜ ግን አለምን ትገዛ ዘንድ አይደለም። የእኛ ከወያኔ ነጻ መዉጣት የአሜሪካንን የአለም መሪነት የሚያቃዉስ መስሎ ከታያቸዉ ግን እዚሁ ዉብ አሜሪካ ሆኜ ያስጠጋችኝን አሜሪካ መንግስት አምርሬ ብፋለመዉ ደስ ይለኛል። በዚህም የተነሳ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዉያን ዘላለም በወያኔ የእሳት መሰውያ ላይ መንደድ መቃጠልና ከስሎ ማለፍ ግዴታችን መሆኑን አልቀበልም በማለት እምዬ አሜሪካን እፋለማለሁ። አገሪቱም እንዲሁ ለወያኔ ቆሌና የወርቅ ጥጃ አምላክ በእሳቱ መሰውያ ላይ እየነደደች ስታልቅ እሳቱን ለማጥፋት የዌንዲን፥ የሱዛን ራይስንና የኦባማን ፈቃድ መጠየቅ እንዳለብን ለማወቅም ለመቀጠልም አልሻም። ይልቁንም እዚህ ላይ ቆም ብለን ማሰብ የሚገባን ከእንግዲህ ወዲያ ህዝባችን ያልተስማማዉንና የሚያፌዝበትን መንግስት ለመቅጣትና ከስራም ማባረር ያለዉን ነጻነት ማወጅ ነዉ። እንደአሜሪካ፥ እንግሊዝ፥ አለም ባንክ፥  የአዉሮፓ ህብረት፥ ወዘተ ያሉ መንግስታትና የቅኝ አገዛዝ ድርጅቶች  “የግልና ተወዳጅ የዉሻ ልጆች ወይም የማንወደድ የዉሻ ልጆች” አድርገዉ እንዳያዩን ጠረጴዛዉን ልንገለብጥባቸዉ ይገባናል። ተወዳጅ “የዉሻ ልጅነትም” ሆነ “የማንወደድ የዉሻ ልጅነት” ይቅርብን። በአፍንጫችን ይዉጣ። ከሁለቱ የትኛዉን ትመርጣለህ? ብባል ሁለቱንም መጥላቴን አዉጃለሁ። ኢትዮጵያዊነትን ማንም የሚሰጥህ መብት ወይም የሚነፍግህና የሚነጥቅህ ምድራዊ ሃይል የለም። በእኔ በኩል በወያኔ የዜግነት ሰጪነትና ነሺነት ስልጣን አዋቂነት ባልታማም ይልቅስ እነሱ ኢትዮጵያዊ በመባላቸዉ ብቻ የቆሰለ አንጀት ይዤ ወደመቃብር እሄዳለሁ። እፋለማለሁ! ተፋለሙ!

 

ዌንዲ ሸርዉድ ግንቦት ሰባትን እንደሚቃወሙና እንደ አልቃይዳና እንደ አይሲስ አሸባሪ ከማለት ባሻገር የሄዱ አይመስለኝም። ለዚህ መግለጫ አጻፋዉን ከግንቦት ሰባት አመራር ብንጠብቅም አቅጣጫዉ ወያኔን የሚቃወምና የሚቋቋም ሁሉ አሸባሪ የሚባል እንደመሆኑ ሁላችንንም በአንድ ቅርጫት ዉስጥ የሚያስቀምጠን ይመስለኛል። ስለሆነም አንድ ግዴታ ዉስጥ ልንገባ የምንገደድ ይሆናል። እኛ አይደለንም የአሜሪካን ጥላቻ የምናተርፈው። አሜሪካ የኢትዮጵያን ህዝብ ፍቅር ጨርሳ እዳታጣ እፈራለሁ። የዘመኑ ፖለቲካ ይህን እየመሰለ መምጣቱን የአሜሪካ የፖለቲካ መሪዎች ማጤን አለባቸዉ ባይ ነኝ። አሜሪካና እንግሊዝ ከ Palmerston ፍልስፍና (ቋሚ ጠላትና ቋሚ ወዳጅ የለንም፤ ቋሚ ጥቅም እንጂ) ከሚለዉ ወጥተዉ በ21ኛዉ ክፍለዘመን እንኳን በሰዉ ልጆች በአጠቃላይና በመንግስታትም እኩልነት ለማመን አልቻሉም። ፕሬዚዳንት ኦባማ በግልፅ ቋንቋ አለምን እንገዛለን፥ መግዛት አለብን ይሉናል። እዚያ ላይ ልንለያይ ነዉ። ወያኔ ሊገዛ ይችላል፤ እየታየም ነዉ። የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አይገዛም፥ አይነዳም። የመጨረሻዉ ትልማችን የኢትዮጵያ ህዝብ ራሱን ይገዛ – ራሱን ይመራ ዘንድ ነዉ። የመጨረሻው ፈታኝ ችግር ቢመጣ እንኳን፥ ኢትዮጵያ በማንም እንድትገዛ አልስማማም።

 

ከላይ እንደጠቀስኩት ሴቲቱ የሰጡት መግለጫ አልተቋጠረም። ወያኔን የነካ (ግንቦት ሰባትን ጨምሮ) ምን ይደርስበታል? የተንጠለጠለ አቋም እንጂ በግልጽ የተነገረ ነገር የለም። በመለስ ቋንቋ እንመለስበትና “ጣቶች፥ እጆችና፥ አጽቆች እንቆርጣለን” አላሉም። በዋሽንግተን የሚገኙ የወያኔ መንግስት ጠላቶችን እያነቅን ወደአዲስ አበባ በመላክ እናስደስታቸዋለን እንዳልተባለ እገምታለሁ። እዚህ ላይ ስንደርስ በእርግጥ የአሜሪካን ዲሞክራሲ ዉበት ማሰብ አለብን። የዚችን ታላቅ አገር መስተንግዶ አክብሬና ዲሞክራሲ በስራ ላይ የሚዉልበትን የየቀኑን ህይወቴን እያየሁ፥ አሜሪካንን እያደነቅሁና እያፈቀርኩ እኖራለሁ። ማንም እንዲነካት ነክቶአትም አደጋ እንዲያደርስባት አልሻም። አሜሪካ ለሁላችንም የስደት ቤታችን ናት። እኛም የአሜሪካ ህልም ተቋዳሾች ነን። መንፈሳዊ ቤቴ ናት። በዚህ አንጻር በዲሞክራሲ ስም መሪዎቿ በየአገሩ የሚያደርሱት ጉዳት ይቀፈኛል።

 

ከህዝብ ይልቅ አምባገነንነት የሚመረጥበትና “በእግዚአብሄር እንታመናለን” (In God we trust) የሚል መሪ መፈክር ያነሳ መንግስት አላማና መርሁ በአሳማ ፊት የወደቀ እንቁ ይሆንብናል። የሴቲቱ ዌንዲ ሸርዉድ ንግግግር በዕንጥልጥል ነዉ የቀረበዉ። ከዉግዘት ባሻገር ሌላ (ሌሎች) እርምጃዎች አሉ? ይኖራሉ? አነጋገራቸዉን በሚመለከት እሸት እሸት የሆነ ማስረጃ በማቅረብ ሰዉ ፊት ለመቅረብ በማይችሉበት ሁኔታ ያሳፈሯቸው ምሁራንና ድርጅቶች ነበሩ። እንደ ዋሽንግተን ፖስት ያሉ የሚዲያ አውታሮች ሳይቀሩ ከዚህ ሁሉ በኋላ ለወያኔ አገዛዝ መቀጠል ሲባል በኢትዮጵያዉያን ታጋዮችና ተቋሞቻቸዉ ላይ አንድ አይነት ስውር ይሁን ገሃድ ርምጃ ቢወሰድ የአሜሪካንን አመራር ውስልትና የሚመሰክርና በሁላችንም ኢትዮጵያዉያን ላይ የተቃጣ ጥፋት አድርጌ እወስደዋለሁ። አቅሜ ደካማ ሊሆን ይችላል፤ መንፈሴ ጠንካራ ነው።

