Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

የአንድነት የወላይታ ዞን ምክር ቤት ስብሰባን የመለስን ቲቨርት የለበሱ የመንግስት ካድሬዎች በኃይል አደናቀፉት

$
0
0

daniel tefera

የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ደህንነታቸው አደጋ ላይ ነው፡፡

የሟቹን የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር የአቶ መለስ ዜናዊ ምስል ያለበት ቲሸርት የለበሱ ከ 10 የሚልቁ የመንግስት ካድሬዎች በወላይታ ሶዶ እየተደረገ የነበረውን አንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን ምክርቤት ስብሰባን በሀይል ማደናቀፋቸውን ከስፍራው ለፍኖተ ነጻነት የደረሰው ዘገባ አመለከተ፡፡
ካድሬዎቹ የስብሰባ አዳራሹን በሃይል በመስበር ከተሰብሳቢዎቹ ላይ የተለያዩ ሰነዶችን የቀሙ ሲሆን ብብደባ በመፈፀም ላይ ናቸው፡፡ በስብሰባ አዳራሹ ውስጥ የነበሩት የአንድነት ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ እና ምክትል ኃላፊ የሆኑት አቶ ዳንኤል ሺበሺ ደህንነታቸው አደጋላይ መሆኑን ለፍኖተ ነፃነት ተናግረዋል፡፡


የኢሕአዴግ መንግስት የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ዶክመንተሪ ሊያዘጋጅ ነው ተባለ

$
0
0

ዶክመንተሪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ ቅድመ ዝግጅት አካል እንደኾነ ተጠቁሟል

‹‹ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› ለሚለው የማኅበሩ ጥያቄ ምላሽ አልተሰጠም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ የሲኖዶሱን ይኹንታ አግኝቶ በመላው አገሪቱ የሚንቀሳቀሰውን የማኅበረ ቅዱሳንን አመራርና አባላት በአክራሪነት የሚከስ ነው የተባለ ዶክመንተሪ ፊልም ለማዘጋጀት መታቀዱ ተጠቆመ፡፡
mahbere-kidusan-300x168
የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ አንዳንድ ሓላፊዎች አቀብለውታል በተባለ መረጃ እንደሚታገዝና በመንግሥት አካል እንደሚሰናዳ የተገለጸው የዶክመንተሪ ዝግጅቱ በማኅበሩ ኻያ አመራሮች እና አባላት ላይ እንዳነጣጠረ ተገልጧል፡፡ መንግሥት በምርጫ – 97 ውጤትና በተከታይ ኹኔታዎቹ ላይ ባካሔደው ግምገማ፣ የማኅበረ ቅዱሳን አባላት ናቸው የሚባሉ ግለሰቦች በተለይ በገጠር ቀበሌዎች ለተቃዋሚዎች ተሰሚነት ማግኘት በምክንያትነት መጥቀሱ በዜና ጥቆማው የተመለከተ ሲኾን ‹‹የአክራሪነትና የጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግ ነው›› በሚል የሚያቀርበው ክሥም ከዚኹ የሚነሣና ለመጪው የ2007 ሀገራዊ ምርጫ የሚደረግ ቅድመ ዝግጅትም አካል እንደኾነ ተነግሯል፡፡

በቅድመ ዝግጅቱ የሚወሰዱ ርምጃዎች የማኅበሩን አቅሞችና እንቅስቃሴዎች በመቆጣጠር በተለይም የማኅበሩ መሠረቶች ናቸው የሚባሉ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ግቢ ጉባኤያትን ‹‹በሴኩላሪዝም መርሖዎች የመግባቢያ ሰነድ›› ጠርንፎ ‹የአገልግሎት ቅኝቱን የማስተካከል› ዓላማ እንዳላቸው የገለጸው የዜና ምንጩ፣ ይህም ካልተሳካ በተከታታይ አስተዳደራዊ ርምጃዎችና የተቃውሞ ቅስቀሳዎች ማኅበሩን በማወከብ ተቋሙን ለዘለቄታው የማፍረስ ውጤት ሊኖረውም እንደሚችል አመልክቷል፡፡’

ከአዲስ አበባ ሀ/ስብከት አብያተ ክርስቲያናት የተጠሩ ናቸው የተባሉ አስተዳዳሪዎችና ሠራተኞች የሚሳተፉበት እንደኾነ የተገለጸና ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ በማኅበሩ አገልግሎት ላይ ቁጥጥሩን እንዲያጠብቅ የሚጠይቅ ስብሰባ በዛሬው ዕለት በቤተ ክህነቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሔድ የተዘገበ ሲኾን ዓላማውም ‹‹በአክራሪዎችና ጽንፈኛ ፖሊቲከኞች ምሽግነት፣ የቤተ ክህነቱን አሠራር ባለማክበርና ከቤተ ክህነቱ በላይ ገዝፎ በመውጣት›› ማኅበሩ የሚከሰስባቸውን ኹኔታዎች በማጠናከር ለታቀዱት ርምጃዎች የሚያመቻች ነው ተብሏል፡፡

በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ላይ በማተኮር የተማረው ትውልድ ሃይማኖቱን የሚወድ፣ ግብረ ገብነት ያለው፣ ሀገሩንና ቤተ ክርስቲያኑን በዕውቀቱ፣ በሞያውና በገንዘቡ የሚያገለግል ብቁ ዜጋ ይኾን ዘንድ በቅዱስ ሲኖዶስ ጸድቆ በተሰጠው መተዳደርያ ደንብ መሠረት በመሥራት ላይ እንዳለ የሚገልጹ የማኅበሩ አባላትና ደጋፊዎቹ፣ ማኅበሩ ለቀረቡበት ክሦች የሚመች አደረጃጀት ይኹን ባሕርይ እንደሌለው በመግለጽ ተጠሪ ከኾነለት ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጋራ በአሠራር ሒደት የሚፈጠር ክፍተትን በማጦዝ የሚሰነዘሩ ውንጀላዎች ተቀባይነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ የተጠቀሱት ክሦች ላቀረቡት አካላት ‹‹የሚነገረውና የሚጻፈው እኛን የሚገልጸን ስላልኾነ ማስረጃ አቅርቡና እንነጋገርበት›› የሚል ጥያቄ ቢቀርብላቸውም ለሠለጠነ ውይይት ፍላጎት እንደሌላቸው አባላቱ አስረድተዋል፤ በምትኩ ‹‹ርምጃ እንወስዳለን›› በማለት በተለያዩ መድረኮች ማኅበሩን ማሳጣትና መክሠሥ እንደሚመርጡም ለፋክት መጽሔት አስታውቀዋል፡፡

ታቅዷል የተባለው የዶኩመንተሪ ዝግጅት እውነት ከኾነም ማኅበሩን ብቻ ሳይኾን የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን የማዳከም አጠቃላይ ዘመቻ አድርገው እንደሚቆጥሩትና በቀላሉ እንደማይመለከቱት አሳስበዋል፡፡

ምንጭ፡ ፋክት መጽሔት ቅጽ ፪ ቁጥር ፴፰፤ መጋቢት ፳፻፮ ዓ.ም.)

ወላይታ ሶዶ ነፃነት አልባዋ የማፊያ ካድሬዎች ከተማ!!!

