Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

የሠማዕታት ጥሪ (ኢሕአፓ))

$
0
0

EPRPበተለያዩ ምክንያቶች የምትወዱትንና ዘወትር ከአዕምሮአችሁ ለአንድ አፍታም ቢሆን የማይጠፋውን ድርጅታችሁ ኢሕአፓን ራሳችሁን አግልላችሁ  ወይንም ያላግባብ እንድትገለሉ ተደርጋችሁ የቆያችሁ የዛ ጀግና ትውልድ የኢሕአፓ/ኢሕአሠ፣ ኢሕአወሊ አባላት፣ አካላትና ደጋፊዎች ለነበራችሁ በሙሉ  ኢሕአፓዊ ሠላመታችን ይድረሳችሁ።”  —ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ—–


የቅማንት ብሄረስብ ተወላጆች ደብዳቤ ለጎንደር ሕዝብ (በሰሜን አሜሪካ ከምንኖር የቅማንት ብሄረሰብ ተዎላጆች)

$
0
0

Gondorውድ ወገኖቻቸን፤ በመጀመሪያ “ታሪክን ከሥሩ፤ መጠጥን ከጥሩ” እንዲሉ፤ ለዛሬ ይህችን መልክት አዘል መጣጥፋቸን ለናንተ ለማቅረብ ሥንነሳ፤ ለተነሳንበት ቁምነገር ትርጉም ይሰጥ ዘንድ በአባቶች ምሳሌ  ጀመርን። በመሆኑም፤ ትኩረታችን እና መነሻችን፤ የኢትዮጵያችን ሰሜናዊ ክ/ሀገር የሆነችው ጎንደር ላይ  ሲሆን፤ መድረሻችን ደግሞ፤ በዚሁ ክ/ሀገር የሚኑሩትን እጅግ ረጅም ታሪክ ያላቸውን የቅማንት  ብሔረሰብ ወገኖቻችን ወቅታዊ ችግር መሰረት ያደረግ ነው።    —ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ—–

Hiber Radio: ኢትዮጵያ ከሰሜን ኮሪያ በምስጢር መሳሪያ መግዛቱዋ ተሰማ

$
0
0
የህብር ሬዲዮ ሚያዚያ 12  ቀን 2006 ፕሮግራም
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<<…ኢትዮጵያውያን የፋሲካን በዓል በውጭ አገር ስናከብር በአገር ቤት በዓሉን በደስታ ለማሳለፍ ያልቻሉ ኑሮው የከበዳቸው እንዳሉ መርሳት የለብንም…>>

ብዑዕ አቡነ ዮሴፍ የኔቫዳ፣የአሪዞናና ዩታ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

ላሊበላ በውጭ ጎብኒ እይታ  

ኦቲዝም ምንድነው? እውን ልጆቻችንን አውቀን በጊዜ ተገቢውን ቴራፒ እንዲወስዱ እናደርጋለን?

በኦቲዝም ውስጥ ያሉ ልጆች ያሏቸው ልጆች ወላጆች ምን ይላሉ?

ሰናይት አድማሱ የስነ ልቦና ባለሙያ እና  

ወ/ሮ ፌበን ፋንቱ ወላጅ ከሎስ አንጀለስ ማብራሪያ ሰጥተውናል (ክፍል ሁለት ሙሉውን ያዳምጡ)

 የጋዜጠኛ ነብዩ ሲራክ ማስታወሻ ከሳውዲ እስር ቤት  

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

የኬንያ መንግስት 65 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በአልሸባብ ስም አሰረ

በሳውዲ 3ሺህ ኢትዮጵያውያን የሚማሩበት ት/ቤት በቆንስላው ቸልተኝነት የመማር ማስተማሩ ሂደት እየተስተጓጎለ ነው

መምህራን የስራ ማቆም አድማ አድርገዋል

ግብጽ ለደቡብ ሱዳን በራሷ ወጭ ግድብ ልስራ አለች

ኢትዮጵያ ከሰሜን ኮሪያ በምስጢር መሳሪያ መግዛቱዋ ተሰማ

በአገር ቤት የዘንድሮም የበዓል ገበያ የዋጋ ንረት የታየበት ነበር

ኢትዮጵያዊቷን የሆቴል አስተናጋጅ ለመድፈር የሞከረ የሳውዲ ዜጋ በነጻ ተለቀቀ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

ሰማያዊ ፓርቲ ለእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ በመኪና ቅስቀሳ ጀምረ

$
0
0

ፖሊስና የደህንነት አባላት የሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ አካባቢ የሚገኘውን ህዝብ በር እያንኳኩ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲን በድምጽ ብክለት ክሰሱት!›› እያሉ እየቀሰቀሱ ነው፡፡ ነገር ግን አብዛኛዎቹ የሰፈሩ ነዋሪዎች ‹‹እስካሁን አልረበሹንም፣ ሊረብሹንም አይችሉም፡፡›› እያሏቸው ነው፡፡
ከዚህ በፊት ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ በዝግጅት ላይ እያለ አመራሮቹ ጃን ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ በታሰሩበት ወቅት ፖሊስ ‹‹ህዝቡ ነው የድምጽ ብክለት አድርሰውብናል በሚል›› የከሰሳችሁ ማለቱ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ መሠረት ለእሁዱ የተቃውሞ ሰልፍ በአዲስ አበባ ጎዳናዎች የመኪናው ቅስቀሳ ጀምሯል፡፡ የመጀመሪያው ቡድን ለቅስቀሳ ወጥቷል፡፡
semayawi 1

semayawi 2

ሰበር ዜና –የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች ታገቱ

$
0
0

ethiopia-blue-party-300x164በአሁኑ ወቅት ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አቶ ስለሽ ፈይሳ እና የህዝብ ግንኙነቱና የሰላማዊ ሰልፍ አስተባባሪ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ብርሃኑ ተክለያሬድን አግቷቸዋል፡፡ አመራሮቹ የታገቱት ከፓርቲው ጽ/ቤት ወጥተው የእግር ጉዞ እያደረጉ  በነበሩበት ወቅት ነው፡፡

እስካሁን ድረስ በፖሊስ መያዛቸው የታወቁ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት

  የታገቱ አመራሮች
1.      ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት -የፓርቲው ሊቀመንበር
2.      ስለሽ ፈይሳ- ምክትል ሊቀመንበር
3.      ብርሃኑ ተክለያሬድ-የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ
4.      ዳዊት ጸጋዬ
5.      አወቀ ተዘራ
6.      ኢብራሂም አብዱሰላም
7.      ሁሴን
8.      ሙሉጌታ መኮንን
 ጉለሌ ፖሊስ መምሪያ የታሰሩ
1.      ዮናስ ከድር
2.      እየሩስ ተስፋው
3.      እመቤት ግርማ
4.      የሽዋስ አሰፋ
5.      አበራ
6.      አበበ መከተ
 ካሳንቺስ ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት
1. ብሌን መስፍን
2. አስናቀ በቀለ
3. መስፍን
4. ተስፋዬ አሻግሬ
5. እዮብ ማሞ
6. ኩራባቸው
7. ተዋቸው ዳምጤ
  የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የሚገኙት
1. ፍቅረ ማሪያም አስማማው
2. እያስፔድ ተስፋዬ
3. ጋሻው መርሻ
4. ተስፋዬ መርኔ
5. ሀብታሜ ደመቀ
6. ዘሪሁን ተስፋዬ
7. ጌታነህ ባልቻ
8. ንግስት ወንዲፍራው
9. ሜሪን አለማየሁ ናቸው

