Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍትዊ ግደይ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተገደሉ፤

$
0
0

newsየአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ (አወጋን) አመራሮች በዛሬው እለት እንደገለጹልኝ ከሆነ የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ፍትዊ ግደይ ወረኢሉ ከተማ በሚገኘው መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ የአቶ ፍትዊ ባለቤት ባሉበት በአወጋን አባላት በጥይት መገደላቸው የታወቀ ሲሆን አቶ ፍትዊ የደቡብ ወሎን ሠው በከፍተኛ ሁኔታ ሲያስሩ ሙስሊሙን «ፅንፈኛ»፣ ክርስቲያኑን «የድሮ ስርዓት ናፋቂ» በማለት በወሎ ክፍለ ሐገር ታሪክ ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ የወሎ ሙስሊምና ክርስቲያንን ለመከፋፈል የሞከረ ግለሠብ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን የአቶ ፍትዊን ግድያ ተከትሎ በወረኢሉ ከተማ ፍተሻው በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከሩን ለመታዘብ መቻሉን አመራሮቹ ይገልፃሉ።

በመጨረሻም የአቶ ፍትዊ ግደይ ግድያ ለሌሎች የህወሓት አመራሮች እና ጀሌዎች ትምህርት ይሆን ዘንድ የሟቹን ግለሠብ በሞተበት ሠዓት የተነሳውን ፎቶ ከነሙሉ መረጃው በድህረ ገፆች እና በማህበራዊ ሚዲያዎች እንደሚለቀቅ አስታውቀዋል።

~~ሁኔ አቢሲኒያ~~

The post በአማራ ክልል የደቡብ ወሎ ዞን የደህንነት ቢሮ ሀላፊ አቶ ፍትዊ ግደይ መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ ተገደሉ፤ appeared first on Zehabesha Amharic.


የምርጫ ቦርድን ልጓም ማን ይግታው???

$
0
0
2010-05-22T122316Z_783959720_GM1E65M1KO302_RTRMADP_3_ETHIOPIA-ELECTIONS_0_0በእኔ እምነት ምርጫ ቦርድ ልጓሙን በጥሶ መፈርጠጥ ጀምሯል፡፡ አዎ ምርጫ ቦርድም ሆነ ኢህአዲግ በህግ የበላይነት ሊያምኑና ህግን ሊያከብሩ ብሎም በተሰጣቸው ገደብ መሰረት ሊንቀሳቀሱ ይገባል፡፡ ይህ ባልሆነበት ሁኔታ ዴሞክራሲ፣የህግ የበላይነት ….ወዘተ እያሉ መደስኮሩ ጉንጭ ከማልፋት በተዘለለ ለዜጎች ጠብ የሚልላቸው ነገር አይኖርም፡፡ መንግስታት አንባገነን በሆኑበት አግባብ ገለልተኛ ተቋማትን መገንባት አስቸጋሪ ነው፡፡
በሀገራችንም እየሆነ ያለው ይህ ሀቅ ነው፡፡ ምንም እንኳ የሀገሪቱ የይስሙላ ህገ መንግስት በአንቀፅ 102 1-2 ስለምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ተቋምነት ቢደነግግም፤ እውነታው ግን ከዚህ ፍፁም ያፈነገጠና ምርጫ ቦርድ ገለልተኛ ለመሆን ቀርቶ የመንግስት ክንፍ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ….እሺ ይኸንንም ይሁን ብለን እንቀበል፤…ኢህአዲግ ያላከበረውን ህገ-መንግስትና የህግ ማእቀፍ ምርጫ ቦርድ ያከብራል ብለን አንጠብቅ፤…ነገር ግን ምርጫ ቦርድ ከአንድ ተቋም ነኝ ከሚል መዋቅር የማይጠበቅና እጅግ የወረደ ተግባር ሲሰራ እየተመለከትንበት ያለው ሁኔታ በጣም የሚያሳዝንና ተቋሙንም ሆነ የተቋሙ አመራሮችን ከታሪክ ተጠያቂነት የሚያድናቸው ሆኖ አናገኘውም፡፡
ምርጫ ቦርድ እንደተቋም ያስፈፅማቸውና ሊተገብራቸው ዘንድ የሚጠበቁ ተግባራት በህግ ተለይተው ተቀምጠውለት ሳለ በፓርቲዎች አሰራርና የውስጥ ጉዳይ እንደርጎ ዝንብ ጥልቅ እያለ፤በማያገባውና በህግም ሆነ በአሰራር በማይመለከተው ተግባር ውስጥ ህገ-ወጥ ተግባር መፈፀሙ ምናልባትም የሀገራችን ህግ ምን ያህል እንደወረደና የምርጫ ቦርድ ማንአለብኝነት ከኢህአዲግ የጀርባ እጅ ጋር መያያዙንና የህወሀት/ኢህአዲግና/የምርጫ ቦርድን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታነት ቁልጭ አርጎ የሚያመላክት ነው፡፡
በህግ የበላይነት በሚያምኑ መሪዎችና ህዝቦች መካከል ፤…‹‹ህግ›› ማለት ልጓም ነው፡፡ አንድ ፈረስ በተፈቀደለት አቅጣጫና ፍጥነት በተገቢው ሁኔታ ይሄድ ዘንድ ልጓም ይበጅለታል፡፡ ልጓሙ ህግ ነው፤ ፈረሱ ከልጓም ከወጣ በሰውም ላይ ሆነ በራሱ ላይ አደጋ ሊያስከትል ይችላል፡፡ …..ልጓሙን ይዞ ፈረሱ ላይ ተግባራዊ የሚያደርገው ደግሞ የጋሪው አሽከርካሪ ነው፡፡ ስለዚህ ባለጋሪው ከፍተኛ ሀላፊነት አለበት ማለት ነው፡፡…..በህዝብም ላይ ተመሳሳይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ህዝቦች በጋራ ተስማምተው ያወጡት ህገ-መንግስትና የየተቋማቱ ልዩ ልዩ ማስፈፀሚያ ህጎችና የህግ ማእቀፎች በሀገሪቱ ላይ ለሚደረገው ማንኛውም እንቅስቃሴና አሰራር ልክ እንደ ልጓሙ ሁሉ ገደብ አድርገውለታል፡፡ …..ከዚህ ልጓም የወጣ ደግሞ፤ …..ህገ-ወጥና የህግን የበላይነት የማያከብር ይባላል፡፡
በሀገራችን ያለው ሁኔታ በልጓም (በህግ) የበላይነት ማመን በወሬ ደረጃ ሆኖ የምናገኘው ኢህአዲግም ሆነ ሌሎች ተቋማት ህግንና አሰራርን በገሀድ ሲጥሱትና ተጠያቂ የሚሆኑበት አሰራር ሳይኖር ሲቀር ነው፡፡ …..ለነገሩ የሀገሪቱ መንግስት ነኝ ባይ ፓርቲ ህጉን እንዳሻው እየጣሰና እየረገጠ ባለበት ሁኔታ ሌሎች ተቋማትና ግለሰቦች ህጉን ቢጥሱ ምን ሊደንቀን ይገባል??? ……. ሰሞኑን እንደተከታተልነው ምርጫ ቦርድ ከተፈቀደለትና ከሚመለከተው ተግባር ውጭ በመውጣት በአንድነት ፓርቲ ላይ የጀመረው የውንብድናና የማንአለብኝነት ተግባር እጅግ አሳፋሪና የወረደ ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ …….ምርጫ ቦርድ ‹‹ፅድቁ ቀርቶብኝ፣……›› እንደሚባለው ምንም እንኳ እንደአንድ ገለልተኛ ተቋም ለፓርቲዎች የሚጠበቅበትን ሀላፊነት ከአድሏዊነት በፀዳ መልኩ ማገልገል ቢሳነውም በማያገባው ሁሉ ጥልቅ እያለ የሚፈፅመው የህግ ጥሰትና የአሰራር ዝቅጠት ድርጊቱ ሆን ተብሎና በኢህአዲግ ተልእኮ አስፈፃሚነት የሚሰራ ትወና ለመሆኑ ማስረጃ ነው፡.
ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ የከፈተው የተልእኮ ዘመቻ፤……. መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሊያውቀውና ሊገነዘበው የሚገባ ታሪካዊ ስህተት ነው፡፡ ምርጫ ቦርድ እስካሁን በህዝብና በፓርቲዎች ላይ እየፈፀመ ያለው ደባ እንዳለ ሆኖ ልጓሙን የበጠሰው ይህ ተቋም በቀጣይነት ለፓርቲዎች ህግ ላውጣ፤ የፋይናንስ ጉዳያችሁን ላስተዳድር፤የዲሲፕሊንና ሌሎች የፓርቲው እርምጃ በኔ በኩል ይፈፀም፤…ለኢህአዲግ መስገድ በኔ በኩል የሚፈፀም የፓርቲዎች ግዴታ ነው፤የየፓርቲዎችን ፕሬዝዳንት በኢህአዲግ መልማይነት በእኔ አፅዳቂነት ይፈፀም ……. ወዘተ የሚሉ ወራዳና የወረዱ ተግባራትን እንደሚፈፅም አልጠራጠርም፡፡ይህ ተቋም በህዝብ ላይ ለፈፀመው ደባና ንቀት ተጠያቂ የሚሆንበት ቀን እሩቅ አይሆንም፡፡
አንድነት ፓርቲና ሌሎች የምርጫ ቦርድ መረን ለቀቅ ድርጊት ሰለባ የሆኑ ፓርቲዎች ግን የህዝብን አደራ ተሸክመው፤በዚህ ተልካሻና የማይከበር ተቋም ሴራ ከትግሉ መራቅ እንዴሌለባቸው የሚታመን በመሆኑ፤…… በተባበረ ክንድ የምርጫ ቦርድንም ሆነ የኢህአዲግን ውጥን የሚያከሽፍ የትግል ስልት ነድፈው እንደሚንቀሳቀሱ አልጠራጠርም፡፡ ….ምናልባት ፓርቲዎች ባመጡት ጠንቅ ሳይሆን በኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ ሴራ ትግሉ ደም የሚያቃባና በመስዋትነት የታጀበ ሊሆን ይችላል፤ ነገር ግን ለዚህ ደም መፋሰስ ተጠያቂዎቹ ኢህአዲግና ምርጫ ቦርድ መሆናቸውን መላው ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ሊረዳው የሚገባ ሀቅ ነው፡
አመሰግናለሁ!!!
አንብበው ሲጨርሱ ሼር ማድረግዎትን አይርሱ!!!
ድል የህዝብ ነው!!!

The post የምርጫ ቦርድን ልጓም ማን ይግታው??? appeared first on Zehabesha Amharic.

ሥርዓቱ የምርጫ ካርድ ያልወሰዱትን ስኳር በመከልከል ማስፈራራት ጀምሯል

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን አነደድ ወረዳ የቦቀል ቀበሌ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ስልልወሰዳችሁ ስኳር አይሰጣችሁም መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ በአካባቢው ስኳርን ጨምሮ ሌሎች አቅርቦቶች በስፋት እንደሚጠፉ የተናገሩት ነዋሪዎቹ ዛሬ ጠዋት የቀበሌ ካድሬዎች በድምጽ ማጉያ ‹‹ዛሬ ስኳር ስለመጣ ቀበሌ ድረስ መጥታችሁ እንድትወስዱ፡፡ የመጣው ስኳር ውስን በመሆኑ ሊያልቅ ስለሚችል ዛሬውኑ መጥታችሁ እንድትወስዱ እናሳስባለን፡፡ ከዛሬ ውጭ ላታገኙ ትችላላችሁ፡፡›› እያሉ ሲለፉ እንዳረፈዱ ተናግረዋል፡፡
election
ሆኖም መጥቷል የተባለው ስኳር ለማግኘት ወደ ቀበሌው ያመሩት ነዋሪዎቹ ስኳሩን ለመውሰድ ሲጠይቁ ‹‹የምርጫ ካርድ ወስዳችኋል?›› የሚል ጥያቄ እንደሚቀርብላቸው ግልጸዋል፡፡ የምርጫ ካርድ የሚያሳዩ ነዋሪዎች ስኳሩ ሲሰጣቸው፤ ያላወጡት በአስቸኳይ ምርጫ ካርድ አውጥተው እንዲመለሱና ስኳር እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ተብሏል፡፡ በአንጻሩ ስኳር ለመውሰድ የምርጫ ካርድ ማውጣት የለብንም ያሉት ነዋሪዎች ስኳር እንደማያገኙ የተነገራቸው ሲሆን ‹‹እንደዜና የምርጫ ካርድ ወሰድንም አልወሰድንም ስኳር የማግኘት መብት አለን›› ያሉ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበው እንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
በጠዋቱ የቀበሌ ነዋሪዎች ያሰሙት የነበረውን ለፈፋ ሰምቶ ወደ ቀበሌ ያመራ ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ መምህር የምርጫ ካርድ ካላመጣ ስኳር እንደማይሰጠው ተነግሮት መመለሱን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ መምህሩ ‹‹የምርጫ ካድር የመውሰድና ያለመውሰድ መብት አለኝ፡፡ የማምንበት ፓርቲ ሲኖር የምርጫ ካርድ እወስዳለሁ፡፡ ካልሆነ ግን አልወስድም፡፡ ብወስድም ስኳር ለማግኘት ብዬ አይደለም፡፡ እንደማንኛውም ዜጋ ስኳር የማግኘት መብት አለኝ፡፡›› በሚል የቀበሌ ሰራተኞቹን ለማስረዳት ቢሞክርም ‹‹እኛ ስኳር ስጡ የተባልነው ካርድ ለወሰደ ብቻ ነው፡፡ ካርድ ካልወሰድክ አይሰጥህም›› ተብሎ እንደተመለሰ ገልጾልናል፡፡

The post ሥርዓቱ የምርጫ ካርድ ያልወሰዱትን ስኳር በመከልከል ማስፈራራት ጀምሯል appeared first on Zehabesha Amharic.

የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ

$
0
0

የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ
ብሄራዊ ምርጫ ቦርድና ኢህአዴግ በወሰኑብን ፖለቲካዊ ውሳኔ ምክንያት አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲን ተነጥቀናል ያሉ የአንድነት ፓርቲ አባላት› በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስታወቁ፡፡

negere ethiopia
በእነ በላይ ፍቃዱ አመራርነት አንድነት ፓርቲን በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ሲመሩ የነበሩ አመራሮች ዛሬ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቁት ከቀድሞ ፓርቲያቸው አንድነት ጋር የፕሮግራምም ሆነ የስትራቴጂ ተመሳሳይነት ወዳለው ሰማያዊ ፓርቲ ተቀላቅለው ሰላማዊ ትግላቸውን ለመቀጠል መወሰናቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡
መግለጫውን የ‹ቀድሞው አንድነት ፓርቲ› አፈ ጉባዔ የነበሩት አቶ አበበ አካሉ፣ ምክትል አፈ ጉባዔው አቶ ፀጋዬ አላምረው፣ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ነገሰ ተፋረደኝ እንዲሁም የወጣቶች ጉዳይ ኃላፊው አቶ ስንታየሁ ቸኮል ሌሎችን በመወከል ሰጥተዋል፡፡
‹‹የምናምነው በሰላማዊ ትግል ብቻ ነው፡፡ ይህን ሰላማዊ ትግል ለመምራት ደግሞ ሰማያዊ ፓርቲ ብቁ ነው ብለን በማመን ፓርቲውን ተቀላቅለናል›› ብለዋል በመግለጫው ላይ የተወከሉት አዲሶቹ የሰማያዊ አባላት፡፡
በዚህ መሰረትም በርከት ያሉ አመራሮችና አባላት በይፋ የሰማያዊ ፓርቲ የአባልነት ፎርም ሞልተዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአንድነት አባላት ሰማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን አስመልክቶ መግለጫ ለመስጠት ወደ ሰማያዊ ቢሮ ባቀኑበት ወቅት ፖሊስ ሰማያዊ ፓርቲ ቢሮ ድረስ በመግባት ‹‹በሰማያዊ ስም መግለጫ የሚሰጡ አካላት እንዳሉ ሰለሰማን ነው›› በሚል ለፓርቲው አመራሮች ጥያቄዎችን አቅርበዋል፡፡

ምንጭ :- ነገረ-ኢትዮጵያ

The post የአንድነት አባላት በይፋ ሰማያዊ ፓርቲን ተቀላቀሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አንድነትንና ሰማያዊን አዋህደዋቸዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

$
0
0

የአንድነት መዋቅር በጣም ብዙ ነው፡፡ በየ ክፍለሀገሩ (በጎንደር፣ በወሎ፣ በጎጃም፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በሌሎቹም) ለምዝገባ በተንቀሳቀስንበት ወቅት አብዛኛዎቹ በብዙ መንገድ ተባባረውናል፣ በግልጽም ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር እየሰሩ ነው፡፡ ብዙዎቹም እኛ በሌለን ቦታ ላይ የሰማያዊ ፓርቲን ፎርም ሞልተው ቀድመው ተመዝግበዋል፡፡ ይህን ስል ደግሞ ሰማያዊ በህግ ይህን የማድረግም መብት ስላለን ነው፡፡ የሰማያዊ ስራ አስፈጻሚ አንድ አባል ሙሉ አባል ለመሆን 6 ሳምንት መጠበቅ አለበት የሚለው አስፈላጊ ነው ብሎ ሲያምን ይህን በአንድ ቀን ውስጥ አባል የማድረግ ስልጣን አለው፡፡ በዚህ ደንባዊ አካሄድ የአንድነት አባላት በኢህአዴግና በምርጫ ቦርድ በፓርቲያቸው ላይ ባደረሰባቸው ችግር በአንድ ቀን አባል እንዲሆኑ ወስነናል፡፡
Yilkal Getnet
ስለዚህ ጉዳይ ከእነ በላይና ተክሌም ጋር ረዘም ላለ ጊዜ ውይይት አድርገንበታል፡፡ የአንድነት አባላት በግል መጡ የሚባለው ለህግ ሲባል እንጅ ብዙዎቹ የአንድነት አባላት እስከታችኛው መዋቅር ድረስ ከዛሬ ቀደም ብለው ከሰማያዊ ፓርቲ ጋር አብረው እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ነገር ለበጎ ነው ይባላል፡፡ እነዚህ ሁለት ፓርቲዎች እንዴት እርስ በእርሳቸው ይወዳደራሉ? ተመሳሳይና ተቀራራቢ ፕሮግራም እያላቸው ለምን አንድ አይሆኑም? እየተባለ ከህዝቡም ከጋዜጠኞችም ጥያቄ ሲመጣ ቆይቷል፡፡ በአንድ በኩል ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ ተቃዋሚዎችን አዳከምን ብለው በአንድነት ላይ ውሳኔ ሲያስተላልፉ ሁለቱን አንድነትና ሰማያዊን አዋህደዋቸዋል ማለት እችላለሁ፡፡ ከዚህም በኋላ ሰማያዊ እነሱን የሚያሳትፍ አመራር በመፍጠር በምክር ቤትም፣ በስራ አስፈጻሚም ሆነ በሌሎች ቦታዎች ችሎታቸውና ብቃታቸው መሰረት በማድረግ እንዲሰሩ የሰማያዊ አመራር ክፍት መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ፡፡ የአንድነት አባላት በብቃታቸው በየቦታው ተመድበው እንዲሰሩ አስፈላጊውን ሁሉና ቀናነት ያለው አመራር እንደምናደርግ ይህን ትግል ለተቀላቀላችሁ አባላት ቃል እገባለሁ፡፡
ምንጭ :- ነገረ-ኢትዮጵያ

The post ‹‹ኢህአዴግና ምርጫ ቦርድ አንድነትንና ሰማያዊን አዋህደዋቸዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት appeared first on Zehabesha Amharic.

