Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

ሰማያዊ ፓርቲ የአርበኞችን ቀን ሊያከብር ነው –በተጨማሪም የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ቅጣት ተጣለባቸው

$
0
0

ሰማያዊ ፓርቲ ሚያዝያ 27/2006 ዓ.ም የአርበኞችን ቀን በጽ/ቤቱ ታዋቂ የታሪክ ተመራማሪዎችንና ሌሎች ምሁራንን ጋብዞ እንደሚያወያይ ምክትል የህዝብ ግንኙነቱ አቶ እምላዕሉ ፍስሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ምክትል የህዝብ ግንኙነቱ እንዳስታወቁት ስነ ስርዓቱ ሰኞ ሚያዝያ 27 ከጠዋቱ 3 ሰዓት የሚጀምር ሲሆን ማንኛውም ኢትዮጵያዊ በፕሮግራሙ መሳተፍ ይችላል ብለዋል፡፡ ‹‹የስነ ጽሁፍ ተሰጥዖ ያላቸውና በበዓሉ ስራቸውን ማቅረብ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንንም  እንዲሳተፉ እንፈልጋለን ያሉት ኃላፊው›› ፕሮግራሙን ወጣቶች ስለ አባቶቻቸው ታሪክ እንዲያውቁ ከማድረግም ባሻገር ስራቸውን በማስታወስ ታካቸውን ለመዘከር እንደሚፈልጉ አክለው ገልጸዋል፡፡

 

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ህግን ለማስከበር በመጣራቸው ተጨማሪ ቅጣት ተጣለባቸው

ethiopia-blue-party-300x164ሚያዝያ 19/2006 ዓ.ም ለተካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ በቅስቀሳ ላይ የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት በ1000 (አንድ ሺህ ብር) ዋስ እንዲወጡ መወሰኑን ተከትሎ ‹‹እኛ ነጻ ነን፡፡ ገንዘብ አስይዘን እንወጣም፡፡ ስራችን ህግ ማስከበር እስከሆነ ድረስ እየታሰርንም ቢሆን ህግ እናስከብራለን፡፡ በመሆኑም ነጻ እስካልተለቀቅን ድረስ እሰሩን፡፡›› በማለታቸው ተጨማሪ ክሶችና ቅጣቶች እየተጣለባቸው ነው፡፡ በትናትናው ዕለት ሜሮን አለማየሁና ትግስት ወንዲፍራው ‹‹ግቢ በመረበሸ›› ተጨማሪ ክስ መከሰሳቸው ይታወቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት በቤላ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙ 14 ያህል የሰማያዊ ፓር አመራሮችና አባላትም ተመሳሳይ ክስ የተመሰረተባቸው ሲሆን ባለፈው ከፍላችሁ ውጡ ከተባሉት 1000 (አንድ ሺህ ብር) በተጨማ 600 (ስድስት መቶ ብር) ጨምረው ከፍለው እንዲወጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡

እነዚህ አመራሮችና አባላት መጀመሪያ የካ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው የነበሩ ቢሆንም እስረኛውን በማሳመጽና በመረበሽ ከመከሰሳቸውም በተጨማሪ ወደ ቤላ ፖሊስ ጣቢያ ተዛውረዋል፡፡ በወቅቱ ድብደባና ማዋከብ እንደደረሰባቸው የሚናገሩት ታሳሪዎቹ ‹‹ህግን ለማስከበር የምናደርገውን ጥረት እንደ ህገ ወጥነት ተቆጥሮ ተጨማሪ ክስና በደል ቢፈጸምብንም እኛ ህግ ማስከበራችንን እንቅጥላለን›› ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በጉለሌ ፖሊስ ጣቢያ የሚገኙትና ዛሬ ስምንት ሰዓት ላይ ፍርድ ቤት የቀረቡት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት እያንዳንዳቸው 5500 ብር አስይዘው እንዲወጡ ተፈርዶባቸዋል፡፡ ታሳሪዎቹ ይህንን ውሳኔ በመቃወም ‹‹ነጻ ካልተለቀቅን አንወጣም!›› ያሉ ሲሆን ከዳኛው የተሰጣቸው መልስ እንዳሳዘናቸው ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡  ‹‹ዳኛውና አቃቤ ህጉ ተመካክለው ነው የገቡት፡፡ በእያንዳንዳችን 5500 ብር እንድንከፍል ሲፈርዱ፤ ‹እኛ ተማሪዎችና የመንግስት ሰራተኞች ነን ከየትም አምጥተን መክፈል አንችልም!› አልናቸው፡፡ እነሱ ልክ አንድ ሰው እቃ ሲገዛ እንደሚከራከረው ‹በቃ! 2000 ብር ይሁንላችሁ› አሉን፡፡›› ያሉት ታሳሪዎቹ በህግ ሳይሆን በዘፈቀደ እየተሰራ መሆኑ አሳዝኗቸዋል፡፡ በሌላ በኩል  ‹‹ህገ ወጥ ቢሆንም በሌላ አካባቢ የታሰሩት የእኛ ጓደኞች 1000 ብር ነው እንዲከፍሉ የተወሰነባቸው፡፡ የእኛውን ለምንድን ነው 5500 ያደረጋችሁት?›› ብለው ሲጠይቁ ዳኛው ‹‹ቅጣቱ ከጣቢያ ጣቢያ ይለያያል፡፡›› የሚል አስገራሚ መልስ እንደሰጧቸው ገልጸውልናል፡፡


ከአዲስ አበባ ፕላን ተማሪዎቹ አይቀድሙም?

$
0
0
ዳዊት ሰሎሞን

2_nበዛ ካሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እየሰማናቸው የምንገኛቸው ዜናዎች አስደንጋጭ ናቸው፡፡ለነገሩ ገዢው ፓርቲ የሚከተለው ሩሲያን ከመፈረካከስ ያላደነ የፖለቲካ መስመር እንዲህ አይነት ፍሬ ማፍራቱ የማይጠበቅ አልነበረም፡፡እናም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑ ተማሪዎች የአዲስ አበባ አካባቢዎችን ወደ አዲስ አበባ ይጠቀልላል የሚል ስጋት ባሳደረባቸው የከተማይቱ ማስተር ፕላን ላይ ያላቸውን ተቃውሞ ለመግለጽ የተቃውሞ ሰልፎችን ለማድረግ ዝግጅት አጠናቅቀው ወደ ትገበራው ሲያመሩ ግጭት ተፈጥሮ በዛ ያሉ ተማሪዎች መጎዳታቸውን ሰምቼያለሁ፡፡


በእኔ እምነት ማስተር ፕላኑን ያዘጋጀ አካል ፊት ለፊት ቀርቦ ለመነጋገር ስህተት ከተሰራም እርማት ለመውሰድ ለምን እንደማይደፍር አይገባኝም፡፡መቼም ተማሪዎቹ ተቃውሞ ያቀረቡት መሬታችን ተቆርሶ ለባዕድ አገር ሊሰጥብን ነው በማለት አይመስለኝም፡፡ስጋታቸው ቤተሰቦቻቸው ከያዟት ኩርማን መሬት ጋር የሚጋመድ ይመስለኛል፡፡ ነገ ቤተሰቦቻቸቸው የያዟትን ኩርማን መሬት በሊዝ ለአንዱ ባለ ጊዜ ተሰጥታ ፎሪ እንዳይወጡ ሳይሰጉ አልቀሩም፡፡ይህንን ስጋት በፖሊስ ቆመጥና በፌደራል መሳሪያ ማስወገድ ይቻላል እስካልተባለ ድረስ መነጋገር መቅደም ይኖርበታል፡፡


እባካችሁ ለንግግር ዕድል ስጡ፡፡

በአንድነት ፓርቲ የሰላማዊ ሰልፍ ጥሪ ላይ ዘመቻ ተከፍቷል

$
0
0

ዳዊት ሰሎሞን


በአዲስ አበባ ከተማ ያለውን የኢኮኖሚ፣የማህበራዊና ፖለቲካዊ ችግሮች በተመለከተ የከተማይቱ ነዋሪ አደባባይ በመውጣት ድምጹን ከፍ ባለ መንገድ በዕሪታ እንዲያሰማ አንድነት ፓርቲ ለፊታችን እሁድ ጥሪ እያደረገ ይገኛል፡፡ነገር ግን ጥሪው በመብራት መጥፋት፣በንጹህ ውሃ አለመኖር፣በትራንስፖርት፣በቴሌ ኮም ኢንዳስትሪው ኋላ ቀርነት
ብቻ እንደሆነ በማስመሰል ለማንከኳሰስ የሚደረጉ ዘመቻዎች በፓርቲው ላይ ተከፍተዋል፡፡


