Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

የሕወሓቱ ልሳን ወይን ጋዜጣ አዘጋጅ ደብዛው ጠፋ

$
0
0

woyennews
አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

የወይን ጋዜጣ አዘጋጅ በመሆን ህወሓትን ለረጅም ግዜ ሲያገለግል የነበረው ጋዜጠኛ ሐገዞም መኮነን አዲስ አበባ ከሚገኝ ቤቱ ከጠፋ ሁለት ሳምንታት አለፉ። ጋዜጠኛ ሐገዞም መኮነን ወይን ጋዜጣ ሲያዘጋጅ ቆይቶ ከቅርብ ግዜ ወዲህ የህወሓት የዓፈና ተግባራትና አካሄድ በግልፅ መቃወም ከጀመረ ወራት አስቆጥሯል።

ከወይን ጋዜጣ አዘጋጅነት ለቆ የወይን ጋዜጣና የህወሓት የዓፈና ስትራተጂዎች የሚያጋልጥ መፅሓፍ ፅፎ ሊያስመርቅ በዝግጅት ላይ እያለ ያልታወቁ የፀጥታ አካላት በሌሊት ከቤቱ እንደወሰዱትና እስካሁን ያለበት እንደማይታወቅ ተገልፀዋል። ከወራት በፊት ማህተመስላሴ ገብረእግዚአብሄር የተባለ የሰሜን የፌደራል ፖሊስ የሎጂስቲክስና ፋይናንስ ሓላፊ በመቐለ ከተማ 16 ቀበሌ በፀጥታ ሃይሎች መገደሉ ይታወሳል።

በፀጥታ ሃይሎች የተፈፀመ ሙስና እንዳያጋልጥ በሚል ምክንያት ነው የተገደለው። በህወሓት አባላት ላይ ተደጋጋሚ ዓፈናና ግድያ ይፈፀማል፤ ግን አይጋለጥም። የማይጋለጥበት ምክንያት ግልፅ ነው።


የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በ‹‹አኬልዳማ›› ፕሮግራሙ ላይ በቀረበበት ክስ ተረታ

$
0
0

ሪፖርተር

በፕሮግራሙ ያስተላለፈውን ስም አጥፊ ዘገባ እንዲያርም ታዟል

የኢትዮጵያ ሬዲየና ቴሌቪዥን ድርጅት ከኅዳር 16 እስከ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. በተከታታይ ሦስት ክፍሎች ‹‹አኬልዳማ››  በሚል ባቀረበው ዘጋቢ ፕሮግራም፣

ክብርና ዝናን የሚያጠፋ በድምፅ፣ በምስልና በጽሑፍ በተቀነባበረ መንገድ ስሙን እንዳጠፋው በመግለጽ፣ አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) በመሠረተበት የፍትሐ ብሔር ክስ ተረታ፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ዘጠነኛ የፍትሐ ብሔር ችሎት መጋቢት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. በሰጠው ውሳኔ፣ አንድነት ፓርቲ መጋቢት 24 ቀን 2004 ዓ.ም. ባቀረበው ክስ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅትንና ፕሮግራሙን አቅርቧል በተባለው አቶ አብዲ ከማል ላይ ክስ መመሥረቱን አስታውሷል፡፡

ETVአንድነት በክሱ እንዳብራራው፣ በዲስፕሊን ግድፈት ከፓርቲው የተባረሩትን፣ በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት በራሳቸው ፈቃድ የለቀቁትንና በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው በሕግ ቁጥጥር ሥር የሚገኙትን ግለሰቦችና ተከሳሾች፣ የፓርቲው አባል እንደሆኑ አድርጐ በፕሮግራሙ ማሳየቱ አግባብ አለመሆኑን በክሱ አቅርቧል፡፡ ፓርቲውንና ሕጋዊ አባላቱን ሁከትና ብጥብጥ ፈጣሪዎች እንደሆኑ አድርገው ስም ማጥፋታቸውን አክሏል፡፡ ፓርቲውና ሕጋዊ አባሎቹ አሸባሪ ተብሎ በሕግ የተፈረጀው ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት፣ በህቡዕ በፓርቲው ውስጥ ሰርጐ እንደገባና እንደተደራጀ እያወቁ ሽፋን እንደሰጡ አድርገው ማቅረባቸውን አንድነት በክሱ አካቶ አቅርቧል፡፡ ፓርቲውን ግንቦት 7 የተባለው ድርጅት ለህቡዕ አደረጃጀት እየተጠቀመበት መሆኑንና የፓርቲው አባል ያልሆኑትን ወይም አባል ለመሆናቸው ምርጫ ቦርድ ያላረጋገጠለትን የሰዎች ስም በመጥቀስ አባል እንደሆኑ አድርገው በማቅረብ ተከሳሾቹ የፓርቲውን ስም ማጥፋታቸውን በመዘርዘር ለችሎቱ ክሱን ማቅረቡን ውሳኔው ያስረዳል፡፡

ተከሳሾቹ ስም የሚያጠፋውን ፕሮግራም የሠሩት ሆን ብለው፣ አቅደውና አስበው፣ ፓርቲው በሌሎች ወገኖች እንዲጠላ፣ እንዲዋረድ፣ እንዲሳቅበት፣ ያለው ተወዳጅነት፣ እምነት፣ መልካም ዝና ወይም የወደፊት ዕድሉ እንዲበላሽ በማድረግ፣ በቀጣዩ ምርጫ ሕዝቡ ጥርጣሬና ውዥንብር ውስጥ ገብቶ ድምፅ እንዲያጣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ የሚያገኘውን የሞራልና የገንዘብ ድጋፍ ለማዳከም በማሰብ የተፈጸመ መሆኑን አንድነት በክሱ ዘርዝሮ ማቅረቡን ክሱ ያብራራል፡፡

ድርጅቱና አቅራቢው የስም ማጥፋት ዘገባውን የሠሩት በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 24(1) የመልካም ስም መከበር መብትን፣ የብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ ቁጥር 533/1999 አንቀጽ 30(1) እና አንቀጽ 16(1)ሠን አንቀጽ 30(2)ን በመተላለፍ መሆኑንም የውሳኔው መዝገብ ይገልጻል፡፡ ሌላው ዘገባውን ከሠሩ በኋላ የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ ቁጥር 590/2000 አንቀጽ 40(1)ለንም ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆናቸውን አንድነት በክሱ መጥቀሱንና የምስክሮችንም ስም ለፍርድ ቤቱ ማቅረቡን ውሳኔው ያብራራል፡፡

ተከሳሹ ድርጅት በሰጠው ምላሽ ስም የማጥፋት ወይም የሐሰት ዘገባ አለመሥራቱን፣ በፕሮግራሙ የዘገበው እውነት መሆኑን፣ የማንንም ስም ለማጥፋት አቅዶ የሚንቀሳቀስ ተቋም አለመሆኑን፣ የፌዴራል መንግሥትና የሕዝብ መገናኛ ብዙኃን ድርጅት በመሆኑ በሕግ የተጣለበትን እውነትን የመዘገብና ለሕዝብ መረጃ የማቅረብ ግዴታውን በአግባቡ የሚወጣ ተቋም መሆኑንም አስረድቷል፡፡

በፕሮግራሙ ያቀረበው ዘገባ እውነትና ትክክለኛ መሆኑን፣ ሁሉንም የሚመለከቱትን አዋጆች ባከበረና መሠረት ባደረገ መንገድ መሆኑን፣ ሕዝብ መረጃ የማግኘትን መብት መሠረት ባደረገ የሕግ አስከባሪ አካላት የወሰዷቸውን ዕርምጃዎች ምንነት ማሳወቅ ግዴታ ስላለበት፣ በተጨባጭ መረጃ ተደግፎ የቀረበ እንጂ የማንንም ስም ለማጥፋት ተብሎ የተላለፈ ፕሮግራም አለመሆኑን በምላሹ አካቷል፡፡ የከሳሽ መልካም ስምና ክብሩ የተጐዳበት ዘገባ አለማስተላለፉንም አክሏል፡፡

በአዋጅ ቁጥር 590/2000 አንቀጽ 40(1) መሠረት አንድነት ፓርቲ ስሜና ክብሬ ተጐድቷል የሚል ከሆነ፣ በቅድሚያ ጉዳቱን ማረጋገጥ እንዳለበት ገልጾ፣ ፓርቲው ስሙና ክብሩ ባለመጐዳቱ የላከውን ማስተባበያ እንዳልተቀበለው በመልሱ አስታውቋል፡፡

የአባላቱ መልካም ስም መጥፋቱን ገልጾ ፓርቲው የመሠረተውን ክስ በሚመለከት ተከሳሹ እንዳስረዳው፣ አባሎቹ እነማን እንደሆኑ ባለመግለጹና በዘገባው መሠረት የተፈጸመውን በደል አለማረጋገጡን በመጥቀስ ክሱ ውድቀ እንዲደረግለት ፍርድ ቤቱን ጠይቋል፡፡ ድርጅቱ ዘርዘር ያለ መከራከሪያ ነጥቦችን በማቅረብ የተመሠረተበትን ክስ ተቃውሟል፡፡

በሁለተኛነት የተከሰሰው አቶ አብዲ ከማል በበኩሉ ባቀረበው የመከራከሪያ ሐሳብ የፕሮግራሙ አዘጋጅ አለመሆኑን በመግለጽ፣ አቅራቢ መሆኑንና በአዋጅ 590/2000 መሠረት ፕሮግራም አቅራቢ የሚከሰስበት ኃላፊነት እንደሌለ በማስረዳት፣ የቀረበበትን ክስ በመቃወሙ ፍርድ ቤቱም ተቀብሎ ክሱን በመሰረዝ በነፃ አሰናብቶታል፡፡

ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር መርምሮ የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት በሦስት ክፍሎች ባቀረበው ‹‹አኬልዳማ›› ፕሮግራም የአንድነትን ስም አጥፍቷል ወይስ አላጠፋም? አጥፍቷል የሚባል ከሆነ በአዋጅ ቁጥር 590/2000 አንቀጽ 40(1) መሠረት ማስተባበል አለበት የለበትም? የሚሉ ጭብጦችን ይዞ መመርመሩን ውሳኔው ይገልጻል፡፡

‹‹አኬልዳማ››  ፕሮግራም ከኅዳር 16 እስከ 18 ቀን 2004 ዓ.ም. ድረስ መቅረቡ አለማከራከሩን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ገልጿል፡፡ አንድነት ከፓርቲው በሥነ ምግባር ጉድለት የተባረሩትን፣ በራሳቸው ፈቃድ የለቀቁትንና አባል ያልሆኑትን ወይም አባል መሆናቸው በምርጫ ቦርድ ያልተረጋገጠውን የድርጅቱ አባል እንደሆኑ በማስመሰል ‹‹አኬልዳማ›› ፕሮግራም ላይ ዘግቧል የሚለውን ፍርድ ቤቱ በጥልቀት መመርመሩን በውሳኔው ገልጿል፡፡

ፓርቲው በቴሌቪዥን ዘገባው የፓርቲው አባል እንደሆኑ ተደርጐ ተዘግቧል ያላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ገልጾ በክሱ ባለማቅረቡ፣ ጥያቄው ለፍርድ ቤቱም ሆነ ለተከሳሽ ድርጅት አስቸጋሪ መሆኑንና በደፈናው መቅረቡ ተከራካሪ ወገን የመከራከር መብትንም የሚያጣብብ ሆኖ በማግኘቱ፣ የአንድነትን ክርክር ውድቅ ማድረጉን ውሳኔው ያሳያል፡፡ በፍትሐ ብሔር ሥነ ሥርዓት ሕግ ቁጥር 33 እና 231 ድንጋጌዎች መሠረት የቀረበ አለመሆኑንም ጠቁሟል፡፡