ሴቶች በባሎቻቸው ላይ የሚሄዱባቸው 7 ምክንያቶች [Top 7 Reasons Why Women Cheat]

$
0
0

women cheating ‹‹ወንዶች አካላዊ ፍላጎታቸውን ለማስታገስ፤ ሴቶች ደግሞ ለተለያዩ ስሜታዊ ምክንያቶች ይወሰልታሉ›› ሲባል ሰምተው ይሆናል፡፡ ጥቂትም እውነትነት ሳይኖረው አይቀርም፡፡ በቅርቡ ሴቶች በፍቅረኞቻቸው ላይ የሚወሰልቱባቸውን ምክንያቶች ለማወቅ በሚል አንድ ጥናት ተደርጓል፡፡ ‹‹አሳሳሙ ይደብረኛል…›› ከሚለው እስከ ‹‹ለበቀል ነው›› የሚሉ ምላሾች ተገኝተዋል፡፡ ጥናቱ እንስቶችን ለመወስለት ያነሳሳሉ ያላቸውን ሰባት ምክንያቶች እንደሚከተለው አቅርቧል፡፡

1. ፍቅር ስሜት አልባ ሊሆን
‹‹…ከጆን ጋር ለሶስት ዓመታት አብረን ኖረናል፡፡ በጣም ጥሩ ሰው ነው፡፡ አብሬው መሆን ያስደስተኛል፡፡ ይሁን እና ፍቅራችን ስሜት አልባ ነው፡፡ አብዛኞቹ የምናውቃቸው ሰዎች የተጋቡ ወይንም ለመጋባት የተጫጩ ናቸው፡፡ ጆን ሳይፈልግ ቀርቶ ሳይሆን ጉዳዩን ሲያነሳው ወዲያው ወሬ ስለምቀይርበት ነው፡፡
ወደ አውስትራሊያ በስራ ምክንያት ሁሌም ከሚማርከኝ የስራ ባልደረባዬ ጋር ተጓዝኩ፡፡ በጣም አስደሳች ወቅትም አሳለፍን፡፡ ከጆን ጋር የተለያየሁት እንደተመለስኩ ነበር፡፡ የሰራሁት ተግባር ደረቴን አስነፍቶ የሚያኮራኝ ባይሆንም ከጆን ያጣሁትን ከዚህ ልጅ አግኝቼ ነበር፡፡ ለሶስት ዓመታት በፍቅር ከቆየን በኋላ አሁን ተጋብተን በደስታ በመኖር ላይ ነን›› ስትል ጊሴል የተባለች የ30 ዓመት ወጣት በቀድሞ ፍቅረኛዋ ላይ እንድትሄድ የገፋፋትን ምክንያት ገልፃለች፡፡

2. ፍቅር ካለቀ በኋላ ለመለየት መፈለግን ደፍሮ አለመናገር
‹‹ከቀድሞ ፍቅረኛዬ ከሾን ጋር ከመለያየታችን በፊት በጣም የሚወዳት ውሻው ሞታበት ልቡም በጣም ተሰብሮ ስለነበር ካንተ ጋ ያለኝ የፍቅር ግንኙነት አልቆለታል… መለያየት አለብን›› ብዬ ብነግረው ጭካኔ ይሆንብኛል ብዬ በማሰቤ ስሜቱ እስኪስተካከል ድረስ ለወር ወይንም ከዚያ ለበለጠ ጊዜ ልጠብቀው ወሰንኩ፡፡ ሞራሉ ጥሩ በሆነበት፣ ነገሮች የተስተካከሉ በመሰሉበት እና እኔም ለመንገር በተዘጋጀሁበት ወቅት ደግሞ ከስራው ተባረረ፡፡ በድጋሚ ኑሮው እስኪስተካከል መጠበቅ ጀመርኩ፡፡ በዚህ መሀል ‹‹ፍቅርስ ከዚህ ጋር… ብዬ የምመኘውን አይነት ሰው አገኘሁና አብሬው መሆን ጀመርኩ፡፡ በጊዜ ሂደት ለሾን የሚሰማኝን ነግሬ ተለየሁት፡፡ ከሱ ጋር እያለሁ ከሌላ ሰው ጋር ፍቅር መጀመሬ ግን አልነገርኩትም ነበር፡፡ ይህን ቢያውቅ ኖሮ የሱን ስሜት ለመጠበቅ ብዬ ያደረኩትን ነገር ሁሉ ከታላቅ ክህደት ይቆጥረው ነበር፡፡ ለሱ ያለኝ ስሜት ተንጠፍጥፎ ባለቀበት ወቅት መንገር እንደነበረብኝ ኋላ ላይ ተሰምቶኛል›› ስቴሲ 30 ዓመት ዕድሜ ያላት የሌክሲንግተን ኗሪ፡፡

sexual-problems3. ርቀት ለፍቅርና ለታማኝነት ጠንቅ ነው
‹‹ከምንኖርበት ስፍራ 320 ኪሎ ሜትር በሚርቅ ኮሌጅ ስኮላርሺፕ አግኝቼ ስሄድ ከፍቅረኛዬ ከክሬግ ጋር ፍቅርን በሩቁ ማስኬድ የምንችል መስሎኝ ነበር፡፡ የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ወራት ነገሮችን ባሰብኩበት መንገድ ማስኬድ ችዬ ነበር፡፡ ነገር ግን ቀናት እየገፉ በሄዱ ቁጥር ላብራቶሪ ውስጥ አብሮኝ ከሚማረው ሄንሪ ከተባለ ወጣት ጋር ፍቅር እንደያዘኝ ተረዳሁ፡፡
እንደቀልድ የተጀመረ ልፊያ ቀስበቀስ ወደ አንሶላ መጋፈፍ አደረሰን፡፡ ስልጠናው ከተጠናቀቀ በኋላ ወደ ግሬክ እቅፍ ተመልሼ ገባሁ፡፡ ነገር ግን ከሱ ጋር ጊዜ ማሳለፍ አዳጋቻ ሆነብኝ፤ ይሁንና እሱንም ስለምወደው ልለየው አልፈለግኩም፡፡
ሄነሪን በተደጋጋሚ ብጎበኘውም ለኔ የሚሆን አይነት ሰው እንዳልሆነ ሳውቅ ከሱ ጋር ያለንን ግንኙነት አቋረጥኩ፡፡ ስለውስልትናዬ ለግሬክ ምንም አለመናገሬ የጥፋተኝነት ስሜት እንዲያድርብኝ አድርጎኛል፡፡ ይህን ስህተቴንም ባለማወቅ በልጅነት አዕምሮ የተፈፀመ ብዬ ራሴን ለመሸንገል ሞክሬያለሁ፡፡ ኮርሱን ካጠናቀቅኩ ከአራት ዓመታት በኋላ አሁንም ከግሬክ ጋር ነኝ›› ታማራ በፖርትላንድ የምትኖር የ33 ዓመት ሴት ናት፡፡

4. ብቸኝነት እና የማንም አለመሆንን መፍራት
‹‹የሁለት ዓመት ፍቅረኛዬ ዴቭ አልፈልግሽም ብሎ ከተለየኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ከኤሪክ ጋር መውጣት ጀመርኩ፡፡ በወቅቱ ስሜቴ በጣም ተጎድቶ ስለነበር ኤሪክ ዋነኛው አጽናኜ ነበር፡፡ ከኤሪክ ጋር ለአምስት ወራት እንደቆየሁ ዴቭ ተመልሶ በመምጣት አብሮኝ መሆን እንደሚፈልግ ነገረኝ፡፡ በጣም ናፍቆኝ ስለነበር አብሬው መሆን ጀመርኩ፡፡ ይህን የማደርገው ከኤሪክ ሳልለያይ ነበር፡፡ ይህን ወድጄ ያደረኩት አይደለም፡፡ ምናልባት ዴቭ መልሶ ቢከዳኝ ከኤሪክ ጋር ለመቀጠል እንዲመቸኝ የቀድሞ ጉዳቴ ያስተማረኝ ጥንቃቄ ሳይሆን አይቀርም፡፡ ነገር ግን አልተሳካልኝም፡፡ ዴቭ አሁንም ከዳኝ ኤሪክ ደግሞ የኔንና የዴቭን ነገር ከጓደኛቹ ሰማ፡፡ ሌላኛውን ትምህርት በሚያም መልኩ ተማርኩ- ከሁለት ወንዶች ጋር ግንኙነት መጀመር ትርፉ ከሁለቱም ሳይሆኑ መቅረት እንደሆነ›› ጄን የ28 ዓመት ወጣት ስትሆን በኦክፓርክ ከተማ ኗሪ ነች፡፡

5. ከመጥፎ ግንኙነት ለመውጣት መሻት
‹‹ኢታን ከሚባልና ሁሌም ከሚተቸኝ ልጅ ጋር ግንኙነት ጀምሬ ነበር፡፡ በየጊዜው ስለክብደቴ፣ ስለ አለባበሴ እና ደባሪ ስለመሆኔ እያነሳ ይተቸኝና ያሸማቅቀኝ ነበር፡፡ ምንም እንኳን ጓደኞቼ እና ቤተሰቦቼ በጣም ቢጠሉትም፣ እኔን እያበሻቀጠ የፈለገውን ቢለኝም እኔ ግን ከሱ መለየትን አልፈለኩም፡፡ በአንድ የሳምንቱ መጨረሻ ዕለት ፓርቲ ላይ ዊልን ተዋወቅሁት፡፡ ከኢታን ፍፁም የተለየ ደግ፣ ጣፋጭ እና ለጋስ እንዲሁም ፍፁም የተረጋጋና አብረውት ቢውሉ የማይሰለች አይነት ልጅ ነው፡፡ የሳምንቱን የመጨረሻ ቀናት በሙሉ አብረን ካሳለፍን በኋላ ከበሰሉ ወጣቶች ጋ ፍቅር እንዲህ አስደሳች ነው ስል አሰብኩ፡፡ እሁድ ምሽት ለመጀመሪያ ጊዜ ዊልን ሳምኩት፡፡ ብዙም ሳልቆይ ከኢታን ጋር ያለኝን ግንኙነት አቋረጥኩ፡፡ ከዊል ጋር ለሶስት ዓመታት በፍቅረኝነት ከቆየን በኋላ በጋብቻ ተጠቃለልን፡፡›› አሊሰን የኒውዮርክ ኗሪ ስትሆን የ30 ዓመት ወጣት ነች፡፡

6. ከማንነት ጋር የሚስማማንን ሰው ፍለጋ
‹‹የፍሎሪዳ ተወላጅ በመሆኔ በባህር ዳርቻዎችና በጀልባዎች ላይ መንሸራሸር እወዳለሁ፡፡ የመሀል ሀገር ልጅ የሆነው የቀድሞ ፍቅረኛዬ ክሪስ ደግሞ ይንንን ይጠላ ነበር፡፡ በየጊዜው የት ሄደን መዝናናት እንዳለብን እያነሳን እንጨቃጨቅ ነበር፡፡ ሁልጊዜም እሱ አሸናፊ ነበር፡፡ ለስምንት ወራት ያህል አብረን ከቆየን በኋላ አንድ ዕለት ከጓደኞቼ ጋር ጀልባ ተከራይተን ኪይዌስት ወደተባለ ስፍራ ሄድን፡፡
የጀልባዋ ካፒቴን የባህር ዳርቻዎችን የሚወድ፣ ሳቢና መልከመልካም ወጣት ነበር፡፡ ቀኑን ሙሉ ከሱ ጋር ስጫወት አሳለፍኩ፡፡ ያን ዕለት ምሽትም ለብቻችን ጥሩ ጊዜ አሳለፍን፡፡ ወደ ቤቴ ስመለስ ለክሪስ ስለሆነው ምንም አልነገርኩትም፤ እኔም የጥፋተኝነት ስሜት አልተሰማኝም፡፡ ግማሹ እኔነቴ ክሪስ በጣም ግትር በመሆኑ በሱ ላይ መሄዴ ይገባዋል የሚል ስሜት ነበረው፡፡ ከክሪስ ጋር አብረን መዝለቅ አልቻልንም፡፡ ከተለያየን በኋላ የምይዛቸው ወንድ ጓደኞች የባህር ዳርቻን የማያፈቅሩ ከሆነ እርቃቸዋለሁ›› ሊዝ ቺካጎ የምትኖር የ32 ዓመት ሴት ነች፡፡

7. መቃጠልና መንገብገብ ምን እንደሚመስል ይየው
የቀድሞ ፍቅረኛዬ የለየለት ሴሰኛ ነበር፡፡ እቀይረዋለሁ ብዬ አስቤ የነበረ ቢሆንም ልክ አልነበርኩም፡፡ አብረን እያለን ሌሎች ሴቶችን እንደሚያወጣ ወሬ ብሰማም ስጠይቀው ሁሌ ሽምጥጥ አድርጎ ይክዳል፡፡ አንድ ምሽት አንዲት ልጅ ደወለችልኝና ከፍቅረኛዬ ጋር ሶስት ወር የሞላው ግንኙነት እንዳላቸው፤ ከሌላ ሴት ጋርም ግንኙነት እንዳለው ማወቋን ስትነግረኝ በንዴት ጦፍኩ፡፡ እጅግ በመናደዴም ሽቅርቅር ብዬ ለብሼ ጓደኞቼ ዘንድ ሄድኩ፡፡ ምሽቱንም ከአንድ መልከመልካም ወጣት ጋር አሳለፍኩ፡፡ ለፍቅረኛዬ ያንምሽት ያደረኩትን ነገር እንዲሁም ስለሌሎቹም ሴቶች ማወቄን ስገልጽለት ፊቱ ላይ ያየሁት ነገር ትልቅ እርካታ ሰጠኝ፡፡ ወራዳና የማይረባ መሆኑን ነግሬም አባረርኩት፡፡›› አሻንቴ በኮሌጅ ፓርክ የምትኖር የ25 ዓመት ወጣት ነች፡፡
ከላይ በእውነተኛ ታሪክ ተደግፈው የቀረቡትና ሴቶችን ለውስልትና የሚገፋፉ ድርጊቶች አብዛኞቹ በወንዶቹ ስህተት እና የእውቀት ማነስ የተነሳ የተከሰቱ ናቸው፡፡ ሴቶችን በማንነታቸው ማክበርና ማፍቅር እንዲሁም ማንነታቸውን መቀበል ለዘላቂ ፍቅር ዋነኛው መሰረት ነው፡፡

The post ሴቶች በባሎቻቸው ላይ የሚሄዱባቸው 7 ምክንያቶች [Top 7 Reasons Why Women Cheat] appeared first on Zehabesha Amharic.

[የፓስተሩ ጉዳይ] –“በአስገድዶ መድፈር አንድን ሰው ለመክሰስ ቀላል ነው; ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማሰኘት ከባድ ነው” –የህግ ባለሙያ

$
0
0

pastor
የፓስተር ተከስተ; የወ/ሮ ሆሳዕና አደዳና የባለቤታቸው የአቶ መላኩ የሺዳኛ ጉዳይ አነጋጋሪነቱ ቀጥሏል:: ሁሉም የራሱ አስተያየት በተለያየ መንገድ እየገለጸ ሲሆን የስነልቦና ባለሙያዎች የየራሳቸውን ግምት እየሰጡ ነው:: የራስን ጉድፍ ሳያዩ የሰውን መመልከት አግባብ ባይሆንም ጉዳዩ ለመማሪያነት ከመቅረቡ አኳያ ባለሙያዎች የሚሰጡትን አስተያየት ማቅረቡም በራሱ አስተማሪ ነው::

ወ/ሮ ሆሳህና በፓስተር ተከስተ ላይ ከአስገድዶ የወሲብ ጥቃት ጋር የተያያዘ አቤቱታ በአሜሪካ ድምጽ ላይ አሰምታ አይተናል:: በቃለ ምልልሷ ላይ ከተናገረቻቸው ተነስቶ ብዙ ጥያቄዎችን ማንሳትን ቢቻልም ለመሆኑ በአሜሪካ ህግ አስገድዶ መድፈር (ሬፕ) እንዴት ይታያል? በዚህ ጉዳይስ ከሳሽ እና ተከሳሽ ፓስተር እንዴት ሊዳኙ ይችላሉ የሚለውን እንድታዩ አንድ ግንዛቤ የሚሰጥ ዘገባ እናስተናግዳለን::

ነዋሪነታቸውን በዋሽንግተን ዲሲ ያደርጉት ዶ/ር ፍጹም አቻምየለህ በፓስተር ተከስተ እና በወይዘሮ ሆሳህና አደዳ ላይ አስተያየት አይስጡ እንጂ በዘ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ በአሜሪካ የአስገድዶ መድፈር ህግ ዙሪያ እንዲህ ይላሉ; እኛም ለብዙሃን ምላሽ ይሆናል ስንል አስተናግደናል::

