Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

መንበረ ጵጵስናውን እንግሊዝ ሀገር ለንደን ከተማ ያደረገው የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በሎንደን ከተማ ነዋሪ የሆኑትን «ቄስ» ብርሃኑ ብሥራትን ከሥልጣነ ክህነት አገልሎት መሻራቸውን አስታወቀ፤

$
0
0

 

«ቄስ» ብርሃኑ ብሥራትን

«ቄስ» ብርሃኑ ብሥራት

የዛሬ አርባ ዓመት ገደማ በአውሮፓ ለመጀመሪያ ጌዜ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳ ዘኢትዮጵያ መልካም ፈቃድ በአባ አረጋዊ ወልደ ገብርኤል(ቆሞስ) በኋላ ብፁዕ አቡነ ዮሐን አስተዳዳሪነት ለረጅም ጊዜ መንፈሳዊ አገልግሎት ስትሰጥ በቆየችውና ቀጥሎም በእንግሊዝ ሀገር እና በመላው ዓለም በሚገኙ የጽዮን ወዳጆጅ ኦርቶዶክሳውያን ክርስቲያኖች የዘወትር ጸሎት፣  የጉልበትና የገንዘብ አስተጽዖ በአንድ ሚሊዮን ሰባት መቶ ሺህ የእንግሊዝ ገንዘብ በለንደን ከተማ ማዕከላዊ በሆነ ቦታ የራስዋ የሆነ ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገዝታ ለሕዝበ ክርስቲያኑ የተሟላ አገልግሎት በመስጠት ላይ ትገናለች። ይሁን እንጂ የሕንጻው ክፍያ ከተጠናቀቀ በኋላ ጥቂት ግለሰቦች ቤተ ክርስቲያኑን ከቅዱስ ሲኖዶስ ማዕከላዊ አስተዳደር፣ ከቃለ ዓዋዲው መመሪያና ትዕዛዝ አስወጥተው በግለሰብ አደረጃጀት ሕንጻውን በግል ይዞታ ለመቆጣጠር ባወጡት የተሳሳተ ዕቅድና ዓላማ ምክንያት ችግር ተፈጥሮ መንፈሳዊ አገልግሎቱ በግፍ ተቋርጦ ቤተ ክርስቲያኑ ከዘጠኝ ወራት በላይ አላግባብ ተዘግቶ ካህናትና ምዕመናንን በከፍተኛ ደረጃ ሲያዛዝናቸውና ሲያስለቅሳቸው ቆይቷል።

 

በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የተፈጠረው መንፈሳዊና ክርስቲያናዊ መንገድ ያልተከተለ፣ ከመጠን ያለፈና መረን የለቀቀ ረብሻ እጅግ በጣም በሚያሳዝን ሁኔታ በአብዛኛው በማኅበራዊ መገናኛ ብዙኃን ተዘግቦ በዓለም ላይ ያሉትን የቤተ ክርስቲይናችን ተከታዮች ሁሉ ያሳዘነ፣ በስደት የሚገኘውን የማኅበረሰባችን ገጽታ ያበላሸ አሳዛኝ ታሪክ ሆኖ የተዘገበ ተግባር ሲሆን፤ ቄስ ብርሃኑ ብሥራት የዚህ  ሕገ ቤተ ክርስቲያን የጣሰ፣ በቃለ ዓዋዲ የማይመራ የአመጽ ቡድን አስተባባሪና መሪ በመሆን  ለችግሩ ሁሉ ከፍተኛ አስተዋጽዖ ያደረጉና እያደረጉ የሚገኙ አርዓያነት የጎደላቸው ግለሰብ መሆናቸውን ካህናትና ምእመናን ሲያሳውቁ ቆይተዋል።

 

ቀደም ሲል የተፈጠረውን ችግር ለመፍታት በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማቲያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  ትዕዛዝ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል እና ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተልከው ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ጋር በመሆን ለችግሩ መፈትሄ ለመስጠት ከአንድ ወር በላይ ከፍተኛ ሙከራ ያደረጉ ቢሆንም ሊሳካ አልቻለም። ከአንድ ወር በላይ ለፈጀው የሰላም ጥረት አለመሳካት ምክንያቱ በ«ቄስ» ብርሃኑ ብሥራት እንመራለን የሚሉ ግለሰቦች ደንብ በማርቀቅ ስም «ፕሮቴስታንታዊ» ዓላማና አወቃቀር ያለው «መተዳደሪያ ደንብ» አርቅቀው ቤተ ክርስቲያኑን ለረጅም ጊዜ ተመዝግቦበት ከቆየው የቤተ ክርስቲያኗን ሃይማኖታዊ ልዕልና የማይጋፋ፣ ሕጋዊ የንብረትና ፋይናንስ ቁጥጥር ያለው የእንግሊዝ ሀገር የምግባረ ሰናይ (Charitable Trust) ምዝገባ  አስወጥተው፤ ኃላፊነቱ በተወሰነ የግል ኩባንያ (Private Company Limited by Guarantee) አስመዝግበው ሕንጻ ቤተ ክርስቲያኑን ለመቆጣጠርና የሚፈልጉትን ሁሉ ለማድረግ በቡደን ተደራጅተው ያወጡትን ዕቅድ መመሪያ አድርገው የሚንቀሳቀሱ በመሆናቸው እንደሆነ ተገልጿል። በዚህ ምክንያት ብጹዓን ሊቃለ ጳጳሳቱ በትዕግሥት የተቻላቸውን ያህል ቢሞክሩም ግለሰቦቹን ከስህተታቸው አስተምሮና አርሞ ወደ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ለመመለስና የተፈጠረውን ችግር በመንፈሳዊ አስተዳደራዊ ዳኝነት ለመፍታት ካለመቻላቸውም በላይ፤ «ቄስ» ብርሃኑ ብሥራት የዚህ ሁሉ የተሳሳተና ከሕገ ቤተ ክርስቲያን የወጣ መንገድ ጠራጊ በመሆን፤ ሊቃነ ጳጳሳቱ የሰጡትን መንፈሳዊ መመሪያ ተግባራዊ ለማድረግ ፈቃደኛ አለመሆናቸው  ችግሩን ይበልጥ እንዳባባሰው ተገልጧል።

 

ብጹዓን ሊቃነ ጳጳሳቱ የተዘጋውን ቤተ ክርስቲያን ከፍተው በሐዘንና በልቅሶ ላይ ላሉት ምዕመናን መንፈሳዊ አገልግሎት ለመስጠት ሙከራ ቢያደርጉም፤ እነዚሁ ወገኖች የሌሎች እምነት ተከታዮችንና የፓለቲካ ቅራኔ አለን ብለው የተደራጁትን ሁሉ በማስተባበር በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ቅጥ ያጣ የረብሻና የሁከት ሰልፍ በማድረግ ቤተ ክርስቲያኑን እንዳይከፈት እጅግ በጣም አስቸጋሪና አሳዛኝ የሆነ ተግባር ሲፈጽሙ መቆየታቸው ተገልጿል።

 

ለሁለተኛ ጊዜ ሊቀ ጳጳሱ አቡነ እንጦንስ ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም (25/8/2013) ግራ ቀኙን ጎራ ለይተው በተሰበሰቡበት በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ ተገኝተው «የተፈጠረውን ችግር በጠጴዛ ዙሪያ በሕገ ቤተ ክርስቲያን ይፈታ፣ ቤተ ክርስቲያኑ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ ተከፍቶ መንፈሳዊ አገልግሎት ይከናወንበት» በማለት መንፈሳዊ መመሪያ ቢሰጡም ግለሰቦች ቤተ ክርስቲያንኑ እንዳይከፈት አመጻቸውን አጠናክረው  ሲያካሂዱ እንደነበረ በወቅቱ በመገናኛ ብዙኃን የተዘገበውን ማስረጃ በማድረግ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

 

በመቀጠልም ብፁዕ አቡነ ገብርኤልና ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ጋር በመሆን ለሦስተኛ ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ከፍቶ አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ሙከራ ቢያደርጉም አሁንም የቤተ ክርስቲያኑን ሕንጻ በግል ባለቤትነትና ይዞታ ለመቀማት የተነሱት የቄስ ብርሃኑ ተከታዮች በፈጠሩት ኢ-ክርስቲያናዊ አመጽ ምክንያት ቤተ ክርስቲያኑን መክፈት ሳይቻል እንደቀረ ታውቋል።

በወቅቱ ቤተ ክርስቲያኑ እንዳይከፈት ለማደረግ የተደረገውን አመጽ፣ በሊቃነ ጳጳሳቱ ላይ የውረደውን የስድብ ውርጅብኝ፣ ባጠቃላይ ሁከቱንና እረብሻውን በቦታው ላይ ተገኝተው የተመለከቱት የደቡብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ «በቤተ ክርስቲያን ሕይወቴ ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን ለጸሎትና ለቅዳሴ እንዳይከፈት ሲያውክ፣ ሰይጣን ሥጋ ለብሶ ሲንቀሳቀስ ያየሁበት ወቅት ቢኖር ይህ ነው» በማለት በጥልቅ ሀዘን ገልጸውታል።

 

የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ባለባቸው መንፈሳዊ ኃላፊነት ቄስ ብርሃኑ ብሥራትን በአካል አነጋግሮ መመሪያና ምክር ለመስጠት በተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም፤ ቄሱ ግለስቦቹ በቤተ ክርስቲያን ላይ የሚያሳዩትን ፍጹም ሕገ ወጥ አመጽ እንደ ትልቅ ደጀን በመቁጠር ለመንፈሳዊ ጥሪው በጎ ምላሽ እንዳልሰጡ ታውቋል። ካህናትንም በሽምግልና መኖሪያ ቤታቸው ድረስ በመላክ የሚሄዱበት መንገድ ሁሉ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን የጣሰ መሆኑን በመግለጽ የእናት ቤተ ክርስቲያንን ማከላዊ አስተዳደር ጠብቆ ወደማስጠበቁ በጎ ጎዳና እንዲመለሱ ቢጠየቁም ሊመለሱ እንዳልቻሉ ተብራርቷል።

 

ከዚያም አስቀደሞ ሰኔ 7 ቀን 2005ዓ.ም፣ ሐምሌ 24 ቀን 2005 ዓ.ም አንዲሁም ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም በተጻፈ ደብዳቤ ሊቀ ጳጳሱ ምክርና መመሪያ ለመስጠት ቢጠሯቸው ጥሪውን አክብረው ለመገኘት ፈቃደኛ አለመሆናቸው ተገልጧል። በጠቅላላው «ቄስ» ብርሃኑ ብሥራት ክህነቱን በመንፈሳዊ አደራነት ለሰጠቻቸው ቅድስት ቤተ ከርስቲያን ሕግጋትና ቀኖና ከመታዘዝ ይልቅ ግለሶቦቹን ስቶ በማሳት ከዛም አልፎ እነሱን በአዳራሽ በመሰብሰብ እራሳቸውን በራሳቸው በሕገ ወጥ መንገድ የቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ አድርገው በመሾም፤ በሕዝብ የተመረጠውን ሰበካ ጉባዔ የቤተ ክርስቲያን ቁልፍ፣ ሀብትና ንብረት አስረክቡኝ የሚልና የሚያስገድድ ደብዳቤ መጻፋቸው የገለሰቡን ሕግ የመተላለፍ ተግባርና ከቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ቁጥጥር ውጭ የሆኑ መሆኑን እንደሚያስረዳ በስፋት ተብራርቷል።

 

በሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት መመሪያ፣ በደብሩ ሰበካ አስተዳደር ጉባኤ ያላሰለሰ ጥረት፣ “አቅሌስያ” በሚል ስም በተደራጁ ካህናት፣ ምዕመናንና የሰንበት ት/ቤት አባላት ድጋፍ፣ ከሕግ አማካሪ በተገኘ ብስለት የተሞላበት የሕግ ምክር፣ በአካባቢው ፖሊስና ጸጥታ ኃይሎች ቀና ትብብር ታህሳስ 20 ቀን 2006 ዓ.ም የእመቤተችን ቅድስት ድንግል ማርያም መታሰቢያ ውርኀዊ በዓል ዋዜማ ዕለት ቁጥራቸው ብዙ የሆነ ሕዝበ ክርስቲያን በተገኙበት ከዘጠኝ ወራት በላይ ከቄስ ብርሃኑ ብሥራት ጋር የጠበቀ ግንኙነት ያላቸው እነዚሁ ወገኖች ባስነሱት ኢ-ክርስቲያናዊ አመጽ ምክንያት በግፍ የተዘጋው ቤተ ክርስቲያን በብጹዕ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንጦንስ ቡራኬ ተከፍቶ በአራቱም ማዕዘን ወንጌል እየተነበበ ቅዳሴ ቤቱ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን በሚያዘው መሠረት ተከፍቶ መንፈሳዊ አገልግሎቱን በይፋ እየተከናወነበት  መሆኑን የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አስታውቋል።

 

ቀጥሎም  በዘመነ አስተርዕዮ የሚከበሩት ዓበይት በዓላት የጌታችንና መደንኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የልደት፣ የጥምቀትና የእመቤታችን በዓላት ሁሉ በሊቀ ጳጳሱ መሪነት በብዙ ሺህ የሚቆጠር ምዕመናን በተገኙበት በለንደን ደብረ ጽዮን ቅደስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ታይቶ በማይታወቅ ታላቅ ድምቀትና አንድነት ተከብሯል። በተለይም የጥምቀቱ በዓል በለንደን ከተማ የሚገኙ አድባራት ታቦታት፣ ካህናት፣ ምእመናን እና የሰንበት ት/ቤት መዘምራን በአንድነት ሆነው “ጃንሜዳ በለንደን” የተባለለት ታላቅ የአንድነት በዓል የተከበረ መሆኑ ተዘግቧል። ይህ ሁሉ ሲሆን «ቄስ» ብርሃኑ ብሥራት  የቤተ ክርስቲያኑን ሕንጻ በኃይል ቀምተው በግለሰብ ይዞታ በገለልተኝነትና በግል ባለቤትነት ለመቆጣጠር የሚጓዙትን በማሳመጽ በግቢው ውስጥ ድንኳን በመጣል «በእኛ እምነት ቤተ ክርስቲያኑ አልተከፈተም» በማለት ሊቀ ጳጳሱ ከመሚመሩት ጉባዔ ከፍለው ከመሠረታዊው ኦርቶዶክሳዊ የሥርዓተ ሃይመኖት አፈጻጻም ተለይተው መዋላቸው ተረጋግጧል።

 

