Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic Âť News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live
↧

በግማሽ ዓመት 47 ሺ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል * በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል

$
0
0

ሰሞኑን 35 ስደተኞች የያዘ ጀልባ የመን ሳይደርስ ሰጥሟል
በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል
“በህጋዊ ምዝገባ የስራ ጉዞ መታገዱ ህገወጥ ስደትን አባብሷል”

yemen

በህጋዊ ምዝገባ ወደ አረብ አገራት የሚደረግ ጉዞ ከታገደ ወዲህ፣ በየመን በኩል እየተሰደዱ ለአደጋ የሚጋለጡ ኢትዮጵያዊያን መበራከታቸውንና ባለፉት ስድስት ወራት 47ሺ ያህል ስደተኞች የመን እንደገቡ RMMS ሰሞኑን ገለፁ፡፡ የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኮሚሽን እና ሌሎች አለማቀፍ ድርጅቶች በጋራ ያቋቋሙት ይሄው ተቋም እንደሚለው፣ ዘንድሮ የስደተኞቹ ቁጥር ከአምናው በእጥፍ ይበልጣል፡፡ ባለፉት አስራ ሁለት ወራት ውስጥ 250 ስደተኞች የመን ለመግባት ሲሞክሩ፣ በባህርና በበረሃ ጉዞ ላይ መሞታቸውን ተቋሙ ጠቅሶ ከስደተኞቹ መካከል ሰማኒያ በመቶ ያህሉ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን ገልጿል፡፡ ሰሞኑን በባህር ጉዞ ላይ በተፈጠረ አደጋ አንድ ጀልባ መስመጡን የዘገበው ኤኤፍፒ፤ ጀልባዋ 35 ስደተኞችን አሳፍራ ነበር ብሏል፡፡ ከጉዞ አደጋ በተጨማሪ ስደተኞቹ የመን ከገቡ በኋላም ግማሽ ያህሉ በወሮበላ ቡድኖች እንደሚታገዱ የገለፀው RMMS፤ ከእገታ ለመለቀቅ ከቤተሰብ ገንዘብ እንዲያስልኩ ይገደዳሉ ብሏል፡፡ ለስደት የሚገፋፉ ዋና ዋና ምክንያቶችን ለማወቅ በሺ በሚቆጠሩ ስደተኞችና በትውልድ አካባቢዎቻቸው ላይ ጥናት ያካሄደው ይሄው ተቋም፤ በኢትዮጵያ ዋናዎቹ መንስኤዎች የኑሮ ችግር እንዲሁም ህይወትን የሚያሻሽል ነገር ፍለጋ ናቸው ብሏል፡፡ የፖለቲካ ችግርም የተወሰነ ጫና እንደሚፈጥር ተቋሙ ጠቅሶ፣ የደላሎች ድርሻ ግን ብዙዎች እንደሚያስቡት አይደለም፤ ከመቶ ስደተኞች መካከል በደላላ ግፊት ለስደት የሚነሳሱት ከሁለት ወይም ከሦስት አይበልጡም ብሏል፡፡

ብዙ ወጣቶች ወደ ስደት የሚያቀኑት አደጋ ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ባለማወቃቸው ነው ለማለት እንደሚያስቸግር ተቋሙ ሲያስረዳ፤ በአመት ውስጥ ወደ የመን ከገቡት ኢትዮጵያዊያን መካከል ሩብ ያህሉ ከሳዑዲ አረቢያ ወደ አገራቸው የተባረሩና ካሁን በፊት ስደትን የሞከሩ ናቸው ብሏል፡፡ ከቅርብ ወራት ወዲህ የስደተኞቹ ቁጥር የተባባሰበት ሌላው ምክንያት፣ በህጋዊ ምዝገባ ወደ ሳዑዲ አረቢያና ወደ ኩዌት ሲደረግ የነበረው የስራ ጉዞ በመንግስት መታገዱ ነው ብሏል – የተቋሙ ጥናት፡፡ በሌላ በኩል ሶማሊያ ውስጥ ከድህነት በተጨማሪ የሰላም እጦት ወጣቶችን ለስደት እንደሚገፋፋ ተቋሙ ገልፆ፤ በኤርትራ ደግሞ ከኑሮ ችግር ሌላ ዋነኛው ግፊት የመንግስት ከፍተኛ የፖለቲካ አፈና ነው ብሏል፡፡ በሊቢያና በግብጽ በኩል ወደ አውሮፓ ለመግባት ከሚሞክሩ ስደተኞች መካከል ከሶሪያዊያን በመቀጠል በቀዳሚነት የሚጠቀሱት ኤርትራዊያን መሆናቸውን የጠቀሰው ይሄው ተቋም፤ ባለፉት አራት ወራት 15ሺ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ እንደተሰደዱ ገልጿል፡፡ ስደት የተባባሰው በድህነትና በአፈና ምክንያት አይደለም በማለት የኤርትራ መንግስት ሲያስተባብል፤ ወጣቶች እንዲሰደዱ በማድረግ አገሪቱን ኦና ለማድረግ አለማቀፍ ሴራ እየተካሄደብኝ ነው ብሏል፡፡

ምንጭ: አዲስ አድማስ ጋዜጣ

The post በግማሽ ዓመት 47 ሺ ኢትዮጵያዊያን ወደ የመን ተሰደዋል * በዓመት 200 ገደማ ኢትዮጵያውያን በበረሃ እና በባህር ጉዞ ላይ ሞተዋል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ልደቱ አያሌው በቀጣዩ “ምርጫ”አልወዳደርም አሉ –“ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ምንም ነገር አይመጣም”ሲሉ ምርጫውን አጣጣሉት

$
0
0

lidetu ayalew
“ቴአትረ ቦለቲካ” የሚል መፅሃፍ ሊያወጡ ነው

በመጪው ግንቦት በሚካሄደው አገራዊ ምርጫ ካለፈው ምርጫ የተለየ ውጤት ቨመጣል ብለው እንደማይጠብቁ የተናገሩት የቀድሞው የኢዴፓ ፕሬዚዳንት አቶ ልደቱ አያሌው፤ በምርጫውም እንደማይወዳደሩ አስታወቁ፡፡ በ “ቴአትረ ቦፖለቲካ ፣ አሉባልታና የአገራችን ፖለቲካ ገመና” በሚል ርዕስ የፃፉት አዲስ መፅሀፍ በቅርቡ በገበያ ላይ እንደሚውልም ተናግረዋል፡፡

“የኢህአዴግን አካሄድና የተቃዋሚው ጎራ ያለበትን ሁኔታ ሳየው በግንቦቱ ምርጫ ካለፈው የተለየ ነገር ይመጣል ብዬ አላስብም” ያሉት አቶ ልደቱ፤ ኢህአዴግ ምርጫውን ሙሉ በሙሉ በራሱ ቁጥጥር ስር አድርጎ እንደቀጠለ ነው፣ ተቃዋሚው ጎራም ካለፉት ስህተቶቹና ድክመቶቹ ተምሮ ራሱን ለማሻሻል ያደረገው ብዙ ነገር የለም ሲሉ ምክንያታቸውን ገልፀዋል፡፡ “ድፍረት አይሁንብኝ እንጂ ተቃዋሚው ጎራ በፓርላማ ያለችውን አንድ መቀመጫ አስጠብቆ ይቀጥላል ወይ የሚለው በራሱ ለኔ ጥያቄ ነው” ሲሉም ጥርጣሬያቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በተቃዋሚ ፓርቲ ዙሪያ የተደረጉ የትብብር ሙከራዎች ትግሉን የጎዱ እንጂ የጠቀሙ አይደሉም ሲሉ የሚሞግቱት አቶ ልደቱ፤ ፓርቲዎች በእንተባበር ጥያቄዎች ባይዳከሙ ኖሮ በአሁኑ ወቅት ሁለት ወይም ሶስት ጠንካራ ፓርቲዎች ይኖሩን ነበር ብለዋል፡፡

“ቴአትረ ቦለቲካ፡ አሉባልታና የአገራችን ፖለቲካ ገመና” የተሰኘ ሶስተኛ መፅሃፋቸው በቅርቡ እንደሚወጣ የጠቆሙት አቶ ልደቱ፤ መፅሃፉ በኢትዮጵያ ፖለቲካ አሉባልታዎች ዙሪያ እንደሚያጠነጥን ተናግረዋል፡፡ አሉባልታ የተቃውሞ ጎራውን ትግል ክፉኛ እንደጎዳውም ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ገልጸዋል፡፡

The post ልደቱ አያሌው በቀጣዩ “ምርጫ” አልወዳደርም አሉ – “ካለፉት ምርጫዎች የተለየ ምንም ነገር አይመጣም” ሲሉ ምርጫውን አጣጣሉት appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ንብረት የሆነው መሬት በተጭበረበረ ካርታ ለባለሃብቶች መሸጡ ተነገረ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ በተለየ ስሙና ቦታው እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ንብረት የሆነውን መሬት አዲስ የተመረጠው ሰበካ ጉባኤ ለባለሃብቶች በተጭበረበረ ሰነድ እየሸጠ ነው ሲሉ ምእመናን ብሶታቸውን አሰሙ::
news
“ለማን አቤት ይባላል? ለፈጣሪ እንጂ” የሚሉት እነዚሁ ተቆርቋሪ ምእመናን “በቅርቡ የተመረጡት የሰበካ ጉባዔ አባላት በቤተክርስትያን ስም ሁለት ማህተም በማሰራት የቤተክርስትያኑ ንብረት የሆነውን ቦታ በማጭበርበር እየሸጡት ነው፡፡” ነው ይላሉ:: ምዕመናኑ አክለውም “የቤተክርስትያኑ ሰንበቴ ቤት የነበረውን ክፍት ቦታ ለቤተክርስትያኑ ገቢ ማስገኛ በማለት ለግለሰብ ቢያከራዩትም ሰነዱን በማጥፋት ካርታ አስወጥተው እንደሸጡት ታውቋል:: አሁን ደግሞ የማቴዎስ ግቢ የሚባለውን የቤተክርስቲያኑን ቦታ አገልጋይ ካህናትን በማስወጣት ለግለሰብ ለ20 ዓመት ሊሸጡት እየተደራደሩ ነው:: ይህንንም ለማሳመን ሁለት ዓይነት የተጭበረበረ ሰነድ አቅርበዋል:: ስለዚህ የሚመለከታችሁ ሁሉ ይህንን የቤተክርስትያን ቦታ በመሸጥ ላይ የተመሰረተ እኩይ ተግባር በህግ አምላክ ብለን እናስቁማቸው::” ሲሉ ጥሪያቸውን አቅርቧል::

በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የአዲስ አበባ መሬቶች ለሕወሓት ሰዎች እና ለውጭ ባለሃብቶች በልማት ስም ተቸብችበው ያለቁ በመሆኑና የመሬትም እጥረት ስላለ የቤተክርስቲያን መሬቶችን ወድ መቀራመቱ ተደርሷል:: በቅርቡ አዲስ አበባን በማስፋፋት በሚል ሰበብ በወጣው አዲስ ማስተር ፕላን የኦሮሚያ ገበሬዎች መሬት ተቀምቶ ለባለሃብት ሊሰጥ ነው በሚል በተነሳ የሕዝብ ጥያቄ በርካቶች የጥይት ራት መሆናቸው ይታወቃል::

እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ስላሴ ቤተክርስትያን ንብረት የሆነውን መሬት አለአግባብ ለባለሃብት ቸብችበዋል የተባሉትን የሰበካ ጉባኤ አባላት ዘ-ሐበሻ ለማናገር ያደረገችው ጥረት አልተሳካም:: እንደደረሰን መረጃ ከሆነ ግን የቤተክርስቲያናችን ንብረት ሊሸጥ አይገባም የሚሉ ሰዎች ተቃውሟቸውን አደባባይ ይዘው ለመውጣት እየተዘጋጁ ነው::

The post እንጦጦ የሚገኝው መንበረ ስብሃት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ንብረት የሆነው መሬት በተጭበረበረ ካርታ ለባለሃብቶች መሸጡ ተነገረ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር በሓገራችን ኢትዮጵያ ዕለት ተዕለት እየተንሰራፋ የመጣውን አምባገነናዊ ስርዓት ያወግዛል

$
0
0

ሁላችንም እንደሰማነው የወያኔ ኢህአደግ አምባገነን መንግሥት ህዝብ ያቋቋማቸውን የአንድነትትና የሚኢአድን ድርጅቶች ፋሸሸታዊ ጡንቻውን በመጠቀም ከዚህ ቀደም በቅንጅት ላይ እንዳደረገው ሁሉ የምረጫ ቦረድ ተብዬው ቡድን አማካኝነት ፓረቲዎቹን ለተለጣፊ ስብስቦች አሳልፎ ሰጥቷል ፡፡
Tensaye
ይህንን ሕገወጥ እና አምባገነናዊ ማናለብኝነት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት ቆሞ ሊያወግዘውና ሊታገለው ይገባል፡፡
በመሆኑም የአንድነት የድጋፍ ማህበር በስዊድን በሓገራችን የዲሞክራሲ ሥርዓት እሰኪሰፍን የህግ የበላይነት እስኪረጋገጥ የሰብዓዊ መብቶች እስኪከበሩ ድረስ ትግሉን እደሚቀጥል ያረጋግጣል ፡፡

ይህ ጥሪ፡-
በዓለም ላይ ለምትገኙ ኢትዮጵያዊያኖች ሁሉ፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ዲሞክራሲ እንዲሰፍንና የኢትዮጵያን ሕዝብ እኩልነቱና ሰብዓዊ መብቱ ተጠብቆ እንዲኖር ለምትታገሉ የፖልቲካ ድርጅቶች፤ የሰብዓዊ መብት ታጋዮች እና ግለሰቦች በሙሉ ይህንን አምባገነናዊ ሥርዓት በህበረት እንድንታገልና ሴራውን እንድናከሽፍ ጥሪያችንን እናስተላልፋልን፡፡

ጥር 23 ቀን 2007 ዓም (ፌብርዋሪ 1 ቀን 2015)

በስዊድን ያአንድነት የድጋፍ ማህበር
ሰቶከሆለም፡፡

The post በስዊድን የአንድነት የድጋፍ ማህበር በሓገራችን ኢትዮጵያ ዕለት ተዕለት እየተንሰራፋ የመጣውን አምባገነናዊ ስርዓት ያወግዛል appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በአዲስ አበባ የተሰራው የቀላል ባቡር ገና ከመጀመሩ የመኪና አደጋን አስተናገደ

$
0
0

car accident

ኢትዮጵያ ቴሌቭዥን በስህተት ጠቅላይ ሚኒስተር መለስ ዜናዊ በምርቃቱ ላይ ተገኙ ሲል የዘገበለት የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ገና በተመረቀ በአንድ ሳምንቱ የመኪና አደጋ አስተናገደ::

ከአዲስ አበባ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው አንድ መኪና የባቡሩን መተላለፊያ አጥር ደርምሶ ገብቷል:: እንደ ተሰማው መረጃ ከሆነ ሹፌሩ ጠጥቶ ሲያሽከረክር እንደነበር ቢነገርም ከፖሊስ በኩል የተሰጠ መግለጫ የለም::

ኢትዮጵያ ውስጥ በመኪና አደጋ በንብረትና በሰው ሕይወት ላይ እያደረሰ ያለው ጥፋት ቸል ሊባል የሚገባው አይደለም::