አስገድዶ መድፈር
-R a p e

አስገድድሞ መድፈርን 50ዎቹ ክፍለ ሀገሮችም ሆኑ የፈደራሉ መንግስት እንደከባድ ወንጀል ነው የሚቆጥሩት። እንዲህ ዓይነቱ ወንጀል በቨርጂኒያ ከ5 ዓመት እስከ እድሜ ልክ፣ ለዲሲ ደግሞ 50ሺ ብር ቅጣትና አምስት ዓመት፣ በአካል ላይ ጉዳት ከደረሰ ደግሞ እስከ እድሜ ልክ ሊያሳስር ይችላል። ወንጀሉ ከ14 ዓመት በታች በሆነ ሕጻን ላይ ከተፈጸመ ግን፣ ከ20 እስከ 30 ዓመት እስር ሊያስከትል ይችላል።
አስገድዶ መድፈር ማለት፣ ያለ ውዴታ በማስገደድ፣ በማስፈራራት፣ ኃይል በመጠቀም ወይንም በመጠጥ፣ በመድኃኒት፣ በአልኮል፣ ብሎ ም በአደንዛዥ እጽ ምክንያት የመስማማት አቅም ከሎለው ወይም ከደከመ ሰው ጋር ግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም ማለት ነው።
እድሜያቸው ለአቅመ አዳም ካልደረሱ ህጻናት ጋር ( እንደየክፍለ አገሩ 13 ወይም 14 ዓመት ካልሞላቸው ህጻናት ጋር) የግብረ ሥጋ ግንኙነት መፈጸም በራሱ እንደ አስገድዶ መድፈር ይቆጠራል (Statutory Rape) ። ይህ የሆነበት ምክንያት ህጻናቱ የመስማማት ችሎታ የላቸውም ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። ብዙዎቹ ክፍለ አገሮች ባልተጋቡ ሰዎች መካከል ብቻ ሳይሆን በተጋቡ ሰዎች መካከልም አስገድዶ መድፍረን ይከለክላሉ። ይቀጣሉ።
የአስገድዶ መድፈር ህጎች ታሪክ እንደሚያሳየው ህጎቹ ሲወጡ ሴቶችን ከጥቃት ለመከላከል ነበር የወጡት። የዛሬ ህጎች ግን ሁለቱም ጾታዎች ላይ ልዩነት አያሳዩም። ከዚያም አልፎ አዳዲስ ህጎች በጋብቻ ውስጥ የሚፈጸመውን አስገድዶ መድፈርንም አጥብቀው ይከለክላሉ። ቀደም ያሉት ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ የአስገድዶ መድፈር 83 ፐርሰንቱ የሚፈጸመው በሚተዋወቁ ሰዎች መካከል ነው። የድርጊቱ 36 ከመቶ ደግሞ የሚፈጸመው በተደፋሪው ቤት ነው። ድርጊቱም የሚፈጸምበት ሰዓት በብዛት ከ6 ፔም እስከ 6 ኤ ኤም ባለው ሰዓት ውስጥ ነው። ጥናቶቹ እንደሚያሳዩት መጠጥ፣ አደንዛዥ እጽ መውሰድ ለእንዲህ ዓይነት ድርጊት ፈጻሚም ሆነ ሰለባ ለመሆን ትልቅ ሚና ይጫወታል።
“ በአስገድዶ መድፈር አንድን ሰው ለመክሰስ ቀላል ነው። ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማሰኘት ከባድ ነው; ተከሳሽን ለመከላከልና ነጻ ለማውጣት ደግሞ በጣም ከባድ ነው” ማቲው ሴል እንዳለው “ በአስገድዶ መድፈር አንድን ሰው ለመክሰስ ቀላል ነው። ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማሰኘት ከባድ ነው። ተከሳሽን ለመከላከልና ነጻ ለማውጣት ደግሞ በጣም ከባድ ነው።” ይህ ማለት በአጠቃላይ አስገድዶ መድፈር ለከሳሽም ለተከሳሽም፣ ለፍርድ ቤትም አስቸጋሪና ውስብስብ ከሚባሉት ወንጀሎች አንዱ ነው። ፖሊስና አቃቢ ሕግ ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማሰኘት ዋነኛ መረጃቸው የህክምና የምርመራ ውጤቶች፣ የምስክርነት ቃሎች፣ ፎቶ ግራፎች፣ ቪዲዮዎች፣የስልክ ልውውጦች፣ የፈጻሚ እና የተፈጸመበት ግለሰብ የግንኙነት ታሪክ፣ የትውውቅ ጊዜ እና ለአቅመ አዳም ካልደረሱ ጋር ደግሞ ከተፈጸመ የህጻኑ ወይም የህጻኒቷ የልደት ሰርትፍኬት ሊሆኑ ይችላሉ። ተከሳሽ በበኩሉ ወይም በበኩሏ ደግሞ ስምምነት መኖሩንና ምንም ዓይነት ኃይል አለመጠቀሙን
ወይም አለመጠቀሟን ብሎም ተጠቂዋ ወይም ተጠቂው የመስማማት ሙሉ ችሎታ እንደነበራት ወይም እንደነበረው ማሳየት ይኖርበታል ወይም ይኖርባታል። ተጠቂው ለአቅመ አዳም ያልደረሰ ሰው ወይም ህጻን ከሆነ ግን የህጻኑን እድሜ አለማወቅ በራሱ መከላከያ ሊሆን አይችልም።
ከላይ ለማሳየት እንደተሞከረው አስገድዶ መድፈር ከባድ ወንጀል ነው። ለብዙ ዓመት ከማሳሰሩም በላይ እስከ ሕይወት መጨረሻ ድረስ የሚኖሩበትን አድራሻ ማስመዝገብ እንደ ግዴታ ይሆናል (requires a sex offender registration) ። አሜሪካዊ ዜጋ ካልሆኑ ደግሞ ከዚህ አገር መባረርን ያስከትላል።

ስለዚህ በሥራ አጋጣሚ፣ ወይንም በምንዝናናበት ጊዜ የሚያጋጥሙንን እድሎች እንጠቀም በሚል ሰበብ የመስማማት ችሎታ የሌላቸው ወይም በመጠጥም ሆነ በአደንዛዥ እጽ ምክንያት የመስማማት ችሎታቸው የደከመባቸው ሰዎች ጋር የሚፈጸም የግብረ ሥጋ ግኙነት እንደ መድፈር ስለሚቆጠር፣ ብዙ ዓመት እስር ብሎም ሎሎች ሕይወትን የሚያውኩ ነገሮች ስለሚያስከትል ከእንደዚያ ዓይነት ድርጊት መቆጠብ ያስፈልጋል።

The post [የፓስተሩ ጉዳይ] – “በአስገድዶ መድፈር አንድን ሰው ለመክሰስ ቀላል ነው; ተከሳሽን ጥፋተኛ ለማሰኘት ከባድ ነው” – የህግ ባለሙያ appeared first on Zehabesha Amharic.

እስር ቤት እያሉ የስኳር ሕመም መድሃኒታቸው እንዳይገባላቸው ተከልክለው የነበሩት የመአህድ አመራር መቶ አለቃ ተሰማ ሕይወታቸው አለፈ

$
0
0

meto aleka
መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እስር ቤት ውስጥ በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

የህዳር 27/28 የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የጠራው የአዳር ሰልፍ ወቅት ተይዘው በደረሰባቸው ከፍተኛ ድብደባ እና ለሶስት ቀን የስኳር በሽታ መድሃኒት እንዳይገባላቸው በመከልከላቸው ለህመም የተዳረጉት የመላው አማራ ሕዝብ ድርጅት (መአሕድ) ምክትል ፀኃፊ መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ ከእስር ከተፈቱበት ጊዜ ጀምሮ ለሁለት ወር ሆስፒታል ከቆዩ በኋላ በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ በአዳሩ ሰላማዊ ሰልፍ ወቅት ተይዘው ከፍተኛ ድብደባ የደረሰባቸው ሲሆን ለአምስት ቀናት ቀዝቃዛና ጨለማ ቤት ውስጥ ታስረው ቆይተዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ከታሰሩበት ጊዜ ጀምሮ ይዘውት የነበረውን የስኳር በሽታ መድሃኒታቸውን በመቀማታቸው፣ እንዳይገባላቸው በመከልከላቸውና በወቅቱም ህክምናም ባለማግኘታቸው ለከፍተኛ ህመም በመዳረጋቸው ለሁለት ወር ያህል ዘውዲቱ ሆስፒታል ቆይተዋል፡፡

መቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ እስር ቤት እያሉ በደረሰባቸው ችግር ምክንያት ዘውዲቱ ሆስፒታል ከገቡበት ታህሳስ 4/2007 ዓ.ም ጀምሮ ከፍተኛ ህመም እየተሰቃዩ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡ የመቶ አለቃ ተሰማ ወንድሙ የቀብር ስነስርዓት ዛሬ ጥር 27/2007 ዓ.ም በቦሌ ሚካኤል እንደሚፈጸም ለማወቅ ተችሏል፡፡

The post እስር ቤት እያሉ የስኳር ሕመም መድሃኒታቸው እንዳይገባላቸው ተከልክለው የነበሩት የመአህድ አመራር መቶ አለቃ ተሰማ ሕይወታቸው አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሦስቱ መሥሪያ ቤቶች በደመወዝ ጭማሪው ላይ ያደረጉት እንቅስቃሴ በተግባር ሲመዘን

$
0
0

በ  ብርሃኑ ፈቃደ

ባለፈው በጀት ዓመት ትልልቅ መነጋገሪያ ሆነው ካለፉ ክስተቶች መካከል የደመወዝ ጭማሪ ዋናው ነበር፡፡ ለመንግሥት ሠራተኛው ማኅበረሰብ ይደረጋል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው የደመወዝ ጭማሪ ብዙ አነጋገሮ፣ የዋጋ ንረትንም አስከትሎ ማለፉን መንግሥት ያምናል፡፡

ማመን ብቻም ሳይሆን ‹‹ኢኮኖሚያዊ መሠረት የላቸውም›› ባላቸው የዋጋ ጭማሪዎች ላይ ዕርምጃ እወስዳለሁ በማለት በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ ሲያሰማ ከርሟል፡፡

ea90fe2b72ed2402a39aace6e0307144_Lበአዲስ አበባና በክልሎች የችርቻሮ ሱቆች ላይ የተወሰዱት ዕርምጃዎች ይታወሳሉ፡፡ በዋጋ ጭማሪው ላይ የተሳተፉት ግን ትልልቅ አስመጪዎችና ትልልቅ ፋብሪካዎች እንደነበሩ መንግሥት ከሰጠው መግለጫ ለመታዘብ ተችሏል፡፡ እርግጥ አምራቾቹን በማወያየት ዋጋ እንዲያስተካክሉ ማድረጉን፣ እንዲያተካክሉ ማግባባቱንና አሻፈረኝ ሲሉ ያንገራግሩ በነበሩት ላይም ማስጠንቀቂያ በማውጣት እንዲታቀቡ ለማድረግ መቻሉን የገለጸው መስከረም በባተ ሰሞን ነበር፡፡

የንግድና የሸማቾች ጉዳይ ከሚመለከታቸው የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች መካከል በመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ጭማሪ አሳበው ዋጋ አንረዋል ያላቸውን አካላት በማነጋገር፣ ሲያስፈልግም በማስጠንቀቅና ዕርምጃ በመውሰድ ሥራ ተጠምዶ እንደነበር ቀድሞ የገለጸው የንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ነበር፡፡

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መርከቡ ዘለቀ በዓመቱ መጀመሪያ በጠሩት ጋዜጣዊ መግለጫ ወቅት፣ ካነሷቸው ነጥቦች መካከል በተለይ በሐምሌ ወር 2006 ዓ.ም. የተደረገውን የደመወዝ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ የተደረጉ የዋጋ ጭማሪዎችን የዳሰሰ ነበር፡፡ የዋጋ ጭማሪውን ለማርገብ ዕርምጃዎች መወሰዳቸውን አስታውሰዋል፡፡

የደመወዝ ጭማሪውን መነሻ አድርገው ምንም ዓይነት ‹‹የኢኮኖሚ ምክንያት ሳይኖር›› የዋጋ ጭማሪ በማድረግ በተለይ በምግብና ምግብ ነክ በሆኑ ሸቀጦች ላይ የታየው የዋጋ ለውጥ ችግር ፈጥሮ እንደነበር አቶ መርከቡ ያስታውሳሉ፡፡ በተለይ አገር ውስጥ በሚመረቱና በሚፈበረኩ ፈሳሽ የምግብ ዘይቶች፣ የታሸጉ ውኃዎች፣ ዱቄት፣ ፓስታ፣ ማካሮኒ፣ ሩዝ ላይ የታየው የዋጋ ጭማሪ የተጋነነ እንደነበር ገልጸው ነበር፡፡ የግል ትምህርት ቤቶችና የግል ጤና ተቋማት ላይ የታየው የዋጋ ለውጥ ጎልቶ መታየቱንም መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን ጡዘት ያረግባል ተብሎ አብይ ኮሚቴ ተቋቁሞ የነበረ ሲሆን፣ ይኸው ኮሚቴ ምርመራ በማካሄድ የዋጋ ንረቱን ለማርገብ ሲንቀሳቀስ ነበር፡፡ ዋጋ ጨምረዋል ከተባሉ የንግዱ ማኅበረሰብ አባላት ጋር ውይይት ተደርጎም የጨመሩትን ዋጋ እንዲያስተካክሉ መደረጉን ገልጸው ነበር፡፡ አቶ መርከቡ የዋጋ ንረቱ በፍላጎትና በአቅርቦት ላይ ወይም በእሳቸው አገላለጽ ምንም ዓይነት ኢኮኖሚዊ ክስተቶች ሳይኖሩ የተደረገ ከመሆኑ በላይ፣ የደመወዝ ጭማሪ የተደረገው ከአገሪቱ ሕዝቦች አንድ ከመቶውን ብቻ ለሚወክለው የመንግሥት ሠራተኛ በመሆኑ፣ ይህ ክፍል አገልግሎት ሰጪ እንጂ አምራች ባለመሆኑ የጎላ የፍላጎት ጭማሪ እንደማይከሰት እየታወቀ ዋጋ መጨመሩ አግባብ አለመሆኑን ባለሥልጣኑ ሲያስታውቅ መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

የዋጋ ጭማሪውን ሊያነሳሱ የሚችሉ የተፈጥሮ አደጋዎች ሳይከሰቱ፣ የዓለም የገበያ ሁኔታ በነተረጋጋበት መልኩ የተደረገው የምግብና ምግብ ነክ ሸቀጦች ላይ የታየው ጭማሪ አግባብ ባለመሆኑ፣ ዋጋው ወደነበረበት መጠን እንዲመለስና እንዲስተካከል ለማድረግ መሞከሩን ዋና ዳይሬክተሩ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በመሆኑም የአገር ውስጥ የምግብ ሸቀጥ አምራቾች ዋጋ እንዲያተካክሉ በተነገራቸው መሠረት አስተኮ ምግብ ኮምፕሌክስ፣ ያምሮት ምግብ ኮምፕሌክስ፣ ጀማነሽ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ድሬዳዋ ፉድ ኮምፕሌክስ የመሳሰሉትን ጨምሮ ትልልቅ የምግብ ሸቀጥ አምራች ፋብሪካዎች ዋጋ እንደሚያተካክሉና ከወደመዝ ጭማሪ በፊት የነበራቸውን የመሸጫ ዋጋና ያስተካከሉትን ዋጋ ጭምር ለመንግሥት ማሳወቃቸውን፣ በችርቻሮ ከመሸጥ ጀምሮ በኅብረት ሆነው ለሚመጡ ሸማቾች ከጅምላ መሸጫ ዋጋ ቀንሰው ለማቅረብ ፍላጎት እንዳላቸው በዋና ዳይሬክተሩ መግለጫ ተመልክቷል፡፡ ቢራ ፋብሪካዎች፣ የታሸገ ውኃ አምራቾች ወዘተ ዋጋ እንዲያተካክሉ ጥሪ ተደርጎላቸው አስተካክለዋል፤ ያንገራገሩም ነበሩ ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ 1671 የግል ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ሲሆን አብዛኞቹ የዋጋ ጭማሪ አሳይተዋል፣ ያሳዩት የዋጋ ጭማሪም ከፍተኛ እንደነበርና በርካቶችም ዋጋ ለመቀነስ አንገራግረው እንደነበር አቶ መርከቡ አስታውሰዋል፡፡ ጥናት ተደርጎም በየዓመቱና በየመንፈቁ ዋጋ የሚጨምሩ ትምህርት ቤቶች እንዳሉ መታወቁንም ተናግረዋል፡፡ በርካታ ትምህርት ቤቶች የዋጋ ለውጥ ለማድረግ ፈቃደኛ ሳይሆኑ ተገኝተዋል፡፡ በሕግ ይጠየቃሉ ተብሎ እንደነበርም ይታወሳል፡፡ በተለይ 24 ትምህርት ቤቶች ትልቅ ችግር አለባቸው ተብሎ ተለይተው እንደነበርም አይዘነጋም፡፡

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ዕርምጃዎች

ምንም እንኳ የንግድ ውድድርና የሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን፣ በዚህ መልኩ መንቀሳቀሱን ቢገልጽም፣ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮም ሆነ የንግድ ሚኒስቴር ያደረጉትን እንቅስቃሴ በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተው ነበር፡፡ በጥቅምት ወር የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በምክትል ኃላፊው አቶ ገመቺስ መላኩ አማካይነት በሰጠው መግለጫ፣ የሦስት ወራት ሪፖርቱ ውስጥ ካካተታቸው ነጥቦች መካከል የግብይትና ገበያ የማረጋጋት ሥራዎች ይጠቀሳሉ፡፡

ንግድ ቢሮው በገበያ ማረጋጋት መስክ አከናወንኳቸው ካላቸው ተግባራት መካከል የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪን ሰበብ በማድረግ የተደረጉ የዋጋ ጭማሪዎችን አትቷል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ምክንያት ያላቸውንና የሌላቸውን የዋጋ ጭማሪዎች በመለየት፣ የዋና ዋና የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች የጅምላና ችርቻሮ ዋጋን በመከታተል መረጃ መስጠቱን ያስታወቀው ንግድ ቢሮው፣ ሕገወጦችን በማስጠንቀቅና እምቢ ያሉትን በመቅጣት (በብዛት በማሸግ) ዕርምጃ መውሰዱን ይፋ አድርጎ ነበር፡፡ ከዚህ ባሻገር በፌደራልና በከተማው አስተዳደር መሥሪያ ቤቶች ለሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች በየመሥሪያ ቤቶቻቸው ሸቀጦችን እንዲገኙ በማድረግ የዋጋ ንረቱን ለመግታት እንደሞከረ አቶ ገመቺስ መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

ይህም ብቻ አይደለም፡፡ እስከ መስከረም መጨረሻ በነበረው የሩብ ዓመት ውስጥ ጥሬ ስንዴ 334,600 ኩንታል፣ የስንዴ ዱቄት 244 ሺሕ ኩንታል፣ ስኳር 259,196 ኩንታል ለከተማው ነዋሪ፣ በተለያዩ ተቋማት በኩል ማከፋፈሉን አቶ ገመቺስ አስታውቀዋል፡፡ ይህ ግን በታሰበው ወይም በታቀደው ልክ የሆነ እንዳልነበር ልብ ይሏል፡፡ ለአብነት ለአዲስ አበባ ይከፋፈላል ተብሎ የታሰበው የጥሬ ስንዴ ዱቄት መጠን ግማሽ ሚሊዮን ኩንታል ነበር፡፡ የስንዴ ዱቄት መጠኑ ደግሞ 462 ሺሕ ኩንታል ሲሆን የስኳር መጠን 306 ሺሕ ኩንታል ይሆናል ተብሎ ይጠበቅ ነበር፡፡ የአቅርቦቱ መጠን ከዕቅዱ ጋር ሳይጣጣም ቀረ፡፡ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በፓልም ዘይት ረገድ ካሰበው በላይ አቅርቦት በገበያው ውስጥ መኖሩን ይፋ ማድረጉም አይዘነጋም፡፡ 10.5 ሚሊዮን ሊትር ፓልም ዘይት ለማቅረብ አቅዶ 13.3 ሚሊዮን ሊትር ገደማ በማቅረብ ተሳክቶልኛል ብሏል፡፡

ንግድ ሚኒስቴር ምን አለ?