ፓርቲውንና ሕጋዊ አባላቱን በሕግ ከተፈረጀው ግንቦት 7 ጋር በህቡዕ ግንኙነት እንዳላቸው በማስመሰል፣ አመራሮቹ ግንቦት 7 በህቡዕ በፓርቲው ውስጥ ሰርጐ እንደገባና እንደተደራጀ እያወቁ ሽፋን ሰጥተዋልና ግንቦት 7 አንድነትን ለህቡዕ አደረጃጀት እየተጠቀመበት መሆኑን በመግለጽ፣ ፓርቲው የመሠረተውን ክስና ተከሳሽ ድርጅት ያቀረበው ምላሽ ፍርድ ቤቱ ትኩረት ሰጥቶ መመርመሩን ውሳኔው ያብራራል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለትክክለኛ ፍትሕ አሰጣጥ ይረዳ ዘንድ ‹‹አኬልዳማ›› በሚል ርዕስ በሦስት ተከታታይ ክፍሎች የቀረበውን የቴሌቪዥን ዘገባ አስቀርቦ መመልከቱን በውሳኔው ገልጿል፡፡

በተላለፉት ዘገባዎች ውስጥ የአንድነት ፓርቲን ስም ተከትለው የሚነሱ ስምንት ነጥቦችን ለማግኘት መቻሉን በውሳኔው ዘርዝሮ አቅርቧቸዋል፡፡ በመሆኑም የአንድነት ፓርቲም ሆነ አመራርና አባላቱ በክሱ እንደዘረዘረው በሕግ ከተፈረጀው ግንቦት 7 ጋር ግንኙነት እንዳላቸው በዘገባው መተላለፉ የሚያከራክር አለመሆኑን ፍርድ ቤቱ በሰጠው የውሳኔ ዝርዝር ውስጥ አካቶታል፡፡

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 24(1) መሠረት ማንኛውም ሰው ሰብዓዊ ክብሩና መልካም ስሙ የመከበር መብት እንዳለው መደንገጉን የጠቀሰው ፍርድ ቤቱ፣ አንድነት ፓርቲ መልካም ስሙ ሊከበርለት እንደሚገባ በውሳኔው አስፍሯል፡፡

አንድ ሰው በንግግሮቹ፣ በጽሑፎቹ፣ በሌላ ዓይነት አድራጐቶቹ በሕይወት ያለውን የአንደኛውን ሰው ስም በማጥፋት፣ ሰው እንዲጠላው፣ እንዲያዋርደው፣ እንዲሳቅበትና በእሱ ላይ ያለው እምነትና መልካም ዝናውና የወደፊት ዕድሉ እንዲበላሽ ያደረገ ሰው፣ በፍትሐ ብሔር ሕግ ቁጥር 2044 መሠረት ጥፋተኛ እንደሚባል ፍርድ ቤቱ በውሳኔው ጠቁሟል፡፡ ጥፋተኛ መሆኑ በፍርድ ቤት ውሳኔ ያልተረጋገጠበትን ሰው ተጠርጣሪም ቢሆን እንኳ፣ በሕግ የሚያስቀጣ ወንጀል ሠርቷል ማለት ስም ማጥፋት እንደሆነ በፍትሐ ብሔር ሕግ 2109(ሀ) መደንገጉን ፍርድ ቤቱ ጠቅሶ፣ አንድነትን የሽብር ሁከትና ብጥብጥ ፈጣሪ፣ እንዲሁም በሕግ አሸባሪ ከተባሉ ድርጅቶች ጋር ግንኙነት ያለው ከመሆን አልፎ የሽብር ተልዕኳቸውን እንዲያሳኩ አመቻች የሆነ መሆኑን የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድረጅት መግለጹን በውሳኔው አስፍሯል፡፡

ተከሳሽ ድርጅት በጠቀሳቸው የሽብር፣ የሁከትና የብጥብጥ ፈጣሪ መሆንና በሕግ አሸባሪ በመባል ከተፈረጁ ድርጅቶች ጋር ሆኖ መገኘት፣ በፀረ ሽብርተኝነት አዋጅ ቁጥር 652/2001 አንቀጽ 5፣ 6 እና 7 መሠረት በወንጀል ሊያስቀጣ እንደሚችል የጠቆመው ፍርድ ቤቱ፣ ድርጊቱ ባልተረጋገጠበት ሁኔታ በአንድነት ፓርቲ ላይ ዘገባ ማስተላለፍ የፍትሐ ብሔር ሕግ 2044 እንዲፈጸምበት ከማድረግም በተጨማሪ፣ በፍትሐ ብሔር ሕግ 2109(ሀ) መሠረት ተከሳሽ ስም ማጥፋቱን የሚያረጋግጥ መሆኑን በውሳኔው አረጋግጧል፡፡

ተከሳሹ ያስተላለፈው ዘገባ እውነትና በመረጃ የተደገፈ መሆኑን ገልጾ ያቀረበው መከራከሪያን ፍርድ ቤቱ ውድቅ ማድረጉን፣ የከሳሹ የክስ አቤቱታ ውድቅ እንዲደረግ ተከሳሽ መጠየቁ የሕግ ድጋፍ እንደሌለው፣ ተከሳች በአጠቃላይ የሕገ መንግሥቱን አንቀጽ 24(1)ን፣ የብሮድካስት አገልግሎት አዋጅ 533/1999 አንቀጽ 30(1)ንና አንቀጽ 30(2)ንና የመገናኛ ብዙኃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ 590/2000ን የተላለፈ መሆኑን ፍርድ ቤቱ በውሳኔው አብራርቷል፡፡

በመሆኑም በአዋጅ 590/2000 መሠረት ከሳሽ በ‹‹አኬልዳማ›› የቴሌቪዥን ፕሮግራም ዘገባ ስሙ የጠፋበትን ማስተባበያ ዘገባ የሚያርም መልስ በቴሌቪዥን ጣቢያው እንዲያስተባብል ፍርድ ቤቱ መፍረዱን መጋቢት 23 ቀን 2006 ዓ.ም. በሰጠው ዝርዝር ውሳኔ አስታውቋል፡፡

 

አንድነት –ህግን እያከበርን የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን!! (ሰልፉ ለሚያዚያ 5 ተላለፈ )

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)
UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY
(UDJ)
ህግን እያከበርን የማስከበር ኃላፊነታችንን እንወጣለን!!
——————————————

ከአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ከዕለት ወደ ዕለት እየተባባሰ በመጣው የማህበራዊ ግልጋሎት አቅርቦት እጥረትናአለመመጣጠን ምክንያት መንግሥት በተደጋጋሚ ጊዜ የእርምት እርምጃዎችን እንዲወስድ ቢጠየቅም የወሰደው እርምጃ ባለመኖሩ ፓርቲያችን መጋቢት 28 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ‹‹የእሪታቀን›› በሚል መሪ ቃል ታላቅ ሠላማዊ ሠልፍ እንደሚያደርግ ለህዝብ በመገናኛ ብዙሃን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡

ሆኖም «የአዲስ አበባ ከተማ ሠላማዊ ሠልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ክፍልበመጋቢት 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓም በቁጥር አ.አ ከስ/1ዐ/3ዐ.4/236 በላከልን ደብዳቤ ሠላማዊ ሠልፉን ለማድረግ በጠየቅንበት ቀን ተመሳሳይ የህዳሴ ግድብ ፕሮግራሞች ስላሉ ተለዋጭ ቀንእንድናቀርብ ጠይቆናል፡፡ በዚሁ መሠረት ለመጋቢት 28 ቀን 2ዐዐ6 ዓም ለማድረግ የያዝነውን ፕሮግራም ለማሸጋገር የህግ ግዴታ ስላለብን ለሚያዚያ 5 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም ያዛወርን መሆኑንለኢትዮጵያ ሕዝብ በአክብሮት እንገልፃለን፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ የአዲስ አበባ ምክር ቤት
መጋቢት 26 ቀን 2ዐዐ6 ዓ.ም
አዲስ አበባ

UDJ

 

 

 

 

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ለማስመለስ የኢህአዴግ ልኡካን በጄኔቫ

$
0
0

ETH J

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ወደ ኢትዮጵያ ለማስመለስ በአቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራ ከፍተኛ የኢህአዴግ ልኡካን ቡድን ጄኔቭ፣ ስዊዘርላንድ ከርሞ ባለፈው ሳምንት ተመልሷል።

በፓርላማው የህግ እና የአስተዳደር ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሊቀ-መንበር የሆኑት አቶ አስመላሽ ወልደ-ስላሴ የተመራው ይህ ቡድን ከ March 13፣ 2014 ጀምሮ የስዊዘርላንድ መንግስት አካላት ጋር በሃይለመድህን ጉዳይ ላይ ለቀናት ተወያይቷል።  ስዊዘርላንድ ረዳት ፓይለቱን አሳልፋ እንድትሰጥም ቡድኑ ብዙ ሙከራ አድርጎ እንደነበርና ሙካራው ሁሉ ሳይሳካ መቅረቱንም ለማወቅ ችለናል።

ቡድኑ የስዊስ ፌዴሬሽን የህግ አካላትን ለማሳመን ካቀረበው ምክንያት ዋነኛው፣ ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ የአእምሮ በሽተኛ መሆኑን እና ይህንንም ከራሱ ቤተሰብ አባላት እንዳረጋገጡላቸው ገልጸዋል።  የስዊዝ መንግስት ግን ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል። ለዚህም የሰጠው ዋነኛ ምክንያት፤ የሞት ፍርድን ተግባራዊ ለሚያደርግ መንግስት ማንንም አሳልፌ አልሰጥም የሚል ሲሆን ይህ ባይሆንም፣  በስዊዘርላንድ እና በኢትዮጵያ መሃል ተጠርጣሪ እስረኛን የማስመለስ ውል የለም ብለዋል።

በተያያዘ ዜና ወንድሙ ዶ/ር እንዳላማው አበራ እና በጀርመን የምትኖር እህቱ ሃይማኖት አበራ ጄኔቭ ድረስ በመምጣት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራን ከሚገኝበት እስር ቤት ጎብኝተውታል። የስዊስ ጠበቆችም የፓይለቱ መብት እንዲከበር አጥብቀው እየሰሩ ይገኛሉ። መገናኛ ብዙሃን ላይ ሲደሰኩሩ የነበሩ አንዳንድ የኢትዮጵያ የህግ ባለሞያዎች እዚህ ጉዳይ ላይ እንዲተባበሩ ሲጠየቁ አሳፋሪ ምላሽ መስጠታቸውንም ጉዳዩን በቅርብ ከሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ለመረዳት ችለናል።

ረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ባለፈው የካቲት 10፣ 2006 ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድ ንብረት የሆነውን ቦይንግ 767 አግቶ ጄኔቭ ስዊዘርላንድ ላይ በማሳረፍ እዚያው የፖለቲካ ጥገኝነት መጠየቁ ይታወሳል። የአለም ዜና ርዕስ ሁሉ ትኩረት ስቦ የነበረው ይህ ልዩ ክስተት የኢትዮጵያን የሰብአዊ መብት ሁኔታና የአስተዳደር በደል አደባባይ በማውጣቱ የገዢው ፓርቲ አባላትን እጅግ እንዳበሳጨ ይነገራል።

አንዳንድ መገናኘ ብዙሃን እንደገለጹት የአጎቱ ድንገተና ህልፈት ርዳት ፓይለቱን አስቆጥቶት ነበር። የሃይለመድህን አበራ አጎት፤ ዶ/ር እምሩ ሥዩም ህይወት በድንገት ማለፍ ለብዙዎች ያልተፈታ እንቆቅልሽ ነው።  ዶ/ር እምሩ ሥዩም የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህር ነበሩ።

በአለም ዙሪያ ያሉ ኢትዮጵያውያን ወጣቱ ፓይለት ሃይለመድህን አበራን መደገፋቸውን እንደቀጠሉ ሲሆን በረዳት ፓይለቱ ስም የተከፈቱ ድረ-ገጾች እና የፌስቡክ መድረኮች ላይ ሰፊ ዘመቻ በማድረግ ላይ ይገኛል።

የስዊዝ ቴሌቭዥን በረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ዙርያ አንድ ዘጋቢ ፊልም የሰራ ሲሆን ይህ ዘገባ ለትንሽ ግዜ እንዲዘገይ ተደርጓል። ዘጋቢ ፊልሙ አየር ላይ ያልዋለበት ምክንያት የረዳት ፓይለት ሃይለመድህን አበራ ጠበቆች እንዲዘገይ በመጠየቃቸው ነው ሲሉ ጉዳዩን የሚከታተሉት ኢትዮጵያውያን ገልጸዋል።

 

 

የጃኪ ጎሲ የሰሜን አሜሪካ የሙዚቃ ኮንሰርቶች የሕግ ጥያቄዎች አሉበት፤ ይሳካ ይሆን? አላሙዲ ከጃኪ ጀርባ አለ?

