Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

አቃጠሉት አሉ!!! -ከ-ከተማ ዋቅጅራ

$
0
0

Awasaትላንትና ማታ ለአዋሳ ከተማ ነዋሪዋች ከባድ ቀን ነበረ። ከባድ ብቻ  ሳይሆን አስደንጋጥም ነበረ። በአዋሳ ከተማ አዲስ ከተማ  ተብሎ የሚጠራው ቦታ የገበያ ማእከሉ ከፍተኛ ንብረት እና በሰው ህይወት ጉዳት ያስከተለ የእሳት አደጋ አስተናግዳለች። በዚህ ሌሊት በከተማዋ የተነሳው እሳት እየተንቀለቀለ ወደ ሰማይ ይወረወር ነበረ። ይህ ለአዋሳ ህዝብ ከባድ ሌሊት ላይ ጭኸቱ ከየት እንደሆነ በማይታወቅ መልኩ ከተማዋ በሃዘን ጭኸት ስትናወጥ ነበረ። እጅግ ዘግናኝ ሌሊት ነበረ።

አዋሳ ! አዲስ ከተማን ማን አቃጠላት? የእሳቱስ መንስኤ ምንድን ነው? በጅምላ በአንድ ላይ እሳት ይነሳል እንዴ? አካባቢዋን እንቃኛት።

አዲስ ከተማ ተብሎ በአዋሳ ውስጥ የተመሰረተች አዲስ መንደር አዲስ ሰፈር በአዲስ ምስረታ የተመሰረተች እና እያደገች ያለች ከተማ ናት። ይህቺ ከተማ በእሳት የጋየችውን መንደር  መንግስት ለመንገድ ስራ እንደሚፈልገው እና በመንደሯ ውስጥ የሚያልፍ መንገድ ለመገንባት እንደሚያስብ ለነዋሪው ተነግሮአቸው ነበረ። ታዲያ ልማትን የሚቃወም የለም። ህዝቡ ተጠቃሚ የሚያደርግ እና ትክክለኛነቱን የታመነበት ከሆነ መንገድ በመሰራቱ ተቃውሞ  የሚያሰማ አለ  ብዬ አልገምትም። ታዲያ መንገድ ለመስራት እሳት ማስነሳት ለምን አስፈለገ? መንገድና እሳት ምንድነው ዝምድናቸው? እሳት ከመንገድ ጋር ምንም ዝምድና የላቸውም። እሳት ከወያኔ ጋር ግን ዝምንድና አላቸው። ተዛማጅነታቸው በ3 መንገድ ነው።

1ኛ. ለግምት የሚያወጡትን ወጪ ስለሚያስቀርላቸው። ምክንያቱም እሳቱ  የተነሳው በግለሰቦች የጥንቃቄ ጉድለት ነው በማለት እሳቱ ንብረትን ማውደሙን ካረጋገጡ በኋላ እሳት አደጋ መጣ ለማስባል ባለቀበት መጥቶ ውሃውን ረጨት ረጨት አድርጎ ካጠፋ በኃላ ቦታው አካባቢው ከሳቱ በፊትም ከሳቱ በኋላም በፌድራል እንዲከበብ በማስደረግ እዝቡን ካራቁ በኋላ ሌላ ተቀያሪ ቦታ ይሰጣችኋል በማለት ህብረተሰቡን ለከፋ እንግልት መዳረግ እና መንግስት የራሱን  ጥቅም ማስጠበቅ።

2ኛ. የሰው ህይወትን ጉዳት ላይ መጣል አልያም የንብረት መውደም ስለሚያስደስታቸው ነው። ወያኔ ህዝብን የመጥላት እና የመናቅ ሰይጣናዊ አባዜ ስለተጠናወተው እንደዚ አይነቱን ተግባር በማድረግ ህዝብን ለስቃይና ለመከራ ሲዳረጉ ማየት ስለሚያስደስተው።

3ኛው እና ዋንኛው ደግሞ ጭንቀት ሲበዛበት ነው። ይህ ማለት ወያኔ ከፊቱ ከባድ ነገር እንደሚመጣበት በሚያውቅበት ግዜ ሃሳብን ለመስረቅ የሚጠቀምበት ዘዴ ነው። በአሁኑ ግዜ ወያኔን አንፈልግህም፣ ወያኔ አያስተዳድረንም፣ ወያኔ በቃን፣ የሚሉ ጥያቄ በርትቷል። በትጥቅም ትግል ያስጨነቁትም ኃይሎች አሉ፣ ታዲያ የህዝቡ ሃሳብ በአንድ ተቀናጅቶ ትኩረቱን ወደ ወያኔ ካዞረ ስልጣኑን እንደሚያጣው ያውቃል ስለዚህ ለዚህ ፍራቻው እንደዚ የወረደ ተግባር እና ሰይጣናዊ ስራ ይሰራል።

ወያኔ መንግስት ከአሁን በኃላ ሁሉም ነገር ያበቃለት ይመስለኛል። አንዴ ድሬድዋን ቢያቃጥል አንዴ አዲስ አበባን ቢያቃጥል አንዴ አዋሳን ቢያቃጥል የህዝቡ መልስ ግን አንድ ነበረ። ይህንን የወረደ እና አሳፋሪ ስራ የሚያደርገው ወያኔ እንደሆነ አረጋግጠው በመናገር ላይ ናቸው። ህዝብ መሪ ነን ከሚሉት ቀድሞ ሄዷል።

ለአዋሳ ህዝብ ይህ ድርጊት በደል ነው። ወያኔ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው ዛሬም በአዋሳ ህዝብ ላይ አድርጎታል። ልክ እንደ ጸበል የሁሉንም ክልል እንደሚያደርስ ጥርጥር የለኝም። የህዝ ንብረት እንዳይቃጠል፣ ህዝባችን የእሳት ሰለባ እንዳይሆን፣ የህዝባችን እንባ በከንቱ እንዳይፈስ፣ ህዝባችን ለፍቶ ያፈራው ንብረት በአንድ ሌሊት በማጣት ወደ ስቃይ እንዳይገባ፣ ዋናውን እሳት ቤንዚን እና ክብሪት የሆነውን ወያኔን ቀድሞ ማጥፋት ነው። ያኔ በህዝብ ላይ እና  በህዝብ ንብረት ላይ እሳት የሚያስነሳ አይኖርም።

ከ-ከተማ ዋቅጅራ                                                                                                      23.02.2015                                                                                                                   Email- waqjirak@yahoo.com

The post አቃጠሉት አሉ!!! -ከ-ከተማ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.


ከኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል (ሸንጎ)ና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC) ሁሉን አቀፍ የሆነ አማራጭ ኃይል ተወያይቶና ተስማምቶ ስለማቋቋም አስፈላጊነት የተሰጠ የጋራ መግለጫ

$
0
0

shengoENTCየኢትዮጵያ ሀገራችንና ህዝባችን ሰቆቃና በደል ከጊዜ ወደጊዜ እይባሰ በመሄድ ላይ ይገኛል። የዜጎች የኑሮ ዋስትና ከዕለት ዕለት ጥያቄ ውስጥ እየገባ ነው። ምንም እንኳን የበደሉን ጥልቀት መዘርዘር ለቀባሪው አረዱት ቢሆንም ባጭር ሀርጎች ብንጠቅስ፤ የጨቋኙና የከፋፋዩ የህውሀት ወያኔ አገዛዝ የህዝቦቿን መከባበርና አንድነት በጥላቻና በመከፋፈል ለመተካት የሚጥርበት፤ ዜጎች አላግባብ የሚታሰሩባት፣ የሚገደሉባት፤ የሚሰደዱባት፤ ነፃ ፍትሐዊና ዲሞክራሲያዊ ምርጫ የማይካሄድባት፤ ዜጎች ከመኖሪያቸውና ከቀዬአቸው የሚፈናቀሉባት፤ ለሕግ ተገዢ ያልሆነ ፍጹም አምባገነናዊ ሥርዓት ያለባት፤ ዜጎች የገዢው ፓርቲ አባል ካልሆኑ በነፃነት ሠርተው መኖር የማይችሉባት፤ በተግባር ያልዋለ ህገ-መንግሥት ያላት፤ ከገዢው ፓርቲ ቁጥጥርና ነፃ የሆኑ የመገናኛ ብዙሀንና የማህበረሰብ ድርጅቶችና የሌሉባት፤ የኃይማኖት ነጻነት በፖለቲካ የበላይነት የሚመራባት፤ በሀገሪቱ የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት-የምርጫ ቦርድ፤ ፍርድ ቤቶች፤ ፖሊሶች፤ የደህንነት መስሪያ ቤቶች፤ መከላከያና ሌሎች የገዢው ፓርቲ ፖለቲካ መጠቀሚያ የሆኑባት፤ ዜጎች እንደ ሰው በሃገራቸው የመኖር መብቶች በሌለበት፤ የእድገት ምልክቶች ናቸው ተብለው የተሰሩ ህንፃዎችና ቤቶች በቁመታቸው ባዶ ሆነው መገኘታቸው እንደ ብሄራዊ ልማት የሚቆጠርባት፤ ወጣቶች ተምረው በሃገራቸው ሰርተው ለመኖር ስለማይችሉ የሚሰደዱባት ወዘተ ሀገር ሆናለች።

—-[ሙሉውን መግለጫ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ]—

The post ከኢትዮጵያ ሕዝብ የጋራ ትግል (ሸንጎ)ና የኢትዮጵያ ብሄራዊ የሽግግር ምክር ቤት (ENTC) ሁሉን አቀፍ የሆነ አማራጭ ኃይል ተወያይቶና ተስማምቶ ስለማቋቋም አስፈላጊነት የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዚህ ሁሉ እልቂት “ኩሹፍ” ሲገለጥ – ( አርአያ ተስፋማሪያም)

$
0
0

10422405_1581759842070160_3657759649011452265_nጠ/ሚ/ር ሃ/ማርያም፣ ባለቤታቸውና ሌሎች አንገታቸው ላይ ስላጠለቁት በተመለከተ አንድ የቀድሞ አንጋፋ የድርጅቱ ታጋይ በግል ያደረሱኝ መልእክት እንዲህ ሲል ይጀምራል « በታጋዮች ዘንድ “ኩሹፍ” ተብሎ ይጠራል። ታጋዩ ከሞተ በኋላ የሚገነዝበት ጨርቅ ነው። ድርጅቱ አላማ ያለው የመሰለው አብዛኛው ታጋይ ያን ጨርቅ አንገቱ ላይ በማጥለቅ ለመሰዋት (ለመሞት) ቁርጠኝነቱን የሚያሳይበት ነበር። 98 በመቶ የሚሆነው ተዋጊ ያልተማረ ስለነበረ የድርጅቱ አላማና አካሄድ ሊያውቅበት የሚችል አንድም መንገድ አልነበረም። በእሱ ደምና አጥንት ተረማምደው ሲያበቁ የራሳቸውን ድብቅ አጀንዳ አስፈፀሙ። 36 ሺህ የህወሀት ታጋዮችን ገና በጠዋቱ አባረው ለአስከፊ የጐዳና ህይወት ዳረጓቸው።

ኢትዮጵያውያን ወንድማማቾችን በብሄር ፖለቲካ እርስ በርስ እንዲናቆሩ እነመለስ የጥፋት ወጥመድ ዘረጉ። “ፓርቲው ወዴት እየሄደ ነው?..ግምገማ መካሄድ አለበት፤ ሙስና ተቀጣጥሏል..” የሚሉ ጥያቄዎችን ያነሱና ከጋንታ እስከ ሬጅመንት አዛዥነት (ኋላ መኮንኖች) ቦታ የነበራቸው 5 ሺህ ታጋዮች ሆለታና ታጠቅ እስር ቤቶች ታጐሩ። አቶ መለስ 36 ሺህ ታጋይ በ84 ዓ.ም ሲያባርሩ «ጓሃፍ ፅረጉለይ..» ማለትም “እነዚህን ቁሻሻ ጥራጊዎች አስወግዱልኝ” ነበር ያሉት። ትእዛዙን ደግሞ ስዬ አብርሃ ተፈፃሚ አደረጉ። ለ5 ሺህ መኮንኖች ደግሞ ያቀረቡት ሰበብ «መፈንቅለ ፓርቲ ለማድረግና እኔን ለመገልበጥ ሲያሴሩ..» የሚል የፈጠራ ክስ በመለስ ዜናዊ ቀረበባቸው። በሆለታ እስር ቤት በ1988 ዓ.ም እንዶድ የተባለ መርዝ ጨቅጭቀው የጠጡ 1 ሺህ 5 መቶ (1,500) መኮንኖች ህይወታቸው ሲያልፍ የሁሉም ሬሳ በአንድ ጉድጓድ በሌሊት እንዲከተት ተደረገ።

በታጠቅ ከ1 ሺህ የሚበልጡ በተላላፊ ሳንባ እንዲያልቁ ተፈረደባቸው። የዚህ ሁሉ እልቂት ምስጢሩ ታጋዮቹ “የሃየሎም ግሩፕ” በሚል በነመለስ ስለተፈረጁ ነበር። እነሱን ከጨረሱ በኋላ እሱንም አስገደሉት። ሃቁ ይህ ሲሆን ዛሬ እነሃ/ማርያምና ሌሎቹ ባልዋሉበትና ባልነበሩበት ትግል ያን “ሽኩፍ” አጥልቀው መታየታቸው ያሳፍራል። ለነገሩ በታጋዩ መስዋእትነት የተረማመዱት የዛሬው ሚሊየነሮች አጥልቀው ታይተው የለ!! ታሪክና ጊዜ ይፈርደናል!» ይላል። …በነገራችን ላይ የሆለታና ታጠቅ እስር ቤት የጅምላ እልቂትና ስቃይ በተመለከተ በ1994 ዓ.ም ጥቅምት ወር አንስቶ የአንዳንድ ሟች ታጋዮች ፎቶ በማስደገፍ እንዲሁም በእስር ቤት የፃፏቸውን መልእክቶች በማያያዝ በኢትኦጵ ጋዜጣ በተከታታይ መረጃው ይፋ ተደርጓል።

The post የዚህ ሁሉ እልቂት “ኩሹፍ” ሲገለጥ – ( አርአያ ተስፋማሪያም) appeared first on Zehabesha Amharic.