ንግድ ሚኒስቴርም ተመሳሳይ ይዘት ያለውን፣ የግማሽ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ለተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው ባለፈው ሳምንት ነበር፡፡ ሚኒስትር ከበደ ጫኔ የመንግሥት ሠራተኞችን የደመወዝ ጭማሪ ምክንያት በማድረግ ተፈጥሯል ስለተባለው የዋጋ ንረት፣ ከላይ ከተጠቀሱት ሁለት መሥሪያ ቤቶች ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያለው ሪፖርት አሰምተዋል፡፡ ‹‹የመንግሥት ሠራተኞችን ደመወዝ መጨመርን ሰበብ በማድረግ ያለበቂ ምክንያት በሸቀጦች ላይ ዋጋ በጨመሩ አምራች ድርጅቶች፣ አስመጪዎችና ቸርቻሪ ነጋዴዎችን በተደጋጋሚ በማወያየት የማስተካከያ ዕርምጃ በመውሰድ ለመቆጣጠር ጥረቶች ተደርገዋል፤›› ብለዋል፡፡

ከዚህ ባሻገር የመንግሥት ዋጋ ተመን የሚመለከታቸው መሠረታዊ የሚባሉትን ፍጆታ ሸቀጦች በሚመለከት ሪፖርታቸው እንዳመለከተው፣ 2.5 ሚሊዮን ኩንታል የስንዴ ዱቄት በተመረጡ ፋብሪካዎች ተፈጭቶ፣ ለዳቦ ጋጋሪዎች እንዲሰራጭ ታቅዶ ነበር፡፡ ከዚህ ውስጥ 2.2 ሚሊዮን ኩንታል መሰራጨቱን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል፡፡ ከሦስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ ስኳር ለማሰራጨት ታስቦ እንደነበር ሆኖም የ1.8 ሚሊዮን ኩንታል ብቻ መሳካቱን ተናግረዋል፡፡ እንደ አዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሁሉ በንግድ ሚኒስቴርም ስኬታማ የተባለው የዘይት ስርጭት ነው፡፡ 135.7 ሚሊዮን ሊትር ይሰራጫል ተብሎ የተሠራጨው ግን 145 ሚሊዮን ሊትር መሰራጨቱን (ለጅንአድ ግን 160.5 ሚሊዮን ሊትር ቀርቦለታል) በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡

ይህ ሁሉ ቢባልም ግን በአገሪቱ የሚታየው የዋጋ ንረት እንደቀጠለ ነው፡፡ የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የታኅሣሥ ወር 2007 ዓ.ም. የአገር አቀፍና የክልሎች የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክሶች (የሸማቾች ዋጋ መመዘኛ ኢንዴክስ ማለት ሸማቾች ለተወሰኑ ዕቃዎችና አገልግሎቶች የከፈሉትን አማካይ የዋጋ ለውጥ ለመለካት የሚያገለግል ተቋሚ አኃዝ ነው ሲል ኤጀንሲው መፍቻ አስቀምጧል) የሚጠቁሙት የዋጋ ግሽበት መመዝገቡን ነው፡፡

በታኅሣሥ ወር 2007 ዓ.ም. የተመዘገበው የ12 ወራት ተንከባላይ አማካይ አገራዊ አጠቃላይ የዋጋ ግሽበት ካለፈው ተመሳሳይ ወቅት አኳያ በ7.4 ከመቶ ጭማሪ አሳይቷል ያለው የማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ ሪፖርት፣ በታኅሣሥ ወር የታየው የምግብ ዋጋ የ12 ወራት ተንከባላይ ግሽበትም 5.4 ከመቶ መድረሱን ይጠቁማል፡፡ ምግብ ነክ ያልሆኑ ሸቀጦች የዋጋ ግሽበትም በ9.6 ከመቶ ጭማሪ ታይቶባቸዋል፡፡ በሌላ በኩል የታኅሣሥ ወር የ2007 ዓ.ም. የዋጋ ግሽበት ካለፈው ዓመት ታኅሣሥ ወር ጋር ሲነፃፀርም በ7.1 ከመቶ ጭማሪ በማሳየት የዋጋ ግሽበት ማስከተሉ ታውቋል፡፡ ንግድ ሚኒስቴርን ሆነ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የዋጋ ግሽበትን በሚመከት በሪፖርታቸው ያካተቱት ነገር አልታየም፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post ሦስቱ መሥሪያ ቤቶች በደመወዝ ጭማሪው ላይ ያደረጉት እንቅስቃሴ በተግባር ሲመዘን appeared first on Zehabesha Amharic.

ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በድጋሚ ዛሬም ችሎቱን ሞገቱ * ማረሚያ ቤቱ ዛሬም ከፍርድ ቤቱ የበላይ መሆኑን አስመሰከረ

$
0
0

የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ችሎት በዛሬውም እለት 2 የቪዲዬ ማስረጃዎችን በማስደመጥ ቀጥሎ ውሎዋል
– ማረሜያ ቤቱ ዛሬም ከፍርድ ቤቱ የበላይ መሆንን አስመስክሮዋል
* ምንም የተፈጠረ አዲስ ነገር የለም ሲል ምላሽ ሰጥቶዋል

(ቢቢኤን ÷ ጥር 27/2007) የህዝበ ሙስሊሙ መፍቴሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ችሎት በዛሬው እለትም ቀጥሎ የዋለ ሲሆን ችሎቱ በዛሬው ውሎ 2ት የቪዲዬ የሰነድ ማስረጃዎችን አድምጦ ውሎዋል።
Mandela+Obama+The Ethio-Muslims cause
ለችሎቱ በቅድሜያ በማስረጃነት ቀርቦ የነበረው በማስረጃ ተራ ቁጥር 27 የተቀመጠውን ስኔ 2004 ወሎ ባቲ በሙስሊሙ ማሀበረ ስብ የተዘጋጀውን የሰደቃና አንድነት ፕሮግራም ሲሆን ጠበቆቹ ባሲያዙት ጭብጥ መሰረት ኡስታ በድሩ ሁሴን በፕሮግራሙ ላይ አንድነትን ከሌሎች እምነቶች ጋር ተቻችሎ መኖርን የሌሎችን እምነት ስለማከርና መብታቸውን ስለ መጠበቅ ያደረገውን ንግግር በቀረበው ሲዲ በዝርዝር መመልከት ተችሎዋል:: ኡስታዝ በድሩ ሁሴንም በየአንዳንድ ንግግሩ ሰላማዊነትንና አንድነትን ሲሰብክ በተጨባጭ ለማየት ተችሎዋል።

በመቀጠለም ለችሎቱ ቀርቦ የነበረው የቪዲዬ ማስረጃ ሰኔ 17/2004 በተመሳሳይ መልኩ በአዲስ አበባ በኮልፌ ቀራኔዬ በአስረር መስጂዶች ትብብር ተዘጋጅቶ በሀምዛ መስጂድ የተደረገውን የሰደቃና አንድነት ፕሮግራም አስመልክቶ ሲሆን ሲዲው የሚያስረዳው 1ኛ 2ኛ 7ኛ ተከሳሾች አድርገውታል ስለተባለው አመፅ ቀስቃሽ ንግግር ሲሆን ሲዲው በተቃራኒው ተከሳሾቹ ያደረጉት ንግግር መቻቻልን እንዲሁም ሌሎች ሰላማዊ የሆኑ ንግግሮችን ማድረጋቸውን የተከሳሽ ጠበቆች ባሲያዙት ጭብጥ መሰረት የቀረበው ሲዲ በሚገባ አስረድቶዋል:: በቀረበው ካሴት ጥራት ምክኒያት የሀምዛ መስጂዱ ፕሮግራም ሁሉንም ማየት ያልተቻለ በመሆኑ የተቀረትን ፕሮግራሞች የአሚራችን ኡስታዝ አቡበከር አህመድ ንግግር ጨምሮ በቀጣይ ቀነ ቀጠሮ እንዲቀርቡ ትእዛዝ ተሰጥቶባቸዋል።

የእለቱ ችሎት በዚሁ የተጠናቀቀ ሲሆን ችሎቱ ቀጣዩን ትእዛዝ ከመስጠቱ በፊት ቀደም ሲል ለፍርድ ቤቱ ቀርቦ በነበረው የማረሜያ ቤቱ አቤቱታ በተሰጠው ምላሽ የተከፋትና የምላሹ አስጣጥ ያስከፋቸው የሰላም አንባሰደሮቹ በአሚሩ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ አማካኝነት በደጋሚ ፍርድ ቤቱን በሚገባ ሞግቶዋል።

ማረሜያ ቤቱ በቀረበው አቤቱታ ለፍርድ ቤቱ እንዲስጥ በታዘዘው ምላሽ በተከሳሾች ላይ ምንም የተለየ ነገር አልፈፀምንን ከወትሮ የተለየ አዲስ ነገር የለም ያቀረቡት አቤቱታ ሀሰት ነው ሲል በፁፍ ባስገባው ምላሽ የሰጠ ሲሆን ይሄንንም አሚራችን አቡበከር አህመድ አይን ያወጣ ክህደት ሲል ምላሹን አውግዞታል።

የተሰጠው ምላሽ ፈፅሞ የውሸት ነው ስለሆነም በእጃችን ያለው እህቶቻችን ባለ ቤቶቻችን እኖቶቻችን በማረሜያ ቤት ጠባቂዎች የደረሰባቸውን የቪዲዬ ማስረጃ በፍርድ ቤቱ ይታይልንና ፍርድ ቤቱ ተገቢውን ውሳኔ ይስጥል ብለው አቤቱታቸውን ቢያቀርቡም ካንጋሮ ፍርድ ቤቱ ግን የመወሰን አቅም እንደሌለው በዳኞቹ አንደበት አረጋግጠዋል ችሎቱ በቀረበው አቤቱታና ምላሹ ላይ ተወያይተው ወይም ደህንነቶችን አማከረው ለነገ ውሳኔ እንደ ሚሰጡ በማሳወቅ ለነገ ችሎቱ እንዲቀጥል ትእዛዝ በመስጠት የእለቱ ችሎት ተጠናቆዋል።

The post ኡስታዝ አቡበከር አህመድ በድጋሚ ዛሬም ችሎቱን ሞገቱ * ማረሚያ ቤቱ ዛሬም ከፍርድ ቤቱ የበላይ መሆኑን አስመሰከረ appeared first on Zehabesha Amharic.

[ኢት-ኢኮኖሚ ET- ECONOMY] –“ጅብ ከሚበላህ ጅቡን ብላውና ተቀደስ!!!”የኢትዬጵያ ቢራ ፋብሪካዎች (Ethiopian Beers Factories)

$
0
0

ethiopian beers
ፀ/ት ፂዬን ዘማርያም

በኢትዩጵያ በቀ.ኃ.ሥ ዘመነ መንግስት 1922 እኤA ቅዱስ ጊዬርጊስ ቢራ ፋብሪካና በ1963 እኤአ ሜታ አቦ
ቢራ ፋብሪካ ተገንብተዎል፡፡ በደርግ ዘመን በ1984 እኤአ ሐረር ቢራ ፋብሪካና፣ በ1988 እኤአ በደሌ ቢራ ፋብሪካዎች ተገነቡ፡፡ እንዲሁም በህወሃት/ኢህአዴግ ዘመን በ1995 እኤአ ዳሽን፣በ2014 እኤአ ሐበሻና፣ በ2015 እኤአ ራያ ቢራ ፋብሪካዎች ተገንብተዋል፡፡ አጠቃላይ የሰባቱ ቢራ ፋብሪካዎች የግንባታ ወጭና ልዩ ልዩ ማሽኞች ግዥ 16,020,903,086.81 (16 ቢሊዩን፣020ሚሊዩን 903ሽህ 086 ብር) እንደሆነ ጥናቱ ያሳያል፡፡ የቢራ ፋብሪካዎቹ ግንባታና ማሽነሪዎች በሙሉ ከባህር ማዶ ሃገራት ሰለሚመጡ በአመዛኙ የውጭ ምንዛሪ እንደሚያስፈልጋቸው ይታወቃል፡፡ በሃገሪቱ በሰባቱ ቢራ ፋብሪካዎች የተፈጠረው የስራ እድል ለሦስት ሽህ አምስት መቶ ሠራተኞች እንደተቀጠሩ ይገመታል፡፡

በአሁኑ ግዜ፣ ከሰባቱ ስድስቱ የቢራ ፋብሪካዎች በውጭ ሃገር ባለሃብቶች ንብረትነት ተዘዋውረዋል፡፡

ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post [ኢት-ኢኮኖሚ ET- ECONOMY] – “ጅብ ከሚበላህ ጅቡን ብላውና ተቀደስ!!!” የኢትዬጵያ ቢራ ፋብሪካዎች (Ethiopian Beers Factories) appeared first on Zehabesha Amharic.

ምስጋና –ለነፃነት ዬተስፋ አውራ! –ከሥርጉተ ሥላሴ

$
0
0

ከሥርጉተ ሥላሴ 04.02.2014 /ሲዊዘርላንድ / ዙሪክ/

UDJ general meeting 1አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ በወያኔ ሴራ ከነፃነት ትግሉ ጎራ የተገለለው የአንድነት ጨርቃ ጨርቆች ማለት የተጣፉት ዲሪቶ – ተቀዳጆቹ፤ ማሽኖቹ – ተሰባሪዎቹ፤ ህንፃው ከእድሳት እጥረት ፈራሹ – ቁሶቹ ብቻ እንጂ ለነፃነት ትግሉ ተስፋ አንዱ ብሄራዊ መንገድ ለነበረው የአንድነት መንፈስ፣ አባላት፤ አካላት፤ ደጋፊዎችና ቅን ወገኖች አይደለም። ወያኔ ወልቃይት – ጠገዴን – አዲረመጽን ሰቲትንና ንጥር ሃብቱን በወረራና በዘመንተኝነት ወሰደ። የሰቲትና የአካባቢውን ዕውን መንፈስ ግን ከጎንደር መንፈስ ፈጽሞ መነጠል አይደለም ከቅርቡ መድረስ አልቻለም። ስለምን? ወያኔ በወረራ የወሰዳቸው ክልሎች ኗሪዎች የሚያቀኑት ወደ እትብት ባዕታቸው ወደ ጎንደር ነው። ለተለጣፊ ማንነት ጨዋው ህዝብ ጊዜ የለውምና።

አንድነት ከመበቻው ጀምሮ የበርካታዎችን ወገኖች ቀልብ የሳበ ብቻ ሳይሆን ያደራጀና የመራ የቅንጅት ንጹህ መንፈስ የረበበት ፓርቲ ከመሆኑም በላይ፤ ፈተናን አብዝቶ የተቀበለ አውራ ፓርቲ ነው። መስዋዕትነትንም የከፈለ። የደማ የተጎዳ። አብዛኞቹ የታሰሩት የነፃነት ትግሉ ጋዜጠኞች ቢሆኑ ለአንድነት መንፈስ እጅግ በጣም ቅርብ ናቸው። ወያኔ የማዕዘን ድንጋይ ሊሆኑ የሚችሉ ትንታግ ወጣት የአንድነት መሪዎችን አስርጎ በሳገባቸው ክህደቶች በዬጊዜው የካቴና ሰለባ ቢያደርግበትም፤ በማያቋርጥ ሁኔታ የአንድነት ኃይልና ብርታት መጠንከር፤ ጉልበታምነት፤ ዛሬ ከወሰደው ወያኔያዊ ዳፍንት እርምጃ ሌላ መስረጃ ማቅረብ የሚያስፈልግ አይመስለኝም። ሀገር ውስጥ የወያኔ የስጋት ማዕከል ድርጁው አንድነት ነበር። ለጥቃቱ ቀዳሚ መስመረኛም አንድነት … ነገ ደግሞ  በአንድነት ጥላ ላይ ላይ ወመኔው ወያኔ እንደሚያነጣጥር ይታወቃል።

አንድነት እጅግ ጎምርቶ የሚነገርለት ኪንግ ማርቲን ሉተር ከፈጸመው ተግባር የላቀውን ከውኗል። አሁን መኢህድና አንድነት በባህርዳር አዘጋጅተውት የነበረው „ ከባዶ ጭንቅላት ባዶ እግር“ ይሻላል እጅግ ሥልጡን ሰላማዊ ሰልፍ፤ አዲስ አባባ ላይ የነበረው „ዲግሪ ድንጋይ ተሸክሞ፤ እንስራ ተዝቅዝቃ በውሃ ጥማት፤ የ21ኛው ምዕተ ዓመት ሥልጣኔ ውጤት የኢንተርነት አገልግሎት እግር ከወርች ታስሮ“ ያ ዬሰላማዊ ሰለፍ ወርቃማ ዬተግባር ታሪክ እራሱ የተስፋ ገድሉን ችሎ ሊጽፈው ከቶውንም አይችልም። በልቦናችን ውስጥም ማንም ሊነቀንቀው ያልቻለና አሁንም ቅድምም እዬመጣ የሚቀሰቅስን፤ የሚያስተምረን ብቁ ያደገ ዬተግባር ተቋማችን ነው። ተደላድሎ በውስጥ ለውስጥ፤ ከውስጥ ተቀምጧልና።

በሌላ በኩል አንድነት ደፋርም ነበር። እንደ ብሄራዊ ፓርቲነቱ በጎሳ የተደራጁትን ወገኖች ቢሆን ፈቅዶ የተቀበለ። ከፍ ያለውን ቦታ ለእነሱ አክብሮ የሰጠ፤ ከራሱ ትሁት ወገኖች የቀረበበትን የሰላ ወቃሳ የቻለና በሂደቱም በጎና በጎ ባልሆኑ ገጠመኞችም የተማረ ፓርቲም ነው ማለት እችላለሁ። ይህን ሳላዬው ወይንም ይህን ሞክሬው ቢሆን የሚል ጸጸት በአንድነት ፓርቲ ሊኖር ከቶውንም አይችልም። አንድነት ፓርቲ ሁሉንም ዓይነት ፈተናዎች፤ ችግሮች፤ ስቃዮችና አሳሮች በመቻል ከውስጡ ከነቀዙ፤ ከውጪው አውሬ፤ ከለስላሳው ደጋፊ ሳይቀር የተሰነዘረበት- የተዶለተበትን፤ በተቆርቋሪነትም ከወገኖቹም ከሚሰነዘረው ተከታታይ ስሉ ወቃሳ ሁሉን ተቀብሏል። ማደጉም፣ መደራጀቱም ጎሰኛውን ወያኔ እረፍት ስለነሳው፤ ታይቶ ተሰምቶ በማይታወቅ ሁኔታ ብሄራዊ የዜግነት መብቱን በአደባባይ ይሄው ተነጠቀ። ይህ ወያኔ የወሰደው ዘረክራካ  እርምጃ ወያኔ አለኝ ለሚለው የዲፕሎማሲያዊ ግኙነቱም ቢሆን እሳት የሚተፋ የነገ መጥፊያው ይመስለኛል። አንድ ብሄራዊ የህዝብ ፓርቲ እንዴት በአንድ ተማላ ቀላጤ ይሰረዛል? ቀን ያልፋል ታሪክ ግን ይዘከራል።

አንድነት ፓርቲ ለሰላማዊ ትግሉ ተስፋ ስኬታማነት ሞቷል፤ ቆስሏል፤ ታስሯል፤ ተግድሏል፤ ተሰዷል። የሞቱት ሙተው የተረፉት በርካታ ወጣቶች ከተሰደዱ በኋላ ስለማይናገሩት እንጂ በቤተሰቦቻቸው የአንድነት ደጋፊነት ምክንያትነት ሳይቀር ሀገራቸውን የለቀቁ  አባና እማ ወራዎች እጅግ በርካታ ናቸው። ከዚህ ሲዊዝ ውስጥ አንድ ወጣት አግኝቼ ነግሮኛል። የአንድነት መንፈስ የቅንጅት መንፈስ ነው የሚለው የመነሻ ጉዞው እርገትንም ስመረምረው በግሌ እውነት መሆኑን አገናዝቤበታለሁ። እንዴት በተመስጦ ውስጥ እንደ ነበር ወጣቱን ሳስተውለው መህተሙ …. ነገረኝ።

ዘመነ 2014 እራሱን ሸኝቶ ዘመነ 2015ን ለመቀበል በተሰናዳበት የመሰናዶ ወቅቱ አንድነት ለፍትህና ለዴሞክራሲ ያወያዬ በስሜን አሜሪካ የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ድርጅት አንድ የቴሌፎን ኮንፈረንስ ተዘጋጅቶ ነበር። ታህሳስ 28.2014 ይመስለኛል። ዕለተ ሰንበት ልክ 20.00 ነበር በሰዓቱ ስበስባው የተጀመረው። እኔም ጸጋዬ ራዲዮ ፕሮግራሜን እና እኔውን እራሴን ወክዬ ታዳሚ ነበርኩኝ። መቼም የእነወጣት አቶ ሃብታሙ አያሌው እስር የአንድነትን ተስፋ ጋር የነበረው መስተጋብር እጅግ ፈታኝ ስለ ነበር አሁን አንድነት እንደዛ ዓይነት ትንታግ፤ ዓላማውን ያወቀ፤ ለብሄራዊ ሰንድቅዓላማችን፤ ለብሄራዊ ማንነታችን ተቆርቋሪ ታታሪ፤ ተናግሮ የሚያሳምን ዬት ያገኛል የሚል ከፍ ያለ ስጋት እኔ በግሌ አድሮብኝ ነበር። በኋላ ግን የተከበሩ ዬአንድነት ሊቀመንበር የአቶ በላይ ፈቃዱ አጭር ክሽን ያለ መግለጫ ሳዳምጥ ተሰፋዬ አቆጠቆጠ። አብሶ ጋዜጠኛ ሃብታሙ ላቀረበላቸው ጠንካራና ሁለገብ ጥያቄ የሰጡትን መልስ ሳዳምጥ ወይ አንቺ ሀገር ስለ አንቺ የሚቆረቆሩ ጠንካራዎችን ስታመርቺ የምታዳሪ ብርቅና ውብ ሀገር ነበር ያልኩት። የእውነት የሚያኮራ ነበር። ካርዴ አቋርጦኝ እንጂ ከውይይቱ ባልወጣ በወደድኩኝ ነበር። እስከ ነበርኩበት እስከ እህት ዊንታ ጥያቄ ድርስ ታሪካችን ስለሆነም ቀድቸዋለሁም። ዛሬ ላይ ሆኜ ሳስበው እንኳንም ነበርኩኝ፤ እንኳንም ቀዳሁት። የመጨረሻው የገናናው የአንድነት ብሄራዊ ፓርቲ የተስፋ ድምጽ ነበርና። የትናንቱ የቅንጅት መራራ ስንብት እንሆ ዛሬም ተደገመ ///  መራራ ስንብት …. ህም!

