Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

የወያኔ መከላከያ ሰራዊት መካከል አለመግባባቱ ተባብሶ ቀጥላል

$
0
0

15በመከላከያ ሰራዊት የሰሜን እዝ አባላት የሆኑት ወታደሮች በአገልግሎት ማብቂያ በሚል ምክንያት ያልተፈለጉትን ለማሰናበት ተብሎ በተካሄደ ስብሰባ ላይ ብዛት ያላቸው ወታደሮች አገልግሎታችን ግዜ ያበቃ በመሆኑ መሰናበት አለብን በማለታቸው የተነሳ ስብሰባው እንደተቋረጠ ታወቀ።

ምንጮቻችን በላኩልን መረጃ መሰረት- በሰሜን እዝ በክፈለ ጦሩ አዛዦች ሜጀር ጀነራል ገብራት አየለና ብርጋዴር ጀነራል ማዓሾ በየነ የተመራው ስብሰባ ግንቦት 21 2007 ዓ/ም የተካሄደ ሲሆን። እንደ አጀንዳ ያቀረቡት ደግሞ ከአስርና ከስባት አመት በላይ ካገለገሉት መካከል የተወሰኑትን ለማሰናበት በሚል ቢነጋገሩም ብዛት ያላቸው የሰራዊቱ አባላት ግን ከተባለው የአገልግሎት እድሜ በላይ ያገለገሉ ስለሆኑና። ላቀረቡት የውሳኔ ሃሳብ በመቃወም“ ግዳጃችን ስለፈፀምን የሚገባንን ሰጥታችሁ ሸኙን” በሚል በአንድ ድምፅ ስለተቃወሙ ስብሰባውን እንደተቋረጠ ለማወቅ ተችሏል።

መረጃው በማከል እንዳስረዳው- በአገልግሎት ስም የተወሰኑት ልንሸኝ ነው የሚለውን ሃሳብ እንደ ሽፋን እንጂ ዋናው አላማው ግን በወታደሩ ውስጥ በተካሄደው የግንቦት 16/ 2007ዓ/ም ምርጫ በረከት ያለ ድምፅ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች ተሰጥቶ በመገኘቱ የተነሳ ይህ ደግሞ ለሰራዊቱ አዛዦች የራስ ምታት ስለሆነባቸው በምርጫ ጊዜ ለተቃዋሚ ፓርቲዎች መርጠው ሊሆኑ ይችላሉ የተባሉት ወታደሮች ለመቀነስ የታለመ ሴራ ቢሆንም ነገር ግን ሳያስቡት ግርግር በመከሰቱ አጀንዳውን እንዳስቆሙት መረጃው ጨምሮ አስረድታል

አሰግድ ታመነ

The post የወያኔ መከላከያ ሰራዊት መካከል አለመግባባቱ ተባብሶ ቀጥላል appeared first on Zehabesha Amharic.


ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ አረፈ

$
0
0

darios modi

ግንቦት 13 1983 ዓ.ም የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኮለኔል መንግስቱ ኃይለማርያም ወደ ዙምባብዌ ሲሸሹ ዜናውን በኢትዮጵያ ራድዮ በማንበቡ በታሪክ ውስጥ የሚጠቀሰው ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ::

ከአዲስ አበባ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው የጋዜጠኛው ፈረሳይ ለጋሲዮን በሚገኝ አንድ ቤተክርስቲያን ሰኔ 14 ቀን 2007ዓ.ም ይፈጸማል::

The post ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ አረፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

መድረክ በኦሮሚያ 2፣ በደቡብ 1 እንዲሁም በትግራይ 1 አባላቶቹ መገደላቸውን ይፋ አደረገ

$
0
0

በኦሮሚያ 2 አባላት ተገድለዋል፤ 640 ታስረዋል ብሏል

(አዲስ አድማስ) መድረክ በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞንና በትግራይ ክልል ሁለት አባላቱ በ3 ቀናት ልዩነት እንደተገደሉበት አስታወቀ፡፡ ባለፈው ማክሰኞ በትግራይ ክልል የመድረክ አባል የነበረው አቶ ታደሰ አብርሃ እንደተገደለበት በመግለጫው ያስታወቀ ሲሆን ከትናንት በስቲያ ሐሙስ ደግሞ በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን አቶ ብርሃኒ ኤረቦ የተባሉ የመድረኩ አባል ተገድለው ትናንት ጠዋት አስከሬናቸው መገኘቱን የመድረክ ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡ በምዕራብ ትግራይ ዞን የአረና/መድረክ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ ሆነው በዘንድሮው ምርጫ በዞኑ የምርጫውን ሥራ በማደራጀት፣ በመቀስቀስና ታዛቢዎችን በመመደብ ከፍተኛ ሚና ሲጫወቱ የቆዩት አቶ ታደሰ አብርሃ አርአያ በመኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተደብድበው መገደላቸውን መድረክ አስታውቋል፡፡ ባለፈው ማክሰኞ ከምሽቱ 3 ሰዓት ላይ ለጊዜው ማንነታቸው በግልጽ ተለይቶ ያልታወቁ 3 ሰዎች ወደ ቤታቸው በመግባት በተፈጸመባቸው አሰቃቂ ድብደባ ሕይወታቸውን ያጡት አቶ ታደሰ፤ በምርጫው ቅስቀሳ ወቅትም በኢህአዴግ ካድሬዎችና ታጣቂዎች ድብደባ ተፈጽሞባቸዋል ያለው መድረክ፤ “ምርጫውሲያልፍ አንድ በአንድ እንለቅማችኋለን፤ የትም አታመልጡንም” የሚል ዛቻና ማስፈራሪያም ደርሶባቸው ነበር ብሏል፡፡
beyene_petros
በዞኑ በሚገኘው ማይካድራ ከተማ ነዋሪ የነበሩት አቶ ታደሰ አብርሃ፤ ድብደባው እንደተፈጸመባቸው ጉዳዩን የሰሙት አቶ መሰለ ገ/ሚካኤል /በዞኑ የአረና/መድረክ ተወካይ/ ለጉዳተኛው የሕክምና ዕርዳታ እንዲደረግላቸው ለማስተባበርና ወንጀለኞችንም ተከታትሎ ለማስያዝ ከቤታቸው በሞተር ብስክሌት ወጥተው ሲንቀሳቀሱ ፖሊሶች ይዘው “መንጃ ፈቃድ በእጅህ አልያዝክም” በሚል ሰበብ ሞተር ብስክሌታቸውን ወስደው ፖሊስ ጣቢያ በማስገባታቸው፣ለተጎጂው ከመድረሳቸው በፊት ሕይወታቸው ማለፉን መድረክ በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡ የ48 ዓመቱ ጎልማሳ አቶ ታደሰ አብርሃ፤ ባለትዳርና የአንድ ሴት ልጅ አባት የነበሩ ሲሆን የቀብር ሥነ ሥርዓታቸውም በነጋታው ረቡዕ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች በተገኙበት ተፈጽሟል ብሏል፡፡በሌላ በኩል በትግራይ ክልል በምርጫው ሰሞን ዕጩዎች በሚቀርቡበት ወቅት የታሰሩ 17 የአረና/መድረክ አባላት አሁንም በመቀሌ ወሕኒ ቤት ታስረው እንደሚገኙ መድረክ አስታውቋል፡፡ በደቡብ ክልል የተለያዩ ዞኖች እና ወረዳዎችም በአባላቱና በምርጫው ወቅት በታዛቢነት ያገለገሉ ግለሰቦች ላይ የተለያዩ መከራዎችና እንግልቶች እየተፈፀሙ መሆኑን የፓርቲው መግለጫ ጠቁሟል፡፡ በእሳት ቤት ንብረትን ማቀጠልን ጨምሮ ከቤት ማፈናቀልና እስራት በአባላትና ደጋፊዎች ላይ እየተፈፀመ ነው ያለው መድረኩ፤ “ተቃዋሚዎችን መርጣችኋል ወይም ህዝቡ እንዲመርጣቸው ቀስቅሳችኋል” በሚል ግለሰቦችን ማሰቃየቱና ማዋከቡ ተጠናክሮ እንደቀጠለ አስታውቋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በሚገኙ የተለያዩ ዞኖችና ወረዳዎችም ከምርጫው ዋዜማ ጀምሮ እስካሁን 640 አባላትና ደጋፊዎቹ መታሰራቸውን የጠቀሰው መድረኩ ሁለት አባላት ሲገደሉ 66 መደብደባቸውን፣ 7 አባላቱም በጥይት ተመተው እንደቆሰሉ መድረክ በመግለጫው አመልክቷል፡፡ በመድረኩ አባላት ላይ እየደረሰ ያለውን ግድያ፣ እንግልትና ስቃይ በተመለከተ በዝርዝር ለምርጫ ቦርድ አቤቱታ ማቅረባቸውን የጠቆሙት የፓርቲው ሊቀመንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ “በአባላቶቻችን ላይ እየደረሰ ባለው ግድያ የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም እየሆነብን ችግር ላይ ነው ያለነው” ብለዋል፡፡

መንግስት በጉዳዩ ላይ ሊያነጋግራቸው እንደሚገባ ያሳሰቡት ፕ/ር በየነ፤ መድረኩ በአባላቱ ላይ እየደረሱ ነው ላለው በደል ድምፁን ከማሰማት ወደኋላ እንደማይል ገልፀዋል፡፡ አክለውም ከትናንት በስቲያ በደቡብ ክልል ሃዲያ ዞን የመድረክ አባል የሆነና በምርጫው ጉልህ
ተሣትፎ የነበረው አቶ ብርሃኑ ኤረቦ፣ ፖሊሶች ከቤት አስገድደው ከወሰዱት በኋላ ወንዝ ውስጥ
ሞቶ አስከሬኑ አርብ ጠዋት እንደተገኘ ፕ/ር በየነ ለአዲስ አድማስ ገልፀዋል፡፡