$
0
0

ከወላይታ ዞን የአንድነት ፓርቲ አመራሮች የእስርና እንግልት ማብራሪያ

 

የአንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራና ድርጅት ጉዳይ ም/ሃላፊ አቶ ዳንኤል ሺበሺ በደቡብ ቀጠና በወላይታ ዞንና በሲዳማ ዞን አዋሳ ከተማ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር የፓርቲውን የትግል ስትራቴጅክ ዕቅዶች ላይ ማብራሪያ፣ ደንብና ፕሮግራም ለመስጠት እንዲሁም የስራ ጉብኝት ለማድረግ በ 12/07/06 ወደ ወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ተገኝተው ነበር፡፡ በ13/07/06 ደግሞ ከሶዶ ከተማ ስራ አስፈፃሚና ከወረዳ አመራር አባላት ጋር የፓርቲያችንን ደንብ፣ ፕሮግራምና ቀጣይ የስራ አቅጣጫ አስመልክቶ የተሰናዳው ውይይት ላይ ለመታደም ከ32 በላይ አመራሮችም ተገኝተው ነበር፡፡

ቅዳሜ በ 13/07/06 ዓ.ም ከአባላት ጋር ባለው ዕቅድ መሰረት የፓርቲያችንን ህጋዊ ሰነዶችን ለወረዳና ለዞን አመራሮች ለመስጠት፣ ቀጣዩን ሀገራቀፍ ምርጫ አስመልክቶ መረጃ ለመለዋወጥ ምርጫችን የነበረው የፓርቲያችን አባል የሆነውና ወጣ ብሎ ፀጥታ የሰፈነበት ግቢ ነበር፡፡ ይህንን ለማድረግ ህገ መንግስታዊ መብት ነበረን፡፡ የአንድነት ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች የፖለቲካ ደንብና ፕሮግራማቸውን ለዞንና ለወረዳ አመራሮች ለማስጨበጥ ፈቃድ እንደማያስፈልግ ጠንቅቀን እናውቅም ነበር፡፡

በተለይም ሃለማሪያም ደሳለኝ በሞግዚትነት ወደ ስልጣን ከመጡ በኋላ ወላይታ ሶዶ ነፃነት አልባ ከተማ እንደሆነች ለማረጋገጥ ችለናል፡፡ ወላይታ በካድሬ ተወጥራለች፡፡ ዝርዝሩን በቀጣይ እንደምናቀርብ ቃል እየገባን ለአሁን በእኛ ላይ የደረሰውን በቅንጭቡ እንደሚከተለው ለኢትዮጵያ ህዝብና ለታሪክ እናቀርባለን፡፡

1. 32 የሚሆኑ አንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራሮች የተሰባሰቡት ከላይ በገለፅነው አላማና ህገ መንግስታዊ መብታችንን ተጠቅመን ቢሆንም ለውይይት ቅድመ ዝግጅት ስናደርግና ውይይቱን ለመጀመር ስንዘጋጅ መታወቂያ የሌላቸው ከ 8-10 የሚሆኑ ጡንቻቸው የፈረጠመ ግለሰቦች እንደ ኮማንዶ ለውይይት የተገናኝበትን የአባላችንን ጊቢ ሰብረው በመግባት የያዝናቸውን የፓርቲ ሰነዶች፣ ሳምሰንግ ጋላክሲ ስልኮችና ያገኙትን ሁሉ ዘርፈው ሂደዋል፤ አመራሮችን ደብድበዋል፡፡

2. እነዚሁ ደብዳቢዎች ታርጋ ቁጥር በሌላቸው ሞተሮች በመታጀብ ፖሊስ ይዘው በመምጣት ፕሮግራማችንን ለማደናቀፍ በሃይልና በጉልበት ወደ ፖሊስ ጣቢያ ወስደውናል፡፡
3. ፖሊስ ጣቢያውም እኛን የደበደቡንንና ንብረታችንን የቀሙንን ሲቢል ለባሽ ካድሬዎች በመልቀቅ የአንድነት ፓርቲ 20 አመራሮችን የወላይታ ሶዶ ከተማ ፖሊስ አዛዥ ሻለቃ ላሊሼ ኦሌ ቢሯቸው አስገብተው ችግሩን እንደሚቀርፍ አመራር ካነጋገሩንና ቃላችንን ከተቀበሉ በኋላ ሞባይሎቻችንን በመንጠቅ እንድንታሰር አድርገዋል፡፡
4. የእስሩ ሰዓት ከቀኑ 5፡00 ጀምሮ ነው፡፡ እንድ ቀፋፊና አስቀያሚ ማጎሪያ ውስጥ ካስቀመጡን በኋላ ከምሽቱ 2፡00 ላይ ህገወጥ ስብሰባ አድርጋችኋል በማለት ቃል ስጡ የሚል ምዝገባና ህገ ወጥ ስብሰባ እንዳደረግን እንድንመሰክር ለማስገደድ ቢሞክሩም እኛ መብታችንን እንደተጠቀምን እንጂ እነሱ እንደተረጎሙት ህገ ወጥ ስብሰባ እንዳላደረግን ሀቁን ስንነግራቸው እንዲሁም ሀሰትን ከመቀበል መታሰር እንደሚቻል የአንድነት አባላት ቁርጠኛ እንደሆንን ሲያውቁ ግራ ተጋብተው የበላይ አካል እስከሚያረጋግጥላቸው ጠብቀው ከእኩለ ለሊት በኋላ (ከምሽቱ 6፡30) በኋላ በእስር ላይ የቆዩ ከ20 በላይ ከፍተኛ አመራሮች እንዲወጡ ተደርጓል፡፡ ይሄ የሆነው ለመፍታት ታስቦ ሳይሆን ከወረዳ የመጡ አባላት ማደሪያ ቦታ እንዲያጡና ለአደጋ እንዲጋለጡ በማሰብ ነው፡፡

5. ስንታሰር ከተዘረፉ ሞባይሎች ውጭ በፖሊስ ጣቢያ አዛዡ ተይዞ የነበረው የታሳሪዎች ሞባይል ባልታወቀ ነገር ተነክሮ ከአገልግሎት ውጭ ተደርጓል፡፡ ሞባይላችን የተነከረውና ከጥቅም ውጭ የተደረገው በኬሚካል ይሁን በሌላ ነገር አልተረጋገጠም፡፡ የማንኛችንም ሞባይል ግን ከጥቅም ውጭ ሁኗል፡፡ ይሄ የሆነው የፖሊስ አዛዡ አቶ ላሊሼ ቢሮ የታሰረ ሞባይላችን ነው፡፡

ነገ ምን እንደሚገጥመን ማወቅ አይቻልም፡፡ ያረጋገጥነው ነገር ቢኖር ወላይታ ሶዶ ነፃነቷን የተነፈገች፣ በታርጋ አልባ ሞተሮች የምትታመስና ምንም ዋስትናና ህግ የሌለባት ከተማ መሆኗን ነው፡፡ ስለዚህ ነፃነት አልባዋ ወላይታ ነፃ መውጣት አለባት!!!

የአንድነት ፓርቲ የወላይታ ዞን አመራር አባላት ከምሽቱ 9፡00 ሠዓት

 

ሶዶ ከተማ

UDJ

በአዲስ አበባ አንድ አንበሳ አውቶቡስ 15 ሜትር ጥልቀት ካለው ድልድይ ገባ፤ 8 ሰዎች ሞቱ

$
0
0
ዘነበወርቅ ድልድልይ የገባው አውቶቡስ ሲወጣ

ዘነበወርቅ ድልድልይ የገባው አውቶቡስ ሲወጣ

(ዘ-ሐበሻ) በአዲስ አበባ ከተማ ከካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ የነበረ አውቶቡስ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊትለፊት ረዥም ድልድይ ውስጥ ገባ፤ በዚህ አሰቃቂ አደጋ ስምንት ሰዎች መሞታቸው ይፋ ሆነ።

አውቶቡሱ ቁጥራቸው እስካሁን በውል ያልታወቁ ተሳፋሪዎችን ጭኖ ይጓዝ የነበረ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ሲያስታውቅ የአውቶቡሱ ቁጥር 66 እንደሆነ ታውቋል።

ካራ ቆሬ ወደ ለገሃር ሲጓዝ ዘነበወርቅ አለርት ሆስፒታል ፊት ለፊት ባለው ረዥም ድልድይ ውስጥ በገባው አውቶቡስ የተነሳ በአደጋው እስካሁን አንድ እግረኛን ጨምሮ አራት ወንድ እና አራት ሴት ተሳፋሪዎች ህይወታቸው እንዳለፈ ሲገለጽ 46 የሚሆኑት ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ዘ-ሐበሻ ያገኘችው መረጃ ያመለክታል። የአውቶቡሱ ሹፌር እና ትኬት ቆራጭ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በሕይወት ተርፈዋል።

የአውቶቡሱ አደጋው መንስኤ ላይ መሆኑ ሲታወቅ በአውቶቡሱ ድልድይ ውስጥ መግባት ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖች በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸው መሆኑ ዘ-ሐበሻ ጨምሮ የደረሳት ዜና ያስረዳል።

ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ ጥያቄ አፈናና እሰራት ምላሽ አይሆንም! ከሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤትየወጣ የአቋም መግለጫ