ሸዋ ከፍርድ ቤት በኋላ ተናገረ፡ “ጃኪ ድል አላደረገም፤ ኮንሰርቱ ቢፈቀድም የፍርዱ ሂደት ይቀጥላል”– $500,000 ይፈልጋል

$
0
0

Shewa
(ዘ-ሐበሻ) በሸዋ ኢንተርቴይመንት እና በድምፃዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ዙሪያ ባለው አለመግባባት ዛሬ ፍድር ቤት ቀርበው፤ ሸዋ ኢንተርቴይመንት ያቀረበው የኮንሰርቱ ይቁም ጥያቄ በፍርድ ቤቱ ውድቅ እንዳደረገው ዘ-ሐበሻ ጠዋት ላይ ዘግባ እንደነበር ይታወሳል። ጃኪ ጎሲ ከፍርድ ቤቱ የኮንሰርቱ ይደረግ ውሳኔ በኋላ በፌስቡክ ገጹ “እውነት ወጣች” ሲል ሲገልጽ ሸዋ ኢንተርቴይመንት ባለቤት አቶ ሸዋ ኢተና በበኩሉ “ጃኪ ድል አላደረገም፤ ኮንሰርቱ ቢደረግ በሕይወታችሁ ላይ የሚያደርስባችሁ ጉዳት ምንድን ነው? በሚል ዳኞቹ ኮንሰርቱ እንዲደረግ ቢፈቅዱም፤ ገና የፍርድ ቤቱ ሂደት መታየት ጀመረ እንጂ አላለቀም” ሲል ለዘ-ሐበሻ ገልጿል። በቀጣይ ቀጥሮዎች ፍርድ ቤቱ ጉዳዩን ማየት እንደሚጀምር የገለጸው ሸዋ የ500 ሺህ ዶላር ካሳ ጥያቄ እንዳቀረበም ለዘ-ሐበሻ አረጋግጧል።

አጭሩን ቃለምልልስ ያድምጡ፤ ጃኪ የሚሰጠውን ምላሽ ዘ-ሐበሻ ትጠብቃለች።

ሰበር ዜና- እስካሁን ድረስ ሰባት Ethiopian Online Activists and Bloggers በፖሊስ ታድነው ታስረዋል

$
0
0

Abrha Destaእስካሁን ድረስ ሰባት Ethiopian Online Activists and Bloggers በፖሊስ ታድነው ታስረዋል። ዘላለም ክብረት፣ ማህሌት ፋንታሁን፣ በፈቃዱ ሀይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ፣ ተስፋአለም ወልደየስና ኤዶም ገላን። የኢህአዴግ ፖሊስ እያደናቸው ይገኛል። የታሳሪዎች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። አሳዛኝ የአምባገነኖች እርምጃ! It is so!!!

ከኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

የጋዜጠኞቹና የአክቲቪስቶቹ እስር አሳሳቢ ነው፡፡

EJFትላንት ሚያዝያ 17 2006 አመሻሽ ላይ ዞን 9 በተሰኘ ድረ ገጽ (ብሎግ) ላይ በሳል ፖለቲካዊና ማህበራዊ  ትችቶችን በማቅረብ ከሚታወቁት ፀኀፍት መሀከል 7 ቱ (ማህሌት ፋንታሁን በፍቃዱ ሀይሉ ናትናኤል  ፈለቀ ዘላለም ክብረት አጥናፍ ብርሀነ አቤል ዋበላ ኤዶም ካሳዬ ) እና የአዲስ ነገር ባልደረባ የነበረው  ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ በመንግስት የጸጥታ ሀይሎች በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ይታወቃል፡፡
ግለሰቦቹ በተለያየ ቦታ በየስራ ገበታቸዉ ላይ እያሉ ሁሉም በተመሳሳይ ሰ ዓት በፀጥታ ሀይሎች ተይዘዉ በማዕከላዊ ምርመራ ማዕከል ታስረዉ የሚገኙ ሲሆን፤ የተለያዩ መረጃዎች እንደሚጠቁሙት እስሩ  በደንብ የታሰበበት ነበር፡፡  የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ታሳሪዎቹ ታሰሩ ከተባለበት ሰዓትና ደቂቃ ጀምሮ የሚገኙበትን አጠቃላይ ሁኔታ ለማጣራት አየሰራ ሲሆን ፤ እስካሁን በሰበሰበዉ መረጃ መሰረት ልጆቹን ለእስር የሚያበቃ ምን  አይነት ማስረጃ እንደተገኘባቸው ለማወቅ አልቻለም፡፡
ሆኖም ግን ለእስር ከመዳረጋቸው በፊት ከመንግስት ሲርስባቸዉ በነበረዉ ህገወጥ ድርጊቶች ምክንያት ለረጅም ጊዜ ስራቸዉን ካቋረጡ በኋላ በቅርቡ ወደ ስራ መመለሳቸዉን ይፋ አድርገው እንደነበር  ከድረገጻቸው ላይ ለመረዳት ችለናል፡፡ ይህ ጉዳይ እስሩን ይበልጥ አሳሳቢ አድርጎብናል፡፡
ስለሆነም የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መንግስት ታሳሪዎቹን ለማሰር ያበቃዉ ተጨባጭ ማስረጃ ካለ  ለህዝብ ይፋ እንዲያደርግ፤ ያ ካልሆነ ግን እስረኞቹን በአስቸኳይ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲለቅ  እናሳስባለን፡፡
የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ

 


የጃኪ ጎሲ የሕግ አማካሪ ተናገሩ፡ “ሸዋ ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮን፣ ሔኖክ አበበንና ጆኒ ራጋን ከሷል”፤ በሸዋ ላይ የ$400,000 ካሳ ክስ አቅርበናል

$
0
0

የጃኪ ጎሲ የሕግ አማካሪ ተናገሩ፡ “ሸዋ ከዚህ ቀደም ቴዲ አፍሮን፣ ሔኖክ አበበንና ጆኒ ራጋን ከሷል”፤ በሸዋ ላይ የ$450,000  ካሳ ክስ አቅርበናል
(ዘ-ሐበሻ) ከደቂቃዎች በኋላ የጃኪ ጎሲ የዋሽንግተን ዲሲ ኮንሰርት ከመጀምሩ አስቀድሞ ከዘ-ሐበሻ ጋር ቃል የተመላለሱት የጃኪ ጎሲ የህግ አማካሪ የሆኑት አቶ መንግስቱ አስፋው የፍርድ ሂደቱ የጃኪ የሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቶች ከመደረጋቸው በፊት ቢጠናቀቅ እንኳ የሌሎች ከተማዎችን ኮንሰርቶች ምንም የሚያሰጋ ነገር እንደለሌለና በተሳካ ሁኔታ እንደሚደረጉ አስታወቁ። የሕግ አማካሪው “ለጃኪ ክስ መከላከያዎችን ስናሰባስብ ከዚህ ቀደም ሸዋ ኢንተርቴይመንት በቴዲ አፍሮ፣ በሄኖክ አበበና በጆኒ ራጋ ላይ ክስ መመስረቱን ማስረጃውን አግኝተናል” ካሉ በኋላ በተለይም ሄኖክ አበበና ጆኒ ራጋ በዋሽንግተን ዲሲ በሸዋ የተነሳ የደረሰባቸውን ሸዋ የጃኪን ኮንሰርትም ለማሰናከል 11ኛው ሰዓት ላይ ክስ መመስረቱን በማስታከክ አብራርተዋል።

