Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

አድዋ! –ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

hqdefaultዋ! አድዋ ፤ ያ ሑዳዴ

መድፍን ፈንጅን ፤ በጎራዴ

ባሕር ተሻግሮ ፤ የሐበሻን ምድር

ቅኝ ሊገዛ ፤ ይሄ ደፋር!

አንች አድዋ ፤ የበኩር ልጅ

ላንቺ ውልደት ፤ ስንቱ ሲፈጅ

ተጸንሰሽ ፤ ከውጫሌ

ለደም መሬት ፤ ለአሞሌ

እርግዝናሽ ፤ ዘጠኝ ወሩ

ዓመታትን ፤ ማስቆጠሩ

ክፉውን ቀን ፤ ይዞ አሳሩ

ከብቱ እረግፎ ፤ ባገር ምድሩ

ሰው ሁሉ አልቆ ፤ በችጋሩ

በፋሽስት ሸር ፤ በእኩይ ግብሩ

ከብት የሚፈጅ ፤ ደዌ ረጭቶ

በምን ታርሶ ፣ በምን ለምቶ

የገበሬው ፤ ሀብት ጠፍቶ

አከርካሪው ፤ ተመትቶ

የሚቀመስ ፤ እህል ታጥቶ

ረሀቡ ፤ ሕዝቡን በልቶ

ምኑ ተብሎ ፤ ስንቱን ነግሮ

የግፍ ግፉ ፤ ተዘርዝሮ

ዝም ይሻላል ፤ ምን ተቆጥሮ

በክፉው ቀን ፤ ራብ ደክሞ

ያለቀ ሕዝብ ፤ በአዋጅ ተሞ

በዚያ ድቀት ፤ ተጎድቶ

አፈር ልሶ ፤ ግድ ተነሥቶ

አይቀር ነገር ፤ የሀገር ጥሪ

ነፍሱ የሷ ፤ እሱ አኗሪ

ጉልበት ሆኖት ፤ የሀገር ፍቅሩ

አስቆጥቶት ፤ መደፈሩ

ገሰገሰ ፤ ወደ አድዋ

ጠላት ሊግት ፤ የሞት ጽዋ

አድዋ ላይ ፤ ከግንባሩ

ሊሞሻለቅ ፤ ሲተም ጦሩ

እንደ ሙላት ፤ ደራሹ ጎርፍ

ሲያስገመግም ፤ ጠላት ሊቀስፍ

ከተፍ ሲል ፤ ፊት ለፊቱ

ጥሊያን ራደ ፤ ልብ አጥቶ

ባለ የሌለ ፤ መሣሪያ አጉል

እያስጓራ ፤ ሲከላከል

በመድፍ አረር ፤ በመትረየስ

ግማሽ ሲቀር ፤ ሲሠዋ ነፍስ

ጠጋ ሲባል ፤ ወደ ምሽግ

ሌላ አሳር ፤ ምን ይደረግ?

በስል ችንካር ፤ በውጋቱ

በጠርሙስ ጦር ፤ በስለቱ

ምሽግ ማዶ ፤ በተከለው

አርበኛውን ፤ እንዲያስቀረው

ጠርሙስ አልፎ ፤ የፈንጅ ንጣፍ

ፋኖ የሚፈጅ ፤ በነፍስ ወከፍ

ያ ባዶ እግር ፤ ቢቀረደድ

ቢሸረከት ፤ ቢጎራረድ

ማን ተሰምቶት ፤ ለማን ታውቆ?

በፈንጅውም  ፤ ረግፎ አልቆ

ሊነሣ ይሻል ፤ ሞቶም ወድቆ

በወደቀው ፤ ተረማምዶ

ምሽግ ሰብሮ ፤ ጥሶ ንዶ

በጠላት ላይ ፤ ማት አውርዶ

ቆርጦ ሲጥል ፤ አንገት ጎርዶ

በፉከራ ፤ ቀልቶ አጭዶ

ሲፈጅ ሲማርክ ፤ ቆልቶ አሳዶ

ብቻ በሀገር ፤ በሕዝብ ፍቅር

በሚፋጀው ፤ እንደ ገሞር፡፡

አንች የረፋድ ፤ የድል ፀሐይ

የወጣሽው ፤ አድዋ ላይ

ከአባትሽ ፤ ከምኒልክ

ድባቅ መትቶ ፤ ካገባው ልክ

ከጣይቱ ፤ ከእናት ኩሩ

ፋኖዎቹ ፤ እያጋፈሩ

አድዋ ላይ ፤ ከአፈሩ

በቅዱሱ ፤ ጊዮርጊስ ለት

ተራድቶሽ ፤ ተርፈሽ ከሞት

ሰዓቱ ሲደርስ ፤ መወለጃሽ

በጭንቅ ምጥ ፤ የተወለድሽ

በሰው አጥንት ፤ በሰው ልጅ ደም

የታረስሽው ፤ የዓለም ሰላም

የሐበሻ ዘውድ ፤ የድል ማማ

በአጥንት ዕዳ ፤ በደም ጉማ

ምታስከፍይ ፤ ቃል ሲሰማ

ያችን ገልቱ ፤ ከንቱ ሮማ፡፡

አድዋ ቅኔ ፤ አድዋ ዜማ

የምትማርክ ፤ ምትስማማ

ለሰው ልጅ ልብ ፤ ያላት ግርማ

የአውሬን ልብ ፤ ምታደማ

በአፍታ ፍልሚያ ፤ ፈጣን ሽኝት

ወዲያው ብልት ፤ እዚያው ጥጥት

በአርበኛ ወግ ፤ በፋኖ ደንብ

ሳይገመት ፤ ሳይታሰብ፡፡

ነጭ በጥቁር ፤ በግፍ ገኖ

በጨካኝ ክንድ ፤ ይዞ አፍኖ

ጥቁሩ ሲኖር ፤ ተኮንኖ

መገልገያ ፤ ዕቃ ሆኖ

አሜን ወዴት ፤ አለሁ ብሎ

አንገት ሰብሮ ፤ ተገልሎ

በምድሪቱ ፤ በመላ ዓለም

በግፍ ሲኖር ፤ አጥቶ ሰላም

ለነጭ ተድላ ፤ ጥሮ ማስኖ

እሱ እንደሚያንስ ፤ ከልቡ አምኖ

ቅስም ሐሞቱ ፤ ነኩቶ ፈሶ

መራር ሐዘን ፤ ልቡ ውስጥ ነግሦ

ሲኖር ዘወትር ፤ ቀንበር አዝሎ

አድዋ ላይ ፤ የድሉ አውሎ

አሽቀንጥሮ ፤ ሸክሙን ጥሎ

ነጩን እባብ ፤ ላይድን ገሎ

አነሣለት ፤ ከስር ነቅሎ

አስበርግጎ ፤ አስደንብሮ

ፈነቃቅሎ ፤ ጥልቅ ሰርስሮ፡፡

እናም ዓለም ፤ ተገደደ

ውዳቂ ሐሳብ ፤ በግድ ካደ

አዲስ ታሪክ ፤ ተሰነደ

የተጠላው ፤ ተወደደ

ሰው መሆኑን ፤ የአዳም ዘር

ከነጭ ቢጫ ፤ ከቀይ ፍጡር

እንደማያንስ ፤ ምን ቢጠቁር

አረጋግጦ ፤ ቆመ በክብር

እድሜ ለዚያች ፤ የድል ፀሐይ

ለበራችው ፤ አድዋ ላይ

የባርነት ፤ ሰንሰለቱን

በጣጠሰ ፤ እግር ብረቱን

ተቀዳጀ ፤ ነጻነቱን

ቀበረለት ፤ ባርነቱን

የሀገሩ ፤ የመብቱ

ራሱ ሆነ ፤ ባለቤቱ

ዕድሜ ለዚያች ፤ የድል ፀሐይ

ለበራችው ፤ አድዋ ላይ

የምዕት ዓመታት ፤ ጣር ጨለማ

ተወገደ ፤ ድል ተሰማ

ያች ፀሐይ ፤ የድል ጮራ

ደማቅ ጸዳል ፤ የገድል አውራ

የከበረች ፤ ስጦታ ናት

ምንም ነገር ፤ የማይተካት

ከሐበሻ ሕዝብ ፤ ለጥቁር ዘር

ለተገፋው ፤ ለበላ አሳር፡፡

የካቲት 19 2007ዓ.ም.

The post አድዋ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on Zehabesha Amharic.


በቤይሩት ኢትዮያዊቷ ራሷን አጠፋች በሚል ሰበብ….. ኤምባሲው ያለምንም ምርመራ ሬሳዋን አሳፍሩ ማለቱ ብዙዎችን አሳዘነ

$
0
0

በግሩም ተ/ሀይማኖት
ኢትዮጵያዊኖች በአረብ ሀገራት ስደታቸው ጥሩም መጥፎም ይገጥማቸዋል፡፡ ብዙ ጊዜ ራሳቸውን አጠፉ በሚል ሰበብም አሰሪዎቻቸው ይገሏቸዋል፡፡ እንዴት ሞቱ የሚል ማጣሪያ ወይም ምርመራ አይደረግም፡፡ ከተቻለ ሬሳቸው ይላካል ካልሆነም ፍሪጅ ውስጥ ተቀምጦ ለተማሪዎች መለማመጃ ይደረጋል፡፡ የሚፈለግ አካልም ይወሰዳል፡፡ ሁሌም ይሄው ነው፡፡
ethiopian woman Arabባለፈው ሳምንት ሰኞ ዕለት ቤይሩት ውስጥ ሳይዳ ሀበፊ የተባለ አካባቢ አንዲት ኢትዮጵያዊት ሞተች፡፡ በአሰሪዎቿ በኩል ራሷን አጠፋች ነው የተባለው፡፡ በፎቶው ላይ እንደምታዩት ከልጅቷ ቁመት ያነሰ መስኮት ላይ ገመድ አስራ ነው ታንቃ የሞተችው ያሉት አሰሪዎቿ፡፡ ራሷን ለማጥፋት የሚያበቃ ምንም አይነት ችግር አልነበረባትም፡፡ ለሞት የዳረጋትን ነገር ቢያስቡ ቢያሰሉ የሚያገኙት ፍንጭ በማጣታቸው በርካታ ጓደኞቿ በሁኔታው ከፍተኛ የሆነ ጥርጣሬ አደረባቸው፡፡
እንዴት ከእሷ ቁመት ባጠረ ቦታ ላይ ታንቃ ሞተች? ሁኔታው አጠራጣሪ ነው ብለው ቤይሩት ላለው ኢትዮጵያ ኤምባሲ ደጋግመው ጥርጣሬያቸውን አመለከቱ፡፡ ኤምባሲው ከወትሮ አሰራሩ የተለየ ሁኔታ የለውም፡፡ በእነአለም ደቻሳ ጊዜ የታየው አለመቆርቆር መልኩንም ቅርፁንም አለወጠም፡፡ እንዲያውም ችላ ባይነቱን አሳድገውት የወሰዱት ርምጃ ብዙዎችን ያሳዘነ፣ እንባ ያራጨም ሆነ፡፡
መቼ ይሆን ለሞታችን መብታችን ለመረገጡ ሰሚ እና ተከራካሪ የምናገኘው የሚለው የዘውትር ጥያቄ ደጋግሞ ብልጭ እንዲል አደረገ፡፡ ኤምባሲው ለሉብናናዊቷ አሰሪ ስልክ በመደወል ያላትን እቃ ሰባስባችሁ አምጡ፡፡ በቃ!….
ለልጅቷ ቤተሰቦች ደውለን እንዲከሱ ለማድረግ ቢሞከርም ስልካቸው ሊነሳ አልቻለም፡፡ ያለው አማራጭ ለውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማሳወቅ ነውና ይህን ተግባር አከናወንን፡፡ መፍትሄ ይገኝ ይሆን? ሬሳዋ ፍሪጅ ውስጥ ተቀመጦ ቀረ፡፡ መቼ አስታውሰው ይልኩት ወይም ይቀብሩት ይሆን? ኢንሹራንሷንስ ኤምባሲው ዝም ይል ይሆን? ያነጋግራል፡፡

The post በቤይሩት ኢትዮያዊቷ ራሷን አጠፋች በሚል ሰበብ….. ኤምባሲው ያለምንም ምርመራ ሬሳዋን አሳፍሩ ማለቱ ብዙዎችን አሳዘነ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ዜና አትስሙ”ለሚለው ፓስተር ምላሽ –ክንፉ አሰፋ

$
0
0

በከፊል የተቀዳውን የፓስተሩን ንግግር የሰማሁት “ሰልማ”  የተሰኘውን ፊልም አይቼ እንደተመለስኩ ነበር። በዚህ አመት ለአራት የኦስካር ሽልማት የበቃው “ሰልማ” ፊልም ኦፕራ ዊንፍሬን ጨምሮ ምርጥ አክተሮች ይተውኑታል። ፊልሙ እ.ኤ.አ. በ1965 በዩናይትድ ስቴትስ የጥቁሮች የመምረጥ መብት ገፈፋን ተከትሎ፣  ዶክተር ማርቲን ሉተር ይህ መብት እንዲከበር የሚያደርገውን ትንቅንቅ ያሳየናል።  ፓስተር  ሉተር ለዜጎች የመምረጥ መብት እንዲከበር ያለማቋረት በመስበኩ ሲደበደብ፣ ሲንገላታና ሲታሰር እናያለን። በአላባማ ግዛት የሚኖሩ ጥቁሮች መብታቸውን ስለጠየቁ ብቻ የመርዝ ጭስ ቢረጭባቸው፣ ቢደበደቡ፣ ቢታሰሩ እና ቢገደሉም ሉተር ተስፋ አልቆረጠም።  ሰቆቃውን በብሄራዊ ቴሌቭዥን የሚያዩ ሁሉ በቁጭት ትግሉን ተቀላቀሉ።  ከግዜ  በኋላም የ”ሰልማ” እና የ”ሞንትጎመሪ” ጥቁሮች የመምረጥ መብታቸው ተጠበቀ።  በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተውን ይህንን ፊልም የሚያዩት ሁሉ በእንባ ይታጠቡ ነበር።

እዚህ ላይ ተስፋ ያለመቁረጥን ብቻ ሳይሆን የሜድያን ሚና፣ በተለይ ደግሞ የቴሌቪዥንን ሃይል እናይለን። ዘረኞች እና አንባገነኖች ሜዲያን የሚጠሉት ያለምክንያት አይደለም። በዩናይትድ ስቴትስ ዘረኝነቱ እንደተጠበቀ ሆኖ የመገናኛ ብዙሃኑ ነጻ በመሆኑ ህዝቡን ነጻ ሊያወጣው ችሏል።

የኛ ፓስተር ደግሞ ጭራሽ “ዜና አትስሙ” ሲል ይደመጣል። በዚያ በተነሳሽነት እና በቁጭት ስሜት ሆኖ የፓስተሩን ንግግር ለሚሰማው ደግሞ በጣም ያበሳጫል።  “አትስሙ” ሲል የመስማት መብትን መጋፋቱን አላስተዋለው ይሆናል። ፓስተሩ በዚህ አላበቃም የኢሳት ሰዎች ቅዥታሞች ናቸው ሲልም ይዘልፋል። ቀን ከለሊት ይቃዣሉ ሲል ፍርድ ሰጥቷል። ፍርድ ለመስጠት እርሱ ማን ሆኖ? መጽሃፍ የሚለን “አትፍረድ ይፈረድብሃል” ነው።

ክፉውን ነገር አትቃወሙ የሚል ነገር በመጽሃፍ ቅዱስ የለም። እንዲያውም በብሉይ ዘመን ነብያት የገዥዎችን ክፉ ስራ ያወግዙ ነበር። ይህ ሰው መንፈሳዊ ነኝ የሚለን ከሆነ ኢትዮጵያ በሚሰራውን ክፉ ነገር አንዲት ቀን ተቃውሞ ያውቃል?