እርግጥ ነው ለአንድነት
የኑሮ ውድነት፣የስራ አጥ ቁጥር መበራከትና እንደ ንጹህ ውሃ ፣መብራትና የቴሌ ኮም አገልግሎት ደካማነት አነገብጋቢ ጉዳዮች ተደርገው መወሰድ እንደሚገባቸው ያምናል፡፡
ሰልፉ ግን ከላይ ለመጥቀስ ከሞከርኳቸው ዐቢይ ጉዳዮች በተጨማሪ ‹‹የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ይመለከታል፡፡
የመልካም አስተዳደር እጦት ለእርስዎ ምንድን ነው?
የቢሮክራሲው መንዛዛት፣ሙስናው ፣ፍትህ ማጣቱ፣አድልዎ መደረጉ፣ስራ ለመቀጠር የድርጅት አባልነት መስፈርት መደረጉ፣በአስተሳሰብዎ የተነሳ ልዩነት እየተደረገብዎ መሆኑ፣የኑሮ ውድነቱ፣አፈናው፣እስራቱ ወዘተ አ

179

በሱዳን በኢትዮጵያውያን ላይ የሚፈጸመው ግፍ ቀጥሏል፤ ኢትዮጵያውያኑ የድረሱን ጥሪ አቀረቡ

$
0
0

ካርቱም ሱዳን ያሉት የኢትዮጵያውያን ስደተኞች እየደረሰባቸው ያለው መከራ እና ስቃይ በተመለከተ የተጥናቀረ ፁሁፍ።

በሱዳን ከሚገኙ ኢትዮጵያውያን የተላለፈ ጥሪ

እኛ ሃገር ሱዳን የምንገኝ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን በደል እለት በእለት እየተከታተልን ጮኸታችን ሰሚ ያግኝ ዘንድ እናጋልጣለን። በመጀመሪያ የእሮሮችን ጹሁፍ እንደጠቀስነው የጊዜ ገደቡ አልፎ አፈሳው በከፍተኛ ደረጃ ቀጥሏል ወያኔና የሱዳን መንግስት ያዘጋጁት የስድስት ወር ጊዚያዊ መታወቂያ ለማውጣት የሚከፈለው ገንዘብ መጠን 110 የሱዳን ፓውንድ ነበር አሁን ግን 170 ደርሷል። ያም ሆኖ መታወቂያው ከእስር እና ከአፈሳ አልታደጋቸውም።

የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)

የካርቱም ከተማ ከፊል ገጽታ (ፎቶ ፋይል)


ባአሁኑ ጊዜ ሱዳን ውስጥ ያለው የሙቀት ደረጃ 50 ዲግሪሴንቲግረድ በደረሰበት ግዜ 400 የሚሆኑ ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን እምዱሩማን እስርቤት ይሰቃያሉ እነዚህ እህቶቻችንና ወንድሞቻችን የመጨረሻ እጣቸው ፍርድ ቤት ቀርበው የገንዘብ መቀጮውን ከከፈሉ በኋላ ወደ ሃገር መባረር ነው።
የሰሩበትንም ሆነ የደከሙበትን ገንዘባቸውንና የቤት እቃቸውን እንኳን የመያዝ ወይም የመሸጥ ጊዜ አይሰጣቸውም። በጣም የሚገርመውና ልብን የሚያደማው ለዘህ ሁሉ ስራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ባጀት መድቦ አፈሳውን ለሚያደርገው የሱዳን ሰራዊት መገልገያ መኪናዎች ሙሉ ወጨው የሚሸፈነው ወያኔ ነው። ይህ ሆኖ እያለ እስር ቤት ውሰጥ እህት ወንድሞቻችን ከፍተኛ ግፍ እየተፈፀመባቸው ይገኛል ። ይህንን ቤት ለቤት ገፈፋ በተመለከተ የስደተኞች ጉዳይ ተመልካች የሆነው መስሪያቤት ዩኤን አች ስአር (UNHCR) አሳምሮ ስለሚያውቅ ሆት ላይን አዘጋጅቶ ችግር ለሚገጥመው ስድተኛ መፍትሄ ይሰጥ ይመስል 0183587005 ቁጥር ለጥፏል:: በጣም የሚያሳዝነው ይህ ሁሉ ግፍ በ ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ሲፈፀም የሰብአዊ መብት ተከራካሪ ነን የሚሉ ድርጅቶች አንዳችም ድምፅ አለማሰማታቸው ነው።

እዚህ ላይ ወጭ ላላችሁ ወገኖቻችን ማስገንዘብ የምንፈልገው ሱዳኖች ለማንኛውም አለማቀፋዊ ስምምነቶች በቀላሉ የማይገዙ መሆናቸውን ነው። ይሄን ያልንበት መክኒያት ካርቱም በሚገኘው (UNHCR) መስሪያቤት ውስጥ ሁሉንም እኛ ካላደርግነው አይሆንም ነው የሚሉት ነጮቹ በነጻነት እንዲሰሩ ጭራሽ አይፈቅዱላቸውም። ባጠቃላይ መስርሪያቤቱ ወያኔ በገዛቸው የሱዳን የጸጥታና የስለላ ሰዎች የተሞላ ስለሆነ አንድ ስደተኛ ችግሩን ለማስረዳት ከፍተኛ መከራ ነው የሚያጋጥመው። ወያኔ ስልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ ሱዳን ውስጥ ያለውን የስደተኛውን እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር እንዲያመቸው (UNHCR) ፕሮቲክሽን ኦፊስ ውስጥ የሚሰሩትን በሙሉ በመዳፉ አስገብቷቸዋል። ምን ችገር አለባቸውሁ ሃገራችሁ ዲሞክራሲ ተትረፍርፏል ለምን ሃገራችሁን አትገቡም እያሉ የሚሰብኩ የወይኔ አባሳደሮች ናቸው። አንዳንድ የሙያው ሰነመግባር የሚያስገድዳቸው ሰራተኞች የመስሪያቤቱ ሕግ በሚደነግገው መሰረት መስራት ሲፈልጉ እነዚህ ሰላይ ናቸው ተብለው በሱዳን መንግስት እንዲባረሩ ይደረጋል። ይታያችሁ እንግዲህ ካርቱም ሱዳን ያለ ስደተኛ ይህን ሁሉ ግፍና መከራ ነው እየተጋፈጠ የሚኖረው።

ሃቁ ግን ኢትዮጵያውይኖች በጠራራ ፀሃይና በለሊት በሱዳን ሰክሪቲዎች ከቤታቸው እየታፈሱ ለወያኔ ባለስልጣናት ተላልፈው ተሰተዋል ያለምንም ከለላ።የሱዳን መንግስት ወደ ሃገሩ የሚገባውን የማንኛውንም ሃገር ዜጋ መቆጣጠር መብት እንዳለው ይታመናል ሆኖም በእኛ ላይ ግን ሰባዊነት የጎደለው
በደል በሱዳን ፖሊሶች ይፈፀምብናል መታወቂያ መቅደድ በያዙት ነግር ሁሉ መደብደብ ፣ መሳደብ ብር መቀማት በሲቶች እህቶቻችን ላይ ይህ ነው የማይባል ለማመን የሚቸግር ግፍ ይፈፀምባቸዋል። ወንዶች እስረኞችን ደግሞ በርሃ በመውሰድ የእርሻ ስራ የሰሯቸዋል። አንዳድ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን መታወቂያችን ይቀዱብናል በለው በመስጋት ኮፒ ይዘው የተገኙት ዳኛው በሚያሳዝን ሁኔታ ገንዘብ ቀጥቶ ወደሃገራቸው እንዲባረሩ ወስኖባቸዋል ባአንዳንድ አካባቢ ደግሞ ጭራሽ እኛ የስደተኛ መታውቂያ አናውቅም በዚህ አካባቢ ኗሪ መሆናችሁን የሚያስረዳ መታወቂያ ማውጣት አለባችሁ ተብለው 20 የሱዳን ፓውንድ በመክፈል ያወጡ ስደተኞች አሉ።