አስገደ ገ/ስላሴ በባለስልጣናቱ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው ገለጹ

$
0
0
አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

መጽሐፋቸው ላይ ስም አጥፍተዋል በሚል ተከሰው የህወሓት ባለስልጣናትን በመከላከያ ምስክርነት ቢጠሩም ባለስልጣናቱ በተደጋጋሚ በቀጠሮው ቀን ባለመገኘታቸው ለምስክሮች በሚያወጡት ወጭ ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው አቶ አስገደ ገ/ስላሴ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡

ጥር 10/2007 ዓ.ም አቶ አስግደ በምስክነት ከጠሯቸው የህወሓት ባለስልጣናት መካከል ጀኔራል ጻድቃን ሲገኙ አቶ ስዩም መስፍን፣ አቶ ስብሃት ነጋ፣ አባይ ጸሃዬ፣ አርከበር እቁባይና ሌሎችም ባለስልጣናት ያልተገኙ ሲሆን ለየካቲት 13/2007 ዓ.ም በፖሊስ ተይዘው እንዲቀርቡ ሲወሰን ጄ/ር ጻድቃንን ጨምሮ ሌሎቹም በትዕዛዙ መሰረት ሳይገኙ ቀርተዋል ብለዋል፡፡ ባለስልጣናቱ በዳኛዋ ትዕዛዝ መሰረት የካቲት 13/2007 ዓ.ም ባለመቅረባቸው ለሶስተኛ ጊዜ ለየካቲት 24/2007 ዓ.ም በፖሊስ ተይዘው ቀርበው እንዲመሰክሩ ታዟል፡፡

ባለስልጣናቱ በቀሩባቸው ቀጠሮዎች አቶ አስገደ ከትግራይ አውራጃዎችና ከአዲስ አበባ ድረስ ለመጡ ምስክሮች የትራንስፖርት ወጭ በመሸፈናቸው ከፍተኛ ኪሳራ ድርሶብኛል ብለዋል፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ በተላለፈው ቀጠሮም ባለስልጣናቱ ላይመጡ ይችላሉ ያሉት አቶ አስግደ ‹‹በእነሱ ምክንያት ከፍተኛ ወጭ እያወጣሁ ነው፡፡ አሁንም ለሶስተኛ ወጭ ላወጣ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ከፍተኛ የገንዘብ ኪሳራ አድርሰውብኛል፡፡›› ብለዋል፡፡

The post አስገደ ገ/ስላሴ በባለስልጣናቱ ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ እንደደረሰባቸው ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች መፈክር የተፃፈባቸው ወረቀቶች ተበትነው አደሩ

$
0
0

addis ababa flyer

addis ababa flyer 2

addis ababa flyer 3
አቡ ዳውድ ኡስማን

በአዲስ አበባ ትላንት ለሊቱን በተለያዩ አካባቢዎች ሙስሊሞችን የማሰር ዘመቻውን በመቃወም በራሪ ወረቀቶች ተበትነው እና ተለጥፈው ማደራቸውን ምንጮች አስታወቁ፡፡

ወረቀቶቹ በመንገድ ጋር ግድግዳዎች ላይ፣ በመንገድ ምልክቶች ላይ፣ በመብራት ፖሎች ላይ የተለጠፉ ሲሆን በየመንገዱም መበተናቸው ታውቋል፡፡
ትላንት ሌሊቱን ፒያሳ አምፒር አካባቢ፣ በሜክሲኮ ቄራ መንገድ ላይ፣ በጦር ሃይሎች፣በቦሌ ፒኮክ እና ወሎ ሰፈር፣ በመገናኛ፣ በመካኒሳ፣በቤተል እና በሌሎች ቦታዎች ላይ ወረቀት ተበትነው ማደራቸው ታውቋል፡፡

ከተበተኑት እና ከተለጠፉት መፈክሮች መካከል እስራት ትግላችንን አያስቆመውም፣መስዋትነት የኢስላም መንገድ ነው፣ሺ ሰው ቢታሰር ሺ ሰው ይተካል፣ ለኢስላም መታሰር ክብር ነው፣ ትግላችን ከምረጫው ቡሃላም ይቀጥላል፣ ድምፃችን ይሰማ፣ትግላችን ይቀጥላል የሚሉና ሌሎች በርካታ መልዕክቶችን የያዙ ወረቀቶች በመተናቸው ተገልፆል፡፡

መንግስት በአዲስ አበባ ሙስሊሞች የማሰር ዘመቻውን አጠናክሮ በቀጠለበት ወቅት ህዝበ ሙስሊሙ እስራት መፍትሄ እንደማይሆን በተግባር ያረጋገጠ መልዕክት በትላንትናው ለሊት አስተላልፏል::

The post በአዲስ አበባ በተለያዩ አካባቢዎች መፈክር የተፃፈባቸው ወረቀቶች ተበትነው አደሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

በደብረ ማርቆስ የሰማያዊ እጩ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው

$
0
0

debrezeytበምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ለተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ እጩ ሆነው የቀረቡት አቶ ሳሙኤል አወቀ በፖሊስ የእስር ትዕዛዝ እንደወጣባቸው ታወቀ፡፡

የህግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ሳሙኤል አወቀ ከዚህ ቀደም ‹የዳኞችን ስም በማጥፋት› ክስ ተመስርቶባቸው ጉዳያቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙ ገልጸው፣ አሁን በፖሊስ የወጣባቸው የእስር ትዕዛዝ መሰረቱ ምን እንደሆነ በውል ማወቅ አለመቻላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡

‹‹አንድ የምርጫ ተወዳዳሪ ያለውን የኢሚውኒቲ መብት ረስተው ጉዳዩን በውል ባላወቅሁት ሁኔታ የእስር ትዕዛዝ ማውጣታቸው እኔን ከፖለቲካው ለማግለል ነው፡፡ አሁን ለስራ ጉዳይ ባህር ዳር ነኝ፡፡ በዚሁ ጉዳየን ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞች አስረድቼ በስልክ አውርተውበታል፡፡ አግባብ አለመሆኑንም አምነዋል፡፡ ግን እኔ ላይ ጫና ለማሳደር ትዕዛዙ እንደወጣ አውቄያለሁ›› ብለዋል አቶ ሳሙኤል፡፡

የወጣው የእስር ትዕዛዝ ‹‹በፖሊስ ታሰሮ እንዲቀርብ›› የሚል መሆኑን የገለጹት አቶ ሳሙኤል፣ በቀጣይ የፍርድ ቤት ቀጠሯቸው በስም ማጥፋት ለቀረበባቸው ክስ መከላከያ ማቅረብ እንደሚችሉ እየታወቀ ታስሮ ይቅረብ መባላቸው መሰረቱ ግልጽ አለመሆኑን ተናግረዋል፡፡

The post በደብረ ማርቆስ የሰማያዊ እጩ የእስር ትዕዛዝ ወጣባቸው appeared first on Zehabesha Amharic.

ጠበቃቸውን እንዳያገኙ የተከለከሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በጨለማ ቤት መታሰራቸውን ገለጹ

$
0
0

(ነገረ ኢትዮጵያ) በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ የሚገኙት የሦስት ተቃዋሚ ፓርቲዎች የቀጠና/ዞን አመራሮች ለ16 ተከታታይ ቀናት በጨለማ ክፍል መታሰራቸውን ለፍርድ ቤት አስታወቁ፡፡

newsዛሬ የካቲት 17 ቀን 2007 ዓ.ም በፌደራሉ የመጀመሪያ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት የቀረቡት የሰማያዊ (የፓርቲው የጎንደር አደራጅ አቶ አግባው ሰጠኝ)፣ የአንድነት እና መኢአድ የዞን አመራሮች ‹‹መረጃ አውጡ፣ የደበቃችሁትን ሁሉ ተናገሩ›› እያሉ እንደሚደበድቧቸውና በጨለማ ክፍል እንዳሰሯቸው ተናግረዋል፡፡ ፖሊስ አሁንም መረጃየን ሰብስቤ አልጨረስኩም በሚል ተጨማሪ 8 ቀናት ጠይቆ ተፈቅዶለታል፡፡
ተጠርጣዎቹ በማዕከላዊ እየደረሰባቸው የሚገኘውን ሰቆቃ አስመልክተው ለፍርድ ቤት አቤት ማለታቸውን ተከትሎ ፍርድ ቤቱ ፖሊስ የቀረበበትን አቤቱታ እንዲያስተካክል ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በጎንደርና ጎጃም አካባቢዎች የዛሬ አራት ወር ገደማ በፖሊስ ታስረው ወደ አዲስ አበባ ማዕከላዊ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲዛወሩ የተደረጉ ሲሆን፣ ጠበቃቸው በተደረገባቸው ክልከላ ምክንያት ተጠርጣሪዎቹን ካገኟቸው 2 ወር እንደሞላቸው ተናግረዋል፡፡ ከተጠርጣሪዎቹ መካከል አቶ አግባው ሰጠኝ እየተፈጸመበት ያለውን የመብት ጥሰት በመቃወም የርሃብ አድማ ላይ መሆኑ የታወቀ ሲሆን አድማውን ከጀመረ ሁለተኛ ቀኑ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

ፍርድ ቤቱ በሰጠው የጊዜ ቀጠሮ መሰረት አመራሮቹ የካቲት 25 ቀን 2007 ዓ.ም ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

The post ጠበቃቸውን እንዳያገኙ የተከለከሉት የተቃዋሚ ፓርቲዎች አመራሮች በጨለማ ቤት መታሰራቸውን ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሳውዲ የታገተችው ኢትዮጵያዊት የሰቆቃ ደምጽ !

$
0
0

unnamed (2)ገነት አበበ ሞላ ትባላለች  የልጅነት ግዜዎን ሩጣ  ያልጠገበች በ አስራዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ ኮረዳ ነች። ከዛሬ 3 አመት  በፊት ነበር በኑሮ ውድነት የተጎሳቆሉ ቤትሰቦቾን ከደህንነት ለመታደግ በወቅቱ እስከ ገጠር በዘለቀው የአሰሪና ሰራተኛ የደላሎች ዘመቻ ከአርሲ ኮሌ ወረዳ ኩዬ ከተማ ተመልምላ  የማይጨበጠውን የአረቡን ዓለም መከራ ለመጋፈጥ፡ተስፋ ሰንቃ ወደ ሳውዲ አረቢያ ያቀናቸው ። በወቅቱ በስው ልጆች  ህይወት ዶላር ለማግበስበስ   በየአካባቢው በተከፈቱ የአሰሪና  ሰራተኛ ኤጀንሲ ደላሎች ከእናቶቻቸው ጉያ ተነጥቀው ለአቅመ ሄዋን ያለደረሰውን  እድሜዎቻቸውን ቆልለው  ፓስፖርት የወሰዱ ህጻናት ሳይቀሩ በቀን ከስክ 1500 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያን የኮንተራት ሰራተኞች  የለህይወት ዋስትና ወደ ሳውዲ አረቢያ  በጅምላ ይላኩ የነበረበት  ወቅት በመሆኑ  ወጣት ገነትም ሰው እንደሆነው  እሆናለሁ ብላ በፌስታል የተሞሉ ልብሶቾን  እንደነገሩ ይዛ  የምተወዳቸውን ወላጆቾኝ  በዕንባ  የተሰናበተቸው ።   አንድም ቀን ከቤት ወጥታ  የማታውቀው ገነት አስረክበው ወደ ቀዬያቸው የተመለሱ ወላጆቾ የገነትን ድምጽ ቢናፍቁም ባህር አቋርጣ ሳውዲ ሄደች ከተባለ ወዲህ ወራት ተቆጥረው ዓመት ቢደፍንም ገነትን  የበላ ጀብ  አልጮህ አለ ።

ወትሮስ ለማን አቤት ሊባል ?  « የገነትን ስቃይ ማን ይወቅላት » ክፉ አጋጣሚ ሆኖ  በአሰሪዎቾ  « ኃይል»  ወደ ሚባል   ገጠራማ የሳውዲ ግዛት  ለስራ የተወሰደችው ገነት ወግ ባህሉ ቋንቋው ባዕድ  በሆነባት ሃገር ሁሉም ነገር እንዳሰበቸው እና እንደተነገራት አልነበረም።  ታዲያ ገነት ከቤትሰቦቾ ጋር ስትለያይ  ሲያነቡ  የነበሩት አይኗቾ  እንባ እንደቋጠሩ ነበር    ፍጹም ከባድ የሆነውን የአረቡን ዓለም የቤት ስራ የተጋፈጠቸው  ፡፤  በማለዳው ምናምን ቢጤ ቀማምሳ ለአመታት ተጠርጎ የሚያውቀውን አቧራ የለበስና ቆሻሻ የተከመረበትን ግቢ  ከአሰሪዎቾ በምለክት በተሰጣት  ተዕዛዝ  ስታፀዳና ከ 4 ያላነሱ  መኪኖችን  ስታጥብ  የዋለቸው ።  በዚህ መልኩ ለወራት የተዋሃዳትን የአሰሪዎን የቤት ውስጥ  ስራ ጨምሮ  የማይመለክታትን ከባድ ስራዎች ሁሉ  ካጠናቀቀች በኃላ  ለሌላ አረብ ተላልፋ እይተሰጠች  የቤት ሰራተኛ ለሌላቸው የሰፈሩ አረቦች  ሁሉ አገልጋይ ሆናለች ። ገነት እረፍት የላትም እንደ ዘበኛ መኪና በመጣ ቁጠር የግቢ በር ትከፍታለች የአሰሪዎቾን መኪናና ግቢ ታጥባለች ከባድና ቀላል የሆኑ እቃዎችን እስከ 3ኛ ፎቅ ተሸክማ በመውጣት ከአቅሞ በላይ የሆነና የማይመለከታትን ስራ በግዳጅ እንድትሰራ ትደረጋለች።  ከቤተሰቦቾ  ከተለየች ወዲህ በስልክ ወላጆቾን አጊታቸው የማታውቀው  ገነት ከሥራው ክብደት ይልቅ  በናፍቆት ከሰውነት ጎዳና የወጣው ስውነቷና የልጅነት ወዝዎ  በቁም የተገነዘች ሬሳ አስመስሏታል ፡፡

