Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

በሚኒሶታ የተጠራው የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሳይጀመር ተበተነ (አጠቃላይ ዘገባ)

$
0
0

ፖሊስ የአባይ ቦንድ ይሸጥበታል የተባለውን አዳራሽ ዘግቶ እየጠበቀ

ፖሊስ የአባይ ቦንድ ይሸጥበታል የተባለውን አዳራሽ ዘግቶ እየጠበቀ

(ዘ-ሐበሻ) “ይህ ድፍረት ነው፤ ይህ ሁሉ ኢትዮጵያዊ በሚገኝበት ከተማ ያውም ፖስተር ለጥፎ ኑ ቦንድ ግዙልኝ ብሎ መለጠፍ እብደት ነው።” ነበር ያለን በሚኒሶታ የጠራውን የቦንድ ስብሰባ ለማክሸፍ ከተሰባሰቡት ኢትዮጵያውያን አንዱ። “ቀድሞ የወያኔ ስብሰባ በዚህ ከተማ ሲደረግ በድብቅ ነበር። ፖስተር ለጥፈው ኑ! ሲሉን እኔ ይሄ ስድብ ነው፤ ወይም የሚሰሩትን አያውቁም ብዬ ነበር” በማለት ሃሳቡን አካፍሎናል።
የሚኒሶታ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ይሄድባቸዋል በተባሉ አካባቢዎች “የአባይ ቦንድ ቀን” በሚል እሁድ ኦገስት 25 ቀን 2013 ከቀኑ 2ሰዓት እስከ ምሽቱ 8 ሰዓት የቦንድ ሽያጭ የሚገልጽ ፖስተር ተለጥፏል። የዚህን ፖስተር መለጠፍ ያሉ በሚኒሶታ የሚኖሩ አክቲቪስቶች ባለፈው ረቡዕ በቴሌኮንፍረንስ ተገናኝተው እንዴት ይህን ስብሰባ እንደሚያሰናክሉ ተወያይተው ነበር። እንደከዚህ ቀደሙ ወያኔ ስብሰባ ሲጠራ ከውጭ ሆኖ መቃወም ያለፈበት ፋሽን መሆኑን ተስማምተው ስብሰባው ውስጥ ገብቶ ድምጽን ማሰማት በሚል ተስማምተው ቀኑ ተቆረጠ። በሌላ በኩልም በሚኒሶታ የሚገኙ የድምጻችን ይሰማ አባላቶች በከተማዋ በሚገኙ መስጊዶች አርብ ዕለት የአባይ ቦንድ ሽያጭን ለማክሸፍ የተነጋገሩ ሲሆን በዚሁ መሠረት ሁሉም ቀኑን በጉጉት ሲጠብቅ ቆይቷል።
“ወያኔ ገንዘብ አለው፤ 2 ቦታ ስብሰባ አዘጋጅቶ አንዱ ጋር ተቃውሞ ሲደርስበት በሌላው ቦታ ሲያደርግ ቆይቷልና ይህን ለማጥናት በቦንዱ ሻጭ አስተባባሪዎች መሃል የራሳችንን ሰዎች አስቀምጠን ጉዳያቸውን እንከታተል” ነበር ያለን አክቲቪስት ሰለሞን በላይ “ያሰብነው ተሳክቷል” ሲል ለዘ-ሐበሻ ገልጿል።
ከድምጻችን ይሰማ፣ ከክርስትና እምነት ተከታዮች፣ ከተለያዩ የፖለቲካ አቋም ካላቸው ወገኖች የተውጣጡ ኢትዮጵያውያን ስብሰባው ይደርግበታል በተባለው የሴንት ፖል ላኦ ኮምዩኒቲ አዳራሽ ደጃፍ የተገኙት ስብሰባው ይደረግበታል ከተባለው 2 ሰዓት ቀድመው ነበር። ስብሰባው ሊጀመር አንድ ሰዓት ሲቀረው ሕዝቡ የኢሕአዴግ ተወካዮችን ሲመለከት “ድምጻችን ይሰማ፤ ከአባይ በፊት የሙስሊሞች መብት ይከበር፣ እነበቀለ ገርባ ይፈቱ፣ እነእስክንድር ይፈቱ…” የሚል ድምጽ ማሰማት ሲጀምሩ ቦንድ ሽያጩን ከሚያስተባበሩት መካከል ወደ ሕዝቡ በመጠጋት ፎቶ ግራፍና ቪድዮ ለማንሳት ይሞክራል። ህዝቡም ፎቶ አታንሳን፤ ቪድዮ አትቅረጸን በሚል ልጁን ቢቃወሙትም አልሰማም አለ። በአማርኛ ቋንቋ እያናገሩት በትግርኛ ይመልስላቸዋል። “ሃገር ቤት የቀረጻችሁት ይበቃል” በሚል በተነሳው ግብግብ ካሜራ የያዘው የኢሕ አዴግ ተወካይ ክፉኛ የተደበደበ ሲሆን ካሜራውም ተሰባብሮበታል።
ወዲያውኑ የሴንት ፖል ከተማ ፖሊስ ወደ አካባቢው በመድረስ ጉዳዩን ሊያረጋጋ ሲሞክር ጉዳዩ እየተካረረ መጣ። ከ20 የማያንሱ የፖሊስ መኪናዎች አካባቢውን ወረሩት። ቦንድ ለመሸጥ የመጣም፤ ሊቃወም የመጣም በአካባቢው እንዳይደርስ ፖሊስ ቦታውን ከቦት የዋለ ሲሆን የቦንድ ሽያጩም ሳይጀመር በተነሳው ግብግብ ተበትኗል።

የአይን እማኞች ለዘ-ሐበሻ እንደገለጹት የቦንድ ሽያጩን የሚያስተባብሩት ኢሕ አዴጋውያን በሌላ ቦታ ሽያጩን ለማድረግ ቢሞክሩም ሳያሳካላቸው ቀርቷል።
በሚኒሶታ ለአባይ ቦንድ ሽያጭ ስብሰባ ሲጠራ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን ከዚህ ቀደምም እንዲሁ የቦንድ ሽያጩ በ0 መጠናቀቁ ይታወሳል።
ይህን ቦንድ ያስተባበሩትን ወገኖች ዘ-ሐበሻ አግኝታ ለማነጋገር ያደረገችው ጥረት ባይሳካም፤ በቀጣይ እድሉን እንዳገኘን ለማቅረብ እንሞክራለን። ለጊዜው ግን ይህን ተቃውሞ ካስተባበሩት አክቲቪስቶች መካከል ከ2ቱ ጋር ዘ-ሐበሻ ቆይታ አድርጋለች ይከታተሉት።
ቃለ ምልልስ ክፍል 1
[jwplayer mediaid="6706"]

ቃለ ምልልስ ክፍል 2
[jwplayer mediaid="6700"]


Hiber Radio: ኮ/ል መንግስቱ ከዙምባብዌ ባለስልጣናት ጋር በምስጢር መከሩ

$
0
0

የህብር ሬዲዮ ዕሁድ ነሐሴ 19 ቀን 2005 ፕሮግራም

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

<<...ፍቼ ላይ ካድሬዎች ለበላዮቻቸው በመለስ ስም እየቀሰቀሱ ሕዝቡን ሊያስወጡ ሲሉ ከሰውናል ።የእኛ ጉዳይ የመለስ ሳይሆን የነጻነት ጥያቄ ነው ብለናቸዋል..ተጽኖውን ሁሉ ተቋቁሞ ሕዝቡ አደባባይ ወጥቶ ብሶቱን ገልጿል...>> አቶ አበበ አካሉ የአንድነት የም/ቤት አባል ከፍቼ የሰጡት ማብራሪያ ሙሉውን ያዳምጡት

ዶ/ር ማርቲን ሉተር ኪንግ ከዛሬ ሃምሳ ዓመት በፊት ንግግር ያደረገበት አደባባይ ኦባማ ምን አይነት ንግግር ያደርጋሉ? የማርቲን ሉተር ኪንግን ሰላማዊና ጉዞ ወደ ዋሽንግተን ሰልፍ ቃኝተናል፡ በ<<ህልም አለኝ ንግግሩ>> ምን ብሎ ነበር(ወቅታዊ ዘገባ አለን

ስትሮክ ራሱ ብቻውን በሽታ አይደለም የሌሎች በሽታዎች ውጤት ነው።የልብ ህመምና ስትሮክን ማምታታት አያስፈልግም።…የወሊድ መከላከያ የሚወስዱ ሴቶች ሊጠነቀቁ ይገባል…የተለያዩ ሱሶች ስትሮክን ያመጣሉ…ውፍረት ደግሞ …>>

ዶ/ር ኤፍሬም መኮንን ስለ ስትሮክ መንስኤና መከላከያ ለህብር ከሰጡት ሰፋ ያለ ሙያዊ ማብራሪያ የተወሰደ

(ሌሎችም ቃለ መጠይቆች አሉን)

ዜናዎቻችን
- የኦሮሞ መብት ተሟጋች የሆነው ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳ ቃሊቲ እስር ቤት ውስጥ ሞተ

- አሟሟቱ እንዲጣራ ለእንግሊዝ ፓርላማ ጥያቄ ቀርቧል

- የታሰሩት የሙስሊሙ መሪዎች ነገ ፍ/ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል

- መንግስት ሙስሊሙን የሚቃወም ሰልፍ በአዲስ አበባ ሊያደርግ ነው

- በሚኒሶታ ለአባይ ቦንድ ግዢ የተጠራ ስብሰባ በውዝግብ በጸጥታ ሀይሎች ውሳኔ ተቋረጠ

- ኮ/ል መንግስቱ ከዙምባብዌ ባለስልጣናት ጋር በምስጢር መከሩ

- ሙጋቤ ቃለ መሀላ ፈጸሙ

- ጅቡቲ አንድ መቶ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ከመስጠም ታደገች

- ኤርትራ ከኢትዮጵያ ወገን ጦርነት ሊከፈትብኝ ነው የሚል ስሞታ እያሰማች መሆኑ ተገለጸ

- አገዛዙን ለመጣል ያሰቡ ተቃዋሚዎች ጣሊያን ሰሞኑን ይሰበሰባሉ

ሌሎችም ዜናዎች አሉን

ኢሕአዴግ እሁድ በአ.አ ሰላማዊ ሰልፍ ጠራ፤ ድምጻችን ይሰማ “መንግስት ሙስሊሙን እየዘለፈ ነው”አለ

$
0
0

hailemariam and samora(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዛሬ እንደዘገበው “አክራሪዎች በእምነት ስም የህዝብን ሰላም ለማደፍረስ የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በመቃወም እሁድ ነሃሴ 27/2005 ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ገለፀ” ብሏል። በሌላ በኩል ድምጻችን ይሰማ “አክራሪነትን ለመዋጋት ተብለው በተዘጋጁ ስብሰባዎች ጸረ እስልምና የሆኑ ዘለፋዎች እተበራከቱ ነው!” ሲል ተቃውሞውን አሰማ።

ኢሕአዴግ የፊታችን እሁድ በአዲስ አበባ የጠራው ሰልፍ ሁሉም የሀይማኖት ተከታዮች በሰላም አብሮ ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ ነው ሲል ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ “ለእስልምና ጥላቻ ያላቸው የመንግስት ሃላፊዎችና ካድሬዎች አጋጣሚውን የእስልምናን ሃይማኖት ለማራከስ ተግባር እያዋሉት ነው” ብሎታል።

“ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ በእምነት ስም የሀገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ ጥረት የሚያደርጉ አካላትን በመቃወም በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በተደጋጋሚ ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉ የሚታወስ ነው፡፡” ሲል የኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ሲዘግብ ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ “መንግስት አክራሪነትን ለመዋጋት በሚል እያዘጋጃቸው ባሉ ስብሰባዎች የእስልምና ሃይማኖት ላይ ዘለፋዎች እየተሰነዘሩ ነው፡፡ በየክፍለ ከተማውና ወረዳዎች ለካድሬዎች እና የሀይማኖት አባቶች ተብለው በሚካሄዱ ስብሰባዎች ‹‹የእስልምና ሃይማኖት የአክራሪዎች መፈልፈያ ነው››፣ ‹‹እስልምና የሚባል ነገር ነው ሰላም የነሳን›› ከሚሉ ተነስቶ ሌሎችም በርካታ ስድቦች እና ዘለፋዎች እየተንጸባረቁ ነው፡፡ በተለይ ባለፈው ረቡእና ሐሙስ የአዲስ አበባ ፍትህና ጸጥታ ቢሮ ባዘጋጀውና በስድስት ኪሎ ስብሰባ ማእከል በተደረገው ስብሰባ ሲንጸባርቅ የነበረው ስሜት ሕዝቡ ያወረዳቸው የመጅሊስ ሹመኞችን ጨምሮ ኢማሞችን ሁሉ አንገት ያስደፋ እንደነበር ታውቋል፡፡ ብዙዎችንም የመንግስትን አካሄድ በድጋሚ እንዲያጤኑት የጋበዘ ሆኗል፡፡” ብሏል።
muslim1

