Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

ነገ አርብ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ ከተሞች የመሰባሰብና የሰደቃ ፕሮግራም እንደሚኖር ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ

$
0
0

sedeka

ጁሙዓ በአንዋር መስጂድ እና በክልል ማእከላዊ መስጂዶች ተሰባስበን በመስገድ ለወኪሎቻችን አጋርነታችንን እንግለጽ!
የአንድ ብር ሰደቃ መርሃ ግብር ይኖረናል!

እስካሁን ለወኪሎቻችን ያለንን አጋርነት በተለያዩ መንገዶች ስንገልጽ ቆይተናል፡፡ የረመዳን ጁሙዓዎች ደግሞ አጋርነታችንን ለመግለጽ ከምንጠቀማቸው አመቺ ገጠመኞች ይመደባሉ፡፡ በእስካሁኑ የትግል ቆይታችን አንድነታችንን አጠንክረን ችግሮቻችንን በጋራ እንደተጋፈጥን ሁሉ አሁንም በዚሁ አንድነታችን እንደምንቀጥል ማረጋገጥ አስፈላጊ ተግባር ነው፡፡ይህን በተግባር ላይ ለማዋል የፊታችን ጁሙዓ በአዲስ አበባ አንዋር መስጂድ እና በክልል ደግሞ በማእከላዊ በሆኑ መስጂዶች ላይ ተሰባስበን የመስገድ እና በቀኑም ለችግረኞች በነፍስ ወከፍ የአንድ ብር ሰደቃ የመስጠት መርሃ ግብር ይኖረናል፡፡ በመሆኑም መርሃ ግብሩን ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ሁላችንም እንረባረብ ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን!

የጁሙዓ ቀጠሯችን በአንዋር እና በክልል ማእከላዊ መስጂዶች ነው! ኑ…. ለወኪሎቻችን አጋርነታችንን እንግለጽ!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post ነገ አርብ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ ከተሞች የመሰባሰብና የሰደቃ ፕሮግራም እንደሚኖር ድምፃችን ይሰማ አስታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.


ኦባማን የኢትዮጵያ መንገዳቸው ቱሪናፋ አያደ ርጋቸውም ? –ከቢላል አበጋዝ

$
0
0

ጁን 25 ቀን 2015

ዋሽንተን ዲ ሲ ፡

ቱሪናፋ የሚለውን ቃል ሐበሻ የተባለው መዝገበ ቃላት: ወሬኛ።ጉረኛ።ወሬ የሚያበዛ ይለዋል።ይህ ጽሁፍ ለዘለፋ ሳይሆን በፕሬዚዳንት ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት ላይ ለመወያየት ነው።እኒህን ነጥቦች እዩልኝ።

Obama Ethiopiaኦባማ ለምርጫ ሲቀርቡ “ይቻላል ፡አዎን ይቻላል” ብለው እኛንም አስብለውን ነበር።ለአሃጉራችንም በጎ ያደርጋሉ ብለንም ተመኝተን ነበርን።መመረጣቸውንም ኮርተንበትም ነበር።የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው የአገዛዝ ዘመናቸውን ጥላሸት የሚቀባው ነው።ይህ ደግሞ ለሳቸው ክፉ ነው። ወደ ስልጣን ሲመጡ የአፍጋኒስታንና የኢራቅን የውጭ ጉዳይ ችግሮችን ተረክበዋል።በስልጣን እያሉ ሶሪያ እና የመን ተጨምረዋል። እድላቸው ሆኖ የቋጠሩት ሁሉ የሚፈታባቸው ናቸው። ተቀናቃኞቻቸው ውሳኔ ላይ ቆራጥነት የለህም ይሏቸዋል።ስተተኛና ዳተኛ ያደርጓቸዋል። ይህ ጽሁፍም አፍቅሮ ህወሃት ተግባርዎ ስተት ነው ለማለት ነው። ከኢትዮጵያውያን በተረፈም ዓለም እየታዘበዎት ነው።የኢትዮጵያ ህዝብ እምነቱ በኢትዮጵያ አምላክ ላይ ሲሆን የህወሃት እምነት በስዎ ላይ ነው። ለኢትዮጵያ ሁሌም መጨረሻው ላይ ይፈርድላታል።ህወሃት እንደ ጃፓን ሲኒ መሰባበሩ ግድግዳ ላይ ተጽፏል።

የኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መሄድ ለማንም ግድ አይሰጥም። ስለ  ኢትዮጵያ ካሰብን እውነቱ ይህ ነው። የእስልምና ሃይማኖት ኢትዮጵያን አትንኩ ሲል መጽሃፍ ቅዱስ እጆችዋን ወደፈጣሪዋ ትዘረጋለች ይላል።ዛሬ ደግሞ ደካማ በጸሎቱ፡ብርቱው በጉልበቱ፡ በንብረቱ እግዜርን አለኝታ አድርጎ ኢትዮጵያን ከህወሃት መንጋጋ ሊያወጣት የቆረጠበት ስለሆነ “ኦባማ አላወቁበትም” ከማለት ሌላ፡ አምባገነኖች ጋር ጓይላ ቢጨፍሩ “እንታይ ገድሸኒ” እንላቸዋለን።

ካስተዋልነው ዛሬ የአፍሪካ አሀጉር  ከነዚያ የመንግስት ግልበጣ የዞትር ወግ ከነበረባቸው ዘመናት አልፎ ይገኛል።ስለዴሞክራሲ መስፋፋት የሚጽፉት አውራ ምሁራን  ፍራንሲስ ፉኪያማ እና አማርትየ ሳን እንደሚሉት  ጭቆና እየተገረሰሰ ነጻነት እያበበ ነው ባጠቃላዩ ሲታይ።በአሃጉራችን ናይጄሪያ፡ ጋና፡ ላይቤሪያ፡ ደቡብ አፍሪካ ፡ቦስዋና  ለምሳሌ ያህል ይጠቀሳሉ። የዚህ ሂደት ተቃራኒው ክሚታይባቸው አገራት አንድዋ ኢትዮጵያ ናት።

ኢትዮጵያ ከህዝብዋ ብዛት መልክአ ምድርን ይዞ የዓለም ፖለቲካ ሽኩቻ ላይ ያለችበቱ አቀማመጥዋ ዋና ቦታ እዲኖራት የግድ ነው።የምንወዳት ስለሆነ ልንክባት ሳይሆን እውነታው ይህ ነው።ሀያላን ከደጇ እማይጠፉትም ለዚሁ ነው።ሁሉም ለጥቅሙ።ታዲያ ሁለት አሳዛኝ ጉዳዮች አሉ።አንደኛውና ዋነኛው የገዛ ጥቅሟን የሚጻረር ፍጹም አምባገነን መንግስት ተንሰራፍቶባት ይሄው ዘመናት ፈጅቷል።ሁለተኛው ያለውን አደገኛ መንግስት በግዜ እንዳይተካው የተቃዋሚው ሀይል በህብረት ሆኖ ዛሬ አለመጎልበቱ ነው።ትልቅ መሻሻል እያየን መሆኑ የማይካድ ቢሆንም።

ይችን ዴሞክራሲና ፍትህ ቧልት የሆኑባትን ኢትዮጵያ  ፕሬዝዳንት ኦባማ ለምን ለጉብኝት መረጥዋት ? በመጀመሪያ የአስተዳደር ዘመናቸው “አምባገነኖች ወዮላችሁ !”ሲሉ ቆይተው የአምባ ገነኖች የንብ ቀፎን ያስመረጣቸውን ምክኛት መመርመር ድንቅ ነው።ዛሬ ኢትዮጵያ ትልቅ እስር ቤት ናት።የታሰረ ልጠይቅ ብለው ይሆን ? ዘር ማጥፋት የተካሄደባቸውን ስፍራዎች በዓይናቸው በብረቱ ለማየት? ሻል ያሉ ምክንያቶች እናስብ እንጂ! ጎበዝ! የአባታቸውን አገር የደፈረውን አል ሸባብን ከምድር ገጽ ለማጥፋት ?እግረ መንገዳቸው ደቡብ አፍሪካ ከመያዝ ያመለጠውን የሱዳኑን አል በሺር ጎራ ብለው ጋማውን ይዘው ዋንታናሞ ኩባ ሊሰዱት? ይህስ እንዴት ይረሳል። የአፍሪካ አምባ ገነኖችን አንድ ጋ አዲሳባ ሲማግጡ ሲያገኟቸው አንዱን በካልቾ! ሌላውን በኩርኩም! የቀረውን በቴስታ።ጉድ ሊያፈሉ ነው ለምርጫ ጊዜ እንደፎከሩት። ላቶ መለስ ለቅሶ ሊደርሱ? ይበቃል:: እኒህ የአስቂኙ ጓደኛዬ ወጎች ናቸው። አንድ ነገር እውነት ነው።ዋይት ሀውስ ከኦባማ ቤት በር ፊት ለፊት “ሚስተር ኦባማ! እረ ሚስተር ኦባማ ! አይሰሙም እንዴ ?”  እያለን እንጮህ ለነበርነው ልጅነታችንን አስጨርሰውናል።በፖለቲካ ትግል ይህ አቢይ ጉዳይ ነው።ካባቶቻችን አልማር ያልነውን እንድንማር አድርገዋል።ትግሉ ባገር ቤት ባሉ ኢትዮጵያውያንና፡ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ባንድ ወገን ወያኔ በተቃራኒ መካከል ነው። ኦባማ ላሻቸው ወገን ቲፎዞ ይሁኑ።ባሻቸው በመሰላቸው ጊዜ። የመን የሆነው ይህ ነው። አሊ አብደላ ሳሊህ የኪሳቸው መሀረብ ነበር። የዛሬውን ሳይሆን።እኛ ኢትዮጵውያን  ከሚገድለን የበለጠ የናቀን ላይ ቂም እንይዛለን። አንረሳም።ዴሞክራሲ ሲሉ ወያኔ ያረገው ምርጫ ይበቃችኋል ነው። በዚህ እንተወውና ሌሎች ምክንያቶችን እናቋጥር።እኛ ምን ቸገረን ሲሻቸው ሰሜን ኮሪያም ሄደው ከዚያ ድንቡሼ የአገሩ መሪ ጋር ቅርጫት ኳስ ይጫወቱ።ያችን አፈነዳታለሁ የሚላትን ነገርም ቢቀሙት ለዚያ አካባቢ ሰላም ነው።ከዚህ የተረፈውን ያገራችን ሙያተኛ ቀልደኞች ይቀጥሉበት።ዋና ጭብጥ ነገሮችን ከፌዙ በተረፈ ከዚህ በታች እንወያይ:: አካባቢያችንን በተመለከተ።