ባአጠቃላይ የሱዳን መንግስት ስደተኛውን በተመለከተ የተምታታ እና አንድ ወጥ የሆነ አስራር የለውም ይሄ ደግሞ የገቢያ ግርግር ለሊባ ያመቻል እንደተባለው ሆኗል ወያኔ በገንዘቡ ብመመካት የፈለገውን ነገር በስደተኛው ላይ ማድርግ እንዲችል እና የፈለጋቸውን ሰዎች ደግሞ እያነቀ እንዲውስድ በሩን
ከፍቶለታል። ከሁሉም በላይ ለዜጎቹ ክብር የለለው በነሱ ስቃይ ለሚደሰተው ወያኔ አሁን ሱዳን ውስጥ የሚደረገው የስደተኛ ወከባ ስደተኛውን ወደ ሊላ መከራ እየገፋው ነው ይሄውም ወዲ ሊቢያ መሰደድ በስሃራ በርሃ ላይ ተሰቃይቶ መሞት በባህር ላይ ማለቅ ሆኗል የስደተኛው እጣ ፈንታ:: ወያኔ ሱዳን ሃገር ስደተኛ እንዳይኖር የሚፈልግበት የራሱ የሆነ ምክኔያት አለው ይሄውም ለሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብ ግልጽ ነው። ወያኔ ትንሽ የፖለቲካ እንከን ከሱዳን ጋር ቢገጥመው ሱዳን ሱዳን ውስጥ ያለውን ስደተኛ ያስታጥቃል የሚል የራሱ የሆነ ፍራቻ አለው። አውንታው ግን በጭራሽ ለጎርረቤት
ሃገሮች እንደ ወያኔ ለጋስ የጠየቁትን የሚሰጥ መንግስት ሊመጣ እንደማይችል የታወቀ ነው።

ሱዳንን ከኢትዮጵያ ጋር ከሚያዋስነው አካባቢ ለጉልበት ስራ ከሚመጡ የወሎ ፣የጎጃም፣ የጎንደር የአማራ ተወላጆች ሆን ተብሎ እርስ በ እርሳቸው እንዲጨፋጨፉ ስውር ነፈሰ ገዳዮችን በመከከላቸው በማሰማራት ከፍተኛ የዘር ማጥፋት ወንጀል እየተካሔደ እንደሆነ ከ አሁን በፊት ዘ ሀበሻ የህዋ ሰሌዳ በመጠኑ እንደዘገበው ይታወቃል አሁንም በሰፊው ጥናት ተደርጎበትና ታቅዶበት የሚከናወን ስራ ለመሆኑ በመረጃ የተደገፈ ዘገባ እናቀርባለን።

ከላይ የተዘረዘሩት ስደተኛውን የማዋከብ እና በሰላም ሰርቶ እዳይኖር የሚደረገው በወያኔ በጎ ፈቃድ መሆኑን ስደተኛው በሙሉ ጠንቅቆ ያውቀዋል። አሁን ሱዳን ውስጥ የሚደረገው ነገር ልክ ሳውዲ ያ ሁሉ ግፍ ከመፈጸሙ በፊት ሲደረግ የነበረው አይነት ይመስላል መጠኑ የተለያየ ቢሆንም ማለትም ጋዚጦች ስለ ሃበሻ መጥፎ ነገር መጻፋ ባአጠቅላይ የሚታዩ የሚነበቡ የሚደመጡ የዜና አውታሮች ስለዚሁ ጉዳይ በስፋት መቀስቀስ ጀምረዋል። ሱዳኖችም የሃገሪቱ ኢኮኖሚ ባሽቆለቆለ ቁጥር የወያኔ ተንኮል እና ሴራ ተጨምሮበት ጥላቻቸው በሃበሻ ላይ ጎልቶ እየወጣ ነው። ባአጠቃላይ ሁኔታዎች የሚያመለክቱት የሚመጣው ጊዜ ካለፈው የከፋ እንደሆነ ነው።

ወድ ወገኖቻችን እሮሮዋችን ጣራ አልባ እንዳይሆን ለሚመለከተው ለሰባዊ መብት ተከራካሪ ድርጅቶች የስደተኛውን ጉዳይ ሊሚመለከቱ መስሪያ ቤቶች (ድርጅቶች) ባጠቃላይ ይህ ጉዳይ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ለሚመለከታቸው ድርጅቶች ይህንን የግፏአን ድምጽ ታሰሙልን ዘንድ እንማጸናለን።

ከ አክብሮት ጋር

ፍቅር ሰላም ለመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ!!

6 ኪሎ ዩኒቨርሲቲ ውጥረት ነግሷል፤ የታጠቁ ኃይሎች ወደ ዩኒቨርሲቲው ገብተዋል

$
0
0

6 killo Universityጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን
ጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን ከአዲስ አበባ እንደዘገበው እንደ ሰደድ እሳት በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እየተዛመተ የሚገኘው ተቃውሞ ዛሬ ማረፊያውን አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ አድርጓል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ራሳቸውን ከጥቃት ለመከላከል የሚያስችላቸውን ትጥቅ በአግባቡ የታጠቁ ልዩ ሃይሎች ወደ ትምህርት ቤቱ ዘልቀው ገብተዋል፡፡ የዩኒቨርስቲው ፕሬዘዳንት ዶክተር አድማሱ ጥያቄ ያቀረቡ ተማሪዎችን በማነጋገር ከሚመለከተው አካል ጋር በመነጋገር መፍትሄ እንደሚፈልጉ ነግረዋቸዋል፡፡

ተጨማሪ መረጃ እንደደረሰን እናቀብላችኋለን

ይህ በእንዲህ እንዳለ በአዲስ አበባ በተለይም በቤተመንግስት አካባቢ ያለው ጥበቃ በከፍተኛ ሁኔታ እንደጨምረ ተያይዞ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ። ይህን የጥበቃ መጠናከር በኢትዮጵያ የተለያዩ ክልሎች የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም ባነሱት ተቃውሞ የተነሳ መንግስት ከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንዳለ የሚገልጽ ነው ሲሉ አንዳንድ የውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ። በተለይም ተማሪዎቹ ባነሱት ተቃውሞ ላይ ሕወሓት ጠፍጥፎ የሰራው ኦሕአዴድ አባላት አቋማቸው ለ2 መከፈሉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

በቃሊቲ እና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!!

$
0
0

MillionsVoice1በቃሊቲ እና በዝዋይ የሚገኙ ታሳሪዎች የርሀብ አድማ ሊያደርጉ ነው!! ህዝቡ በነቂስ በመውጣት የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ እንዲቀላቀል ጥሪ አቅርበዋል!! በቃሊቲና በዝዋይ ማረሚያ ቤቶች በግፍ ተፈርዶባቸው በእስር ላይ የሚገኙ የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ‹‹የእሪታ ቀን ›› በሚል መሪ ቃል የሰየመውና እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም የጠራውን ህዝባዊ ሰላማዊ ሰልፍ በማስመልከት ከህዝብ ጎን ሆነን ድምፃችንን እንዳናሰማ በግፍ የተወረወርንበት እስር ቤት ቢያግደንም ከአርብ ጀምሮ ሰላማዊ ሰልፍ እስከሚደረግበት እለት ድረስ የርሀብ አድማ በማድረግ ከህዝቡ ትግል ጎን በመቆም አጋርነታችንን እናሳያለን ሲሉ ለፍኖተ ነፃነት ገለፁ፡፡ ህዝቡ ከየቤቱ በነቂስ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፉን እንዲቀላቀልም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Millions of voices for freedom – UDJ

ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉና የአንድነት የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶ ዘካሪያስ የማነብርሃን ታሰሩ –ፖሊስ ህገ ወጥ እስሩን ቀጥሏል