ቄስ ወይንም ፓስተር ሲሆኑ ስራቸው ወንጌልን መስበክ ነበረበት። “ዜና አትስሙ” ማለት ወንጌል አይደለም። ፖለቲካ ነው። ለዚያውም ያንድ ወገን ፖለቲካ። እንዲህ አይነት መልእክት በቤተ-ክህነት ውስጥ ማስተላለፍ መንፈሳዊነት አይደለም። ንግግሩ  የጉባኤውን የግንዛቤ አቅም ዝቅ ከማድረግ የሚመጣ ንቀትም ይመስላል።

በኢትዮጵያ ያለው እውነታ ይህ ነው። ዜጎች በሽብር ስም ይታሰራሉ፣ ሰዎች ያለአግባብ ይሰቃያሉ፣ ወገኖቻችን ያለአግባብ ይገደላሉ፣…  መሬታቸው ለባእዳን እየተሰጠ ይፈናቀላሉ፣ ባለስልጣናቱ ያለ አግባብ ሃብት እያካበቱ ነው፣ ምርጫ ይጭበረበራል…. ዜናዎቹ እነኝህ ናቸው። ይህንን ሰምቶ የራሱን ግንዛቤ የመስጠት መብቱ የሰሚው ነው። ይህንን አትስሙ ማለት ምን ማለት ነው?
ESat

ዶክተር ማርቲን ሉተርም ፓስተር ነበር። ህልም ያለመ ፓስተር። ዜና ከመስማት ባሻገር ህዝብን ለመብቱ እንዲነሳ የሰበከ ፓስተር። በአመጽ-አልባ ትግል የጥቁሮችን መብት ያስጠበቀ ፓስተር። ፐሉተር ህልም የጥቁሮች የመምረጥ መብት  ብቻ ላይ አላበቃም።  አንድ ቀን ጥቁር ሰው ዩናይትድ ስቴትስ አሜሪካን  ይመራታል ብሎ ነበር። ይህ ህልሙ ከሞላ ጎደል በባራክ አኦባማ እውን ሆኗል።

እንዲህ አይነት አመለካከት ላላቸው የሃይማኖት መሪዎች፤ ዲታቆን፣ ቄስም ሆነ ፓስተሮች በሙሉ አንዲት መል እክት አለችኝ። ህልም ባይኖራችሁም፣ የዜጎች ህመም ባይሰማችሁም፣ ግፍን መቃወም ባትፈልጉም፤  ዝም ብላችሁ ወንጌልን ብቻ ስበኩ።  መንፈሳዊ ባልሆነ ንግግር የሌላው መብት አትጋፉት።

The post “ዜና አትስሙ” ለሚለው ፓስተር ምላሽ – ክንፉ አሰፋ appeared first on Zehabesha Amharic.

አድዋን ስንዘክር፡ –ማተቤ መለሰ ተሰማ

$
0
0

Battle of Adwaአስደናቂ ለሆነ የረጅም ዘመን አኩሪ ታሪክ ባለቤት የሆነችው፡ እናት ሃገራችን ኢትዮጵያ፡ ከ1762 እስከ 1845 ዓ.ም ድረስ በነበረው 70 አመት ጊዜ ውስጥ፡ በዘር ባይሆንም ልክ እንደዛሬው፡ ልጆቿ ተከፋፍለው፣ ልማትና ብልጽግናዋ ተገትቶ፣ ለሁለንተናዊ ውድቀት የተዳረገችበት ወቅት ነበር።

እጅግ በጣም የሚገርመው ደግሞ፡ ለዚያ ውድቀት የዳረጋት፡ የትግራዩ ተወላጅ እራስ ስዑለ ሚካኤል፡ አማቱንና በወቅቱ የነበሩትን ንጉስ አጼ ኢዩአሰን በቤት አሽከሮቻቸው አሳንቆ በማስገደሉ ነበር።

34

ማተቤ መለሰ ተሰማ

እንግሊዝ አጼ ቲዮድሮስ፡ ያሰሩባትን ዜጎቿን እነ ቆንሲል ካሜሮንን፡ በሃይል ለማስፈታት፡ ወደ ኢትዮጵያ ጦሯን በላከች ጊዜ፡ በሮቤርት ናፒር የሚመራው ወራሪው ጦር ከምጽዋ ዙላ፣ ከዙላ ሰናፈ፣ ከሰናፈ አሸንጌ፣ ከአሸንጌ ሙጃ፣ ከሙጃ መረዋ፡፡ በማረፍ እየተዝናና እና መንገድ እየሰራ ሚያዚያ 2 ቀን 1860 ዓ.ም. በሸሎ እሰኪደርስ ድረስ፡ መንገድ በመምራትና በመንከባከብ አምጥተው፡ የእኒያን ብሄራዊ ጀግና፡ የአጼ ቲዮድሮስን እልፈተ ህይወት ያፋጠኑት፡ አሁንም የትግራዩ ተወላጅ፡ ካሳ ምርጫ፡ ወይንም በንግስና ስማቸው አጼ ዩሃንስ እንደ ነበሩም ይነገራል። ምንም እንኳን በሗላ ከወራሬ ጋር ሲፋለሙ በክብር ቢወድቁም።

ዛሬ በምናሰበው በ1888 ዓ.ም አድዋ ላይ በተካሄደው፡ የኢትዮጵያና የኢጣልያን ጦርነት ጊዜ በእራስ መኮንን የሚመራው ቀዳሚ ጦር። አምባላጌ እንደደረሰ ገና መሬት ሳይዝ በወጊያ የጠመዱትም የትግራይ ተወላጅ ባንዳዎች ናቸው።

በ1928 ዓ.ም በሁለተኛው የኢጣልያ ወረራ ወቅት፡ አርበኛው ፊትለፊ ከጠላት ጋር ሲፋለም፡ በትግራይ በቀሉ ባንዳ በደጃዝማች ሃይለስላሴ ጉግሳ፡ የሚመራው የትግራይ ተወላጆች ስብስብ፡ ተመሳስሎ በጀርባ እየገባ ያልተጠበቀ አድጋ በማድረስ፡  ለሽንፈታችን ትልቅ አስተዋጽኦ ከማድረጉም በላይ፡ ሲሸሽ እየተከታተለ የደከመውንና ቁስለኛ ወንድሙን በመግደል፡ ከኢጣልያን የከፋ በርካታ የኢትዮጵያን አርበኛ ፈጅቷል።

ሀምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. አቡነ ጴጥሮስ አዲስ አበባ ላይ ሲረሸኑ፡፡

ህዳር24ቀን 1929 ዓ.ም. አቡነ ሚካኤል ጎሬ ላይ ሲረሸኑ፡፡

የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም. በግራዞያኒ ትእዛዝ አዲስ አበባ ላይ ከ30 ሺህ የማያንስ ህዝብ ሲጨፈጨፍ፡፡ ትዕዛዝ ፈጻሚዎቹ  አሁንም ትውልደ ሰሜን ወንድሞቻችን  ነበሩ።

1969ዓ.ም ሶማሌ ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅትም፡ ወያኔ መቃድሾ ከተማ ቢሮ ከፈቶ፡ በተለይ በሰራዊታችን ውስጥ የእሱን ሰው አሰርጎ በማስገባት፡ ለጠላት መረጃ ከማቀበል ጀምሮ፡ የሶማሌ የስለላ ማዕከል፡ የኢትዮጵያ ጦር ግንኙነት የሚያደርግበትን፡ ሬዲዮ እየጠለፈ ሲያቀርብለት በመተርጎም፡ ለሶማሌ ሰራዊት እየሰጠ በኢትዮጵያዊያን ላይ ጉዳት እንዲደርስ በማድረግ ትልቅ ክዕደት ሲፈጽም ነበር።

በአብዛኛው ማለት በሚያስደፍር ሁኔታ፡ በሃገራችን ላይ ወረራ በተሰነዘረ ቁጥር በርካታ የትግራይ ተወላጆች፡ ከጠላት ጎን በመሰለፍ የእናታቸውን ጡት ሲነክሱ ለመኖራቸው ድርሳናቶቹ ሁሉ ቁልጭ አድርገው ያመላክቱናል።

ዛሪም ታሪክ እራሱን ደገመና፡ ትግራይ የፈለቁ ጉዶች ናቸው፡ እኛን በዘርና በሃይማኖት ከፋፍለው፡ ኢትዮጵያ የምትባል ሃገር እንደምስራቅ ጀረመንና እንደ ዩጎዘላቢያ ከዓለም ካርታ እንድትፋቅና እኔ ኢትዮጵያዊ ነኝ በማለት አፍ ሞልቶ ደረት ነፍቶ የሚናገር ዜጋ እንዳይኖር 24 አመት ሙሉ ሽንጣቸውን ገትረው በመስራት ላይ ያሉት።

ይህንን ስል ግን ትውልደ ትግራይ ሆነው፡ ለአገር አንድነትና ለወገን ነጻነት፡ የተጋደሉ አልነበሩም። አሁንም፡ የሉም እያልሁ አይደለም። ትናንት እነ አሉላ አባነጋን፣ እነ እራስ ስዩም መንገሻን፣ እነ ደጃዝማች አርያን እነ እራስ መነገሻ ስዩምን፣ ወ.ዘ.ተ. ዛሪም የትግራይ ዲሞክራሴያዊ ንቅናቄ ሰዎችን በተለይም የድርጅቱ መሬ የነበረውንና አሁን በህይወት የሌለውን ፍስሃ ሃይለማርያምን የመሰለ የሃገር

2.. ፍቅር ያንገበግበው የነበረውን። እነ ገብረመደህን አርያን፣ እነ አብርሃ በላይን፣ እነ አብረሃ ደስታን፣ እነ አስራት አብርሃምን ያፈራች ስለሆነ።

መነሻዬ የኢትዮጵያን ታሪክ፡ ወይንም የትግራይ በቀል የጥፋት መልክተኞችን ጉድና ሁላችንም ተደራሲዎች የሆንበትን፡ የወያኔን መግለጫ ቃላት መለኪያ መስፈርት የማይገኝለትን፡ የግፍ ክምር እየናድሁ የምታውቁትን በመድገም ጊዜያችሁን ለማባከን አስቤ አይደለም።

ይልቁንም በትግራዩ ተወላጅ፡ በእራስ ስዑለ ሚካኤል፡ መሰሬ ተንኮል ተበታትና የነበረችዋን ኢትዮጵያን፡ እምዬ ምኒልክ። እንዴት መልሰው እንደገነቧት በአይነ ህሌናችሁ ወደሗላ እንደትመለከቱ ለማነሳሳትና ለውይይት ሃሳብ ለማጫር  የተጠቀምሁበት ነው እንጅ።

ወደዛሬው ምልከታየ ስገባ።

አጼ ምኒልክ ነሃሴ 12 ቀን 1836 ዓ.ም በሽዋ ክፍለ ሃገር በተጉለትና ቡልጋ አውራጃ አንጎለላ ኪዳንምህረት ተወለዱ። ከ12 አመት እድሜያቸው ጀምሮ በግዞትም፣ በማደጎም፣ በአማችነትም ከአጼ ቲዮድሮስ ቤት አደጉ።

ከእድገታቸው እስከ ንግስናቸው ያለውን ታሪክ ለጊዜው ላቆየውና። ከነገሱ በሗላ በተለይም ከዛሬው መሰባሰቢያችን ጋር በቀጥታ የተያያዘውን ከፋሽትት ኢጣልያን ወራሬ ጦር ጋር ያደረጉትን ተጋደሎ ባጭሩ ልጥቀስ።

እምዬ ምኒልክ መላዋን ኢትዮጵያን ከማስረዳደራቸው በፊት። የሽዋ ንጉስ በነበሩበት ወቅት ከኢጣልያን መንግስ ጋር ወዳጅ በመሆናቸው እስከ መሳሬያ እርዳታ ድረስ ያገኙ ነበር። በሗላ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ግን። ኢጣልያን  ኢትዮጵያን ለመውረር በነበራት ፍላጎት መሰረት በአጼ ዩሃንስ ጊዜ የጀመረችውን ወረራ እያሰፋችና  እየገፋች ስትመጣ። በምኒልክና በኢጣልያን መንግስት መካከል የቆየው መልካም ግንጉነት እየሻከረ ሄደ።

አጼ ምኒልክ ከኢጣልያን ጋር የነበረው ወዳጅነታቸው እንዲቀጥል አጥብቀው  ቢጥሩም። በኢጣልያን በኩል ግን ተቀባይነት አላገኙም ነበር። በተለይም የውጫሌ ውል እየተባለ በሚጠቀሰው አንቀጽ 17 ላይ በኢጣልያነኛ የተጻፈው ሃገራቸውን እንደሚጎዳ ሲገነዘቡ ክተት ሰራዊት ምታነጋሬ በማለት የሚከተለውን ጥሬ ለመላው ኢትዮጵያ ህዝብ አስተላለፉ።

የአጼምኒልክ ጥሪ ሙሉ ቃል

እግዚያብሄር በቸርነቱ እስካሁን ጠላት አጥፍቶ አገር አስፍቶ አኖረኝ። እኔም እስካሁን በእግዚያብሄር ቸርነት ገዛሁ። እንግዴህ ሞት ለሁሉ ነውና ብሞትም በእኔ ሞት አላዝንም። ደግሞ እግዚያብሄር አሳፍሮኝ አያውቅም። ከእንግዴህም ያሳፈረኛል በዬ አልጠራጠርም።

አገር የሚያጠፋ፣ ሃይማኖት የሚለውጥ፣ ጠላት እግዚያብሄር የወሰነልንን የባህር በር አልፎ መጧል። እኔም የሃገሬን ከብት ማለቅ የሰውንም መድከም አይቸ ዝም ብለው እያለፈ እንደፍልፈል መሬት ይቆፈር ጀመር። አሁን ግን በእግዚያብሄር እረዳትነት ሃገሬን አሳልፊ አልሰጥም።

የሃገሬ ሰው ከአሁን በፊት የበደልሁህ አይመስለኝም። አንተም እስካሁን አላስቀየምከኝም። ጉልበት ያለህ በጉልበትህ እርዳኝ። ጉልበት የሌለህ ለልጅህ፣ ለሚስተህ፣ ለሃይማኖትህ ስትል በሃዘን እርዳኝ። ወስልተህ የቀረህ ግን በሗላ ትጣላኛለህ። ማርያምን ለዚህ አማላጅ የለኝም። ዘመቻየ በጥቅምት ነውና የሽዋ ሰው እስከ ጥቅምት እኩሌታ ወረኢሉ ከትተህ ላግኝህ።

የጥሬው መጨረሻ።

በማለት ካዘዙ በሗላ በእራስ መኮነን የሚመራውን ቃፊር ጦር አስቀድመው እሳቸው ህዳር 2 ቀን 1888 ዓ. ም ከአዲስ አበባ በመነሳት ወደ ሰሜን አመሩ።

ንጉሱ በመንገድ ላይ እንዳሉ በራስ መኮነን የሚመራው ቀዳሚ ጦር አምባላጌ ደረሰ። በዚህ ወቅት የኢጣልያን ጦር። የኢትዮጵያን ጦር ከመንግድ እንደመጣና እንደደከመ እንደገናም ቦታ ሳይዝ። ለመምታት ተዘጋጅቶ ቅድም እንዳልኩት በርካታ ትግራይ በቀል ባንዳዎችን በማሰለፍ ውጊያ ከፈተበት። ግን ከ6 ስአት በላይ በፈጀው ጦርነት። ኢጣልያን የመጀመሬያውን የሸንፈት ጽዋ። በእራስ መኮነን ጦር ተጎነጨና ከአምባላጌ ምሽጉ ተባበረ።

አጼምኒልክም ታህሳስ 29 ቀን 1888 ዓ.ም መቀሌ እንደደረሱ። አዚያ ሰፍሮ የነበረውን የጠላት ጦር ዙሬያውን በማስከበብ የሚጠጣው ወሃ ከማሳጣታቸውም በላይ። በውጊያም መድረሻ ስላሳጡት

3.

ያለቀው አልቆ የተረፈው የሃገር ሽማግሌዎችን አማላጅ በመላኩ መንገድ ተከፍቶለት ወደ አዲግራት ሸሸና ለሁለተኛ ጊዜ ሽንፈቱን አጣጣመ።

በዚህ ዘመቻ በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፈው ሰራዊት። መቶሽህ እንደሚደርስ የሚገመት ሲሆን። ከዚህ መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆነው አርበኛ ጦርና ጎራዴ ብቻ የታጠቀ እንደነበርና ጠብመንጃ ያለውም ቢሆን ጠላት ከታጠቀው ዘመናዊ መሳሬያ ጋር ሲነጻጸር የሰማይና የመሬት ያህል የተራራቀ እንደነበር የታሪክ ጸሃፍት ያሰምሩበታል።

በዚህ ጦርነት በኢትዮጵያ በኩል የተሰለፉ ዋና ዋና የጦር አዝማቾች።

  1. እትጌ ጣይቱ ብጡል፡

2.ንጉስ ተክለ ሃይማኖት፡

3.ፍታውራሪ ገበየሁ፡

4.ደጃዝማች ጫጫ፡

5.እራስ መኮንን፡

6.እራስ መንገሻ ስዩም፡

7.እራስ መንገሻ አቲከም፡

8.እራስ ሚካሌል፡

9.እራስ ወሌ ብጡል፡

10.ደጃዝማች በሻህ አቡዬ፡

11.እራስ ጉግሳ፡

12.እራስ አሉላ አባነጋ፡

13.ዋግሹም ጓንጉል፡

14.እራስ ወርቄ  የተባሉት ነበሩ።

በኢጣልያን በኩል የጦር አዛዦች ደግሞ፡

  1. ጠቅላይ አዛዡ ሌትና ጀሪናል ባራቲይሪ፡
  2. ጀኔል ዦሴፔ ኦሪሞንዱ፡
  3. ጀኔራል አማኑኤል ደቦርሜዳ፡
  4. ጀኔራል ማቲዮስ አልቤርቶኒ፡
  5. ጀኔራል ዦሴፔ ኤሌና፡
  6. ኮሎኔል ቫሊንዞኖ፡ ነበሩ።

በዚህ የሃይል አሰላልፍ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም ልክ የዛሬ 119 አመት ከሌሊቱ በ11 ስአት በኢጣልያን ተንኳሽነት  አድዋ ላይ ወሳኙ ጦርነት ተከፈተ።

ሊነጋጋ ሲል ከሌሊቱ በ11 ስአት የተጀመረው ጦርነት። ቀኑን ሙሉ ውሎ ከሌሊቱ 5 ስአት በኢትዮጵያ አሸናፊነት ተጠናቀቀና ሃገራችን ኢትዮጵያ በጥቁር አንበሶች ልጆቿ አጥንት ክስካሽና ደም ፍሳሽ ሃያልነቷ በአም ሁሉ ተናኘ።

ውጤቱም የአለም ህዝብን  አስደነቀ። የጀግኖች አባቶቻችን አይበገሬነትም በማያጠራጥር ሁኔታ ታወቀ።  በኢጣልያን በኩል ከተሰለፉት የጦር አዛዦች መካከል ከጠቅላይ አዛዡ ከሌትና ጀኔራል ባራቲይሪ በቀር ሌላው የጦር አዛዥ ጀኔራልና ከፍተኛ መኮንን በሙሉ ተደመሰሱ።

በኢጣልያን በኩል ከተማረከውና ቆስሎ ከሸሸው ሌላ 9215 ተዋጊ ሲሞት። ከኢትዮጵያ 7000 ሰው ሞቷል። ከዚህ ውስጥ ከወገን የሞቱ አዋጊዎች።

  1. ደጃዝማች በሻህ አቡዬ፡
  2. ደጃዝማች ጫጫ፡
  3. ፍታውራሪ ገበየሁ፡
  4. ፍታውራሪ ተክሌ፡
  5. ቀኛዝማች ታፈሰ አባይነህ፡
  6. ፍታውራሪ ዳምጠው፡
  7. ደጃዝማች ማናዬ፡

4.