ከአመታት በፊት አሜሪካ በሶማሊያ የማይታረም ስተት ሰርታለች።እንዲያው ከኢራቅም ከሌሎቹም የቀበሌው ችግሮች በፊት የሶማሊያ ይቀድማል።ከዚያ ወዲያ ዘሎ መግባት በኢራቅ።ዘሎ መግባት በየመን።ጎረቤት ሲታማ ለኔ ብለህ ስማ ነው።በዚህ በኩል ሲያስቡት ይዘገንናል::ህወሃት ልትጨምረን የምትፈልገው ገደል የመንን ይመስላል። ቶሎ ህብረት ፈጥረን ጊዜ ሳንወስድ ወያኔን እናስወግድ የሚለው ዓላማ በተጨባጭ ከዚህ ምክንያት ይነሳል። አገር የማዳን ትግል ሲባል ይሄው ነው።ኢትዮጵያ ሌላዋ ስተት አንዳትሆን::

የሶማሊያን ችግር ለመፍታት አማሪካ ዘወር ማለት አለባት።ሌሎች አውሮፓ፡ቻይና ሩሲያ ህንድ እኒህ ብልሃትና ዘዴው ተቀባይነትም ስለሚኖራቸው የተሻሉ ሽማግሌዎች ይሆናሉ።አልሸባብን ከአልቃይዳ ጉያ ሊያወያወጡ የተሻለ እድል አላቸው። የተቀረው አረብ ገንዘብ ያልቸገረው ቲርኪሚርኪ ነው።ምንአልባት ትናንሾቹ የአረብ ኤሚሪቶች ቦታ ይኖራቸዋል።ከዚህ የሰላም ሙከራ ውጭ ወያኔን ወታደራዊ ሀይል አቅራቢ አድርጎ፤ሰው አልባ አውሮፕላን ይዞ ለመዝመት ከሆነ የፈሪ በትር ይሆናል።የኢትዮጵያ ሰራዊትም ከድንበሩ ተሻግሮ በከንቱ አይሞትም።ስለዚህ ህወሃትም መለስ ዜናዊ አንዴ በልቶበት የነበረውን ዘዴ መቀየር ይገባት ነበር።መለስ ትቶት የሄደው ግምብ ራስ ሁሉ ተመልሶ ከዚያው! አዲስ ብልሃት ከየት ይምጣ ? ከሶማሊያም ሌላ የመን ሄዶ የአገራችን ሰው ለምን ይማገድ?ያውም ድንበር በማያስከብር ከሃዲ ቡድን እየተመራ።ማሃይም የህወሃት ጄኔራሎች ቀድመው ይግቡበት።ገንዘቡ ወደነሱ ኪስ ሞቱ ለተራው ወታደር መሆኑ ፍትሃዊ አይሆንም።

የየመንም ጉዳይ ውሉ ከተፈታ ቆየ። አሁን ተተብትቧል።የአየር ድብደባ አይፈታውም።የአየር ድብደባ ቀድሞ ቬትናም በኋለ አፍጋኒስታን አልፈየደም።በዚህም ግጭት የአውሮፓ፡ቻይና ሩሲያና የህንድ ሚና ካአሜሪካ ይሻላል።ላሁን ፍጥጫው የጥይት ድምጹ ሞቱ ስደቱ መቆሚያው አይታይም።

ቻይና የዛሬ አርባ አምስት ዓመታት፡ እኤአ 1970 መጀመሪያ ታንዛም የባቡር መስመርን በምስራቅ አፍሪካ ዘርግታለች።ይህ የባቡር መስመር ታዛንያን እና ዛምቢያን የሚያገናኝ  1710 ኪሎ ሜትር የሚደርስ በስድስት ዓመት ያለቀ ነው። ይህን ተግባር የምናነሳው የቻይናን አፍሪካን በጇ ማድረግ ስራ ቀደም ያለ እቅድ ያለው እንዳአማሪካ አንዴዚህ  አንዴዛ እንዳልሆነ ለማሳየት ነው።ዛሬ ቻይና በአፍሪካ ተንሰራፍታለች።ለአምባ ገነኖች የጡት እናት እየሆነችም ቢሆን። ስለዚህ ኦባማ የአፍሪካን ወዳኝነት ለማግኘት ከሆነ ዉሻ ከሄድ ጅብ ጮኸ ነው።አምባ ገነኖቹንም ብዙ ገንዘብ ስላስለመደቻቸው ክፍያው ይበዛባቸዋል።ቻይናን ካፍሪካ ዘወር በይ የሚል የማን ወንድ፡ ነው?

ታዴያ የዲሞክራሲያዊ እና የሰብአዊ መብት ረገጣው ላይ ከመሳለቅ በተቀረ ከላይ ባነሳናቸው ጭብጦች ተነስተን የኦባማ ጉዞ ምን ይፈይዳል?ኬንያ ዘመድ ጥየቃ ቢያደርጉ መልካም ነው።ናይሮቢ ኤሌትሪክ አለ ስልክ ይሰራል ውሃ አለ። በጠቅላላው ካአዲሳባ ይልቅ ይመቻቸዋል። እዚያ ብቻ ቢሄዱ መልካም ነበር። ቱሪናፋን በስዋሂሊ ብችለው ደስ ይለኝ ነበር።

 

ኢትዮጵያን አምላክዋ ይጠብቃታል:: እብሪተኞችን ያንበረክካል!

በግፍ የታሰሩ ጋዜጠኞች፡የሀይማኖት መሪዎችን፡ የፖለቲካ መሪዎችን ለማስፈታት እንጩህ! የፍርድ ያለህ ! የነጻነት ያለህ!

ህወሃትን ከምድር ገጽ አጥፍተን ሽብርተኛ ዝር እማይልባትን ኢትዮጵያ እንገነባለን!

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

 

The post ኦባማን የኢትዮጵያ መንገዳቸው ቱሪናፋ አያደ ርጋቸውም ? – ከቢላል አበጋዝ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ –ኮርኩማ አፍሪካ

$
0
0

የኢትዮጵያ ሙዚቃ አብዮተኛ ቴዲ አፍሮ አዲሱን ነጠላ ዜማ ለሕዝብ ለቀቀ:: ቴዲ በዋሽንግተን ዲሲ የፊታችን ሐሙስ ጁላይ 2 ያለው ሲሆን አዲሱ ነጠላ ዜማው ከወዲሁ የሶሻል ሚዲያውን አጥለቅልቆታል::

በስጋት ቀፎን ተይዞ እስራት
አዋቂው ሸሽቶ ረሃብ ነግሶ ርዛት
በምድሯ ሊቆይ ማንስ ይደፍራል
ታንኳ ላይ ወጥቶ ወንዝ ይሻገራል
አለቀ ሰዋ ባህር ገብቶ ሄዶ(4×)
………

ውሃ ቢገባ በአፍሪካ መርከብ
አቤት ቢል ተጓዥ ሃሳብ ለማቅረብ
ይሰምጣል እንጂ ከባህር አብሮ
ቀዛፊው ላሳብ አይሰጥም ቶሎ
……….

ዮንጂ ከረ
ቤቴ ኖረ
ወጥቶ ቀረ
ግዶ ግዶ
ወይ ግዶ ወይ ግዶ
………..

ኮርኩማ ኮርኩማ ወንዝ አሻገረችው
ኮርኩማ አፍሪካ
የንን የሰው ጫካ
ኮርኩማ አፍሪካ
ባዶ አደረገችው
ኮርኩማ አፍሪካ
የሚለውን አዲሱን የቴዲ ነጠላ ዜማ ዘ-ሐበሻ እነሆ ትላለች::

teddy afro

The post ቴዲ አፍሮ አዲስ ነጠላ ዜማ ተለቀቀ – ኮርኩማ አፍሪካ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአንዋር መስጊድ ደማቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲሰማ ዋለ * “ኮሚቴውን በነጻ ከመልቀቅ የተሻለ አማራጭ የለም”

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ትናትም ዛሬም “ኮሚቴው ነፃ ነው.. በነፃ ይሰናበት” እያሉ ፍትህን የሚጠይቁ ሙስሊሞች በአንዋር መስጊድ ደማቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲያሰሙ ዋሉ:: በተያዘው የረመዳን ጾም የሕወሓት መንግስት ካንጋሮው ፍርድ ቤት እስር ቤት ባሉት የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ፍርድ ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቶ የነበረ ቢሆንም ላልተወሰነ ጊዜ ማራዘሙ መዘገቡ ይታወሳል::

ዛሬ በአንዋር መስጊድ እና በተመረጡ የክልል ከተሞች በተደረገው በዚሁ የድምፃችን ይሰማ ተቃውሞ ሕዝቡ መፈክሩን በመያዝ በየመስጊዱ ኮሚቴውን በነጻ ከመልቀቅ የተሻለ አማራጭ የለም ሲል በአንድ ድምጽ ሲያሰማ ውሏል::

“የተከሰሰነው ነው እኛ ነን:: በነፃ ከማሰናበት ውጭ ያነሰን ብይን ያለ አማራጭ አንቀበልም” ያሉት ሕዝበ ሙስሊሙ ማህበረሰብ አባላት መንግስትን አሁንም በሰላማዊ መንገድ ፍትህ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል::
muslim addis abeba

muslim addis 2

muslim addis

muslim

The post በአንዋር መስጊድ ደማቅ ሰላማዊ ተቃውሞ ሲሰማ ዋለ * “ኮሚቴውን በነጻ ከመልቀቅ የተሻለ አማራጭ የለም” appeared first on Zehabesha Amharic.