$
0
0
ዳዊት ሰሎሞን
ጋዜጠኛ ነብዩና የአንድነት ሊቀመንበር ታሰሩ
ጋዜጠኛ ነብዩ ሃይሉ የቀስቃሾቹን እንቅስቃሴ ለመዘገብ በወጣበት ለእስር ተዳርጓል፡፡በካዛንቺስ ፖሊስ ጣብያ ከነብዩ ጋር የአዲስ አበባ የአንድነት ሊቀመንበር ዘካሪያስ የማነብርሃንና ዘላለም ደበበ ይገኙበታል፡፡የጣብያው ኃላፊዎች ‹‹ቤተ መንግስት አካባቢ ቀስቅሳችኋል››የሚል ውንጀላ አቅርበውባቸዋል፡፡

ፖሊስ ህገ ወጥ እስሩን ቀጥሏል አንድነቶችም በእስሩ አልበረገጉም

ከአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ለተቸረው ሰላማዊ ሰልፍ የአንድነት አባላት በራሪ ወረቀት በማደል፣ፖስተሮችን በመለጠፍና በመኪና ቅስቀሳ ሲያደርጉ የእውቅናው ደብዳቤ እውቅና ግልባጭ የደረሰው ፖሊስ አባላቱን በማሰር ስራ መጠመዱ አስገራሚ ቢሆንም የፓርቲው አባላት ቅስቀሳውን ከማድረግ አልተቆጠቡም፡፡
ፖሊሶቹ ለያዟቸው የአንድነት አባላት ወረቀት ለመበተን፣ፖስተር ለመለጠፍና የመኪና ላይ ቅሰቀሳ ለማድረግ ፈቃድ አምጡ በማለት ይጠይቃሉ፡፡ነገር ግን ለሰላማዊ ሰልፍ እውቅና ከሚሰጥ ወረቀት በስተቀር ለቅስቀሳ ተብሎ የሚሰጥ ወረቀት ባለመኖሩ የፖሊስን እስር አስገራሚም አስተዛዛቢም አድርጎታል፡፡ 
የአንድነት አባላት በአሁኑ ወቅት በካዛንቺስ፣በቦሌና ንፋስ ስልክ ፖሊስ ጣብያዎች ታስረው ይገኛሉ፡፡

61 10

 

miilion v 2

አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት የረሃብ አድማ ላይ ነው

$
0
0

Free Andualem

ፍኖተ ነፃነት

የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) ም/ሊቀመንበርና የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የነበረውና ‹‹ሽብርተኛ›› በሚል የእድሜ ልክ እስራት የተፈረደበት አቶ አንዷለም አራጌ በቃሊቲ እስር ቤት ከሌሎች እስረኞች በተለየ ሁኔታ እሱ ላይ ብቻ ትኩረት ተደርጎ መብቱ በመጣሱ፤ እንዲሁም በተፅእኖና ክልከላ ሰለባ በመሆኑ ከትላንት ጀምሮ የረሃብ አድማ ላይ መሆኑን ቃሊቲ የሚገኙ የፍኖተ ነፃነት ምንጮች ገለጹ፡፡


ማኅበረ ቅዱሳን የጠራውና በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጽ/ቤት የተፈቀደው ጉባኤ በፓትርያርኩ ውሳኔ ተከለከለ

$
0
0
  • Mhbere Kidusanዛሬ ሚያዝያ ፳፫ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ከቀኑ 8፡00 – 11፡00 በኢትዮጵያ ብሔራዊ ሙዝየም አዲሱ አዳራሽ ‹‹ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲሁም አያያያዝና አጠባበቅ›› በሚል ርእስ የተጠራው የጥናት ጉባኤ ክልከላ መንሥኤ ‹‹የሥልጣን ተዋረድንና የዕዝ ሰንሰለትን ባልተከተለ መልኩ በቀጥታ የአድባራትንና የገዳማትን አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች እንዲሁም በቤተ ክርስቲያኒቱ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸውን ስብሰባ መጥራት›› የሚል ነው፡፡
  • ለጥናታዊ ጉባኤው የተጠሩት የገዳማትና አድባራት አለቆች ቤተ መዘክር ያላቸው ሦስት አብያተ ክርስቲያን ብቻ መኾናቸውን የገለጹት የጉባኤው አስተባባሪዎች በበኩላቸው÷ ማኅበሩ ለቤተ ክርስቲያን አባቶች፣ ጉዳዩ ለሚመለከታቸው ባለድርሻዎች፣ ምሁራንና እንግዶች ጥሪ ያደረገው ዕቅዱና አስፈላጊነቱ ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ቀርቦ ከተመከረበትና ከተፈቀደ በኋላ መኾኑን አስታውቀዋል፡፡
  • ፓትርያርኩ ማኅበሩ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ለብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ተጠሪ የኾነበትን አሠራር በመሻር ማንኛውንም ስብሰባዎቹንና ጉባኤዎቹን ኹሉ ያለልዩ ጽ/ቤታቸው ፈቃድ እንዳያካሒድ ከሕጉ ውጭ በቀጥታ ለማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት በላኩት የልዩ ጽ/ቤታቸው ደብዳቤ አሳስበዋል፡፡
  • የፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የጥናታዊ ጉባኤውን መከልከል በተመለከተ በቀጥታ ለማኅበሩ የዋናው ማእከል ጽ/ቤት ደብዳቤ ለመጻፍ የተገደደው፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ማቴዎስ ስለጉባኤው እንደሚያውቁና ዝግጅቱም የአሠራር ክፍተት እንደሌለበት ለልዩ ጽ/ቤቱ የበላይ ሓላፊ በማሳወቅ ሊታገድ እንደማይገባው በመከራከራቸው ነው፡፡
  • ሕገ ቤተ ክርስቲያኑ የዋናውን መሥሪያ ቤት ማለትም የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን መምሪያዎችና ድርጅቶች ጨምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ ሥር የሚገኙትን የሥራ ዘርፎች ኹሉ በበላይነት የማስተዳደር ሥልጣንና ተግባር የሚሰጠው ለጠቅላይ ሥራ አስኪያጁ ነው፡፡ በዚኽ ረገድ የፓትርያርኩ ሓላፊነት በቅዱስ ሲኖዶስ የሚወጡ ሕጎችን፣ ደንቦችንና መመሪያዎችን በፊርማቸው የማስተላለፍ፣ በተግባር ላይ መዋላቸውንም መከታተልና መቆጣጠር ነው፤ ፓትርያርኩ የሚፈጽሟቸው ተግባራት ካሉም ዓበይትና የቅ/ሲኖዶሱ ውሳኔ ያረፈባቸው መኾን እንደሚገባቸው ተደንግጓል፡፡
  • በፓትርያርኩና በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ መካከል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሥራ አለመግባባቶች እየተባባሱ የመጡ ሲኾን መንሥኤውም÷ በአማሳኞችና ጎሰኞች የሚመከሩት ፓትርያርኩ የማኅበረ ቅዱሳንን አገልግሎት ጨምሮ የጠቅላይ ቤተ ክህነቱን የሥራ ዘርፎች በቀጥታ የመምራትና የማስተዳደር ሓላፊነት ያለባቸውን ብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁን በመጋፋት የጀመሩት አካሔድ ነው፡፡
  • ፓትርያርኩ የሚመለከታቸውንና የማይመለከታቸውን ዐውቀውና ለይተው በብቃት የመምራት አቅም ያጡትን ያኽል በዙሪያቸው የከተሙ አማሳኞችንና ጎጠኞችን መሸጋገርያ ያደረገውን ውጫዊ ተጽዕኖ በቀጥታ ተቀብሎ ለማስፈጸም የሚታይባቸው ፍጥነትና ታዛዥነት በእጅጉ እንዲናቁና እንዲጠሉ እያደረጋቸው ይገኛል፡፡