The post መድረክ በኦሮሚያ 2፣ በደቡብ 1 እንዲሁም በትግራይ 1 አባላቶቹ መገደላቸውን ይፋ አደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

ታላቁ ዲፕሎማት አምባሳደር ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ ጉግሳ (ሮቤል አባቢያ) አረፉ

$
0
0

ዘሐበሻን ጨምሮ በተለያዩ ድረገጾች ስለሃገራቸው ሮቤል አባቢያ በሚል ስም ስለሃገራቸው ሲጽፉ የከረሙት ታላቁ ዲፕሎማት አምባሳደር ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ ጉግሳ ባደረባቸው ህመም ዩጋንዳ ካምፓላ ኢንተርናሺናል ሆስፒታል በ79 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ።

Robel Ababiya

በንጉሱ ዘመን የኢትዮጲያ አየር ሃይል አካዳሚ ከፍተኛ መምህርና ሃላፊ በደርግ ጊዜ ደሞ አገሪቱ በዚያድባሬ ጦርነት በተከፈትባት ቀውጢ ሰዓት የታላቋ ሶቬትህብረት የኢትዮጲያ አንባሳደር ሆነው ወሳኝ ሚና ተጫውተዋል። ከዛም የሲቪል አቬሽን ባለስልጣን ዋና ዳሬክተር ሆነው በኮሎኔል መንግስቱ ሃይለማርያም ተሹመው ሰርተዋል።

በርካታ አየር ማረፍያዎችንም አስገንብተዋል። ደርግ ሊወድቅ አካባቢም በሲቪል ኢንጂነሪንግ ሙያ በተባበሩት መንግስታት ተቀጥረው ኡጋንዳና ቦትስዋና ላይ ሰርተዋል። በዩጋንዳ ካምፓላ የሚገኘውን የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ካምፓላ መካነሰላም መድሃንያለም ቤተክርስትያንን ከባለቤታቸው ወይዘሮ ወርቅነሽ በልሁ ጋር በመሆን በመመስረቱ ሂደት አብይ ድርሻ ያበረከቱ ሲሆን የስደተኛው ሲኖዶስ የአፍሪካና አውሮፓ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ኤልያስ ልዩ አማካሪ በመሆንም አገልግለዋል።

ኮነሬል ጸጋዬ ሶስት ሴቶች ልጆችና ሁለት ወንድ የልጅ ልጅ አፍርተዋል። ላለፉት 24 አመታት ካገራቸው እርቀው የኖሩት ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ የቀብር ስነስርዓታቸው የፊታችን ሰኞ በትውልድ አገራቸው ኢትዮጲያ እንደሚፈጸም ለቤተሰቡ ቅርበት ካላቸው ወገኖች የተገኘው መረጃ እንደሚጠቁም ፔን ዘኢትዮጲያ ዘግቧል።

The post ታላቁ ዲፕሎማት አምባሳደር ኮነሬል ፀጋዬ መሸሻ ጉግሳ (ሮቤል አባቢያ) አረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቢዩ ተከሥተብርሃን ተፈራ 40 ቀን መታሰቢያ

እነ ወይንሸት ሞላ እንዲፈቱ ተወሰነ

$
0
0

9271_728586630600331_5995106938468341166_nበነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰሩት ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ዛሬ ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ቀርበው እንዲፈቱ ተወስኗል፡፡ አቃቤ ህግ እነ ወይንሸት ሞላ አንድ ላይ ሆነው ፈጽመውታል ያለውን ክስ ማስረዳት እንዳልቻለ የገለጸው ፍርድ ቤቱ ከተከሳሾቹ መካከል የኤርሚያስ ፀጋዬ መከላከያ ምስክሮች በቦታው እንዳልነበረ እንዳስረዱ ገልጾ በነጻ እንዲለቀቅ ወስኗል፡፡

የወንይሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ የመከላከያ ምስክሮች ተከሳሾቹ በቦታው እንዳልነበሩና ወንጀሉን እንዳልፈፀሙ አላስረዱም በሚል የጥፋተኝነት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡ የተከሰሱበት ወንጀል እስከ 6 ወር እንደሚያስቀጣ የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ላይ የሁለት ወር እስር የፈረደባቸው ሲሆን ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆኑ ከእስር እንዲፈቱ ወስኗል፡፡

በሌላ በኩል 3ኛ ተከሳሽ የሆነው ማስተዋል ፈቃዱ ‹‹የተከሰስኩት በፖለቲካ አመለካከቴ ነው›› በማለቱ ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን ተቃውመሃል በሚል 3 ወር እስራት ፈርዶበታል፡፡ ከሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ጀምሮ ሁለት ወር በእስር ላይ የቆየ በመሆኑም ለአንድ ወር በእስር እንደሚቆይ ይታመናል፡፡

The post እነ ወይንሸት ሞላ እንዲፈቱ ተወሰነ appeared first on Zehabesha Amharic.

“በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል። የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን”–አርከበ ዕቁባይ

$
0
0

Arkebe Equbai

“በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል። የኤሪትራን ወደብ እንጠቀማለን” ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ። ይሄ “ትንቢት” ምን ማለት ነው?
– ሻዕቢያ ይወድቅና በምትኩ ሌላ መንግስት ተተክቶ ግንኙነቱ ሰላም ይሆናል። እናም ወደቡን እንደገና እንጠቀማለን ነው?
– ኢህአዴግ ሻዕቢያን አስወግዶ በምትኩ ከእሱ ጋር የሚስማማ መንስግስት አስመራ ላይ መስርቶ ወደቡን እንጠቀማለን ነው?
– ኢሳያስ አፈወርቂ በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ ይሞትና አዲስ የሚመጣው መሪ ነገሩን ወደነበረበት ይመልሳል ነው?
– ሻዕቢያ ተገዶ ሀሳቡን በመቀየር ነገሮች ወደነበሩበት ይመለሳሉ ነው? ወዘተ

ከዚያ በፊት ስብሃት ነጋ ስለ ኤሪትሪያ የተናገረው ንግግርስ? ምን አይነት እርምጃ ለመውሰድ አቅደው ነው?

ከአቤኔዘር ይስሃቅ

በዚያም ሆነ በዚህ ምነው ህወአቶች ስለ ኤሪትሪያ በትውልድም በዜግነትም ኤሪትራዊ ከሆኑት ኤሪትራውያን በላይ ተጨነቁ? ሀገር ቤት እነሱ ሕዝብ እያስለቀሱ “ኢሳያስ ሕዝቡን እየጨቆ ነው ኤርትሪያ ላይ ሕዝቡ እያለቀሰ ነው . . .” ብለው እያላዙ ነው። በተለይ ሰሞኑን ደግሞ ብሶባቸዋል። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች ማለት ይሄ ነው smile emoticon አሁን እናንተ በየትኛው ሞራላችሁና ንጽሕናችሁ ነው ሻዕቢያን የምትተቹትና የምታወግዙት?
ሌላው ልብ ልንነው የሚገባው በሽግግሩ ወቅት የዛሬ 22 አመት ባልተሰጣቸው የሕዝብ ይሁንታና የሕግ ውክልና የኤሪትሪያ ሕዝበ ውሳኔ/Referendum/ እንዲካሄድ እንዳደረጉና ኢትዮዽያን ወክለው መግለጫ እንደሰጡ ሁሉ ኡሁንም ህወአቶች ማድረግ የሚፈልጉትን ነገር ለማድረግ እያቀዱና እየመከሩ ያሉት ከኢትዮዽያ ሕዝብ ጋር በመመካከከርና የሕዝቡን አስተያየት መሰረት በማድረግ ሳይሆን በራሳቸው ፍላጎትና መንገድ ነው።
ለማንኛውም ሰው ቤት ገብታችሁ ለመፈትፈት ከምተሞክሩ መጀመሪያ የራሳችሁን የቤት ሥራ በደንብ በሰራችሁና ሀላፊነታችሁን በተወጣችሁ። ኤሪትራውያን የራሳቸውን ችግር ለመፍታት ከፈለጉ ከበቂ በላይ ናቸው። የማንም ዕርዳታና ጣልቃ ገብነት አያስፈልጋቸውም። ኢህአዴጎች የሶማሊያም፣ የሱዳንም፣ የኤሪትሪያም፣ የጂቡቲም፣ የደቡብ ሱዳንም ችግር ፈቺ መስለው ጣልቃ በመግባት ቀጠናው ውስጥ እንደ መንደር ጉልቤ እያቅራሩ ነው። አደገኛው ነገር እነሱ ነገ ከሥልጣን ላይ ይነሳሉ። ነገር ግን በኢትዮዽያ ስም በመነገድ እየሰሩት ባለው ስራ ግን ለሀገራችን ዘላቂ ችግርና ጠላት እያበዙብን ነው።

The post “በሚቀጥሉት 10 አመታት ውስጥ ለውጥ ይመጣል። የኤርትራን ወደብ እንጠቀማለን” – አርከበ ዕቁባይ appeared first on Zehabesha Amharic.

አንጋፋውና ዕውቁ ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ ካረፈ ቀናት አለፉ።በቅድሚያ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናት ይሁን!