5 የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ኤርትራ ገብተው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቀሉ

$
0
0

agazi
(ዘ-ሐበሻ) የአማራ ብሔር ተወላጆች የሆኑ 5 የአጋዚ ጦር አባላት የነበሩ የስርዓቱ ታጋዮች የሕወሓትን መንግስት በመክዳት አስመራ ገቡ:: እነዚሁ 5 ታጋዮች ኤርትራ የሚገኘውን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቅለዋል::

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሰላማዊ ትግል ይታገሉ የነበሩም ሆነ የሕወሓት ጦርን ሲያገለግሉ የነበሩ በርካታ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን በመምረጥ ወደ ኤርትራ በመሄድ የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን እየተቀላቀሉ መሆኑን ለዘ-ሐበሻ የሚደርሱ መረጃዎች ያመለክታሉ::

ሰሞኑን ይህንኑ ንቅናቄ የተቀላቀሉት 5ቶ የአጋዚ ጦር አባላት

1ኛ. ግራማ ተላይነሕ
2ኛ. ሄኖክ እንዳልካቸው
3ኛ ስለሺ ተስፋሁን
4ኛ. ምርት ይሁን መንገሻ
5ኛ ስማቸው ካሴ ይባላሉ።

The post 5 የአጋዚ ክፍለጦር አባላት ኤርትራ ገብተው የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄን ተቀላቀሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቶ አስገደ ገ/ሥላሴ አዲሱ “የመለስ ራዕይ ሲፈተሽ”መጽሐፍ በአሜሪካ መሸጥ ጀምሯል – (የት እንደሚገኝ እንጠቁምዎ)

$
0
0

አቶ አስገደ ገብረሥላሴ የ’መለስ ራዕይ ሲፈተሽ’ የሚል መጽሐፍ ማሳተማቸው ይታወሳል:: መጽሐፉ በሰሜን አሜሪካም ለገበያ የቀረበ ሲሆን የት ቦታዎች እንደሚገኝ ፎቶ ግራፉ ላይ በመጫን ማየት ትችላላችሁ::
asegede gebresilase

The post የአቶ አስገደ ገ/ሥላሴ አዲሱ “የመለስ ራዕይ ሲፈተሽ” መጽሐፍ በአሜሪካ መሸጥ ጀምሯል – (የት እንደሚገኝ እንጠቁምዎ) appeared first on Zehabesha Amharic.

7 ኢትዮጵያውያን በደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ጥገኝነት ጠየቁ

$
0
0

airplane

ህጋዊ መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነድ አልያዙም ተብሏል
– የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአ/አ ስንነሳ ህጋዊ ሰነድ ነበራቸው ብሏል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በአየርላንድ ርዕሰ መዲና ደብሊን በኩል ወደ አሜሪካ ሎሳንጀለስ የጀመረውን አዲስ በረራ ለማስመረቅ ባለፈው ቅዳሜ ከአዲስ አበባ በመነሳት ባደረገው ጉዞ፣ ተሳታፊ የነበሩ 7 ኢትዮጵያውያን መንገደኞች፣ አውሮፕላኑ ደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ሲያርፍ ወደ ኢሚግሬሽን ክፍሉ አምርተው ጥገኝነት መጠየቃቸውን አይሪሽ ኢንዲፔንደንት ትናንት ዘገበ፡፡ሁለት ህጻናትን ጨምሮ ጥገኝነት የጠየቁት 7 መንገደኞች በአየር ማረፊያ ጣቢያው ሲደርሱ ምንም አይነት መታወቂያ ወይም የጉዞ ሰነዶችን አልያዙም ነበር ያለው ዘገባው፣ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቃል አቀባይ ግን፣ በአውሮፕላኑ ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎች በሙሉ ከአዲስ አበባ ሲነሱ ህጋዊ ሰነዶችን ይዘው ነበር፣ ስለ ጥገኝነት ጠያቂዎቹ የግል ጉዳይ ግን አስተያየት መስጠት አንፈልግም ብለዋል፡፡
አየር መንገዱ ላለፉት ከ40 በላይ አመታት ወደ አውሮፓ አገራት በረራ ሲያደርግ መቆየቱን ያስታወሱት ቃል አቀባይዋ፣ የምናጓጉዘው የተሟላ ህጋዊ የጉዞ ሰነድና ተገቢ ቪዛ ያላቸውን መንገደኞች ብቻ ነው ሲሉ መናገራቸውንም ዘገባው ገልጧል፡፡አንድ የአገሪቱ የህግ ክፍል ቃል አቀባይም የተለያዩ አገራት መንገደኞች በደብሊን አየር ማረፊያ ጣቢያ ሲደርሱ ጥገኝነት መጠየቃቸው የተለመደ የዘወትር ክስተት ነው፣ ባለፈው አመት ብቻ 221 መንገደኞች ለትራንዚት አርፈው ጥገኝነት ጠይቀዋል ብለዋል፡፡

The post 7 ኢትዮጵያውያን በደብሊን አውሮፕላን ማረፊያ ጥገኝነት ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፀሃፍ፦ አሰባሳቢ ማንነት፣ ባንድ ሃገር ልጅነት የኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ፀሃፊ፦ ዩሱፍ ያሲን ምስክርነት፦ (በጥላሁን አፈሣ)

$
0
0

Download (PDF, 162KB)

Yasu Yasinመንደርደሪያ ሃሳብ የዛሬ ሁለት ዓመት አካባቢ ይመስለኛል። “For Love of Country: Debating The Limits of Patriotism” በሚል ርዕሥ እንደ ኤውሮፓ አቆጣጠር(“እ.ኤ.አ”)በ 1996 ዓ.ም፣ የተጻፈች አንዲት ትንሽ መጽሐፍ በርዕሷ ተስቤ፣ ከአሮጌ መጽሃፍት ተራ ገዝቼ ያነበብኩት። እዚች መጸሃፍ ላይ ለሰፈሩት የተለያዩ ምሁራን አስተያየቶች መንስኤ የሆነችው፤ Martha Nussbaum የተባለች ታዋቂ ምሁር፣ ከዚች መጽሃፍ እትመት ሁለት ዓመታት ቀደም ብላ፣ “Patriotism and Cosmopolitanism” በሚል ርዕስ በቦስተን ሪቪው ላይ ያሳተመቻት አንዲት 25 ገጾች ያዘለች መጻጽፍ ነበረች። ፕሮፌሰር ኑስቦም፣ በጽሁፏ ላይ ያሰፈረችው አሟጋች አስተያየት ባጭሩ ሲጠቃለል፦ ያለንባት ዓለም እየተዋሃደች በመጣችበት በአሁኑ ዘመን፣ በተለምዶ ከያዝነው ጠባብ የአገር ወዳድነት (patriotism)እምነታችን ተላቀን፣ እራሳችንን በሰው ዘርነታችን ብቻ የምንገልጽበት የአንዲቷ ዓለማችን ዜጎች (cosmopolitan)አርገን መቀበል ይገባናል ነበር የሚለው።

—[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

The post ፀሃፍ፦ አሰባሳቢ ማንነት፣ ባንድ ሃገር ልጅነት የኢትዮጵያ እጣ ፋንታ ፀሃፊ፦ ዩሱፍ ያሲን ምስክርነት፦ (በጥላሁን አፈሣ) appeared first on Zehabesha Amharic.


እነዋሽንግተን ፖስት የኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት አብጠለጠሉ – Addis Admass

$
0
0

Obama Ethiopiaአለማየሁ አንበሴ

“የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ስለዲሞክራሲ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል”

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በቀጣዩ ሐምሌ ወር ኢትዮጵያን ይጐበኛሉ መባሉን ተከትሎ ታላላቅ አለማቀፍ ሚዲያዎችና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቸ ተቋማት ተቃውሞአቸውን እየገለፁ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ፤ ፕሬዚዳንቱን እንዲመጡ የሚያደርጋቸው የአገራችን የውስጥ ስኬት ነው ሲል ተቃውሞውን አጣጥሎታል፡፡ የኦባማ ወደ ኢትዮጵያ መምጣትን ርዕሰ ጉዳያቸው ካደረጉ የአሜሪካ ሚዲያዎች አንዱ የሆነው ዘ ዋሽንግተን ፖስት በርዕሰ አንቀፁ ባሰፈረው ተቃውሞ፤ “የኦባማ ኢትዮጵያን መጐብኘት ስለዲሞክራሲ የተሳሳተ መልዕክት ያስተላልፋል” ብሏል፡፡ በእንግሊዝ ከፍተኛ ተሰሚነትና ተነባቢነት ያለው ዘ ጋርዲያንም ጉብኝቱን አስመልክቶ በርዕሰ አንቀፁ ባሰፈረው ሃተታ፤ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ዲሞክራሲያዊ ላልሆኑ ስርአቶች እውቅና መስጠት ነው ሲል ክፉኛ ተችቷል፡፡ ኦባማ ጋናን በጎበኙበት ወቅት፤ “መጀመሪያ የምንደግፈው የተጠናከረ ዲሞክራሲያዊ መንግስትን ነው” በሚል የተናገሩትን ዘንግተውታል ያለው ዋሽንግተን ፖስት፤ የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ኢትዮጵያን የመሳሰሉ በሰብአዊ መብት ረገጣ ለሚታሙ ሃገራት እውቅናና ከለላ መስጠት ነው ሲል ተቃውሟል፡፡ “በቅርቡ ሠላማዊና ዲሞክራሲያዊ የመንግስት ሽግግር ያደረገችው ናይጄሪያን የመሳሰሉ በዲሞክራሲ ጐዳና ላይ እየተጓዙ ላሉ ሀገራት እውቅና መንፈግ ነው” ሲልም የታቀደውን የኢትዮጵያ ጉብኝት ጋዜጣው አብጠልጥሎታል፡፡ ጉብኝቱ ኢትዮጵያና አሜሪካ ያላቸውን የዘመናት ግንኙነት እንዲሁም ሃገሪቱ በቀጠናው ያላት የፀጥታ አስከባሪነት ሚናና ፈጣን የኢኮኖሚ እድገቷን ታሳቢ ያደረገ ነው መባሉን ያስታወሰው ዋሽንግተን ፖስት፤ የሀገሪቱ መንግስት በዚያው ልክ ነፃ ሚዲያ የማያበረታታ እንደውም ያሉትንም እያጠፋና የፖለቲካ ጫናዎች እያሳደረ የሚገኝ መሆኑን ጠቅሶ ጉብኝቱን ተቃውሟል፡፡