  1. ፍታውራሪ ወልደ ሚካሌል።
  2. ቀኛዝማች ተገኘወርቅ፡
  3. ፍታውራሪ አምባዬ።
  4. ቀኛዝማች ተሰማ ወልዴ፡
  5. ፍታውራሪ ሸንኮሩ፡
  6. ባላንበራስ በለው፡

14.ባላንበራስ አደራ ወ.ዘ.ተ. ይጠቀሳሉ።

ማጠቃለያ

በጣም የሚገርመው የአውሮፓ ሃያላን መንግስታት። አፍሪካን በቅኝ ለመግዛት። እንደ ቅርጫ ስጋ የተከፋፈሉበትና። እርስ በርስ ላለመነካካት የተፈራረሙት የካቲት 26 ቀን 1877 ዓ.ም ከአድዋ ጦርነት ከ3 አመት በፊት ሲሆን። በክፍፍሉም።

1ኛ. እንግሊዚ፡ ግብፅን፣ ሱዳንን፣ ናይጀርያንና ኬንያን።

2ኛ. ፈረንሳይ፡ ምህራብና ሰሜን አፍሪካን።

3ኛ. ፖርቱጋል፡ አንጎላንና ሞዛቢክን።

4ኛ. ጀርመን፡ ታንዛንያንና ቶጎን።

5ኛ. ቤልጅም፡ ኮንጎን።

6ኛ. ኢጣልያን፡ሶማልያንና ሊብያን ወ.ዘ.ተ በማድረግ ሲከፋፈሉ።

ኢትዮጵያን አልነኳትም ነበር። ምክናያታቸውም የረጅም ዘመን የተጠናከረ መንግስትና። አይበገሬ ህዝብ  እንዳላት ስለሚያውቁ።  እንደሆነ ይነገራል የተጨበጠ ማስረጃ ባይኖርም።

ዛሪስ በእኔና እናንተ ድርሻ። ሃገራችን ኢትዮጵያ በዓለም ህዝብ ዘንድ የነበራትን ክብር እንዳስጠበቀች ነች ወይ? የሚል ጥያቄ  ቢነሳ ሁላችንንም የሚያስማማን መልስ። አይደለም የሚለው እንደሚሆን አልጠራጠርም። ለምን? ከተባለ ልንሰጠው የምንችለው ምላሽ ግን የተለያየ እንደሚሆን እገምታለሁ።

በበኩሌ የእኔና የእናንተ ትውልድ ፈጹም እራስ ወዳድ ስለሆነ። ሌላው ሞቶለት እሱ ተጠቃሚ መሆንን ስለሚያሰላ ነው የሚል ነው ።

እናንተስ በእኔ ሃሳብ ትስማማላችሁ? አይደለም ሌላ ምክናያት ስላለ ነው ወኔ የከዳን የሚል ካለ ለመስማት ዝግጁ ነኝ። መልካም ውይይት እያልሁ እንደ እናንተው ቁጭ ብዬ የግል አስተያይቴን መሰንዘር እችል ዘንድ ዝግጅቴን በምትከተለዋ አጭር የግጥም ስንኝ ልቋጭ።

እርዕሷንም አድዋ ብያታለሁ!!

አድዋ

ከሰሜን ከደቡብ ከመግቢያና መውጫ፣

ከምስራቅ ከምእራብ ከሉም አቅጣጫ።

ቋንቋ ሳይለያቸው ዘር ማንዘር ሳይቆጥሩ፣

አማራ ኦሮሞ በማለት ሳይጠሩ፡

በዚያች የቁርጥ ቀን ቀድመው የደረሱ፣

ጥንት አባቶቻችን እነዝናር ልብሱ፡

ምሳሌ በመሆን በኩራት ሲጠሩ፣

ከመቃብር ጀርባ ዝንታለም ሊኖሩ፣

በአድዋ መልካ ላይ ታሪክን የሰሩ።

አባቶች ነበሩን የሃገር መከታ፣

ህይወት የሚሰጡ በመሆን አለኝታ።

እጅ ለእጅ ተሞሻልቀው በታጠቁት ካራ፣

ፈንጥቀው ያአለፉ እንደ ንጋት ጮራ።

ምኒልክ ለአድዋ ባቀረቡት ጥሪ፣

ያች ጣይቱ ብቱል ሆነች የጦር መሬ።

አዎ!! አድዋ!! አድዋ!! አድዋ!!

5.

የዛሬ ማፈሪያ የትናንት መኩሪያዋ፡

የዛሬ ማፈሪያ የትናንት መኩሪያዋ።

አመሰግናለሁ፡

ማተቤ መለሰ ተሰማ

በ2007 የ119ኛው የአድዋ የድል ባል በኖርዌይ የኢትዮጰያ ማህበር ሲያከብር የቀረበ የውይት መነሻ።

The post አድዋን ስንዘክር፡ – ማተቤ መለሰ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ኢትዮጵያ ከሰሜ ኮሪያ መሳሪያ መግዛት አለመግዛቷን ምርመራ መጀመሩ; እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ማቋረጧ; 125 ኢትዮጵያውያን ወደሃገራቸው መላካቸው; የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማድመጥ ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መመደቧ; ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ መከልከላቸውና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


ህብር ሬዲዮ የካቲት 22 ቀን 2007 ፕሮግራም
እንኳን ለ119ኛው የአድዋ ድል በዓል አደረሰዎ

አቶ ኦባንግ ሜቶ በህብር ሬዲዮ 5ኛ አመት እና 119ኛ የአድዋ ድል በዓል በተከበረበት ወቅት በቬጋስ ተገኝተው ያደረጉት ንግግር(ሙሉውን ያዳምጡ )

<...ኢትዮጵያውያን የአድዋን ድል ብቻ መዘከር ሳይሆን በአድዋ ሳቢያ የፋሺስቱ ጣሊያን አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ከ40 ዓመት በኋላ መቶ የጨፈጨፈበትን ንብረት የዘረፈበትንና ያወደመበትን የግፍ ድርጊት በአለም አቀፍ ደረጃ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝና የኢትዮጵያም ተገቢውን ካሳ እንድታገኝ የጀመርነውን ጥረት ማገዝ...የተቃውሞ ፊርማውን ...> አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የአለም አቀፍ ፍትህ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ስራአስኪያጅ ከተናገሩት የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡ )

ስለ ፕሮስቴት ካንሰር ከዶ/ር ሙሉጌታ ካሳሁን ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ
አድዋ ግጥም በመርሻ አያሌው
ጣይቱ ግጥም በሐይማኖት ይመኑ

(ልዩ ዘገባ የሩሲያው የተቃውሞ መሪ መገደልና የቀሰቀሰው አለም አቀፍ ተቃውሞ)
ሌሎችም
ዜናዎቻችን:-
የእንግሊዝ መንግስት ለኢትዮጵያ አገዛዝ የሚያደርገውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር ዕርዳታ ማቋረጡን ገለፀ።

ኢትዮጵያ ማዕቀብ ከተጣለበት ሰሜን ኮሪያ የጦር መሳሪያ ትግዛ ወይም አትግዛ ለማጣራት የተባበሩት መንግስታት ምርመራ ጀመረ

አንድ ከፍተኛ የደቡብ አፍሪካን ዲፕሎማት ከሁለት ዓመት በፊት አዲስ አበባ ላይ ለመግደል በተጠነሰሰ ሴራ እጇ አለበት የተባለችው ሱዳን አቋሟን ገለፀች።

ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መደበች:: የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማዳመጥ ነው ተብሏል።
የመኢአድ በተለያየ ደረጃ ያሉ ከመጭው የይስሙላ ምርጫ እራሳቸውን ማግለላቸውን ቀጥለዋል ፓርቲው በጉዳዩ ላይ የሰጠው መግለጫ የለም።

125 ኢትዮጵያውያን ስደተኞች ከየመንና ከታንዛኒያ ወደአገራቸው እንዲመለሱ ተደረገ።

የአገር ቤቱ አገዛዝ የፖለቲካ ጥገኝነት የሰጣቸው የቀድሞው የየመን ፕሬዝዳንት ቢሊየነር መሆናቸው ተጋለጠ።

ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ ተከለከሉ። በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ጦማሪያን ዛሬም የአገራቸው የነፃነት ጉዳይ እንደሚያሳስባቸው ገለፁ::

“የነፃነት ጥያቄዎች እስኪመለሱ ሙያዊ ነገሮችን ወደ ጎን ማድረግ ያስፈልጋል:
ጦማሪ ናትናኤል ፈለቀ።
በእስር ላይ የሚገኙት የዞን ዘጠኝ ጦማሪያንና ጋዜጠኞች ዛሬም የአገራቸው የነፃነት ማጣት እንደሚያሳስባቸው ለጥየቃ ለሄዱ ጋዜጠኞች ገለፁ

The post Hiber Radio: ኢትዮጵያ ከሰሜ ኮሪያ መሳሪያ መግዛት አለመግዛቷን ምርመራ መጀመሩ; እንግሊዝ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን የ4.9 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ ማቋረጧ; 125 ኢትዮጵያውያን ወደሃገራቸው መላካቸው; የኢትዮጵያን የልብ ትርታ ለማድመጥ ግብፅ የአባይ ወንዝን ለመገደብ ለደቡብ ሱዳን 2 ቢሊዮን ዕርዳታ መመደቧ; ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋን ለመጠየቅ ቃሊቲ የሔዱ መከልከላቸውና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

አበበ ገላው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የ20 ሚሊዮን ዶላር ቅጥፈት አጋለጠ

$
0
0

dr_tedros_adhanom
ቴድሮስ አድሃኖም ያራገቡት የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት የፈጠራ ወሬ መሆኑ ተረጋገጠ * የአውስትራሊያ መንግስት እና የሮተሪ ፋውንዴሽን በሪቱ ጃለታን አናውቃትም ገንዘብም አልሰጠንም አሉ

በአበበ ገላው

(አዲስ ቮይስ) ሰሞኑን የህወሃት መራሹ መንግስት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የሆኑት ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም በአንድ የአውስትራሊያ ትምህርት ቤት የ8ኛ ክፍል ውድድር አሸናፊ በመሆን እና አስደናቂ ውጤት በማምስመዝገብ 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በማሸነፍ ያገኘችውን ገንዘብ ለልማት ለማዋል ኢትዮጵያ ትገኛለች የተባለችን የ14 አመት ልጅ በመገናኛ ብዙሃን እና በማህበራዊ ድረ ገጾች ከማስተዋወቅ አልፈው በቢሯቸው ከልጅቷ ጋር ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸው ይታወሳል።

ሚኒስትሩ በሪቱ ጃለታ አህመድ ገና በለጋ እድሜዋ ይህን ያህል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ለልማት በማዋሏ ለኢትዮጵያዊያን በተለይ ደግሞ ለዲያስፖራው አርአያ መሆኗን በይፋ አውጀው ነበር። ወጣቷ የሽልማት ገንዘቡን በሙሉ አባቷ አቶ ጃለታ አህመድ በተወለዱበት በምስራቅ ሀረርጌ፣ ጋራ ሙለታ፣ ትምህርት ቤት ልታሰራበት ማቀዷን ለጋዜጠኞች በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተገኝታ ከሚኒስትሩ ጋር በጋራ በሰጠችው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ይፋ ያደረገች ሲሆን ገንዘቡ የተገኘው ከፊሉ ከአውስትራሊያ መንግስት፣ ከፊሉ ደግሞ ከአውስትራሊያ የሮተሪ ክለብ መሆኑን ይፋ አድርጋ ነበር።
tewedros
ይሁንና ሸልማቱን አዘጋጀ የተባለው ባደን ፓወል ኮሌጅ በመባል የሚጠራው የመንግስት ትምህርት ቤት ስለጉዳዩ ምንም የሚያውቀው ነገር ባለመኖሩ ግራ በመጋባት ጉዳዩን ለምርመራ ወደ ፖሊስ መምራቱን ለማረጋገጥ የቻልን ሲሆን የአውስታራሊያ መንግስት እና ሮታሪ ፋውንዴሽን በበኩላቸው ለአዲስ ቮይስ በተናጠል በሰጡት መግለጫ እንዳረጋገጡት ለታዳጊዋ ምንም አይነት ገንዘብ አለመስጠታቸውን እንዲሁም ስለ እርሷም ሆነ ስለተባለው ውድድርና ሽልማት ሰምተው እንደማያውቁ አረጋግጠዋል።

የአውስትራሊያ የውጭ ጉዳይና ንግድ ሚኒስቴር በጹሁፍ በላከልን መግለጫ አንደገለጸው የአውስትራሊያ መንግስት በኢትዮጵያ ጋራ ሙለታ ትምህርት ቤት ለማሰራት 10 ሚሊዮን ዶላር ሰጠ መባሉን አስተባብሏል። ሚኒስቴሩ አክሎም በኢትዮጵያ ለትምርት በቀጥታ ድጋፍ ባይሰጥም ኢትዮጵያ ከሌሎች ሃገሮች ጋር ተጠቃሚ በሆነችበት አለም አቀፍ የትምህርት የጋራ ትብብር (Global Education Partnership) በኩል ድጋፍ እንደሚሰጥ ጠቁሞ ኢትዮጵያ በትብብሩ በኩል በሚሰጠው የገንዘብ እርዳታ ተጠቃሚ ነች በማለት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጄና ሃንድ አክለው ገልጸዋል።
Bruce Allen
በአውስትራሊያ የሮታሪ ፋውንዴሽን ስራ አስኪያጅ የሆኑት ብሩስ አለን በበኩላቸው ስለ ተሸላሚዋም ልጅም ይሁን ስለሽልማቱ ከዚህ በፊት ሰምተው እንደማያውቁ አስገንዝበው ድርጅቱ የተባለውን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ እንኳን ለልጅ ሊሰጥ ለራሱም የበጎ አድራጎት ፕሮጀክቶች ማስፈጸሚያ በቂ ገንዘብ እንደሌለው አስረግጠው ተናግረዋል። ስራ አስኪያጁ አክለው እንደገለጹትም ባለፈው አመት የበጀት አመት ሮተሪ በ አውስትራሊያ ያሰባሰበው ገንዘብ መጠን 5.6 ብቻ መ ሆኑን ጠቁመው 10 ሚሊዮን ዶላር ለልጅቷ በሽልማት መልክ ሰጠ መባሉ በጣም የሚያሳዝን ክስተት መሆኑን ገልጸዋል። ባለፈው አመት ሮታሪ ኢንተርናሽናል በአለም አቀፍ ለትምህርት ነክ እንቅስቃሰዎች የሰጠው ገንዘብ 6.5 ሚሊዮን ዶላር በቻ የበረ ሲሆን ይህም ገንዘንብ ለ66 ፕሮጄክቶች መከፋፈሉን ለማወቅ ተችሏል።