በአስሪዎቾ ታግት በደል የሚፈጸምባት ገነት ከሚፈፀምባት ግፍ እና በደል  እግር ወደ መራት በመሄድ እርሷን ከባርነት ለመታደግ   የሞከርቸበትም አጋጣሚ እደነበር ይነገራል።  ከዚያ ወዲህ  ገነትን ለማግባባት ብዙ ሞክረው እንዳልተሳካላቸው  የተረዱት አሰሪዎቾ ገነት ላይ የሚያደርጉትን ክትትል በማጠናከር  የስራ ግዳጆዎን  ስትጨርስ ባዶ ቤት ይቆለፉባታል። የቤት ሰራተኛ እጥርት  የገጠማት  ሳውዲ አረቢያ  ውስጥ  በአሰሪዎቾ የታገተቸው ኢትዮጵያዊቷ ወጣት ገነት አበበ ለአሰሪዎቾ እያበረከተች ካለው   ነጻ አገልግሎት ባሻገር  በወር እስከ  3800 በሚደርስ ክፍያ   ለሦስተኛ  ወገን ተላልፋ በመሰጠት ጥሩ የገቢ ምንጭ እስከ መሆን መድረሷ ይነገራል። ከአንዱ የአረብ  መኖሪያ ወደ ሌላው የአረብ መኖሪያ ቤት እይተቀባበሉ  ያለ በቂ እረፍት የአረብ አገልጋይ ለመሆን የተገደደቸውን   ኢትዮጵያዊት  የኮንተራት ሰራተኛ  ከማለት ይልቅ በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ህጋዊ ፈቃድ አጊቶ  በሚንቀሳቀስ አሰሪና ሰራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ  የተሸጥች ባሪያ ማለት ይቀላል።

አዲስ አበባ ውስጥ በተለምዶ  ሚክሲኮ አደባባይ  አካባቢ   ሴብሪን « sebirn » እይተባለ በሚጠራ  አንድ  ኤጀንሲ አማካኝነት  ተዋውላ     ህጋዊ  በሆነ መንገድ ለስራ ሳውዲ እንደገባች የሚነገርላት ገነት  ዛሬም  የይደርሱልኝ ይሰቅቃ ድምጾን ታሰማለች ፡፤

አሁን አሁን ለህይወቷ የምትሳሳው ገነት  ይገሉኛል በሚል ስጋት በድብደባ ከተጓሳቆለው አካሏዎ ባሻገር  ሌሎች  ምስጢራዊ በደሎችን  ለግዜው ከመግለጽ መቆጠቧን ለልጅቷ ቅረበት ያላቸው ወገኖች ይገልጻሉ። እነዚህ ወገኖች አቤቱታቸውን በጅዳ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ቢገልጹም  እስክ አሁን  የገነት የሰቆቃ ድምጽ ምላሽ አላገኘም፤

ስሞኑን በደሞዝ ጥያቄ  በጥይት የቆሰለችውን  ኢትዮጵያዊት  ከወራት ቆይታ በኃላም ቢሆን  እወንታውን በአካል  ሂደው ያረጋገጡት  የጅዳ ቆንስላ ጽ/ቤት ሃላፊዎች የሰቆቃ ድምጽ ለምታሰማው  ወጣት ገነት አበበ ሞላ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ይጠበቅባቸዋል   ። ይህ በዚህ እንዳለ  በዚህ መልኩ ሳውዲ አረቢያ ውስጥ በ 10 ሺህ የሚቆጠሩ እንደ ጨው ተበትነው ያሉበት ሁኔታ በውል የማይታወቅ  ግፍ እና በደል እያሰትናገዱ የሚገኙ እህቶች መኖራቸው በተደጋጋሚ ተገልጾል።

Ethiopian Hagere Jed Bewadi

The post በሳውዲ የታገተችው ኢትዮጵያዊት የሰቆቃ ደምጽ ! appeared first on Zehabesha Amharic.


በአዲስ አበባ አንበሳ አውቶቡሱ መንገድ ስቶ የቤት መኪናውን ገጨ

$
0
0

anbesa bus
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በየቀኑ እየደረሱ ያሉ የመኪና አደጋዎች ቁጥር ከ እለት ወደ እለት እየጨመረ መሄዱ ነዋሪዎችን በከፍተኛ ስጋት ውስጥ እንደከተተ የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ይናገራሉ:: በዚህ በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ላይ እንኳ በጊዜው ስለመኪና አደጋዎችና ስለሚወድመው የሰው ሕይወትና ንብረት በተደጋጋሚ ጽፈናል:: አሁን ደግሞ ከአዲስ አበባ የደረሰን መረጃ እንደሚያመለክተው አራት ኪሎ የድል ሐውልት አደባባይ አካባቢ ከስድስት ኪሎ መስመር ወደ ለገሀር ይጓዝ የነበረ የአንበሳ ከተማ አውቶቡስ ባገጠመው የፍሬን ችግር ከአንድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ የሁለቱም ተሽከርካሪ ሹፌሮች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል::

በዚህ የመኪና አደጋ በተሳፋሪዎች ላይ የደረሰ ጉዳት ባይኖርም አደጋው በፎቶ ግራፍ ላይ እንደምትመለከትት በጣም አሰቃቂ ነበር:: ከስድስት ኪሎ ከሚገኘው ቤታቸው ሃገር አማን ብለው ወደ ሥራቸው በማሽከርከር ላይ የነበሩትና ጉዳት የደረሰባቸው አቶ ግርም ጎርፉ የተባሉ ግለሰብ የአንበሳ አውቶቡሱ ድንገት መስመሩን ስቶ በመምጣት እንደገጫቸው ገልጸዋል::

The post በአዲስ አበባ አንበሳ አውቶቡሱ መንገድ ስቶ የቤት መኪናውን ገጨ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ –“የፊታችን አርብ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል!”

$
0
0

muslim addis 3

‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› —– ረቡእ የካቲት 18/2007 – ድምፃችን ይሰማ

መንግስት ህገ መንግስታዊ መብቶቻችንን በመጣስ ላለፉት ሶስት ዓመታት ከፍተኛ በደል ሲፈጽምብን ቆይቷል፡፡ እኛም እንደህዝብ ድምጻችንን አዋሕደን እና በአንድነት ቆመን ሰላማዊ ትግል ስናካሂድ ቆይተናል፡፡ ትግላችን እስካሁን አንድም ከሰላማዊነት መርህ ዝንፍ ሳይል የቆጠለ ሲሆን መንግስት ትግሉን ለማስቆም የሚወስዳቸው ግልብ እና አገር አጥፊ እርምጃዎችም ከመርሃችን ሊያዛንፉን እንደማይችሉ በተደጋጋሚ በተግባር ለማረጋገጥ ችለናል፡፡

ሰሞኑን መንግስት በተለመደው ግፍ መር እርምጃው በርካታ ሙስሊም ወንድምና እህቶችን በማሰር ዘመቻ ላይ ተጠምዷል፡፡ አንዳችም ጥፋት ያልፈጸሙ ወጣቶችንም የ28 ቀን የፍርድ ቤት ቀጠሮ በመጠየቅ ወደማጎሪያ ካምፖቹ አስገብቷል፡፡ ይህ ‹‹ሙስሊሞችን በማሰር ከትግላቸው አስቆማለሁ!›› ከሚል መናኛ ቀቢጸ ተስፋ እና ባዶ ምኞት የመነጨ ለመሆኑ እማኝ መጥራት አያሻም – ካሁን ቀደምም መንግስት ሲፈጽመው የቆየው፣ ግና ሊያሳካቸው ያልቻለው ህልሙ ነውና!

አዎን! ደጋግመን ስናሳይ እንደቆየነው ሁሉ ህዝብን ማንገላታት አንጂ ማሸነፍ ፈጽሞ የሚቻል አይደለም! ህዝብ ምንጊዜም አሸናፊ ነው! በአላህ ፈቃድ ያሸንፋልም! ይህን ህገወጥ እና ሊሳካ የማይችል እኩይ የመንግስት ምኞት በተለያዩ ስልቶች መታገል የነፍስ ወከፍ ሐላፊነታችን የሚሆነውም ለዚሁ እንጂ ለሌላ አይደለም፡፡ በመሆኑም ከነገ ወዲያ አርብ የካቲት 20/2007 መላው አገሪቱን ያሳተፈ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል፡፡ የተቃውሞውን መርሃ ግብር አስመልክቶ በነገው እለት የምናሳውቅ በመሆኑ እስከዚያው መረጃውን ላልደረሳቸው ሁሉ በማዳረስ ተዘጋጅተን እንጠብቅ፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ አይደለምና!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ! አላሁ አክበር!

The post ከድምፃችን ይሰማ የተላለፈ ጥሪ – “የፊታችን አርብ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ ይኖረናል!” appeared first on Zehabesha Amharic.

ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው አነጋጋሪ ዘፈን የ1 ደቂቃ ማስታወቂያ ተለቀቀ (ይዘነዋል)

$
0
0

ባለፈው ሳምንት ዘ-ሐበሻ የላፎንቴኑ ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር በመሆን ሃገራዊ ስሜት ያለው ዘፈን መስራታቸውንና በቅርብ ቀን እንደሚለቀቅ መዘገቧ ይታወሳል:: በዚህም መሠረት ዛሬ የዚህ አነጋጋሪ ዘፈን የአንድ ደቂቃ ተቆርጦ በሶሻል ሚድያዎች ተለቋል::

ሙሉው ዘፈንን በሚቀጥለው ሳምንት በዘ-ሐበሻ ድረገጽ ይጠብቁ:-

Birhanu Tezera and Jacky Gosee

The post ብርሃኑ ተዘራ ከጃኪ ጎሲ ጋር የሠራው አነጋጋሪ ዘፈን የ1 ደቂቃ ማስታወቂያ ተለቀቀ (ይዘነዋል) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ

$
0
0

ኢሳት ዜና :-የህወሀትን 40ኛ ዓመት አክብረው ሲመለሱ እግረ መንገዳቸውን በ አማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎችን እየጎበኙ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ሀይለማርያም ደሳለኝ ፤የካቲተ 16 ቀን በወልቃይት ሊያደርጉት የነበረውን ጉብኝት የህዝቡን ተቃውሞ በመፍራት መሰረዛቸው ነዋሪውን ክፉኛ አስቆጥቷል።
H Desalegn
የወልቃይት ነዋሪዎች ለኢሳት እንደገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የካቲት 16 ቀን ወልቃይትን እንዲጎበኙ በአካባቢው ሹመኞች መነገሩን ተከትሎ በየገጠር የሚኖረው ህዝብ ሳይቀር በመሰባሰብ እና ምሳ በማሰናዳት ሲጠባበቃቸው ቢውልም የውሀ ሽታ ሆነው ቀርተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአካል አግኝቶ የአስተዳደራዊ በደል ጥያቄውን ለማቅረብ ከ8 ሺህ በላይ ህዝብ ተሰባስቦ እንደነበር የገለጹት የነዋሪዎቹ አስተባባሪዎች፤ ህዝቡ ተቃውሞውን ለመግለጽና ጥያቄ ለማቅረብ እንደተዘጋጀ የተረዱት የአካባቢው ሹመኞች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ወልቃይት እንዳይገቡ አድርገው ቅጠታ ወደ ደጀና እንደወሰዷቸው ተናግረዋል።

ይህ በመሆኑም ተሰባስቦ ሲጠባበቅ የነበረው ህዝብ በቁጣና በብስጭት ወደ ቤቱ መመለሱን የገለጹት አስተባባሪዎቹ፤ ንዴታቸውን መቆጣጠር የተሳናቸው የአካባቢው ወጣቶችም በአደባባይ የህወሀትን ባንዲራ በማቃጠል የዚያኑ እለት ለትግል ወደ በረሀ መውጣታቸውን ተናግረዋል።
ቀርቦ በማናገር እንጂ ከህዝብ በመደበቅ ወይም በመሸሽ ከችግር መሸሽ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሊረዱት ይገባል ያሉት ነዋሪዎቹ፤ አንድ የሀገር መሪ- ከህዝብ ጋር የዚህ ዓይነት ድብብቆሽ ጨዋታ ውስጥ መግባቱ እጅግ እንዳሳፈራቸውም ገልጸዋል።

<<አማራዎች ሆነን ሳለን ያለፍላጎታችን ወደ ትግራይ ክልል እንድንጠቃለል ተገደናል፣ የማንነት ጥያቄያቸን ምላሽ እንዲያገኝ ጥያቄ በማቅረባችን ለበርካታ ዓመታት ተነግረው የማያለቁ በደሎችና ግፎች እየተፈጸሙብን ነው>> የሚሉት ወልቃይቶች፤ << በቅርቡ በተደራጀ ሁኔታ በደብዳቤ ላቀረብነው አቤቱታም እስካሁን ከመንግስት ምላሽ አላገኘንም፤ መንግስት መልስ የማይሰጠን ከሆነ፤ ራሳችን መልስ ለመስጠት እንገደዳለን>፡>በማለት አስጠንቅቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የወልቃይት ህዝብ ላለማየት ተራምደውት ያለፉት አቶ ሀይለማርያም ትናንት ምሽት ከ አቶ አርከበ እቁባይና ከአማራ ክልል ርእሰ-መስተዳድር ከ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በመሆን ኮምቦልቻ ከተማ መግባታቸው ታውቋል።