ቄስ ብርሃኑ ብሥራት በርዕሰ አድባራት ሎንደን ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሊቀ ጳጳሱ ሥርዓተ ቅዳሴ እየመሩ ባለበት፣ መንፈሳዊ ትምህርት፣ ቃለ ምዕዳንና ጽሎተ ቡራኬ በሚሰጡበት ተመሳሳይ ሰዓት፤ ግለስቦችን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ በመከልከል በተመሳሳይ ጊዜ ሁለተኛ ተአምረ ማርያም፣ ሁለተኛ ኪዳን፣ ሁለተኛ ወንጌል፣ ሁለተኛ ሥርዓተ ቅዳሴ እያደረጉ፣ ቤተ መቅደስ ገብቶ ያልተባረከ ማዕጠንት እያጠኑ በቤተ ክርስቲያን የአንድነት መንፈሳዊ አገልግሎት በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ እጅግ በጣም ታይቶ የማይታወቅ መንፈሳዊነት የጎደለው፣ ክህነታዊ አርዓያነትና ኃላፊነት የተለየው ተግባር ሲፈጽሙ መቆየታቸው በስፋት ተብራርቷል።

 

ቄስ ብርሃኑ ብሥራት ከ1986 ዓ/ም ጀምሮ በብጹዕ አቡነ ዮሐንስ አሳሳቢነት፤ በብጹዕ ወዱስ አቡነ ጳውሎስ መልካም ፈቃድ ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በጀት ተፈቅዶ በወቅቱ በአዲስ አበባ ከተማ ይኖሩ ለነበሩት ባለቤታቸውና ቤተ ሰቦቻቸው ጊዜው ይፈቅድ በነበረው መሠረት በወር ብር 500(አምስት መቶ ብር) ይከፈላቸው እንደነበር፣ እስከ ቅርብ ጊዜ ደረስ በርዕሰ አድባራት ለንደን ደብረ ጽዮን አራት እሁድ ብቻ ቀድሰው በየወሩ ከአንድ ሺህ አንድ መቶ ሰማንያ ሁለት የእንግሊዝ ገንዘብ  ቋሚና መደበኛ ክፍያ ይከፈላቸው እንደነበር ታውቋል። ነገር ግን ቄሱ ቤተ ክርስቲያኗ ከቅዱስ ሲኖዶስ ማዕከላዊ አስተዳደርና ከሀገረ ስብከት አመራር ተለይታ ገለልተኛ ሆና እሳቸው ብቻ ተጠቃሚ ለመሆን ባላቸው የተሳሳተ ዓላማ ምክንያት፤ ከአሁን በፊት ከመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ለሐዋርያዊ ተልዕኮ ወደ እንግሊዝ ሀገር ተልከው በሚመጡ አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ላይ አድማና አመጽ በማስነሳት መንፈሳዊ ተልዕኳቸውን በአግባቡ እንዳይወጡ እንቅፋት ሲፈጥሩና ስቶ የማሳት ተገባር ሲፈጽሙ እንደቆዮ ስለመሆናቸው በሕይወተ ሥጋ ካሉት መካከል ብፁዕ አቡነ አትናቴዎስ፣ ብፁዕ አቡነ አረጋዊ፣ ብጹዕ አቡነ ገብርኤል፣ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ፣ ብጹዕ አቡነ ኢሳይያስ፣ ሊቀ ካህናት ብርሃኑ ገብረ አማኑኤል፣ ንቡረ ዕድ አባ ወልደ ማርቆስ፣ እና ሌሎችም  በአስረጂነት ሊጠቀሱ የሚችሉ መሆኑን ተገልጧል።

 

በመጨረሻም ቄስ ብርሃኑ ብሥራት ግየሚመሯቸው ግለሰቦች በተከራዩላቸው ጠበቃቸው አማካኝነት ብፁዕ አቡነ እንጦንስ ሊቀ ጳጳስ ወደ ደብረ ጽዮን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን መጥተው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳይሰጡና በቤተ ክርስቲያኑ ግቢ ውስጥ እንዳይታዩ ለማድረግ የፍርድ ቤት ዕገዳ ለማውጣጥ ከፍተኛ ኢ-ክርስቲያናዊ የሆነ ሙከራ እንዳደረጉ የሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት አታውቋል ።

 

የሀገረ ስበከቱ ሊቀ ጳጳስ አቡነ እንጦንስ ባለባቸው ኃላፊነት ቄስ ብርሃኑ ብሥራትን መክሮ፣ አስተምሮና ገስጾ  ወደ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ለመመለስ የተቻላቸውን ሁሉ በማድረግ ሰፊ ጊዜ የወሰደ ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርጉም ሊመለሱ ባለማቻላቸው የተሰማቸውን ከፈተኛ ሐዘን ገልጸው ከጸለዩ በኃላ የሚከተለውን ውሳኔ እንዳስተላለፉ ተዘግቧል።

 

ከዚህ ሁሉ ጥረት በኋላ ከመጽሐፍ ቅዱስ “ንግራ ለቤተ ክርስትያን” (ማቴ፤ 18፡18) የሚለውን፣ ቀኖና ሐዋርያት አንቀጽ 39፣ ከቃለ ዓዋዲ አንቀጽ 63፤ ቁጥር 2 እና 3 ያሉትን ኃይለ ቃላት በማገናዘብ፤ ይልቁንም ፍትሕ መንፈሳዊ «ካህኑ ኤጴስ ቆጶሱን አልታዘዘው ቢል (ቢንቀው)፣ ብቻውን ቤተ መቅደስ ቢሠራ፤ ኤጴስ ቆጶሱም ሦስት ጊዜ ቢጠራው ትዕዛዙን ተቀብሎ መልስ ባይሰጥ፣ እሱ ከማዕረገ ክህነቱ ይሻር፤ ተከታዮቹም ይሻሩ።» (ፍመ. ምዕራፍ 6፤ አንቀጽ 228፤ 3ኛረስጠብ 22) በማለት የደነገገውን ዋቢ በማደረግ “ቄስ” ብርሃኑ ብሥራት በየትኛውም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ አድባራትና ገዳማት ሁሉ በቅስና የሥልጣነ ክህነት መንፈሳዊ አገልግሉት አንዳይሰጡ ከሥልጣነ ክነታቸው የተሻሩ መሆኑን ገልጸዋል።

 

ብጹዕ ሊቀ ጳጳሱ የጻፉት ደብዳቤ እንደሚያስረዳው ከእንግዲህ “ቄስ” ብርሃኑ ብሥራት እንደተለመደው በማን አለብኝነትና በዕብሪት በስልጣነ ክህነት የሚሰጡት ማንኛውም መንፈሳዊ አገልግሉት በሐዋርያት ትዛዝ “ዘአሰርክሙ በምድር ይኩን እሱረ በሰማያት፤ ወዘፈታሕክሙ በምድር ይኩን ፍቱሐ በሰማያት” መሠረት ሀብተ መንፈስ ቅዱስ የማያሰጥ ሀብተ ስርየት የተለየው የታሰረና የተሻረ መሆኑን አብራርተው፤ “ቄስ” ብርሃኑ ብሥራት ይህን መንፈሳዊ ዳኝነትና ውሳኔ ተቀብለው ተግባራዊ ባያደርጉና በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ላይ ቢያምጹ በውግዘት ከማኅበረ ቤተ ክርስቲያን ሊለዩ እንደሚችሉ አስጠንቅቀዋል።

 

በመጨረሻም የሰሜን ምዕራብ አውሮፓ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወደፊት በዚህ ዓይነት የኢትዮጵያ አርቶዶክስ ተዋሕዶ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን የሚያፈርስ፤ በቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ አስተዳደር በአመጽ ክንዱን የሚያነሳ፣ በጠቅላላው ከአንዲት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአምልኮት አፈጻጸም ሥርዓት እና ቀኖና እንዲሁም ከቃለ አዋዲው መንፈሳዊ የአንድነት መመሪያ ውጭ ሆኖ ለመንቀሳቀስ የሚሞክር ወይም እንዲህ ያለውን ሕገ ወጥ ተግባር የሚያበረታታ፣ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተባባሪ የሚሆን አገልጋይ ካህን ቢኖርና በበቂ ማስረጃ ከተረጋገጠበት ቤተ ክርስቲያን ልትታገሰው የማትችል መሆኑን በጥብቅ አሳስበዋል።

 

የ“ቄስ” ብርሃኑ ብሥራት ሥልጣነ ክህነት የተሻረበትን ሕጋዊ ደብዳቤ ሙሉ ቃል ከዚህ ቀጥሎ ይመልከቱ።

 

Download (PDF, 1021KB)

 


የኢትዮጵያ ሙስሊሞች በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ያካሄዱት ደማቅ የተቃውሞ ትእይንት ቪድዮዎችን ይዘናል

$
0
0

በአዲስ አበባ እና በክልል ከተሞች ደማቅ የተቃውሞ ትእይንት ተደረገ (ቪድዮዎች ይዘናል)
በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስኪድን ጨምሮ በተለያዩ የሃገሪቱ ዋናዋና ከተሞች ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!›› በሚል መሪ ቃል ህዝበ ሙስሊሙ እያካሄደው ያለው መስጂድ ተኮር የዘመቻ እንቅስቃሴ አካል የሆነው እና የዘመቻው ማጠናቀቂያ የጁምኣ የተቃውሞ ትእይንት በደመቀ መልኩ ተካሂዷል::

ህዝቡን ከመስጂዱ ለመነጠል በመንግስት በኩል እየተሰራ ያለውን ህገ ወጥና ኢ-ህገ መንግስታዊ ስራም ለራሱ ተረድቶ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማትና መስጂዶቹን በዒባዳ በማድመቅ ላይ ነው የሚገኘው፡፡ ይህ ወቅታዊና አንገብጋቢ የመስጂድ ባለቤትነትን የማረጋገጥ እንቅስቃሴ የመንግስትን እና የመጅሊስን ሴረኞች እንቅልፍ ማሳጣቱንም ከተለያዩ አቅጣጫዎች የሚመጡ የውስጥ መረጃዎች እያጋለጡ ነው፡፡ ‹‹ሰላታችንን በመስጂዳችን!››ዘመቻ የዛሬው ጁሙአ ድረስ ቀጥሎ የቆየ ሲሆን በአዲስ አበባና በተመረጡ የክልል መስጂዶች ላይም አስቀድሞ የነበሩንን ቋሚ ትዝታ ጥለው ያለፉ ግዙፍ ተቃውሞዎችን በሚያስታውስ መልኩ የደመቀ የተቃውሞ ስነስርአት በማድረግ በሰላማዊ ሁኔታ ዘመቻው መጠናቀቁ ታውቋል::

በዚህም መሰረት ከቀኑ ስድሰት ጀምሮ በአዲስ ወደ አዲስ አበባ አንዋር መስኪድ እና በተለያዩ ከተሞች በሚገኙ የተቃውሞ ወደተመረጡ መስኪዶች የተመመው ህዝበ ሙስሊሙ የመስኪዶችን ውስጥ እና ደጅ በመሙላት መስኪዶቹ የራሱ ሃብት መሆናቸውን እና ሙስሊሙ ህዝብ ሰላም ፈላጊ መሆኑን በደመቀ ተቃውሞ ነጭ ምልክቶችን በማውለብለብ ገልጿል::

ህዝበ ሙስሊሙ ዘመቻውን በተሳካ መልኩ በማድረግ ሰላማዊ ተቃውሞውን አሰምቶ ከኮሚቴው ጎን ዛሬም ቃሉን አክብሮ እንደቆመ በማሳየት በሰላም መመለሱን ለማረጋገጥ ተችሏል::

[የሳዑዲ ጉዳይ] ዲፕሎማቱ የኢትዮጵያ አለም አቀፍ ት/ቤትን ተቆጣጠሩ፤ ለተመዘበረው 1.7 ሚሊዮን ሪያል «ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ» ወላጆችን ባለዕዳ አደረጉ

$
0
0

saudi arabia
ከኢትዮጵያ ሃገሬ ከሳዑዲ አረቢያ ጂዳ

ከ1500 በላይ በሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚተዳደር የሚታወቀው በሪያድ አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት በዲፕሎማቱ ቁጥጠር ስር መዋሉን የሚገልጹ ምንጮች ለዛሬ ማርች 28 2014 በኤምባሲው ደብዳቤ የስብሰባ ጥሪ ተላልፎላቸው የነበሩ ወላጆች ባለመገኝታቸው የስብሰባው አዳራሽ ባዶ ሁኖ መዋሉን አክለው ገልጸዋል፡:

ንበረትነቱ በሪያድ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ማህበር እንደነበር የሚነገርለትን ት/ቤት ኤምባሲው ለመቆጣጠር እያደረገ ያለው ጥረት ከግልጥቀም የመነጨ መሆኑንን የሚናገሩ ውስጥ አውቂ ምንጮች ት/ቤቱን ከኮሚኒቲው በመነጠል ከወላጆች በሚመረጥ የቦርድ አስተዳደር ይመራል በሚል ሽፋን ላለፉት 5 አመታት በት/ቤቱ ጥሬ ገዝንዘብ ላይ ግልጽ የሆነ ምዝበራ መፈጸሙን ይናገራሉ። ይህን አለም አቀፍ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ት/ቤት ዲፕሎማቱ ልግል ጥቅማቸው ለማዋል ያልፈነቀሉት ድንጋይ ያልበጠሱት ቀጠል እንደሌለ የሚናገሩ ወገኖች ከዛሬ 7 ወር በፊት ለይስሙላ ህብረተሰቡ በቦርድ አባልነት ለመሳተፍ የሚያስችለውን ማስታወቂያ አውጥተን የሚቀርብ ሰው አጣን ለማለት የመወዳደሪያውን ማመዘኛ ዲግሪ እና ከዛ በላይ ከፍ በማድረግ ማንኛውም ወላጅ በቀላሉ ማቀረብ የማይችላችውን ተጨማሪ ድብዳቤዎች እንዲያቀርብ የሚጠይቅ መስፈርቶችን በማስቀመጥ ወላጆች ት/ቤታቸውን ለማስተዳደር እንዳይችሉ መደረጋቸውን ይገልጻሉ።

ይህ በዚህ እንዳለ ወላጆች ባላቸው አቀም እና የትምህርት ደረጃ አቋቁመው ለዘመናት ያለማንም ድጋፍ እና ረዳት በማስተዳደር ለዚህ ያበቁትን የልጆቻቸውን ዕውቀት መገብያ ማዕከል ኤምባሲው ለመንጠቅ በሪያድ የዲያስፖራው ሃላፊ እንደሆኑ የሚነገርላቸው አቶ ተመስገን ኡመርን በጓሮ በር አሾልኮ በመስገባት ቀደም ብለው ያዘጋጇቸውን ታማኝ አገልጋይ የቦርድ አባላት ስልጣን ካፀደቁ በሃላ ዛሬ ወላጆችን ለማደናገር በኤምባሲው ማህተም በተደገፈ ደብዳቤ ስብሰባ መጥራታቸው የዲፕሎማቱን አላውቂ ሳሚነት በግልጽ ያሳይል ተብሏል።