$
0
0

የምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ባለቤት ሸዋ ኢተና የጃኪ ጎሲን የሙዚቃ ኮንሰርት በሰሜን አሜሪካ ለማየት ለሚጠባበቁ ወገኖች ጥሪ አቀረበ። ከዚህ ቀደም የስራ ፈቃድ አውጥተንለት ወደ ሰሜን አሜሪካ እንዲመጣ ጉዳዩን ጨርሰን ኮንሰርት እስከመሰረዝ ደርሰናል፤ በዚህም ኪሳራ ደርሶብናል በሚል የሚከሰው የሸዋ ኢንተርቴይመንት በተለይም በቅርቡ ዋሽንግተን ዲሲን ጨምሮ በተለያዩ የአሜሪካ ግዛቶች ድምጻዊው ኮንሰርት ያቀርባል ብለው ሰዎች ገንዘባቸውን እንዳያፈሱ ጥሪውን አቅርቧል። “ጃኪ ባለን ስምምነት መሰረት [ከሌላ ሰው ጋር] (ምንም ዓይነት ኮንሰርት) መስራት አይችልም” የሚለው ሸዋ “በጃኪ ላይ ስለሚወሰደው እርምጃ ሕዝቡ እንዳያዝን” ይላል። የሸዋ ባለቤት ከኢትዮቲብ ድረ ገጽ ጋር ካደረገው ቃለ ምልልስ እናስቀንጭብዎ እና አወዛጋቢው ጃኪ በድጋሚ በማወቅም ይሁን በማያውቀው መንገድ ከሌሎች ጋር ስለመላተሙ የሚዘግበውን ጽሁፍ ከታች አቅርበናል። ከዚህ ቀደም ጃኪ ለዘ-ሐበሻ ‘ከምነው ሸዋ ጋር ምንም ስምምነት ኖሮኝ አያውቅም” ሲል መናገሩ አይዘነጋም።

የድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ያሜሪካ ዝግጅት ለ 2ኛ ጊዜ ውዝግብ አስነሳ

ይህ በጃኪ ኮንሰርት ዙሪያ ተክደናል የሚሉ ወገኖች ያሰራጩት መረጃ ነው።

ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በጥቂት ነጠላ ዜማዎቹ ከፍተኛ ዝናን ያገኘ ወጣት ድምፃዊ ነው። ጃኪ ጎሲ የኢትዮጵያን ባህላዊ የአዘፋፈን ስልቶች ከዘመናዊው ሙዚቃ ጋር የሚያዋህዱ ማራኪ ስራዎቹ በህዝብ ዘንድ እጅግ ፈጣን እውቅናን አጎናጽፈውታል። ይህ ወጣት ድምፃዊ በኢትዮጵያ የሙዚቃ አለም ገና ከጅምሩ የደረሰበት ደረጃ ወደፊት ብዙ ሊሰራና ከፍተኛ ዝናን ሊጨብጥ እንደሚችል አመላካች ነው።

ከዚህ በፊት እንደሚታወቀው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከምነው ሸዋ ኢንተርቴይመንት ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ውዝግብ ውስጥ ገብቶ እንደነበር ይታወቃል። ጃኪ ጎሲ በ2012 በፈረንጆቹ አቆጣጠር በሰሜን አሜሪካ ሃገራት ሊያደርጋቸው የነበሩ የሙዚቃ ኮንሰርቶች በዚህ ውዝግብ ምክንያት በመሰረዛቸው ብዙ አድናቂዎቹን እንዳሳዘነ ይታወሳል።

jacki gosseeበጃኪ ጎሲ ዙሪያ ከዚህ በፊት የተፈጠረው ውዝግብ ብዙ ኢትዮጵያውያን አድናቂዎቹን ማስከፋቱ የሚያሳዝን ክስተት ሆኖ ሳለ፤ ዘንድሮም በዚሁ አርቲስት ዙሪያ በሌሎች የኢንተርቴንመንት ስራን በሚሰሩ ሁለት ድርጅቶች መካከል በድጋሚ የተፈጠረው የሚያስገርም ውዝግብ የበለጠ ህዝብን የሚያሳዝን፣ የድምፃዊውንም ስምና ዝናን የሚያጎድፍ፣ እንዲሁም በዙሪያው አብሮ ለመስራት ሽር ጉድ የሚሉትን ፕሮሞተሮች ስምና ስብእናን ከጥርጣሬ ውስጥ የሚከት በመሆኑ፤ በጉዳዩ ዙሪያ ላሉ አካላትና ለአንባቢያን ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ ነው።

ነገሩ እንዲህ ነው፤ ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንና ማሂ ፕሮደክሽን በሰሜን አሜሪካ አትላንታ ከተማ የሚገኙ ሁለት የኢንተርቴንመንት ስራን የሚሰሩ ድርጅቶች ሲሆኑ፤ የሺ ማርት ደግሞ በዚሁ በአትላንታ የሚገኝ የሃበሻ ሱቅ ነው። ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቶች ለማዘጋጀት ከየሺ ማርት እና ከኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን ጋር በመሆን በጋራ ስምምነት ያደረጉ ሲሆን፤ ይህንኑ ለማስፈጸምላለፉት ሁለትአመታት ወደ ሰሜን አሜሪካ ለመግባት የሚያስችለውን ፕሮሰስ ለመጨረስ ሙከራ በማድረግ ላይ ቆይቷል። ሆኖም በኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን አማካኝነት እየተሞከረ የነበረው የፕሮሰስ ሂደት ሳይሳካ በመቅረቱ ምክንያት፤ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን ከሌላ አካል እርዳታ አስፈልጎት ነበር።

በዚህም መሰረት ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን እዚሁ አትላንታ የሚገኘውን ማሂ ፕሮደክሽን የአርቲስት ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ እንዲያስጨርስለት በመጠየቅ፤ ስምምነት አድርጎ ነበር። ስምምነቱን ባጭሩ ለመግለጽ ያክል፤ ማሂ ፕሮደክሽን የድምፃዊ ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ ካስጨረሰ ድምፃዊው በሰሜን አሜሪካ ከሚያደርጋቸው ኮንሰርቶች ውስጥፕሮደክሽኑ በሚመርጠው አንድ ቦታ ላይ ድምፃዊ ጃኪን ሊያሰራ፤ ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንም ቃሉን አክብሮ ይህንኑ ሊያስፈጽም ነበር።

እንደ ማሂ ፕሮደክሽን መረጃ ከሆነ በዚህ ስምምነት መሰረት ማሂ ፕሮደክሽን የድምፃዊ ጃኪ ጎሲን የቪዛ ፕሮሰስ አስጨርሶ ድምፃዊው ወደ ሰሜን አሜሪካ የሚያስገባውን ቪዛ በእጁ እንዲገባ አድርጓል። ነገር ግን ኢቫንጋዲ ፕሮደክሽን የገባውን ቃል አክብሮ መፈጸም ሲገባው፤ ማሂ ፕሮደክሽን ያደረገውን ውለታ እንደማያውቅና የድምፃዊ ጃኪ ጎሲ የቪዛ ጉዳይ ያለቀው በሼክ ማሃሙድ አል አሙዲን በኩል እንደሆነ በመናገር ላይ ይገኛል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ማሂ ፕሮደክሽን በተፈጠረው ሁኔታ ስለተበሳጨ ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ በዝግጅት ላይ እንደሆነ ይናገራል።

(ከዚህ ቀደም የተሰረዘው የጃኪ ኮንሰርት ፍላየር)

(ከዚህ ቀደም የተሰረዘው የጃኪ ኮንሰርት ፍላየር)

እዚህ ላይ በጣም የሚገርመው ጉዳይ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በኢቫንጋዲ ፕሮደክሽንና በማሂ ፕሮደክሽን መካከል ስምምነቱ ሲደረግና የቪዛ ጉዳዩ ያለቀው በማሂ ፕሮደክሽን በኩል መሆኑን እያወቀ ችላ በማለቱ ምክንያት ለሁለተኛ ጊዜ ውዝግብ ውስጥ መግባቱ ነው። ጥፋተኛው ማንም ሆነ ማን፤ የዚህ ፅሁፍ ዋናው አላማ ድምፃዊ ጃኪ ጎሲን ጨምሮ ሶስቱም አካላት ውዝግቡ የሚያስከትለውን መዘዝ ከወዲሁ ተገንዝበው በቶሎ መፍትሄ እንዲያበጁለት በአፅንዖት ለማስገንዘብ ነው።

በመጨረሻም ፅሁፋችንን ላነበቡና ሃሳባችንን ለተጋሩ ሁሉ ከፍ ያለ ምስጋናችንን እያቀረብን፤ የምንሰናበተው ይህንን ጎጂና ደስ የማይል ውዝግብ በተመለከተ፤ ጉዳዩ በቀጥታ የሚመለከታቸው አካላት የሚሰጡትን መልስ ጨምሮ፤ ሰፋያለ መረጃ በቅርቡ ይዘን እንደምንቀርብ ቃል በመግባት ነው::
——————————–

አንባቢያንስ ምን ትላላችሁ? ይህ ተወዳጅ ድምጻዊ እንደዚህ ያሉ ውዝግቦች ውስጥ መግባት ነበረበት ወይ? አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ካወጣው 4 ዘፈን አኳያ ይህ ሁሉ ነገር ይገባዋል ወይ? በሌሎች ወገኖች እንደሚከሰሰው አላሙዲ ጋር ስሙ መያያዙ በልጁ የወደፊት ሥራ ላይ የሚፈጥረው ነገር ይኖራል? አስተያየታችሁን ጻፉት።

ነገ በደሴ ለሚደረገው የተቃውሞ ሰልፍ እየተደረገ ያለውን ቅስቀሳ የሚያሳይ ፎቶ ዜና

$
0
0

የአንድነት ፓርቲ “የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪ ቃል 2ኛውን ዙር ሕዝባዊ ንቅናቄ በደሴ ከተማ ነገ እሁድ ኤፕሪል 6 ቀን 2014 ዓ.ም በሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ ያደርጋል። የደሴ ነዋሪዎች አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን እንዲያሰማ አንድነት ጥሪ ያቀረበ ሲሆን የፓርቲው መሪዎች ሳይቀሩ ሕዝብ በተሰበሰበት በመገኘት በራሪ ወረቀቶችን በመበተን፣ በሞንታርቦ እና በሌሎችም መንገዶችም በመቀስቀስ ላይ ይገኛሉ። ነገ እሁድ በደሴ የሚደረገውን ሰልፍ በማስመልከት እየተደረገ ያለውን ቅስቀሳ የሚያሳየውን ፎቶዎች ይመልከቱ።
udj dessie 2

udj dessie 3

udj dessie 4

udj dessie 5

udj dessie 6

udj dessie 7

udj dessie 8

udj dessie 9

udj dessie

ህወሓት በአፅቢ (እንዳስላሴ) ረብሻ ለመቀስቀስ እየሞከረ ነው፤ ነገ እሁድ አረና ለጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳውን ቀጥሏል