ከዚህ በፊት በአለም ላይ ተሰምቶና ታይቶ የማይታወቀውን ይህን “ታልቅ ውድድር” እና የ20 ሚሊዮን ዶላር ሽልማት አዘጋጀ የተባለው የአውስትራሊያው የመንግስት ትምህርት ቤት1800 ተማሪዮችና 180 ሰራተኞች የሚሆኑ ያለከፍያ በበጎ አቃድ የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን አመታዊ በጀቱ 12 ሚልዮን የአውስትራሊያ ዶላር ነው። ይህም ማለት የትምህርት ቤቱ አመታዊ በጀት ለ14 አመቷ ልጅ ሰጠ ከተባለው ሽልማት በ8 ሚሊዮን ዶላር የሚያንስ ሲሆን የሽልማት ገንዘቡን ትምህርት ቤቱ እንዴት እንዳሟላው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩም ይሁኑ ተሸላሚዋ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ ማብራሪያ አልሰጡም።

ሌላው አስገራሚ ጉዳይ በሪቱ ሽልማቱን አገኝ በተባለው ያለፈው የበጀት አመት የአውስትራሊያ መንግስት በገዘብ እጦት ምክንያት ከሰሃራ በታች ላሉ የአፍሪካ አገሮች የሚሰጠውን እርዳታ መጠን ከ225 ሚሊዮን በ37በመቶ በመቀነስ ወደ 133 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር በመቀነሱ በአለም አቀፍ ደረጃ ሲተች የበነረ ሲሆን የበጀት ቅነሳ ያደረገው ለልጅቷ ለመስጠት አለመሆኑን ግን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ መግለጫ ለመረዳት ተችሏል።
ይሁንና ይህ ጉዳይ በዙዎች ዘንድ ሆን ተብሎ ለስውር አልማ የዋለ የህወሃት ውስብስብ ተንኮል ጋር የተያያዘ ነው በማለት ጥራጣሪያቸውን በስፋት በመግለጽ ላይ ይገኛል ።

The post አበበ ገላው የዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖምን የ20 ሚሊዮን ዶላር ቅጥፈት አጋለጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ ቢጀምርም ለቅስቀሳ የወጡት እየታፈኑ መሆኑ ተገለጸ

$
0
0

semayawi party
ሰማያዊ ፓርቲ ዛሬ የካቲት 24/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሁሉም ክፍለ ከተሞች ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ መጀመሩን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት አቶ ዮናታን ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ:የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን ፖሊስ ጣቢያ ተወሰደ፡፡

በዛሬው ዕለት ፓርቲው የመኪና ላይ የድምጽ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀቶችንም እያደለ ይገኛል፡፡

ይህ በ እንዲህ እንዳለ በሽሮሜዳ አካባቢ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን በፖሊስ ታግቶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተወሰደ ነው፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በዛሬው ዕለት ፓርቲው የመኪና ላይ የድምጽ ቅስቀሳ እያደረገ ሲሆን ለአዲስ አበባ ነዋሪዎች በራሪ ወረቀቶችንም እያደለ ይገኛል፡፡ በሽሮሜዳ አካባቢ በቅስቀሳ ላይ የሚገኘው የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ቡድን በአሁኑ ሰዓት በፖሊስ ታግቶ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተወሰደ ነው፡፡ ፖሊስ ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው ከማለት ያለፈ ለአፈናው ምንም ምክንያት አልሰጠም::

በሌላ ዜና የምርጫ ቅስቀሳ ላይ የነበሩ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች ታሰሩ::
ዛሬ የካቲት 24/2007 ዓ.ም በአዲስ አበባ ጉለሌ ክፍለ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ ሲያደርጉ የነበሩ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች በፖሊስ ተይዘው ታስረዋል፡፡ ፓርቲው ዛሬ በሁሉም የአዲስ አበባ ክፍለ ከተሞች ላይ በጀመረው ቅስቀሳ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ቅስቀሳ ላይ የነበሩት ዘላለም ደሳለኝ፣ ምዕራፍ ይመር፣ ይድነቃቸው ፍሬው ተክለና ሳምሶን ግዛቸው ሽሮ ሜዳ ፖሊስ ጣቢያ ታስረው ከቆዩ በኋላ ወደ ላዛሪስት ፖሊስ ጣቢያ ተዛውረዋል፡፡ ከታሰሩት አራት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል ዘላለም ደሳለኝና ይድነቃቸው ፍሬው ዕጩ ተመራጮች ናቸው፡፡
ፖሊሶች በቅስቀሳ ላይ የነበሩትን አባላት በያዙበት ወቅት ‹‹ተልከን ነው›› ማለታቸው የታወቀ ሲሆን ‹‹ቅስቀሳ በቴሊቪዥን እንጅ በመኪና አልተፈቀደም፣ ቅስቀሳ መፈቀዱን አናውቅም፣ ይቀስቅሱ የሚል መመሪያ አልተላለፈልንም›› የሚሉ ምክንያቶችን መስጠታቸው ታውቋል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳ ቢጀምርም ለቅስቀሳ የወጡት እየታፈኑ መሆኑ ተገለጸ appeared first on Zehabesha Amharic.

በዝቋላ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ * የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር ማርያም እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው

$
0
0

በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊበን ዝቋላ ወረዳ አዱላላ ከተማ በሚገኘው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ መቀስቀሱን የገዳሙ መነኰሳት እየተናገሩ ነው፡፡

ከጠዋቱ 2፡00 ገደማ የተቀሰቀሰው የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር ማርያም እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው፡፡

ይህ አቅጣጫ፣ የገዳሙ ሞፈር ቤት የሚገኝበት መውጫ መንገድ ሲኾን በአኹኑ ሰዓት በበርካታ ቦታዎች ጭስ እንደሚታይ በመነኰሳቱ ተገልጧል፡፡

የቃጠሎው መንሥኤ በውል ባይታወቅም እሳቱ በአካባቢው ባለው ከባድ የነፋስ ኃይል ወደ ገዳሙ መውጫና በገዳሙ ዙሪያ እንዳይስፋፋ ተሰግቷል፡፡

የአቅራቢያው ነዋሪ ኅብረተሰብ በጥሩንባ በተላለፈው የድረሱልን ጥሪ የተሰባሰበ ሲኾን ወደ ወረዳው ጽ/ቤትም ተደውሎ የአስተዳደሩ አባሎችና የፖሊስ ኃይል በስፍራው መድረሳቸው ተገልጧል፡፡ ‹‹ቃጠሎውን በቅጠልና በአፈር ለመከላከልና መዛመቱን ለመቀነስ የነፋሱን ጋብ ማለት እየተጠባበቅን ነው ብለዋል፤›› አንድ የገዳሙ መነኰስ፡፡

በጥንታዊውና ታሪካዊው ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ሲደርስ የአኹኑ የመጀመሪያ አይደለም፡፡ መጋቢት ፲ ቀን ፳፻፩ ዓ.ም. በደረሰው የእሳት ቃጠሎ እንደ አርዘ ሊባኖስና የሐበሻ ጥድ ያሉት አገር በቀል ዛፎች በስፋት ወድመዋል፡፡ መጋቢት ፰ ቀን ፳፻፬ ዓ.ም. የተቀሰቀሰው ቃጠሎ ደግሞ ተኣምራዊና ግራ አጋቢ ጠባይዕ የታየበት ነበር፡፡ በምሥራቃዊ አቅጣጫ በሚገኘው የመንግሥት ደን ውስጥ ተከሥቶ በአንድ ገጽ ኃይሉ ሲቀንስ በሌላ አቅጣጫ እየተዛመተ ገዳሙን ጨርሶ ለማጥፋት በተቃረበበት ኹኔታ ከአዲስ አበባ፣ ከቢሾፍቱና ከአዳማ በተመሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፣ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች፣ በጎ አድራጊ ምእመናንና አካላት መተባበር እንዲኹም በመከላከያና በፖሊስ ኃይሎች እገዛ መገታቱ የሚታወስ ነው፡፡
gedam
በመጪው መጋቢት ወር መጨረሻ በገዳሙ የጠበል – ሐይቅ የኢሬቻን በዓል ለማክበርና በደብረ ዝቋላ የአባ ገዳ ሐውልት ለመትከል በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የባህልና ቱሪዝም ቢሮ መታቀዱንና በመንግሥት ብዙኃን መገናኛ መገለጹን ተከትሎ ቤተ ክርስቲያናችን በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ በኩል ለክልሉ ርእሰ መስተዳድር በጻፈችው ደብዳቤ ተቃውሞዋን በማሰማት ላይ እንዳለች ይታወቃል፡፡ጥንታዊውና ታሪካዊው የዝቋላ ደብረ ከዋክብት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ዛሬ በሚታወቅበት ቦታ ላይ ከተገደመ ከ700 ዓመታት በላይ አስቆጥሯል፡፡ በገዳሙ ደጅ ጠኚውን፣ አፈር ጠባቂውንና የአብነት ትምህርት መምህራንና ደቀ መዛሙርትን ሳይጨምር እስከ 350 መነኰሳትና መነኰሳዪያት እንደሚገኙበት ተዘግቧል፡፡

The post በዝቋላ ገዳም ዙሪያ የእሳት ቃጠሎ ተቀሰቀሰ * የእሳት ቃጠሎው የጀመረው ወንበር ማርያም እየተባለ በሚጠራው በገዳሙ ሰሜናዊ አቅጣጫ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.


የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ከኃላፊነቱ አነሳ

$
0
0

‹ውሳኔው ፖለቲካዊ ነው›› አቶ አዲሱ ጌታነህ

11043128_885271564848776_4028315024485403437_nየአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ተወካይ እንዲሁም የምዕራብ ጎጃም፣ ምስራቅ ጎጃምና አዊ ዞን የምርጫ ግብረ ኃይል አባል የሆነውን አቶ አዲሱ ጌታነህን ‹‹ማኔጅመንቱን ያውካል፣ የስራ ተነሳሽነት የለውም›› በሚል ከኃላፊነቱ ማንሳቱን በደብዳቤ አሳውቋል፡፡

ይሁንና መስሪያ ቤት ጥቅምት 23/2007 ዓ.ም በብቃቱ መሰረት በኃላፊነት እንደመደበው በደብዳቤ የገለጸ ሲሆን አሁን የተወሰደው እርምጃ ከወቅቱ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ጋር የተያያዘ መሆኑን አቶ አዲሱ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡

‹‹ባህርዳር ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ኃይል እየተፈጠረ ነው፡፡ በተለይ የአንድነት መዋቅር ሰማያዊን ከተቀላቀለ በኋላ ከፍተኛ ስራ እየተሰራ ይገኛል፡፡ ይህንም ተከትሎ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮች ጋር ያደረግናቸው ውይይቶች ብአዴንን አስደንግጦታል›› ያለው አቶ አዲሱ መስሪያ ቤቱ የወሰደበት እርምጃ ፖለቲካዊ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የምዕራብ ጎጃም ዞን የሰማያዊ ፓርቲ መዋቅር በአካባቢው ህዝብ ላይ የሚደርሰውን በደል፣ እንዲሁም ምርጫ ቦርድ ከዕጩ ምዝገባ ጋር በተያያዘ የሚፈጥራቸውን ችግሮች ለሚዲያ በማጋለጥ ላይ መሆኑ ከኃላፊነት ለመነሳቴ አንድ ምክንያት ነው ሲል ገልጾአል፡፡

የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የቦርድ አባላት የብአዴን ከፍተኛ አመራሮች ሲሆኑ ከእነዚህም መካከል የባህርዳር ከተማ ከንቲባ አቶ ላቀ አያሌው፣ የክልሉ ም/ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ያለው አባተ፣ የክልሉ የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ኃላፊ አቶ አየነው ይገኙበታል፡፡

The post የአማራ ክልል ከተሞች ልማትና ግንባታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራርን ከኃላፊነቱ አነሳ appeared first on Zehabesha Amharic.

የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ መርቆሬዎስ 25ኛ ዓመት በዓለ ሢመትና በዋሽንግተን ዲሲ

የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ -በጴጥሮስ አሸናፊ

$
0
0

እለተ ሰኞ  ፌብሯሪ 17  ቀን 2014  ዓ/ም ማለዳ

Haile Medhin Aberaአንድ  ንብረቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሆነና በበረራ ቁጥር ET 702 የተመዘገበ ቦይንግ 767  የመንገደኞች ማመላለሻ አውሮፕላን በጣሊያን በኩል አድርጎ ወደ ስዊዘርላንድ የአየር ክልል ይገባል። የስዊዝ የአየር ክልል ጠባቂዎችም በጧት የመጣባቸውን  ጥቁር እንግዳ ማንህ ወዴት ነህ ማለት። የአውሮፕላኑን የበረራ ሂደት ሙሉ በሙሉ በብቸኝነት የተቆጣጠረው ረዳት አብራሪ ሃይለመድህን አበራም ቆፍጠን ብሎ አኔ ነኝ ! ማለት። አንተ ማን? ምነው ምን ፈልገህ ነው ወደ አየር ክልላችን የገባኸው?  የአየር ክልል ተቆጣጣሪዎቹ ቀጣይ ጥያቄ ነበር ። የበርካታ ወገኖቹን የብሶትና የግፍ መልዕክት ይዞ በስዊዝ  አየር ላይ የሚያንዣብበው ሃይለመድህንም  “ለጊዜው  የምፈልገው  የስዊዝ  መንግስት የፖለቲካ  ጥገኝነት እንዲሰጠኝ ፣ ለኢትዮጵያ መንግስትም  ተላልፌ እንዳልሰጥና  አውሮፕላኑን ጄኔቫ  ላይ በሰላም  ማሳረፍ ነው” የምትል ቅልብጭ ያለች ቃል ነበረች። በሁለቱም በኩል የተለያዩ መረጃዎችን ከተለዋወጡ በዃላ አውሮፕኑን ማሳረፍ እንደሚችል የተፈቀደለት ሃይሌም በተካነው ልዩ የማብረር ችሎታ ካለምንም ኮሽታ አውሮፕላኑን ጄኔቫ ክዋንትራን አየር ማረፊያ  202 መንገደኞችንና የበረራ ሠራተኞችን እንደያዘ በሰላም አሳርፎ ፤ እሱም “ያልጠረጠረ”  የምትለዋን ብሂል ቋጥሮ  ይዟት ነበርና  በመስኮት  በኩል  በገመድ  በመውረድ ለስዊዝ የደህንነትና ፖሊስ አባላት እጁን በሰላም በመስጠትና ቃሉንም  ለማስመዝገብ ወደሚመለከተው የመንግስት መስሪያ ቤት  አመራ።

ሃይለ መድህን የአውሮፕላኑን የበረራ ሃላፊነት በብቸኝነት ከተቆጣጠረ ጀምሮ ከስዊዝ ፖሊሶች ጋር በአካል አስገተገናኘበት ጊዜ ደረስ ያደረጋቸውን በሙሉ በአፅንኦት የተከታተሉ አንድ አሜሪካዊ የቀድሞ ፓይለትና አሁን ደግሞ የግል የበረራ ተቋም ባለቤትን እንዳስደመማቸው እንደገለፁለት ወዳጄ ጋዜጠኛ አበበ ገላው አጫውቶኛል።

ከዚያስ ፧ ከዚያ በኳላማ የአለም ታላላቅና ታናናሽ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች ዋና ዜና ሃይለመድህንና የተጠለፈው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሆነ። የቴሌቪዥን መስኮቶች በሃይለመድን ምስሎች ተሞሉ ፣ ሬድዮኖች ደጋግመው ደጋግመው ስሙን ያነሳሉ፣ ማህበራዊ ሚዲያዎች እነ ፌስቡክና ትዊተር ስለ ሃይለመድህን በሚያወሱ ወሬዎች ኮሜንት ፣ ላይክ ፣ ሼር እና  ሪትዊት ስራ በዝቶባቸው ነበር።

በአራቱም መአዘን የሚገኙ የጦቢያ ልጆች ቀፏቸው እንደተነካባቸው ንቦች ተነሱ። ሃይለመድህን ነፃ ይሁን የሚሉ ድምፆች ማስተጋባት ጀመሩ። ” ነፃ ሃይለመድህን ” የሚል አለም አቀፍ አስተባባሪ ግብረ ሃይል ተቋቋመ ፣ ሰላማዊ ሰልፎች በመላው አለም  በከፍተኛ ድምቀት ተካሄዱ ፣ በሃይለመድን ስም  ድረ ገፅና የማህበራዊ ሚዲያ ገፆች ተከፈቱ ፣ “ሀይለመድህን ብሔራዊ ጀግናችን ነው” የወቅቱ መሪ መፈክርም ሆነ።

አዎ!  ሕወሓት በሚከተለው ዘረኝነትንና ጠባብነትን መርህ ባደረገው የፖለቲካ አመራሩ ምክንያት ሠርቶ መብላት ላልቻለው ፣ በስደት ምክንያት በበረሃ አውሬና በባህር አሣ ለሚበላው ፣ ከሐገር ቤት አልፎ የሌሎች ሐገራትን ወህኒ ቤቶችን ለሚያጨናንቀው፣ የእምነት ተቋሙ ተደፍሮ ሲኖዶስና መጅሊስ ለሚመረጥለት፣ የእምነት አባቶችም በአባይ ፀሐዬ በኩል ለሚሾምለት፣ በሃገር ቤት ለመኖር ለመረጠም በገዛ ሀገሩ የሁለተኛና ሦስተኛ ዜግነትን ተቀብሎ እንዲኖር  ለሚገደደውና ከፈጣሪ የተሰጠውና በአለም አቀፍ ተቋማት የተደነገገውን  ኢትዮጵያም የተቀበለቻቸውንና  የፈረመችባቸውን  ሰብአዊ መብቶቹን ለተገፈፈው ኢትዮጵያዊ እንደ ሀይለመድህን አይነት ብሶቱን በአለም አደባባይ የሚያሳይለትና የሚያጋልጥለት ሲያገኝ እንዴት ብሔራዊ ጀግናው አያደርገው!