*                           *                              *

  • ጥናታዊ ጉባኤው÷ ማኅበረ ቅዱሳን በመተዳደርያ ደንቡ መሠረት ስለ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልማት፣ ዕድገት፣ ታሪክ፣ ቅርስና መሰል አርእስተ ጉዳዮች ጥናት የሚያደርጉ ሰዎችን በተለይም ወጣት ምሁራንን ለማበረታታትና በተቻለው ኹሉ ለመርዳት፤ ሃይማኖታቸውን የሚጠብቁ፣ ቤተ ክርስቲያናቸውን የሚከባከቡና ሀገራቸውን የሚወዱ ብቁ ዜጎችን ለማፍራት በተጣለበት ሓላፊነት መሠረት ከቤተ ክርስቲያን ጋራ ተያያዥነት ባላቸው ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ጥናትና ምርምር ለማከናወን ባቋቋመው የጥናትና ምርምር ማእከል በየኹለት ወሩ የሚካሔድ መደበኛ መርሐ ግብር ነው፡፡
  • የማኅበሩ የጥናትና ምርምር ማዕከል በየኹለት ወሩ የሚያካሒደው መደበኛ ጥናታዊ መድረክ አካል የኾነውና የሚመለከተው የብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጽ/ቤት ዝርዝር ይዘቱን ከአንድ ወር በፊት በጋራ ውይይት ጭምር እንዲያውቀው ተደርጎ የተጠራው ጥናታዊ ጉባኤ፣ በጥንታዊ የብራና መጻሕፍት ዓይነትና የይዘት ትንተና እንዲኹም ጥበቃ ላይ ያተኮረ መኾኑ የመርሐ ግብሩ መግለጫ ያመለክታል፡፡par
  • ሊቀ ጠበብት አክሊለ ብርሃን ወልደ ቂርቆስ ‹‹ዜና መጻሕፍተ ብራና›› በተሰኘውና በ፲፱፻፷፮ ዓ.ም. በተካሔደው ሦስተኛው የኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ጥናት ጉባኤ ላይ ባቀረቡት ጽሑፋቸው እንደገለጹት÷ ጥንታዊ የብራና መጻሕፍታችን ገበታቸው የወርቅ የኾነ፣ የብርዓቸው አጣጣልና የብራናቸው ንጽሕና፣ የቅርፃቸው ማማርና ውበት ሲመለከቱት በእውነት የእነርሱን መልክና ቅርፅ የኑሮ ቤት አድርጎ መኖር እንጂ በዚኽ ዓለም በሥጋዊ ኑሮ ታስሮ መኖርን አያስመኙም፡፡
  • ከቅዱሳን ገድላትና ድርሳት ባሻገር አያሌ ‹የቴዎሎጊያ እና ፊሎሶፊያ› ሀብት ያካበቱት ጥንታዊ የብራና መጻሕፍት በይዘታቸው ‹‹እግረ ኅሊና ያልደረሰበት፣ የአእምሮ ክንፍ ያልበረረበት የተሸሸገ ጥበብና ያልተሞከረ ስውር ፍልስፍና›› የተካበተባቸው ናቸው ያሉት ሊቁ÷ ያልተከፈተውን የዕውቀት ጎዳና፣ ዓይን ያላየውን ዦሮ ያልሰማውን በጥበበኞች ያልታሰበውን ብልሃትና ሥነ ጥበብ መፈለግና መሻት ፈልጎም ማግኘትና አግኝቶም በፍሬውና በመልኩ መጠቀም ከአኹኑ ትውልድ የሚጠበቅ አዲስ አለኝታ፣ አዲስ ተስፋ፣ አዲስ የምሥራች መኾኑን አመልክተዋል፡፡
  • የተማረው ትውልድ የጠፋባትን የወርቅ ቀለበት ለማግኘት ባጡ፣ ቆጡ፣ ማዘንቱ፣ ማቶቱ ሳይቀር ኹሉንም በጥንቃቄ እያገላበጠች የምትፈልገውን ልባም ሴት መምሰል እንዳለበት ሊቁ በጽሑፋቸው መክረዋል፡፡ የበሬ ቆዳው በገዛ ሞራው እንዲለፋና እንዲለሰልስ የሀገራችን መልክና ቅርፅ በገዛ ሥነ ጽሑፋችንና ቅርፃችን ማሣመር እንድንችልና በዝግ ቤት ከየቤተ መቅደሱ ምህዋርና ከዋሻ ውስጥ ወይም ከመንደርና ደንበኛ ካልኾነ ዕቃ ቤት ተደብቆ ትውውቁ ከሌሊት ወፍና ከአይጥ መንጋ ጋራ የኾነውን የአባቶቻችንን ሥነ ጽሑፍ እያሠሥንና እየመረመርን ለተከታዩ ትውልድ እንድናቆይም በጥናታቸው አደራ ብለው ነበር፡፡
  • የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ መምሪያዎች የበጀት እጥረትንና የሰው ኃይል ውሱንነትን በመጥቀስ ተግባራቸውን ማከናወንና የታሰበውን ለውጥና ውጤት ማምጣት እንደተሳናቸው ሰሞኑን በአስተዳደር ጉባኤው ላይ ቀርቦ ከተገመገመው የስድስት ወር ዕቅድ ክንውን ሪፖርታቸውበተረዳንበት ኹኔታ ያልነበሩና የሌሉ ለመኾን የተቃረቡትን ጥንታዊ የብራና መጻሕፍታችን ላይ ያተኮረው ጥናታዊ ጉባኤ የተከለከለበት ዋነኛ ምክንያት ታድያ፣ በልዩ ጽ/ቤቱ ደብዳቤ እንደተመለከተው ዝግጅቱን ካለማወቅ አልያም የዝግጅት ሒደቱ የሥልጣን ተዋረድንና የዕዝ ሰንሰለት አልተከተለም ከሚለው የተለመደ የማሰናከያ ስልት ጋራ በርግጥም የተያያዘ እንዳልኾነ ግልጽ ነው፡፡
  • የልዩ ጽ/ቤቱ የክልከላ ውሳኔ ከታወቀበት ከትላንት ቀትር ጀምሮ ደብዳቤውን እያሰራጩ የሚገኙት በፓትርያርኩ ዙሪያ በአማካሪነትና ረዳትነት ስም ከተጠጉት እነንቡረ እድ ኤልያስ ኣብርሃ ጋራ የዓላማና የጥቅም ግንኙነት ፈጥረው የሚንቀሳቀሱት አማሳኞቹ እነኃይሌ ኣብርሃ መኾናቸው ሲታይ የክልከላ ውሳኔው ምንጭ፣ የአብነት መምህራን ሀገር አቀፍ ጉባኤ ከታገደበት የካቲት ወር ጀምሮ የተጠናከረውና ማኅበሩን ብሎም ቤተ ክርስቲያኒቱን የማዳከም ልዩ ተልእኮ ባላቸው ባለሥልጣናት ጭምር ተደግፎ የቀጠለው ጫና ስለመኾኑ ግልጽ ያደርገዋል፡፡
  • የማኅበሩ አመራር ስለፓትርያርኩ ልዩ ጽ/ቤት የክልከላ ደብዳቤ ከብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ ጋራ መምከሩ የተገለጸ ሲኾን በብፁዕ ዋና ሥራ አስኪያጁ አማካይነት የጽሑፍ ምላሽ እንደሚሰጥ ተመልክቷል፤ የጎሰኝነት ሰለባ በመኾንና ለአማሳኞች ሽፋን በመስጠት በበታች ሠራተኞች ዘንድ ሳይቀር ክፉኛ እየተናቁና እየተጠሉ በመጡት ፓትርያርክ ዙሪያ የተኮለኮሉትን ጥቅመኞች የማጋለጥ እንቅስቃሴም ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት እየተገለጸ ይገኛል፡፡
  • 22holy-synod-2004-ginbot-annual-meeting-decision-on-mahibere-kidusan 221

 

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ የሚያደርጉትን ሰላማዊ ትግል እንደሚደግፍ አጋርነቱን አሳያ