ታስታውሱ እንደ ሆነ አዲሱ የአንድነት አመራር በህጋዊ ጉባኤ ውክልና ካገኘ በኋላ ከእራሱ ከአዲሱ ብሄራዊ አመራር የሚወጡ ጹሑፎች፤ የፈጠሩት ሰብቃ ወይንም ግጭት፤ እንዲሁም የገዢው ጎሳ ድርጅት ወከባ፤ በተጨማሪም የውስጥ ተውሳኮች ጉንተላ አይሎ ስለነበር እኔ በግሌ ለአዲሱ አመራር ድርብርብ ኃላፊነትና በፈታና የታጨቁ ወቅቶች ይሆኑበታል የሚል ስጋት ነበረብኝ። ከቴሌፎን ኮንፍረንሱ ውይይት ተሳታፊዎች የሚቀርቡ ጥያቄዎችም በአማዛኙ ከዚህ ፈታኝ ሁኔታ ጋር የተያያዙና ተቆርቋሪነታቸውም ልብ የሚነካ ነበር። የወቅቱ የአንድነት ሊቀመንበር የተከበሩ አቶ በላይ ፈቃዱ ግን አጅግ በተረጋጋ፤ በሰከነ ደም ነበር ለቀረበላቸው ጥያቄ መልስ የሰጡት። መልሶቹ ከሆደ ሰፊነት ተነስተው፣ መዳረሻቸው የነፃነት ትግልን የተረጎመ፣ የነፃነትን ሥነ – ተፈጥሮ መንፈስን ያነበበ ነበር። እኔ በግሌ እጅግ ነበር የኮራሁባቸው። እኒህ ሰው በአመራር ዘመናቸው ለአመራር አካላቱም ሆነ ለአባላቱ ያለውን የመብት ድንበር የማይጥሱ ይሆናሉ የሚል ህልምም ነበረኝ።

አንድነት ሲመሰረት መዋቅሮቹ እጅግ ብዙ ስለነበሩ እኔ በግሌ በዛ የማለት አቋም ነበረብኝ። አንደኛው ምክንያቴ ለሥራ ቅልጥፍና ቢሮክራሲያዊ ነገሮችን ያበራክታል ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የበጀት አቅሙን በማሰብ ነበር። ይህ ማለት ከአመሰራረቱም አንድነት በብቁ ሁኔታ መዋቅሩን አደራጅቶ የተመሰረተ ነበር ማለት ይቻላል። በዚህ ወካባ ውስጥ ሆኖ በአብዛኛው የሀገራችን ቦታዎች የነበረው እንቅስቃሴም ሆነ ተቀባይነት አጅግ ውብ አበረታች ነበር። ተስፋም።

አንድ ብሄራዊ ፓርቲ በህገመንግስታዊ መብቱ ተጠቅሞ መደራጀቱ፤ ሰፊ መሰናክሎችን አልፎ እድገቱን ሲጠብቅ እንዲህ በዓዋጅ ሲፈርስ ዓይን ባወጣ ውንብድና ፓርቲው ቋሚና ተንቀሳቃሽ ንብረቱ ሲወረር ከቅንጅት ቀጥሎ አንድነት ሁለተኛ መሆኑ ነው። ይህ አቁሳይ እርምጃ ቀጣዩን እርምጃ አሳምሞ ተስፋ ቆራጭነትን ያሳዝለው ይሆን? ይህ የሁሉም ጥያቄ ነበር …

ነገር ግን ሥልጡኑ አመራር ያደገና የበሰለ እርምጃ ነው የወሰደው። ይህ ማለት አንድነት ሲታገል የነበረው ለማልያ ፍቅር አለመሆኑን በደማቅ ተግባሩ አሳዬን። ከፍተኛው አመራር ዝቅ ብሎ ወርዶ ለብሄራዊ ነፃነታችን ተስፋ ሲል እንደ አንድ ዜጋ ይነጠፍልኝ፣ ይጎዝጎዝልኝ፣ ይጨብጨብልኝ ሳይል ከሚመስለው ፓርቲ ጋር ተቀላቀለ። ቀደመ! በለጠ! ይህም ብቻ አይደለም ለአባላቶቹና ለደጋፊዎቹ እኔ የተቀላቀልኩትን ብቻ ተቀላቀሉም አላለም። ወደ ዬሚመቻቸውና ወደ ዬሚያምኑበት ፓርቲ ተቀላቅለው የነፃነት ትግሉን በመንፈስ፤ በአካል፤ በጊዜና በፋይንስ እንዲረዱ ፍጹም የሆነ የጠራ ንጹህ መመሪያ በመስጠትም ነው። ይህም ሌላ ብልህ የላቀ የቁምነገር ታሪክ አባትነትም ነው። አባወራነት ከግራጫማ ትርጉማዊ በሳል ልቦና ጋር።

አንድነትን ተጠልለው፣ አንድነትን የደገፉ መስለው በተለጣፊነት ሲጎረጉሩ፣ ሲቦረቡሩ የነበሩት አሁን በአንድነት አደጋ ምን ተሰማቸው? ጎረበጣቸው? ይህን ለታዛቢ ትቼ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን አንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ለአደረገው እጅግ የላቀ የጀግንነት ተጋድሎ አድናቆቱን በተግባር ከጎኑ በመቆም ማስመስከር ያለበት ይመስለኛል። ጥበቃ ሊያደርግላቸውም ይገባል። አንድነት ለሰላማዊ ትግሉ የተስፋ ማህደር ነበርና።

ሌላው የሚነሳው የሰማያዊ ፓርቲን አንድነት መቀላቀል በሚመለከት የተስረከረኩ ነገሮች ሊቀርቡ ይቻላሉ። አንድ መዘንጋት የሌለበት ነገር ሰማያዊ የአንድነት የበኽር ልጁ መሆኑን ነው። የአብራኩ ክፋይ የማህጸኑ ወተት መሆኑ ነው። በሌላ በኩልም የልምድ፣ የተመክሮ ጉዳይም ተጨማሪ አነጋጋሪ ጉዳይ ሊሆን ይችላል። 12 ክንድ ነጠላ 25 ሲሆን ኩታ 50 ሲሆን ጋቢ ይሆናል። ድርብ ሙቀት ከበሰለ ተመክሮ – ከአፍላ ጉልበት ጋር ገደል ይሰራል። በፓርቲ ህይወት ውስጥ የአመራር ተከታታይነት የሚባለውም ይሄው ነው። ልምድና ተምክሮ ዕድሜን ሳይሆን የሚቆጥረው ብቃትን፤ የማድረግ አቅምን፤ የመሆን መቻልን በመገኘትን ነው። አንድነት የወሰደው እርምጃ ለእኔ እንከን የለሽ ፍጹም ነው። እንኳንም የበኽር ልጁ አስቀድሞ ጎጆ ወጣለት። ጎጆ የወጣው ልጁ ደግሞ በአጭር ጊዜ በተግባር የበቀለ ሰብል ያፈራ አንቱ ነው። እኔ የቤተሰቧ እማወራዋ ችግር በደረሰብኝ ጊዜ ጎጆ ያወጣኋቸው ታናሾቼ ናቸው ህይወቴን እንዲሰነብት ያደረጉት። ለአንድ ቀንም መጠለያ ማግኘት ትርጉሙ – ጥልቅ ነው። ዬአንድምታ ዐዋቂዎች ቢያመሳጥሩት። ብሄራዊው አንድነት በመከራው ዕለት ጃንጥላ አገኘ። ጃንጥላው ደምና ሥጋው ነው። ደምና ሥጋው ህይወቱ ነው። „አይዟችሁ!“ ቃለ ወንጌል ነው ዛሬ ለአንድነት። እንኳንስ የአብርኃሙ አዕማደ ሚስጢር ዕውንነት። እርምጃው ጥልቅና ብልህም ነው። ውጪ ያለውን የነፃነት ረሃብተኛነት መንፈስንም ይገራል። ሀገር ቤት ያለውን በወመኔው ወያኔ የተናደውን ጥግ አልቦሽነትንም ይፈውሳል – ወጌሻው ጃንጥላ።

እኔ እንደማስበው ቀጣዩ ጊዜ ከመቼውም ጌዜ በመጠን የሰፋ የሱባኤ ወቅት ይሆናል። ቢያንስ በእጅ ባለ ነገር ጠንቃቃ መሆን መልካም ነው። ያተርፋል። ለምሳሌ –  ጥንቃቄ የሚያሰፈልገው ነገር  ጹሑፎች /ፌስ ቡክም ላይ ሆነ ድህረ ገጽ ላይ/ ፤ ቃለ ምልልሶችንም ቢሆኑም ማዕከላዊ ለማደረግ ቢሞከር እጅግ መልካም ነው። ግጭት ከራስ ወገን ጋር የሚፈጥሩ ጎረምሳ መንፈሶች ሁሉ አደብ መግዛት ያለባቸው – ይመስለኛል። በአጅ የተያዘ ድል እንኳን ቢሆን ጥበቃ ሊደረግለት ይገባል። ከመታወጁ በፊት ጊዜና ሁኔታን ማዬቱ ይበጃል። ምክንያቱም ለአለስፈላጊ መስዋዕትነት ጥበቃ ማድረግ ስለሚያስፈልግ። አሁን የእኛ አይደለም። ለእኛ ላልሆነው ዘመን ደግሞ ሁሉም የደህንነት ሠራተኛ ለብሄራዊ ፍላጎቱ መሆን አለበት።

አሁንስ ወያኔ አሰርጎ አያሰገባንም? ቀጣይ እርምጃ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ወያኔ ቢወስድ ምን ማደረግ ይኖርበታል? ሰላማዊ ትግሉ ቀድሞ ሊዘጋጅባቸው የሚገባቸውን ጉዳዮች ከልብ ሆኖ መምከር፤ ማድመጥ፤ ሊያተኩርበት የሚገባ መሰረታዊ ጉዳይ ነው። የነፃነት ትግሉ መንፈስ አሁን ሌላ ፈታኝ ሽግግር ላይ ስለሆነ ያለው ትንፋሽን ሰብስቦ፤ ደምን በረድ አድርጎ፤ ቀጣዩን ፈተና በዬአቅጣጫው በማስተዋል መመርመር ብቻ ሳይሆን መፍትሄዎችንም ቀድሞ አዘጋጅቶ መጠበቅ ይኖርበታል። ሰላማዊ ትግል ሲመሰረትም ኑሮውን ሙት መሬት በማደረግ ነው። ሙት መሬት ላይ ሆኖ ተጋድሎ ደግሞ የሚያስከፍለው መስዋዕትነት እጥፍ ድርብ – ድርብርብርም ነው። ስለምን? ገዢ መሬቱን የሚቆጣጠረው ገዢውና ጨቋኙ ጎሳዊ ድርጅት በመሆኑ። የሰላማዊ ትግሉ ያለው አንጡራ ሃብት የነጠረ እውነት ብቻ ነው። እውነት ደግሞ በፈተና ጦር የተከበበ ነው። ጥሶ ለመወጣት ጊዜና ሙሉ የህዝብ ድጋፍን ይጠይቃል። ሌላው ስጋቴ የተከበሩ አቶ በላይ ፈቃዱ ሊቀመንበር በነበሩበት ጊዜ ከነበረው ውጥረት የባሰው አሁን ይመስለኛል። ያን ጊዜ በውጪ ዲፕሎማሲው ማህበረበሰብ አነሰም በዛም የተወሰነ ተጽዕኖ ስለነበረው ይሻላል፤ አሁን እኒህ የአንድነት መሪ አውላላ ሜዳ ላይ ናቸው። ስለዚህ ለወያኔ ጥቃት በጣም የተጋለጡ በመሆኑ ጥንቃቄው ቢኖር መልካም ነው።

ይህም ማለት ከዚህ የባሰ ነገር ወያኔ ቤት አልባ ባደረጋቸው የነፃነት ትግሉ አርበኞቻችን ላይ ሆነ በሰማያዊ ፓርቲ ቢያመጣ እንኳን የነፃነት ትግሉ፤ የሰላማዊ ትግሉ አካል የሆነውን „የድምጻችን ይሰማ“ መንገድ፤ መንገዱ እንዲሁን በምልስት ሂደቱን መመርመር ያለበት ይመስለኛል። „ድምጻችን ይሰማ“ ቢሮ የለውም፤ የታወቀ አመራር አካላት የሉትም፤ መዋቅራዊ ሰንሰለትም የለውም፤ መሪዎቹ በሙሉ እስር ላይ ነው ያሉት። ነገር ግን ተግባሩ የዓለም መምህር ነው። „ድምጻችን ይሰማ“ ለእኔ የሰላማዊ ትግሉ ሐዋርያ ነው። በቅጽበት ለአባላቱ በተመሳሳይ ደቂቃ መረጃ የማከፋፈልና የመምራት አቅሙ ሰለጠኑ ከሚባሉት ሀገሮች እጅግ የበለጠ ነው። ስልቱ ልዩ ፍጹም ልዩ ነው …. እያንዳንዱን የትግል ደቂቃ ከዚህ በሳል ተመክሮ ጋር በማቀናጀት ተስፋን ማፋፋት ብቻ ሳይሆን በዚህ መስመር ተስፋንም ማግኘት ይቻላል የሚል ጽኑ እምነት አለኝ። ሌላው ቀርቶ „የድምጻችን ይሰማ አባላት“ በውጪ ሀገር ያላቸው ተሰትፎ ግንባር ቀደም ነው። በ2014 የሲዊዝ የኢሳት የድጋፍ ገንዘብ መሰባሰቢያ ስብሰባ ላይ „የድምጻችን ይሰማ አባላት“ የሮመዳን ፆማቸውን የፈቱት እዛው ስብሰባ አዳራሽ ውስጥ ሁሉን ነገር አሰናድተው መጥተው ነበር። ለእኔ ይሄ ለነፃነት ትግል አምክንዮ ልዑቅ ጉልላታዊ ታሪኬ ነው። እንጃ መንፈሳቸውን እንዴት አድርጎ አምላኬ እንደ ቀባው አላውቅም። የነጠረ ዕንቁ ነው የትግላቸው ሂደትና ስልቱ። የትም ቦታ፤ በዬትኛውም ሁኔታ እነሱ አሉ። ቅመም ናቸው። …. እንከተለው … „ያልተሄደበት መንገድ“ የማገዶው ወንድሜ የአንድነቱ ዬአቶ ዬአንዱአለም አራጌ መጽሐፍ የሥነ ሕሊናው ዐይኑ እፍታ ……

ክውና – የተከበራችሁ የአንድነት አባላት፤ የአንድነት አመራር አካላት፤ የአንድነት ደጋፊዎች፤ የአንድነት የተስፋ ራህበተኞች ወገኖቼ ለከፈላችሁት እጅግ የመረረ መስዋዕትነት የብሄራዊ ነፃነታችን የተስፋ አውራ ባላወለታችን ጉልህ ታሪካችንም ናችሁ፤ እና እኔ ታናሻችሁ ሥርጉተ ሥላሴ ዝቅ ብዬ እግዚአብሄር ይስጥልኝ እላለሁ። አመስግናችኋለሁ! እወዳችኋለሁ። አርበኝነታችሁ አስተምሮኛል። እውነት ናችሁ። እውነት ወርቅ ነው። አይዝግም። ይፈልቃል። አይዛችሁ! መሸቢያ የተጋድሎ ጊዜ።

አንድነት ብሄራዊ መንገዳችን ነው!

እግዚአብሄር ይስጥልኝ።

 

 

 

 

 

 

The post ምስጋና – ለነፃነት ዬተስፋ አውራ! – ከሥርጉተ ሥላሴ appeared first on Zehabesha Amharic.

በብአዴን ወስጥ በተፈጠረ አለመግባባት የድርጅቱ መስራች ታደሰ ካሳ በምሬት ማልቀሳቸው ተሰማ

$
0
0

ጥር ፳፯(ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የብሔረ አማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ብአዴን) ፤የድርጅቱን የትግል ጉዞ የሚተርክ አዲስ መፅሃፍ አስጽፎ የድርጅቱ መስራች በሆኑትና በቅጽል ስማቸው <<ጥንቅሹ>>ተብለው በሚጠሩት በአቶ ታደሰ ካሳ እያስገመገመ ሲሆን፤ በመጽሀፉ ይዘት ላይ በአመራሮቹ መካከል ላይ ከፍተኛ አለመግባባት ተፈጥሯል።
tinkishu
በግምገማው ላይ የብአዴን መስራች አይደለህም የተባሉት ታደሰ ካሳ፤ << ለላፉት 30 ዓመታት የማላውቀው ታሪክ ነው የተነገረኝ>> ሲሉ በንዴት ተናግረዋል።

አቶ ታደሰ ይህን ሲሉ በጓዶቻቸው ፦ መስራቾች ከ37 ታጋይነት ወደ36 ዝቅ እንዲሉ መወሰኑንና እርሳቸውም መስራች ባለመሆናቸው ስማቸው እንዲወጣ መደረጉን ሲነገራቸው ከፍተኛ ንዴት ውስጥ ከመግባታቸውም ባሻገር አመራሮቹ ለሁለት ተከፍለው እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ ሲከራከሩና ሲጨቃጨቁ አምሽተዋል።
በውይይቱ፤ መጽሀፉ ታደሰ ካሳን ከመስራችነት በማውጣት እንዲታተም የሚል ሀሳብ በተደጋጋሚ በመነሳቱ አቶ ታደሰ ካሳ እንባ አውጥተው እስከማልቀስ መድረሳቸውን ምንጮቻችን ጠቁመዋል። በመጨረሻም አቶ ታደሰ ካሳ ወይም ጥንቅሹ የብአዴንን ጉዞ በሚተርከው በፅንአት ቁጥር አንድ እና ሁለት መፅሃፍ ስማቸውን በመስራችነት ጠቅሰው ቢጽፉም፤ የድርጅት ጓዶቻቸው በመስራችነት እውቅና እንደማይሰጧቸው በማስረገጥ ውይይታቸውን አጠናቀዋል።

በአሁኑ ስዓት በፖለቲካ ጫና ዳር እየወጡ ያሉት አቶ ታደሰ ካሳ፤ የብአዴን የልማት ድርጅት የሆነውን ጥረት ኮርፖሬትን እንዲመሩ ተመድበዋል። ብአዴን- ኢህአዴግ ከድሮው የኢትዩጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅንቄ (ኢህዴን) ተፀነሶ የህውሃትን ህልም ለማሟላት ሲል ከህብረ ብሄራዊነት ወደ ብሄር ድርጅትነት መቀየሩ ይታወቃል።