$
0
0

መጋቢት 14/2006 ዓም አዲስ አበባ

የሰማያዊ ፓርቲ ብሄራዊ ምክር ቤት መጋቢት 14 ቀን 2006 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ ዓመት አራተኛ መደበኛ ስብሰባው የካቲት 30 ቀን 2006 ዓም የሴቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ በተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት ላይ ፖሊስና ፍርድ ቤት በመተባበር የፈጸሙትን ሕገ መንግስት የጣሰ ተግባር፣ እንዲሁም ከአሜሪካ መንግስት በደረሳቸው ግብዣ መጋቢት 12 ቀን 2006 ዓም ምሽት ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ቦሌ አውሮፕላን ማረፈያ በተገኙት የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ላይ ራሳቸውን ከህግ በላይ ያደረጉ የደህንነት ኋይሎች የፈጸሙትን አሳፋሪና ሕገ ወጥ ተግባር በመመርመር የሚከተለውን የአቋም መግለጫ አውጥቷል፡፡

  1. የሴቶችን ቀን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀው ሩጫ ላይ የተገኙ የሰማያዊ ፓርቲ ሴት አባላት በሩጫው ከተሳተፉ በሺዎች የሚቆጠሩ ሴቶች የሚለዩት የነጻነትን ቀን ሊያከብሩ በተገኙበት ቦታ ስለ ነጻነት፣ስለ ፍትህ፣ስለዴሞክራሲ፣ስለ ሰብአዊ መብት ወዘተ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው በማሰማታቸው ብቻ ነው፡፡ ነገር ግን በህገ መንግሥቱ አንቀጽ 29/2 «ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሀሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው» ተብሎ የተደነገገውን ከምንም ያልቆጠረውና ሕጉን ሳይሆን ጠመንጃውን ተማምኖ፣ የሙያውን ሥነ ምግባር ሳይሆን የአለቆቹን ትዕዛዝ አክብሮ እንደሚሰራ በተግባሩ ያረጋገጠው ፖሊስ እነዚህን የሰማያዊ ፓርቲ ሴት ወጣቶች አፍሶ ሲያስር አንዳችም ህጋዊ ምክንያት አልነበረውም፣ የፖሊስ ሕገ ወጥ ተግባር በዚህ ሳያቆም የታሰሩ የትግል አጋሮቻቸው የሚገኙበትን ቦታና ሁኔታ ለማወቅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ የሄዱ የፓርቲው አመራር አባላትንም አሰረ፡፡ ዋስትና ለማስከልከል አይደለም ለክስ የሚያበቃ ምንም ምክንያት ሳይኖረው ለፍ/ቤት ምርመራየን አልጨረስኩም የግዜ ቀጠሮ ይሰጠኝ በማለት አባላቱ ለአስር ቀናት በጣቢያ እስር እንዲጉላሉ በማድረግ ሕግን ለማስከበር ሳይሆን የፖለቲከኞችን ፍላጎት ለማስፈጸም የቆመ መሆኑን በተግባር አረጋግጠ፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህንን ሕገ መንግሥቱን በግልጽ የጣሰ የፖሊስ ተግባር በጽኑ እያወገዘ፣ፖሊስ የግለሰቦች ሥልጣን ጠባቂ ሳይሆን ሕግ አስከባሪ መሆኑን በተግባር እንዲያሳይ ይጠይቃል፡፡
  2. የሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 19/4 «የያዛቸው የፖሊስ መኮንን ወይም ህግ አስከባሪ በጊዜው ገደብ ፍርድ ቤት በማቅረብ የተያዙበትን ምክንያት ካላስረዳ ፍርድ ቤቱ የአካል ነጻነታቸውን እንዲያስከብርላቸው የመጠየቅ ሊጣስ የማይችል መብት አላቸው፡፡» ተብሎ የተደነገገውንእንዲያቀርቡ አዟል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምር ፍርድ ቤቱ ለህግ የበላይነት የሚሰራና  በመተላለፍ ታሳሪዎቹን የዋስትና መብት ከልክሎ ለሁለት ግዜ ለፖሊስ የግዜ ቀጠሮ የፈቀደው ፍርድ ቤት፣ የእኔ ሥልጣን አይደለም መደበኛ ፍርድ ቤት አቅርቡዋቸው በማለት ካሰናበት በኋላ የምርመራ መዝገቡ ለክስ አይበቃም ተብሎ በአቃቤ ሕግ ውድቅ የተደረገበት ፖሊስ መልሶ እዛው ፍርድ ቤት ሲያቀርባቸው እያንዳንዳቸው 1300 ብርና የሰው ዋስ በጣምራ ለፍትህ መከበር የቆመ አለመሆኑን በተግባር ያረጋገጠበትን ይህን ተግባር እያወገዘ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 79/2 «በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው» እንዲሁም በአንቀጽ 79/3 ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፣ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም »ተብሎ የተደነገገው በተግባር እንዲገለጽ አጥብቆ ይጠይቃል፡፡
  3. የፓርቲያችን ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ወደ አሜሪካ የሚያደርሳቸውን አስፈላጊ የጉዞ ሰነድ አሟልተው ሻንጣቸው አውሮፕላን ላይ ካስጫኑ በኋላ ፓስፖርታቸው በደህንንት ኋይሎች ተቀዶ ጉዞአቸው እንዲስተጓጎል ተደርጓል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ብሔራዊ ምክር ቤት ይህን ሕገ ወጥ ብቻ ሳይሆን እጅግ አሳፋሪ የሆነና የደህንነት ክፍሉን ብቻ ሳይሆን የአየር መንገዱንም ስም የሚያጎድፍ ተግባር በጽኑ እያወገዘ ድርጊቱን በፈጸሙት ማን አለብኝ ባዮች ላይ ከሕግ በላይ ሊሆኑ እንደማይችሉ የሚያሳይ ሕጋዊ ርምጃ አንዲወሰድ እንጠይቃለን፡፡ 4–መንግሥት ለዜጎች ዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄ እስራት አፈናና ማስፈራራት ምላሽ እንደማይሆን ከታሪክ በመማር ለዜጎች የመብት ጥያቄ ትክክለኛውን ምላሽ እንዲሰጥና ትግሉ ሰላማዊ፣ ዓላማው ሕዝባዊ ግቡ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን እውን ማድረግ ከሆነው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የጥፋት እጁን እንዲያነሳ አጥበቀን እንጠይቃለን ፡፡

ለማኝዋ ስትሞት አራት ሚሊየን ዶላር ተገኘባት

$
0
0

ክንፉ አሰፋ

አንዲት የተጎሳቆለች ወይዘሮ በሪያድ ጎዳናዎች ላይ ምጽዋት ትጠይቃለች። አላፊ አግዳሚው እቺን ወይዘሮ አይቶ አያልፋትም። ሰደቃ እየወረወረላት ያልፋል። በተለይ በበዓል ወራት ገቢዋ በእጥፍ ይጨምራል።

milw1አይሻ ትባላለች። ነዋሪነትዋ ሪያድ ሳውዲ አረቢያ ነው። ላለፉት 50 አመታት በልመና ስራ ስትተዳደር ቆይታ በተወለደች በ100 አመትዋ በያዝነው ሳምንት እሁድ እለት ከዚህ አለም በሞት ተለይታለች። አማሟቷም ድነገት ነበር ይላል አረብ ኒውስ።

ጉድና ጅራት ከወደኋላ ነው እንዲሉ የአይሻ ህልፈት አለምን ያስደመመ ጉድ ይዞ መጣ። ለሃምሳ አመታት በልመና የተሰማራችው ወይዘሮ ሚሊየነር ኖራለች። የወርቅ ጌጣጌጦች እና የጥሬ ገንዘብ ሃብትዋ አራት ሚሊየን ዶላር ሲሆን በጂዳ ከተማ የአራት ትላልቅ ህንጻዎች ባለቤትም ነበረች።

የአይሻን ንብረት የሚወርስ ዘመድ የለም። አብሮ አደግ ነኝ የሚል አህመድ አል ሰይድ የሚባል ሰው ግን የውርስ መብት አለኝ ብሏል። በእርግጥ አይሻ ሌላ ዘመድ የላትም። እህትና እናትዋ ለማኞች ነበሩ። ወላጆችም በልመና ይተዳደሩ የነበሩ መሆናቸውን የጠቀሰው የአረብ ኒውስ፣ አይሻ ንብረታቸውን በከፊል ከነሱ በውርስ እንዳገኙም ዘግቧል። አሁን ሁለቱም ሞተዋል።