እንደ መንግታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ዋና መስሪያ ቤት  (UNHCR) መረጃ በፈረንጆቹ 2013 ዓ/ም አጋማሽ ድረስ ብቻ ከአርባ ሁለት ሺህ (42,000) በላይ ኢትዮጵያውያን ስደት ጠይቀዋል ።

በውጭ መንግተስታት ዘንድ በተለይም እርዳታ በሚለግሱት ምእራባውያን ዲሞክራሲያዊና ሰብአዊ መብት አክባሪ መስሎ ለመታየት የሚዳዳው የሕወሓት/ኢሕአዴግ መንግስት የደረሰበትን ፖለቲካዊ ኪሳራ ሂሳብ ለማወራረድ  “ሀይለ መድህን የአእምሮ በሽተኛ ነው” የሚል ዘመቻ ቢጀምርም ወንዝ ሊያሸጋግረው አልቻለም ።

በመቀጠል ህወሓት የወሰደው ርምጃ የመንግሥት ባለስልጣናትን ወደ ስዊዝ በመላክ የስዊዝ ባለሥልጣናትን አግባብቶና አሳምኖ ሀይለመድህንን ወደ ኢትዮጵያ ለመውሰድ መሞከር ነበር (የየመን መንግሥት በነፃነት ታጋዩ አንዳርጋቸው ፅጌ ላይ ያደረገውን እዚህ ላይ ማስታወሱ ተገቢ ነው) የስዊዝ ባለሥልጣናት ግን በፍፁም አይሞከርም የሚለው ቃል መልሳቸው ነበር።

ከዚህም በኋላ ሕወሓት የስዊዝ መንግሥት ባለሥልጣናትን ለማስፈራራት ይመስላል አንድ ከፍተኛ የህወሓት አባልና የመንግሥት ባለሥልጣን በድጋሜ ወደ ስዊዝ ላከ። የተላኩትም ሰሞኑን ከአንዲት የ14 አመት በአውስትራሊያ ነዋሪ ከሆነች ትውልደ ኢትዮጵያዊት “በሽልማት ያገኘችውን ” 20 ሚሊዮን የአውስትራሊያ ዶላር ተረከብኩ ያሉት የፌስቡክና ውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ  ቴድሮስ አድሐኖም ነበሩ   ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2014 ዓ/ም። ስዊዞቹም እንኳን አንተና ባለራእዩ መሪያችሁ አፈሩን አራግፎ ቢመጣም ወይ ፍንክች አሏቸው መሰለኝ የፌስቡክ ሚንስትሩ ወደመጡበት ለመመለስ ሻንጣቸውን ከሸከፉ፣ ጠባቂዎቻቸውና አጃቢዎቻቸውን በቦታቸው መኖራቸውን ካረጋገጡ በኋላ ለመውጣት ሲዘጋጁ ከፕሮቶኮላቸው አንዱ ጠጋ ብሎ አንድ ነገር ሹክ አላቸው ። ቴድሮስ አድሐኖም የስዊዝ ባለሥልጣናትን ከሚያነጋግሩባት የስዊዝ የመንግሥት መቀመጫ በሆነችው በርን ከተማ ላይ ከሚገኘው መሥሪያ ቤት በቅርብ ርቀት ለጀግናው ሀይለመድህን ፍትህና ነፃነትን  የሚጠይቁ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ሰላማዊ ሰልፈኞች ስላሉ ፣ ከመሥሪያ ቤቱ ሲወጡ እንዳያገኟቸው ጥንቃቄ እንዲደረግ ነበር የፕሮቶኮሉ መልእክት ።

ሰኔና ሰኞ የተገጣጠሙባቸው የማርክ ዙከርበርግ ቋሚ ደንበኛ ( valued customer)  ቴዲ በከፍተኛ አጀባና ጥንቃቄ ሰላማዊ ሰልፈኞቹ በሌሉበት አቅጣጫ አፈተለኩ። መቼም የፌስቡክ ደንበኛ ሆኖ መስራቹንና ባለቤቱን አሜሪካዊውን ማርክ ዙከርበርግን የማያውቅ የለም። ይኸው ለነ ቴድሮስ አድሐኖም ምስጋና ይግባና በያዝነው ሳምንት ፎርብስ መጽሔት ይፋ ባደረገው የአለማችን ሀብታሞች ደረጃ መሠረት ዙቢንገር በዚህ አመት ለመጀመሪያ ጊዜ ሃያዎቹ ቱጃሮች ውስጥ በመግባት የአለማችን 16ኛው ሃብታም ለመሆን ሲችል የሀብቱም መጠን 33.4 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል ። ድሮስ የተሰጣቸውን ከፍተኛ የስራ ኃላፊነት ገፋ በማድረግ አብላጫ  ጊዜያቸውን ፌስቡክ ላይ ፎቶ ሲለጥፉ የሚውሉና የሚያድሩ እንደ ቴድሮስ አይነት ደንበኞችን ይዞ  እንዴት ገቢው አያድግ!

የስዊዘርላንድ መንግሥት ተወካዮች ከህወሓት ባለሥልጣናት ጋር ስላደረጉት ተደጋጋሚ ውይይት ፣ ከኢትዮጵያውያንና ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን አውታሮች እንዲሁም ከሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ለሚደርሷቸው ጥያቄዎች ጠቅለል ያለ መልሰ ለመስጠት ያስችላቸው ዘንድ ሜይ 9 ቀን 2014  ዓ/ ም ለመንግሥት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጡ። በመግለጫቸውም:  የኢትዮጵያ መንግሥት በተደጋጋሚ ረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ተላልፎ እንዲሰጣቸው ያቀረቡት ጥያቄ ውድቅ መደረጉን ፣ ወደፊትም ተላልፎ የሚሰጥበት ሁኔታ እንደማይኖር ፣ የፍርድ ሒደቱን በስዊዝ ፍርድ ቤቶች ችሎት እንደሚታይ፣ የስዊዝ መንግስትም የህግ ከለላ እንደሚያደርግለት፣ ያቀረበውም የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ከፍርድ ሂደቱ መጠናቀቅ በኋላ እንደሚታይና አዎንታዊ መልስም እንደሚኖረው ( በስዊዝ ረዘም ላለ ጊዜ ለመኖር የሚያስችለውን ፈቃድ እንደሚያገኝ)  አስረግጠው ተናገሩ ።  በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የተገኙት የሀይለመድህን ጠበቆች ቡድን መሪ ዶ/ር ፊሊፕ ኩራ ( እሳቸው እንኳን ይችን ዶክተር መባል አይፈልጓትም የተገዛች ስላልሆነች ነው የተጠቀምኩባት) የስዊዝ መንግሥት ያሳለፈው ውሣኔ ተገቢ የሆነና ትክክለኛ መሆኑን ገልፀው አንድ ተከሳሽ በተመሳሳይ ክሶች በሁለት የተለያዩ ሃገሮች ችሎት ፊት ይቅረብ የሚል አለም አቀፍ ሕግም እንደሌለ ተናግረዋል ።

በድፕሎማሲው መንገድ እንዳልተሳካላቸው የተረዱት እነ ጭር ሲል አልወድም አዲስ ነገር ይዘን ብቅ ብለናል አሉ። ይሄኛውስ ምንድነው?  ይሄኛውማ  ሀይለመድህን ባይኖርም በሌለበት ( in absentia) ሞት፣ የእድሜ ልክ እስርና ሌሎችንም ጠንካራ ውሳኔዎችን በማሳለፍ አለም አቀፍ ዝናን ባተረፈው ፍርድ ቤታችንና የፍትሕ ስርአታችን አቃቤ ሕግ ክስ መስርቶበት እንዲያስፈርድበት እናደርጋለን የሚል ነበረ።

ፍትሕ ሚኒስቴር በረዳት አብራሪ ኃይለመድን አበራ ላይ  በከፍተኛው ፍርድ ቤት 3ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ሁለት ሲሆን፤ የመጀመሪያው በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዴሪ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 507/1/ ላይ የተመለከተውን በመተላለፍ፡-
‹‹…በዋና አብራሪ ፓትዮዝ ባርቤሪ አማካኝነት ከአዲስ አበባ በሱዳን በኩል ወደ ጣሊያን ሀገር ሮም ከተማ መንገደኞችን ለማድረስ በማጓጓዝ ላይ እንዳለ ዋናው አብራሪው የበረራ መቆጣጠሪያውን ክፍል ከውስጥ በመቆለፍ፣ ያለፍቃድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ አውሮፕላኑን በቁጥጥር ሥር በማድረግ የአውሮፕላኑ የበረራ ቡድን አባላት በሩን እንዲከፍት ሲጠይቁት አርፋችሁ የማትቀመጡ ከሆነ በአውሮፕላኑ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ ብሎ በማስፈራራት፤ እንዲሁም የአውሮፕላኑን የመዳረሻ አቅጣጫ ያለአግባብ በማስቀየር ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ፈቃድ ውጭ ወደ ስዊዘርላንድ አየር ክልል ውስጥ በመግባት ተሳፋሪዎች እና የአውሮፕላኑ ሠራተኞች ሕይወት እና ደህንነት አደጋ ላይ እንዲወድቅ አድርጎ በመጨረሻ በጄነቭ ከተማ ውስጥ ያለመዳረሻው እንዲያርፍ በማድረጉ እና ተሳፋሪዎችን ለአደጋ በማጋለጡ በፈፀመው በሕገ-ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን መያዝ ወይም ማገት›› የተከሰሰ መሆኑን ያትታል፡፡

በሁለተኛነት ክስ ደግሞ በዚሁ የወንጀል ሕግ አንቀጽ 508/1/ ላይ ያለውን መተላለፍ የሚል ሲሆን፤ ክሱም በአጭሩ እንዲህ ይላል፡-
‹‹…ያለፍቃድ እና በሕገ-ወጥ መንገድ አውሮፕላኑን በቁጥጥር ሥር በማድረግ የአውሮፕላኑ የበረራ ቡድን አባላት በሩን እንዲከፍተው ሲጠይቁት አርፋችሁ የማትቀመጡ ከሆነ በአውሮፕላኑ ላይ እርምጃ እወስዳለሁ በማለት በማስፈራራት አውሮፕላኑን በድንገት እና በፍጥነት ሁለት ጊዜ ከፍ እና ዝቅ (dive) በማድረግ በአውሮፕላኑ ውስጥ ያሉትን የመንገደኞች ምግብ ማቅረቢያ ቁሳቁሶች እንዲገለባበጡ በማድረግ፣ የአውሮፕላኑን የመዳረሻ አቅጣጫ ያለአግባብ በማስቀየር፣ ከአትዮጵያ አየር መንገድ ፈቃድና እውቅና ውጭ ስዊዘርላንድ አየር ክልል ውስጥ በመግባት ስዊዘርላንድ ከተማ ጀኔቭ በመግባት አየር ላይ በማንዣበብ ከቆየ በኋላ እንዲያርፍ በማድረግ በፈፀመው በሕገ-ወጥ መንገድ በጉዞ ላይ ያለን አውሮፕላን አስጊ ሁኔታ ላይ መጣል ወንጀል ተከሷል፡፡›› ይላል ።

በፌ/አቃቤ ሕግ ብርሃኑ ወንድምአገኝ ፊርማ ለፍርድ ቤቱ የቀረበው ማመልከቻ ከስ ቻርጁን ጨምሮ አስራ አንድ ገፅ ሲሆን፤ የዋና አብራሪው፣ የአምስት የበረራ አስተናጋጆች እና የአራት ሰዎች ስም ዝርዝር በመስክርነት ተገልፆአል፡፡ በሰነድ ማስረጃነት ደግሞ አየር መንገዱ በ27/6/06 ዓ.ም ለፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ የጻፈው አራት ገጽ እና ሲቪል አቬየሽን በ21/6/06 ኃይለመድንን በተመለከተ የጻፈው ማብራሪያ ከነአባሪው ሁለት ገጽ ቀርቧል፡፡

የኃይለመድን አበራን የጤንነት ሁኔታ በተመለከተ አየር መንገዱ ለፌደራል ፖሊስ በላከው ደብዳቤ በስድስት ወር ውስጥ አምስት ጊዜ ያህል ለቀላል ሆድ ቁርጠት፣ ራስ-ምታት፣ ጉንፋንና ተቀምጥ ወደ ድርጅቱ ክሊንኪ ከመሄዱ ያለፈ ምን ችግር ያሌለበት ጠኔኛ እንደሆነ ገልፆአል፡፡ ሲቪል አቬሽንም በተመሳሳይ መልኩ በላከው ደብዳቤ አብራሪው አመታዊ የጤና ምርምራ አድርጎ እ.ኤ.አ. እስከ 22/12/2014 ዓ.ም ድረስ ጤነኛ መሆኑን ማረጋገጫ ሰርተፍኬቱን አድሶ እንደሰጠው አስታውቋል፡፡
( እዚህ ላይ በመጀመሪያ መንግሥት ኃይለመድህን የአእምሮ በሽተኛ ነው ብሎ እንደነበር ልብ ይሏል)
አየር መንገዱ ከዚሁ ጋር አያይዞ ሁለት መቶ ሀምሳ ሶስት ሺህ፣ ሶስት መቶ ሰላሳ ስድስት ብር ከአራባ ሁለት ሳንቲም (253,336.42) ዩሮ ኪሳራ እንደደረሰበት እና በቀጣይም ተጨማሪ ክፍያዎች እንደሚኖሩበት አሳውቋል፡፡

ህወሓት/ ኢሕአዴግ ራሱ ከሣሽ ራሱ ፈራጅ ሆኖ በሚተውንበት የፍርድ ቴአትር ቤት መታየት የጀመረው ድራማ የተጠበቀውን ተመልካች ማግኘት ካለመቻሉም በላይ የክሱም ስክሪፕት በጥሩ ፀሀፈ ተውኔት ስላልተፃፈ ቴአትሩን ለማየት ለታደሙትም ታማኝና ጥቂት የስርአቱ ልማታዊ ደጋፊዎችና ጋዜጠኞች የእንቅልፍ መድኃኒት ሆነባቸው ፣ አለም አቀፍም፣ ሐገር አቀፍም፣ ልማት አቀፍም ትኩረት አጣ።

አዲሱ ትኩረት መሳቢያ ቴአትር
—————————————-
ባሳለፍነው ሳምንት አውሮፕላን የተጠለፈበትን አንደኛ አመት ለማሰብም ይመስላል ሕወሓት አዲስ ዘዴ አግኝቻለሁ ይላል።
አዲሱ ዘዴ የተባለው ምንድነው ቢሉ፣ ኢንተርፖል በሚባል የአለም አቀፍ ፖሊስ ተቋም  በኩል “ሀይለመድህን አበራ የሚባል ረዳት  አውሮፕላን አብራሪዬ ጠፍቶብኛልና እባካችሁ ያያችሁ” የሚል የተማፅኖ ጥሪ ማሰማት ነው። በዚያውም የኢንተርፖል አባል መሆኔን እወቁልኝ ነው።  “የኢንተርፖል አባል መሆን ብርቅ ነው እንዴ?  ” አለ አሉ ይህን የሰማው ኮንስታብል ዶክሌ። ወደው አይስቁ !