The post በብአዴን ወስጥ በተፈጠረ አለመግባባት የድርጅቱ መስራች ታደሰ ካሳ በምሬት ማልቀሳቸው ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ሰብሳቢ ዳኛው ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ

$
0
0

በላይ ማናዬ

1969226_659617997497195_64263730987588908_nበእነ ሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸው በፍርድ ቤት እየታየ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማርያን እና ጋዜጠኞች ሰብሳቢ ዳኛው የተፋጠነ ፍትህ የማግኘት መብታችንን አላስከበሩልንም በሚል ከችሎት እንዲነሱ የጠየቁበት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ፡፡
ዛሬ ጥር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ለ19ኛ ጊዜ የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት የቀረቡት ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ጥር 26 ቀን 2007 ዓ.ም በጽሑፍ ያቀረቡት አቤቱታ በፍርድ ቤቱ ውድቅ ተደርጓል፡፡
ፍርድ ቤቱ የተከሳሾችን አቤቱታ በንባብ ያሰማ ሲሆን፣ አቤቱታውን ሁለቱ ቀሪ ዳኞች (ሰብሳቢ ዳኛው በሌሉበት) እንደመረመሩት በመግለጽ ብይናቸውን በንባብ አሰምተዋል፡፡ በብይኑ መሰረትም ተከሳሾች ሰብሳቢ ዳኛው ከችሎት ይነሱልን የሚለውን አቤቱታ ፍርድ ቤቱ አልተቀበለውም፡፡
ተከሳሾች አቤቱታውን ምክንያት ላይ ተመርኩዘው ቢያቀርቡም፣ ውሳኔዎቹ የተሰጡት በሦስቱ ዳኞች መሆኑን በመግለጽና የቀረቡት ቅሬታዎች በማስረጃ ያልተደገፉ ናቸው በሚል ሰብሳቢ ዳኛው ላይ የተነሳው አቤቱታ ተቀባይነት የሌለው ነው ብሏል ፍርድ ቤቱ፡፡
ስለሆነም ሁለቱ ዳኞች ብይኑን አሰምተው ሲጨርሱ ችሎቱ ሰብሳቢ ዳኛው ባሉበት እንደሚቀጥል በመግለጽ ተሟልተው እንደገና ለመግባት ሁለቱ ዳኞች ከችሎት ወጥተዋል፡፡ በመቀጠልም ሰብሳቢ ዳኛውን ይዘው ተመልሰው በችሎት እንደገና ተሰይመዋል፡፡
ከአጭር ቆይታ በኋላ ሦስቱም ዳኞች እንደገና መሰየማቸውን ተከትሎ ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ይደረጋሉ የሚል ግምት የነበር ቢሆንም ሰብሳቢ ዳኛው ‹‹ሁለቱ ዳኞች በእኔ ላይ የቀረበውን አቤቱታ መርምረው በችሎት እንድቆይ ብይን ቢሰጡትም፣ በግሌ እንዲህ አይነት ቅሬታ እየቀረበብኝ እያለ የምሰጠው ውሳኔ አመኔታን ስለማያገኝ በግሌ ከዚህ ችሎት መነሳት እንደምፈልግ ማመልከቻ አስገብቻለሁ፡፡ ስለሆነም ተከሳሾች አዲስ ዳኛ ሲመደብላቸው ቃላቸውን ቢሰጡ ይሻላል›› በማለታቸው ተለዋጭ ቀጠሮ እንዲሰጥ ተወስኗል፡፡
በዚህ መሰረትም በአዲስ ሰብሳቢ ዳኛ ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ በሚል ለየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል፡፡
በሌላ በኩል 7ኛ ተከሳሽ የሆነው ጦማሪ አቤል ዋበላ በትናንትናው ዕለት ከፍርድ ቤት ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት በመኪና ሲመለስ ጀምሮ በማረሚያ ቤት ፖሊስ የመብት ጥሰት እንደተፈጸመበት አቤቱታ አቅርቧል፡፡
አቤል በፖሊስ ከፍተኛ ዛቻና ማስፈራሪያ እንደተፈጸመበትና ማታ ላይም በሰንሰለት ታስሮ እንዳደረ ለችሎቱ አስረድቷል፡፡ በተጨማሪም አቤል በማዕከላዊ ምርመራ በነበረበት ወቅት በደረሰበት ድብደባ ጆሮው በመጎዳቱ የጆሮ ማዳመጫ ያደረገውን እንደነጠቁት አስረድቷል፡፡ ፍርድ ቤቱም አቤቱታው በጽሑፍ እንዲቀርብና በሚቀጥለው ቀጠሮ ማረሚያ ቤቱ መልስ እንዲሰጥበት ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

The post ጦማርያኑና ጋዜጠኞቹ ሰብሳቢ ዳኛው ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ውድቅ ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደር ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታውን እንዲመልስ እየጠየቁ ነው

$
0
0

• ‹‹ከምርጫው በኋላ ይመለስላችኋል ተብለናል›› አርሶ አደሮቹ

የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን እንዲመልሱ እያሳሰቡ መሆኑን አርሶ አደሮቹ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ከወራት በፊት ጀምሮ የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ሲጠይቁ እንደነበር ያስታወሱት አርሶ አደሮቹ፤ አሁን ምርጫው መቃረቡን ተክትሎ ካድሬዎች ቤት ለቤትና ስብሰባ ላይ ከሚናገሩት በተጨማሪ በየ ቤተክርስቲያኑም አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ ጥያቄ እያቀረቡ ነው ብለዋል፡፡
news
አርሶ አደሮች የመሬት ይዞታቸውን እንዲመልሱ የሚጠይቁት ካድሬዎች ‹‹የእርሻ መሬት ካርታ ውስጥ ሊካተት ስለሆነ ነው፣ በህገ ወጥ መንገድ የግጦሽ መሬት የሚያርሱ ስላሉ ነው፣ መሬት ይዞታ ላይ መስተካከል ያለባቸው ጉዳዮች አሉ….›› እና የመሳሰሉትን ምክንያቶች እንደሚሰጡ የገለጹት አርሶ አደሮቹ የመሬት ይዞታ ደብተራቸውን የማስረከብ ግዴታ እንዳለባቸውና ከምርጫ በኋላ እንደሚመለስ ተነግሮናል ብለዋል፡፡

ምርጫ በተቃረበበት ወቅት የመሬት ይዞታ ደብተር መሰብሰቡና ከምርጫ በኋላ ይመለስላችኋል መባሉ በመጭው ምርጫ ኢህአዴግን አይመርጡም ተብለው በሚታሰቡት አርሶ አደሮች ላይ ፍርሓትና ጫና ለመፍጠር ሳይሆን እንዳልቀረም አርሶ አደሮቹ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

The post የብአዴን ካድሬዎች የክልሉ አርሶ አደር ከምርጫው በፊት የመሬት ይዞታውን እንዲመልስ እየጠየቁ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


ጋዜጠኞችና ጦማሪያኑን የሚዳኙት የመሐል ዳኛ በራሳቸው ፈቃድ ከችሎቱ ራሳቸውን አገለሉ

$
0
0

(አዲስ ስታንዳርድ) ሦስቱ ጋዜጠኞችና ስድስቱ ጦማሪያን ዛሬ በልደታ ፍርድ ቤት 19ኛ ምድብ ችሎት ቀርበው ለ የካቲት 11 ተቀጠሩ፡፡ በ26/05/2007 ዓ.ም. የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ ይቀየሩልን ሲሉ በፅሁፍ ያቀረቡት አቤቱታ የግራና የቀኝ ደኛው ውድቅ ሲያደርጉት የመሀል ዳኛው አቶ ሸለመ በቀለ በራሴ ፈቃድ ከችሎቱ እራሴን አንስቻለሁ ሲሉ ለፍርድ ቤቱ ታዳሚ ገልፀዋል፡፡
edom Jpurnalist
በተያያዘ ዜና ሰባተኛ ተከሳሽ ጦማሪ አቤል ዋቤላ ትላንት ከፍርድ ቤት ወደ ማረሚያ ቤት በሚመለስበት ወቅት እጅህ በካቴና ለምን አልታሰረም ብለው የማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች እጄን በውሻ ሰንሰለት አስረው አሳድረውኛል ብሎም ዛቻና ዘለፋ ደርሶብኛል እንደዲሁም ማአከላዊ ታስሬ እያለሁ በደረሰብኝ ድብደባ ጀሮዬ ላይ ጉዳት ስለደረሰ ለማደዳመጥ ጀሮዌ ላይ የማረገውን ድምፅ ማዳመጫ መሣሪያ በማረሚያ ቤቱ ሰራተኞች ተነጥቂያለሁ ሲል እንባ በተናነቀው ንግግር ለፍርድ ቤቱ ተናግሯል፡፡ ፍርድ ቤቱ ለማረሚያ ቤቱ ተወካይ ለምን ይህ እንደተደረገ እና ያደረገውን ሰው በፅሁፍ እንዲያቀርብ ለየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም እንዲያቀርብ ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

ሦስቱ ጋዜጠኞች እና ስድስቱ ጦማሪያን ደኛው ይቀየርልን ሲሉ ያቀረቡት አቤቱታ አግባብ አይደለም ያለው ፍርድ ቤቱ በወንጀለኛ መቅጫ አንቀፅ 2519 መሠረት የ500 ብር ቅጣት ይቀጡ የነበረው በስሜታዊነት ነው በማለት መቀጫውን ውድቅ አድርጓል፡፡ በየካቲት 11 ቀን 2007 ዓ.ም. የእምነት ክህደት ቃል በአዲስ የመሀል ዳኛ መሠረት ይሰማል ሲል ፍርድ ቤቱ ውሳኔውን አስተላልፏል፡፡

The post ጋዜጠኞችና ጦማሪያኑን የሚዳኙት የመሐል ዳኛ በራሳቸው ፈቃድ ከችሎቱ ራሳቸውን አገለሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

የትግራይ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ፓሊስን በኢትዮጵያዊያን ለማስጠላት የሚደረገው ጥረት ከሽፏል!

$
0
0

pg7-logoህወሓት ንፁሀንን ለመደብደብ የሚያበቃ በቂ ክፋት ያለው ልዩ ጦር ሲያሰለጥን ቆይቷል። ይህን ልዩ ጦር የፓሊስን መለያ እያለበሰ ነውረኛ ሥራዎችን እንዲሠራ በማድረግ በአንድ በኩል ንፁሀንን የመጉዳት በሌላ በኩል ደግሞ ፓሊስን በሕዝብ የማስጠላት መንታ ግቦችን ለማሳካት ተጠቅሞበታል። ይህ ልዩ ጦር በአለፉት ጥቂት ሳምንታት ባዶ እጃቸው ለተቃውሞ በወጡ ነብሰ ጡር ሴቶች ላይ ሳይቀር ባሳየው ጭካኔ፣ በሰማያዊ እና በአንድነት ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎች ላይ ባደረሰው ድብደባ መጠን እና ባካሄደው የግለሰብ ንብረቶች ዝርፊያ የሥርዓቱ ባህርይ ፈጽሞ ከሰውኛ ተፈጥሮ እየወጣ እንደሆነ አመላካች ነው። በእነዚህ ድብደባዎች ወቅት በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት በማድረግ ከፍተኛ ጉዳት እንዲደርስባቸው ተደርጓል። በትግራይ ተወላጆች ላይ የተለየ ትኩረት የተደረገው በደብዳቢዎቹ የግል ውሳኔ ሳይሆን ከበላዮቻቸው በተሰጠ ትዕዛዝ ነው ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ ያምናል።

በአርበኞች ግንቦት 7: እምነት መሠረት የፓሊስ ከፍተኛ አዛዦች ህወሓቶች ቢሆኑም አብዛኛው የሠራዊቱ አባል በህወሓት ዘረኛና ፋሽስታዊ አገዛዝ የተማረረ፤ የሥርዓቱ መለወጥ የሚፈልግና ሥርዓቱን ለመለወጥ የሚደረገውን ትግል የሚደግፍ ኃይል ነው። ስለሆነም ህወሓት የተለየ ጦር አሰልጥኖ የፓሊስ ልብስ በማልበስ ነውረኛ ወንጀል በማሠራት ፓሊስን ለማስጠላት የሚያደርገው ሴራ ሊጋለጥ ይገባል ብሎ ያምናል። የፓሊስ ሠራዊት አባላትም በስማቸውና በደንብ ልብሳቸው የሚደረገውን ደባ ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ እንዲያጋልጡ አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።

ህወሓት እንደሚያስበው እና የኢትዮጵያም ሕዝብ እውነት አድርጎ እንዲቀበለው እንደሚፈልገው የትግራይ ሕዝብ በጅምላ የህወሓት አፍቃሪና ደጋፊ አይደለም። እንዲያውም በተፃፃሪው ህወሓት ከትግራይ ተወላጆች ልብ እየተነቀነ ነው። የትግራይ ሕዝብ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ትሕዴን/ደምህት) ከትግራይ የበቀለ፤ ህወሓትን በአመጽ ለመፋለም የቆረጠ ኃይል ነው። አርበኞች ግንቦት 7 በትግራይ ውስጥ ብዙ ደጋፊዎች ያሉት መሆኑ የምናውቀው ሀቅ ነው። አረና ትግራይ ህወሓትን በሰላማዊ መንገድ ለመታገል የተነሳ ተሰሚነቱን በከፍተኛ ደረጃ እያደገ የመጣ እና አቶ አብርሀ ደስታን የመሰለ ወጣት ኢትዮጵያዊ የፓለቲካ መሪ ያወጣ ድርጅት ነው። ህወሓት አንድነት ፓርቲ ላይ የመረረ አቋም ከወሰደባቸው ምክንያቶች አንዱ በትግራይ ውስጥ ያለው ተቀባይነት በከፍተኛ ፍጥነት እየጨመረ መምጣቱ ነው። ህወሓት የትግራይን ሕዝብ ከተቀረው የኢትዮጵያ ሕዝብ በጅምላ ለማጣላት የሚያደርገው ጥረት ማክሸፍ ይኖርብናል ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 ያምናል፤ ለዚህም ተግቶ ይሠራል። አርበኞች ግንቦት 7 ከትግራይ የዲሞክራሲ ኃይሎች ጋር በመተባበር ፀረ ህወሓት ትግል በትግራይ ውስጥ መቀጣጠል ይኖርበታል ብሎ ያምናል። በዚህም መሠረት ትግራይ የህወሓት መቀበሪያ የመሆኗ ጊዜ ሩቅ አይደለም።

በዘንድሮው የ2007 የሴራ ምርጫ አማካይነት ተድበስብሰው የመጡ እነዚህ ሁለት ክፋቶች ማለትም ፓሊስን በሕዝብ ማስጠላት እና የትግራይ ተወላጅ የሆኑ የዲሞክራሲ ወገንተኞችን ለይቶ ማጥቃት ከበስተጀርባቸው ያዘሉት እኩይ ዓላማ መጋለጡ መንገዳችን ያጠራልናል ብሎ አርበኞች ግንቦት 7 በጽኑ ያምናል። በአንድነትና በመኢአድ የተፈፀው የድርጅትና የንብረት ዘረፋም የዚሁ ፕሮጀክት አካል መሆኝ ግልጽ ነው፤ ነገ ተመሳሳይ ነገር በሰማያዊ ፓርቲም ላይ ይፈጽም ይሆናል።

በመሆኑ ከ2007 የሴራ ምርጫ ትሩፋቶች በትግራይ ሕዝብና በፓሊስ ሠራዊት ጀርባ የሚደረገው ደባ መጋለጡ ነው። ይህ ድል ጽኑ መሠረት እንዲይዝ ህወሓትንና የትግራይን ሕዝብ የመነጠል እና ፓሊስ የሕዝብ አጋር መሆኑን የማረጋገጥ ሥራዎችን አጠናክረን መሥራት እንዳለብን አርበኞች ግንቦት 7 ያሳስባል።

ድል ለኢትዮጵያ ሕዝብ !

The post የትግራይ ሕዝብንና የኢትዮጵያ ፓሊስን በኢትዮጵያዊያን ለማስጠላት የሚደረገው ጥረት ከሽፏል! appeared first on Zehabesha Amharic.

በአማራና ትግራይ ድንበር የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት የተጠራው ስብሰባ ተበተነ

$
0
0

10847516_869729569744011_6150249400860109437_oጥር ፳፰(ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራና በትግራይ ክልል ድንበሮች አካባቢ የተነሳውን ችግር ለመፍታት ከፌደራል መንግስት ፣ ከትግራይና ከአማራ ክልል የተውጣጡ ከፍተኛ ባለስልጣኖች ጥር 26 ቀን 2007 ዓም ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ 300 ነዋሪዎችን ሰብስበው ያነጋገሩ ቢሆንም፣ መግባባት ሳይቻል በመቅረቱ ለየካቲት 4 በድጋሜ መቀጠሩን የአካባቢው ምንጮች ገልጸዋል።የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር ሽፈራው ተክለማርያም፣ የአማራ ክልል ፕ/ት ገዱ አንዳርጋቸው፣ የትግራይ ክልል ፕ/ት አባይ ወልዱ፣ ቴዎድሮስ ሃጎስ፣ የሰሜን ምእራብ እዝ አዛዥ ሌ/ጄ ብርሃኑ ጁላ፣ የመከላከያ ዘመቻ ሃላፊ ሜ/ጄኔራል ገብረእግዚአብሄር መብራቱ እና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣኖች በስብሰባው ላይ ተገኝተዋል።
በመጀመሪያው ቀን ስምምነት ባለመደረሱ በማግስቱ ከሁለቱም ክልሎች የተውጣጡ 30 ነዋሪዎች ከባለስልጣናቱ ጋር ተሰብስበው የነበረ ቢሆንም፣ አሁንም ሳይሳሙ በመቅረታቸው ለየካቲት አራት ቀጠሮ ይዘው ተለያይተዋል። በአማራ ክልል በኩል የሚኖሩ ነዋሪዎች የትግራይና የአማራ ክልሎች ድንበር ተከዜ ሆኖ እያለ ፣ ክልሉ ከዚህ ቀደም በጉልበት ከተከዜ በመሻገር ሁመራ እና ዳንሻ የመሳሰሉ ቦታዎችን መቆጣጠሩንና አሁን ደግሞ እስከመተማ ያለውን ቦታ በመያዝ ሰሜን ጎንደርን በግማሽ ለማጠቃለል ያስባል በማለት የክልሉን የመስፋፋት ፖሊሲ ተቃውመዋል።

በትግራይ ባለስልጣናት በኩል ደግሞ የክልሉ ድንበር እስከመተማ ይደርሳል የሚል አቋም የተንጸባረቀ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች የያዙት አቋም የትግራይ ክልል ባለስልጣናትን አበሳጭቷል።

በአካባቢው ከፍተኛ ቁጥር ያለው የሰራዊት አባላትና የፌደራል ፖሊሶች የተሰማሩ ሲሆን፣ ህዝቡን ያስተባብራሉ የተባሉ የአካባቢው መሪዎች እየተለቀሙ በመታሰር ላይ ናቸው።በአካባቢው ያለው ውጥረት በቀላሉ አይበርድም የሚሉት ነዋሪዎች፣ ችግሩ ቶሎ ካልተፈታ ወደ ግጭት ሊያመራ ይችላል በማለት ያስጠነቅቃሉ።

በቋንቋና ዘር ላይ የተመሰረተ የፌደራል ስርዓት ከተመሰረተ ጊዜ አንስቶ በክልሎች መካከል የሚታየው የድንበር ውዝግብ እየጨመረ በመሄድ ላይ ነው።በኦሮምያና በሶማሊ፣ በኦሮምያና በደቡብ፣ በአፋርና በአማራ፣ በአማራና በትግራይ፣ በደቡብና በጋንቤላ፣ በትግራይና አፋር እንዲሁም በሶማሊና በአፋር ባልተፈቱ የድንበር ግጭቶች በርካታ ዜጎች አልቀዋል።

Source:: Ethsat

The post በአማራና ትግራይ ድንበር የተነሳውን ውዝግብ ለመፍታት የተጠራው ስብሰባ ተበተነ appeared first on Zehabesha Amharic.