 

ለአሜሪካ የምንነግራት ኢትዮጵያውያን ጦርነት ላይ ናቸው። ከእንግዲህ ወዲያ ገላጋይ የሚፈልጉ አይመስለኝም። ይህም ሲባል ሰላምን አንፈልግም ማለት አይደለም። የጦርነት ፖለቲካ መለጠጥና ከሰላም ባሻገር ማደግ መሆኑንም እናውቃለን። ጦርነቶች የሚፈጸሙት እንደገና በሰላማዊ አደባባዮች በሚደረግ ምክክርና ውይይት መሆኑንም አንስተውም። ወያኔ ከዚያ በላይ ሄደ – ከሒትለርም ጉዞ አልፎ ዜጎቻችንን ጨፍጭፏል። አገር ሸጦአል። አንድነታችንን አቃውሶአል። ጦርነት አውጇል። በህዝቡ ላይ። ስለዚህ ግንቦት ሰባትና ሌሎች ሃይሎች ይህን በእግዚያብሔርና በህዝቡ ስም የሚያካሄዱትን ትግል ማንም ለመቃወም የሞራልና የትውልድ መብት የለውም። ተውን!

 

የኦባማ አመራር በእነ ግንቦት 7 ላይ አንድ አይነት የሚሳዝን አቋም ከያዘ (አያደርገዉም እንጂ) ወያኔን የነካ አሜሪካንን ነካ ማለት ይመስላል። ሐቁ ግን የኢትዮጵያ ህዝብ በግንቦት ሰባት ሆነ በሌላ ድርጅቶቹ ወያኔን ይፋለማል፤ ያንበረክካል። ለታሪክ የፍትህ አደባባይም ያቀርበዋል። ይህንን መሰረታዊ የአገሬን ህዝብ መብት ኦባማ፥ ዌንዲ፥ ካርተር….. ባርተር ሊቀሙ ሊያቆሙ አይችሉም። በየጆሮዎቻቸዉ ሹክ ብለን ሳይሆን በጩኸት ልናስቀር የሚገባን ሐቅ ይህን ይመስላል። አትርዱን፤ አትፍረዱልንም። ግን ትግላችንን አክብሩልን። አትንኩን። ዳግመኛም የአሜሪካ አባቶች ለእዉነት ስለመቆም፥ ከተገፉ ህዝቦች ጎን ስለመሰለፍ፥ በጭቆናና በግፍ ላይ በመዝመቱ ሒደት የነበራቸዉን አቋም መርምሩ። አሜሪካ ለዘላለም ትኑር!

 

 

The post እርዱን ፍረዱልን አንልም፤ በነፃነት ተጋድሎአችን አይግቡብን! – ከጸጋዬ ገብረመድህን አርአያ appeared first on Zehabesha Amharic.


መኮንን ጌታቸው ጌይል ስሚዝን በምስክርነት መስሚያ መድረክ ላይ ተቃወማቸው

$
0
0

mekonen
ጋዜጠኛ መሳይ መኮንን እንደዘገበው የዲሲ ወጣቶች ግብረ ሃይል አባል መኮንን ጌታቸው የህወሀት ደጋፊ በመሆን የሚታወቁትና ለUSAID ሃላፊነት የታጩትን ጌይል ስሚዝን በመቃወም በምስክርነት መስሚያ መድረክ ላይ ተቃውሞ አሰምቷል።

ጌይል ስሚዝ በኢትዮጵያ የሚፈጸመውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ የአሜሪካን መንግስት ጀርባ እንዲሰጥ ከሚያደርጉ ሰዎች አንዷ ናቸው።

መኮንን የሟቹን ሳሙኤል አወቀን ፎቶግራፍ በመያዝ ተቃውሞውን አሰምቷል።

መኮንን ጌታቸው ከዚህ ቀደም የሕወሓትና ተላላኪ ባለስልጣኖቻቸው ወደ አሜሪካ ሲመጡ የገቡበት ገብቶ ሲጋፈጣቸው መክረሙ የሚታወስ ነው::

The post መኮንን ጌታቸው ጌይል ስሚዝን በምስክርነት መስሚያ መድረክ ላይ ተቃወማቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

የአረናው አመራር አባል በ3 ሰዎች ታንቀው ተገደሉ

$
0
0

ዓምዶም ገብረስላሴ ከመቀሌ እንደዘገበው: ኣቶ ታደሰ ኣብርሃ የተባሉ የዓረና-መድረክ ኣባልና የምዕራባዊ ዞን የዓረና ኣመራር ኣባል ትናንት ማታ 09 / 10 / 2007 ዓ/ም በሶስት ሰወች ታንቀው ተገደሉ።

Tadese Aberhaኣቶ ታደሰ ኣብራሃ በቓፍታ ሑመራ ወረዳ ማይካድራ ቀበሌ ኑዋሪ ሲሆኑ በዘንድሮው ምርጫ ወቅት በቀበሌው ኣስተዳዳሪዎች፣ ካድሬዎች፣ የሚቀርቧቸው ሰዎች ከዓረና-መድረክ ኣባልነታቸው እንዲለቁ የተሸመገሉ፣ የተለመኑና በመጨረሻም ዛቻዎች ሲደርስባቸው እንደነበረ ይታወቃል።

ኣቶ ታደሰ ማታ 03:00 በ 3 ሰዎች ኣንገታቸው የታነቁ ሲሆን ሶስቱ ሰዎች ሙቷል ብለው የተዋቸው ቢሆኑም ሂወታቸው እስከ 09:15 ኣላለፈችም ነበር። ኣቶ ታደሰ ኣብራሃ የ48 ዕድሜ ጎልማሳ ነበሩ።

ኣደጋው 3 ሰዎች እንደፈፀሙባቸው፣ በኪሳቸውም 300 ብር የነበረ ቢሆንም ሰዎቹ ሊወስዱት እንዳልቻሉ ተናገረው ነበር።

የኣቶ ታደሰ ሬሳ በሑመራ ሆስፒታል ላለማስመርመር የማይካድራ ፖሊስ ትራፊክ በዓረና ኣባላት ላይ ከፍተኛ ጫና የፈጠሩ ሲሆን የተለያዩ የመንግስት ኣካላትም ምርመራው እንዳይካሄድ የተለያዩ ጫናዎች እንደፈጠሩ ኣባሎቻችን ከስፍራው ገልፀውልናል።

ሬሳው ወደ ሑመራ ወስዶ ለማስመርመር የሚጠቅም መኪና ለመከራይ ሲባል ኣባሎቻችን የተካራት ሞተር ሳይክ በፖሊስት ትራፊክ ተከልክላለች።

የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ቤት ኣካራይና ሌሎች ሰዎች ከኣደጋው በተያያዘ ጫና እየተፈጠረባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችለዋል።

የኣቶ ታደሰ ኣብራሃ ግድያ በሳምንት ውስጥ የወጣት ሳሙኤል ኣወቀን ጨምሮ ለሁለተኛ ግዜ በፖለቲከኞች ላይ የተፈፀመ ግድያ ሲሆን ከ2007 ዓ/ም በዓረና-መድረክ ኣባላት ለሁለተኛ ግዜ የተፈፀመ ግድያ ያደርገዋል።

ባለፈው ታህሳስ ወር የደቡባዊ ዞን የዓረና-መድረክ ኣስተባባሪና የማእከላይ ኮሚቴ ኣባል የነበረው ኣቶ ልጃለም ኻልኣዩ በኣዲስ ኣበባ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች መገደሉ ይታወቃል።

ይህ ተግባር በስፁም የሚወገዝና በሰላማዊ ትግል ላይ ሽብር የሚፈጥር ተግባር ነው።

በሰለማዊ መንገድ የሚታገሉ ፖለቲከኞች የሚፈፀም ግድያ ይቁም…!