አህመድ አል ሰይድ ንብረቱን “አይሻ ለኔ አውርሳኝ ሞታለች እኔም ተቀብዬ ለድሆች እንዳከፋፍል ይፈቀድልኝ” ብሎ ነበር። ከመንግስት ያገኘው ምላሽም ግን የለም።

ልመናውን እንድትተው ቢወተውታትም አሻፈረኝ ማለቷን ለመገናኘ ብዙሃን ገልጿል።

ሌላው የሚገርመው ነገር አይሻ ህንጻዋ የሚኖሩትን ሰዎች የቤት ኪራይ አታስከፍላቸውም ነበር።

millwm2አይሻ ሚሊየነር ነበረች። አንድ ቀን ጥሩ ምግብ ሳትበላ፣ ጥሩ መኝታ ላይ ሳትተኛ፣ ጥሩ ቤት ውስጥ ሳትኖር፣ ጥሩ ልብስ ሳትለብስ ኖራ ለዘላለሙ አሸለበች። ግን ይህ ለምን ሆነ የሚለው ጥያቄ ምላሽ አላገኘም።

አልፎ አልፎ የዚህ አይነት ክስተቶችን በአለም ላይ እናያለን። በሺዎች የሚቆጠሩ የኔብጤዎች ያሉባት ኢትዮጵያም በዚህ ስራ ከፍተኛ ሃብት እና ንብረት ያፈሩ ለማኞች አጋጥመውኛል።

እርግጥ የልመና ገንዘብ ስላልተለፋበት ይጣፍጥ ይሆናል። ልመናም እንደ አደንዛዥ እጽ ሱስ ያስይዝ ይሆን?

ድምፃዊ ጌድዮን ዳንኤል የጎዳና ተዳዳሪ ሆኗል፤ የሕዝብን እርዳታ ይሻል

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “ላጽናናሽ”፣ “በተራ” እና በሌሎችም በተሰኙት ሙዚቃዎቹ የሚታወቀውና 2 ሙሉ አልበም የሰራው ድምፃዊ ጌድዮን ዳንኤል በአዲስ አበባ የጎዳና ተዳዳሪ ለመሆን እንደተዳረገና እርዳታ እንደሚያስፈልገው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ዘገበ።

በአዲስ አበባ ታትሞ የሚሰራጨው አዲስ ጉዳይ መጽሔት ጓደኞቹን ጠቅሶ እንደዘገበው ድምፃዊው የአእምሮ ህመም ምልክቶች ከታዩበት ረዥም ጊዜ ሆኖታል። መጽሔቱ ያነጋገረው የድምጻዊው ጓደኛ “ጌድዮን ካልጠጣ ሰላማዊ ሰው ነው ከጠጣ ግን በጣም ኃይለኛና ሰውን የሚያስቸግር ሰው ነው” ሲል ይገልጸዋል። ሌሎች ደግሞ ድምጻዊው ሊያገኝ የሚገባውን የሳይካትሪስት ህክምና አለማግኘቱ ለዚህ እንዳበቃው ይናገራሉ”"

ጌድዮዎን በተለይ 2ኛ አልበሙን ካወጣ በኋላ ብዙም ተቀባይነት አለማግኘቱ ለዚህ የአእምሮ ችግር እንዳበቃው የሚገልጹ የቅርብ ወዳጆቹ አሉ። እንደ አዲስ ጉዳይ መጽሄት ከሆነ ይህ ወጣትና ጥሩ ብቃት ያለውን ድምጻዊ ሕይወት ለማስተካከል የሙያ አጋሮቹ፣ ማንኛውም ተቋም፣ እንዲሁም ግለሰቦች ሊተባበሩት ይገባል።

የጌድዮን 3 ሙዚቃዎችን እናስደምጣችሁ እና

ጊዜ የወጣለት ፌደራል 5 ህጻናትን አንበርክኮ ፎቶ ይነሳባቸዋል (ፎቶ)

$
0
0

“… ግን እስኪያልፍ ያለፋል” ያለው ማን ነበር? ተመልከቱ በአዲስ አበባ ጊዜ የወጣለት ፌደራል ፖሊስ 5 ህጻናትን አንበርክኮ ፎቶ ሲነሳባቸው።
federal


የሽረ ባጃጆች አድማ መቱ: መንግስትም አገደ

$
0
0

አብርሃ ደስታ ከመቀሌ

የሽረ እንዳስላሴ ከተማ ባለስልጣናት ከ450-500 የሚሆኑ የባጃጅ ሹፌሮች ሰብስበው ኩንትራት (ኮንትራክት) እየጫናቹ ነው፤ መንግስት የማይፈልገውን አገልግሎት እየሰጣቹ ነው በሚል ሰበብ ማስፈራራታቸው ተከትሎ የባጃጅ ሹፌሮች የስራ ማቆም አድማ በማድረግ ባጃጆቹ ከከተማ ዉጭ በማስቆም ተቃውሞአቸውን እየገለፁ ይገኛሉ። የመንግስት አካላትም አድማው ተከትሎ ባለባጃጆቹ መንግስት ባዘዛቸው መሰረት ለመስራት ፍቃደኛ ካልሆኑ ፍቃድ እንደማይሰጣቸው በመግለፅ እንዳይንቀሳቀሱ አግዷቸዋል። አሁን ባለባጃጆቹ አድማ ላይ ናቸው፤ መንግስትም አግዷቸዋል። በከተማው ምንም የባጃጅ እንቅስቃሴ አይታይም።
Abrha Desta
ብዙ የከተማው ኗሪዎች ታክሲ አጥተው በመንግስት አካላት ላይ ጫና በመፍጠራቸው ባለስልጣናቱ አምስት ሚኒባሶች ከመነሃርያ የታክሲ አገልግሎት እንዲሰጡ ቢያዙም ህዝቡ በቂ አገልግሎት ማግኘት አልቻለም። ባለ ባጃጆቹ መንግስት መፍትሔ ካልሰጣቸው ሰለማዊ ሰልፍ እንደሚወጡ ለዓረና ፅሕፈትቤት (የሽረ ከተማ ቢሮ) አስታውቀዋል። ከወር በፊት በመቐለ ከተማ ተመሳሳይ ችግር እንደነበር ይታወቃል።

በሌላ ዜና ዓረና ከሀገረሰላም ህዝብ ጋ ተወያየ።

ትናንት እሁድ (መጋቢት 14, 2006 ዓም) ዓረና ፓርቲ በደጉዓ ተምቤን ወረዳ ሀገረሰላም ከተማ ህዝባዊ ስብሰባ አካሂደዋል። ለእሁዱ ስብሰባ ቅዳሜ ቅስቀሳ የተደረገ ሲሆን የሀገረሰላም ህዝብ በጥሩ ሁኔታ ተቀብሎናል።