$
0
0

May 1/2014

በዛሬው ቀን በኖርዌይ በተከበረው አለም አቀፍ የሰራተኞች ቀን ላይ በመገኛት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አንድነትና ሰማያዊ ፓርቲ በሀገር ቤት የሚደረገውን ሰላማዊ ትግል እንደሚደግፍ አጋርነቱን አሳያ::
UDJ & Blue  ሜይ 1, አለም አቀፍ የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን በየአመቱ በመላው አለም በተለያዩ አህጉራት በደማቅ ሁኔታ እንደሚከበር ይታወቃል:: ይህ መከበር ከጀመረ ከመቶ ሃያ አመት በላይ የሆነው የላብ አደሮችና የሰራተኞች ቀን ዘንድሮም ሜይ 1 ቀን 2014 (ሚያዚያ 23 ቀን 2006 ዓ.ም ) በተለያዩ አህጉራት ተከብሮል::   በዛሬውም ቀን ሜይ 1 ቀን 2014 በኦስሎና በኖርዌይ በተለያዩ ከተሞች በደማቃ ሁኔታ የተከበረ ሲሆን የተለያዩ  የፖለቲካ ድርጅቶች፣  በሰብአዊ መብትድርጅቶች፣  ሌሎችም ድርጅቶች እንዲሁም በኖርዊይ የሚኖሩ የተለያዩ ሀገራት  ማህበረሰብ ክፍሎች (community) የየሀገራቸውን ባንዲራ እና የየድርጅታቸውን አርማ በመያዝ የሰራተኛውን መብት መከበር የሚጠይቁና ሌሎችንም የተለያዩ መፈክሮችን፣ አርማዎችን በመያዝ  በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል::   በኦስሎ እና በተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎች የድጋፍ ድርጅቱ ለአባሎቹ ባደረገላቸው የሰልፍ ጥሪ መሰረት ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዚሁ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ የሚደርሰውን የሰብዊ መብት እረገጣ የተቃወሙ ሲሆን ለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውንም ድጋፍ አሳይተዋል:: በአሁኑ ሰአት የወያኔ መንግስት በኢትዮጵያሕዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን የሰበሃዊ መብት እረገጣ ፣አፈና፣ እስራትና ግድያ በመቃወም አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እና ሰማያዊ ፓርቲ ሰለማዊ ትግል እያደረጉ እንዳለና በሰላማዊ ትግል የወያኔን መንግስት እየተፋለሙት እንደሆነ ይታወቃል:: የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አባሎችና አመራሮች የተለያዩ መፈክሮችን በመያዝ እና በማሰማት ለአንድነት እና ሰማያዊ ፓርቲ ያላቸውን የድጋፍ አጋርነታቸውን በማሳየት በደማቅ ሁኔታ አክብረዋል:: ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !!! ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ

ሰበር ዜና፦ በአሮማያ ዩኒቨርሲቲ በፈነዳ ፈንጂ ሰባ ሰዎች ተጎዱ

$
0
0

በሃረር አሮማያ ዪኒቨርሲቲ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በፈነዳ ፈንጂ እግር ኳስ በማየት ላይ በነበሩ ሰባ ተማሪዎች ላይ ጉዳት መድረሱንና አንድ ሰው መሞቱን የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ አስታወቀ።

Breking Newsዝርዝሩን ይዘን እንመለሳለን

በአንድነት ፓርቲ ቅስቀሳ – ቪዲዮ ይዘናል

ካዛንቺስ በሚገኘው ፖሊስ ጣቢያ የታሰሩት የአንድነት አመራሮችና ጋዜጠኛ ፍ/ቤት ቀርበው የ11 ቀን ቀጠሮ ተጠየቀባቸው፡፡

$
0
0

Neb34የአንድነት ፓርቲ ሥራ አስፈፃሚና የአዲስ አበባ ሰብሳቢ አቶ ዘካርያስ የማነብርሃን ፣አቶ ዘላለም ደበበ የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ቋሚ ኮሚቴ አባል እና የፍኖተ ነፃነት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ እንዲሁም የመኪናው ሹፌር ነፃነት ዘገየ ሜክሲኮ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ዛሬ ቀርበው ሰላማዊ ሰልፍ እንጂ ለመኪና ቅስቀሳ አልተፈቀደም ፤ ቅስቀሳውን የደረጉት የተከለከለ ቦታ ነው ድርጊቱም ያደረጉት ሆነ ብለው ብጥብጥና ሁከት ለማስነሳት ነው፣ የዋስትና ቢሰጣቸው ከግብረአበሮቻቸው ጋር በመሆን ሁከት ያስነሳሉ በማለት የዋስትና መብታቸውን ተከልክለው የ11 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ኢቲቪ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ የሚያደርገውን ሰላማዊ ሰልፍ ማስታወቂያ አላስተናግድም አለ፡፡

$
0
0
የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው

የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው

አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) እሁድ ሚያዝያ 26 ቀን 2006 ዓ.ም ለሚያደርገው ሰላማዊ ሰልፍ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ድርጅት አላስተናግድም ማለቱን የአንድነት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ አያሌው ገለጹ፡፡ የህ/ግ ኃላፊው እንደገለጹት ከሆነ ማንኛውንም ህጋዊ አካል ወይንም ዜጋ በእኩልነት ማስተናገድ የሚገባው የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳያቀርብ አናስተናግድም ማለቱ አንድ የሕዝብ አገልጋይ ነኝ ከሚል ተቋም የማይጠበቅ እና ተቋሙ በእርግጥም የህዝብ አገልጋይ አለመሆኑን በድጋሚ በተግባር ያረጋገጠበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡ እንደ ህዝብ ግንኙነቱ ገለፃ ፓርቲው ጉዳዩን በቸልታ እንደማያየው እና ወደ ፍርድ ቤት እንደሚወስደውም ታውቋል፡፡ የኢትዮጵያ ቴሌቪዢን የማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ አቶ ሰይፉ አለምሰገድና ወ/ት ሸዋዬ የማስታወቂያ ክፍል ኤክስፐርት በእጅ ስልካቸው ደውለን ምላሽ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የነሱን ሀሳብ ልናካትት አልቻልንም፡፡

 

 

 

etv

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ (ኢጋመ) ፕሬዝደንት ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ ተሰደደ

$
0
0

betre yacobከሳምንት በፊት የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ ፕሬዝዳንትና ምክትል ፕሬዝዳንት በአፍሪካ ህብረት ጋባዥነት የኢትዮጵያን ችግርና አፈና በተለይ ላይ ሚዲያው ላይ ያለውን ጫና እና ጋዜጠኞች ላይ የሚደርሰውን አፈና ለመግለጽ ወደ አንጎላ አቅንተው ነበር፡፡ በጉዳዩ ሰፊ ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ለአፍሪካ ህብረትም የመፍትሄ ሀሳብ ማቅረቡና ለሰብአዊ መብት ኮሚሽነሩም መልስ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ ስብሰባው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ አገሩ ለመመለስ በሚዘጋጅበት ወቅት የዓለም አቀፍ የጋዜጠኛ ማህበራትን ጨምሮ ሌሎች የዓለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ እሱን ለማሰር የተደረገው ዝግጅት በተጨባጭ ማስረጃ ስላቀረቡለት መሰደዱን የነገረ ኢትዮጵያ ምንጮች ገልጸዋል፡፡ የዞን ዘጠኝ ጦማሪዎች በታሰሩበት ወቅት ፖሊስ የበትረ ያቆብን ቤት በመፈተሸ ያገኘውን ወረቀት ሁሉ እንደወሰደም ምንጮቻችን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አንጎላ በተደረገው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ኮሚሽነሩን በግል እንዳገኛቸውና ኮሚሽነሩም በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ በመግለጽ እንዲሚያገኙት ቃል ገብተውለት እንደነበር ተገልጻል፡፡ በተጨማም ከበርካታ የአፍሪካ ህብረት ባለስልጣናት ጋር ስለ ኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታና በሚዲያው ላይ ስለሚደረገው ጫና የተወያዩ ሲሆን አብዛኛዎቹ በተለያዩ መንገዶች እገዛ ለማድረግ ቃል ገብተውለት እንደነበር ከታማኝ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በስብሰባው ወቅት ኢትዮጵያንና የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክን ወቅታዊ ሁኔታ የሚገልጹ ጽሁፎች ለተሰብሰብሳቢዎቹ ተበትነዋል፡፡

የኢትዮጵያ ጋዜጠኞች መድረክ መቋቋም ያስፈራቸው ሌሎች የጋዜጠኞች ማህበራት በትረ ያቆብን ለሂውማን ራይትስ ዎች፣ ለሲፒጄ፣ ለአርቲክል 19ና ሌሎች የጋዜጠኞች ማህበራት ይሰራል፣ ይሰልላል፣ የእነዚህ ድርጅቶች ተላላኪ ነው፣ ሪፖርት ይጽፋል በሚል በመግለጫቸውና ‹‹የጋዜጠኞች ክብ ጠረጴዛ›› በተባለው ፕሮግራም ይከሱት እንደነበር ጋዜጠኛ በትረ ያቆብ አገር ውስጥ በነበረበት ወቅት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጻል፡፡

