Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

አንድ ምሽት ከቴዲ አፍሮ ጋር በፍራንክፈርት 

$
0
0

Teddy afro
በልጅግ ዓሊ

የቴዲ አፍሮ ዝግጅት በፋራንክፈርት ሲደረግ በቦታው ተገኝቼ ነበር ። ብዙ ጊዜ ዘፋኝ ሲመጣ አልገኝም ። ዘንድሮ ግን ወያኔ በእሱ ላይ ያደረገውን ተንኮል መቃወም የሚቻለው በዝግጅቱ በመገኘት በመሆኑ ሰብሰብ ብለን ተገኝተን ነበር። ሰልፉ ሳይጠነክር ቀደም ብለን ለመግባት በጊዜ ነበር የደረስነው። ሰዓቱን ጠብቀን ከፍለን ገባንና ጥግ ላይ ወንበር ፈልገን መጠበቅ ጀመርን ። እሱ ወደ መድረክ እስከሚወጣ በልዩ ልዩ ዘፈን እየተዝናናን ቆየን ። ወጣት ይጎርፋል፣ አለባበስ ይታያል፣ ዓመት በዓሉን ዓመት በዓል አስመስለውታል። የአዲስ ዓመት ዋዜማ . . .  ለቀጣዩ የፈረንጆች ዓመት ዝግጅቱ ተጠናቋል። አዳራሹ እኩለ ሌሊት ላይ እየሞላ መጣ።

የሚጠበቀው ቴዲ አፍሮ ወደ መድረክ ሲወጣ ወጣቶች ያብዱ ጀመር። እሱ “ፍቅር ያሸንፋል“ ይላል። ወጣቶቹ ይጮኻሉ። “እወዳችኋለሁ“ ሌላ ጩኸት። አዳራሹ ድብልቅልቅ አለ ! ደስታና ጩኸት ይፈራረቁ ጀመር። ለአንድ ጊዜ  እንኳን ቢሆን ይህንን ዓይነት አቀባበል የኢትዮጵያ ገዥዎች መቼ ይሆን የሚያገኙት ? ብዬ አሰብኩ። በ2015 ይኽንን ብመኝ የተጋነነ ይሆናል?

በተከታታይ አራት ዘፈን ተዘፈነ ። ልዩ ልዩ ዓይነት ጭፈራ ታየ ፣ ውስጥ ሙዚቃ ፣ ደጅ ርችት ፣ መድረኩ ላይ ጭፈራ ቀለጠ ። 2015 በደስታ ተጀመረ ። ለዛሬም ቢሆን ችግራችንን ሁሉ ልንረሳ የተስማማን ይመስላል። ተስፋችንን አንግበን ለፍቅር የተነሳን ሆንን። ፍቅር ያሸንፋል ቴዲ ፣ እኛም ያሸንፋል . . . ። አጠገቤ የነበረው ጓደኛዬ ግን ዘመን መቀየሩን ረስቶት ያሸንፋል እያለ ግራ እጁን ቡጢ ጨብጦ መፈክር ያሰማል። ሌላው አውርድ እጅህን እዚህ ቡጢ አያስፈልግም ይለዋል። የፍቅር ጠላቶችን አደቅበታለሁ ሲል ተሳሳቅን። ወጣቱ መድረኩ አካባቢ እኛ ጥግ ጥጉን ይዘን እስክስታውን ወረድነው።በቴዲ ዘፈን ምንጃርኛም ይሞከራል። ያልተሞከረ አልነበረም። ፍራንክፈርት ቀለጠች . . .  ቤት የቀረም ሰው ያለ አይመስልም . . .  አዳራሹ ምንም ትልቅ ቢሆን ተጨናንቋል። አዲስ ዘመን በአዲስ ተስፋ ተጀመረ።

እንደ ድንገት አንድ ወጣት ከጭፈራው ብዛት ደክሞት አጠገቤ ተቀመጠ።

ደከመህ ? ብዬ ጠየቅሁት ።

ጭንቅላቱን በማወዛወዝ አዎን አለኝ።

ትንሽ ትንፋሽ እሲከያገኝ ጠበቅሁና ቴዲን ትወደዋለህ ? መልሱን በአማርኛ ስጠብቅ በትግርኛ ቀጠለ። በንግግር ልንግባባ አልቻልንም። አማርኛ አይችልም።  ቴዲ አዲስ ዘፈን ሲጀምር ወጣቱ አብሮት ይዘፍናል። ወጣቱ የቴዲን ዘፈን በቃሉ ያወርደዋል። ከቴዲ አፍሮ ጋር በዘፈን ይግባባሉ። ከእኔ ጋር ግን በቋንቋ ልንግባባ አልቻልንም። ለዘመናት የቆየው ጦርነት ምክንያት የወጣቱን ቋንቋ አለመናገራችን ይሆን?? ሃሳብ መጣ ።  አሁን ስለ ወጣቱ የማወቅ ፍላጎቴ ጨመረ ።

ሁሉን ዘፈን ታውቀዋለህ ?

አሁን ገባው መሰለኝ  አዎ ሁ.. ሉ   ን አለኝ በአማርኛ በትግርኛ አነጋገር ። ገና ዘፈኑ ከማለቁ በፊት ልጁ እየሮጠ ወደ ዳንሱ ገባ ። እኔን ጥሎ ከቴዲ ጋር በሙዚቃ ሊግባባ ከነፈ . . . ።

ከጎኔ የነበረው ለጭፈራ የሄደው የጓደኛዬ ትርፍ ቦታ ለወጣቶች መተዋወቂያ ጠቀመኝ ። አንዲት በረጅም ጫማ ላይ የቆመች ወጣት መጣች ።

“መቀመጥ ይቻላል?“ እየተቅለሰለሰች ጠየቀችን ። ባለቤቱ እስከሚመጣ ፈቀድኩ ።

“ይህ ጫማ እግርሽን አያደክመውም?“ ወሬ መጀመሪያዬ ሆነ ።

“ትለምደዋለህ ፤ ከዚያ ብዙም አይሰማህም።“ ስለ ጫማው አስረዳችኝ።

“እዚህ ሃገር ቆይተሻል?“ የሚቀጥለው ጥያቄ ነበር ።

“ ገና አራት ወሬ ነው ?“

“ገና አዲስ ነሻ ? ”

” አዎ ነኝ።”

“የት ነው የተመደብሽ ? ” ከፍራንክፈርት ራቅ ያለ ቦታ ጠራችልኝ ።

“እና ለቴዲ አፍሮ ብለሽ ነው ከዛ ድረስ የመጣሽው ? ”

“ታዲያስ!” አለችኝ በመደነቅ ። አመላለስዋ ለቴዲ ያልተመጣ ለማን ይመጣል? የሚል ጥያቄ ያዘለ  ይመስላል።

ቴዲ አዲስ ዘፈን ጀመረ ። ጥያቄዬን ሳልጨርስ ጥላኝ ነጎደች። ጫማዋን ግን እዛው ጥላው በረረች።

እኔም በተራዬ መድረኩ ጋር ብቃ አልኩ። ከዘፈኖቹ ማህል ቴዲ መፈክሩን ያሰማል። “ ፍቅር ያሰኝፋል“ ወጣቶቹ በሞላ በአንደነት እንደ መፈክር ይደግሙታል ። ሲዘፍን ይከተሉታል ፣ ቴዲ አውቆ ማሕል ላይ ሲያቆም እነርሱ ይሰማሉ ። በዚህ ምሽት ሁሉም ደናሽ ፣ ሁሉም ዘፋኝ ሆኗል ። ጩኸቱ ስለበዛ ለዕረፍት ወደ ውጭ ወጣ አልኩ ። አዳራሹ ውስጥ አንድ ሺህ የሚሆን ሰው አለ ። ደጅ ከ200 -300 የሚሆን ሰው ለመግባት ቆሟል። ይህ ሁሉ ሰው እንዴት ሊሆን ነው ራሴን ጠየቅሁ ። ሕዝብ እንደ ጉድ ይጎርፋል። ይዘፈናል ይጨፈራል፣ ይፈከራል ፣ ቴዲ እውዳቸኋለሁ ይላል፣ ወጣቶቹም በጩኸት ፍቅራቸውን ይገልጹለታል።

ተመልሼ ቦታዬ ተቀመጥኩ ። አሁን ከብዙ ወጣቶች ጋር ተዋወቅሁ። ቦርሳና ጫማ እኔጋ እያስቀመጡ መሄድ ተጀመረ ። ለዚህ የታማኝነት ሥራ በመብቃቴ አልከፋኝም ። ወጣት ሲደሰት ከማየት በላይ ምን የሚያስደስት ነገር አለ ። ኢትዮጵያ ፣ ኤርትራ የሚለው ነገር ቦታ አልነበረውም ። ቴዲም ያውቅበታል፣ ፍቅር ያሸንፋል ! እያለ ፍቅርን ይዘራዋል። ወጣት በቡድን ሆኖ አብሮ ይጨፍራል። የመግባቢያ ቋንቋ የቴዲ ዘፈን ሆኗል። እኔም ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ የጫማና የቦርሳ ጥበቃዬን በሰፊው ይዠዋለሁ። ተስማምቶኛል። አይሆንም ብዬ በዘመኑ ቋንቋ አላካብድም ።

ሌላ መጣ ቦታ ጠየቀኝ ። የተለመደው መልስ ተሰጠው ። ኤርትራዊ እንደሆነ ገብቶኛል። ቀስ በቀስ ተግባባን። ለምንድነው ቴዲን የምትወዱት ?

“ቴዲ እንደ ሌሎቹ አያካብድማ ? ኤርትራ ፣ ኢትዮጵያ ገለመሌ ፣ ገለመሌ አይልም ። ይመቻል። ዛሬ እዛ ፍራንክፈርት ሌላም ዘፈን አለ ። “ማህበረኩም“ ያዘጋጀው ነው ።  ከአስመራ የመጡ ታዋቂ ዘፋኞች አሉ። እዛ ማንም አልሄደ ፣ እዚህ ነው የመጣነው።” ብዙ ነገር አስረዳኝ ። እኔም “ማህበረኩም“ ምን እነደሆነ ማጣራት ጀመርኩ ። የሻብያ እጅ ያለበት ድርጅት እንደሆነ ሰማሁ። ገረመኝ ሻዕብያን በዘፈን ማሸነፍ ተቻለ ማለት ነው ?  “ቦለኛ“ የሚተሰኘ የቀድሞ የኤርትራውያን የዘፈን ዝግጅት ታሰበኝ ። ያኔ ወርቅና ጌጥ ሳይቀር የሚሰጥበት ዘመን ነበር ። የዛን ጊዜ ማነው ከቦለኛ የሚቀር።  አሁን ግን ቴዲ በዘፈን አሸነፈ ። የወጣቱን ፍላጎት የወያኔም፣ የሻዕብያም እንዳልሆነ ታዬ . . .  የምን ጦርነት ፣ የምን የሕዝብ እልቂት ፍቅር ያሸንፋል ። ወጣት ተሰብስቦ አንድ ላይ ይጨፍራል ፣ ይፋቀራል፣ ይዝናናል . . .  የጦርነት ጡሩምባ ለዛሬም ቢሆን ቆሟል . . .  የክፍፍል አባዜ ቆሟል ቴዲ የፍቅር ጦሩን ይዞ ዘመቻውን ካለውጊያ ቀጥሏል።

በዚህ ምሽት አንድ ነገር ተመኘሁ በሚቀጥለው ዓመት እነዚህን ወጣቶች የሚያፋቅር ፣ የቴዲ አፍሮን ጥሪ ቀጣይነት ተመኘሁ። ፍቅር የሚያሸንፍበት ቢሆን ብዬ ተመኘሁ። እነዚህ ወጣቶች የሚያፍሩበትን ሳይሆን የሚኮሩበትን ሃገር ተመኘሁ። ቴዲ አፍሮን አሥመራ ንግስት ሳባ ስታዲዩም ውስጥ መድረክ ላይ ሆኖ ፍቅር ያሸንፋል ሲል መስማትን ተመኘሁ። ከሁሉ በላይ ግን ማካበድን የማያውቅ የወጣትነትን ዘመን ተመኘሁ። . . .  በወያኔና በሻብዕያ ትምክህት ሊገዳደሉ የሚችሉ ወጣቶች በአንድነት ሲጨፍሩ ማየትን የመሰለ መልካም ስጦታ ከቴዲ አፍሮ 2015 ተሰጠን። እኛም በደስታ ተቀበልነው ።