$
0
0

ደረጀ ሃብተወልድ

darios modi

አንጋፋውና ዕውቁ ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ

አፈንዲ ሙተቂና እንዳለ ተሽ የዳርዮስ ትዝታዎችን በጥሩ ሁኔታ ሰፋ አድርገው አጫውተውናል።
ሰለስቱ ካለፈ እኔም አንዲት ዳርዮስን አጋጥማዋለች የተባለችን ፈገግ የምታሰኝ ነገር ልመርቅላችሁ። (ይህን ነገር ካዳርዮስ ሰማሁ ብሎ ያጫዎተኝ አንድ ጋዜጠኛ ጓደኛዬ ነው)
ኢህአዴግ ሥልጣን የተቆጣጠረ ሰሞን ነው። የኢትዮጵያ ራዲዮ ድርጅት መስሪያ ቤትን ታጋዮች ሞልተውት ነበር።በወቅቱ የመጸዳጃ ቤቱ የአንደኛው ክፍል ቁልፍ ተበላሽቶ ነበር። ወደዚያ ክፍል ለመጸዳዳት የሚመጡ አስቀድመው፦”ሰው አለ?” ብለው በመጠዬቅ ምላሽ ካላገኙ ብቻ ነው የሚገቡት። አንድ ቀን ዳርዮስ እዚያ ቁልፉ የተበላሸው ክፍል ውስጥ እያለ አንዱ ታጋይ ይመጣና ፦”ሰው አለ?” ብሎ ሲጠይቅ ዳርዮስ ከውስጥ ሆኖ ለጨዋታ ያህል ፦”የለም” ይለዋል። ያው ድምጽ ከሰማ አይገባም በሚል እሳቤ ማለት ነው። ይሁንና ዳርዮስ ያልጠበቀው ነገር ሆነ። ታጋዩ ከውስጥ “የለም” የሚል ድምጽ እየሰማ በሩን ከፍቶ ወደ ውስጥ ገባ። ሲገባ ዳርዮስ ከውስጥ አለ። ታጋዩ ይኽኔም ፦ይቅርታ!” ብሎ አልተመለሰም። ይልቁንም ይበልጥ ደሙ ፈላና ዳርዮስን እንደሚከተለው ተናገረው፦” አንተ በደርግ ኢሰፓ ጊዜ ስታጭበረብር ከረምክ። አሁን ደግሞ ሽንት ቤት ተቀምጠህ ታጭበረብራለህ!!”

The post አንጋፋውና ዕውቁ ጋዜጠኛ ዳርዮስ ሞዲ ካረፈ ቀናት አለፉ።በቅድሚያ ለቤተሰቦቹና ለወዳጅ ዘመዶቹ መጽናናት ይሁን! appeared first on Zehabesha Amharic.


የአሸባሪው ቡድን ዛቻ በሮመዳኑ * ISIS ሳውዲውን ኮሜዲ የናስርን አንገት እንደሚቀላ ዛተ

$
0
0

የማለዳ ወግ …የአሸባሪው ቡድን ዛቻ በሮመዳኑ …

እንደ ሮመዳኑ መረጃ ግብአት …
* ISIS ሳውዲውን ኮሜዲ የናስርን አንገት እንደሚቀላ ዛተ
* “የምጠበቀው በፈጣሪ ቸርነት ነው! ” ናስር አል ቁሰቢ

ነቢዩ ሲራክ

ታዋቂው የሳውዲ የቴሌቪዥን ኮሜዲ ድራማ ተዋናይ ናስር አል ቁሰቢ በያዝነው ሮመዳን ባቀረበው አንድ አስተማሪ ኮሜዲ ከጽፈኛው የአይ ሲ አይ ኤስ ISIS ወይም ዳአሽ አሸባሪ ቡድን አባላትና ከደጋፊዎች ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደተሰነዘረበት አስታውቋል ።
መቀመጫውን ዱባይ እንዳደረገ የሚነገረው ሳውዲው ኮሜዲ ናስር አል ቁሰቢ በዘንድሮ ሮመዳን ባዘጋጀው ተከታታይ ” ሰለፊ ” በተባለ ፕሮግራም ላይ አሸባሪ ቡድኑን አስመልክቶ ባቀረበው ዝግጅት ነው ። በዚህ የሮመዳን የመጀመሪያ ሳምንት ዝግጅት ላይ ሶርያ ውስጥ የአሸባሪ ቡድን ጋር ያለውን ልጁን ለመፈለግ ወደ ሶርያ ያቀናውን አባት እስመልክቶ ያቀረበው አጭር ድራማ ነው። እንደ ቀልድ በተላለፈው እጅግ ተጽዕኖ መፍጠር መቻሉ የተሰደሰው ዝግጅት ሲጀምር ልጁን ሊፈልግ የሄደ አባት ወደ የአሸባሪዎችን መቀላቀሉንና በአሸባሪው ቡድን ውስጥ የሚካሔዱትን መረን የለቀቁ ሰብአዊ መብት ረገጣዎች ፣ የአሸባሪዎችን ጨካኔ በተገቢ መንገድ ያሳያል። ዝግጅቱ ሲጠናቀቅም አባት ልጁን ለመቅላት ስለት በአንገቱ ላይ በጭካኔ ቦታ መርጦ ሲያሳርፍና ልጅ አንገቱን ሰጥቶ የአሁን አራጅ አባቱ በልጅነት በፍቅር ያሳደገበትን ሁኔታ ከጎን በምናብ ጨረፍታ ያሳያል …
ስሜትን ፈንቅሎ መልዕክት በሚያስተላልፍ መንገድ ፣

Saudi Arabiaበቀልድ በታጀበው የናስር ዝግጅት አዲስ ነገር ባይቀርብም አለም ያወቀው እውነት የሮመዳን ታዳሚ ደጋግሞ ያጤነው ዘንድ ያመላከተ እንደነበር በመዘገብ ላይ ነው። ናስር በዚህ ዝግጅት የአሸባሪውን ISIS ቡድንን ልክ ያለፈ ጭካኔና ርክሰት የማይጨበጥ ጥልቅ የኪነ ጥበብ ውጤቱ አሳይ ቶበታል ። ለዚህ ድንቅ ተጽዕኖ ፈጣሪበለተባለ ስራው ክብርና ዝናን በአድናቂዎቹ ሲያሰጠው ፣ በጽንፈኛ ቡድን ደጋፊዎች ዘንድ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ አስከትሎበታል !

ትወናውን በመሪነት አሳምሮና እያዋዛ በማቅረቡ የሚታወቀው ኮሜዲ ናስር በዘንድሮው የ”ሰለፊ ” ድንቅ ዝግጅት ጅማሬ ባቀረበው ISIS የተመለከተ ዝግጀት የግድያ ዛቻ ከላኩለት መካከል Julaybib Al-Jazrawi ከተባለ ሰው የደረሰው መካከል ” ፈጣሪ ምስክሬ ነው እኛ ሙጃህዲኖች ያንተን ጭንቅላት ከቀረው ገላህ ቀልተን ካልለያየን እረፍት አናገኝም ! … ” የሚል ከበድ ያለ ዛቻ ይገኝበታል !

የተሰነዘረበትን ሰሞነኛ ዛቻና ማስፈራሪያ አስመልክቶ ሲናገር ” የመጀመሪያውን ክፍል ከለቀቅኩ ጀምሮ በበርካታ ማስጠንቀቂያና ስድቦች የተሞሉ መልዕክቶች አጥለቅልቀ ውኛል ፣ ለሁሉም ተረጋጉ በማለት ረመዳን ከሪም የሚል ምላሽ ነው የሰጠኋቸው ” ብሎ በማሟረት በቲዊተር መልስ መስጠቱ ተጠቅሷል ! ታዋቂው ሳውዲ ኮሜዲ ይህን ምላሽ ከሰጠ በኋላ ዛቻ ማስፈራሪያውን በሚመለከ ት የአረብ መገናኛ ብዙሃንና የማህበራዊ ድህረ ገጾች ሰሞነኛ የሮመዳን መነጋገሪያ አርዕስት አድርገውታል ። ጉዳዩ በስፋት መሰራጩቱን ተከትሎ አርቲስት ናስር ከመገናኛ ብዙሀን በኩል ዛቻ ማስፈራሪያው ያሰጋው እንደሁ ተጠይቆ ሲመልስ ” የምጠበቀው በፈጣሪ ቸርነት ነው! ” ሲል እንቅጩን መመለሱ ተዘግቧል ! ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሜዲ ናስር ISIS አስመልክቶ ያስተላለፈው አጭር ዝግጅት ትልቅ ተጽዕኖ ፈጣሪ በሆኑ ተሞካሽቷል ። አሸባሪውን ቡድን እርቃኑን የሚያወጣ እጥር ምጥን ያለ ዝግጅት ነው በሚልም ደስታቸውን የሚገልጹ ቁጥርም በተመሳሳይ ሁኔታ ከፍ ያለ መሆኑ ተጠቁሟል !
አርቲስት ኮሜዲ ናስር አል ቁሰቢ ሮመዳን በመጣ ቁጥር ከሳውዲ አልፎ በመላ አለም የሚገኙ አረብ ተናጋሪ የቴሌቪዠን ተከራታታዮች ዘንድ በስፋት ይታወቃል ። ” ጣሽ ማጣሽ ” ተብሎ በሚታወቀው ፕሮግራም ላይ ከጓደኛው አብደላ ሰርሃን ጋር ሮመዳን ተጀምሮ እስኪያልቅ በሚያቀርባቸው ልዩ ልዩ አጫጭር አስተማሪ ዝግጅቶች ዝነኝነትን ያተረፈ ኮሜዲ ነው ። ናስርና አብሮት ሲሰራ ባላቸው ውህደት አድናቆትን ያተረፈው ባልንጀራው አብደላ ድንበራቸው የማይደፈር የሳውዲ የሀይማኖት መሪዎችን ጨምሮ በመንግስት ከፍተኛ ተቋማት የሚታዩትን ችግሮች እየነቀሱ በማቅረቡ ተወዳጅነት አትርፈው ነበር ። ይህም ሲሆን ባልተለመደ መንገድ ለሮመዳን በሚቀርቡት ዝግጅቶች ዙሪያ በሳውዲ መንግስት ብቸኛ ፈቃድ ያለው ዝግጅት “ጣሽ ማጣሽ ” እንደ ነበር በስፋት ይታመናል !