“የሁሉም ሀይማኖት ተከታዩች በተገኙበት የሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የሀይማኖት ተከታዮቹ አብሮ በሰላም ለመኖር ያላቸውን ቁርጠኝነት ማሳያ መሆኑን የአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በርሁን አርአያ ገልጸዋል” ሲል ዜናውን ያተተው ኢቲቪ የሀይማኖት እኩልነት ባልተከበረበት ወቅት ጭምር ህዝቡ ጠብቆ ያቆየውን የመቻቻልና የአብሮነት እሴት ጥቂት አክራሪዎች ለማደፍረስ መሯሯጣቸውን ለመቃወም ሁሉም የሀይማኖት ተከታዮች በዕለቱ እንደሚሳተፉ ርዕሰ ደብር በርሁን አርአያ ጠቁመዋል ካለ በኋላ እሁድ 27/2005 በሚካሄደው ሰላማዊ ሰልፍ የሁሉም ቤተ እምነት መሪዎች እና ተከታዮቻቸው የሰላም መልእክቶችን በመያዝ ከየአቅጣጫው ወደ መስቀል አደባባይ ያመራሉ ተብሎ ይጠበቃል” ሲል ዘገባውን አጠናቋል።

ድምጻችን ይሰማ በበኩሉ “በዚህ በቢሮ ሀላፊው አቶ ጸጋዬ ሀይለማርያምና በደህነነት መስሪያ ቤት ሀላፊዎች በተመራው ስብሰባ የተገኙና ቀድመው ንግግር የሚያደርጉበት አጀንዳ የተሰጣቸው የፓርቲ ካድሬዎች በከፍተኛ ሁኔታ የእስልምናን ሃይማኖት የሚያራክሱ ንግግሮች ሲያደርጉ ከመታየታቸውም በላይ አንዳንዶች ለእስልምና ያላቸውን ጥላቻ ከመግለጽ ጭምር አንኳ አልተቆጠቡም፡፡ የሱና ምልክት የሚንጸባረቅባቸው አካላትን መንግስት ሊታገላቸው እንደሚገባ ያሳሰቡት እነዚህ ካድሬዎች የእስልምና ሃይማኖት መንፈሳዊ ተግባራትን ሁሉ የአክራሪነትና አሸባሪነት መገለጫዎች አድርገው ሲፈርጇቸው ተደምጧል፡፡ አቶ ጸጋዬ ኃይለማርያም ከመንግስታዊው ሃይማኖት የማጥመቅ ዘመቻ ጀምሮ ሙስሊሙን ህብረተሰብ ሲዘልፉና በሙስሊሞች መካከል የልዩነት እሾህ ለመትከል ሲሯሯጡ የቆዩ ግለሰብ እንደሆኑ በድምጽ ማስረጃ ጭምር መጋለፁ ይታወሳል፡፡” ብሏል።

የአንድነት የራት ምሽት በቶሮንቶ ከተማ

በሐውዜን ከተማ የህዝብ ተወካዩ ህዝብ እያስፈራራ ነው

$
0
0

-ከአብርሃ ደስታ (መቀሌ)

Abrham Destaበሐውዜን ከተማ እየተፈፀመ ያለው ያስተዳደር ብልሹነትና የልማት አድልዎ የህዝብ ቁጣ ከቀሰቀሰ ሰንብቷል። ሐውዜን የከተማነት ደረጃ ተነፍጓታል። ህዝቡም ከወረዳ አስተዳደር ጀምሮ እስከ ዞን፣ ክልልና ፌደራል መንግስት ድረስ የልማት ጥያቄውን ያስተጋባ ቢሆንም አግባብ ያለው መልስ የሚሰጥ የመንግስት አካል ግን ፍፁም አልተገኘም።

ጥያቄውና መነሳሳቱ ቀጥሏል። በጉዳዩ የሐውዜን ወረዳ ባለስልጣናት በሁለት ተከፍሏል፤ (1) የወረዳው ስራ አስፈፃሚ አባላትና (2) የወረዳው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት። የስራ አስፈፃሚዎቹ ቡድን አቶ አሕፈሮም ወ/ገብርኤል በሚባል የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ የሚመራ ሲሆን የህዝቡ ጥያቄ ‘የጠላቶች ፖለቲካዊ መነሳሳት ነው’ በሚል ሰበብ የወረዳው ህዝብ በማስፈራራት፣ በማሰርና በጥቅማጥቅም ለመደለል በመሞከር የልማት ጥያቄው ለማዳፈን የሚጥር ነው።

የወረዳው የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አባላት ግን የሐውዜን ህዝብ እያነሳው ያለው የልማት ጥያቄ አግባብነት ያለውና አስቸኳይ መፍትሔ የሚሻ ጉዳይ መሆኑ አስረግጠው የሚናገሩ ናቸው። በዚህ አቋማቸው ምክንያት የወረዳው የህዝብ ተወካዮቹ ‘ዓረና የላካቸው ጠላቶች’ ተብለው ተፈርጀዋል። (‘ዓረና’ እየተባሉ ያሉ ሰዎች ህወሓትን ወክለው የተመረጡ የህወሓት አባላት ናቸው)።

ስራ አስፈፃሚዎቹ ለምክርቤት አባላቱ ያስፈሯሯቸዋል፤ ከሓላፊነታቸው ሊያባርሯቸውና ሊያስሯቸው እንደሚችሉ ይነግሯቸዋል። በሐውዜን ሁሉ የተገላቢጦሽ ነው። በመርህ ደረጃ ከፍተኛ ስልጣን ያለው አካል ስራ አስፈፃሚ ሳይሆን ምክርቤት ነው፤ ምክንያቱም የምክርቤት አባላቱ ህዝብ ይወክላሉ፣ የህዝብ ተወካዮች ናቸው። ታድያ ስራ አስፈፃሚዎች ካስፈራሯቸው ምን ዋጋ አለው?

የህዝብ ተወካዮቹ (ቢያንስ በመርህ ደረጃ) የመንግስት አካላት ናቸው። ስራ አስፈፃሚዎቹ ግን በገዢው ፓርቲ የተመለመሉ የፖለቲካ ሹማምንት ናቸው። ተወካዮቹ ጥያቄው ሲደግፉ የፖለቲካ ሹመኞቹ ግን ‘ጉዳዩ የፖለቲካ ውሳኔ’ በመሆኑ ህዝቡ ጥያቄውን እንዲያቆም ጥረት ያደርጋሉ።

የወረዳው ህዝብ ተወካዮች ለጥያቂያቸው መልስ ባለማግኘታቸው የወረዳው የፌደራል ምክርቤት (ፓርላማ) ተወካይ ጠርተው ለማነጋገር ወሰኑ። የወረዳው ህዝብ ወክሎ በፓርላማ የተቀመጠው ሰው የወከለውን ህዝብ የመልካም አስተዳደርና የልማት ጥያቄዎች ማንፀባረቅ እንዲሁም መፍትሔ ማፈላለግ ሕገ መንግስታዊ ግዴታው ነው። ህዝብ ሲቸገር ከህዝብ ጎን መሰለፍ አለበት፤ ምክንያቱም የህዝቡ ድምፅ ለማሰማትና ለመወከል ነው ፓርላማ የገባው።

አቶ አረጋዊ አፅብሃ ይባላል። የድምፂ ወያነ ሰራተኛ ነበር። ህወሓትን ወክሎ የሐውዜንን ህዝብ በፓርላማ ለመወከል በወረዳው ተወዳደረ። አሁን የሐውዜን ህዝብ የልማት አድልዎ ሲደርስበት የፓርላማ ተወካዩ ተጠራ። (ሳይጠራም በራሱ መምጣት ነበረበት፤ ምክንያቱም ህዝቡ ከመወክል ሌላ ህገመንግስታዊ ስራ የለውምና።)

አቶ አረጋዊ ወደ ሐውዜን ቢመጣም ጥያቄው ካነሱ የወረዳው ተወላጆችና የምክርቤት አባላት ጋር ለመነጋገር ፍቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። የፌደራል የምክርቤት አባል ሁኖ ከስራ አስፈፃሚዎቹ የፖለቲካ ሰዎች ወግኖ ጥያቄው ላነሳ ህዝብ በጠላትነት ፈርጆ በከጠር ጣብያዎች (ንኡስ ወረዳዎች) እየተዘዋወረ የጣብያና ቁሸት አስተዳዳሪዎች ህዝቡን ጥያቄውን እንዲያቆም እንዲያስፈራሩት እያስፈራራቸው ይገኛል።

የህዝብ ተወካይ ተብሎ የህዝብን ችግር ከመፍታት ይልቅ ህዝብ የልማት ጥያቄ እንዳያነሳ ማስፈራራት ምን ይሉታል? ደግሞስ ህዝብ የመወከል እንጂ ህዝብ የማስፈራራት ስልጣን ማን ሰጠው? የህዝብ ጥያቄ ማንፀባረቅ ሲገባው የህዝብ ጥያቄ ለማዳፈን ጥረት ያድርግ!? ለመሆኑ ስልጣኑ ምንድነው? ለምንድነው የመረጥነው? ሁላችን መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ነው።

አንድ የፓርላማ ተወካይ ስራው በደንብ ካልተወጣ የሚወሰደው እርምጃ ምንድነው? መልሶ መጥራት (Recalling) ከሐላፊነቱ ማባረር። የፓርላማ ተወካዩ ስራ ምንድነው? ህዝብን ወክሎ የህዝብን ጥያቄ በሚመለከተው አካል በኩል መልስ እንዲያገኝ ማድረግ። አሁን ስራው በአግባቡ እየተወጣ ነው? አይደለም። የተሰጠው ሕገመንግስታዊ ሐላፊነት ወደጎን በመተው ተገልብጦ ህዝብ እያስፈራራ ይገኛል። ስለዚህ በሕገመንግስቱ መሰረት ‘የማስመለሻ ትእዛዝ’ (Recalling Claim) ሊሰጠው ይገባል። ካሁን በኋላ የሓውዜንን ህዝብ ወክሎ ፓርላማ ሊቀመጥ አይገባውም። ሌላ የህዝብን ጉዳይ ወክሎ የሚናገር ሰው መመረጥ አለበት።

የሓውዜን ጉዳይ ህወሓትን (የነአባይ ወልዱ ቡድን) በሁለት ሳይከፍል አልቀረም። ጉዳይ በተደጋጋሚ እየተወያዩበት ነው። በህወሓት ማእከላዊ ኮሚቴ አባላት ስብሰባ አቶ ኢያሱ ተስፋይ የተባለ (የማእከላዊ ኮሚቴ አባል) ‘የሐውዜን ጉዳይ መፍታት ያቃተን ለምንድነው?’ የሚል ጥያቄ ያነሳ ሲሆን የሚያረካ መልስ የሰጠ ባለስልጣን ግን አልነበረም።

በአሁኑ ሰዓት (ከሳምንት በፊት ጀምሮ) የሐውዜን ወረዳና የምስራቃዊ ዞን አስተዳዳሪዎች ከክልል ባለስልጣናት ጋር በጉዳዩ በመቐለ ከተማ እየተወያዩና እየተገማገሙ ናቸው። በግምገማው መሰረት (እስካሁን) የሐውዜን ህዝብ ጥያቄ ለማዳፈን የቤት ስራ ተሰጥቶት የነበረ የምስራቃዊ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ገብረ ከስልጣኑ እንዲባረር ተወስኗል።

አቶ ገብረ የሐውዜንን ጉዳይ እንደምንም ብሎ ማስቆም እንዲችል ታዞ የነበረ ቢሆንም ህዝብ ማሳመን አቅቶት ከሐውዜን ኗሪዎች ጋር ተጣልቶ፣ ህዝቡን ሰድቦ፣ ስብሰባ ረግጦ የወጣ ሰው ነው።

ደግሞስ ህዝብ ልማት አያስፈልገውም ብሎ ለህዝብ ማሳመን ይቻላል እንዴ? ከንቱ ልፋት ነው። ህዝብ ማሳመን የሚቻለው ልማት እንደሚያስፈልገው በመንገር እንጂ ልማት እንደማያስፈልገው በመንገርና በማስፈራራት አይደለም። ብቻ ይገርማል።

የሐውዜን ህዝብ የልማት ጥያቄውን የሚጋራ የራሱ ተወካይ ያስፈልገዋል።

አሜን!

መንግሥት ለተፈጠረው ችግር በአስቸኳይ ማስተካከያ እንዲያደርግ እንጠይቃለን!!!!