ስለ  ሕዝብ ፍቅር የሚዘፍኑ በሰላም ይክረሙ !

beljig.ali@gmail.com

01.01.2015

ፍራንክፈርት


የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ ዜናዎች ዘገባዎች እና የተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮችን ያዳምጡ

$
0
0


የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ ዜናዎች ዘገባዎች እና የተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮችን ያዳምጡ
የኢትዮጵያ ወጣቶች ድምጽ ዜናዎች ዘገባዎች እና የተለያዩ ሃገራዊ ጉዳዮችን ያዳምጡ

ወያኔ የጉራጌ ማህበረሰብ ከሌላው የህብረተሠብ ክፍል ለማጋጨት በወልቂጤ ዩኒቨርሥቲ እየፈጸመው ያለው ደባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው ይገባል

$
0
0

By Seyoum Workneh

ከላይ በርዕሱ ላይ የጉራጌ ማህበረስብ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል ብዬ የተጠቀምኩት ወያኔ/ኢህአዴግ በጉራጌ ዞን በቸሃ ወረዳ ጉብሬ ከተማ ላይ በህዝብ ድጋፍና እርብርቦሽ የተመሠረተችው ወልቂጤ ዩኒቨርሥቲ ውሥጥ በተግባር እያደረገ ያለውን ጉዳይ ነጠል አድርጌ ለማሣየት እንጂ ወያኔ በሁሉም የሐገራችን ክፍል የተሠማራበት እኩይ ተግባር ጠፍቶኝ እንዳልሆነ ልትረዱልኝ እፈልጋለሁ። ባጠቃላይ ወያኔ ኢትዮጵያ ሐገራችን ለማጥፍት ግቡ አድርጎ የሚንቀሳቀሥ የትኛውንም ህዝብ ሊወክል የማይችል በጥቂት ማፍያ ወንበዴዎች የሚመራ የሆዳሞች ድርጅት ነው። የመጨረሻ የሆነውን ሐገር የማፍረሥ አላማቸው እውን እሥኪሆን ድረሥ ሀገሪቷን መምራት ሥለ ሚፈልጉ ህዝቡ አንድ እንዳይሆን የተቻላቸውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኻላ እንደሚያደርጉ ልንገነዘብ ይገባል።

welktie

ከፋፍለህ ግዛ (በዘር) መርህ የሚከተለው ወያኔ ላለፉት 23 ዓመታት ህዝቡን እርሥ ብርሥ እንዳይተማመን፤ እርሥ በርሥ እንዲተላለቅ፤ እርሥ በርሥ እንዲጥላላ አያሌ ሥራዎችን ሠርቷል። ህዝቡን በዘር፣ በሐይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በእምነትና በሌሎችም ተመሣሣይ ጉዳዮች ለመከፍፈል በፖሊሢ ደረጃ ተቀርጾ ሢመሩበት የነበረና አሁንም ያለ ህዝብ ፍቃድ የገፉበት ጉዳይና ፖሊሢ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ3000 አመት በላይ ተከባብሮና ተቻችሎ፣ ያሉትን ልዩነቶች አጥብቦ የኖረባት ሐገር ዛሬ የዘር ፖለቲካን በማራመድ በህዝብ ዘንድ ጥላቻን በማሥፈንና ልዩነቶችን በማሥፍት የኢትዮጵያ ህዝብ ሆድና ጀርባ ለማድረግ ተግተው እየሠሩ ነው። ወያኔ በዚህም ተግባሩ ከልማት መንገድ ይልቅ የጥፍት መንገድ መምረጡን ያመለክታል።

ወያኔ በዚህም መሠሪ ተግባሩ ሙሉ በሙሉ ተሣክቶለታል ማለት ባይቻልም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ግን የዚህ ተግባር እርዝራዦች፣ አደር ባዮች፣ አጎብዳጆችና ሆዳሞች ግን አልጠፉም። አንዳንዶቻችን የወያኔ መሠሪ ተግባርና አላማ ጠንቅቀን የምናውቅ ብንሆንም ከወጥመዱ ማለፍ ያልቻልን ደካሞችም መኖራችን ግን አልቀረም። ወያኔ ሁላችንም ጠባብና ትምክተኛ እንድንሆን እንደሚፈልግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ የሚያውቀው ይመሥለኛል። ይህ ከሆነ ደግሞ ሁላችንም ወጥመዱ ውሥጥ እንዳንደናቀፍ አሥፈላጊ ጥንቃቄ መውሠድ ይጠበቅብናል። ያ ሳይሆን ሲቀር ግን እራሣችን ወያኔ ባዘጋጀው መረብ ውሥጥ ተጠልፈን ትክክለኛ መሥመር እየተከተሉ ያሉትን ማደናቀፋችን ወይም እየተከተሉት ላለው የለውጥ ጎዳና እንቅፍት መሆናችን አይቀሬ ነው። በዚህ ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሣሪያ ሆነናል ማለት ነው።

ወደ ዋናው ጽሁፌ ሥመለሥ ወያኔ በወልቂጤ ዩኒቨርሥቲ እያደረገ ያለውን ነገር አሣሣቢ ደረጃ ላይ በመድረሡ ምክንያት ነው። ይህም ዩኒቨርሥቲው ውሥጥ ወያኔ የራሡን ሠዎች በማዘጋጀት ፍራሽ ከተደረደረበት ክፍል እሥከ የተማሪ ማደሪያ የሆኑትን ዶርሚተሪዎችን በማቃጠል ከሌላ ክልል የመጡት ተማሪዎች ድርጊቱን እንደፈጸሙት በማድረግ የጉራጌ ማህበረሰብ ከሌላ ክልል ለመጡትን ተማሪዎችም ሆነ ሥለ ሌላው ማህበረሰብ የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረው ለማድረግና እርሥ በርሥ ለማጋጨት ነው። በመሠረቱ የጉራጌ ማህበረሠብ በሁሉም የሐገራችን ክፍል በተለያዩ የግልና የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተለይ የንግድ ሥራ ላይ ተሠማርቶ የሚሠራ ህዝብ እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም የሐገራችን ክፍል የሚመጡ ሠዎች ጋር በደንብ የመገናኘት አጋጣሚ ሥላለው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል ጨዋ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። በዚህም ምክንያት ወያኔ የሚፈጸማቸው ድርጊቴች ወይም የወያኔ ሴራዎች ጠንቅቆ የሚያውቅ ሕዝብ ነው።

ባሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 25, 2014 እኤአ ጠዋት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች (አንደኛው ከአማራ ክልል የመጣ, ሁለተኛው ከኦሮምያ ክልል) መጣላታቸውን ተከትሎ ከኤሮምያ ክልል የመጡት ተማሪዎች የግቢው ህንጻዎች ላይ በሌሊት አደረሱት የተባለውን ጉዳት ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ ላይ የፈጠረው መጥፌ ሥሜት ነው። እዚህ ላይ ሁሉም የጉራጌ ማህበረሰብ ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር የዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ መሆኑን ነው። ምክንያቱም የኦሮሞ ህዝብ ለብዙ አመታት ከጉራጌ ማህበረሰብ አብሮ የኖረና ተጋብቶ የተዋለደ እንደመሆኑ መጠን ምንም አይነት ችግር እንደሌለባቸው ነው። ሥለዚህ የተፈጠረው ድርጊት በማንም ይሁን በማን ወያኔ ህዝቡን ለማጋጨት ሆን ብሎ የፈጸመው እንጂ ከኦሮሞ ምህበረሰብም ሆነ ተማሪዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ነው። ለወደፊትም ቢሆን ጥንቃቄ ልንወስድ ይገባል።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

የጠለምትና የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ የጎንደሬዎች . . .(አንዱዓለም ተፈራ)

$
0
0

አንዱዓለም ተፈራ – የእስከመቼ አዘጋጅ

ታህሣሥ ፳ ፭ ቀን ፳ ፻ ፯ ዓመተ ምህረት ( 01/03/2015 )

welkaiyt

በጠለምት፣ በበየዳ፣ በጃናሞራ፣ በወልቃይት፣ በጠገዴ፣ በአርማጨኾ ነዋሪው እየተባረረ፣ ሀብቱ እየተዘረፈ፣ ያንገራገረው እየተገደለ፤ ሰው በምሬትና በሰቀቀን ኑሮውን መግፋት አቅቶት አጣብቂኝ ላይ ገብቷል። ትናንት ቡያ ነበር ክልሉ። ትናንት በሀከር ነበር ክልሉ። ቀጥሎ ራስ ደጀንን ወደነሱ አካተቱት። ጠገዴን ጠቀለሉት። ገፍተው ስሜን አውራጃን በሙሉ ጠቀለሉ። ወገራ አውራጃን ሽራርፈው ወሰዱና ጎንደር አውራጃን ተጠጉ። አሁን ዘለው የጎንደር ከተማውን ገነት ተራራ፤ የትግራይ መሬት እያሉ ለትግራይ ልጆቻቸው እያሰተማሩ ነው። ጎንደር ከምድረ ገጽ እንድትጠፋ እየተገፋ ነው። ይህ የመኖርና ያለመኖር፤ ውሎ የማደርና በወጡበት የመቅረት፤ ተገፍቶ ተገፍቶ የገደል ጫፍ ላይ የተንጠለጠለ ሕይወት ሕዝቡን ሰቅዞ ይዞታል። ይህ ጉዳይ የጎንደሬዎች ብቻ ጉዳይ አይደለም። አዎ! በዋግም ተመሳሳይ ተግባር እየተፈጸመ ነው። የዋግ ጉዳይ የወሎዬዎች ብቻ ጉዳይ አይደለም። በመተከል ተመሳሳይ ተግባር እየተፈጸመ ነው። ይህ ጉዳይ የጎጃሜዎች ብቻ ጉዳይ አይደለም። በሐረርና በአርሲም ሲጀምር በግልጽ ይህ ጉዳይ ተተግብሯል። በጉራፈርዳና በደቡብ ክልል የተደረገው ኢትዮጵያዊያንን በያለንበት ሰቅጥጦናል። ይህ ጉዳይ የአንድ አካባቢ ወይንም የተወሰኑ ሰዎች ጉዳይ አይደለም። ይህን ካልተገነዘብንና መልስ ካላዘጋጀን፤ ለተከታዩ ሂደት ተጠያቂዎች፤ እኛው ጆሯችንን ደፍነን፣ ዓይኖቻችንን ጨፍነን፣ ዝም ያልነው በሙሉ ነን። የአካባቢው ሰው ብቻ ተቆርቋሪና እርምጃ ወሳጅ ነው የሚል እምነት ካለን፤ ከትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በምንም መንገድ ያልተለየን ነን። ለምን ይኼን ጉዳይ ክብደት ሠጥቼ የጽሑፌ ማጠንጠኛ እንዳደረግሁት ላስረዳ፤

ጉዳዩ፤ ጠለምት፣ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ አርማጨኾ፣ በየዳ፤ ብራ ዋስያ፣ ሻግኔና ላሄን፣ ድብ ባሕር፣ አብደራፊና ሁመራ፤ከጎንደር ተነጥቀው ለትግራይ ተሠጥተዋል። በጠቅላላው የስሜንና የወገራ አውራጃዎች ወደ ትግራይ ገብተዋል። ይህ በጎንደር ሲሆን፤ በተመሳሳይ መልኩ የወሎው ዋግ ተነጥቆ ለትግራይ ተሠጥቷል።

ጉዳዩ፤  በነዚህ ቦታዎች የነበረው ነዋሪ፤ በደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረው አማራ፤ ሀገርህ አይደለም ተብሎ እንደተፈናቀለው፣ እንደተገደለው፣ ሀብቱ እንደተነጠቀበትና እንደተባረረው ሁሉ፤ እኒህም ለዚሁ ዕጣ ተዳርገዋል። መሬታቸው ብቻ ሳይሆን፤ ሀብታቸው ተዘርፏል። ከብቶቻቸው ተነድተዋል። እህላቸውን ተነጥቀዋል። ያንገራገሩት ተገድለዋል። እሽ ያሉት በወባና በተላላፊ በሽታ እንዲያልቁ ባልሆነ ቦታ ሰፍረዋል።