ለማንኛውም “ረዳት አብራሪዬን ያያችሁ” ለሚለው በኢንተርፖል በኩል ለተሰራጨው ቀይ ማዘዣ( Interpol red notice) የመጀመሪያውን መልስ የሰጠችው ስዊዝ ነች ” አዎ እኔ አይቻለሁ እንቁልልጬ አይነት መልስ ።

ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 27 ቀን 2007 ዓ/ም በፈረንሳይኛ ቋንቋ ለሚታተመው “ለ ማታ”  (Le Matin) ጋዜጣ አስተያየታቸውን የሰጡት የሀይለመድህንን ጉዳይ የሚያየው የኮንፌዴሬሽኑ አቃቤ ሕግ ቃል አቀባይ ጃኔት ባልመር “ለኢንተርፖል ተላልፎ ይሰጣል ወይ?  ለሚለው ጥያቄ በፍፁም አይሆንም አይሞከርም ነው መልሴ ብለዋል ።

ጃኔት ባልመር ይቀጥላሉ ” የ31 አመቱ ሀይለ መድህን በአሁን ጊዜ ስዊዝ ውስጥ በሕግ ጥላ ስር ይገኛል። በፍርድ ቤትም ጉዳዩ እየታየ ነው። በኢትዮጵያም ከአለም አቀፍ የሕግ ሂደት ባፈነገጠ ሁኔታና በስዊዝ ችሎት መቅረቡ እየታወቀ ክስ እንደተመሠረተበት ፣ እኛም አሳልፈን እንደማንሰጠው አሳውቀናል ። ኢንተርፖልም የቀይ መያዣ( ማሳሰቢያ) ጥሪውን ያስተላለፈው በኢትዮጵያ መንግሥት ጥያቄ መሆኑን አሳውቋል ። ” ይላሉ።

የሀይለመድህን ጠበቃ ፊሊፕ ኩራም ለዚሁ ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት ” የኢትዮጵያ መንግሥት ሀይለመድህንን በይፋ ” ከሐዲ ” ብሎ ፈርጆታል ። በመሠረታዊውን የፍትህ ስርአት  (fundamental rule of law)  “አንድ ሰው በተመሳሳይ ክስ በሁለት የተለያዩ ችሎቶች መቆም የለበትም” የሚለውን በመፃረር ከኛም እውቅና ውጪ  በሌለበት ለመክሰስ ወስኗል ። በምን አይነት መልኩ ነፃ በሆነ የፍርድ ሂደት ጉዳዩ እየታየ እንደሆነም እኔ በበኩሌ የማውቀው ነገር የለም። የኢትዮጵያ መንግሥት በየጊዜው የተለያዩ ውጤት አልባ የማሰናከያ ቀመሮችን  እየፈጠረ ነው ” ይላሉ ።

የአቃቤ ሕጉ ቃል አቀባይ ጃኔት ባርመር “ለኢትዮጵያ መንግስት የአፀፋ መልስ የለንም። ለመንግስታችን የፖለቲካ ጥገኝነት ጥያቄ ያቀረበው  የሀይለመድህን አበራ  የፍርድ እጣ እዚሁ በጥሩ ሁኔታ ይወሰናል ። በርግጥ የፍርድ ሂደቱ ብዙም አልገፋም። ክፍት ችሎቶች የሉም። ምርመራዎች እንደቀጠሉ ናቸው ። ጉዳዩ ገና በምርመራ ላይ ያለ ስለሆነ ከዚህ በላይ ብዙ መናገር አልችልም  ” ብለዋል ።

ጠበቃ ፊሊፕ ኩራም “ሀይለ መድህን  በጣም ደህና ነው ። ስለ ፍርድ ሂደቱም  መናገር የምችለው:  እንዲህ መጓተቱ የተለመደ ባይሆንም ከንብረት ጋር የተያያዙ የተለያዩ መረጃዎችን ከተለያዩ ሐገሮች ለማግኘት ስንሞክርና መልስ ለማግኘት ረዘም ያለ ጊዜ መውሰዱ ነው። ልዩ ወደሆኑት  ቴክኒካዊ መረጃዎች  ስንመጣ ይህም ራሱን የቻለ የቴክኒክና የሳይንስ ምርመራ ይጠይቃል። በመጨረሻም የኮንፌዴሬሽኑ የህዝብ አቃቤ ሕግ  በመርህ ደረጃ 202 መንገደኞችን በሙሉ የሚያነጋግር ሲሆን አሁንም ከተሳፋሪዎቹ ስለራሳቸው  መረጃዎችን እየጠበቀ ይገኛል ። ” ብለዋል

የረዳት አብራሪ ሀይለመድህን አበራ ጉዳይ ከፌብሩዋሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም  እስከ ፌብሩዋሪ 28 ቀን 2015 ዓ/ም ድረስ የነበረውን የአንድ አመት ጉዞ ባጭሩ ይሄን ይመስላል።

ሀይለመድህን አበራ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ኦገስት 30 ቀን 1983 ዓ /ም  በጣና ሃይቅ ዳርቻ በምትገኘው ባህርዳር ከተማ ቀበሌ 03 ተወልዶ ያደገ ሲሆን የአንደኛ ደረጃ ትምህርቱን በመጋቢት 28 ፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን ደግሞ ባህርዳር ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታትሏል።

ከፍተኛ ትምህርቱን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በአርክቴክቸር  ትምህርት ክፍል በመከታተል ላይ እያለና ለማጠናቀቅም አንድ ሴሚስተር ብቻ ሲቀረው በማቋረጥ ከልጅነት ጀምሮ ይመኘው የነበረውን የበረራ ትምህርት ለመከታተል የኢትዮጵያ አየር መንገድን የበረራ ት/ቤት ተቀላቅሏል። ፌብሩዋሪ 17 ቀን 2014 ዓ/ም አውሮፕላኑን ጠልፎ ጄኔቫ ስዊዘርላንድ እስካሳረፈበት ጊዜ ድረስ በአየር መንገዱ በረዳት አብራሪነት አገልግሏል። ከከጠለፋውም በኋላ የአየር መንገዱ የበረራ ክፍል ሃላፊ የነበሩት ካፒቴን ደስታ ዘሩ ከሥራቸው መልቀቃቸው ይታወቃል ።

በመጨረሻም በቅርቡ የኢትዮጵያ አየር ሐይል አባላት የሆኑ መኮንኖችና የበረራ ቴክኒሺያኖች በተለያዩ አቅጣጫዎች ሥርአቱን እየከዱ በመጥፋት ላይ መሆናቸውን እያየን ነው። በተለይም ወደ ጎረቤት ሐገር የኮበለሉት አንድ ተዋጊ ሄሊኮፕተር ይዘው መሆኑንም ራሱ መንግሥት በሚቆጣጠራቸው ሚዲያዎቹ  አረጋግጦልናል ።

ከ25 እስከ 30 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣውን ሄሊኮፕተር እና ለስልጠና ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰባቸውን የበረራ ባለሙያዎችን ያጣውና በማጣት ላይ ያለው ህዝባዊ ወያነ ሐርነት ትግራይና አመራሮቹ ረዳት አብራሪ ሀይለ መድህን አበራ ብቻ ገበናቸውን የገለጠባቸው  ለማስመሰል ወደ ምእራባውያን ሐገሮች ባለሥልጣናቱን መላክና ኢንተርፖልን ደጅ መጥናት ውሀ አያነሳላቸውም።

ምነው ዶ/ር  ቴድሮስ በነካ እጅዎ ወዳደጉባትና ወደተማሩባት ኣስመራ ጎራ ብለው የሄሊኮፕተሯንና የበረራ ባለሙያዎቿን ጉዳይንም ቢመክሩባትስ?
ከስዊዝስ  ኣስመራ አትቀርብዎትም?

The post የረዳት አብራሪ ሐይለመድህን አበራ ጉዳይና የአንድ አመት ጉዞው ባጭሩ -በጴጥሮስ አሸናፊ appeared first on Zehabesha Amharic.

የትናንቱን የጭላሎ ተራራ የእሳት አደጋ በመቀስቀስ የተከሰሰው ግለሰብ በ10 ዓመት እስራት ተቀጣ

$
0
0

b921dbb2d1617779408d5dd6f6a9f717_Lአዲስ አበባ፣ የካቲት 25፣ 2007 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በአርሲ ዞን በጢዮ ወረዳ በጭላሎ ተራራ ላይ ትናንት የተከሰተውን ቃጠሎ የቀሰቀሰው ግለሰብ በአስር ዓመት አስራት ተቀጣ። የወረዳው ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው  ችሎት የግለሰቡን ጉዳይ የተመለከተ ሲሆን፥ ተከሳሹ ቃጠሎውን መቀስቀሱን በማመኑ በ10 ዓመት እስራት ቀጥቶታል።

ቃጠሎውን የቀሰቀሰው ግለሰብ በዲገሉና ጢጆ ወረዳ ከቡቾ – ስላሴ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደ ቦሬ – ጭላሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ወደሚገኘው ወንድሙ ጋር በእንግድነት የመጣ መሆኑንም ፖሊስ ገልጿል። የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር ኡርጋ ግዛው እንደገለጹት፥ ትናንት ጠዋት ረፋድ ላይ በተራራው ላይ በሚገኝ ደን ላይ የለኮሰው እሳት እስከ ምሽቱ ሁለት ሰዓት ከቆየ በኋላ ነው በቁጥጥር ስር ውሏል።

ቦሬ – ጭላሎ ቀበሌ ገበሬ ማህበር የተነሳው ቃጠሎ ወደ ሻላ – ጨብቲ፣ ቡርቃ – ጭላሎ እና ሀሮ – ቢላሎ የገጠር ቀበሌ በመዛመት በተፈጥሮ ሀብት ላይ ጉዳት ማድረሱንም ጠቁመዋል። በቀበሌዎቹ የተቀሰቀሰውን እሳት ለመከላከል የአካባቢው አርሶ አደሮች፣ ነዋሪዎች፣ የወረዳና ዞን ፀጥታ ኋይሎች ባደረጉት ከፍተኛ ርብርብ ከዘጠኝ ሰዓታት በኋላ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስታውቀዋል።

አደጋው በሰውና እንስሳት ላይ ጉዳት አለማድረሱ ተመልክቷል። በቃጠሎው የወደመውን የደን ይዞታ መጠን ለማጣራት ፖሊስ ከወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት ጋር እየሰራ ነው ብለዋል።

በጥበቡ ከበደ /ተጨማሪ መረጃ ከኢዜአ/

The post የትናንቱን የጭላሎ ተራራ የእሳት አደጋ በመቀስቀስ የተከሰሰው ግለሰብ በ10 ዓመት እስራት ተቀጣ appeared first on Zehabesha Amharic.

አዲስ አበባ የሚገኘው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከብርሃኑ ተዘራ ጋር በሰራው ዘፈን የተነሳ ከደህንነት ሃይሎች ማስፈራሪያ እየደረሰው መሆኑ ተሰማ * ስልኩ ተጠልፏል

$
0
0
ጃኪ እና ብርሃኑ ከሙዚቃ አቀናባሪው ሄኖክ ነጋሽ ጋር በስቱዲዮ ውስጥ

ጃኪ እና ብርሃኑ ከሙዚቃ አቀናባሪው ሄኖክ ነጋሽ ጋር በስቱዲዮ ውስጥ

ጃኪ የተቀረጸው ዘፈኑን በሄኖክ ነጋሽ ኮምፒውተር ሲያደምጥ

ጃኪ የተቀረጸው ዘፈኑን በሄኖክ ነጋሽ ኮምፒውተር ሲያደምጥ

(ዘ-ሐበሻ) ብርሃኑ ተዘራ (ብሬ ላላ) ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው ወቅታዊ ዘፈን በብዙዎች ዘንድ ተወዳጅነትን ካተረፈ በኋላ አዲስ አበባ የሚገኘው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ስልኩ በደህንነቶች መጠለፉን እና በስር ዓቱ ሰዎችም ከፍተኛ ማስፈራሪያና ዛቻ እየደረሰው እንደሚገኝ ለድምጻዊው ቅርብ የሆኑ ወገኖች ለዘ-ሐበሻ አስታወቁ::

በዛሬው ዕለት ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ፃፈው በሚል “ዘፈኑን ተሰርቄ ነው; ጃኪ የፖለቲካ ዘፈን አይዘፍንም” የሚል ጽሁፍ በፌስቡክ የተሰራጨ ሲሆን ይህ ጽሁፍ በአድናቂዎቹ እንጂ በጃኪ ጎሲ አለመፃፉን የደረሰን መረጃ ያመለክታል:: የጃኪ ጎሲ የግል 2 ፌስቡክ አካውንቶቹ ላይ ይህ ዜና እስከተዘገበበት ጊዜ ድረስ ከብርሃኑ ተዘራ ጋር ስለዘፈነው ዘፈን የሰጠው አስተያየት የለም:: ሆኖም የድምጻዊው አድናቂዎች ዘፈኑ ካለርሱ እውቅና ውጭ የተሰራ አድርገው የለጠፉት መረጃ ብዙዎችን ከማደናገሩም በላይ በተለይ ለአራት ቀናት ጃኪ ጎሲ በዋሽንግተን ዲሲ የሙዚቃ አቀናባሪው ሄኖክ ነጋሽ ጋር ሄዶ ከብርሃኑ ጋር ሲቀረጽ የተመለከቱ የዓይን እማኞች “ጃኪ ለምን ይዋሻል?” የሚሉ አስተያየቶችን በየሶሻል ሚዲያው እያሰራጩ ነው:: ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ በፌስቡክ ገጹ ምንም ያለው ነገር ባለመኖሩ አስተያየት ከመስጠት መቆጠብ ይሻላል የሚሉ ወገኖች; ጃኪ በስሙ በወጣ መግለጫ የተነሳ በስሙና በቀጣይ ሥራው ላይ ከፍተኛ ኪሳራ ሳያደርስበት አቋሙን እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል::

ጃኪ በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባ የሚገኝ ሲሆን የደህንነት ኃይሎች ስልኩን በመጥለፍ ከማን ጋር እንደሚያወራ እንደሚከታተሉት ዘፈኑን እንዲያስተባብል ከፍተኛ ጫና እያደረጉበት መሆኑን ለድምፃዊው ቅርብ የሆኑ ምንጮች ጠቁመዋል:: ጃኪ ከዚ ቀደም “ማን እንደ ሃገር” የሚል ነጠላ ዘፈን ሰርቶ የለቀቀ ሰሞን ዋሽንግተን ዲሲ የሚገኘው የድምፅአዊው የቅርብ ወዳጅ ተወዛዋዡ አብዮት መሃል ላይ ሰማያዊ የሌለበትን አረንጓዴ ቢጫ ቀይ ባንዲራ በኪሊፕ ሰርቶ ሲለቅ ጃኪም ይህን የሙዚቃ ክሊፕ ፌስቡኩ ላይ ሼር ሲያደርግ ደህንነቶች እንዴት ሕገመንግስቱ የማይፈቅደውን ባንዲራ በክሊፑ ላይ ትጠቀማለህ? በሚል ባደረሱበት ማስፈራሪያ ከፌስቡክ ገጹ ዘፈኑን ማስወጣቱን የሚጠቅሱት እነዚሁ የቅርብ ወገኖች አሁንም ደህንነቶች በሚያደርሱበት ወከባ ከፍተኛ ጫና ውስጥ እንደሚገኝ ጠቁመዋል::

በጃኪ ስም አድናቂዎቹ የለጠፉት አደናጋሪ የፌስቡክ መልዕክት; ይህ በጃኪ የግል 2 ፌስቡክ አካውንቶች ላይ አልወጡም

በጃኪ ስም አድናቂዎቹ የለጠፉት አደናጋሪ የፌስቡክ መልዕክት; ይህ በጃኪ የግል 2 ፌስቡክ አካውንቶች ላይ አልወጡም


በዚህ ዘፈን ዙሪያ ድምፃዊው ብርሃኑ ተዘራን አግኝተን ለማነጋገር ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም::

The post አዲስ አበባ የሚገኘው ድምፃዊ ጃኪ ጎሲ ከብርሃኑ ተዘራ ጋር በሰራው ዘፈን የተነሳ ከደህንነት ሃይሎች ማስፈራሪያ እየደረሰው መሆኑ ተሰማ * ስልኩ ተጠልፏል appeared first on Zehabesha Amharic.