የኮሜዲ ናስርና አብደላ ” ጣሽ ማጣሽ ” ካሳለፍናቸው ሁለት አመታት ወዲህ በባልንጀሮች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት ተወዳጁ ዝግጅት ሊቀጥል አልቻለም ። “ጣሽ ማጣሽ” የተባለው ዝነኛ በሮመዳን ዝግጅት በውስጥ ዝብሪት ከተዘጋ በኋላም ሳውዲው ኮሜዲ ናስር በ”አረብ ጎት ታለንት ” ዳኝነት ፈገግ በሚያሰኘው አስተያየቱ አፍቃሪዎቹን ሲያዝናና መክረሙ ይጠቀሳል !
ቸር ያሰማን !
ነቢዩ ሲራክ
ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓም

The post የአሸባሪው ቡድን ዛቻ በሮመዳኑ * ISIS ሳውዲውን ኮሜዲ የናስርን አንገት እንደሚቀላ ዛተ appeared first on Zehabesha Amharic.

እነ ወይንሸት ሞላ ከእስር እንደተለቀቁ ታፈነው ታሰሩ

$
0
0

9271_728586630600331_5995106938468341166_n

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

መንግስት አይ ኤስ አይ ኤስን ለመቃወም በጠራው ሰልፍ ሰበብ ታስረው ሰኔ 15/2007 ዓ.ም በቄራ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት እንዲፈቱ የተወሰነላቸው ወንይሸት ሞላ፣ ኤርሚያስ ፀጋዬ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ዛሬ ሰኔ 16/2007 ከእስር ተፈትተው ሲወጡ በፖሊስና ደህንነቶች ታፍነው ታስረዋል፡፡

ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ታስረው የነበሩት ኤርሚያስ ፀጋዬና ዳንኤል ተስፋዬ ከእስር ከተፈቱ በኋላ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በር ላይ ጠብቀው ያፈኗቸው ሲሆን ፖሊሶቹ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳልያዙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተመሳሳይ የ6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ፖሊሶች ወይንሸት ሞላንና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት አፍነው መልሰው እንዳሰሯቸው ታውቋል፡፡

የቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት ወይንሸት ሞላ፣ ዳንኤል ተስፋዬና ቤትሄልየም አካለ ወርቅ ላይ የሁለት ወር እስር ፈርዶ፤ ከሚያዝያ 14/ 2007 ጀምሮ ሁለት ወር ከአንድ ቀን የታሰሩ በመሆኑ ከእስር እንዲፈቱ ወስኖ ነበር፡፡ ኤርሚያስ ፀጋዬንም በነፃ እንዲለቀቅ ወስኖለት ነበር፡፡ ይሁንና ፖሊስና ደህንነቶች የፍርድ ቤቱን ውሳኔ በመጣስ አፍነው እንደገና አስረዋቸዋል፡፡

The post እነ ወይንሸት ሞላ ከእስር እንደተለቀቁ ታፈነው ታሰሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ginbot 7አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ከሰነዓ አለም አቀፍ አውሮፓላን ጣቢያ ታፍነው ከተወሰዱ በዛሬው ዕለት ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ. ም፣ አንድ ዓመት ይሞላቸዋል። የወያኔ አረመኔዎች ይህን ዓይነት የውንብድና ተግባር ሲፈጽሙ በከፍተኛ ደረጃ ያሰሉት፣ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በማፈን፣ ንቅናቄው ብሎም ሕዝቡ፣ ለዕኩልነት፣ ለፍትህና ለነጻነት፣ የሚያደርገውን ትግል ለማዳከምና ከተቻለም ደግሞ ለማጥፋት እንደሆነ፣ ምንም የማያጠራጥር ጉዳይ ነው።
ለመሆኑ የወያኔዎች ስሌት በምን ያህል ትክክል ነበር ?

ባለፈው አንድ አመት ውስጥ፣ ወያኔ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የፈጸመው የውንብድና አፈና ተግባር፣ ንቅናቄያችን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በሐገር ውስጥም ሆነ በውጭ ባለው ሕዝብ ልብ ውስጥ እንዲገባ አድርጎታል። ሌላው ቀርቶ ከአፈናው በፊት በተለያዩ ምክንያቶች ንቅናቄያችንን በጥርጣሬ የሚመለከቱ ወገኖች በአደባባይ ወጥተው፣ ” እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” በማለት አቶ አንዳርጋቸውና ንቅናቄው ለሚታገሉለት ሕዝባዊና ሐገራዊ ዓላማ መቆማቸውን በግልጽ አሳይተዋል። እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ዜጎች በሐገር ውስጥ፣ በምድር ላይና በውጭ ሐገር የሚገኘውን የንቅናቄያችንን አካላት ተቀላቅለዋል። ቀደም ሲል በንቅናቄያችን በተለያዩ ደረጃዎች ይሰሩ የነበሩ ዓባላቶች ከአፈናው በኋላ ለትግሉ ያላቸውን ቁርጠኝነት በከፍተኛ ደረጃ ጨምረዋል።

የአቶ አንዳርጋቸውን አፈና ተከትሎ፣ የንቅናቄው አመራር መሰረታዊ የትግል እንቅስቃሴዎቹን በስፋትና በጥልቀት በመፈተሽ አስፈላጊውን ማሻሻያዎችና ማስተካካያዎችን አድርጓል። ንቅናቄያችን አቶ አንዳርጋቸው ለረጅም ጊዜ የደከሙለትን ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በጋራ የመታገለን ጥረት አሳክቶ፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ዓርበኞች ግንባር ጋር ሙሉ ለሙሉ ተዋህዷል። ከዚህም በተጨማሪ የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄን ጨምሮ፣ ከሌሎች አምስት በምድር ላይ ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋራ በጥምረት ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሷል።

በሌላ በኩል ያለፈው አንድ አመት የወያኔ የዘረኛ ዓምባገነን ቡድን ከመቼውም ጊዜ ይልቅ በሕዝብ ላይ የሚፈጽመውን የአፈና፣ የግድያ፣ የዕስርና የድብደባ ውንብድና ተግባር አጠናክሮ የቀጠለበት ዓመት ነበር ። ለዚህም ጸረ ሕዝብ ተግባሩ፣ በባህርዳር ከተማ ሰላማዊ ሰዎች ላይ ያደረሰውን ግድያ፣ በሰላም እንታገላለን ብለው ይንቀሳቀሱ የነበሩትን የአንድነትና የመኢሀድ ድርጅቶች ማፍረስ ብቻ ሳይሆን፣ ዓባሎቻቸው ላይ ያደረሰውን ከፍተኛ የድብደባና የዕስር ወንጀል መጥቀስ ይቻላል። ከዚህም በተጨማሪ በኦሮምያ፤ በአፋር፤ በጋምቤላ፤ በኦጋዴን፤ በትግራይና በደቡብ ክልሎች ይህ ነው የማይባል አፈና፤ ግድያና የሕዝብ መፈናቀል በሰፊው አከናውኗል:: ከምርጫው ጋር ተያይዞም በአደረበት ስጋት የተነሳ በርካታ፣ በተለይ ወጣቶች ላይ፣ የመደብደብ፣የማዋከብ የዕስርና የግድያ ተግባር የፈጸመው በዚሁ አቶ አንዳርጋቸውን ከአፈነበት ቀን ጀምሮ በተቆጠረው የአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነበር። በጣም የሚገርመው ለራሱ አመቻችቶ ያዘጋጅውን ምርጫ እንኳን ሙሉ በሙሉ አሸነፍኩ ብሎ ከአወጀም በኋላም፣ ከምርጫው በፊት በሕዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን ወንጀል አጠናክሮ መቀጠሉ ያለበትን የስጋትና ጭንቀት ደረጃ የሚያሳይ መረጃ ነው ።

የወያኔ በራስ የመተማመን ደረጃ ከመቼውም ወቅት ይልቅ እጅግ አሽቆልቁሎ የታየውም ባለፈው አንድ አመት ጊዜ ውስጥ ነበር። በሐገር ውስጥ ይነሳብኛል ብሎ በሚያስበው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ስጋት ምክንያት ይህን ስጋት ለመቀነስ በአንድ መንገድም ይሁን በሌላ ይረዱኛል ብሎ ያሰባቸውን በአካባቢው የራሳቸው ጥቅምና ፍላጎት ያላቸውን ቀደም ሲል ወቀሳ ቢጤ እንደመሰንዘርም ዕልህም እንደመጋባትም ይዳዳቸው የነበሩትን መንግስታት ባለሥልጣኖች በመማጸንና ሐገር ውስጥ በመጋበዝ ማንነቱን አበጥሮ ለሚያውቀው የኢትዮጵያ ሕዝብ በአደባባይ ወጥተው ወያኔ ያልሆነውን ነው ብለው ምስክርነት እንዲሰጡለት ማድረጉ የወያኔ ስጋት የደረሰበትን ከፍተኛ ደረጃ የሚያሳይ ሌላው መረጃ ነው።

በዚህ አጋጣሚ ንቅናቄያችን አቶ አንዳርጋቸውን አፍነው ለወያኔ የሸጡትን የየመን ባለሥልጣኖች ድርጊት በሚመለከት በጊዜው በሰጠው መግለጫ ላይ በግልጽ እንዳስቀመጠው፣ “ጊዚያዊ ጥቅምን በማየት የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዕኩልነት፣ ለፍትህና ለነጻነት የሚያደርገውን ትግል ከወያኔ ጋር በቀጥታም ሆን በተዘዋዋሪ በመተባበር ለማፋን መሞከር፣ ታሪካዊ ስህተት መስራት ነው!” እንዳለው ሁሉ፣ ዛሬም የሌሎች መንግስታት ባለ ሥልጣኖች እንደ ትላንትናዎቹ የየመን ባለሥልጣኖች ጊዚያዊ ጥቅምን ብቻ በማየት ሌላ ታሪካዊ ስህተት እንዳይደግሙ ከወዲሁ ለማሳሰብ ይወዳል።