ዛሬ ጧት የኮምቦልቻ ከተማ ተማሪዎች – ለአቶ ሀይለማርያም አቀባበል ለማድረግ በሚል ከትምህርት ገበታቸው በግዳጅ መወሰዳቸውን የገለጹት ምንጮችን የከተማውም ነዋሪ በተመሳሳይ መንገድ ለ አቀባበል ተብሎ በግዳጅ እንዲወጣ መደረጉን ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማለዳ ላይ የዛሬ ዓመት የተመረቀውን የ ኮምቦልቻ አውሮፕላን ማረፊያ እንደ አዲስ እንዲመርቁ ከተደረገ በሁዋላ ለአዋሽ-ኮምቦልቻ የባቡር ሀዲድ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን የገለጹት ምንጮቹ፤ የመሰረት ድንጋይ የማኖር ፕሮግራሙ የተካሄደውም የሽህ መሀመድ ሁሴን አል አሙዲ የቆርቆሮ ፋብሪካ አጠገብ በተጣለ ዳስ ውስጥ እንደነበር አመልክተዋል።

ወደ ዳሱ እንዲገቡ የታደሙት << አዋሽ -ኮምቦልቻ ሀራ ገበያ>> የሚል መግቢያ ባጅ የተሰጣቸው የኢህአዴግ ካድሬዎች ብቻ መሆናቸውን የጠቀሱት ምንጮቹ፤ ይሁንና ከነበረው እጅግ ጥብቅ ፍተሻ አኳያ፤ ተጋባዦቹ የኢህአዴግ አባላት ሳይሆን አደገኛ ጠላት ነበር የሚመስሉት ብለዋል።

አቶ ሀይለማርያም የመሰረት ድንጋይ ማስቀመጣቸውን ተከትሎ “ኢህአዴግን ምረጡ” የሚል ቅስቀሳ መደረጉን የጠቀሱት ምንጮች፤ የመሰረት ድንጋይ ሊጥሉ መጡ የተባለውም ሆነ ከአመት በፊት የተመረቀን አውሮፕላን ማረፊያ እንደ አዲስ እንዲመርቁ የተደረገውም ለምርጫው ህዝቡን ለማታለል እንደሆነ በደንብ ገብቶናል”ብለዋል።

የምንልሰውና የምንቀምሰው ባጣንበት ወቅት በባቡር ፕሮፓጋንዳ ሊያታልሉን አይችሉም ያሉት ነዋሪዎቹ፤ በትራንስፖርትም ረገድ ቀደም ሲል 1 ብር የነበረው የታክሲ ታሪፍ እስከ 3 ብር፣ 2 ብር የነበረው እስከ 6 ብር ደርሶ ህዝቡ እየተማረረ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

The post ሀይለማርያም ደሳለኝ የወልቃይትን ህዝብ ለማነጋገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ

$
0
0

ANAASO Blueእንደሚታወቀው የኢህአዴግ አገዛዝ ከጊዜ ወደ ጊዜ ጸረ ዲሞክራሲ አካሄዱ እየባሰበት የመጣና መሠረታዊ መብቶችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ ማፈኑን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፡፡ በቅርቡ በአንድነትና በመኢአድ ፓርቲ ላይ አገዛዙ በሚያዝዛቸው የተቋማት ኃላፊዎች ቀጭን ትዕዛዝ የፓርቲዎቹ ሕልውና ለጥቂት ግለሰቦች ተላልፎ ተሰጥቷል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህገ-ወጥ ድርጊት መቼዉም ቢሆን ተቀባይነት አይኖረውም! ለአገራችን የሠላማዊ የስልጣን ሽግግር ከባድ መሠናክል ሊሆን እንደሚችል ሁሉም ይገነዘባል ብለን እናምናለን፡፡ የኢህአዴግ የምርጫ ቦርድ እንዲህ ዓይነቱን ክፉ ስራ ሲወስን የአገራችንን የረጅም ሠላም አይተው ሣይሆን በአገዛዙ ቁንጮ ሰዎች በመታዘዝ በተቋም ስም የሚሠሩት የማደናገር የድንቁርና ተግባራቸዉ አንድ አካል ነው ብለን እናምናለን፡፡ ማህበራችን ይህን ድርጊት እጅጉን ያወግዛል። በመሆኑም ድርጊቱን በጋራ እንቃወማለን።

በምርጫ ቦርድ ስም የተወሰነው ህገ-ወጥ ውሣኔ ምክንያት መላ የአንድነትና የመኢአድ አባላት የፖለቲካ እንቅስቃሴአቸው ተገድቧል፡፡ ይሁን እንጂ ለአገራቸው ካላቸው ፅኑ ፍቅር አኳያ ትግሉን ለማስቀጠል ከሠማያዊ ፓርቲ ጋር አብሮ ለመሥራት የአባልነት ፎርም በመሙላት ትግሉን ቀጥለዋል፡፡ ይህ ዓይነቱ የአባላት ቆራጥ ውሣኔ ሊበረታታና ሞራል ሊሰጠው የሚገባ ነው ብለን እናምናለን! እኛም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የሁለቱ የድጋፍ ማህበራት ሙሉ በሙሉ ድጋፋችንን እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡

ስለሆነም በሰሜን አሜሪካ የምንገኝ የአንድነትና የሠማያዊ የድጋፍ ማህበራት በጋራ በኮሜቴ ደረጃ ተዋቅረን በዋና ዋና ጉዳዬች ላይ ማለትም በፋይናንስ፤ በእስረኞች ጉዳይ እና በዲኘሎማሲው ዙሪያ ሙሉ በሙሉ በትብብር አብረን እየሠራን የሰማያዊ ፓርቲንና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሣኔ አሣልፈናል፡፡ በቀጣይም በጋራ የኮሚቴ ውይይቶችን እያደረግን ለሰማያዊ ፓርቲ የሚያስፈልጉ የሞራልና የማቴሪያል ርዳታ እንደምንሰጥ እናረጋግጣለን፡፡
የሰማያዊና የአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበራት
የካቲት 19 2007 ዓ/ም

The post ከአንድነት ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበርና ከሰማያዊ ሰሜን አሜሪካ ድጋፍ ማህበር የተሰጠ የጋራ መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ

$
0
0
10920943_352316331618819_5078649879608517565_n‹‹እስር ከትግላችን አያስቆመንም!›› – ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ስልካችንን እናጠፋለን!
መንግስት ሙስሊሞችን ከያሉበት በማሰር ህገ ወጥ ዘመቻ ላይ መሰማራቱን እና በህዝበ ሙስሊሙ ላይ ግፍ መፈጸሙን በመቃወም ነገ ጁሙዓ ታላቅ አገር አቀፍ ተቃውሞ እንደሚኖረን እና በዛሬው እለትም የተቃውሞው መርሃ ግብር ይፋ እንደሚሆን መገለጹ ይታወሳል፡፡በዚሁ መሰረት እነሆ የነገው አገር አቀፍ ተቃውሟችን በመጠነኛ የቦይኮት ዘመቻ (የራስን መብት በራስ ላይ የመንፈግ ተቃውሞ) የሚጀመር ይሆናል፡፡ኢትዮ ቴሌኮም ለመንግስት ከፍተኛ ትርፍ ከሚያስገኙ ካምፓኒዎች አንዱ ሲሆን
በቀን ከተጠቃሚዎች በሚሊዮን የሚቆጠር ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ሙስሊሙ
ማህበረሰብ ደግሞ የአገሪቱ ግማሽ እንደመሆኑ መጠን በአንድ ቀን ለቴሌ
የሚያስገኘው ገቢ እንዲሁ በሚሊዮን የሚቆጠር ነው፡፡ በመሆኑም የማይናቅ
ቁጥር ካለው ማህበረሰብ የሚያጣው የአንድ ቀን ገቢ ለኢትዮ ቴሌኮም
በሚሊዮን የሚቆጠር ብር አክሳሪ መሆኑ የሚያጠራጥር አይደለም፡፡ የነገው
ቦይኮት በኢቲዮ ቴሌኮም ካምፓኒ ላይ የሚያተኩረውም ለዚህ ነው፡፡
ነገ ከጠዋቱ 1 ሰዓት እስከምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ ሁላችንም ስልካችንን
በመዝጋት ተቃውሟችንን እናሰማለን፡፡ አስቸኳይ ጉዳይ ካላጋጠመን በስተቀርም
ስልካችንን አንከፍትም፤ አንጠቀምምም፡፡

አስቸኳይ ጉዳይ ሲያጋጥመን ለአፍታ ስልካችንን በመክፈት ቶሎ ጉዳያችንን ፈጽመን ወዲያው እንዘጋለን፡፡
ይህንን አገር አቀፍ እና መላ አገሪቱን ያካለለ ዘመቻ ላልሰሙት ሁሉ በማሰማት ለስኬቱ የቻልነውን ሁሉ መጣር ታላቅ ተግባር ሲሆን ለዲናችን ስንል ለምንከፍለው
መስዋእትነትም ከጌታችን አላህ ዘንድ ምንዳችንን እንተሳሰባለን፡፡ አላህ ፈተናውን
እንዲያነሳልንም አጥብቀን ዱዓ እናደርጋለን፤ ድልም ከአላህ እንጂ ከሌላ
አይደለምና!!!

አዎን! አንድነት ያለው ህዝብ ያሸንፋል!
ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!

ድምጻችን ይሰማ!

The post ለአንድ ቀን የሚቆይ የቦይኮት ዘመቻ በድምፃችን ይሰማ ጥሪ ቀረበ appeared first on Zehabesha Amharic.

የአገርዎ፣ የግልዎ እና የሕዝብዎ ስቃይ እና ሕመም ያሳሰብዎታል? -የአዲስ ቃል ኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት

$
0
0

የአዲስ ቃል ኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት

የአገርዎ፣ የግልዎ እና የሕዝብዎ ስቃይ እና ሕመም ያሳሰብዎታል?

arkofthecovenantዛሬ በዓለማችን ዙሪያ የሰው ልጅ መከራም ዕውቀትም እየበዛ፣ ሁኔታዎች ሁሉ ለሰው ልጅ ስጋት ሆነው ባለበት ወቅት ፣ ኢትዮጵያ ተብላ በምትታወቅ ምድር እና ሕዝብም ላይ በአገር ውስጥም በውጭም ያለው የመከራ ስጋት፣ ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ቁርኝት ያለው ኢትጵያዊውን ወይም ትውልደ ኢትዮጵያዊውን ብቻ ሳይሆን፣ ከአገሪቱዋ ጋር በአንድም በሌላም የጥቅም ግኑኝነት ያላችውን ባዕዳን አገራትን፣ አለያም የመሳሪያ ሸቀጦቻቸውን ለማራገፍ የእርስ በእርስ ጦርነት ቀጥሎ ሊነሳባት የሚችል አገር የትኛዋ ናት? ብለው የገበያ ጥናት የሚያደርጉትን መሳሪያ አምራች ድርጅቶችን ሁሉ ሳያነጋገር የሚቅር አይመስልም ፡፡

የምድሪቱዋ እና የሕዝቡ ዕጣ ፈንታም  በምሑራን፣ በታዋቂ  ሰዎች፣ በጀግኖች እና በስመጥሮች አለያም በምዕራቡ፣ በምስራቁ ወይም በዓረቡ ዓለም እርዳታ ለጋሾች ወይም ብድር አበዳሪ አገሮች፣ በተባበሩት መንግሥታት፣ በአውሮፓ ሕብረት፣ በአፍሪካ አንድነት ድርጅት፣ በፖለቲካ ድርጅቶች ወይም ንቅናቄዎች፣ ብቻ ሊፈታ ይገባዋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ሲሆን፣ ባለፉት ዘመናትም የነዚህን ድርጅቶችም ሆን ግለሰቦችን በር በማንኩዋኩዋት ምን ያህል አመርቂ ውጤት እንደተገኘ፣ የተጨበጠ መረጃ ለጊዜው ባይኖረንም፣ ኢትዮጵያዊ ነኝ ብሎ የሚያምነውም፣ ኢትዮጵያዊ አይደለሁም ብሎ የሚለውንም ከዛች ምድር የወጣ ሰው ሁሉ፣ ለሐገሪቱዋና ለሕዝቡ ቀጣይ መፍትሔ ለማምጣት እና ሁሉም ተዋዶ እና ተከባበሮ የሚኖርባትን አዲሲቱን ኢትዮጵያ ለመገንባት ያገባኛል የሚል ሰሜት ሊኖረው ግድ የሚልበት ወቅት ላይ የተደረሰ ይመስላል፡፡

ቅጥሩዋ እየፈራረሰ፣ ሕዝቡዋም ግራ በመጋባት በተበታተነበት ሁኔታ፣ ቅጥሩዋን ከሚሰሩ ጋር ሁሉ እጅ ለእጅ በመያያዝ፣ የሕዝቡ መከራ መከራዬ፣ የሕዝቡ ደስታ ደስታዬ ስለሆነ ላበረክት የምችለው ጉዳይ አለኝ፣ ስለዚህም ያገባኛል የሚለው ግን ምን ያህሉ እንደሆነ ቤት ይቁረጠው?