$
0
0

blue party
ከሰማያዊ ፓርቲ የተሰጠ መግለጫ
ፓርቲያችን ሰማያዊ በህገ መንግሥቱ በተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብቱን ተጠቅሞ ለመንግሥት ጥያቄዎችን በማቅረብ ግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. ታላቅ ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በተሳካ ሁኔታ አድርጓል፡፡
መንግሥት ላቀረብናቸው ጥያቄዎች በሦስት ወር ውስጥ መልስ የማይሠጥ ከሆነ በተጠናከረና በተደራጀ መልኩ ጥያቄያችንን በድጋሚ በህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ እንደምናቀርብ በግንቦት 25/2ዐዐ5 ዓ/ም. በተደረገው ሠልፍ ላይ ለህዝብ ቃል በገባነው መሠረት ነሃሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በድጋሚ ሰልፍ ጠርተን አስፈላጊውን ዝግጅት እያደረግን መሆኑን ለህዝብ በልዩ ልዩ መገናኛ ዘዴዎች ገልፀናል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም ለሰልፉ በሰላም መጠናቀቅ አስፈላጊው ትብብር እንዲደረግልን አዋጁ በሚጠይቀው መሠረት ለአዲስ አበባ መስተዳድር ስብሰባና ሰላማዊ ሰልፍ ማሰወቂያ ክፍል ጉዳዩን እንዲያውቀው አድርገናል፡፡
ይሁን እንጂ ፓርቲያችን ህዝባዊ ተቃውሞ ሰልፍ በጠራበት ግዜና ቦታ ላይ በሌላ አካል ሰልፉ መጠራቱን በትናንትናው ዕለት ነሀሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በመንግሥት ቴሌቪዥን ዜና ሰምተናል፡፡ በተጨማሪም ለመንግሥት መዋቅር ዜጐች በዚህ ሰልፍ እንዲወጡ በግድ እንዲፈርሙ እየተደረገ መሆኑን ከአዲስ አበባ ኑዋሪዎች አረጋግጠናል፡፡
bluee
ሰማያዊ ፓርቲ አስፈላጊውን የህግ ቅድመ ሁኔታ አሟልቶ ነሐሴ 26/2ዐዐ5 ዓ/ም. በመስቀል አደባባይ የጠራውን ተቃውሞ ሰልፍ ለህዝብ ያሳወቀና አስፈላጊውን ዝግጅት ያጠናቀቀ በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ሠዓት በሌሎች አካላት የተጠራው ሰልፍ ከመረጃ እጥረት ከሆነ እንዲሠረዝ እየጠየቅን ይህ ካልሆነ ግን ሰማያዊ ፓርቲ በህጋዊ መብቱ የሚያደርገውን የተቃውሞ ሰልፍ ሆን ብሎ ለመረበሽና አቅጣጫውን ለማስቀየስና በዜጐች መካከል ግጭት ለመፍጠር የታቀደ ስለሆነ ለሚፈጠረው ችግር ተጠያቂ መንግሥት መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብና የሚመለከታቸው አካላት እንዲያውቁት በአፅንዖት እንገልፃለን፡፡
በመጨረሻም መንግስት ዜጐችን ያለፈቃዳቸው በማስፈረም ተገደው ሰልፍ እንዲወጡ ማድረግ ህገ ወጥ ስለሆነ፣ በአስቸኳይ እንዲያቆም እንጠይቃለን፡፡
ነሃሴ 21/2ዐዐ5 ዓ/ም.

የኢህአዴግ ስውር ሴራ በሮቤ ከተማ ተጋለጠ!!! ሐገሪቷን የሚያስተዳድራት ማነው? የባሌ ሮቤ ሰላማዊ ሰልፍ ለምን ተደናቀፈ?

$
0
0

አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትሕ ፓርቲ (አንድነት)

UNITY FOR DEMOCRACY AND JUSTICE PARTY (UDJ)

 

ከአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት) የተሰጠ ማብራሪያ

የሚሊየኖች ድምፅ ለነፃነት ንቅናቄ በአራቱም የኢትዮጵያ ማዕዘናት የነፃነት ድምፅ ማስተጋባት ከጀመረ እንሆ ዛሬ ስልሳ ሰባተኛ(67) ቀኑን ይዟል፡፡ ፓርቲያችን በእዚህ ታላቅ ሕዝባዊ የነፃነት ንቅናቄ መሪር የሆነ ውድ ዋጋ እየከፈለ ድምፅ አልባ ለሆኑት ሚሊዮኖች ኢትዮጵያውያን ድምፅ በመሆኑ ታላቅ ደስታ ይሰማዋል፡፡

ላለፋት ስምንት ዓመታት ሰቆቃ እና ግፍ በገዢዎቻችን ሲፈፀምበት የኖረው የገጠሩም ሆነ የከተማው ታላቁ ህዝባችን ‹አንድነት ፓርቲአችን አስትንፋሳችን› በማለት  አንድነት ፓርቲ ባመቻቸለት ህዝባዊ ስብሰባዎች እና ሠላማዊ ሠልፎች በነቂስ በመውጣት የታፈነ ብሶቱን በግልፅ በአደባባይ ላይ በማሰማቱ ኢህአዴግ እና ህዝቡ ዛሬም ድረስ ተለያይተው እንዳሉ አንድነት ፓርቲ በማያወላዳ ሁኔታ በሚሊዮኖች ድምፅ ንቅናቄ በህዝባችን መሀል በመገኘት አረጋግጧል፡፡

ኢህአዴግ የቀረው በውሸት እና በሴራ የተሞላ የቅጥፈት ፕሮፖጋንዳ ብቻ መሆኑን ይበልጥ ያረጋገጠልን የባሌ ዞን አስተዳደር እና የሮቤ ከተማ አስተዳደር ያዘጋጁት በሀገር ሽማግሌዎች ስም የተቀነባበረው የእናደራድራችሁ አሳፋሪ ድራማ ለኦሆዴድም ሆነ ለኢህአዴግ ታላቅ ውድቀት ነው፡፡

አንድነት ፓርቲ በባሌ ሮቤ ከተማ ሠላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ህጉ በሚያዘው መሰረት ነሐሴ 13/2005 የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያ ደብዳቤ ለከተማዋ አስተዳደር አስገባ፡፡ ጉዳዩን የሚከታተሉት የፓርቲው ተወካዮች ደብዳቤው ከገባ ከ48 ሠዓት በኋላ ወደ መደበኛ ቅስቀሳቸው መግባት እንደሚችሉ ህጉ እንደሚፈቅድላቸው የተረዱት የፓርቲያችን ትንታግ ታጋዮች ጊዜ ሳያባክኑ የተዘጋጀውን የቅስቀሳ በራሪ ወረቀት በከተማ ውስጥ ማሰራጨት ጀመሩ፡፡

ሁኔታውን በቅርብ ሲከታተሉት የነበሩት የፌደራል መንግስት እና የክልሉ መንግስት ከሮቤ ከተማ አስተዳደር ጋር በመቀናጀት አንድነት ፓርቲ ላይ ያጠመዱት ሴራ ለመተግበር የከተማው ከንቲባ አቶ አብዱል ላጥፍ ነሓሴ 13/2005 ለገባላቸው የፓርቲው ደብዳቤ መልስ ያሉትን ነሓሴ 13/2005 ቀን እንደ ተፃፈ ተደርጎ ፓርቲው አላማ ያሉትን ዘርዝረው ነሓሴ 17/2005 ዓ.ም ደብዳቤ ለፓርቲው ተወካዮች ሰጡ፡፡ የተባሉትን ሰበቦች እና ምክንያቶችን በሙሉ አሟልቶ ፓርቲው የእዚያኑ ዕለት በደብዳቤ ምላሽ ቢሰጥም የከተማው አስተዳደር ባለስልጣኖች ከንቲባውም ጭምር ቢሮአቸውን ዘግተው ጠፉ፡፡ መዝገብቤትም ለማስገባት የተደረገው ጥረት በመዝገብ ቤት ሰራተኞች እምቢ ባይነት ሳይሳካ ቀረ፡፡ የአምባ ገነኑን የኢህአድግ ባለስልጣኖችን ነውረኛ ስራ ቀድሞ የሚያውቀው የአንድነት ፓርቲ የተዘጋጀውን ደብዳቤ በሪኮማንዴ በፓስታ ቤት በኩል አንዲደርሳቸው በማድረግ ምንም መፈናፈኛ ሰበብ እንዳያገኙ አደረገ፡፡                                                                                                                            ግራ የገባቸው የከተማው አስተዳዳሪዎች ተሰባስበው ከላይ በተሰጣቸው ትእዛዝ መሰረት አንድነትን የማጥቅያ ሌላ ሴራ ተጠቅመው መጥታችሁ የሰላማዊ ሰልፍ ማሳወቂያውን ቅፅ ሙሉ በማለት ለተወካዮቻችን ጥሪ አደረጉ፡፡ የፓርቲው ተወካዮች ስራቸውን እየሰሩ ቅፁን የሚሞሉ እና የሚፈርሙ አባላትን በመመደብ ተወካይ ብቻ ወደ ወስተዳድሩ ፅ/ቤት ላኩ፡፡ የጠበቃቸው ግን የተቀናጀ ሴራ ነው፡፡ አንድነት ፓርቲን በህግ የሚያስጠይቅ እንዲሁም ያዘጋጁትን የሀይል ርምጃ ህጋዊ የሚያደርግ፤ ደብዳቤ ካስገባን 48 ሰዓታት ባነሰ ጊዜ ሰልፍ እወጣለሁ ብሎ ፓርቲው ነሓሴ 17/2005 ደብዳቤ እንዳስገባ ተደርጎ ይህንኑ ቀን የጠቀሰ ቅፅ አዘጋጅተው የአንድነትን ተወካዮች አንዲፈርሙ ተጠየቁ፡፡ ቀድሞውኑ ሴራው የገባው የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራር በሰጠው መመርያ መሰረት ቅፁ ላይ የምንፈርመው ደብዳቤአችንን ያስገባንበትን ነሐሴ 13/2005 ቀን ከጠቀሰ ብቻ ነው በማለት የአንድነት ተወካዮች አንፈርምም አሉ፡፡

አንድነት ፓርቲን በጉልበትም በህግም ለማኮላሸት ኢህአድግ ያዘጋጀውን ሴራ በጥበብ ማክሸፍ ተቻለ፡፡ ኢህአዴግ ለሌላ ሴራ ማቀንቀኑን ወድያውኑ ተያያዘው፡፡

የፓርቲው ቀስቃሽ ቡድን በ50.000 የሚገመት በራሪ ወረቀት መበተኑን እና ከ5.000 በላይ ፖስተር በእለቱ በመለጠፍ የፓርቲውን መልእክት ለታፈነው የሮቤ ከተማ ህዝብ አደረሰ፡፡ በሁለት መኪና መጠነኛ ቅስቀሳ ካደረገ ከ 1፡00 ሰዓት በኋላ መኪናዎቹ ከነቀስቃሽ ቡድኑ ከነሀሴ 18/2005 እስከ እሁድ ነሀሴ 19/2005 ድረስ በታጣቂዎች ከቆሙበት አንዳይንቀሳቀሱ ታገቱ፡፡ የትራፊክ ፖሊሶችም መኪናዎቻችንን በማገት ያለቆቻቸውን ትዕዛዝ ተግባራዊ አደረጉ፡፡ በዚህ መሀል ነው በሽማግሌ ስም ያደራጃቸውን 15 የሚሆኑ የኦህዴድ ካድሬዎች ‹‹ነገ የሚከሰተው ደም መፋሰስ አሳስቦን ነው የመጣነው እናወያያችሁ›› በማለት ከምሽቱ 1፡30 ባረፍንበተ ሆቴል ተሰባስበው የመጡት፡፡ ለሀገር ሽማግሌ ክብር የሚሰጠው አንድነት ፓርቲ ሽማግሌዎች የተላኩበትን ዝርዝር መልእክት ካዳመጠ በኋላ የእሁዱን ሰላማዊ ሰልፍ በምንም ተአምር እንደማንሰርዘው፤ ይልቁንም የከተማው መስተዳድር ለፖሊስ የሀይል እርምጃ ውሰዱ ብሎ ያስተላለፈውን መመሪያ እንዲስብና ህገመንግስቱን እንዲያከብር ሽማግሌዎቹ ምክራቸውን ለገዢው ፓርቲ ባለ ስልጣኖች እንዲለግሱ መልእክት በመንገር ውይይቱ ከምሽቱ 3፡00 ሰዓት ተጠናቀቀ፡፡ በኢህአድግ የተለመደ ቀመር የቅስቀሳ ጊዜያችንን በጉልበት እና በማስመሰል ለመስረቅ የተደረገውን የተለመደ ቅንብር አንድነት ፓርቲ ቀድሞ የሚያውቀው ጉዳይ በመሆኑ ሁለት ተደራዳሪዎችን ብቻ በመመደቡ ሌላው ግብረኃይል ሳይዘናጋ የቅስቀሳ ወረቀቱን በማሰራጨቱ ኢህአዴግ ያሰበውን አንድነትን የመነጠል ሴራ ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

እነዚያው የሀገር ሽማግሌዎች የተባሉ ግለሰቦች ‹‹መስተዳድሩ አሁን ሊያነጋግራችሁ ዝግጁ ነው፡፡ ቢሮ ድረስ ኑ እና ተወያዩ›› በማለት በሰላማዊ ሰልፉ ቀን እሁድ ከጥዋቱ 1፡00 ሰዓት እኛን ቀጥረውን በሰዓቱ ስንደርስ የኦሆዴድ ባለስልጣኖች ግን የጠዋቱ የቅስቀሳ ስዓታችንን ለመስረቅ ከጠዋቱ 1፡40 በሁለት ኮብራ መኪና እና ታርጋ በሌላት በአንድ መኪና በደህንነት ባለ ስልጣኖች ታጅበው መጡ፡፡

ውይይቱ በዞኑ ም/አስተዳዳሪ አቶ ሰሎሞን አወያይነት የከተማው ከንቲባ፣ የኦሆዴድ ተጠሪ የኮምኒኬሽን ሀላፊ ሌሎችም ከ15 ያላነሱ ባለ ስልጣኖች እንዲሁም በርካታ የሀገር ሽማግሌዎች በተገኙበት ሦስት የመንግስት ካሜራዎች ተጠምደው ውይይቱ ተጀመረ፡፡

የሽማግሌ ካባ የለበሱት የኦሆዴድ ካድሬ የሆኑት የሀገር ሽማግሌዎች ተወካይ ነኝ ያሉት ግለሰብ ውይይቱን በንግግር ሲጀምሩ ‹‹እናንተ የነፍጠኛን ስርዓት ልታመጡብን ነው፡፡ እኛን ሳታነጋግሩ ሳንፈቅድላችሁ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዴት አሰባችሁ? አሁንም ይህንን ሰላማዊ ሰልፍ አታደርጓትም፡፡ የሮቤ ህዝብ እኛን ዎክሎናል መንግስት እንኳን ቢፈቅድላችሁ እኛ ሽማግሌዎች አይደረግም ብለናል አቁሙ›› በማለት የተጫኑትን ዉሳኔ በሚደንቅ ሁኔታ አስተላለፉ፡፡ በእዚያው መድረክ የኢህአዴግ/ኦህዴድ ማንነት እና ጭንብል ለዓለም ህዝብ ተጋለጠ፡፡ አንድነት ፓርቲም ይህንን ከላይ እስከታች ባሉ ባለስልጣኖች የተቀነባበረውን ድራማ በካሜራ ቀርፆ ያስቀረ በመሆኑ በእጃችን የሚገኘውን የውይይቱን ይዘት የያዘውን ቨድዮ እንድትመለከቱ በአክብሮት  እየጋበዝን አንድነት ፓርቲ የኢህአዴግን እውነተኛ ገፅታ በመረጃ ማጋለጡን  አጠናክሮ ዛሬም ነገም ይቀጥላል፡፡