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

Arena-Tigray-logoየዓረና አባላት ለነገ እሁድ መጋቢት 28 በአፅቢ (እንዳስላሴ) ከተማ ለሚደረግ ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ እያደረጉ ይገኛሉ። በዓድዋ ቅስቀሳ ስናደርግ “እንዳትነኳቸው፣ በሰላም ይቀስቅሱ!” ብሎ መመርያ የሰጠ በመቐለ ከተማ የሚገኝ የህወሓት ከፍተኛ አመራር ዛሬ በአፅቢ ከተማ በምናደርገው ቅስቀሳ ረብሻ እንዲነሳ መመርያ መስጠቱ ከአንድ ሰዓት በፊት ሰማሁ። አላመንኩም ነበረ። ለማረጋገጥ ወደ አፅቢ ደወልኩ።

የዓረና አባላት ቅስቀሳ ሲያደርጉ ገብረማርያም የተባለ የወረዳው የሚልሻ አዛዥ ወጣቶችን አሰባስቦ የሚታደለውን ወረቀት መቅደድና መሳደብ መጀመራቸው ተነገረኝ። በራሪ ወረቀቱ መቅደድና መሳደብ የጀመረው የወረዳው ዋና አስተዳድሪ ሲሆን እሱን ተከትለው የሚረብሹ የተደረጁ ወጣቶችም ነበሩ። አሁን ህዝቡ ጣልቃ ገብቶ የሚረብሹ ወጣቶችን አስፈራርቷል። ዋና አስተዳዳሪውን በህዝብ ተሰድቧል። አሁን ሁኔታው ተረጋግተዋል። አቅጣጫው ግን በተደራጀ መልኩ የሚከናወን የዓዲግራትን ዓይነት ይመስላል። በአፅቢ ወንበርታ በጣም ብዙ የዓረና አባላትና ደጋፊዎች አሉ። ከወራት በፊት ህወሓትን ተቃውመው ዓመፅ አስነስተው እንደነበር ይታወሳል። አሁን ወደ አፅቢ እየሄድኩ ነው።

የተጋላቢጦሽ! ተቃዋሚ ፓርቲ ሰላምና ፀጥታ እንዲከበር ጥረት ሲያደርግ ገዥው ፓርቲ (መንግስት) ደግሞ ረብሻ ለመቀስቀስ ጥረት ያደርጋል፤ ስልጣኑ ተጠቅሞ የህዝብን ሰላም የሚበጠብጡ ወጣቶች በክፍያ ያደራጃል፣ ሰለማዊ ሰው እንዲደበድቡ ያበረታታል። ዓመፅ መቀስቀስ ለምዷቸው ይሆን?! ዓረና ግን ሰለማዊ ፓርቲ ነው። ለህዝብ ነፃነት ስንል እንደበደባለን፤ ለሰላም ስንል መስዋእት እንሆናለን። ምክንያቱም የሰላም መንገድ ሰለማዊ መሆን መሆኑ እንረዳለን። ትግሉ ስንጀምር ብዙ መስዋእትነት እንደሚያስከፍለን እናውቃለን። የአፅቢ ህዝብ እንደሚተባበረንም እርግጠኞች ነን።

በደሴ ፖሊስና የደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች የሰላማዊ ሰልፉን ቅስቀሳ ለማደናቀፍ ያደረጉት ሙከራ ሳይሳካ ቀረ

$
0
0

April 5, 2014 8:00 am

የፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ባልደረቦች ክስተቱን በፎቶግራፍ አንስተዋል

የአንድነት ከፍተኛ አመራሮችን ያካተተውን የቅስቀሳ ቡድን ተግባር ለማደናቀፍ ፖሊሶችና ደህንነት ነን የሚሉ ግለሰቦች በስውር ቪዲዮ በመቅረፅ እና ስለሙስሊሙ የመብት ጥያቄ የሚስተጋቡ መፈክሮችን ለማስቆም ሙከራ አድርገዋል፡፡ በተለይም የከተማዋ የፀጥታ ዘርፍ ሀላፊ ቅስቀሳው በተደረገባቸው ስፍራዎች በመገኘት የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችን ለማስፈራራትና ከቅስቀሳ ቡድኑ አባል ላይ የቅስቀሳ ቁሳቁስ ለመንጠቅ ሲሞከር በዝምታ ተመልክተዋል፡፡ ይህ ሁሉ የማደናቀፍ ሙከራ ቢደረግም ቅስቀሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል፤  የደሴ ህዝብ ከአንድነት ፓርቲ ጎን በመሆን ቅስቀሳውን አጧጡፎታል፡፡

101

1015
1017

 

 


አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታው መድሃኔዓለም ቤ/ክ ተቃውሞ ገጠማቸው (ቪዲዮ ይዘናል)

$
0
0

አቡነ ዘካሪያስ በሚኒሶታ ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ከፍተኛ ተቃውሞ ደረሰባቸው። በቪድዮ ተደግፎ በደረሰን መረጃ መሠረት ምዕመናኑ “ጎጃም ላይ የተሰረቀው ገንዘብ ሚኒሶታ ላይም አይደገምም” በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አሰምተውባቸው አንዳችም ንግግር ሳያደርጉ ከደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ እንዲወጡ መደረጋቸው ተገልጿል።

ከዚህ ቀደም ሲያስተምሩ “በኢትዮጵያው ሲኖዶስ ስር ካልገባችሁ ኢትዮጵያ መቀበር የለም”፣ የሚሶታውን መድሃኔዓለም ቤ/ክ “በረት” ሲሉ ገልጸውታል በሚል ከፍተኛ ተቃውሞ የደረሰባቸው አቡነ ዘካሪያስ ከአቡነ ማርቆስ ጋር በመሆን ቤተክርሲያኑ በመንታ መንገድ ላይ ባለበት ሰዓት የመጡት ለመከፋፈል ነው በሚል ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ምዕመናን ይከሳሉ። የአቡነ ዘካሪያስን የአቡነ ማርቆስን የሚኒሶታ ደብረሰላም ቤ/ክ የተቃውሞ ውሎ የሚያሳይ ቪድዮ ይመልከቱ፤ ከታች ደግሞ ለሰላም እና ለአንድነት የቆሙ ም ዕመናን ያቀረቡትን ወቅታዊ ጽሁፍ ይመልከቱ አቡነ ዘካሪያስ የጎጃምን ሃገረ ስብከት በሚመሩበት ወቅት ስላጎደሉት ገንዘብ በቪኦኤ ሲጠየቁ “ገንዘቡ ጎሎብኛል፤ ለምኜ እከፍላለሁ” ማለታቸውን ብዙዎች ያስታውሱታል።

አቡነ ዘካሪያስን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፤ እንዳገኘናቸው ይዘን ለመቅረብ እንሞክራለን።

በእግዚአብሔር ስም አሜን። 4/5/2014

ለሰላምና ለአንድነት የቆሙ ምእመናን
አንድነትን፣እርቅንና ሰላምን ከራሳችሁ ጀምሩ!

በኢተዮጵያ ቤተክርስቲያን ታሪክ ውስጥ እንደዚህ ዘመን ትልቁ ትንሽ የሆነበት ኃይማኖቱን በእለት ጥቅምና ሹመት ለውጦ ሁሉም ከትልቅ እስከትንሽ ለሆዱ ያደረበት ጊዜ የለም። የቀደሙት አባቶቻችን የቤትከርስቲያንን መብትና ሉአላዊነት ከማስከበር አልፈው ለአገራቸውም አርበኛና ሰማዕታት በመሆን
በታሪ የላቀች ሉዐላዊት ሃገርንና ርትዕት ኃይማኖትን አቆይተውልናል። ራቅ ያለውን ታሪክ ትተን የቅርቡን የጣሊያን ፋሺስት ወረራ ዘመን እንኳን ብናስታውስ ብዙ ካህናት አባቶች ከጀግኖት አርበኞች ኢትዮጵያውያን ጋር ሆነው ለአገራቸውና ለኃይማኖታቸው ሰማእትነትን ተቀብለዋል። ታላቁ ጻድቅና
አርበኛ ሰማእት ቅዱስ አቡነ ጴጥሮስ የሰሩት እጅግ አስደናቂ ታሪክ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀስ ነው።

መንጋውን እንዲጠብቅ በወንጌል የታዘዘ እረኛ ሕይወቱን እስከ ሞት ድረስ ለበጎቹ አሳልፎ ይሰጣልና ኅዝቧም ምድሪቷም አይገዙልህ ብለው ጠላትን በማውገዝ በእግዚአብሔርም በሰውም ዘንድ የማይረሳ አኩሪ ተጋድሎን በደም ቀለም ጽፈውልን አልፈዋል። ዛሬስ? ንዑዳን ክቡራን የተባሉ አባቶች ለስማቸውና ለክብራቸው የሚገባ ሥራ እየሰሩ ይሆን?

በአደባባይ ቤተክርስቲያን በአላውያንና በመናፍቃን ሹማምንት ስትሰደብ፣ገዳማቶቿ ሲደፈሩና ሲቃጠሉ፣ ካህናትና ምእመናን ሲታረዱ፣ ጥንታዊትና ታሪካዊት የሆነች ሃገርን ያቆየች ቤተክርስቲያን እንደወፍ ዘራሽ የትም ከበቀሉ ድርጅቶች ጋር ትቆጠሪያለሽ እንደ አዲስ ተመዝግበሽ ፈቃድ አውጥተሽ ብቻ ነው
መንቀሳቀስ የምትችይው ስትባል፣ ቤተክርስቲያን የነፍጠኛ ዋሻ ናት እያሉ በገሃድ አላውያኑ ሲሳደቡ፣ መለኪያው ኦርቶዶክስ የነበረውን ሰብረነዋል እየተባለ ሲፎከር የዛሬዎቹ አባቶች ጳጳሳት ምን እየሰሩ ነበር? ይሆን? እውነቱን እውነት ሐሰቱን ሐሰት ማለት ለምእመናን ብቻ የተጻፈ የወንጌል ቃል ነው እንዴ?