በንቅናቂያችን እምነት ከዚህ በላይ በጥቂቱም ቢሆን ለማሳየት እንደተሞከረው ያለፈው አንድ ዓመት ያሉት መረጃዎች በሙሉ የሚያሳዩት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን በማፈን ለማዳከም ያሰበው ትግል ይበልጥ ተጠናክሮና ተቀጣጥሎ በርካታ አንዳርጋቸውዎችን ከማፍራቱም በላይ ብዙዎች ለነጻነታቸው መተኪያ የሌላትን ህይወታቸውን እስከመስጠት የሚያደርስ ዕልህ ውስጥ ገብተዋል። ወያኔ እንዳሰበውና እንዳሰላው ትግሉ መዳከም ሳይሆን መሬት እያያዘና እየተጠናከረ በመምጣቱ የወያኔ ስጋት ከመቼውም ጊዜ ይልቅ እየጨመረ ሄዷል። ይህም ሁኔታ የዛሬ አንድ ዓመት በፊት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ሲያፍን ያሰላው ስሌት እጅጉኑ የተሳሳተ እንደነበረ በግልጽ አረጋግጧል። የወያኔ የአፈና ተስፋ ገና በአፈናው ማግስት እንደ ጧዋት ጤዛ ተኗል። ከአለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በመላው ሀገሪቷ ተጠናክሮ የምናያቸው የወያኔ የጭካኔ እርምጃዎች የሚያመለክቱት ይህንኑ ስጋትና ጭንቀት ነው። የወያኔ የቅዥትና የስጋት የዛፍ ላይ እንቅልፍ፣ ወደ ከፍተኛ ደረጃ ተሸጋግሮና ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ንቅናቄያችን፣ አርበኞች ግንቦት 7፣ ለዕኩልነት ለፍትህና ነጻነት የሚደረግ ትግል፣ በተለይ እንደወያኔ ባለ ዘረኛ አምባገነን ቡድን በበላይነት በሚዘወር ሐገራዊ ሁኔታ ውስጥ፣ ምን ያህል ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን አስቀድሞ ጠንቅቆ ያውቃል። ይህም ሆኖ ግን ባለፈው አንድ ዓመት፣ የትግል ጓዳችን የሆኑት አቶ አንዳርጋቸው በወያኔ እጅ ከወደቁበት ጊዜ ጀምሮ እየደረሰባቸው ያለውን መከራና ስቃይ እንዲሁም ይህ ሁኔታ በቅርብ ቤተሰቦቻቸው ላይ ያስጀመረውን የጭንቀት ዘመን፣ ለአንድ ሴኮንድም ቢሆን መዘንጋት አይችልም።

ንቅናቄያችን አርበኞች ግንቦት 7 በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በአፈናው የተነሳ የደረሰው መከራና ስቃይ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ለፍትህ ለዕኩልነትና ለነጻነት በመቆማቸው በወያኔ አረመኔዎች ቁም ስቅላቸውን የሚያዩት በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሰቆቃ የሚያበቃው፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተባብሮ በሚያደርገው ሁለ ገብ ትግል በመሆኑ ማንኛችንም በአቶ አንዳርጋቸውም ሆነ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ ያለው ጥቃት እንደራሳችን ጥቃት አድርገን የሚሰማን ወገኖች በሙሉ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ከታፈኑበት አንድ አመት ወዲህ የተጀመረውን ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አጠናክረን ወደ ውጤት ደረጃ በማድረስ መጭው ዘመን የሕዝብ የፍትህ የእኩልነትና የነጻነት ተስፋ የሚለመልምበት ፣ የወያኔ አምባገነን ሥርዓት እድሜ የሚያጥርበት ዘመን እንዲሆን የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ንቅናቄያን ወገናዊ ጥሪውን ያቀርባል።

ክብር ለፍትህ ለእኩልነትና ነጻነት መስዋትዕነት ለከፈሉና እየከፈሉ ላሉ ታጋዮች!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

አርበኞች ግንቦት7 ለአንድነትና ዴሞክራሲ ንቅናቄ
ሰኔ 16 ቀን 2007 ዓ.ም.

The post የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ ከዓርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ

$
0
0

ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ, ኦስሎ ተካሄደ!!!

የግንቦት 7 ዋና ፀሀፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በየመን የፀጥታ ሃይሎች ታግተው ለዘረኛውና አፋኙ የወያኔ ቡድን ተላልፈው የተሰጡበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ደረጃ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ በወጣቶች ክፍል አስተባባሪነት በጁን 23/ 2015 በእንግሊዝ ኢምባሲ ፊት ለፊት እልህና ቁጭት የተሞላበት ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ተካሂዷል።

በሰልፉ ላይ ከተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የተገኙ በርካታ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከ13፡30 ስዓት ጀምሮ ታላቋ ብርታኒያ ለዜጋዋ አቶ አንዳርጋቸው ልዩ ትኩረት አድርጋ ከዘረኛው ወያኔ ነጻ በማውጣት ወደ ቤተሰቡ እንዲመለስ ለማሳሰብ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው የነጻነት ታጋዩን አንዳርጋቸውን በተመለከተ የተለያዩ  መፎክሮችን አሰምተዋል።

s3

በዝግጅቱ ወቅት ከተሰሙት መፎክሮች መካከል “አንዳርጋቸው የነጻነት ታጋይ እንጂ አሸባሪ አይደለም” አንዳርጋቸው ነጻ  ይወጣ ዘንድ እንግሊዝ ግፊት ታድርግ”፣ “በአንዳርጋቸው ላይ ለአንድ ዓመት ሙሉ እየደረሰበት ያለው የስቃይና የመከራ ዘመን ይብቃ”፣ እንግሊዝ ዜጋሽ የት ነው?”፣ “እንግሊዝ! ዜጋሽ አደጋ ውስጥ ነውና ደህንነትና ጥበቃ ያዝፈልገዋል፣ የህግ ከለላም እንዲሁ”  “አዎ! እኛ ሁላችን አንዳርጋቸው ነን!” ነጻነት፣ ፍትህና ዲሞክራሲ ያስፈልገናል” በማለት ከፍተኛ ሀገራዊ ስሜት በተንጸባረቀበት መልኩ ጩኸታቸውን አሰምተዋል።

በመቀጠልም አርበኞች ግንቦት ሰባት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ የተሰጠውን መግለጫ ለተሳታፊዎች በድምጽ ተነቧል። መግለጫውም የአቶ አንዳርጋቸው በወያኔ መታገት ንቅናቄው የበለጠ

s21

እንዲጠነክርና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር ውህደት በመፍጠር ትግሉን ወደፊት እንዲሄድ አድርጎታል እንጂ ወያኔ እንዳሰበው ትግሉ ወደ ኋላ እንዳልቀረ ይጠቅሳል።

በመግለጫው ማጠቃለያም በአቶ አንዳርጋቸው ላይ በአፈናው የተነሳ የደረሰው መከራ ስቃይ ብቻ ሳይሆን በአሁኑ ጊዜ ለፍትህ ፣ ለእኩልነትና ለነፃነት በመቆማቸው በወያኔ አረመኔዎች ቁም ስቅላቸውን የሚያዩ በርካታ ቁጥር ያላቸው ዜጎች ሰቆቃ የሚያበቃው የኢትዮጵያ ህዝብ ተባብሮ በሚያደርገው ሁለ ገብ ትግል በመሆኑ ማንኛችንም በአቶ አንዳርጋቸውም ሆነ በሌሎች ወገኖቻችን ላይ እየደረሰ  ያለውን ጥቃት እንደራሳችን አድርገን የሚሰማን ወገኖች በሙሉ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ከታፈኑበት አንድ አመት ወዲህ የተጀመረውን ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ አጠናክረን ወደ ውጤት በማድረስ የመጪው ዘመን የህዝብ የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ተስፋ የሚለመልምበት የወያኔ አምባገነን ስርአት እድሜ የሚያጥርበት ዘመን እንዲሆን ሁላችንም የምንችለውን ሁሉ እንድናደርግ ወገናዊ ጥሪ አስተላልፈዋል።

በመጨረሻም በዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በተወካዮች አማካኝነት ለኢምባሲው ከተሰጠ በኋላ የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት  ዝግጅቱ በታቀደለት ስዓት በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

 

The post አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በወያኔ የታፈኑበትን አንደኛ ዓመት ምክንያት በማድረግ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከገዥው ወገን የምንለይበት፤ አንዱዓለም ተፈራ –የእስከመቼ አዘገጅ

$
0
0

ማክሰኞ፤ ሰኔ ፲፮ ቀን ፳፻፯ ዓመተ ምህረት

tplfእኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለትግሬዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦሮሞዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአማራዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሶማሌዎች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአፋሮች ጥብቅና እቆማለሁ፣  እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለኦጋዴኖች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለአኙዋኮች ጥብቅና እቆማለሁ፣ እኔ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የበለጠ ለሲዳማዎች ጥብቅና እቆማለሁ፤ የሚል ግለሰብም ሆነ ድርጅት፤ ከያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ይልቅ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ጋር የበለጠ የጋራ የሆኑ መቀራረቢያ ጉዳዮች ስላሉት፤ ሰፈሩን ወደዚያ ቢያቀና ይቀለዋል።