በሮቤ ከተማ ለቅስቀሳ የተላከው ቡድን በመስተዳድሩ ባለስልጣናት ትእዛዝ ከምሽቱ 4፡00 ስዓት አልጋ ከያዙበት ታይታኒክ ሆቴል በግፍ ተባረው፤ የያዙትን ቦርሳ እንኳን ከመኝታ ክፍላችው ሳያወጡ በግፍ አውላላ ሜዳ ላይ ወንጀል እንዲፈፀምባቻው የከተማው መስተዳድር የፍፀመውን መንግስታዊ ውንብድና ፓርቲአችን በዝምታ የሚያልፈው ጉዳይ አይደለም፡፡ የመኪና ሹፊሮቻችንን በውድቅት ሌሊት ጭንብል ባጠለቁ ከ 20 በላይ ታጣቂዎችን በማሰማራት በማስወረር በጉልበት ክፍላቸው ውስጥ በመግባት ስለተፈፀመው ወንጀል አንድነት ፓርቲ በህግ የሚጠይቅ ሲሆን ታላቁ የሮቤ ከተማ ነዋሪ ህዝብ መብቱን ለማስከበር ያደረገውን ትንቅንቅ አንድነት ፓርቲ ከልብ ያደንቃል፡፡ ምስጋናውንም በእዚህ አጋጣሚ ያቀርባል፡፡

ድል ለታፈነው የኢትዮጵያ ህዝብ!!!

   አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ

ነሐሴ 21 ቀን 2005 .

አዲስ አባባ

UDJ

 

 

በሜልበርን ሁለንም ኢትዮጵያዊ ማህበረሰብ ያሳተፈ ጉባኤ ተካሄደ

$
0
0

melboune-news ዲሞክራሲ ለኢትዮጵያ ድጋፍ ቡድን ያሳተባበረውና በሜልበርን የሚገኙ ኢትዮጵያዊ ማህበረሰቦችን ያሳተፈው ጉባኤ ባለፈው እሁድ በደመቀ መልክ ተከናውኗል።

ሙሉውን ዜና ለማንበብ እዚህ ይጫኑ


እሁድ ሰማያዊ ፓርቲና ኢሕአዴግ በመስቀል አደባባይ የጠሩት ሰልፍ እያወዛገበ ነው

$
0
0

‘‘ቀድመን ሰልፍ የጠራነው እኛ ነን’’

 ሰማያዊ ፓርቲ

‘‘የቀደምነው እኛ ነን’’

- የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ

‘‘ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ የሚያካሂደው ሰልፍ ህገ-ወጥ ነው’’

- የአ.አ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ የስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት

 

በዘሪሁን ሙሉጌታ

blue partyeprdf

በመጪው እሁድ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ መስቀል አደባባይ የተጠራው ሰላማዊ ሰልፍ በማወዛገብ ላይ ነው። ቀደም ሲል ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንደሚያካሂድ ቢያስታውቅም፤ የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በበኩሉ ነሐሴ 20 ቀን 2005 ዓ.ም በጽ/ቤቱ በሰጠው መግለጫ በተመሳሳይ ቀን ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ይፋ አድርጓል።
ይህንን ተከትሎ በፓርቲው እና በአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ መካከል የቀደምኩት እኔ ነኝ በማለት በመወዛገብ ላይ ሲሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍና የስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት በበኩሉ፤ ሰልፍ እንደሚካሄድ ቀድመው ያሳወቁት የሃይማኖት ተቋማቱ በመሆኑ በዕለቱ የሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ የሚካሄድ ከሆነ ህገወጥ ነው ብሏል።
የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ጉዳዩን በማስመልከት ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደተናገሩት ፓርቲው ከወር በፊት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያካሂድ በጽ/ቤቱ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ይፋ ማድረጉን በማስታወስ ፓርቲያቸው ሰላማዊ ሰልፉን ለማካሄድ በቅድሚያ ጥያቄ ማቅረቡን ተናግረዋል።
እንደ ፓርቲው ሊቀመንበር ገለፃ ፓርቲው አስቀድሞ ቀን መቁረጡንና በተባለውም ቀን ሰልፉን ለማካሄድ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰላማዊ ሰልፍ፣ ስብሰባና የማኀበራት ፈቃድ ጽ/ቤት በአካል በመቅረብ ጭምር የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተናግረዋል። በወቅቱ ጽ/ቤቱ ደብዳቤውን ለመቀበል ፍላጎት ባያሳይም በህጉ መሠረት ማሳወቅ ብቻ በቂ በመሆኑ ደብዳቤውን በጽ/ቤቱ አስቀምጠው መመለሳቸውንና በኋላም ጽ/ቤቱ በፖስታ ቤት በኩል በሬኮማንዴ ለፓርቲው ሰልፍ የት እንደሚያካሂድ፣ ምን ያህል ሰው እንደሚሳተፍ ማብራሪያ በመጠየቁ ፓርቲው በበኩሉ ለጽ/ቤቱ ወዲያውኑ ምላሽ መስጠቱን ተናግረዋል። ሆኖም ጽ/ቤቱ በህጉ መሠረት በ48 ሰዓታት ውስጥ ምላሽ መስጠት ሲገባው ዝምታን በመምረጡ፣ ዝምታው ደግሞ ሰልፉ እንደተፈቀደ የሚጠቁም በመሆኑ በሰልፉ ዙሪያ ፓርቲው ዝግጅት ማድረግ መቀጠሉን አስታውቀዋል።
ከጽ/ቤቱ እስካሁን (ነሐሴ 21 ቀን 2005 ዓ.ም) ምላሽ ባለመገኘቱም ፓርቲው በዕለቱ የጠራውን ሰለማዊ ሰልፍ ከማካሄድ ወደኋላ የሚመልሰው የህግ መሠረት ባለመኖሩ ሰልፉን እንደሚያካሂድ አስታውቀዋል። ፓርቲው ከነገ ሐሙስ ጀምሮ በአምስት ተሽከርካሪዎች በአስሩም ክፍለ ከተማ መጠነ ሰፊ ቅስቀሳ ለማካሄድ መዘጋጀቱን ተናግረዋል። በመላ ከተማዋና በአካባቢዋም በመቶ ሺህ የሚቆጠር ወረቀት እንደሚበተንና ሰልፉም ካለፈው ሰልፍ ልምድ በማግኘት ከፍተኛ ስራ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ይሁን እንጂ ባለፈው ሰኞ (ነሐሴ 20 ቀን 2005) በዋና ጽ/ቤቱ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን ያስታወቀው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ የቦርድ ሰብሳቢ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ በተለይ ለሰንደቅ ጋዜጣ እንደገለፁት በዕለቱ ሰማያዊ ፓርቲ ሰላማዊ ሰልፍ መጥራቱን እንደማያውቁና ጽ/ቤታቸውም ቀደም ብሎ ሰልፉን ሲያዘጋጅ መቆየቱን ተናግረዋል።
ምንም እንኳ ርዕሰ ደብር በሪሁን አርአያ የሃይማኖት ጽ/ቤቱ በመስቀል አደባባይ ሰላማዊ ሰልፍ ለማካሄድ ያሳወቀበትን ቀን ለመናገር ባይፈልጉም በዕለቱ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በሰጡበት ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ በ10ሩም ክፍለ ከተሞች እና በ116 ወረዳዎች በተካሄደ ሕዝባዊ የሰላም ኮንፈረንስ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፍትህ ቢሮ ጋር በመተባበር በከተማ ደረጃ ነሐሴ 15 እና 16 ቀን 2005 ዓ.ም በተዘጋጀው ማጠቃለያ የሰላም ኮንፈረንስ የተለያዩ ሃይማኖት መሪዎችና ተከታዮቻቸው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማችን እየታየ ያለው የአክራሪነትና የፅንፈኝነት እንቅስቃሴ የሀገራችንን ልማት የሚያውክ፣ በሰላም አብሮ የመኖር እሴቶቻችንን የሚያናጋ እና የሃይማኖት መልክ የሌለው የጥፋት እንቅስቃሴ ከመሆኑም በላይ በሕገ-መንግስታችን የተደነገገውን የኃይማኖት እኩልነትና የእምነት ነፃነት የሚፃረር ስለሆነ በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞአችንን እንግለፅ በማለት የኮንፈረንሱ ተሳታፊዎች መንግስት ሁኔታዎችን እንዲያመቻች፣ የኃይማኖት ተቋማት የጋራ ጉባኤም እንዲያስተባብር መወሰኑን ተናግረዋል።
ከዚህ መግለጫ መረዳት የሚቻለው የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት ሰልፉን ለማካሄድ ጥያቄ ያቀረበው ነሐሴ 15 እና 16 በኋላ መሆኑን መረዳት ይቻላል። በአንፃሩ ሰማያዊ ፓርቲ ነሐሴ 16 ቀን 2005 ዓ.ም የማሳወቂያ ደብዳቤ ማስገባቱን አመልክቷል።
የአዲስ አበባ ሰላማዊ ሰልፍና ስብሰባ ማሳወቂያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ ብዙነህ ጉዳዩን በተመለከተ የእውቅና ጥያቄ በማቅረብ ቀዳሚ የነበሩት የአዲስ አበባ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጽ/ቤት በመሆናቸው ሰማያዊ ፓርቲ በዕለቱ ሰልፍ እንዲያካሂድ አልተፈቀደለትም ብለዋል። ሰልፉ የሚካሄድ ከሆነም ህገወጥ ነው ከማለት ውጪ ሁለቱም ወገኖች የሰላማዊ ሰልፍ ያሳወቁበትን ቀን እና ሌሎች ዝርዝር ጉዳዮችን ከመናገር ተቆጥበዋል።n

(ምንጭ ዛሬ በአዲስ አበባ ታትሞ የወጣው ሰንደቅ ጋዜጣ)

 

የሕወሐት ባለስልጣናት የአሜሪካ ቆይታ፤ የከዱ አሉ – (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

$
0
0

ከኢየሩሳሌም አርአያ

abay welduበአባይ ወልዱ የሚመራውና ሰባት ከፍተኛ የሕወሐት ባለስልጣናት የተካተቱበት ቡድን በአሜሪካ አራት ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ እንደገጠመው በስፍራው የተገኙ ምንጮች አስታወቁ። ቡድኑ በዋሽንግተን ኢትዮጲያ ኤምባሲ በጀመረውና በመቀጠል በላስቬጋስ፣ ሲያትልና ካሊፎርኒያ ከተሞች ባካሄደው ስብሰባ “አላማ” አድርጎ የያዛቸው ጉዳዮች እንደነበሩ የጠቆሙት ምንጮች፣ እነሱም፥ “የመለስ ፋውንዴሽን፣ የአባይ ግድብና የ40/60 የቤቶች ግንባታ.” ሲሆኑ፣ ለነዚህ ማስፈፀሚያ “ገንዘብ አዋጡ” የሚለው ዋናው ግብ እንደነበር አስረድተዋል። በተለይ ደግሞ « በትግራይ ተወላጁ ዘንድ ሕወሐት የለም፣ ተከፋፍሏል፣ ተዳክሟል፣ ፓርቲው ሰው የለውም፤» የሚለውን እራሱ ቡድኑ በማንሳት ለገዛ ጥያቄው መልስ ሲሰጥ « ሕወሐት አሁንም ሃይል አለው፤ አልተዳከመም» በማለት አድራጊ- ፈጣሪ በመሆን ስልጣኑን በበላይነት ተቆጣጥሮ እንደያዘና ቡድኑ የመጣውም “አይዟችሁ” ለማለት እንደሆነ መገለፁን በቅርብ የተከታተሉት ምንጮች አስታውቀዋል። ቡድኑ በተጨማሪም ፥ « ልማት አልምተናል፤ ትግራይ እየለማ ነው፤ ህዝቡን ተጠቃሚ እያደረገነው ነው» ከማለቱ ባሻገር « በትግራይ ተወላጁ ላይ አደጋ ተደቅኗል፤ የሙስሊሙ፣ የትምክህተኞችና የሽብርተኞች አደገኛ እንቅስቃሴ እያንዣበበ መሆኑን፣…የተደቀነብህን አደጋ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤ ያለበለዚያ ግን ሊያጠፉህ ነው፤» ሲሉ መናገራቸውን የገለፁት ምንጮች አክለውም፣ « አባላት የሆናችሁ ተወደደም ተጠላ መሬትና መኖሪያ ቤት እንሰጣችኋለን፤ ለዚህም ከእኛ ጎን መሰለፍ አለባችሁ» በማለት ሊሸነግሉ መሞከራቸውን ጠቁመዋል።