ባለፈው ዓመት ከሰኔ ወር ጀምሮ 34 ጋዜጠኞች ከሀገር እንዲሰደዱ መደረጋቸውን ጋዜጣው ጠቁሞ፣ ሃገሪቱ ጋዜጠኛ አሳሪ በመባል ከሚታወቁ የአለም ሀገራት በቀዳሚነት መሰለፏን ጠቅሶ የኦባማን ጉብኝት ተችቷል፡፡

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዊንዲ ሸጋርማን በቅርቡ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት “ኢትዮጵያ ዲሞክራሲዋን እያጠናከረች ነው፣ የምታከናውነው ምርጫም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ ነው” የሚል ምስክርነታቸውን በሰጡ ማግስት፣ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት የምርጫ ውጤቱን ከ99.6 በመቶ ወደ መቶ በመቶ ማሳደጉ፣ ዲሞክራሲውን ጥያቄ ውስጥ ከትቶታል ሲል ነቅቷል ዋሽንግተን ፖስት፡፡በዘንድሮ ምርጫ ተቃዋሚዎች እንግልትና እስራት እንደተፈፀመባቸው፣ አለማቀፍ ታዛቢዎች ምርጫውን እንዳይታዘቡ መከልከላቸውን፣ በምርጫው ማግስትም ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አንድ የተቃዋሚ ፓርቲ እጩ ተወዳዳሪ የነበሩ ፖለቲከኛ እንደተገደሉ የጠቀሰው ጋዜጣው፤ ሆኖም መንግስት ስለተገደሉት ሰዎች ኃላፊነት አልወሰደም ብሏል፡፡ የተረጋጋ፣ ሰላማዊና በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ምርጫ ያካሄደችው ናይጄሪያ እያለች ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን መጎብኘታቸው ለለውጥ ላልተዘጋጀው የኢትዮጵያ መንግስትና ለአሳፋሪው
የምርጫ ውጤት እውቅና መስጠት ነው ያለው ዋሽንግተን ፖስት፤ ለአፍሪካውያንም ዲሞክራሲ ጠቃሚ አይደለም የሚል መልዕክት ያስተላልፋል ሲል ጉብኝቱን አጥብቆ ተቃውሟል፡፡ ታዋቂው የእንግሊዝ ጋዜጣ ዘ ጋርዲያን በበኩሉ፤ የኦባማ ኢትዮጵያን መጎብኘት ለጨቋኝ መንግስት ስጦታ ነው ሲል ፅፏል፡፡ “ሃገሪቱ በኢኮኖሚ እያደገች ቢሆንም በዜጎች ሰብአዊ መብት አያያዝና በፕሬስ ነፃነት እንዲሁም ዲሞክራሲያዊ ምርጫ በማካሄድ በኩል ተወቃሽ ነች፣ የዲሞክራሲ ተምሳሌት ልትሆንም አትችልም” ብሏል ጋዜጣው በርዕሰ አንቀፁ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችም የፕሬዚዳንቱን የኢትዮጵያ ጉብኝት አበክረው ተቃውመዋል፡፡ “የኢትዮጵያ ምርጫ በአፈና ስር ያለ የፖለቲካ ልምምድ ነው”

ያለው ‹ፍሪደም ሃውስ› የተሰኘ የሰብዓዊ መብት ተቆርቋሪ ቡድን፤ የኦባማ ጉብኝት ለፖለቲካና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መቀጨጭ አጋርነትን ማሳየት ነው ሲል በመግለጫው ተችቷል፡፡ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር አቶ ሬድዋን ሁሴን፤ አንዳንድ ወገኖች የኦባማን ወደ ኢትዮጵያ መምጣት እየተቃወሙ መሆኑን እንደሚያውቁ ጠቁመው፤ ፕሬዚዳንቱን እንዲመጡ የሚያደርገው የሀገራችን የውስጥ ስኬት ነው ብለዋል፡፡

“የኦባማ መምጣት ትልቅ ትርጉም አለው” ያሉት አቶ ሬድዋን፤ ፕሬዚዳንቱ ኢትዮጵያን ለመጐብኘት የማቀዳቸው ሚስጥር የኢኮኖሚ እድገቱ እንዲሁም ሀገሪቱ ለሠላም እያበረከተች ያለው አስተዋጽኦ ስኬታማና አይነ ግቡ መሆኑ ነው ብለዋል፡፡ “በ112 አመታት የዲፕሎማሲ ታሪክ የአሜሪካ 44ኛው ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ ኢትዮጵያን መጐብኘት ትልቅ የገጽታ ግንባታ ይኖረዋል፤ ቤታችን መጽዳትና መሞቅ መጀመሩንም ያረጋግጣል” ብለዋል ሚኒስትሩ፡፡

Source: Addis Admass Newspaper

The post እነዋሽንግተን ፖስት የኦባማን የኢትዮጵያ ጉብኝት አብጠለጠሉ – Addis Admass appeared first on Zehabesha Amharic.

ፕሬዝደንት ኦባማ ጉዞአቸዉን እንዲሰርዙ ለመጠየቅ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ

$
0
0

ቃልዎን ጠብቆ መገኘት

“እፍሪካ ጠንካራ የዲሞክራሲ ተቋም እንጂ ጠንካራ አምባገነን መሪ አያስፈልጋትም”

የአሜሪካ ፕረዝዳንት ባራክ ኦባማ በመጭው ሀምሌ ወር ኢትዮጵያን ለመጎብኘት የያዙት ፕሮግራም ስለህዝቦች ሰብአዊ መብት መገፈፍ የሚናገሩት ለይስሙላ እንጂ በተግባር ግድ እንደማይሰጣቸው ያሳያል። ዜጎችን በመጨቆን፣ ጋዜጠኞችን በማሰር፣ የዉሸት ምርጫ በማካሄድ፣ የተቀናቃኝ ፓርቲዎችን በማፈራረስ እና አባሎቻቸዉን በማሰር እንዲሁም በመግደል፣ የአገርን ሃብት ለጢቂቶች መበልጸጊያ በማድረግ፣ አብዛኛዉን ምስኪን ዘጋ ተስፋ አቶ ካገር እየተሰደድ ለሞትና ለባርነት በመዳረግ ወዘት የሚያዉቁትን የወያኔ ኢሃደግ ስርኣትን እንደመልካም የአፍሪካ አስተዳደር ቆጥሮ መጨባበጥ እና በቤተመንግስት መገባበዝ አግባብ እንዳልሆነ አስቀድሞ ለማሳሰብ እና ጉዞአቸዉን እንዲሰርዙ ለመጠየቅ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ

ቀን   አርብ ጁላይ ፫
ሰአት   ፱ ኤ ኤም
ቦታ   ሗይት ሃውስ

 

protest-against-obama-visit-628x941

The post ፕሬዝደንት ኦባማ ጉዞአቸዉን እንዲሰርዙ ለመጠየቅ የተጠራ ሰላማዊ ሰልፍ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ የሚሳተፉ ከተለያዩ የካናዳና የአሜሪካ ከተሞች የመጡ ቡድኖች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ በፎቶ ግራፍ::

$
0
0

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ የሚሳተፉ ከተለያዩ የካናዳና የአሜሪካ ከተሞች የመጡ ቡድኖች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ በፎቶ ግራፍ::

11214209_897954850276722_4524430455891172151_n - Copy 11228121_897954766943397_4460564768293891951_n - Copy 1506069_897954783610062_4937945577979240180_n - Copy 11403234_897954980276709_8091184175990810284_n - Copy 11692648_897954726943401_22432999789610882_n - Copy 11659455_897954570276750_4538163869172761761_n - Copy

The post የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌስቲቫል በሰሜን አሜሪካ የሚሳተፉ ከተለያዩ የካናዳና የአሜሪካ ከተሞች የመጡ ቡድኖች ራሳቸውን ሲያስተዋውቁ በፎቶ ግራፍ:: appeared first on Zehabesha Amharic.

32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በሜሪላንድ በድምቀት ተከፈተ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በሰሜን አሜሪካ በየዓመቱ የሚደረገው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫል ዛሬ በሜሪላንድ በርድ ስታዲየም በርካታ ኢትዮጵያውያን በተገኙበት በድምቀት ተከበረ::

ethiopia soccer 4

ethiopia soccer 3

ethiopia soccer 2

ethiopia soccer 1

ከአሜሪካ እና ከካናዳ የመጡ ከ30 በላይ ቡድኖች በስታዲየሙ በመገኘት በዚሁ በመክፈቻ ዝግጅት ላይ ራሳቸውን አስተዋውቀዋል:: በዚህ ዝግጅት ላይ ለእንግሊዙ አርሰናል ክለብ እየተጫወተ የሚገኘው ጌድዮን ዘላለም የተገኘ ሲሆን ከሕዝቡም ደመቅ ያለ አድናቆት ተችሮታል::

በዚሁ የመክፈቻ ዝግጅት የፌደሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ተስፋዬ ባሰሙት ንግግር የዘንድሮው ዝግጅት በርካታ ሕዝብ በመገኘት በመከፈቱ መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት ደማቅ ዝግጅቶች እንደሚኖሩ ጠቁመዋል:: እንደ ፕሬዚዳንቱ ገለጻ ረቡዕ ምሽት የብሄራዊ ትያትር 60ኛ ዓመት በዓል በታሪካዊ ሁኔታ ይከበራል; የፊታችን ሐሙስ አርብና ቅዳሜም ከ እግር ኳሱ በተጨማሪ ታላላቅ አርቲስቶች የሚገኙባቸው ትልልቅ የሙዚቃ ኮንሰርቶች እንደተዘጋጁና ሕዝቡም በነዚህ ስፍራዎች እየተገኘ እንዲዝናና ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