ዲፕሎማቱ በኤንባሲ ሽፋን ህገወጥ ተግባር በመፈጸም ላይ እንደሚገኙ የሚናገሩ ወገኖች 1500 በላይ የሆኑ ወላጆች በባለቤትነት እንደሚቆረቆሩለት የሚነገርለትን ት/ቤት ቁጥራቸው ከ 50 የማይበልጥ የት/ቤቱ ጉዳይ የማይመለክታቸውን ደጋፊዎቻቸውን ሰብስበው አዳራሽ በማስገባት «አይጥ በበላው ዳዎ እንዲሉ » ምንም የማያውቁትን ወላጆች የ 1.7 ሚሊዮን ሪያል ባለእዳ የሚያደርግ ሪፖርት በዲይስፖራው ሃላፊ አማካኝነት በማቅረብ ዲፕሎማቱ የመረጣቸውን ህገ ወጥ የቦርድ አማራር አባላት ህጋዊ ለማድረግ ከወላጆች ጀርባ ዛሬ የፈጸሙት ደባ በህግ ሊያስጠይቃቸው የሚገባ ብሄራዊ ወንጀል መሆኑን ገልጸዋል። ስብሰባው ላይ በሳውዲ አረቢያ የኢትዮጵያው አምባሳደር ዶ/ር መሃመድ ህሰን መገኘታቸውን ለማረጋገጥ ተችሏል። በዚህ ዙሪያ የዲያስፖራውን ሃላፊ አቶ ተመስገን ዑመርን ለማነጋገር ያደርኩት ሙከራ አልተሳካም::

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 61 – PDF

$
0
0

ጋዜጣውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 61 ወጥታለች። በሚኒሶታ የምትኖሩ ከ92 በላይ ቦታዎች ላይ ጋዜጣችን ስለተቀመጠ ማግኘት ትችላላችሁ። በውጭ ያላችሁ ደግሞ በPDF አቅርበንላችኋል።

zehabesha 61 page page 13 to 24
* ከሚኒሶታ አልፎ በዓለም አቀፍ ደረጃ መነጋገሪያ እየሆነ የመጣው የሚኒሶታው ደብረሰላም መድሃኔዓለም ቤ/ክ ጉዳይ ዓብይ ር ዕሳችን ነው። ጉዳዩ ወደ ወሳኝ ምዕራፍ ተሸጋግሯል፤ ብዙሃን በጉጉት ሲጠበቁት የነበረው ጠቅላላ ጉባኤም ተጠርቷል።

* የተመስገን ደሳለኝ አዲስ ጽሁፍ “ኑ እንዋቀስ! ኢሕ አዴግን እናፍርሰው” የጋዜጣችን አካል ሆኗል

* የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት የነበሩት አቶ አለማየሁ አቶምሳ እንዴት በምግብ መመረዝ ሊሞቱ ይችላሉ? – አንድ የህክምና ባለሙያ በምግብ መመረዝ የተነሳ የሚከሰቱ 4 በሽታዎችን ይዘውልናል – ያንብቡት።

* በቀድሞው ጦቢያ መጽሔት ላይ ተወዳጅ ብ ዕሩን የምታነቡለት ጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ “የመስዋዕትነት ወንጌል” የሚል ጠንካራ ዘገባ አድርሶናል – ያንብቡት።

በእንመካከር አምዳችን፡ 3 ጉዳዮች ተይዘዋል።

* “ፍቅረኛዬ በወሲብ ወቅት ተቃጠልኩ፤ አሳመምከኝ እያለች አስቸገረችኝ”
* ትዳር የሚመሰርቱት ምን ዓይነት ፍቅረኞች ናቸው?
* ሰዎች “ውስጣዊ ውበት እወዳለሁ” ሲሉ እሰማለሁ ምንድ ነው? ለሚሉት የባለሙያ ምላሾችን ይዘናል።

በአሜሪካ ጉዳይ አምዳችን፦
* ቤትዎ ከመሸጡ በፊት ከመንግስት በሚያገኙት ዕርዳታ ማትረፍ ይችላሉ ይለናል የጠበቃ ሳምሶን በዙ ጽሁፍ። ቢያነቡት ይጠቀማሉ።
* በሰሜን አሜሪካ ሁካ (ሺሻ) በጣም እየተለመደ የመጣ ነገር ሆኗል። ለመሆኑ ሁካ ምን ይጠቅማል? ምን ይጎዳል? የሚል አስተማሪ ዘገባ ይዘናል። ለጤናዎ የሚያስቡ ከሆነ ያንብቡት።

እንደተለመደው በጤና አምዳችን 3 ጉዳዮችን ይዘንላችኋል።
* ምን ልብላ? What Should I Eat?
* የማደንዘዣ ቴክኒክ ምስጢር፤ ከህሊናችን ስንርቅ የት እንገባለን?
* ኢንዶስኮፒ ለማን እና ለምን? – ያንብቧቸው።

ለእረፍትዎ አምዳችን ላይ 2 ጉዳዮች ተይዘዋል።
* የጆሮ፣ አፍንጫና ጉሮሮ አስገራሚ ወዳጅነት
* ሰዎች ከእንስሳ ሊለዩ የሚችሉባቸው 15ቱ ልዩ ዘዴዎች

በስፖርት አምዳችንም 3 ጉዳዮች ተስተናግደዋል።

* የዓለም ዋንጫ እየተቃረበ ቢሆንም የጀርመን አቋም አሳሳቢ ሆኗል፤
* ስለማን.ሲቲ፣ባርሴሎና እና እንግሊዝ ዣቪ ይናገራል
* ቲያጎ የባርሴሎናው ዣቪ አልጋ ወራሽ – ይዝናኑባቸው።

በሴቶች ጤና አምዳችን ሴቶችን በብዛት ስለሚያጠቃው የኩላሊት ኢንፌክሽን ላይ ጥሩ ዘገባ አቅርበናል።

ምን ይሄ ብቻ?
የዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ የኤፍሬም እሸቴ፣ የዶ/ር ፍቅሬ ቶለሳን ጨምሮ ሌሎች አዝናኝና አስተማሪ ዘገባዎችን ከማስታወቂያዎች ጋር አጅበን ይዘናል። ያንብቡን።

የዓረና መሪዎች በእንደርታ ኲሓ ከተማ በፖሊስ ታሰሩ

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

Arena-Tigray-logoየዓረና አመራር አባላት የሆኑት አቶ ብርሃኑ በርሀ፣ መምህር የማነ ንጉሰና አቶ ፅጋቡ ቆባዕ በፖሊስ ተደበደቡ፤ በመጨረሻም በኲሓ ከተማ ፖሊስ ታሰሩ። የታሰሩበት ምክንያት ለስብሰባ በማይክሮፎን ቀስቅሳችኋል የሚል ነው። ነገ እሁድ በኲሓ ከተማ ማዘጋጃቤት አዳራሽ ስብሰባ ለማድረግ የተፈቀደልን ሲሆን ቅስቀሳ ለማካሄድ ግን ተከልክለናል። ዛሬ ጧት አቶ ዓምዶም ገብረስላሴና መምህር ዮሃንስ ካሕሳይ ቅስቀሳ ሲያደርጉ በዓይናለም ከተማ ለሰዓታት ታስረው ተለቀዋል። የህወሓት ካድሬዎች ዓረና የማዳበርያ ዕዳ እንደሚሰርዝ፣ መሬት የህዝብ እንደሚያደርግ፣ የሊዝ አዋጅ እንደሚያስቀር ወዘተ በማይክሮፎን እንዳይናገር አስጠንቅቁት ተብለናል ሲሉ የህወሓት ካድሬዎች ራሳቸው አረጋግጠውልናል። አሁን የኲሓ ከተማ ቅስቀሳችን በአባሎቻችን መደብደብና መታሰር ምክንያት ለግዜው ቁሟል። ስብሰባው ግን ነገ ይካሄዳል።

ዓረና ፓርቲ ነገ እሁድ ከእንደርታ ህዝብ ጋር በኲሓ ከተማ ለሚያደርገው ህዝባዊ ስብሰባ ቅስቀሳ እንዳያደርግ ተከለከለ። ህወሓቶች ህዝባዊ ስብሰባ እንድናደርግ የፈቀዱልን ሲሆን ህዝቡን ለማሳወቅ ቅስቀሳ ማድረግ ግን አይፈቀድም አሉን። ህወሓቶችን ያስፈራ ጉዳይ የትግራይ አርሶአደሮች የብድር ብዝበዛ ያቀጣጠለው የህዝብ ተቃውሞ ነው። ቅስቀሳው ግን ይቀጥላል። ህዝብ አማራጭ ሐሳብ የመስማት መብት አለው። የህወሓት ዓፈና እንቃወማለን።

በሌላ በኩል ደቡብ ሕብረት-ኢሦዴፓ ፓርቲ ዛሬ ቅዳሜ መጋቢት 20, 2006 ዓም በሀዋሳ ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ ጠርቷል። ዓረና ፓርቲም ተጋብዟል። የዓረና ተወካይ አቶ ካሕሳይ ዘገየ ንግግር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል። ደቡብ ሕብረት -ኢሦዴፓ በደቡብ ክልል እንቅስቃሴ መጀመሩ የሚያኮራ ነው። የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ፓርቲም በኦሮምያ ክልል ቅስቀሳ እንደሚጀምር ይጠበቃል።

“ከእናቴ በመጣላቱ ከቤት ወጥቶ ያልተመለሰው አባቴን አፋልጉኝ”–ቅድስት ሙላት ከሳዑዲ አረቢያ

$
0
0

የአፋልጉኝ ጥሪ

ተፈላጊ አባቴ ሙላት ገ/አምላክ ሃብተጊዮርጊስ በ1985 ዓ.ም ከእናቴ በመለያየታቸው ምክንያት ከቤት ወጥቶ የቀረ ስለሆነ ያለበትን አድራሻ የሚያውቅ ካለ ቢተባበረኝ በፈጣሪ ስም እጠይቃለሁ። በስልክ ቁጥር 000966530210347 ሊደውሉልኝ ይችላሉ።

ፈላጊ ልጅ ቅድስት ሙላት ገ/አምላክ – ሳዑዲ አረቢያ።

ዘ-ሐበሻ ይህችን መልዕክት በአየር ላይ ብታውሉልኝ ብዬ ነው።
afalegugn

በነገሌ ቦረናው ግጭት ከ30 ሰዎች በላይ ተገድለዋል፤ ግጭቱ አልቆመም

$
0
0

ነገሌ ቦረና (ፎቶ ፋይል)

ነገሌ ቦረና (ፎቶ ፋይል)


ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ በደቡብ ኢትዮጵያ በነገሌ ቦረና ከከተማው ስም ስያሜ ጋር በተያያዘ በጉጂ እና በቦረና ማህበረሰቦች መካከል በነገሌ ቦረና አካባቢ በተነሳ ግጭት ከ30 ሰዎች በላይ መሞታቸውን እና ግጭቱም አለመቆሙን የአከባቢው ባለስልጣናት ምንጮች ማምሻውን በላኩልን መረጃ ገለጹ። ከባለፈው እሁድ ጀምሮ በአከባቢው የተነሳው ግጭት በመስፋፋት ከፍተኛ የሆነ ንብረት ያወደመ ከመሆኑም በላይ ከነገሌ ከተማ ውጪ ለጉላ እና አርዶታ በተባሉ አከባቢዎች ግጭቱ ተስፋፍቶ መቀጠሉ ታውቋል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ወደ ግዛቴ ግጭቱ ዘልቆ ሊገባ ይሽላል በሚል ፍራቻ ኬንያ ወታደሮቿን በድንበር አከባቢ አስፍራል እያስጠበቀች መሆኑ ታውቋል።

የኢሕአዴግ ፌዴራል ፖሊሶች እና የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሃይል ፖሊሶች በቦታው ደርሰው የነበረ ቢሆንም የአከባቢው ህብረተሰብ ቀየውን በመልቀቅ እየተሰደደ መሆኑን ታውቋል። በከፈትና ፍጥነት እየተስፋፋ የመጣውና የጎሳ ፌዴራሊስም ፖለቲካ ውጤት የሆነው ይህ ግጭት በአካባቢው ባለስልጣናት እና የሃገር ሽማግሌዎች ለመፍታት ቢሞከርም ሳይሳካ ግጭቱ እንደቀጠለ ታውቋል።

ሚሊዮኖች ድምጽ –የነጻነት ደዉል በአዲስ አበባ፣ በአዋሳ እና በደሴ ተደዉሏል!

$
0
0
MILLIONS OF VOICE FOR FREEDOM !

አንድነት ፓርቲ

የአንድነት ፓርቲ ሰላማዊና ሕጋዊ በሆነ መንገድ የሚንቀሳቀስ ድርጅት ነው። በኢትዮጵያ የፌዴራልም ሆነ የክልል ባለስልጣናት የተለያዩ ሕጎችና ደንቦች ሊያወጡ ይችላሉ። ነገር ግን ሕገ መንግስቱ የሕጎች ሁሉ የበላይ ነው። በሕገ መንግስቱ የተቀመጡ መሰረታዊ የሕግ አንቀጾችን ማንኛዉም አካል ሊሽረው ወይንም ሊቀለብሰው አይችልም።

የኢትዮጵያ ሕገ መንግስት አንቀጽ 30 ዜጎች ነፍጥ ሳይዙ የመሰባሰብ፣ ሕዝባዊ ሰላማዊ ሰልፎች የማድረግ፣ ፔትሽኖችን የማሰባሰብ ሙሉ መብት እንዳላቸው ይደነግጋል።

“Everyone shall have the freedom, in association with others, to peaceably assemble without arms, engage in public demonstration and the right to petition. Appropriate procedure may be enacted to ensure that public meetings and demonstrations do not disrupt public activities, or that such meetings and demonstrations do not violate public morals, peace and democratic rights.”