ከዋሽንግተን ስብሰባ (ለሁለት ተከፍሎ ነው የተካሄደው) በኋላ ወደ ሶስቱ ከተሞች ተከፋፍለው እንደሄዱ ሲታወቅ፥ ሲያትል አቶ ብርሃነ ማረት፣ እንዲሁም ላስቬስጋስ አባይ ወልዱና ተክለወይኒ አሰፋ መሄዳቸው ታውቋል። በተለይ በላስቬጋስ ጠንካራ ተቃውሞ የገጠማቸው እነአባይ ስብሰባው ከቀኑ 2፡00 ሰዓት ይጀመራል ተብሎ ከአራት ሰዓት በኋላ ዘግይቶ አመሻሽ ላይ መጀመሩን ምንጮች ገልፀዋል። ስብሰባው ሲጀመር ከላይ የተገለፁትን ጉዳዮች ያደመጠው ተሰብሳቢ ተከታዮቹን ጥያቄ አቀረበ፤ « ዴሞክራሲ አለ ትላላችሁ፣ ነገር ግን ዴሞክራሲ የለም፤ በሃሳብ የሚቃወማችሁን ታስራላችሁ፣ ታንገላታላችሁ፣ የሰብአዊ መብት ረገጣ ታካሂዳላችሁ፤ ከእናንተ የተለየ ሃሳብ ያለውን ትፈራላችሁ፤ ለምንድነው ይህን ሁሉ የምታደርጉት?….በማ.ረ.ት.(ማህበር ረድኤት ትግራይ) በትግራይ ሕዝብ ስም የምትሰበስቡትን ገንዘብ ለአራጣ ብድር እና ለፖለቲካ መጠቀሚያ በመሳሪያነት እያዋላችሁት ነው። ለምን?….ትእምት (ኤፈርት) ማነው ባለቤቱ?..በማን ነው የሚመራው?..ማነው የሚቆጣጠረው?..ለመሆኑ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል ወይ?..እነማናቸው እየተጠቀሙበት ያለው?» የሚሉት ዋና ዋናዎቹ ጥያቄዎች እንደነበሩ ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን፣ አባይ ወልዱ « እኔ አልመልስም፣ ተ/ወይኒ መልስ ይስጥበት» ቢሉም ነገር ግን ግልፅና አግባብ ያለው ምላሽ ከመስጠት ይልቅ ወደ ማመናጨቅና ቁጣ ያመሩት ተ/ወይኒ በዚህ ድርጊታቸው በርካታ ተሰብሳቢዎችን እንዳሳዘኑ አስረድተዋል። በዚህ የተበሳጨው ተሰብሳቢ « ጥያቄያችን አልተመለሰም» በማለቱና ሁከትና ያለመደማመጥ በማየሉ ስብሰባው እንዲቋረጥ መደረጉን የጠቆሙት ምንጮች፣ የጥያቄና ተቃውሞው መብዛት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናቱ የመረጡት ማምለጫ በላስቬጋስ ተወካያቸው በሆነውና መድረክ ሲመራ በነበረው አቶ ተወልደ በኩል፥ « አዳራሹን የተከራየንበት ሰአት አብቅቷል፤ ስለዚህም ስብሰባው አብቅቷል » በማለት በአስቂኝ ሰበብ መቋረጡን አያይዘው ገልፀዋል። እነአባይ ከአዳራሹ ሲወጡ ቀድሞ ውጭ ሆኖ ይጠብቃቸው በነበረው ተሰብሳቢ ውግዘትና ስድብ እንደደረሰባቸው ያስታወቁት ምንጮች « ሌባ..ሌባ…ሙሰኞች..» የሚሉ ተቃውሞዎች ጎላ ብለው እንደተሰሙ አመልክተዋል።

ስብሰባዎቹን የታዘቡ ወገኖች በሰጡት አስተያየት እንዲህ ብለዋል፤ « በአንድ በኩል ልማት እያካሄድን ነው፤ እያሉና ገንዘብ እየጠየቁ በሌላ በኩል “ትግራዋይ አደጋ ተደቅኖብሃል፣ ከጎናችን ሆነህ ተከላከል፤” ማለት እርስ በርሱ የሚጋጭና ድጋፍ የማግኛ የፖለቲካ የፖለቲካ ቁማር ነው። ያልተጠየቁትን የፓርቲውን ህልውና (ስለ ሕወሐት) አንስቶ መነገሩም አስገራሚና አጠያያቂ ነው።» ሲሉ ትዝብታቸውን የጀመሩት እነዚህ ወገኖች በማያያዝም፥ « እነዚህ ሰባት ባለስልጣናት ወደ አሜሪካ የመጡት ከነዘመዶቻቸው፣ ጋሻ ጃግሬዎቻቸው ሲሆን፣ ባለስልጣናቱ የመንግስት ወኪሎች እንደመሆናቸው – በማን ገንዝብ ነው የሚንቀሳቀሱት?..የሚለው መጠየቅ አለበት። በሕዝብ ገንዝብ እየተንፈላሰሱ እንደሆነ ግልፅ ነው። የትግራይ ተወላጁን ብቻ ለይተው ስብሰባ የሚጠሩት ለምንድነው?…በእርግጥ ስላሰቡለት ነው?…የሚሉት ሲፈተሹ .መልሱ በጭራሽ አይደለም ነው። አላማቸውና ትኩረት የሰጡት የትግራይ ተወላጁን እየተንከባከቡት እንደሆነና ተጠቃሚ መሆኑን ለማሳየት በመፈለግ፣ እግረ-መንገዳቸውን ከቀሪው ኢትዮጲያዊ ወገኑ ጋር በመነጠል..ድጋፍ ለማግኘትና በውስጣቸው የተፈጠረውን ቀውስ በዚህ በኩል ቀዳዳውን ለመድፈን የሚደረግ የስልጣን እድሜ ማራዘሚያ ስልት ነው። ..ደግሞስ ሕወሐት “አጋር” ከሚላቸው ብ.አ.ዴ.ን፣ ኦ.ህ.ዴ.ድ.፣ ደቡብ ሕዝቦች ተለይቶ፣ በሕዝብ ገንዘብ ስብሰባ የሚጠራበትና ያሻውን የሚያደርግበት አግባብ ምንድነው?..የሚለው ከዚህ ጋር መታየት ያለብት ነው። ፖለቲካዊ ፍጆታና ማንአለብኝነት በፓርቲው በመነገሱ እንደሆነ ደግሞ ግልፅ ነው።» ብለዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አሜሪካ ከመጡት ሰባት የሕወሐት ባለስልጣናት መካከል- ማለትም አባይ ወልዱ፣ ብርሃነ ኪ/ማሪያም፣ ተ/ወይኒ አሰፋና ዳንኤል አሰፋ በዋነኛነት ሲጠቀሱ፣ ከሰባቱ ሶስቱ ስብሰባውን ሳያካሂዱ ከቡድኑ ተገንጥለው በአሜሪካ መቅረታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል። ቤተሰቦቻቸውን ይዘው (ልጆቻቸውን ጭምር) በመምጣት አሜሪካ ጥገኝነት ጠይቀው መቅረትን የመረጡት ባለስልጣናት ውስጥ የሕወሐት ማ/ኮሚቴ አባላት እንዳሉ ያረጋገጡት ምንጮች በቅርቡ ዝርዝሩን ይፋ እንደሚያደርጉ አስታውቀዋል።

 

 

በፍቼ በአንድነት ፓርቲ አባላት ላይ የደረሰ ድብደባ

የኢሕአዴግ ወታደራዊ ትጥቅ ማምረቻ ፋብሪካ ተቃጠለ

$
0
0

(ይህን የሚሊተሪ ልብስ የሚያመርተው ፋብሪካ ነው የተቃጠለው)

(ይህን የሚሊተሪ ልብስ የሚያመርተው ፋብሪካ ነው የተቃጠለው)

በመከላከያ ሚኒስትር የትጥቅና ወታደራዊ ልብስ ስፌት ፋብሪካ ህንጻ ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የአይን እማኞች ማስታወቃቸውን ኢሳት ራድዮ ዛሬ ዘገበ። የእሳት አደጋ ቃጠሎ በሕንፃው ላይ ጉዳት እንዳደረሰና እንዳወደመ የዘገበው ኢሳት ራድዮ የአደጋውን ምንጭ እያጣራሁ ነው ብሏል።
ከአዳማ ከተማ ወደ ወንጂ በሚወስደው መንገድ ላይ በሚገኘው ወታደራዊ የልብስ ስፌት ፋብሪካ ላይ በደረሰው የእሳት አደጋ በፋብሪካው ላይ ከፍተኛ የንብረት ጉዳት መድረሱን የዘገበው ራድዮው በ18 ሚሊዮን ብር ወጪ በቅርቡ የተገነባው ፋብሪካው የተለያዩ ወታደራዊ ዩኒፎርሞችን ለሀገር ውስጥና ለውጭ ገበያ የሚያቀርብ ሲሆን የደረሰው አደጋ መንስኤ ሊታወቅ አልቻለም ብሏል።
እንደ ራድዮው ዘገባ ከሆነ በፋብሪካው ላይ የደረሰውን ቃጠሎ ለማጥፋት ከአዳማ ከተማ የእሳት ማጥፊያ ባለመኖሩ ደብረ ዘይት ከሚገኘው አየር ሀይል እሳት ማጥፊያ እስከሚደርስ ድረስ የተነሳውን እሳት ማጥፋት አለመቻሉን የአይን እማኞች ተናግረዋል፡፡ ለአንድ ሰዓት ያህል በቆየው የእሳት አደጋ ግምታቸው ከፍተኛ የሆነ ማሽኖች ላይ ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ሲሆን ከአራት ቀናት በፊት መንግስት በከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ የገዛቸው ማሽኖች በፋብሪካው ገብተው እንደነበረ ታውቋል ሲል ኢሳት ራድዮ ዘገባውን አጠናቋል።

ከአደጋው በስተጀርባ ሊደበቅ የተፈለገ የሙስና ወንጀል ይኖር ይሆን?

የኢቲቪው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ ተደበደበ

$
0
0

በኢትዮጵያ ቴሌቭዥን ዜናዎችንና መንግስታዊ መግለጫዎችን በማንበብ የሚታወቀው ጋዜጠኛ ተመስገን በየነ መደብደቡን ጓደኛው ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ አረጋገጠ። ጋዜጠኛ ደመቀ ከበደ “ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው – ጥቂት ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ” በሚል በፌስቡክ ባሰራጨው መግለጫ የጋዜጠኛውን መደብደብ ማረጋገጡን ገልጾ መደብደቡን ግን አውግዟል።

ጽሑፉ ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ በሚል ዘ-ሐበሻ እንደወረደ እንዲህ አቅርባዋለች፦

ኤዲቶሪያል ፖሊሲና ዜና አንባቢ ለየቅል ናቸው -
ጥቂት ነገር ስለ ተመስገን በየነ ጉዳይ

(ከደመቀ ከበደ)

temesgen beyeneከትናንት በስቲያ አንድ ወዳጄ ‹‹ተመስገን በየነ ተደበደበ የተባለው እውነት ነወይ›› ሲል ኢንቦክስ አደረገኝ፡፡ ላጣራና እነግርሀለሁ ብዬው ተለያየን፡፡

****** **** ***** *****
ተመስገንን በቅርበት አውቀዋለሁ፡፡ በጣም ሰላምተኛ፣ ትሁትና ስራውን አክባሪ ነው፡፡ ከውድነህ ክፍሌ ጋር በፋና ኤፍ ኤም 98.1 ላይ የአየር ሰአት ወስደው ይሰሩ በነበረበትና እኔም ከመልቀቄ በፊት ወደ ስቱዲዮ በመጣ ቁጥር የበዛ ትህትናውን እየለመድኩት መጣሁ፡፡ ከዚያ በኋላም ሜሮን ጌትነት፣ አንሙት አብርሀም፣ እሱ /ተመስገን/ እና ሌሎች አምባሳደር ለሆኑለት የልመና ማስወገድ ጉዳይ የተቻለውን ሲያደርግ በዘገባ ጉዳይ ብዙ ተረዳድተናል፡፡ በቃ ስራውን ያከብራል፤ የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈፀም ትጉህና አርአያ ነው – አሁንም ከትህትና ጋር፡፡

ሰሞኑን ስለ እሱ የሰማሁትን በሁለት መልኩ ለማጣራት ጣርኩ፡፡ አንደኛው ከእሱ ከራሱ እና ከባለቤቱ /የቀድሞ ባልደረባዬ እምርታ አስፋው / ጋር ደወልኩ፡፡ የሁለቱም ስልኮች ኦፍ ናቸው በተደጋጋሚ ብሞክርም፡፡ / እስካሁን ድረስ/

ሁለተኛው ከቅርብ ወዳጆቼ እውነቱን ለማጣራት ደወልኩ፤ /ከባለቤቱ ወዳጆችና ከ‹‹አምባሳደርነት›› ወዳጆቹ ማለት ነው፡፡ ከላይ የጠቀስኳቸው ናቸው/
‹‹ጉዳት መድረሱንና ህክምና በመከታተል ላይ›› መሆኑን ነገሩኝ፡፡
‹‹ማን እና ለምን›› ለሚለው ግን መልስ አልነበራቸውም፡፡ ሊኖራቸውም አይችልም፡፡

ከተደጋጋሚ ሙከራዬ በኋላ የባለቤቱ /ከደቂቀቃወች በፈት/ እምርታ ስልክ ጠራ – አነሳችው፡፡
‹‹አሁን በመልካም ጤነነት ላይ ይገኛል፡፡ ትንሽ ቆይተህ ደውልለትና ራሱን አናግረው፤ አሁን ደክሞት ሰለተኛ ነው እንጅ እየተሸለው ነው፡፡›› አለችኝ፡፡
‹‹ምክንያቱ ግን ምንድን ነው›› ስል ደገምኩ ጥያቄዬን፡፡
‹‹አላወቅንም፤ ጉዳዩን ፖሊስ ይዞታል፡፡ ከተጣራ በኋላ እንነግርሃለን›› ብላኝ ‹‹እግዜር ይማረው ብዬ›› ተለያየን፡፡

የሆነውን እስኪ ከሰብአዊነት ብቻ እየመዘንን ‹‹እየተወሩ ያሉ›› ምክንያቶችን እንይ፡፡ ሰብአዊነትን ሰው ከመሆን ጋር ብቻ ሚዛናችን ነው!!