ሸዋ ኢንተርቴይመንት በፍርድ ቤት የጃኪን ስም በመጥፎ ነገር እንዳያነሳ ተነግሮት እያለ በዘ-ሐበሻ ላይ ወጥቶ የተናገረው በሕግ ሊያስጠይቅ እንደሚችል የጠቆሙት አቶ መንግስቱ የጃኪ ኮንሰርትን ለማሰናከል ባደረገው ጥፋት እስከ 400 ሺህ ዶላር በሚጠጋ የካሳ ክፍያ በሕግ ጠይቀነው ጉዳዩ በፍርድ ቤት ተይዟል ብለዋል። ሸዋ ኢንተርቴይመንትም በተመሳሳይ የ$500 ሺህ ዶላር የካሳ ክፍያ ክስ መመስረቱን ለዘ-ሐበሻ መግለጹ ይታወሳል። አቶ መንግስቱ በጃኪ ጎሲና ኢቫንጋዲ ፕሮዳክሽንን ወክለው ለዘ-ሐበሻ የሰጡትን ቃለምልልስ ይከታተሉት።

ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ተጠናቀቀ፤ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ “ውሃ ጠማን”አለ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ በአዲስ አበባ ከተማ የጠራውን ‘የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ” ሰላማዊ ሰልፍ በብዙ አፈና ታጅቦ ማጠናቀቁን ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። በተደጋጋሚ በዚህ ሳምን በድረገጻችን ላይ እንደዘገብነው የዛሬውን ሰላማዊ ሰልፍ ለማሳካት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት በአዲስ አበባ ከተማ ቅስቀሳ በሚያደርጉበት ወቅት እስር እና እንግልት ሲደርስባቸው ቆይቷል።

ዛሬም መነሻውን ከፓርቲው ጽ/ቤት ተነስቶ በአዋሬ፣ አድዋ ድልድይ፣ ባልደራስ አድርጎ መድረሻው ወረዳ 8 ሜዳ የካ ሚካኤል ታቦት ማደርያ ባደረገው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ፖሊስ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ የማንገላታትና የማሸማቀቅ ሥራዎችን ሲሰራ እንደነበር የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ጠቁመዋል።

በአዲስ አበባ ያለውን የመብራት እጦት፣ የትራንስፖርት፣ የውሃ እጦት፣ የኔትወርክ እጥረትና ሌሎች የማህበራዊ ቀውሶችን ያስተጋባው የዛሬው የሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከተሰሙት መፈክሮች መካከል
“ውሃ ጠማን ውሃ ጠማን”
“ፍትህ ናፈቀን ፍትህ ናፈቀን”
“ውሽት ሰለቸን ውሽት ሰለቸን”
“የሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ባስቸኳይ ይፈቱ”
“በቀለ ገርባ አሽባሪ አይደለም”
“ኦልባና ለሌሳ አሽባሪ አይደለም”
“አቡበክር አሸባሪ አይደለም”
“አንዷለም አራጌ አሽባሪ አይደለም”
“እስክንድር ነጋ አሽባሪ አይደለም”
“ናትናኤል መኮንን አሽባሪ አይደለም”
“ርዮት አለሙ ጋዜጠና እንጂ አሽባሪ አይደለችም” የሚሉና ሌሎችም ድምጾች ከሰልፉ ተሳታፊዎች ተደምጠዋል።

በተለይም ተሰላፊው “እኛ ኢትዮጵያኖች አንለያይም፤ እኛ ኢትዮጵያኖች አንድ ነን” የሚሉና “የተነጠቁ መብቶቻችን ይመለሱልን” ሲሉ ጩኸታቸውን ያሰሙ ሲሆን መንግስት የለም ወይ? እያሉም ሲጮኹ ነበር።

በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉትና በቅስቀሳው ወቅት ታስረው ባለፈው አርብ ማምሻውን የተለቀቁት ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለሰልፈኛው “ወደ ሰልፉ የመጡትን እና ስልፉን ያስተባበሩትን ወጣቶች እና መላውን ባለ መብት ተሳታፊ አመሰግናለሁ። ስርዓቱ በሙስና ተጨማልቋል፡፡ አገራችን አደጋ ላይ ወድቃለች፡፡ ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር ሆነን እጣ ፈንታችን እንወስን። በየትኛውም አገር አምባገነን እንዲሁ ለሕዝቡ መብት አይሰጥም። አስፈላጊውን መስዕዋትነት መክፈል አለብን” ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ቀጥለውም “ከ19 አመት ጀምሮ እስከ 63 አመት ያሉት አባላትና አመራሮቻችን ታስረዋል፡፡ ክርስቲያኖች፣ ሙስሎሞች ወጣቶች፣ ኢንጅነሮች፣ ሌሎቹም ታስረውብናል። ይህም የኢህአዴግ አምባገነንነት ያሳያል፡፡ ሰማያዊ ለሁሉም የህዝብ ክፍል እንደሚቆምም በዚህ ሰልፍ የታሰሩት አባላትና አመራሮቻችን ማሳያ ናቸው ነው። ክብርና ፍርሃት፣ ማጎብደድ የኢትዮጵያውያን ባህል አይደለም፡፡ ማሸነፍን ያስተማርን ህዝቦች ነን፡፡ ሙስሊም ክርስቲያኑ በጨዋነት አብሮ የሚኖርባት አገር ናት፡፡ እነሱ ግን ይከፋፍሉናል፡፡ አሁን በአዋራጅ ሁኔታ ላይ እንገኛለን። ይህን ለማስቆም ከእነአስፈላጊው መስዋትነት ሌት ተቀን እንሰራለን” በማለት ንግግራቸውን አስመተዋል።

የሰልፉን ሁኔታ የሚያሳውን ፎቶዎች ይመልከቱ
addis ababa semayawi
blu paty8

addis ababa semayawi

blue paty 7

blue party 6

blue party 5

blue party 4

blue party 2

blue 6

“እኛም ከሚሊዮኖቹ ውስጥ ነን” (የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ))

$
0
0

PDF-  ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

ሚ ሚያዝያ 19፣ 2006 (ኤፕሪል 27፣ 2014)

የኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል ሸንጎ (ሸንጎ)፣ በአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)  እየተቀነባበረ በሚካሄደው “የሚሊዮኞች ድምፅ” ንቅናቄ ውስጥ “እኛምከሚሊዮኞቹ ውስጥ ነን” በማለት ለተጀመረው እንቅስቃሴ ሙሉ ድጋፉን እንደሚሰጥ ሲገልጽ በታላቅ ደስታ ነው። በዚህም መሠረት የዚህ እንቅስቃሴ አካልነታችንንበተግባር ለመግለፅ በአዳማ (ናዝሬት) የሚካሄደውን እንቅስቃሴ በስፖንሰርነት ለመደገፍ ዕድሉ ስለገጠመን እጅግ ደስተኛ ነን።

ሸንጎ በተደጋጋሚ እንደገለጸው፣ በሀገራችን ውስጥ የሰፈነው የግፍ፣ የአድልዖና የከፋፋይነት ሥርዓት ማብቃት አለበት።  ሥርዓቱ የሀገሪቱን ሕዝብና ሁሉንም የሀገሪቱን አካባቢ በከፍተኛ አደጋ ላይ ጥሏል። ኢትዮጵያን የባሕር በር የሌላት ከማድረግ ጀምሮ ዜጎቿን እርስ በርስ በጥርጣሬ እንዲተያዩ  አልፎም እያንዳንዱ ዜጋ ያለፍትኅ እየተጎተተ የሚታሠርበት፣ የሚደበደብበት፣ ከሥራና ከንብረቱ የሚፈናቀልበት ሀገር እስከመሆን ደርሰናል። ገዥው ቡድንና ሥርዓቱ የሚመራበት ፖሊሲና ተግባሩ እንኳንስ ለአብዛኛው ኢትዮጵያዊ ቀርቶ፣ ለራሱ ለሥርዓቱ ደጋፊዎች የማይበጅ እንደሆነ ሁሉም የሚገነዘበው ነው።