ሰሞኑን በዚህ በሜኒሶታ ደብረሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን በጥቂት አማጽያን ግለሰቦች የቤተክርስቲያናችንን ሰላምና አንድነት ለማደፍረስ ተጠንሶ እየተካሔደ ባለው ስርዓት አልበኝነት አንዳንድ ከኢትዮጵያ የመጡና እዚሁ የከረሙ ‘ጳጳሳት’ ቢመከሩና ቢዘከሩ እምቢ ብለው በእሳት ላይ ቤንዚን ለማርከፍከፍ መጥተዋል። የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች እንዲሉ ለ3 አመታት ያህል ሲለፋበትና ከፍተኛ ውጣ ውረድ ሲደረግበትቆይቶ ወደ ፍጻሜ ደርሶ የነበረውን የኢትዮጵያ ቤተክርስቲይያን የሰላምና የእርቅ ሂደት በኢትዮጵያ ሥልጣን ላይ ካለው ኃይል ጋር በመሆን ካፈረሱ በኋላ አሁን ደግሞ የቤተክርስቲያን አንድነትና ሰላም ፈላጊ መስለው ምእመናንን ለመከፋፈልና የቤተክርስቲያንን ችግር ከድጡ ወደማጡ ለማውረድ የሾማቸውን ኃይል ተልዕኮ ለመፈጸም እየዳከሩ እገኛሉ።

በቤተክርስቲያን አባቶች ዙሪያ ያለው ልዩነት በግልጽ በፖለቲካ ጣልቃገብነት የተፈጠረ መሆኑን ሁላችንም ጠንቅቀን እናውቃለን። ይሁን እንጂ የችግሩን መንስዔ በመሸፋፈን ምእመናን እውቀት አንሷቸው የቤተክርስቲያን ስርአት የተበላሸ ይመስል የራሳቸውን ጥፋትና ችግር የችግሩ መንስ ኤ የሆነውን ኃይል
በሚቃወሙ ምእመናን ላይ በመላከክ ለማጭበርበር ሲሞክሩ ይታያሉ። ወያኔ ያበላሸውን ቀኖና ቤተክርስቲያን ወደጎን በመተው፤ ለሥልጣንና ለጥቅም አድረው ዋናውን ችግር ለመፍታት ከመንበርከክ ይልቅ እናንተም እንደእኛ ለሆዳችሁ እደሩ፣ ባንዳ ሁኑ እያሉ የማይገባ ነገር ሲናግሩና ሲሰሩ ማየት እጅጉን ያሳዝናል።

በመሰረቱ አባቶች እንደ አባቶች ሊከበሩና ሊታዩ የሚችሉት እንደ አባት ሆነው የሃገርና የቤተክርስቲያን ጠላት ከሆነው ኃይል ራሳቸውን ሲያገሉ አልያም ያልፍርሃት ክፉ ስራውን ሲቃወሙ ነው። ቄሱም ዝም መጽሐፉ ዝም ከሆነ ግን ቄሱም ቄስ አይደለም መጽሐፉም መጽሐፍ አየደለም!!!

በፖለቲካኖች ታቅዶ ቤተክርስቲያናችንን ለመንጠቅ እየተካሔደ ያለውን ታላቅ ሴራ ለማክሸፍ እየተደረገ ባለው ትንቅንቅ ላይሁላችሁም በመገኘት ምንደኞችን እንድናሳፍር ጥሪያችንን እናቀርባለን።

በአማራ ክልል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎች ሜዳ ላይ ወድቀዋል ሰማንያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል በጀት ስለሌለን ምንም ያደረግነው የለም

$
0
0

 

በአማራ ክልል ከአምስት ሺህ በላይ ዜጎች ሜዳ ላይ
ወድቀዋል ሰማንያ ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል
በጀት ስለሌለን ምንም ያደረግነው የለም
አቶ አማረ በሪሁን የወረዳ የብአዴን ኃላፊ
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ በመቄት ወረዳ ቀበሌ 0 40 ልዩ ቦታው አሳሳ በተባለ ቦታ መጋቢት 20 ቀን 2006 ዓ. ከምሽቱ 4 ሰዓት ላይ የተነሳው እሳት አደጋ ለሰላሳ ድስት ሰዓት ማለትም ለአንድ ቀን ተኩል በመንደድ በአካባቢው ያሉ ሰማንያ ቤቶችን ከነ ሙሉ ንብረታቸው ሲያወድም አቶ ጫኔ አካሉ የተባለ አርሶ አደር ሲሞት ሌሎች ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ሰዎች የቆሰሉ መሆናቸውን ከአካባቢው ባገኘነው መረጃ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአደጋው መንስኤ ምን እንደሆነ ለማወቅ በአካባቢው ለሚገኙ አርሶ አደሮች ጥያቄ ያቀረብን ሲሆን ሲመልሱም እኛ የአደጋውን መንስኤ ምን እንደሆነ አላወቅንም ነገር ግን ማንም ሳይደርስልን የአርባ ሁለት አባወራ ከነቤተሰባቸው ሙሉ በሙሉ ንብረታችን ወድሞ አሁን ያለምንም መጠለያ ሜዳ ላይ ወድቀናል እባካችሁ ምግብ እንኳን የሚያቀምሰን ድርጅት ከተገኘ ድምፃችንን አሰሙልን ብለዋል በአካባቢው ያሉ የወረዳና የቀበሌ መስተዳድር አካላትን ለጊዜው ማግነት ያልቻልን ሲሆን ለነዋሪዎቹ ግን በመንግስት በኩል የተደረገ ድጋፍ አለ ወይ ብለን ላቀረብንላቸው ጥያቄ ሲመልሱ የወረዳው አስተዳደር አካላት መጥተው ፎቶ አንስተውን ቪዲዮ ቀርፀውን ሄደዋል እስኪ ፍረዱን እኛ ማደሪያ እጥተን የሚቀመስ ቸግሮን ፎቶና ቪዲዮ ምን ይሰራልናል ብለው ይጠየቃሉ ፡ ፡ አሁን ቤታቸው የወደመባቸው አርሶ አደሮች ንብረታቸው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ እንዲሁ ሜዳ ላይ ወድቀው ይገኛሉ፡ ፡ በቀጣይም አስተዳደርቹን ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ባይሳካም የወረዳው ብአዴን ፅ/ ቤት ኃላፊ የሆኑትን አቶ አማረ በሪሁን በተንቀሳቃሽ ስልካቸው አግኝተን ስለጉዳዩ ማብራሪያ ጠይቀናቸው ነበር ሲመልሱም ‹‹ ልክ ነው አደጋው ተከስቷል ተጎጂዎቹም ችግር ላይ እንዳሉ አውቀናል ነግር ግን እርዳታ ለመስጠት ባጀት ስለሌለን ምንም ያደረግንላቸው ነገር የለም ወደ በላይ አመለክተናል ምላሹን እየተጠባበቅን ነው ብለዋል ፡፡

jano

 

 

የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል

$
0
0
Millions of voices for freedom – UD

የሚሊዮኖች ድምፅ ለመሬት ባለቤትነት” በሚል መሪቃል በደሴ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል፡፡ በስፍራው የሚገኙት የአንድነት ፓርቲ ከፍተና አመራሮችና የዞን አመራሮች በሰልፉ ለተሳተፈው የደሴ ህዝብ ምስጋና አቅርበዋል፡፡ #Dese #UDJ “እድሜ ለአንድነት አስተነፈሰን” የደሴ ነዋሪ.  ይህ ሁሉ አልፎ ዛሬ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በአስተዳደሩ ላይ በተለይም በመሬት ይዞታ ባለቤትነት ጉዳይ እና አላግባብ ስለታሰሩት ኢትዮጵያውያን ድምጹን ከፍ አድርጎ እያሰማ ይገኛል:: ሰላማዊ ሰልፉ እንደተጀመረ ፖሊስ መንገዱን በመዝጋት ሰልፈኛውን ለማወክ ጥረት አድርጎ ነበር:: ህዝቡ ግን ፖሊስን እየጣሰ ሰልፉን በሰላማዊ መንገድ እያደረገ ነው::

የደሴው ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ እየተካሔደ ቢሆንም የአዲስ አበባው ዋና ጽ/ቤት ከፍተኛ በሆነ የፖሊስ ሀይል ተከቧል፡፡

ተቃውሞ ሰልፍ ላይ ከሚስተጋቡ መፈክሮች ውስጥ
- መሬት ለህዝብ ይመለስ
- ጭቆና በቃን
- ድል የህዝብ ነው
- በግፍ የታሰሩ ይፈቱ

- አንድነት ኃይል ነው
- የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ

1025

19034

1024

 

11 100

10250312_615933295158275_1305539042701871448_n

የጠበቆች ማህበር በአርቲስት ግሩም ኤርሚያስ ላይ የወንጀል ክስ መመስረታቸው ተሰማ

$
0
0

girum ermias

በአዲስ አበባ ታትሞ የሚወጣው ማራኪ መጽሔት እንደዘገበው በቅርቡ በሰይፉ ፋንታሁን የኢቢኤስ ሾው ላይ ቀርቦ በአዲስ ፊልሙ ላይ አደንዛዥ ዕፅ ተጠቅሞ መስራቱን ለማህበረሰቡ ያሳየው አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ የጠበቆች ህብረት በጋራ የወንጀል ክስ አቅርበውበታል።

ጠበቃ ማቲያስ ግርማ ለማራኪ መፅሄት እንዳስረዱት በክሱ ላይ ሰይፉ ፋንታሁንና አለማየሁ ታደሰ ደጋፊ ሀሳብ በመስጠታቸው ክስ ይመሰረትባቸዋል ብለዋል። አርቲስቱ ምንም እንኳ ለፊልም ግብዓት “መስለው ሳይሆን ሆነው” ለመስራት ያደረጉት ተግባር ቢሆንም ህብረተሰቡን ከወንጀል ለመጠበቅ ሲባል ክስ እንደተመሰረተባቸው የጠበቆች ተወካዩ አስረድተዋል።

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ

አርቲስት ግሩም ኤርሚያስ በፊልሙ ላይ

“ይህንን የበለጠ ማጣራት የነበረባቸው ፖሊስና አቃቤ ህግ ቢሆኑም ፣ በግልፅ በሀገሪቱ የአየር ክልል የተላለፈውን መረጃ ዝም ማለታቸው እንዳሳዘናቸውም ገልፀዋል። በሀገሪቱ የወንጀል ህግ ስርዓት በተለይ ግሩም በክሱ ጥፋተኛ ከተባለ እስከ ሰባት አመት እንዲሁም የ50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል።

በኢትዮጵያ የወንጀል ህግ 1996/97 አንቀፅ 525 ንዑስ አንቀፅ/ሀ መሰረት እስከ ” አደንዛዥ ዕፅን እራሱ ወይም ሌላ ሰው ሊጠቀምበት በማሰብ የገዛ፣የተጠቀመ፣ እንዲጠቀም ያደረገ፣,,,” ከ7 ዓመት እስከ 50ሺ ብር ቅጣት ይጠብቀዋል። እነ ሰይፉ ደግሞ “ወንጀልን ባለማወቅ” ክስ ተመስርቶባቸዋል።

መጽሔቱ ዘገባውን ሲያጠናቅቅ ለግሩም በቅርብ መጥሪያ ይደርሰዋል ተብሎ ይጠበቃል ብሏል።

Hiber Radio: የኖርዌይ አምባሳደር ማዕከላዊ በመሄድ ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱትን የቀድሞ የጋምቤላ ፕ/ት ለማየት ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ

$
0
0

[jwplayer mediaid="28869"]

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 28 ቀን 2006 ፕሮግራም
<…አቶ ኦኬሎ አኳይ ከጁባ ታፍኖ ማዕከላዊ ነው።…አኪልዳማ አይነት ድራማ ሊሰራበት ይችላል።የወያኔ እሱን መያዝ በጋምቤላ ተፈጽሞ ለዓለም አቀፉ ፍ/ቤት ማስረጃው የቀረበውን የዘር ጭፍጨፋ ወደሁዋላ አያስቀርም። ማስረጃው ወጥቷል … >

አቶ ኦባንግ ሜቶ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተጠይቀው ለህብር ከሰጡት (ሙሉውን ያዳምጡ)

<… አሁን ያሉት ሰዎች የደገሱልን የእርስ በእርስ እልቂት ነበር። የኢትዮጵያ ህዝብ ጨዋ ሕዝብ በመሆኑ ያንን የደገሱለትን እልቂት አክሽፎታል።…አሁንም እነዚህ ሰዎች ያዋረዱትን የአገራችንን ባንዲራ በጋራ ሙስሊምም ሆነ ሙስሊም ያልሆነው በጋራ ለመብቱ መቆም ባንዲራዋን ነጻ ማውጣት አለበት …> ሐጂ ነጂብ መሐመድ የፈርስ ሒጅራ ፕሬዝዳንት በቬጋስ በኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ላይ ካደረጉት ንግግር መሐከል ቀሪውን ያዳምጡት