‹‹ተመስገን የተደበደበው በኢቴቪ ዜና የተነሳ ነው›› – እንበል፡፡ ‹‹ማን ደበደበው›› የሚለውን ማጣራቱ ለኔ ፅሁፍ ጠቃሚ አይደለምና ብዙ አልዘላብድም፡፡ ግን ‹‹በኢቴቪ ዜና የተቆጡና የተበሳጩ አካላት ወይም ግለሰቦች ነናቸወው ከተባለ ይሀህ መታየት አለበት፡፡

በሚዲያ ህግ አንድ የሚዲያ ተቋም የሚተዳደረው ‹‹በኤዲቶሪያል ፖሊሲው›› ነው፡፡ የሚዲያ ህገ መንግስት ይባላል፡፡ ይህ ‹‹ኤዲቶሪያል›› እንደየ ሚዲያው ፍላጎት፣ እንደየ ሚዲያው ማሰራጫ አገር፣ እንደየሚዲያው ገዥዎች እሳቤና እውቀት የሚወሰን ነው፡፡ እንደኛ አገር ባሉ ታዳጊ አገራት የሚዲያዎች ኤዲቶሪያል ፖሊሲ ከአገሪቱ ህገ – መንግስት ጋር የተቆራኜ ነው፡፡ የመንግስት ጣልቃ ገብነት ይበዛበታል፡፡ ኢቴቪም ከዚህ የወጣ እንዳልሆነ መንገር ለቀባሪ ማርዳት ይሆናል ፡፡

ታዲያ በማንኛውም ሚዲያ ተቀጥሮ የሚሰራ ሁሉ / ይህ የግል ሚዲያዎችንም ይጨምራል/ ኤዲቶሪያሉን አክብረው የመስራት ግዴታ አለባቸው፡፡ በኤዲቶሪያሉ ያልተስማማ መልቀቅ ብቻ ነው ምርጫው፡፡ ጋዜጠኞች የቤቱ ኤዲቶሪያል ፈፃሚ ሲሆኑ አለቆች ደግሞ አስፈፃሚ ናቸው፡፡
ወደ ዜና አንባቢዎች ስንመጣ ደግሞ፤ ዜና አንባቢዎች የተሰፃቻን ዜናች ያላንዳች መነካካት የሚያነቡ ናቸው – ፖስተኛ ማለት ነው ዜና አንባቢነት፡፡ የተሰጠህን መቀበል ብቻ!!

የሙሉ ጊዜ ዜና አንባቢ / የሚዲያው ቋሚ ተቀጣሪ/ እና የፍሪላንስ ዜና አንባቢዎች አሉ፡፡

ተመስገን በየነ የፍሪላንስ ዜና አንባቢ ነው፡፡ የኢቴቪ ጋዜጠኞች የሰሩትን ዘገባ ከማንበብ የዘለለ ምንም ሚና የሌለው፡፡ እንደ ጋዜጠኛ ወጥቶ መረጃ ቃርሞ ወይ ኤዲት አድርጎ የማቅረብ አንዳች ተልዕኮ የለውም፡፡
ይህን ነው ‹‹ለምን›› እንድል ያደረገኝም ፤ ብዬም ወደእናንተ ያስፃፈኝም ‹‹ይኸወ የአንባቢነት እንጅ የመረጃ ቃራሚነት ወይም ሃያሲነት›› ሚና የሌለው መሆኑ ነው፡፡

አሁንም ‹‹ተደባዳቢው›› አካል ማንም ሆነ ምንም ድርጊቱ ትክክል ነው ብዬ አላምንም፡፡ ‹‹ድብደባ›› በሰው ልጅ ላይ ተገቢ አለመሆኑን የማልደግፈው ሰው በመሆኔ ብቻ ነው፡፡ ምናልባት ያነበባቸው ዜናዎች ያስቆጡት ‹‹አካል›› ወይም ‹‹ግለሰብ›. የፈፀመው ከሆነ ለኔ ‹‹አህያውን ፈርቶ ዳውላውን›› ይሆንብኛል፡፡ አሁንም እደግመዋለሁ ፤ ተመስገን በዜና አንባቢነቱ ከሆነ የተደበደበው ነውር ነው – ፖስተኛ ሳይሆን ፖስታውን የፃፈው ነው መጠየቅ ካለበት መጠየቅ ያለበት፡፡ / መደብደብ ያለበት አላልኩም/

እህስ ሌላ ጉዳይ አስደብድቦት ከሆነስ ብለን እንጨምር፤

ዘረፋ የሚፈፅሙ ማጅራት መቺዎች ከሆኑም ‹‹ህግና እግዜር›› መፍትሄ ይሰጡት ዘንድ እመኝለታለሁ፡፡

በማንኛውም ምክንያት ‹‹በቂም ተነሳስቶ›› ተፈፅሞ ከሆነም ‹‹ከድብድብና ስድብ›› ወደ ቅርርብና ፍቅር መምጣት ይቻላል ባይ ነኝ፡፡ በእኔ እምነት ሰውን ከማያግባባው የሚያግባባው ነገር ይበልጣል፡፡ ፍቅር ያሸንፋል!!

የደህንነት ከፍተኛ ባለስልጣን በቁጥጥር ስር ዋለ

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

ህወሓት በሁለት ቡድኖች መከፈሉ ይታወቃል። የደህንነት ሓላፊዎችም እንዲሁ በሁለት የተከፈሉ ናቸው። ሁለቱ የደህንነት ሓላፊዎች አቶ ጌታቸው አሰፋና አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል ናቸው። በሁለቱም ከፍተኛ ጠብ አለ። አቶ ጌታቸው የነ አርከበ ቡድን ሲሆን አቶ ወልደስላሴ ግን የነ አባይ ወልዱ ሁኖ የወይዘሮ አዜብ መስፍን የቀኝ እጅ ነው።

ሁለቱም የደህንነት ተጠሪዎች በደም የሚፈላለጉ ናቸው። ባለፈው የህወሓት ጉባኤ አቶ ወልደስላሴ ለማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት ተጠቁሞ አቶ ጌታቸው ጠንከር ያለ ትችት በማቅረቡ ሳይሳካለት ቀርተዋል። መለስ በህይወት እያለ (በአዜብ ምክር መሰረት) አቶ ጌታቸውን በአቶ ወልደስላሴ ለመተካት አቅዶ ነበር (ሞት ቀደመው እንጂ)።

አቶ ጌታቸው ለመለስ ከማይታዘዙ የህወሓት መሪዎች አንዱና ዋነኛው ነው። ከመለስ ጋር በብዙ ነጥቦች ላይ አይስማሙም፤ የተባለውን ሁሉ የሚሰማ አይደለም። ጠንካራ ነው። ከሙስና የፀዳ የህወሓት ባለስልጣን አቶ ጌታቸው አሰፋ ነው።

የትግራይ ቡድን የአዲስ አበባውን ለማሸነፍ በመለስ ራእይ ስም ከህዝብ መነጠል ችላል። የአዲስ አበባው ደግሞ በሙስና ሰበብ የትግራይ ቡድኑን እያሰረ ይገኛል።

ዛሬ የኢህአዴጉ ሚድያ ‘ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት’ የሃገር ውስጥ የደህንነት መምሪያ ሃላፊው አቶ ወልደስላሴ ወልደሚካኤል በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ስር መዋላቸው ነግሮናል። ጥሩ መጠላለፍ መሆኑ ነው። አቶ ወልደስላሴ የነ አቶ ገብረዋህድ ጓደኛ ነው። አቶ ወልደስላሴ ከታሰረ ወይዘሮ አዜብ መስፍንስ?

ለማንኛውም ቸር ያሰማን!

ድምፃችን ይሰማ ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት አክራሪነትን እንደማይደግፍ በመግለጽ ኢሕአዴግን ሊያሳፍረው ነው

$
0
0

ከድምጻችን ይሰማ

የትኛውንም አይነት አክራሪነት ሙስሊሙ ህብረተሰብ እንደሚያወግዝ በእሁዱ ሰልፍ በአደባባይ ያስመሰክራል!
ጁምአ ነሐሴ 24/2005

‹‹አክራሪነትን ሕገ-መንግስቱ ቢፈቅድ እንኳን አንቀበለውም!›› ኮሚቴዎቻችን

ለዚህች አገር ሰላም እና ደህንነት መንግስትን ጨምሮ ሁሉም ወገን ከአክራሪነት ሊርቅ ይገባዋል!

muslim1አክራሪነት ማለት ድንበር ማለፍ ማለት ነው፡፡ አክራሪነት ዜግነት የለውም፣ በእምነት አይወሰንም፣ በቦታ አይከለልም፣ በሐገር አይለይም፡፡ በግል፣ በህብረት፣ በመንግስት ደረጃ ሊከሰት የሚችል ነው፡፡ አክራሪነትን ከማንም በፊት ያወገዙት ነብያችን (ሰ.ዐ.ወ) ስለሆኑና የጥፋት አቅጣጫ መሆኑን ስለጠቆሙን አክራሪነትን ለመቃወም ከማንም በፊት ቀድመን የምንገኘው እኛው ነን፡፡ አክራሪነትን የምንቃወመው መሰረታችን ለአክራሪነት የሚመች ስላልሆነ ነው፡፡ ተቻችሎ መኖርም ቋሚ አጀንዳችን ስለሆነ ነው፡፡ ለዚህች አገር በሰላም መኖር ሁሉም ወገን ከሁሉም አይነት አክራሪነት ርቆና እውነተኛ የሰላም ፈላጊ ሆኖ መኖር አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው፡፡ ህዝቦች በጋራ በተግባቡበት ህግ በሰላም የመኖር፣ በሃይማኖቶች መካከል መከባበር የአስተምህሮታችን መሰረት ሲሆን በሚሊዮኖች ፊርማ ወክለን በግፍ የታሰሩትን ኮሚቴዎቻችንን ጨምሮ መስዋእትነት የምንከፍልለት ሰላማዊ ትግላችን በኢትዮጵያ የሃይማኖት ነፃነት እና የሃይማኖቶች ተከባብሮ የመኖር ሂደት አካል ነው፡፡ አክራሪነት ማለት ግን ዛሬ ፖለቲከኞች እንደሚጠቀሙት ተለክቶ እንደሚሰፋ ልብስ ሊያጠቁት የሚፈልጉትን አካል ሁሉ በልክ በልኩ አሰፍተው አልብሰው የሚያጠቁበት መቆመሪያ አይደለም፡፡

ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ለሁለት አመታት ስንቃወም የኖርነውም መንግስታዊ ሃይማኖት (አህባሽ) በመንግስት ሙሉ እቅድ እና ትግበራ አማኞችን ለመከፋፈልና የእርስበርስ ፀብ ለመፍጠር ከሌሎች ሃይማኖቶችም ጋር አብሮ የመኖር ገመድን ሊበጥስ ‹‹ከመንግስት የወረደ ነውና ተቀበሉት›› ተብሎ ስለተጫነብን ነው፡፡ መሪዎቻችንም ሆኑ በሺ የሚቆጠሩ ንፁሃን በእስር የሚማምቅቁት ብሎም በርካቶች የሞቱትና የተደበደቡት ‹‹እኔ ከመረጥኩላችሁ ውጭ ትክክለኛ እምነት የለም›› የሚልን አክራሪነት በመቃወም እንጂ በሌላ አይደለም፡፡ መንግስት የእምነት መብት መጠየቃችንን አክራሪት ሲል ፈርጆታል፡፡ ይህ መብት መጠየቅን በአክራሪነት የሚፈርጅ ፖለቲካዊ አክራሪነትን በፅኑ እናወግዛለን፡፡ በሃገራችን ተጨባጭ ፅንፈኛ የፖለቲካ አካሄድ የትክክለኛው አክራሪነት መፈልፈያ መሆኑን እያየን ነው፡፡ በዚህ አክራሪነት ከማንም በላይ የተጠቃነው እኛ ነንና አክራሪነትን በፅኑ እናወግዘዋለን፡፡ ይህንንም ለማሳየት ነው የእሁዱን ሰልፍ የምንሳተፈው፡፡

የነሃሴ 26 ሰልፍ ህዝበ ሙስሊሙ ከሌላ ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቹ ጋር የሚገናኝበት፣ ስለሃገሩ ስላም ያለውን ቀናዒነት የሚያሳይበት መድረክ በመሆኑ ሙስሊሙ ከሌሎች ሃይማኖት ተከታይ ወንድሞቹ ጋር ሰላምታ በመለዋወጥ አድራሻ በመለዋወጥ ጠንካራ አብሮነትን የሚያጠናክርበት ነው፡፡ ትናንት የጥምቀት በዓሉን ታሳቢ በማድረግ የተቃውሞ መርሃግብሩን የከለሰለትና ቦታ ከቀየረለት ህዝበ ክርስቲያን ጋር ነሃሴ 26 በአንድነት ቆሞ አክራሪነትን በጋራ እያወገዘ ሰላማዊነቱን ያስመሰክራል፡፡ በተጨማሪም የነሃሴ 26 የቅዋሜ መድረክ ከሁሉም እምነት ተከታዮች ጋር ያለንን ትስስር የምናጠናክርበትና ሰላማዊ የመብት ጥያቄአችንን ይበልጥ የምናስረዳበት መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ሰልፉን እንደጠራው የሚነገርለት የሃይማኖት ጉባኤ ውስጥ ያሉ የሃይማኖት አባቶች ለዚህች ሃገር እውነተኛ የሰላም አስተማሪና ተጠሪ መሆናቸውን፣ ለችግሮች መፍትሄ በማፈላለግ በመሰለፍ ሃገራዊ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ አደራ የምንልበትም ዕለት ነው፡፡