ይህ አስከፊ ሁኔታ እንዲያከትምና በሕጋዊና ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲተካ ለማድረግ ደግሞ በአንድ በኩል የተቃዋሚ ድርጅቶች ተሰባስበው የተቀነባበረ ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ ሲገባቸው በሌላ በኩል ደግሞ ኢትዮጵያውያን ሁሉ የተጀመሩትን አበረታች እንቅስቃሴዎችን በተግባር እንዲያጠናክሩ ይጠበቃል። በዚህ መልክ ስንሰባስብና ሃላፊነት በመውሰድ ትግሉን ስናጠናክር የወገኖቻችን ስቃይና በሀገራችን ላይ የተጋረጠው አደጋ ማብቂያና የብሩኅ ተስፋ ዘመን መጀመሪያ ጊዜ እጅግ የቀረበ ይሆናል።

ለዚህ ነው ሸንጎው በኢትዮጵያ ሀገራችን አንድነት የሚያምኑትን የተቃዋሚ ኃይሎች በጋራ እንድንሰባሰብ ደግሞ ደጋግሞ የሚጠራው። ለዚህም ነው ሸንጎ “እኛምከሚሊዮኞቹ ውስጥ ነን” በማለት በአንድነት አቀነባባሪነት የተጀመረውን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ የሚደግፈው። ለዚህ ነው ሸንጎው ሁሉም ኢትዮጵያዊ የዚህ የነፃነት ትግል አካልነቱንና አጋርነቱን በተግባር እንዲያሳይ  በቀጣይነት የሚጥረውና የሚያበረታታው።

አንድነት ኃይል ነው!

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ!

 
shengo

ጃኪ ጎሲ ተሾመ አሰግድን ይቅርታ ጠየቀ

$
0
0

jacky teshome
በApril 24, 2012 ዓ.ም የዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ዕትም ላይ ዝነኛው ድምጻዊ ተሾመ አሰግድ “በጠራራ ጸሐይ ተዘረፍኩ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝ” ሲል ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ካለፈቃዴ “የኔ አካል” የሚለውን ተወዳጅ ዘፈኔን ወስዶ ተጫውቷል በተቃውሞ ነበር። ከጊዜ በኋላ ድምጻዊ ጃኪ ጎሲ በጆሲ ሾው ላይ በመቅረብ “ከዚህ በኋላ ተሾመ ይህን ዘፈን የኔ ነው ብሎ መጠየቅ አይችልም፤ ለዜማና ግጥም ደራሲዎቹ ከፍዬበታለሁ” ሲል ተናግሮ እንደነበርም ይታወሳል።

ጃኪ ወደ ሰሜን አሜሪካ ሲመጣ ይታየው የተባሉ ጸሐፊ “ድምጻዊ ጎሳዬ ቀለሙ (ጃኪ ጎሲ) ከተሾመ አሰግድ ለወሰደው ዘፈን ይቅርታ ይጠይቅ ይሆን? ወይስ ማን አለብኝነት ያልፈዋል?” ሲሉ ተሾመ ከዚህ ቀደም የሰጠውን ቃለምልልስ በመጥቀስ አስተያየት ጽፈው ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ሙዚቃ ኮከብነት እየተጓዘ የሚገኘው ጃኪ ይህን አስተያየት በብልህነት የተመለከተው ይመስላል። በዚህም መሠረት ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ ባደረገው የመጀመሪያው የሰሜን አሜሪካ ኮንሰርቱ ላይ ሰው ባልጠበቀው ሁኔታ ዝነኛውን ድምጻዊ ወደ መድረክ በማምጣት አብሮት “የኔአካል” የሚለውን ተወዳጅ ዘፈን ካቀነቀኑ በኋላ ድምጻዊ ጃኪም ካለፍቃዱው ወስዶ በመስራቱ ይቅርታ ጠይቋል። ጨምሮም ዘፈኑን የሰራው ከመውደዱ የተነሳ እንደሆነ ገልጿል። አርቲስት ተሾመ አሰግድም “እዚህ ሃገር ሰንመጣ መንገዱን ያሳየን ሰው አልነበረም። ጥረታችን የቀድሞ ሙዚቃኞቻችን ውለታ እንዲህ በቀላል እንዳይረሳ ሙዚቃዎቹን ስትጫወቱ በፈቃድ ጥያቄ ጠይቃችሁ ተጫወቱ። [የኔ አካል] ከኔ በበለጠ ጃኪ ተጫውቶታል። አብልጦ ነው የተጫወተው፤ ሞቅ አድርጉለት” ብሎ አርቲስቱም ይቅርታውን ተቀብሏል። ጃኪም የሕዝብ ድምጽን ማድመጡ፤ ከምንም በላይ ይህን ስመጥር አርቲስት በመድረክ ጋብዞ እንዲታወስ በማድረጉ ዘ-ሐበሻ አድናቆቷን በዚህ አጋጣሚ እየገለጸች፤ አንባቢዎች በዘ-ሐበሻ የተጀመረው የጃኪና የተሾመ ጉዳይ መቋጨቱን በዚህ አጋጣሚ እንገልጻለን። መልካም የሥራ ዘመን ለሁለቱም።
የይቅርታውን ስነስርዓት ቪዲዮ ይመልከቱ

የግርጌ ማስታወሻ ጥቂት ስለስመጥሩ አርቲስት ተሾመ አሰግድ፦
በኢትዮጵያ ስመ-ጥር ከሆኑ ድምጻዊያን መካከል የሆነውና ብዙዎች “ኢትዮጵያዊው ስቲቭ ዎንደር” የሚሉት ተሾመ አሰግድ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በመስከረም ወር 1945 ተወልዶ በተወለደ በ5 ወሬ ዓይነ ስውር መሆኑን በዘ-ሐበሻ ጋዜጣ ቁጥር 2 ላይ በሰጠው ቃለ ምልልስ መናገሩ ይታወሳል። የመጨረሻ ካሴቱን ካወጣ 17 ዓመት ያለፈው ይህ ድምጻዊ እስካሁን ስንት ካሴቶችን ሰርተሃል በሚል ጥያቄ አቅርበንለት “ጥቂት ካሴቶችን አውጥቻለው:: ትዝታና ባቲ በሚባለው የሙዚቃ ቅኝት በፊሊፕስ አሳታሚነት በ1960ዎቹ አንድ ሸክላ አውጥቼ ነበር:: ከዛ በተረፈ ያልተሳካለት አንድ ካሴት ሰርቼ ነበር:: ከዛ ወዲህ ግን ጅቡቲ ለ5 አመታት ከቆየው በሗላ ከሮሀ ባንድ ጋር በመሆን ‘የኩባያ ወተት”ን ሰራሁኝ:: ይበልጥ ከሕዝብ ጋር ያስተዋወቀኝም ይሄ ሥራ ነው:: በሌላ በኩል ከነራሄል ዮሐንስ; አሰፉ ደባልቄ እና ኬኔዲ መንገሻ ጋር አንድ ካሴት; እንዲሁም ከማርታ አሻጋሪ; በዛወርቅ አስፋው እና ኤልያስ ተባባል ጋር በመሆን አንድ ኮሌክሽን ሰርቼ ነበር:: በራሴ በኩል 2ኛውን ሙሉ ካሴቴን “ደርባባዬ’ን አውጥቼ ነበር:: ብዙም በሕዝብ ዘንድ አልገባም:: ግን አልፎ አልፎ ሰዎች ያውቁታል::” ሲል መልሷል።