በሌላ በኩልም በአገሪቱ ላይ ከልማት እና ከዕድገት በስተቀር፣ ሰው አልተበደለም፣ ሕዝብ፣ አልታሰረም፣ አልተሰደደም፣ አልሞተም፣ ነጻነቱንም አልተነፈገም፣ ሕዝቡዋ፣ ሳይራብ፣ ሳይታረዝ፣ ሳይሰደድ፣ ሳይታምም በነፃነት ደልቶት እየኖረ ስለሆነ፣ ችግርም ቢኖር በአይን የሚታየው ልማት እና ያገሪቱዋ መሻሻል ስለሚበልጥ፣ የሚሰቃየው ሕዝብ ላገሪቱዋ ማደግ የሚከፈለው ዋጋ ነው ብሎ በማሰብ፣ የሰውን ልጅ ክቡር ሕይወት ከቁሳዊ ነገር ባነሰ መልኩ በመመልከት እና ተቃዋሚዎች የሌለውን ችግር እየጋነኑ ሕዝቡን ያሸብሩታል ብሎ በማመን፣ በሥልጣን ላይ ካለው  መንግሥት ጋር በመተባበር ለመንግሥት ዓላማ ለመታገልና በሥልጣን ላይ መቆየትም እንዳለበት የሚያምኑም የአገሪቱ ልጆችም ሆኑ ፣ ባዕዳንም እንደማይታጡ ልብ ማለት ይገባል፡፡

በአገሪቱና በሕዝቡ ላይ በደል እና መከራ እንዳለ ቢያወቁም፣ ወደ አገር ቤት እንደፈለጉ መመላለስ የሚፈለጉ፣ ያላቸውን ሐብት እና ንብረት ማጣት የማይፈለጉ፣ ዘመዶችን መጠየቅ፣ ትዳር መመስረት…ወዘተ የሚፈለጉ፣ ከመንግሥት ጋር ላለመቀያየም ካላቸው ፍርሐት የተነሳ ባገሪቱም ሆነ በሕዝቡ ላይ የሚደርሰው መከራ አያገባኝም በማለት መሰማትም ማየትም አልፈልግም ማለትን የመረጡ፣ ካለባቸው የግል ችግርም የተነሳም የአገርን ችግር ለመስማት አቅም ያጡ፣ በዘር እና በጎሳ ማንነት ምክንያት ኢትዮጵያዊነት የሚለው ሰሜት ከውሰጣቸው እንዲጠፋ በመደረጉ ምክንያትም ከተደራጁበት ብሔረሰብ፣ ቤተ እምነት ወይም የፖለቲካ ድርጀት አመለካከት በስተቀር የሌላው ጉዳይ አያገባኝም ብለው እንዲገደቡ የተደረጉት ባንድ በኩል፣ በሌላው በኩል ደግሞ የማንኛውም ዘር፣ ጎሳ፣ ፖለቲካ፣ ሐይማኖት ወይም  እምነት ጉዳይ አጥር ሳይሆንባቸው፣ የሰው ልጅ መከራና ስቃይ  እንደሰው ብቻ ተሰምቶአቸው፣ የትውልዱ ሕመም ያመኛል እና ፈውስ ያስፈልገናል፣ እኔንም ያገባኛል ከሚለው ጋር ፣ የየራሱን ጎራ ለይቶ ተፋጦ ያለበት የቀዝቃዛ ጦርነት ካምፕ በስውርም በገሐድም በአገር ውስጥም በውጭም ከትሞ በደፈጣ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል፡፡

በኢትዮጵያ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት፣ በኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተመረጠ፣ ከጫካ መጥቶ ሥልጣንን በጉልበት የያዘ፣ በጉልበት እና በግድ ሕዝቡን እያስጨነቀ፣ እየገደለ፣ እያሰረ፣ እያሰደደ፣ በሕዝቡ ላይ፣ አካላዊ፣ ማሕበራዊ፣ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ  እና ሥነልቡና ላይ ከፍተኛ በደል እና ስቃይ ያደረሰ፣ ሀገርን የበታተነ፣ ዳር ድንበርን የቆረሰ እና ያስቆረሰ፣ ዘረኛው የወያኔ መንግሥት፣ ስለሆነ፣ በምንም መልኩ ይሁን ከሥልጣን መወገድ አለበት፣ ሰለዚህ ለዚህ ዓላማ ከቆሙ በሰላማዊም ሆነ በትጥቅ ትግል ከሚያምኑ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች ጎን በመቆም የምችለውን ሁሉ ላበረክት ይገባኛል ብለው የሚያመኑት እና ወደ አደባባይም እየወጡ ያሉት ጥቂት የሚባሉ አይደሉም፡፡

በሐይማኖታዊ አመለካከት ምክንያት ለመንግሥት ባለሥልጣናትም ሆነ ለሕዝቡ መጸለይ እንጂ፣ ማመጽም መቃወመም አያገባኝም፣ ስለዚህ ራሱ ፈጣሪ፣ ወይም በሌሎች በኩል መላ እስከሚያመጣ ድረስ አኔ እርፌ  መቀመጥ አለብኝ ከሚሉት ሌላ፣ ሐይማኖታዊ አመለካከቴ ለወገን መከራ፣ ረሐብ፣ መሰደድ፣ መታሰር፣ መታመም፣ መታረዝ ግድ እንዲለኝ ያዘኛልና፣ ለዚህ በጎ ተግባር ከተሰማሩት ሁሉ ጎን በመቆም ማደረግ የሚገባኝን ሁሉ ማበርከት ይገባኛል ብለው በሚያምኑት መሐል፣ አንደኛው ራሱን ጻድቅ ሌላውን ሐጢያተኛ አድርጎ እንዲመለከት እና፣ ቤተ እምነቶችም በመንግሥት ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች ስውር እና ገልጽ ሽኩቻ፣ በአገር ውስጥም በውጭም ምዕመናኑን ባለተቁዋረጠ ግራ መጋባት ውሰጥ እንዲዋከቡና፣  ማን ከማን ጋር መነጋገር ወይም አለመነጋገር፣ ማን ከማን ጋር ማህበራዊ ግንኙነት ሊኖረው እነደሚገባ፣ ወይም እንደማየገባ ፈርተው እና ተገድበው፣ የተቃዋሚ ወይም የደጋፊ መሪዎችን፣ ወይም የቤተ እምነቱን መሪዎች ባረኮት ካላገኙ እንዳይንቀሳቅሱ፣ ያገር ቤት ፖለቲካው መዘዝ በውጭም ያለውን ሕዝብ  የመኖር ነጻነቱን ገፍፎ የሕሊና እስረኛ እያደረገው ይገኛል፡፡

ከኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያውያን ጋር የተያያዘ ጉዳይ ላይ መካፈል፣ መስማት፣ መናገር ወይም በስብሰባ ላይ መገኘት ፖለቲከኛ ያስብለኝ ይሆናል በሚል ፍራቻ ፣ የሐይማኖት መሪዎች፣ ወይም የፖለቲካ ሰዎች ባሳደሩባቸው ተጽዕኖ፣ በፍርሐት ታስረው እንዲቀመጡ በወሰኑላችው አጥር ውስጥ ተደበቀው በመኖርየራሳቸውን ነጻነት በገዛ ፈቃዳቸው አስነጥቀው መኖር የሚፈለጉ እና  ፖለቲካ እና ፖለቲከኛነትን እንደ ወንጀል የሚመለከቱትም ደግሞ በሐገር ውስጠም በውጭም በፍርሕት እስር ቤት ውስጥ ወዶ ገባዎች ሆነዋል፡፡

ሕዝቡ በአንዱ ወይ በሌላው ምክንያት፣ ባገሩም ሆነ በተሰደደበትም ምድር በነጻነት እንዳይኖር፣ እንዳያስብ፣ እንዳይናገር፣ ሐሳቡን በነፃነት እንዳይገለጽ፣ በየስፍራው ራሳቸውን መለስተኛ ነገሥታት አድርገው በሾሙ ሰዎች ወይም ቡድኖች ባሳደሩበት ተጽዕኖ፣ በግልጽ እና በስውር የሥነ ልቦና ጫና ውስጥ እንዲቀመጥ መደረጉ ፈውስ የሚያስፈልገው ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህ ወዶም ሆነ ተገዶ ለዚህ ባርነት የተጋለጠ ሁሉ ፈውስ ያስፈልገዋል፡፡ ሁላችን በማወቅም ይሁን ባለማወቅ የዚህ ጥቃት ሰለባ ሆነናል፡፡ ራሳችንን ነጻ ሳናወጣ ሌላውን ነጻ ማውጣት እንደማንችል ማመን አለብን፡፡ በኢትዮጵያ ምድር ያለውን ችግር ለማቃለል፣ አገርን እየመሩ ያሉትም ሆነ ወደፊትም ለመምራት የሚፈለጉት ሁሉ ራሳችውን ከዚህ ባርነት ነጻ ማውጣት እና፣ በሌላውም ላይ የጫኑበትን ቀንበር ማውረድ ይኖርባቸዋል፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት መሪዎች ምንም አይነት ስም ቢሰጣችው በአለም አቀፉ መድረክ ለጊዜውም ቢሆን አገሪቱዋን ወክለው የተቀመጡ ስለሆኑ፣ በአገር ውስጥም ሆን በውጭ በስደት ለሚኖረው ሕዝብ መከራ እና ስቃይ ግንባር ቀደም ተጠያቂ የሚያደረጋቸው መሆኑን አውቀው ማሰተካከል እንዲያደርጉ ምክር እንደተለገሳቸው፣ በአገር ውስም በውጪም ያሉ አማካሪዎቻቸው በአደባባይ እያጋለጡት ያለ ሚሰጥር ነው፡፡

እነእርሱም የሚከተላቸውን የበቀል ጅራፍ ከመፍራት ይመስላል፣ «ሥልጣን ወይም ሞት!» ብለው እንዲገፉበት እና ሰላማዊ የፖለቲካ ድርጀቶች እንኩዋን በሰላማዊ መንገድ የሚያደርጉትን አማራጭ እንቅስቃሴ በማፈን የሕዝብን ቁጣ እያባባሱና፣ የነገሮች አዝማሚያ ወደ ከፋ ሁኔታ እንዲቀጥል ጥርጊያ መንገዱን እያፋጠኑት ስለሚመስል፣ ላደረጉት መልካምም ሆነ ክፉ ነገር፣ ተጠያቂነታችውን በማመን፣ እነእርሱ ራሳቸው በየጊዜው ያጠፋውንም ሆነ ያላጠፋውን ሕዝብ ወይም ግለሰብ «ይቅርታ ጠይቁ! «እያሉ እንደሚያዙት ሁሉ ፣ እነርሱም ያጠፉ እና ሊያጠፉም የሚችሉ ሰዎች መሆናችውን በመገንዘብ፣ ሕዝብን ይቅርታ በመጠየቅ፣ በጨዋነት፣ ያገር መሪዎች ያባትነት ባሕሪን ተላበሰው፣ ወገንን በማስታረቅ ማገልገል ሲገባችው፣ የማሰተዳር አቅማቸውም ተሙዋጦ ካለቀባቸው፣ እና በሠላም ከሥልጣን መውረድ እንኩዋን ቢኖርባቸው፣ ትውልዱን መታደግ ተቀዳሚ ተግባር በማደርግ ለሠላም እጃቸውን ቢዘረጉ እና፣ ምድሪቱዋ ላለፉት አርባ ዐመታት በርካታ  ትውልድን ስትገበር የቆየችው ሳያንስ፣ ዛሬም የአንድ አገር ሕዝብ የሆነውና ወንድማማች ሕዝብ፣ እንደገና ሊጠፋፋ ሲያደባ እያዩ እና እየሰሙ በቸልታ ማለፍ የሕዝቡ ደም በእጃቸው መሆኑን ሊገነዘቡት ይገባል፡፡

ስለዚህ፣

ይህ ከላይ የጠቀስናቸው ልዩነቶች ሁሉ እንዳሉ ሆኖ፣ ኢትዮጵያ አሁን ያለችበት ደረጃ በቅርቡ መላ የማይደረግለት ካልሆነ፣ እጅግ አሳሳቢና፣ የአደጋ ደመናም ያንዣበበባት በሚመስል፣ ወደ እርስ በእርስ ጦርነት ውስጥ ሊያስገቡ የሚችሉ ሁኔታዎች እየተመቻቹ እንደሆነ በርካታ ስጋቶች የሚጠቁሙ ሲሆን፣   ከችግሩም በመሸሽ ወገን አገር እየለቀቀ እና እየተሰደደ፣ በበረሐ እና በባሕር የሚያልቀው ሕዝብ እየተበራከተ፣ በአገር እና በውጭ እስር ቤት እየማቀቀ፣ ያለውን ሕዝብ ለመታደግ፣ ምንም አይነት የፖለቲካ፣ የሐይማኖት፣ የዘር አመለካካት ልዩነት ሳያግደን ፣ እያንዳንዱ በነፃነት እንዲያስብ፣ በነጻነት እንዲናገር፣ በነጻነት የፈለገውን ሊሰማ፣ በነጻነት፣ ሊንቀሳቀስ፣  ፈጣሪ አስቀድሞ የሰጥዎትን፣ በመቀጠልም በስደት ባሉበትም አገር የዲሞክራሲ መብት በሰጠዎ መብት ተጠቅመው፣ ሐሳብን በነፃነት በመለዋወጥ፣ መኖር መብትዎ  በመሆኑ፣ ያገባናል የሚሉ የፖለቲካ፣ የሲቪክ ድርጅቶች፣ የሐይማኖት ተቁዋማትም ሆኑ ግለስቦች የሚያደረጉት እንቅስቃሴ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በሥልጣን ላይ ያለው መንግሥት ቢቅጥልም አለያም በውድም ሆነ በግድ ቢውርድም፣