ጉዳዩ፣  በነዚህ በተነጠቁ ቦታዎች አጎራባች ሆነው የሚገኙት ነዋሪዎች፤ የተነጠቁትን ወገኖቻችንን በማስጠጋት ለወደፊት የባለቤትነት ጥያቄ እንዳያነሱና ሰላም እንዳያገኙ፤ ጎንደሬዎችን እርስ በርስ በማፋጀት ለማጥፋት፤ ሌላ አጀንዳ አውጥቶ፤ በአርማጨኾና በጭልጋ አካባቢ ያሉትን፤ ቅማንትና አማራ በማለት ከፋፍሎ፤ ጥልቅ ግጭት በመፍጠር ለማተላለቅ ቁስቆሳውን እያጧጧፈው ነው።

እንግዲህ ነጥቡ ይህ ጉዳይ ከፍተኛ ትኩረት ሊሠጠው የሚገባው ሀገራዊ አጀንዳ ነው። ያካባቢው ወገናችን ለብቻው ጥቃቱን እስከዛሬ ችለውታል። በዝርዝር ላስቀምጥ፤

  • ከሌሎች የሀገራችን ክፍሎች በባሰ መንገድ በጎንደር በኩል የኢትዮጵያ ደንበር በስፋት ተደፍሯል። መሬቱ ለሱዳን ተሠጥቷል። ከሌሎች የሀገራችን ክፍሎች በባሰ መንገድ የጎንደር ለም መሬት ወደ ትግራይ ተወስዷል።
  • በነዚህ አካባቢዎች ይኖሩ የነበሩት ወገኖቻችን፤ ተለቅመው በመባረር በቦታቸው የትግራይ ሰዋች እንዲሰፍሩ ተደርገዋል። ሕዝቡ ማንነቱን ሳይጠየቅ የተደረገው ነጠቃ፤ ከውጭ የመጣ ወራሪ ከሚያደርገው ግፍና በደል ያልተለየ ነው።
  • በጎንደር ከተማ ውስጥ ሥልጣኑንና ሀብቱን አሟጠው የያዙት የትግራይ ተወላጆች ናቸው። ይህ የከተማውን ወገናችን በጣም ከማማረሩ በላይ፤ የቂም መርዝ እየተከለ ነው።

ይህ ያካባቢውን ወገናችን ወደየት ይገፋዋል?

  • ቀሪው ኢትዮጵያዊ ስላልደረሰልኝ፤ ዝም ብዬ መጠበቄ አያዛልቀኝም። እናም ራሴን ላድን ወደሚል፤
  • የራሴን ዕድል ራሴ ልወስን ወደሚል፤
  • የኔ አጀንዳ የሌሎች አጀንዳ ስላልሆነ፤ የራሴን አጀንዳ ራሴ ብቻ ማንገብ አለብኝ ወደሚል፤

እና ምን መደረግ አለበት?

ሀ)       ታሪኩን መርምረን ማጥናት የያንዳንዳችን ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው። በተለይ በትግሉ ዙሪያ የምንገኝ በሙሉ፤ ይህ ግዴታ፤ ከራሳችን አልፎ ሌሎችን በዚህ ለማጠቃለል ኃላፊነቱ አለብን። ለዚህ በጉዳዩ የጠለቀ እውቀት ያላቸውና አካባቢውን ጠንቅቀው የሚያውቁት ይምሩ።

ለ)       የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በአሁኑ ሰዓት፤ ትግሬዎችና አማራዎች በቦታ ባለቤትነት ሳቢያ፤ በመካከላቸው የዕልቂት ጦርነት እንዲኖር እያራገበ ነው። አለመታደል ሆኖ መተላለቁ ተጀምሯል። የመለስ የኢንተራሐምዌ ምኞት የሚተገበርበት በር እየተከፈተ ነው። የርሱ ምኞት የራሱን ሥልጣን ለማራዘም ማማካኛ ነበር፤ ሀቅ ሲሆን ደግሞ የራሱን ደጋፊዎችና ወገኖች አደጋ ላይ ሊጥል ነው። እናም ይህ ሁላችንን ሊያሳስበን ይገባል። ክብደት እንሥጠው።

ሐ)      ዋናው መፍትሔ አንድ የትግል ማዕከል ባስቸኳይ መፍጠሩ ነው። በየቦታው የተኮለኮለው የየራስ ድርጅትና የየአካባቢ መሰባሰብ፤ ለኢትዮጵያ መጥፋት ምክንያት ይሆናል። በየድርጅቶቻቸው ተሸጉጠው እኔ እንዲህ፣ እነሱ እንዲያ የሚባለው ፉገራ ያቁም። ለነገዋ ኢትዮጵያ፤ ተወቃሹ የትግሬዎችን ነፃ አውጪ ግንባር ሳይሆን እኛው ራሳችን ነን። የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባርማ የኢትዮጵያ ጠላት ነው። ማን ለኢትዮጵያ አልተውቆረቆርክም ብሎ ያማዋል! ይህ ድርጅት እኮ፤ “እኛ” እና “እነሱ” በማለት፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ጠላት ብሎ ፈርጆ፤ ኢትዮጵያን ለማጥፋት የቆመና የራሱን አዲስ ሀገር ለመመሥረት ካልሆነለት ደግሞ ትግራይን ገንጥሎ የራሱ ሀገር ለማድረግ ቆርጦ የተነሳ ጠላት ነው። እናም ሁሉን የየአካባቢ አጀንዳ ባንድነት ያቀፈ የትግል ማዕከል ባስቸኳይ ካልተፈጠረ፤ እንዲህ የባሳቸውንና በመኖርና በመጥፋት መካከል ያሉትን መቆጣጠር አይቻልም። ብሶታቸው ትክክል ነውና የሚወስዱትም እርምጃ ትክክለኛ ይሆናል። በሚያውቁትና በጃቸው ባለ እንጂ በምኞት በኛ አጀንዳ አይታገሉም።

መ)      በተጨማሪ ደግሞ፤ እስላሞች ለብቻቸው፣ በደቡብ የተፈናቀሉት ለብቻቸው፣ መምህራን ለብቻቸው፣ ነጋዴዎች ለብቻቸው፣ ቤት ያጡ ለብቻቸው እየተባለ የሚደረገው ተከላካይነት በተናጠል ለመመታት መዘጋጀት ነው። ለየብቻ እስከቆምን ድረስ ደግሞ፤ በያንዳንዱ ለየብቻ በቆመ ተከላካይ ስብስብ ውስጥ ያሉ ጠንካራ አባላት፤ ወደፊት በመግፋት ብቻቸውን ለማደጋቸው ጥርጣሬ ሊኖረን አይገባም። ደግሞም የቴክኖሎጅው አመቺነትና የወጣቶቻችን ቀልጣፋነት፤ ባጭር ጊዜ ውስጥ ለመሰብሰብና ለማደግ እንደሚያስችል የማይረዳ የለም። ስለዚህ ልንሰጋ ይገባናል። ስለዚህ፤ እያንዳንዳችን የያዝነውን አጀንዳ፤ ከዚህ ሀገራዊ ጉዳይ አንጻር ክብደትና ቅለቱን በማነጻጸር፤ ባስቸኳይ አንድ የትግል ማዕከል መፍጠር አለብን። ለዚህ መፈጠርና አለመፈጠር ተጠያቂዎቹ እኛውና እኛው ብቻ ነን።

የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር በጎንደር የሚያደርገው ተግባር፤ ኢትዮጵያን ለማጥፋት ከሚያደርገው ግስገሳ የተከተለ ነው።  በቀጥታ ሲታይ ለሙን መሬት በቋሚነት ለመውሰድ፤ ግጭቱን ምክንያት ለማድረግና ወታደሮቹን ለማስፈር ያቀደው ሲሆን፤ በተዘዋዋሪ መንገድ ደግሞ፤ ትግራይን ገንጥሎ ለመውሰድ ካለው ዕቅዱ አኳያ፤ የትግራይን የመሬት ይዘት ዓለም አቀፋዊ ድንበር ለማድረግ፤ የአካባቢውን ነዋሪ ለማጥፈት ያዘጋጀው ነው። ቁጭ ብለን ሞት እንዲወስደን እንጠብቅም ያሉት፤ ራሳቸውን መከላከል ጀምረዋል።

ይህ ጉዳይ፤ በሐረር፣ በአርሲ፣ በጉራፈርዳና በሌሎች አካባቢ በአማራው ወገናችን ላይ የደረሰው ቀጣይ እርምጃ ነው። ብዙዎቹ በደረሰባቸው ግፍ ምክንያት፤ ከፍተኛ የንብረትና የሕይወት መስዋዕትነትን እየከፈሉ ናቸው። ጀግንነቱ፣ ቆራጥነቱ፣ ለወገን ያላቸው ፍቅር የማያጠያይቀው የአካባቢው ተወላጆች፤ ዝም ብሎ ማየቱ በቅቷቸዋል። ሌሎች ኢትዮጵያዊ ወገናቸው፤ ጭንቀታችሁ ጭንቀታችን ነው፤ ቁስላችሁ ቁስላችን ነው፤ ብለው አብረዋቸው ካልቆሙ፤ ያናንተ ጉዳይ የኛም ጉዳይ ነው ብለው አብረው ካልተባበሩና የአካባቢው ተወላጆች ብቻውን ከቆሙ፤ የብቻቸውን አጀንዳና የብቻቸውን እርምጃ እንዲወስዱ መንገዱን እየቀደድንላቸው ነው። ይህ የኢትዮጵያ ሕዝብ ጉዳይ ነው። ለብቻቸው መቆም የለባቸውም ብሎ ከሩቅ መደንፋት ይቻላል። ይህ ግን አፍራሽ እንጂ ገንቢ አይደለም። ለብቻቸው እንዳይቆሙ አብሯቸው መሰለፍ ያስፈልጋል።

ለአካባቢው ተወላጆች፤

ላላችሁባቸውና ለምታምኑባቸው ድርጅቶች ንቁ ተሳታፊዎች በመሆን፤ የናንተ ጉዳይ የየድርጅቶቹ ጉዳይ እንዲሆን ጣሩ። በመሠረቱ ደግሞ በአንድነት ታግለን ይሄን የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መንግሥት ማስወገድ ካልቻልን፤ ወዳልታወቀ የወደፊት እየተጓዝን ነው። እናም ትኩረታችን ይሄን መንግሥት ለማስወገድና በሂደቱ ጉዳያችን ቅድሚያ የሚሠጥበት እንዲሆን መጣር አለብን። አሁንም ዋናው መፍትሔ የትግሬዎች ነፃ አውጪ ግንባር መውደቅና የኢትዮጵያ ሕዝብ መንግሥት መቋቋም ስለሆነ፤ ይሄን መግፋት አለባችሁ። በሂደቱ ይህ የጎንደር ጉዳይ ሀገራዊ አጀንዳ ሆኖ እንዲቀርብ መጣር የሁላችን ኃላፊነት ነው። ይህ ኢትዮጵያዊነትን መቀበል ማለት ነው። ይህ ጉዳይ የኔ ብሎ መነሳት፤ ከፍተኛ ትኩረት ሊሠጠው ይገባል። eske.meche@yahoo.com

ከአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

$
0
0

ታኀሳስ 23/04/2007 ዓ ም

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ታጋዮች ከወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ ህዝብ ጎን በመሰለፍ በዘረኛውን ናዚ ወያኔ መከላከያና ከትግራይ ተስፋፊ ታጣቂዎች ጋር ከባድ ውጊያ አያካሄደ ይገኛል።አዴሃን ከኤርትራ/ሻቢያ/ ምድር ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለውጤት የሚያበቃውን የአደረጃጀት ስልት በመንደፍ /በመቀየስ/ ወደ ተጨባጭ ስራ መግባቱን ይፋ ማድረጋችን ይታወሳል።

አዴሃን በሁሉም የአገራችን አካባቢዎች የሚያደርገው እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይም የወያኔ ስርአት አረመኔያዊ አገዛዝ ግፊት ቀማሽ ለሆነው ከወልቃይት ጠገዴና አርማጭሆ አካባቢ ልዩ ትኩረት በመስጠት እየተንቀሳቀሰን እንገኛለን። ከዚህ ቀደም ህውሃት በወረራ የያዛቸውን የወልቃይት ጠገዴና የአርማጭሆ ሰፋፊ ለም መሬቶችን አስተማማኝ ለማድረግ እና አዳዲስ መሬቶችን ለመያዝ የነደፈውን እስትራቴጂ ተግባራዊ ሊያደርግ እየተዘጋጀ መሆኑንና ታላቋን ትግራይ ለማስፋት ባለው ህልም መሰረት ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ መሆኑን August 19 – 2014 ” ህወሃት በወልቃይትና ጠገዴ ህዝብ ላይ ተጨማሪ የዘር /ማጽዳት/ፍጅት ለማካሄድ እየተዘጋጀ ነው።” በሚል ርዕስ መረጃዎችን ይፋ አድርገን ነበር።

