Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

የዋሺንግተን ዲሲ የጋራ ግብረሃይል “በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ የተፈረደው ፍርድ በ90 ሚሊዮን ሕዝብ ላይ የተፈረደ ፍርድ ነው”ሲል አወገዘ

$
0
0

abubeker

ጋዜጣዊ መግለጫ

የፍትሕ ያለህ

ፍትሕ የትንሽ የትልቁ የስላሙም የክርስቲያኑም የንግግር አልፋና ኦሜጋ ከሆነ ሰነበተ አብያተ ክርስቲያናት ጸሎታቸውን ፣መስኪዶች ሶላታቸውን የሚያሳርጉት ስለ ፍትሕ እየጮሁ ነው።የጥንቱን ታሪክ እንዳለ ብናቆየው እንኳ ባሳለፍነው ከሬት የመረረ ወያነያዊ ስርዓት ፍትሕ በውን ተከስታ ልትትታይ ቀርቶ በዳሰሳና በሽታ እንኳ ደብዛዋ ጥፍቶ የ፺ ሚሊዮን ህዝብ የምኞት መዝሙር ሆና ፪፭ አመታትን አስቆጠረች። ዛሬም የፍትሕ ያለህ የህዝብ መዝሙር ሆኖ ቀጥሏል።

የፍትሕ ያለህ በሚል ርዕስ መግለጫ ስናውጣ ባለፈው ፪፭ አመታት የተደሰኮረልን ፍትሃዊ ስርዓት፣ሰፈነ የተባለው ሰላማዊና ልማታዊ አገዛዝ፣ጮቤ የተረገጠለት ዲሞክራሲ ቢከፍቱት ተልባ ስለሆነብን ነው።

በርካቶች በእንበለ ፍርድ በወያኔ ተከሰው በወያኔ ተመስክሮባቸው በወያኔ ዳኛ በወያኔ አቃቤ ህግ በወያኔ የግፍ ሰንሰለት አሳራቸውን የበሉ በዚያውም ያሸለቡ ደብዛቸው የጠፋ ለዛሬ ቤቱ ይቁጠራቸው ለማለት ተገደናል። ላሁኑ ግን በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ላይ ሰሞኑን የተጠበቀ ግና አስደንጋጭ ስለሆነው በንጹሃን የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊዎች ላይ የተበየነው ብይን ለተበየነባቸው ጀግኖች ሳይሆን ሃዘናችንን የምንገልጸው በራሱ ላይ ስለፈረደው የፍትሕን ገመድ ገምዶ አንገቱ ላይ ስላጠለቀው የወያኔ ስርዓት ነው።
ከ፱፯ ዓመተ ምህረት ምርጫ ህዝባዊ እንቅስቃሴ በሗላ በሃይል ተጨፍልቆ ብልጭብልጭ ሲል የከረመው ህዝባዊና ኢትዮጵያዊ ወኔ ድንገት ሰሜን ምዕራብ አዲስ አበባ ከዓወሊያ ተቋም ገንፍሎ ምድሪቷን ያጥለቀለቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ትግል ስንቃኘው እንደዜጋ አድናቆት ስንቸረው በመብት ትግሉ ሂወት ያስከፈላቸውን አሳሳ፣ገርባ፣ኮፈሌዎችን፣እንዲሁም በፈሪ በትር የተቀጠቀጡትን አካል የጎደለባቸውን፣ ባኑዋር መስኪድ የጥቁር ሽብር ሰለባ የሆኑትን፣ለፍትሐዊ ትግሉ ቀንዲል ሆነው ዛሬ ለጠየቁት ጥያቄ ከ፯ እስከ ፪፪ አመት በሚል የቀልድ ቲያትር መጋረጃ የተዘጋባቸውን ወንድም እህቶች ታላቅ ወገናዊ አክብሮት እንሰጣለን።

ትግሉ የጋራ ነው ድሉም እንደዚሁ>>> እኛ በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ የምንገኝ የጋራ ግብረሃይል በዚህ ሳምንት የሰማነው እምበለ ፍርድ የጠበቅነው ነውና ባንደነቅም ሆኖም ግን እንዲህ አይነት በ፺ ሚሊዮን ህዝብ ላይ የተቀለደ ቀልድን አንስቅለትም። እንዲያውም ትንታጎቹን ፈጣሪ ያበርታቸው፣ቤተሰቦቻቸውን አምላክ ያጽናናቸው ስንል ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ባጠቃላይ አብሽሩ የሚል መልዕክት እናስተላልፋለን።

ፍትሕ የተዘነበለችው ባጠቃላይ በኢትዮጵያውያኖች ላይ ነውና ለዚህ ሁሉ አብነቱ የፍትሕ ያለህ የሚል ጩኸታችን የሚቆመው ይህ ጸረ እስላም፣ጸረ ክርስቲያን ጸረ ሃገር የሆነው ሰይጣናዊ ስርዓት በጸሎትም በሁለገብ ትግልም በተባበረ ህዝባዊ እምቢታም ተመንግሎ ነጻነታችንን ስንጎናጸፍ ብቻ ነው ብለን እናምናለን።ለዚህም በኛ በኩል ሰላም ላጠጠበት ህዝባችን፣ፍትሕ ለጠፋበት ወገናችን፣በኩልነት ለምታኖረን ኢትዮጵያችን ባስገባን ቀዳዳ ሁሉ ገብተን የመጨረሻዋ እስትንፋሳችን እስክትቆም ድረስ አብረን ተባብረን ለመታገል ስለፍትሕ በሚጮህ ህዝባችን ስም ቃል እንገባለን።

እግዚዓብሄር ትልቅ ነው
አላህ ወኩበር


Viewing all articles
Browse latest Browse all 2784

Trending Articles



<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>