  1. የምድሪቱን እና የሕዝቡን እጣ ፈንታ ጉዳይ ላይ በመመካከር፣ እንደ ሰው ልጅ በመከባበር እና በመደማመጥ፣ ወገን ከደረሰበት መከራና ስቃይ ለመፈውስ፣ ተቀራረቦ መነጋገር እና እርቅ ያስፈልጋል ብለን ስለምናምን፣ እርቁ ደግሞ ከራስ ጋር ከመታረቅ ጀምሮ፣ ከወገን ጋር ሕብረት እስከመፍጠር ድረስ የሚዘልቅ ስለሆነ፣ ሰው ሁሉ አንዱ ሌላውን በመፍራት፣ አንዱ ሌላውን ወገኑን በመሰለል፣ ሕጋዊ ባለሆነ የፍርሕት እስር ቤት ውስጥ ያለ ወገን ሁሉ ከዚህ የባርነት ሕመም መፈወስ አለበት ብለን ስለምናምን፣

 

  1. እርቅ ሲባል የተበዳይ ቁስል እና ሕመምን ከመፈወስ ይጀምራል እና፣ እስካሁን በሕዝቡ ላይ ለደረሰው መከራና በደል፣ ተጠያቂ ሊሆኑ የሚገባችው እና ወንጀል በመፈጸም በትውልዱ ላይ ለደረሰው መከራ ተጠያቂነት ያለባችው ሁሉ፣ ሕግ በሚፈቅድው መሰረት ወደ ፍርድ አደባባይ ሊያቀረቡዋችው በሚችሉ አካላት በኩል ሊወሰድ የሚገባውን እርምጃ፣ ለሕግ ባለሙያዎች፣ የፖለቲካውን እና የኢኮኖሚውን፣ጉዳይ እንዲሁ ለሚመለከታችው ባለሙያዎች በመተው፣ የተቀረው ሕዝብ ግን ወደ ሠላም፣ ወደ መፈቃቀር እና ወደ እርቅ የሚደረስበትን መንገድ ለማዘጋጀት ጥርጊያ መንገድ ማበጀት ያስፈለጋል ብለን ስለምናምን፣

በትውልድ በሐይማኖቶችና በዘሮች መካከል ያለው የመራራቅ እና የጥላቻ ሕመም ሊፈወስ ይገባዋል በሚል መርሆ፣ ማንኛውንም ዘር፣ የሐይማኖት፣ ወይም የፖለቲካ ድርጅትን የማይወክለው እና ዓለም አቀፋዊ አገልግሎት ያለው The Ark of the New Covenant Healing ministry  (የአዲስ ቃልኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት) www.adonairapha.org ከላይ በተጠቀሱት ሁለት ነገሮች ያምናል፡፡ እነዚህንም በተግባር ለመፈጸም የሚቻለውን ሁሉ እያደረገ ሲሆን በሌላ በኩልም ደግሞ «ከጎሳ ይልቅ ለሰብዓዊነት ቅድሚያ እንስጥ» በሚል መርህ አቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመሩት የአዲሲቱ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ Solidarity Movement for a New Ethiopia www.solidaritymovement.org ለእርቅ፣ ለሰላምና ለፍትህ ካለው ዓላማ ጋር በመተባበር፣ «ለመተማመን እንነጋገር»  በሚል መሪ ሐሳብ ኢትዮጵያውያንን የሚያገናኝ መድረክ ከከፈተ ጥቂት ወራቶች ተቆጥረዋል፡፡እስካሁን በዋሽንግተን ዲሲ እና በሜኒሶታ ሁለት መድረኮችን ያዘጋጀ ሲሆን፣ ሶስተኛውን መድረክ ከፈውስ አገልግሎታችን ጋር በመተባበር በቅርቡ በኖርዌይ፣ ለማድረግ አስበናል ይህን መሳይ ጉባዔ ሲደረግ በምድረ አውሮፓ የመጀመሪያው ሲሆን፣ የውይይት መድረኩ በኖርዌይ ተጀምሮ በሌሎች ሀገራትም የሚቀጥል ሲሆን፣ ውይይታችን ሁሉ ከጥላቻ፣ ከበቀል፣ ከመናናቅ እና ከምሬት ነጻ የሆኑ ጉባዔዎችን በማድረግ ለወገኖቻችን ፈውስን ለማመጣት ቅድሚያ ሰጥተን እየሰራንበት ያለው ጉዳይ ነው፡፡

ስለዚህ በቅርቡ የተለያ አመለካከት ያላቸው ሰዎችን በመጋበዝ፣ በመፈራረስ ላይ ያለች ኢትዮጵያን ለማዳን እና በአገር ውስጥም ሆነ በውጭም ያለውን ሕዝብ ከደረሰበት የአካል እና የሥነልቦና፣ ጉዳት እንዲያገግም የሚያደረግ  ፈውስ ለትውልዱ ለማምጣት፣ ሌሎች ድርጅቶች እና ግለሰቦችን ከመውቀስ  ይልቅ፣ እኛስ ምን ማበርከት እንችላለን? ብለን ትውልዱን የመታደግ ምክር ለመመካከር፣ በዚህ አገር እና ትውልድን  የማዳን ጉበዔ ላይ እንዲገኙ በማክበር እየጋበዝንዎ! የስበሰባውን ስፈራ እና ተጋባዥ እንግዶችን  ስም ዝርዝር በተከታታይ እናስታውቃለን፡፡ ስለ ጉባኤው ያለዎትን አስተያየት በሚከተሉት ኢሜይል አድራሻዎች  ሊልኩልን ይችላሉ፡፡

የዚህን ደበዳቤ መልዕከት ሊያገኙዋቸው ለሚችሉዋቸው የመንግሥት መሪዎች እና ደጋፊዎቻቸው፣ ለመንግሥት ተቃዋሚዎች እና ደጋፊዎቻቸው፣ ለአያገባኝም ባዮች ሁሉ እንዲያደርሱልን በታላቅ ትሕትና እንጠይቃልን?

ከማክበር ሠላምታ ጋር

ሰዋሰው ስለሺ ዮሐነሰን

የአዲሰ ቃልኪዳን ታቦት የፈውስ አገልገሎት መስራችና መሪ

The Ark of the New Covenant Healing Ministry

www.adonairapha.org

mail@adoniarapha.org

ወይም

Obang Metho,
Executive Director of the SMNE
Phone 202 725-1616
Email:Obang@solidaritymovement.org
Website: www.solidaritymovement.org

 

ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውምማቴ. 9፣12

ከላይ የተጠቀሰው ቃል የሰውን ልጅ ክቡርነት በመረዳት፣ ለሰው ልጅ ሲል ሕይወቱን ሊሰዋ ወደ ዓለም የመጣው ኢየሱስ ክርስቶስ፣ የሰዎች ችግር እና መከራ እየተሰማው ዘር፣ ጎሳ፣ ማሕበራዊ ማንነትን ሳይለይ፣ በአካልም፣ በአዕምሮም በሥነልቦናም ሕመም የደረሰባቸውን ሰዎች፣ ለመታደግ፣ ለማጽናናት እና ለመፈወስ በሚጉዋጉዋዝበት ጊዜ፣ የሌላውን ድካም እና ሐጢያት በማጉላት ራሳቸውን ጻድቅ አድርገው የሚመጻደቁ ፈሪሳውያውያን እና ቀሳውስት (የቤተ ዕምነት መሪዎች)፣ ከሐጢያተኛ እና ከቀራጮች ጋር ለምን ግንኙነት ያደርጋል? ብለው ሲከስሱት፣ “ፈሪሳውያንም አይተው ደቀ መዛሙርቱን። መምህራችሁ ከቀራጮችና ከኃጢአተኞች ጋር አብሮ ስለ ምን ይበላል? አሉ ኢየሱስም ሰምቶ፣ “ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም” ነገር ግን ሄዳችሁ። ምሕረትን እወዳለሁ መሥዋዕትንም አይደለም ያለው ምን እንደ ሆነ ተማሩ፤ ኃጢአተኞችን ወደ ንስሐ እንጂ ጻድቃንን ልጠራ አልመጣሁምና አላቸው።»

የሕዝብዎ እና የአገርዎ ሕመም የሚሰማዎት ከሆነ ራስዎን አያግልሉ!

The post የአገርዎ፣ የግልዎ እና የሕዝብዎ ስቃይ እና ሕመም ያሳሰብዎታል? -የአዲስ ቃል ኪዳን ታቦት የፈውስ አገልግሎት appeared first on Zehabesha Amharic.


ኢህአዴግ 98 ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!! –“ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ

$
0
0

birr4123111

ይህ ዘገባ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ዘገባ ነው

ኢህአዴግ በዓለም ባንክ በኩል ከእንግሊዝ የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤት ሊለግስለት ታቅዶ የነበረው 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) የገንዘብ ድጋፍ ነጠፈበት፡፡ አቶ ሬድዋን አልነጠፈብንም ይላሉ፡፡ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው “የታላቅ ሥራ ውጤት ነው፤ እናመሰግናለን” ብለዋል፡፡

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) “ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!! ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!” በሚል ርዕስ የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ያካሂድ ስለነበረው ፕሮግራም በዘገበበት ወቅት የሚከተለውን ዜና አትሞ ነበር፡- “ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡”

ይህ ለመሠረታዊ ልማት እንዲውል በዓለም ባንክ በኩል የሚሰጠውን ገንዘብ የሚደጉሙት ምዕራባውያን አገራት ሲሆኑ አንዷ ተጠቃሽ አገር እንግሊዝ ናት፡፡ ሆኖም ኢህአዴግ ከምዕራባውያን በዓለም ባንክ በኩል የሚያገኘውን ገንዘብ ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እያዋለው መሆኑ ለዓለም ባንክ ተደጋጋሚ መረጃዎች ሲቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይ ሟቹ መለስ በቀጥታ በሰጡት ትዕዛዝ 424 የአኙዋክ ተወላጆች ከተገደሉ በኋላ ኢህአዴግ በቦታው ያሰማራው የመከላከያ ሠራዊት በሥፍራው የሚኖሩትን ከመኖሪያ ቀያቸው በማፈናቀል እምቢ ያሉትን በግድ በማስነሳት፣ በመግደል፣ አስገድዶ በመድፈር፣ በማሰቃየት፣ ወዘተ ግፍ ሲፈጽም መቆየቱ በተለያዩ ዓለምአቀፋዊ ዕውቅና ባገኙ ዘገባዎች ሲነገር ቆይቷል፡፡ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ ልማት በማለት የሚሰጠው ገንዘብ ኢህአዴግ ወታደሮቹን የግፍ ሥራ ላይ በማሰማራት ደመወዝ የሚከፍልበት መሆኑን በመጥቀስ ወደ ኬኒያ የተሰደዱ የክልሉ ነዋሪዎች አቤቱታ አቅርበው እንደነበር ጎልጉል በወቅቱ የዘገበው ዜና ነበር፡፡ ““ኢህአዴግ አንገቱን ታንቋል”፤ዓለም ባንክ ርምጃ ለመውሰድ ጫፍ ደርሷል” በሚል ርዕስ የተጻፈውን ዜና ለማንበት እዚህ ላይ ይጫኑ፡፡

money lostከዚሁ ጋር በተያያዘ “ሚስተር ኦ” በመባል የሚጠሩት አኙዋክ ተወላጅ ኢህአዴግ የዕርዳታ ገንዘብ ለሰብዓዊ መብት ረገጣና ለራሱ የፖለቲካ መጠቀሚያነት እንዳዋለው በመጥቀስ የእንግሊዝ መንግሥት ከግብር ከፋይ ዜጎቹ የሚያገኘውን ገንዘብ አምባገነንነት እየደገፈበት መሆኑን በተለይም የዓለምአቀፍ ልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ተጠያቂ ስለሆነ ከዚህ እንዲታቀብ ክስ መመሥረታቸው ይታወቃል፡፡ የክሱ ሒደት እየተካሄደ ባለበት ባሁኑ ወቅት ሚስተር ኦ በተደጋሚ እንደመሰከሩት ኢህአዴግ ነዋሪዎችን በግዳጅ ከቀያቸው በማፈናቀል የሚያካሂደው የግዳጅ ሰፈራና የመንደር ምሥረታ ሕገወጥ መሆኑ በመቃወማቸው በተደጋጋሚ ከፍተኛ ድብደባ እንደረሰባቸው ተናግረዋል፡፡ ብዙዎች ለአካላዊ ሥቃይ ደርሶባቸዋል፣ ሴቶች ክብረንጽህናቸው ተደፍሯል፣ አዛውንትና ህጻናት ለአሰቃቂ መከራ ተዳርገዋል፤ ይህንንም እርሳቸው እንዳዩ ሚስተር ኦ ይመሰክራሉ፡፡

የሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ወደ ውሳኔ ሊደርስ ባለበት ወቅት የልማት መ/ቤቱ ይህንን ዓይነት ውሳኔ መውሰዱ ከፍርድ ቤቱ ጉዳይ ጋር የሚያያዝ እንደሆነ ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ይናገራሉ፡፡ የልማት ተራድዖ መ/ቤቱ ቃል አቀባይ ግን የመ/ቤታቸው ውሳኔ ከሚስተር ኦ የፍርድቤት ጉዳይ ጋር ያልተያያዘ እንደሆነ መናገራቸውን የእንግሊዙ ዘጋርዲያን ጋዜጣ ዘግቧል፡፡ መ/ቤቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሰው ኢትዮጵያ “የዕድገት ስኬት” እያስመዘገበች በመምጣቷ የመሠረታዊ ልማት አገልግሎት የገንዘብ ዕርዳታ የማያስፈልጋት በመሆኑ ነው ብለዋል፡፡