በፊንጫ ስኳር ቃጠሎ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ታወቀ

$
0
0

(ሰንደቅ ጋዜጣ) ፊንጫ ስኳር ፋብሪካ መጋቢት 5 ቀን 2007 ዓ.ም. ከቀኑ 5 ሰዓት ገደማ የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ማቀጣጠያ ክፍል በተነሳ ቃጠሎ የአንድ ሠራተኛ ሕይወት ሲያልፍ በአስራ ስድስት ሠራተኞች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ማድረሱን የኮርፖሬሽኑ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳይሬክቶሬት የሚዲያ ግንኙነት የቡድን መሪ ለሰንደቅ ጋዜጣ አረጋገጡ።
news
የሚዲያ ግንኙነት ቡድን መሪው አቶ ጋሻው አይችሉም ስለቃጠሎው ከሰንደቅ ጋዜጣ ተጠይቀው ሲያስረዱ፣ “የሸንኮራ አገዳ ገለባ (ባጋስ) ማቀጣጠያ ክፍል ለፋብሪካው አማራጭ የኃይል አቅርቦት የሚሰናዳበት ክፍል ሲሆን ለማቀጣጠያ ግብአትነት የሚውለው የአገዳ ገለባ ደረቅ በመሆኑ በቀላሉ ቃጠሎ ሊነሳበት የሚችልበት እድል ሰፊ ነው። የተነሳውን የእሳት ቃጠሎ ለማጥፋት በተደረገው ርብርብ የአንድ ሰራተኛ ሕይወት ሲያልፍ፣ በአስራ ስድስት ሠራተኞች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። ቀላል አደጋ ከደረሰባቸው ሠራተኞች መካከል አምስቱ በፋብሪካው የሕክምና ማዕከል ተገቢውን እርዳታ ተደርጎላቸው በጥሩ ጤንነት ላይ የሚገኙ ሲሆን፤ አስራ አንዱ ግን በቤቴል ሆስፒታል ተኝተው እየታከሙ ናቸው” ብለዋል።

በፋብሪካው የተነሳው የእሳት ቃጠሎ በዕለቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን የቡድን መሪው ጠቁመው፤ የፋብሪካው ሰራተኞች፣ የአካባቢው ነዋሪዎች፣ መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ እና የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት እሳቱን በማጥፋት ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው። እንዲሁም ሁለት ሂሊኮፕተሮችም ተሳታፊ እንደነበሩ ጠቅሰዋል።

ለቃጠሎው መነሳት ትክክለኛ ምክንያቱን እየተጣራ መሆኑ የገለፁት አቶ ጋሻው፣ የደረሰውም ውድመት ምን ያህል እንደሆነ ግምቱ እየተሰራ ነው ብለዋል። ለጊዜው ግን ለቃጠሎው መነሻ ምክንያት ያለው ግምት የአካባቢው ሙቀት ሳይሆን አይቀርም ሲሉ ግምታቸውን አስቀምጠዋል።
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ ቃጠሎው ከደረሰበት ቅዳሜ መጋቢት 5 እስከ መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓ.ም ድረስ ስራ ለማቆም የተገደደ ሲሆን፤ ከማክሰኞ መጋቢት 8 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ አገዳ መፍጨት በመጀመሩ ከ16 ሰዓታት በኋላ ስኳር ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።
የፊንጫ ስኳር ፋብሪካ በተደረገለት አዲስ የፋብሪካ ማስፋፊያ ግንባታ የመፍጨት አቅሙን በቀን ወደ 10ሺ ኩንታል ማሳደጉ ይታወቃል። በሙሉ አቅሙ መስራት ሲጀምር በቀን 12ሺ ኩንታል ያመርታል ተብሎ ይጠበቃል።3⁄4

The post በፊንጫ ስኳር ቃጠሎ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

“በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል”–ድምጻችን ይሰማ

$
0
0

(ፎቶ ፋይል)

(ፎቶ ፋይል)


የህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ አሳታፊ የትግል ስልት ነው!

ረቡዕ መጋቢት 9/2007

የኢትዮጵያ ሙስሊም በእምነቱ ላይ የተቃጣውን የአስተሳሰብና የጥቃት ዘመቻ ለመመከት፣ አስተሳሰቡን በኢስላማዊ አስተሳሰብ ለማረቅ፣ በሽፋን የሚደረገውን ጥቃት በህግ እልባት ያገኝ ዘንድ ባደረገው የትግል ሂደት ከላይ ወደታች የሆነ የተመሪነት ስርዓት ብቻ ሳይሆን ከታች ወደላይ ፍሰት ያለው መሪዎችን የመምራት ሥርዐት መፍጠር ችሏል፡፡ ይህም ህዝበ ሙስሊሙን የትግሉ ባለቤትና የመሪዎቹም መሪ አድርጎታል፡፡
ህዝበ ሙስሊሙ አደባባይ የወጣው ‹‹በጊዜ ሂደት ይፈታሉ፣ አልያም ከሀገሪቷ ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር አብረው ይቀረፋሉ›› በሚል በሆደ ሰፊነት የተሸከማቸውን ስር የሰደዱ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ተቋማዊና መሰል ችግሮች ለመጠየቅ ሳይሆን ተገድበው የተሰጡትን መሰረታዊ መብቶች መልሶ የመንጠቁን እኩይ ዘመቻ ለመግታት ነው፡፡ የእነዚህ እኩይ ተግባራት ድምር ውጤት ዘመን ተሻጋሪና በእምነታችን ላይም ሆነ በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ማንነታችን ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ አደጋ መረዳቱ ለህዝበ ሙስሊሙ የመንቃት ምንጭ፣ ለትግሉም ገፊ ሀይል ከመሆን ባሻገር ህዝቡን ፅናት ያላበሰና ለመስዋእትነት ያዘጋጀ ነበር፡፡

ከሰው ልጅን የታሪክ ምዕራፍ ሰፊውን ቦታ የሚሸፍነው ትግል ነው፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የሰው ልጆች በግልም ይሁን በህብረት ለተለያየ ዓላማና ግብ የተለያዩ ስልትና መርሆዎችን የተከተሉ ትግሎችን አካሂደዋል፡፡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ደግሞ የህዝብን ንቃተ ህሊና መጎልበት የሚያመላክት የሰለጠነ የሰላማዊ የመብት ትግል መገለጫ ነው፤ ምክንያቱም መንግስት የህዝብን ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ ከማድመጥ ይልቅ የህዝብን ድምፅ በኃይል ለማፈን የሚያደረገው ጥረት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመጣ ቁጥር ህዝብ የመንግስትን ደጅ ከማንኳኳት ይልቅ መንግስት ላይ ዘርፈ ብዙ ጫና በመፍጠር መንግስት ወደህዝቡ ደጅ እንዲመጣ የሚያስገድዱ ለእምቢተኝነት የተሰጡ የእምቢተኝነት ምላሾችን አማራጭ አድርጎ ይወስዳልና! በተጨማሪም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተለየ መዋቅር የማይጠይቅ፣ ሁሉም ህብረተሰብ በየአካባቢውና በየዘርፉ የሚታገልበትና የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ የትግል ስልት ሲሆን ተጽእኖ ፈጣሪነቱም ዓይነተኛ መሆኑ አሌ የሚባል እንዳልሆነ ታሪክ ይመሰክራል፡፡

ይህ ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ምክኒያታዊ የለውጥ እርከኖችን ተሻግሮ የመጣ እንደመሆኑ ተግባራዊነቱ ዋስትና ያለው፣ ከጠባቂነት የሚያላቅቅ፣ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ የተዘረጋው የመብት ትግል በሰላማዊነት እና ቁርጠኝነት ድልድይ ላይ ተሻግሮ የችግርን ወንዝ እንዲሻገር ያስችላል፡፡ ይህን ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ማዳመጥ ደግሞ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ህዝብ የመሪዎቹ መሪ መሆኑን ማሳያም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ ትብብር መንፈግ (እምቢተኝነት) ላይ ያተኮሩ የተቃውሞ መንገዶችን በመጠቀም የምናካሂዳቸው መርሃ ግብሮች ይኖሩናል፤ በአላህ ፈቃድ! ሁላችንም በዚህ መሰሉ ትግል ላይ ግንዛቤያችንን የሚያዳብሩ ጽሁፎችን በማንበብ እና መንፈሳዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ዝግጅት በማድረግ ሰላማዊ ትግላችንን እስከድል ደጃፎች ለማድረስ የገባነውን ቃል እናድስ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post “በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል” – ድምጻችን ይሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.


በሀሰት አልመሰክርም በማለት አውነቱን በፍርድ ቤት የተናገረው ሙጂብ አሚኑ ለሚያዚያ 7 ተቀጠረ

$
0
0

mujib
ቢቢኤን መጋቢት 9/2007
በነ ኤልያስ ከድር መዝገብ በተከከሰሱ ሙስሊሞች ላይ በሀሰት እንዲመሰክር ታፍኖ ማእከላዊ የተወሰደው ሙጂብ አሚኑ በሀሰት እንዲሰክር አቅርበውት አስገራሚ ታሪክ ሰርትዋል፡፡ በወንድሞቼ ላይ በሀሰት አልመሰክርም በማለት እውነቱን በፍርድ ቤት አስረድትዋል፡፡
ለዚህ እኩይ አላማቸው ማስፈጸሚያ አልሆንም ያለው ሙጂብ አሚኑ በሽብርተኝነት ክስ ተመስርቶበት በማእከላዊ ይገኛል፡፡ በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ቀርቦ የነበረ ሲሆን ለሚያዚያ 7 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡
መንግስት የሰራው አይን ያወጣ ሸፍጥ ሁሉንም ያስገረመ ሲሆን ወጣት ሙጂብ አሚኑ የሚመጣውን ሁሉ ዋጋ ለመክፍል በመቁረጡ፤ እውነትን በመጋፈጡ በበርካቶች አድናቆትን ተችሮታል፡፡ ሙስሊሞች ለሱ ያላቸውን አጋርነት ለማሳየት በዛሬው እለት በፍርድ ቤት በርካቶች ተገኝተዋል፡፡

The post በሀሰት አልመሰክርም በማለት አውነቱን በፍርድ ቤት የተናገረው ሙጂብ አሚኑ ለሚያዚያ 7 ተቀጠረ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ድጋፍ ለማሰባሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀናሉ

$
0
0

የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና የሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

በሰሜን አሜሪካ የሰማያዊ እና የአንድነት ፓርቲዎች ድጋፍ አሰባሳቢ ድርጅቶች በትብብር ለመስራት መስማማታቸው ይታወሳል። በስምምነቱ መሰረት የመጀመሪያው የጋራ ስራቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበርን የሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት በጋራ ማስተባበር አድርገው ጀምረዋል፡፡ በዚህም መሰረት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት በጋራ ኮሚቴው በተደረገላቸው ጥሪ መሰረት በመጪው ሚያዚያ (ኤፕሪል) ውስጥ በሰሜን አሜሪካ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዝግጅታቸውን አጠናቀዋል፡፡

የጉብኝቱ ዋና ዓላማ፤ በመጪው ግንቦት በሚካሄደው ምርጫ ውስጥ ለሚሳተፉ የሰማያዊ ፓርቲ እጩዎች ገንዘብ ማሰባሰብ ሲሆን፤ በተጨማሪም፤ በኢትዮጵያ የምርጫ ሂደት ምን ይመስላል፣ ምርጫው ውስጥ መቆየት ያለው ፋይዳ፣ የሰማያዊ ፓርቲ አጠቃላይ ገፅታና እንቅስቃሴ ምን ይመስላል፣ በሚሉት ጥያቄዎች ላይ ውይይት ይደረጋል፡፡ የፓርቲውን የሰላማዊ ትግል ስትራቴጂዎች በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያዉያን ማስረዳትና በነዚህ ጉዳዮች እንዲሁም ባጠቃላይ የአገራችን ወቅታዊ ሁኔታዎች ዙሪያ ከኢትዮጵያዊያን ጋር ዉይይት ማኪያሄድም የዝግጅቱ አካል ነው፡፡

የጉብኝቱ ጊዜያዊ መርሃ ግብር እንደሚከተለው ሲሆን ወደፊት እነደየሁኔታው ሊቀየር፤ ሊጨመር፤ ወይም ሊቀነስ የሚችል መሆኑንም አስቀድመን እናሳስባለን።

የየከተሞቹ ዝርዝር ፕሮግራም በቅርቡ በመገናኛ ብዙኋን ይፋ የሚደረግ ሲሆን፤ በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ባቅራቢያቸው በሚደረጉት የዉይይት መድረኮች ላይ ተሳታፊ በመሆን ስለኢትዮጵያ አገራችን እንዲሁም ስለወገናችን የወደፊት እጣፈንታ ዉይይት እንዲያካሂዱ ኮሚቴዉ ጥሪዉን ያስተላልፋል።

በየከተሞች የምትገኙ የሰማያዊ እና የአንድነት ድጋፍ ሰጪ ማህበራት አባላትም ይህ ፕሮግራም የተሳካ እንዲሆን የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድትለግሱ የጋራ ኮሚቴዉ ጥሪ ያደርጋል።

ከአክብሮት ሰላምታ ጋር

የሰማያዊ እና የአንድነት የሰሜን አሜሪካ የድጋፍ ድርጅቶች የጋራ ኮሚቴ

ለበለጠ መረጃ info@semayawiusa.org ኢሜል በማድረግ ወይም በ (202) 556 – 3078 መልክት በመተው አዘጋጅ ኮሚቴዉን ሊያገኙ ይችላሉ።

semawi

The post የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌትነት ድጋፍ ለማሰባሰብ ወደ ሰሜን አሜሪካ ያቀናሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሸዋ ረገድ ገድሌ –ዳንኤል ክብረት

$
0
0

የምታስፎክር ሰንጋ ገለሌ

በጦር መካከል ሳይሆኑ አያሌ

በጥይት ገዳይ ነጭ ብርገድሌ

የሴት ወንድ ናት ሸዋረገድ ገድሌ

DSC_0419ተብሎ የተገጠመላቸውን፣ በአምስት ዓመቱ የጠላት ወረራ ጊዜም አኩሪ ጀብዱ የፈጸሙትን የአርበኛዋን የሸዋረገድ ገድሌን ታሪክ የሚተርክ መጽሐፍ ሰሞኑን ቀርቧል፡፡ ‹ሸዋ ረገድ ገድሌ፣ የአኩሪ ገድላት ባለቤት›  ይሰኛል፡፡ ሺበሺ ለማ ጽፎት ዶክተር ክፍሌ ማርቆስ ገድሌ አሳትመውታል፡፡

በአምስት ዓመቱ የፋሽስት ወረራ ጊዜ ለሀገራቸው አኩሪ ገድል በመፈጸምና ለነጻነታችን ዋጋ በመክፈል ስማቸው ከሚነሡ ሴቶች ሸዋረገድ ገድሌ ግንባር ቀደም ናቸው፡፡ በ1878 ዓም የተወለዱት ወ/ሮ ሸዋ ረገድ ገድሌ ሁለገብ እንደነበሩ ታሪካቸው ያሳያል፡፡ የቤተ ክህነቱን ትምህርት ተምረዋል፡፡ ትዳርን አልፈልግም ብለው ምናኔን መርጠው ኢየሩሳሌም ድረስ ተጉዘዋል፡፡ ከመጀመሪያዎቹ የባንክ ተጠቃሚዎች፣ የአክሲዮን ገዥዎች፣ የፋብሪካ ተካዮች መካከል አንዷ ነበሩ፡፡ የጉለሌ ቅዱስ ገብርኤልንም ያስተከሉት እርሳቸው ነበሩ፡፡

 

የሸዋረገድን ስም ይበልጥ ከፍ አድርጎ ያስጠራው አርበኛነታቸው ነው፡፡ የኢጣልያ ጦር ሊጎርሰን ማሰፍሰፉ ሲሰማ በአዲስ አበባ ከተማ በሀገር ተቆርቋሪ ዜጎች በተቋቋመው የሀገር ፍቅር ማኅበር አባልነት መጀመሪያ ከተመዘገቡት ጥቂት ሴቶች መካከል አንዷ እርሳቸው ነበሩ፡፡ ወራሪው ፋሽስት አዲስ አበባ ሲገባና የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የኢጣልያ ባንዴራ ሲተካ ወ/ሮ ሸዋረገድ ገድሌ ስቅስቅ ብለው አለቀሱ፡፡ በዚህ ምክያትም በኋላ  ‹የኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የገናናው የኢጣልያ ሰንደቅ ዓላማ ሲውለበለብ በማየትሽ አልቅሰሻል›› በሚል ተከሰው ነበር፡፡ ሸዋረገድም ያለምንም ፍርሃት ‹አዎ አልቅሻለሁ፤ ያገሬን መወረርና መዋረድ ያወቅሁት የኛ ሰንደቅ ዓላማ ወርዶ የናንተ ሲውለበለብ በመታየቱ ነው፡፡ ሰው ለእናት ሀገሩ ቢያለቅስ ነውሩ የት ላይ ነው?›› ብለው ነበር የመለሱት፡፡

 

ወ/ሮ ሸዋረገድ ለአርበኞች ስንቅ በማቀበል፣ መሣሪያ በመግዛት፣ መረጃ በማሰባሰብ፣ መድኃኒት በመላክና ሞራል በመስጠት አምስቱን ዓመት በተጋድሎ ነው ያሳለፉት፡፡ በዚህ ምክንያት በተከሰሱ ጊዜም ‹‹ለአርበኞች ስንቅ ማቀበሌ እውነት ነው፤ይህንንም ያደረግኩት ለሀገሬ ክብር ብዬ ነው፡፡ ሰው እንኳን ለሀገሩ የእናንተ ወይዛዝርት ሀገራቸው ያልሆነቺው ኢትዮጵያን ለመውረር የጣታቸውን ቀለበት ሳይቀር መስጠታቸውን ትናገራላችሁ፡፡ እኔም ለሀገሬ የሠራሁት ሲያንሰኝ እንጂ አይበዛብኝም›› ነበር ያሉት፡፡

ወ/ሮ ሸዋረገድ ከሚጠቀሱላቸው ሥራዎቻቸው አንዱ ለቀይ መስቀል ማኅበር የነበራቸው ድጋፍ ነው፡፡ በጦርነቱ ዋዜማ ሐምሌ 1 ቀን 1927 ዓም ለተቋቋመው የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማኅበር ንብረታቸውን ሸጠው አስረክበዋል፡፡ እሥር ቤት በገቡ ጊዜ ከተከሰሱበት ወንጀል አንዱም ‹ቀይ መስቀልን ትረጃለሺ› የሚል ነበር፡፡ ሸዋረገድ ቀይ መስቀልን ከመርዳትም ባሻገር ኢትዮጵያውያን ወይዛዝርት እራፊ ጨርቅ እንዲያሰባስቡ በማድረግ ለአርበኞች ቁስል ማሸጊያ ይልኩላቸው ነበር፡፡