የኢትዮጵያ ሕዝብ ከአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ጋር መሠረታዊ ልዩነቱ፤ እያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊያን፤ “እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ። በሀገሬ በኢትዮጵያ የማደርገው ማንኛውም የፖለቲካ ተሳትፎ፤ በኢትዮጵያዊነቴ ብቻ ነው። በኢትዮጵያዊነቴ ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ባልተለዬ ሁኔታ፤ እኩል በፖለቲካ ምኅዳሩ፤ የግለሰብ ዴሞክራሲያዊ መብቴ ተከብሮልኝ፤ በማንኛውም የሀገሬ ክልል፤ የመኖር፣ ሀብት የማፍራት፣ በአካባቢውና በሀገር አቀፍ የፖለቲካ ሂደት ተሳትፎ የማድረግ ሙሉ መብት አለኝ።” ስንል፤ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ደግሞ፤ “የለም ኢትዮጵያ የትግሬዎች፣ የአማራዎች፣ የኦሮሞዎች፣ የደቡቦች፣ የሶማሌዎች፣ የአፋሮች፣ የአኝዋኮች ነች። ግለሰብ ኢትዮጵያዊ የሚባል የለም። እናም የፖለቲካ ተሳትፎ የሚደረገው በነዚህ ክልሎች ዙሪያ እንጂ፤ በኢትዮጵያዊነት አይደለም።” የሚለው ነው።

ከዚህ በመነሳት፤ አምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት፤ አስተዳደሩን በዚህ ላይ ተከለ። በሂደቱም የተለያዩ ለየብቻቸው የተካተቱ ክልሎችን መሠረተ። አያንዳንዱ የዚህ ገዢ ቡድን ተቀጥላ ጥገኛ የክልል የፖለቲካ ድርጅት፤ የራሱን የክልሉ ተወላጆች ብቻ በክልሉ ለመክተትና ለማስተዳደር ሙሉ መብት አገኘ። እናም በገዥው ቡድን ፈቃድና ፍላጎት፤ ሌሎችን ከክልሉ ማባረር፣ ሀብታቸውን መዝረፍ፣ መግደል፣ አይቀሬ ሆነ። በተግባርም ተፈጸመ። ሀገራችንን ፍጹም ወደማትመለስበት አዘቅት ለመክተት፤ ይኼው ገዥ ቡድን ተሯሯጠ። ተከትለው የሚሄዱት የሕዝቡን ድምጽ ማፈን፣ ሀገሪቱን እስር ቤት ማድረግ፣ አንገቱን ሰብሮ የማይገዛውን ማሰር፣ ማባረርና መግደል፤ ተዥጎደጎዱ። ለዚህ ተቃውሞ፤ ኢትዮጵያዊያን የተለያዩ ድርጅቶችን መሥርተው በመታገል ላይ ናቸው። እንግዲህ በዚህ ትግል፤ ሁለት ሰፈሮች ብቻ በገሃድ አሉ። አንደኛው የሕዝቡ ሰፈር ነው። ሌላው የአምባገነኑ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ሰፈር ነው። የግለሰብ ሆነ የድርጅት ጉዳይ እዚህ ቦታ የለውም። የግለሰብ እምነት ወይንም የድርጅት መርኀ-ግብር፤ ከሁለቱ መርጠን ባንዱ ሰፈር እንድንሰለፍ ያደርገናል። የሰልፉ መለያ ደግሞ፤ የፖለቲካ ፍልሰፍናችን እና ከዚህ የሚመነጨውና በተግባር ለማዋል የምንፈልገው የአስተዳደር መመሪያ ነው።

ይህ ነው የአሁኑ የሀገራችን የኢትዮጵያ የፖለቲካ እውነታ። ይሄን በጁ ያልጨበጠ ማንኛውም ሂደት፤ መዳረሻው ተመልሶ ያው ነው። የድርጅት መሪዎችም ሆኑ ታጋይ ግለሰብ ኢትዮጵያዊያን፤ መሠረታዊ የሆነውን የልዩነት ነጥብ በማንገት፤ ትግሉን መልክ ሠጥተን መሄድ አለብን። አማራ ነኝና ከሌሎች የበለጠ ለአማራዎች እኔ ነኝ ተቆርቋሪ፣ ለኦሮሞዎችም፣ ለትግሬዎችም፣ ለሶማሌዎችም፣ ለአፋሮችም፣ ለአኙዎኮችም፣ ለሲዳማዎችም እኔ ነኝ ተቆርቋሪ የሚለው አባባል፤ የኢትዮጵያዊነት ጠላት ነው። እንደ ኢትዮጵያዊ ካላሰብን፤ ኢትዮጵያዊነት በውስጣችን የለም። እንደ ኢትዮጵያዊ ካልታገልን፤ ኢትዮጵያ የለችም። በሀገራችን፤ ለኢትዮጵያዊያን ሉዓላዊነት፣ ለሀገራችን ዳር ደንበር መከበር፣ ለያንዳንዳችን ዴሞክራሲያዊ መብት የምንታገለው በኢትዮጵያዊነታችን ነው። አንዳችን ከሌላችን ጎን የምንሰለፈው፣ የያንዳንዳችን ጉዳይ የሌላችን በመሆኑ ነው። አለዚያ፣ አንተም ለራስህ እኔም ለራሴ ከሆነ፤ ትግሉ ለኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያ ሳይሆን፤ በየኪሳችን ለያዝነው ዘውድ ነው። መነሻችን ይሄ ከሆነ፤ መድረሻችን ኢትዮጵያ ናት።

ይሄን እንድጽፍ ያስገደደኝ፤ ስለሰላማዊ ትግል የመጀመሪያውን ክፍል ባቀረብኩበት ወቅት፤ ከሌሎች የተላኩልኝ አፀፋዎች ነው። የገዥውን ስም ለምን “ትግሬዎች” ትላለህ የሚለው በተደጋጋሚ የቀረበልኝ ቢሆንም፤ ባሁኑ ሰዓት ቁንጮው ላይ ደረሰ።

እናም ይሄን ጻፍኩ። እኔ ራሳቸውን እንዲጠሩበት በመረጡት ስም ነው የጠራኋቸው። ለኔ ካላይ እንደገለጽኩት የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ነው። ኢትዮጵያ አንድ ናት። ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊያን ናት። በትግራይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን፤ ትግሬዎች ይባላሉ። በአፋር ያሉት ኢትዮጵያዊያን አፋሮች ይባላሉ። ታዲያ ትግሬዎችን ነፃ አወጣለሁ ብሎ የተነሳ ግንባር፤ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ነኝ ሲል፤ ሌላ ምን ብዬ ልጠራው ነው። የትግራይ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ካልኩማ፤ ሰፈሬ ከገዥው አምባገነን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር አይሆንም ወይ? ለኔ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንጂ የትግራይ ሕዝብ፣ የአማራ ሕዝብ፣ የኦሮሞ ሕዝብ፣ የሶማሌ ሕዝብ፣ የሲዳማ ሕዝብ፣ የአኝዋክ ሕዝብ፣ የቤንሻንጉል ሕዝብ፣ የወላይታ ሕዝብ የለም። እናም፤ የትግራይ ሕዝብ ነፃ አውጪ ግንባር ብዬ አልጽፍም። ለምን ይሄን ጽፍክ የሚለኝ ካለ፤ ሄዶ ስም ያወጣውን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር ይጠይቅ።

በሀገራችን ያለው ትግል፤ ሀገርን ከአምባገነን ፀረ-ኢትዮጵያ የሆነ ጠላታችን አንጻር፤ ልዩነታችን በግልጽ ወጥቶ፣ ተሰላፊዎች ባደባባይ ታውቀን የቆምንለት እንጂ፤ አንዳችን ሌላችንን የምንለማመጥበት ጉዳይ አይደለም። ትግሉ የመላ ሕዝቡ እንጂ፤ የዚህ ወይንም የዚያ ወገን የግል ጉዳይ አይደለም። ታጋዩን የሕዝብ ወገን ወደ አንድ ማሰባሰቡ የትግሉ የመጀመሪያ ግዴታ ነው። በርግጥ መተባበር የዲፕሎማቲክ ሥራ እንጂ፤ አንተም ባፈተተህ የሚባልበት ሂደት አይደለም። በቅርቡ የተለያዩ ታጋይ ድርጅቶች ቢያንስ ተገናኝተው ለመነጋገር ይችሉ እደሆነ በማሰብ፤ ጥረት አድርጌ ነበር። ይሰበሰቡና መፍትሔ ያቀርቡልናል የሚል ብዥታ አልነበረኝም። ነገር ግን፤ በሂደቱ ሁላችን ሀገራችን ያለችበትን አደጋ በመመልከትና ቅድሚያ ለሀገር ብለን፤ በድርጅት ያሉትም ሆነ ግለሰብ ታጋዮች፤ የመሰባሰቡን ሂደት ያቀላጥፉታል ብዬ ነበር። አልተሳካም። ትግሉ ከገዥው አምባገነን ጋር የምንፋለምበትን ጉዳይ በቅርብ በልብ አንግተን፤ የጠራና ፀሐይ የሞቀውን ልዩነታችንን ባደባባይ አንግተን የተነሳንበት ግብግብ ነው። ይሄን ላስደስት፤ ያንን ላቆላምጥ የሚባልበት አይደለም። በተለይ በሥልጣን ላይ ያለን መንግሥት ለመለወጥ የሚደረግ ትግል፤ የጠራ አመለካከት ከሌለው፤ ትግሉ ውጤታማ አይሆንም። ጠላት ማነው፣ የምንታገለው ለምንድን ነው? ግባችን ምንድን ነው? መመለስ ያለባቸው ጥያቄዎች ናቸው። በዚህ ትግል፤ ጠርተው የሚወጡ ጽንሰ-ሃሳቦች አሉ። እኒህ የትግሉን ሂደት ይተረጉሙታል። ግንዛቤን ያዳብራሉ። በሥልጣን ላይ ያለውን ገዢ ቡድን ማንነቱን ለመግለጽ የምንጠቀምበት ስም፤ ራሱን ግልጽ አድርጎ የሚጠራበትና የሚጠራበት መሆኑ፤ በትግሉ ላይ ትልቅ አስተዋፅዖ አለው። የምናየው የትግል አሰላለፍ ትርጉሙ የሚመነጨው፤ ከግንዛቤያችን ላይ በመቆም ነው።