መንግስት ነብሰገዳዮች ወደ ፍርድ ያቅርብ…!

ፈጣሪ ነብሳቸው ገነት ውስጥ ያኑርልን ኣሜን።

ነፃነታችን በእጃችን ነው።

IT IS SO..!

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/7865#sthash.EPhkL0ka.dpuf

The post የአረናው አመራር አባል በ3 ሰዎች ታንቀው ተገደሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሳሙኤል አወቀ መገደል የነፃነት ትግሉን አያስቆመውም !!

$
0
0

semawi

“ለማንኛውም የምከፍለው ዋጋ ለለሃገሬና ለነፃነት ነው፡፡ በአካል ብታሰርም ህሊናዬ አይታሰርም፡፡ ከገደሉኝም ትግሌን አደራ!!! አገራችን የወያኔ ዘረኞች ብቻ መፈንጫ መሆን የለባትምትግላችን የነፃነት፤ ጉዞአችን ጎርባጣ፤ መድረሻችን ነፃነት፤ ታሪካችን ዘላለማዊ ነው፡፡  ሳሙኤል አወቀ ፊስቡክ ገፅ ላይ የተገኘ ሰኔ 8/2ዐዐ7 ዓ.ም፡፡

awkeምስራቅ ጎጃም ግንደ ወይን 1978 ዓ/ም ተወልዶ – በህግ የዲፕሎማ እና ዲግሪውን ሰርቷል፡፡ ሣሙኤል አወቀ የሠማያዊ ፓርቲ መስራች አባልና ከዚያም በፊት እንደ ሌሎች ጓደኞቹ ከቅንጅት ጀምሮ በአንድነት ፓርቲ ውስጥ ሲታገል የቆየ ጠንካራ ኢትዮጵያዊ ነበር፡፡ ሣሙኤል በሙያው የህግ ባለሙያና በጥብቅና ስራ በግል እየሠራ ጎን ለጎን ደግሞ ለአገሩ ከነበረው ፅኑ ፍቅር የተነሣ በሠላማዊ ትግል በማመን ገና በልጅነቱ ትግሉን ተቀላቅሎ በግፍ እስከተገደለ ድረሥ በንቁ የፖለቲካ አመራር ሲታገል ቆይቷል፡፡ ሣሙኤል የሠማያዊ ፓርቲ ከተመሠረተ ጀምሮ በከፍተኛ ኃላፊነት  በንቃትና በተደራጀ መልኩ  በተወከለበት ቀጠና በምስራቅ ጎጃም ዞን ሲያደራጅና ሲያስተባብር ነበር፡፡

ሳሙኤል አወቀ በአካባቢው ዘንድ የተከበረ እና ምስጉን ወጣት ነበር፡፡ በቅርቡም በተደረገው ሃገራዊ ምርጫ ፓርቲውን ወክሎ የዞኑ የተወካዬች ም/ቤት ጠንካራ ተወዳዳሪ እንደነበር አስመስክሯል፡፡  ሣሙኤል በምሰራቅ ጎጃም አካባቢ እታች አርሦ አደሩ መንደር በመዝለቅ በንቃት ሲያደራጅና ሲያስተባብር የነበረ በየአካባቢው ይደርስ የነበረውን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ አስተዳደራዊ ጭቆናና በደል እየተከታተለ ለሕዝብ መረጃ ሲያቀብል እንደነበረ! በተለይም በፓርቲው ልሣን በነገረ ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ አምደኛ በመሆን ተከታታይ መረጃዎችን ሲያቀብል የነበረ ጠንካራ የማይበገር ታጋይ እንደነበር ተገንዝበናል፡፡

በትናትናው ዕለት ማለትም ሰኔ 8 ቀን 2ዐዐ7 ዓ.ም የወያኔ ኢህአዴግ የፀጥታ ሃይሎች ከምሽቱ አንድ ሰዓት ተኩል አካባቢ ከሚኖርበት ቤት አጠገብ ደ/ማርቆስ ከተማ ውስጥ እጅግ አሠቃቂ ድብደባ ተፈጽሞበት በግፍ ለተገደለው የሰማያዊ ፓርቲ አመራር አባል ሣሙኤል አወቀ አለም ሃዘናችን ፅኑ፣ መራርና ፈጽሞ ለአፍታም ያህል የማይረሳ የዘመናችን የነፃነት ትግል አርዓያ ዋና ተምሣሌት፣ እንዲሁም ለኢትዮጵያችን እንደቀደሙት ጀግኖች እንደነ አቡነ ጴጥሮስ የታሪክ ባለአደራ የወቅቱ የትግል ጥሪ ፈር ቀዳጅ ጀግናችን ነው፡፡  ለሣሙኤል አወቀ ቤተሰቦች እግዚአብሔር እንዲያፅናናቸው እየተመኘን ዛሬ ሣሙኤል በአካል ከትግል አጋሮቹ ጋር ባይኖርም የሥራው ተምሣሌት ግን ለነፃነት ትግሉ ጉዞ ህያው ሥንቅ ሆኖ ይቀጥላል፡፡

ሣሙኤልን በጥቅም ሣይደለል በኃይል በማስፈራራት ወይም በአካሉ ላይ ድብደባ በመፈጸም ትግሉን ለማስቆም ያልቻሉት የወያኔ ኢህአዴግ ቅልብ ወንጀለኞች በአካሉ ላይ ያደረሱት ጉዳት አልበቃ ብሏቸው በትናትናው ዕለት በስለት ፊቱንና አካሉን በመቆራረጥ ማንነቱን መለየት እስከማይቻል ድረስ በጭካኔ ገድለው ጥለውታል፡፡  ይህ ዓይነቱ የመንግስታዊ አሸባሪነት የመጀመሪያ ሣይሆን በተደጋጋሚ የታዬና አገዛዙ ጠንካራ ተቃዋሚ አመራሮችን በተመሣሣይ ጥቃት ሲያደርስ እንደቆየ ሕዝቡ ያውቃል፡፡ በኢትዮጵያ ተንሠራፍቶ ያለው ኢሰብአዊ አምባገነን ዘረኛ መንግስት በሕዝቡ ላይ በተለይም በተቃዋሚ ፓርቲ  አመራሮችና  በነፃው ኘሬስ አባላት ላይ ከፍተኛ በደሎች ማለትም እስራት፣ ድብደባ፣ግድያና ሁለገብ የሆነ የስነ ልቦና፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ሃይማኖታዊ ወንጀል እየፈጸመ ይገኛል፡፡ የሣሙኤል አወቀ የግፍ ግድያ ከላይ እነደተጠቀሰው አገዛዙ ሕዝቡን የሚያጠቃበት መለያ ባህረው አንድ አካል መሆኑን አስረጅ ሊሆን የሚችልና  አገዛዙ ምን ያህል በጥላቻ እንደተጠመደና እጅግ አሣሣቢ ደረጀ ላይ መድረሱን ያሣያል፡፡  የወንድማችን የሣሙኤል የግፍ  አገዳደል አልበቃ ብሏቸው የአገዛዙ ቅልብ ነፍሰ ገዳዬች በሣሙኤል ቀብር ላይ የተገኙትን ሌሎች አመራር አባላት ከቀብሩ ስነስርዓት ሲመለሱ አግተው አስረዋቸዋል፡፡

ውድ የኢትየጵያ ሕዝብ ሆይ፦

ይህ አይነቱ እጅግ ዘግናኝ በደል ሃዘናችንንና ቁጭታችንን ያባብሰዋል እንጅ ለነፃነት የተጀመረውን መራር ትግል ለአፍታም አያስቆመውም፡፡ በአገርቤትም በውጭም የምንኖር የሠላማዊ ትግል ደጋፊዎችና አራማጆች እንዲሁም መላው አገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን የአገዛዙን ሰይጣናዊ ስራ በአንድ ድምፅ ማውገዝና መቃወም ይገባናል፡፡ ዛሬ በሣሙኤል ሞት ልባችን እንደቆሰለ ነገ በሌሎች ሣሙኤሎች ተመሣሣይ ግፍ እንዳይፈጸም ሁላችንም በአንድ ላይ እንነሣ!  አገዛዙን በጋራ ታግለን ማስወገድ ይኖርብናል፡፡

 

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

እግዚአብሔር የሣሙኤልን ነፍስ በገነት ያኑርልን!