የሩዋንዳ ጭፍጨፋ ሃያኛ ዓመትን የተመለከተ ወቅታዊ ዘገባ

የህወሃት መሪዎች ሱዳንን ከህልውናቸው ጋር በማያያዛቸው ስለ ሱዳን ህልውና ለአሜሪካ ዲፒሎማቶች የተናገሩበትን የዊክሊክስ ያጋለጣቸውን የምስጢ ር መልዕክቶች (ልዩ ዘገባ )

 

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

የኖርዌይ አምባሳደር ማዕከላዊ በመሄድ ከደቡብ ሱዳን ታፍነው የተወሰዱትን የቀድሞ የጋምቤላ ፕ/ት ለማየት ጥያቄ ማቅረባቸው ተገለጸ

አሜሪካ ለግብጽ የምትሰጠው ዕርዳታ በተዘዋዋሪ ኢትዮጵያን ለማፈራረስ እየዋለነው ሲሉ ብቸኛው የተቃዋሚ የፓርላማ አባል ወቀሳ አቀረቡ

ታንዛኒያ 43 ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን አሳልፋ ሰጠች

የአረና አመራሮችና አባላት ዛሬም ትግራይ ውስጥ ተደበደቡ

የታሰሩም አሉ

አንድነት በጠራው የዛሬው የደሴ የተቃውሞ ሰልፍ ከ60 ሺህ በላይ ሕዝብ አደባባይ ወጥቶ ቁጣውን ገለጸ

ጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ለሁለተኛ ጊዜ ታሰረ

የጀርመን ድምጽ ራዲዮ ለማስፈታት እንዳልተሳካለት ገልጾ ለሱ ደህንነት ሲባል ሁኔታው እንዳይጋጋል ጠየቀ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ በፓሪስ የማራቶንን ሪኮርድ ሰበረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

 

ያልዘሩትን ማጨድ ከቶ አይቻልም! (ግንቦት7)

$
0
0

April 5, 2014

G7የወያኔ መንግስት የኢትዮጵያን ብሄር ብሄረሰቦች አጋጭቶ በመካከላቸው ጥርጣሬና መፈራራት አንግሶና የታሪክ ጠባሳዎችን እንደ አዲስ በመጓጐጥ እያደማ ከፋፍሎ ለመግዛት ካለመታከት ያደረጋቸው ሙከራዎች ገና ፍሬ ባያፈሩም ቁጥቋጦዎቹ መብቀል ጀምረዋል። እዚህም እዚያም በካድሬዎች የውስጥ ለውስጥ ተልእኮ የሚለኮሱ እሳቶች መብለጭለጭ ጀምረዋል። ሌላው ቀርቶ በአንድ ብሄረሰብ መሃል ሳይቀር በከባቢ ልዩነቶች ብቻ መናቆሮችና መጋደሎች እያስተዋልን ነው። ሰሞኑን በጉጂና በቦረና ኦሮሞዎች መካከል የወያኔ ሎሌዎች በሚያበረታቱት አተካሮ የብዙ ወገኖቻችን ህይወት ጠፍቷል። ሰዎች ከኑሮአቸው ተፈናቅለዋል። ወያኔ እንደኳስ ጨዋታ ተመልካች ዳር ሆኖ ይመለከታል፣ ያጨብጭባል።

ሰሞኑን ባህርዳር ከተማ ውስጥ በተካሄደ የስፖርት ውድድር ላይ አሳፋሪ ክስተት ነበር። ለሰሚው የሚቀፍ ብልግና የተቀላቀለበት ስድብና ቁርቋሶ አይተናል። ከበስተጀርባ ሆነው ይህንን ለፍቅር ብቻ ሊውል የሚገባ የስፖርት ዝግጅት መርዝ ረጭተውበታል። ከዚህ ላቅ ያሉ የተንኮል ድግሶችም ተደግሰው ህዝብ ውስጥ በወያኔ ከተነዙ የመርዝ ቢልቃቶች ውስጥ ስራ ላይ ሳይውሉ ቀርተዋል።

ይህ በታሪካችን ታይቶ የማይታወቅ ዘር የሚዘራው ወያኔ ያልተከፋፈለ ህዝብ አይገዛልኝም በሚል ፍልስፍና እንደሆነ በተደጋጋሚ እያየን ነው። ሶማሌ ክልል ውስጥ በተቋቋሙ ልዩ ፖሊስ በሚል ስያሜ በሚጠሩ የመንግስት ሃይሎች ጥቃት ቁጥሩ እጅግ በርካታ የሆነ የኦሮሞ ማህበረሰብ ከኖረበት መሬት ተጠራርጎ እንዲወጣ ተደርጓል። ብዙዎቹ ተገድለዋል። ብዙ ደም መቃበት ተፈጥሯል። በየክልሉ ምስኪን የአማራ ገበሬዎችን መሬት ንብረት በመንጠቅ አከባቢውን ለቀው እንዲሄዱ አድርገዋል። መሄጃ የለንም ያሉትንም ቀጥቅጠው እንደገደሏቸው ሰሞኑን ከጅባትና ሜጫ አካባቢ ያሉ መረጃዎችን አይተናል።

እነዚህ በየቦታው የሚብለጨለጩ እሳቶች በዚህ ከቀጠሉ ሁላችንም ወደ ሚያቃጥልና የሚለበልብ የሰደድ እሳት ማደጉ አይቀርም። የወያኔ ባለሟሎች ካለምንም ይሉኝታና ማሰላሰል ይህንን እሳት እያራገቡ ይገኛሉ።

ይህንን አደገኛ አዝማሚያ በንጭጩ ማስወገድ የሚችለው ራሱ ህዝቡና የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ የነጻነት ሃይሎች ድምጽና ህብረት እንጂ የወያኔ መንግስት አይደለም። ስለዚህ ህዝቡ በተለይም ወጣቶች ከዚህ ወጥመድ ሰብረው እንዲወጡ ግንቦት 7 የነጻነት፣ የፍትህና የዲሞክራሲ ንቅናቄ አጥብቆ ያሳስባል። ተመሳሳይ ተንኮሎችንም ማጋለጡን ይቀጥላል። የብሄርሰብ ልሂቃንም ይህንን መርዝ እንዲቋቋሙ፣ ይልቁንም ወያኔ እንዳይመቸው ይበልጥ መቀራረብና ፈተናውን በጋራ እንድንቋቋም ጥሪያችን በድጋሜ እናቀርባለን።

ያልተዘራ አይታጨድም። ወያኔ የዘራልን መርዝ የሚያፈራው መርዝን እንጂ ሌላ አይደለም። ልዩነቶቻችን እንደዘመኑ በሰለጠነ ዲሞክራሲያዊ መንገድ እንጂ በተያዘው መንገድ ማስወገድ አይቻልም።

ዞሮ ዞሮ በዚህ ሳይጣናዊ የወያኔ መሰሪ ሴራ ለምትፈስ ለእያንዳንዶ የደም ጠብታ ተጠያቂው የወያኔ ጉጅሌ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። በመሆኑም ለመከፋፈል ከመመቻቸት ይልቅ አንድነታችን በማጥበቅ የነጻነት ሃይሎችን በመቀላቀል ራሳችን እና የሀገራችንን ህልውና ከዚህ ከወያኔ የመከፋፈል መርዝ እንታደግ።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!!

ግልጽደብዳቤ፤- ይድረስ ለአባ ኃይለ ሚካኤል የደብረ ሰላም መድኃኔዓለም በሚኔሶታ አስተዳዳሪ፣

$
0
0

ጉዳዩ፡ከዚህ፡ቀደም፡የሰማሁት፡በአስተዳደርዎ፡ጉድለት፡ምእመኑን፡በመከፋፈል፡በማውገዝም፡ያካሄዱ ት፡የነበረውን፡ውዝግብ፡በተንቀሳቃሽ፡ምሥል፡በማዬቴ፡የተሰማኝን፡ኀዘን፡ለማስታዎቅም፡ጭምር፡ነው።የተቀ ባው፡ጌታችን፡መድኃኒታችን፡” ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

 

debereselam-medhanialem


ማኅበረ ቅዱሳን በፓርቲ ፖለቲካ የማይጠረጠርባቸው ምክንያቶች (የግል ምልከታ)

$
0
0

(ኤፍሬም እሸቴ)

     ይህ ጽሑፍ የእኔን የግል ምልከታና አስተያየት ብቻ የሚመለከት እንጂ በዚህ ጽሑፍ ውስጥ ስሙ የተጠቀሰውን ማኅበርም ሆነ ከእርሱ ጋር የአገልግሎት ግንኙነት ያላቸውን ተቋማት የማይመለከት መሆኑን አበክሬ በመግለጽ ልጀምር።

አንድ ብሒል አለ። ውሸትን ደጋግመው ቢናገሩት እንደ እውነት የሚቀበለው ሰው መፍጠር ይቻላል። ስለዚህም ሐሰተኞች ሐሰታቸውን ሳያሰልሱ በተናገሩት መጠን፦ አንደኛ ራሳቸውንም በሐሰታቸው እውነትነት ያሳምናሉ፤ ብሎም ሌሎችን ማሳመን ይችላሉ። ደጋግሞ የመናገር ጥቅሙ ይኼው ነው።

mahbere qdusanአንዳንድ እውነት የያዙ ሰዎች ደግሞ “እውነት እስከያዝን ድረስ ደጋግሞ መናገር ለምን ይገባል?” ብለው ያቀርባሉ። እውነት አላቸው። ፀሐይ ሲወጣ ጨለማ መሸሹ፣ ሻማ ሲለኮስ ብርሃን መፈንጠቁ ላይቀር “ጨለማን ማውገዝ ምን ጥቅም አለው?” ይላሉ። ይህም እውነት ነው። “ጨለማን ደጋግሞ ከማውገዝ አንድ ሻማ ማብራት” እንደተባለው። ነገር ግን ሐሰት ተደጋግማ በመነገሯ ተከታይ መፍጠር እስከቻለች ድረስ እውነትን ደጋግሞ በመናገር የሚመጣ ምን ችግር አለ? ሻማውንም እየለኮሱ እውነቱንም ደጋግሞ መናገሩስ? ስለዚህ በእውነት ተደጋግሞ መነገር፣ በሻማ መለኮስም አምናለኹ። ደጊመ ቃል እንዲሉ የኢትዮጵያ ሊቃውንት።

እንኳን አገር ቤት ያለው አንባቢ ይቅርና እኛ ከአገራችን በብዙ ሺህ ማይሎች ርቀን የምንገኘው ሳንቀር በየዕለቱ የምንኮመኩመው አዲሱ ትኩስ ዜና የማኅበረ ቅዱሳን እና “የተጠመደለት ወጥመድ” ጉዳይ ነው። በማኅበራዊ ድረ ገጾች እና በጡመራ መድረኮች፣ እንዲህ በሕትመት ውጤቶች በሰፊው ሽፋን ያገኘ ጉዳይ ሆኗል። ብዙ ኢትዮጵያውያን (እምነት ሳይለይ) ይህንን ጣልቃ ገብነት በጽኑዕ እየተቃወሙት እያወገዙት ነው። “ማኅበረ ቅዱሳን አክራሪ የሚባል ከሆነ እኔም አክራሪነትን እወደዋለኹ” የሚሉ ሐሳቦች በብዛት ተጽፈው ተመልክቻለኹ።

“የአክራሪነቱ ነገር”፣ ነፍሳቸውን ይማረውና አቶ መለስ በፓርላማ ተናግረውት በነበረ ጊዜ፣ እኔን ጨምሮ ብዙ ፀሐፍት አስተያየታቸውን የሰጡበት ከመሆኑ አንጻር ወደዚያ መመለስ አይገባ ይሆናል። ማኅበሩ ከፓርቲ ፖለቲካ ጋር ግንኙነት እንዳለው በመንግሥት ሰዎች እና በደጋፊዎቻቸው የሚነሣውን ሐሳብ በተመለከተ ግን የግል አስተያየቴን ላሰፍር እወዳለኹ።