The post በአዲስ አበባ የተሰራው የቀላል ባቡር ገና ከመጀመሩ የመኪና አደጋን አስተናገደ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ሪሳላ ኢንተርናሽናል በሚኒሶታ 2ኛውን ዙር ታላቅ የሙስሊሞች ኮንፍረንስ ሊያካሂድ ነው * ታላላቅ ሰዎች ይገኛሉ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “ለእምነትህ ምን አበርክተሃል?” በሚል መርህ 2ኛው ዙር የኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኮንፈረንስ በሚኒሶታ ለ2 ቀናት እንደሚደረግ ሪሳላ ኢንተርናሽናል ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫው አስታወቀ::

አርብ ፌብሩዋሪ 20 ቀን ከቀትሩ 4 ሰዓት በድምቀት እንደሚከፈት በሚጠበቀው በዚህ 2ኛው ዙር ኮንፈረንስ ላይ 20 በላይ ታላላቅ የሃይማኖት አባቶች እና ታላላቅ ሰዎች እንደሚገኙ ታውቋል::

በሚኒያፖሊስ ኮንቬንሽን ሴንተር በሚደረገው በዚሁ የሪሳላ ኢንተርናሽናል ኮንፈረንስ ላይ
1. ሼክ አብዲ ሁሴን
2. ሼክ መሀመድ ከዲር
3. ሃጂ ነጂብ መሀመድ
4. ሼክ ካሊድ ኡመር
5. ጋዜጠኛና አክቲቭኢስት ሳዲቅ አህመድ
6. ቦና መሀመድና ሌሎችም ታዋቂ ሰዎች የሚገኙ ሲሆን ኮንፈረንሱ ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 22, 2015 ዓ.ም ከቀትሩ 3 ሰዓት እስከ ምሽቱ 10 ሰዓት ተደርጎ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል::

ለበለጠ መረጃ ሪሳላ ኢንተርናሽናል ለዘ-ሐበሻ የላከውን ቀጣዩን በራሪ ወረቀት ይመልከቱ::
Minnesota Muslim

The post ሪሳላ ኢንተርናሽናል በሚኒሶታ 2ኛውን ዙር ታላቅ የሙስሊሞች ኮንፍረንስ ሊያካሂድ ነው * ታላላቅ ሰዎች ይገኛሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የሸንጎ ድምጽ ቅጽ 3 ፣ ቁ 3

$
0
0

ምርጫና አፈና አብረው አይሄዱም!

shengoዓመታቱ ዞረው መግጠማቸው የተፈጥሮ ሕግ ነውና በሃገራችን የ2002 „”የምርጫ” ግርግር አልፎ የ2007 ምርጫ ግርግር ጀምሯል። ህወሓት/ ኢሕአዴግ ዝግጅቱን የጀመረው በ2002ቱ ምርጫ ማግሥት ሲሆን፤ ተቃዋሚዎች ደግሞ የተቀላቀሉት ሰሞኑን እንደሆነ እንመለከታለን። ሸንጎ ይህንን የምርጫ ጉዳይ አስመልክቶ መጋቢት ወር 2006 ዓ. ም (ከ ዘጠኝ ወራት በፊት ማለት ነው) የመልዕክቱ ዋና ጉዳይ አድርጎ ያቀረበው ይህንኑ በ2007 ዓ. ም ይካሄዳል የተባለውን ምርጫ እንደነበር እናስታውሳለን። በዚህም መልዕክት ምርጫው ነፃና ፍትሃዊ እንዲሆን፤ በቅድሚያ መሟላት አለባቸው በማለት አስቀምጧቸው የነበረውና የምርጫው ጊዜ እየተቃረበ ባለበት ባሁኑ ጊዜም ያለው ሁኔታ እንደገና እንድንመለስባቸው የተገደድንባቸው ጉዳዮች የሚከተሉት ነበሩ። –-[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—-

The post የሸንጎ ድምጽ ቅጽ 3 ፣ ቁ 3 appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ከEBC (የቀድሞ ETV) እና ከሰው ለሰው አዘጋጆች ምስጋናም ሆነ ሽልማት አልጠብቅም

$
0
0

ታሪኩ ደሳለኝ (የተመስገን ደሳለኝ ወንድም)

ትናንት የካቲት 1/2007 ዓ.ም በሸራተን ሆቴል በተደረገው የሽልማት ሥነ-ሥርዓት ላይ ከEBC እና ከሰው ለሰው አዘጋጆች የጥሪ ካርድ ሊደርሰኝ ቀርቶ ዝግጅቱ እንዳለ እንኳን የሰማሁት ትላንት ከዝዋይ እስር ቤት ስመለስ አንድ ሰው ደውሎ የዝግጅቱን መግቢያ ትኬት ካለህ ሲለኝ ነው፡፡
tariku desalegn
እኔና ሰው ለሰው ድራማ

በዚህ ተከታታይ ድራማ ላይ ከክፍል 57 እስከ 87 ድረስ (ምዕራፍ ሦስት ሙሉው) ሲኒማቶግራፊው የተሰራው በእኔ አማካኝነት ነበር፡፡ በስራው ላይ በነበርኩበት ወቅት የካሜራው ቴክኖሎጂ DSLR እንዲሆን፣ አንድ ሰው ሁለት ሦስት ስራ ከሚመደብ ለያንዳንዱ ስራ እራሱን የቻለ አንድ ሰው እንዲቆጣጠረው ጥረት አድርጊያለሁ፡፡ ይሄም በመሆኑ አዘጋጆቹ የሚያስቡትን ሁሉ የሚሰራ ክሩ ተፈጥሮአል፡፡ ከዚህ ባለፈም ከሳምንቱ አንዱን ቀን የሰራነውን ስራ የምንገመግበት ቀን እንዲኖር ሃሳብ አቅርቤ የስራው አካል ሆኖአለ፡፡ በዚህም ሰህተቶቻችንን ወዲያው ማረም ችለናል፡፡ የድራማውን ታሪክ በሲኒማቶግራፊ (ማለትም በብርሃን፣ በካሜራ እንቅስቃሴ እና በፍሬም) መግለፄን ግን ሌላ ባለሞያ ቢናገረው ይሻላል ብዬ አልፈዋለው፡፡

እኔና EBC

ከአንድ ወር ከ 11 ቀናት በፊት የኢትዮጲያ ኢንተርናሽናል 9ኛው የፊልም ፌስቲቫል ሲደረግ በቀሚስ የለበስኩለት ፊልም በሲኒማቶግራፊነት ሳሸንፍ የሽልማቱን መታሰቢያነት በእስር ላይ ለሚገኘው ለወንድሜ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ይሁንልኝ ማለቴ ይታወሳል፡፡ EBC ፌስቲቫሉን በሚመለከት ከ 6 ቀን በኋላ በእሁድ መዝናኛ ፕሮግራሙ ላይ በሰራው ዜና ላይ ሰፊ ሀተታ ከመስጠቱም በላይ ተሸላሚዎቹንም ኢንተርቪው አድርጎ አቅርቧል፡፡ ስለኔ ይቅርና ስለ ፊልሙ መሸለም ምንም ሳይል አልፎታል፡፡ ዛሬ ደግሞ ለረጅም ወራት የሰራሁበት ድራማ መጠናቀቂያ ላይ አልጠሩኝም…. በዚህ አጋጣሚ ዛሬ የተሸለማቹሁ ባለሞያዎች እንኳን ደስ ያላቹህ እላለሁ
በመጨረሻም

ከሰው ለሰው ድራማ ሰሪዎች ላይ አንድን ሰው የበለጠ ላመስግን፡፡ “መስፍን ጌታቸው” (ሞገስ) በተናገርከው በመፅናትህና እኔና አንተ ስለምናውቃቸው ነገሮች ሁሉ፡፡

The post ከEBC (የቀድሞ ETV) እና ከሰው ለሰው አዘጋጆች ምስጋናም ሆነ ሽልማት አልጠብቅም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የከምባታ ህዝብ ነገ የተቃውሞ ሰልፍ ሊወጣ ነው

≫ Next: Hiber Radio: ኤርትራ በርካታ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሱማሊያ ላንድ አስገብታለች መባሉና ማስተባበሏ.. ከኢትዮጵያ የሔዱ ቤተ እስራኤላውያን ለተለያዩ ህመሞች ስለመጋለጣቸው…በኬንያ ያሉ ጋዜጠኞችን መንግስት አፍኖ ለመውሰድ በተዘዋዋሪ መንገድ መግለጹ.. ሰማያዊ ፓርቲ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ እንደ አንድነት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፅሙበት እየሰራሁ ነው ማለቱና ሌሎችም
$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) የከምባታ ህዝብ ሆን ተብሎ መሰረተ ልማት እንዳይገነባለት በመደረጉና በተራድኦ ድርጅቶች የተሰሩት መሰረተ ልማቶች ስራ ላይ እንዳይወሉ በደኢህዴን ከፍተኛ አመራሮች እየተፈፀመበት የሚገኘውን በደል በመቃወም ነገ ማክሰኞ የካቲት 2/2007 ዓ.ም በዱራሜ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ የከምባታ ህዝቦች ኮንግረንስ ሊቀመንበር አቶ ኤርጫፎ ኤርዴሎ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የከምባታ ህዝብ በተመሳሳይ ጉዳይ ህዳር 26/2007 ዓ.ም ዱራሜ ላይ የተቃውሞ ሰልፍ አድርጎ የነበር ሲሆን የነገው ሰልፍም የክልሉ መንግስት ችግሮቹን ለመቅረፍ ዝግጁ ባለመሆኑ ነው ብለዋል፡፡
news
ከምባታ ውስጥ ሊሰራ የታሰቡና የተጀመሩ ስራዎችን የደኢህዴን ባለስልጣናት ወደተወለዱባቸው አካባቢዎች እንደሚታጠፉ የገለጹት አቶ ኤርጫፎ አንገጫ የተባለ ቦታ ላይ ተራድኦ ድርጅት የሰራው ሪፈራል ሆስፒታል ተሰርቶ ካለቀ በኋላ መገዘጋቱን እንዲሁም ቃጫ ቤሮ ወረዳ በተራድኦ የተሰራ ሆስፒታል ስራ ላይ እንዳይውል መደረጉን በምሳሌነት ጠቅሰዋል፡፡ በተጨማሪም የሚሰሩ መንገዶች የባለስልጣናቱ ዘመዶች በኮንትራክተርነት ስለሚይዟቸው ይጠናቀቃሉ በተባሉበት ጊዜ እንደማይጠናቀቁና ለሙስና የተጋለጡ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ በሙስና እና በዝምድና ምክንያት መንገዶች እንዳይሰሩ የሚያደርጉት ባለስልጣናቱ ህዝቡ ጥያቄ በሚያነሳበት ወቅት ‹‹መሰረተ ልማት ስለሌላችሁ ወደ ከምባታ መጥቶ ለማልማት አልተቻለም፡፡›› የሚል መልስ እንደሚሰጡ ገልጸዋል፡፡
በከምባታ ህዝብ ላይ የሚደርሰው በደል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ በመምጣቱና የደኢህዴን ባለስልጣናት ችግሩን ለመቅረፍ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ህዝቡ የሚፈጸምበትን በደል ለማሰማት ከጠዋቱ 3 ሰዓት ጀምሮ በዱራሜ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያደርግ ተገልጾል፡፡ የተቃውሞ ሰልፉ ህዝቡ ራሱን በማስተባበር የጠራው መሆኑም ተገልጾአል፡፡

The post የከምባታ ህዝብ ነገ የተቃውሞ ሰልፍ ሊወጣ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

Hiber Radio: ኤርትራ በርካታ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሱማሊያ ላንድ አስገብታለች መባሉና ማስተባበሏ.. ከኢትዮጵያ የሔዱ ቤተ እስራኤላውያን ለተለያዩ ህመሞች ስለመጋለጣቸው…በኬንያ ያሉ ጋዜጠኞችን መንግስት አፍኖ ለመውሰድ በተዘዋዋሪ መንገድ መግለጹ.. ሰማያዊ ፓርቲ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ እንደ አንድነት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፅሙበት እየሰራሁ ነው ማለቱና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የካቲት 1 ቀን 2007 ፕሮግራም

<<...ሕይወታችን አደጋ ላይ ነው። የኬኒያ መንግስትና ዩ.ኤን.ኤች.ሲ.አር በጋራ ነው የሚሰሩት...ኢ/ር ተስፋሁን ጨመዳም ከዚሁ ኬኒያ ታፍኖ ተወስዶ ነው በኢትዮጵአ እስር ቤት የሞተው እኛ እስካሁን የስደተኝነት ከለላ እንኳ አላገኘንም …>>

ጋዜጠኛ አቦነሽ አበራ ከኬኒያ በስደት ካለችበት በቅርቡ ሂዩማን ራይት ዎች ላዘጋቸው ዶክመንተሪ ኢትዮጵያ በኢትዮጵያ በጋዜጠኞች ላይ ስለሚደርሰው ጫና ምስክርነት በመስጠቷ አገዛዙ በራሱ ሚዲያ ባወጣው ጽሁፍ ይዤ አገር አስገባለሁ ማለቱን አስመልክቶ ስላለባቸው ስጋት ከገለጸችው (ሙሉውን ያዳምጡ)

<...ቀድሞ አገር ቤትም እያለን በዚሁ በስርዓቱ ድህረ ገጽ አይጋ ፎረም ላይ እንደምንከሰስና ጋዜጦቹ እንዲዘጉ እንድንታሰር ሲጻፍ ነበር ወዲያው ተከሰስን...አሁንም አገር ቤት አፍነው ሊወስዱ ነው ሚዲያው በውጭ ያለው ወገናችንና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች አስቀድመው ከመታፈናችን በፊት ሊጮሁልን ይገባል...> ጋዜጠኛ ቶማስ አያሌው አገዛዙ በዩማን ራይት ዶክመንተሪ በዲፕሎማሲው በደረሰበት ኪሳራ ሳቢያ አፍኖ ሊወስዳቸው ማቀዱ ያጋለጠበትን ጽሁፍ በተመለከተ ላደረግንለት ቃለመጠይቅ ከሰጠው ምላሽ የተወሰደ (ሙሉውን ያዳምጡ )

<...ሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድና ገዢው ፓርቲ እንደ አንድነት እንዳያፈርሱት ሁሉንም ቀዳዳዎች እየደፈነ ፓርቲውን ከተቀላቀሉት የአንድነት አመራሮችና አባላት ጋር ትግሉን አጠናክሮ ይቀጥላል...ሰላማዊ ትግል አላበቃለትም...> አቶ ዮናታን ተስፋዬ የሰማያዊ ፓርቲ የሕዝብ ግንኙነት ሀላፊ ለህብር ሬዲዮ ከሰጠው ቃለ መጠይቅ (ሙሉውን ያዳምጡ)

<...ታክስዎን ሲያሰሩ ሊጠነቀቁ የሚገባቸው ጉዳዮች በተለይ አይ.አር.ኤስ የሚያተክርባቸው ትኩረት ሳቢ ጉዳዮችን ማወቅ ለጥንቃቄ ይረዳል በተለይ ደግሞ...> አቶ ተካ ከለለ ከአትላንታ የቲኬ ሾው አዘጋጅ ስለ ታክስ ከሰጡን ሰፊ ማብራሪያ የተወሰደ(ሙሉውን ተከታተሉ)

የአፍሪካ ዋንጫ ፍጻሜና ታሪክ ራሱን የደገመት የዋንጫው ፍጻሜ(ልዩ ሪፖርት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

አገዛዙ ኬኒያ በስደት ላይ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጋዜጠኞችን አፍኖ ለመውሰድ እቅድ እንዳለው በተዘዋዋሪ ይፋ አደረገ