የህዝቡን ስሜት ያስደነገጣቸው ባለስልጣናት የከተማው ወጣቶች ሰብስበው በስድስት መኪኖች ጭነው ስልጠና አለ፣ ስራ ይሰጣችኋል፣ አበል ይሰጣችኋል ወዘተ በማለት ሕዋነ ወደሚባል ከተማ ሲያጓጉዟቸው አመሹ። ሌሊትም ቁጥራቸው በዉል ያልታወቁ ወጣቶች ሲጓጓዙ አደሩ። ቁጥራቸው ያልታወቀ ወጣቶችም ቅዳሜ ማታ በፖሊሶች እየታደኑ ታስረዋል፤ የዓረና ስብሰባ እስኪጠናንቀቅ ድረስ። ጥረቱ ግልፅ ነበር። ወጣቶቹ በዓረና ስብሰባ እንዳይሳተፉና በአባልነት እንዳይመዘገቡ ለማራቅ ነው፤ ዓረና ከወጣቶች ጋር እንዳይገናኝ ለማድረግ ነው። በብዙ አከባቢዎች በዓረና ስብሰባ የሚሳተፉ ወጣቶች ናቸውና።
ወጣቶቹ ከከተማ በመውጣታቸው ምክንያት የስብሰባው ተሳታፊ ብዙ አልነበረም። ነገር ግን ከብዙ የገጠር ጣብያዎች የተወከሉ አርሶአደሮች፣ መምህራንና የተመሪዎች ተወካዮች ነበሩ። እናም ስብሰባው የተሳካ ነበር ማለት ይቻላል።
አንዳንድ የህወሓት ካድሬዎች (የከተማው የካቢኔ አባላት) በዓረና አባላት ላይ ችግር ለመፍጠር ሞክረው ነበር። አልጋ እንዳንይዝ ባለሆቴሎችን ያስፈራሩ ነበር፣ በአንዳንድ አባሎቻችንም አክታ የመትፋትና የመሳደብ እንዲሁም ለመረበሽ ጥረት ሲያደርጉ ነበር። ግን እነዚህ ተግባራት የፈፀሙ የከተማው የካቢኔ ሐላፊዎች በተናጠል (በግል) የሰሩት እንጂ እንደ የዓዲግራቱ ቀውስ ሆን ተብሎ በፓርቲ ደረጃ የተፈፀመ አልነበረም። ምክንያቱም በሀገረሰላም ካድሬዎች ችግር ሲፈጥሩ ፖሊስ ያስቁመው ነበር። በዓዲግራት ግን ፖሊስ የችግሩ ተሳታፊ ነበረ።
እሁድ ጧት ስብሰባ የጠራንበት የከተማው ማዘጋጃቤት በፖሊሶችና ካድሬዎች ተከቦ ለስብሰባ የመጣ ህዝብ ለማስፈራራት ጥረት ተደርጓል። ብዙዎች እንዲመለሱ ተደርጓል። ባጠቃላይ የህወሓት ባለስልጣናት በዓረና አባላት ላይ ይፈፅሙት የነበረ ግፍ ወደ ተሰብሳቢው ህዝብ አሸጋግረውታል።
አሁን ጥቃት የሚፈፀመው በዓረናዎች ሳይሆን ጥያቄ በሚያነሳና በዓረና ስብሰባ ለመሳተፍ ፍላጎት ባለው ሰለማዊ ህዝብ ላይ ነው። የህዝብ የመሰብሰብ መብት እየጣሱ ነው ማለት ነው። የደጉዓ ተምቤን ህዝብ ለውጥ እንደሚፈልግ አረጋግጦልናል።

Hiber Radio: “ቦሌ ኤርፖርት ፓስትፖርቴን የሰጠሁት ሰራተኛ አለቃዬን ላነጋግር ብሎ ገብቶ የፓስፖርቴን አንድ ገጽ ቀዶ በመጣል አንድ ገጽ ጎሎታል አለኝ፤ ቀረሁ”–ኢንጂነር ይልቃል

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

የህብር ሬዲዮ መጋቢት 14 ቀን 2006 ፕሮግራም

<<...አሜሪካ ለመምጣት ቦሌ ፓስፖርቴን የሰጠሁት የኢሚግሬሽን ሰራተኛ ቆይ አለቃዬን አነጋግሬ ልምጣ ብሎ ወደ ሌላ ቢሮ ገብቶ ተመልሼ ሲመጣ ፓስፖርትህ አንድ ገጽ ጎሎታል አለኝ። አንድ ገጽ ቀዶለት ነበር የመጣው። ድርጊቱ ከአገር እንዳልወጣ የተደረገ ነው ..አገሪቱም እነሱም ምን ያህል የወረደ ደረጃ ላይ እንዳሉ የሚያሳይ አሳፋሪም አስቂኝም ድራማ ነበር.. .>>

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር ወደ አሜሪካ እንዳይመጡ ስለታገዱበት ሁኔታ ለህብር ከሰጡት ማብራሪያ የተወሰደ

<<...ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት በኩዌት ያሉ ወገኖቻችን ያሉበትን ሁኔታ በተመለከተ ማጣራት እያደረግን ለኩዌት መንግስትም በየኤምባሲያቸው በኩል በኢትዮጵአውያን ላይ በኩዌት ሚዲያ የሚደረገውን ቅስቀሳ ተከትሌ የጥቃት ሰለባ እንዳይሆን መብታቸው ተጠብቆ አገራቸው የሚሄዱትም እንዲሄዱ እንቅስቃሴ ጀምረናል። ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችንም ስለ ጉዳዩ እናሳውቃለን...>>

ወ/ት ሜሮን አሀዱ የዓለም አቀፉ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት ተቆርቋሪ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ በኩዌት ስላሉ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ከህብር ጋር ካደረገችው ቆይታ

ደብዛው የጠፋው የማሌዢያ አየር መንገድ ጉዳይ እና ያልተሳካው ፍለጋ እስከምን ይዘልቃል (ልዩ ዘገባ)

በቬጋስ ለስራ ማቆም አድማ ወጥቶ ሕይወቱ ስላለፈው የታክሲ አሽከርካሪ መታሰቢያና የተቃውሞው ተሳታፊዎች የወደፊት እርምጃ ውይይት

ሌሎችም ዝግጅቶች

ዜናዎቻችን

* በኦጋዴን የልማትና የኢኮኖሚ ጥያቄ ያቀረቡ የአገር ሽማግሌዎች መታሰር በአካባቢው ውጥረትና ስጋት ማስነሳቱ ተነገረ

* የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ቦሌ ላይ በድንገት ከፓስፖርታቸው አንድ ገጽ ተቀዶ ወደ አሜሪካ እንዳይወጡ የታገዱበት ሂደት አስገራሚ ድራማ ነበር አሉት

* በወላይታ ተደብድበው የታሰሩት የአንድነት ፓርቲ አመራሮች ትላንት ተለቀቁ

- የተነጠቁት ሞባይላቸው ባልታወቀ ነገር ተነክሮ እንዲበላሽ ተደርጓል

* አሜሪካ ከኢትዮጵያ የምትወስዳቸው የማደጎ ህጻናት ቁጥር ማሽቆልቆሉ ተገለጸ

* በአዲስ አበባ ተሳፋሪዎችን የጫነ አንበሳ አውቶብስ ድልድይ ውስጥ ገብቶ የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት አለፈ

* ኤርትራ በጥቂት ቀናት ውስጥ ሶስት ጄኔራሎቿን በሞት አጣች

* የአስመራው መንግስት ኢትዮጵያ አዲስ የዲፕሎማሲ ዘመቻ ከፍታብኛለች አለ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

የሒሳብ አያያዝ ባለሞያ የለም ወይ ባገሩ? (በለንደን ለምትገኝ ደብረ ጽዮን ቤተ ክርስቲያን አባላት)

የአንዱአለም አራጌ ቀን በዋሺንግቶን ዲሲ ከተማ

ከምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ የተፈናቀሉ ገበሬዎች አዲስ አበባ ገቡ፤ “ብንመለስ ሊገድሉን ይችላሉ”

$
0
0

geberewoch ethiopia
ከዳዊት ሰለሞን

ተፈናቃዩቹ ከጎንደር አካባቢ ተነስተው ከዛሬ 20 ዓመት በፊት ወደ ምዕራብ ሸዋ ዞን አምቦ ዳኖ ወረዳ በመውረድ በእርሻ ስራ የተሰማሩ ገበሬዎች ናቸው፡፡ከ1996ዓ.ም ጀምሮ በተለያየ ደረጃ ‹‹ክልላችንን ለቅቃችሁ ውጡ››ሲባሉ ቆይተዋል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ማስፈራሪያው ወደ ግድያ፣ድብደባና ወከባ በማደጉ ለአቤቱታ አካባቢያቸውን ጥለው አዲስ አበባ ለመግባት ተገደዋል፡፡ከተፈናቃዩቹ መካከል የተወሰኑት ወደ ፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አቶ ካሳ ተ/ብርሃን ጽ/ቤት በማምራት አፈ ጉባኤውን ለማናገር ቢሞክሩም ሊያገኟቸው አልቻሉም፡፡የአፈ ጉባኤው ጸሐፊ ጉዳያችሁ ታይቷል ወደ መጣችሁበት ተመለሱ››ያለቻቸው ቢሆንም ተፈናቃዩቹ ‹‹ብንመለስ ሊገድሉን ስለሚችሉ አንመለስም››የሚል አቋም ይዘዋል፡፡

