Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

የመስጊድ ኢማሞች የሚሾሙት በመንግስት በራሱ መሆኑን መንግስት አመነ!!!

$
0
0

ሕዝቡ ሳያውቀው ሕገ መንግስቱ ተቀይሮ ይሆን?

መንግስት ‹‹እኔ በሾምኳቸው የመስጊድ ኢማሞች (አሰጋጆች) አልሰገዳችሁም›› በሚል ንጹሀን ሙስሊም ግለሰቦች ላይ ክስ ያቀረበበት ሰነድ ተገኘ!!!
ከፍርድ ቤት የውስጥ ምንጮቻችን የተገኘውና በፌደራል አቃቤ ህግ አቶ ብርሀን አለባቸው ፊርማ በታህሳስ 4/2006 የተጻፈው ይኸው የክስ ሰነድ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አዲስ ከተማ ምድብ የቀረበ ሲሆን ሁለት መስጂድ ውስጥ በኢማምነት ያሰገዱ ሙስሊም ግለሰቦችንም ተከሳሽ አድርጎ አቅርቧል፡፡
muslim

ሰነዱ እጅግ አስገራሚውን ክስ ሲያብራራ አንደኛና ሁለተኛ ተከሳሽ በቁባ መስጂድ የአህባሽ ተከታዩን ኢማም ተከትሎ ለመስገድ ፍቃደኛ ያልሆነውን ህዝበ ሙስሊም ማሰገዳቸውንና በዚህ ተግባራቸውም ‹‹የሃይማኖት ሰላም ስሜት›› መንካታቸውን ገልጿል፡፡ ቃል በቃልም ሁለተኛ ተከሳሽ ‹‹መንግስት በሾመው ኢማም ቦታ ላይ በመቆም ሳይፈቀድለት የእነሱን ተከታዮች በማሰገድ ሰላማዊው ሙስሊም እንዳይሰግድ በማድረግ…›› ወንጀል መስራቱን ገልጿል፡፡
እስካሁን ‹‹መንግስት በሃይማኖት ጣልቃ አይገባም የሚለውን ህገ መንግስታዊ መርህ አልጣስኩም›› እያለ ሲከራከር የቆየው መንግስት በተለያዩ አጋጣሚዎች ሲጋለጥ የቆየ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን አሁን ግን መከራከሩ እንደማያዋጣው አውቆ በማን አለብኝነት ‹‹እኔ የሾምኩትን ኢማም አልተከተላችሁም›› በሚል ፍርድ ቤት ችሎት ማሰየም መጀመሩ ‹‹ህገ መንግስቱ አንድ ቀን ይከበር ይሆናል›› ለሚሉ ወገኖች ትልቅ መርዶ ይዞ መጥቷል፡፡ የአገሪቱ ‹‹የፍትህ›› አካላት የሆኑት ዳኞች እና አቃቤ ህጎች መንግስት የሾመውን ኢማም ተከትላችሁ አልሰገዳችሁም›› በሚል ኢ-ህገ መንግስታዊ ክስ ላይ በይፋ መሰየማቸውም ለሀገሪቱ የፍትህ ስርአት የቁልቁለት አዘቅት መሆኑ አያጠራጥርም!
ህዝበ ሙስሊሙ ከ1987 ጀምሮ በመንግስት ሹመኞች ቁጥጥር ስር የዋለውን መጅሊስ ተቀባይነት የነሳውና ለመሪ ተቋሙ መመለስም እስካሁን እየታገለ ያለው መጅሊሱ የመንግስት ካድሬዎች መጫወቻ በመሆኑ እንደሆነ የሚታወቅ ሲሆን በመጅሊሱ ስም የሚካሄዱት ሁሉም ተግባራት በመንግስት የሚሾፈሩ መሆናቸውም የአደባባይ ምስጢር ሆኖ ቆይቷል፡፡ የዛሬውን ዜና ልዩ የሚያደርገው ግን መንግስት ‹‹ሽብርተኝነት›› እና ሌሎች የማስመሰያ ስሞች ሳያስፈልጉት ‹‹እኔ የመረጥኩልህን እምነት አልተከተልክም፤ እኔ በሾምኩልህ ኢማም አልሰገድክም›› ሲል በግልጽ በሰነድ ጭምር ምስክር ጠርቶ ችሎት ፊት ሰዎችን ማቆሙ ነው፡፡ ይህም ይፋ መውጣቱ መንግስት የደረሰበትን የሃይማኖታዊ አፈና ደረጃ ለመላው ዓለምና ለሰብአዊ መብት ተከራካሪ ተቋማት ይበልጥ ይፋ የሚያደርግ መሆኑ አያጠራጥርም፡፡
አዎን! የመንግስት ሃይማኖታዊ ጭቆና በምንም መልኩ መደበቅ የማይችልበት ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ግን ከሁለት አመታት በላይ ኢ-ፍትሀዊነትን ሲታገል የቆየው ህዝበ ሙስሊም የበለጠ በትግሉ ላይ እንዲጠናከር የሚያደርገው እንጂ ተስፋ የሚያስቆርጠው አይደለም፤ ህዝብ ተስፋ አይቆርጥም! ህዝበ ሙስሊሙ የሃይማኖት ነጻነቱ እስኪከበርና የዜግነት መብቱን የሚጋፉ አሰራሮች እስኪቀረፉ ድረስ በጽናት መታገሉን ይቀጥላል፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!!!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!


ኢትዮጵያዉያን በዛሬዉ እለት ረዳት ፓይለት ሐይለመድህን አበራን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ

$
0
0

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 17/2006 (ቢቢኤን )፦ቁጥራቸዉ በመቶዎች የሚቆጠር እትዮጵያዉያንንና ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን በዛሬው እለት ዋሽንግተን ዲስ በሚገኘዉ የሲዉዘርላንድ ኤምባሲ ፊትለፊት ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ ሲሆን የሲዉዘርላንድ መንግስት ረዳት ፓይለቱን ለኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጥም ጠይቀዋል።
ጠለፋዉ ለከት ያጣ ጭቆና ዉጤት ነዉ ያሉት ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዎች ሐይለመድህን አንባገነናዉያን የፈጠሩት ስጋት ሰለባ የሆነ ሙያተኛ ቢሆን እንጂ ለማንም ለምንም ስጋት የሚሆን አይደለም ሲሉም ድምጻቸዉን አሰምተዋል።
ረዳት ፓይለት ሐይለመድህን በአንባገነናዊዉ የኢትዮጵያ መንግስት ተንገፍግፎ የዘጠና ሚሊዮን ህዝብ ድምጽን ለማሰማት መስዋእትነት የከፈለ ጽኑ ኢትዮጵያዊ ነዉ፤ ከተስፋሪዎች መጉላላት በስተቀር ማንንም አደጋ ላይ አልጣለም፤ ሐይለመድህን የኛ ጀግና ነዉ! የሲዉዘርላንድ መንግስት እንደወንጀለኛ ሳይመለከተዉ በነጻ ሊለለቀዉ ይገባል ሲሉም ተማጽነዋል።
IMG_6350
የሲዉዘርላንድን መንግስት በመወከል ከኤምባሲ የመጡት ግለሰብም ሰላማዊ ሰልፍ አድራጊዉ ሰላማዊ መሆኑን አድንቀዉ ካመሰገኑ በሗላ የተሰጣቸዉን ደብዳቤ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚልኩ በማስታወቅ የተቻለዉን ሁሉ እንደሚያደርጉ ቃል ገብተዋል።

ረዳት ፓይለት ሐይለመድህን አበራን በየካቲት 10/2006 ሁለት መቶ ሁለት ተሳፋሪዎችን የጫነዉን ቦይንግ 767-300 በረራ ቁጥር ET-702 በመጥለፍ ጄኔቫ አሳርፎ የፖለቲካ ጥገኝነት የጠየቀ ሲሆን እስከ አሁን በሲዉዘርላንድ መንግስት ቁጥጥር ስር ይገኛል።
IMG_6353 (1)

የሐይለመድህን ቤተሰቦች ፓይለቱ የአእምሮ ህመም እንዳጋጠመዉ መናገራቸዉ ታዉቋል ።ብዙዎች ግን የኢትዮጵያ መንግስት ያንሰራፋዉ የመብት ረገጣ እንዳይታወቅበት ነዉ ቤተሰቦቹን በማስገደድ የአእምሮ ህመም አለበት እንዲሉ ያደረገዉ በማለት ይተቻሉ።
IMG_6357
ዛሬ በዋሽንግተን ዲሲ ሰላማዊ ሰልፍ ያደረጉ እትዮጵያዉያንንና ኢትዮጵያዉያን አሜሪካዉያን ረዳት ፓይለቱ ጤነኛ ነዉ የአእምሮ ህመም የሚለዉ አሉባልታ በኢትዮጵያ መንግስት የተፈበረከ ነዉ ሲሉ ያጣጥላሉ።

Photo credit: Kebadu belachew

ኢትዮጵያዉያን በዛሬዉ እለት ረዳት ፓይለት ሐይለመድህን አበራን በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ (VIDEO)

ድሬዎች ለሰማያዊ ፓርቲ፡ “ኢሕአዴግ ክፉ መንግስት ነው፤ አብረናችሁ እንታገላለን”

$
0
0

*‹‹ወደ ድሬዳዋ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች፤

ዘገባ በጌታቸው ሽፈራው

ድሬዳዋ፡- ሰማያዊ ፓርቲ (ሰማያዊ) በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮችና በፓርቲው የትግል አቅጣጫ ዙሪያ ከድሬዳዋ ከተማ ነዋሪዎች ጋር የካቲት 16 ቀን 2006 ዓ.ም በከተማዋ ተገኝቶ ባደረገው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ተወያየ፡፡

በስብሰባው ላይ ፓርቲው እስካሁን ያደረጋቸውን ህዝባዊ ትግሎችና ያስገኛቸውን ዋና ዋና ውጤቶች በድርጅት ጉዳይ ኃላፊው አቶ ጌታነህ ባልቻ በኩል ለነዋሪዎች ገለጻ አድርጓል፡፡ በተጨማሪም በፓርቲው ሀገራዊ አላማና የፖለቲካ ፕሮግራም ዙሪያ ለከተማዋ ነዋሪዎቹ ገለጻ ተደርጎላቸዋል፡፡
Birhanu Tekeleyared, engreer yilikal and Engeener Getaneh Balcha
‹‹ወደ ድሬዳዋ ከተማ መጥታችሁ ስላነጋገራችሁን ደስ ብሎናል›› ያሉት የከተማዋ ነዋሪዎች፣ ‹‹ምርጫ ሲደርስ ብቻ ወደ እኛ የመምጣቱን የቆየ ልምድ ሰብራችሁ ከአሁኑ ራሳችሁን ስላስተዋወቃችሁንና የትግል አጋራችሁ እንድንሆን ስለፈቀዳችሁ እናመሰግናለን›› ብለዋል፡፡ በስብሰባው ላይ የተገኙ አንድ አስተያየት ሰጭ በድሬዳዋ ከተማ ስላለው ወቅታዊና የፖለቲካ ሁኔታ አንስተው፣ በኢህአዴግ አገዛዝ የድሬዳዋ ነዋሪዎች እየደረሰባቸው ያለውን በደል አጋልጠዋል፡፡

‹‹ኢህአዴግ የማይገባበት ነገር የለም፤ ወዳጅ መስሎ በመሐላችን እየገባ ያጣላናል፡፡ ኢህአዴግ ክፉ መንግስት ነው፡፡ እንኳን መጣችሁልን እንጂ አብረናችሁ እንታገላለን፤ ለነጻነታችን ለመታገል ሞትን አንፈራም›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

በድሬዳዋው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከህዝቡ በርካታ ጥያቄና አስተያየቶች የተሰነዘሩ ሲሆን በፓርቲው ከፍተኛ አመራሮችም ምላሽ ተሰጥቷቸዋል፡፡ የድሬዳዋ ነዋሪዎች መሬትን፣ ብሄር ብሄረሰብን፣ ሰንደቅ አላማን፣ የታሰሩ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን፣ ምርጫ-2007ን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የውህደት አጀንዳን እና ሌሎች በርካታ አንኳር ጉዳዮችን አንስተዋል፡፡

የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለተነሱት ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በተለይ የብሄር ብሄረሰቦችን መብት በተመለከተ ‹‹በኢትዮጵያ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች እንዳሉ እንገነዘባለን፡፡ ነገር ግን ፓርቲያችን በግለሰብ ነጻነትና መብት ያምናል፡፡ ምክንያቱም የግለሰብ መብት ከተከበረ የቡድን መብትም አብሮ እንደሚከበር እናውቃለን፡፡ እስኪ ለአብነት የግለሰብ መብት ተከብሮ የቡድን መብት የማይከበርበት ሁኔታ ካለ እናንሳ…የለም፡፡ ስለዚህ ትኩረታችን በግለሰብ መብት መከበር ከሆነ የቡድን የሚባሉ መብቶችም አብረው መከበራቸው እሙን ነው›› በማለት አስረድተዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ‹ሞደሬት ሊብራሊዝም› አይዶሎጅን እንደሚያራምድ የተናገሩት ሊቀመንበሩ፣ የመሬትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ከዚህ መነሻነት የተቃኙ እንደሚሆኑ ጠቅሰዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት በተመለከተም ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ አብሮ በመስራትና በትብብር ያምናል፡፡ ነገር ግን ሁሌም ምርጫ ሲደርስ እንደሚደረገው በሩጫ ወደ ውህደት ለመግባት አንፈልግም፡፡ ካለፉት የሌሎች ተሞክሮዎች ብዙ ተምረናል፡፡›› ብለዋል፡፡

semayawi party Drie Dawa
ሰማያዊ ፓርቲ ድሬዳዋ በነበረው ቆይታ በዚያው የከፈተውን ቢሮና የአካባቢውን መዋቅር የማስተዋወቅና የማጠናከር ስራም ሰርቷል፡፡ ፓርቲው በሌሎች ከተሞችም ተመሳሳይ ስራ መስራቱን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማወቅ ተችሏል፡፡

Hiber Radio: የረዳት አብራሪው መጪው ዕጣና ከዚህ በፊት በአውሮፕላን ተደብቆ ቤልጂየም የገባው ኢትዮጵያዊ እንዴት በስርዓቱ ማጭበርበር ተላልፎ ተሰጠ?