ሰልፉ የሃይማኖቶች ጉባኤ ከሚባለው ተቋም ጋር ህዝብ የሚኖረው የመጀመሪያ የአደባባይ ግንኙነት በመሆኑ የተቋሙን አሰላለፍ በተግባር ለማየት ምቹ አጋጣሚ ነው፡፡ በመሰረቱ የሃይማኖቶች ጉባኤ መንፈሳዊ መሪዎች ያሉበት በመሆኑ ‹‹አክራሪነትን እናወግዛለን›› በሚል መሪ ቃል በጠሩት ሰልፍ የአደባባይ ውንብድና ቢፈፀም በወከላቸው አማኝ እና በተወከሉለት እምነት ላይ ታላቅ ክህደትን መፈፀም ነው የሚሆነው፡፡ መንግስትም ይህንን ሰልፍ ለርካሽ የፖለቲካ ትርፍ ለማዋል ከተሯሯጠ በሃገሪቱ እምነት የሚጣልበት ነፃ ተቋም ፈፅሞ አለመኖሩን ማስመስከር ሲሆን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ መግባቱን ደግሞ ያለ እፍረት መደበኛ ተግባሩ እንዳደረገው ለመላው ኢትዮጵያዊ በገሃድ የሚያውጅበት አጋጣሚ ይሆናል፡፡ በዚህ አጋጣሚም መንግስት ሰልፉን ለሃገራዊ መግባባት እንዲያውለው አጥብቀን እንጠይቃለን፡፡ ዜጎች በሃይማኖታቸው ተከብረው መብት በመጠየቃቸው ሳይሸማቀቁና ሳይበደሉ የሚኖሩባትን ኢትዮጵያ ለቀጣዩ ትውልድ ለማቆየት መልካም አጋጣሚ በመሆኑ መንግስት እድሉን በአወንታዊ መልኩ ሊጠቀምበት ይገባል እንላለን፡፡

ከዚህ ውጭ ግን ‹‹የሃይማኖቶች ጉባኤ ጠርቶታል›› ለተባለው ሰልፍ ተሳትፎ መንግስት የህዝብን ጓዳ ማስጨነቁ፣ ሰልፉን በማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ሙሉ በሙሉ በማስፈፀም በሃይማኖት ውስጥ ጣልቃ ገብነቱን በግልፅ እያሳየ ነው፡፡ መንግስት ‹‹አክራሪነትን እዋጋለሁ›› በሚል ሽፋን እምነታችንን ክፉኛ ጣልቃ ገብቶበታል፡፡ አሁን ደግሞ ‹‹አክራሪነትን እናወግዛለን›› በሚል ሽፋን ህዝብን በግዳጅ ጭምር በማስወጣት ይህን ሰልፍ ከሃገራዊ መግባባት ይልቅ ለእኩይ አላማ ሊጠቀምበት አስቦ ከሆነ ተግባሩን በፅኑ እናወግዛለን፡፡ ይህ ተግባር የመንግስት መዋቅር ከዚህ ቀደም ፖለቲካን ሽፋን አድርገው የሃይማኖት እና የቡድን አጀንዳን ለማስፈፀም ለሚሯሯጡ አመራሮች እንደተጋለጠ ሁሉ፤ አሁን ደግሞ በሙሉ መዋቅሩ በሃይማኖት ሽፋን ፖለቲካዊ ቁማር ለመጫወት አስቦ ከሆነ በፅኑ እናወግዘዋለን፡፡

በመሆኑም ይሄን ሽፋን ገልጠን በማውጣትና መንግስት ሊደበቅበት ያሰበበትን ካባ በማውለቅ ‹‹አክራሪነትን አዎ እናወግዛለን!››፣ ‹‹በአክራሪነት ሽፋን ግን በእምነታችን ጣልቃ መግባትንም በተመሳሳይ እናወግዛለን›› ልንል ወደ ሰልፉ እንተማለን፡፡ በሰልፉ ላይ በመገኘት መንግስት ሰልፉን ከተቀመጠለት ስያሜ ውጪ ለህገ ወጥ ተግባሩና ፖለቲካዊ ትርፍ ማጋበዣው መጠቀሚያ እንዳያደርገው እናደርጋለን፡፡ ሃላፊነት በጎደለውና ከልክ ባለፈ ንቀት የሙስሊሙን እምነት ለመበረዝ ሲሞክርና አማኙን በማንገላታት ለመፍጠር የታለመው ሀገራዊ ትርምስ አልሳካ ሲል ዛሬ አሰላለፍን በመቀየር በሃይማኖቶች ሽፋን ህዝብን በህዝብ ላይ ለማነሳሳት የተቀመረ ስሌት ካለ እንደማይሳካ የፊታችን እሁድ በተግባር እናስመሰክራለን፡፡ ይህን ክፉ ራዕይ ዳግም መና ለማስቀረት ዛሬም ከሃገር ወንድምና እህቶቻችን ጋር እምነትና አስተሳሰብ ሳይለየን እጅ ለእጅ በመያያዝ ለዘመናት በገዢዎች ያልተናደውን አንድነታችንን እናጠናክራለን፡፡

የነሃሴ 26 ሰልፍን ስንሳተፍ አክራሪነትን በመቃወም እና አብሮነትና ተቻችሎ መኖርን በተግባር እናሰይበታለን፡፡ ሆኖም አክራሪነትን ከመቃወም ውጭ በሰልፉ ላይ የሚስተናገዱ ማንኛውንም አይነት አፍራሽ መርሃ ግብሮች ካሉ በፅኑ እናወግዛለን፡፡ ሁሌም ደጋግመን ስንገልጸው እንደነበረው ሁሉ የሙስሊሙ ህብረተሰብ ጥያቄም ሆነ እንቅስቃሴ ሰላማዊ፣ አገራዊ እና ህዝባዊ መሆኑን እንዲሁም ይምነት እንጂ የፖለቲካ ጉዳይ አለመሆኑን እና ከመብት እና የፍትህ ጥያቄ ውጭ የተለየ መልክ እና ይዘት እንደሌለው ለሁሉም ኢትዮጵያውያን አሁንም ደግመን ማስረገጥ እንሻለን:: በመሆኑም ሙስሊሙ ኅብረተሰብ በሙሉ ከእነ ቤተሰቡ ነቅሎ በመውጣት በእሁዱ የተቃውሞ መርሐ ግብር ላይ እንዲሳተፍ ጥሪ ተላልፏል፡፡ ሁላችንም እዛው እንገናኛለን፡፡ ለእለቱ ከሚቀመጠው መርሐግብር ክንውን ሳንላቀቀ የተቀመጠውን ብቻ በመፈጸም አክራሪነትን ከሌሎች ኢትዮጵያውን እህቶችና ወንድሞች ጋር በመሆን በተግባር እናወግዛለን፡፡

የነሀሴ 26 መርሐግብር አፈጻጸም በተመለከተ
ጁምአ ነሐሴ 24/2005

በዕለቱ መደበኛውን የሰልፍ መርሃግብር ሙሉ በሙሉ በቋሚነት የምንከተል ሲሆን በተጨማሪ ግን

* ሁሉም የሃይማኖት አባቶች ሰላምን፣ ፍቅርን እና መቻቻልን እንደሚሰብኩ፣ እኩይ ተግባራትን እና አክራሪነትን እንደሚቃወሙና የሰላም እንደራሴዎች እንደሆኑ ለማሳየት እንዲሁም የሃይማኖት አባቶቹ ለወከሉት እምነትና በእምነቱ ስር ላሉ አማኞች ያለንን ክብር ለማሳየት ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት የማናምንበትን ወይም ሞራላችንን የሚነካ ንግግር ቢያደርጉ እንኳ በጥሞና ንግግራቸውን እናደምጣለን፡፡ በምንም መልኩ የሃይማኖት አባቶቹ ንግግር ሲያደርጉ ንግግራቸው እንዲቋረጥ አናደርግም፡፡ ንግግራቸውን እንዳጠናቀቁም የሰላም መገለጫ የሆነ ነጭ ነገር እናውለበልባለን፡፡ ለዚህም መሃረብ፣ ነጭ ወረቀት፣ ሶፍት እና መሰል ቀላል ነገሮችን መጠቀም እንችላለን፡፡

* ህዝብ በይፋ ባወረደው ህገ-ወጥ የቀበሌ ሹመት የመጡ የመጅሊስ ሹመኞች ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት ንግግራቸውን እስኪጨርሱ ያለምንም ድምፅ ሁለቱንም ጆሯችንን በመዳፋችን ደፍነን እንቆያለን፡፡

* ንግግር የሚያደርጉ የመንግስት ባለስልጣናት ካሉ በሚሊዮኖች ፊርማ የወከልናቸው ኮሚቴዎቻችንን በማሰር መላውን መብት ጠያቂ ህዝበ ሙስሊም ያሰሩ መሆናቸውን ለመግለጽና የነጠቁንን መብታችንን በመመለስ ሕዝቡን ከእስራት እንዲፈቱት ለመጠየቅ ንግግራቸውን እስኪጨርሱ ያለምንም ድምፅ ሁለት እጃችንን ወደላይ ከፍ አድርጎ በማንሳትና በማጠላለፍ ምልክት ብቻ እናሳያለን፡፡

ማስታወሻ፡-

- ወደሰልፉ የምንሄደውም ሆነ የምንመለሰው ሌሎች የሰልፉ ተሳታፊዎች በሚሄዱበት ሁኔታ ሲሆን በዋናው መርሐግብር ላይም ሆነ ከዚያ በፊት እና በኋላ ከተጠቀሱት ውጭ ሌላ ምንም አይነት እንቅስቃሴ ማድረግ በጭራሽ የለብንም፡፡


“ትግላችን የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር ተሸጋግሯል!”–ሰማያዊ ፓርቲ

$
0
0

semayawi partyሰማያዊ ፓርቲ ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ.ም. ባካሄደው ታላቅ ሕዝባዊ የተቃውሞ ሰልፍ ለመንግሥት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች መልስ ባለማግኘታቸው ለሕዝብ ቃል በገባነው መሠረት በድጋሚ ተቃውሞ ሰልፍ አቅዶ አስፈላጊውን እንቅስቃሴ እያደረገ ነው፡፡ ለዚህም ሥራ መሳካት ለሚመለከተው የመንግሥት አካል ነሐሴ 13 ቀን 2005 ዓ.ም. በደብዳቤ ያሳወቀ ሲሆን፣ መጀመሪያ ባቀረብነው ደብዳቤ ላይ ያልተካተቱ ጉዳዮችን እንድናካትት ነሐሴ 15 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈልን ደብዳቤ ተጠይቀን አስፈላጊውን መልስ አሟልተን ነሐሴ 17 ቀን 2005 ዓ.ም. በተፃፈ ደብዳቤ አሳውቀናል፡፡
በአዋጁ በግልፅ እንደተደነገገው ሰላማዊ ሰልፍ ማድረግ ህገ መንግሥታዊ መብት እንደሆነና ማንም ሊከለክለን እንደማይችል በማያሻማ መንገድ ተገልጿል፡፡ ሰልፉን የማሳወቁ ዓላማ የጥበቃ አገልግሎትና አንዳንድ አስተዳደራዊ ድጋፎችን ለማግኘት ነው፡፡ በዚህ አሰራር ውስጥ መንግሥት የጥበቃና የቦታ ችግር ካለ ሰልፉን ለሌላ ጊዜና ቦታ እንዲያደርግ ለሚመለከተው አካል ደብዳቤ በደረሰው በ24 ሰዓት ውስጥ በፅሑፍ መልስ ይሰጣል የሚል ድንጋጌ አለ፡፡ ነገር ግን በመንግሥት በኩል ላቀረብነው የመብት ጥያቄ ምላሽ መሰጠት ሲገባው እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ የመንግሥት መዋቅር ሙሉ በሙሉ በመጠቀምና ዜጐችን አስገድዶ ሰልፍ እንዲወጡ በማስፈረም ሰማያዊ ፓርቲ ሰልፍ በጠራበት ቀንና ቦታ ሌላ ሰልፍ በተደራቢ በሃይማኖት መቻቻል ስም ህገ መንግሥቱን በመጣስ የሃይማኖት ተቋማትን ለራሱ የድርጅት ፖለቲካ መጠቀሚያና የሰማያዊ ፓርቲን ህጋዊ እንቅስቃሴ ለመግታት እየተጠቀመበት ነው፡፡ ይህ አሰራር እንዲስተካከል መንግሥትን በመግለጫ ብንጠይቅም የተሰጠን ምላሽ ግን በሚያሳዝን ሁኔታ የሀገሪቱን ህገ መንግሥትና የሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ መብትን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዲኤታ እንዲሁም ሰልፍ ጠሩ በተባሉ አካላት ግልፅ የሆነና የተቀነባበረ ህገ ወጥ ሴራ ሆኗል፡፡
ስለሆነም በነገው ዕለት ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ.ም. የምናደርገው ሰላማዊ ሰልፍ ከዚህ ቀደም ያቀረብናቸው ጥያቄዎቻችን እንዲመለሱ ለመንግሥት ጥያቄ ማቅረብ ከመሆን አልፎ የህግ የበላይነትን ወደ ማስከበር አድጓል፡፡ በመሆኑም በመንግሥት የሚደረገው ዓይን ባወጣ ሁኔታ ህግን የመጨፍለቅ ተግባር እንዲቆም ለምናደርገው ትግል የኢትዮጵያ ሕዝብና ዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ ከጐናችን እንዲቆም ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡
ምንጊዜም የተባበረ የሕዝብ ትግል ያሸንፋል!
ነሐሴ 25 ቀን 2005 ዓ.ም.
አዲስ አበባ