የዘንድሮው የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን 32ኛ ዓመት በዓል መታሰቢያነቱ በሊቢያና በደቡብ አፍሪካ ላለቁት ኢትዮጵያን መታሰቢያ እንደሆነ የገለጹት ፕሬዚዳንቱ የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎች ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዋል:: የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተወካይ ባሰሙት ንግግር የሊቢያውን ሰቆቃ አስታውሰው “እግዚአብሔር ኢትዮጵያን አይረሳትም” ብለዋል::

የመድሃኔዓለም ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ተወካይ ቄስ በሪሁን መኮንን በሊቢያው ሰቆቃ ሊያስተምረን ስለሚገባ ነገር ተናግረዋል:: የሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ልዩነት ሳይበግራቸው በአንድነት በመቆም ሊሰሩ እንደሚገባ ይህ ሃዘን አስተምሮናል ብለዋል:: በሰሜን አሜሪካ የሙስሊም ኮሙዩኒቲ ተወካይ ሼክ ሱለይማን ነስረዲን በበኩላቸው በሊቢያ የተገደሉት ወገኖች የተገደሉት ክርስቲያን በመሆናቸው ሳይሆን ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው ነው ሲሉ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የሃይማኖቶች መከባበር ለመጠቆም ሞክረዋል::

በዛሬው የመክፈቻ ጨዋታ የላስቬጋሱ አበበ ቢቂላ የሲያትሉን ዳሸን 2ለ0 – ዴንቨር የሚኒሶታውን ኒያላ 4ለ0 – ቺካጎ ፒላደልፊያን 2ለ1 – ኦሃዮ ቦስተንን 4ለ1 ሲያሸንፉ የሎሳንጀለሱ ዳሎል የዲሲው ዩናይትድ 1ለ1 እንዲሁም የሎሳንጀለሱ ስታርስ ከሜሪላንዱ ከቅዱስ ሚካኤል ጋር 1ለ1 ተለያይተዋል::

ethiopia soccer 5
በሌላ በኩል የፌዴሬሽኑ ዋና ጸሃፊ አቶ ያሬድ ነጋሽ ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት በዛሬው የመክፈቻ ዝግጅት መደሰታቸውን ገልጸው በቀጣይ ቀናት በርካታ ሰው እንደሚገኝ ያላቸውን ግምት ገልጸዋል:: በሃይማኖት አባቶቹ መል ዕክት መደሰታቸውንም ገልጸዋል::

በድምቀት የተከፈተው የኢትዮጵያውያን የስፖርት እና የባህል ፌስቲቫልን በስፍራው የሚገኙት የዘ-ሐበሻ አዘጋጆች በየቀኑ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ ይዘግቡላችኋል::

The post 32ኛው የኢትዮጵያውያን የስፖርትና የባህል ፌስቲቫል በሜሪላንድ በድምቀት ተከፈተ appeared first on Zehabesha Amharic.

የህብር ሬዲዮ ሰኔ 21 ቀን 2007 ፕሮግራም 32ተኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ቬስቲቫል በደማቅ ሁኔታ መከፈትን አስመልክቶ ውይይት ከጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ እና ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር የመክፈቻውን ስነ ስርዓት በተመለከተ ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡት)

$
0
0

Habitamu<…የእንግሊዝ መንግስት ያወጣው መግለጫ በዓለም ዙሪያ የኢትዮጵያውአን ያላሰለሰ አቤቱታ ውጤት ነው። ወያኔ ያንን ተከትሎ ደህና ነው ማለቱ የሚታመን አይደለም ደህና ከሆነ ለምን አያሳዩትም …ለመጀመሪያ ጊዜ ለእንግሊዟ ንግስት ኤልሳቤት ደብዳቤ አስገብተናል ክርክራችን አቤቱታችን ከእንግሊዝ መንግስት ጋር ነው ይህንኑ ደብዳቤ ሰሞኑን…>  ወ/ሮ ብዙአየሁ ጽጌ የአቶ አንዳርጋቸው ታላቅ እህት የእንግሊዝ የውጭ ጉዳይ ማስጠንቀቂያን ተከትሎ የኢትዮጵያው አገዛዝ በሰጠው ምላሽ ላይ አነጋግረናቸው ከሰጡን  (ሙሉውን ያዳምጡ)

<…ሕወሃት የፕ/ት ኦባማ መምጣት የምርጫችንን ዲሞክራሲያዊነት ያሳያል እያለ ሲቀሰቅስ ሕዝቡ ግድ አልሰጠውም …የኦባማ መምጣት የስርዓቱን አፈና የሚያበረታታ ነው ባይመጡ ጥሩ ነበር የግድ ከመጡ ግን ለስርዓቱ ጠበቅ ያለ ማስጠንቀቂያ መስጠት አለባቸው። በውጭ ያለው ወገን ኦባማ እንዳይመጡ የሚያደርገው ጥረት መቀጠል አለበት…>

አቶ አምዶም ገ/ስላሴ የአረና የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ  የፕ/ት ኦባማ አፈና ወደ ነገሰባት ኢትዮጵያ ይሄዳሉ መባሉን በተመለከተ ከተናገረው( ሙሉውን ቃለ ምልልስ ያዳምጡ)

የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ውስጥ ስለሚካሄደው የሰብአዊ መብት ረገጣ በተመለከተ አርብ ዕለት ያወጣው ዓመታዊ ሪፖርት ዳሰሳ

<<በኢትዮጵያ ውስጥ የጸጥታ ሀይሎች ከሕግ በላይ ናቸው። በአገሪቱ ውስጥ ስለመብት መከበር መጠየቅ የሕይወት ዋጋ ያስከፍላል >> የስቴት ዲፓርትመንት ሪፖርት (ልዩ ዳሰሳ)

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻን ሕጋዊነት ማጽደቁ የአገሪቱን ማህበረሰብ ከሁለት ከፍሎ ማወዛገቡና ዓለም አቀፍ አንድምታው

አክራሪው አይሲስ ሰሞኑን አራት ግብረ ሰዶማውያንን በዘግናኝ ሁኔታ መግደሉን ይፋ ማድረጉ

<<ግብረ ሰዶሞችን ካልተቀበላችሁ እያሉ በእርዳታ ስም የሚያስፈራሩን እኚህ ፕ/ት ባራክ ኦባማን ለመሆኑ ማን ነው የወለዳቸው ? እዚህ አገር ዮሃንስን ከዮሃንስ ጋር ማሪያን ከማሪያ ጋር ማጋባት በጭራሽ አይሞከርም>> የዙምባብዌው ፕ/ት ሮበርት ሙጋቤ( ልዩ ጥንቅር)

የባሻ ይገዙ ትዝብት በተመሳሳይ ጾታ ጋብቻ ላይ (ግጥም)

 ሌሎችም

ዜናዎቻችን

የሕወሓት መሪዎች የአዲስ አበባና የትግራይ በሚል በሁለት ተማድነው በስልጣን ሽኩቻ ላይ መሆናቸው ተገለጸ

የአቶ አንዳርጋቸው ልጅ በወላጅ አባቷ መታሰር ዙሪያ ለንደን ውስጥ ተውኔት ተጫወተች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አትሌት ከድል በሁዋላ በጉልበት ሰጭ እጽ ሳቢአ ከአውሮፓ ውድድር ታገደች

የታንዛኒያ ፖሊስ ከአምስት የተለያዩ ምዕራብ አገሮች የሄዱ ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር አዋለ

የፕ/ት ባራክ ኦባማ የኢትዮጵያ ጉብኝት እቅድ ላይ ተቃውሞው እንደቀጠለ ነው

የሙስሊሙ ማህበረሰብ በአገዛዙ የፍርድ ቤት ድራማ ከዋናው የትግሉ መነሻ ጥያቄ እንደማያፈገፍግ ገለጸ

ሁበርና ሊፍት በቬጋስ በሴፕተምበር ስራ ይጀምራሉ ተባለ

የኬኒያ መንግስት ከኢትዮጵያ የሚያገኘውን የኤሌክትሪክ ሀይል ለጎረቤቶቹ አሳልፎ እንደሚሸጥ አስታወቀ

 ሌሎችም ዜናዎች አሉ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ  ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 630 ሰዓት እስከ 8  ሰዓት ህብር ሬዲዮ ድህረ ገጽ ወይም በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው በእንግሊዝ ለምትኖሩ 01405770140 በስልክ ማዳመጥ ይቻላል። ዘወትር በድህረ ገጻችንና በዘሐበሻ እንዲሁም በተጠቀሱት ስልኮች ማዳመጥ ይቻላል።

The post የህብር ሬዲዮ ሰኔ 21 ቀን 2007 ፕሮግራም 32ተኛው የሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያውያን የስፖርት ቬስቲቫል በደማቅ ሁኔታ መከፈትን አስመልክቶ ውይይት ከጋዜጠኛ ሔኖክ አለማየሁ የዘ-ሐበሻ ዋና አዘጋጅ እና ከጋዜጠኛ ነጻነት ሰለሞን ጋር የመክፈቻውን ስነ ስርዓት በተመለከተ ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡት) appeared first on Zehabesha Amharic.

‎ወኪሎቻችንን‬ በነጻ ከማሰናበት ያነሰ አንዳችም ብይን አንቀበልም! –ድምጻችን ይሰማ የተሰጠ ማሳሰቢያ!