መንግስት በደቡብ ጉራጌ ዞን ከእምድብር ከተማ ወጣቶች ጋር በስተርጅና “ሌባና ፖሊስ”ጨዋታ እየተጫወተ ይገኛል

$
0
0

በደቡብ ክልል በጉራጌ ዞን ቸሃ ወረዳ እምድብር ከተማ ላይ የፋሲካ ማግስት ማታ የደቡብ ክልል ልዩ ሀይሎች ከከተማው ወጣቶች ጋር ግጭት ውስጥ ገቡ።
Gurage Kilele
በፋሲካ ማግስት አምሽተው ወደ ቤታቸው በመግባት ላይ ከነበሩ ወጣቶች ከወልቂጤ—ሆሳዕና መንገድ የመልሶ ግንባታ በማካሄድ ላይ የሚገኘውን የCGGC ካምፓኒ ንብረት ለመጠበቅ ከተመደቡ የደቡብ ክልል ልዩ የፖሊስ ሀይሎች ጋር በተፈጠረ አለመግባባት ፖሊሶቹ ወጣቶቹን መደብደብ ሲጀምሩ ወጣቶቹ ባሰሙ የይድረሱልኝ ጩኸት የከተማው ሰው በብዛት በመውጣት ለማረጋጋት ሲሞክር ፖሊሶቹ ተኩስ በመክፈት እስከ 12 ጥይት የተኮሱ ቢሆንም በተኩሱ የተጎዳም ሆነ የሞተ ሰው የለም።

ፖሊስ ለምን ይህን እርምጃ እንደወሰደ ሲጠየቅ “በጥበቃ ላይ በነበርንበት ወጠቶቹ መጥተው ድንጋይ ወረወሩብን” በማለን ምክንያታቸውን ሲገልጹ ወጣቶቹ በበኩላቸው ይህ ሆን ብሎ የተቀነባበረና የአካባቢው ወጣቶች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ከመንገዱ ጋር ተያያዥዥ የሆኑና ሌሎች ልማታዊ መብቶችን በመጠየቃችን የወረዳው አመራሮች በማቄማቸው እና ይህን የመብት ጥያቄ በማጠልሸን የጥያቄዎቻችንን መልክ ማስለወጥ በመፈለጋቸው የተሸረበ ሴራ ነው በማለት ሲገልፁ በአካባቢውም የነበሩ የአይን እማኞች አንድ ማንነቱ ያለኙት ወጣት ከአንድ ሹፌር ጋር ተጣልቶ ለሱ የወረወረው ድንጋይ ወደ ፖሊሶቹ አልፎ ድንጋዩ ሳይገባ እዳልቀረ ግምታቸውን ያስቀምጣሉ።በማያያዝም በወቅቱ ድለኘንጋይ ወርዋሪው ሮጦ ሲያመልጥ በወቅቱ በመንገዱ ሲያልፉ የነበሩ ልጆችን ይዘው ሲደበድቡ ድንጋይ ተወረወረበት የተባለው ሹፌር ወደ ፖሊሶች በመምጣት ወርዋሪው ጓደኛው እንደሆነና ድንጋዩንም የወረወረው እየተቀላለዱ እንደነበበር ሲገልፅላቸው እንደሰሙ አክለው ገልፀዋል።

በአሁን ሰዓት 4 የከተማው ወጣቶች በዕለቱ ተይዘው ወልቂጤ ከተማ እሚገኘው አበሽጌ ወረዳ ፖሊስ ጣቢያ የተወሰዱ ሲሆን በወቅቱ ግርግሩ ሲፈጠር በቦታው ያልነበሩ ወጣቶችን ፖሊስ ለመያዝ እንቅስቃሴ ሲያደርግ መረጃው ቀድሞ የደረሳቸው ወጣቶች ከተማዋን ትተው በመውጣት ለስደት ተዳርገዋል።

በወረዳዋ እጅግ ዘርፈ ብዙ አስተዳደራዊ ችግሮች እንዳሉ የወረዳዋ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ሲገልፁ ይደመጣሉ።ከነዚህም ውስጥ በተለያየ ጊዜ በሚሾሙ ባለስልጣናት የተመዘበረው ከግብአት ገቢ መሆን ያለበት ከ3.4 ሚሊየን ብር በላይ በመመዝበሩ ወረዳዋ ባለ ዕዳ በመሆኗ የመንግስት ሰራተኞች ከሌላው ወረዳ በተለየ ከ10—20 ቀናት ዘግይተው ደሞዝ እንደ ሚወስዱና ይህን ተከትሎ እጅግ ብዙ ሰራተኞች እንደሚፈልሱ ይታወቃል።

የኢትዮጵያ እስር ቤቶች ከሕሊና እስረኞች ነጻ መሆን አለባቸው !

$
0
0

UDJ Headየኢህአዴግ ፖለቲካ ዜጎችን የማሰር፣ ዜጎችን የማሸበር ፖለቲክ ነው። በቅርቡ በዞን ዘጠኞችና ጋዜጠኖች ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ የሚያሳየው፣ አገዛዙ ሃሳብን በሃሳብ መመከት ሲሳነው የሃይል እርምጃ ለመዉሰድ ወደ ኋላ የማይል መሆኑን ነው።

ኢሕአዴግ ሽብርተኝነትን ለመከላከል ሳይሆን፣ ሰላማዊ ዜጎችን ለማሸበር ሲል ያወጣዉ የጸረ-ሽብርተኝነት ሕግ እንዲሰረዝ በመጠየቅ፣ የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ ማድረጉ ይታወሳል። በአገሪቷ ክፍሎች ያሉ ሚሊዮኖች፣ አገዛዙ ዜጎችን በማሸበር እንዲያቆም ቢጠይቁም፣ አገዛዙ፣ የሕዝብን ጥያቄ በመናቅ ፣ አሁንም ኢትዮጵያውያን እየታሰሩ ናቸው። አሁንም የግፍ ቀንበር በሕዝባችን ላይ እየተጨነ ነው።

የአንድነት አባላት፣ ዜጎች ሃሳባቸውን በነጻነት በመግለጻቸው የማይታሰሩባት ኢትዮጵያን ለመገንባት፣ የታሰሩት ያለ አንዳች ቅድመ ሁኔታ እንዲፈቱ ለማድረግ ይታገላል። በተለያዩ እስር ቤቶች የታሰሩ ወገኖቻችን፣ አገዛዙ እንደሚለው ሽብርተኞች ሳይሆኑ ፣ «ለመብታቸው፣ ለነጻነትናቸውና ለአገራቸው ክብርና አንድነት የቆሙ፣ ብርቅዬ የኢትዮጵያ ጀግኖች ናቸው» ብሎ ነው የሚያምነው።

የታሰሩ እስረኞችን ለማበረታታት፣ ለነርሱም መፈታት አንድነት ያለዉን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ፣ ሚያዚያ 19 ቀን 2006 ከፍተኛ የአንድነት አመራር አባላት በሶስት እስር ቤቶች (ቃሊቲ፣ ቂሊንጦና ዝዋይ) አመርተው ነበር።

የአንድነት ሊቀመንበር ኢንጂነር ግዛቸው ሽፈራው፣ አቶ አስቻለው እና አቶ አክሉ ግርግሬ በቃሊት እስክንደር ነጋ፣ ርዮት አለሙን እና አንዱዋለም አራጌን ለመጎነብኘት የሄዱ ሲሆን፣ ርዮት አለሙን እና እስክንደር ቢያገኙም አንድዋለምን ማነጋገር አትችሉም ተብለዉ ተመልሰዋል። ርዮት አለሙ፣ በአካል ጤንነቷ በጥሩ ሁኔታ ላይ ባይገኝም፣ በመንፈሷ ግን በጣም ትልቅ ጥንካሬ እንደሚታይበት ለማረጋገጥም ችለዋል።

በአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሃፊ፣ አቶ ስዩም ነገሻ የሚመራ ቡድን ደግሞ ወደ ቂሊንጦ እሥር ቤት ነበር ያመራው። ከአቶ ስዩም ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የነበሩ ሲሆን፣ በዚያም የታሰሩ ሰላማዊ የሙስሊም ችግር መፍተሄ አፍላላጊ ኮሚቴ አባላትን አግኝተው አነጋግረዋል።

የአንድነት ሁለቱ ሊቀመናብርት አቶ ተክሌ በቀለን እና አቶ በላይ በፍቅዱን፣ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊው አቶ ዳንኤል ተፈራን፣ የሕዝብ ግንኙንተ ክፍል ሃላፊው አቶ ሃብታሙ አያሌውን፣ ደራሲና የአንድነት ደጋፊ አቶ አስራት አብርሃ ያቀፈ ወደ ሃያ የሚጠገ የአንድነት አባላትና ደጋፊዎች ቡድን ፣ ወደ ዝዋይ በማምራት በዚያ ከሚገኙ በርካታ እስረኞች ጋር ሰፊ ዉይይት አድርጓል። ናትናኤል መኮንን፣ አንድዋለም አያሌው፣ ዉብሸት ታዬ፣ ጀነራል አሳምነው፣ ሻምበል የሺዋስ፣ በቀለ ገርባ፣ ኦልባና ለሌሳ፣ አበበ ቀስቶ ..እንዲሁም በርካታ እስረኞች ለማነጋገር ተችሏል።

«እኛ በአካል ብንታሰርም፣ በመንፈሳችን ነጻ ሰዎች ነን። ነጻነት ያለ ትግል፣ ነጻነት ያለ ዋጋ አይገኝም። እኛ ዋና እየከፈልን ያለነው ለነጻነትና ለኢትዮጵያ ነው። ሁሉም ኢትዮጵያዊ ከፍርሃት፣ ከዝምታ፣ ከራስ ወዳድነት ተላቆ የድርሻዉን ለማበርከት ይዘጋጅ» ሲሉም፣ የሕሊና እስረኞች፣ ለኢትዮጵያውያን መልክት አስተላልፈዋል።

የአንድነት ፓርቲ የፊታችን ሚያዚያ 26 ቀን በአዲስ አበባ የ«እሪታ ቀን» በሚል ሰላማዊ ሰልፍ እንደጠራ ይታወቃል። በዚህ ሰልፍ ከዉሃ፣ መብራት፣ ትራንስፖርት ችግር በተጨማሪም፣ በቃሊቲ፣ በቂሊንጦና በዝዋይ ለታሰሩ ጀግኖቻችን፣ እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ የአገዛዙ የግፍ በትር ላረፈባቸውና በማእከላዊ ለሚገኙት ለዞን ዘጠኝ ወጣቶችና ጋዜጠኞች ያለንን አጋርነት የምንገልጽበት አጋጣሚ ተመቻችቷል።

ኑ ፣ እንነሳ ! ድምጻችንን እናሰማ ! የግፍ አገዛዝ በቃን እንበል ! ከሚሊዮኖች አንዱ እንሁን !

በኢሕአፓ ዙሪያ ለታገሉ ኃያሎች በሙሉ የትንሣኤ ጥሪ ቀረበ

$
0
0

April 2014
የትንሳኤ ጥሪ

ጋዜጣዊ መግለጫ

ዉድ ወገኖቻችን !
ኢሕአፓ ከተመሰረተ ይሄዉና አርባ ሁለት አመቱን አስቆጠረ ።ለድርጂቱ መመስረት ዋና ዋና ናቸዉ የሚባሉት የሕዝብ የሥልጣን ባለቤትነት ጥያቄና የመሰረታዊ መብቶች ጥያቄ ግን አሁንም መልስ አላገኙም፣ እንዲያዉም ከመሰረታዊ የሕዝብ መብቶች ጥያቄ ባሻገር ባደጋ ላይ የወደቀዉን የሃገር ሉዓላዊነት ጥያቄ ለመመለስ ትግል ግድ እየሆነ መጥቶአል።

ዛሬ ኢሕአድግ/ወያኔ በሚከተለዉ የፖለቲካ መስመር ምክንያት እየተበረታቱ በቋንቋና በሃይማኖት ክልል ተሰባስቦ መደራጀት በመስፋፋት ላይ ነዉ።በዚህም ምክንያት ጥራት ያለዉና ጠንካራ ሁሉንም የሕብረተሰብ ክፍሎች በማሰባሰብ ትግሉን የሚመራ ድርጅት ጎልቶ ሊወጣ አለመቻሉ አሳዛኝ ክስተት ሆኗል።

ያ ትዉልድ በኢትዮዽያዊነቱ በመኩራት ለመላዉ የኢትዮዽያ ህዝብ መብት መከበር ያደረገዉ ትግል እንደ ትልቅ ትዝታ በየቦታዉ የሚነሳ ቢሆንም ከመሰዋአትነት የተረፉት የዚያ ትዉልድ አካሎች በልዩ ልዩ ምክንያት አሁንም እየተከፋፈሉ በመምጣታቸዉ “ምነዉ የጀመሩትን ትልቅ አላማ ከግቡ ለማድረስ ተቻችለዉ ትግላቸዉን አይቀጥሉም? የከፈሉት መሰዋአትነት ሳያንስ ለምን ታሪካቸዉን አያስከብሩም? ምነዉ ተክቶን ታጋይ አልፎአል የኛም ትግል ይቀጥላል ፣ልጔዝ በድል ጎዳና በተሰዉት ጔዶች ፋና”እያሉ በመዘመር የገቡትን ቃል ኪዳን ለምን ከፍፃሜ አያደርሱም?” በማለት የሚጠይቀዉ የሕብረተሰብ ክፍል ቀላል አይደለም።

በተለይም ደግሞ አዲሱ ትዉልድ እንደ ዓረዓያ ሆኖ የሚታይ ኃይል ከፊቱ ማየት በመፈለጉ ከዚያ ቅን አገርና ወገን አፍቃሪ ትዉልድ ከፍተኛ ሥራ ሲጠብቅ ከግምት በታች ሆኖ መገኝቱ ለህሊና ሰላም የሚሰጥ ጉዳይ ሆኖ አልተገኝም። አዎ ምንም እንኳን የመከፋፈል ችግር ቢገጥመዉም በኢሕአፓ ሥም ተሰልፈዉ የሚታገሉ ሐይሎች እንዳሉ ሁላችንም የምናዉቀዉ ገሀድ ነዉ።በሌላ በኩል ደግሞ ከድርጂት ዉጭ ሆነዉ ለትገሉና ለድርጂቱ በነበራቸዉና አሁንም በላቸዉ ቀና አመለካከት ልባቸዉ የሚቃጠል በጣም በርካታ የዚያ ትዉልድ አካሎች መኖራቸዉ የሚካድ አይደለም።

ታዲያ ይህን ሁኔታ የተገነዘብን የዚያ ትዉልድ አካሎች ያን ጀግና ኢትዮጲዊ ትዉልድ እንደገና አሰባስቦ መንቀሳቀስ ቢቻል ለኢትዮዺያና ለኢትዮዺያዉያን ትልቅ ጥቅም ያስገኛል የሚል ሙሉ እምነት ስለአለን ይህን ስብስብ ጀምረናል።