ከ26 የሚልቁ ሰዎች በአደባባይ ድብደባ ደርሶባቸው እጅና እግራቸው እንደተሰበረ የሚናገሩት ተፈናቃዩቹ‹‹አቶ ጌጡ ክብረት የተባለ ግለሰብ በገበያ ቦታ በገጀራ ተቆራርጦ ህይወቱ ማለፉን በሀዘን ስሜት ተውጠው ይናገራሉ፡፡ በአዲስ አበባ ማረፊያ ባለማግኘታቸው ለችግር መጋለጣቸውን የሚገልጹት ተፈናቃዩቹ ወደ አንድነት ለዴሞክራሲና ለፍትህ ጽ/ቤት በመምጣት ‹‹ፍትህ እንድናገኝ ለኢትዩጵያ ህዝብ ሰቆቃችንን አሰሙልን››በማለት ተማጽነዋል፡፡

የአንድነት ፓርቲ ዋና ጸሐፊ አቶ ስዩም መንገሻ ‹‹ህገ መንግስቱ በግልጽ እያንዳንዱ ዜጋ በፈለገው ክልል በመሄድ ንብረት ማፍራት እንደሚችል ቢደነግግም መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን ህገ ወጥና አስቸጋሪ ነው››ብለዋል፡፡

[የመልካም አስተዳደር እጦት በወሎ] የዘረፈ፣ እግር የቆረጠ፣ ሕዝብን በጥይት እየገደለ ያለ ስልጣን ላይ ሆኖ ይንደላቀቃል

$
0
0

(የሰሜን ወሎ ሕዝብ በገበያ ላይ - ፎቶ ፋይል)

(የሰሜን ወሎ ሕዝብ በገበያ ላይ – ፎቶ ፋይል)


ለዘ-ሐበሻ ድረ ገጽ አዘጋጆች
ክቡር ሰላምታየ ይድረሳችሁ

ከዚህ በመቀጠል የዘወትር የፕሮግራምችሁ ተከታታይ ስሆን ይህን የመልካም አስተዳደር ችግር አየር ላይ እንድታውሉልኝ እየጠየኩ እን ሁልግዜው ለሁሉም የምታቀርቡትን አስተያየት ሙያችሁ በሚፈቅደው መሠረት እንደምታቀርቡልኝ ወይም አየር ላይ እንደምታውሉልኝ በመተማመን ነው፡፡
በሰሜን ወሎና ዞን በሀብሩ ወረዳና በመርሳ ከተማ እንደማንኛውም የኢትዮጵያ አካባባቢ በየግዜው የሚስተዋሉት የመልካም አስተዳደርና የሙስና ችግሮች ነዋሪውን የከተማና የገጠር ህዝብ እግር ተወርች ሰቅለው ይዘውታል፡፡ ለየት የሚያደርገው ነገር ቢኖር ከመንግስት ደቀመዛሙርት መሰል ሚዲያዎች የምንተነፍስበት ወይም ሃሳባችንን የምንገልፅበት አማራጭ አለመኖሩ ነው፡፡ ይህም የናንተ የዘገባ አድማስ ሁሉንም አካባቢዎች የሚሸፍን አለመሆኑ ይመስለኛል ፡፡

ከዚህ በተረፈ ጉዳዩ አዲስና ልዩ ባይሆንም ድግግሞሽና አንደኛው ከሌለኛው ሲነፃፀር በጣም የከፋ እየሆነ በመምጣቱ ነው፡፡ በዚህም ምክንያት አቤቱታው በምድር ላይ ያሉት ቱባ ባለስልጣኖች ጆሮ ነፊውን በየእምነቱ በፈጣሪው መፀለይ እና አቤት ለማለት ተገዷል እናም የናንተ የአቀራረብ ብስለት ታክሎበት መልዕክቱን ለአየር ታውሉልኛላችሁ ብዩ ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡
መቸም የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ሲነሳ ተነግሮ አያልቅም ነገር ግን ቀደም የተፈፀመው በደል ላያንሰው አዳዲስና ከፀሐይ ጋር አብረው ብቅ የሚሉት የትም የለሉ ቢሆንም የቅርቡን ለመግለፅ ያህል
1. በመርሣ ከተማ አስተዳደር ነዋሪ የሆኑ 35 /ሰላሳ አምስት/ መንጃ ፈቃድ ያላቸው ነዋሪዎች በአማራ ክልል በቅርቡ እንዳያወጡ በመከልከላቸውና

ሙስና የበዛበት አሰራር ስላለ ወደ ተሻለውና አገሪቱን በበላይነት ወደ ሚመራው ክልል 1 ህዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ በመሄድ መንጃ ፈቃድ አውጥተው አሁን በከተማው የትግራይ ክልል መንጃ ፈቃድ አማራ ክልል ላይ አይሰራም በማለት ታግደዋል ፡፡ ክልሉ በማንና በምን እንደሚመራ ካለመታወቁም በላይ የወያኔን መሪነት ብአዴን መካዱ ይሆን ወይስ በአንድ አገር ሁለት ዓይነት ህግ መኖሩ ነው መልስ ያጣ ጉዳይ ሆኗል፡፡

2. በዚሁ በመርሣ ከተማ ዙሪያዋን በሚገኙ ወደ ከተማ የተከለሉ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ አራሽ ገበሬ ለፍቶና ጥሮ ለአመታት ጥሪቱን በሚያስጨርስ ሁኔታ የሰራውን ቤት ለምሳሌ አቧሬ አካባቢ የአቶ ሙመድ ሰይድ ቤት 8X9 የሆነ ቤት አገልግሎት በማይሰጥ መልኩ አፍርሰው ወደ ሌሎች መሰል ግለሰቦች ሲገቡ ነዋሪው ህዝብ በነቂስ ወጥቶ ባለስልጣኖቹን በመፈታተኑ እንዲባረሩ አድርጓቸዋል፡፡ በሌላ በኩል በ25/6/2006 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 /አራት ሰዓት ተኩል / አካባቢ በዚሁ ከተማ ልዩ ቦታው መልካጨፌ ከተባለው አካባቢ የ8 /ስምንት/ ሰው አርሶ አደር ቤት አፍርሰው ወደቀጣዩ ሲሸጋገሩ ጉዳዩ ያበሳጨው ነዋሪ ህዝብ ከአንድ መቶ በላይ የሚቆጠር ፖሊስ ፣ሚሊሻ አመራር በመሆን ህዝቡ በአመፅ በመነሳት ከሃምሳ በላይ ጥይት ተተኩሶ ሁለት ግለሰብ አርሶ አደሮች የህዝብ ተወካይ ነን በሚሉ ታጣቂዎች ተመትተው ቆስለው ህክምና ላይ ሲገኙ የጣፋው ጠፍቶ ቀሪውን በትግል ማዳን ችሏል ይሁንና መብቱን መገፋቱ ሳያንሰው ብሎም በቤት ውስጥ የነበሩ መንታ የወለደች ሴት ሜዳላይ እንድትወድቅ ተደርጓል ድርጊቱን ለምን ተከላከላችሁ ተብለው ሁከት ፈጣሪ በመባል ማረሚያ ቤት ገብተው ይገኛሉ ፡፡ ቀሪዎቹ ነዋሪዎች የተተኮሰውን ጥይት ዋጋ እንዲከፍሉ ተጠይቀዋል፡፡ ይህ የህዝብ ወገናዊነት ወይስ ምን ይሉታል ?