$
0
0

የህብር ሬዲዮ የካቲት 16 ቀን 2006 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<...ረዳት አብራሪ ሀይለመድሕን አበራ ለኢትዮጵአውያን ጀግናችን እንደ የኔሰው ገብሬ ነው...ስዊዘርላንድ ኤምባሲ ፊት ለፊት በዲሲ የምናደርገው ሰልፍ አገሪቱ ለህወሃት ጨካኝ አገዛዝ አሳልፋ እንዳትሰጠው ለመጠየቅ ነው ...>

አክቲቪስት መስፍን አስፋው ከዋሽንግተኑ የድጋፍ ሰልፍ አስተባባሪዎች አንዱ ለህብር ከሰጠው ቃለ መጠይቅ

<<...የአማራ ሕዝብን ያዋረደው ብአዴን ወኪል ነኝ ብሎ እንዳያወራ ! አቶ አለምነው ለፍርድ እንዲቀርብ ይቅርታም እንዲጠይቅ...>> የመኢአድ ሊቀመንበር አቶ አበባው መሐሪ በባህር ዳር ለተቃውሞ ለወጣው ሕዝብ ካደረጉት ንግግር

<<... የአማራን ሕዝብ ያንቋሸሸውና ያዋረደው አቶ አለምነው ለፍርድ ካልቀረበና ይቅርታ ካልጠየቀ ተቀውሞ ሰልፉ ይደገማል...>>

ኢ/ር ግዛቸው ሽፈራው የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር በባህር ዳር ለተሰበሰበው ሕዝብ ካደረጉት ንግግር የተወሰደ(ዘገባውን ያዳምጡ)

የረዳት አብራሪው መጪው ዕጣና ከዚህ በፊት በአውሮፕላን ተደብቆ ቤልጂየም የገባው ኢትዮጵያዊ እንዴት በስርዓቱ ማጭበርበር ተላልፎ ተሰጠ?( ወቅታዊ ዘገባ ይዘናል)

የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር እና የህወሃት በሸር የተወጠነ ድርድር ሲቃኝ(ክፍል ሁለት)

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

- ስዊዘርላንድ ከአገሯ ረዳት አብራሪዎን አሳልፋ እንዳትሰጥ እየተጠየቀ ነው

- ነገ በዲሲና በፍራንክፈርት አርብ በስዊዘርላን የአገሪቱን መንግስት ለመጠየቅ ሰልፍ ይደረጋል

- ኦብነግ ሰሞኑን ሰባት የኢትዮጵያውን አገዛዝ የጸጥታ ሰዎችን ገደልኩ አለ

- በባህር ዳር ነዋሪዎች ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር ይሻላል ሲሉ ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ አደረጉ

- የአማራን ብሔር የተሳደቡ የክልሉ ም/ል ፕሬዝዳንት ለፍርድ እንዲቀርቡ ተጠየቀ

* ለተቃውሞ ሰልፍ የወጡ ገበሬዎች ታስረዋል

- ሱዳን ውስጥ በወረበሎች የተደፈረች ኢትዮጵያዊት ትፋተኛ ተባለች

- በቤይሩት ቦንብ ፍንዳታ ኢትዮጵያዊቷ ሕይወቷ አለፈ

- በሚኒሶታ የሚኖሩ የኦሮሞ ማህበረሰብ ዘርፈ ብዙ የሆነ ድህረ ገጽ ሊከፍቱ ነው

በቬጋስ የየካቲት 12 የሰማዕታት ቀን ተከበረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

የኢትዮጵያ ሴቶች ጉዳይ ሚ/ር ዘነቡ ታደሰ ዩጋንዳ የጸረ ጌይ ሕግ ማውጣቷን ተቹ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ኢትዮጵያ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት ዘነቡ ታደሰ ኡጋንዳ የጸረ ጌይ አዋጅ ማውጣቷን መተቸታቸውን ሃፊንግተን ፖስት የተባለው ጋዜጣ ሚኒስትሯ በትዉተር ገጻቸው የጻፉትን አስተያየት አያይዞ ባቀረበው ዘገባው አስታወቀ። እናት ድርጅታቸው ኢሕአዴግ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ የአፍሪካ ጊዮች ስብስባ እንዲደረግ መፍቀዱና በጁፒተር ሆቴል ይደረጋል በተባለው በዚህ ስብሰባ ከፍተኛ ተቃውሞ መነሳቱ ይታወሳል።

በትዊተር ገጻቸው ዘነቡ ታደሰ ኡጋንዳ የጸረ ጌይ (ጸረ የተመሳሳይ ጾታ ግንኙነትን) አዋጅን ካጽደገቀች በኋላ በእንግሊዘኛው There is no place for hate, discrimination in my beloved Africa. It’s not Governments’ business to make dress code or anti-gay laws #Uganda.” ብለው ጽፈዋል ያለው ሃፊንግተን ፖስት የኡጋንዳን መንግስት ሕጉን በማጽደቁ ተችተዋል ብሏል።

“ስለአለባበስም ሆነ የጸረ ጌይ ሕግ ማውጣት የመንግስት ጉዳይ መሆን የለበትም” በሚል የተናገሩት የኢትዮጵያ የሴቶች ጉዳይ ሚኒስተር ዘነቡ ታደሰ የጌይን ሕግ መጽደቅ ይደግፋሉ በሚል መነጋጋሪያ ሆነዋል።

ዘነቡ ታደሰ በትዊተር ገጻቸው የጻፉት የሚከተለው ነው፦

zenebu Tadesse

በአባይ ግድብ ጉዳይ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር እየተነጋገርኩ ነው አለች

$
0
0

ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 18/2006 (ቢቢኤን) ፦አራት ነጥብ ሰባት ቢሊዮን ዶላር ይፈጃል የተባለዉ ግድብን እንገነባለን በማለት የኢትዮጵያ መንግስት በቦንድ ስም ገንዘብ ለመሰብሰብ ያደረገዉ ሙከራ እምብዛም አለመሳካቱ ይታወቃል። የኢትዮጵያ መንግስት የግንባታዉ ፕሮጀክት ሰላሳ አራት ከመቶ ተጠናቋል ቢልም ግብጽ ባሰማችዉ ተቃዉሞ የግድቡ ግንባታ መስተጓጎሉን የመገናኛ ብዙሗን ዘግበዋል።
ABAY
የኢትዮጵያ ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኑ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ “ኢትዮጵያ ችግሩን ለመቅረፍ ከሱዳን ጋር ዉይይት ጀምራለች” ሲሉ ገለጸዋል። ግብጽን ወደ ዉይይቱ ሒደት ለማምጣት እየተጣረ መሆኑን የገለጹት ሚኒስቴር ሒደቱ ምን እንደሚመስል ግን ያመላከቱት ነገር የለም።

ሱዳንና ግብጽ ከግድቡ ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ኢትዮጵያ ብትገልጽም፤ ሁለቱ አገራት ግን ለጉዳዩ አዎንታዊ ምላሽ ሲሰጡ አልተስተዋልም። ግብጽ ሰማኒያ ከመቶ የሚሆነዉ የዉሃ ሐብቷ ከአባይ እንደሚመጣ ይታወቃል፤ የአባይን ጉዳይ እንደ ህልዉና ስለምትመለከትዉ የህዝብ ድጋፍ የሌለዉ የመላኒየሙ ግድብ እንደምን ዉጤታማ ይሆናል የሚለዉ ጉዳይም አጠያያቂ እየሆነ ነዉ።

ግድቡን ለመገንባት እስከ ሐያ ሺ የሚደርሱ ኢትዮጵያዉያን መፈናቀላቸው የታወቀ ሲሆን 70 ሚሊዮን ኩቢክ ሜትር ዉሃን ያከማቻል ተብሎ የተነገረት ግድብ ከፈነዳ ከፍተኛ የዉሃ መጥለቅለቅ ሊፈጥር ይችላል የሚል ስጋት አለ።

ኢትዮጵያ ግድቡ በአዉሮፒያኑ ቀመር 2017 ሲጠናቀቅ እስከ ስድስት ሺ ሜጋ ዋት የሚደርስ የኤለክትሪክ ሐይልን ለማመንጨት ብቃት ይኖረዋል ትላለች። ይህ ዉጥን ከግድቡ ባላንጣዎች ከሱዳናን ግብጽ ብቻ ሳይሆን” አባይ ከመገደቡ በፊት የመብት ጥሰቱ ይከበር” ከሚሉ ኢትዮጵያዉያንም ጭምር ጽኑ ተቃዉሞ እየገጠመዉ ነዉ። ኢትዮጵያ ከፕሮጀክቱ ዋነኛ ባላንጣ ከግብጽ ጋር በቀጥታ መነጋገር ሲገባት፤ ከሱዳን ጋር ዉይይት መጀመሯ ለምን እንደሆነ የዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴሩ ግልጽ አላደረጉም።
ABAY 2
በተያያዘ ዜናም ጠቅላይ ሚኒስቴር ሐይለማሪያም ደሳለኝ ቀደም ሲል በህዳር 24/2006 ወደ ሱዳን ተጉዘዉ የስራ ጉብኝት ማድረጋቸዉንና ህወሃት የተመሰረተበትን 39ኛ አመት ለማክበር የሱዳኑ ፕሬዝዳንት ኡመር ሐስን አልበሽር በየካቲት 11/2006 ወደ መቐሌ መጓዛቸዉን ይታወቃል።ይህ ከወትሮ የተለየ ቁርኝት እንደምን ተከሰተ በማለት ጥያቄ የሚያነሱ ወገኖችም አሉ።

የሱዳን የዉጪ ጉዳይ ሚኒስቴር አሊ አልቀርዲ በህዳር 23/2006 ኢትዮጵያና ሱዳን ያላቸዉን የድንበር ልዩነት አስወግደዉ መስማማታቸዉን ይፋ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ድንበሯን ለሱዳን ቆርሳ ለመስጠት መስማማቷ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት ያለዉ ብቻ ሳይሆን ህወሃት በስልጣን ለመቆየት የተቃዋሚ ሐይላትን ለመግታት አጎራብች አገራትን እየደለለ ነዉ የሚሉም አሉ።ህወሃት ስልጣኑ በህዝብ ከተወሰደ ሐብትን ወደ አጎራባች አገሮች አሽሽቶ ለመደላደል የሚያደርገዉ ሴራ ይኖራል በማለት ጉዳዩን ከመልካዓምድራዊ የፖለቲካ አለመረጋጋት ጋር የሚያይዙም አሉ።

አንድንድ ተንታኞች ደግሞ አባይን መገደብ የሚለዉ ሐሳብ ሶስት ዲሞክራሲያዊ ያልሆኑ አገራት አንባገነናዊ መንግስቶች በስልጣን ላይ ለመቆየት የሚያደርጉት ወከባ ነዉ፤ የኢትዮጵያ መንግስት በግድቡ ስም ገንዘብ ሲሰበስብ፤ ሱዳንና ግብጽ ደግሞ ብሔራዊ የሆነ ስጋት እንዳንዣበበ በመስበክ ህዝብን የሚያደናግሩበት ትርኢት ነዉ ይላሉ።

ቀድም ሲል ባሶንዳ በሚባለዉ የሱዳን የጠረፍ ከተማና አካባቢ 77 ኢትዮጵያዉያን በሱዳናዉያን መገደላቸዉን ቢቢኤን ዘግቦ ነበር ።ይህ ከጉዳዩ ጋር ግንኙነት እንዳለዉ ባይታወቅም፤ የሚታወቀዉ ነገር ግን የኢትዮጵያ ዉሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሆኑት አቶ አለማየሁ ተገኑ የአባይ ግድብ አስመልክቶ ከሱዳን ጋር ዉይይት መኖሩን መናገራቸዉ ነዉ።