ጋዜጠኞቹ በማንኛውም ሰዓት ታፍነን ልንወሰድ እንችላለን የሚል ስጋት ላይ ወድቀዋል

ከኢትዮጵያ የሔዱ ቤተ እስራኤላውያን ለተለያዩ ህመሞች መጋለጣቸውን የአገሪቱ ታዋቂ ጋዜጣ ዘገበ

ኤርትራ ሰሞኑን በርካታ ታንኮችንና ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ወደ ጎረቤት ሶማሌ ላንድ አሸጋግራለች የሚል ወቀሳ ቀረበባት

አገሪቱ መረጃውን በፅኑ እያስተባበለች ነው

ሰማያዊ ፓርቲ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ እንደ አንድነት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፅሙበት እየሰራሁ ነው አለ

ሰላማዊ ትግሉን ፓርቲውን በብዛት ከተቀላቀሉ የአንድነት አባላትና አመራሮች ጋር አጠናክሮ ትግሉን እንደሚቀጥል ገለፀ

በአዲስ አበባ የተሰራው ቀላል የባቡር ማገጃ የመኪና አደጋ አስተናገደ

በቂ መሸጋገሪያና በጣቢያዎቹ ላይ በቂ ወረፋ መ
ጠበቂያ የሌለው በመሆኑ ህብረተሰቡ ቅሬታ እያነሳበት ነው።

ትብብሩ ለጠራው የአዳር ተቃውሞ የሰልፉን ጥሪ የበተነው የሰማያዊ አባል ላይ ከነገ በስቲያ ቅጣት ሊጥል የአገዛዙ ፍርድ ቤት ቀጠሮ ሰጠ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: ኤርትራ በርካታ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሱማሊያ ላንድ አስገብታለች መባሉና ማስተባበሏ.. ከኢትዮጵያ የሔዱ ቤተ እስራኤላውያን ለተለያዩ ህመሞች ስለመጋለጣቸው… በኬንያ ያሉ ጋዜጠኞችን መንግስት አፍኖ ለመውሰድ በተዘዋዋሪ መንገድ መግለጹ.. ሰማያዊ ፓርቲ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ እንደ አንድነት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፅሙበት እየሰራሁ ነው ማለቱና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

“በማሪያም መንገድ ከተከለከለ ፣ በገብርኤል መንገድ የሚመጣ ይኖራል” –አቶ አስራት አብርሃም

≪ Previous: Hiber Radio: ኤርትራ በርካታ ታንኮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ወደ ሱማሊያ ላንድ አስገብታለች መባሉና ማስተባበሏ.. ከኢትዮጵያ የሔዱ ቤተ እስራኤላውያን ለተለያዩ ህመሞች ስለመጋለጣቸው…በኬንያ ያሉ ጋዜጠኞችን መንግስት አፍኖ ለመውሰድ በተዘዋዋሪ መንገድ መግለጹ.. ሰማያዊ ፓርቲ ገዢው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ እንደ አንድነት ተመሳሳይ ጥቃት እንዳይፈፅሙበት እየሰራሁ ነው ማለቱና ሌሎችም
$
0
0

Asrat Abrhaአቶ አስራት አብርሃም በአቶ በላይ ፍቃዱ ይመራ በነበረው አንድነት ፓርቲ ተ/ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ነበር::ሰሞኑን በአንድነት ፓርቲ ላይ በተፈጸመው ድርጊት ዙሪያ አዲስ አበባ ከምትታተመው ፍቱህ መጽሔት ጋር ቃለ ምልልስ አድርጓል፡፡

ፍቱን፡- በሰላማዊ ትግል ለውጥ ለማምጣት የሚታገልን እንደ አንድነት ያለ ፓርቲ በዚህ ደረጃ ለማጥፋት መወሰን እጅግ ግራ አጋቢ ነው የሚሉ አስተያየቶች አሉ? አቶ አስራት፡- አዲስ ነገር ጋዜጣን ለማጥፋት የወሰነ መንግስት ሌሎች ሚዲያዎችን ለመታገስ እንደሚከብደው ግልጽ ነው፣ ምክንያቱም አዲስ ነገር በሃሳብ የሚሞግት ሚዲያ ነበር::አንድነትም ከሌሎች በተሻለ ሁኔታ ከጥላቻ ፖለቲካ እየወጣ ነበር፣ ለኢአዴግ አመራሮችም ቢሆን ያን ያህል የከፋ አመለካከት አልነበረውም:: እንዲያውም እነሱ ሣይጠይቁ የሚያልፉበትን መንገድ ለማመቻቸት ፍላጐት ነበረው:: -–[ሙሉውን ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—–

The post “በማሪያም መንገድ ከተከለከለ ፣ በገብርኤል መንገድ የሚመጣ ይኖራል” – አቶ አስራት አብርሃም appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አቶ አርከበ እቁባይ መለስ ዜናዊን መግደል ጀምረዋል (ሪፖርታዥ)

$
0
0

Arkebe Equbay - Ethiopia
በአንድ የቅርብ ስብሰባ ላይ አቶ አዲሱ ለገሠ አቶ አርከበን ሲነቅፉ “ ቆይ ቆይ አርከበ እኔ እዚህችጋር አንድ ጥያቄ አለችኝ። እስኪ ይሄ ያዘጋጀኸው ዶክመንት ከመለስ አስተምህሮ ጋር እንዴት እንደሚሄድ አስረዳኝ……”

አቶ አዲሱ በኢህአዴግ ድርጅታዊ መዋቅር ውስጥ እንጂ በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሉም። አቶ አርከበ ደግሞ በመንግሥት እንጂ በድርጅቱ መዋቅር ውስጥ የሉም። መዋቅር የማያገናኛውቸው ከሆነ ሁለቱን ከአንድ ስብሰባ ምን አስቀመጣቸው? የመከራከሪያቸው ፍሬ ነገርስ ስለምን የመለስ አስተምህሮ ሆነ? የመለስ አስተምህሮ ራዕይና ሌጋሲ የአገሪቱ አቅጣጫ መመሪያ ማስፈራሪያ እየሆነ ዋነኞቹን ባለሥልጣናት ሳይቀር እያከራከረ ይመስላል። ወደታች ወረድ ብለን እንመለከተዋለን።
ለማናኛውም አቶ መለስ ዜናዊ ሞልተውን ለሄዱት የውድቀትም ሆነ የእድገት ሰሌዳ፣ ከአንዳቸው እንደርስ ዘንድ ምን ያህል ጊዜ ይቀረናል? በራዕይ የተገለጠላቸውን የኢትዮጵያ የወደፊት እጣ ምልክቱን እናይ ዘንድ ምን ያህል መጓዝ ይኖርብናል? ወይስ ደርሰናል ? ወይስ አቅጣጫውን ስተን ሌላ መንገድ ይዘናል? ከእድገቱ ወይስ ከቁልቁልቱ አፋፍ ላይ ነን? በፈጣኑ እድገታችን ፋፍተን እንደ ጽጌረዳ ፈንድተን እንፈካለን ወይስ እንደ ፈንጂው እንጠፋለን? ወዴት እየሄድን ነው?
በወቅቱ እንደተዘገበው 8ኛው የኢህ አዴግ ጉባዔ የተካሄደው ከመስከረም 5-7/2003 ዓ.ም አዳማ የኦሮምያ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ነበር። ጉባዔውን በመምራት ላይ የነበሩት አቶ መለስ፣ የአምስት- ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ላይ የተደረገው ውይይት በቂ እንደሆነ ገልፀው፣ ‹‹የቀረበውን ሪፖርት መፅደቁን የምትደግፉ፣ ያደረጋችሁትን ባጅ ከፍ አድርጋችሁ አሳዩ›› ሲሉ ጠየቁ። ጉባዔተኛው በሙሉ አንገታቸው ላይ ያንጠለጠሉትን ሰማያዊ የጉባዔ ተሳታፊነት መለያ ወደ ሰማይ ቀሰሩ።
‹‹እቅዱን የምትቃወሙና ድምፅ የማትሰጡ?››
ማንም የለም።
“የአምስት- ዓመት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጸድቋል።” አሉ።
አዳራሹ በጭብጨባ ተሞላ።
የአቶ መለስ በዚህ ጉባኤ ባሰሙት ንግግር እንዲህ አሉ
IMG_0683

አቶ መለስ ዜናዊ ከሞቱ በኋላ ግን ድርጅታቸው ዛሬ ላይ ቆሞ ሲያየው የአቶ መለስ እቅድ ያለቅጥ የተለጠጠ ነበር። ምክንያቱም አልተሳካም። የማይሳካው ነገርም የታቀደው ሆን ተብሎ ነው። አቶ መለስን ልክ አልነበሩም በማለትና እሳቸውን በማምለክ መካከል በመንገላታት ላይ የሚገኘው ድርጅታቸው በጣም የሚያስቅ መግለጫ ይዞ ወጥቷል። የአቶ መለስን ስህተት እንኳ እንድ ራዕይ አይቶት ከሰማይ ከዋክብትን ከማርገፍ ጋር አመሳስሎታል። በሌላ በኩል ደግሞ አቶ መለስ ከላይ በንግግራቸው “wdnþ× lþb‰L ygbà xK‰¶nT ymSfN«„N xdU tÌqÜmN” እ ያሉትን አደጋ ዛሬ መልሶ የሚያመጣ ወይም ድላቸውን የሚቀለብስ አደጋ በገዛ ጓዶቻቸው መጥቶባቸዋል። በቦንድ ሽያጩ ትላልቅ ኢንደስትሪ ዞኖችን በማቋቋም ስም ትላልቅ የውጭ ኢንቨስተሮችን ጓዶቻቸው ወደ አገር ውስጥ እየጋበዙላቸው ነው። ምክንያቱም አቶ መለስ ያሉት እድገት አልመጣም። አገሪቷ በኢኮኖሚ ቀውስ ተዘፍቃ ከሌሎች ችግሮቿ ጋር አብጣ ልትፈነዳ ሰከንድ የምትቆጥር መስላለች…. በኢህአዲግ አመራሮች መካከል ይቅር እንጂ አቶ መለስም ድርጅታቸውንና አገሪቱን ከማይሆን ነገር ውስጥ ዘፍቀዋት ሄደዋል….

መወቃቀስ መያዛቸው ይሰማል። ቀጣዩ አቅጣጫ ይህ ሊሆን ይገባል አይገባም መባባላቸው እየተሰማ ነው። ክርክሩ ንትርክ ከንትርክም አልፎ የተካረረ መስመር እየያዘ መምጣቱ ይሰማል። ይህ ወደ ፖለቲካው ሽኩቻ አድጎ ወይም ሰበብ ሆኖ እንደ ኤርትራው ጦርነት ክፍፍል ዘመን ኢህአዴጎችን ለሁለት እንዳይከፍላቸው አስግቷል። ወይም አስጎምዥቷል።
በሌላ አነጋገር አቶ መለስ ልክ ነበሩ ወይስ አልነበሩም ይከለሱ ወይስ አይከለሱ የሚል ትርጓሜ እየፈጠረ ይመስላል። የመለስ ራዕይ ወይም አስተምህሮ አራማጆችና አስጠባቂዎች ባንድ በኩል ከላሾችና ምንትስሊብራሎችየተባሉትደግሞ በሌላ በኩል ሆነው ለመወጋገዝ በተጠንቀቅ ሆነዋል። የክፍፍል ዓይነቱ ብዙ ነው። ፓርቲ ውስጥ ያሉትን የመንግሥት ሰዎች በአንድ በኩል መንግሥት ውስጥ የሌሉ የፓርቲ ሰዎችን ደግሞ በሌላ በኩል ማሰለፉም እየተሰማ ነው። ለዚህ ሁሉ የልማትና የትንራንስፎርሜሽን እቅዱ ዋነኛው መነጋገሪያ ወይም የመዋጊያ ሜዳ መስሏል።
ሰበብ ሆኖ የሚያነጋግረው ይሄ የ 5 ዓመት እቅዱ ዋነኛው ይሁን እንጂ ከአቶ መለስ ሞት በኋላ እያደገ የመጣው መናናቅና ዓይን የሚሞላ ሰው በድርጅቱ አመራር ውስጥ አለመገኘት መሆኑም ይወራል። ሥልጣን የባለ ራዕዮች ስለሆነ የነበረውን ማስቀጠል ወይም አዲስ ራዕይ መውለድ ወቅቱ የጠየቀው ጥያቄ መስሏል። ይህ ሁሉ ተደማምሮ የመጀመሪያውን እቅድ አፈጻጸምን በመገምገምና በሁለተኛው ትራንስፎርሜሽን አስተቃቀድ ላይ አለመግባባት ደንቅሯል። በዚህ ጽሑፍ የምናየው እነዚህን ይሆናል።

የገዢው ፓርቲ የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት በየዓመቱ የአገሪቱን አጠቃላይ የፖለቲካና ኢኮኖሚ አቅጣጫና ግብ አስመልክቶ ግምገማ ያደርጋሉ። በተለይ የአምስት ዓመቱን የልማትና የትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ይቃኛሉ። አሁን የአምስት ዓመቱ እቅድ ሰኔ ላይ አልቆ ሁለተኛው የአምስት ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ይፋ መደረግ ይጀምራል። በዚህም መሠረት ከወራት በፊት በጥቅምት 2007/ ኖቨምበር 2014 ላይ የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል። በዚሁ ስብሰባ የመጀመሪያውን እቅድ ጉድለቶችና ችግሮች ገምግሞ በሁለተኛው የአምስት አመት የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መነሻ ማዕቀፍ ላይ ተወያይቶ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ እንዲመጣ አዟል፡፡ የእቅዱ ዋናው ማጠንጠኛ አቅጣጫ የኢንዱስትሪያላዜሽን ትራንስፎርሜሽን ማረጋገጥ እንደሚሆን አስምሮበታል፡፡

ይሄ የኢንደስትሪያላዜሽን ትራንስፎርሜሽን ወይም የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ ጉዳይ “ዋነኛ” ሆኖ መውጣቱ በአቶ መለስ ብዙም የማይደገፍ አካሄድ መሆኑና አፈጻጸሙም ላይ ልዩነት መኖሩ ይታወቃል። የትራንስፎርሜሽኑ ምሶሶ ኢንደስትሪ መሆኑ በመርህ ደረጃ ተቀባይነት ቢኖረውም በኢንደስትሪ ዞን አመሠራረት ፖሊሲ ዙሪያ አሁን ያለው የኢህአዴግ አመራር ለሁለት ተከፍሏል። የኢንዱስትሪ ዞኖቹ የት የት አካባቢ ነው መቋቋም ያለባቸው መጠናቸውና አገልግሎታቸው እንዴት ይሆናል የፋይናንስ ድጋፉንስ ከየት ያገኛሉ በየትኞቹ የምርት ዓይነቶች ላይ ማተኮር አለባቸው እነዚህ ሁሉ ኢህአዴጎቹን ያስማሙ አልሆኑም።

