(ዘ-ሐበሻ) የሃገሬን ድንበር በሕገወጥ መንገድ አቋርጠው ገብተዋል ያለቻቸውን 40 ኢትዮጵያውያንን በቁጥጥር ስር ማዋሏን ማላዊ አስታወቀች:: ከታንዛኒያ ዝቅ ብላ ከሞዛምቢክ ከፍ ብላ ከዛምቢያ አጠገብ በአፍሪካ ካርታ ላይ የምትታየው ማላዊ በሃገራቸው መንግስት ተማረው የተሰደዱ እነዚሁኑ ኢትዮጵያውያን ፍርድ ቤት እንደምታቀርብ ታውቋል::
ከኢትዮጵያ ተሰደው መድረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ ያደረጉ ወገኖች በተለይም በኬንያ, በታንዛኒያ, በዛምቢያ, በማላዊ, በሞዛምቢክ, በዙምባብዌና በሌሎችም ሃገሮች ችግር የሚገጥማቸው ቢሆንም “በሃገሬ መከራ ከሚበላኝ ተሰድጄ የሆንኩትን ልሁን” በሚል ስሜት የሚደርስባቸው ችግር ምንም እንደማይመስላቸው ከተለያዩ ስደተኞች የሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ::
የማላዊ መንግስት እነዚህን 40 ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን ኢትዮጵያውያኑን ከሃገር ወደ ሃገር ያሻግራሉ ያላቸውን የሃገሩን ዜጎችም አስሯል::
40ዎቹ ኢትዮጵያውያን ከሃገራቸው የወጡት መድረሻቸውን ደቡብ አፍሪካ በማድረግ ነው::