በሱዳን ስለሞቱት 77 ኢትዮጵያዉያን የሚናገር ይኖር ይሆን?የኢትዮጵያ እና የሱዳን መንግስታት ስል ድንበር ስምምነት፣የጋራ ስለሆነ ደህነነትና ጥበቃ፣ህገወጥ የሆነ የሰዎች ዝውዉርን ስለመግታት፣የኤለክትሪክ ሐይልን ስለመጋራት፣የአባይን ግድብን አስመልክቶ ስለሚደረጉ ዉይይቶች ብቻ ነዉ እየገለጹ ያሉት።

በአዲስ አበባ ራሱን ያጠፋው የ24 ዓመቱ የጥበቃ ሠራተኛ ከኪሱ ደብዳቤ ተገኘ

$
0
0

bole

ባለፈው የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም በቦሌ አካባቢ አንድ የጥበቃ ሠራተኛ 3 ጊዜ ጥይት ወደ ሰማይ ከተኮሰ በኋላ ራሱን እንዳጠፋ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ ዘግበን፤ ለምን ራሱን ሊያጠፋ እንደቻለ የሚገልጽ መረጃ አለመገኘቱን ዘግበን ነበር። በአዲስ አበባ ከተማ ታትሞ የሚወጣው ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬው ዕትሙ እንደገለጸው ሟች በሱፈቃድ በጋሻው ራሱን ለማጥፋት የወሰነበት ደብዳቤ በኪሱ ተገኝቷል፤ ሲል ዘግቧል። ሟች ጊዜውን ባይጠቅሰውም በተወለደበት አካባቢ ነዳጅ የጫነ ተሳቢ ፍሬን ተበጥሶ ከሞት ማምለጡን፣ መሞት ካለበት ደግሞ ራሱን በራሱ ማጥፋት እንዳለበት መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፎ በኪሱ መገኘቱ ተዘግቧል።

የሪፖርተር ዘገባ እንደወረደ፦

ወጣቱ የጥበቃ ሠራተኛ በሱፈቃድ በጋሻው በኪሱ ውስጥ ከተገኙት የተለያዩ መታወቂያዎች መረዳት እንደተቻለው፣ አጋር የጥበቃ ሠራተኞች ማሠልጠኛ ተቋም ተቀጣሪ ነው፡፡ በተጨማሪም የኮሌጅ ተማሪ መሆኑን በሚገልጸው መታወቂያ ላይ እንደሠፈረው ከሆነ፣ በ1982 ዓ.ም. የተወለደና የ24 ዓመት ወጣት ነው፡፡ በምን ምክንያት ከፖሊስ ባልደረባነት እንደለቀቀ ባይታወቅም፣ የ13ኛ ኮርስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አባል እንደነበር በቅርብ ከሚያውቁት ወዳጆቹ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በባንኩ አሠራር አንድ የጥበቃ አባል 24 ሰዓት ሠርቶ 24 ሰዓታት የሚያርፍ በመሆኑ፣ ሟች በሱፈቃድም የካቲት 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ጠዋት አዳሪ ጓደኛውን ከቀየረ በኋላ፣ ባንኩን ለመጠበቅ የቻለው ለ24 ሰዓታት ሳይሆን ለሰባት ሰዓታት ብቻ ነው፡፡ ወጣቱ ‹‹ኑሮ መሮኛል›› በማለት እያማረረ እያለ በመሀል የያዘውን ጠመንጃ ቃታ በመሳብ አንድ ጊዜ ወደ ላይ ሲተኩስ፣ አብረውት የነበሩ ሴት ፈታሽና ሌሎች የባንኩ ተጠቃሚዎች በመደናገጥ ወደ ውስጥና ወደ ውጭ ሽሽት ይጀምራሉ፡፡ ሁለተኛውን ጥይት በመተኮስ ወደ ሚሊኒየም አዳራሽ በኩል በፍጥነት መራመድ መቀጠሉን በሥፍራው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

ሦስተኛውን ጥይት ወደ ላይ ከተኮሰ በኋላ አራተኛውን አንገቱ ሥር በመደገን ተኩሶ፣ ራሱን ማጥፋቱን የዓይን እማኞቹ አስረድተዋል፡፡

ሟች በሱፈቃድ ተወልዶ ያደገው በጉለሌ አካባቢ እንደሆነ፣ አሁንም ከቤተሰቡ ጋር እየኖረ እንደሚገኝ፣ ጊዜውን ባይጠቅሰውም በተወለደበት አካባቢ ነዳጅ የጫነ ተሳቢ ፍሬን ተበጥሶ ከሞት ማምለጡን፣ መሞት ካለበት ደግሞ ራሱን በራሱ ማጥፋት እንዳለበት መወሰኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ጽፎ በኪሱ መገኘቱም ተሰምቷል፡፡


በዳላስ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ለተጎዱ ወገኖቻቸው መርጃ ግማሽ ሚሊዮን ብር ሰጡ

$
0
0
አቶ ብርሃን መኮንን ከዳላስ ፎርት ወርዝ አካባቢ የተዋጣውን ገንዘብ ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በዋሽንግተን ዲሲ ተገኝተው ሲያስረክቡ

አቶ ብርሃን መኮንን ከዳላስ ፎርት ወርዝ አካባቢ የተዋጣውን ገንዘብ ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በዋሽንግተን ዲሲ ተገኝተው ሲያስረክቡ

(ዘ-ሐበሻ) በቴክሳስ ግዛት በዳላስና ፎርት ወርዝ አካባቢ ከተማ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ባለፈው ኖቬምበር 2013 ዓ.ም ጉዳት ለደረሰባቸውና ወደ ሃገራቸው ለተመለሱ ኢትዮጵያውያን ወንድም እና እህቶቻቸው ማቋቋሚያ የሚውል 31 ሺህ ዶላር ወይም ግማሽ ሚሊዮን ብር አዋጥተው ሰጡ።

ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ አረቢያ ጥቃት ከደረሰባቸው በኋላ በዳላስና ፎርት ወርዝ አካባቢ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በከፍተኛ ቁጣ ሰላማዊ ሰልፍና የሻማ ማብራት ምሽት በማድረግ ቁጣቸውን እና ሃዘናቸውን መግለጻቸው በወቅቱ በዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ የተዘገበ ሲሆን የአካባቢው ነዋሪዎች ከማዘን እና ከመቆጣት ባሻገር ገንዘባቸውን በማዋጣት ወደ ሃገር ቤት ለተመለሱት ኢትዮጵያውያን ማቋቋሚያ እንዲውል በሚል ይህን 31 ሺህ ዶላር አሰባስበው ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት IOM የአሜሪካ ቅርንጫፍ ሰጥተዋል።

የማህበሩ ሊቀመንበር የሆኑት አቶ ብርሃን መኮንን በዳላስ ፎርት ወርዝ የተሰባሰበውን 31 ሺህ ዶላር (በዛሬው የአዲስ አበባ የዶላር ምንዛሪ ዋጋ 595 ሺህ 150 ብር) ወደ ዋሽንግተን ዲሲ በማምራት ለዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት በቼክ ካስረከቡ በኋላ እርዳታው እንደሚቀጥል ገልጸዋል። በሕዝቡ ቃል ተገብቶ ያልተሰበሰበው ገንዘብም በቀጣይ እንደተሰበሰበ ለIOM እንደሚሰጥ ሊቀመንበሩ ጨምረው ገልጸዋል።

የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ከሳዑዲ የተመለሱ ኢትዮጵያውያንን ለማቋቋም በአዲስ አበባ የተለያዩ ሥራዎችን እያከናወነ መሆኑን የገለጸ ሲሆን ከ160 ሺህ በላይ የሳዑዲ አረቢያ ተመላሽ ኢትዮጵያውያንን ለማቋቋም ከፍተኛ ሥራ እንደሚጠብቅ፤ ኢትዮጵያውያን በዓለም አቀፍ ወገኖቻቸውን ለመርዳት የሚያደርጉትን ጥረት እንደሚያደንቅ ድርጅቱ በተደጋጋሚ መግለጹ ይታወሳል።

ታግደው የነበሩት መምህር ግርማ ወንድሙ ከፓትርያርክ አቡነ ማትያስ በመላው ዓለም እየተዘዋወሩ እንዲያገለግሉ ፈቃድ ተሰጥቷቸዋል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) መምህር ግርማ ወንድሙ በእስጢፋኖስ ቤ/ክ ከቀኖና ውጭ የማጥመቅ ሥራ እየሰሩ ነው በሚል መታገዳቸውን፤ የእገዳ ደብዳቤውን ጭምር በማያያዝ ዘ-ሐበሻ በወቅቱ መዘገቧ አይዘነጋም። ይህን እገዳ ተከትሎም መምህር ግርማ “እኔ አስማተኛ ወይም ጠንቋይ አይደለሁም” በሚል ለላይፍ መጽሔት የሰጡትን ቃለምልልስ በዘ-ሐበሻ ላይ አስነብበን ነበር። አሁን የደረሰን መረጃ ደግሞ የመምህር ግርማ ዜናን የሚቋጭ ይግሆናል።

የዘ-ሐበሻ ምንጮች በማስረጃ አስደግፈው እንዳደረሱን መረጃ ከሆነ መምህር ግርማ ወንድሙ በፓትሪያርክ አቡነ ማትያስ ፈቃድ በዓለም ዙሪያ እየተዘዋወሩ የወንጌል አገልግሎትና እንዲሁም የህሙማን ሐብተ ፈውስ እንዲሰጡ ተፈቅዶላቸዋል። ከምንጮቻችን የደረሰን የተፈቀደበት ደብዳቤም የሚከተለው ነው።

Memher Girma

Memher Girma

አንድነትና መኢአድ የአድዋ ድል በዓልን በእግር ጉዞ ለማክበር ለጠየቁት ጥያቄ መንግስት “ጥያቄውን ለመመለስ እችገራለሁ”አለ

$
0
0

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)ና የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) 118ኛውን የአድዋ በዓል ምክንያት በማድረግ ቀበና ከሚገኘው የአንድነት ጽ/ቤት ተነስቶ ምኒልክ አደባባይ ሲደርስ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ ጉዞውን ወደ (መኢአድ) ጽ/ቤት በማድረግ ስለ አድዋ የድል በዓል ውይይት እንደሚያደርጉ የካቲት 19 ቀን 2006 ዓ.ም የማሳወቂያ ደብዳቤ ቢያስገቡም በዛሬው ዕለት የአዲስ አበባ መስተዳድር የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ኦፊሰር በተጻፈ ደብዳቤ በብሔራዊ ደረጃ ፕሮግራም በመያዙ የናንተን ጥያቄ ለማናስተናገድ እንቸገራለን በሚል በደብዳቤ ምላሽ ሰጥቷል፡፡

UDJ and AEUP

“በባህር ዳር ከተማ የታየው ህዝባዊ ተቃውሞ በሌሎች የሀገራችን ክፍሎችም ተጠናክሮ ይቀጥላል”–የአንድነት መግለጫ

$
0
0

bahr dar 4
ከአንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ!!!