ለምሳሌ አንዳንዶቹ ኢንደስትሪያል ዞን (ፓርክ) ላይ ማተኮር አለብን ባዮች ናቸው። የሆነ አካባቢ ትልቅ ቦታ ተከልሎ የተንጣለለ መሬት ይሰጣል። ገንዘብ ይቀርባል። ባንኩ ታክሱ ሁሉ ነገር እዚያው ይጠናቀቃል። ልክ ሞጆ ላይ ለቻይኖቹ እንደሆነው ትልቅ ኢንደስትሪ ዞን ማለት ነው። እዚህኛው ላይ ጥያቄ የሚያነሱት አመራሮች እንደዚያ ያለ ትልቅ ዞን ሲቋቋም የአገር ባለሀብቶች አቅሙ አይኖራቸውም። እንደዚያ ያለ ካፒታል የሚኖራቸው የውጭ ኩባንያዎች ስለሆኑ አገር ቤት ያለው ባለሀብት እየቀነሰ ይመጣል። ያ ደግሞ እንደ ኬንያና መሰል አገሮች ኢንቨስትመንቱን የሚቆጣጠሩት የውጭ ኢንቨስተሮች ይሆናሉ። ይህ አገሪቱን አሳልፎ ለውጭ ባለሀብቶች የመክፈት ስለሆነ የኒዮ ሊብራሎች አስተሳሰብ ነው። ይህ ከኢህአዴግ መርህ፣ ከመለስ አስተምህሮ ጋር ይቃረናል። ስለዚህ እናንተ ካላሾች በራዦች (ሪቪዥኒስት) ናችሁ…. ባዮች ናቸው።

ከሱ ይልቅ በትንናሽ መንደሮች (ሳተላይት) መካከለኛ ኢንደስትሪ ማቋቋም እንደሚሻል ይከራከራሉ። በየተወሰነው ትናንሽ ከተማ ትናንሽ የጎጆ ኢንደስትሪዎችን ብንቋቁም ይሻላል። ያቺ ለአካባቢው ነዋሪ የሥራ እድል ትፈጥራለች። አካባቢውም ለኢንደስትሪው የሚሆን ግብአት (ጥሬ እቃና የሰው ኃይል) በመስጠት ይደግፋል። ስለዚህ መደጋገፍ ይኖራል፡ ፡ ለትንንሽ መንደሮችና ከተሞች እንዲሁም ለገበሬዎች ትንሽ ትንሽ እየሰጡ ከተሠራ እነሱ እያደጉ ይመጡና በረጅም ጊዜ ሂደት ውስጥ ራሳቸውን ወደ ትላልቅ ኢንደስትሪዎች ማሳደግ ይችላሉ ባዮች ናቸው።
ትራንስፎርሜሽን አብይ ዓላማው ገጠሬን ወደ ከተማ መለወጥ ግብርናን ወደ ኢንደስትሪ መቀየር ኤክስፖርት ላይ የተመሠረተ ምርት በማፍራት የአገሪቱን ገቢና የህዝቡን የኑሮ ደረጃ ማሻሻል የሚለው ሲናገሩት ቢጣፍጥም አብረው ሊሄዱ የሚችሉ የአመራርና የአስተዳደር ብቃት በቦታው አልተገኘም። የግል ባለሀብቱም ሚናው በግልጽ አልተመለከተም። አንደኛ ይህንን ህልም ሊደግፍ የሚችለው የግል ባለሀብቱ የፋይናንስ ድጋፍ ሊያገኝ የሚችልበት የብድርም ሆነ የፋይናንስ ምንጭ የለም። የአገር ውስጥ ባንኮች እንዳይበድሩ በመመሪያ ታስረዋል። እያንዳንዱ ባንክ የሚያበድረውን ብድር 27% ቦንድ እንዲገዛ ይገደዳል። ይህ ማለት ለግል ባለሀብቱ ሊያበድር ከሚችለው ገንዘብ ለቦንዱ ይከፍላል ማለት ነው። ስለዚህ ባንኮች ብዙ ባበደሩ ቁጥር ክፍያቸው እየመጨረ ይሄዳል፡፡ በመካከሉ ባለሀብቱ ገንዘብ አያገኝም። ለዚሁ ተብለው የተቋቋሙት እንደ ልማት ባንክ ያሉት የመንግሥት አበዳሪዎችም ቢሆኑ የባንኩ ኃላፊ ሰሞኑን እንደገለጹት ከሆነ መስፈርቱ ቀላል አይደለም። ለተመረጡ ዘርፎች ያውም ተበዳሪዎች ቢያንስ 30 ከመቶ የማዋጣት ኃላፊነት ይኖርባቸዋል። ከውጭ ባለሀብቶች ይልቅ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ጋር ሲስተያይ የአገር ውስጥ ባለሀብቶች ከባንኩ ብድር የማግኘት ተጠቃሚነታቸው ከመቶ ፐርሰንት ወደ 75 በመቶ እየወረደ መምጣቱም ተገልጿል። ይህም እያደገ ሄዶ ወደፊት አብዛኛውን የባንኩን ብድር የውጭ ባለሀብቶች ጠቅልለው ሊወስዱ የሚችሉበት አቅጣጫ ይታያል።
ሌሎቹ ደግሞ ሲከራከሩ የፋይናንስ ምንጫችንን ከውጭ ቢሆን አፈላልገን እናገኛለን። ለዚህም መፍትሔ የተለያዩ የፋይናንስ ምንጮችን አፈላልጎ ማግኘት ነው እንጂ እንዲሁ በር ዘግቶ መቀመጥ አያዋጣንም ባዮች ናቸው። የቦንድ ሽያጩ ነገር የመጣው እዚህጋ ይመስላል።።
meles zenawi
መለስ ቢኖሩ ቦንዱ አይኖርም! መለስ እየሞቱ ነው!

የመለስ ሌጋሲ አስጠባቂዎቹ አመራሮች እነ አቶ በረከት እና አባይ ፀሐዬ ቦንዱን በጥብቅ ተቃውመውታል። የቦንዱ ሽያጭ የፓርቲው ዶክመንት ከሚፈቅደው ውጭ አገሪቱን ለውጭ ኃይሎች በርግዶ መስጠት ነው። ለትላልቅ ፕሮጀክቶቻችን የአገር ውስጥ የፋይናንስ አማራጮችን ገና ተጠቅመንና ፈልገን አልጨረስንም። በኒዮ ሊብራሎች ኃይልና ግፊት ነው እዚህ ውስጥ የገባነው ብለው ያምናሉ። ቦንዱ ከኢህአዴግ እምነት ውጭ የተደረገ ፣ ሁሉንም ነገር ከፍቶ የመስጠት ኢኮኖሚውን ለውጭ ኃይላት የመክፈት የመጀመሪያው ዝንባሌና ምዕራፍ ነው። ነገ መለስ ተሟግቶ ያቆየውን ቴሌ ይሸጥ፣ ባንኮች ለውጭ ባለሀብቶች ባለቤትነት ክፍት ይሆኑ…የሚለው ክርክር ጅማሬ ነው ባዮች ናቸው።

የእነዚህ ከፍተኛ አመራሮች ምሬት ስናይ ምናልባትም ወደፊት “ቦንድና ሉአላዊነት በኢትዮጵያ” የሚል መጽሐፍ በክፍፍል አፈንግጦ በሚወጣ ሌላ ባለሥልጣን እናነብ ይሆናል። ምክንያቱም ጨዋታውና መወነጃጀሉ ሁሉ እንደ ኢትዮ ኤርትራ ወቅት ክፍፍል ከላሽና ተቸካይ መባባልን እያመጣ ነው። ሌሎች ተንበርካኪ ይሏቸው የነበሩ ባለሥልጣናት አሁን ደግሞ በተራቸው ተንበርካኪ የሚባሉበት ሁኔታ የተፈጠረ ይመስላል።

የክፍፍሉን ደረጃ አስገራሚ የሚያደርገው ሌላው ነገር ደግሞ የቦንዱ ሽያጭ ውሳኔ የተወሰነበትና ለህዝብ ይፋ የተደረገበት መንገድ ነው። ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃ/ማርያም (ከአማካሪያቸው አቶ አርከበ ጋር) ቦንድ ሽያጭ የመግባቱን ውሳኔ ሲወስኑ የኢህአዴግን ሥራ አስፈጻሚ አልተነጋገረበትም። በመጀመሪያ በሚኒስትሮች ም/ቤት ተወሰነ። ከዚያ ወደ ፓርላማ ሄደ። ከፓርላማውም በፓርላማው ጠቅላላ (በአዳራሹ) ሳይሆን በኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ብቻ ነው የታየው።

ይህን የሰሙት የፓርቲው የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ተቆጡ። እነ ኃ/ማርያም ሥራ አስፈጻሚውን ሳታስፈቅዱ ለምን ገባችሁበት ተብለው ሲጠየቁ ፍርጥም ያለ ምላሽ ሰጡ። 1ኛ የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሊነጋገር የሚገባበት ጉዳይ አይደለም። ሁለተኛ የመንግሥት ሚኒስትሮችና ፓርላማው ተነጋግሮበት ወስኗል። 3ኛ በዚያ ላይ የሚኒስትር ም/ቤት አባላትም ውስጥ ቢሆን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት አሉ። ሁሉም የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚዎች የሚኒስትሮች ም/ቤት አባል ባይሆኑም ከሞላ ጎደል ሁሉም ሚኒስትሮች ግን የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ አባላት ናቸው። የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ አባላት 60 ሲሆኑ የሚንስትሮች ም/ቤት አባላት ደግሞ 30 ናቸው። እዚህ ላይ አቶ ኃ/ማርያም ሥር የተጠለሉ የፓርቲው አንጃዎች (ከአቶ መለስ የተማሩትን) ጨዋታውን በሚገባ አውቀውታል። እንዲያውም ይባስ ብለው እንዴ ምን ማለት ነው? ምንስ ቢሆን እኛን እንዴት አታምኑንም? እዚያ ቦታ ስታስቀምጡን ከድርጅታችን ውጭ እንዴት ልንወስን እንችላለን በማለት ተቆጡ።

ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ ሆነና እነዚያም እንዲሁ ይተዋወቃሉና ውስጣቸው እያረረ በሉ ላሁኑ ይሁን አሉ። እንደዚህ ዓይነት ነገር ግን ለወደፊቱ መደገም የለበትም ይህ ቀላል ውሳኔ አይደለም የድርጅቱን መርሆ የታላቁ መሪያችንን አስተምህሮ የሚቃቀረን ነው አባሎቻችንን ማረጋጋት ይኖርብናል ዓይነት ነገር ብለው ሂስ አስውጠው እንዳይደገም ማስጠንቃቂያ ሰጡ።

ለዚህም ይመስላል አቶ ሱፍያን ወዲያው አደባባይ ወጡና ስለቦንዱ ስለሶቭሪን ቦንዱ መግለጫ ሰጡ። “ሶቭሪን ቦንድ መሸጥ ማለት የኢኮኖሚ ፖሊሲያችንን ቀይረናል ማለት አይደለም። ለሚቀጥለው ሶስትና አራት ዓመት ሌላ የቦንድ ሽያጭ አናወጣም” ብለው ተናገሩ። እዚህ ላይ ፖሊሲ ስለመቀየር አለመቀየር መናገርን ምን አመጣው? ቦንዱንስ የማይሸጡት ለምንድነው? ያቀርብነው ቦንድ የ1 ቢሊዮን ቢሆንም ያገኘነው ግን 2.5 ቢሊዮን ለመግዛት ፈቃደኛ የሆነ ገበያ ነው። ያህን ያህል ገበያ ካገኙ፣ ቦንዱም ያን ያህል ተፈላጊ ከሆነ፣ ለሚቀጥሉት ዓመታት አንሸጥም ማለትን ምን አመጣው? አይለመደንም እንደማለት ይመስላል።

ይህ ዓይነት ልዩነትና መቀበጣጠር የኖረው ሁሉም መሪያችን ነው ብለው የሚያከበሩት ሰው ባለመኖሩ ነው። ሁሉም የሚያከበሩት መሪ (ግለሰብና) ድርጅት የሌለበት ሁኔታ ነው የሚታየው። አንዱ ላንዱ ያለው አክብሮት ጤነኛ አይመስልም። መጥፎ ስሜትም እያሳደሩ ነው። ይህ ከኢኮኖሚ ወጥቶ የፖለቲካ ጉዳይ የማይሆንበት ምክንያት የለም። እነዚህ ሰዎች ልዩነታቸውን ምን ያህል በሰለጠነ መንገድ ይፈታሉ? ከዚህ ገፍተው የሞትና የሽረት ትንቅንቅ (የሰርቫይቫል) ቢያደርጉና ቢሞክሩ ሁሉም ነገር ሌላ መልክ ይኖረዋል።

እነ አርከበ/ኃይለማይርም የቦንዱን ውሳኔ ለብቻቸው ሲወስኑ ምክንያት ነበራቸው። ለምሳሌ ከአቶ መለስ ራዕይ የተለየው የኢንደስትሪያል ዞኑ ፖሊሲ ጉዳይ ሁለቴ ተጥሏል። ቦንዱን በራሳቸው ከወሰኑ በኋላ ለፓርቲው ማስረዳት የመረጡት በዚህ ምክንያት ነው። ይህንም ብናቀርብ ይጥሉብናል። ሰለዚህ ለራሳችን ለምን አናደርገውም የሚል ብልጠት መኖሩ ተነግሯል። በሌላ በኩል ከአቶ መለስ ራዕይ ጋር በተቸከሉትና በቻልነው ፍጥነት ተጠዳድፈን ካፈጠጠብን ቀውስ እውንጣ በሚሉት አባላት መካከል ፍትጊያ ቢርኖም ችግሩ በአንድና በሁለት የመከፈል ሳይሆን ቢያንስ ወደ ሶስት የሚጠጋ ቡድን መፈጠሩም ይሰማል።

በረከት አዲሱ አባይ ፀሐዬ የመለስ ሌጋሲ እናስጠብቅ ባዮች ሆነው አንድ ቡድን ናቸው። አርከበ ዋነኛው ሆኖ ኃይለማርያም ሱፍያን ተክለወልድና ደብረፅዮን ደግሞ ሌላኛው ቡድን ሲሆኑ የማሻሻያ ለውጥ ያስፈልጋል ባዮች ናቸው። ጄኔራል የተባሉት እነ ሳሞራ የመለስ ራዕይ ከሚለው ውጭ ጉዳዩ ብዙም ስለማይገባቸው አገሪቱን በሥልጣን እያሳደረ ነው የሚባለው ሠራዊታቸው ከማንኛቸው ጋር እንደሚቆም ለመገመት ሳያዳግት አልቀረም። ገና እጅ ያልሰጡት እነወይዘሮ አዜብና ቀሪዎቹ የህወሓት ሥራ አስፈጻሚዎች ከሠራዊቱ ጋር ማንዣበባቸው ይሰማል።

ይህ ጽሑፍ በዘኢትትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል; ርዕሱን ግን እኛ ቀይረነዋል::

The post አቶ አርከበ እቁባይ መለስ ዜናዊን መግደል ጀምረዋል (ሪፖርታዥ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የማለዳ ወግ …የተገፊዋ እናት ደብዳቤ …! ነቢዩ ሲራክ

$
0
0

* ያልተመቻቸው የእኛ እናቶችን እንባ ..
ታሪካችን በጦርነት ተከቦ ዘመን በዘመን ሲተካ ፣ የቀደመው ይሁን ቢባል እንኳ በዘመነችው አለም መካከል ያለች ቀሪ በዛሬይቱ ኢትዮጵያ የሃገሬ እናቶች እንባ የሚጠርገው አጥቷል። ከዘመነ ጃንሆይ ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ እስከ ደርግ ፣ ከዚያም አሁን እስካለንበት የኢህአዴግ አገዛዝ ለሀገር ሰላም ፣ ለዲሞክራሲና ፍትህ የዜግነት ድርሻቸውን የሚወጡ ፣ የተጉና ” ስለ ሃገሬና ህዝቤ ያገባኛል ” ያሉ ልጆችን በአብራካቸው ያፈሩ እናቶች መከረኛ እናቶች ናቸው። ልጆቻቸው ፍትህን ናፋቂ ፣ መብታቸውን ጠይቂ ናቸውና ” እንደ ጋሪ ፈረስ ጋሪ አንነዳም ” ያሉ ኩሩ ዜጎችን አፍርተዋልና ህግና መመሪያ እየወጣ ፣ የወጣው ህግና መመሪያ እየተጣሰ ቤታውን አጨልሞታል ። ትናንት የነበረው ዛሬም የቀጠለው ደረቅ አሳዛኝ እውነት ይህ ነው !