ሽብርተኛው ወያኔ/ኢህአደግ በሀይማኖቶችና በህዝቦች መካከል ግጭት ለመፍጠር የሚያደረገውን እኩይ ሴራ እናወግዛለን! -ENTC

$
0
0

entc-logo-5ባሳለፍናቸው ወራት በኢትዮጵያ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች እየደረሱባቸው ያሉ አፈናዎችንና እስሮችን በመቋቋም ህዝቡ  ለመብቱ እንዲቆም እያደረጉ ያሉትን የማነቃቃትና የማንቀሳቀስ ስራ፤ እንዲሁም የኢትዮጵያ ሙስሊሞችም ሳይገድሉ  እየተገደሉ ያለመታከት ከአንድ አመት በላይ ፍጹም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ለጥያቄያቸው ምላሽ በመሻት ድምዳቸውን  በማሰማታቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የሽግግር ምክርቤት ያለውን አድናቆትና አክብሮት ይገልጻል። እንቅስቃሴዎቹም  የሽግግር ምክርቤት ከሚከተለው የህዝባዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ጋር ተዛማጅ በመሆናቸው ሙሉ ድጋፋችንን መግለጽ  እንወዳለን ።ቀጣዩን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

የአባይ ቦንድ ሽያጭ በጉተምበርግ ከሸፈ፤ ድብድብ ተነሳ (Video)

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) የኢሕአዴግ በየሃገሩ እየጠራው የነበረው የአባይ ቦንድ ሽያጭ በመክሸፍ ላይ ይገኛል። በየከተማው ስብሰባው እየተበጠበጠ በመበተን ላይም ነው። ባለፈው ሳምንት በሚኒሶታ የአባይ ቦንድ ሽያጭ ሳይጀመር የተበተነ ሲሆን በዚህ ሳምንት ደግሞ በጉተምበርግ ኢትዮጵያውያን የአባይን ቦንድ ሽያጭ አክሽፈዋል። የቦንድ ሽያጩ በተጠራበት አዳራሽ በመግባት በተነሳው ተቃውሞ ድብድብ ተነስቶ የነበረ ሲሆን ሕዝቡ ወንበሮችን አንስቶ ወርውሯል። ሕዝቡ ስብሰባውን ከተቆጣጠረውና የኢሕ አዴግ ተወካዮችን ከአዳራሹ ካባረረ በኋላ “ኢትዮጵያ ሀገራችን…” እያለ ሲዘምር ይታያል። ቪድዮውን ይመልከቱ።

የፌደራል ፖሊስ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችን ደበደበ፣ ተቃውሞ ሰልፉን አደናቀፈ

$
0
0

ከርእየ- ሁለንተና ከአዲስ አበባ
semayawi partyዛሬ ነሐሴ 26 ቀን 2005 ዓ. ም ሠማያዊ ፓርቲ በጠራው የተቃውሞ ሰልፍ ገዥው ፓርቲ ለማደናቀፍ ከፍተኛ ውዥንብር፣ ድብደባና ሁከት ፈፀመ፡፡ ከ3 ወር በፊት ግንቦት 25 ቀን 2005 ዓ. ም ባደረገው የተቃውሞ ሰልፍ፡- ጋዜጠኞች፣ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች፣ የሀይማኖት ተወካዮች፣ በግፍ የታሰሩ ዜጎች ባስቸኳይ እንዲፈቱ በስብሰባው ያሳወቀ ሲሆን ምላሽ ባለማግኘቱ ነው ሰልፍ የጠራው፡፡
ይሁንና ገዥው ፓርቲ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሚል መልምሎ ባስቀመጣቸው ካድሬዎቹ አማካኝነት የተቃውሞውን ስብሰባ ያደናቀፈ ሲሆን በ25/12/05 ዓ. ም ምሽት ወታደሮቹን ልኮ በቢሮው ውስጥ የነበሩትን አመራሮችና ደጋፊዎችን ደብድቧል፡፡ አቶ ማርቆስን ጨምሮ በርካታ ሰዎች ክፉኛ ተደብደበው በ5 እስር ቤቶች ከፋፍሎ ካሰረ በኋላ ከምሽቱ 5፡00 ፈቷቸዋል፡፡ ኢንጅነር ይልቃልም ታስረው ተፈተዋል፡፡ ዛሬ ጠዋት 12፡ 00 ጀምሮ በጽ/ ቤቱ ከፍተኛ ቅስቀሳ የነበረ ሲሆን ወታደሮች በህገ ወጥ ገብተው በማስቆም ፖስተሮችን በመቅደድ፣ ጀኔሬተሮችን በመቀማት፣ ከፅ/ ቤታቸው እንዲወጡ አድርገዋል፡፡
በአንጻሩ በሀይማኖት ተቋማት ስም የጠራው ስብሰባ፡- እድሮች፣ የቀበሌ ነዋሪዎች፣ የቀጠና ካድሬዎች፣ በአነስተኛና ጥቃቅን ያደራጃቸው፣….በሎንችና፣ በአዜብ ቀንዶ፣ በአሮጌ አውቶቡሶች በመጓጓዝ መስቀል አደባባይ ከተገኙ በኋላ ያለምንም ተልእኮ ተበትነዋል፡፡ አብዛኞቹ በእግራቸው ተመልሰዋል፡፡ አላማው የሰማያዊ ፓርቲን የተቃውሞ ሰልፍ ማደናቀፍ ብቻ ነበር፡፡
ይህ የገዥው ፓርቲ ግፍ በዜግች ላይ ከፍተኛ ቁጣና እምቅ እልህ አንደሚፈጥር ታውቋል፡፡

በዛሬው ሰልፍ ላይ ከወጡት መካከል ከ200 በላይ ሙስሊሞች ታሰሩ

$
0
0

Muslim Etiopia 1

Muslim Etiopia 2

Muslim Etiopia 3

Muslim Etiopia 4

Muslim Etiopia 5(ዘ-ሐበሻ) ኢሕአዴግ በሃይማኖቶች ጉባኤ ስም ሽብርተኝነትንና አክራሪነትን ለመቃወም የጠራው ሰልፍ ላይ ፖሊስ ሙስሊሙን ብቻ እየመረጠ ማሰሩን ድምፃችን ይሰማ በፎቶ ግራፍ ጭምር ባወጣው መረጃ አስታወቀ። “ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ እንዲገኝ በየወረዳው አውቶቡስ የተዘጋጁ መሆኑ ሲታወቅ አውቶብሶችን ደልድለው ሰውን ያስገቡት የወረዳ ሀላፊዎች ናቸው፡፡ የአውቶብሶቹ ወጪዎች የተሸፈነውና ስምሪት የተደረገው በመንግስት ሲሆን የሰልፉ አዘጋጅ የተባለው የአዲስ አበባ የሃይማኖቶች ጉባኤ የሚባል “አሻንጉሊት” እንዳልታየ ድምጻችን ይሰማ ገልጿል። ኢሕአዴግ በዛሬው ሰልፍ 1 ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ወጣልኝ ቢልም አብዛኛው ሰልፈኛ ከድምጻችን ይሰማ የመጡ ናቸው።

በተለይ በመጨረሻው ሰዓት ላይ ድምጻችን ይሰማ ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ ተገኝቼ “እኔም አክራሪነትን እንደምቃወም እገልጻለሁ” ባለው መሠረት በርከት ያሉ ሙስሊሞች ወደ መስቀል አደባባይ የተመሙ ቢሆንም ከመንገድ ላይ ፌደራል ፖሊሶች በመቆም ሙስሊሞቹን እየመረጡ ወደ ሰልፍ እንዳይሄዱ ሲያደርጉ እንደእዋሉ የአይን እማኞች ገልጸዋል። ከፖሊስ ተርፈው በመስቀል አደባባይ የተገኙት ሙስሞች ደግሞ ተቃውሟቸውን ለመግለጽ እጃቸውን ወደ ጆሯቸው ባስጠጉ ቁጥር የደህንነትና የፖሊስ አካላት ለምን እጃችሁን አስጠጋችሁ እያሉ ውክቢያ ሲፈጽሙ ነበርና “ለምን ወደዚህ ሰልፍ መጣችሁ?፡ በሚል ሲያዋክቧቸው እንደዋሉ ተዘግቧል። ፖሊሶቹ ስም እየጠየቁ የሙስሊም ስም ያለውን ይመልሱ እንደነበርም ከተገኙት መረጃዎች ለማቀቅ ተችሏል።

በመስቀል አደባባይ ከተገኙት ሙስሊሞች ውስጥ ቁጥራቸው ወደ ከ200 ባልይ የሚሆኑትን ፖሊስ ይዞ ያሰረ ሲሆን ሰልፉ እስኪጠናቀቅ ድረስ በኢግዚብሽን ማዕክል አስሯቸው ከቆየ በኋላ በአውቶቡስ ወዳልታወቅ ሥፍራ እንደወሰዳቸው የደረሰን መረጃ ያመለክታል። ዘ-ሐበሻ ጉዳዩን ለማጣራት ባደረገችው ሙከራ እስካሁን እነዚህ ሙስሊሞች ያሉበት ያልታወቀ ሲሆን ምናልባትም “ሽብር እና ሁከት ለመፍጠር” በሚል መንግስት አንድ ድራማ በመሥራት ክስ ሊመሰርትባቸው እንደሚችል ታዛቢዎች ይናገራሉ።

ዛሬ ኢሕአዴግ በጠራው ሰልፍ ላይ በመገኘት “የትኛውንም አይነት አክራሪነት እንደማንቀበልና እንደምናወግዝ ዛሬ በድጋሚ በተግባር አሳይተናል” ብሏል ድምጻችን ይሰማ ከሰልፉ መጠናቀቅ በኋላ።

በሌላ በኩል ከሕወሓት የንግድ ድርጅቶች ውስጥ አንዱ የሆነው ራድዮ ፋና የዛሬውን ሰልፍ በማስመልከት ያቀረበው ዘገባን ለግንዛቤ እንዲረዳችሁ በሚል እዚህ አምጥተነዋል።

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች አክራሪነትንና ሽብርተኝነትን በመቃወም አደባባይ ወጡ

አዲስ አበባ ፣ ነሀሴ 26 ፣ 2005 (ኤፍ. ቢ. ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር በአስሩም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ነዋሪዎች አክራሪነትና አሸባሪነትን በመቃወም ዛሬ በመስቀል አደባባይ ሰለማዊ ሰልፍ አካሄዱ።

ሰለማዊ ሰልፉን የጠራው የአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖትች ጉባኤ ጽህፈት ቤት ሲሆን ፥ ለዛሬ ማለዳ በተጠራው ሰለፍ ላይ ቁጥሩ ከአንድ ሚለየን የሚልቅ ሕዝብ በሰላማዊ ሰልፉ ላይ ተሳተፏል።

የማለዳው ዝናብና ቀዝቃዛ የአየር ሁኔታ ሳይበግረው ከአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም አቅጣጫዎች በመትመም መስቀል አደባባይ የተገኙ ነዋሪዎች “ ሕገ መንግስታችን በአክራሪዎችና ደጋፊዎቻቸው አይናድም ” ፣ “ አክራሪነት ቻው ቻው ” ፣ “በኪራይ ሰብሳቢዎች ስር የተጠለሉ አክራሪዎችን አንሻም” ፣ “የምንፈልገው ሰላምና ሰለም ብቻ ነው ” ፣ “ መንግስት በአክራሪዎችና አሸባሪዎች ላይ አስፈላጊውን እርርምጃ ይውሰድልን ” ፣ ” የፀረ ሽብርተኝነት ህጉን እንደግፋለን ” የሚሉና ሌሎች በርከት ያሉ መፈክሮችን አሰምተዋል።

ከአዲስ አበባ ከተማ የሃይማኖትች ጉባኤ ጽህፈት ቤት የተወከሉ የክርስትናና የእስልምና ሃይማኖቶች አመራሮች ለሰልፈኞቹ ባሰሙት ንግግር ነዋሪዎቹ የጽህፈት ቤቱን ጥሪ አክብረው በመገኘታቸው አመስግነው ሰልፉ ኢትዮጵያ የምትታወቅበት መቻቻል አንድናትና እኩልነት በድጋሚ የተረጋገጠበት መሆኑን አመልክተዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ዲሪባ ኩማም ባሰሙት ንግግር መንግስት የነዋሪዎችን ጥያቄ በማክበር በአሸባሪዎችና አክራሪዎች ላይ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን ጠቁመዋል።

የሰላማዊ ሰልፉ ተሳፊዎች በሰልፉ ጠሪዎችና በክብር እንግዶች የተላለፉ መልዕክቶች ከሰሙ በኋላ የኢትዮጵያን ህዝብ መዝሙር በመዘመር ወደየመጡበት ተመልሰዋል።

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>