$
0
0

11659418_872378946176521_8166061036471164171_nኮሚቴዎቻችን ላይ የሚተላለፈው ውሳኔ ቀጣይ የትግል አቅጣጫችንን የሚቀርፅ ጉዳይ  ቢሆንም በራሱ ግን የትግላችን መዳረሻ አይደለም፡፡ ትግላችን ከመነሻው የተገነባው፣ በሂደትም የውድ ኮሚቴዎቻችንን እስርና እንግልት ጨምሮ በርካታ መስዋእትነት የተከፈለበት የተሸራረፉ መብቶቻችንን በማስከበርና የእምነት ነፃነታችንን በህገ መንግስቱ  መሰረት በማረጋገጥ ዓላማ ላይ ተመስርቶ ነው፤ ይህ ዛሬ አንስተነው ነገ የምንቀይረው  መፈክር፣ አልያም በሌሎች አጀንዳዎች የሚዋጥና የምንዘነጋው ጉዳይ ሳይሆን  ለተፈፃሚነቱ አስፈላጊውን ሁሉ መስዋእትነት የምንከፍልበት ትግላችን የተጠረገበት ጎዳና ነውና! ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል! ድምጻችን ይሰማ! አላሁ አክበር!

The post ‎ወኪሎቻችንን‬ በነጻ ከማሰናበት ያነሰ አንዳችም ብይን አንቀበልም! – ድምጻችን ይሰማ የተሰጠ ማሳሰቢያ! appeared first on Zehabesha Amharic.

ለዋይት ሃውስ ይደውሉ፣ ፋክስ ይላኩ (የመጀመሪያ ዙር)

$
0
0

እንደሚታወቀው የአሜሪካኑ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ በዚህ ወር መጨረሻ ለጉብኝት ወደ ኬንያ ሲሄዱ ኢትዮጵያ ጎራ የማለት እቅድ እንዳላቸው ተገልጿል። ይሁንና የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ከጥቅሙ ጉዳቱ የሚያመዝን በመሆኑ ነጻነት ናፋቂ የሆነውና በአለም ዙሪያ ተበትኖ የሚገኘው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ወደ ዋይት ሃውስ በመደወል እንዲሁም ፋክስ በማድረግ
በትህትና ፕሬዚዳንቱ ለዜጎቿ ምድራዊ ሲኦል እንድትሆን የተደረገችውን አገራችንን መጎብኘት አንባገነኖችን እንደማበረታታት ሊቆጠር ስለሚችል ድምጻችንን በስፋትና በተከታታይ እናሰማ። ከዚህ በታች ያለውን ደብዳቤ ስምና አድራሻችሁን በመጻፍ ፋክስ ብታደርጉ፣ እንዲሁም በማህበራዊ ድረገጾች በስፋት በማሰራጨት ትብብር እንድታደርጉ በትህትና እጠይቃለሁ።
ስልክ ለመደወል በስራ ሰአት በ +1 (202) 456–1414 ይደውሉ ask to talk to Denis McDonough, The President’s Chief of Staff / or leave a message
ፋክስ ለማድረግ +1 202-456-2461 በመጠቀም መልእክትዎን ያድርሱ።

Obama Ethiopia

 

 

The post ለዋይት ሃውስ ይደውሉ፣ ፋክስ ይላኩ (የመጀመሪያ ዙር) appeared first on Zehabesha Amharic.


የዶክተር ነገደን ‘ይድረስ ለግንቦት ከየካቲት’ ካነበብኩ ወዲህ……- ትችት ከብንያም ሰለሞን

$
0
0

ስላለፈውም ስለመጭውም የፖለቲካ ጉዞ በልበ ሙሉነት ትንታኔ ለመስጠት ድፍረት አግኝቻለሁ !!!

ትችት ከብንያም ሰለሞን

Negede-Bookkእንደ አ.አ. በ2014 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲሲ በኤሶፕ አሳታሚ የታተመው ባለ 444 ገጽ አዲስ መጽሃፍ በእኔ ግምት በአገራችን ዘመናዊ የ40 ዓመታት የፖለቲካ ሂደት ለበርካታ ጥያቄዎች መልስ የሚሰጥ መጽሃፍ ነው፡፡ በማንኛውም የእድሜ፣ የእውቀትና የስራ ልምድ ክምችት ላለው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ስለሃገሩ ጠለቅ ያለ እውቀት እንዲኖረው በእጅጉ ይረዳዋል፡፡ እኔ ይችን አጭር አስተያየት የጻፍኩት ስለ መጽሃፍ ግምገማ ሙያና ብቃት ኖሮኝ አይደለም፡፡ አስተያየት መስጠት መመስከር ነውና ከመጽሃፉ ያገኘኋቸው በርካታ ቁም ነገሮች ለረጅም ጊዜ በውስጤ መልስ ሳያገኙ ለኖሩ ጥያቄዎች ያልጠበኳቸውን አጥጋቢ መልሶች እንዳገኝ ስለረዳኝ ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ምንድን ናቸው ? ከመልሴ በፊት መንደርደሪያ ላስቀምጥ፡፡

ከአጼ ኃይለ ስላሴ ንጉሳዊ ስርአትና በደርግ ዘመነ መንግሥት አሁን ደግሞ በትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር አገዛዝ ውስጥ አልፌአለሁ፡፡ ወጣቱን ለለውጥ ፍላጎት አነሳስቶ ሳይደራጅ በስሜት ተነሳስቶ የህዝብ ጥያቄዎችን አንግቦ ሊነሳበት የቻለው ምክንያት ምንድን ነው? አብዮት ብሎ አመጽ ከየት መጣ? ለግብታዊ እንቅስቃሴ ያነሳሳውና የገፋፋው የሃገር ውስጥና ዓለም አቀፋዊ የፖለቲካ ካምፖች ሚና በኢትዮጵያ አብዮት ላይ የነበራቸው ተጽእኖ ምን ነበር? የአጴው ስርአት ተገርስሶ ከወደቀ በኋላ ወታደራዊው ጁንታ ሊተካ የቻለበት ዋና ዋና ምክንያቶች ምንድን ነበሩ? በደርግ ዘመን ውስጥስ ምን ችግሮች ተከሰቱ? የአስራ ሰባት አመቱስ ጦርነት ምን አስከተለ? ኤርትራ እንዴት ልትገነጠል በቃች? የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባርን ለመፍጠር የረዳው ሁኔታ ምን ነበር? ከአንዱ ስርአት ወደሚቀጥለው ስርአት ስንሸጋገር በጎና ክፉ ነበሩ ወይም ናቸው የምንላቸው ነጥቦች ምንድን ናቸው? የወያኔን ነጻ አውጭ ግንባር ለስልጣን ያበቁት የውስጥና የውጭ ችግሮችና አመቺ ሁኔታዎች ምንድን ናቸው? የወያኔ መሪዎች የግላቸው የህይዎት መዋዕል አሁን ለሚከተሉት የአምባገነንነት አመራር ምን አስተዋጽኦ ይኖረው ይሆን?

ለእነዚህና ሌሎች ተያያዥ ጥያቄዎች ጥርት ባለ ቋንቋና ቀላል አገላለጽ የዶክተር ነገደ ጎበዜ መጽሃፍ አጥጋቢ መልሶችን ይዞ ቀርቧል፡፡ በሌሎች መጽሃፍት ውስጥ ያልተዳሰሱና ብዙ ልፋትን የጠየቁ ሥራዎች መሆናቸው ለመጽሃፉ ልዩ ዋጋ ይሰጡታል፡፡

መጽሃፉ ከመግቢያው ሌላ በአራት አበይት ምእራፎች የተከፈለና ዋናውን ትኩረት በኢትዮጵያ ውስጥ የተደረጉ የለውጥ ሙከራዎች ላይ አድርጎ ዘመናዊ ሥልጣኔ ከጀመረበትን ወቅት በመነሳት ብዙ ጊዜ የማናገናዝበውን የወቅቱን ዓለማዊ ሁኔታ ማለትም ከጣልያን ወረራ በፊት የነበረውን የጃፓናይዘርስን የለውጥ ሙከራ እንደ መንደርደሪያ በመጥቀስ የታሪኩን ቅደም ተከተል በዘመን ሂደት ጠብቆ ይተነትናል፡፡

በተለይ በዘመኑ የነበረውን የባእዳን መንግሥታ ስውር ደባና ግልጽ ወረራ፣ እንደዚሁም ለለውጥ የተደረጉ የተለያዩ ሙከራዎች እንዴት እንደተጀመሩና በምን ምክንያት ሊከሽፉ እንደቻሉ ያብራራል፡፡ ብዙ ተስፋ ተጥሎበት የነበረው ሃገሪቱን ዘመናዊ የማድረግ ይህ የመጀመሪያው ጥረት በወረራው ሳቢያ ከሸፈ፡፡ በወቅቱ በይፋ ደረጃ መላው አለም የመንግስታት ማህበርን (ሊግ ኦፍ ኔሽንስን) ውሳኔ አክብሮ ይህንን ወረራ ቢያወግዝም የነበረው ተጨባጭ ሁኔታ ግን ሃያላን የተባሉት በሙሉ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከየራሳቸው ምክንያት እየተነሱ እንግሊዝና ፈረንሳይ ኮሎንያሊስቶች ብቻ ሳይሆኑ ሶቭየቶችም አሜሪካኖችም ከልፈፋቸው ባሻገር በተግባር እንዴት ከወራሪው ጎን ተሰልፈው እንደነበረ፣ በዚህ ሁሉ ትርምስ መሃከል ደግሞ በተጨባጭ መሳሪያ በማቀበል ከሃገራችን ጎን ቆሞ የነበረው አዶልፍ ሂትለር እንደነበረና የነዚህን ሁሉ ምክንያቶች እየዘረዘረ ያስረዳል፡፡

ከዚያም ከወረራው በኋላ የለውጥ ሃሳብ እንደገና እንዴት እንዳንሰራራ፣ የታህሳሳውያን የለውጥ ሙከራ በተለይም በመንግስቱ ነዋይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ውስጥ ተዋናዮቹ እነማን ነበሩ ? አላማቸውስ ምን ነበረ? ሙከራቸው ለምን ከሸፈ? የሚሉትን መሠረታዊ ጥያቄዎች በጥልቀት ይፈትሻል፡፡