ምንጭ፡- ነገረ ኢትዮጵያ


በዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች መልዕክት አስተላለፉ፤ (የረሃብ አድማ መምታት ጀምረዋል)

$
0
0

ZIWAY PRISONበዝዋይ የሚገኙ የፖለቲካና የህሊና እስረኞች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት ጥያቄያቸው እንዲመለስ ጫና ለመፍጠር የምግብ ማቆም አድማ ጀመሩ። አድማው ለ3 ቀን እንደሚቆይ ታውቋል፡፡ ጥያቄያቸውም፡-

1ኛ፦ የፖለቲካው ሥነ -ምህዳር እንዲሰፋና የፓርቲዎች በነፃነት የመንቀሳቀስና የመደራጀት መብት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣

2ኛ፦ አፋኝ የሆኑት የመያዶች ህግ፣ የፀረ-ሽብር ህግ፣ የፕሬስ ህግ እንዲሻሩና ነፃ የሙያ ማህበራት ላይ የሚደረገው አፈና እንዲቀም፣

3ኛ፦ በግሉ ሚዲያ ላይ የሚደረገው ማስፈራሪትና አፈና በአስቸኳይ እንዲቆምና የፕሬስ ነፃነት ሳይሸራረፍ እንዲከበር፣

4ኛ፦ የመከላከያ፣ የፖሊስና የደህንነት አካላት በህገ መንግሥቱ መሠረት የተሰጣቸውን ኃላፊነት በገለልተኝነት እንዲወጡ፣

5ኛ፦ ፍርድ ቤቶች፣ የምርጫ ቦርድ፣ የህዝብ ሚዲያው ነፃና ገለልተኛ ሆኖ እንዲዋቀር፣

6ኛ፦ የፖለቲካ እስረኞች፣ የታሰሩ ጋዜጠኞች እና የህዝበ ሙስሊሙ ተወካዮች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በአስቸኳይ እንዲፈቱ፣

7ኛ፦ በመላ ሀገሪቱ የሚገኙ እስር ቤቶችን በተመለከተ፡-

ሀ) የሰብአዊ መብት ጥሰትን የፈፀሙ ማለትም በድብደባ አካል ያጎደሉና በድብደባ የሰው ህይወት ያሳለፉ የተቋሙ አባላት ህግ ፊት እንዲቀርቡ፣
ለ) በደረቅ ወንጀል ለታሰሩ እስረኞች የሚደረግ ዝውውር፣ ይቅርታ፣ ምህረት እና አመክሮ ህግ በሚፈቅደውና መድሎ በሌለበት ሁኔታ እንዲፈፀም፣
ሐ) በሁሉም እስር ቤቶች ውስጥ ‹‹ጨለማ ቤት›› በመባል በሚጠሩት የብቻ እስር ቤቶች ውስጥ የታሰሩ እስረኞች ከጨለማ ቤቶቹ ወጥተው ከሌሎች እስረኞች ጋር እንዲቀላቀሉ።
መ) የምግብ፣ የውሃ፣ የአልባሳት፣ የግል ንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች አቅርቦት በአስቸኳይ እንዲሻሻል እንዲሁም እስረኞች ከሚጎበኟቸው ሰዎች በወር የሚፈቀድላቸው 1ዐዐ ብር በቂ ባለመሆኑ ክልከላው እንዲነሳ፣ የመረጃ በነፃነት የማግኘት መብታችን እንዲከበር (ሬድዩ የማዳመጥና የግሉ ሚዲያ ውጤቶች የሆኑ ጋዜጦች እንዲገቡልን) የርቀት ትምህርት መማር እንዲፈቀድ፣ ከውጭ የሚላኩልንን ፖስታዎች በአግባቡ እንዲደርሱን።

8ኛ፦ በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 28 ላይ በተደነገገው መሠረት በሰው ልጆች ላይ አሰቃቂ ድብደባና አካል ማጉደል ወንጀል መሆኑን በመፃረር በሀገሪቱ ያሉ የምርመራ ጣቢያዎች በተለይም በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ (ማእከላዊ) ውስጥ ይህንን ወንጀል የፈፀሙና እየፈፀሙ ያሉ የፖሊስና የደህንነት አባላት ለፍርድ እንዲቀርቡ።

9ኛ፦ በሀገራችን ያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ምስቅልቅል በዘላቂነት ለመፍታት መንግሥትና ተቃዋሚ የፖለቲካ ኃይሎች ብሔራዊ መግባባትና እርቅ እንዲያወርዱ። በመጨረሻም በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ ያለችበትን አሳሳቢ ሁኔታ በአግባቡ በመረዳት ልዩነትንና ህልውናን ጠብቆ ለጋራ የነፃነት አጀንዳ በጋራ ተባብሮ መታገል የወቅቱ ዋነኛ ጥያቄ በመሆኑ የሀገሪቱ የፖለቲካ ኃይሎች ሁሉ ተባብረው እንዲታገሉና የኢትዮጵያ ህዝብም ከጎናቸው እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን። በመጨረሻም ከዚህ በላይ በዝርዝር ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ያገኙ ዘንድ ለጊዜው ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው የፖለቲካ እስረኞች ከአርብ ሚያዚያ 24 ቀን እስከ እሁድ ሚያዚያ 26 ቀን የሚቆይ የ3 ቀን የረሃብ አድማ አድርገናል።

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ!!

1ኛ አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚአብሔር
2ኛ አቶ ደረጀ አበበ
3ኛ አቶ ናትናኤል መኮንን
4ኛ አቶ ክንፈ ሚካኤል ደበበ (አበበ ቀስቶ)
5ኛ አቶ አንዷለም አያሌው
6ኛ ሻ/ል የሽዋስ ይሁንአለም
7ኛ አቶ ምትኩ ዳምጤ
8ኛ አቶ አበበ መልኬ
9ኛ አቶ ማንደፍሮ አካልነው
1ዐኛ አቶ ገበየሁ ብዙነህ
11ኛ አቶ ዩሐንስ ተረፈ
12ኛ አቶ መሠለ ድንቁ
13ኛ አቶ ፍቃዱ ባሳዝን
14ኛ አቶ የገባው አለሙ
15ኛ አቶ እሱባለው አሌ
16ኛ አቶ ጥላሁን ባለው
17ኛ አቶ አስቻለው አራጋው
18ኛ አቶ በእውቀት ደሳለኝ
19ኛ አቶ ካሳሁን ጌጡ

ግልባጭ
- ለኢትዮጵያ ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች በሙሉ
- ለተባበሩት መንገሥታት ድረጅት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን
- ለአውሮፓ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚሽን
- ለአሜሪካ መንግሥት የውጭ ጉዳይ መ/ቤት
- ለአፍሪካ ህብረት የሰብአዊ መብት ኮሚች
- ለ Human Rights watch
- ለ Amnesty international
- ለ CPJ እና ለሀገር ውስጥና ለውጭ የሚዲያ ተቋማት በሙሉ፡፡

የማለዳ ወግ … እነሆ የጨለመው ነጋ ! … ነጻ ወጣሁ ! አመሰግናለሁ (ጋዜጣኛ ነብዪ ሲራክ)

$
0
0

ነቢዩ ሲራክ

እነሆ 60 ፈታኝ የመከራ ቀናቶች በትዕግስት ተገፍተው አለፉ ፣ ክፉውን ቀን ለማለፍ የትዕግስት ጽናት ብርታት ተስፋየ ምንጩ በመላ አለም የምትገኙ ወገን ወዳጆቸ ነበራችሁና ላደረጋችሁልኝ እና ላሳያችሁልኝ የሞራል ድጋፍ ልባዊ ምስጋና አቀርባለሁ ! አሰልችውን ቢሮክራሲ አልፈው ፣ በማይጨበጠው ቀጠሮ ሳይሰላቹ ሌት ተቀን እኔን ሀፐነው ታመው ጉዳዬን ለምስለኔ አቅርበው ድቅድቅ ጨለማው እነወዲገፈፍልኝ ያደረጉትን ለማመስገን ቃላት ያጥረኛል ! ለደህንነታቸው ስል በስም ለማንሳት የማይቻለኝ ወንድሞቸ ብርታት ፈጣሪ ታክሎበት ለዛሬው ንጋት ደርሻለሁ ! ተመስገን ! ነግቶም በአይኔ ሲንቀዋለሉ ከነበሩት ብላቴና ልጆቸና ከመላ ቤተስብ ዘመደ አዝማድ ጓደኛ አፍቃሪዎቸ ለመገናኘቴ ምክንያት እናነተ በአካል ከጎኔ የቆማችሁ ነበራችሁና በሁሉም ስም ምስጋና ወደር የለውም !Nebiyu Sirak