በአንድ በኩል ጠላታችን የሚታወቀው ራሱ ነኝ ብሎ ባወጣው ስም እንጂ፤ እኛ በምናወጣለት ስም አይደለም። በሌላ በኩል ደግሞ በመካከላችን እብሪተኛን እብሪተኛ ማለት ካልቻልን፤ ታጋዮች ሳንሆን ወሬኞች ነን። ከሁሉም በላይ የሀገሬ ጉዳይ ብሎ ያልተነሳ ታጋይ፤ የሕዝቡ ወገን ሊሆንም ሆነ ታግሎ የሕዝቡን ድል ሊያስገኝ አይችልም። ቢሳካለት ገዥውን መተካት ነው ሩጫው።

 

The post ከገዥው ወገን የምንለይበት፤ አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘገጅ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሃይለማርያም ደሳለኝ የጃኪ ጎሲና የአርከበ የኤርትራ ጉዞ ወሬ

$
0
0

Hailemariam desalegn

ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ፣ አስመራ ድረስ ሄደዉ ከአቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር ለመነጋገር ዝግጁ እንደሆኑ ለአልጃዚራ በዲሴምበር 2012 ገልጸው ነበር:: ሰሞኑን ደግሞ የመለስ ራዕይ የሚባል ገደል ይግባ ያሉት አቶ አርከበ እቁባይ የመንግስት አቋም በሚንጸባረቅበት ዘመን መጽሔት “በኤርትራ ለውጥ ይመጣል; የኤርትራን ወደብ መጠቀም እንጀምራለን” ባሉ በነጋታው ድምፃዊው ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) አስመራ ሄጄ የሙዚቃ ኮንሰርት ማቅረብ እፈልጋለሁ ብሎናል:: የጃኪና የአርከበ ምኞቶች የተገለጹት በመንግስት ሚዲያዎች ነው:: ፎቶውን ይመልከቱና አስተያየትዎን ያስቀምጡ::

The post የሃይለማርያም ደሳለኝ የጃኪ ጎሲና የአርከበ የኤርትራ ጉዞ ወሬ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ አይሲኤስን ለመቃወም ሰልፍ የወጣችው ወ/ሮ ንግስት ወንድይፍራው እስራት ተፈረደባት

$
0
0

nigist wendifraw

አረመኔው የሕወሓት መንግስት አይ ኤይ አይ ኤስ በኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ላይ ላይ የፈፀመውን ዘግናኝ ድርጊት ለመቃወም በተጠራው ሰልፍ ሰበብ የታሰረችው ወ/ሮ ንግስት ወንዲፍራው ዛሬ ሰኔ 17/2007 ዓ.ም ቄራ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት ቀርባ የ8 ወር እስራት እንደፈረደባት ከሰማያዊ ፓርቲ የተገኘ መረጃ አመለከተ::

“የውጭ ሬሳ የአገር አንበሳ” እየተባለ የሚጠራው ይኸው አረመኔው የሕወሓት አስተዳደር አይሲኤስን ለመቃወም የወጡ በርካታ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያኑን ያሰረ ሲሆንከነዚህም ውስጥ ንግስት ወንዲፍራው ግንቦት 19/2007 ዓ.ም ያለ ማዘዣ ከ3 አመት ልጇ ጋር በፖሊስና ደህንነቶች ተይዛ 6ኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስራ መቆየቷ ይታወሳል::

The post በአዲስ አበባ አይሲኤስን ለመቃወም ሰልፍ የወጣችው ወ/ሮ ንግስት ወንድይፍራው እስራት ተፈረደባት appeared first on Zehabesha Amharic.


ጂ ሜይል በስህተት የተላከ መልዕክት ለማጥፋት የሚያስችል መተግበሪያ ጥቅም ላይ አዋለ

$
0
0

gmail
በሙለታ መንገሻ
ጂ ሜይል / Gmail/ በስህተት የላክነውን መልዕክት በ30 ሴኮንድ ውስጥ ለማጥፋት የሚያስችል /undo/ መተግበሪያ ጥቅም ላይ ማዋሉን አስታውቋል።

ይህም በስህተት የላክነው መልዕክት የላክንለት ሰው እንዳያየው የሚያስችል ነው ተብሎለታል።

የጂ ሜይል አካውንት ያላቸው ሰዎችም ሴቲንግ ውስጥ በመግባት undo የሚል ቦታ ላይ በመጫን የሴኮንዱን እርዝመት በመሙላት መጠቀም የሚቻል መሆኑን ኩባነያው አስታውቋል።

አዲሱ የጂ ሜይል አገልግሎትም በስህተት የላክነውን መልዕክት የላክንለት ሰው ጋር ደርሶ ከመታየቱ በፊት ለማጥፋት የሚረዳ በመሆኑ ሰዎችን ከስህተት የጸዳ ስራ እንዲሰሩ ያስችላልም ተብሏል።

ጂ ሜይል ከ11 ዓመታት በፊት አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን፥ እስካሁንም በዓለም ዙሪያ ከ900 ሚሊየን በላይ የጂሜይል አካውት ያላቸው ሰዎች እንዳሉም ጎግል ባሳለፍነው ወር ባወጣው ሪፖርት አስታውቋል።

ምንጭ፦ news.sky.com

The post ጂ ሜይል በስህተት የተላከ መልዕክት ለማጥፋት የሚያስችል መተግበሪያ ጥቅም ላይ አዋለ appeared first on Zehabesha Amharic.

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ ህይወት አዳነ

$
0
0

jersy
(አድማስ ዜና) ባህሬን ፦ አሲያ አብዱ ትባላለች፣ ባህሬን ከመጣች ሁለት ሳምንት ቢሆናት ነው፣ እሷ እንደምትለው ፣ የመጣችው ለደላላ 8ሺ ብር ከፍላ ሲሆን፣ የልብ ህመም አለባት፣ እናም ከመጣች በኋላ መስራት አልቻለችም። ስለዚህ አስሪዎቿን መስራት እንዳቃታትና ወደ አገሯ መመለስ እንደምትፈልግ ትነግራቸዋለች።

እነሱ ግን ፣ ያወጣነውን ወጪ መልሰሽ፣ ከዚያም የራስሽን ትኬት ገዝተሽ ነው እንጂ፣ እንዲሁ አንለቅሽም ይሏታል። ከዚያም ለአራት ቀናት ያህል በአንድ ክፍል ውስጥ ዘግተውባት ስታለቅስ ትከርማለች፣ ታዲያ በመካከል ከነበረችበት አራተኛ ፎቅ መስኮት ከፍታ ለመወርወር ስትዘጋጅ፣ ድንገት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ የለበሰ ወጣት ሲያልፍ በመመልከቷ በጩኸት ድረስልኝ ትላለች። ልጁም ያለችበት ተጠግቶ፣ ክፎቅ ላይ እንዳትወድቅ በመለመን አሳምኖ፣ እዚያው እንደቆመ፣ ለባህሬን የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እና ለፖሊስ ይደውላል።

የኮሚኒቲው ተወካይ ከቦታው ደርሶም ጉዳዩን ካየ በኋላ፣ ፖሊስ እስኪመጣ ድረስ ከውጭው ከባድ ሙቀት ለመራቅ ጥግ ይዞ ሳለ፣ ከልጅቷ ቤት ጩኸት ይሰማል፣ ሮጦ ፎቁ ላይ በመውጣት ሲገባም፣ አስሪዋ ልጅቷን ማሰቃየቱና ጨለማ ቤት ማስቀመጡ እንዳይታወቅበት፣ በጓሮ ይዟት ሊወጣ ሲጎትታት ይደርሳል፣ ያን ጊዜ እሷን አስጥሎ፣ ወዲያውም ርዳታው ደርሶ ልጅቷ በህይወት ተርፋ የባህሬ ኮሚኒቲ ጽህፈት ቤት በአሁኑ ሰአት እንደምትገኝ ታውቋል።

The post የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ማሊያ ህይወት አዳነ appeared first on Zehabesha Amharic.

ቆራጡ የዲሞክራሲ ታጋይ ዳዊት አስራደ ከሀገር ተሰደደ!!

$
0
0

እየጎመዘዘኝ የሰማሁት ዜና ነው!!