አዎ የእናት አብራክ ጀግና ማፍራቱ አላቆመምና የጀግና አርበኛ እናቶች እንደ ትናንቱ ሁሉ ዛሬም የእኛ እንደ ከፋቸው ፣ ሰርክ እንደተሸበሩና ሰላማቸውን አጥተው ኑሮን ለመግፋት ተገደዋል። የእሳተ ነበልባል ለወጥ አራጅ እናቶች ናቸውና ይገፋሉ ፣ በገዛ ሃገራቸውና በቀያቸው ፣ በስጋትና በሽብር ተከበው ኑሮን በመከራ ፣ በደል እየተፈጸመባቸው ለመሆኑ ብዙ ማሳያዎችን ከቀደመው እስከ ቀረበው ፣ ከቀረበው እስከምንገፋው የለው የእኛ ሀገር የፖለቲካ ምህዳር የፈጠረው አሳዛኝ የተገፊ እናቶች ታሪክ ዋቢ ነው … !

ትንታጉ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ …

ተመስገን ደሳለኝ ደርግ በወደቀ ማግስት “ክፉው ዘመን አለፈ ፣ መጨራረስ መገዳደል እልባት አገኘ ” ተብሎ ተስፋ በተጣለበት ፣ “ዲሞክራሲ ሰፈነ !” ተብሎ አዋጅ ነጋሪት በተጎሰመ ፣ በተነገረበት ” የዲሞክታሲያዊ እኩልነት ህገ መንግስት ” የጸደቀ ሰሞን የአንደኛ ደረጃ አስኳላ ትምህርቱን ያላጠናቀቀ ገና በአስራዎቹ የእድሜ ክልል የነበረ ወጣት ነው ። ባለፉት 23 አመታት ግን ተግቶ ትምህርቱ የተከታተለው ብትቱ ታዳጊ እስከ ከፍተኛ ትምህርት ዘልቆ እውቀትን በመገብየት በተገቢ መንገድ አጠናቀቀ ።

ጎልማሳው ተሜ ….የሃገር ፍቅሩን ከቀሰመበት የትምህት ረድፍ አልፎ ተርፎ ፣ ከጎረቤት ፣ ከከባቢው ወርሷም አደገ … እናም ከጥቂት አመታት በፊት ነፍሱ ሲፈቅድ በተሰጠው የመጻፍና ማንበብ መብት ማዕቀፍ ብዕር ጨበጠ .. ተመስገን አውነትን ይዞ ፣ ዲሞክራሲን መከታ አድርጎ ያልተመቸውን የፖለቲካ አካሔድ ተቃዋሚ ፣ ገዠ ፖርቲ ሳያይና ግራ ቀኝ ሳይለይ ይሞግት ገባ ። የተዋጣለት ጋዜጠኛና የፖለቲካ ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትንታኝ ጸሃፊ ለመሆን ከበቁት የዘመናችን ትንታግ ሰላማዊ ትግል አርበኞች መካከል አንዱ ለመሆን ለተመስገን ጊዜ አልፈጀበትም ! እናም ስራውን ተግቶ ቀጠለ …

ጋዜጠኛ ተመስገን የመጻፍ የመናገር መብቱን ተጠቅሞ ፣ በሰላማዊ በሆነ መንገድ ለሃገሩ ይሆናል ያለውን ሰላማዊ የትግል ስልት በማመላከት ፣ ወጣቱ ፍርሃትን አስወግዶ ለሰላማዊ ትግል እንዲተካ መስበክ ያዘ ፣ መሰናክል ጋሬጣው ከማንሳት ይልቅ … ጋዜጠኛ ተመስገን ብዙ ታገለ ፣ አታገለ … ማለቱ ብቻ ይቀላል !

የቆየው ውርስ ተከትሎናልና ፣ ጥላቻውን አድገንበታልና የዚያ ወጣት ትንታግ የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ መንገድ በዘባተሎው ፖለቲካ ተሰናከለ ! … ባለ ራዕዩን ብዕረኛ ፓለቲካው ጠልፎ ጣለው ! ተሜ ግን የዋዛ አይደለም ” … ለእኔ ሳይሆን ለታገልኩለት አላማ ጸንታችሁ ታገሉ ! ” እያለ የወህኒውን ህይዎት በጸጋ ተቀብሎት ኑሮን መግፋት ይዟል ! …

ተገፊዋ የተመስገን እናት …

… የተሜ እናት ግን እያነቡ ነው … ብዙ ማለት አልችልም ፣ የተገፊዋን እናት ደብዳቤ ደርሷል ፣ አዝኛለሁ ! የምንሰማቸው ከሆነ …ተገፊዋ እናት በአብራካቸው ክፋይ በልጃቸው በጋዜጠኛ ተመስገን ላይ ወህኒ ቤት ውስጥ ህግ እየተጣሰ የሚፈጸምበት መበት ገፈፋ ሰላም ነስቷቸው ” የሰው ያለህ ፣ የህግ ያለህ! ” ብለውናል ። የእኒህ እናት ጩኽትና ሮሮ የሀገሬ ለውጥ አራማጅ ጀግና ልጆችን የወለዱ እናቶች ሁሉ ጥሪ ለመሆኑ ላፍታ አልጠራጠርም ። ምንም እንኳን ይህ አሁን ድረስ የቆየና የቀጠለው የሀገሬ እናቶች መከራ አንዱ ክፍል ቢሆንም ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላለፉት 30 ቀናት ከማንም ጋር እንዳይገናኝ መደረጉና የእናቱ አቤቲታ ጉዳዩን ጀሮ ገብ መልስ የሚያሻው ቀዳሚ ጉዳይ አድርጎታል ።

ዛሬ ጋዜጠኛ ተመስገን ጥፋት ምንድን ነው? ፍርዱስ ፍትሃዊና ተመጣጣኝ ነውን ብለን አንጠይቅም ፣ አንሞግትም ! ዛሬ የምንሞግት የምንጠይቀው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በእስር መብቱ አይጣስ ፣ ህገ መንግስቱ ይከበር እያልን ነው ። ተመሰወገን ከሚወዱ ከሚናፍቁት አቅመ ደካማ እናቱ ፣ ከቤተሰብ ከቅርብ ዘመዶቹ ፣ ከሐይማኖት ፣ ከሐኪምና ከህግ አማካሪ ጋር የመገናኘት ህገ መንግስታዊ መብቱን እንዲያከብርለት እንደ ዜጋ ድምጻችን የማሰማት ቢያንስ የሞራል ግዴታ አለብን ! ግፍ ሲበዛ ጥሩ አይሆንም ፣ ጆሮ ያለው ይስማ !

ፍትህ እንሻለን !

ነቢዩ ሲራክ
የካቲት 3 ቀን 2007 ዓም

—————————–

ቀን 02/06/2007 ዓ.ም

ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

አዲስ አበባ

ጉዳዩ፡- የልጄ ተመስገን ደሳለኝን ጉብኝት ይመለከታል

ወሮ ፋናዬ እርዳቸውጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከአብራኬ የወጣ ሁለተኛ ልጄ ነው፡፡ ገና ከህፃንነቱ ጀምሮ ለሰው አሣቢ፣ ሀገር ወዳድና ታታሪ ስለመሆኑ ከእኔ በላይ የሚያውቁት ይመሰክራሉ፡፡ ልጄ ተመስገን ለወገኔ አሰብኩ ባለ በእስር ቤት ያለጎብኚ እየተሰቃየብኝ ይገኛል፡፡ መቼም፣ የእናት ሆድ አያስችልምና እባካችሁ ልጄን ታደጉት፡፡ እባካችሁ ቢያንስ ካለበት እየሄድኩ የልጄን አይን እንዳይ እንዲፈቀድልኝ ተባበሩኝ፡፡

የልጄን ድምጽ ከሠማሁ ይኸዉ አንድ ወር ሞላኝ፡፡ ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ለወንድሙ ብሎ የቋጠረዉን ምሣ ይዞ ዝዋይ ማረሚያ ቤት ቢሄድም በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ተደብድቦ የያዘውን ምግብ እንኳ ሣያደርስ ሜዳ ላይ ተደፍቶ ተመልሷል፡፡ መቼም እናንተም ልጆች ይኖራችኋል፤ ደግሞም የልጅን ነገር ታውቁታላችሁ፡፡ እኔ አሁን በእርጅና ዕድሜዬ ላይ እገኛለሁ፡፡ ከአሁን በኋላ ብቆይም ለትንሽ ጊዜያት ነው፡፡ በዚህች ጊዜ ውስጥ ልጄን እየተመላለስኩ እየጠየኩ፣ ድምፁን እያሰማሁ፣ አይዞህ እያልኩ ብኖር ለእኔ መታደል ነበር፡፡ እባካችሁ እርዱኝ የልጄ ድምጽ ናፈቀኝ፡፡ እሱን መጎብኘት የተከለከለበት ምክንያት ምን እንደሆነ እንኳን እስካሁን አላወቅሁም፡፡ ከወንድሙ ድብደባ በኋላም ጥር 10 ወደ ጠዋት አካባቢ የሄዱት ጓደኞቹ እና ወንድሞቹ ሳያዩት ተመልሰዋል፡፡

ተምዬ ስታመም የሚያስታምመኝ፣ “አይዞሽ እማዬ” የሚለኝ ረዳቴ ነው፡፡ ሌላ ዘመድ የለኝም፡፡ የምተዳደረውም ልጆቼ ለፍተውና ደክመው በሚያመጧት ትንሽ ብር ነው፡፡ ዛሬ ግን ይኸዉ ልጆቼም ወንድማቸውን ለማየት እየተንከራተቱ ነው፡፡
በእናታችሁ ይዣችኋለሁ፤ ከቻላችሁ ልጄ እንዲፈታልኝ እና እኔም ያለችኝን ቀሪ የእድሜ ዘመን አይን አይኑን እያየሁ እንድኖር እንድታደርጉልኝ፤ ይህን ማድረግ ከአቅም በላይ ከሆነ ደግሞ ካለበት ድረስ እየተመላለስኩ እኔና ሌሎች ልጆቼ እንዲሁም ወገኖቹ እንዲጠይቁት ቢደረግልኝ ስል በአክብሮት እጠይቃችኋለሁ፡፡ ልጄን አውቀዋለሁ፡፡ አንድ ነገር ሲገጥመዉ ሆድ ይብሰዋል፡፡ ቢያንስ እንኳን ቤተሰቦቹን ሲያይ ስለሚፅናና ይኸዉ እንዲፈቀድልኝ እማፀናለሁ፡፡ እኔ ምንም አቅም የሌለኝ አሮጊት ነኝ፡፡ ሁሉንም ለናንተ ሠጥቻችኋለሁ፡፡ ከእግዚአብሄር ጋር እንደምታስተካክሉልኝ እና እንደገና የልጄን ፊት እንዳይ እንደምታደርጉኝ ሙሉ ተስፋ አለኝ፡፡

እንግዲህ የየካዉ ቅዱስ ሚካኤል ይከተላችሁ፡፡ መቼም የእናትን ሆድ ታውቁታላችሁ፤ የልጅ ነገር አያስችልም፡፡ ሆድም ቶሎ ይሸበራል፡፡ ስለዚህ እባካችሁ እኔንም ልጆቼንም እርዱን እንላለን፡፡

ከሰላምታ ጋር

ወ/ሮ ፋናዬ እርዳቸው

ግልባጭ

– ለጠ/ሚኒስተር ፅ/ቤት
– የህግና፣ ፍትህና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ                         –

ለአፈ-ጉባኤ ፅ/ቤት    –  የሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ሰመጉ)   –  ለእምባ ጠባቂ

– ለአሜሪካ ኢምባሲ

– ለእንግሊዝ ኢምባሲ
Please Share

 

 

The post የማለዳ ወግ …የተገፊዋ እናት ደብዳቤ …! ነቢዩ ሲራክ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

ኢትዮጵያዊያን ዋሺንግተን ላይ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ደጅ ወጡ

$
0
0

ሄኖክ ሰማእግዜር

ሕጋዊና ሕዝባዊ ድጋፍ ያላቸውን የፖለቲካ ፓርቲዎች ማፍረስ ሰላማዊ ትግሉን አደጋ ላይ ይጥላል ያሉ ኢትዮጵያዊያንና ትውልደ-ኢትዮጵያ ሠልፈኞች ዛሬ ዋሺንግተን ውስጥ በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ደጅ ላይ ተሰልፈው ድምፃቸውን አሰምተዋል፡፡ በኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ሂደት ሀገርን የማይጠቅሙ አፈናዎች ቢበራከቱም ሰላማዊ ትግላችን ይቀጥላል ብለዋል ሠልፈኞቹ።

በዩናይትድ ስቴይትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት እጅግ የቀዘቀዘው የዋሽንግተን ዲሲ አየር ሳይበግራቸው የቆሙት ኢትዮጵያዊያን በዚህ የምርጫ ዓመት የኢትዮጵያ መንግሥት የዴሞክራሲ አፈናውን አጠናክሯል ሲሉ የተቃውሞ ድምፅ አሰምተዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ

[jwplayer mediaid=”38874″]

 

IMG_9399 IMG_9394 IMG_9398 IMG_9419
IMG_9404
IMG_9400

The post ኢትዮጵያዊያን ዋሺንግተን ላይ በውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ደጅ ወጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች የስደተኞችን ሻንጣ ዘረፉ

$
0
0

ከአንድ አመት በፊት የሳውዲ አረቢያ መንግስት በህገወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሃገር ዜጎች ግዛቱን ለቀው እንዲወጡ ያስቀመጠው የግዜ ገደብ መጠናቀቁን ተከትሎ አይሌ ኢትዮጵያውያን ጅዳ እና ሪያድ ከተማ ወደ ሚገኙ የኢትዮጵያ ኮሚኒቲ ግቢ መጉረፋቸው ይታወሳል ። በወቅቱ ከነበረው ስረዓት አልበኝነት ህይወታቸውን ለመታደግ አቅሙ የቻለ ጎረምሳ ልብሶቹን በሻንጣ አጭቆ እግር አውጭኝ ሲል አይን ያልገለጹ ህጻናት ልጆቻቸውን በወጉ መሰብሰብ ያልቻሉ እናቶች ለክፉ ቀን ትሆነኛለች ብለው የሸመቷትን ወርቅ እና የተለያዩ ጌጣጌጦቻቸውን የያዘች አነስተኛ ሻንጣ አንጠልጥለው ከቀማኞች የታደገናል ወዳሉት በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት በማቅናት ለተውሰኑ ቀናቶች ተጠልለው ሻንጣዎቻቸው በካርጎ ጭነት እንደሚላክ ቃል ተገብቶላቸው ለልጆቻቸው ተለዋጭ የረባ ጨርቅ እንኳን ሳይዙ ባዶ እጃቸውን ወደ ሃገር ቤት ማቅናታቸው ይነገራል ።
Jida