 

The post የሳሙኤል አወቀ መገደል የነፃነት ትግሉን አያስቆመውም !! appeared first on Zehabesha Amharic.

የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ

$
0
0

ለገሰ ወ/ሃና
Mamushet-Amare (1)የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈታ ቢወስንም ፓሊስ ሳይፈታው ቀረ ዘሬ ሰኔ 10/10/2007 ዓም በአራዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቀርቦ በዝግ የታየው ችሎት ማሙሸት አማረ በ5000:00 ዋስ ከእስር ይለቀቅ ቀጣይ ሀምሌ 02/2007 ዓም ይቅረብ ብሎ አዟል እኛም ለዋስትና የተጠየቀውን ገንዘብ ከምሳ በፊት ገንዘቡን አስይዘን የማስፈቻ ወረቀት ብናወጣም ከህግ በላይ የሆነው ፓሊስ ግን ማሙሸትን አለቅም ብሎ ለሁለተኛ ጊዜ የፍርድ ቤት ውሳኔ ሽሮ አስሮታል በዛሬው ችሎት ዋስትና አስይዘው ይዉጡ የተባሉት ሁሉ ሲወጡ ማሙሸት ግን አልወጣም የተጠየቀውን ዋስትና አስይዘን ለምን አይለቀቅም ብለን ላቀረብነው ጥያቄ የተሰጠን መልስ ማሙሸት ይለቀቅ የሚለውን መፈረም የሚችለው ሰው የለም የሱ ጉዳይ የሚመለከታቸ ሠዎች ተመካክረው ነው የሚፈታው የሚል መልስ ሰጥተውናል በትዕዛዙ መሠረት ነገም ተጨማሪ ጥረት እናደርጋለን ፓሊስ እንዳለፈው በእንቢተኝነቱ ከፀና እስከ ሀምሌ 02/2007 ዓም ድረስ በእስር ሊቆይ ይችላል ከዛስ በኋላ ያለው ምን ታውቆ የመላው ኢትዮጵያአንድነትድርጅት ( መኢአድ ) አባላትና ቤተሰቡ ለሁለተና ጊዜ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ በማመን አቀባበል ለማድረግ የመጣውን ሰው አሳፍረው መልሰውናል ሁኔታው እጅግ አሳዛኝ ነበር ፡፡

The post የመላው ኢትዮጵያአንድነት ድርጅት ( መኢአድ ) ፕሬዝደነንት አቶ ማሙሸት አማረ ፍርድ ቤት የፍርድ ቤት ውሎ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ!

$
0
0

ethiopia-blue-party-300x164አንድ በስልጣን ላይ የተቀመጠ አካል ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን ደህንነት መጠበቅ መሆኑን ጤነኛ አዕምሮ ያለው የሰው ልጅ የሚገነዘበው ጥሬ ሃቅ ነው፡፡ እንደ እርግማን ዛሬ በኢትዮጵያ የስልጣን እርካቡን የተቆጣጠረው ቡድን የሚገዛቸውን ዜጎች የሚያያቸው እንደጠላት እንጅ የመንግስትን ጥበቃ እንደሚፈልጉ፤ በጠላትነት የፈረጃቸው ዜጎች በከፈሉት ግብር ስልጣን ላይ መቆየት መቻሉን እንኳን ባለስልጣናቱ መረዳት ተስኗቸዋል፡፡

ሰኔ 8 ቀን 2007 ዓ.ም በደብረ ማርቆስ ከተማ እጅግ በሚሰቀጥጥ ጭካኔ እንደ እባብ ተቀጥቅጦ የተገደላው የሰማያዊ ፓርቲ ቆራጥ ታጋይ ሳሙኤል አወቀ የስርዓቱ አገልጋዩች ለዓመታት ሲያስፈራሩት፣ ሲደበድቡት፣ ሰርቶ የመኖር መብቱን ሲጋፉት፣ ያልተሳከ የመግደል ሙከራ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲፈፅሙበት መቆየታቸውን የሚያረጋግጡ በርካታ ማስረጃዎች ተይዘዋል፡፡ ሳሙኤል ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነችና ጥበቃ እንዲያደርጉለት የጠየቃቸው የፀጥታና የፍትህ አካላት በተገላቢጦሽ ተጨማሪ ዛቻና ማስፈራሪያ ያደርሱበት እንደነበር አይዘነጋም፡፡ አንድ ወጣት በተወለደበት ምድር በሕይወት የቆየባቸውን ጊዚያት በስጋት እንዲኖር ከተፈፀመበት ግፍ በተጨማሪ በሕይወት የመኖር መብቱ በአረመኔዎች እጅ ስትነጠቅ የህዝብን ፀጥታና ደሕንነት እናስከብራለን የሚሉ አካላት በመሃል ከተማ እንኳን ደርሰው ለመታደግ አቅሙም ሆነ ፍላጎቱ አልነበራቸውም፡፡

ሳሙኤል በአሰቃቂ ሁኔታ ከመገደሉ በፊት በተለያዩ ጊዚያት ለሚመለካታቸው አካላትና ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተላልፋቸው የነበሩ መልዕክቶች እንደተጠበቁ ሆነው በተለይ ግንቦት 25 2007 ዓ.ም በራሱ ገፅ በሆነው “የፌስ ቡክ” ማህበራዊ ሚዲያ ካስተላለፈው መልዕክት መረዳት እንደሚቻለው በተደራጀ ሁኔታ ሕይወቱ አደጋ ላይ እንደሆነች አስረግጦ ተናግሯል፡፡ ሆኖም የሚሰማውና የሚጠብቀው ምንም አካል እንዳልነበረ ይልቁንም ለመገደሉ ተባባሪ የሆኑ የመንግስት አካላት እንደነበሩ ስጋቱን በገለፀ በቀናት ውስጥ ሕይወቱ በአሰቃቂ ሁኔታ መቀጠፏ ጉልሕ ማስረጃ ነው፡፡

በሰላማዊ ትግል ፅኑዕ እምነት የነበረው ሳሙኤል አወቀ ይደርስበት የነበረውን ለቁጥርና ለዓይነት አታካች የሆነ በደል ተቋቁሞ፣ ትግሉን እንዲያቆም ወይም የሚወዳትን ሕይወቱን አሳልፎ የሰጠላትን ሐገሩን ለቆ እንዲሰደድ ይህ ካልሆነ ግን የእሱን ሕይወት ለማጥፋት እጅግ ቀላል መሆኑን የስርዓቱ ባለስልጣናት እና ካድሬዎች ደጋግመው ቢነግሩትም በጭቆና ስር ለሚማቅቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ የገባውን ቃል ከማጠፍ ይልቅ ሕይወቱን ለመሰዋት እንደሚቀለው የገባውን ቃል በተግባር አስመስክሮ አልፏል፡፡ በማሰርና በመደብደብ አላማውን እንደማያስቀይሩት፤ ከገደሉት ግን ቀሪ ታጋዮች በተለይም የእድሜ አቻዎቹ የሆኑ የእርሱ ትውልድ የሚሰዋለትን ዓላማ ከግብ እንዲያደርሱ “ትግሌን አደራ!! አደራ!!” በማለት ተማፅኖ አስቀምጧል፡፡

እኛም እንላለን፡፡ አደራህ ከባድ ነው፡፡ ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!!!