 

ሸዋረገድ ከርዳታው ጎን ለጎን ለአርበኞቹ የመረጃ ምንጭም ነበሩ፡፡ በከተማው የሚገኙ የጠላት መረጃዎችን በማሰባሰብና ወደ አርበኞች በምሥጢር በመላክ አርበኞች እንዲጠቀሙባቸው አድርገዋል፡፡ በዚህና በሌሎች ገድሎቻቸው ምክንያትም የሞት ፍርድ ተፈርዶባቸው ነበር፡፡ በፈጣሪ ቸርነት ግን ሳይፈጸምባቸው ቀርቷል፡፡ የሞት ፍርዱ ባይፈጸምባቸውም የኢጣልያን እሥር ቤት ከሚያዘወትሩት አንዱ ሸዋረገድ ሆነዋል፡፡ በየጊዜው ይታሠራሉ፤ ይፈታሉ፡፡ በመጨረሻ ግን አዚናራ ወደምትባል ከሰርዲኒያ ሰሜናዊ ምዕራብ ወደምትገኝ ደሴት ታሥረው ተልከዋል፡፡

 

እዚያም ቢሆን ጽናታቸው አልተሰበረም፤ ወኔያቸውም አልተሰለበም፡፡ የሚያደርጉት ቢያጡ በእሥር ቤት የሚቀርብላቸውን የተበላሸ ምግብ በአሣሪዎቻቸው ፊት በመድፋትና ጦማቸውን በመዋል ፋሽስትን ይቃወሙ ነበር፡፡ በዚህ ሁኔታም ለአንድ ዓመት ከመንፈቅ ታሥረው ተፈቱ፡፡ አዲስ አበባ ሲገቡ ግን ትግላቸውን ቀጠሉ እንጂ አላቆሙም፡፡ ሕዝቡም

 

የዘበኛ ሱሪ ካኪና ገምባሌ

እንኳን ደኅና መጣሺ ሸዋረገድ ገድሌ

ብሎ ተቀበላቸው፡፡

 

በተለይም በጅቡቲ የነበረ አንድ ኢትዮጵያዊ የሰጣቸውን ‹የይሁዳ አንበሳ› የሚል ጽሑፍና ዓርማ ያለበትን ወረቀት ከንጉሡ የተላከ የሚመስል መልእክት እየጻፉ ወደ በረሐ በመላክ አርበኞችን አበረታተውበታል፡፡ የአዲስ ዓለም የጣልያን ምሽግ ኅዳር 5 ቀን 1933 ዓም በአርበኞች ሲሰበር ዋናውን መረጃ የሰበሰቡትና ዐቅድ የነደፉት ሸዋረገድ ነበሩ፡፡ ከምሽጉ ሰበራ በኋላም ደጀን መሆኑን ትተው ራሳቸው ወደ ውጊያ ዐውድማ ገቡ፡፡ በተለይም መቂ አካባቢ ከሻለቃ በቀለ ወያ ጦር መካከል ተሰልፈው ተዋግተዋል፡፡ በኋላም ጅማ አካባቢ ከነበረው ከገረሱ ዱኪ ጦር ጋር ለመገናኘት ተጓዙ፡፡ በዚያ እያሉም ጠላት ድንገተኛ አደጋ ጥሎ ገጠማቸው፡፡ ለአራት ሰዓት ያህልም ተዋግተው ተማረኩ፡፡ ወደ እሥር ቤት ተወስደውም የፊጥኝ ታሠሩ፡፡

 

በ1933 ዓም ሀገሪቱ ከፋሽስት ኢጣልያ ወረራ ነጻ ስትወጣ ሸዋረገድ ገድሌ አርበኞችን ወደመርዳትና የበጎ አድራጎት ሥራን ወደ መሥራት ገቡ፡፡ በንግዱም መስክ ተራመዱ፡፡ ሀገራቸውን እስኪበቃቸው አገልግለው፤ ግሼን ማርያም ሄደው ሥጋወደሙን ተቀብለው፤ ከዚያም ወደ ላሊበላ ተጉዘውና ተሳልመው፤ የመጨረሻቸው መሆኑን እየተናገሩ ጥቅምት 22 ቀን 1942 ዓም ዐረፉ፡፡ ሕዝቡም

 

እናንት ወጥ ቤቶች በርበሬ ቀንጥሱ

እናንት ሥጋ ቤቶች ሰንጋውን ምረጡ

ሸዋረገድ ገድሌ ለገና ሲመጡ፡፡

ቤተሰቧ ሰፊ ገናና ጥምቀት

ሸዋረገድ ገድሌ እንደምን ትሙት፡፡ ብሎ ገጠመላቸው፡፡ 

 

ሰፊ ነው ታሪካቸው፡፡ ልብ የሚያሞቅ፤ ወኔ ቀስቃሽ፤ አስደማሚ፤ ከዐለት የበረታ ጽናት፤ ከእቶን የጋለ አርበኝነት፤ ከትንታግ የተንቀለቀለ የሀገር ፍቅር ታገኙበታላችሁ፡፡ ምናለ አደባባዮቻችን በንግድ ኩባንያዎች ስም ከሚጠሩ በነ ሸዋረገድ ገድሌ ስም ቢሰየሙ ብላችሁም ትቆጫላችሁ፡፡

The post ሸዋ ረገድ ገድሌ – ዳንኤል ክብረት appeared first on Zehabesha Amharic.

በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል!

$
0
0

የህዝብ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ አሳታፊ የትግል ስልት ነው!
ረቡዕ መጋቢት 9/2007

Photo File

Photo File

የኢትዮጵያ ሙስሊም በእምነቱ ላይ የተቃጣውን የአስተሳሰብና የጥቃት ዘመቻ ለመመከት፣ አስተሳሰቡን በኢስላማዊ አስተሳሰብ ለማረቅ፣ በሽፋን የሚደረገውን ጥቃት በህግ እልባት ያገኝ ዘንድ ባደረገው የትግል ሂደት ከላይ ወደታች የሆነ የተመሪነት ስርዓት ብቻ ሳይሆን ከታች ወደላይ ፍሰት ያለው መሪዎችን የመምራት ሥርዐት መፍጠር ችሏል፡፡ ይህም ህዝበ ሙስሊሙን የትግሉ ባለቤትና የመሪዎቹም መሪ አድርጎታል፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ አደባባይ የወጣው ‹‹በጊዜ ሂደት ይፈታሉ፣ አልያም ከሀገሪቷ ሁለንተናዊ ዕድገት ጋር አብረው ይቀረፋሉ›› በሚል በሆደ ሰፊነት የተሸከማቸውን ስር የሰደዱ መንፈሳዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ ተቋማዊና መሰል ችግሮች ለመጠየቅ ሳይሆን ተገድበው የተሰጡትን መሰረታዊ መብቶች መልሶ የመንጠቁን እኩይ ዘመቻ ለመግታት ነው፡፡ የእነዚህ እኩይ ተግባራት ድምር ውጤት ዘመን ተሻጋሪና በእምነታችን ላይም ሆነ በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ማንነታችን ላይ የሚያደርሰውን ከፍተኛ አደጋ መረዳቱ ለህዝበ ሙስሊሙ የመንቃት ምንጭ፣ ለትግሉም ገፊ ሀይል ከመሆን ባሻገር ህዝቡን ፅናት ያላበሰና ለመስዋእትነት ያዘጋጀ ነበር፡፡

ከሰው ልጅን የታሪክ ምዕራፍ ሰፊውን ቦታ የሚሸፍነው ትግል ነው፡፡ በተለያዩ ወቅቶች የሰው ልጆች በግልም ይሁን በህብረት ለተለያየ ዓላማና ግብ የተለያዩ ስልትና መርሆዎችን የተከተሉ ትግሎችን አካሂደዋል፡፡ የማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የትግል ስልት ደግሞ የህዝብን ንቃተ ህሊና መጎልበት የሚያመላክት የሰለጠነ የሰላማዊ የመብት ትግል መገለጫ ነው፤ ምክንያቱም መንግስት የህዝብን ጥያቄ ጆሮ ሰጥቶ ከማድመጥ ይልቅ የህዝብን ድምፅ በኃይል ለማፈን የሚያደረገው ጥረት ከዕለት ወደ ዕለት እየጨመረ በመጣ ቁጥር ህዝብ የመንግስትን ደጅ ከማንኳኳት ይልቅ መንግስት ላይ ዘርፈ ብዙ ጫና በመፍጠር መንግስት ወደህዝቡ ደጅ እንዲመጣ የሚያስገድዱ ለእምቢተኝነት የተሰጡ የእምቢተኝነት ምላሾችን አማራጭ አድርጎ ይወስዳልና! በተጨማሪም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እምቢተኝነት የተለየ መዋቅር የማይጠይቅ፣ ሁሉም ህብረተሰብ በየአካባቢውና በየዘርፉ የሚታገልበትና የተናጠል መስዋእትነትን የሚቀንስ የትግል ስልት ሲሆን ተጽእኖ ፈጣሪነቱም ዓይነተኛ መሆኑ አሌ የሚባል እንዳልሆነ ታሪክ ይመሰክራል፡፡

ይህ ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ምክኒያታዊ የለውጥ እርከኖችን ተሻግሮ የመጣ እንደመሆኑ ተግባራዊነቱ ዋስትና ያለው፣ ከጠባቂነት የሚያላቅቅ፣ እስከ ድል ደጃፎች ድረስ የተዘረጋው የመብት ትግል በሰላማዊነት እና ቁርጠኝነት ድልድይ ላይ ተሻግሮ የችግርን ወንዝ እንዲሻገር ያስችላል፡፡ ይህን ህዝባዊ የለውጥ ፍላጎት ማዳመጥ ደግሞ ተገቢ ብቻ ሳይሆን ህዝብ የመሪዎቹ መሪ መሆኑን ማሳያም ጭምር ነው፡፡ በመሆኑም በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ ትብብር መንፈግ (እምቢተኝነት) ላይ ያተኮሩ የተቃውሞ መንገዶችን በመጠቀም የምናካሂዳቸው መርሃ ግብሮች ይኖሩናል፤ በአላህ ፈቃድ! ሁላችንም በዚህ መሰሉ ትግል ላይ ግንዛቤያችንን የሚያዳብሩ ጽሁፎችን በማንበብ እና መንፈሳዊም ሆነ ስነ ልቦናዊ ዝግጅት በማድረግ ሰላማዊ ትግላችንን እስከድል ደጃፎች ለማድረስ የገባነውን ቃል እናድስ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!
አላሁ አክበር!

The post በመጪዎቹ ሳምንታት በቦይኮት እና ህዝባዊ እምቢተኝነት ላይ ያተኮሩ መርሃ ግብሮች ይኖሩናል! appeared first on Zehabesha Amharic.

136 መምህራን የሥራ ማቆም አድማ መቱ • ‹‹ከአሁን በኋላ ለመምህራን ማህበርና ለአልማ አንከፍልም!››

Next: የነአብርሃ ደስታ, ሃብታሙ አያሌውና ሌሎችም የፍርድ ቤት ውሎ:- ‹‹እኔ አሸባሪ አይደለሁም፡፡ ኢህአዴግ አሸባሪ ነው፡፡ ለሽብር ሀሳቡም ፍላጎቱም የለኝም›› ዳንኤል ሺበሺ ‹‹የተባለውን ለነገር አለማድረጌን ከእኔ በላይ የከሰሰኝ መንግሥት ጠንቅቆ ያውቃል›› ሀብታሙ አያሌው ‹‹ለእኔ ብቸኛው አሸባሪ ህወሃት/ኢህአዴግ ነው፡፡ እኔ የህወሃት/ኢህአዴግ ተቃዋሚ ነኝ›› አብርሃ ደስታ ‹‹ይሄ 19ኛ ችሎት የጦር ፍርድ ቤት ችሎት እየመሰለ ነው›› የሺዋስ አሰፋ ‹‹ሃይማኖቱንና ማኅበረሰቡን ከሚፈራ ህዝብ ወጥቼ እንዲህ አይነት ተግባር አልፈጽምም›› ባህሩ ታዬ
$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በምስራቅ ጎጃም ዞን የደብረወርቅ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 136 መምህራን ዛሬ መጋቢት 10/2007 ዓ.ም የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገለፁ፡፡ መምህራን ላይ እየተፈፀመ ያለውን የአስተዳደር በደል ተከትሎ 92 መምህራን ‹‹እኛ በደል እየደረሰብን ቢሆን መምህራን ማህበር ችግራችን እየፈታልን ባለመሆኑ ከአሁን በኋላ አባል እንዳልሆንን እንዲታወቅ፣ በየወሩ ከደመወዛችን እንዳይቆረጥብን›› በሚል ፊርማ አስገብተዋል፡፡ ከመምህራን ማህበር በተጨማሪ በየወሩ ከደመወዛቸው ለአልማ የሚቆረጠው ገንዘብም እንዲቆም መምህራኑ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡
news
ባለፉት የመምህራን ስልጠናዎች የምስራቅ ጎጃም መምህራን ላይ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶ እንዲሰራበት ማሳሰቢያ ተሰጥቶ እንደነበር የገለጹት መምህራኑ በተለይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ ዘላለም ጌታነህ የወረዳው መምህራን ማህበር ፀኃፊ ከሆኑ በኋላ ጫናዎች እንደበዙባቸው ገልጸዋል፡፡ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትና መምህራን ማህበር ፅ/ቤት የሚሰራው አቶ ዘላለም ዕጩ መሆኑ ከታወቀ በኋላ መምህራኑ አራት ጊዜ እንዲፈርሙ የተጠየቁ ሲሆን ይህም አቶ ዘላለም ለመምህራን ማህበሩ እያደረገ ባለው አስተዋጽኦና በፖለቲካ አቋሙ ምክንያት እየተፈፀመ ያለ በደል ነው ብለዋል፡፡

የመምህራኑን ፊርማ ተከትሎም መጋቢት 9/2007 ዓ.ም የወረዳው ምክር ቤት 18 ያህል መምህራንን ብቻ ጠርቶ ‹‹እንወያይ›› ባለበት ወቅት መምህራኑ ‹‹ካወያያችሁ ሁላችንም አወያዩን እንጅ እኛን ብቻ ነጥላችሁ ልታወያዩን አይገባም፡፡›› በማለታቸው ምክር ቤቱና መምህራኑ ሳይግባቡ ተለያይተዋል፡፡ መምህራኑ በትናንትናው ዕለት ስራ ገበታቸው ላይ እያሉ ተጠርተው ‹‹እንወያይ›› ቢባሉም በዝምታ ተቃውሟቸውን በመግለፃቸው የወረዳው አስተዳዳሪ አቶ በለጠ ገሰሰ ‹‹አንወያይም ብላችሁ አምጻችኋል፡፡ ስለዚህ ነገ ስራ እንዳትገቡ፡፡ ስራ ገብታችሁ ትምህርት ቤቱ ውስጥ የሰው ነፍስ ቢጠፋ ተጠያቂዎቹ እናንተ ናችሁ፡፡›› በሚል እንደዛቱባቸው መምህራኑ ገልጸዋል፡፡ የወረዳው የትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ፍቅረአዲስ ሙሉሰው በበኩላቸው ‹‹ለአንድ ቀን ብቻ ሳይሆን ለአንድ ወርም መግባት የለባቸውም›› በሚል መምህራኑ ላይ ቅጣት እንዲወሰን መጠየቃቸው ተገልጾአል፡፡

መምህራኑም ለምክር ቤቱ ‹‹በቃል የነገራችሁንን ውሳኔ በጽሁፍ ስጡን›› የሚል ጥያቄ ቢያቀርቡም ውሳኔው በጸሁፍ ሊሰጣቸው እንዳልቻለና የወረዳውን ባለስልጣናት ውሳኔ የሰሙት 136 መምህራን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የስራ ማቆም አድማው ዛሬ ጠዋት ከተጀመረ በኋላ ተማሪዎች 3፡20 ላይ ክፍል ጥለው በመውጣት መምህራኑን መደገፋቸው ተገልጾአል፡፡
ደብረወርቅ የሰማያዊ ፓር ሊቀመንበር የኢ/ር ይልቃል ጌትነት የትውልድ ቦታ መሆኑን ተከትሎ የብአዴን ካድሬዎች በህዝቡ ላይ ከፍተኛ ጫና እያሳደሩ እንደሚገኙ ምንጮች ገልጸዋል፡፡

The post 136 መምህራን የሥራ ማቆም አድማ መቱ • ‹‹ከአሁን በኋላ ለመምህራን ማህበርና ለአልማ አንከፍልም!›› appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>