ከጊዜ ወደ ጊዜ አምባገነናዊ የአፈና መዋቅሩን በማጠናከር ለመድብለ ፓርቲ የፖለቲካ ሥርዓት በር መዝጋቱን አጠናክሮ ለብቻው አውራ ፓርቲ ለመሆን እየታተረ ያለው የኢህአዴግ መንግሥት ደርግ በውድቀቱ ዋዜማ ወደ ተላበሰው ባህሪ እየተሸጋገረ እንደሆነ ተስተውሏል፡፡

የዚሁን ድርጅታዊ ባህሪ ውርስ በዋነኛነት ከሚያስፈጽሙት የግምባሩ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ብአዴን ኢህአዴግ በአማራው ህዝብ ላይ እየፈፀመው ያለው የንቀት እና የማጥላላት ዘመቻም አብይ ተደርገው ሊወሰዱ ከሚችሉ የግንባሩ አፍራሽ ተግባራት በዋነኝነት ሊጠቀስ የሚችል ነው፡፡

የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር እና የብአዴን ጽ/ቤት ኃላፊ የሆኑት አቶ አለምነው መኮንን የክልሉን ህዝብ የናቀ እና ያዋረደ አስነዋሪ ንግግር ካደረጉ በኋላ ከጥፋታቸው ከመታረም ይልቅ በክልሉ ቴሌቭዥን ያንኑ አምባገነናዊ ባህሪያቸውን እንደያዙ የግሌ ብቻ ሳይሆን የድርጅቴ አቋም ነው ሲሉ መመለሳቸውም መላውን የሀገሪቷን ህዝብ ያስቆጣ ተግባር ነው፡፡

UDJ
ይህንን አስነዋሪ ተግባር የፈጸመውን ብአዴንን ከ70 እስከ 80 ሺህ የሚደርሱ የባህር ዳር ከተማና የአካባቢው ነዋሪዎች ከፓርቲያችን ጎን በመሰለፍ እሁድ የካቲት 16 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም የባህር ዳርን ጎዳና እና አደባባዮች በህዝባዊ ማዕበል ሲያስጨንቁ መዋላቸውም ሰላማዊ ትግሉ የደረሰበትን ሁኔታ በግልፅ የሚያስገነዝብ ነው ማለት ይቻላል፡፡ የኢህአዴግ መንግሥት በአንፃሩ ዛሬም ከስህተቱ ለመማር ያልተዘጋጀ በመሆኑ ይህን የሰፊ ህዝብ ቁጣ በማጣጣል አፋኝ እና ተሳደቢ መሪዎቹን ከጉያው ላለመነጠል እየሞከረ እንደሆነም አስተውለናል፡፡ ፓርቲያችን አንድነት ለዴሞክራሲ እና ለፍትህ ፓርቲ አንድነት የባህር ዳር እና አካባቢው ነዋሪዎች ላደረጉት ህዝባዊ ትገል ከፍተኛ ክብር እና አድናቆት አለው፡፡ ይህንን ህዝባዊ መሠረታችንን ወደ ላቀ ደረጃ በማሸጋገር በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ተቃውሞው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ልናረጋግጥ እንወዳለን፡፡

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ይህንን የህዝብ ጥያቄ አለመቀበሉን እየገፋበት በመሆኑም በባህርዳር የታየው ህዝባዊ ተቃውሞ ቤሎች የሀገራችን ክልሎች ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲሆን አቶ አለምነው መኮንን በፍርድ አደባባይ ለማቆም በአጭር ጊዜ ውስጥ ክስ መስርተን ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ እናረጋግጣለን፡፡

በመጨረሻም በዚህ ፈታኝ የትግል ምዕራፍ ፡-
1ኛ. መላው የኢትዮጵያ ህዝብ
2ኛ. በውጭ ሀገር የምትኖሩ ኢትዮጵያውያን፤ የፓርቲያችን አባላት እና ደጋፊዎች ከጎናችን በመሆን ትግላችንን እንድትደግፉ ጥሪ እናቀርባለን !!!!

በባህርዳር የታየው ህዛባዊ መነቃቃትና የትግል ስሜት በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ይደገማል !!!

ድል የህዝብ ነው !!!
የካቲት 20 ቀን 2006 ዓ.ም

በጭምቷ ሀገረ ሲዊዝ መዲና በበርን ከተማ ረ/ አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ –ያበራል ሲሉ ወገኖቹ ዛሬ ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ።

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ (ሲዊዘርላንድ ዙሪክ)

„ታሪክ ሠራ ጀግና ሲዊዝ ላይ ገባና“

„ታሪክ ሠራ ጀግና ሲዊዝ ላይ ገባና
ዓለም አነጋግሮ ትኩረት ስቧልና፤

ተልኮ የመጣ ተብሎ ኃይለመድህን
መልእክቱን ለማድረስ ኢትዮጵያን ለማዳን፤
አጀብም አሰኜ ዓለም ተደመመ
ጣሊያንን ቆልፎ ታሪኩን ደገመ!

ታሪክ ሠራ ጀግና ጄኔብ ላይ ገበና
አለም አነጋግሮ ትኩረት ስቧልና!

እዚች ሲዊዝ ላይ ለአመታት ጩኸናል
በብርድም ተገርፈን፣ ጸሐይ አቃጥሎናል፤
ሰሚም አልነበረም ችላ ብለውናል።
የወያኔ ሴራ ተጋለጠ ለኣለም
ኢትዮጵያ ሽፍታ እንጂ መሪ መንግሥት የለም።
ገለጠው ጉዱነን የወያኔን ሥራ
ደቀቀ ወያኔ በአንድ ቀን በራራ።

ታሪክ ሠራ ጀግና ሲዊዝ ላይ ገባና
ዓለም አነጋግሮ ትኩረት ስቧልና።

ዬድርሻን መወጣት፤ ሁላችን እንልመድ
ከፍቶልናል ጀግናው፤ የነጻነት መንገድ።
ወደርም የለውም የዚህ ፍጹም ጀግና
ሲያበራ ይኖራል ብልሁ ገናና!
አበጀህ ብለናል ከጎኑ እንቆማለን
ሲነኩን የማንወድ የበላይ ዘሮች ነን።
ብሶት በደላችን የኖረው ታምቆ
ነገረ ለዓለም ግዜውን ጠብቆ።
Hailemedhin Abera
ታሪክ ሠራ ጀግና ሲዊዝ ላይ ገባና
ዓለም አነጋግሮ ትኩረት ስቧልና።“

የጣሊያን አከርካሪ የሰበረው የኣድዋ ደማቅ የጥቁሮች ድልና የጄኔባ ዳግማዊ ድል የመንፈስ ሐሤታዊ ቅብብል የታዬበት የረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ተገኘ ገድልን በመደገፍ ዛሬ የካቲት 28.02.2014 ለእናት ሀገራቸው ክብርና ነፃነት እንዲሁም ብሩህ ተስፋና የህግ የበላይነት ቀናዕይ የሆኑ ከመላ ሲዊዘርላንድ ችለው የመጡ ኢትዮጵውያን ወጣት የነፃነት ኮከባችን የወሰደው እርምጃ አድምቆናል፤ ኮርተንበታልም፤ ከጎኑ እንቆማለን፤ ተስፋችንና ነፃነታችን ነው ሲሉ የሲዊዝን ዋና ከተማን ይልቁንም በማዕከላዊ ምክር ቤቱን ግዛታዊ ደንበር በወልዮሽ በመሆነው በኢትዮጵያዊ ጨዋነት ድምጻቸውን በልበ ሙሉነትና በድፍረት ለሲዊዝ መንግሥታዊ አስተዳደር አቅርበዋል።

ሲወዝ ልክን አውቀ መኖርን፣ እንደ ወጣትንት የሚጫን ጎረምሳዊ መንፈስንና ስሜትን አርግቦ ርጋታን ይሸልማል፣ የመብትና የግዴታ ጣሪያና ግድግዳን በአግግባቡ ተርጉሞ ከህግ ጥሰት ይታደጋል፣ „ይበቃኛልን“ አስተምሮ ኑሮን ያስጥማል፣ መሬት በያዘ ጉዳይ ላይ አቅምን ማፈሰስን ይሰብካል፣ ልታይ ልታይ አለማለትን ያውጃል፣ በልክ መኖርን ሆኖ ያሳያል፣ ውስጥን ሆኖ መዝለቅን ያትምበታል፣ ለህግ መገዛትን ያስነብባል፣ ማድመጥን ይሰጣል፣ መጠበቅን ያጠጣል፣ መክደነን በገፍ ያቀናል። ለዚህም ነው ጀግናው ረዳት /አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ዓለምን በግራሞት በአስደመመው ትዕይንት በኋላ እንኳን አንድም ፎቶ ማግኘት ያልተቻለው እንኳንስ እራፊ ዜና። ሚስጥርነቱንም፤ ልቅናውንም ሆነ ብቃቱንም ሳስበው እኔ በግሌ ሲዊዘርላንድ በልኩ የተዘጋጀት የሥደት ጊዜውን ሱባኤ በጽናት የሚከውናባት ገዳማዊ ሀገሩ ናት እላለሁ። መንፈሳዊ ህይወት ዳር ድንበር የለውምና። ልኩ ናት ሲዊዝ።

New Picture (6)

የዛሬው ሰላማዊ ሰልፍ ታዳሚዎች ውስጥ እንዲህ ይነበባል። ሃይለመድህን ነፃነት ታሪካችን መጸሐፍ ነው፤ አርማችን ለነፃነት ፍለጋ የወሰደው እርምጃ ለአንባገነን አልገዛም በማለት የእንቢተኝነት ሰላማዊ እርምጃ አግባብ ነው፤ ድምጹ ድምጻችን ነው። የሲዊዝ መንግሥት እስካሁን ላደረገለት እንክብካቤ እያመሰገነን ለነፃነት አረበኛችን የመኖሪያ ፈቃድ ዕውቅና ይስጥልን፤ ድህንነቱንም ይጠብቅልን። የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄው አግባብ ያለው መልስ ይሰጠው በማለት አቅም ባለው ድምጽ በፈረንሳይኛ፤ በጀርመንኛና በእንግሊዘኛ ወለዊ ስሜታቸውን እጅግ በሚመስጥ ወገናዊ ስሜት የእድሜ የፆታ፤ የሃይማኖት ልዮነት ሳይገድባቸው በጸደቀው ማንታቸው አብነት ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ሲያሰሙ ነበር የዋሉት።

ሰልፈኞቹ በሀገራችን በኢትዮጵያ ያለውን ኢፍትኃዊ የሽፍታ አመራር፤ የጥቂት ብሄርተኛ ቡድን መሪ የሆነው የወያኔ አስተዳደር የሚያደርሰውን ሰባዕዊ ጭቆናና አንባገነናዊ አገዛዝንም ስለመሆኑ በመስማማት በአኃታዊ ስሜት ገልጸዋል። ሲዊዝ የሚኖሩ ኢትጵውያን ጀግናቸው የነፃነት መሪያቸው ከመሆን ባሻገር ከምንም ዓይነት የወንጀል ተግባር ጋር የተያያዘ ታሪክ አለመኖሩን በመግለጽ አሸባሪው የወያኔ ኃርነት ትግራይ አስተዳደር ነው ሲሉ ሥልጣን ላይ ያለውን የቲፒኤልኤፍን አስተዳደር አጥብቀው አውግዘውታል። በተጨማሪም ወያኔ ገዳይ ነው! ወያኔ ፋሽስት ነው! ወያኔ አፋኝ ነው! በማለትም በጉልበታም ድምጽ በወያኔ አስተዳደር ያላቸውን ግልጽ አቋምና ጥላቻ በአንድ ድምጽ አሰምተዋል። ከዚህም ሌላ በኢትዮጵያ የአኩልነት፤ የነፃነት የህግ የበላይነት ምክነት በማውሳት ከቶውንም ምልክት የማይታይበት መሆኑን አበክረው ገልጸዋል። ነፃ ጋዜጦኞች፤ የስብዕዊ መብት ተሟጋቾችና የፖለቲካ መሪዎች በእስር ላይ እንደሚገኙም በመግለጽ ኢትዮጵያም እስረኛ ስለመሆኗም አክለው በወላዊ ድምጽ አሰምተዋል። በሌላ በኩል ቀደም ሲል ሀገራችን የሥልጣኔ ምንጭና የታሪክ እንብርት ስለመሆኗም በውስት ገልጸዋል።

እኔም እንደማምንበት ለዘመኑ ለዛሬ ለነገም የተስፋ ብሩኽ ጮራ ረዳት አውሮፕላን አብራሪው ኃለይለመድህን አበራ ለነፃነት ፈላጊ ቤተሰቦች ሁሉ የመንፈስ ቋንቋችን ነው። ብልሁ ወጣት ዓለም ያጸደቀውንና የደነገገውን የታህሳስ 10 ቀን 1948 የሰው ልጅ ተፈጥሯዊ ሰብዕዊ መብት አከባበር 30 አንቀፆች መርሆ አባል ሀገሮች ምን ያህል ተፈጻሚ እንደ አደረጉት እንደገና ይከልሱት – ይፈትሹት ዘንድ በዝምታ ተግባር የቤት ሥራ ሰጥቷቸዋል። በስክነት በድርጊት ፍሬዎቹ አስገነዝቧል። የድንቅ ቁንጮ ገድለኛ ወጣት መንፈስ ስለ ሰብዕዊ መብት የተደነገጉት ባለ 30 አንቀጻት በአንባገነናት ምን ያህል ጫና እንዳለበቻውና እንደሚጠቀጠቁም በማሳሰብ በትህትና እንደገና ለመመርምር ጉባኤ እንዲቀመጡ ለሊቃነቱ መከሯል ።

ከዚህ በተጨማሪም ረዳት አውሮፕላን አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ለሲዊዝ መንግሥት የአዬር ጥበቃውን ሥርዓት አስምልከቶም ትኩረት እንዲሰጠው ነግሯል። በሌላ በኩል እንደነዚህ ያሉ ያልተለመዱ ክስተቶችን እንዴት ሲዊዞች ሊያስተናግዱ እንደሚችሉም ሰፊ የማስተዋል መስክ ከፍቶላቸዋል። ከዚህ ሌላ ኢትዮጵውያን መከራችን አላለቀምና፤ እነ ከልታሜ በሀገራችን ተሰደን፤ በስደትም ተሰደን ባላቤት አጥተን መንከራተታችን እውቅና እንዲያገኝም ሰፊ የዋቢነት አኩሪ ተግባርም ፈጽሟል። ከሀገር ሀገር ለምንከራተተው ወገኖቹ እንደ አናንያን እንደ ሚሳኤል እንደ አዛርእያን ለነፃነታችን እራሱን ሰጠ። ብዙ ነገር እንደሚያጣ ቢውቀውም ፍቅርን እንደ እናት በተግባር ተረጎመ። እግዚአብሄር ይስጥልን። የተባረኩና የተቀደሱ ምስጉን ቤተሰቦችህንም እንዲህ ያለ ጠበቃ ወልደው ተንከባክበው አሳድገው ስለ ሰጡን እናመስግናለን።