በሌላ በኩልም November 19- 2014” የጠገዴ ወረዳ ህዝብ አማራ እንጂ ትግሬ አይደለንም በማለት እራሱን ለመከላከል እየተዘጋጀ ነው።” በሚል ርዕስ ለህዝብ የተበተነውን የትግል ጥሪ ፓምፕሌት ጨምረን ይፋ አድርገን እነደነበር ይታወሳል። በመሆኑም ወያኔ የትግራይን የመስፋፋትና አማራውን የማጥፋት አባዜውን እውን ለማድረግ፦ ህዝቡም እራሱን ለመከላከልና ማንነቱን ለማስከበር በጀግንነት ዱር ቤቴ ብሎ የራሱን የጎበዝ አለቃ መርጦ በከባድ መሳርያ የሚታገዘውን የወያኔ ሰራዊት በከፍተኛ ደረጃ እየመከተ ይገኛል። በመሆኑም መላው የኢትዮጵያ ህዝብ በተለይም በቅርብ የሚገኘው አማራውና እንዲሁም በተለያየ መንገድ ወያኔን ለማሰወገድ በትግል ላይ ያሉ ድርጅቶች ከህዝብ ትግል ጎን እንዲቆሙ አሳስበንም ነበር። ይኸው ዛሬ የወያኔ የጸጥታ መከላከያና፡ የትግራይ ታጣቂዎች እንዲሁም ስውር ነብስ ገዳይ ደህንነቶች በማን አለብኝነት በሰላማዊ ህዝብ ላይ ከታህሳስ 17- 2007 ጀምሮ ግልጽ ጦርነት ከፍተዋል። ህዝቡም እራሱን ለመከላከል ሲል በሚቻለው ሁሉ ራሱንና ሀገሩን ከባዳዎች ስብስብ ለመከላከል ዘረኛውን አባገነን ስርአት እየተፋለመው ይገኛል።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ታጋዮችም ሁኔታውን በቅርብ እየተከታተልን ከህዝቡ ጎን በመሰለፍ ታረካዊ ግዳጃችንን እየተወጣን እንገኛለን። በአሁኑ ጊዜ አረመኔው የወያኔ ስርአት በርካታ የመከላከያ ሃይሉን ከትግራይ ግንባሮችና ከመሃል ሀገር ሳይቀር ወደ ስፍራው በማንቀሳቀስ የሚያካሄደውን የማንነት ትግል በሃይል ለመጨፍለቅ እርብርብ እያደረገ ይገኛል ። በተለይ የናዚው ወያኔ የግፍ አገዛዝ ሰለባ ላለመሆን እራሳቸውን መከላከል የማይችሉትን ህጻናት፣ ሽማግሌዎችንና ሴቶች ላይ አረመኔያዊ የሆነ ጥቃት እየፈጸመ ይገኛል።አሁን ባለንበት ሰአት የወልቃየት ጸገዴና አርማጭሆ ህዝብ በከፍተኛ ወኔ እየተጠራራ እየተደራጀ የጀመረውን የነጻነት ትግል ለማጠናከር ዱር ቤተ ብሎ ከያለበት የእከተተ ይገኛል ።

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄም የቻለውን ሁሉ በማድረግ ከህዝቡ ጎን ተሰልፎ የራሱን ታሪካዊ አስተዋፆ በማበርከት ህዝቡን የድል ባለቤት ለማድረግ ተግቶ በሰራት ላይነው ። ሁኔታው የሚመለከታችሁና የሚያሳስባችሁ ወገኖች ሁሉ የተቀጣጠለውን ካለው ህዝባዊ ትግል ጎን እንድትሰለፉ አዴሃን ወቅታዊ ጥሪ ያቀርባል።በሁሉም መስክ ትግሉን ለማጠናከር በየቀኑ ሁኔታውን በመከታተል፣ እንድትሳተፉ በድጋሜ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

፠ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ፠

ሞት ለወያኔ

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ ስ\አስፈፃሚ

 

10897830_1530702910533439_7009177353300305907_n

በአፋር ከ40 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች የትጥቅ ትግሉን ለመቀላቀል ጫካ ገቡ

$
0
0

አኩ ኢብን ከአፋር ለዘ-ሐበሻ እንደዘገበው:-

በሰሜናዊው የአፋር ክልል ከባራሕሌ ወረዳ ቁጥራቸው ከ 40 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች በወረዳውና በመላው አፋር ክልል ላይ የወያኔ ተወካዮች በህዝብ ላይ newsእያደረሱ ያሉትን በደል በመቃወም ወደ ትጥቅ ትግል ከአፋር ኡጉጉሞ ጋር ለመቀላቀል ወደ ጫካ መግባታቸው ተረጋገጠ።

በአፋር ክልል እየተባባሰ የመጣውን የሰብዓዊ መብት ጥሰትና የወያኔ እና አገልጋዮቹ አብዴፓ ፈላጭ ቆራጭነትን ማስወገድ የሚቻለው በህዝብ አንድነትና ቁርጠኝነት መሆኑን አምነው ብዙ ወጣቶች ለአገራቸው መስዋዕት ለመሆን የተዘጋጁ እንዳሉ እሙን ነው።

በዚህ ዜና ላይ ተጨማሪ መረጃ ይዤ እቀርባለሁ።

ዛሬ የወያኔው ፖሊስ ስለለቀቀው የአንዳርጋቸው ጽጌ አዲስ ቪድዮ ዙሪያ የተሰጡ አስተያየቶች

$
0
0

የሕወሓት አስተዳደር ፖሊስ ዛሬ ስለአንዳርጋቸው አዲስ ቪድዮ ለቋል:: በየሶሻል ሚዲያዎችም መነጋገሪያ ሆኗል:: በዚህ ዙሪያ ከሶሻል ሚዲያዎች የተለያዩ አስተያየቶችን ስለቪድዮው ሰብስበናል ያንብቧቸው:-
andargacew Tsige
የጆሜክስ ካሳዬ አስተያየት:-

ሌባና ፖሊስ የሚባለው የገዢው አገልጋይ የሆነው የፌዴራል ፖሊስ ፕሮግራም የአቶ አንዳርጋቸው ጽጌን ቪዲዮ በማሳየት አሜሪካን የሚያስንቅ የምርመራ ሥልት አለን እንደ ሌባ ሻይ ሳንገርፋቸው ይናዘዛሉ በማለት የድፍረቱን (የድድብናውን) ልክ ሊያሳየን ሞክሯል፣ ይህ መራር ቀልድ በአስቀያሚ የማዕከላዊ ምርመራ ሂደት ውስጥ ያለፉትንና ቶርቸርን ያስተናገዱት ጓደኞቼን ሳስብ ድፍረቱ አሳምሞኛል ፤ጓደኞቼም በማዕከላዊ ቆይታቸው የታዘቡት ጥፍራቸው የተነቀለባቸውን ተማሪዎች ሳስብ እነዚህን መርማሪዎች እና ጋዜጠኞች በፍትህ አደባባይ አገኛቸው ዘንድ ዘወትር እናፍቃለሁ፤

ፕሮግራሙ አሜሪካን ሊያብጠለጥል የፈለገበት እና የጠቀሰወው ሰሞነኛው የቶርች ሪፖርት ኢትዮጵያም ተሳታፊ መሆኗን እንዳጋለጠ ዘንግተውት ይሆን ብዬ አልጠይቅም አንዴ ምንም አያመጡም አያውቁም ተብለን ተንቀናልና (ሕዝብን ከመናቅ ካለሆነ ከምን ይመነጫል?)፡፡

በዚህ እጅ እግር የሌለው ከመቆራረጡ የተነሳ አሁንም የመግረፍ እንጂ የካሜራ እውቀት የሌላቸው ብቻ የቀረጹት እንደሆነ በሚያሳብቀው ቀረጻ አልሞተም ለማለት ካልሆነ በቀር እርግጠኛ ነኝ እነሱም አልገባቸውም፡፡

አንድ ሰው ለአንድ ቃለ መጠይቅ 10 ደቂቃ ለሚፈጅ ልብስ ለምን ይቀያይራል?

የሚናገረውን እውነት ነው ብለን እንድናምን በተያየ ቀናት የተቀረጸ ነው ብለን ብንቀበል እንኳ ራሳቸውን የሚያሳጣ እንጂ ምንም የተላለፈ መልዕክት የለም፡፡
ምርመራችሁን ጨርሳችሁ ፈርዳችሁበት እያለ ስለሚበላው ሳይሆን ስለምታደርጉበት እናውቅ ዘንድ እስከዛሬ በፍርድ ቤት ራሱን እንዲከላከል እድል በተሰጠው ነበር፤ እኛም ባመናችሁ ነበር፡፡

ከጠበቆች ከእምነት አባቶች እና ቤተሰብ (ወይም ከኤምባሲው ተወካይ) እንዲያገኘው እድል በተሰጠው ነበር፡፡
ዜጎች በሕግ እስካልተወሰነባቸው ድረስ እንደጥፋተኛ ያለመቆጠር መብት (ሕገ-መንግስቱን መጥቀሴ በራሳቸው ሜዳ ለማሳጣት እንጂ ያከብሩታል በሚል የዋህነት አይደለም) በሕገ-መንግስቱ አንቀጽ 20.3 ዛሬም በፖሊስ ተጥሶ የሙስሊም አመራሮች እና ጋዜጠኞች ሽብርተኛ ተብለው ምስላቸው በአጃቢነት ቀርቧል፤ ግልጽ ባልሆነው ይቅርታ የተለቀቀው አርቲስት ደበበ እሸቱ (ሳይፈረድበት) የአሸባሪነት ማጀቢያ በመሆን ስሙ በድጋሚ እንዲጠፋ ሆኗል፡፡
የሚንቀውን ሕዝብ የሚያስተዳድረው ሕወኃት (ኢሕአዴግ) ልሳን የሆነው ኢብኮ (ኢቲቪ) እና የሌባና ፖሊስ ፕሮግራም የኢትዮጵያ ሕዝብ ደንቆሮ ነው ብሎ ያስባሉ፡፡
እኛስ የእነሱን ግምት በዝምታችን እያረጋገጥን እስከመቼ እንቆይ ይሆን?
————————————————————
የጋዜጠኛ ዳዊት ሰለሞን አስተያየት:-

አንዳርጋቸው ጓደኞቹን ሰላም አላቸው
ፍርድ ቤት የመቅረብ፣ ጠበቃ የማቆም፣ በቤተሰቦቹ ፣በወዳጆቹ የመጎብኘትና ሐኪም የማናገር መብቶቹን የተነፈገ ሰው በአፋኞቹ በተዘጋጀለት ቀረጻ (መቀረጹንም ካወቀ) የተናገረው ነገር በምን አግባብ በምርመራ ጥበብ የተገኘ ሊባል ይችላል?
እውነቱን ለመናገር አንዳርጋቸው ጽጌ በዛሬው ቪዲዩ በስም እየጠራ የጠቀሳቸውን ሰዎች እኔ የምቆጥረው የከበረ ሰላምታ እንደላከላቸውና ትግሉን የምር እንዲገፉበት እንዳበረታታቸው ነው፡፡

ፖሊስ በእሰረኞች አያያዝና በምርመራ ወቅት ይጠቀማቸዋል ስለሚባሉ ኢ ሰብዓዊነት የጎደላቸው ቴክኒኮች ውሸትነት ህዝቡን ማሳመን ከፈለገ
—ማዕከላዊ የወንጀል ምርመራን ለህዝብ ክፍት ያድርግ እያንዳንዱ የምርመራ ክፍል ምን አይነት የምርመራ መሳሪያዎች እንዳሉት ጭምር ህዝብ ይመልከታቸው

–በአሁኑ ወቅት በማዕከላዊ የሚገኙና ከዚህ በፊት በወንጀል ምርመራው ያለፉ ዜጎች ገለልተኛ በሆነ አካል ምን እንደተፈጸመባቸውና እነማን እንደፈጸሙባቸው እንዲናገሩ ያድርግ