ይህ ስርዓት በህግም በሞራልም ኢትዮጵያን የማስተዳደር ብቃት የለውም፡፡ ወንጀለኞች ለፍርድ ይቅረቡ እያልንም አናላዝንም፤ ወንጀለኞቹ የመንግስት አካላት ናቸውና፡፡ በወንድማችንና ገና በለጋ እድሜው በተቀጨው የትግል አጋራችን ላይ የተፈፀመውን ግፍ አይቶ እንዳላዬ ዝም ያለ መንግስት ከዚህ የተሻለ መልካም ነገር ያመጣል ብለን አንጠብቅም፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ግን መልዕክት አለን፡፡ እስከ መቼ በግፍ እንገደላለን?!! ሸፍጠኞችስ እስከ መቼ ይዘባበቱብናል?!! ትግል ለውጤት የሚበቃው በተወሰኑ ቡድኖች ወይም ግለሰቦች መፍጨርጨር ብቻ ባለመሆኑ የግፍ ስርዓት እንዲያበቃ ሁላችንም የሚገባንን የዜግነት ድርሻ እንድንወጣ ጥሪ እናቀርባለን፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በአባላቱና በደጋፊዎቹ በአጠቃላይም የተለየ አስተሳሰብ ስላላቸው ብቻ በካድሬዎች የሚታሰሩ፣ የሚገረፉ፣ የሚሳደዱ፣ የሚዋረዱና የሚገደሉ ዜጎች ለከፈሉት መራራ ፅዋ ክብር ይሰጣል፡፡ መስዋዕትነታቸውም በከንቱ እንዳይሆን እሰከመጨረሻው ይታገላል፡፡

ሳሙኤል “ብታሰርም፣ ብገደልም ይህን ሁሉ የማደርገው ለሐገሬና ለነፃነቴ ነው” ያልከው ቃልህ ከመቃብር በላይ ነው!!!! ቃልህን እናከብራለን፡፡ አላማህንም እናሳካለን!!! ትግል ይቀጥላል . . .

ሰኔ 10 ቀን 2007 ዓ.ም

አዲስ አበባ

The post ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ ጥልቅ የሐዘን መግለጫ! appeared first on Zehabesha Amharic.

ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሰሩት 7 የዓየር ኃይል አባላት ነገ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

ከግንቦት ሰባት ጋር ግንኙነት አላችሁ በሚል የሽብርተኝነት ክስ የቀረበባቸው ሰባት የአየር ኃይል አባላት ነገ ሰኔ 12/2007 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ይቀርባሉ፡፡
ethiopian airforce
አቃቤ ህግ በሰኔ 7/2007 ዓ.ም ባቀረበባቸው ክስ ላይ እንደተመለከተው፣ ተከሳሾቹ የወንጀል ህጉ አንቀጽ 32(1)(ሀ)ን እና የጸረ-ሽብርተኝነት አዋጅ አንቀጽ 7(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ በሽብተኝነት ተከስሰዋል፡፡ በክሱ የተመለከቱት ተከሳሾች የሚከተሉት ናቸው፣

1ኛ. መ/አ ማስረሻ ሰጤ……አድራሻ ድሬዳዋ
2ኛ. መ/አ ብሩክ አጥናዬ……. ›› ድሬዳዋ
3ኛ. መ/አ ዳንኤል ግርማ…… ›› ድሬዳዋ
4ኛ. ገዛኸኝ ድረስ………. ›› ድሬዳዋ
5ኛ. ተስፋዬ እሸቴ…….. ›› ምስራቅ ጎጃም
6ኛ. ሰይፉ ግርማ……. ›› አዲስ አበባ
7ኛ. የሻምበል አድማው…… ›› ምስራቅ ጎጃም፣ ናቸው፡፡

በአቃቤ ህግ ክስ ላይ እንደተመለከተው ተከሳሾች ‹‹….ህገ መንግስቱንና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን በኃይል የማፈራረስ ዓላማ ይዘው ….በሽብር ድርጅት ውስጥ አባል በመሆንና በሽብር ድርጅት ተግባር ላይ ለመሳተፍ በማሰባቸው….›› የሽብርተኝነት ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡

ተከሳሾች ከኢ.ፌ.ዴ.ሪ አየር ኃይል በመክዳት ግንቦት ሰባትን ለመቀላቀል ወደ ኤርትራ ሊያመሩ ሲሉ ባህር ዳር እና ጎንደር ላይ እንደተያዙ በክሳቸው ላይ የተመለከተ ሲሆን፣ በአጠቃላይ የሽብር ድርጅት አባል በመሆን፣ ተልዕኮ በመቀበል፣ አባላትን በመመልመል እና መረጃ በማቀበል የሚል ክስ ቀርቦባቸዋል፡፡
የአየር ኃይል አባላት ተከሳሾቹ በነገው ዕለት አቃቤ ህግ ባቀረበባቸው ክስ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ የክስ መቃወሚያ ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ ተከሳሾች ለወራት ከቆዩበት ማዕከላዊ ወንጀል ምርመራ ወጥተው በአሁኑ ወቅት ቂሊንጦ እስር ቤት እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡

The post ከግንቦት 7 ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው የታሰሩት 7 የዓየር ኃይል አባላት ነገ ፍርድ ቤት ሊቀርቡ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

አለምነህ ዋሴ የእንግሊዙ አምባሳደር ስለአንዳርጋቸው ጽጌ ያቀረቡትን አስደንጋጭ ሪፖርት እንደሚከተለው ዘግቦታል


ሚካኤል ዲኖ ገጹ ላይ ካሰፈረው… –ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ

$
0
0

“አቧራውን ስለማጥራት” ወይስ እውነታውን ስለማድፋፋት!?

Dr Dagnachewእንደአንዳንድ ምሁራን ሁሉ ዶክተር ዳኛቸውም ሀሳቡን በፅሁፍ የመግለፅ ክህሎት ስለሌለው፣ መሐመድ ሀሰን በተባለው ጋዜጠኛ አሰናኝነት፤ ለህትመት እንዲበቃ እየሰራ መሆኑን ከሰማው ከርሜያለሁ። የዶክተር መረራን ስህተት ላለመድገም መጠንቀቁንም አድንቄያለሁ።
በመፅሃፉ መውጣት ዋዜማ፦ ‘በነገው ቀን ይጠብቋት’ አይነት ፖስት ተመልክቼ፤ ‘ሞቱበት እኮ!’ ብዬ አሽማጥጬ ሳልጨርስ፤ የዘራፊ እና ተዘራፊ፣ የውስጥ አዋቂ አባሪ እና የአቧራ አጥሪ ውዝግቦች ተከታተሉብኝ።
በቅደም-ተከተል ከተቀመጡ የመጀመሪያ የሚሆነው ዶክተር ዳኛቸው በአዲስ አድማስ ጋዜጣ ጉዳዩን ይፋ ማድረጉ ነው። ዶክተር በድሉ የትራጀዲውን ሌላ ተዋናይ ጨምሮ የተከሰተበት ሁለተኛው ሲሆን፣ ሶስተኛው እና የዚህ ፅሁፍ መንስኤ የሆነው ደግሞ በአቶ አስራት የቀረበው አቧራማ ማስተባበያ ነው።

አስራት፣ እራሱን በቅጡ በመከላከል ፈንታ በመግቢያ ትረታው፣ በእግረ-መንገድ የተጠቀሰውን ተወቃሽ ስም (ሰለሞን ስዩም) በማጎን፤ ለጉዳዩ ሌላ መልክ ለመስጠት ሲጣጣር ትዝብታችን ሀ… ብሎ ይጀምራል።
በመደናገጥ ወደኋላ ተመልሶ የጠቃቀሳቸው ተጋድሎዎቹም ሆኑ አበርክቶዎቹም ቢሆኑ፤ አሁን ላይ እየተወቀሰበት ካለው ጉዳይ ጋ አንዳች ቀጥተኛ ግንኙነት እንደሌላቸው ስናጤን አግራሞታችን መጨመሩ አይቀርም።