ማኅበሩ ፖለቲካ ውስጥ አለበት? ለመሆኑ ፖለቲካ ውስጥ መግባት/ አለመግባት ምንድነው? ማንኛውም ሰው የተባለ ፍጡር ፖለቲካዊ አመለካከት አለው። ፖለቲካ አልወድም የሚሉ ሰዎች ራሳቸው እንኳን ፖለቲካዊ አቋም አላቸው። ልዩነቱ እያወቁ ማወቅ እና ሳያውቁ መኖር ናቸው። የተለያዩ ሐሳቦች እስካሉ ድረስ፣ አስተዳደሮች፣ ገዢዎችና ተገዢዎች እስካለን ድረስ ፖለቲካዊ አመለካከቶች መኖራቸው ግድ ይመስለኛል። “ፖለቲካ እና ኮረንቲ በሩቅ” የሚለው ሰው ራሱ በኮረንቲ ከመጠቀም፣ ሕይወቱ በፖለቲካ ተጽዕኖ ሥር መውደቁ እስካለ ድረስ ፖለቲካ የማይነካው ኢትዮጵያዊ አይኖርም።

ይኼ በፖለቲካ ምሁራን ሳይሆን እኔን በመሳሰሉ ለፖለቲካው ዕውቀት ተርታ በሆንን ሰዎች ቋንቋ “ፖለቲካ ውስጥ መግባት ወይም አለመግባት” የምንለው የፓርቲ ፖለቲካ ውስጥ መግባት ማለታችን እንደሆነ ይሰማኛል። ፖለቲከኞች የምንላቸው እንደዚያ ያሉ ሰዎችን ነውና። ማኅበረ ቅዱሳን “ፖለቲካ ውስጥ ገባ/ አልገባም” የሚለውንም የምፈታው በዚሁ አንድምታውና አገባቡ ብቻ ነው።

ማኅበሩ በብዙ ሺህዎች የሚቆጠሩ አባላት አሉት። አባላቱ ሰዎች እንደመሆናቸው ፖለቲካዊ አመለካከት አላቸው። ማኅበሩን በአባልነት ለመቀላቀል የሚያበቃቸው ግን ይህ ፖለቲካዊ አመለካከታቸው አይደለም። የአባላቱ የዓላማ አንድነትና መሠረቱ ማኅበሩ የሚያራምደው ቤተ ክርስቲያናዊ አቋም ብቻ ነው። በሃይማኖትና በአገልግሎት ዓላማ አንድ ናቸው እንጂ በፖለቲካ ርዕዮት የተሰባሰቡ አይደሉም። ሲጀመርስ ስለ ፖለቲካ አመለካከታቸው የት ተጠያይቀው? የት ተገማግመው? የት ተለካክተው? በየትኛው ጊዜ?

ስለዚህም ማኅበሩ አንድ ሃይማኖታዊ አቋም ያራምዳል እንጂ “አንድ ፖለቲካዊ አቋም” የሚባል የለውም። ሊኖረውም አይችልም። ለምን? ምክንያቱም “ፖለቲካዊ አቋምን ለማራመድ” መጀመሪያ ፖለቲካዊ አቋም መያዝ ያስፈልገዋል። ያንን ለማድረግ ደግሞ አባላቱን በሙሉ በዚህ ፖለቲካዊ አቋም ማሳመን ያስፈልጋል፤ ያንን ማድረግ ደግሞ አስቸጋሪ ብቻ ሳይሆን ማኅበሩ የያዘውን ሃይማኖታዊ አቋም የሚጻረርና ማንም ሳይነካው እንዲፈርስ የሚያደርገው ድማሚት ነው።

እዚህ ላይ መነሣት ያለበት ቁምነገር፤ የማኅበሩ አባላት በሃይማኖታዊም ሆነ በፖለቲካዊ አስተሳሰባቸው ራሳቸውን የቻሉ (ማለትም ማመዛዘን የሚችሉ) ክርስቲያኖች እንጂ የአንድ ቡድን ጀሌዎች አለመሆናቸውን ነው። ራሱን የቻለ አስተሳሰብ ያለው ማንኛውም ሰው፣ አባል የሚሆንበትን ድርጅት ያያል፤ ይመዝናል፣ ያስባል። እንደማይጠቅመውና እንደማይስማማበት ከተረዳ ይተወዋል። ጀሌ ግን የተነገረውን ተቀብሎ እንደ በቀቀን ያስተጋባል፤ ሳያውቅ አባል ይሆናል፤ በጥቂት ጥቅም ይደለላል፣ የሚኖርለትም-የሚሞትለትም ቋሚ መርሕ አይኖረውም።

ማኅበረ ቅዱሳንን እና አባላቱን በአገራችን ላለፉት 40 ዓመታት በጠነነው የፖለቲካ ድርጅት ጀሌነት መገምገም ትክክል የማይሆነው ለዚህ ነው። አባላቱ አገልጋዮች እንጂ ካድሬዎች አይደሉም። አመራር ላይ የሚቀመጡት ሰዎች በተራቸው ለማገልገል እንጂ ከሌላው አባል የተለየ መርሕ ለማራመድ አይችሉም። እናራምድ ቢሉም አባላቱ ጀሌዎች ስላልሆኑ ሊከተሏቸው የሚችሉበት ምንም መንገድ አይኖርም። የአባላቱ አንድነት በሃይማኖት እና በሃይማኖት ብቻ ነው። በበሰለ ሚዛን የሚለካቸው ቢኖር ኖሮ በዘር፣ በቋንቋ፣ በፖለቲካ አቋም፣ በትምህርት ደረጃ፣ በዕውቀት፣ በዕድሜ ወዘተ ወዘተ የተለያዩ እንጂ እንደ ሜዳ አህያ አንድ ወጥ እና ልሙጥ አለመሆናቸውን ይገነዘባል።

ስለዚህ አንድ አባል በግልጽ አንድ የፖለቲካ ድርጅት ውስጥ ገብቶ የዜግነት ድርሻውን መወጣት ቢፈልግ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቃል። በማኅበሩ ውስጥ ያለውን የአመራር ኃላፊነት ማስረከብ ይኖርበታል። በዚህ ደረጃ በይፋ ከአመራርነታቸው በሰላም ተሰናብተው ወደፈቀዱት ይፋዊ የፖለቲካ መስመር መጓዝ የቻሉ ሊኖሩ እንደሚችሉ እገምታለሁ። ማኅበሩንም የፖለቲካ ድርጅታቸውንም መምራት የሚችሉበት መንገድ አይኖርም። እነርሱ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለማቸውን በማኅበሩ ላይ ለመጫን ቢፈልጉም እንኳን “የፍላጎት መላተም” (“conflict of interests”) ስለሚኖር ሊሳካላቸው አይችልም። የማኅበሩ አባላት በፖለቲካ መሳተፍ የዜግነት መብታቸው ሲሆን በማኅበሩ አገልግሎት መሳተፍ ደግሞ ሃይማኖታዊ የትሩፋት ሥራ እንደመሆኑ ማቻቻል የአባሉ ፈንታ ነው።

ማኅበሩ በፖለቲካ ውስጥ ገብቷል የሚለው (በተለይ በቤተ ክህነቱ ዙሪያ ያሉ ሰዎች) ከ1980ዎቹ ጀምሮ ሲያዜሙት የነበረ የሰለቸ ዜማ ነው። የሚነቅፉት ግን ማኅበሩ “ኢሕአዴግን አይደግፍም” ብለው ስላሰቡ እንጂ “ተቃዋሚ ነው ብለው ስላመኑ” ብቻ አይደለም። ለነገሩ እነዚህ መንግሥትን በዱላነት ለመጠቀም የሚፈልጉ፣ በመንፈሳዊም በዓለማዊም ሚዛን ቢመዘኑ ውኃ የማያነሱ ደመናዎች “ፖለቲካ” የሚሉት አጎብዳጅነትን ነው። መንግሥት እነሱን ይጠቀማል። እነሱም በአቅማቸው በመንግሥት ይጠቀማሉ።

ታዲያ ማኅበሩ የትኛውንም የፖለቲካ ድርጅት እንደማይደግፍ ነገሩን ሥራዬ ብሎ ለሚከታተል ለማንኛውም ሰው ግልጽ ሆኖ ሳለ በዚህ ጉዳይ መወንጀሉ ለምን አስፈለገ? ክርስቶስ አምላካችን ራሱ “ግብር አትክፈሉ ይላል? ለቄሳር አትገዙ ብሏል፤ ንጉሣችን ሳይሆን ንጉሥ ነኝ ብሏል” የሚል ፖለቲካዊ ክስ እንደቀረበበት ሃይማኖትን ብለው የሃይማኖት አገልግሎት ላይ የተሠማሩ ሰዎች በየዘመኑ የሚከሰሱበት ጉዳይ መሆኑን ማስተዋል ያስፈልገናል።

ቅዱስ ሉቃስ “ይህ ሕዝባችንን ሲያጣምም ለቄሣርም ግብር እንዳይሰጥ ሲከለክል ደግሞም፦ እኔ ክርስቶስ ንጉሥ ነኝ ሲል አገኘነው ብለው ይከሱት ጀመር” ሲል እንደጻፈው (ሉቃስ 23፥2)። በሌላው ዓለም ያለውን እንኳን ትተን በአገራችን ያለውን ብናስታውስ፣ ነገር ሰሪዎች በየዘመኑ የነበሩ ቅዱሳን አባቶቻችንን ከነገሥታቱ ጋር በማጋጨት በአደባባይ እስከመገረፍ ያደረሱበት ጊዜ፣ በግዞት በእስር እንዲማቅቁ ያደረጉበት ወቅት እንዳለ ታሪክ ያስተምረናል። ሊቁ አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫን እና የደብረ ሊባኖስ እጬጌ ጻድቁ አባ ፊሊጶስን ለአብነት ብናንሣ አባ ጊዮርጊስ እንደተጋዘ፣ አባ ፊሊጶስ በአደባባይ ራቁቱን እንደተገረፈ እናነባለን።

ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ አገልግሎት ላይ ያለ ማኅበር ትናንት እንደፈላ እንደ ክረምት አግቢ ሊታይ አይችልም። መንግሥት ይኼ ሁሉ ሐቲት አይጠፋውም። ማኅበሩ ተቃዋሚም ደጋፊም እንዳይደለ መግለጹ እስካሁን ጉንጭ አልፋ ከመሆን አልዘለለም። መደገፍ የማይችል አካል፣ ባይቃወምም እንኳን ገለልተኛ መሆኑ ለአደጋ ያጋልጠናል በሚል “ባልበላውም ጭሬ ላፍሰው” የዶሮ ፍልስፍና የተቃኘ ነው።

ከዚህም ባሻገር አባላቱ ከአንድ ዘርና ቋንቋ፣ ባህልና ፖለቲካዊ አቋም የመጡ አለመሆናቸው፤ ይልቁንም ሕብረ ብሔረሰባዊና ኢትዮጵያዊ መሆናቸው እንቅልፍ የሚነሣቸው አካላት መኖራቸው ግልጽ ነው። “አዳሜ በየቅርጫትህ ግባ” ሲባል አንድ ቅርጫት ውስጥ የማይጨመሩ፣ ከሌላውም ቅርጫት ካለው ጋር ዝምድናና ፍቅር ያላቸው፤ ከቅርጫታቸው ውጪ የሚያስቡ ሰዎች ያሉበት ማኅበር መሆኑ የሚያስፈራቸው አሉ።