11659237_1018365658188047_2011915667152766052_nወጣቱ ፖለቲከኛ ዳዊት አስራደ የሚወዳቸውን ቤተሰቡንና ልጁን ትቶ ከሀገር መሰደዱ ተሰምቷል፡፡ ዳዊት ከ13ቱ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ የስራ አስፈጻሚ እንዲሁም የብሄራዊ ምክር ቤት አባልና የአንድነትን የአምስት አመት ስትራቴጂክ እቅድም ከሌሎች የፓርቲው አመራሮች ጋር በመሆን የነደፈ ሙሉ ማንነቱን ለሀገር ትግል የሰጠ ቁርጥ ኢትዮጵያዊ ልጅ ነው፡፡ በ2002 ዓ.ም በአማራ ክልል ምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያለ በመኪና ተገጭቶ ለ6 ወራት ተኝቶ ከሞት ድኗል፡፡

በ97 ዓ.ም በቅንጅት ፓርቲ ውስጥ ፖለቲካዊ ተሳትፎውን የጀመረው ዳዊት አስራደ የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ መስራች አባልም ነበር፡፡ ዳዊት በፓርቲው የተለያዩ ሓላፊነቶች ላይ የሰራ ሲሆን ለአብነትም

– በወጣቶች የትምህርትና ስልጠና ዘረፍ

– የብሄራዊ ምክር ቤት ቋሚ አባል

– የብሄራዊ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና ዋና ጸሀፊ

– የኢኪኖሚ ጉዳዮች ሃላፊና በተለያዩ የአድሆክ ኮሚቴዎች ውስጥ በሀላፊነትና በአባልነት ሰርቷል፡፡

የአንድነትን የ5 አመት እቅድና ስትራቴጂ ከነደፉት ሰዎች መካከልም ዳዊት አለበት፡፡ በ2002 ምርጫ አንድነት መድረክን ወክሎ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሰላም ከተማ ተወዳዳሪ ነበር፡፡ ሆኖም በ2007 የአንድነት ፓርቲ በምርጮ ቦርድ ለነ ትግስቱ አወል መሰጠቱን በመቃወም ከፓርቲው ሙሉ በሙሉ ቢገለልም በገጠመው ተደጋጋሚ እስርና እንግልት ምክንያት ሀገሩን ትቶ ሂዷል፡፡

መንግስት በሽብር ቡድኖች በሊቢያ የተቀጠፉ ኢትዮጵያውያንን ለማውገዝ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ቪዲዮ ቀርጻሃል›› በሚል ሚያዚያ 14 ቀን 2007 ዓ.ም. በፖሊስ ተይዞ ቄራ ፖሊስ ጣቢያ ገባ፡፡ ሰልፉን በሞባይል በቀረጸበት የ25000.00 ብር ዋስ እንዲለቀቅ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ምድብ ችሎት ወሰነ፡፡ ሆኖም አቃቢ ህግ ወዲያውኑ በ14 የተደረገውን ሰልፍ ለማወክ በ13 ከ200-300 የሚሆኑ ወጣቶችን አደራጅተሃል የሚል ተጨማሪ ክስ መሰረተበት፡፡ ይህን ክስ ደግሞ በ6000.00 ብር መያዣ ይፈታ ሲባል በእለቱ ስብሰባው ላይ ችግር ፈጥረሃል የሚል ክስ ታከለለት፡፡ ለዚህ ደግሞ 5000.00 ብር አስይዝ ተባለ፡፡

ሚያዚያ 14 በቄራ፣ ከሚያዚያ 15- 21 በፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያዎች ታስሮ ቆየ፡፡ ሚዚያ 21 ቀን ባስያዘው ገንዘብ ተፈቶ ሳይሰደድ ሲቀር ይምሰላል በግንቦት 3 ቀን ከፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ተደወለለት፡፡ ያስያዝከውን ንብረት ውሰድ ነጻ ነህ አሉት፡፡ ሲሄድ ግን ታሰረ፡፡ ሶስት ቀን ፔፕሲ ፖሊስ ጣቢያ ከቆየ በኋላ ወደ ማእከላዊ ተወሰደ፡፡ ከዚያ በኋላ ባሉት ጊዘያት እስከ ሰኔ 5 ቀን በማእከላዊ እስር ላይ ቆይቶ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የአቃቂ ምድብ ችሎት በእለቱ እንዲፈታ ወሰነ፡፡ እስካሁን ያዝያዘው 36000.00 ያልተመለሰለት ሲሆን ሰኔ 19 ቀን ፍርድ ቤት እንዲገኘ ሌላ ቀጠሮ ተሰጠው፡፡

ዳዊት በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ባሉ መርማሪ ፖሊሶች ከኢህአዴግ ጋር እንዲሰራ ግብዣ ቀርቦለት ነበር፡፡

ዳዊት አስራደ በተለያዩ ባንኮች በተለያየ የሃላፊነት ቦታ ላይ ሰርቷል፡፡ አገር ጥሎ በወጣበት ወቅትም በህብረት ባንክ ዋና መስሪያ ቤት የአንድ ክፍል ዋና ሓላፊ እና ጥሩ ደመዝ ተከፋይም ነበር፡፡ ዳዊት የአንድ ልጅ አባትና ባለትዳር ነው፡፡

ሆኖም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ስርዓቱ እግር ተወርች አስሮ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ በዚህ ሳምንት አገሩን ጥሎ መጥፋቱ ተገልጧል፡፡

(ዛሬ የሰማሁት መራር ዜና ነው- የዳዊት አስራደ ስደት፡፡ ይህን ቆራጥ ሰላማዊ የዲሞክራሲ ታጋይ በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ የሚወደውን ልጁን፣ የሚያፈቅራትን ሚስቱን እና ሀገሩን ትቶ መሰደዱን ስሰማ ከልቤ አነባሁ፡፡ )

– See more at: http://satenaw.com/amharic/archives/8067#sthash.3jr38q3y.dpuf

The post ቆራጡ የዲሞክራሲ ታጋይ ዳዊት አስራደ ከሀገር ተሰደደ!! appeared first on Zehabesha Amharic.

የአቶ አስገደ ገ/ሥላሴ አዲሱ “የመለስ ራዕይ ሲፈተሽ”መጽሐፍ በአሜሪካ መሸጥ ጀምሯል – (የት እንደሚገኝ እንጠቁምዎ)

$
0
0

አቶ አስገደ ገብረሥላሴ የ’መለስ ራዕይ ሲፈተሽ’ የሚል መጽሐፍ ማሳተማቸው ይታወሳል:: መጽሐፉ በሰሜን አሜሪካም ለገበያ የቀረበ ሲሆን የት ቦታዎች እንደሚገኝ ፎቶ ግራፉ ላይ በመጫን ማየት ትችላላችሁ::
asegede gebresilase

The post የአቶ አስገደ ገ/ሥላሴ አዲሱ “የመለስ ራዕይ ሲፈተሽ” መጽሐፍ በአሜሪካ መሸጥ ጀምሯል – (የት እንደሚገኝ እንጠቁምዎ) appeared first on Zehabesha Amharic.

መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለበት ይገኛል

$
0
0

Shimeles Kemal
<<ሰለፊስቶች ባሉበት ሁሉ ጦርነት፣ሁከት፣ብጥብጥ ይኖራል>> አቶ ሽመልስ ከማል ከተናገሩት!

 

አቡበከር አህመድ
መንግስት በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለ ሲሆን ከምርጫ ማግስት በአዳማው ቲታስ ሆቴል በተካሄደውና የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ባዘጋጀው ስብሰባ ላይ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ዋና ኃላፊ የሆኑት አቶ ሬድዋን ሁሴንና በተለይ ምክትላቸው አቶ ሽመልስ ከማል መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ዘልቆ መግባቱን የሚያስረዱ ንግግሮችን አድርገዋል። አቶ ሬድዋን ሁሴን በዋናነት ሽብርተኝነት በተመለከተ በምዕራባውያን እይታና በኢትዮጵያ መንግስት እይታ መካከል ያለውን ልዩነት አብራርተዋል።
ምክትላቸው አቶ ሽመልስ በበኩላቸው በአሁኑ ወቅት በሀገራችን በእስልምና እምነት ስር ሰለፊዝም በሚባለው አስተምህሮት አማካኝነት ወደሽብር እየገባች እንደሆነ ያስረዱ ሲሆን በንግግራቸውም <<ሰለፊዝም ባለበት ቦታ ሁሉ ጦርነት አለ የሰለፊዝም አስተሳሰብ የሚያራምዱ አካላት ሁሉ ዓለማዊ መንግስት አይቀበሉም በሸሪዓዊ ስርዓት ብቻ ነው የሚያምኑት የሀገርን ህልውና ያፈራርሳሉ ለምሳሌ አይኤስአይኤስ (ISIS) የተባለውም ቡድን ይሄ ነው አላማው በሀገራችንም እነዚህ አካላት እራሳቸውን ማጠናከር ጀምረው እስከሚኖሩበት አከባቢም መነጠል ጀምረዋል ለምሳሌ ኮልፌና አየር ጤና ይሄንን አስተሳሰብ ልንከላከለው ይገባል ከዚህ ቀደም በሀገራችን የነበረው የሱፊዝም እስልምና ተከታዮች ከህብረተሰቡ ጋር አብረው መኖር ይችላሉ። አሁን የዚህ ተከታዮች እየጠፉ ነው አስተማሪዎቻቸውም እንዲጠፉ እየተደረገ ይገኛል ይሄንን አስተምህሮት ልንደግፈው ይገባል ለዚህ ትልቁን ድርሻ እየተወጣ ያለው አንዱ የሰለፊዝም አካል ወሀቢዝም የሚባለው አስተምህሮት ነው። በሀገራችን ከ2004 ጀምሮ የተከሰተው የእምነት ችግር ከዚሁ ጋር ይያያዛል በወቅቱ ለዚህ ተጠያቂዎቹ አሁን በእስር ላይ ሆነው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ ይገኛሉ ወሀብዮችና ሰለፊስቶች አንድ ናቸው በአካሄድ ብቻ ልዩነት አላቸው እነዚህ አካላት ከዚህ በላይ ከተጠናከሩ እንደ ናይጄሪያ ትልቅ ቀውስ ማስከተላቸው አይቀርም በገንዘብ አቅም በኩል ጎልበተዋል በቴክኖሎጂም ሚፈልጉትን የሚፈፅሙበት ላይ ይገኛሉ>> በማለት በጥቅሉ መንግስት አሁንም በእስልምና ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደሚቀጥል የሚያረጋግጥ ንግግር አድርገዋል።
ከመድረኩ ተሳታፊዎች በርካታ ጥያቄዎች የተጠየቁ ሲሆን ከዚህም ውስጥ ፓሊስ በህግ ስር ታራሚዎችን የሚይዝበት መንገድ አግባብነት፣ የፕሬስ ነፃነትና የመሳሰሉት ይገኙበታል።
ምንጭ: ሪፓርተር

The post መንግስት አሁንም በእስልምና እምነት ላይ ጣልቃ መግባቱን እንደቀጠለበት ይገኛል appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>