ታላቅ ማሳሰቢያ።

ጀግናችን! ነፃነትን የተራቡ ህዝቦች በዬትኛውም መስክ፤ በዬትኛውም ሁኔታ ብሶታቸውን፤ እንቢተንነታቸውን ሊገልጹበት የሚችሉበት መንገድ ህግና ሥርዓት ሊደነገግለት እንደማይችልም ኮሽ ሳያደርግ ካለምንም ግድፍት ለሰው ልጆች ህይወት ያለውን ጠንቃቃ ተፈጥሮም አሳይቷል። ይህ ድርጊትና አፈጻጻም እያንዳንዱ የዐለም ህዝብ ሊታደምበት የሚገባ ይመስለኛል። ወያኔም እራሱ ለፍትህ አሰጣጡ በአዎንታዊ ረድፍ መሰለፍ አለበት ህሊና ካለው።

ዓለም ጉዞ ላይ ናት። እኔ ባልጓዝ ቤተሰቤ ይጓዛል። ቤተሰቤ ባይጓዝ እኔ እጓዛለሁ። ወይንም ሁለታችንም። ስለዚህ ለባለመክሊቱ ረዳት አብራሪ የሚሰጠው የርትህ መልስ ዓለምን ለነገ የሚያድን ወይንም የሚገድል ይሆናል። ልድገመው ለባለመክሊቱ አውሮፕላን ኢትዮጵያዊ ረዳት አብራሪ የሚሰጠው የርትህ መልስ ዐለምን ነገ የሚያድን ወይንም የሚገድል ይሆናል። ስለምን? ነገ በዬትኛውም ጊዜና ሁኔታ ዬትም ሀገር መሰሉ ተግባር መፈጸሙ አይቀሬ ነው።

የአስተዋዩ ረዳት አብራሪ ኃይለመድህን አበራ ሁለት ግልጽና ጥያቄ አሉታዊ ምላሽ ከተሰጠው፤ ተጓጓዥን ሆነ አውሮፕላኑን ለመታደግ እጅግ ዓለም ይከብዳታል። በስጋትም ትወረራለች – ። ከጉዞ ውጪ አለም አትታሰብምና። ትርፉ አዬር ላይ አመድ ማፈስ ብቻ ይሆናል ተስፋውም። ህይወትም ንብረትም አይተርፍም። ስለዚህ እያንዳንዱ ዬዐለም ዜጋ፤ ዓለም አቅፍ ድርጅቶች፤ አህጉር አቀፍ ድርጅቶች፤ የዬሀገሮች አስተዳደሮች ሁሉ በተደሞና በአንክሮ ሆነው በባለቤትነት ስሜት ለጥያቄው ተገቢውን አዎንታዊ ምላሽ ለመስጠት መሰናዳት የግድ ይኖርባቸዋል።

በመጨረሻ ከሐሤቴ በላይ ሐሤቱ ብርኃን ኃይለመድህን አበራ በህይወት መኖሩ። ከዚህ አንፃር መላመቶችን ሁሉ መልክ ሊየስዝ የሚችልበትን ቀንና ሰዓት መጠበቅ ሁላችንም ግድ ይለናል። እንኳንስ እኛ የወለዱት ወላጆቹ ይህ ቅብዕ ጸጋ መክሊት ዕንቡጣቸው ስለመኖሩ ሆነ ውስጡን ስለማወቃቸው የሚያውቀው መዳህኒዓለም አባታችን ብቻ ስለሆነ የተከደነ ሲሳይን እራሱን እራሱ እስኪተረጉምልን ድረስ አደቡን ይስጠን ለሁላችንም። አሜን!

ጀግናችን አጀንዳችን!
ጀግናችን ረዳት አውሮፕላን አብራሪው ኃለመድህን የነፃነት ሐዋራያችን ነው!
ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።
ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል!

ሥነ ግጥም — ከሰላማዊ ሰልፉ ላይ በገጣሚ ነጂብ አሊ የቀረበ ነው። ለዚህም ነው በትምህርተ – ጥቅስ ውስጥ የገባው የእኔ አይደለምና። አመሰግንለሁ የኔ ውድ ሸበላ ወጣት – እመቤቴ!

የሰላማዊ ሰልፉ – ፎቶ በአቶ ሚሊዎን።

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

በኖርዌይ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች በዛሬው እለት ሰላማዊ ሰልፍ አደረጉ (ከገዛኸኝ አበበ ኖርዌይ)

$
0
0

gezahegn abebe (1)
ዛሬ የካቲት 21/2006 ዓ ም እለት በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች ከተለያየ ስፍራ በመሰባሰብ ደማቅ እና ደስ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ በኖርዌይ ኦስሎ ከተማ ሲያደርጉ ውለዋል :: በዚህ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ የኢሳት ቴሊቨዥን ጋዜጠኞች የሆኑት ጋዚጠኛ ደረጄ ሀብተወልድ ከኒዘርላንድ እና ጋዜጠኛ መታሰቢያ ቀጸላ ከለንደን የተገኙ ሲሆን እነኚህ በኖርዌይ የሚኖሩ ኢትዮጵያኖች በጊዜው የነበረው ብርድ እና ዝናብ ሳይበግራቸው ድምጻቸውን ሲያሰሙ ውለዋል:: ሰላማዊ ሰልፉ በሁለት አላማዎች ላይ በማተኩር የተደረገ ሲሆን ረዳት ፓይለት ሃይለመድን አበራን በመደገፍ እና የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን መሬት ለሱዳን አሳልፉ እየሰጠ ያለውን ድርጊት በመቃወም ነበር::
1959213_10203351622850970_1144408807_n
የመጀመሪያው ሰላማዊ ሰልፍ ሕዝቡ በቀኑ አስራ ሁለት ሰአት ኦስሎ በሚገኛው ሲውዘርላንድ ኢንባሴ በመገኛት የተጀመረ ሲሆን የሰልፉም ወና አላማ የነበረው የሲውዘርላንድ መንግስት ረዳት ፓይለት ሃይለ መድህን አበራ ለአረመኔው የኢትዮጵያ መንግስት አሳልፎ እንዳይሰጥ እና ረዳት ፓይለት ፓይለት ሃይለ መድህን አበራ በሲውዘርላንድ መንግስት የፖለቲካ ጥገኝነት እንዲያገኝ ለመጠየቅ ሲሆን በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የተለያዩ መፈክሮች ተሰምተዋል ከነዚህ ውስጥም ጥቂቶቹ ሃይለ መድህን ሰላማዊ እና ንጹህ ሰው ነው ስለዚህ ሲውዘርላንድ መንግስት ጥገኝነት እንዲሰጠው ሃይለ መድህን ጀግና ነው በጭቆና እና በመከራ ውስጥ የሚኖረው ኢትዮጵያዊ መከራ ለማሳየት ሲል ነው ወጋ የከፈለ እንጂ ወነጀለኛ አይደለም እና ሌሎችንም መፈክሮች ሲያሰማ ውለዋል::

በመቀጠለም ጕዞቸውን ወደ ኖርዌይ የወጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መስሪያ ቤት በማድረግ አባቶቻችን ደማቸውን ያፈሰሱበትን የኢትዮጵያጵያን መሬት እና ድንበር የወያኔ መንግስት ለሱዳን አሳልፈው እየሰጡ ያለውን ተግባር በማውገዝ የተለያዩ መፈክሮች ያሰሙ ሲሆን የኖርዊይ መንግስትም ይህን አረመኔ እና ለሀገሩ ለድንበሩ እና ለገዛ ለሕዝቡ ደንታ የሌለውን የወያኔ መንግስት ከመርዳት እንዲቆጠብ ጠይቀዋል ::
1966705_10152288930034743_531168688_n
የኖርዌይ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር የጠበቀ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዳለው እና የወያኔንን መንግስት በገንዘብ ከሚረዱ ሀገሮች ግንባር ቀደሞ ኖርዌይ መሆኖ ይታወቃል::

በኢንቨስትመንት ስም አፍሪካ ውስጥ የሚደረገውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ የካናዳ የፓርላማ አባላትና እውቅ ምሁራንን ያሳተፈ ውይይት በኦታዋ ተደረገ

$
0
0

Coalition for Equitable Land Acquisitions and Development in Africa በምህጻረ ቃል CELADA በመባል የሚታወቀው በካናዳ ኦታዋ ውስጥ የተቋቋመ ድርጅት በአፍሪካ እየተኪያሄደ ያለውን የመሬት ቅርምት አስመልክቶ በርካታ የፓርላማ አባላት፣ የተራድኦ ድርጅት ሃላፊዎች የዩኒቨርሲቲ መምህራን በተገኙበት በአፍሪካ በኢንቨስትመንት ስም የሚደረገውን የመሬት ቅርምትና ካናዳ ልትይዘው የሚገባትን ፖሊሲ በተመለከተ በኦታዋ ፌብሩዋሪ 25 ቀን 2014 ዓም የተሳካ ስብሰባ አድርገዋል።
በሚሊየን የሚቆጠሩ በእርሻ የሚተዳደሩ ማህበረሰቦችን አግባብ በሌለው ሁኔታ የማፈናቀሉ ሥራ እጅጉን ተጧጡፎ ያለው በተለይ በአፍሪካ በመሆኑ CELADA የተሰኘው ድርጅት ይህ ጉዳይ አለም አቀፍ ትኩረት ያገኝ ዘንድ የበኩሉን ለማድረግ ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት በተለያየ ተቋማት ውስጥ የሚያገለግሉ ካናዳውያን እንዲሁም ከበርካታ አፍሪካ ሀገራት የመጡና በአህጉሪቱ ውስጥ እየሆነ ያለው ነገር ይመለከተናል የሚሉ ትውልደ አፍሪካ ምሁራንን ጭምር ያካተተ ነው። በዚህ ድርጅት ውስጥ በርካታ ትውልደ ኢትዮጵያውያን ምሁራንም የሚሳተፉበት ሲሆን ከመስራች አባላት አንዱ ታዋቂው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የሆኑት አቶ ኦባንግ ሜቶ ናቸው።
New Picture (7)
የስብሰባው ዓላማ ድርጅቱን ከፓርላማ አባላትና በሀገሪቱ ውስጥ የፖለቲካ ተጽእኖ ማሳደር የሚችሉና አለም አቀፍ እውቅና ካላቸው ካናዳውያን ጋር ማስተዋወቅ ሲሆን። በዋነኛነትም ይህ ህገወጥ የመሬት ነጠቃና ቅርምት በሚደረግባቸው አገሮች ውስጥ የካናዳ ግብር ከፋይ ሕዝብ ገንዘብ ተጨማሪ የመጨቆኛ መሳርያ በመሆን ለአምባገነን መንግስታት እንዳይውል ለሚደረገው እንቅስቃሴ ድጋፍ ማሰባሰብያም ነበር።
ስብሰባውን በንግግር የከፈቱቱ የፓርላማ አባል የተከበሩ ሄለን ላቫንዴር ሲሆኑ ለስብሰባው ዝግጅትና ስኬትም ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያደረጉ ናቸው። እርሳቸውም የጉዳዩን አሳሳቢነት አጽንኦት ሰጥተው ከተናገሩ በሁዋላ መድረኩን ለመስራችና የወቅቱ ሊቀመንበር ለሆኑት ለፕሮፌሰር ሮይ ኩልፔፐር አስተላልፈዋል። ሮይም የስብሰባውን ተካፋዮች አመስግነው በበኩላቸው ይህ ጅምር ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሚያስፈልጉባቸውን ጉዳዮች በመዘርዘር የድርጅቱ ማለትም የ CELADA ዓላማና ግብም በመላው አፍሪካ እየተከናወነ ባለው የመሬት ነጠቃና ቅርምት ዙርያ ያጠነጠነ መሆኑን አስረድተው ለእለቱ ተናጋሪዎች እድል ሰጥተዋል።
New Picture (9)
የመጀመርያው ተናጋሪ እውቁ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የተከበሩ ኦቶ ኦባንግ ሜቶ ሲሆኑ ከንግግራቸው ቀደም ሲልም ጥቂት ደቂቃዎች የሚፈጅ በሊቢያ አማካይነት በማሊ ውስጥ የተደረገው የመሬት ቅርምት የሚያደርሰውን አፍራሽ ተጽእኖ፣ የሕዝቡን ቁጣና ተቃውሞ የሚያመለክት ፊልም እንደ መግቢያ ካሳዩ በሁዋላ የችግሩን ጥልቀትና ውስብስብነት በማስረዳት ኢትዮጵያ ውስጥ እየተከናወነ ያለውንም ነገር በመጥቀስ ካናዳ ልትወስድ የሚገባትን አቋም፣ ሊኖራት የሚገባውን ፖሊሲ በማሳሰብ ንግግራቸውን አብቅተዋል። አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ የያዘችው አቋምም የጉዳዩን አሳሳቢነት የሚያመለክት በመሆኑ ካናዳም የምትለግሰውን እርዳታ በዚሁ መነጽር ትመለከተው ዘንድ አሳስበዋል።
የማዳጋስካር ተወላጅዋ የ CELADA አባል የሆኑት ማጊ ራዛፊምህኒ ለበርካታ አመታት ለUNICEF ያገለገሉ ሲሆኑ በማዳጋስካር እየሆነ ያለውን የሀገሪቱ ፖሊሲ አገም ጠቀም የሆኑ እርምጃዎችን ቢወስድም አደጋው የከፋ መሆኑን በመግለጽ እርሳቸውም ተመሳሳይ ጥሪ ለካናዳ ሕዝብና መንግስት አቅርበዋል።
New Picture (8)