ይላል አንቀጹ።

በአዲስ አበባ፣ በደሴና በአዋሳ ሰላማዊ ሰልፎች ይደረጋሉ። በሰልፉ የጥበቃ ኃይላት ያሰማሩ ዘንድ ለባለስልጣናት አስፈላጊዉ የማሳወቅ ደብዳቤ ተልኳል። በታሰበው ቀንና ቦታ ሌሎች እንቅስቃሴዎች ካሉና በቂ የጥበቃ ኃይል ማሰማራት ባለስልጣናት ካልቻሉ፣ ቀኑ እንዲራዘም ወይንም የሰልፉ ቦታ እንዲቀየር ሊጠይቁ ይችላሉ። ከዚያ ዉጭ ሰልፎችን የመፈቀድም ሆነ የመከልከል መብት ባለስልጣናት የላቸውም። ይሄ መታወቅ አለበት። ከከለከሉ ወይንም መፍቀድ አለብን ካሉ፣ በቀጥታ የአገሪቷን ሕግ ያፈርሳሉ ማለት ነው። ሕገ ወጥ የሚሆኑት እነርሱ ናቸው ማለት ነው።

ሰልፍ ማድረግ አመጽ አይደለም። የአንድነት ፓርቲ፣ የሰማያዊ ፓርቲ ላለፉት በርካታ ወራት የተለያዩ ሰልፎች አድርገዋል። በሰዉም ሆነ በንብረት ላይ አንድም ጉዳት አልደረሰም። ከፖሊሶች ጋር ምንም አይነት ግብግብ አልተፈጠረም። አንዲት ጠጠር አልተወረወረችም። ኢሕአዴጎች ይሄን ልብ እንዲሉ ያስፈልጋል። እነርሱ ሌላው ሕግ ማክበር አለበት እንደሚሉት፣ ሕግን ማክበሩ ያዋጣቸዋል።

እንግዲህ ሁላችንም እንዘጋጅ፤ ዉስጥ ውስጡን ማጉረምረም ይበቃናል። እርስ በርስ ማንሾካሾክ ይበቃናል። ከሚሊዮኖች ጋር ሆነን ድምጻችንን በድፍረት፣ በአደባባይ እናሰማ። ፈርተን እና ተስፋ ቆርጠን ከተደበቅን፣ ከሸሸን፣ ዝምታን ከመረጥን፣ በሙስናና በመልካም አስተዳደር እጦት የተዘፈቁት ገዢዎቻችን የደገፍናቸው ነው የሚመስላቸው። እንነሳ፣ እንቀሳቀስ። ሕገ መንግስቱ ይፈቅድልናል። ኢትዮጵያዊ የዜግነት ግዴታም አለብን።

እኛ ጥይት አንተኩስም ! ጠጠር እንወረወርም! ጥላቻን አንዘምርም። ክርስቲያን፣ ሙስሊም፣ ኦሮሞ፣ ትግሬም፣ አማራ፣ በብሄረሰቡ መታወቅ የማይፈልገው ቅልቅሉ..…ሁላችንም፣  በዘር፣ በኃይማኖት ሳንከፋፈል፣ ሚሊዮኖች ሆነን ድምጻችንን እናሰማለን። በርግጠኝነት የሚሊዮኖችን ጥያቄ ሊንቅ የሚችል ማንም ኃይል የለምም፣ ሊኖርም አይችልም።

እንግዲህ የነጻነት ደዉል በአዲስ አበባ፣ በአዋሳ እና በደሴ ተደዉሏል። ጥሪ ቀርቧል። ትኩረቱ ወደነዚህ ከተሞች ይሆናል!!!!!

በላስ ቬጋስ፣ በአትላንታ እና ዴንቨር የሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን እነዚህ ሶስት ከተሞችን ስፖንሰር በማድረግ ድጋፋቸውን በመግለጻቸዉ ሊመሰገኑ ይገባል። ሌሎቻችንም ተደራጅተን፣ ሶሊዳሪቲ በማሳየት የሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !

 

እንበርታ ፣ እንጎብዝ ! ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !

millionsforethiopia@gmail.com


የቀድሞው የጋምቤላ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፈኑ “ወያኔ እጅ ገብተዋል”

$
0
0

downl44የጋምቤላ ክልልን ሲመሩ ቆይተው ባለመስማማት የኮበለሉት የቀድሞው የክልሉ ፕሬዚዳንት ደቡብ ሱዳን ከሆቴል ውስጥ ታፍነው መወሰዳቸው ተጠቆመ። ዜናው በገለልተኛ ወገን ባይገለጽም ኖርዌይ በስደት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ይኖሩ የነበሩት አቶ ኦኬሎ አኳይ በኢህአዴግ በጥብቅ የሚፈለጉ ሰው ነበሩ።
በመለስ ዜናዊ ውሳኔ በአኙዋክ ተወላጆች ላይ በጅምላ የተከናወነውን ጭፍጨፋ አስመልከቶ ተቃውሞ በማሰማት የኮበለሉት አቶ ኦኬሎ ወደ ደቡብ ሱዳን ከማምራታቸው በፊት ኬንያ እንደነበሩ፣ ከኬንያ ወደ ደቡብ ሱዳን ለምን እንደተጓዙ የዜናው ምንጮች በይፋ ከመናገር ተቆጥበዋል። ስማቸው እንዲደበቅላቸው የጠየቁ የጋምቤላ አስተዳደር ባልደረባ ለጎልጉል የአካባቢው ዘጋቢ እንደተናገሩት አቶ ኦኬሎ ደቡብ ሱዳን ሆቴል በተቀመጡበት መታፈናቸውን አረጋግጠዋል።

“ወያኔ እጅ ገብቷል” ሲሉ ያከሉት እኚሁ ሰው “አቶ ኦኬሎ ብረት በማንሳት ወያኔን ለመታገል ከተነሱ ጋር ተቀላቅለዋል በሚል ስማቸው መመዝገቡንና ወደ ደቡብ ሱዳን ማቅናታቸው በመታወቁ ህወሃቶች እጅ ሊወድቁ ችለዋል” ብለዋል። ምንጩ ይህንን ይበሉ እንጂ አቶ ኦኬሎ አክዋይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያቀኑበትን ምክንያት በርግጠኛነት ሃላፊነት ወስዶ የገለጸ ወገን አልተደመጠም። ኢህአዴግም ቢሆን የቀድሞውን ሹመኛ ስለመያዙ ይፋ ያደረገው ነገር የለም። ከደቡብ ሱዳን ቀውስ ጋር በተያያዘ የኑዌር ተወላጅ ከሆኑት ሬክ ማቻር ጦር ጋር በመሰለፍ የሳልቫ ኪርን ሃይል ሲወጉ ከተገደሉ ወታደሮች መካከል የኢህአዴግን ሰራዊት መለያ የለበሱ ኑዌሮች መገኘታቸው ውዝግብ አስነስቶ እንደነበር ያመለከቱት ምንጭ “ደቡብ ሱዳን እየወጋት ካለው ኢህአዴግ ጋር አብራ የቀድሞውን የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳደር ከምድሯ ላይ እንዲታፈኑ መፍቀዷ ቅሬታ ያስነሳል” ብለዋል።

ከቤተሰባቸው ተነጥለው በስደት ከሚኖሩበት ኖርዌይ ወደ ደቡብ ሱዳን ያመሩት የቀድሞው የጋምቤላ ርዕሰ መስተዳድር ደቡብ ሱዳን በህወሃት ሙሉ ቁጥጥርና ፈቃድ የምትንቀሳቀስ አገር መሆኗን እያወቁ ወደዛ ማቅናታቸውን ባሥልጣኑ “ታላቅ ጥፋት” ብለውታል። ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። በቅርቡ አቶ ኦሞት ኦባንግ መኮብለላቸውና በብዙዎች ዘንድ አውሮጳ እንዳሉ ቢነገርም በትክክል ያሉበት አገር በይፋ አለመታወቁን መዘገባችን ይታወሳል።
goolgule.com/

ያልተሳካው የበድር ኢንተርናሽናል ሽምግልና

ፖሊሱ ሚኒባሷን በጥይት መታት፤ አንዲት እህት ወዲያው ሞተች ሁለቱ ቆሰሉ

$
0
0

የህዝብን ደህንነት እንዲጠብቁ የሰለጠኑ ፖሊሶች የንፁሀንን ህይወት በማጥፋት ስራ ላይ ተጠምደዋል

news
ትላንትና ማታ ከእምድብር ወደ አዲስ አበባ ይጓዝ የነበረ ሚኒባስ በአካባቢው የጥበቃ ተረኛ በነበረ ፖሊስ በጥይት ከተመታ በኋላ በውስጡ ከነበሩ ተሳፋሪዎች መሀከል የአንድ ከአረብ ሀገር ተመላሽ እህታችን ህይወት ወዲያው ሲያልፍ ሁለት ሰዎች ላይ ደግሞ የአካል ጉዳት ተከስቷል ይላል ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ።

እንደደረሰው መረጃ ከሆነ ፖሊሱ ይህን እርምጃ የወሰደው ሚኒባሱ ኮንትሮባንድ የጫነ መኪና መስሎት እንደሆነ በአካባቢ የነበሩ የአይን እማዬች ቢገልጹም የጥበቃ ፖሊሱ ይህን እርምጃ ከመውሰዱ በፊት ወደ ላይ ተኩሶ መኪናውን ለማስቆም ወይም ለማስጠንቀቅ ያደረገው ጥረት አለመኖሩን አክለው ይገልፃሉ።

አደጋው የደረሰው በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ልዩ ስሙ ጋሶሬ እየተባለ በሚጠራው መንደር ሲሆን በቅርብ ጊዜ ይህ አካባቢ ከወልቂጤ ከተማ ተካሏል) የእምድብር ከተማ ነዋሪ የሆነችው ሟች ኮከቤ አለማየሁ ባለ ትዳር እና የሁለት ልጆች እናት ስትሆን በቅርብ ጊዜ ከአረብ ሀገር ተመልሳ ኑሮዋን ለማቸነፍ አነስተኛ ሱቅ ለመክፈት ለሱቅ እሚሆን እቃ ለማምጣት ወደ አዲስ አበባ እየተጓዘች በነበረበት ጊዜ ነው የለፋችለት ትዳሯን እና መስዋዕት የከፈለችላቸውን ልጆቿን ለሚያሳጣት ጥይት በፖሊሱ የተላከባት። አስክሬኑ ለምርመራ ወደ አዲስ አበባ ምኒሊክ ሆስፒታል ተወስዷል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በመንግስት በታጠቁ ፖሊሶች ህይወታቸው እየተነጠቁ ያሉ ምስኪን ዜጎች ቁጥር በሀገራችን እየጨመረ ይገኛል።

ለሟች ቤተሰቦች ሀዘኑ መራራ ቢሆንም መጽናናትን ለቆሰሉ ቁስላቹ የውሻ ቁስል ይሁንላቹ የሚሉት የዚህ ዘገባ አጠናቃሪዎች “የንፁሀንን ደም ለማጥፋት የሰለጠኑ የሚመስሉትን ፖሊሶችን እያሰለጠኑ ለሚያወጡ ማሰልጠኛዎች እባካችሁ ምልመላና የስልጠና አሰጣጣችሁን በመቀየር ፖሊስ የንፁሀን ጠባቂ እንጂ ስጋት መሆናቸውን አስቁሙልን” ሲሉ ጥሪያቸውን ያቀርባሉ”"

የአቶ ድሪባ ኩማ አስተዳደርና በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባ

$
0
0

<div>ረፖርተር
መጋቢት 22, 2006 ዓ.ም</div>
<div><strong>በአዲስ ከንቲባና ነባር ካቢኔ ሥራውን የጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሰባተኛ ወሩን ይዟል፡፡</strong></div>
<div>

አስተዳደሩ የቆየባቸው ሰባት ወራት የሥራ ክንውን የከተማውን ነዋሪዎች ብሶትና ችግር የፈታ ሳይሆን፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች ጐልተው የታዩበት ነበር ማለት ይቻላል፡፡

የአቶ ድሪባ ኩማ አስተዳደርና በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባከ2001 ዓ.ም. እስከ 2005 ዓ.ም. ለአምስት ዓመታት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርን በከንቲባነት ሲመሩ ከነበሩት አቶ ኩማ ደመቅሳ የአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤትን ቁልፍ የተረከቡት አቶ ድሪባ ኩማ፣ የከተማውን ነዋሪዎች ሲያንገሸግሻቸው የቆየውን የመልካም አስተዳዳር እጦት ችግር በመጠኑም ቢሆን ይፈቱታል የሚል ግምት ተሰጥቶዋቸው እንደነበር ሪፖርተር ያነጋገራቸው አንዳንድ የከተማው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡ ነዋሪዎቹ ቅድሚያ ግምት የሰጡት ዝም ብለው ሳይሆን በፌዴራል መንግሥት ጭምር ትኩረት ተሰጥቶ መሠራት ያለባቸው በዋናነት፣ የመልካም አስተዳደር እጦትና የሙስና ጉዳዮች በመሆናቸው ጭምር ነው፡፡ የፌዴራል መንግሥት መቀመጫ የሆነችው አዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ለሚጠይቋቸው የመብትም ሆነ ሌሎች ጥያቄዎች ተገቢ የሆነ ምላሽ ማግኘት ባለመቻላቸው፣ የመልካም አስተዳደር እጦትን በማንሳት ጠዋት ማታ ሲያማርሩ መክረማቸው የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን አስተያየት ሰጪዎቹ ይገልጻሉ፡፡

የከተማውን ነዋሪዎች ብሶትና የዕለት ከዕለት ምሬት የተሰማቸው በሚመስል ሁኔታ፣ የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ተክተው የተመረጡት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ደሳለኝም ትኩረት ሰጥተው ከሚንቀሳቀሱባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል በዋነኛነት የጠቀሷቸው የመልካም አስጸዳደር እጦትንና ሙስናን መዋጋት እንደነበር ነዋሪዎች ያስታውሳሉ፡፡

ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ ከንቲባ መሾሙን ተከትሎ፣ በአስተዳደሩ መዋቅር ላይ ለውጥ ተደርጐ የአገልግሎት አሰጣጥ ለውጥ ያመጣል የሚል ግምትም ነበር፡፡ አስተዳደሩም ለውጥ ለማምጣት ቆርጦ የተነሳ በሚመስል ሁኔታ ለሰው ኃይሉ ግምገማዊ ሥልጠና ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ በሥልጠናውም 500 ከፍተኛ አመራሮች፣ 3,000 መካከለኛ አመራሮችና 52 ሺሕ ሠራተኞች ተሳትፈዋል፡፡

<a href=”http://www.zehabesha.com/wp-content/uploads/2014/03/የአቶ-ድሪባ-ኩማ-አስተዳደርና-በቅሬታ-የምትናጠው-አዲስ-አበባ.jpg”><img class=”size-medium wp-image-26797 alignleft” alt=”የአቶ ድሪባ ኩማ አስተዳደርና በቅሬታ የምትናጠው አዲስ አበባ” src=”http://www.zehabesha.com/wp-content/uploads/2014/03/የአቶ-ድሪባ-ኩማ-አስተዳደርና-በቅሬታ-የምትናጠው-አዲስ-አበባ-300×187.jpg” width=”300″ height=”187″ /></a>ነገር ግን መልካም አስተዳዳርን በማስፈንም ሆነ በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የኅብረተሰቡ ቅሬታ የሚፈታ አልሆነም፡፡ በዋናነት የመልካም አስተዳደር እጦት ከሚስተዋልባቸው የሥራ ዘርፎች መካከል መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎች፣ የትራንስፖርት አቅርቦት፣ ንፁህ የመጠጥ የውኃ አቅርቦት፣ የመኖሪያ ቤት አቅርቦትና በአስተዳደሩ ሥልጣን ክልል ውስጥ ባይሆንም የኤሌክትሪክ መቆራረጥና የቴሌኮሙዩኒኬሽን ችግሮች በስፋት የሚስተዋሉ ናቸው፡፡