መቼም የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት የሆኑት እነአቡበከር በፍርድ ቤት የተናገሯቸው ለጆሮ የሚሰቀጥጡ የጭካኔ የምርመራ አይነቶች የፖሊስ ፕሮግራሙ አቅራቢ እንደተናገረው የተፈጸሙባቸው በአይ ኤስ አይ ኤስ ወይም በአሜሪካን ወታደሮች አይደለም ፡፡እነአቡበከር ይህን ግፍ በሰውነታቸው ያሳለፉት በማዕከላዊ የወንጀል ምርመራ ነው፡፡
—————————————–
የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን አስተያየት:-

ህወሀቶች አቶ አንዳርጋቸውን ዛሬ አሳዩን። አሜሪካን ሚስጢር የምታስወጣው በማሰቃየት ነው እኛ ግን በፍቅርና በእንክብካቤ ነው የሚለውን እንድናምንላቸው የሄዱበት ዙሪያ ጥምጥም በራሱ ያደክማል። ለማንኛው አንዲን በማየቴ በግሌ ደስ ብሎኛል፡፡ በተቃዋሚዎች ዙሪያ ህወሀቶች እንዲናገርላቸው ያደረጉት የሚመስለው ግን ያው ቀድመን የገመትነው ነው። ገና ከዚህ የባሰውንም ሊያሳዩን ይችላሉ።
—————————————–
የጋዜጠኛ ደረጀ ሃብተወልድ አስተያየት:-
ምዕራባውያን ሀገሮች- በሰላማዊና በትጥቅ ትግል ከሚንቀሳቀሱ አንዳንድ ተቃዋሚዎች ጋር እንዲያደራድሩት ጥያቄ እንዳቀረበ በኢሳት በመነገሩ የተበሳጬው የኢህአዴግ መንግስት፤ በዛሬውፖሊስ ፕሮግራም መቶ ቦታ የተቆራረጠ የአቶ አንዳርጋቸውን ንግግርና ምስል በማቅረብ ምላሽ ለመስጠት ሞክሯል። ወይ ጭንቀት!!!
አንዳርጋቸው፤ሁሌም ጀግና ነህ!!!
——————————
ሳም ቮድ ሶን አንዳርጋቸው የተባሉ ግለሰብ የሰጡት አስተያየት:-
ወያኔ አሁንም እንደለመደው ቆርጦ እና ቀጥሎ በ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ ይሄንን ቪድዮ ለቋል እውነታው ግን እስካሁን ድረስ የ ኢንግሊዟ አምባሳደር ባለፈው ለጉብኝት በሄዱበት ወቅት የት ቦታ እንደወሰዷቸው አና አካባቢውን የት ቦታ እንኳ እንደታሰረ እንደማያውቁ ባለፈው ገልፀዋል እናም ወያኔ ለፕሮፖጋንዳው እንዲመቸው አድርጎ ቆርጦ እና ቀጥሎ ይሄንን ቪድዮ ለቀቀ እውነት አንዳርጋቸው ምን ተጠይቆ ነው የተናገረው ለምን የጠያቂው ድምፅ እና ጥያቄው ምን እንደሆነ አያሰሙንም ደሞ ይህ ቪደዮ አሁን የተቀረፅ ለመሆኑ ምንም አይንአይንተ ማስረጃ የለም::
———————————–
የሁኔ አቢሲኒያ አስተያየት:-

በዛሬው እለት በፖሊስ ፕሮግራም የተለቀቀው የጋሽ አንዳርጋቸው ጽጌ ቪዲዮ ጋሽ አንዳርጋቸው ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰበት ያስታውቃል።
ከሞቀ ኑሮው መካከል ስለህዝቡ ሲል እንዲህ ይሰቃይ? እስከመቼ ጀግኖቻችንን ለጅብ ሰጥተን ልንተኛ ይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ምርመራ የምናደርገው ሰብአዊ በሆነ መልኩ ነው እያለን ነው – የወያኔ ፖሊስ::

የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ እንቅስቃሴ ደጋፊዎች ህብረት የአቋም መግለጫ

$
0
0

UCMየኢትዮጵያ ሙስሊሞች ሰላማዊ ና ህጋዊ የመብት ማስረከብ ትግል ከጀመረ እነሆ ሶስት አመት አስቆጠረ ለዚህ ሰላማዊ የመብት ትግል መነሻ የሆነው ሙስሊሙ ህብረተሰብ ሶስት ህጋዊ የመብት ጥያቄዎችን ለመንግስት በማቅረብ ምላሽ እንዲሰጣቸው በወከላቸው የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አማካኝነት ከመንግስት ጋር ውይይት ከጀመሩ ቦኋላ መንግስት ከሙስሊሙ ህብረተ ሰብ ለቀረበለት ጥያቄ መልስ ከመስጠት ይልቅ የህዝበ ሙስሊሙን ጥያቄ ይዘው የቀረቡትን ህዝቡ መርጦ የወከላቸው መሪዎቹን አስሮ ጥያቄዎቻቸውን በማዳፈን መልስ ለመስጠት ፈቃደኛ ባለመሆኑ ነበር። --[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]=—–


Hiber Radio: “አንዳርጋቸው በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ይህን እንደተናገረ ይታወቃል”–ኤፍሬም ማዴቦ የግንቦት 7 ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ (እና ሌሎችም ዘገባዎች)

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ ታህሳስ 26 ቀን 2007 ፕሮግራም

ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለብርሃነ ልደቱ አደረሳችሁ !

< ...በአንዳርጋቸው ላይ የተለያዩ የፕሮፖጋንዳ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩ አስቀድመን አውቀናል ።በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደተናገረ ይታወቃል። ይሄኛው ቪዲዮ ከዚህ ቀደም አገዛዙ ካሳያቸው ሁሉ መናኛ ነው አስገድደው እንደሚያናግሩት የታወቀ ነው።ይሄ ስርዓት በሰቆቃ የተገነባ ነው...የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግንቦት ሰባት እና አብረውት ከሚሰሩት ሁሉ የሚጠብቀው ነገር አለ። የትግላችን የመጨረሻ እርምጃ ላይ ደርሷል...ለጠላታችን ግን መጣንልህ ...>>

አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የግንቦት ሰባት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ የ ዝብ ግንኙነት ሀላፊ የህወሓት አገዛዝ ትላንት በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ያሰራጨውን ፊልም ጉዳይ በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ ጠቅሰዋል (ሙሉውን ያዳምጡ)

<... ምርጫው ውስጥ ለመግባት ወይም ላለመግባት አልወሰንም ለምርጫው ግን መስራት ያለብንን እየሰራን እንቆያለን...ያነሳናቸው ጥያቄዎች ባልተመለሱበት ሁኔታ በእኛ በኩል ምርጫ መግባት አለመግባት የሚታሰብ አይደለም። ያነሳነውን ጥአቄ ለማስመለስ የሚከፈለውን መስዋዕትነት ለመክፈል እኛ ቆርጠናል እነሱም....>>

አቶ ግርማ በቀለ የዘጠኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች ትብብር ዋና ጸሐፊ የትብብሩን ሁለተኛ ዙር የትግል መርሐ ግብር መተመለከተ ለህብር ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

<<..የቤቴ ዋጋ ጨምሯል በሚል ተጨማሪ ብድር መውሰድ ብዙ ጊዜ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል...በዕዳ ብዛት የሚሄዱበትን አጥተው በአጣብቂኝ ራሳቸውን ያጠፉ ኢትዮጵያውያን እኮ አሉ መጠንቀቅ ያስፈልጋል ...>>

አቶ ተካ ከለለ በአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ የቤት ዋጋ ጨምሯል በሚል ስለሚወሰድ ተጨማሪ ብድር የሚያስከትለውን ጥቅምና ጉዳት አብራርተዋል(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በአቶ አንዳርጋቸው ላይ የተሰራ የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ፊልም በራሱ የሰብአዊ ጥሰትን ያሳያል

የጅቡቲ ሰራዊት የኢትዮጵያን ግዛት ዘልቆ መግባቱ የአፋር ተወላጆችን አስቆጣ

አፋሮች የክልሉን ፕሬዝዳንት ለፍርድ ለማቅረብ ዝተዋል

የኤርትራው ፕ/ት ኢሳያስ አፈወርቂ በአገራችን ላይ ጦርነት ታውጆብናል ጠላቶቻችንን እናሸማቅቃለን ሲሉ ዛቱ

ከኢትዮጵያ ስለኮበለሉት ፓይለቶች ዛሬም ዝምታን መርጠዋል

ሕጋዊው ቅዱስ ሲኖዶስ በስሜ የተሰራጨው ህገደንብ የተሳሳተ ነው ሲል አስታወቀ

ኢትዮጵያዊ ደም ያለው ጌዲዮን ዘላለም ለአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን በመጫወት የመጀመሪያ ሊሆን ነው ተባለ

በአቶ አንዳርጋቸው ላይ አገዛዙ ይፋ ያደረገው ፊልም የስርዓቱን ኢሰብዓዊ አያያዝ ሊያስተባብል መሞከሩ እንደማይሳካ ተገለፀ

ፊልሙን ተከትሎ ከአገር ውስጥና ከውጭ በማህበራዊ ሚዲያው በስርዓቱ ላይ ተቃውሞው ቀጥሏል

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

(ህብርን ከዘሐበሻ፣አፍሮ አዲስ ድህረ ገጾችእና በሌሎችም ያዳምጡ። በተጨማሪ በማንኛውም ቀን በስልክ ለማዳመጥ 2139924347 ይደውሉ)ነ

Hiber radio Las Vegas ይህ ህብር ሬድዮ _የወቅታዊ መረጃ ምንጭ ነው። ህብር ሬድዮ በአቤኔዘር ኮሙኒኬሽን ሴንተር እየተዘጋጀ ከላስ ቬጋስ ከተማ፣ ዘወትር ዕሁድ በአካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 6፤30 ሰዓት እስከ 8 ሰዓት በ1340 ኤ.ኤም የአየር ሞገድ ያዳምጡ። በቀጥታ በስልክ ለማዳመጥ 712 -432-8451 መደወል ብቻ በቂ ነው።

\

ዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ለአስራ አምስተኛ ጊዜ ተቀጠሩ

$
0
0

zone 9

በዛሬው እለት በካንጋሮ ፍርድ ቤት የቀረቡት የዛኦን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ከዚህ ሁሉ ኢ-ፍትሃዊ እስር በኋላም ቢሆን ከፊታቸው ላይ ሳቅና ፈገግታን ሊነጠቁ ያልቻሉ መሆኑ በግልጽ ለአምባገነኖች እና አሽከሮቻቸው አሳይተዋል:: በሙሉ ራስ መተማመን ስሜት እና በታላው ብሩህ መንፈሳቸውን ተላብሰው ካንጋሮ ፍርድ ቤት ይደረሱት ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን የአሸናፊነት ስሜት በፊታቸው ይነበባል::ፖሊስ ጉዳዩን የሚከታተሉ እና በፍርድ ቤቱ የተገኙትን ስልካቸውን እንዲያጠፉ ያደረገ ሲሆን በችሎት ክተሰየሙት ዳኛ አንዱ መቀየራቸውም ታውቋል:;እንዲሁም ፖሊስ ያሰራቸውን ጦማርያን እና ጉዳዩን ሊክታተሉ የመጡትን በአይን እንኳን እንዳይነጋገሩ ሲያዋክብ ታይቷል::

በኢሕአዴግ አቃቢ ህግ የተፈበረኩ የሃሰት ክሶች ላይ ቡድን ድርጅት የተባሉት፣የተከሳሾች የሥራ ድርሻ እንዲሁም የ48ሺህ ብር ጉዳይ አልተሻሻሉም ከተባሉት ክሶች ውስጥ ተካተዋል።በተጨማራም የተለያዩ ስልጠናዎችን ወስደዋል የተባለው በዝርዝር እንዲቀርብ አዟል። ከዚህ ውጪ ያሉ የክስ ማሻሻያዎች ተቀባይነት አግኝተዋል። ፍርድ ቤቱ አልተሻሻሉም ብሎ የጠቀሳቸው አራት ነጥቦች በድጋሚ ተሻሽሎ እንዲቀርብ ለጥር 6 ቀጠሮ ሰጥቷል። (ምኒልክ ሳልሳዊ እንደዘገበው)