3. የህዝብን ሀብትና ንብረት ስልጣናቸውን ተጠቅመው የከበሩ የወረዳ አመራሮች ከመጠየቅ ይልቅ ወደ ፓርላማ እንዲገቡ ለከፍተኛ ትምህረት ተቋም ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ መሬት በሽልማት የሚሰጥበት ለህገ-መንግስቱ መሬት መሸጥ መለወጥ ላሳር የተባለበትን ለካቢኔ በሽልማት የሚሰጥበትን ሁኔታ ሲኖር ከዚህ እንደሚቀጥለው ይሆናል

ለአብነት ያክል፡-
• የቁጥር 27 ቀበሌን የገበሬውን መሬት የሸጡ ወይም እንዲሸጥ በቃለ ጉባዔ የያዙ የከፍተኛ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ ሲበረታቱ የቀበሌው አስተዳዳሪ ግን በ9/ዘጠኝ/ አይነት ክስ ተከሶ ማረሚያ ቤት ይገኛል

• በተጨማሪ11/አስራ አንድ ቤት /ያቃጠለ የአንድ ሰው እግር የቆረጠ ይባስ ብሎ በዚሁ ድርጊቱ ሳይበቃው ከሌላ የካቢኔ ጓደኛው ጋር በመሆን በሽጉጥ ከስደት ተመላሽ የሆነን ግለሰብ በሴት ምክንያት ጠግቦ አደሮች እጁ ላይ ተመትቶ በሆስፒታል በመረዳት ላይ ሲገኝ ይህ ሳያንስ ቤተሰቦቹ ተለቅመው እንዲታሰሩ ተደርጎ ሲቀጡ ጉዳዩን የፈፀሙት ባለስልጣኖች እድሜ ለስልጣን ብለው ሌላውን ባለተራ የጥይት ማረፊያቸውን ይጠብቃሉ።

4. የወረዳው አመራር /የሀብሩ ወረዳ ማለቴ/ ነው ከክልል በመጣ የኦዲት ባለሙያ በተረጋገጠው መሠረት አንድ አመራር ከ44 – 75 ሽህ ብር ከ365 ቀን በላይ በውሎ አበልና መሰል የወጭ ዘዴ ተጠቅሞ ከህግ ውጭ ማድረጋቸው ስለተረጋገጠ የክልሉ ኦዲተር ሪፖርት ቀርቦ እያለ እስካሁን ድረስ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው የሚባለውን በነሱ ላይ ስለማይሰራ በፍታብሄርም ሆነ በወንጀል እንዳይጠይቁ ጠያቂና ተጠያቂ ጠፍቶ የአገር ሀብት ባክኖ ቀርቷል፡፡ አቤት የሚባልበት ቦታ ጠፍቷል ፡፡

5. ከዚህ በላይ የተዘረዘሩት ጉዳዮች ማለትም የገጠር ወረዳውና የከተማ አስተዳደሩ የሚፈፅማቸውን አላግባብ የሆኑ አሰራሮች መከታተልና መቆጣጠር የተፈፀመውንም ሆነ ችግሮች እንዳይፈፀሙ መከላከል ሲገባቸው ይባስ ብለው የወረዳው ፍ/ቤት ሰብሳቢ ዳኛ ከዳኝነት ነፃ የሆነው እንኳ ሳይቀር የፍትህ ጽ/ቤት ኃላፊ ካቢኔ ተብየው እነዚህ አመራሮችና ሙሰኞች በህግ እንዳይጠየቁ ምርመራ ሲጀመር ከዞን ጀምሮ ምርመራ እንዲቋረጥ እየተደረገ የዳኝነት ነፃነት በሚጋፋ መልኩ በህግ ፊት ሁሉም ሰው እኩል ነው ተብሎ በህገ-መንግስቱ አንቀጽ 25 ላይ በግልፅነት ተቀምጦ እያለ ለአመራር /ተሿሚ / ህጉ የማይሰራበት ለሌች ዜጎች ግን ተተንትኖና ተዘርዝሮ የሚሰራበት ወረዳ በመሆኑ ህግ አልባነት ወይስ ህግ የተላበሰ አሰራር ይህን ሁሉም መልሶ አጥቶበታል።

በአጠቃላይ በከተማችንና በወረዳችን ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር የሰዎች ሰብዓዊ መብት አለመከበር ድብደባ ዛቻና ማስፈራራት በመጠቀም ስልጣናቸውን ለማራዘም ከላይ ታች የሚባዝኑ ስለሆነ ለሀገርም ሆነ ለህዝብ የማይጠቅም በመሆኑ ይህነን አስነዋሪ የ21ኛው ክፍለ ዘመን የማይመጥንና የማይገልጽ ነውር ተግባር በህዝቡ ስምና በራሴ ስም ለአየር ይበቃ ዘንድ መልካም ትብብራችሁን ከአክብሮት ጋር እንደማትነፍጉኝ በመተማመን አቀርባለሁ፡፡
የዘወትር አንባቢያችሁ ይነበብ ታምሩ
ከመርሳ ከተማ

ጉለቶቹን ለማጣራት ካስፈለገ ስልክ የከተማ አስተዳደሩ
ከንቲባ ስልክ 0921522287
የገጠር ወረዳ አስትዳደር ስልክ 0333330007(49)
የገጠር ፖሊስ ስልክ 03333300022(21) ክፋታቸው ካልበረታ ማገኘት ይቻላል፡፡

መታመን በቀድሞ ነው !! (ዳንኤል ፍቅሬ)

$
0
0

ዳንኤል ፍቅሬ

የሰሞኑ የኪዌት ጉዳይ ሁላችንንም እያነጋገረ ያለ ጉዳይ ነው በተለይ በቅርቡ ከሳውዲ አረብያ የችግር ትኩሳት ትንሽ መብረድ ጋር ተያይዞ  በኪዌት የባለ ስልጣን ልጅ መገደል የወገኔን ችግር   ያብስዋል ብዬ  ነገሩን ትኩረት ሰጥቸው  እየተከታተልኩ ነው :: በጣም ትኩረቴን የሳበው እና የታዘብኩተ  የኪዌት የፓርላማ አባላት ተወያይተው የወሰኑት ጉዳይ ነው ::

The lawmaker stressed the need to oblige housemaids to undergo tests regularly to ensure they are not suffering from any psychological illness. 

.የቤት ውስጥ ሰራተኞች ቅጥር ውደ ኪዌት ሲመጡ የአምሮአቸው ሁኔታ ይጠና ማለታቸው ትክክል ቢሆንም እኔ ግን በትዝብት እና በግርምት ነው የተመለከትኩተ :: ምነው ስንቱን ወገኖቻችንን ሲገድሉ ሲያርዱ ሲያንገላቱ የነሱን የራሳቸውን  አእምሮ ሁኔታ አለማጤናቸው ?? እውነት ትክክል የሆነና ያልሆነ  ነገር ለካ እንደ ሃገሩ ይለያያል እነሱ ሲፈጽሙት እና እኛ ስንፈጽመው የሚሰጠን ስያሜ ለየቅል ነው ለካ :: በአረቡ አለም ስንት ህሊናን የሚያስትና እሚያንገፈገፍ ዘግናኝ ግፍ ተፈፅሞብን እንዳለፈ ቤቱ ይቁጠረው እውነቱን ነው ትልቁ መጽሓፍ ያለው ” በራስክ ውስጥ ያለውን ትልቁን ምስሶ የሚአክል ጉድፍ እያለ የወንድምክን ትንሽዋን የአይን ጉድፍ ላውጣ ማለቱ …………” የሚለው  የሚስማማቸው ይመስለኛል::

            ያገራችን  መንገስትም ለአንድ ዜጋው የሚሰጠው  ክበር ሰለሌለ የሚከፍለው ዋጋ የዛኑ ያህል የከፋ ነው:: አንድ ዜጋ በሚፈጥረው ችግር ህብረተሰበን ብሎም አገርን እንደሚጎዳ በቅጡ የተገነዘበው አልመሰለኝም እኔ ሳስበው ችግሩ ሁላችንንም ያካትታል በተለይ መንግስትን!!! ” ምቼም መንግስት የሚታመነው በባለፈው ስራው ነው” በተለይ አረብ አገር ባሉ ዜጎቻችን ላይ ሲበደሉ  ሲገደሉ መሬት ለመሬት ሲጎትቱአቸው አሁን ያለው መንግስት ለወገኑ ጥብቅና ሲቆም ሲታገልላቸው መብታቸውን ለማስከበር ደፋ ቀና ሲል አላየንም ከነሱ ጋረ ሆኖ በችግራችን ላይ ችግር ሲጨምርብን እንጂ !!  በየሃገሩ ተበትነው ያሉ ዜጎቻችን አለሁ የሚል  መንግስት ወገን ከሌለ ምኑን መንግስት ሆነልን!!  አገር ውሰጥም ተገብቶ ጭቆናወና ችግሩ እየቀጠለ የሚሄድ ከሆነ አሁንም እንዳየነው ፍልሰቱ መቀጠሉ የማይቀር ነው :: በቅርቡ ከሳውዲ የተመለሱት ወዳገራቸው ገብተው በያቅጣጫው ወደ ውጭ  የተበተኑት ይሄ ያደባባይ ሚስጥር ነው :: እና ለዚች ወገናችን  ከተብደለችው አንጻር ፍርድዋ እንዲቀልላት በጎ አደራጊ ደረጅቶች ወይ ገለሰብ እንድረስላት ::

 


ሁለተኛውን ዙር የሚሊየኖች ድምጽ እንቅስቃሴን በመደገፍ: ላስ ቬጋስ የአዲስ አበባዉን – አትላንታዎች አዋሳን -ዴንቨሮች ደሴን –ቃሌ እና ደብተራው ቁጫንና ድሬደዋን ስፖንሰር አደረጉ !