በመሬት ቅርምት ላይ ጠንካራ አቋም በመያዝ በተለያየ መስክ ስኬትን ያገኘው የኦክሰፋም ካናዳ ዳይሬክተር የሆኑት ሮበርት ፎክስ በበኩላቸውም የሁኔታውን አሳሳቢነትና አደገኛነት በመግለጽ መሬትም እንደማንኛውም ሸቀጥ ሊሸጥ ሊለወጥ ይችላል በሚል መርህ ሕዝቡን ማፈናቀልና ሀብት ማጋበስ በሚፈልጉ ሰዎች የገንዘብ ፈሰስና ለሀገራቸው ሕዝብ ደንታም በማይሰጣቸው ባለስልጣኖች ግፍ እየተፈጸመ መሆኑንና አብራርተው ምንም እንኳ ችግሩ ዛሬ የአፍሪካ ቢሆንም ነገ ግን ሁላችንንም የሚያስጨንቅ ጉዳይ መሆኑን መዘንጋት የለብንም ብለዋል። በመቀጠልም መሬትን እንደ ተቀማጭ ሀብት የሚያዩት ከበርቴዎች ትላልቅ የእርሻ መሬቶችን በልማት ስም በመግዛት አጥረው ካለምንም ልማት በመያዝ የመሬት ዋጋ የሚያሻቅብበትንና ከፍተኛ ትርፍ የሚያጋብሱበትን ጊዜ እየጠበቁ ነው በማለት በአፍሪካ ድሀ ገበሬዎች ላይ የሚሰራውን ግፍ ተናግረዋል። ለዚህም ምሳሌያቸው ሞዛምቢክ ነበር። ሞዛምቢክ ውስጥ ለውጭ ባለሃብቶች ከተሰጠው መሬት ውስጥ 70% የሚሆነው ታጥሮ የመሬት ዋጋ ውድ የሚሆንበትን ጊዜ የሚጠብቅ ሸቀጥ ሆኗል ብለው ነበር። በዚህም ምክንያት መልማት ያለበት መሬት በከበርቴዎች ተይዞ ሳለ ሚሊየኖች ግን በረሃብ ያልቃሉ የሚል አንድምታ ያለውን አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። እንደ ደቡብ ሱዳን ያለ ገና የጸና መንግስትና ፖሊሲ የሌለበት ሃገር ውስጥ በሀገሪቱ ውስጥ መልማት ካለበት መሬት ውስጥ 10% በውጭ ኢንቨስተሮች ተይዟል።
New Picture (12)
ይህ እጅግ በጣም ሰፊ መሬት ነው። ኢትዮጵያን እንደምሳሌ በጠቀሱበት ንግግራቸውም የ140 የእግርኳስ ሜዳን የሚያህል ስፋት ያለው የአበባ እርሻ ልማት ውስጥ በርካታ ወጣት ሴቶች በቀን ሰራተኛነት ተቀጥረው በአለም ላይ ያሉ ኬሚካሎችን ሄርቢሳይድ፣ ፈንጂሳይ፣ ኢንሴክቲሳይድ፣ ባክቴሪሳይድ ወዘተ በቆዳቸው በሳንባቸው እየሳቡ ያለ እድሜአቸው የሚረግፉ እንዲሆኑ መገደዳቸውን በመግለጽ የመሬት ቅርምቱ በተለይም በሴቶች ላይ ያስከተለውን አደገኛ ተጽእኖ ለተሰብሳቢዎች ገልጸዋል። ተጋንኖ የሚነገረው የእርሻው ኢንቨስትመንት የስራ እድል ይፈጥራል፣ የምግብ ምርት ያሳድጋል ለማህበራዊ አገልግሎቶች አመቺ እድል ይሰጣል የሚባሉት መደለያዎች ፈጽሞ ከእውነት የራቁ መሆናቸውን ሲገልጹ በመሰረቱ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ የሰራተኛ ቁጥርን በመቀነሱ እንጂ በስራ እድል ፈጣሪነቱ አይታወቅም ብለዋል። ኢንቨስተሮችም የሀገሬውን ህዝብ የመቀለብም ሆነ በሀገር ውስጥ የሚሸጥ ምግብ የማምረት ግዴታም የሌለባቸውና እንዲያውም የእርሻ መሬትን በአብዛኛው ለምግብ የሚሆን ሳይሆን ለስኳርና የነዳጅ ዘይት ለማምረቻ የሚጠቀሙበት መሆኑን ገልጸዋል። ኮካኮላ የስኳር ምርቱን በዚህ ጉዳይ ከሚጠቀሱ አምራቾች ባለመግዛት የጥፋቱ ተካፋይ ላለመሆን የወሰደው እርምጃ አበረታች መሆኑንም ለተሰብሳቢው ገልጸው የመሬት ቅርምቱ ለአጭርጊዜም ይሁን ለረጅም ጊዜ ሕዝባዊ ጠቀሜታ እንደሌለው አክለዋል። በመጨረሻም ካናዳም ሆነች የበለጸጉ ሀገሮች በዚህ ጉዳይ ላይ የሚወስዱት አቋም ወቅታዊም አስፈላጊም መሆኑን አበክረው ተናግረዋል።
New Picture (10)
ሌላው ተናጋሪ ብሩስ ሙር ሲሆኑ የ Canadian Hunger Foundation (CHF) ዳይሬክተር የነበሩና በተለያዩ አንጋፋ ድርጅቶች ውስጥ በቦርድ አባልነት በዳይሬክተርነት ያገለገሉና በአሁኑ ወቅት የ ‘North South Institute’ የቦርድ ሰብሳቢ፣ የ Forum of Democratic Global Governance (FIM) የቦርድ አባል እንዲሁም የ ‘Transparency International’ አባል ናቸው። ብሩስ ሙር በአስከፊው የኢትዮጵያ ድርቅ ወቅት ለውጪ ሰዎች መጓጓዝ አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ እስከ ኮረም ድረስ ዘልቀው የችግሩን ስፋትና ክብደት ከተመለከቱ በሁዋላ ለካናዳ መንግስትና ለዐለምም የችግሩን መጠን ያሳወቁ በዚህም ሳቢያ ከፍተኛ እርዳታ ለኢትዮጵያ እንዲደርስ አስተዋጽኦ ያደረጉት ሲሆኑ በዚሁ የመሬት ቅርምትና የለጋሽ አገሮች ሚና በተለይም ካናዳ ሊኖራት ስለሚገባው ፖሊሲ አጠር ያለ ግን ጥልቅና ጠበቅ ያለ አስተያየት ሰንዝረዋል። እንደ እርሳቸው አባባልም የከተማዎች የከፋ ድህነት የገጠሩ ጉዳይ ችላ መባሉን አመልካች ነው በማለት ተናግረዋል። በማከልም ከ 2000 -2010 ዓ ም በሰነድ የሚታወቅ የመሬት ይዞታ ዝውውር 200 ሚሊየን ሄክታር ሲሆን ከዚህ ውስጥ 134 ሚሊየኑ በአፍሪካ ውስጥ ነው። ይህም ጉዳዩ ለ አፍሪካ እጅግ አሳሳቢ መሆኑን ያመለክታል። የምግብ እጥረት ከተከሰተ በሗላ ሳውድአረብያ ከ ኢትዮጵያ ብዙ መሬት ገዝታ ነበር በጣም የሚገርመው በ2009 ዓም ሳውዲ የመጀመርያ ምርቷን ከኢትዮጵያ በወሰደችበትና ሕዝብዋን በመገበችበት ወቅት ወርል ፉድ ፕሮግራም አምስት ሚሊየን የ ኢትዮጵያ ረሃብተኞችን መግቦ ነበር። ይህ የሚናገረው ትልቅ እውነት አለ፣ ይህ የሚያመለክተው ትልቅ ክፍተት አለ በማለት የተሰማቸውን ገልጸዋል።
New Picture (11)
ሌሎች ተሰብሳቢዎችም አስተያየታቸውን የሰጡ ሲሆን ይህ ጥልቅና ውስብስብ ጉዳይ ለፓርላማ አባላት ቀርቦ ካናዳ ልትወስድ ስለሚገባት አቋም በቂ ግንዛቤ ማስጨበጡ እንደ አማራጭ ቀርቧል። በተለይም የግብር ከፋዮች ገንዘብ ለሕዝብ መፈናቀል ተጨማሪ መሳርያ እንዳይሆን ካናዳውያን ኢንቨስተሮችም ይህንን በመረዳት እንደዚህ ያሉ አገሮች ውስጥ የሚደረግ ኢንቨስትመንት የሚያስከትለውን ተጽዕኖና የሚያመጣውንም አደጋ ልብ እንዲሉ እንዲደረግ ሁሉም የድርሻውን እንዲያደርግ በየአቅጣጫው መረባረብ አስፈላጊነቱን ጠቅሰዋል።
በመዝጊያ ንግግራቸው ላይ የ CELADA ሊቀመንበር ፕሮፌሰር ሮይ በዚህ የመሬት ቅርምት ዙርያ በዚህ ጉባዔ ላይ የተገኛችሁ በጉዳዩም ላይ በቂ እውቀት ያላችሁ ጠበብቶች አላችሁና የኤክስፐርት ምስክርነታችሁን ለፓርላማ አባላት በማቅረብ ይህንን ውስብስብ የሆነ ነገር በማስረዳት እንደምትተባሩ አምናለሁ። በየአቅጣጫው በያዝነው ስራ እንበርታ ለዚህ አንገብጋቢ ችግር መፍትሄ ለማስገኘት የየበኩላችንን እናድርግ በማለት ተሰብሳቢዎቹንና ለዚህ ስብሰባ ስኬት አስተዋጽኦ ያደረጉትን ሁሉ አመስግነው የእለቱ መርሃግብር በዚሁ ተጠናቋል።
New Picture (13)


ከአውሮፕላኑ ጠለፋ በኋላ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ም/ሥራ አስኪያጅ ካፒቴን ደስታ ዘሩ ለቀቁ

$
0
0

Desta Zeru Ethiopian captain

በአንድ ጎሳ እና ቋንቋ አመራር ስር ወድቋል በሚልና በዘረኝነት ሰራተኞቹን ፍዳቸውን እያሳየ ነው በሚል የሚተቸው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ምክትል ስራ አስኪያጅ እና የበረራ ክፍል ሃላፊ የሆኑት ካፒቴን ደስታ ዘሩ ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን የኢትዮጵያ የሽግግር ምክር ቤት ምንጮቹን ጠቅሶ ለዘ-ሐበሻ በላከው መረጃ አስታወቀ። እንደ ሽግግር ምክርቤቱ ዘገባ የስልጣን መልቀቂያው ጉዳይ ግልጽ ምን እንደሆነ አይታወቅም።

ሌሎች ምንጮች የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ተጠልፎ ወደ ስዊዘርላንድ በረዳት ካፒቴን ሃይለመድህን አበራ ካረፈ በኋላ በአየር መንገዱ ውስጥ በተነሳው አለመግባባት ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶችን እየሰጡ ይገኛሉ።

ምንጮቹ የአየር መንገዱ አብራሪዎች በቂ እውቀት እና ችሎታ እያላቸው ከውጪ አብራሪዎችን በማስመጣት ለኢትዮጵያውያኑ እድገት እና የበረራ ፍቃድ መከልከል እንዲሁም አላስፈላጊ የሆነ መንግስታዊ የደህንነት ወከባ እና የአይነ ቁራኛ ጥበቃ በአብራሪዎች ላይ ከመደረጉም በላይ የስራ መብቶቻቸው እና የሰብአዊ መብቶቻቸው በዘረኝነት ላይ የተመረኮዘው የአየር መንገዱ ማንጅመንት እንደማያከብርላቸው እነዚሁ ምንጮቹ አክለው የሚገልጹ ሲሆን፤ በወያኔ ፈጠራ ረዳት አብራሪው ሃይለመድህን አበራን “የአእምሮ በሽተኛ ነው” በሚል የተወራው ወሬም በአየር መንገዱ የሚበሩ ሰዎች ቁጥር እንዲቀንስ ምክንያት እየሆነው እንደሆነም ምንጮች ይናገራሉ።