Jida 1
በወቅቱ በዚህ መልክ ወደ ቆንስላ ጽ/ቤት ቅጠር ግቢ የሚመጣውን ወገን ሃብትና ንበት በሃላፊነት ተረክቦ ወደ ሃገር መላክ የሚችል አካል ባለመኖሩ በጅዳ እና አካባቢው የሚኖሩ ታዋቂ ግለሰቦች ከዲፕሎማቱ ጋር በመተባበር አንድ ወገን ለወገን የሚል ኮሚቴ በማዋቀር ኢትዮጵያኑንን ወደ አህገር በሰላም እንዲገቡ ስፊ የማስተባበር ዘምቻ ይካሄድ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ይገልጻሉ ። ይህ ኮሚቴ ወደ ሀገር ተመላሽ ወገኖችን ስምና አድራሻ እየመዝገበ በአደራ ተቀብሎ ከሚሰበስበው ንብረት ባሻገር በተለያዩ ግዜያት በአሰሪዎቻቸው ተደብድበው ተድፍረውና ደሞዛቸው ተነጥቆ ወደ ቆንስላው ቅጠር ግቢ የሚመጡ እህቶች ጉዳያ ተድበስብሶና በደልን ተሸክመው ወደ ሃገር መሸኝት እንደሌለባቸው በማመን የቆንስላው ባለስልጣናት በዚህ ዙሪያ አንድ አይነት ሚና መጫወት እንደሚገባቸው እያደረገ በነበረው ግፌት ኮሚቴው ከተሰጠው ሃላፊነትና ተግባር አፈንግጦል በሚል ቅሬታ በአካባቢው የ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎችና የአሰሪ እና ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች በተፈጠረው አለመግባባት የማህበሩ መስራቾች በቆንስላው ዲፕሎማቶች ተእዛዝ ወደ ቆንስላው ግቢ እንዳይገቡ በመታገዳቸው የወገን ለወገን ህልውና ገና ከጅምሩ በአደራ የተረከበውን ንበረት ሜዳ ላይ በትኖ ይከስማል ።

መንገደኛ እና ሻንጣ በተለያዩበት የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት የጎዞ መስተንግዶ አሳዛኝ ትራጀዲ በተፈጠረው ስረአት አልበኝነት የተጠቀሱትን ሻንጣዎች ከአደጋ ለመከላከል ባሉበት ሁኔታ ሸራ ለብሰው ቀሩ ። እህቶች ለአመታት ይደርስባቸው የነበረውን እንደወላፈን የሚፋጅ የአረብ ወይዛዝርት ቁጣ እና ግልምጫ ተቋቁመው ባገኙት ደሞዝ የሸመቱት ወርቅና የተለያየ ጌጣጌጦችን የያዙ ሻንጣዎች የኢትዮጵያ አየር መንገድ የካርጎ አገልግሎት አቆመ በሚል ሰንካላ ምክንያት ወደ ሃገር እንዳይልኩ በቆንስላው ዲፕሎማቶች እገዳ ተጣለባቸው ። የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ቅጠር ግቢ ተቆልለው የሚታዩት እነዚህ ሻንጣዎች ለወራት ዝናብ እና ፀሃይ እይተፈራረቀባቸው ባለቤት አልባ ሆነው ደፍን አመት ካስቆጠሩ በኃላ ሰሞኑን በሻንጣዎቹ ላይ አስነዋሪና አስዛኝ ተግባር ተፈፀመ ። በተለይ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ግቢ ውስጥ ከተደረደሩ ሻንጣዎች ውስጥ የአባዛኛው ቁልፍ መስበሩን የሚናገሩ ውስጥ አውቂዎች ሻንጣዎቹ ላይ የተፈፀመው ዘረፋ የዲፕሎማቱ እጅ እንዳልበት በመረጃ ስደገፈው ይናገራሉ። የቆንስላ ግቢውን ጭር ማለት እንደ መልካም አጋጣሚ ተጠቅመው ማታ ማታ በስብሰባ ሽፋን ያለወትሮቻው ቆንስላው ግቢ እያደሩ የሚወጡትን ከዲፕሎማቱ ጋር የቀርብ ግንኙነት ያላቸውን የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባላት ይጠረጥራሉ ።

​ይህ በዚህ እንዳለ ሰሞኑን የ ሰማያዊ «ማንዋል» ፓስፖርት የአገልግሎት ዘመን ማብቃቱን ተከትሎ ፓስፖርት ለማስለወጥና ለማሳደስ የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት በተከስተው የባለጉዳዩች መጨናነቅ ዲፕሎማቱ ህጋዊ በሆነ መንገድ ወደ ቆንስላ ጽ/ቤት ለሚገባው ተስተናጋጅ የ3 ወር እና ከዚያ በላይ ቀጠሮ እይተሰጠው ሲሸኝ በሌላ አቅጣጫ ለሚስተናገድ ባለጉዳይ ከ 5 ቀን ባልበለጠ ግዜ ውስጥ ሁሉም ነገር እንዲምያልቅለት የሚናገሩ ባለጉዳዩች ዲፕሎማቱ እይሰጡ ባለው በሙስና የነቀዘ አገልግሎት ክፉኛ መማረራቸውን ይናገራሉ ፡፤ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ውስጥ የበጎ ፈቃድ አገልጋዩች በሚል ሽፋን ከዲፕሎማቱ ጋር ጥብቅ ቁረኝነት ያላቸው የዚህ ወንጀል ተባባሪ ደላሎች እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። በዚህ ዙሪያ ለማነጋገር በቀርቡ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ሃላፊ ሆነው የተሾሙትን አንባሳደር ውበሸትንም ሆነ ዲፕሎማት ሼሪፍ ኬሬን በአካል ለማገኘት ያደረኩት ሙከራ ለግዜው አልተሳካም ።

Ethiopian Hagere Jed Bewadi

The post በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች የስደተኞችን ሻንጣ ዘረፉ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

በራሪ ወረቀት የበተነው የሰማያዊ አባል 2 ወር ከ10 ቀን ቅጣት ተበየነበት

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) የ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ህዳር 28 ቀን 2007 ዓ.ም ጠርቶት ለነበረው የአዳር ሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ በራሪ ወረቀት ሲበትን በፖሊስ ተይዞ በእስር ላይ የቆየው የሰማያዊ ፓርቲ አባል ጥፋተኛ ተብሎ የ2 ወር ከ10 ቀን የቅጣት ውሳኔ ተላለፈበት፡፡
semayawi
ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ‹‹ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ፡- ነጻነት ለፍትሓዊ ምርጫ›› የሚል አርዕስት ያለውና በትብብሩ ፓርቲዎች የተዘጋጀውን የተቃውሞ ሰልፍ መቀስቀሻ በራሪ ወረቀት ሲበትን በአዲስ አበባ በፖሊስ የተያዘውና ‹‹የመንግስትን ስም በማጥፋት›› ክስ ተመስርቶበት ጉዳዩ በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው አቶ ሲሳይ ዘርፉ ጥፋተኛ ተብሎ ቅጣቱ ተወስኖበታል፡፡
ሆኖም ግን አቶ ሲሳይ በፖሊስ ከተያዘበት ህዳር 24 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ ዋስትና ተከልክሎ በእስር ላይ በመቆየቱ ዛሬ የካቲት 3 ቀን 2007 ዓ.ም የተላለፈበትን የ2 ወር ከ10 ቀን የቅጣት ውሳኔ መጨረሱ ተገልጾ ከእስር እንዲፈታ ትዕዛዝ ተሰጥቷል፡፡

The post በራሪ ወረቀት የበተነው የሰማያዊ አባል 2 ወር ከ10 ቀን ቅጣት ተበየነበት appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

የአልፋ ቀራኒዮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍል ጥለው ወጡ • ‹‹የተማሪዎች ጥያቄ የእኛም ጥያቄ ነው›› መምህራን

$
0
0

ዳይሬክተራችን ያለ አግባብ ተነስቶብናል ያሉ ዓለም ባንክ አካባቢ የሚገኘው የአልፋ ቀራኒዮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍል ጥለው ከግቢ መውጣታቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ዳይሬክተራቸው ለትምህርት ቤቱ አስተዳደር ባለመመቸቱ ከቦታው እንደተነሳ የገለጹት ተማሪዎቹ ዛሬ የካቲት 2/2007 ዓ.ም ጠዋት ላይ ‹‹በዳይሬክተሩ ጉዳይ እንድታነጋግሩን እንፈልጋለን፡፡ እኛ የምናውቀው ምንም ስህተት እንደሌለበት ነው፡፡›› ብለው ሲጠይቁ የትምህርት ቤቱ ስራ አስኪያጅ ‹‹ስለዚህ ጉዳይ እናንተ አያገባችሁም፡፡ ከፈለጋችሁ ተማሩ፡፡ ካልፈለጋችሁ ለቃችሁ መውጣት ትችላላችሁ፡፡›› እንዳሏቸው ስማቸውን መግለጽ ያልፈለጉ የአልፋ ቀራኒዮ አንደኛ ደረጃ መምህር ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
news
በተለይ የ7ኛ 8ኛ ክፍል ተማሪዎች ጥያቄያቸው ካልተመለሰላቸው መማር እንደማይፈልጉ በመግለጻቸው በሩ ተከፍቶ ከግቢ እንዲወጡ ተደርገዋል ተብሏል፡፡ ተማሪዎች ከትምህርት ቤቱ ግቢ ወጥተው ውጭ መቆማቸው ተከትሎም ግጭት ይፈጠራል የሚል ስጋት እንደተፈጠረ መምህራኑ ገልጸዋል፡፡
‹‹ርዕሰ መምህሩ ከተማሪዎችና ከመምህራን ጋር ተግባብቶ በመስራቱ ለትምህርት ቤቱ አስተዳዳሪዎች ስላልተመቸ እንጅ ያጠፋው ጥፋት የለም፡፡ የተማሪዎች ጥያቄ የእኛም ጥያቄ ነው፡፡ ሆኖም የርዕሰ መምህሩ ጉዳይ ብቸኛ ችግራችን አይደለም፡፡ ትምህርት ቤቱ በበርካታ ችግሮች የተተበተበ፣ ለመምህራንና ተማሪዎች የማይመች ትምህርት ቤት ሆኗል፡፡›› ሲሉም መምህራኑ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

The post የአልፋ ቀራኒዮ አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪዎች ክፍል ጥለው ወጡ • ‹‹የተማሪዎች ጥያቄ የእኛም ጥያቄ ነው›› መምህራን appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
↧

የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ ልጅ በጎዳና ሕይወት –“የአበበ ልጅ ስለሆንኩ እርዱኝ አልልም; ግን መንከራተት ሰልችቶኛል”

$
0
0

abebe bekila son
አዲስ አበባ ስታዲየም … ዘወትር ማለዳ ለልምምድ የሚወጡና የሚገቡ ሯጮችን ማየት የተለመደ ነው፡፡ ከትንሽ እስከ አንጋፋ፤ ከጀማሪ እስከ ታዋቂ፤ ከእግረኛ እስከ ባለመኪና አትሌቶች ይመላለሱበታል፡፡ ሁሉም አንድ ህልም አላቸው፦በአለም አደባባይ ስኬታማ አትሌት መሆን፡፡ ህልማቸውን እንደሚደርሱበት ደግሞ እርግጠኞች ናቸው፡፡ ለዚህ ደግሞ መነሻ አላቸው፡፡ እውነት አላቸው! ታሪክ አላቸው! አበበ ቢቂላ…የእነሱ እውነትና እምነት፡፡ የእነሱኩራትና ተስፋ! የዚህ ጀግና አትሌት ልጅ… ኢትዮጵያ አበበ… ግን እንደ ብዙዎች አትሌቶች በአባቱ ኩራትና ተስፋ ከልቡ ውስጥ የለም፡፡ ጀግንነቱን አልወረሰም፡፡

ታሪኩንም የሚያካፍለው አላገኘም፡፡ መኖር የፈተነው ህይወት፣ ማንነት ያሰቃየው ሰውነት ይዞ ጎዳና ላይ ወጥቷል፡፡ ከእድሜያቸው በላይ በላይ ገርጅፈዋል፡፡ አዲስ አበባ ስታዲየም ሲወጡና ሲገቡ የሚታዩ አትሌቶች፣ የአበበ ቢቂላን ታሪክ ለአለም እያወሩ ኩራታቸውን የሚገልጹቱ፣ እርሱን ተስፋቸው ያደረጉ፣ ድልንም የተጎናጸፉቱ፣ አዲስ አበባ ስታዲየም ዋና መውጫያና መግቢያ በር ፊት ለፊት ተቀምጦ የሚውለውን ልጁን ማየት አልቻሉም፣ ወይም አልፈለጉም፡፡ ወይም… ወይም….ወዘተ… የጀግናው ልጅ ግን ያያሉ፡፡ ያያሉ… ሊያውም በአንክሮ ያያሉ፡፡ ግን አይናገሩም፡፡ በዝምታ ያያሉ፡፡ ይታዘባሉም፡፡ ‘የአበበ ቢቂላ ልጅ ነኝና እባካቹ እርዱኝ፣ ርቦኛልና አጉርሱኝ’ ማለት ያሳፍራቸዋል፡፡ ብቻ ዝም ብለው ስታዲየሙ እያዩ ይተክዛሉ፡፡ አይናቸው እንባ እያቀረረ ወደ ፈጣሪያቸው ይማጸናሉ፡፡ “ፈጣሪ ሆይ አንተ ለኔ መሆን ከቃተህና ሰው ፊት የምታቆመኝ? እኔስ ምን በደልኩህ? አባቴን ፍቅርና ክብር ሳላጣጥም በስቃይ እንድኖር ስለምን ፈረድክብኝ? ብቻ ግን ተመስገን! ተመስገን!” ……………አሁን ኢትዮጵያ አበበ እድሜያቸው ገፍቷል፡፡ ኑሮ አድክሟቸዋል፡፡ ከአስር አመት በላይ የቆዩበት የጎዳና ህይወት አንገሽግሿቸዋል፡፡ ፍላጎታቸው ብዙዎች እንደሚያስቡት የአበበን ሀብትና ንብረት መውረስ ወይም እውቅና መፈለግ አይደለም፡፡ ማረፍ ነው የሚፈልጉት፡፡
“እኔ የአባቴን ሀብት ንብረት ስጡኝ፣ አካፍሉኝ ብዬ አልሟገትም፡፡ የአበበ ቢቂላ ስለሆንኩም እርዱኝ አልልም፡፡ በዚህ እድሜዬ የአዲስ አበባን ጎዳናዎች እየዞርኩ መለመን አቅቶኛል፡፡ ማረፍ ነው የምፈልገው”

Source: Yegara.com

The post የጀግናው አትሌት አበበ ቢቂላ ልጅ በጎዳና ሕይወት – “የአበበ ልጅ ስለሆንኩ እርዱኝ አልልም; ግን መንከራተት ሰልችቶኛል” appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

አበበ ገላው በአባዱላ ገመዳ 2 የውሸት ዲግሪዎች ግዢ ዙሪያ ማስረጃዎችን ለቀቀ

$
0
0

aba dula
[Updated](ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የሃሰት ዲግሪዎችን ከአሜሪካና አውሮፓ እንዲሁም ከቻይና እየገዙ እንደሚጠቀሙ በተደጋጋሚ እየተጋለጠ መሆኑ የሚታወስ ነው;; አበበ ገላው የዛሬ አንድ ወር ገደማ የዶ/ር ኮንተንጢኖስ በርሀን የሃሰት ዲግሪዎችን ያጋለጠ ሲሆን አሁን ተረኛው አባዱላ ገመዳ ናቸው ብሏል::

“ክቡር አፈጉባኤ አባዱላ ገመዳ አሜሪካ ሴንቸሪ ከሚባል የዲግሪ ወፍጮ ቤት የሃሰት ዲግሪዎች ገዝተው ጥቅም ላይ ማዋላቸው ተረጋገጠ” ሲል በፌስቡክ ገጹ ያስታወቀው አበበ ገላው ማስረጃዎቹን ዛሬ ለቋል::