<em><strong>መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎች</strong></em>

የሙስና መፈንጫ ናቸው ተብለው ከተፈረጁ አራት ዘርፎች መካከል አንዱና ዋነኛው መሬትና መሬት ነክ ይዞታዎች ዘርፍ ነው፡፡ በተለይ የቀድሞው ከንቲባ አቶ ኩማ ደመቅሳ የአስተዳደሩን ሥልጣን ከተረከቡበት ከ2001 ዓ.ም. ጀምሮ በዘርፉ ማሻሻያ ለማድረግ ብዙ ሥራዎች ተሠርተዋል፡፡

ከተሠሩት ሥራዎች መካከል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ዘርፍን መዋቅር መለወጥ፣ የሰው ኃይሉን ማሟላትና ለሥራው ብቁ ማድረግ ነው፡፡ የሕግ ክፍተቶችን ለመሙላት ደግሞ የፌዴራል መንግሥት የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ አዋጅ በኅዳር ወር 2004 ዓ.ም. ወጥቷል፡፡ በዚህ አዋጅ መነሻነት በርካታ ደንቦችና መመርያዎች በአስተዳደሩ ወጥተዋል፡፡

በዚህ መሠረት አስተዳደሩ የመሬት ልማትና ማኔጅመንት ቢሮ ከማቋቋሙም በተጨማሪ፣ በሥሩ የግንባታ ፈቃድ አሰጣጥና ክትትል ባሥልጣን፣ የይዞታ አስተዳደር የሽግግር ጊዜ አገልግሎት ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት፣ የመሬት ልማትና ከተማ ማደስ ኤጀንሲና የመሬት ባንክና ማስተላለፍ ኤጀንሲ መሥሪያ ቤቶች እንዲቋቋሙ ተደርጓል፡፡

እነዚህ መሥሪያ ቤቶች የሚመሩባቸው ሕግጋትና ልዩ ልዩ የሕግ ማዕቀፎች ከመውጣታቸውም በተጨማሪ የሰው ኃይል እንዲሟላላቸው ተደርጓል፡፡

ከአቶ ኩማ ደመቅሳ ሥልጣኑን የተረከቡት አቶ ድሪባ ኩማ የሥልጣን ዘመን፣ የመሬት ዘርፍ በተቀመጠው ዕቅድ መሠረት ቢደራጅም ሙሉ በሙሉ ማለት በሚቻል ሁኔታ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ነዋሪዎች ቅሬታ ማንሳታቸው አልቀረም፡፡

በመሬት ተቋማት ላይ እየቀረቡ ከሚገኙ ቅሬታዎች መካከል ከዓመታት በፊት የቀረቡ የመሬት ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸው፣ ለአገር ይበጃሉ የተባሉ ፕሮጀክቶች የሚያቀርቡት የማስፋፊያ ቦታ ጥያቄዎች አለመስተናገዳቸው፣ ለዓመታት ታጥረው የተቀመጡ ቦታዎች ላይ ዕርምጃ አለመወሰዱ፣ ለጥቃቅን ጉዳዮች ሳይቀር ውሳኔ የሚሰጥ አመራር መጥፋት የሚሉት ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም የሰነድ አልባ ይዞታዎች ካርታ አሰጣጥ የተጓተተ መሆኑና ለተነሺዎች የሚሰጠው ካሳ ፍትሐዊ አለመሆኑ ከሚነሱ ችግሮች መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

አስተዳደሩ እነዚህን ችግሮች በተመለከተ ያለው አቋም በሕግ መሠረት ሊስተናገዱ የማይችሉ ናቸው የሚል ነው፡፡ አለፍ ሲልም ‹‹ችግሩን ተገንዝበናል፣ የኅብረተሰቡን ቅሬታ እንደ ግብዓት ወስደናል…›› የሚል መሆኑን ጥያቄያቸው ያልተመለሰላቸው ነዋሪዎች ይናገራሉ፡፡ የሊዝ ሕጉ በዋነኛነት መሬት የሚቀርበው በጨረታ አግባብ ነው ይልና የከተማው ከንቲባ ግን ፋይዳ ያለው ፕሮጀክት ነው ብለው ካመኑ ለካቢኔ ቀርቦ በልዩ ሁኔታ ሊስተናግድ እንደሚችል ይገልጻል፡፡

ነገር ግን ፋይዳ አላቸው ተብለው በልዩ ሁኔታ ይስተናገዳሉ የሚባሉት ፕሮጀክቶች በግልጽና በዝርዝር ባለመቀመጣቸው፣ የመሬት ቢሮ ሠራተኞች የሚቀርቡላቸውን ጥያቄዎች ለማስተናገድ ዝግጁዎች እንዳይሆኑ አድርጓል ሲሉ የሕግ ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡

በዚህ ምክንያት የከተማው የሊዝ ማስፈጸሚያ መመርያና በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው የሊዝ አዋጅ ብዙም ሥራ ላይ ሳይውሉ እንዲሻሻሉ መመርያ መሰጠቱ እየተነገረ ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ባለሀብቶች ቀደም ሲል የቀረቡት የመሬት ጥያቄዎች ሊስተናገዱ ባመቻላቸው ቅሬታቸውን ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት እያቀረቡ ይገኛሉ፡፡

የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ ጌታቸው ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ወደ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የሚያስኬዱ አንዳንድ ነገሮች መኖራቸውን፣ የሊዝ አዋጁና የሊዝ አዋጅ ማስፈጸሚያ የትርጉም ችግር ከመጣ እንደሚሻሻል ጠቅሰው፣ የመሬት አቅርቦትን በተመለከተ ግን አስተዳደሩ ትኩረት አድርጎ የነበረው ለኮንዶሚኒየምና ለ40/60 ቤቶች የሚያስፈልጉ ቦታዎችን ማቅረብ ነው፡፡ ለጨረታ የሚቀርቡ መሬቶችን በማዘጋጀት በኩል የተወሰኑ መጓተቶች እንደነበሩና በሚቀጥሉት ወራት ለጨረታ የሚቀርቡ ቦታዎች ላይ ትኩረት እንደሚደረግ አቶ አሰግድ ተናግረዋል፡፡ አስተዳደሩ በዓመቱ መጀመርያ ላይ 1,200 ሔክታር መሬት ለሊዝ ጨረታ እንደሚያቀርብ ገልጾ ነበር፡፡ ነገር ግን በእስካሁኑ ቆይታ የዚህን ዕቅድ ሩብ እንኳ ለገበያ አለማቅረቡን በርካታ ሰዎች ይናገራሉ፡፡

በመሬት ዘርፍ ችግር የነበሩ ጉዳዮችን የቀድሞ አስተዳደር ቅርፅ አስይዞታል የሚሉ በርካታ የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎችና ባለሀብቶች፣ ከከንቲባ ድሪባ ኩማ በርካታ አገልግሎቶች ቢጠብቁም እንዳልተሳካላቸው እየገለጹ ነው፡፡

<em><strong>ውኃ</strong></em>

አስተዳደሩ በግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸሙ ጥሩ እየተሠራ መሆኑን የገለጸው አንዱ ንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን በሚመለከት ነው፡፡ ንፁህ የመጠጥ ውኃ ጥልቅ ጉድጓዶችን በመቆፈርና ግድቦችን በማስፋፋት እንደሚያቀርብ ገልጿል፡፡ አስተዳደሩ ውኃን በሚመለከት በስድስት ወራት ውስጥ የሠራውን ግልጽ ሆኖ በሚታይ ሁኔታ ባያስቀምጥም፣ በጥቅሉ በበጀት ዓመቱ እየሠራቸው ያሉትንና ሊሠራቸው ያቀዳቸውን ተናግሯል፡፡ በበጀት ዓመቱ በአቃቂ 19 ጥልቅ ጉድጓዶችን እየቆፈረ መሆኑንና 80 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ ማምረቱን በሪፖርቱ ቢገልጽም ወደ ሥርጭት አልገባም፡፡ በለገዳዲ ደግሞ 11 ጥልቅ ጉድጓዶችን መቆፈር መጀመሩንና ሲጠናቀቅ 40 ሺሕ ሜትር ኩብ ውኃ ማምረት እንደሚጀምር ይናገራል፡፡ የድሬ ግድብን በማሻሻልና የለገዳዲ ማጣሪያን በማስፋፋት የውኃን ምርት ወደ 195 ሺሕ ሜትር ኩብ ለማሳደግ እየሠራ መሆኑንም በሪፖርቱ ገልጿል፡፡

በአጠቃላይ አስተዳደሩ የውኃ ምርትን በማሳደግ በኩል ከፍተኛ የሆነ ሥራ እየሠራና የጀመራቸው የጉድጓድ ቁፈራ፣ ግድብ ማስፋፋትና የክረምት ውኃ ጥበቃን በሚመለከት በኩራት እየተናገረ ቢሆንም፣ በከተማው ውስጥ እየታየ ያለው እውነታ ግን የተገላቢጦሽ መሆኑን ሁሉም ነዋሪዎች ይስማሙበታል፡፡

በከተማው በተለይ ባለፉት አራትና አምስት ወራት ውስጥ የውኃ ችግር በከፍተኛ ሁኔታ ምሬት እየፈጠረ ነው፡፡ ቀደም ባሉት ጊዜያት የውኃ እጥረት ያለባቸው የከተማው አካባቢዎች ዳገታማ ቦታዎችና ከማሠራጫ ጣቢያዎች ርቀው የሚገኙ ሲሆን፣ በአሁኑ ጊዜ ግን ከማዕከል አካባቢዎች ጀምሮ የውኃ ችግር ከፍተኛውን ቦታ ይዞ ይገኛል፡፡ የመሠረተ ልማቶች መስፋፋት ለውኃ እጥረት በምክንያትነት ቢጠቀሱም፣ ነዋሪዎች ግን አይስማሙም፡፡ አዲስ አበባ ከተማ እየሰፋች መሆኗን ሁሉም ነዋሪዎች የማይክዱት ሀቅ ነው፡፡ ነገር ግን ከከተማው መስፋፋት ጋር ተያይዞ አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ ሊሠራባቸው ከሚገቡ ነገሮች አንዱና ዋነኛው በቂ የውኃ ምርት ማቅረብ ላይ መሆኑን አንድ ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ የከተማው የውኃና ፍሳሽ ባለሥልጣን ባልደረባ ይናገራሉ፡፡ ባለሥልጣኑ በንፁህ የመጠጥ ውኃ አቅርቦትና ፍሳሽ ማስወገጃ ሥራዎች ላይ ትኩረት ሰጥቶ የሚናገረውና ለመንቀሳቀስ የሚሞክረው በበጀት ዓመቱ መጀመሪያ ወራትና በበጀት መዝጊያ ወቅት መሆኑን ሠራተኛው ይናገራሉ፡፡

የበጀት ዓመቱ ሲጀመር በተለይ ውኃ የማይደርስባቸው ቦታዎች ይመረጡና ቅድሚያ ተሰጥቶ እንዲሠሩ በሚል ብዙ ገንዘብ ወጪ እንደሚደረግ የሚናገሩት ሠራተኛው፣ ፕሮጀክቶቹ ከጅምር ቁፋሮ ሳያልፉ በኃላፊዎች የወረቀት ላይና የዓውደ ጥናት ፕሮፓጋንዳ ታጅበው በጀት ዓመቱ እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል፡፡ በጀት ዓመቱ ሊዘጋ ወር ሲቀረው፣ በተለይ ፍሳሽ ለማስወገድ በሚል የክረምቱን ጭቃ የሚያባብሱ ቁፋሮዎች በየመኖሪያ ሠፈሮች ይቆፈሩና የተረፈው በጀት እንዲጣጣ እንደሚደረግም አክለዋል፡፡ ይኼ አሠራር የተለመደና አሁንም መልኩን ቀይሮ የተለያዩ ሰበቦች እየተደረደሩ፣ ማለትም የመንገድ ሥራ፣ የባቡር ሀዲድ ዝርጋናታና ሌሎችም ምክንያቶች እየቀረቡ የኅብረተሰቡ ንፁህ የመጠጥ ውኃ የማግኘት ችግር ተባብሶ መቀጠሉን አውስተዋል፡፡

የባለሥልጣኑ ባልደረባ እንደገለጹት፣ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ እጦት ከቀናት አልፎ ወራትንም እያስቆጠረ መሆኑን እየገለጹ ናቸው፡፡ በወረቀት ላይ በሚቀርብ ሪፖርት ብቻ የከተማውን የንፁህ መጠጥ ውኃ ችግር ለመፍታት የጉድጓድ ቁፋሮና የግድብ ማስፋፋት ሥራ እያከናወነ ባለበት ሁኔታ፣ ችግሩ ከ25 እስከ 30 ዓመታት የሚወገድበትን ፕሮጀክት ዘርግቶ እየሠራ መሆኑን በስድስት ወራት ያቀረበውን የአፈጻጸም ሪፖርት ነዋሪዎች ውድቅ አድርገውታል፡፡

<em><strong>የቤቶች ልማት ፕሮግራም</strong></em>

አስተዳደሩ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰበት መሆኑን ከሚናገርባቸው ተቀዳሚ ተግባራት መካከል የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር መቅረፍ ይገኝበታል፡፡ በመሆኑም በከንቲባ ኩማ ዘመን የተጀመሩና ያልተጠናቀቁ 95 ሺሕ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ማጠናቀቅና በበጀት ዓመቱ የ65 ሺሕ ቤቶችን ግንባታ ለማስጀመር መሆኑንም መናገሩ ይታወሳል፡፡ በመሆኑም በ2003 ዓ.ም. የተጀመሩ 17,171 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታን 92 በመቶ ማጠናቀቁን ጠቁሟል፡፡ በ2004 በጀት ዓመት ደግሞ በማስፋፊያና መልሶ ማልማት በ16 የተመረጡ ቦታዎች 44,709 ነባር የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ እያፋጠነ መሆኑንም በስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸሙ ላይ አስታውቋል፡፡ ለሌሎች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች 33,593 ቤቶችን ግንባታ እያፋጠነ መሆኑንና ለ40/60 ቁጠባ ቤቶች ተመዝጋቢዎች በአራት ሳይቶች እየገነባ መሆኑን በሪፖርቱ አካቷል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን ግንባታ በሚመለከት አስተዳደሩ በቅርቡ የመሠረት ድንጋይ ያስቀመጠበትን የ50 ሺሕ ቤቶች ግንባታ ጨምሮ በጥሩ ሁኔታ እየሠራ መሆኑንና የነዋሪዎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሆነ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች ከመናገር አላረፈም፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤትን በሚመለከት የሚናገሩትና አስተዳደሩ ‹‹እየሠራሁ ነው›› የሚለው ግን የሚጣጣምና የሚገናኝ አይደለም፡፡