ህወሓት ከወሎ ተጨማሪ መሬት ወደ ትግራይ ለመከለል ዝግጅት ላይ ነው

$
0
0

ናትናኤል መኮንን

740px-Afar_in_Ethiopia.svgከተመሰረተ 40 አመት ሊያስቆጥር ቀናት የቀረውና አሁንም በገንጣይነት ተግባሩ የቀጠለው ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ ከወሎ ተጨማሪ መሬት ለመከለል ዝግጅት ላይ መሆኑ ታወቀ፡፡ ለደሴ ሆስፒታል ባዛር በተደረገበት ወቅት ህወሓት አገር ውስጥና በውጭ የሚገኙ የትግራይ ተወላጅ ባለሀብቶች በባዛሩ እንዲገኙ ያደረገ ሲሆን በወቅቱም ወሎ ውስጥ ሰፊ መሬት እንዲሰጣቸው አድርጓል፡፡ በተለይም ከቆቦ ወደ ወልደያ በኩል 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው አላውሃ የተባለ ቦታ ላይ በርካታ የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ደጋፊና አባል ባለሀብቶች መሬት ተሰጥቷቸዋል፡፡ ውስጥ ለውስጥም ‹‹የትግራይ ድንበር አላውሃ ምላሽ ነው›› በሚል እያስወራ እንደሚገኝ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡አላውሃን ጨምሮ ሌሎች የትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ የወሎ መሬቶች ላይ አርሶ አደሮቹን እያፈናቀሉ ለህወሓት ደጋፊና አባል ባለሀብቶች መሬት ለመስጠት ሰፊ እቅድ እንደተያዘና በሂደት በአካባቢው በርከት ያሉ ትግርኛ ተናጋሪዎች እንዲኖሩ በማድረግ ቦታውን ወደ ትግራይ ለመከለል ሴራ እየተሸረበእንደሚገኝ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል፡፡የቆቦና ሌሎች የትግራይ ድንበር አካባቢ የሚገኙ የወሎ መሬቶች ላይ በርካታ የትግራይ ተወላጆች ተሰጥተው የአካባቢው ተወላጆቹ መሬት አልባ መሆናቸው ይታወቃል፡፡ ይህም ተከትሎ ሰሞኑን ወሎ ውስጥ ተጨማሪ መሬቶች ወደ ትግራይ ሊከለሉ ነው በሚል ህዝቡ ውስጥ ከፍተኛ ውጥረት ተፈጥሯል፡፡ ህወሓት ስልጣን ከያዘ ጀምሮ የጎንደርና የወሎ መሬቶችን ወደ ትግራይ መከለሉ የሚታወቅ ሲሆን በቅርቡ በስፋት የጀመረው መሬትን ለትግራይ ባለሀብቶች የመስጠት እቅድም ወደፊትም ሰፋፊ መሬቶችን ወደ ትግራይ ሊከልል እንደሚችል አመላክቷል፡፡

The post ህወሓት ከወሎ ተጨማሪ መሬት ወደ ትግራይ ለመከለል ዝግጅት ላይ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዲስ አበባ ጉዶች: በማሳጅ ስም የወሲብ ገበያ ደርቷል * ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም ‹ማግኔት› በሚል በውጭ ሚድያዎች መጠራት ጀምራለች (ልዩ ዘገባ)

$
0
0

መነሻ
በቅርቡ ማክቤዝ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ኤች አይ ቪ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ(መታሻ) ቤቶች መስፋፋት በወጣቶችና በሴቶች ላይ የሚያስከትሏቸው አሉታዊ ተፅዕኖዎች በሚል ርዕስ አንድ ጥናት አሰርቶ ነበር፡፡ ወሲብና ወሲባዊ ተግባራት የሚፈፀምባቸውን ማሳጅ ቤቶች በተመለከተ bማህበራዊ ስነልቦና ባለሙያዎቹ አቶ በላይነህ ዘለለውና አቶ ዮሴፍ አህመድ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው በአዲስ አበባ ከተማ በተለይም ቦሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ የሚገኙ መታሻ (ማሳጅ) ቤቶች ውስጥ ህገ ወጥ የሆኑ ማሳጅ ቤቶች በአሳሳቢ ደረጃ ተስፋፍተዋል፡፡ ማሳጅ ቤቶች ለወሲብ ቱሪዝም መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
ethiopia massage
እንደሚታወቀው አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የተለያዩ ሃገራት ዲፕሎማቶችና የውጭ ሃገር ድርጅት ሰራተኞች በብዛት ይኖራሉ፡፡ ትላልቅ አህጉር አቀፍና ዓለም አቀፍ ስብሰባዎችና ጉባኤዎች በተደጋጋሚ ይደረጋሉ፡፡ በነዚህ ጉባኤዎች ላይ ለመሳተፍ የሚመጡ የባህር ማዶ ሰዎች በአብዛኛው ጊዜ አዳራቸውን የሚያደርጉት በህገወጥ ማሳጅ ቤቶችና በትላልቅ ሆቴሎች ውሰጥ በግዥ ከሚቀርቡላቸው ሴተኛ አዳሪዎች ጋር አንዳንዴም በደላሎች አማካኝነት ከሚቀርቡላቸው የቤት ልጆች ጋር እንደሆነ ይነገራል፡፡ በዚህ ሂደት በገንዘብ ተጠቃሚ የሚሆኑ በርካታ ሰዎች አሉ፡ ፡ በወጣት ሴቶች ስነልቦና እና ስነተዋልዶ ጤና እንዲሁም በማህበረሰቡ ግብረገባዊ አስተሳሰብ ላይ የሚነግዱ፣ ኢ – ሞራላዊና ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ገንዘብ የሚሰበስቡ ማሳጅ ቤቶች ድርጊት በጣም አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ይላል ጥናቱ፡፡ ይሁንና ችግሩን ለመፍታት የተደረጉ እንቅስቃሴዎች የሉም ወይም አነስተኛ ናቸው፡ ፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ ጥናቱን ጨምቆ በማቅረብ የጉዳዩን አሳሳቢነት በማሳየት የሚመለከታቸው አካላት በፍጥነት ወደተግባራዊ እርምጃ እንዲገቡ ግፊት ማድረግም ነው፡፡

16ኛው “ዓለም አቀፍ የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ እና የአባላዘር በሽታዎች ጉባኤ በአፍሪካ” (16th International Conference on AIDS and STLs in Africa – ICASA) ከሦስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ እንደተስተናገደ ይታወሳል፡፡ከዚያ ቀደም ብሎ ብዙ ኢትዮጵያውያንን ያስደነገጠና ያወዛገበ አንድ ስብሰባ ሊደረግ ታስቦ ነበር፡፡ “የአፍሪካ ግብረ ሰዶማውያን የቅድመ ኮንፈረንስ ማነቃቂያ ስብሰባ” የተባለው ይህ ስብሰባ በተለይ በሃይማኖት ተቋማት ከፍተኛ ውግዘት ገጥሞት ነበር፡፡ በማህበራዊ ድረ ገጾችና በተለያዩ የሃገር ውስጥ ጋዜጦችና መጽሔቶች (ቁም ነገር መጽሔትን ጨምሮ) ብዙ ፅሁፎች በጉዳዩ ዙሪያ ወጥተው ነበር፡ ፡ ለግብረ ሰዶማውያን መስፋፋትና የወሲብ ቱሪዝም እየጨመረ እንዲመጣ ከሚያደርጉ አባባሽ ነገሮች አንዱ የህገ ወጥ ማሳጅ ቤቶች መኖር ነው፡፡ እንደ ታይላንድ ያሉ ሃገራት ለዚህ ምሳሌ መሆን ይችላሉ፡፡

የወሲብ ቱሪዝም ‹ማግኔት›

በቅርቡ በወጣ አንድ ዓለም አቀፍ ሪፖርት ላይ ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም እየተስፋፋባቸው ከመጡ ሃገራት አንዷ መሆኗን ‹‹Ethiopia has become a magnet for sex tourism›› (ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም ማግኔት እየሆነች ነው) በማለት ይገልጻታል፡፡ ዓለም አቀፍና አህጉር አቀፍ ጉባኤዎችንና ስብሰባዎችን ማስተናገዷ እያስገኘላት ከሚገኘው ኢኮኖሚያዊ ገቢ በተጻራሪ ለማህበራዊ ችግሮች እየዳረጋት መሆኑ ተጠቁሟል፡፡ ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ የውጭ ሃገር ጎብኝዎችና የጉባኤ ተሳታፊዎች ለመጤ ባህሎች እያጋለጧት ነው፡፡ በመጠጥ ቤቶችና በተለያዩ የአዲስ አበባ ጎዳናዎች የሚዘወተረው ወሲባዊ ንግድ ወደ መኖሪያ ቤቶችም ገብቷል፡፡ በተለይ የእንግዳ ማረፊያ ተብለው የተዘጋጁ አንዳንድ ቤቶች ለህገ ወጥ ማሳጅ ቤቶችና ለወሲብ ንግድ መፈጸሚያነት እየዋሉ ነው፡፡

እንደ ተባበሩት መንግስታት የዓለም የቱሪዝም ድርጅት (UNWTO) ‹‹ የቱሪዝምን ቅርጽ እና መረብ በመጠቀም በማንኛውም የወሲብ ነክ እንቅስቃሴ ላይ ለመሳተፍ የሚደረግ ጉዞ ›› የወሲብ ቱሪዝም ወይም ዘመናዊ የወሲብ ንግድ ነው ሲል ይገልጻል፡፡
በዓለማችን ከቅርብ አሥርት ዓመታት ወዲህ የወሲብ ቱሪዝምን ህጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖረው በማድረግ ለሃገሪቱ እንዲሁም ለዘርፉ ተዋንያን ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ሊያመጣ በሚችል መልኩ እየተጠቀሙበት ይገኛሉ፡፡
ከእነዚህ ሃገራት ውስጥ ጀርመን፣ ብራዚል ፣ሞሮኮ፣ ዶሚኒካን ሪፐብሊክ እንዲሁም በምርጥ የእግር ኳሰኞቿ የምናውቃት ኔዘርላንድስ ከአጠቃላይ የሃገራቸው ኢኮኖሚ ከ ሁለት እስከ አምስት በመቶ የሚሆነውን ከዚሁ ዘርፍ ይሸፍኑበታል፡፡
ይህ ዘርፍ በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ በርከት ያሉ አገልግሎት ሰጪዎችን የሚያቅፍ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ አየር መንገዶች፣ሆቴሎች የየብስ ትራንስፖርት ተቋማት የመሳሰሉት ተጠቃሽ ናቸው፡ ፡
ከዚህ በተጨማሪ እነዚሁ ሃገራት በድርጊቱ ለሚሳተፉት ሴት ዜጎቻቸው የማህበራዊ ዋስትናን እስከ ጡረታ ድረስ በመስጠታቸው ድርጊቱ የሚያስከትለው ማህበራዊ ቀውስ ዝቅተኛ ቢሆንም ሞራላዊ ተጠያቂነቱ ግን ከፍ ያለ ነው፡፡

በሃገራችን በተለይም በመዲናችን እና በተለያዩ የቱሪስት መናኸሪያ በሆኑ አካባቢዎች ከራቁት ጭፈራ ቤቶች የጀመረው ይህ የዘመናዊ የወሲብ ንግድ (የወሲብ ቱሪዝም) በአሁኑ ሠዓት በርከት ያሉ የወሲብ ንግድ ተቋማትን፣ ሰፊ የድርጊቱ መረብ፣ እሳት የላሱ ደላሎችን እንዲሁም ሰፋ ያለ ካፒታል የሚያንቀሳቅስ እና ወደ ኢንዱስትሪ ደረጃ ሊሸጋገር የደረሰ ተግባር ሆኗል፡፡ በተለይም የሃገራችን የዲፕሎማሲ እንቅስቃሴ እየተጠናከረ በመጣበት በአሁኑ ወቅት እየጨመረ ያለውን የወጭ ሃገራት ዜጎችን ፍሰት ተከትሎ ዘርፉ ጠንከር ወደማለት እና የአደባባይ ሚስጥር በሚባለው ደረጃ ላይ ለመድረስ ችሏል፡፡

እነዚህ የወሲብ ንግድ ማዕከላት በዘርፉ ተዋንያን እና ቅርበት ባላቸው ወገኖች ዘንድ ‹‹ፍርድ ቤት ›› በመባል የሚታወቁ ሲሆን የድርጊቱ ተሳታፊ ሴቶች ደግሞ ከፈረንሳይኛ ቃል በተወረሰ ነገር ግን ከድርጊቱ ጋር ምንም ተዛምዶ በሌለው ‹‹ትራባዪ›› በሚል ስያሜ ይታወቃሉ፡፡

እነዚህን ‹‹ፍርድ ቤቶች›› እና ‹‹ትራባዪዎች›› ከውጭ ሃገራት ዜጎች ጋር በማገናኘት ረገድ የአንበሳውን ሚና የሚጫወቱት ደላሎች በተለምዶ ‹‹ጋይድ››የሚባሉ ሲሆን የትራባዪዎች (የወሲብ ንግድ ተሳታፊ ሴቶች) ማደሪያ እና መዋያ ቦታ የወሲብ ንግድ ማዕከላቱ ‹‹ፍርድ ቤቶቹ›› ናቸው፡፡
አንድ ፍርድ ቤት በውስጡ ከ 15-20 ለሚሆኑ ‹‹ትራባዪዎች›› ደንበኞቻቸው እስኪመጡ የሚገለገሉበት የማደሪያ አልጋ እና ሌሎች ቁሳቁሶችን የሚያሟሉ ሲሆን ለሚጎበኟቸው የውጭ ሃገራት ዜጎችም በውድ ዋጋ የሚሸጡ መጠጦችን ለሽያጭ ያቀርባል፡፡

አንድ የውጭ ሃገር የወሲብ ደምበኛ የመረጣትን ‹‹ትራባዪ›› ከፍርድ ቤቱ ለአንድ አዳር ወይም ውሎ ይዞ ለመውጣት ከአንድ ሺህ እስከ አምስት ሺህ ብር የሚከፍል ሲሆን እንደየ ፍርድቤቱ ህግ ደግሞ ተጨማሪ የመውጫ የኮቴ የመሳሰሉትን ክፍያ መክፈል ይጠበቅበታል ፡፡
ለአንድ አዳር ወይም ውሎ የተስማማች አንድ ‹‹ትራባዪ›› ሊከፈላት ከተስማማችው የብር መጠን ውስጥ ከ50-70 በመቶ የሚሆነው በወሲብ ተቋሙ ባለቤት እና በደላሎች የሚወሰድ ነው፡፡
እነዚህ የወሲብ ንግድ ተቋማት በአብዛኛው በትላልቅ ቪላ ቤቶች የሚገኙ ሲሆን በተለይም ከቦሌ ድልድይ እስከ ደምበል፣ በሃያ ሁለት ፣ሲኤምሲ፣ መስቀል ፍላወር እንዲሁም የቱሪስት እንቅስቃሴ በሚበዛባቸው አካባቢዎች ተበራክተው ይገኛሉ፡፡

ይህ የወሲብ ቱሪዝም ወይም የወሲብ ንግድ ከወሲብ ንግድ ተቋማቱ ባለፈ መሸታ ቤቶችን፣የጫት ማስቃሚያ ቤቶችን ፣ የእንግዳ ማረፊያዎችን እንዲሁም ሌሎች መሰል ተቋማትን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እንደማስተሳሰሩ መጠን የሚያዘዋውረው የገንዘብ መጠን ከፍተኛ ቢሆንም ከዚህ ዘርፍ መንግሥትም ሆነ የድርጊቱ ተሳታፊ ሴት እህቶቻችን የሚያገኙት ጥቅም ዘላቂነት ያለው እና ቀጥተኛ ባለመሆኑ በህብረተሰቡ ላይ የሚፈጥረው ማህበራዊ ቀውስ ከፍተኛ ነው፡፡

ምንም እኳን ይህ ተግባር በኢትዮጵያ ህጎች የተከለከለ ቢሆንም ድርጊቱን ከመቆጣጠር አኳያ የመንግሥት ጥረት ዝቅተኛ የሚባል ነው፡፡ለዚህም በከተማችን በርክተው የሚገኙት እነዚህ የወሲብ ንግድ ተቋማት ምስክሮች ናቸው፡፡

በዚሁ በወሲብ ንግድ ላይ በሁለት ጎራ የተከፈሉ አስተያየት ሰጪዎች የሚደመጡ ሲሆን በአንደኛው ወገን ድርጊቱ የሃገሪቱን መልካም ስም እና የማህበረሰቡን ሞራል የሚነካ በመሆኑ የቱንም ያህል ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ቢያመጣ ሊወገዝ እና ቁጥጥር ሊደረግበት የሚገባ ተግባር ነው ሲሉ የሚሞግቱ አሉ፡፡ በሌላኛው ጎራ ይህን ተግባር ማስቆም ለሚጠይቀው ቁርጠኝነት ከፍተኛ ትኩረት መስጠት አሊያም ድርጊቱ ይፋዊ በሆነ መንገድ ተፈቅዶ ከድርጊቱ ተዋንያን ከግብር እና ከሌሎች የአገልግሎት ክፍያዎችን በመሰብሰብ የሚገኘውን ገቢ በመጠቀም ድርጊቱ የሚፈጥረውን ማህበራዊ ቀውስ መቀነስ ተገቢ ነው ባዮች ናቸው፡፡

የማሳጅ ታሪካዊ
ዳራ

የማሳጅ ታሪካዊ አመጣጥ በብዙ ሀገሮች የብዙ ሺህ ታሪክ ያስቆጠረ ነው፡፡ በጥንታዊ ጽሑፎች ላይ ተጽፎ እንደሚታየው በምስራቃዊያንና በምዕራባዊያን ስልጣኔ ሰዎችን ለመፈወስና ለማሻል ሰዎችን በመንካት/በማሸት/ እንደሚያደርጉ ታሪካዊ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ አብዛኛውን በአሁኑ ሠዓት የምንጠቀመው የማሳጅ ዘዴዎችና አቀራረቦች አጀማመራቸው ከጥንቱ የማሳጅ ዘዴዎች ነው፡፡በጥንት ጊዜም ቢሆን ማሳጅን የሰዎችን ህመም ለማሻል፣አደጋን ለማሻል(ጉዳቱን ለመቀነስ)፣ሰዎችን ሰውነታችውንና አዕምሮአቸውን ዘና ለማድረግ(ለማዝናናት) እንዲሁም ህመምን ለመከላከልና ለማዳን ሲጠቀሙበት ነበረ፡፡

በምስራቁ ዓለም የማሳጅ ታሪክ እንደሚያሳየው ማሳጅ እንደ መለኮታዊ ተዓምር/ Divinely- created system/ ተደርጎ የሚታይበት ሁኔታ ነበር፡፡በህንድ ሀገር ማሳጅን አይሩቨዳ / Ayurveda/ ብለው ይጠሩት የነበረ ሲሆን፣ይህም ህዝብ ይተገብርበት/ይገለገልበት የነበረው ከ3000 ዓ.ዓ ቀደም ብሎ እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እንዲሁም በተለያዩ አካባቢዎችና ቦታዎች እንዲሁም በደቡብ ምስራቅ ኢሲያ ሀገራትም ተስፋፋተው እንደነበር የታሪክ ድርሳናት ያሳያሉው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ የማሳጅ ህክምና በጥንታዊት ቻይና የረዥም ዓመት ታሪክ ያለው ነው፡፡ይህም የህክምና አይነት ከ2700 ዓ.ዓ አካባቢ ተግባራዊ ይደረግ እንደነበረ የታሪክ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ጥንታዊ ቻይናዊያን ማሳጅን ለህክምና አገልግሎትና ራስን ለማዝናናት ይጠቀሙበት ነበር፡፡