በውጪ አገር ባሉ የተለያዩ የመንግሥት ተቃዋሚ ቡድኖች ዘንድ ማኅበረ ቅዱሳን ሲጠረጠር እንደኖረ እነርሱም በፈንታቸው “ማኅበረ ቅዱሳን የኢሕአዴግ ደጋፊ መሆን አለበት” ሲሉ ኖረዋል። ለምን እንዲህ አላችሁ ሲባሉ ምክንያቱም “ይህንን የሚያህል ትልቅ ተቋም እንዴት ነጻና ፍፁም ሃይማኖታዊ ብቻ ሊሆን ይችላል? ጠርጥር ጠርጥር” የሚል ጥርጣሬ ያቀርባሉ።

ማኅበሩ አብሯቸው ጀብ ጀብ ላለማለቱ ምክንያቱ ዓላማውና ተፈጥሮው መሆኑን ለመቀበል የአገር ውስጡም የዳያስጶራውም ቡድን፣ እነዚያም እነዚያም ይኸው እንደተቸገሩ አሉ። እነዚያ “የዚያ ደጋፊ ነው” እንዳሉት፣ እነዚያም “የዚያ ደጋፊ ነው” እንዳሉት። ማኅበሩ ደግሞ “አነ ዘክርስቶስ፣ አነ ዘቤተ ክርስቲያን፤ እኔ የክርስቶስ ነኝ፣ እኔ የቤተ ክርስቲያን ነኝ” እንዳለ አለ። መጨረሻውን ደግሞ ዕድሜ ይስጠን እንጂ፣ እናየዋለን።

ይቆየን – ያቆየን

 ይህ ጽሑፍ አዲስ አበባ ለሚታተመው የአዲስ ጉዳይ መጽሔት የተጻፈና በዚያም ላይ ለሕትመት የበቃ ነው።

 

 

 

በዋሽንግተን ዲሲ የሽግግር ምክርቤቱ አመራርm ስብሰባ

$
0
0

ውድ ኢትዮጵያውያን፤

አገራችን ምን አይነት ምስቅልቅል ውስጥ እንደሆነች ለማንም ማስረዳት አስፈላጊ አይደለም። ከዚህም አልፎ ተዘጋጅተንና አቅደን ካልጠበቅነው መጭው ስርአት ተመሳሳይ ወይም ከዚህኛው የከፋ ይሆናል ብለን ሁላችንም እንሰጋለን። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሽግግር ምክር ቤት ይህንን የዝግጅት አስፈላጊነትን ጽንሰ ሀሳብ ለህዝብ በአንክሮ ካስገነዘበ ወዲህ ዛሬ ይህ አጀንዳ በተቃዋሚ ድርጅቶች፤ በተለያዩ ተቋማት እንዲሁም በመላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ዘንድ የመወያያ ርእስ ሆኗል።

በመጭው እሁድ ሚያዝያ 5 (April 13, 2014) ባዘጋጀነው ስብሰባ የተለያዩ የማህብረሰባችን ተወካዮች በዚሁ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ንግግር ያደርጋሉ ከህዝብም ጋር ይወያያሉ። ይህ ስብሰባ የተሳካ ለማድረግ በዋሽንግተን ዲሲ አካባቢ የሚገኙ ጓደኞችዎንና ዘመድ ወዳጆችዎን በመጋበዝና እራስዎም በመገኘት የድርሻዎን ያበርክቱ ዘንድ በትህትና እንጠይቃለን። ስለስብሰባው በይበልጥ ለማወቅ፤ ከዚህ ኢሜይል ጋር ተያያዥ ሆኖ የተላከውን በራሪ ወረቀት ይመልከቱ።

የሽግግር ምክርቤቱ አመራር

ENTC-flyer (1)

የሪያዱ ሚስጥራዊ ቦንድ ሽያጭ ከሸፈ!

$
0
0

ሐሙስ ጅዳ ላይ ያልቀናው ቦንድ ሽያጭ ትናንት ሪያድ ከተማም ከሽፏል።
የሁለቱም ከተሞች እቅድ መክሸፍ ምክንያት የሕወሐት ሰዎች ጉልበት የመጠቀም ስሕተት መሆኑ ያመሳስለዋል።ጅዳ ኮሚዩኒቲ አዳራሽ አቶ ከድር የሚባል የሕወሐት ሰው አንዲትን ስብሰባ የምትሳተፍ እህት በጥፊ መትቶ ሞባይሏን ለመንጠቅ ባደረገው ትንቅንቅ ስብሰባው ወደሁከት ተቀይሮ መበተኑ ይታወሳል።ሪያድ ስለሆነው ደግሞ እንከታተል ።
የትናንቱ የሪያድ ስብሰባ ለኤምባሲው ሩቅ ያልሆኑ ከየብሄሩ ሐያ ሰዎች በድምሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሰዎች ብቻ በሚስጥር የተጠሩበት ነበር።መረጃው ለህዝብ ይፋ ከተደረገ በኋላ በርካታ ሰው ወደኮሚዩኒቲው አዳራሽ በማምራት ለመግባት ይጠይቃል።ከመግቢያ በር “የጥሪ ካርድ አምጡ” ይባላል ።”የለንም” ይላል ህዝብ።”ከየትኛው ብሔር ናችሁ?”ብለው በረኞች ሲጠይቁ “ኢትዮጵያውያን ነን።ጉዳዩ እንደዜጋ ይመለከተናል።”ይላሉ።
በዚህ ምልልስ መሐል አንድ ሰው ሞባይል ሲቀርፅ የሕወሐት አባል የሆነ ግለሰብ ይመታውና ሞባይሉን ሊነጥቀው ይሞክራል ።በር ላይ የተሰበሰበው ኢትዮጵያዊ የዚህ ሕወሐት እብሪት አበሳጭቶት ግብግብ ሲጀመር ከአዳራሹ ውስጥ የነበሩ ሌሎች ህወሀቶች መቀመጫ ወንበር በማንሳት የአዳራሹ መስተዋት በመሰባበር ህዝቡን ለመደብደብ ወደውጭ ይወጣሉ።
የኮሚዩኒቲው ፀጥታ አስከባሪ የሳዑዲ ፖሊሶች በመሐል ገብተው ነገሮች በቁጥጥር ስር ዋለ።የችግሩን መከሰት የሰሙት አምባሳደር መሐመድ ሐሰን መጀመርያ ላይ ፀብ ያጫረውን ሰው አምጡልኝ።የኤምባሲው ሰራተኛ ቢሆን እንኳ በህግ ይከሰሳል።”አሉ።ሰውየውን ህወሀቶች አስቀድመው ቢያሸሹትም በሕዝብ ጥቆማ ያሸሸው ሰው ይያዛል።አምባሳደሩ ሰውየው ህወሐት መሆኑን ሲያውቁ አፈገፈጉ።”በቃ ጉዳዩን ጸውስጥ እንጨርሰዋለን።አሁን ወደጉዳያችን እንግባ።”ብለው በግርግሩ ያለጥሪ ከገቡት ሰዎች ጭምር ስብሰባው ተጀመረ።
ገና እንደተጀመረ አንድ ሰው ብድግ ብሎ “ሀገራችን ውስጥ በሃይማኖታችን ምክንያት ቁምስቅል የምታሳዩን አንሶ በሰው ሐገር እንዴት ትደበድቡናላችሁ?”ብሎ እምባ እየተናነቀው ተናገረ!
ከበር ላይ የህወሓት እብሪተኞች የፈፀሙት የንቀት ድርጊት ከዚህ ሰው ንግግር ታክሎ የመንግሥት ደጋፊ የሚባሉ ሰዎችን ሳይቀር አስከፍቶ እያንዳንዱ ሰው ከወንበሩ ብድግ አዳራሹን ለቆ ወጣ!
ኢትዮጵያ የግል መኝታ ቤታቸው የምትመስላቸውና በሌላው ዜጋ የሐገር ባለቤትነት የማያምኑ ጭፍን የህወሓት ግልፍተኞች የሪያድና ጅዳን የህዳሴ ግድብ የልማት ውይይት(የቦንድ ሽያጭ) በዚህ መልኩ አኮላሽተውታል!!

Ethiopians in Jeddah, Saudi Arabia protest at government Officials

 

http://youtu.be/3JTy3tQvU2s

 

የምእራብ ጎጃም ነዋሪዎች በመብራት እጦት መማረራቸውን ገለጹ

$
0
0

ethsatመጋቢት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በፍኖተ ሰላም እና አጎራባች ወረዳዎች ማለትም በቡሬ ፤ በጃቢ ጠናን ፤ ፈረስ ቤት ፤ ይልማና ዴንሳ፣ ፤ሜጫ ፣ አቸፈር እና ቋሪት የሚኖሩ ነዋሪዎች በፍኖተ ሰላም ከተማ በጃቢ አዳራሽ ከመልካም አስተዳደር ችግሮች ጋር በተያያዘ ከክልሉ መስተዳደር ጋር በተደረገ ውይይት በመብራት እጦት ለከፍተኛ ችግር መጋለጣቸውን በምሬት ተናግረዋል።

የመብራት ሃይል ሹሞች በሙስና ተዘፍቀዋል ያሉ አንድ ተናጋሪ ፤ ስራቸውን ለመስራት ጉቦ እንደሚጠይቁዋቸውና ለሚመለከታቸው የመንግስት ባለስልጣናት አቤት ሲሉም የሚሰማቸው ማጣታቸውን ገልጸዋል።

የፖሊስ ባልደረባ የሆኑት ዋና ሳጅን አለማየሁ አዲስ በበኩላቸው መብራት ሃይል መንግስት የማያውቀው በራሱ የሚመራ ድርጅት መሆኑን አስታውሰው፣ ቅሬታችንን ለመንግስት አካላት ስናቀርብ ፖሊሱ ፣ ነዋሪው እንዲሁም ሚኒስትሩ ሳይቀር አሸባሪ ተብሎ እየተፈረጀ ነው ብለዋል።

ዘመኑ አሰፋ የተባሉ የፉነተሰላም ነዋሪ በበኩላቸው በውስጥ ለውስጥ መብራት ችግር ምክንያት የማታ ተማሪዎች በተለይ ሴት ተማሪዎች ለአደጋ እየተጋለጡ መሆኑን ገልጸዋል

Source: Ethsat

ሰበር ዜና፡- ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ ተሾሙ

$
0
0

ሪፖርተር  ጋዜጣ

ወ/ሮ አስቴር ማሞ

ወ/ሮ አስቴር ማሞ

በቅርብ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ በኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት በተመረጡት አቶ ሙክታር ከድር ምትክ፣ ወ/ሮ አስቴር ማሞ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የመልካም አስተዳደርና ሪፎርም ክላስተር አስተባባሪ ሆነው ተሾሙ፡፡

ማክሰኞ መጋቢት 30 ቀን 2006 ዓ.ም. በፓርላማ ሹመቱ የፀደቀላቸው ወ/ሮ አስቴር በተጨማሪ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር ሆነው ተሹመዋል፡፡

በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝ አቅራቢነት በፓርላማው ሹመታቸው የፀደቀው ወ/ሮ አስቴር የመጀመርያዋ ከፍተኛ ተሿሚ ናቸው፡፡

‹‹ሴት ተሿሚ ለዚህ ከፍተኛ ሹመት በማቅረቤ ከፍተኛ ደስታ ይሰማኛል፤›› ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለፓርላማው አባላት ስሜታቸውን ገልጸዋል፡፡ ወ/ሮ አስቴር ሹመታቸው ከፀደቀ በኋላ ቃለ መሐላ ፈጽመዋል፡፡

በተለያዩ ከፍተኛ የፓርቲና የመንግሥት ኃላፊነቶች ላይ የቆዩት ወ/ሮ አስቴር፣ በፓርላማው የመንግሥት ተጠሪ የነበሩ ሲሆን እስከ ሹመታቸው ድረስ በምክትል ፕሬዝዳነት ማዕረግ የ ኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አማካሪ ነበሩ፡፡

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>