ይህ እንቅስቃሴ ለዚያ ባለራዕይ ትዉልድ የትንሳኤ ጥሪ ከመሆኑም ባሻግር አዲሱን ትዉልድ በተአምር ከመስዋእትነት ከተረፈዉ ከዚያ ትዉልድ ጋር እንደ ድርና ማግ አስተሳስሮ ለአገር ሉዓላዊነትና ለመላዉ ህዝብ መብት መከበር ሁሉንም የኢትዮዺያ ልጆች የሚያሳትፍ እንደ ጎሞራ እሳት የሚቀጣጠል ትግል ለመፍጠር አስተዋፅኦ ያደርጋል የሚል ፅኑ እምነት አለን።

ስለዚህ ያ ትዉልድ ላደረገዉ ትግል አክብሮት ያለዉ፣ ለከፈለዉም መሰዋትነት የሚቆረቆር፣በቅንነት የተከፈለዉ የመስዋእትነት ታሪክ ሲበላሽ አላይም የሚል፤ ለሃገሬ የወደፊት እጣ ፋንታ እጄን አጣጥፌ ፣አፌን ቆልፌ፣ለወሬ ተሰልፌ፣ በተግባር ሰንፌ መቀመጥ በቃኝ ያለ፣መላዉ የኢትዮጲያ ህዝብ በእኩልነት ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብተቶቹ ተከብረዉ እንዲኖር የምትፈልጉ፣ኢትዮጵያ እንደ ሃገር ሉአላዊነትዋ ተከብሮ መቀጠልዋን የትወዱ፣ የዚያ ትዉልድ አካሎች በዚህ እንቅስቃሴ ንቁ ተካፋይ እንድትሆኑ በአክብሮት ጥሪያችንን እናቀርባለን።

እንቅስቃሴዉ አንዱን ከዉስጥ አንዱን ከዉጭ የሚያስቀምጥ ሳይሆን ሁሉንም የዚያ ትዉልድ አካሎች በእኩልነት የሚያይና የሚጋብዝ በመሆኑ በተጠቀሰዉ የኢሜል (e-mail) እድራሻ በመጠቀም በቀጥታ በዚህ እንቅስቃሴ መሳተፍ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።በቂ ዝገጅትም ካደረግን በኃላ የተሟላ ሥብሠባ በማድለግ በጋራ የምንሄድበትን አቅጣጫ የምንወስን መሆኑን ከወዲሁ እንገልጣለን።

ይህንን ስብስብ እንድንፈጥር ካነሳሱን ዓላማዎች በጥቂቱ :
1/አሁን በመታገል ላይ ባሉት የኢሕፓ አካሎችና ከዉጭም ባሉት ቆራጥ የኢሕአፓ ልጆች ማህከል መከፋፈሉ ቀርቶ ተሰባስበዉ ጠንካራ ኃይል ሆነዉ የሚወጡበትን ምንገድ ለማመቻቸት።

2/በጥናት ላይ የተመሰረተ እስከተቻለ ድረስ ሁሉን ጔዶች እና ሁሉንም እካባቢዋች ያካተተ ታሪካችን እንዲጻፍ ለማስተባበር የሚፅፉትንም ለመደገፍ።

3/በኢሕአፓ የትግል ታሪክና መታሰቢያዎች ዙራያ የሚሰሩ ሥራዋችን በመተባበር ለመሰራት።

4/በትግሉ መሰዋዓትነት የከፈሉትን ጔዶች የህይወት ታሪክ በማፈላለግና በማሰባሰብ ሥርዓት ባለዉ መልክ እንዲዘጋጁ ለማድረግ ከሚያደርጉም ሀይሎች ጋር ለመተባበርና ለመርዳት።

5/ድርጂታችን ባካሄደዉ ትግል ላይ የተለያዩ ፅሑፎችን (መፃህፍትና አርቲክሎችን) በመፃፍ የዚያን ጀግና ትዉልድ ታሪክ የሚያጠፉትን ኃይሎች ለመቋቋም።

6/በሃገራችን ጉዳይ ላይ ሰፊና መሰረት ያለዉ ዉይይት በማካሄድ የሃገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ ላይ አወንታዊ ኃይል ሆኖ ለመዉጣት መዘጋጀት። የሚሉት ጥቂቶቹ ናቸው
በዚህ ስብስብ ውስት ለመሳተፍ ለመደገፍና ለመገናኛት በዚህ e mail ተጠቀሙ

Tinsae@yahoogroups.com
ማሳሰቢያ
በዚህ ዓይነት ተመሳሳይ አላማ የሚንቀሳቀሱ ቡዱኖች ካሉ አብረን ለመስራት ሙሉ ፈቃደኞች መሆናችንን አስቀድመን እንገልጻለን
ሰለ ትብብራቸሁ እናመሰግናለን


ቅስቀሳው ተጠናክሮ ቀጥሏል -ፖሊስ እውቅና የተሰጠውን የሰላማዊ ሰልፍ የበራሪ ወረቀት ቅስቀሳ ለማስተጓጎል እየሞከረ ነው::

$
0
0

ሜክሲኮ አካባቢ በራሪ ወረቀት ሊያሰራጩ የተንቀሳቀሱ አባላትን ፖሊስ በ5ኛ ፖሊስ ጣቢያ አገተ፡፡ 1- ዳንኤል ፈይሳ 2- አበበ ቑምላቸው 3- አብነት ረጋሳ 4- ሳሙኤል ይትባረክ 5- አያክሉህም ጀንበሩ 6- ዳግማዊ ተሰማ 7- ዳዊት አለሙ 102 103 1030   188864

”የፈሪ ዱላው አስር”ኢህአዲግ ፈርቷል።ለመሆኑ ኢህአዲግ ያሰራቸው ምንም አይነት ድብቅ አላማ የሌላቸው የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እነማን ናቸው?

$
0
0

zone 9ፍርሃት የማያሰራው ነገር የለም።ኢህአዲግ በከፍተኛ የፍርሃት ማጥ ውስጥ ነው።ሁሉንም ይፈራል።አይዞህ አትፍራ ቢሉትም የሚችል አይመስልም።በሕዝብ ላይ የሰራቸው ሕዝብ የሚያውቃቸው እና የማያውቃቸው ብዙ ድብቅ ስራዎች ስላሉት የመፍራት ደረጃው ከዕለት ወደ ዕለት እየባሰበት እንጂ እየተሻለው አልሄደም። የሚደግፉትም ልያፅናኑት አልቻሉም።ከሚገባው በላይ ፍርሃት ሲያንቀጠቅጠው ሲመለከቱ እነርሱም ይብሱን ፈሩ።ብዙ የስርዓቱ ደጋፊዎች እና በሀብት የደለደሉቱ ሀገር ጥለው እየወጡ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ።ይህ ደግሞ ሌላው የፍርሃት ገፅታ ነው።

የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ሌሎች ሰሞኑን የተያዙት ጋዜጠኞች ምንም የተደበቀ አጀንዳ የሌላቸው ግን ህገ መንግስቱ ላይ የሰፈረው ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ይከበር ያሉ በእዚህም መስረት የሕገ መንግስቱን አንቀፅ እየጠቀሱ የሃሳብ የመግለፅ መብታቸውን የተጠቀሙ፣የሚሰሩት በመንግስት መስርያቤቶች የሆነ፣የሚፅፉት አይደለም ምን በልተው ከማን ጋር ውለው እንዳደሩ መንግስት ብቻ ሳይሆን ሕዝብ የሚያውቃቸው ኢትዮጵያውያን ናቸው።ከእዚህ በፊት በሃሳብ የሞገቱትን ሁሉ ”ህገ መንግስቱን እና ስርዓቱን ለመናድ የተንቀሳቀሱ” እያለ ሲያስራቸው የነበረው መንግስት ዛሬ እራሱ ህገ መንግስቱን አክብረው ሕግ እየጠቀሱ የፃፉትን በ20 ዎቹ እድሜዎች ውስጥ የሚገኙ ወጣቶችን ”ሃገርን በውጭ ከሚኖር ድርጅት ጋር ተመሳጥረው ሊያሸብሩ” እያለ ፌዝ አይሉት ቀልድ መሰል ክስ አቅርቦ ማዕከላዊ እስር ቤት አስገባቸው።ምንም አይነት ወንጀል እንደሌለባቸው እራሱ ኢህአዲግ ያውቀዋል።ግፍ መስራት የማይሰለቸው እና በፍርሃት የተዋጠ መሆኑ ግን የእዚህ አይነቱን ተግባር እንዲቀጥልበት አድርጎታል።

”የፈሪ ዱላው አስር” እንዲሉ የኢህአዲግ አባላት ማታ ኢቲቪ ዜና ላይ የግብፅ፣የየመንን በቅርቡ ደግሞ የዩክረንን የህዝብ ንቅናቄ እያዩ በሰላም መተኛት አልቻሉም።ያ ቀፎው እንደተነካ ንብ የሚተመው ሕዝብ አንድ ቀን እኛም ላይ ይነሳል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።ለእዚህም ማስረጃው ኢቲቪ ባለፈው ሰሞን ያሳየው የዩክሬንን አመፅ የተመለከተ ፊልም መጥቀሱ ይበቃል።ፍርሃታቸውን ደግሞ እነ ሚሚ ስብሃቱ ቀዝቃዛ ውሃ ውስጥ ገብቶ እንደሚንዘፈዘፍ ሰው እየተንቀጠቀጡ ሲናገሩ ሕዝብ ታዝቦ ”ወይ ፍርሃት” ብሏል።ግንቦት 20 ስመጣ ጀግና እንደነበሩ ከሃያ ዓመት በፊት የነበሩ አሮጌ ታንኮች ያሳየናል።መለስ ብለው ደግሞ በፈስ ቡክ እና በጡመራ ፈራን ይላሉ።አጀብ ነው።

ኢህአዲግ ፈራሁ ብሎ ያሰራቸው ንፁሃን ጦማርያን እና ጋዜጠኞች እነማን ናቸው? የወጣቶቹን የስራ መስክ ግልፅነት እና ሙያ ተመልክታችሁ ፍረዱ።ለፈሪዎችም እዘኑላቸው።

1/ ጋዜጠኛ ተስፋለም ወልደየስ 
ለተባበሩት መንግሥታት ዜና አገልግሎት ኢሪን ለረጅም ጊዜ የሰራ የእንግሊዝኛው ‘ፎርቹን’ ጋዜጣ አምደኛ እና ዘጋቢ

2/ ጋዜጠኛ አስማማው ኃይለ ጊዮርጊስ
  አዲስ ጉዳይ መፅሄት ከፍተኛ ኤዲተር
3/ ጋዜጠኛ ኤዶም ካሳዬ 
በአካባቢ ጥበቃ የሰለጠነች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ እና በቀድሞው ‘እንቢልታ’ ጋዜጣ ዘጋቢ 
4/ በፍቃዱ ኃይሉ 
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ባለሙያ፣ብሎገር እና ቅድስት ማርያም ዩንቨርስቲ በሙያው የሚሰራ
5/ አቤል ዋበላ 
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሰራተኛ የአየር መንገዱ ‘ግራውንድ ቴክኒሻን’  
6/ ማህሌት ፋንታሁን 
የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ምሩቅ በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ሰራተኛ 
7/ አጥናፍ ብርሃኔ 
የ25 ዓመት ወጣት በፌስ ቡክ ሃሳቡን የሚገልፅ በብሎጉ ላይ ሃሳቡን የገለፀ 
8/ ናትናኤል 
የ 26 ዓመት ወጣት የኢኮኖሚ ባለሙያ፣’የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ባለሙያዎች ማህበር’ አባል
9/ ዘላለም ክብረት 
የሕግ ባለሙያ፣ማስተርሱን ከሰራ ገና ሳምንታት የሆነው በአምቦ ዩንቨርስቲ የሕግ ትምህርት መምህር ናቸው።

ምንጭ - ከጦማርያኑ ውስጥ በውጭ ሀገር የሚገኙት እንዳልካቸው እና ሶልያና ለቪኦኤ የአማርኛው አገልግሎት ሚያዝያ 20/2006 ዓም ከሰጡት መግለጫ የተገኘ።

ጉዳያችን 
ሚያዝያ 21/2006 ዓም

ሰበር ዜና- የቀድሞው የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃምን ጨምሮ ታዋቂ ፖለቲከኞችና ምሁራን አንድነት ፓርቲን ተቀላቀሉ

$
0
0

ፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ

sscgbweui

አቶ አስራት አብርሃም

የቀድሞው የአረና ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ አስራት አብርሃምን ጨምሮ ታዋቂ ፖለቲከኞችና ምሁራን አንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸውን አንድ አንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ከፍተኛ አመራሩ ለፍኖተ ነፃነት እንደገለፁት ታዋቂው ወጣት ፖለቲከኛና ደራሲ አቶ አስራት አብርሃ እና ሌሎች በርካታ ወጣት ምሁራን አንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸው ፓርቲው በሀገር አቀፍ ደረጃ በሁሉም የህብረተሰብ ክፍል እያገኘ ያለውን ተቀባይነት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡ አቶ አስራት አብርሃም በቅርቡ በአንድነት ፓርቲን መቀላቀላቸውን በልዩ መርሀግብር ይፋ እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡ በሂደት አንድነትን እየተቀላቀሉ ያሉ የሌሎች ታዋቂ ፖለቲከኞችና ምሁራን ስም ይፋ እንደሚደረግም ከፍተኛ አመራሩ ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡ አቶ አስራት አብርሃም “ከሀገር በስተጀርባ”፣ “መለስና ግብፅ” ፣ “ፍኖተ ቃዬል” የሚሉና ሌሎች መጽሓፍትን የጻፉ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

 

አንድነት ፓርቲ እሁድሚያዝያ 26 ቀን 2006ዓ.ም “የእሪታ ቀን በሚል” መሪ ቃል ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ዛሬም የተጠናከረ ቅስቀሳ እየተደረገ ነው፡፡

$
0
0

በትላንትናው ዕለት በአዲስ አበባ በተያዩ አካባቢዎች የተረገው ቅስቀሳ በፖሊስ ለማስተጓጎልና ለማገት ቢሞከርም በተሳካ መልኩ ተጠናቋል

5

6

3

4

2

1

ኮተቤ መምህራን ኮሌጅ በተማሪዎች ተቃውሞ እየተናጠ ነው

$
0
0

Breking Newsኮተቤ መምህራን ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተማሪዎች ተቃውሟቸውን እያሰሙ ነው፤ ግጭት እንደተፈጠረም የሚያመላክቱ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በወለጋ፣ጅማ፣መቱ፣አዳማ እና አምቦ ዩኒቨርሲቲዎች የኦሮሞ ተማሪዎች አዲሱን የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን በመቃወም ተቃውሞ ማሰማታቸውና የፀጥታ ሀይሎችም ከፍተኛ ድብደባ እንዳደረሱባቸው ይታወሳል፡፡

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>