ወደ አህጉራችን አፍሪካ ስንመጣም ይህ የማሳጅ ህክምና አይነት በተለያዩ ሀገሮች ተግባራዊ መሆን ከጀመረ በሺ የሚቆጠሩ ዓመታት አስቆጥሯል፡ ፡ለምሳሌ በጥንታዊ ግብጽ የእራሳቸው የሆነ የማሳጅ አይነት ይጠቀሙ እንደነበር በፖፒረስ ላይ ተመዝግቦ ይገኛል፡፡የተለያዩ ተመራማሪዎች እንደሚገምቱት ሪፈሎኤሶሎጂክ/Reflexology/ የሚባለው ማሳጅ አይነት በግብጽ በ2500 ዓ.ዓ አካባቢ እንደተጀመረ ይገመታል፡፡ይህን የማሳጅ አይነት የተወሰነ የሰውነት ክፍልን ብቻ የማሻል ስራ ላይ ያተኩራል፡፡(በሀገራችን ወጌሻ ጋር እንደምንሄደው)
በተለያዩ ጊዜያት እንደሚታየው ማሳጅ የተለያዩ ጠቀሜታዎች እንዳለው ቢታወቅም ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየወደቀ እየተነሳ የቆየበት ሁኔታ ስለነበረ አንዳንድ ባለሙያዎች በተለይም ከጥቂት መቶ ዓመታቶች በፊት ጠቀሜታው ወሳኝ እንደሆነ በመረዳት በ1600 ዓ.ም አከባቢ በምዕራባዊያን የህክምና ባለሙያዎች ድጋሚ ጠቀሜታውን በመገንዘብ ለአገልግሎት እንደ ገና ማዋል ተጀመረ፡ ፡ሆኖም ግን እስከ 19ኛው ክፍለ ዘመን ድረስ ማሳጅ ከፍተኛ እውቅና በማግኘት በብዛት ጥቅም ላይ መዋል ጀመረ፡፡

አዲሱ ጥናት

በቅርቡ ማክቤዝ ሚዲያ ኮሚኒኬሽን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርና ኤች አይ ቪ መቆጣጠሪያና መከላከያ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ጋር በመተባበር ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰራው ጥናት ዋና ዓላማ ‹በሀገራችን መዲና በሆነችው አዲስ አበባ መጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች በተለይም የተለየ ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው መታሻ/Massage parlor/ ማረፊያ ማሳጅ ቤቶች መስፋፋት እያስከተለ ያለውን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፤የስነተዋልዶ ጤና እና ስነልቦናዊ ተፅዕኖዎች እና ቀውሶች በሚመለከት ለችግሩ መነሻ ፣ አባባሽ ምክንያቶች እና የምክረ ሀሳብ/ የመፍትሄ ሃሳቦችን ማቅረብ እንደሆነ› ይገልፃል፡፡
መጤ ባህልና ልማዳዊ ድርጊቶች በወጣቶችና ሴቶች ላይ የሚያደርሷቸው ተጽዕኖዎች በርካታ
መሆናቸውን የሚጠቅሰው ጥናቱ በአፍሪካ ሀገራትም መጤ ባህል በአምራች ትውልዱ ላይ አሉታዊ ተጽኖ እያሳደረው እንደሆነ እንደ አብነትም ለምሳሌ፡ -በግብጽ ፤በሊቢያ(ከጎረቤት ሀገር)፤በሞሮኮ(ወንደኛ አዳሪነት..)፤በኬፕ ቬርዴ(የወሲብ ቱርዝም)እንዲሁም በናይጄሪያ(በፍተኛ ወሲብ ንግድ የሚተዳደሩ ሴቶችን ወደ ሌሎች ሀገሮች በመላክ የቀዳሚውን ድርሻ ከያዙት ሀገራት ውስጥ እንደሆኑ ያብራራል፡፡

ጥናቱ ጉዳዩ ከሚመለከታቸው የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፤ ማለትም ከማሳጅ ማሰልጠኛ ተቋማት፣፤ ከማሳጅ ቤት ተጠቃሚዎች ፤ ከማሳጅ ቤት ሰራተኞች ጋር በርእሱ ዙሪያ ቃለ መጠይቅ በማድረግ የተሰራ ሲሆን ከዚህ `በተጨማሪም በአሳታፊ የአካል ምልከታ ማሳጅ ቤቶችን በመቃኘት መረጃዎች ተሰብስበዋል ይላል ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ አስር ክፍለ ከተማዎች የሚገኙ ሲሆን ከነዚህ ክፍለ ከተማዎች ማሳጅ የሚከናወንባቸው ቦሌ187 ፣ጉለሌ 5 ፣የካ 20፣ አዲስ ከተማ 9 ፣አቃቂ ቃሊቲ 0 ፣ቂርቆስ 77 ፣አራዳ 10 ፣ንፋስ ስልክ 30 ፣ልደታ 3፣ ኮልፌ 8 ሲሆኑ በጠቅላላው 349 (ሶስት መቶ አርባ ዘጠኝ ) ማሳጅ ቤቶች ከአዲስ አበባ ከንግድ እና ኢንዱስትሪ ቢሮ ፈቃድ አግኝተው በመስራት ላይ እንደሆኑ ጥናቱ ያመለክታል ፡፡ አብዛኛዎቹ የሚገኙትም ቦሌ አካካቢ በመሆኑ ቦሌ ክ/ከተማ ውስጥ ከሚገኙ 187 ማሳጅ ቤቶች ውስጥ 35 የሚሆኑ ማሳጅ ቤቶችን በመምረጥ ጥናቱ ተካሂዷል፡፡ የማሳጅ አገልግሎቱ የሚሰጥባቸውም ትላልቅ ህንፃዎች፣ ሰፋ ያለ ግቢ ያላቸው ቤቶች፣ አፓርታማዎችና በከተማዋ ዋና ዋና አካባቢዎች በሚገኙ ፎቆች ላይ የሚገኙ ቤቶች መሆናቸው ተረጋግጧል፡፡ ከእነዚህ ማሳጅ ቤቶች መካከል አብዛኞቹ ወደ ህገወጥ ተግባራት እየገቡ ሲሆን ጥናቱ እንደሚለው ለህገወጥ ማሳጅ ቤቶቹ መስፋፋት ተከታዮቹ ምክንያቶች በዋናነት ይነሳሉ፡-

– ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ለባለቤቱና ወሲባዊ ንግድ ለሚትፈጽሙ ሴቶች ከፍተኛ ገንዘብ ስለሚያስገኝላቸው፣
– ተገልጋዮቹ የተሻለ ነጻነት እንዲሰማቸው ስለሚያደርግ፣
– ወሲባዊ ንግድ የሚፈጽሙ ሴቶች በሆቴልና በጎዳና ላይ ከሚያደርጉት ወሲባዊ ንግድ የማሳጅ ቤቱ በተሻለ ደህንነታቸው እንዲጠበቅ ስለሚያደርግላቸው፣
– ደላሎች ከዚህ ስራ የተሻለ ገንዘብ እያገኙበት ስለሆነ ስራውን እንዲስፋፋ አድርጎታል፣
– ወሲባዊ ማሳጅ ቤቶች ተጠቃሚ የማህበረሰብ ክፍል እየጨመረ መምጣቱና ሌሎችም ምክንያቶች እንዳሉት ጥናቱ ደርሶበታል፡፡

ከገቢ አንፃርም በእነዚህ ማሳጅ ቤቶች ውስጥ መስራት ስለሚያስገኘው ገቢ በጥናቱ ውስጥ የተካተተ አንድ ሰራተኛ የሚከተለውን አስተያየት ሰጥቶ እናገኛለን፡፡ ‹በአሁኑ ሰዓት በመዲናችን ስትዟዟር በተለይም ደግሞ ቦሌ ክ/ከተማ ዞር ዞር እያልክ ብታይ ልክ እንደ ካፌ በየአካባቢው ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ተከፍተው ታገኛለህ፡፡ለዚህ ስራ በዋናነት ምክንያት የሚሆነው ደግሞ ለተጠቃሚው የሚሰጠው ተጨማሪ አገልግሎት (ወሲብ) ነው፡፡ለምሳሌ እኔ እሰራበት የነበረው ቤት ወደ ስድስት ማሳጅ የሚደረግባቸው ክፍሎች ነበሩት፡፡ከእነዚህ ክፍሎች ውስጥ ከምንሰራው ስድስት ወጣቶች ውስጥ እኔ ብቻ ነኝ ወንድ አምስቱ ሴቶች ናቸው፡፡እኛ ሁሌም ቀን ቀን ነው የምንሰራው፡፡ ማታ ፈረቃ የሚሰሩር በሙሉ ሴቶች ናቸው፡፡ እያንዳንዳችን በቀን ወደ 25 የሚጠጉ ደንበኞችን እናስተናግዳለን፡፡የማታ ፈረቃ ሰራተኞች ደግሞ ከ25 በላይ የሚሆን ሰው ያስተናግዳሉ፡፡በቀላሉ 50 ሰዎች ቢያስተናግዱ ለአንድ ሰው ዝቅተኛው ከ500 ብር እስከ 1200 ብር ያስከፍላሉ፡፡ በትንሹ 500 ብር ቢያስከፍሉ በአንድ ቀን 25,000 ብር ያገኛሉ ማለት ነው፤በወር ደግሞ 750,000 ብር ያገኛሉ፡፡ለሰራተኞችና ለአንዳንድ ወጪዎች 250,000 ብር ቢያወጡ ወደ 500,000 ብር ያገኛሉ፡፡በዚህም ምክንያት ማሳጅ ቤቶች እጅግ በፈጣን ሁኔታ እየተስፋፋ ይገኛሉ ፡፡›

እንደዚህ ያለው ስራ በአብዛኛው ሀገር እጅግ በጣም የሚያዋጣ የስራ ዘርፍ ነው፡፡ እንደ ታይላንድ ያሉ ሀገሮች በወሲብ ንግድ በዓመት ውስጥ ወደ 4.3 ቢሊየን ዶላር ያገኛሉ ከወሲብ ንግድ ብቻ፡ ፡ ይህም ብዙ ሰዎች በእንደዚህ አይነት ስራዎች ላይ እንዲሰማሩ ከሚያደርጓቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ እንደሆነ በጥናቱ ተጠቅሷል፡፡ በተመሳሳይ መልኩም በአሜሪካ በተደረገ አንድ ጥናት መሰረት ወሲባዊ ንግድ ወደሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች ስራ እንዲሰማሩ ምክንያት ከሆናቸው አንዱ ህጋዊ ማሳጅ ሲሰሩ የሚያገኙት ገንዘብ ዝቅተኛና ስራው አድካሚ ስለሆነ ወሲባዊ ንግድ ላይ ቢሰማሩ ግን በቀላሉ በዛ ያለ ገንዘብ ስለሚያገኙ ወደዚህ ስራ ይገባሉ ይላል ጥናቱ፡፡

የችግሩ ስፋት
በማህበራዊ ስነልቦና ባለሙያዎቹ አቶ በላይነህ ዘለለውና አቶ ዮሴፍ አህመድ የተደረገው ጥናት እንደሚያሳየው ወሲባዊ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች በሴቶችና በወጣቶች ላይ የማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ስነ-ልቦናዊ እና የስነ-ተዋልዶ ጤና ችግሮችን እንደሚያስከትሉ ያሳያል፡፡ በአንድ ማሳጅ ቤት ትሰራ የነበረች ወጣት ከስራው ጋር በተያያዘ ስለሚያጋጥማት ችግር ምንም አይነት ዋስትና እንደሌላት እንዲህ ስትል ታስረዳለች‹አገልግሎት ፈልጎ የሚመጣው ሰው በጣም የተለያየ ባህሪ ያለው ሰው ነው፡፡በዚህ ምክንያት ሁሉም የተለያየ ፍላጎት ስላለው፤አንዳንዱ ሰው ኮንዶም መጠቀም አይፈልግም፣ሌላው ደግሞ በፊንጢጣ የሚደረግ የግብረ ስጋ ግንኙነት ፈልጎ የሚመጣ አለ፡፡ ይህን ጊዜ ነው እንግዲህ ግጭት የሚፈጠረው፡ ፡ በተለይም ማታ የሚመጡት ወንዶች አብዛኛዎቹ መጠጥ ጠጥተው ስለሚመጡ የጠየቁትን ወሲብ አይነት እንቢ ካልኳቸው በጉልበት ሊፈጽሙብኝ ይሞክራሉ፤ አንዳንድ ከውጭ የመጡ ኢትዮጵያውያን (ዲያስፖራ) ወሲባዊ ፍላጎታቸው የሚረካው እኔን በማሰቃየት፣በመምታት፣በመንከስ ስለሆነ የተለያየ ጊዜ አደጋ ደርሶብኝ ያውቃል፡፡ ግን ይህንን ችግር ለማን ትናገረዋለህ ለባለቤቱ ብትነግረው ቢዝነሱ እንዳይበላሽበት ስለሚፈልግ ለፖሊስ እንድንናገር አይፈልግም እንዲሁም ደንበኞችን ላለማጣት ሲል ምንም እርምጃ አይወስድም፡፡እኔ ተጎድቼ ብቻ ነው የምቀረው ብናገር ሊያባረኝ ስለምችል ዝም ነው የምለው፡፡ ›

እነዚህ ሴቶች ምንም አይነት ጥቃት ቢደርስባቸው ለህግ አስከባሪ አካላት ሄደው አይናገሩም፤ ምክንያቱም የሚሰሩት ስራ በማህበረሰብ የተወገዘና እራሳቸው እራሱ የማያምኑበት ስለሆነ ጉዳት ደረሰብኝ ብለው ለፖሊስ ሪፖርት አያደርጉም፡ ፡ይህ ደግሞ በእነሱ ላይ የሚደርሰውን የሀይል ጥቃት መጠን ለማወቅ አስቸጋሪ ያደርገዋል፡፡የመፍትሄ እርምጃ እንዳይወሰድ ደብቆ ያስቀረዋል ከዚህም አልፎ በሴ ቶ ቹ ላይ የሚደርሰውን አካላዊና ስነ- ልቦናዊ ጉዳት ተገንዝቦ ለመፍታት የሚደረገው ጥረት ያስተጓጉለዋል› ይላል፡፡

ይህ የስነ-ልቦና ችግር በተለይም እንደ ኢትዮጵያ ያሉ ሀይማኖታዊና ወግ አጥባቂ ማህበረሰብ ባለበት እነዚህ ወጣቶችና ሴቶች ከፍተኛ ለሆነ ለስነ-ልቦና ችግር ይጋለጣሉ፡፡በዚህም ምክንያት ወደ ጫትና ሺሻ ቤቶች በመሄድ ሱስ አስያዥ ዕፅና አልኮል በመጠቀም ችግራቸውን ለመርሳት ይሞክራሉ፡፡
የመፍትሔ
እርምጃዎች

ጥናቱ የተለያዩ የመፍትሔ ርምጃዎችን በዝርዝር አስቀምጧል፡፡ ለማህበረሰቡ በቂ ግንዛቤ መፍጠር፣ ባለድርሻ አካላት በጋራ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው፣ የተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ለተከታዮቻቸው ግንዛቤ መፍጠር እንዳለባቸው፣ ባለሀብቱ ኢንቨስትመንቱን ሀገር በሚጠቅም ነገር ላይ እንዲያውለው ተከታታይነት ያለው ትምህርት መሰጠት እንዳለበት፣ህጋዊ ማሳጅ ቤቶችን ማበረታታና ሌሎችም የመፍትሄ ሀሳቦች ተጨምረዋል፡፡ ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው በመስራት እየተፈጠሩ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት የጋራ እቅድ በማውጣት መስራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊ፤ ስነ-ልቦናዊ የስነ ተዋልዶ ጤና ችግሮች ከወሲባዊ ንግድ ከሚካሄድባቸው ማሳጅ ቤቶች ጋር ያላቸው ትስስር ጠንካራና ቀጥተኛ መሆኑንና እነዚህ ችግሮች አምራች የሆኑትን ትውልዶች ለሀገራቸው ማበርከት የሚጠበቅባቸውን እንዳያበረክቱ እያደረጋቸው እንደሆነ ጥናቱ አሳይቶል፡፡ በስተመጨረሻም በመጤ ባህሎችና ልማዳዊ ድርጊቶች አሉታዊ ተፅዕኖ ምክንያት ላልተገቡ ባህሪያት እየተጋለጡ ያለውን ትውልድ ለመታደግ የተለያዩ እርምጃዎችን መወሰድ እንዳለበት ጥናቱ ጠቁሟል፡፡

የተለያዩ የሀይማኖት ተቋማት ሰለወሲባዊ ንግድ አስነዋሪነትና መጥፎ ገጽታዎች ለተከታዮቻቸው በማስተማር ወጣቶችና ሴቶች ከእንዲዚህ አይነት ተግባር እንዲቆጠብ ትምህርት ቢሰጡ፣ ባለሀብቱ ማህበረሰብን የሚጎዱ ተግባራት ላይ ኢንቨስት እንዳያደርግና ሴቶችንና ወጣቶችን ዘለቀታዊ ተጠቃሚ የሚያደርጉ ዘርፎች ላይ እንዲሰማሩ ግንዛቤ መፍጠር ስራዎችን ማከናወን ይኖርበታል:: ለማሳጅ ቤት ባለቤትቶች ህጋዊ ሆነው ለህብረተሰብ ተገቢውን ማሳጅ አገልግሎት እንዲሰጡ በየጊዜ ትምህራታዊ ስልጠና መስጠት ያስፈልጋል :: በህጋዊነት እና የማሰጅን ስነምግባር ጠብቀው የሚሰሩ ማሳጅ ቤቶችን የተለየ ደጋፍ እና እረዳታ በደረግላቸው በቀላሉ ከገበያው የማይወጡ ይሆናሉ፡፡ ትምህርት ቤቶች አካባቢ የተከፈቱ እንዲሁም መኖሪያ አካባቢ የተከፈቱ የወሲብ ንግድ የሚፈጸምባቸው ማሳጅ ቤቶች በቶሎ ካካባቢው ቢነሱ እና በቦታው ለሌሎች የማህበረሰብን የእለት ተእለት እንቅስቃሴ የማያውክ ተግባረት የሚፈፀምባቸው በሆኑ ሀገርም ህብረተሰብንም የሚጠቅም ይሆናል :: ቤተሰብና ትምህርት ቤት በጋራበመጣመርየልጆቻቸውንናየተማሪዎቻቸውን ውሎ በቅርብ ሆነው መከታተል አለባቸው፡፡ በተለያዩ ጊዜ የልጆቹን ሁኔታ ለመገምገም ወላጅና ትምህርት ቤት በጋራ በመዋያየት የሚታዩ ችግሮችን
በእንጭጩ ለመቅጨት ይረዳቸዋል፡:

ይህ ዘገባ ቁምነገር መጽሄት ላይ ታትሞ የወጣ ነው::

The post የአዲስ አበባ ጉዶች: በማሳጅ ስም የወሲብ ገበያ ደርቷል * ኢትዮጵያ የወሲብ ቱሪዝም ‹ማግኔት› በሚል በውጭ ሚድያዎች መጠራት ጀምራለች (ልዩ ዘገባ) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>