በዶክተር በድሉ ላይ በ’አጋለጥከኝ’ መግፍኤ ከተርከፈከፉት፣ የአቶ አስራት ዓውድ-ዘለል ጥይቶች ብስጭት- ወለዶች ናቸውና በቸልታ ልለፋቸው። በእርግጥም በአስራት አብርሀም የፖለቲካ ተክለ-ሰውነት እና ማንነት ደረጃ ላይ የሚገኝ ሰው፣ ሰብእናው በውስልትና እና በንፅህና መካከል ለሙግት ቀርባ ሳለ፣ በመጠሪያ ስም የፊደል ግድፈት ላይ ለማተኮር መሞከሩ የሚይዝ የሚወረውረውን እንዳጣ ያሳያል።
አስራት፤ ዶክተር ዳኛቸው እንደተናደደበት ሲናዘዝልን፣ በትይዩ የክሱን እውነተኛነት እያስረገጠልን እንደሆነ ልብ ማለቱን እጠራጠራለሁ።
የዳኛቸውን ንዴት ሲዘረዝርልንም… አንድም ከመፅሀፉ ጀርባ በሰጠው የተጋነነ አስተያየት (ብለርቡ ላይ የፀሀፊው አስራት ሳይሆን፣ የአከፋፋዩ አስራት መንፈስ እንደሚገን መገመት ይቻላል)፣ አንድም መፅሀፉን በማከፋፈሉ ሳቢያ እንደነበር በመግለፅ ነው።
በተማሪው እና ከስሩ በማይጠፋ “ወዳጁ” የተከዳው ምሁር፣ መናደዱን ከመግለፅ በላይ ምን ሊያደርግ ይችላል?!!!

አስራት ሆይ… ታዲያ ስለግለሰብ ክህደት፣ ብረት አንስቶ ጫካ ይግባ ወይስ ማቅ ለብሶ በሩን ዘግቶ ‘ ወዮ ወዳጅነት’ እያለ ይማቅቅ????? የወዳጅህን መከፋት አቃለህ ማቅረብህስ ምን ማለት ነው?
እስከአሁን ስለጉዳዩ በይፋ ሲናገር ያልሰማነው መሀመድ ሀሰን የተባለውን ፀሀፊ፤ በህግ ለመፋረድ መወሰኑን የተናገረው ዳኛቸው፤ አስራትን ያልጠቀሰው ምናልባት የወዳጅነት ይሉኝታ ይዞት እንደሁ እንጂ አንድነታቸውን ጠፍቶት አይመስለኝም።
አስራት ዝቅ እያለ ሲሄድ ሀፍረቱን መከለል በማይችሉ ብጥቅጣቂ ምክንያቶች እና ህፃን በማይረታላቸው ሽንገላዎች፣ ጉዳዩን ለመሸፋፈን ሲወራጭ በግልፅ መመልከት ይቻላል።
‘ተራ ያልሆነ ወዳጅነት፣ ከአባት እና ልጅ ፍቅር የሚገዳደር ቀረቤታ..’ እያለ የገለፀውን የግንኙነት መደላደል ተጠቅሞ በምንተፋው መተባበሩ ሳያንስ፤ ምንተፋው ዶክተሩን በማስተዋወቅ ረገድ ጠቀሜታው የጎላ እንደሆነ በልበ’ሙሉነት ለማብራራት ሲሞክር እጅግ ያስደነግጣል!!!
የአስራት ካፈርኩ አይመልሰኝ ሰለባውን ከመምከር እስከ እስከመሸንገል ብሎም ዋነኛው ሌባ ድርጊቱን የፈፀመው በቅን መንፈስ ተነሳስቶ መሆኑን እስከመመስከር ይበረታል። አቶ አስራት፣ ዶክተር ዳኛቸው ሰብስቦ ከማሳተም ይልቅ ወጥ ስራ መስራት እንዳለበት መክሮ ሲያበቃ፤ ‘ወደፊት የተሻለ ስራ የመስራት ብቃት እንዳለህ አውቃለሁና ይሄኛውን ዝርፊያ እርሳው’ እስከማለት ይደፍራል።
እውነቱን ለመናገር ” አቧራውን ስለማጥራት” በሚለው ርእሱ ተታልዬ አይኔን ከፍቼ በገባሁበት ፅሁፍ፣ አስራት እራሱን በዘላቂው በጥራት ማየት እንዳልችል በሚያደርግ ሁኔታ አቧራ ሞጅሮብኝ እየተጨናበስኩ ተመልሻለሁ።

በመጨረሻም ግን….
ከእንግዲህ ያለው ደባሪ ታሪክ በኋላ ማንሳት የሚቻለው ነገር…. በተቃዋሚ ፓርቲ፣ በነፃው ሚዲያ፣ በሲቪል ማህበራት… ወዘተ የነፃነት ትግሉን በምናዘምት ፊት-አውራሪዎች ልብ ውስጥ ሳይቀር፤ ይገለጥበት አምባ ያላገኘ.. አምባገነንነት፣ ጥቅመኝነት፣ አድር-ባይነት፣ ይስሙለኝነት፣ ይሉኝታ-ቢስነት እና ጨካኝነት አድፍጧል።
በመላው ኢትዮጵያ ጓዳ ከሚገኘው ማድጋ የተመረዘውን ውሀ እያጠጣን አይደል ዛሬ እነዚህን የመሰሉ አረሞች ያበቀልነው? እንደማህበረሰብ፣፣ ችግሩ እኛም ዘንድ መሆኑ አይካድም።
ቢያንስ ግን የነፃነት ታጋዮች፣ እንዲህ ካለው የሰብዕና እድፍ ራሳችንን ባላፀዳንበት ሁኔታ፣ ምናልባት የወያኔን አገዛዝ ማስወገድ ብንችል እንኳ፣ በአዲስ አቁማዳ ነባሩን ብጥብጥ አገላብጠን እሱኑ እየቀዳን ሕዝቡን ከማሳከር የተሻለ አንዳች ተግባር አንከውንም።

The post ሚካኤል ዲኖ ገጹ ላይ ካሰፈረው… – ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል ቤታቸው እንደፈረሰባቸው የለገጣፎ ነዋሪዎች ገለጹ

$
0
0

‹‹በምርጫው ምክንያት ሊበቀሉን ነው ቤታችን በክረምት ያፈረሱት›› ነዋሪዎቹ

11220142_727121737413487_3102328378380879005_nበ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል ቤታቸው እንደፈረሰባቸው በለገጣፎ አባኪሮስ፣ ገዋሳ አካባቢ ነዋሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ነዋሪዎቹ በተለያዩ ጊዜያት ፖሊስና ካድሬዎች ቤታቸውን በቀይ ቀለም ከቀቡ በኋላ በተደጋጋሚ ገንዘብ ሲቀበሏቸው እንደቆዩና ከሰኔ 09/2007 ዓ.ም ጀምሮ በምርጫው ሰበብ ቤታቸውን እያፈረሱ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ የአካባቢው ህዝብ ‹‹ቤትክን እናፈርሳለን!›› እየተባለ በደተጋጋሚ በሚከፍለው ሙስና የተማረረው እንደሆነ የገለጹት ነዋሪዎቹ በአካባቢው ኢህአዴግ እንዳልተመረጠ ገልጸዋል፡፡ ይህን ተከትሎም ኢህአዴግን ያልመረጡ በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን መርጠዋል የተባሉ ነዋሪዎች ቤት ቀይ ምልክት ተቀብቶ እንዲፈርስ መደረጉን ገልጸዋል፡፡ ከምርጫው ጋር በተያያዘ ቤታቸው እንዲፈርስ ቀይ ምልክት ከተቀባባቸው መካከል ለፖሊስና ካድሬዎች ጠቀም ያሉ ገንዘብ የከፈሉ ነዋሪዎች እንዳይፈርስባቸው ሲደረግ ገንዘብ መክፈል ያልቻልነው ቤታችን ፈርሶብናል ብለዋል፡፡