የመኖሪያ ቤትን ችግር ለመቅረፍ በሚል የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ጽንሰ ሐሳብ የተጀመረው በ1996 ዓ.ም. ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ የከተማው ከንቲባ በነበሩበት ዘመን መሆኑ ይታወሳል፡፡ በወቅቱ ተጋግሎ በነበረው የምርጫ 97 የምረጡኝ ቅስቀሳ ተከትሎ የመጣው የጋራ ቤቶች ግንባታ ምዝገባ፣ በአብዛኛው የከተማ ነዋሪዎች ብዙም ትኩረት አልተሰጠውም ነበር፡፡ ቢሆንም ግን በወቅቱ ከ453 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች መመዝገባቸው ይታወሳል፡፡ ለተከታታይ ዘጠኝ ዓመታት ድጋሚ ምዝገባ ሳይደረግ፣ በ1996 ዓ.ም. ብቻ ለተመዘገቡ ቤት ፈላጊዎች አንድ መቶ ሺሕ ያልሞሉ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ከሰባት ጊዜ በላይ በዕጣዎች፣ ከዕጣ በተጨማሪም በልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎችና በትዕዛዝ ለተሰጣቸው ሰዎች ተከፋፍለዋል፡፡ በ2005 ዓ.ም. መጨረሻ ወራት ላይ በተደረገው ዳግም ምዝገባ ከ800 ሺሕ በላይ ነዋሪዎች ሊመዘገቡ ችለዋል፡፡ አስተዳደሩ ምዝገባውን በአራት የተለያዩ ፕሮግራሞች ከፋፍሎ አካሂዷል፡፡ 10/90፣ 20/80፣ 40/60 እና የመኖሪያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበራት በሚል፡፡

በመኖሪያ ቤት ችግር የሚሰቃዩ ነዋሪዎች ከሚያገኙት ገቢ ላይ በየወሩ እንዲቆጥቡ በመገደዳቸው ኑሮን የከፋ ቢያደርግባቸውም፣ አማራጭ ስለሌላቸው ከልጆቻቸው የትምህርት ቤት ክፍያ፣ ከቤት ኪራይና ከቀለባቸው አብቃቅተው መቆጠቡን ተያይዘውታል፡፡ ቀደም ብሎ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት የተመዘገቡ ነዋሪዎች አስተዳደሩ በቅርቡ በዕጣ እንደሚያከፋፍል ቃል የገባውን የጋራ መኖሪያ ቤት እየጠበቁ ቢሆንም፣ አስተዳደሩ ግን ቃሉን አልጠበቀም፡፡

በዳግም ምዝገባው (ከሐምሌ እስከ ነሐሴ 2005 ዓ.ም.) ለነባር ተመዝጋቢዎች ከ17 ሺሕ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በዕጣ እንደሚከፋፈሉ፣ በድጋሚ በሚያዝያ ወር 2006 ዓ.ም. እንደሚያከፋፍል የተናገረውን ቃል በማጠፍ፣ ዕጣው የሚወጣው በሰኔ ወር ነው በማለቱ ነዋሪዎች ‹‹ድሮም እነሱን ማመን›› በማለት ቅሬታቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እየገለጹ ይገኛሉ፡፡ ሌላው አስተዳደሩ በልማት ምክንያት ለሚነሱ ነዋሪዎች የኮንዶሚኒየም ቤት ለመስጠት ቃል የገባ ቢሆንም፣ የኮንዶሚኒየም ቤቶች ግንባታ ባለመጠናቀቁ በዕቅዱ መሠረት እየሄደ አለመሆኑን የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ አምነዋል፡፡

በመሀል ከተማ በሚገኙ ቦታዎች ላይ ይገነባሉ በሚል በ40/60 ፕሮግራም የበርካታ ቤት ፈላጊዎችን ቀልብ ለመሳብ ፈልጐ የነበረው አስተዳደሩ፣ ያሰበውን ያህል ተመዝጋቢ ባለማግኘቱ በአራት ሳይቶች ላይ እየገነባ ከመሆኑ ባለፈ ብዙም የተሳካ ነገር ሲያደርግ አይስተዋልም፡፡ አዋጭነቱም ጥያቄ ውስጥ የሚገባ በመሆኑ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በማኅበር ከተደራጁት ውስጥ  እንዲካተቱ የተለያዩ ዘዴዎችን በመጠቀም ግፊት እያደረገ መሆኑም ይሰማል፡፡ በማኅበር ተደራጅቶና መሬት ወስዶ ለመሥራት የተጀመረው ፕሮግራምም የተፈለገውን ያህል እንደልሆነ እየተነገረ ነው፡፡ በአጠቃላይ አስተዳደሩ በቤቶች ልማት ፕሮግራም ላይ እያደረገ ባለው እንቅስቃሴ ባለፉት ስድስት ወራት ከወረቀት ላይ ያለፈ አርኪ ሥራ አለመሥራቱን ያመለክታል፡፡

<em><strong>የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ መቆራረጥ</strong></em>

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የቴሌኮምና የኤሌክትሪክ ኃይል መቆራረጥ የከፋ ደረጃ ላይ ደርሷል፡፡ ኤሌክትሪክ በተደረጋሚ ከመቆራረጡም በላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ላይ ለቀናት እየጠፋ መሆኑ የኅብረተሰቡ የዕለት ከዕለት ችግር ሆኗል፡፡

ኤሌክትሪክ በሚቆራረጥበት ወቅት ውኃና የቴሌኮም ኔትወርክ አብረው የሚቋረጡ በመሆናቸው ኅብረተሰቡ ለከፋ ቀውስ እየተጋለጠ ይገኛል፡፡ የኤሌክትሪክ መቆራረጥ በማይኖርበት ወቅት ጭምር ውኃና ቴሌኮም የሚቋረጡ በመሆናቸውም ችግሩን አባብሶታል፡፡

ይህንን ችግር የከተማው ነዋሪዎች በሰፊው የሚያነሱት በመሆኑ፣ አስተዳደሩ ከሁለቱ የፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በጋራ ለመሥራት ኮሚቴ አዋቅሯል፡፡

ከንቲባ ድሪባ ኩማ ባቀረቡት የስድስት ወራት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ይህንን ጉዳይ ጠቅሰዋል፡፡ የከንቲባው ሪፖርት እንደሚለው በኤሌክትሪክና በቴሌኮም ላይ የሚስተዋሉ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት ሥራዎች እየተሠሩ ይገኛሉ፡፡

የመጀመርያው የከተማው መልሶ ማልማትና ግዙፍ የልማት እንቅስቃሴ በሚካሄዱባቸው አካባቢዎች የመሠረተ ልማት (ኤሌክትሪክ፣ ውኃና ቴሌኮም) መስመሮች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡

እነዚህን ችግሮች ለመፍታት ከሁለቱ ተቋሞች ጋር የጋራ ሥራ መጀመሩ፣ ከዓለም አቀፍ ተሞክሮ (ቤንች ማርክ) በመነሳት የተለያዩ የማሻሻያ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

የከንቲባው ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ አሰግድ እንደገለጹት በየ15 ቀኑ በጋራ መድረኩ ውይይት ይደረጋል፡፡ እስካሁን ድረስ የቴሌኮም ችግርን ለመፍታት በ400 ቦታዎች ላይ የቴሌኮም አንቴናዎች መትከያ ያስፈልጋል ተብሎ፣ 327 ቦታዎችን አስተዳደሩ መስጠቱንና ቀሪዎቹ በሕንፃዎች አናት ላይ የሚተከሉ በመሆናቸው ኢትዮ ቴሌኮም ከሕንፃ ባለቤቶች ጋር እየተነጋገረበት መሆኑ ተወስቷል፡፡

የኤሌክትሪክ መቆራረጥን ለማስቀረትም የኤሌክትሪክ መስመሮችና ማስፋፊያ ጣቢያዎችን አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ ሥራዎች እየተሠሩ መሆኑን አቶ አሰግድ አክለዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በኢኮኖሚያዊና በማኅበራዊ ዘርፎች በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡበት ይገኛሉ፡፡ የኅብረተሰቡን ቅሬታ መሠረት በማድረግ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለመፍታት፣ በየወሩ ከኅብረተሰቡ ጋር የሚገናኝበትን አሠራር ከታህሳስ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. ጀምሮ መዘርጋቱን አስታውቆ ነበር፡፡

በዚህ መድረክ በየጊዜው ኅብረተሰቡ በርካታ አንገብጋቢ ጥያቄዎችን ያለማቋረጥ ከማንሳቱም በላይ፣ የአስተዳደሩ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ችግሩን ከመሠረቱ ለማድረቅ እየሠሩ መሆናቸውን ከመናገር አልተቆጠቡም፡፡

ነገር ግን ከጥቃቅን እስከ ትላልቅ የሚነሱት ችግሮች ከመፍታት ይልቅ ይበልጥ እየተተበተቡ መሄዳቸውን በተለያዩ መድረኮች እየተገለጹ ነው፡፡ በዚህም የከተማው ነዋሪዎች እርካታ እንዲያገኙ ማድረግ አልተቻለም፡፡

ነዋሪዎች እንደሚሉት ለችግሮቹ ሁሉ ቁልፍ የሆነው የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች በባለቤትነት ስሜት ሥራዎችን መሥራት አለመቻላቸው፣ ከአቶ ኩማ ጋር የከረመው አሮጌው ካቢኔ እንዳለ ሳይነካ ከአቶ ድሪባ ጋር እንዲቀጥል መደረጉ በምክንያትነት እየተጠቀሰ ነው፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በበርካታ ችግሮች የተተበተበ በመሆኑ መዋቅራዊ ለውጥና በሙያ የበለፀገ የሰው ኃይል ሥምሪት ወሳኝ መሆኑን ነዋሪዎች በአፅንኦት ይገልጻሉ፡፡
<div></div>
</div>

Hiber Radio: ገዢው ፓርቲ ለመጪው ምርጫ በሚል ደጋፊዎቼ ያላቸውን በብድር ስም ገንዘብ መስጠት ጀመረ

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 21  ቀን 2006 ፕሮግራም

 <…ገዢው ፓርቲ በጎንደር ብቻ ሳይሆን በተለያዩ አካባቢዎችም   ለሶስት ዓመት ብድር ውሰዱ እያለ ገንዘብ እየረጨ ነው። ይሄን በጥንቃቄ እየተከታተልን  ነው .. . ሰሞኑን ከአምቦ የተፈናቀሉት ዜጎች ጉዳይ የሁሉም ዜጋ የነገ ህልውና ጉዳይ ነው…  >

አቶ ዳንኤል ተፈራ የአንድነት የድርጅት  በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ተጠይቀው ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት _ዩማን ራይትስ ዎች በኢትዮጵአውያን ላይ የህወሃት አገዛዝ ተቃዋሚዎቼ ባላቸው ላይ እያደረገ ያለውን ስለላና የመብት ረገጣ አስመልክቶ ያወጣው ሪፖርት ቅኝት   (ልዩ ዘገባ)

ሺሻ የሚያስከትለው የጤና መዘዝ ከወሲብ ስንፈት እስከ ጽንስ መቋረጥ የሚያስከትላቸው የጤና ስጋቶች  (ወቅታዊ ዘገባ)

ከዓመት በፊት ለስራ ማቆም አድማ የወጡት የቬጋስ ኢትዮጵአውያንና ኤርትራውያን አሽከርካሪዎች በተመለከተ

የኢሳት የቬጋስ ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅትን የተመለከተ ቃለ መጠይቅ

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

ሕዝቡ የስርዓተን ለፖለቲካ ጠቀሜታ ሲባል እርስ በእርሰ እየተፋጀ እንዲቀጥል የሚደረገውን ሴራ በቃ ብሎ መነሳት አለበት

ገዢው ፓርቲ ለመጪው ምርጫ በሚል ደጋፊዎቼ ያላቸውን በብድር ስም ገንዘብ መስጠት ጀመረ

ኢትዮጵያዊው አርሶ አደር ለንደን ውስጥ የእንግሊዝ መንግስትን ለመክሰስ የሕግ እርዳታ አገኙ

የአረና ሊቀመንበር ትግራይ ውስጥ ለስብሰባ ቅስቀሳ እንደወጡ መታሰራቸው ተሰማ

የታሰሩ የሙስሊሙ መሪዎችን ከአገዛዙ ጋር ለማስታረቅ የሞከረው የበድር ኢንተርናሽናል ሽምግልና አለመሳካቱ ተገለጸ

የታሰሩት የሙስሊሙ ተወካዮች አንድም ጥያቄ አልተቀበሉትም

በጋምቤላ በ1993 በህወሃት የተፈጸመውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመቃወም ከአገር የወጡት የቀድሞው የክልሉ ፕ/ት ደበብ ሱዳን ላይ ታስረዋል ተባለ

የግብጹ ፓትርያርክ የአባይ ግድብ ካይሮን ይጎዳል ሲሉ ቅሬታቸውንና ተቃውሟቸውን ገለጹ

የየመን የጸጥታ ሀይሎች 21 የታገቱ ኢትዮጵያውያን ስደተኖችን አስለቀቁ

ኢትዮጵያዊው የአካል ጉዳተኛ የዓለምን ክብረ ወሰን ሰበረ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

በ ሱዳን ሀገር ውስጥ በኢትዮጽያዊያኖች ላይ ቤት ለቤት አፈሳ

የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ በደሴ ከተማ ተደበደቡ

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት

Aemero

የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ አቶ አዕምሮ አወቀ

በደሴ ከተማ የሚደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ለማስተባበር ወደ ስፍራው የተጓዙት የአንድነት ፓርቲ የሰሜን ቀጠና ኃላፊ አቶ አዕምሮ አወቀ ድብደባና ዝርፊያ እንደተፈፀመባቸው ለፍኖተ ነፃነት አስታወቁ፡፡

ዓርብ መጋቢት 19 ቀን 2006 ዓ.ም ከምሽቱ 1፡15 ላይ በደሴ ከተማ በተለምዶ ቶታል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ዕራት በልተው ሲወጡ ታርጋ የሌለውና መስታወቱ ጥቁር በሆነ ኮብራ መኪና አጠገባቸው መጥቶ ሲቆም ከውጪ ሁለት ሰዎች ገፍተው ወደ መኪናው እንዳስገቡአቸው ጨምረው አስረድተዋል፡፡ በመቀጠልም አፍና አፍንጫቸው ላይ ለጊዜው ምንነቱ ያልታወቀ ፈሳሽ ነገር ከነፉባቸው በኋላ መኪናው ተዘግተው ድብደባ ፈጸመውባቸዋል፡፡ እሳቸውም ድብደባውን ሲከላከሉና የመኪናውን መስታወት ለመስበር ሲታገሉ ደብዳቢዎቹ ከኪሳቸው ውስጥ 1735 ብር፣ የነዋሪነት መታወቂያ፣ የፓርቲው የብሔራዊ ምክር ቤት መታወቂያ ወስደው ከመኪናው ገፍትረው እንደጣሏቸው ገልጸውልናል፡፡ -