የዩናይትድ ስቴት የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢትዮጵያ ዉስጥ ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንዳለ ይፋ አድርጓል (ዜና ትንታኔ)

$
0
0

John Kerry
ዋሽንግተን ዲሲ፤ የካቲት 20/2006 (ቢቢኤን) ፦ የዩናይትድ እስቴስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት (State Department) ባወጣዉ የዘንድሮ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ላይ የኢትዮጵያ መንግስት ያከናዉናቸዋል ያለዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በመዘርዘር ሰፋ ባለ መልኩ አቅርቦታል።
ቀድም ሲል ኢትዮጵያ ዉስጥ በ2003 በተደረገዉ ምርጫ፤ በሟቹና በቀድሞው ጠቅላይ ሚንስቴር መለስ ዜናዊ ይመራ የነበርዉ ኢ.ህ.አዴ.ግ ከ547 የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫ 545 መቀመጫዎች አሸንፏል መባሉን ሪፖርቱ እያመላከተ የምርጫ ጣቢያዎች በመንግስት ሐይላት ቁጥጥር ስር እንደነበሩና አለምአቀፍ ታዛቢዎች ስራቸዉን በተገቢዉ መልኩ እንዳያከናዉኑ ገደብ እንደነበረባቸዉ ይገፃል።

በአገሪቱ ዉስጥ ባለዉ ከፍተኛ የመብት ረገጣ ሳቢያ ዜጎች የመሰብሰብ፣የመደራጀት፣የመናገር መብትን በገሃድ እንደሚነፈጉ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ያስደረግቸዉን ጥናቶች ተመርኩዞ ያብራራል። እነዚህን የዲሞክራሲ እሴቶችን ለመተግበር የሚሞክሩም ይታሰራሉ፣ይንገላታሉ፣ይዋከባሉ፣ዛቻ ይደርስባቸዋል፣ ክብራቸዉ ተነክቶ እንዲሸማቀቁምይደረጋሉ በማለት ሪፖርቱ ያትታል።እርዳታን የሚያስተባብሩ፣ እርዳታን ለጋሽ የሆኑ ድርጅቶች፣ ማህበራዊና ትርፍ አልባ የሆኑ ተቋማት (NGO) የግብረ-ሰናይ ተልእኮ አቸዉን እንዳይፈጽሙ የኢትዮጵያ መንግስት እንደሚከለክል፤ በሰዎች ላይ ህገ ወጥ የሆነ ግድያ እንደሚፈጽም፣ዜጎች ግርፋት-ድብደባ እንደሚደርስባቸዉ፣ ወጥ የሆኑ የማሰቃያ ተግባራት በመንግስት ሐይላት እንደሚፈጽምና በአገሪቱ እስርቤት የሚገኙ ታሳሪዎችን ህይወት ለአደጋ የሚያጋልጹ አሳቃቂ ተግባራትም እንዳሉም በሪፖርቱ ላይ ተገልጿል።

ሰዎች በፍርድ ቤት ሳይበየንባቸዉ በጅምላ ተይዘድዉ ይታሰራሉ፤በፍርድ ቤት የአሰራር ዘይቤም ይሁን በፍትህ ሒደቱ ዉስጥ ግልጽ የሆነ ፖለቲካዊ ጣልቃ ገብነት አለበት፤ ፍርድ ቤቶችም ደካማ ናቸዉ! ሲል ሪፖርቱ ይደመድማል። መንግስት ሀሳብን በነጻነት ለመግለጽ የሚሞክሩ ያገሪቱ ዜጎች ላይ ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ እንደሚወስድ በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን፤ በነሐሴ 2/2005 የኢድ-አልፈጥር በዓል በሚከበርበት ወቅት፤ በሰላማዊ መንገድ ተቃዉሞ ያሰሙ ከነበሩት ሙስሊም ኢትዮጵያዉያን መካከል ከ 1000 በላይ የሚሆኑት በጅምላ ተግበስብሰዉ መታሰራቸዉና ከመካከላቸዉም የሞቱ መኖራቸዉ በሪፖርቱ ላይ አጽንኦት ተሰጥቶታል።የዜጎች ግላዊ መብትን በመግፈፍ፤ በሙስሊሙ ማህበረስብ ላይ ህገወጥ የሌሊት ፍተሻዎችም ተደርገዋል። ግልጽና ስልታዊ በሆነ መልኩም ከቦታ ወደ ቦታ ዜጎችን የማፈናቀል መርሃግብር በመንግስት መፈጸሙን የሚያስረዳዉ ሪፖርት ነጻ መሆን የሚገባዉ የመማርና የማስተማር ሒደት የመንግስት ጣልቃገብነት እንዳለበትም ይገልጻል።

ዜጎች ዲሞክራሲያዊ መብታቸዉን ተጠቅመዉ በነጻነት መንግስትን የመቀየር አቅማቸዉ ሆን ተብሎ የተገደበ ነዉ!በፖሊስ፣በፍርድ ቤቶችና በመንግስት አመራር ዉስጥ በስልጣን መባለግ-ሙሰኝነት-ጉቦኝነት በገሃድ ይተገበራሉ። መንግስት በስልጣን የባለጉንና የህዝብን አደራ ያጎሳቆሉ ወንጀለኞች ችላ በማለት ፖለቲካዊ ዉለታን ይዉላል፤ ፖለቲካዊ ምህረትን ለምግባረ ብልሹ የመንግስት አካላት እንደሚያደርግ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ያጋልጻል።

በኢትዮጵያ ህገ መንግስት የጾታ እኩልነት የተረጋገጠ ቢሆንም በመንግስታዊ የአሰራር መዋቅር ዉስጥ ሴቶች ይጨቆናሉ። ህገወጥ የሆነ የሰዉ ዝዉዉር ይፈሰማል፣ የአካል ጉዳተኞች (የተሳናቸዉ) ማህበራዊ ጭቆና ይደርስባቸዋል፣የ ኤች.አይ.ቪ ኤድስ ህሙማን ማህበራዊ የሆነን በደል ይጋፈጣሉ፣የሰራተኖች መብት የተገደበ በመሆኑ ህፃናትን አስገድዶ የጉልበት ስራ ማሰራቱ የተለመደ መሆኑ በሪፖርቱ ላይ ተዘርዝሯል።

የመንግስት ሐይላት የሰዎችን ደብዛ ያጠፋሉ፤ የሰዎች መሰወር ይስተዋላል! በትግራይ ክልል በአላማጣ ከተማ መንግስት በልማት ስም ቤቶችን በሚያፈርስበት ወቅት አለመግባባት ተፈጥሮ የታሰሩ 12 የአካባዊ ተወላጆች የገቡበት እንደማይተዋቅ እና ተመሳሳይ በሆነ መልኩ በሶማሌ ክልል ያለዉ ልዩ የፖሊስ ሐይል በክልሉ ተወላጆች ላይ ኢሰብዓዊ የሆነ ማንገላታት፣ማሰቃየት፤ ግድያ እደሚፈጽም መታወቁ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ህገመንግስት ቶርቸር (ግርፋት ድብደባ ማሰቃየት)ይከለክላል። ቶርቸርን የመሰሉ የሰዉ ልጅን ክብር ገፋፊ የሆኑ ጭካኔ የተሞላባቸዉ ተግባራት፤በመንግስት የደህነነትና የጥበቃ ሐይላት እንደሚፈጸሙ በማጋለፅ በጥር 9/2005 የተያዘዉ የሙስሊሞች ጉዳይ መጽሔት አምድኛ እና ማኔጂንግ ኢዲተር የነበረዉ ጋዜጠኛ ሰለሞን ከበደ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ በተደጋጋሚ የዚሁ ህገወጥና አስከፊ ተግባር ሰለባ እንደነበር በዩናይትድ እስቴት የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ሪፖርት ላይ በዋቢነት ተጠቅሷል።

በጥቅምት 8/2006 ሁማን ራይትስ ዎች ያወጣዉን ሪፖርት እንደ አብነት በመጥቀስ በመጥቀስ በማእከላዊ የምርመራ ማእከል ዉስጥ መርማሪዎች ታሳሪዎችን በማስገደድ የእምነት ቃል እንደሰጡ እንደሚያደርጉ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት እየገለጸ፤ በማእከላዊ እስር ቤት ዉስጥ ከፍተኛ የሆነ ቶርቸር (ግርፋት-ድብደባ-ማሰቃየትት)፣ ዛቻ፣ማስፈራራርት፣ እስረኞች ላይ ዉሃ መድፋት፣የእስረኞችን እጅ ጣራ ላይ አስሮ ለረጅም ሰዓታት ማቆም፣እሰረኞችን ነጥሎ ለብቻ ማሰርን የመሳሰሉ ኢሰብዓዊ ተግባራት እንደሚፈጽሙና ዲፕሎማቶች፣ኤንጂኦ (በጎ አድራጊ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ትርፍ አልባ ድርጅቶች) እስረኞችን የመጎብኘት ፍቃድ እንደሚነፈጉ ተገልጿል።

በመስከረም 2005 በተገኘዉ መረጃ መሰረት ከ70,000 እስከ 80,000የሚድርሱ እስረኞች መኖራቸዉ ሲታወቅ፤ ከነዚህም መካከል 2500ሴቶች ሲሆኑ 600 ህጻናት ከእናቶቻቸዉ ጋር መታሰራቸዉ እና ታዳጊ ወጣቶች ከአዋቂዎች ጋር አብረዉ እንደሚታሰሩ ተዘግቧል። የአገሪቱ እስር ቤቶች በጣም የተጣበቡ ከመሆናቸዉም ባሻገር ወታደራዊ ተቋማትም እንደ እስር ቤት ማገልገላቸዉ ተዘግቧል። በርካታ እስረኞች ከመጣበብ፣ተነጥሎ ከመታሰር፣ የተማሏ የጤና ግልጋሎት ካለመኖሩ የተነሳ ለአእምሮ ህመም ይዳረጋሉ። ለአንድ እስረኛ የምግብ፣ የዉሃ አቅርቦትን ለመለገስ እና የጤና ግልጋሎት ለመስጠት በቀን ስምንት ብር ከአስር ሳንቲም ብቻ እንደተመደበ የዩናይትድ እስቴትስ የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት አመታዊ የሰዓዊ መብት ሪፖርት ይዘረዝራል።

ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች ከ2004 ጀምሮ ሰላማዊ የሆነ ተቃዉሞን በአወሊያ የትምርት ተቋም ዉስጥ በመጀመር ከአርብ ስግደት (ከጁመዓ ሶላት) በሗላ በቀጣይነት የተቃዉሞ መርሃግብር እንደሚያከናዉኑና፤ ይህ የቅዋሜ ተግባር ምንም ሰላማዊ ቢሆንም የፖሊስ አካላት ሰዎችን በመያዝ አላስፈላጊ ሐይል እንደሚጠቀሙ ሪፖርቱ ያስረዳል። በሐምሌ 14/ 2004 በሙስሊሞች የተደረገዉን ሰላማዊ ተቃዉሞ ተከትሎ መንግስት “የደህንነት ሰጋት” የሚል ማመካኛን በመፍጠር 28 ሙስሊሞችን አስሮ በጥር 24/2005 ክስ ያቀረበባቸዉ ቢሆንም በታህሳስ 3/2006 አስሩን በነጻ አሰናብቶ በአስራ ስምንቱ ላይ ያቀረበዉን ክስ ዝቅ አድርጓል። መንግስት እነዚህን የሙስሊም ታሳሪዎች በአለማችን ላይ ከሚታወቁ አሽባሪ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት አላቸዉ ብሎ በገሃድ ለመፈረጅ መሞከሩም በሪፖርቱ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ መንግስት የመናገር-የመደራጀት-የመሰብሰብን መብት የሚተገብሩ ፖለቲከኞችናና ጋዜጠኞችን እንደሚያስር፣ እንደሚያሰቃይ፣ እንደሚያንገላታ፣ የሚገልጸዉ ሪፖርት ከፖለቲከኞች የመድረኩ አንዱአለም አራጌ ብሎም የኦሮሞን ማህበረስብ መብት በዲሞክራሲ ለማስከበር ከሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ተወላጆች በቀለ ገርባና ኦልባና ሌሊሳ ታስረዉ እየተሰቃዩ መሆናቸዉን፤ ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ከጋዜጠኞች እስክንድር ነጋ፣ሪዮት አለሙና ሰለሞን ከበደ በእስር ይማቅቃሉ ሲልም ሪፖርቱ ያስረዳል።

መንግስት ነጻ-ፕሬስ እንዲከስም በሚያደርገዉ ከፍተኛ ጫና ጋዜጠኞች የእስርና የስደት ሰለባ መሆናቸዉ ቢታወቅም፤ዳግም መንግስት የአፈና መረቡን በመዘርጋት የኢንተርኔት፣ የሳተላይት-ቴሌቭዥን ስርጭትን፣የማህበራዊ መገናኛ መደረኮችን፣የድረ ገጽ የመረጃ አዉታሮችን በማወክ ህዝቡ ማግኘት የሚገባዉን መረጃ ከማፈኑም ባሻገር፤ የጋዜጠኖች፣ የፖለቲከኞች እና የአክትቪስቶችን ኮምፒዉተር ለመሰለል ህገወጥ የሆነ የኮምፒዉተር ቫይረስን መንግስት እንደሚልክ ሲት ዝን ላብ (citizen lab) የተባለዉን ድርጅትን መረጃ ዋቢ ያደረገዉ የዩናይትድ እስቴትስ አመታዊ የሰብዓዊ መብት ሪፖርት የኢትዮጵያ መንግስት የህዝብ የሆኑ የሬዲዮና የቴሌቭዥን ጣቢያዎችን ሙሉ በሙሉ ተጠቅሞ ለፖለቲካዊ ፕሮፓጋንዳ እየተገለገለባቸዉ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

በሳዑዲ አረቢያ የታመቀው የኢትዮጵያውያን ሮሮ ፈንድቶ ዛሬ በሽሚሲ ሁከት ነግሶ ዋለ

$
0
0

* የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለወገኖቻችሁ ድረሱላቸው!
* ተጽእኖ ፈጣሪዎችም እታድክሙን ፣ ሂዱና እየሆነ ያለውን ተመልከቱ!