ይህ መጠኑ እጅግ ከፍተኛ የተባለውና ለኢህአዴግ ንጹህ የውጭ ምንዛሪ ምንጭ የሚያስገኝ ገንዘብ እንደነጠፈበት መሰማቱን አስመልክቶ ጋዜጣው የኢህአዴግ ፅ/ቤት ሃላፊ የሆኑትን ሬድዋን ሁሴን በጠየቃቸው ወቅት የመለሱት አልነጠፈብንም የሚል እንድምታ ያለው ነው፡፡ “እነርሱ ያሉት ዕርዳታውን አንሰጥም ወይም እናቆማለን ሳይሆን ዕርዳታ አሰጣጡ እንደገና ይዋቀራል ነው” በማለት ሬድዋን ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡ ሆኖም 4.9 ቢሊዮን ዶላር (98ቢሊዮን ብር) ዕርዳታ ለመስጠት ከዓለምባንክ ጋር ስምምነት የነበረው የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት “ኢትዮጵያ አድጋለች” በማለት በ2015/2016 በፓውንድ 256ሚሊዮን ብቻ (5በመቶ) ዕርዳታ ለመስጠት መወሰኑን የኢህአዴግ ጽ/ቤት ሃላፊው ሬድዋን ሁሴን አላብራሩም፡፡

ኢህአዴግ ለዕርዳታ የሚሰጠውን ገንዘብ ዜጎችን ለማሰቃየት፣ ወታደር ለመቀለብ፣ ወዘተ እንደሚጠቀምበት በተደጋጋሚ ዘገባዎች እና ማስረጃዎች ሲወጡበት የከረመ ቢሆንም ማስረጃዎቹን ተከትሎ የዓለም ባንክ በዕርዳታ አሠጣጡ ላይ አንዳች ውሳኔ እንዳያደርግ ብዙ ሲደክም ቆይቷል፡፡ በዚህም ምክንያት ጉዳዩ ውሳኔ ሳይሰጥበት እንዲስተጓጎል በማድረግ ለሁለት ዓመታት ያህል እንዲጓተት ማድረጉን ከጉዳዩ ጋር ቅርበት ያላቸው ወገኖች ይመሰክራሉ፡፡

ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ኦባንግ ሜቶ ጉዳዩን ገና ከጅምሩ የሚያውቁትና ድርጅታቸው ለዓመታት ሲሰራበት የነበረ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ በመሆኑንም ይህንን የእንግሊዝ የልማት ተራድዖ መ/ቤት ውሳኔ የጋራ ንቅናቄያቸው ከደጋፊዎቹ ጋር በመሆን ያገኘው ድል እንደሆነ በፌስቡክ ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት አስታውቀዋል፡፡ “ገና ከጅምሩ ከጋራ ንቅናቄያችን ጋር በመሆን ይህንን ሥራ በመደገፍ የተባበራችሁንን ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ለማለት እወዳለሁ፤ ታላቅ ሥራ ተሰርቷል፤ እናመሰግናለን” ብለዋል “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ፡፡ ከዚህ ጋር በተያያዘ አቶ ኦባንግ በተለይ ከጎልጉል ለቀረበላቸው አጭር ጥያቄ በሰጡት አስተያየት የጋራ ንቅናቄያቸው ደስታውን የገለጸው የልማት ገንዘብ በመቋረጡ ሳይሆን በልማት ስም የሚሰጠው ዕርዳታ ለሰብዓዊ መብት ረገጣ በመዋሉና ለዚህም ደግሞ ከበቂ በላይ ማስረጃ ድርጅታቸው ያለው በመሆኑ ነው፡፡ “አገር ብትለማ የሁሉም ደስታ ነው” ያሉት ኦባንግ አገርን በማልማት ሽፋን ደጋፊና ተቆርቋሪ የሌላቸውን ንጹሃን መበደልና የመኖር መብታቸውን መንፈግ ግን በየትኛውም መልኩ እርሳቸውም ሆነ አኢጋን የሚቀበለው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡

ኢህአዴግ በቅርቡ አካሂዳለው ለሚለው ምርጫ እንደ ዕቁብ ዕጣ በማውጣትና በማስወጣት “አልደረሳችሁም” እያለ የተቀናቃኝ ፓርቲ አመራሮችን ከምርጫ እያስወገደ ባለበት፤ ሌሎችንም ሕጋዊ አይደላችሁም እያለ በተለጣፊ ድርጅት በማስበት ኅልውናቸውን እያሳጣ ባለበት ባሁኑ ወቅት በዜጎቹ ላይ የሚያካሂደውን መረን የለቀቀ የመብት ገፈፋ ለሥልጣን ያበቁትን ምዕራባውያንን ያስደሰተ እንዳልሆነ ይነገራል፡፡ የአውሮጳ ኅብረት ምርጫውን አልታዘብም ከማለቱ በተጨማሪ በሚዲያ ላይ የተጫነው አፈና በዓለምአቀፉ የሰብዓዊ መብት ድርጅት ይፋ ከሆነ ወዲህ ማነቆው በኢህአዴግ ላይ እየከረረ መምጣቱን ያሳያል፡፡ ኢህአዴግን ለሥልጣን ከማብቃት አልፋ ነፍጥ አንጋቢዎቹን የህወሃት መሪዎች ጸጉርና ጺም ከርክማ፤ ልብስ አልብሳ፤ ቋንቋ አስተምራ፤ የከተማ አኗኗር እንዴት እንደሆነ አሠልጥና፣ ቶሎ ባይገባቸውም ፕሮቶኮል አስተምራ፣ እስካሁንም ተንከባክባ እዚህ ድረስ ያቆየቻቸው እንግሊዝ እንዲህ ያለውን የውጭ ምንዛሪ ምንጭ ስታደርቅ “ቀጣዩስ ምን ይሆን?” የሚል ጥያቄ እንዲነሳ አድርጓል፡፡ “ምዕራባውያን መግደልም ማንሳትም ያውቁበታል” በማለት አስተያየት የሚሰጡ ወገኖች እንደሚሉት ቀጣዩ የኢህአዴግ ጉዞ በከፍተኛ ሁኔታ ለህወሃት ሲቀጥል ለኢህአዴግ አስጊ ከመሆን ባሻገር በውጭ ምንዛሪ እጥረት በየጊዜው የሚፈጠረውን ግሽበት በዕርዳታ ገንዘብ የሚያስተካክለው ኢህአዴግ እንዲህ ያለው የገንዘብ ማዕቀብ ክፉኛ ያነጥፈዋል ሲሉ ግምታቸውን ይሰጣሉ፡፡ ሙስናው መረን በለቀቀባት አገር ከሕዝብ እየተዘረፈ በተለያዩ አገራት ባንኮች በውጭ ምንዛሪ የሚከማቸውን ገንዘብ በሚካፈሉትም ላይ የድርሻ ቅነሳ የማስከተሉ ጉዳይ አብሮ የሚታይ እንደሆነ ይነገራል፡፡

ከዚህ ዜና ጋር ተያያዥነት ያለውን ጥቅምት 2፤2005 (October 12, 2012) ያተምነውን ዜና ከዚህ በታች እንደሚከተለው እንደገና አትመነዋል፡፡

ኢህአዴግ በ600 ሚሊዮን ዶላር አጣብቂኝ ውስጥ ገባ!!

ብያኔው ከጸና ኪሣራው በቢሊዮን ዶላር ሊደርስም ይችላል!

ኢህአዴግ ከዓለም ባንክ ያገኘውን 600 ሚሊዮን ዶላርና በተመሳሳይ ፕሮጀክት ወደፊት ሊያገኝ የሚችለውን ከፍተኛ ገንዘብ በተመለከተ አደጋ ውስጥ መውደቁ ተሰማ። ኢንስፔክሽን ፓናል (Inspection Panel – IP) የተሰኘ ተቋም ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመለክተው ኢህአዴግ የቀረበበት ውንጀላ ከተረጋገጠ የሚያጣው ገንዘብ በቢሊዮን ዶላር እንደሚደርስ ታውቋል። ይፋ የሆነውን መረጃ አስመልክቶ ከኢህአዴግ ወገን እስካሁን በይፋ የተሰጠ ምላሽ የለም።

ግፍ የሚፈጽሙ መንግስታትን፣ በልማት ስም የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጽሙ ወንጀሎችን መረጃዎችን በስፍራው በመገኘትና ከመሠረቱ ዘልቆ በመግባት አደራጅቶ ተጠያቂ የሚያደርገው ኢንክሉሲቭ ዴቨሎፕመንት ኢንተርናሽናል Inclusive Development International (IDI) ከሰለባዎቹ ውክልና ተሰጥቶታል። ተቋሙም በውክልናው መሰረት ለኢንስፔክሽን ፓናል በዝርዝር የሰለባዎቹን በደል በማተት አሳውቋል።

የኢህአዴግ መከላከያ ሠራዊት የሚያደርሰውን እስራት፣ ግርፋት፣ አስገድዶ መድፈር፣ ከመኖሪያ ቦታ ማፈናቀል፣ የግዳጅ ሰፈራ ወዘተ በማምለጥ ወደ ኬንያ የተሰደዱ የጋምቤላ ነዋሪዎች ይህ ሁሉ ግፍ የሚፈጽምባቸው የኢትዮጵያ መንግሥት በልማት ስም ከዓለም ባንክ በሚያገኘው የዕርዳታ ገንዘብ በመሆኑ ለባንኩ በላኩት የአቤቱታ ደብዳቤ አመልክተዋል።

አቤቱታውን መሠረት በማድረግ የሚደረገው ምርመራ ውጤት ይፋ ሲሆን፣ በሌሎች አገሮች እንደተደረገው በዕርዳታ ስም የሚገኝን ገንዘብ ኢህአዴግ ለፖለቲካ ተግባር መጠቀሙ ሲረጋገጥ፣ በመስከረም ወር መጀመሪያ አካባቢ ከዓለም ባንክ ተፈቅዶ የነበረው 600ሚሊዮን ዶላር ሊከለከል ይችላል፡፡

የዛሬ ዘጠኝ ዓመት አካባቢ በሟቹ ጠ/ሚ/ርና የጦር ኃይሎች ጠቅላይ አዛዥ መለስ ዜናዊ ቀጥተኛ ትዕዛዝ በጋምቤላ ክልል በተለይ የተማሩ ወንዶች ላይ በማተኮር 424 ንጹሐን የአኙዋክ ተወላጆች በተገደሉበት ወቅት በሺዎች የሚቆጠሩት ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ መሰደዳቸው ይታወሳል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ክልሉ ሰላም የለም፡፡ በየጊዜውም የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሲካሄዱበት ቆይቷል፡፡ በተለይም ለም የሆነውን እጅግ ሰፋፊ መሬት ለውጪ ባለሃብቶች በሳንቲም በመሸጥ ላይ የሚገኘው የኢህአዴግ አገዛዝ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በቀድሞው የደርግ ዘመን ሲካሄድ ከነበረው ባለፈ መልኩ እጅግ በሚያሰቅቅ ሁኔታ በመንደር ምስረታና አስገድዶ የማስፈር ፖሊሲ ከመኖሪያ ቀዬ የማፈናቀል ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን የኦክላንድ ተቋም፣ ሂውማን ራይትስ ዎች፣ … የመሳሰሉ ድርጅቶች ያወጧቸው ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

ከ1998ዓም ጀምሮ የመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) በሚል በአራት ተከታታይና ሁለት ተጨማሪ የገንዘብ ድጎማ የሚደረግባቸውን ፕሮግራሞች የዓለም ባንክ በኢትዮጵያ ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ ይህ መሠረታዊ የሆኑ አገልግሎቶችን ለማሟላት ተወጥኖ የሚካሄድ ፕሮጀክት በትምህርት፣ በጤና፣ በእርሻ፣ በንጹህ ውሃ አቅርቦት፣ በገጠር መንገድ ሥራ፣ ወዘተ መስኮች ላይ እንዲውል (PBS I, PBS I-AF (Additional Financing), PBS II, PBS 11-AF, PBS-Social Accountability Program and PBS III) በማለት በተለያዩ ደረጃዎች ለተከፋፈለው ኦፐሬሽን ማስፈጸሚያ የሚውለው ገንዘብ ከ13ቢሊዮን ዶላር የሚበልጥ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ከፍተኛው የዓለም ባንክ ድርሻ 2ቢሊዮን ዶላር ሲሆን የተቀረው በሌሎች ለጋሽ መንግሥታት እና ድርጅቶች የሚሸፈን ነው፡፡ PBS III የተሰኘውን በሦስት ንዑሳን ፕሮግራሞች የተከፋፈለውን ፕሮጀክት ለማስፈጸም በአጠቃላይ የሚፈጀው 6.3ቢሊዮን ዶላር በላይ ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ የባንኩ ድርሻ የሆነውን 600ሚሊዮን ዶላር ቦርዱ መስከረም 5ቀን 2005ዓም አጽድቋል፡፡