የግንቦት 7 ሕዝብ ግንኙነት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ስለ አዲሱ የአንዳርጋቸው ቪዲዮ ተናገሩ (ያድምጡ)

$
0
0

የግንቦት 7 ለፍትህና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ የ ዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ኤፍሬም ማዴቦ የህወሓት አገዛዝ በአቶ አንዳርጋቸው ላይ ያሰራጨውን ፊልም ጉዳይ በተመለከተ ከህብር ሬዲዮ ጋር ቃለ ምልልስ አድርገዋል:: ያዳምጡት::

< ...በአንዳርጋቸው ላይ የተለያዩ የፕሮፖጋንዳ ቪዲዮዎች እንደሚያሳዩ አስቀድመን አውቀናል ።በምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንደተናገረ ይታወቃል። ይሄኛው ቪዲዮ ከዚህ ቀደም አገዛዙ ካሳያቸው ሁሉ መናኛ ነው አስገድደው እንደሚያናግሩት የታወቀ ነው።ይሄ ስርዓት በሰቆቃ የተገነባ ነው...የኢትዮጵያ ሕዝብ ከግንቦት ሰባት እና አብረውት ከሚሰሩት ሁሉ የሚጠብቀው ነገር አለ። የትግላችን የመጨረሻ እርምጃ ላይ ደርሷል...ለጠላታችን ግን መጣንልህ ...>>
የግንቦት 7 ሕዝብ ግንኙነት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ ስለ አዲሱ የአንዳርጋቸው ቪዲዮ ተናገሩ (ያድምጡ)

የወልቃይትን መሬት በተመለከተ በብአዴን አመራሮች መካከል አለመግባባት ተፈጥሯል

$
0
0

ሁኔ አቢሲኒያ

Photo File

Photo File

ከ1983 ዓ.ም ጀምሮ የአማራ ህዝብ መሬት በግፍ እየተቀማ ለትግራይ ነዋሪዎች ከትግራይ ህዝብም ለህወሀት ደጋፊዎች መከፋፈሉ ይታወሳል ይህንን ተከትሎ ላለፉት በርካታ አመታት የራያ፣ የሁመራ እና የወልቃይት ህዝብ ለስደት እና ለጥፋት የተዳረገ ሲሆን ከሰሞኑም የትግራይ ክልልን ለማስፋፋት በተደረገው ጥረት ተቃውሞ ያሰሙ የክልሉ ነዋሪዎች ለድብደባ እና ለእስር መዳረጋቸውን ተከትሎ የአካባቢውን ህዝብ ለማነጋገር ወደስፍራው አቅንተው የነበሩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከፍተኛ ተቃውሞ ድርሶባቸው ወደባህርዳር መመለሳቸውን ተከትሎ በዛሬው እለት ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች እና የክልሉ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከቀኑ 4 ሰዓት ጀምሮ ባህር ዳር የክልሉ መስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ስብሰባው ባለመስማማት እስከ 6፡30 ከተካሄደ በኋላ ተሰብሳቢው የተባለው መሬት የአማራ መሬት ነው የሚል አዝማሚያ በማሳየቱ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የገቡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከምሳ በኋላ ስብሰባው ሲጀመር ከፌዴራል መንግስት መመሪያ መምጣቱን ተናግረው የሚቀጥለው ቅዳሜ ጥር 2 በአቶ አዲሱ ለገሰ እና በአቶ በረከት ስምኦን ሰብሳቢነት ስብሰባው ከእንደገና እንደሚካሄድ ተናግረው ስብሰባውን በትነውታል።

ይህንን ዜና ከባህር ዳር ያደረሰኝ ግለሰብ እንዳረጋገጠልኝ ከሆነ የወልቃይት መሬት ጉዳይ የክልሉን ካድሬ ቁጭት ውስጥ እንደከተተው የታወቀ ሲሆን ቅዳሜ የሚፈጠረውን ጉዳይ ለመገመት አስቸጋሪ መሆኑን ጨምሮ ገልጿል።

ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ ዝዋይ የታሰሩ 16 የፖለቲካ እስረኞች ጠያቂና ምግብ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

• የሰማያዊ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ እንዳይጠይቁ ተከልክለዋል

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን ጨምሮ በዝዋይ የፌደራል ማረሚያ ቤት ታስረው የሚገኙ 16 የፖለቲካ እስረኞች ባልታወቀ ምክንያት ጠያቂና ምግብ እንዳይገባላቸው ተከለከሉ፡፡

temesgen1ዛሬ ታህሳስ 28/2007 ዓ.ም የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ም/ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ በላይ ማናዬ የገናን ዋዜማ ዝዋይ ከሚገኙ እስረኞቹ ጋር ለማሳለፍ ከአዲስ አበባ ተነስተው ወደ ዝዋይ አቅንተው የነበር ቢሆንም ሊጠይቋቸው ያስጠሯቸው የፖለቲካ እስረኞች ‹‹በማንኛውም አይነት ሰው መጠየቅ አይችሉም፡፡ ምግብም አይገባላቸውም፡፡›› ተብለው ሳይጠይቁ ለመመለስ ተገደዋል፡፡

ጠያቂዎቹ ‹‹የመጠየቅ መብት አለን›› በሚል ወደ ውስጥ ለመግባት ግፊት በማድረጋቸው ፖሊሶች ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፣ ጋዜጠኛ ውብሸት ታዬ፣ አበበ ቀስቶ፣ ናትናኤል መኮንን፣ በቀለ ገርባ፣ ጄኔራል አሳምነው ጽጌና ጀኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ ጠያቂና ምግብ እንዳይገባላቸው የተከለከሉትን የ16 የፖለቲካ እስረኞችን ስም ዝርዝር አሳይተዋቸዋል፡፡

የሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶችና የነገረ ኢትዮጵያ ባልደረባ ለእስረኞቹ ምግብና ጠያቂ እንዳይገባ የተከለከለበትን ምክንያት ለማጣራት ቢሞክሩም ፖሊሶች ‹‹የሚጣራ ነገር ስላለ ነው፡፡ እሱ እየተጣራ ነው፡፡›› ከማለት ውጭ ምክንያቱን በግልጽ ሊነግሯቸው አልቻሉም፡፡

ክልከላው እስከመቼ እንደሚቆይ በውል የታወቀ ነገር የሌለ ሲሆን ከአዲስ አበባ ተነስቶ የገናን በዓል ዋዜማ ከእስረኞቹ ጋር ለማሳለፍ ወደ ዝዋይ ካቀናው የሰማያዊ ፓርቲ ልዑክ በተጨማሪ የእስረኞቹ ቤተሰቦችም በክልከላው ምክንያት ሳይጠይቁና ምግብ ሳያስገቡ ተመልሰዋለል፡፡

የአንደርጋቸው ፅጌ አስገራሚ መልዕክት ከማይታወቀው እስር ቤት

$
0
0

ከእያስፔድ ተስፋዬ

ትናንትና በኢትዮጲያ ቴሌቪዥን በፖሊስ ፕሮግራም ላይ ተቆርጦ ተቀጥሎ የተላለፈው የአንዳርጋቸው ፅጌ ድንቅ የትግል ጥሪ መልዕክት ለሊቱን ሙሉ ሲደንቀኝ ነው ያደረው፡፡ ኢቲቪ በነካካ እጇ ያልተቆራረጠውን ሙሉ ቪዲዮ ደግሞ ብትለቅልን እንዴት ሸጋ ነበር፡፡ 

አንዳርጋቸው ፅጌ በተቆራረጠው ቪዲዮም ውስጥ እንኳን ያስተላለፋቸው 3 መልዕክቶች ድንቅ ናቸው፡፡ ሙሉውን ንግግሩን ፅፌ እለጥፈዋለሁ፡፡ እስከዛው ግን መልዕክቶቹ እነኚህ ናቸው፡- 

1ኛ፡- ለወጣቱ የተላለፈ የትግል ጥሪ፡- ወጣቱ የሴት ጓደኛውን ቀጥሮ ሸሚዙን ሲያስተካክል መዋል ሆኗል ስራው፡፡ እንዴት አድርጎ ከኢትዮጲያ እንደሚወጣ እና ደቡብ አፍሪካ ወይም አሜሪካ እንደሚገባ ብቻ ነው የሚያስበው፡፡ ወደ ፖለቲካው የሚመጣው ወጣት ቁጥር እጅግ አናሳ ነው፡፡ ተፒለፍ እና ኢህአፓ ጊዜ የነበረው ፖለቲካ በትምህርታቸው ጎበዝ የነበሩ ተማሪዎችን ሳይቀር ነበር የሚስበው፡፡ አሁን ግን የፊልም አክተር እና ዘፋኞች የሚኖሩበትን ቤት በፊልም እያየ በምኞት ብቻ የሚኖር ወይም እንዲህ አይነት ቤቶች ወዳሉበት አካባቢ ለመሰደድ የሚፈልግ ወጣት ነው ያለው፡፡ በሚል አንዳርጋቸው ወጣቱ ካረፈበት የእንቅልፍ አዚም እንዲላቀቅ እና ለትግል እና ለመደራጀት እንዲዘጋጅ ያስተላለፈው መልዕክት ነው፡፡


2ኛ፡- የተባበረ ትግል ጥሪ፡- አንዳርጋቸው ይህንን ጥሪ ያስተላለፈው ለሶስት አካላቶች ነው፡፡ አንደኛ የኦሮሞ የአማራ እና የደቡብ ኤሊቶች ልዩነታቸውን አጥብበው በህብረት እንዲሰሩ የጠየቀበት፡፡ ሁለተኛ በውጭ ያሉ የፖለቲካ ድርጅቶች 5 እና 20 እየሆኑ ለየብቻቸው የሚያደርጉትንና እንደ አንዳርጋቸው አገላለፅ ‹‹ዩኒቲ ኦፍ ፐርፐዝ›› የሌለበትን ትግል እንዲተው የተናገረበት እና ሶስተኛ ደግሞ በሀገር ውስጥ የሚገኙ ዘጠና ፓርቲዎች 1500 ፊርማ ብቻ እያሰባሰቡ እዚህ እና እዚያ የፈሉበትን ሁናቴ የተቃወመበት ነው፡፡
3ኛ፡- ምርጫ ቀልድ መሆኑን ያጋለጠበት መልዕክት፡- መንግስት ግልፅነት ያለው አሰራር ሳይከተል ተቃዋሚዎች እንዴት ብለው ነው የምርጫ ማኒፌስቷቸውን ማዘጋጀት የሚችሉት የሚል ጥያቄ በቪዲዮው ላይ ሲጠይቅ የሚሰማው አንዳርጋቸው ፅጌ ቃል በቃል ‹‹ምርጫው ቀልድ ነው›› ሲልም ይደመጣል፡፡ 

andargacew Tsige
ሌላው በዚህ ቪዲዮ ላይ ያስተዋልኩት ነገር ከ 6 ደቂቃ ከ 55 ሰከንድ እስከ 7ኛው ደቂቃ ከ 4 ሰከንድ ድረስ እጅግ በጣም ሳግ በተናነቀው እና በተጎዳ ድምፅ ‹‹ከዚህ በኋላ ያለው ነገር የበለጠ ቀውስ እና የበለጠ ኪሳራ በሀገሪቷ እና በህዝቧ ላይ የሚያደርስ ነገር ነው የሚል ዕምነት ነው ያለን›› የሚለው ንግግሩ ነው፡፡ ምኑ ነው የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ ያመጣል ያለው ነገር; ምናልባት ኢቲቪ ትጥቅ ትግሉ የበለጠ ኪሳራ ያመጣል እያለ ነው የሚል ምስል በተመልካች ዘንድ ለመፍጠር አሳባ ነው; ያም ቢሆን ደግሞ ትጥቅ ትግሉ የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ ያመጣል ሲል ማሰማት ነበረባት፡፡ እኔ ግን ሲመስለኝ የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ የሚያመጣ ያለው ምርጫውን እና አሁን ያለውን ስርአት ነው፡፡ ይህን ያልኩበት ምክንያትም በንግግሩ መጨረሻ ላይ የበለጠ ቀውስ እና ኪሳራ የሚያደርስ ነው የሚል እምነት ነው ‹‹ያለኝ›› ሳይሆን የሚለው ‹‹ያለን›› ነው የሚለው፡፡ ይህ ማለት የአንድን ቡድን አቋም እየገለፀ እንዳለ ግልፅ ነው፡፡ በቡድን ደረጃ ያውም አንዳርጋቸው ‹‹እኛ›› እያለ የሚያወራለት ቡድን ደግሞ ስለ ትጥቅ ትግሉ እንዲህ አይነት አቋም እንደሌለው ግልፅ ነው፡፡