ዘገባ ነብዩ ሲራክ ከሳዑዲ አረቢያ

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

ሰሞኑን ከጅዳው የሽሜሲ ጊዜያዊ የእስር ማቆያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ኢትዮጵያውያን ለወራት በእስር ተንገላታን ሲሉ የመረረ ሮሯቸውን ገለጹልኝ ። ሮሯቸወ ሰሚ ማጣቱን አምርረው የገለጹልኝ ወገኖች ከእኔ አልፎ ተርፎ ለጀርመን ራዲዮ የዝግጅት ክፍል ሳይቀር ምሬት ሮሯቸውን ማስተላለፋቸውን ገልጸውልኛል።

ዛሬ ረፋድ ላይም በተንቀሳቃሽ ስልኬ ደውለው እጃችሁን ስጡ ተብለው በሰጡ እየደረሰባቸው ያለው መጉላላት በመክበዱ ወደ የሞት ሽረት አድርገው ቁርጡን ለማወቅ እንደሚገደዱና ይህንንም ” ለጅዳ ቆንስል መስሪያ ቤት ሃላፊዎችና ለአለም ድምጻችን አሰማልን !” ሲሉ እያለቀሱ ሃሳባቸውን ሲያስረዱኝ መጭውን ለመገመት አዳጋች አልነበረም።

የግፉአኑ የአደራ ቃል አለብኝና ስልኬን እንደዘጋሁ ወደ ጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ወደ ተጠባባቂው ቆንስል ጀኔራል ሸሪፍ ከይሩ ደወልኩ ። ስልካቸው ይጠራል ግን አያነሱትም! ደጋግሜ ደወልኩ መልስ የለም … ተስፋ ሰንቄ ወደ ሌላኛዋ የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሃላፊ ወደ ቆንስል ሙንትሃ ደወልኩበ። እርሳቸውም አያነሱም! ደጋገምኩት ፣ መልስ ግን የለም ! የሚያዝ የሚጨበጥ ማጣት እንዴት ያማል?

ከሰአታት በኋላ እኩለ ቀን ከዚያው ከሽሜሲ ተደውሎለወኝ ስልኩን ሳነሳው የሰው ጫጫታ ፣ እሪታ ፣ አኡኡታና የጥይት ድምጽ ሰማሁ … ደዋዩን ወንድም ምን አዲስ ነገር ተፈጠረ ? አልኩት “መረረን ፣ ድረሱልን አልን ፣ የሚሰማን አጣን ፣ እስር ቤቱን ሰብረን ወጣን !” አለኝ ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ መለሰልኝ … ከዚያን ሰአት ጀምሮ እስከ አሁኗ ሰአት ከሽሜሲ የሚደርሰኝ መረጃ ደስ አይልም ! የቆንስል መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች በአካባቢው የተገኙ ቢሆንም መፍትሄ ማምጣት ግን የቻሉ አይመስልም።

የጅዳ ቆንስል ሃላፊዎች ሆይ ለመረጃ ቅርብ ሁኑ ! ወገንን ለመደገፍ ትጉ ! የወገኔን የወገናችሁን ክፉ ደግ መረጃ እንዳላቀብል ፣ አታስተላልፍ ከፖለቲካው ጋር እያገናኛችሁ ከመወንጀል እስከ ተራ አሉባልታ የምትሞጅሩኝ የምትሞግቱኝ ተሰሚነት ያላችሁ ተጽእኖ ፈጣሪዎች ሆይ ! አታድክሙን ! ስሙኝ ? እነሆ እየሆነ ያለውን ሂዱና ተመልከቱ ! የምትቆረቆረቆሩት ለወገኖቻችሁ ከሆነ እነሆ ድረሱላቸው።

በቃ ! ሌላ ምን ይባላል ?
ነቢዩ ሲራክ

በምዕራብ ሃረርጌ የታሰሩት ሼህ ሃሰን በእስር ቤት ሕይወታቸው አለፈ

$
0
0
(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)

ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው፦ በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሃረርጌ በጭሮ ከተማ በሚገኙ ከተለያዩ ወረዳዎች በፖሊስ ተይዘው በጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት ለረጅም ጊዜ ታስረው ለህክምና ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ ከተደረጉት ታሳሪዎች መካከል ሼህ ሃሰን በቂ ህክምና ባለማግኘታቸው ሕይወታቸው ማለፉን ምንጮች አስታወቁ፡፡

በጭሮ ከተማ ከተለያዩ ወረዳዎች በጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት ታስረው ባደረባቸው ከፍተ|ኛ ህመም ምክንያት ማረሚያ ቤቱ ከአንድ አመት በፊት ወደ ፌደራል ማረሚያ ቤት ወደሆነው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ሪፈር በመፃፍ ወደ አዲስ አበባ ሄደው እንዲታከሙ ለማድረግ ሞክሮ ነበር፡፤ ሆኖም ታሳሪዎቹ በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዞን 3 ታስረው የሚገኙ ሲሆን ምንም የረባ ህክምና ሳያገኙ በከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ እንደሚገኙ ምንጮች አስታውቀዋል፤፤

ከምዕራብ ሃረርጌ ጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት ወደ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ከአመት በፊት የተዘዋወሩት ታሳሪዎቹ ስም ዝርዝር እንደሚከተለው ይቀርባል

1.መሐመድ ሐሰን አሊዩ በምዕራብ ሀርርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ

2.መሃመድ አህመድ በምዕራብ ሀርርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ

3.ሼህ ሀሰን በምዕራብ ሀረርጌ ዳሮ ለቦ ወረዳ ገለሞተራ ቀበሌ

4.ከተማ ጸጋዬ መገናኛው በምዕራብ ሃረርጌ መቻሬ ወይም ገመቺስ ወረዳ ሽሬ ቡሉ ቀበሌ

5.ከተማ ለማ ኢሾ በምዕራብ ሃረርጌ መቻሬ ወይም ገመቺስ ሽሬ ቡሉ ቀበሌ

6.ዘውዱ ታሪኩ እንደሻው በምዕራብ ሃረርጌ ዳርጌ ሳውሮ ወረዳ ቀበሌ 34 ነዋሪ የነበሩ መሆናቸው ታውቋል፡፡

ከላይ ከተዘረዘሩት በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በዞን 3 ታስረው ከሚገኙት ታሳሪዎች መካከል በምዕራብ ሃረርጌ የጭሮ ከተማ የደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ ነዋሪ የነበሩት ሼህ ሃሰን በማረሚያ ቤቱ በቂ ህክምና እንዳያገኙ በመደረጋቸው በየካቲት 15/2006 ሂወታቸው ማለፉን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

ሼህ ሃሰን ከጭሮ ከተማ ማረሚያ ቤት በቂ ህክምና እንዲያገኙ በሚል አብረዋቸው ከታሰሩ ሌሎች ታሳሪዎች ጋር ወደ አዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ቢዘዋወሩም ማረሚያ ቤቱ ተገቢ እና በቂ ህክምና እንዳያገኙ በማድረጉ ከዚህ አለም በሞት ሊለዩ እንደቻሉ ታውቋል፡፡ የሼህ ሀሰን ቤተሰቦችም ሊያገኟቸው አለመቻላቸውን የማረሚያ ቤቱ ምንጮች ገልፀዋል፡፡

በተመሳሳይም ሁኔታ ሌላኛው በምዕራብ ሀርርጌ ዞን ጭሮ ከተማ ደባቢስቶ ወረዳ ቡሌ ኢሉ ቀበሌ ነዋሪ የነበረው እና የዞን 3 ታሳሪ የሆነው .መሐመድ ሐሰን አሊዩ በቂ ህክምና ባለማግኘቱ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ በሞት አፋፍ ላይ እንደሚገኝ ምንጮች አስታውቀዋል፡፡

በኢትዬጲያ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ታስረው የሚገኙ ዜጎች ከጊዜ ወደ ጊዜ በህክምና እጦት ምክንያት ሂወታቸው በስቃይ የሚያልፉ ታሳሪዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ እየተሰማ ሲሆን የማረሚያ ቤቶቹ አስተዳደሮች ለሰው ልጅ ሂወት ክብር በመንፈግ ይህን ችግር ከመቅረፍ ይልቅ የፖለቲካ መቅጫ ዘዴ አድርገው መቀጠላቸው ታውቋል፡፡

ከዚህ ቀደም በቂሊንጦ ማረሚያ ቤትም ወረርሽኝ ገብቶ ጋዜጠኛ ዩሱፍ ጌታቸውን ጨምሮ በርካታ የማረሚያ ቤቱ ታሳሪዎች ለህመም ተጋልጠው እንደነበር ይታወሳል፡፤ በማረሚያ ቤቱ ባለው የንፅህና ጉድለት እና መጥፎ ሽታም ኮሚቴዎቻችንንም ጨምሮ ለከፍተኛ የሳይነስ እና ተዛማጅ በሽታዎች ተጋላጭ እንዲሆኑ እንዳደረጋቸው ይታወቃል፡፡

በዳላስ የምትነዳው መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ ሕይወቷ ያለፈው ወጣት ኢትዮጵያዊት ናት ተባለ

$
0
0

melat mamo 11 (ዘ-ሐበሻ) የዳላስ/ቴክሳስ ሚዲያዎች ትናንት ቅዳሜ በፌር ፓርክ አካባቢ የአንድ ሰው ሕይወት መኪና ከባቡር ጋር ተጋጭቶ መጥፋቱን ዘግበው ነበር። የዘ-ሐበሻ የዳላስ ምንጮች እንደጠቆሙት ከባቡሩ ጋር በመኪና ተጋጭታ ሕይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊት ናት።

የዳላስ ፖሊስ ትናንት ማምሻውን በሰጠው መግለጫው ባቡሩ መንገዱን በሚያቋርጥበት ወቅት መብራቶች እና ደውሎች እየተሰሙ የነበሩ ቢሆንም መኪናው ውስጥ የነበረ ሹፌር ይህን ደውልና መብራት ባለማስተዋል በሚያቋርጥበት ወቅት አደጋው ደርሷል። ከዳላስ በደረሰን መረጃ መሠረት በዚህ አደጋ ሕይወቷ ያለፈው ኢትዮጵያዊት ስትሆን ስሟም ሜላት ማሞ እንደሚሰኝ ከፎቶ ግራፏ ጋር የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በዳላስ ፖሊስ መረጃ መሠረት የተሳፋሪዋ ባቡሩና መኪናዋ በፈጠሩት ግጭት የተሳፋሪዋ ሕይወት ወዲያውኑ አልፏል። ይህን ተከትሎ በዳላስ ያሉ ኢትዮጵያውያን በወገናቸው ሕልፈት የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ ላይ ይገኛሉ።

እንደፖሊስ መረጃ ባቡሩ 24 ሰዎችን ይዞ ይጓዝ የነበረ ሲሆን ማንም ሰው ወደ ሆስፒታል ባይወሰድም 4 ሰዎች ጉዳት ደርሶብናል ብለዋል።

ሜላት ሃገሯን እና ወገኗን ወዳድ እንደነበረች የሚያውቋት የሚመሰክሩ ሲሆን በቅርቡ በሳዑዲ አረቢያ በወገኖቻችን ላይ የደረሰን ጥቃት ተከትሎ በዳላስ በተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ድምጿን ስታሰማ ነበር። (ፎቶው ከታች አያይዘነዋል)።

ፈጣሪ ነብሷን በገነት እንዲያኖረው ዘ-ሐበሻ በዚህ አጋጣሚ ሃዘኗን ትገልጻለች።
melat mamo
melat mamo dallas 2

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live