በአስገድዶ ማስፈር፣ መንደር ምስረታና ሌሎች በርካታ የሰብዓዊ መብቶቻቸው የተጣሱባቸው በኬንያ የሚገኙ ሦስት የአኙዋክ ስደተኞች ተወካይ ድርጅቶች በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ ሌሎች የሰብዓዊ ድርጅቶች ጋር በመሆን ባንኩ ሊሰጥ የወሰነውን ገንዘብ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ጥቅም ከመዋል ይልቅ ለኢህአዴግ የፖለቲካ ዓላማ ማስፈጸሚያ እየዋለ መሆኑን በመጥቀስ ለባንኩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጂም ዮንግ ኪም መስከረም 6፤ 2005ዓም ደብዳቤ ልከዋል፡፡ በጥያቄያቸውም መሠረት በዓለም ባንክ በኩል ወደ ኢትዮጵያ የሚፈሰው ገንዘብ “በልማት ስም የኢትዮጵያ መንግሥት በጋምቤላ ክልል ለሚያካሂደው የመንደር ምስረታ እየዋለ ነው” በማለት ይከሳል፡፡ ሲቀጥልም የአኙዋክ ሕዝብ ለዘመናት ከኖረበት መንደር በማፈናቀል “የተሻለ አገልግሎት ይሰጣችኋል” በማለት በግድ የማስፈር ተግባር እየተፈጸመ ሲሆን “የተባለው አገልግሎትም ሆነ ለእርሻ የሚሆን በቂ ቦታ እንዲሁም ለከብቶች የሚበቃ የግጦሽና የውሃ ቦታ የላቸውም” በማለት ሰፈራውን የተቃወሙ ሁሉ እጅግ ከፍተኛ የሆነ የሰብዓዊ መብት ረገጣ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ጠቁሟል፡፡ ይህንን ግፍ የሚፈጽሙት ደግሞ የዓለም ባንክ ለመሠረታዊ አገልግሎት ጥበቃ ፕሮግራም (Protection of Basic Services “PBS Program”) ስም ለልማት እንዲውል ከሚሰጠው የዕርዳታ ገንዘብ በመንግሥት ተቀጥረው ደመወዝ የሚከፈላቸው ሠራተኞች መሆናቸውን ገልጾዋል፡፡ ይህንን ጉዳይ ከዓለም ባንክ ጋር እንዲነጋገሩላቸው Inclusive Development International (IDI) የተባለውን ድርጅት መወከላቸውን አስታውቀዋል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ተመሳሳይ ጉዳዮችን በዓለምአቀፍ ደረጃ በመከታተልና በማስፈጸም የታወቀው IDI በመስከረም ወር አጋማሽ ላይ ጉዳዩ በቀጥታ ለሚመለከተው የመልሶ ማቋቋምና ልማት ዓለምአቀፍ ባንክና (International Bank for Reconstruction and Development (IBRD)) የዓለምአቀፍ ልማት ማኅበር (International Development Association (IDA)) ሥር ለሚገኘው የኢንስፔክተር ፓናል ባለ 18ገጽ ደብዳቤ ጽፏል፡፡ (የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል) ይህ የኢንስፔክተር ቡድን ከፍተኛ ሥልጣን ያለው መ/ቤት ሲሆን የዓለም ባንክ የሚሰጠውን ገንዘብ በትክክለኛ ቦታ ላይ አለመዋሉን በመጥቀስ ክስ የሚያቀርቡ ወገኖችን ጉዳይ በመከታተልና ቦታው ድረስ የራሱን ምርመራ በማካሄድ ውጤቱ ተግባራዊ እንዲሆን የባንኩን እጅ የማስጠምዘዝ ዓቅም ያለው እንደሆነ ከዚህ በፊት ያካሄዳቸው የምርመራ ውጤቶች ይጠቁማሉ፡፡

ይህ የመርማሪ ቡድን የቀረበለትን አቤቱታ መቀበሉንና በጉዳዩ ላይ የማንም ተጽዕኖ የማይደረግበትን የራሱን ምርመራ እንደሚያደርግ ከትላንት በስቲያ ባወጣው ባለ 8ገጽ መግለጫ ላይ አሳውቋል፡፡ ይህ የአቤቱታ ፋይል ቁጥር የተሰጠው ጉዳይ በግልባጭ ለባንኩ ፕሬዚዳንትና ለከሳሽ ተወካይ ድርጅት (IDI) እንዲደርስ ተደርጓል፡፡(የደብዳቤው ሙሉ ቃል እዚህ ላይ ይገኛል)

ጎልጉል የሰሜን አሜሪካ ዘጋቢ ባጠናከረው መረጃ መሠረት ቡድኑ ከያዝነው ዓመት የጥቅምት አጋማሽ በኋላ ወደ ምስራቅ አፍሪካ ያቀናል። ቡድኑ ስደተኞቹ የሚገኙባቸውን፣ እንዲሁም ጉዳዩን በሚመለከት አስፈላጊ የሚላቸውን ቦታዎችና ግለሰቦች ሙሉ በሙሉ ያነጋግራል። ለስራው መሳካት የሚሆነውን ሁሉ በሚፈለግበት ቦታ በመገኘት በግንባር እንደሚያከናውን ለማወቅ ተችሏል።

በተለያየ ጊዜ ኢህአዴግ የሚፈጽመውን ግፍና በደል በማደራጀት ሥርዓቱ ላይ ከትጥቅ የጠነከረ ትግል ማካሄድ እንደሚቻል አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል:: አያይዘውም በመላው አገሪቱ የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ረገጣና የመብት ጥሰት በማሰባሰብ የኢህአዴግን የገንዘብ ምንጭ የማድረቅ፣ ብሎም በእርዳታ ገንዘብ የሚገነባቸውን የአፈና ተቋማት ማስለል እንደሚቻል አስታውቀዋል። ይህንን ታላቅ ስራ የሰሩትን አካላት ልምዳቸውን ለሌሎች በማካፈል አስፈላጊውን ስራ ሊሰሩ እንደሚገባም አሳስበዋል። (የመግቢያው ፎቶ የተወሰደው: ዘጋርዲያን)

 

Source: ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

The post ኢህአዴግ 98 ቢሊዮን ብር ነጠፈበት!! – “ታላቅ ሥራ ተሰርቷል! እናመሰግናለን!” ኦባንግ appeared first on Zehabesha Amharic.

አድዋ መስክሪ –ጌታቸው ከኑርንበርግ ጀርመን

ሰበር ዜና: የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ!

$
0
0

ሂሩት መለሰ – ከሮተርዳም

ሮተርዳም፣ ጥቅምት 28 ቀን 2015 – በስደት ስሙ አለማየሁ ስንታየው በመባል የሚታወቀው የህወሃት ሰላይ ከኔዘርላንድስ ተባረረ። አለማየሁ ስንታየሁ ቋሚ ነዋሪ ከነበረበት ከኔዘርላንድስ እንዲባረር የተደረገው በዚያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በከፈቱበት የስለላ ክስ መሆኑም ታውቋል።

የሮተርዳም ከተማ ፍርድ ቤት በአለማየሁ ላይ የተመሰረተውን የስለላ ክስና ማስራጃ ለረጅም ጊዜ ሲመረምር ከቆየ በኋላ የግለሰቡ የመኖርያ ፈቃድ እና ቤት እንዲነጠቅ፣ የሆላንድን ምድርም በአስቸኳይ ለቆ እንዲወጣ ውሳኔ አስተላልፏል። ከሆላንድ የምመራ ቡድን እንደተረዳነው ከሆነ – የግለሰቡ ቤት ሲፈተሽ ወያኔ የሰጠው እውነተኛ መታወቂያ እና በርካታ የስለላ ሰነዶች ተገኝተውበታል። በእርዳታ ስም የተቋቋመለት ድርጅትም ተፈትሾ ማስረጃዎች እንደተገኙ ለማወቅ ተችሏል።
alemayehu-sentayehu

ይህ ሰው ትክክለኛ ስሙ ዘለቀ ፎላ ይባላል። በደርግ ጊዜ የኢትዮጵያ ሰራዊት አባል ሆኖ ለረጅም አመታት አገልግሏል። ወያኔ ስልጣን ሲቆጣጠር ለፖለቲካ ተሃድሶ አዋሳ ደቡብ ጦር ቅጥር ግቢ ተላከ። በተሃድሶ በነበረበት ጊዜ ቁጥራቸው ብዙ የሆኑ የሰራዊቱ አባላትን ለወያኔ በማጋለጥ ታማኝነቱን ሲያሳይ እንደነበር የዚህ ዜና ዘጋቢ እማኝ ነው። የበርካታ ኢትዮጵያውያን ደም በእጁ ያለው አለማየሁ ከተሃድሶው ከወጣ በኋላ እስራኤል ገደቡ (የፓልቶክ ስሙ ኢዛና) ከተባለ ወታደር ጋር በመሆን የሰላም ተጓዥ ነኝ ብሎ በመገናኛ ብዙሃን ሲታይ ነበር። አለማየሁ እና ኢዛና በየሃገሩ እየዞሩ ስለ አዲሱ ስርዓት መልካምነት ሲሰብኩ ከረሙ። ከዚያም አስመራ ድረስ ተልከው የሻእቢያውን መሪ ኢሳያስ አፈወርቂን በወታደሩ ስም ይቅርታ ጠይቀዋል።

አለማየሁ እና ኢዛና ለወያኔ በሰሩት ውለታ ሆላንድ ገብተው እንዲቀሩ ተደረገ። ይህም የተደረገበት ምክንያት በአውሮፓ የሚኖሩ ኢዮጵያውያንን ተቃዋሚ በመምሰልና በረቀቀ መንገድ እንዲያበጣብጡና እንዲሰልሉ ነው።
በሆላንድ ሃገር የፖለቲካ ጥገኝነት ጠይቆ ለወያኔ ቡድን የስለላ ስራ መስራት ወንጀል ነው። አለማየሁ የሆላንድ ዜግነት ቢኖረው ኖሮ ቅጣቱ የከፋ ይሆን እንደነበር ጉዳዩን እየተከታተሉ ያሉ የህግ ባለሙያዎች ተናግረዋል።
የአለማየሁ መባረር በተሰማ ግዜ በሮተርዳም ያሉ የህወሃት ደጋፊዎች የአቤቱታ ደብዳቤ በመጻፍ ፊርማ ማሰባሰብ ቢጀምሩም ሊሳካላቸው አልቻለም። የአቤቱታ ደብዳቤው ግለሰቡ እዚህ የተወለዱ ሁለት ለጆቹን እየመጣ እንዲጎበኝ ይፈቀድለት የሚል ነበር።
አለማየሁ ስንታየሁ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከሆላንድ ተባረረ። ኢዛና ግን አሁን የተቃዋሚ ጭንብሉን አውልቆ በግልጽ ወያኔ መሆኑን መናገር ጀምሯል። ኢዛና የሆላንድ ዜግነት ቢኖረውም በሆላንድ ሃገር ስራ ሰርቶ አያውቅም። የቀንና ማታ ስራው በፓልቶክ ላይ ነው። ባለፈው ወር ኢትዮጵያ የተጓዙ ዲያስፖራ ኢንቨስተሮችን እየመራ በቴሌቭዥን መግለጫ ሲሰጥ አይተነዋል። ይህ ትርኢት የወያኔ ኢንቨስተሮች በጨበጣ እንደሚንቀሳቀሱም ያሳየናል።

The post ሰበር ዜና: የወያኔ ሰላይ ከሆላንድ ተባረረ! appeared first on Zehabesha Amharic.

የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከበረ

$
0
0

ESM 2

ecm minnesota

(ዘ-ሐበሻ) የኢትዮጵያ ማህበረሰብ (ኮምዩኒቲ) በሚኒሶታ ያዘጋጀው 119ኛው የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከብሮ ዋለ::

በሚኒሶታ ከኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ ከወጣትም ሆነ ከአዛውንቶች የተውጣጡ የተለያዩ የማህበረሰቡ ክፍሎች በተገኙበት በዚሁ በዓል ላይ የአድዋ ድል በዓል በተለይ ለኢትዮጵያውያን እና ለጥቁር ሕዝቦች ያለው ትልቅ ም ዕራፍ ተዘክሯል::

ዛሬ በተከበረው በዓል ላይ በክብር እንግድነት የተገኙትና ስለአድዋ ድል ገለጻ የሰጡት ዶ/ር ዳንኤል ሲሆን የአድዋ ድል ከጥቁር ሕዝቦች ታሪክ ጋር ያለውን ተያያዥነት አውስተው የተለያዩ ገለጻዎችን ሰጥጠዋል::

በዚሁ ዕለት በስፍራው የተገኙ የማህበረሰቡ አባላት እንዲሁ በበዓሉ ዙሪያ ትምህርታዊ አስተያየቶችን እንደሰጡም በስፍራው የተገኘው የዘሐበሻ ዘጋቢ አስታውቋል::

The post የአድዋ ድል በዓል በሚኒሶታ ተከበረ appeared first on Zehabesha Amharic.

የሆሳህና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት ነደደች (ቪድዮና ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0


ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት

ቤተክርስቲያኗ ከመቃጠሏ በፊት

ከተቃጠለች በኋላ

ከተቃጠለች በኋላ

ከተቃጠለች በኋላ

ከተቃጠለች በኋላ


(ዘ-ሐበሻ) እኔ የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ ያሉ በአካባቢው የሚገኙ ነዋሪዎች በፎቶግራፍ እና በቭዲዮ አስደግፈው በላኩት መረጃ የካቲት 21/2007 ዓ.ም በሀዲያና ስልጤ ሀ/ስብከት የሆሳዕና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት መንደዷን አስታወቁ፡

የቃጠሎው መነሻ እስካሁን ያልታወቀ ሲሆን ጉዳዩን ለማድበስበስ የሚደረገው ጥረት ም ዕመናኑን እያስቆጣ መሆኑንም ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ ያመለክታል::

የካቲት 21 ቀን ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ ህዝበ ክርስቲያኑን ለማጽናናት እንዲሁም የገቢ ማሰባሰብ መርሐግብር የሀ/ስብከቱ ሊቀጻጻስ ብጹዕ አቡነ ቀሌምንጦስ በተገኙበት ከአ.አ በመጡ መምህራን እና ዘማሪያን መርሐ ግብር ተዘርግቶ የነበረ ሲሆን ማንኛውም ም እመን የሚቻለውን ስፍራው ድረስ በመገኘት ድጋፍ እንዲደርግ ያልቻለም በጸሎት እንዲያስቡ በእግዚአብሔር ስም ቅድስት ቤተክርስቲያን ጥሪዋን አስተላልፋለች ሲሉ እኔ የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ ያሉ ከስፍራው ዘግበዋል::

ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው በዚሁ ቤተክርስቲያኒቱ በምትገኝበት ከተማ ከሳምንት በፊት በተመሳሳይ እሳት አደጋ አጠና ተራ ወድሟል::

The post የሆሳህና ደብረ ገነት ቅድስት ማርያም ቤ/ክ በእሳት ነደደች (ቪድዮና ፎቶዎች ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>