ከሙከራው መክሸፍ በኋላ የተከተለው ጸጸት ምን ትምህርትን ሊያስገኝ እንደቻለና የህዝቡ ንቃተ ህሊና እንዴት እያደገ እንደመጣ ደረጃ በደረጃ ይመረምራል፡፡ ከዚያ በኋላ እስከ የካቲት ወር መጀመሪያ ድረስ የተከሰቱ እንቅስቃሴዎችን እንዲሁም አቅጣጫቸውን እንዴት ስተው እንደተቀለበሱ ቀጥሎም ህዝባዊ እንቅስቃሴ እንዴት ሊነሳ እንደቻለ ያስቀምጣል፡፡ ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ እንዲሉ ደራሲው ራሳቸው የነበሩበትን አፍላ ተሳትፎ ያስቃኙናል፡፡ በተለይም በሂደቱ ውስጥ ከመሸነፍ ወደ ማጥቃት የተሸጋገሩ ሃይሎች በአብዮቱ አፍላ ወቅት ሁሉም ብሶቱን እያነገበ፣ ሁሉም ብሶትህ ብሶቴ ብሎ እየተጋገዘና ከዚያም ደግሞ ለዘላቂ መፍትሄ ሲባል ሁሉም ለስርአት ለውጥ በሚል አላማ ትግሉ የተጓዘበትን « ሶስትዮሽ » ብለው የጠሩት አካሄድ እንዴት እንደነበረ ያብራራሉ፡፡

ይልቁንም ከሰኔ 66 ዓ.ም. እስከ የካቲት 67 ባለው ጊዜ ወታደራዊው የደርግ መንግሥት እንዴት አድርጎ ሥልጣኑን እየጨመደደ ለመያዝ እንደቻለና መሬት ላራሹ የሚለውን የአርሶ አደሩን ጥያቄ ለመመለስ ሁኔታዎች እንዴት እንዳስገደዱት፣ ድሃ ገበሬዎችና ዘማቾች በአንድ በኩል፣ « ታማኝ ቀልባሾች » በሌላ በኩል ያካሄዱት ወስብስብ ትግል እንዴት እንደነበረ ፍንትው አድርገው አስቀምጠውታል፡፡ ተራማጅ ሃይሎች ደርግ በሚከተለው አመራር ላይ በነበራቸው አስተያየት ጎራ መለየት፣ ቀጥሎም የህዝባዊ ግንባሮች አውታሮች እንደተመሰረቱና በተለይም ገበሬዎች እንዴት በማህበር መደራጀት እንደሚገባቸው የፖሊሲ አመንጭ የነበረው የምሁራኑ የህዝብ ድርጅት ጉዳይ ጊዜያዊ ጽ /ቤት እንዲቋቋም የነበረውን ድርድር፣ ስምምነት የተደረሰባቸውን ሰነዶችና አመሰራረቱን የሚመለከት ትንታኔ ቀርቧል፡፡

በተለይ አዲሱ ትውልድ ስለ ኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ ለመመርመር ሲነሳ ከአጴው ሥርአት ቀጥሎ ምን ተፈጠረ ? የተሞከረውን የለውጥ እንቅስቃሴ ሁሉ ምን አከሸፈው? ለክሽፈቱ አስተዋጽኦ የነበራቸው ኃይሎች ሚና ምን ነበር ? ብሎ ራሱን መጠየቁ እንደማይቀር በመገመት ይህንን መጽሃፍ ማንበቡ ስለ ወደፊቱም የሃገሪቱ የፖለቲካ እጣ ፈንታ ምን ሊሆን እንደሚችል መተንበይ አያዳግተውም ብየ አስባለሁ፡፡ ስለዚህም ከሊቅ እስከ ደቂቅ ይልቁንም በአመራር ላይ ያሉ ኃይሎች ሊያነቡት እንደሚገባ አስባለሁ፡፡

ይልቁንም በአሁኑ ጊዜ በመከሰት ላይ ያለው አምባገነናዊ ሥርአት መነሻና አካሄዱ እንዴት ነው? ያለፉት ትንበያዎችስ የቱን ያህል ተጨባጭ ሆነዋል? ብሎ አካሄዱ የት ላይ መስመር እንደሳተ መገንዘብ ይችላል፡፡ ለምሳሌ በ1967 ዓ.ም. ደርግ ስልጣን ለመያዝ ዳር ዳር ሲል ተማሪዎች ከሌሎች ተራማጅ ሃይሎች ጋር በመሆን ወታደራዊ ጁንታ ሊቋቋም ይችላልና ከዚህ ይልቅ መሆን ያለበት ህዝባዊ መንግስት ነው ሲሉ ተሟግተው እንደነበረ ይታወሳል፡፡ የተፈራውም አልቀረም ደረሰ፡፡ ይሁንና ያን ጊዜም ቢሆን ከደርግ አባላት መካከል ተራማጆችን በመያዝ ህዝቡን ማንቃት፣ ማደራጀትና ማስታጠቅ ሊቀድም ይገባል የሚሉ ሃይሎች እንደነበሩ አይዘነጋም፡፡ ሆኖም የተራማጅ ሃይሎች በሁለት ጎራ መከፋፈልና መዋቀር ለደርግ አምባገነን ሥርአት መፈርጠም አመችቶታል ማለት ይቻላል፡፡ በትግሉ ሂደት አያሌ ምሁራንና ወጣቶች ለለውጡ ሲሉ ወድቀዋል፣ ደማቸውንም አፍሰዋል፡፡

በዚህ ጊዜ የውጭ ጠላቶች ወረራ፣ የኤርትራ ነጻ አውጭ ግንባር ፍልሚያና የትግራይ ነጻ አውጭ ግንባር ዙሪያ ገብ ጦርነት የደርግን ስርአት በ17 አመት ትግል ሊቀጨው ችሏል፡፡ ከዚያ በኋላ የተከሰተው ሁኔታ የረጅም ጊዜ ጦርነት ያስከተለው የሰው ሃይል የመንፈስና የመሰልቸት ሁኔታ ከጫካ በሚነዛው የሬድዮ ስብከት ታጅቦ እነሆ አሁን ያለንበት ሁኔታ ደረስን፡፡

እዚህ ላይ ቆም ብለን መጠየቅ ያለብን ጉዳይ እውነት በኢትዮጵያ ውስጥ የዘር ጭቆና ነበርን? ከኮሙኒስቶች ማኒፌስቶ አጉል ጥራዝነት በኮሙኒስትነት በመንገድ ላይ እንዳለና ከዚያም በኋላ ከአልባንያ ቅጂ ወደ አስመሳይ ካፒታሊስትነት የተለወጠው እስከ 5ኛው ምርጫ ድረስ ሊደርስ የቻለውና ሥልጣንን ጨምድዶ የያዘው፣ ዴሞክራሲን እየሰበከ አምባገነን ሊሆን የቻለው እንዴት ነው? ወደፊትስ በዚሁ አይነት እስከመቼ ሊቀጥል ይችላል?

በዶክተር ነገደ ጎበዜ መጽሃፍ ውስጥ የቀረበውን ትንተና በዚች አጭር አስተያየት ማጠቃለል አይቻልም፡፡ ዓላማዬ ግን መነበብ ያለበት መጽሃፍ ነው በሚል መንፈስ ተነሳስቼ ያቀረብኩት አስተያየት መሆኑን አጠንክሬ ለመግለጽ ብቻ ነው፡፡ መጽሃፉን ያላነበበ አይኖርም ብዬ አስባለሁ፡፡ ሆኖም ግን ተደጋግሞ መነበብ ያለበት ሥራ ይመስለኛል፡፡

በእኔ ግምት የዶ/ር ነገደ ጎበዜ መጽሃፍ በተጨባጭ ማስረጃዎች ላይ የተመሰረተ የኢትዮጵያን ፖለቲካዊ ታሪክ ያሰፈረ ብቻ አይደለም፡፡ ከዓለም አቀፉ ሁኔታዎች ጋር ያገናዘበ፣ በሶሻል በኢኮኖሚና በባህል ላይ የተመሰረተውን የማህበረሰቡን ታሪክ ያናበበ፣ የወደፊቱን አቅጣጫ የሚጠቁም ብዙ ልፋት የተደረገበት የምርምር ስራ ውጤት ይመስለኛል፡፡ በበኩሌ መጽሃፉን ካነበብኩ በኋላ ስለ ኢትዮጵያ የቅርብ ጊዜ የፖለቲካ ታሪክና ስለ መጭው ጊዜ በልበ ሙሉነት ትንታኔ ለመስጠት ድፍረት አግኝቻለሁ፡፡ እንደዚህ ያለ ሥራ አዘጋጅቶ ማቅረብ ለእናት አገር የተከፈለ መስዋእትነት አድርጌ ነውና የምመለከተው ደራሲውን ከልብ ላመሰግን ይገባኛል፡፡ እግዚአብሄር ይክፈልዎት፡፡

ብንያም ሰለሞን

 

 

The post የዶክተር ነገደን ‘ይድረስ ለግንቦት ከየካቲት’ ካነበብኩ ወዲህ……- ትችት ከብንያም ሰለሞን appeared first on Zehabesha Amharic.

የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደዕረቡ መዘዋወሩ ተሰማ በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ እና ውጪ በርካታ የጸጥታ ሃይሎች ነበሩ

$
0
0

hqdefaultዛሬ በጥዋት የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ ሊሰጥ የተቀጠረውን ውሳኔ ተመልክቼ ለመዘገብ ልደታ በሚገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት አምርቼ ነበር፡፡ 3፡30 ሰዓት ገደባ በታችኛው መግቢያ በር ጋር ስደርስ፣ ቁጥራቸው በዛ ያሉ፣ የሚሊተሪ ልብስ የለበሱ የጸጥታ ሃይሎች እና የአዲስ አበባ ፖሊሶች በፍርድ ቤቴ ቅጥር ግቢ በር ላይ ሆነው ሰዎችን በጥብቅ እየተፈሹ ሲያስገቡ አስተዋልኩ፡፡ በአጋጣሚ ከጠበቃ ተማም አባቡልጉ ጋር ተደዋውለን ተገናኝተን ነበር፡፡ ‹‹እነአቡበከርን ከቂሊንጦ አላመጧቸውም፤ ቀጠሮው ለዕረቡ መዘዋወሩን የሚጠቁም መረጃ ሰምቻለሁ፡፡›› አለኝ፡፡ በዚህ ጊዜ ዳርማር አንበሳ ጫማ ቤት ፊትለፊት አንድ የፖሊስ አመራር አራት ሂጅብ የለበሱ ሴት ሙስሊሞችን ‹‹ከዚህ አካባቢ ሂዱ›› እያለ በመቆጣት ከአካባቢው እንዲርቁ ሲያደርጋቸው ተመልክቻለሁ፡፡
በርካታ የጸጥታ ሃይሎች በተሰበሰቡበት የፍርድ ቤት መግቢያ በር ጋር ተፈትሼ ወደውስጥ ዘለኩኝ፡፡ የኮሚቴዎቹ አንዷ ጠበቃ የሆነችውን ወ/ሮ አዲስን አገኘኋትና ስለጉዳዩ ጥያቄ አቀረብኩላት፡፡ ‹‹መደበኛ ባልሆነ መንገድ ዕረቡ የሚል መረጃ አግኝቻለሁ፤ ዕረቡ ችሎቱ ይሰየም አይሰየም ግን በእርግጠኝነት አላወኩም›› የሚል መልስ ሰጥታኛለች፡፡
እኔም የፍርድ ቤት ቅጥር ግቢውን ለቅቴ ስወጣም፣ ከውስጥም ሆነ በውጪ (በፍርድ ቤቱ) በርካታ የጸጥታ ሃይሎች፣ ፖሊሶችና የፍርድ ጉዳዩን ለመታዘብ የመጡ ወንድ እና ሴት ሙስሊሞች ቆመው ተመልክቻለሁ፡፡

The post የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የፍርድ ቤት ቀጠሮ ወደዕረቡ መዘዋወሩ ተሰማ በፍርድ ቤቱ ቅጥር ግቢ እና ውጪ በርካታ የጸጥታ ሃይሎች ነበሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

እነ ወይንሸት ሞላ እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋስ ተጠየቀባቸው •ነገ ደግሞ ይግባኝ በተባለባቸው ጉዳይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ

$
0
0

9271_728586630600331_5995106938468341166_n
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት አይ.ኤስ.አይ.ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤተልሄም አካለ ወርቅ ፖሊስ ምስክሮችን አስፈራርተውብኛል ካለው ጉዳይ ጋር በተያያዘ ዛሬ ሰኔ 23/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት ቀርበው እያንዳንዳቸው የ5000 ብር ዋስ ተጠይቆባቸዋል፡፡

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እነ ወይንሸት ቀደም ብሎ ጉባኤንና ስብሰባን በማወክ በተከሰሱበት ወቅት ምስክሮቼን አስፈራርተውብኛል ያለው ፖሊስ ለምስክርነት የማረሚያ ቤት ፖሊስን ቢያስመዘግብም በዛሬው ዕለት ምስክሮቹን ይዞ መቅረብ ሳይችል ቀርቷል፡፡ በዚህም ተጨማሪ ቀጠሮ ጠይቆ የነበር ቢሆንም፣ እነ ወይንሸት የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀው እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋስ እንዲያስይዙ ፍርድ ቤቱ አዝዟል፡፡

እነ ወይንሸት ሞላ ቀደም ሲል የቄራ ፍርድ ቤት ከእስር እንዲወጡ ውሳኔ በሰጠበት ጉዳይ ላይ የስድስተኛ ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቀባቸው በሚል ነገ ሰኔ 24/2007 ዓ.ም ቂሊንጦ እስር ቤት የሚገኘው ማስተዋል ፍቃዱን ጨምሮ ልደታ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እነ ወይንሸት በፍርድ ቤት ከእስር እንዲፈቱ ቢወሰንላቸውም ፖሊስ ውሳኔውን ባለማክበር አስሯቸው እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

መንግስት ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ከጠራው ሰላማዊ ሰልፍ ጋር በተያያዘ ብዙ ዜጎችን አስሮ እንደሚገኝ መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡

The post እነ ወይንሸት ሞላ እያንዳንዳቸው 5000 ብር ዋስ ተጠየቀባቸው •ነገ ደግሞ ይግባኝ በተባለባቸው ጉዳይ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የፕሬዝዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ጉብኝት ዓለም አቀፍ ተቃውሞው አይሏል።በመጪው ዓርብ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ዋይት ሃውስ ደጅ ተቃውመው ይሰለፉበታል (የፎቶ ጋለሪ)

$
0
0
ፖሊሶች አይ ኤስን በመቃወም የወጡ ወጣቶችን መስቀል አደባባይ ከደበደቡ ገና ሁለት ወር መሙላቱ ነው።
Thousands will demonstrate in front of White house
 
Petition is collecting against the president visit to African North Korea state- Ethiopia

President Obama should not stand against his own nation Human Rights annual report

Dear presedant please mach your speech and act
ፕሬዝዳንት ኦባማ ንግግርዎ እና ድርጊትዎ አንድ መሆን አለበት
 
”ቤታችን ሞቅ ሞቅ ስላለ ነው የመጡት” ያሉት ቃል አቀባይ ሬድዋን ሁሴን ምርጫው መቶ በመቶ አሸነፍን ሲሉ አላፈሩም።
State spokes man Redwan Hussen on press conference confirming as US stands on the side of his dictator’s rule. Another shame to US.

 
ፕሬዝዳንት ኦባማ ደጋግመው ማሰብ አለብዎ።
Presdant Obama needs to think twice
”የኢትዮጵያው ያለፈው ምርጫ የሰሜን ኮርያ ጋር ይመሳሰላል”በኢትዮጵያ የእንግሊዝ አምባሳደር ለሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሳምንት ከሰጡት ቃል።
”Past election has similarity to North Korean one” British Ambassador to Ethiopia in his last week interview to Pro-TPLF news paper ”Reporter Amharic”
 
 
ከምርጫው አንድ ሳምንት በፊት ፖሊስ ሰልፈኞችን በዱላ ይቀጠቅጥ ነበር።
የምክርቤት ተወዳዳሪ ዕጩ ጠበቃ ሳሙኤል ከተገደለ ቀናት እየተቆጠሩ ነው
It is about few weeks since Lawyer Samuel, opposition Semayawi party candidate in the recent election, was killed.
 

ጉዳያችን GUDAYACHN
ሰኔ 25/2007 ዓም (ጁን 2/2015)

 

The post የፕሬዝዳንት ኦባማ በኢትዮጵያ ጉብኝት ዓለም አቀፍ ተቃውሞው አይሏል።በመጪው ዓርብ ብዙ ሺህ ኢትዮጵያውያን ዋይት ሃውስ ደጅ ተቃውመው ይሰለፉበታል (የፎቶ ጋለሪ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ አሳሰበ

$
0
0

amnestyintl.logo.2አምነስቲ ኢንተርናሽናል ትናንት ሰኔ 24/2007 ዓ.ም ባወጣው ሪፖርት የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የፍርድ ቤቱን ውሳኔ አክብረውም የሰማያዊ ፓርቲ አባላትን በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቋቸው አሳስቧል፡፡ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ወይንሸት ሞላን፣ ኤርሚያስ ፀጋዬን፣ ዳንኤል ተስፋዬንና ቤትሄለም አካለ ወርቅን ፍርድ ቤት በአስር ቀናት ውስጥ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲለቀቁ ቢያዝም አራቱ ግለሰቦች አሁንም እስር ቤት ውስጥ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጾአል፡፡

አይ ኤስን ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ላይ ፖሊስ የሀገሪቱንና የዓለም አቀፍ ህግን በመጣስ በሰልፉ ላይ የተፈጠረውን ችግር ለመቆጣጠር ጥሯል ያለው አምነስቲ ኢንተርናሽናል በወቅቱ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላትና አመራሮች መታሰራቸውን አስታውሷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑት ብሌን መስፍን፣ ተዋቸው ዳምጤ፣ ማቲያስ መኩሪያ፣ ስንታየሁ ቸኮል፣ ቴዎድሮስ አስፋው፣ ሜሮን አለማየሁና ንግስት ወንዲፍራው በሰልፉ ሰበብ መታሰራቸውን በአብነት የጠቀሰው ሪፖርቱ ከሰማያዊ ፓርቲ አባላት በተጨማሪ የሌሎች ታሳሪዎች ፍርድም በሂደት ላይ መሆኑን ጠቅሷል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነው ናትናኤል ያለም ዘውድና የፓርቲ አባል ያልሆኑ አራት ግለሰቦችም በሰልፉ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩን ሰድበዋል፣ መንግስትን የሚቃወም መዝሙር አሰምተዋል በሚል ሰበብ ሶስት አመት እንደተፈረደባቸው ሪፖርቱ አውስቷል፡፡
ወይንሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬንና ቤትሄሌም አካለወርቅ ሁለት ወር ተፈርዶባቸው ለሁለት ወር ያህል እስር ቤት በመቆየታቸው እንዲፈቱ ቢታዘዝም ፖሊስ የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ ወደ እስር ቤት እንደመለሳቸውም የአምነስቲ ሪፖርት አስታውሷል፡፡ በእነ ወይንሸት ላይ አዲስ ክስና ይግባኝ እንደተጠየቀባቸው የገለፀው የሰብአዊ መብት ተሟች ድርጅቱ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ወይንሸት ሞላን፣ ኤርሚያስ ፀጋዬን፣ ዳንኤል ተስፋዬንና ቤትሄሌም አካለ ወርቅን እስር ቤት ውስጥ በማጎር የፍርድ ቤቱን ቅቡልነትና የህግ የበላይነትን እየሸተሸሩ ነው ብሏል፡፡ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ላይ የሚያደርሱትን ስቃይ ማቆምና በነፃ የመዳኘት መብታቸውን ሊያከብሩላቸው እንደሚገባም አሳስቧል፡፡

The post አምነስቲ ኢንተርናሽናል የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በአስቸኳይ ከእስር እንዲለቀቁ አሳሰበ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>