10561823_727121734080154_5796908975695142219_nነገረ ኢትዮጵያ ቢሮ ድረስ በመምጣት መረጃውን ያቀበሉን ነዋሪዎቹ ‹‹ኢህአዴግን አልመረጣችሁም፣ ሰማያዊ ፓርቲን ነው የመረጣችሁት በሚል ቤታችን ፈርሶ በአሁኑ ወቅት ከእነ ልጆቻችን ጎዳና ላይ ወድቀናል፡፡›› ብለዋል፡፡ ‹‹እስካሁን ቤታችሁን እናፈርስባችኋለን ብለው በማስፈራራት ከፍተኛ ገንዘብ ሲያስከፍሉን ቆይተዋል፡፡ ቆርቆሮ ገንጥለው ለቆርቆሮው እስከ 2 ሺህ ብር አስከፍለው እንደገና ቆርቆሮውን ይመልሱልን ነበር፡፡ አሁን ደግሞ በምርጫው ምክንያት በአካባቢው ህዝብ ቂም ይዘዋል፡፡ በምርጫው ምክንያት ሊበቀሉን ነው ቤታችን በክረምት ያፈረሱት›› ያለው አንድ ወጣት ሙስና ከፍለው ቤታቸው እንዳይፈርስ ካደረጉት ባሻገር እየዞሩ ቤት የሚያፈርሱት ፖሊሶችና ደህንነቶች በአካባቢው በርካታ ቤቶችን ማስገንባታቸውና የእነሱ ቤት እንደማይፈርስባቸው ገልጾአል፡፡ የካድሬዎች፣ የፖሊሶችና ገንዘብ የሚከፍሉት ሲቀር ‹‹ኢህአዴግን አልመረጣችሁም፡፡ የመረጣችሁት ተቃዋሚዎችን በተለይም ሰማያዊ ፓርቲን ነው›› ተብለው ቤታቸው እንደሚፈርስ ተነግሯቸው ሙስና መክፈል ያልቻሉት ነዋሪዎች ቤት ተመርጦ እየፈረሰባቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ገዋሳ፣ ጪሚሲና ሚሽን የተባሉ አካባቢዎች ቤቶች እየፈረሱ መሆኑን የገለጹ በለገጣፎ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ ‹‹የነዋሪዎች ቤት እየፈረሰ የሚገኘው በምርጫው ምክንያት ነው፡፡ ለገጣፎ አካባቢ ምርጫው መጭበርበሩን ያጋለጡ ሰዎች ከፍተኛ ጫና ደርሶባቸዋል፡፡ እኔ ጋርም እንዳይገናኙም ወከባ ይፈፀምባቸዋል፡፡ አሁን ደግሞ ህዝቡ ኢህአዴግን ባለመምረጡ ቤቱን እያፈረሱበት ነው፡፡›› ብለዋል፡፡

The post ኢህአዴግን አልመረጣችሁም በሚል ቤታቸው እንደፈረሰባቸው የለገጣፎ ነዋሪዎች ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹የታሰርኩት ባልሰራሁት ወንጀል ነው›› አቶ ማሙሸት አማረ

$
0
0

11174891_726615650797429_6899703472592734916_nመጀመሪያ የቀረበብኝ ክስ አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም የተጠራው ሰልፍ ላይ ወጣቶችን አደራጅተህ ሁከትና ብጥብጥ ፈጥረሃል የሚል ነው፡፡ በዚህ ክስ ፖሊስ ሁነኛ ማስረጃ አለኝ ብሎ ፍርድ ቤት ቀርቦ ተከራክሯል፡፡ መንግስት በጠራው ሰልፍ ላይ ሁከትና ብጥብጥ ለማስነሳት ስለጣረ ምርጫ ላይም ተመሳሳይ ችግር ይፈጥርብናል ብሎ ማክበጃ ሁሉ አቅርቧል፡፡ ነገር ግን የሰልፉ ቀን እኔ ከምርጫ ቦርድ ጋር ባለን ክስ ፍርድ ቤት ክርክር ነበረኝ፡፡ መጀመሪያ ሰልፉ ላይ እንዳልነበርኩ ብከራከርም ሰልፉ ላይ መገኘቴን ገልጾ ሲከራከር የነበረው ፖሊስ ፍርድ ቤቱ ሚያዝያ 14/08/07 ተያዝኩ በተባለበት ሰዓት ፍርድ ቤት ውስጥ እንደነበርኩ ጻፈልኝ፡፡ ያንን ሳቀርብ ጠንካራ ማስረጃ አለ ብሎ ሲከራከር የነበረውና ሰልፉ ላይ ብጥብጥ ፈጥሯል ብሎ ያስመሰከረብኝ ፖሊስ ክሱን አንስቻለሁ አለ፡፡

ፖሊስ ክሱን በማንሳቱም በነፃ እንድለቀቅ ተደረገ፡፡ ቤተሰቦቼ የመፍቻ ወረቀት ይዘው ወደ ፖሊስ ጣቢያው ሲሄዱ ፖሊሶቹም ታስሬ የነበርኩበት ቦሌ ክፍለ ከተማ አምቼ ፖሊስ ጣቢያ ወስደው እንደሚፈቱኝ ገልጸውልኝ ከፍርድ ቤት ወጣን፡፡ ሆኖም ግን ወደ አምቼ ወስደንህ ትፈታለህ ያሉኝ ፖሊሶች በቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ፖሊስ ጣቢያ (ሶስተኛ) ይዘውኝ መጡ፡፡
የመጀመሪያውና ፍርድ ቤት ሰልፉ ላይ እንዳልበርኩ የመሰከረልኝ ክስ አላስኬድ ሲል በነገታው ሌላ ክስ መሰረቱብኝ፡፡ በ14/08/07 እንዳልነበርኩ የሚያሳይ ጠንካራ መረጃ ሲገኝ ክሱን ከዛ በፊት አደረጉት፡፡ በመሆኑም ወደኋላ ተመልሰው በ12/08/07 እና በ13/08/07 ወጣቱን አደራጅቶ ወደ ለቅሶ ቤት በመውሰድ ብጥብጥ ፈጥሯል ብለው ከሰሱኝ፡፡ ዛሬ በነበረኝ ችሎት ዳኛዋ 5 ሺህ ብር አስይዜ ከእስር እንድለቀቅ ፈርደው ነበር፡፡ ጓደኞቼና ቤተሰቦቹ መፍቻ ይዘው ሲመጡ ግን አለቆቹ ቢሯቸውን ዘግተው ወጥተዋል፡፡ እኔን በቀላሉ መፍታት የፈለጉ አይመስለኝም፡፡
የመጀመሪያውን ክስ ፍርድ ቤት በፃፈው ደብዳቤ ውድቅ ሆኗል፡፡ አሁን ደግሞ ዳኛዋ እንድለቀቅ ወስነዋል፡፡ ሆኖም ግን ፖሊስ እኔን መፍታት አልፈለገም፡፡ አሁንም ድረስ ታስሬ የምገኘው ባልዋልኩበት ነው፡፡ የታሰርኩት ባልሰራሁት ወንጀል ነው፡፡ እንግዲህ ቀጥሎ የሚመጣውን የምናየው ይሆናል፡፡ ምን እንደሚያደርጉ አላውቅም፡፡

(ይህ ፅሁፍ ትናንት ሰኔ 9/2007 ዓ.ም የነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር ከአቶ ከማሙሸት አማረ ጋር ካደረገው ንግግር የተወሰደ ሲሆን በዛሬው ዕለት ይግባኝ እንደተጠየቀበት ለማወቅ ተችሏል፡፡)

The post ‹‹የታሰርኩት ባልሰራሁት ወንጀል ነው›› አቶ ማሙሸት አማረ appeared first on Zehabesha Amharic.