ቴዲ አፍሮ በጊዮን ሆቴል ለዳግማ ትንሣኤ ለሚያቀርበው ኮንሰርት 1.2 ሚሊዮን ብር ተከፈለው

$
0
0

teddy afro
(ዘ-ሐበሻ) የዳግማ ትንሣኤን በዓል በማስመልከት በአዲስ አበባ ጊዮን ሆቴል የሙዚቃ ኮንሰርቱን የሚያቀርበው ቴዲ አፍሮ 1.2 ሚሊዮን ብር እንደተከፈለው የቅርብ ምንጮች ለዘ-ሐበሻ ገለጹ።

በቅርቡ ሱዳን ካርቱም 2 የተሳኩ የሙዚቃ ኮንሰርቶችን አቅርቦ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሰው ቴዲ አፍሮ የዶን አርትና ፕሮሞሽን፣ ኤቢሲ ትሬዲንግ፣ ጄ አር የሙዚቃ ፕሮዳክሽን እና ኤ ፕላስ ኤቨንትስ የተሰኙት ድርጅቶች በጋራ ባስተባበሩት የጊዮን ሆቴሉ የሙዚቃ ኮንሰርት ለቴዲ የተከፈለው ገንዘብ ድምጻዊውን ከኢትዮጵያ ድምጻውያን ብቸኛው ተከፋይ ሆኖ እንዲቀጥል አስችሎታል።

ኤፕሪል 26 ቀን 2014 ወይም በኢትዮጵያ አቆጣጠር ሚያዝያ 18 ቀን 2006 ዓ.ም በሚደረገው ይኸው የጊዮን ሆቴሉ የቴዲ ኮንሰርት የመግቢያ ዋጋው ስንት እንደሚሆን ከምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ ባይኖርም በጉጉት እየተጠበቀ መሆኑ ግን በከተማው በሰፊው ይወራል።

ቴዲ አፍሮ “ወደ ፍቅር ጉዞ” በሚል በጊዮን ዝግጅቱን ካቀረበ በኋላ በሰሜን አሜሪካና በአውሮፓ ሌሎች ዝግጅቶችን ለማቅረብ እንደሚንቀሳቀስ ጨምሮ የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ ለማፋጀት የገነባውን ‘የመርዝ ብልቃጥ’በያዝነው ሳምንት በሃያ ሚልዮን ብር ወጪ ይመርቃል

$
0
0

ምርቃቱ የሩዋንዳው የዘር ማጥፋት ግጭት ከተጀመረበት 20ኛ ዓመት ጋር ገጥሟል።ባጋጣሚ ወይስ ታስቦበት?

ጉዳያችን
መጋቢት 22/2006 ዓም

ኢትዮጵያን እየመራ የሚገኘው ኢህአዲግ/ወያኔ የኢትዮጵያን ሕዝብ ከቀን ወደ ቀን እርስ በርሱ እንዳይተማመን፣እንዲነቃቀፍ፣እንዲጠራጠር ከእዚህ ባለፈ ደግሞ ግጭት እንዲፈጠር እያደረገ 22 ዓመታትን ዘለቀ።ህዝቡ እለት ከእለት በገዢው መንግስት የሚወጠኑለትን የእርስ በርስ ማጋጫ ተንኮሎች እየተመለከተ ልቦናው በእጅጉ እየደማ ነው።

አንድ ወራሪ የውጭ ጠላት ሊሰራ የሚችለውን ያህል ህዝብን ከሕዝብ ጋር የማጋጨት ሥራ ኢህአዲግ/ወያኔ በትክክል ሰርቶበታል። የሃገሪቱን ፌድራል አስተዳደር በየትኛውም ዓለም ያልታየ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ደገሰላት።ፌድራላዊ አስተዳደር በዘመናዊው ዓለም አንዱ እና አማራጭ የአስተዳደር ዘይቤ ይሁን እንጂ በየትኛውም ሀገር መሰረት የሚያደርገው የመልክዓ ምድርን አቀማመጥ እና ታሪካዊ አሰፋፈርን ነው። እርግጥ ነው ጣልያን ሀገራችንን በወረረ ዘመን አሁን ወያኔ የሚጠቀምበትን የክልል አስተዳደር የመሰለ ቋንቋን መሰረት ያደረገ የአስተዳደር መዋቅር ዘርግቶ ነበር።

አንዳንዶች የአሁኑ ቋንቋን መሰረት ያደረገ አስተዳደር የብሔር ብሄረሰቦችን መብት ከማስከበር አንፃር የሚመስላቸው የዋሃን አይጠፉም።ግን ፈፅሞ አላማው ይህ ላለመሆኑ ብዙ ማስረጃ መጥቀስ ይቻላል።እርግጥ ነው የህዝብ ባህል ማለትም ቋንቋው፣አለባበሱ፣ታሪኩ ወዘተ ሊጠበቅለት እና ከለላ ማግኘት አለበት።ይህ ከለላ በማግኘት መብት  ስም ወንጀል ሲሰራ፣ቁርሾ በባትሪ እየተፈለገ ሲራገብ እና ሕዝብን ከሕዝብ ለማጋጨት ሲውል ነው ወንጀሉ።

ኢህአዲግ/ወያኔ ሕዝብ እርስ በርሱ በጎሳ ሲጋጭ መፍትሄ ለመፈለግ ከመነሳት ይልቅ ጉዳዩን ሲያባብስ እና ቤንዚን ስያርከፈክፍ ማየት ለኢትዮጵያ ሕዝብ ዕለት ከዕለት የሚመለከተው ድራማ ሆኗል። ለእዚህም ብዙ አብነቶችን መጥቀስ ይቻላል። ለእዚህ ፅሁፍ ግን ሁለት ምሳሌዎችን እንጥቀስ -

1/  በዩንቨርስቲዎች ውስጥ ወጣቶች ‘አንተ የእገሌ ነህ አንተ የእንቶኔ ነህ’ ተባብለው ፀብ ሲነሳ ጉዳዩ የመጪው ትውልድ እና የአሁኑ ትውልድ አደገኛ አቅጣጫ ነው ብሎ የችግሩን ስር ለመፍታት ከመጣር እና የጉዳዩን አስከፊነት  በመገናኛ ብዙሃን ከመግለፅ እና ከማስተማር ይልቅ ፖሊስ ይልቁን ከአንድኛው ወገን ቆሞ ሌላውን ሲያስር እና ሲቀጣ መመልከት ዘግናኝ ተግባር ነው።

2/ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት የእርሻ ቦታ ”የእገሌ ዘር ነህ” ተብሎ በክልል መስተዳድሮች ጭምር ሲባረር ለጉዳዩ እንደ መንግስትነት ለመዳኘት ሳይሆን የሚሞከረው እንደ ቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ አባባል ”ቀድመው ባልተወለዱበት ሀገር መስፈር የለባቸውም” እንደ አቶ አለምነህ የብአዴን ቢሮ ምክትል ኃላፊ ደግሞ ”የትዕቢት ልጋግ” ነው የሚሉ መልሶችን መስማት እራስ ያማል።መሪዎቻችን እንዲህ እያሉ ከጉርዳፈርዳ እስከ አሶሳ፣ከአሶሳ እስከ ሐረር፣ ከሐረር እስከ ጅጅጋ፣ ከጅጅጋ እስከ ቦረና ጉጂ፣ ድረስ በብዙ አስር ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን በኢህአዲግ/ወያኔ የጎሳ ፖለቲካ ተሰደዱ፣ተገደሉ።ይህ ሁሉ ሲሆን ግን መንግስት ጉዳዩን እንደ ትልቅ ችግር ሳይሆን እንደ አንድ የማስተዳደርያ ዘዴ እንደቆጠረው በ እርግጠኝነት መረዳት ይቻላል።

በያዝነው ሳምንት  በሃያ ሚልዮን ብር ወጪ የሚመረቀው የመርዝ ብልቃጥ 

Arsi Oleno

በአርሲ ዞን በሂቶሳ ወረዳ ከሃያ ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያሰራውን  ”አኖሌ ሐውልት” እና ሙዝዬም

የእርስ በርስ ግጭቶች ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲሻገሩ የሚጥረው ኢህአዲግ/ ወያኔ ለእርስ በርስ ጦርነቶች እየመረጠ ሃውልት ሲሰራ ከርሞ በእዚህ ሳምንት ደግሞ ለየት ያለ የጥፋት ድግስ የሚሆን ከመቶ አመታት በፊት ለመፈፀሙ ምንም አይነት የታሪክ ማስረጃ የሌለው በዳግማዊ ምኒልክ ዘመን በአርሲ ዞን በሂቶሳ ወረዳ ተፈፅሟል ያለውን የታሪክ ምሁራን ያላረጋገጡትን የፈጠራ ታሪክ ከሃያ ሚልዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ያሰራውን  ”አኖሌ ሐውልት” እና ሙዝዬም  በእዚህ በያዝነው ሳምንት እንደሚመረቅ ኢቲቪ ዛሬ መጋቢት 22/2006 ዓም የዜና እወጃው ላይ አስታወቀ።የፈጠራው ታሪክ ከመቶ ዓመታት በፊት የአፄ ምኒልክ ሰራዊት የኦሮሞ ሴቶችን ጡት ቆርጦ ነበር እና ማስታወሻነቱ ለተቆረጡት ጡት እና እጅ ይሁን” ይላል የሃውልቱ የመሰራት ምክንያትን ኦህዴድ /ኢህአዲግ/ወያኔ ሲናገር። አሳዛኝ የደረስንበት የዝቅጠት ዘመን።በየትኛውም ሀገር ውስጥ በቀደሙ መሪዎች ያውም ከመቶ አመታት በላይ ለሆነው ታሪክ ቀርቶ የቅርቦቹም ቢሆን ለተሰሩ ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች ለመጪው ትውልድ የሚያቆይ የእልቂት ድግስ ከፋች ሃውልት አይሰራም። የሚጠጣ ውሃ፣ የምበላው ምግብ ለሌለው ሕዝብከ 20 ሚልዮን ብር በላይ አውጥቶ መበተን ምን የሚሉት ፈልጥ ነው?

አንድ መንግስት ሕዝብ ከህዝብ ጋር አብሮ የሚኖርበትን ዘዴ ሲቀይስ ልዩነትን እያጎላ ሳይሆን አንድነትን እያሳየ እና እያጎላ ሕዝብ በፍቅር እና በስምምነት እንዲኖር ይጥራል እንጂ እንዴት ከአሁኑ ትውልድ አልፎ ለመጪው ትውልድ ቂም ለማውረስ ተግቶ ይሰራል? ይህ ተግባር ማንን ይጠቅማል? ለመሆኑ ያለፉ ነገስታት በወቅቱ በነበረው የቅጣት መንገዳቸው ሁሉ የቀጡትን የቅጣት አይነት እየዘረዘርን ሃውልት ብንሰራ የቱን ከየቱ እንመርጣለን?

የሃውልቱ ምርቃት እንደ ትልቅ የሀገር ልማት ዛሬ ኢቲቪ ቀድሞ ዛሬ ይናገረው እንጂ ወቅቱ የሩዋንዳው እልቂት የተጀመረበት 20ኛ አመት ጋር ገጥሟል።በሚያዝያ 7/1994 ዓም  እስከ ሐምሌ/1994 ዓም እ ኤ አቆጣጠር የቆየው በቱትሲዎች እና በሁቶዎች መካከል የተደረገው እልቂት ከአምስት መቶ ሺህ በላይ ሕዝብ ሕይወት ቀጥፏል።የሩዋንዳው እልቂት በአንድ ሌሊት ድንገት የደረሰ ጉዳይ አይደለም።በሂደት አልፎ አልፎ በተነሱ ቁርሾዎች ጥርቅም ሳብያ መሆኑን መዘንጋት አይገባም።የዛሬ የባለ ሃያ ሚልዮን ሃውልት ገንቢዎችም ሆኑ አስገንቢዎች መዘንጋት የሌለባቸው  በሰሩት ሥራ ሁሉ የሚጠየቁበት ቀን እንደሚመጣ መጠራጠር አይገባም።የመርዝ ብልቃጡም ይሰበራል የፍርድ ቀኑም ይቆረጣል።

ጉዳያች-gudayachn.blogspot.com/
መጋቢት 22/2006 ዓም

ነጻ መብራት፣ ስልክ እና ውሃ በካሳ መልክ ሊሰጥ ነው (ዳዊት ከበደ ወየሳ)