አባ ዱላ ገመዳ የባችለር ዲግሪያቸውን እና የማስተር ኦፍ አርት ዲግሪያቸው ከአሜሪካው ሴንቸሪ ኮሌጅ በ2001 እና በ204 የገዙ ሲሆን ከ እንግሊዙ ግሪንዊች ዩኒቨርሲቲም ማስተር ዲግሪያቸውን እንዳገኙ ታውቋል::

አባዱላ በውሸት ዲግሪዎች የ80 ሚሊዮኑን የውሸት ፓርላማ ቁጭ ብለው ይመራሉ:: የኦሮሚያን መሬቶች ቸብችበዋል እየተባሉ የሚወገዙት እኚሁ ባለስልጣን በሃብት ደረጃም የሚወዳደራቸው ባለስልጣናት የሕወሓት ሰዎች ብቻ መሆናቸው ይነገራል::

የአበበ ገላው ምስጢራዊ የምርመራ ዘገባ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

(አዲስ ቮይስ) የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ የሆኑት አባዱላ ገመዳ በኢንተርኔት ያለምንም ትምህርት ዲግሪ በመሸጥ ከሚታወቅ አንድ የዲፕሎማ ወፍጮ ቤት (diploma mill) የሃሰት ዲግሪዎችን ገዝተው መጠቀማቸውን አዲስ ቮይስ አረጋገጠ።
አፈጉባኤው የባችለርስ ዲግሪ እ.ኤ.ኤ በ2001 እንዲሁም የማስተርስ ዲግሪ በ2004 አሜሪካን አገር በሚኖረውና አሊ ሚርዛኢ በሚባል ኢራናዊ ከሚንቀሳቀሰው “አሜሪካን ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ” (ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ) ያለምንም ትምህርት መግዛታቸው በመረጃ ተረጋግጧል። አባዱላ ሁለቱንም ዲግሪዎች የህዝብ አስተዳደር ትምህርት ተምረው አንዳገኟቸው ሲገልጹ የቆዩ ሲሆን ይህንንም በፓርላማ ድረገጽ፣በፌስቡክ፣ ዊኪፔድያ፣ በመንግስትና በግል የመገናኛ ተቋማት በይፋ ታትሞ እንዲሰራጭ አድርገዋል። ከዚህም በተጨማሪ ከቻይና መከላከያ ዩኒቨርሲቲ በወታደራዊ አመራር የባችለርስ ዲግሪ እንዳገኙ በህይወት ታሪካቸው ላይ በይፋ ያሰፈሩት አባዱላ እንዲህ አይነት ዲግሪም ይሁን ትምህርት ከቻይና የትምህርት ተቋም አለማግኘታቸው ታውቋል።
ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ከማንም እውቅና ያልተሰጠው ሲሆን አሊ ሚርዛኢ በዋነኛነት ከቤቱ የዲግሪ ሽያጭ እንደሚያከናውን አዲስ ቮይስ በምርመራው ከማረጋገጡም በላይ ምርመራውን ደንበኛ መስሎ ላካሄደው ጋዜጠኛ አበበ ገላው የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪዎችን በ4000 ዶላር ሊሸጥለት ሞክሯል። ይህንንም ህገወጥ የዲግሪ ሽያጭ የሚያረጋግጡ በርካታ የኢሜይልና የሰነድ መረጃዎች ጋዜጠኛው እጅ ገብተዋል።
ከሁለት ሳምንታት በፊት የህወሃቶች ቁንጮ ምሁራን ተደርገው ይቆጠሩ ከነበሩት አንዱ ቆንስጣንጢኖስ በርሄ የማስተርስና የዶክትሬት ዲግሪ ከሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ገዝተው እራሳቸው በዶክተርነትና በፕሮፌሰርነት መሾማቸው መጋለጡ ይታወሳል። በኢትዮጵያ ወንጀለኛ መቅጫ ህግ የሃሰት ዲግሪና ሰርተፍኬት ተጠቅሞ ለራስም ሆነ ለሌሎች ጥቅም ማግኘትና ማስገኘት በማጭበርበር ወንጀል የሚያስከስ ስና እስከ አንድ አመት እስር የሚያሰቀጣ ድርጊት ነው።
የሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ባለቤት ከዚህ በፊት የማጭበርበር ወንጀል ሲፈጽም ተደርሶበት በባለቤትነት ሲመራው የነበረው የሃዋይ ቢዝነስ ኮሌጅን እኤአ 2007 እንዲዘጋ ተደርጓል።
በኢፌዲሪ ህገ መንግስት መሰረት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛው የስልጣን አካል ሲሆን አፈጉባኤው ዋነኛው ህግ አውጭ ተደርጎ ይቆጠራል። የዛሬ አራት አመት አፈጉባኤ ሆነው የተሾሙት አባዱላ ገመዳ (ሚናሴ ወደጊዮርጊስ) ትምርታቸው ከ8ኛ ክፍል አቋርጠው የደርግ ወታደር ሆነው የነበር ሲሆን በኤርትራ በሻቢያ ተማርከው የነበረ ሲሆን በህወሃትና በሻቢያ መካከል በተደረገ ስምምነት መሰረት ከእነ አቶ ኩማ ደመቅሳ (ታዬ ተክለሃይማኖት) ጋር ለህወሃቶች ተላልፈው ከተሰጡ በሁዋላ የኦህዴድ መሪና መስራች እንዲሆኑ ተደርጓል።
የእነ አባዱላን ዲርጊት አሳፋሪ ሲሉ የገለጹት እውቁ ጋናዊው ምሁር ፕሮፌሰር ጆርጅ አይቴ እንዲህ አይነት እርካሽ የማጭበርበርና የማስመሰል ድርጊት የስርአቱን ንቅዘት ፍንትው አድርጎ አንደሚያሳይ ገልጸዋል። ፕሮፈሰሩ ተጠያቂነት የሌለው ህገውጥነት የአንባገነኖች ባህሪ መሆኑን አስገንዝበው አጭበርባሪ የስልጣን ጥመኞች ለውጥ ፈላጊ በሆነው አዲስ ትውልድ መተካት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። አይቴ አገር ለመምራት የምያስፈልገው እውቀት እንጂ ዲግሪ አይደለም ብለዋል። “ዲግሪ መግዛት ይቻላል፣ እውቀት ግን ፈጽሞ አይገዛም” በማለት የእነ አባዱላን ድካም ከንቱነት ጠቁመዋል።
የቀድሞው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስቴር ዴታ የነበረው ኤርምያስ ለገሰ በበኩሉ አባዱላ በራስ መተማመን የሌለው የሃሰት ስብእና በህወሃቾች የተፈጠረለት ግለሰብ በመሆኑ ያንን በዲግሪ ጋጋታ ለመሸፈን የሚያደርገው ጥረት አካል ሊሆን እንደሚችል ግምቱን ሰንዝሯል።
በርካታ ዜጎች ያለምንም ወንጀልና ጥፋት ለበርካታ አመታት ያለፍርድ በእስር በሚሰቃዩባት ኢትዮጵያ እነ አባዱላ በሃሰት ዲግሪ አገር ሲመሩ ማየት ህዝቡን የበለጠ ለለውጥ ሊያነሳስው ይገባል ሲል አስተያተቱ ሰጥቷል።
—-
ተያያዥ መረጃዎች:
Abadula Gemeda’s official biography on Ethiopia’s parliament website (screenshot)

http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/02/Abadula-Gemeda-par.pdf

House of People Representative: Abadula biography

http://www.hopr.gov.et/web/guest/higherofficial

Ethiopia: Abadula Gemeda, Speaker of the Parliament (Addis Fortune)

http://allafrica.com/stories/201309161711.html

Facebook official page: Honorable Abbaaduula Gammadaa

http://addisvoice.com/wp-content/uploads/2015/02/Abadula-facebook-official.pdf

The post አበበ ገላው በአባዱላ ገመዳ 2 የውሸት ዲግሪዎች ግዢ ዙሪያ ማስረጃዎችን ለቀቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

↧

ሃይለማርያም ደሳለኝ የመለስን ሌጋሲ ክደው ከባላንጣቸው ከአቶ አርከበ ጋር ሽር ጉድ ማለታቸው የት ያደርሳቸው ይሆን? (ሪፖርታዥ)

$
0
0

HaileMariam
ምርጫ እና ድርጅታዊ ጉባኤ -አሁን ያለው አመራር ይቀጥላል

አቶ መለስ ያለሰብሳቢ በትነዋቸው የሄዱትና በዓይነ ቁራኛ የሚጠበባቁት የኢህአዴግ ባለሥልጣናት የሚተማመኑበት ድርጅት ሳያውቁት ፈርሷልና መክቶ የሚያድናቸው አይመስልም። ለምሳሌ እንዲህ ያለ ሁኔታ ሲፈጠር ተቃዋሚዎቻቸውን ማራገፍ የሚችሉበት የፓርቲው መዋቅር አካል የሆነው አንዱ መሣሪያ ድርጅታዊ ጉባኤና ምርጫ ነው። በዚህ ወቅት መተማመን ስለጠፋና ከመበላላት መሰንበት ስለተመረጠ በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ድርጅታዊ ጉባኤያቸው ከምርጫው በኋላ እንዲደረግ ተወስኗል። ባለፈው ከተደረገው 9ኛው የኢህአዴግ ድርጅታዊ ጉባኤ በኋላ 10ኛው መደረግ የነበረበት ከምርጫው በፊት ነበር። አሁን ግን መች እንደሚደረግ የት እንደሚደረግ ሳይገለጽ በእንጥልጥል እንዲቀጥሉ ተደርጓል።

የኢህአዴግ ጉባኤ በየሁለት ዓመቱ ይደረጋል። ሁልጊዜ የሚደረገው ከምርጫው በፊት ነው። ድሮ ቢሆን አቶ መለስ ስላሉ በፊት ይሁን በኋላ ምንም ችግር አልነበረውም። ጠቅላይ ሚኒስትር የሚሆኑት እሳቸው መሆናቸው ግልጽ ነበረ። አሁን ግን የኢህአዴግ ጉባኤ ከምርጫው በኋላ መደረጉ ከወዲሁ የሚገልጸው ነገር አለ። ይሄ ማለት አሁን ያለው አመራር እንዳለ ይቀጥላል ማለት ነው። ኃ/ማርያም ባሉበት ይጸናሉ። በርግጥ ፓርቲው ከፈለገ በጉባኤው የድርጅቱን ሊቀመንበር መቀየር ይችላል። ለጠቅላይ ሚንስትርነት ግን የሚወሰነው በምርጫ ውጤት ላይ ተመርኩዞ ነው። ኃ/ማርያም ምናልባት የፓርቲው ሊቀመንበር ላይሆኑ ይችላሉ። ጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ግን እሳቸው ሆነው የመቀጠላቸው ሁኔታ በግልጽ እየታየ ነው። አቶ ኃ/ማርያም (ወይም በሳቸው የተጠለሉት) አሁን ሊቀመበርነቱንም ጠቅላይ ሚኒስትርነቱንም ተጠቅመው እየሠሩ ነው።

ይህ ማለት ግን ሥልጣን ወደ ድርጅቱ ሊሄድ አይችልም ማለት አይደለም። ለምሳሌ በአቶ መለስ ጊዜ ከክፍፍሉ በፊት ድርጅቱን ይመሩ የነበሩት አቶ ተወልደ ነበሩ። መንግሥቱን መለስ፣ ድርጅቱን ተወልደ ሲመሩ ድርጅቱ ከፍተኛ ሥልጣን እንደነበረው ይታወቃል። ወደ ኋላው ላይ ግን በክፍፍሉ ጊዜ፣ ያ ችግር ማምጣቱን የተገነዘቡት አቶ መለስ፣ የድርጅቱን አቅም አሽመድምደው፣ የመንግሥቱን መዋቅር ለማጠናከር ሁለቱንም ጠቅልሎ መያዛቸው ይታወሳል። መለስ ያ አደጋ በትክክል ገብቶታቸው አስተካክለዋል። አሁን ግን ኃ/ማርያም መለስን አይደሉም። ስለዚህ ኃ/ ማርያምን ወይም በሳቸው የተጠለሉትን ለመካለከል የተገደበ ሥልጣን የመስጠት ሙከራ ሊኖር ይችላል።

ህወሓት ምን ያስባል?

አሁን ያሉት ህወሓቶች ምን እንደሚያስቡ ለማወቅ በዚያ ደረጃ ማሰብ የሚችል ሰው ከመካከላቸው አለ ብሎ ማመንን ይጠይቃል። አሁን ቀላል የሚሆነው አንድ ለናቱ ጭንቅላታቸው የሆኑት አቶ መለስ ዜናዊ ምን አስበው ነበር ማለቱ ይሻላል። ምክንያቱም አሁን ያለውን ህወሓት እንደገና ጠፍጥፈው የሠሩት እሳቸው ናቸው። ስለዚህ ስላሁኑ ህወሃቶች ስናወራ ስለ አቶ መለስ እያወራን መሆኑን እያሰብን ነው። ህወሓቶች አሁን ያላቸው ሥልጣን እንዳይጠፋ ይሰጋሉ። እንደ አስተሳሰባቸው በቁጥርም ጠባብ በመሆናቸው የባለብዙ ቁጥር ህዝብና ድርጅት ውክልና ሁሌም ያባንናቸዋል። ስለዚህ የጠቅላይ ሚንስትርነቱን ቦታ የሚሰጡት ሰው ከኦሮሞው ወይም ከአማራው እንዲሆን አይፈልጉም። ኦህዴድ ያው ኦነግነት አለበት ብለው ይጠረጥራሉ። አማራውም ላይ ግልጽ የሆነ የጥርጣሬና የጠላትነት ስሜት አላቸው። ሌሎቹም የድርጅት ቢሆኑ አንዳቸው ላንዳቸው ይጠባበቃሉ። ስለዚህ ማንም ሰው ከደቡብ የመጣ ሰው ላይ የጠነከረ ፍቅርም ሆነ የመረረ ጥላቻ እንደሌለው ያውቃሉ። ደቡብ የመገንጠል ጥያቄ የለውም። በኢትዮጵያዊነቱም ላይ ጥያቄ አያነሳም። በዚያ ላይ 53 የተለያዩ ብሔረሰቦች የሚኖሩበት ጥሩ የፌደራሊዝም አስኳል ነው። የክልሉ ቋንቋም አማርኛ ስለሆነ ጥሩ ነው። አቶ መለስ ይህን በማሰብ ነው ከደቡብ የተወሰኑ ሰዎች መርጠው ከዚያ ውስጥ ነው ኃ/ለማርያን ያሰለጠኑት። እንደሚባለው በሚኒስትርነት ሥልጣን አንድ አስር ሰዎች ከደቡብ ለአቶ መለስ ቀርበው ነበር። ከእነዚያ ውስጥ ነው ኃ/ማርያም የተመረጡት። ችሎታ ያለው ታማኝ የሆነ አምጡልኝና ላሰልጥን ብለው አሰልጠነዋቸዋል ይባላል። አቶ መለስ ከሥጣልን ወርደርው በኃ/ማርያም አማካይነት ሊመሩ ህልም ነበራቸው። ሞት ቀደማቸው። አቶ ኃ/ማርያምም መቸም ሰው ከሆኑ ያቺን ቂም ሳይቋጥሩ አይቀሩም። የመለስን ሌጋሲን ክደው ከባላንጣቸው ከአቶ አርከበ ጋር ሽር ጉድ ማለታቸው የት እንደሚያደርሳቸው ግን ይታያል።

ሁለተኛውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ የመቅረጽ ሽኩቻ

በሚኒስትሮች ም/ቤት በኩል ያለው ዝግጅት የኢህአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ም/ቤት ከመነጋገሩ በፊት አስቀድሞ የተጀመረ ነው። ካለፈው ጁላይ 2013 ጀምሮ ዝግጅት ሲደረግበት እንደነበር ይታወቃል። ለምሳሌ የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት በጁላይ 2013 ላይ ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ሁለተኛውን የእድገትና ትራንስፍሮሜሽን እቅድ እንዲቀርጽ መታዘዙ በወቅቱ ተዘግቧል።

ይሄ ማምን ማለት ነው?