በዚህ ታላቅ ወር እጆቻችን ወደላይ ዘርግተን የተበዳይ ድምፃችንን እናሰማ!!! –ድምጻችን ይሰማ!

$
0
0

አርብ ሰኔ 12/2007
voice of peopleረመዳን የድል ወር ነው፡፡ ለየትኛውም ዓይነት ድል የመጀመሪያው እና ዋነኛው እርምጃ የሆነውን በራስ ላይ ድል የመቀዳጀትን ስኬት እውን ለማድረግ ደግሞ ከረመዳን የተሻለ አጋጣሚ የለም፡፡ ረመዳን የኢብሊስን መታሰር ተከትሎ የሰውን ልጅ ወደታች ከሚጎትተው ስጋዊ ሰሜት ጋር የሚያደርገው ትግል ቀላል የሚሆንበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ነፍስ ተገርታ፣ ባህሪዋ ተስተካክሎ በፅድቅ ስራዎች እንድትመጥቅ ከፍተኛ ልፋትና ትግል ይጠይቃል፤ መልካም ነገሮች ባጠቃላይ ያለልፋት አይገኙምና፡፡ ነፍስ በሰከነ እምነትና አመለካከት የበለፀገች፣ በመልካም ስብእና ላይ የረጋች ስትሆን የሰው ልጅ በየትኛውም የህይወት መስክ ስኬታማ እንዳይሆን እንቅፋት የሚሆኑበትን ነገሮች በቀላሉ የምትሻገርበት ጉልበት ይኖራታል፡፡


ረመዳን ማህበረሰባዊ ተጨባጭን ለመቀየር በሚደረግ ትግል ወሳኝ የሆኑትን ትዕግስት፣ ጽናት እና መስዋእትነትን ለነፍሳችን የምናስታጥቅበትን ምህዳር አመቻችቷል፡፡ ተጨባጩን ለመቀየር በሚደረገው ትግል ማሰብ የማይሰለቸው አዕምሮ፣ ድካም የማይሰማው ጉልበት፣ የማይበርድ ወኔና ስሜትን የተላበሰ ስብዕና ለመገንባት፣ በአስቸጋሪ መሰናክሎች የተሞላውን የጀነት ጉዞ በስኬታማነት ለማጠናቀቅ የሚያስችለውን የኢማን ስንቅ የምንሸምትበት ከአዛኙ ጌታችን የተቸረ መስተንግዶ ነው፡፡ እንግዲህ የወሮች ቁንጮ የሆነውና ታላላቅ ችሮታዎችን እና ትሩፋቶችን ጠቅልሎ የያዘው ረመዳን ከእነሙሉ ስጦታው በአላህ ፀጋዎች ደምቆ ልቦቻችንን በብርሀኑ ሊሞላን እነሆ አንድ ብሎ ጀምሯል፡፡ ከትሩፋቶቹ አንዱ ደግሞ ዱዓ ተቀባይነት በሚያገኝባቸው በርካታ ወቅቶች የታጨቀ መሆኑ ነው፡፡


ዱዓ ሰፊ የኸይር በርና በቀላሉ ወደ ስኬት መዳረሻ አቋራጭ መንገድ ነው፡፡ ዱዓ የነገሮች ባለቤትነት በእጁ ለሆነው አምላክ የሚደረግ መተናነስ፣ ደካማ ባሪያዎቹ መሆናችንን በተግባር የምናሳይበት የአምልኮ አስኳል ነው፡፡ በያዝነው የተከበረ ወር አላህን (ሱ.ወ) እያረፈብን ያለውን የበደል አለንጋ እንዲያስወግድልን፣ ችግሮቻችንን ቀርፎ ቃል የገባልንን ድል እንዲያወርድልን ከየትኛውም ጊዜ በበለጠ ልንማጸነው ይገባል፡፡ የምድር ተረኛ ገዢዎች ውክልናችንን እና ፊርማችንን በሰጠናቸው ወኪሎቻችን ላይ እኩይ ውሳኔ ለመስጠት የያዙት ቀጠሮ ሳምንት ብቻ የቀረው በመሆኑ በዛሬዋ የመጀመሪያ የረመዳን ጁሙዓ የምናደርጋት ዱዓ ትልቅ ዋጋ ይኖራታል፡፡ መልእክተኛው (ሰ.ዐ.ወ) በጁሙዓ ዱዓ ተቀባይነት የሚያገኝባት ወቅት መኖሯን ነግረውናል፡፡ ከረመዳን ጋር ሲደመር ደግሞ መቅቡልነቱ ይጨምራል፡፡ በመሆኑም ከፍትሐዊው አምላካችን አላህ (ሱ.ወ) ፍትሕን በመፈለግ እጆቻችን ወደላይ ዘርግተን የተበዳይ ድምፃችንን ልናሰማ ይገባል፡፡ ለአላህ ያለንን ክብርና መተናነስ፣ ኃይልም ብልሀትም የእርሱ ብቻ መሆኑን በዱዓችን ልንገልጽ ይገባል፡፡ አላህ ዱዓችንን ይቀበለን!


‹‹ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡›› (ሱረቱል በቀራህ 2፡186)
‹‹‹አላህ በቂዬ ነው፡፡ በእርሱ ላይ ተመኪዎች ይመካሉ› በል፡፡››
(ሱረቱ ዙመር 38፡39)
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post በዚህ ታላቅ ወር እጆቻችን ወደላይ ዘርግተን የተበዳይ ድምፃችንን እናሰማ!!! – ድምጻችን ይሰማ! appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዛውንቱ እንግልት –አርአያ ተስፋማሪያም

$
0
0

101አቶ ተክሌ አበራ ይባላሉ። በአሰብ መርከበኛ ሆነው ሰርተዋል። ከአገር ከወጡ 47 አመት ሲሆናቸው፣ በደቡብ አፍሪካ መኖር ከጀመሩ 20 አመት አስቆጥረዋል። በከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቀው የሚገኙት አዛውንቱ አቶ ተክሌ ወደ አገር ቤት መመለስ ቢፈልጉም የማስታወስ ችግር አለባቸው። አቶ ምናሴ አበራ የሚባል ወንድም እንዳላቸውና ጌጃ ሰፈር እንደሚኖር ይናገራሉ። በደ/አፍሪካ የሚኖሩ ወገኖች አዛውንቱን ወደ አገር ቤት ለመመለስ አስፈላጊውን ትብብር በማድረግ ኢትዮጵያ ኤምባሲን በስልክ ሲጠይቁ የተሰጣቸው ምላሽ « የኢትዮጲያዊነት ማስረጃ ከሌላቸው እንዳታመጧቸው» የሚል ነበር። ኢትዮጵያዊነት ማስረጃ ማለት ምን ማለት ነው?..ማነው ይህን የሚሰጠው?…ኤምባሲው እንደሌላ ዜጋ ኢትዮጵያውያንን ምስረጃ አምጡ ይላል!? ..እጅግ ያሳዝናል! ኤምባሲው ይህን ቢልም ኢትዮጵያውያን ጥረታቸውን ቀጥለዋል። የአዛውንቱን ማስረጃ በመፈለግ በሊሴፓሴ አገር ቤት ለመላክ እየሞከሩ ነው።
(በፎቶው አዛውንቱ አቶ ተክሌ አበራ)

The post የአዛውንቱ እንግልት – አርአያ ተስፋማሪያም appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>