ከማዕከላዊው የብሪማን እስር ቤት ወዳጆቸ …በብሪማን ያላፉ ኢትዮጵያውያን የህግ ታሳሪዎች መካከል በግፍ የታሰሩት አሰገራሚ ታሪኮችን ከእናንተው ጋር በአካል ተገኝቸ ” እህ ” ሰምቸ ተምሬባቸዋለሁ ። በእስር ቤቱ ታዛ እና ግድግዳዎች ላይ የጻፏቸው ማስታወሻና ጥቅሶችን ተመልክቸ ተጽናንቸባቸዋለሁ ። አንዷ ተደጋግማ የሰማኋት ጥቅስ ውስጥ እኔም በመከራው ሳልፍ ተስፋን ሰንቄ እዚህ ደርሻለሁ! ” እኔ መውጣት የምፈራው መውጣት ከማልችለው ከመቃብር እንጅ ፣ መውጣት ከምችለው የብሪማን ወህኒ አይደለም! ” ትላለች ! አዎ ያ ቤት መቃብር አይደለም … በተስፋ ኑሩ ! አካላችሁ እንጅ አዕምሯችሁን ማሰር የሚቻለው የለምና ብሩህ ተስፋን ሰንቁ ! ፍትህ ርትዕ የጎደለባችሁን ድምጽ ዛሬም እንደ ትናንቱ ለምሰለኔዎቻችን አሰማለሁ ! አይዟችሁ !

ለእነ እንቶኔ መረጃ ቅበላየን ጠልታችሁ ላሳደዳችሁኝና ላልተሳካላችሁ ! ” ወደ ገደል አፋፍ ገፋነው ! ” በትምክህት የታበያችሁ ፣ ህልማችሁ ያልተሳካ እኩዮችም ቢሆን ያለመታከት በመስራታችሁ በመንገላታቴ አልተጎዳችሁኝምና ደስ አይበላችሁ ! እግሬና እጆቸ በካቴና ታስረው ወደማላውቀው የወህኒ ህይወት ስወረወር የማላውቀውን አውቄ ፣ ተምሬና ኑሮ በመከራ እንዴት እንደሚገፋ እማር ዘንድ ምክንያት ስለሆናችሁኝ አመሰግናችኋለሁ ! አዎ ዛሬ ነጻ ወጥቻለሁ !

ያሳለፍኳቸው 60 የወህኒ ቀናት ራሴን አዙሬ እንዳይ አድርጎኛል። በቀረጣይ ቀናት አረፍ በፍጥነት ከሚስገመገመው የመረጃ ቅብብሎሽ አውድ ገለል ማለት ባይቻለኝም ለአፍታ አረፍ ማለትን መርጫለሁ! በቀጣይ እረፍት ቀናቶቸ ወደ ብላቴና ልጆቸና ቤተሰቦቸ ፣ያለፉ እና በውዝፍ የቀሩትን የቀሩ የአረብ ሃገር ስደቱኛ ህይወት ከጋዜጠኝነት ህይዎት ተሞክሮው ጋር አዙሬ እመለከተው ዘንድ ግድ ይለኛል!

ከአፍታ እረፍት በኋላ እስክንገናኝ ፣ ሁላችሁንም አመሰግናለሁ: )

ሰለም ለሁላችሁ !

ዓረና ለትግራይ ፓርቲ በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እየተወሰደ ያለውን የኃይል እርምጃ አወገዘ

$
0
0

Arena-Tigray-logo (ዘ-ሐበሻ) በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልሎች በተለይም በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው የኃይል እርምጃ ይቁም ሲል ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉአላዊነት ፓርቲ አስታወቀ። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫ “በኦሮሞ ተማሪዎች ላይ በመንግስት ኃይሎች እየተወሰደ ያለው የኃይል እርምጃ ያውግዛል።” ብሏል።

“ለማንኛውም የህዝብ ጥያቄ መልሱ ግድያ ሊሆን እንደማይችል ያምናል።” ያለው ዓረና “የኢህአዴግ መንግስት የህዝብ ጥያቄዎች በአግባቡ መፍትሔ ከማፈላለግ በኃይል ለመጨለቅ መሞከሩ ካለፈው የደርግ ስርዓት መማር አለመቻሉ ያሳያል።” ብሏል።

“ኢህአዴግ ህዝብን ማስተዳደር ባለመቻሉ ምክንያት የህዝብን ተቃውሞ እያየለ በመሄዱ ስልጣን ለህዝብ የሚያስረክብበት መንገድ ማመቻቸት ይኖርበታል።” የሚለው መግለጫው ሰሞኑን እየወሰደው ያለው የኃይል እርምጃ ባስቸኳይ እንዲያቆም ጠይቋል።

“መላው የትግራይ ህዝብ ከተጎጂዎች ጎን እንዲሰለፍና የኢህአዴግን የኃይል ተግባር በግልፅ እንዲያወግዝ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።” ያለው ዓረና ህይወታቸው ባጡ የኦሮሞ ተማሪዎች የተሰማንን ጥልቅ ሐዘን ለመግለፅ እንወዳለን።” ብሏል።
6 killo University

ሰበር ዜና-ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ ልዩ ምርመራ ተደረገበት

$
0
0
ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ

ጋዜጠኛ ነብዩ ኃይሉ

በካዛንቺስ አካባቢ የቅስቀሳ ስራ ይሰሩ የነበሩ አባላት የሚሰሩትን ለመዘገብ ከቀስቃሽ ቡድኑ ጋር የነበረው የፍኖተ ነጻነት ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ነብዩ ሐይሉ በታሰረበት የስድስተኛ ፖሊስ ጣብያ ከተያዘበትና በፍርድ ቤት ከቀረበበት ክስ ጋር በማይገናኝ ጉዳይ ሲቪል በለበሱ ደህንነቶች ምርመራ እንደተደረገበት ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡
የአዲስ አበባ መስተዳድር እውቅና ለሰጠው ሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ስራ ለመስራት ወደ አራት ኪሎና ካዛንቺስ አቅንተው የነበሩት ሁለት የአንድነት አመራሮችና ጋዜጠኛ ነብዩ ሐይሉ ከትናንት ወዲያ ፍርድ ቤት ቀርበው የአስራ አንድ ቀን ቀጠሮ ተጠይቆባቸው ወደ ፖሊስ ጣብያው እንዲመለሱ መደረጋቸው ይታወቃል፡፡
ፖሊስ ተጠርጣሪዎችን በያዘበት ጉዳይ ምርመራ ማድረግ የሚችል ቢሆንም ነብዩን የመረመሩት ሲቪል ለባሾች ከክሱ ጋር ባልተያያዘ መንገድ‹‹ጋዜጠኛ መሆንህን እናውቃለን፡፡ከዞን ዘጠኝ አባላት ጋር ያላችሁን ግኑኝነትም ደርሰንበታል፡፡አዲሱ የጋዜጠኞች ማህበር ከውጪ ድርጅቶች ጋር እንደሚሰራ እናውቃለን››በማለት ማስፈራሪያ አዘል ምርመራ እንዳደረጉበት ምንጮቻችን አጋልጠዋል፡፡

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ከነገው የአንድነት ሰላማዊ ሰልፍ መፈክሮች የተወሰኑት
—–
አንድነት ቅጥር ግቢ ውስጥ ለነገው ሰላማዊ ሰልፍ ዝግጅት ተጧጡፏል፡፡አባላትና አመራሮች መፈክሮቹን ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ ስራዎችን እየከወኑ ይገኛሉ፡፡ከተዘጋጁት መፈክሮች መካከል የተወሰኑትን አቅርበናል፡፡

1027

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>