አቶ መለስ ከሞቱ በኋላ ከአማካሪዎቻቸው ጋር ካቢኔያቸውን የመሰረቱት ወይም “የተመሠረተላቸው” ጠቅላይ ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ ሹመት ከሰጧቸው ሰዎች መካከል አቶ መኮንን ማንያዘዋል ይገኙበታል። አቶ መኮንን በአቶ መለስ ጊዜ ለረዥም ዓመታት በከፍተኛ የመንግሥት ሥልጣን ላይ ቆይተዋል። የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሆነው ከማገልገላቸውም በላይ የመጀመሪያውን የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድን ማሰናዳታቸው ተነግሯል። እንደ መለስ ራዕይ ተደርጎ የተገለጸው እቅድ እሳቸው ያዘጋጁት መሆኑ ነው። አቶ መኮንን በቀድሞ የደርግ መንግሥት አንስቶ በፕላን ጽ/ቤት….የቆየ የረጅም ጊዜ የሥራ ልምድ አላቸው። የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ አባል ባለመሆናቸው ከፓርቲው ይልቅ ከመንግሥት አካላት ጋር ግንኙነታቸው የጠበቀ ነው። የድርጅት አባል ሳይሆኑ በሥልጣን ላይ ከቀሩት ጥቂት ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት መካከል እንደ አቶ ተቀዳ ዓለሙ፣ ኃይሌ አሰግዴ ከመሳሰሉት ውስጥ አሁን ሥልጣን ላይ የሚገኙት እሳቸው ብቻ ናቸው። ሌሎቹ ከአቶ መለስ ሞት ጋር ሄደዋል። ስለሆነም አቶ መኮንን የፓርቲና የመንግሥት ሥልጣንን በማራራቅ የተካኑት አቶ መለስ ዜናዊ ካቀረቧቸው ሰዎች አንዱ ነበሩ። አሁንም በፓርቲውና በመንግሥት መካከል ልዩነት ፈጣሪ ሆኖ በተገኘው የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅዱ ላይ ከፍተኛውን ድርሻ እንዲኖራቸው የሚያደርግ ኃላፊነት ተመልሶ የተሰጣቸው ይመስላል። ከአቶ መለስ ሞት በኋላ አዲስ የተቋቋመው ብሔራዊ ፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው እንዲሰሩ ተሹመዋል። ኮሚሽኑ ደግሞ ቀጣዩን የዕድትና ትራንስሮሜሽን እቅድን እንዲቀርጽ በጠቅላይ ሚንስትሩ ጽ/ቤት ታዟል። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ለራሱ ተጠሪ የሆነ የፕላን ኮሚሽን እንዲያቋቋም መደረጉ በፖሊሲ አማካሪነት ኃ/ማርያምን የከበቧቸውን የአቶ መለስ ቱባ ቱባ ባለሥልጣናት ለመከላከል ይሆን የሚል ግምት ማሳደሩ አይቀርም። ምክንያቱም አማካሪዎቹ የፓርቲ እንጂ የመንግሥትነት ሥልጣን የላቸውም።

ለመሆኑ የ5 ዓመት የልማትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ሀሳብ እንዴት መጣ?

የእቅዱ ሀሳብ ተጸንሶ የተወለደው በሶስት ወር ጊዜ ውስጥ ሲሆን ዘመኑ 2010 ነው። በ2010 የተደረገውን ምርጫ ማሸነፉን ከልቡ ያመነው ወይም በፈለገው ሁኔታ በመጠናቀቁ የተደሰተው ኢህዴግ መሪ የነበሩት አቶ መለስ ዜናዊ ያመጡት ሀሳብ ነው። አቶ መለስ የውስጥም ሆነ የውጭ ጠላቶቻቸውን ድል ነስተው ሲደላደሉ ካሁን በኋላ እዚህም እዚያም ቁጥ ቁጥ የሆነ ፕላን ሳይሆን ሁለገብና አብይ (ግራንድ) የሆነ ፕላን ያስፈልገናል ብለው ተነሱ። ለዚህም ኃላፊነት አቶ መኮንን ማን ያዘዋልንን መርጠው የአምስት ዓመት የልማትና የትራንስፎርሜሽን ፕላን እንዲዘጋጅ አዘዟቸው። አቶ መኮንን ቢሯቸውን ዘግተው ሶስት ወር ያህል ከቀመጡ በኋላ የአገሪቱ መነጋገሪያ የሆነውን ፕላን ይዘው ወጡ። አቶ መለስ ዜናዊ እሱን ተቀብለውና ቀባብተው የአገሪቱ ፕላን አድርገው በይፋ አወጁ። ባለ ራዕይ ያሰኛቸው ይህ ፕላን መሆኑ ይገመታል። መቸም የአቶ መኮንን ማንያዘዋል ራዕይ አይባልም።
አቶ መኮንን በቀድሞው የፕላንና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴርና በኢኮኖሚ ልማትና ትብብር ሚኒስቴር በተለያዩ ኃላፊነቶችና በሚኒስቴር ዴኤታ ማዕረግ አገልግለዋል፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በዴቨሎፕመንት ማኔጅመንት ሲያገኙ፣ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን የተቀበሉት ደግሞ በዴቨሎፕመንት ኢኮኖሚክስ ነው፡፡

ስለትራንስፍሮሜሽኑ አወጣጥ ሌሎች ደግሞ የተለየ አመለካከት አላቸው። የአቶ ኤርምያስን አስተያየት ያንብቡት።

አሁን ታዲይ ሁለተኛውን ልማትና ትራንስፎርሜሽን ለመቅረጽ ምን እየተደረገ ነው?

አቶ ኃ/ርያም የተሰየሙበት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ ቤት አቶ መኮንን ማንያዘዋልን ከሾመ በኋላ አዲስ የተቋቋመው ብሔራዊ የፕላን ኮሚሽን ራሱን በተቋም ደረጃ እንዲያዋቅር ተደርጓል። በተለይ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ እንዳለ ወደ ብሔራዊው ፕላን ኮሚሽን በመውሰድ በመደራጀት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ መንደፍ መጀመሩም ተመልክቷል። እቅዱ ገና ሳይጠናቀቅ ግን በፓርቲው ባለሥልጣናት በኩል እክል የገጠመው መስሏል።

በፓርቲው ውስጥ ያሉት ሰዎች በመንግሥትነት ያስቀመጧቸው ጓዶቻቸው የሚወስኗቸው ውሳኔዎች ከፓርቲው መርህ ውጭ እየሆነ ነው በማለት ጭቅጭቅ ማሰማት ጀምረዋል። ፖሊሲውን ማን ይቅረጽ የሚል ጥያቄው የሥልጣን መገለጫ እየመሰለ ሲያነታርክም ሰንብቷል። ለዚህ ንትርክ እልባት ለመስጠት ይመስላል የሁለተኛውን የትንራንስፎርሜሽን እቅድ በሚመለከት መንግሥት ያቋቋመው የብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን አልበቃ ብሎ ሌላ ተደራቢ ኮሚቴ መቋቋሙን ሰሞኑን ሰምተናል። ሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ጃንዋሪ1 8/2015 እትሙ የፌዴራል መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረገውን ሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በማዘጋጀት ላይ መሆናቸውን ዘግቧል።

እንደጋዜጣው ዘገባ የአምስት ዓመቱ ዕቅድ በስምንት ዘርፎችና ኮሚቴዎች ተከፍሎ እየተዘጋጀ ነው። እቅዱ እንደ ቀድሞው በጠቅላይ ሚኒስትሩ (አቶ መለስ) ራዕይና ትእዛዝ ብቻ መቀረጹና መዘጋጀቱ ቀርቶ አሁን ሁሉም ባለስልጣናት የየራሳቸውን ራዕይ የሚያኖሩበት እየመሰለ ነው። በተቋም ደረጃ በብሄራዊ ፕላን ኮሚሽን ደረጃ እንኳ እንዲዘጋጅ አልተፈለገም። በመሆኑም ፕላኑ በሚቀጥሉት ጉዳዮች ላይ የሚያተኩር ሆኖ የኮሚቴ ሰብሳቢዎች ተመድበውለታል።

• የማክሮ ኢኮኖሚ ጉዳዮች፣ የዕቃዎችና የአገልግሎቶች ኤክስፖርት-የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትሩ አቶ ሱፊያን አህመድ
• የግብርናና የገጠር ትራንስፎርሜሽን- የጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ በረከት ሰምዖን-
• የኢንዱስትሪ ልማትና የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ለውጥ- በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ ዶ/ር አርከበ ዕቁባይ
• ዘመናዊ የከተማ ልማትና የኮንስትራክሽን ዘርፍ አቅም ግንባታን- በጠቅላይ ሚኒስትሩ አማካሪ አቶ ዓባይ ፀሐዬ
• የሰው ሀብት ካፒታል ማሳደግና የቴክኖሎጂ አቅም ግንባታን – ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን
• ወሳኝ የመሠረተ ልማት ግንባታዎችና የማስፈጸም አቅም ግንባታ- በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪና የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል
* ልማታዊ መልካም አስተዳደር፣ ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ከምንጩ በማድረቅ ተወዳዳሪነትን ማጎልበት – ወ/ሮ አስቴር ማሞ
ዴሞክራሲን ማስፈን፣ ብሔራዊ መግባባት መፍጠርና የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሥራን የመተለከተ- አፈ ጉባዔ አባዱላ ገመዳ

በእነዚህ ኮሚቴዎች የታቀደው አገራዊ ዕቅድ ውይይት ከተደረገበት በኋላ አገሪቱ ለአምስት ዓመታት የምትመራበት ብሔራዊ ሰነድ እንደሚሆን የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ከሁለተኛው የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ የሚጠበቀው ምንድነው?

-የአቶ መለስ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ የታሰበውን መዋቅራዊ ለውጥ አላማምጣቱ በግልጽ እየተነገረ መሆኑ ይታወቃል። ሪፖተር ቀደም ሲል ስለ እቅዱ አፈጻጸም ጥናት ያደረጉና በጉዳዩ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚንስትር አቶ መለስ ዜናዊና አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ጋር ጭምር የተወያዩና በአማካሪነት የሠሩ ሁለት ጃፓናዊ ባለሙያዎችን ፕሮፌሰር ኪኒቺ ኦህኖ እና ፕሮፌሰር ኢዙሚ ኦህኖን ጠቅሶ እንደዘገበው በትራንስፎርሜሽኑ ይፋ የተደረገው የኢንዱስትሪ ፖሊሲ የሚፈለገውን ለውጥ አላመጣም። ለኢንዱስትሪ የሚመች ምንም መዋቅር ቀድሞ ባለመዘርጋቱ ነው። ዕቅዶቹን ሊያስተገበሩ የሚችሉ ተቋማትና ባለሙያዎች በሚያስፈልገው መጠን አልተሟሉም። በወዲህም በኩል ብቁ የሆኑ ኢንዱስትሪዎች ባለመኖራቸው የታቀዱት የወጪ ንግድ ግቦች አልተሳኩም።
መንግሥት በሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን ለውጥ ይመጣል ብሎ ተስፋ ካደረገባቸው መካከል ትልልቅ የውጭ ኩባንያዎች መምጣታቸው ዋናው ነው፡፡ የቻይና፣ የህንድ፣ የቱርክና የኮሪያ አምራቾችን ጨምሮ ከቅርብ ጊዜ በኋላ የጃፓን ትልልቅ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት ኢንቨስት ሊያደርጉ ማሰባቸው ለለውጡ ታሳቢ የተደረጉ ተስፋዎች ናቸው፡፡

ያለፈው እቅድ ተሳክቷል?

አቶ መለስ የአገሪቱን አጠቃላይ ገቢ በእጥፍ እናሳድጋለን ብለው ነበር። አልተሳካም። ያኔ 37 ቢሊዮን አካባቢ ነበር አሁን 40 ቢሊዮን ነው- አላጠፈም።
እንደ ኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ የአዲስ ዓመት ንግግር ከሆነ አልተሳካም። ፕሬዚዳንቱ በሰፕቴምበር 2014 በአራተኛው የህዝብ ተወካዮችና የፌዴሬሽን ምክር ቤቶች አምስተኛ የሥራ ዘመን የመጀመሪያ የጋራ ስብሰባ ላይ ያደረጉት የመክፈቻ ንግግር ይህን አያረጋግጥም። የ እቅዱ መለያ ባህርያት ተደርገው ከተወሰዱት ግዙፍ ሜጋ ፕሮጀከቶች መካከል ብቸኛው ተቀዋሚ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት (ፓርላማ) አባል ግርማ ሰይፉ ይህንን የ እቅዱን አለመሳካት ለፓርላማው አባላት የደረሰውን ሪፖርት አጣቅሰው ጽፈዋል። የጽሑፋቸው ፍሬ ነገር የአምስት ዓመቱን የልማትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ያወጣው ኢህ አዴግ እቅዱን ማሳካት አልቻለም። ምክንያቱም ራሱ ያወጣውን እቅድ እንኳ ማሳካት የሚችል ድርጅት አይደለም በማለት የእቅዱን ውጤት አብጠልጥለውታል።

የእቅዱን ዋና ዋና ትልሞች ለምሳሌ የአስፋልት መንገድ ሳይጨምር የገጠር ቀበሌዎችን ከዋና መንገድ ጋር የሚያገናኙ ከ71 ሺ ኪሎ ሜትር ክረምት ከበጋ የሚያገለግሉ መንገዶች ግንባታ አለመሳካቱን፣ 10 ሺ ሜጋ ዋት የሚደርስ የኢነርጂ ልማት ተግባራዊ አለመደረጉን፣ በማዳበሪያ ምርት ከፊል የሀገር ውስጥ ፍጆታን ይሸፈናል የተባለው አለመፈጸሙን ወዘተ እየጠቀሱ ነቅፈዋል። የ እቅዱ ዋነኛ ማጠንጠኛ የሆነው የኢንደስትሪ ሴክተሩንም አንስተው “የማኑፋክቸሪንግ ሴክተሩ የተጣለወን ሃያ በመቶ እድገት ለማሳካት የሚያስችል የግል ሴክተር ተነሳሽነት አይታይም፤ ቢመጣም ማነቆ ብዙ ነው፡፡” ብለዋል።

ይህ ጽሑፍ በዘ-ኢትዮጵያ ጋዜጣ ላይ ታትሞ ወጥቷል:: ርዕሱን ግን ለድረገጽ አንባቢዎች በሚስማማ መልኩ ቀይረነዋል::

The post ሃይለማርያም ደሳለኝ የመለስን ሌጋሲ ክደው ከባላንጣቸው ከአቶ አርከበ ጋር ሽር ጉድ ማለታቸው የት ያደርሳቸው ይሆን? (ሪፖርታዥ) appeared first on Zehabesha Amharic.

↧
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>