በመጨረሻም ቪዲዮውን ደግሜ ደጋግሜ ካየሁት በኋላ የገባኝ ነገር ቢኖር አንዳርጋቸው ባገኛት ትንሽ ቀዳዳም ቢሆን መልዕክቱን ማስተላለፉን እና ምናልባትም ይህ መልዕክት በቴሌቪዥን እንዲሰራጭ ያደረጉት ሰዎች የውስጥ አርበኛ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው፡፡

የአውስትራልያ እና የኢየሩሳሌም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ አባ መቃርዮስ የልደትን በዓል በማስመልከት ያስተላለፉት መልዕክት

$
0
0

አባ መቃርዮስ ሊቀ ጳጳስ ዘኢየሩሳሌም ወአውስትራልያ ወዘኵሎን አድያሚሃ
ABBA MEKARIOS ARCHBISHOP OF THE DIOCESE OF JERUSALEM AND AUSTRALIA

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
ክብር ለእግዚአብሔር በአርያም ሰላምም በምድር ይሁን ሉቃስ 2፤14

Abune Mekariosለተወደዳችሁ በአውስትራልያና በመላው ዓለም ለምትገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካህናትና ምዕመናን! እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት በሰላም አደረሳችሁ።

የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ሰውና እግዚአብሔር የተገናኙበት፤ ትንቢተ ነቢያት የተፈጸመበት፤ እርቅና ሰላም የተሰበከበት ምድራውያንና ሰማያውያን ፍጥረታት በአንድ ላይ እግዚአብሔርን ያመሰገኑበት፤ በዓል ነው።

በዚህ ቀን የሩቅ ምሥራቅ ነገሥታት በኮከብ እየተመሩ በመምጣት ለተወለደው ንጉሥ ወርቅ ዕጣን ከርቤ እጅ መንሻ አቅርበዋል። ወርቅ ለመንግሥቱ፤ ዕጣን ለክህነቱ፤ ከርቤ ማኅየዊ ለሆነ ሞቱ ምሳሌ እንደሆነ ሊቃውንት ይተረጉማሉ::

Read Full Story in PDF


በስደት ከሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤ/ክ የልደትን በዓል በማስመልከት የተላለፈ ቃለ ቡራኬ

ጎበዝ ጠንከር ነው –ግርማ ሰይፉ የአንድነት ም/ሊቀመነበር

$
0
0

Girma  Seifuምርጫ ቦርድ ማንም ይዘዘው ማንም ወይም በግል ተነሳሽነት እያደረገ ያለው ነገር የኢትዮጵያን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ከምን ጊዜውም በለይ ወደኋላ ለመመለስ እንደሆነ መላው የኢትዮጵያ ህዝብ ሊረዳው ይገባል፡፡ ምርጫ ቦርድ ምርጫ እንዲያሰተዳድር በተሰጠው ኃላፊነት የፓርቲዎች አስተዳደሪ ለመሆን እየቃጣው ያለ ተቋም ነው፡፡ ስናከብረው ለመከበር ፈቃደኛ አልሆነም፡፡ ለዚህ ተቋም መጠናክር የበኩላችንን መወጣት አለብን ብለን የተነሳን ፓርቲዎችን ጭምር እየገፉ አለቆቹን ለማስደሰት ደም ተግቶ እየሰራ ይገኛል፡፡ ይህን የሚያደርጉትን ሰዎች ደግሞ በህዝብ ፊት ለብይን እንዲቀርቡ በግልፅ ማጋለጥ ይኖርብናል፡፡
ትላንትና ዶ/ር አዲሱ በሚዲያ ቀርቦ የተናገረው በምንም መልኩ አንድነትን አይመጥንም፡፡ የተቀሩት የቦርድ አባላትም ይመጥነናል ካሉ ትዝብት ላይ ይወድቃሉ፡፡ የምርጫ ቦርድ አባላት ሳያገባቸው እንፈትፍት ሲሉ መፈተፍቱን ለእኛ ተዉልን ነው ያልናቸው፡፡ ዶ/ር አዲሱ በሚዲያ የቦረድ ውሳኔ ሊሆን ይችላል ብሎ ካቀረበ በኋላ ዛሬ ታህሳስ 28 2007 ቦርድ ተሰብስቦ ውሳኔ ሰጥቶዋል፡፡ ይህን ውሳኔ እንገራችሁ ብለው በስልክ ከጠሩን በኋላ የአንድነት ፓርቲ የወረዳ አባላት የሆኑትንም በተመሳሳይ መልክ ጠርተው ነበር፡፡ ለነገሩ ይህ አካሄድ አንድነትን ስለማይመጥን በፅሁፍ እንዲገልፁልን ነግረናቸው ተመልሰናል፡፡ ለማንኛውም ዶ/ር አዲሱ የሰጠው መግለጫ ይህ መግለጫ እንዲሰጥ የወሰኑትን ጨምሮ ለተቀሩት የቦርድ አባላት ያላቸውን ንቀት የሚያሳይ ነው፡፡ ቦርዱ ተሰብሰቦ ምንም ዓይነት ውሳኔ ከመወሰኑ በፊት ውሳኔውን ሚዛን የሚያሳጣ መግለጫ ለመስጠት ምን እንዳጣደፋቸው መገመት ቀላል ነው፡፡ በልባቸው የሚደግፉትን ፓርቲ ለማንገስ ያላቸውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ነው፡፡
ልክ የዛሬ አምስት ዓመት አንድነት ላይ ተመሳሳይ ግብ ግብ ተፈጥሮ ነበር፡፡ የዚህ ተልዕኮ ፈፃሚዎች ዛሬ ላይ ሆነው ምን እንደተጠቀሙ ሲያሰላስሉ ምን እንደሚሰማቸው ባላውቅም ዛሬ በዚህ ተግባር ላይ የተሰለፉት አባላት ደግሞ ምን እንደሚያደርጉ መጠበቅ ነው፡፡ ለመማር ያልተፈጠረን ሁሉ ምንም ማድረግ ይቻላል? ማንም ተላላኪና ላኪ ሆኖ ቢያገለግልም ዛሬ የተሰማኝ ነገር አንድነት በምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን እንደዚህ ዓይነት ተቋማት በምን ያህል ደረጃ ለመዋረድ ዝግጁ እንደሆኑ ለመረዳት የሚያስችል ነው፡፡ አሁንም ትግሉ መራራ፣ የሚያስከፍለው መስዋህትነትም ውድ ሊሆን እንኳን ቢችል የአንድነት አባላት በድል እንደሚወጡት ምንም ጥርጥር የለኝም፡፡ እሩቅ እንደሆነ አውቀን ለጀመርነው ትግል አቋራጭ እንደማንፈልግ መግለፅ ይኖርብናል፡፡
ውድ የአንድነት አባላት ለቀጣይ አንድነት ከምርጫ ቦርድ አሻጥር ለማላቀቅ ለምናደርገው ትግል ቀበቶ ጠበቅ ነው፡፡ ከሰማይ በታች አንድነት ለመፍታት የማይችለው ፈታኝ ነገር ምርጫ ቦርድም ሆነ በውሰጥችን ያሉት ዙንቢዎች ሊያቀርቡ አይችሉም፡፡ ጎበዝ ጠንከር ነው፡፡

 

ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ – አቶ ተክሌ በቀለ የአንድነት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር
አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን ጋርና በምን ሁኔታ እንደሚፈልገዉ ፓርቲያችን ሶስተኛዉን (የአዉሮፓና አሜሪካ ታዛቢዎች የሌሉበት ምርጫ መሆኑን፤የህዝብ ታዛቢዎች የተበላሸ የምርጫ ሂደትና ፓርቲዎችን የማፈራረስ/የማዳከም ስራዎች) ነጥብ አስመዝግቧል፡፡
በዚህ ሂደት ላይ ሰፊ እዉነታ ለህዝብ ይቀርባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ከምርጫዉ ቦርድ መጋረጃ ካሉት ወገኖች ጋር በሃሳብ እየተሸነፈ ግን ተሳትፎዉ ያለተቋረጠ አንድ ከፍተኛ አመራር እንዳለ እናዉቃለን፡፡ሁሉን ነገር በደንብና በመርህ የምንሰራዉ ለኢህኣዲግ/ምርጫ ቦርድ ካለን ፍርሃት ሳይሆን ለወደፊቱ ለምናስተዳድረዉ ህዝባችንና ለኢትዮጵያችን ፖለቲካ ክብር ስንል ነዉ፡፡እናም ከደንብ ወጥተን የሰራነዉ ክዋኔም በግፍ የገፋነዉ አመራርም፤አባልም የለም፡፡በመቻቻል መንፈስ ዲሰፒሊን ተጥሶም እንዲጓተት ተደርጓል፡፡ይህንንም የኢህኣዴግ ተባባሪነት ለታሪክ አስቀምጠነዋል፡፡
ምርጫ ቅንጦት ሆኖብን፤የተከበሩ እየተባሉ ለመጠራት ሳይሆን እፊታችን ላይ ያለ እድልና ስልትም ስለሆነ አንድነት ፓርቲ መጪዉን ምርጫ የምር እንዲሆን ወስኗል፡፡ ኢህኣዴግ ደግሞ ማበላሸቱን ተያያይዞትል፡፡ምርጫ በአምባገነን ቡድኖች ለሚገዙ አገራት ለለዉጥ እንዱ ስልት እንጂ ብቸኛዉ አለመሆኑ ይታመናል፡፡ፓርቲያችን ለለዉጥ ተደራጅም ይላል፡፡እዉነተኛ ፓርቲዎች ከምርጫዉ ባሻገር ላለዉ ግብ እንዲዋሃዱና እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርቧል፤ስልቶችን ለማቀራረብም እየጣረም ነዉ፡፡የአንድነት ኣባላት በያለንበት ድርብ ሃላፊነት አለብን፡፡ለአንድነት ሃይሎች ስልቶቻችን ሁሉ በማቀራረብ የተጀመረዉ የስልጣን ሃይሎችን እያራገፉ ትግሉን በሰለጠነና አንድነቱን በጠበቀ መልኩ የማስቀጠልና ልዩነቶችን በማቻቻል ሰፊ መሰረት የማንበር ሃለፊነት አለብን፡፡ ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ፤ፊታችንን ወደ ዋናዉ ግብ እናድርግ፤ከሃዲዱ አንወርድም!

 

አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል  – አቶ ኪዳኔ አመነ – የመድረክ ወጣት አመራር
አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ በተመለከተ ብዙ እየሰማን ነው፡፡ ፓርቲው ራሱን የማፅዳት ሃላፊነት ከተወጣ በኋላ ገዢው ፓርቲ ጥርሱን የነከሰበት ይመስላል፡፡ ብዙ ፈተና እየገጠመው ነው፡፡ በምርጫ ቦርድ ጥያቄ መሰረት ጠቅላላ ጉባኤ በድጋሚ እስከማድረግም ደርሰዋል፡፡በኔ እምነት አንድነት ፓርቲ በበኩሉ ብዙ ርቀት የሄደ ይመስለኛል፡፡ ትእግስታቸው አደንቃለሁ፡፡ ፓርቲው በውስጡ ከጥቂቶች በቀር በዙዎቹ ቁምነገር የሚያስቡ የምናከብራቸውና የምንወዳቸው ጥሩ ሰዎች አሉት፡፡ ትርጉም ያለው የፖለቲካ እንቅስቃሴ ከሚያደርጉ ጥቂት ፓርቲዎች አንድነት አንዱ ነው፡፡ እናም በኢትዮጵያ ዴሞክራሲ ና እውነተኛ ፍትህ ለማምጣት የአንድነት መኖር ከፍተኛ ትርጉም አለው፡፡ ፓርቲው የአንድነት ፓርቲ አባላትና የኢትዮጵያ ህዝብ ብቻ ሣይሆን የራሳችን አቋምና መስመር ይዘን በሌላ ፓርቲ ያለን ሰዎች እንኳ አንድነት እንዲኖር አጥብቀን እንፈልጋለን፡፡ ወደፊት አንድነትም እኛም ቤታችን እያፅዳን መንገድ ላይ መገናኘት አለብን፡፡

 

ያኔ ብቻ ነው ኢትዮጵያን የምናድናት፡፡ እንዳንራመድ ቀይዶ የያዘን ገመድ እየበጣጠስን፤ ፀረ-ለውጥና አድሃሪ አቋምን እየመከትንና እያፀዳን የዴሞክራሲ እና የሉዓላዊነት ፍለጋው ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል፡፡
አሁን አንድነት ግልፅ ጦርነት የታወጀበት ይመስላል ፡፡ አንድነቶች አሁን ነው የፖለቲካ ፅናታቸው በጥበብ ማሳየት ያለባቸው፡፡ ወንድሞቻችን በርቱ!!!