$
0
0
(ዳዊት ከበደ ወየሳ) 
በመብራት መቆራረጥ የሚሰቃየው የኢትዮጵያ ህዝብ “እፎይ” የሚልበትን ቀን ሁሉም ይናፍቃል። የአባይ ወንዝ ከተገደበ በኋላ የሚመነጨው የኤሌክትሪክ ሃይል ከኢትዮጵያ አልፎ ለሱዳን እና ለግብጽ እንደሚበቃም ይነገራል። ከዚህ ግድብ በተጨማሪ የግልገል ጊቤ 2 እና 3 ፕሮጀክት ሲጠናቀቅ ኢትዮጵያ የሚኖራት የመብራት ሃይል በአስር እጥፍ እንደሚጨምር የዘርፉ ሙያተኞች ይመሰክራሉ።
በዚህ አጋጣሚም በመብራት መቆራረጥ እና እጦት የሚሰቃየውም ህዝብ የሚካስበት አጋጣሚ ይፈጠራል። መብራት ሃይል ዛሬ ያወጣው መግለጫ እንዳረጋገጠው ከሆነ፤ “እስካሁን መብራት ያጣውን የኢትዮጵያ ህዝብ ነጻ የኤሌክትሪክ ሃይል ወይም ግምቱ ታውቆ በጥሬ ገንዘብ ካሳ ይከፈለዋል።” ተብሏል። የቴሌኮምዩኒኬሽንም በበኩሉ የመብራት ሃይልን ተነሳሽነት አድንቆ በቴሌም በኩል እስካሁን በኔት ዎርክ መቆራረጥ ሲሰቃይ የነበረውን ህዝብ ለመካስ፤ በኢትዮጵያ የሚሰራውን “አባ ዱላ” የሚል ስያሜ የተሰጠውን የስልክ ቀፎ ለደንበኞቹ በነጻ እንደሚሰጥ ወይም ከመቶ እስከ 1ሺህ ብር ዋጋ የሚያወጡ ሲም ካርዶችን የሚያድል መሆኑን አሳውቋል።
የመብራት ሃይል እና የቴሌን ካሳ አከፋፈል ያደነቀው የውሃ ሃብት ልማት በበኩሉ በሸገር ሬድዮ ሰበር ዜና አሰምቷል። ሰበር ዜናውን ያነበበው አለምነህ ዋሴ ሲሆን፤ “አስደሳች ዜና ለውሃ አፍቃሪዎች” በማለት ነበር ዜናውን የጀመረው። በመቀጠልም… የውሃ እና ሃብት ልማት ሚንስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው ከሆነ፤ “በቅርቡ ውሃን በፕላስቲክ እየሞላን የመሸጥ ፈቃድ ከፌዴራሉ መንግስት ተቀብለን ስራችንን ለመጀመር በዝግጅት ላይ ነበርን። የገፈርሳ የአባ ሳሙኤል እና የቀበና ውሃዎችን እያጣራን ለህዝቡ ጓዳው ድረስ በቧንቧ አቅርበንለታል። አሁን ግን የመብራት እና የቴሌን ፈለግ በመከተል ህዝቡን ለመካስ ተነስተናል። አባይ ይገደባል፣ ህዝቡም ነጻ ውሃ ያገኛል።” ብለዋል። በዚህም መሰረት የውሃ እና ሃብት ልማት በቅርቡ እያሸገ የሚሸጣቸውን የፕላስቲክ ውሃዎች ለደንበኞቹ በነጻ የሚሰጥ መሆኑን ገልጾ፤ ይህንን የሚያስተባብሩ እና የሚያድሉ ሰራተኞቹ ወደ መንደሮች እና ኮንዶሚኒየሞች ሲመጡ፤ ህብረተሰቡ አንድ ለአምስት በመሆን አስፈላጊው ትብብር እንዲያደርግላቸው የባለልጣኑ መስሪያ ቤት አደራ ብሏል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ፤ “ወንዞች ይገደቡ ይዋሉ ለልማት” በሚለው የድሮ የደርግ ዜማ በመታጀብ ዜናውን ለህዝብ አቅርቦ የነበረው ሰይፉ ፋንታሁን ባልታወቁ ታጣቂዎች መታገቱ የ-ኢትዮፒሊንካ አዘጋጅ የሆነው ብርሃኔ ለዝግጅት ክፍላችን ገልጿል። እንደብርሃኔ አባባል ከሆነ፤ “ሰይፉን ያገቱት… ይህን የመሰለ ዜና… እንዴት በደርግ ዜማ አጅበህ አቀረብክ በማለት ነው። እንደአሰራር የሰይፉን ድርጊት ብንቃወምም የአጋቾቹን ድርጊት ግን አጥብቀን አውቅዘናል። ይህንንም ድርጊት በመቃወም ለጠቅላይ ሚንስትሩ ቢሮ ደብዳቤ ጽፈናል።” ብሏል።
እኛም ዜናችንን ከማጠናቀቃችን በፊት “እንኳን ለዛሬው April Fool በሰላም እና ጤና አደረሳቹህ እንላለን።” ከላይ በApril Fool ስም ዜናውን እናቅርብ እንጂ እውነት ይህ ህዝብ በአንድም ሆነ በሌላ መንገድ መካስ እንዳለበት እናምናለን።

ሕወሓት በምርጫ 2007 በትግራይ ክልል ሊሸነፍ እንደሚችል አመነ

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

Arena-Tigray-logoዓረና ፓርቲ በትግራይ ክልል ወረዳዎች በመዘዋውር ባሰብሰበው መረጃ መሰረት በ2007 በሚደረገው ሀገራዊ ምርጫ ገዥው ፓርቲ የህዝብን ድምፅ ካከበረ ህወሓት በመላው ትግራይ ሙሉ በሙሉ ይሸነፋል። አንድ የህወሓት የስራ አስፈፃሚ አባል (ለግዜው ስሙ ይቅር) በዓዲግራት ከተማ ለተሰበሰቡ ከምስራቃዊ ዞን የተውጣጡ የህወሓት ካድሬዎች “እናንተ በምትፈፅሙት በደል ምክንያት በ2007 ምርጫ እንሸነፋለን። ግን አንዳንድ የምናደርጋቸው ነገሮች ስለሚኖሩ ሙሉ በሙሉ ተስፋ አትቁረጡ። ለራሳችሁ ዕጣ ፈንታ ስትሉ በደንብ ስሩ” ማለቱ ታውቋል። ካድሬዎቹም “በናንተ (የላይኞቹ አመራሮች) ችግር ነው የምንሸነፈው፤ ህዝብ የማይቀበለውን ነገር እንድናሳምን ታስገድዱናላቹ” የሚል መልስ በመስጠታቸው የእርስበርስ ንትርክ መከፈቱ ታውቋል። ከስብሰባው በኋላ ካድሬዎቹ የንትርኩ ነጥቦች ለዓረና አባላት አስረድተዋል።

በዓረና እንቅስቃሴ የሰጉ የህወሓት መሪዎች ህዝብን በገንዘብ መደለል ጀምረዋል። ባሁኑ ግዜ የትግራይ ህዝብ በህወሓቶች በሦስት ደረጃዎች ተከፍሎ ግሬድ ተሰጥቶታል። ግሬድ A, B ና C። ግሬድ “A” ታማኝ የህወሓት ካድሬ፣ ግሬድ “B” መሓል ሰፋሪ፣ ግሬድ “C” ተቃዋሚ (ዓረና)። በዚሁ መሰረት ህወሓትን ለማገልገል ፍቃደኛ የሆነ ሰው (ታማኝ ካድሬ A) ለስብሰባ ይጠራና የማዳበርያን ዕዳ ለመክፈል የሚያግዘው 3000 ብር የውሎ አበል ተብሎ ይሰጠዋል። 3000 ብር ከተቀበለ በኋላ ተቃዋሚዎችን ይታገላል፣ ህወሓት እንዲመረጥ ያግዛል፣ ታማኝ የህወሓት አገልጋይ ይሆናል። ለህወሓት ታማኝ ያልሆነ ለስብሰባ አይጠራም፤ ገንዘብም አይሰጠውም። በ3000 ብር የምርጫ ድምፅ መግዛት ይሉታል እንዲህ ነው። የምርጫ ድምፅ እየተገዛበት ያለ ገንዘብ የህወሓት ሳይሆን በግብር መልክ የተሰበሰበ የመንግስት ገንዘብ ነው። መንግስት ብር አነሰኝ እያለ ግብር እየጨመረ ነጋዴዎች ንግዳቸውን ይዘጋሉ። ህወሓቶች ደግሞ የሰበሰቡትን ገንዘብ ለምርጫ ጅንጀና ይጠቀሙታል።

(ከዚህ ቀደም የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች - ፎቶ ከአብርሃ ደስታ) - ፎቶ ፋይል

(ከዚህ ቀደም የአረናን ሕዝባዊ ስብሰባ እንዳይሳተፉ የተከለከሉ የሽሬ ነዋሪዎች – ፎቶ ከአብርሃ ደስታ) – ፎቶ ፋይል

የትግራይ አርሶአደሮች እንደዚህ በፖለቲካ ታማኝነት በዉሎ አበል መልክ ገንዘብ እየተሰጣቸው የማዳበርያ ዕዳቸውን መክፈል ከቻሉ ጥሩ ነው። ባንዳንድ አከባቢዎች ግን የዉሎ አበሉ መጠን ይለያያል። ለምሳሌ በደቡባዊ ምስራቅ ዞን ለየት ያለ አጋጣሚ ተፈጥሯል። ህወሓቶች በሁሉም ዞኖች እንደሚያደርጉት ሁሉ ታማኝ የተባሉ (ለምርጫ ሊያገለግሉ የሚችሉ) 200 የሳምረ አርሶአደሮች መለመሉ። አርሶአደሮቹ ሲመለመሉ “ለስብሰባ ትሄዳላቹ፣ 3000 ብር አበል ይሰጣችኋል፤ ስለዚህ 3000 ብሩን ለማግኘት በመጪው ሰኔ ላይ ለምትወስዱት ማዳበርያ 1200 ብር አሁን ክፈሉ” ይሏቸዋል። አርሶአደሮቹም 3000 ብሩን ለማግኘት 1200 ብር እንደምንም ብለው ከፈሉ። ከሳምረ ለስብሰባ ተብሎ ወደ ሕዋነ ተወሰዱ፤ ፖለቲካ ተጀነጀኑ። በመጨረሻ እነሱ 3000 ብር እየጠበቁ 640 ብር ብቻ እንደሚሰጣቸው ተነገራቸው። ከ640 ም 600 ው መቆጠብ አለባቹ በሚል ሰበብ በህወሓቶች እጅ ሲቀር 40 ብር ብቻ ለትራንስፖርት ተሰጣቸው። አርሶአደሮቹ አሁን ቅሬታቸው አካፍለውናል።

አዎ! የህዝብ ድምፅ ከተከበረ ዓረና ሙሉ በሙሉ ያሸንፋል። እናም ህወሓቶች በሰለማዊ መንገድ ስልጣን ያስረክባል። የህወሓት ካድሬዎችም መብታቸው ተጠብቆላቸው በሰላም በሀገራቸው ይኖራሉ። ከፈለጉ በመንግስት መስራቤት በሙያቸው ተቀጥረው ይሰራሉ፣ ወይም ህወሓት ተቃዋሚ ፓርቲ አድርገው ለሚቀጥለው ምርጫ ለመወዳደርና ለማሸነፍ ይሞክራሉ። በሰለማዊ መንገድ ስልጣን ለማስረከብ ካልፈለጉ ግን በሃይል እስኪወገዱ ድረስ በስልጣን ይቆያሉ። በሃይል ከተሸነፉ እንደ የደርጎቹ ከሀገር ተጠርገው ይባረራሉ፤ የደርግ ባለስልጣናት ዕጣ ፈንታ ይቀምሳሉ።
ስልጣን ለህዝብ እናስረክብ፤ ሰለማዊ የስልጣን ሽግግር ይኑር። ስልጣን ለህዝብ ካላስረከብን ግን ሌላ ታጣቂ ሃይል ይነጥቀዋል። ከዛ ስልጣን ባላንጣን መምችያ ዱላ ይሆናል። ዱላው ከህዝብ ጋር መሆን አለበት።

==================
ሰላማዊ ሰልፍ በደርግና ህወሓት

“የትግራይ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ከተነፈገ እነሆ 22 ዓመታት አለፉ” ብዬ ለፃፍኩት “ከ22 ዓመታት በፊት ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ ይፈቀድ ነበር እንዴ? በደርግ ግዜስ ሰለማዊ ሰልፍ ይፈቀድ ነበር ማለት ነው?” የሚል ጥያቄ መጣብኝ።

የደርግ ዘመን በትግራይ ክልል የጦርነት ግዜ ነበረ። በጦርነት ግዜ ሰለማዊ ሰልፍ አይፈቀድም። በደርግ ግዜ ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ በህገመንግስት የተደነገገ መብት አልነበረም። በደርግ ዘመን ስርዓት አልነበረም። ደርግ ትግራይን አልተቆጣጠረም ነበር። ግማሹ የትግራይ መሬት በደርግ ወታድሮች ቁጥጥር ሲሆን ግማሹ ደግሞ በህወሓቶች እጅ ነበረ (ሓራ መሬት ትግራይ)። ስለዚህ አንድ መንግስት የዜጎችን መብት ለማስከበር መጀመርያ ስርዓት መመስረት አለበት። በሁሉም አከባቢዎች አስተዳዳራዊ ስራና ቁጥጥር ሊኖረው ይገባል። ደርግ በትግራይ አስተዳዳራዊ ቁጥጥር አልነበረውም። የዜጎችን መብት ለማስከበር ሕገመንግስት መደንገግ አለበት። በደርግ ግዜ ሕገመንግስት አልተደነገገም ነበር ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ደርግ ወታደራዊ መንግስት ነበርና። ወታደራዊ መንግስት ሕግ አያከብርም፤ ስለ ስልጣኑ እንጂ ስለ ህዝብ መብት አይጨነቅም።

ስለዚህ የትግራይ ህዝብ ሰለማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱ ተነፈገ ሲል በደርግ ግዜ መብቱ ተከብሮለት ነበር ማለቴ አይደለም። መልእክቱ ህወሓትም ከደርግ እሻላለሁ፣ ደርግን አስወግጄ የህዝብ መብት አስከብራለሁ፣ ነፃነት እፈቅዳለሁ እያለ የትግራይን ህዝብ ድጋፍ አሰባስቦ ቤተመንግስት ከገባ በኋላ ሌላ ደርግ ሆነብን ለማለት ተፈልጎ ነው።

ህወሓት ራሱ ከደርግ ጋር ማወዳደር ቢተው ጥሩ ይመስለኛል። ምክንያቱም በደርግ ግዜኮ (በትግራይ ማለቴ ነው) ስርዓት አልነበረም። የደርግ ዘመንኮ የጦርነት ዘመን ነው የነበረው። ስለዚህ አንድ መንግስትነት ተቆጣጥርያለሁ የሚል ስርዓት ራሱ ከጦርነት ዘመን ጋር እንዴት ያወዳድራል? ህወሓት ራሱ መፈተሽ ያለበት አሁን መስራት ካለበትና መስራት ከሚጠበቅበት አንፃር መሆን አለበት።

በሐዋሳ ከተማ 2 ትምህርት ቤቶች በቋንቋ የተነሳ ብጥብጥ ተነስቶ ሰዎች ቆሰሉ

$
0
0

hawasa federal policeከዳዊት ሰለሞን

በሀዋሳ ከተማ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚማሩ የሲዳማ ተወላጆች የሚኒ ሚዲያ ፕሮግራም በሲዳመኛ ቋንቋ ይተላለፍ፣ ታቦር 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የሚለውን ታፔላ በሲዳመኛ ቋንቋ ይጻፍ በሚል መነሻና ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ረብሻ ተፈጥሮ የፌደራል ፖሊሶች ወደ ግቢው ሲጠጉ ተማሪዎቹ ድንጋይ በመወርወር በርካታ ፖሊሶች ቆስለዋል፡፡ ፖሊሶቹ በወሰዱት ርምጃ ብዙዎች ለጉዳት ተዳርገዋል፡፡

በሐዋሳ ከተማ በሚገኙ ሁለት የከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ የሚገኙ ተማሪዎች እንደቀሰቀሱት በተገመተ ረብሻ ከፍተኛ ጉዳት በተማሪዎችና በአስተማሪዎች ላይ መድረሱ ተሰምቷል፡፡

የትምህርት ቤቱ የመማሪያ ቋንቋ እንዲለወጥ በጠየቁ የኦሮሞ ተወላጆችና በሲዳማ ተወላጆች መካከል ረብሻው መቀስቀሱን ከስፍራው ያናገርኳቸው ሰዎች በስልክ ገልጸውልኛል፡፡ ረብሻውን ለማብረድ ፖሊሶች መሳሪያ መተኮስ በመጀመራቸውም የተጎዱ ሰዎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ተገምቷል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ሐዋሳ ውስጥ የተኩስ ድምጽ ያለ ማቋረጥ እንደሚሰማም ምንጮች ተናግረዋል።

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>