 

ሪክ ለመስራት እንዘጋጅ –አቶ ተክሌ በቀለ የአንድነት ተቀዳሚ ም/ሊቀመንበር

$
0
0
ተክሌ በቀለ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት

ተክሌ በቀለ የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት

አንድነት ፓርቲ የኢህኣዴግን ምንነት ላላመኑ ወገኖች ለማጋለጥ በትጋትና በስሌት ሲሰራ ቆይቷል፡፡እየሰራም ነዉ፤እዚህ ደርሷል፡፡ “የሆደ ሰፊዉን ምርጫ ቦርድ” ሆድ በገሃድ አጋልጧል፡፡በነአሞራዉና ወዲ ቐሺ(በተጋሩ ሁሉ) ትግልና ሞት የሚቀልዱትን በህዝብ ፊት ወጥተዉ ዛሬም እንዲዋሹና ለኢትዮጵያችን የፖለቲካ ታሪክ እነማን ምን እንደሆኑ አንድነት ፓርቲ የበኩሉን ሚና ተጫዉቷል፡፡ ለኔ ከባድመ ዉሳኔና ልህዝቡ በወቅቱ ከተነገረዉ ጋር ይመሳሰላል፤ይጠጋጋል፡፡ኢህኣዴግ ምርጫዉን እንደማይፈልገዉ፤ከፈለገዉም ለተለመደዉ ቀልዱ ከነማን ጋርና በምን ሁኔታ እንደሚፈልገዉ ፓርቲያችን ሶስተኛዉን (የአዉሮፓና አሜሪካ ታዛቢዎች የሌሉበት ምርጫ መሆኑን፤የህዝብ ታዛቢዎች የተበላሸ የምርጫ ሂደትና ፓርቲዎችን የማፈራረስ/የማዳከም ስራዎች) ነጥብ አስመዝግቧል፡፡

በዚህ ሂደት ላይ ሰፊ እዉነታ ለህዝብ ይቀርባል የሚል እምነት አለኝ፡፡ከምርጫዉ ቦርድ መጋረጃ ካሉት ወገኖች ጋር በሃሳብ እየተሸነፈ ግን ተሳትፎዉ ያለተቋረጠ አንድ ከፍተኛ አመራር እንዳለ እናዉቃለን፡፡ሁሉን ነገር በደንብና በመርህ የምንሰራዉ ለኢህኣዲግ/ምርጫ ቦርድ ካለን ፍርሃት ሳይሆን ለወደፊቱ ለምናስተዳድረዉ ህዝባችንና ለኢትዮጵያችን ፖለቲካ ክብር ስንል ነዉ፡፡እናም ከደንብ ወጥተን የሰራነዉ ክዋኔም በግፍ የገፋነዉ አመራርም፤አባልም የለም፡፡በመቻቻል መንፈስ ዲሰፒሊን ተጥሶም እንዲጓተት ተደርጓል፡፡ይህንንም የኢህኣዴግ ተባባሪነት ለታሪክ አስቀምጠነዋል፡፡

ምርጫ ቅንጦት ሆኖብን፤የተከበሩ እየተባሉ ለመጠራት ሳይሆን እፊታችን ላይ ያለ እድልና ስልትም ስለሆነ አንድነት ፓርቲ መጪዉን ምርጫ የምር እንዲሆን ወስኗል፡፡ ኢህኣዴግ ደግሞ ማበላሸቱን ተያያይዞትል፡፡ምርጫ በአምባገነን ቡድኖች ለሚገዙ አገራት ለለዉጥ እንዱ ስልት እንጂ ብቸኛዉ አለመሆኑ ይታመናል፡፡ፓርቲያችን ለለዉጥ ተደራጅም ይላል፡፡እዉነተኛ ፓርቲዎች ከምርጫዉ ባሻገር ላለዉ ግብ እንዲዋሃዱና እንዲተባበሩም ጥሪ አቅርቧል፤ስልቶችን ለማቀራረብም እየጣረም ነዉ፡፡የአንድነት ኣባላት በያለንበት ድርብ ሃላፊነት አለብን፡፡ለአንድነት ሃይሎች ስልቶቻችን ሁሉ በማቀራረብ የተጀመረዉ የስልጣን ሃይሎችን እያራገፉ ትግሉን በሰለጠነና አንድነቱን በጠበቀ መልኩ የማስቀጠልና ልዩነቶችን በማቻቻል ሰፊ መሰረት የማንበር ሃለፊነት አለብን፡፡ ታሪክ ለመስራት እንዘጋጅ፤ፊታችንን ወደ ዋናዉ ግብ እናድርግ፤ከሃዲዱ አንወርድም!

የውድ ኮሚቴዎቻችን የሰው ምስክር የማሰማት ሂደት በዛሬው ዕለት ተጠናቋል!

$
0
0

ፈኢዝ መሀመድ ለታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል፣ ለኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ፣ እንዲሁም ለኡስታዝ ካሚል ሸምሱ ምስክርነቱን ሰጥቷል!

ማክሰኞ ታህሳስ 28/2007

የህዝበ ሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎቻችን ችሎት ከግንቦት 5/2006 ጀምሮ አቃቂ ክፍለ ከተማ በሚገኘውና በተለምዶ ‹‹08 አዳራሽ›› ተብሎ በሚጠራው ቦታ የመከላከያ ምስክራቸውን ማስደመጥ ከጀመሩ በኋላ የፍርድ ሂደቱ ሰሚት አካባቢ በሚገኘው በፌደራሉ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ቦሌ ምድብ ችሎት እንዲከታተሉ ሲደረግ የቆየ መሆኑ ይታወሳል፡፡ በዚሁም መሰረት ከግንቦት 5/2006 ጀምሮ የመከላከያ ምስክራቸውን ሲያስደምጡ የቆዩ ሲሆን የዛሬውን ጨምሮ በአጠቃላይ 153 ምስክሮችን አስደምጠው የሰው የመከላከያ ምስክሮቻቸውን በዛሬው ዕለት አጠናቅቀዋል።

10923644_887061558011868_2343527696380665851_n
በዛሬው ችሎት ምስክርነቱን ለሶስት የኮሚቴው አባላት የሰጠው ፈኢዝ ሙሀመድ ሲሆን የመጀመሪያውን ምስክርነቱን ለታሪክ ምሁሩ ኡስታዝ አህመዲን ጀበል አሰምቷል፡፡ አቃቤ ህግ በኡስታዝ አህመዲን ጀበል ‹‹ኢሜል ውስጥ አገኘሁት›› ብሎ ያቀረበው መረጃ እርሱ የጻፈው እንዳልሆነ ያስረዳው ፋኢዝ ሙሃመድ የተባለውን ኢሜል ለኡስታዝ አህመዲን የላከለት ራሱ መሆኑን እና ኢሜል ያደረገውም ከሰለፊያ ጋዜጣ፣ ከኢቲቪ፣ እንዲሁም ከተለያዩ ጋዜጦችና መፅሄቶች ያገኘውን መረጃ መሆኑን ገልጿል፡፡ ከላካቸው ጽሁፎች ውስጥም በወቅቱ የመጅሊስ አካላት ሲናገሩ የነበሯቸውን ንግግሮች እና መጅሊስ የአህባሽ ስልጠና መስጠቱን የሚያመለክቱ መረጃዎች መኖራቸውን ለፍርድ ቤቱ አስረድቷል።
ፋኢዝ ቀጣይ ምስክርነቱን የሰጠው ለኡስታዝ ካሚል ሸምሱ እና ለኡስታዝ አህመድ ሙስጠፋ ሲሆን ኡስታዞቹ ለስሜት አለመገዛትን፣ እውቀት በኢስላም ያለውን ቦታ እና ሃይማኖታዊ መቻቻልን እና እኩልነትን አስመልክቶ ከሰጧቸው ትምህርቶችና ስለጠናዎች ጋር በተያያዘ የቀረበባቸውን ክስ በማስመልከት ክሱን አስተባብሎ ምስክርነቱን ሰጥቷል፡፡ ከአቃቤ ህግ ለቀረበለት መስቀለኛ ጥያቄም በአግባቡ መልስ ሰጥቷል።

644398_887061511345206_3213473828817844196_n

በዛሬው ዕለት ለውድ ኮሚቴዎቻችን ሊመሰክር የነበረው ሁለተኛ ምስክር ላፕቶፕ ኮምፒዩተሩ ከማዕከላዊ ስላልመጣ የቪዲዮ ማስረጃ በሚያቀርቡበት ወቅት አብሮ ምስክርነቱን እንዲሰጥ ትዕዛዝ የተሰጠ ሲሆን የሰው ምስክርነት የማሰማት ሂደቱም ዛሬ ማብቃቱ ታውቋል፡፡ ውድ ኮሚቴዎቻችን ቅሬታዎች እንዳሉባቸው በማሳወቅ አቤቱታ ለማቅረብ ያደረጉት ሙከራም ‹‹በቢሮ በኩል ቀርባችሁ አስረዱ›› በሚል ተቀባይነት አለማግኘቱ ታውቋል፡፡

ቀጣዩ ቀጠሮ የፊታችን ሰኞ ጥር 4/2007 ነው።
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምፃችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

ኮማንደር ቢኒያም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝን በድቅድቅ ጨለማ ብርድ ላይ እያስተኛው በማሰቃየት ላይ ነው

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በካንጋሮው ፍርድ ፍትሃዊ ባልሆነ ፍርድ እስር ቤት የተወረወረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ፍርድ ቤት በማያውቀው ሁኔታ በአንድ የህወሓት ኮማንደር በእስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት እንደሚገኝ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።

Temesgen Desalegn behindbarኢትዮጵያ በአሁኑ ሰዓት ማን እንደሚመራት በማይታወቅባት ሁኔታ አንድ ደህንነት ወይም ወታደር የፈለገውን የማዘዝ ስልጣን ያለው ሲሆን እንገዛለታለን የሚሉትን ህገመንግስት ወደ ጎን በመተው የፈለጋቸውን እርምጃ እየወሰዱ በመሆኑ በስር ዓቱ ውስጥ ያለውን አለመደማመጥ ያሳያል የሚሉ የፖለቲካ ተንታኞች በቅርቡ ድምፃዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን በአንድ ደህንነት ት ዕዛዝ ብቻ ለ3 ሳምንታት ከሃገር እንዳይወጣ ፓስፖርቱን መቀማቱን ያስታውሳሉ።

በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በዝዋይ እስር ቤት እየደረሰ ያለው ስቃይ ኮማንደር ቢኒያም በሚባል አዛዥ ሲሆን ተመስገንን በአንድ ምሽት ከ5 ጊዜ በላይ በድቅድቅ ለሊት በማስወጣት ብርድ ላይ እንደሚያስተኙት ከስፍራው የደረሰው መርጃ ያጋልጣል።

በተለይ ተመስገን ደሳለኝ “የመንግስት ገመና” በሚል ከእስር ቤት ከፃፈ በኋላ ደህነነቶች እና ይኸው ኮማንደር ቢኒያም የሚባል አዛዥ የእንግልሃለን ሬሳህን እዚህ ብንጠለው ዞር ብሎ የሚያይህ የለም በሚል እንደሚያስፈራሩት የጠቆሙት የዜና ምንጮቻችን ድብደባ እንደተፈጸመበትም ታውቋል።

ኢትዮጵያ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ግለሰቦች የሚያዙባት፤ በአንድ ግለሰብ ትዕዛዝም ሕይወት የሚጠፋባትና የሚበላሽባት ሃገር እየሆነች መምጣቱ የስርዓቱን ደጋፊዎች ሳይቀር እያስቆጣ እንደሚገኝ ከተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>