$
0
0

ሚሊየነች ድምጽ – ላስ ቬጋስ የአዲስ አበባዉን የመጀመሪያ ስብሰባ ስፖንሰር አደረገች!

የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በአገሪቷ ዉስጥ ባሉ አሥራ ሰባት ከተሞች፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ ስብሰባ በማድረግ የሚጀመር ሲሆን፣ በሌሎች ከተሞች ከአንድነት ጽ/ቤቶች ወደ አደባባይ በሚሄድ ትይንተ ሕዝቦች ይደረጋሉ።Las Vegas1

ላስ ቬጋስ፣ ኔቫዳ፣ ከአዲስ አበባ ጋራ ሶሊዳሪቲ በመመሰረት ፣ በዚያ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን፣ በአዲስ አበባ ለሚደረገዉ ሕዝባዊ ስብስበ የሚያስፈልገውን ወጭ ሙሉ ለሙሉ ለመሸፈን የተዘጋጁ ሲሆን፣ «ከሚሊዮኖች አንዱ ነን» እያሉም ነው።

ይህ የሚሊየነሞች እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው።

በዳያስፖራ የሚሊየነሞች ግብረ ኃይል፣ በላስ ቬጋስ ያሉ ኢትዮጵያዉን ላሳዩት አኩሪና ኢትዮጵያዊ እንቅስቃሴ ያለዉን አድናቆት እየገለጸ፣ በሌሎች ከተሞችም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸውን እያደራጁ ፣ አገር ቤት ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ካለው ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ፣ ትግሉን እንዲቀላቀሉና ከሚሊዮኖች አንዱ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል።

በምትኖሩበት ከተማ ተደራጅታችሁ፣ ከዚህ ግብረ ኃይል ጋር በመስራት በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ፣ በሚከተሉት አድራሻ ሊያገኙን ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

millionsforethiopia@gmail.com
404- 518-7858

 

የሚሊዮኖች ድምጽ – አትላንታዎች ከአዋሳ ጎን በመቆም የሚሊዮኖች አንዱ ሆኑ !

የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በአገሪቷ ዉስጥ ባሉ አሥራ ሰባት ከተሞች፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ ስብሰባ በማድረግ የሚጀመር ሲሆን፣ በሌሎች ከተሞች ከአንድነት ጽ/ቤቶች ወደ አደባባይ በሚሄድ ትይንተ ሕዝቦች ይደረጋሉ።

አትላንታ ጆርጂያ ከአዋሳ ከተማ ጋር ሶሊዳሪቲ በመመሰረት ፣ በአዋሳ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በሚሊዮኖች ድምጽ ዘመቻ በከተማቸው ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን ወጭ ሙሉ ለሙሉ ለመሸፈን የተዘጋጁ ሲሆን፣ አትላንታዎች  «ከሚሊዮኖች አንዱ ነን» እያሉ ነው።

Atlantaይህ የሚሊየነሞች እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው።

በዳያስፖራ የሚሊየነሞች ግብረ ኃይል፣ በአትላንታ ያሉ ኢትዮጵያዉን ላሳዩት አኩሪና ኢትዮጵያዊ እንቅስቃሴ ያለዉን አድናቆት እየገለጸ፣ በሌሎች ከተሞችም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸውን እያደራጁ ፣ አገር ቤት ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ካለው ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ፣ ትግሉን እንዲቀላቀሉና ከሚሊዮኖች አንዱ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል።

እስካሁን የላስ ቬጋስ ኢትዮጵያዉያን የመጀመሪያዉን የአዲስ አበባ እንቅስቃሴ፣ የቃሌ ፓልቶክ ክልፍ በደቩብ ክልል ቁጫ የሚደረገዉ እንቅስቃሴ፣ የደብተራዉ ፓልቶክ ክፍል ደግሞ አንጋፋዋን ድሬዳዋ ስፖንሰር እንደሚያደርጉ ማሳወቃችን ይታወሳል።

በምትኖሩበት ከተማ ተደራጅታችሁ፣ ከዚህ ግብረ ኃይል ጋር በመስራት በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ፣ በሚከተሉት አድራሻ ሊያገኙን ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

millionsforethiopia@gmail.com

404- 518-7858

 

 

የሚሊዮኖች ድምጽ – ዴንቨሮች ከደሴ ጎን በመቆም የሚሊዮኖች አንዱ ሆኑ !

የሚሊዮኖች ድምጽ ንቅናቄ በአገሪቷ ዉስጥ ባሉ አሥራ ሰባት ከተሞች፣ ሕዝባዊ እንቅስቃሴዎች እንደሚያደርግ ይፋ ማድረጉ ይታወቃል። እንቅስቃሴ በአዲስ አበባ ሕዝባዊ ስብሰባ በማድረግ የሚጀመር ሲሆን፣ በሌሎች ከተሞች ከአንድነት ጽ/ቤቶች ወደ አደባባይ በሚሄድ ትይንተ ሕዝቦች ይደረጋሉ።

Denverዴንቨር ኮሎራዶ ከደሴ ከተማ ጋር ሶሊዳሪቲ በመመሰረት ፣ በደሴ የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በሚሊዮኖች ድምጽ ዘመቻ በከተማቸው ለሚያደርጉት እንቅስቃሴ የሚያስፈልገውን ወጭ ሙሉ ለሙሉ ለመሸፈን የተዘጋጁ ሲሆን፣ አትላንታዎች  «ከሚሊዮኖች አንዱ ነን» እያሉ ነው።

ይህ የሚሊየነሞች እንቅስቃሴ የአንድ ፓርቲ እንቅሳቅሴ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንቅስቃሴ እንደመሆኑ፣ በአገራችን ዴሞክራሲና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ የሚፈልጉ ዜጎች ሁሉ ሊቀላቀሉት፣ ሊደግፉት፣ የራሳቸው ሊያደርጉት የሚገባ እንቅስቃሴ ነዉ። ይህ እንቅስቃሴ የሚሊዮኖች እንቅስቃሴ ነው። የእያንዳንዳችን እንቅስቃሴ ነው።

በዳያስፖራ የሚሊየነሞች ግብረ ኃይል፣ በዴንቨር ያሉ ኢትዮጵያዉን ላሳዩት አኩሪና ኢትዮጵያዊ እንቅስቃሴ ያለዉን አድናቆት እየገለጸ፣ በሌሎች ከተሞችም የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን እራሳቸውን እያደራጁ ፣ አገር ቤት ከፍተኛ መስዋእትነት እየከፈለ ካለው ሕዝብ ጎን እንዲቆሙ፣ ትግሉን እንዲቀላቀሉና ከሚሊዮኖች አንዱ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል።

እስካሁን የላስ ቬጋስ ኢትዮጵያዉያን የመጀመሪያዉን የአዲስ አበባ እንቅስቃሴ ስፖንሰር ያደረጉ ሲሆን፣ የአትላንታ ኢትዮጵያዉያን በአዋሳ፣ የቃሌ ፓልቶክ ክልፍ በደብብ ክልል ቁጫ፣ የደብተራዉ ፓልቶክ ክፍል ደግሞ በአንጋፋዋ በድሬዳዋ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ስፖንሰር እንደሚያደርጉ ማሳወቃችን ይታወሳል።

በምትኖሩበት ከተማ ተደራጅታችሁ፣ ከዚህ ግብረ ኃይል ጋር በመስራት በአገር ቤት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን ስፖንሰር ማድረግ የምትፈልጉ፣ በሚከተሉት አድራሻ ሊያገኙን ይችላሉ።

 

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

millionsforethiopia@gmail.com

404- 518-7858

 

 

የሚሊዮኖች ድምጽ – ቃሌ እና ደብተራው ቁጫንና ድሬደዋን ስፖንሰር አደረጉ !

በደቡብ ክልል፣ በጋሙ ጎፋ ዞን የምትገኝ ወረዳ ናት። ወደ 150 ሺህ የሚጠጋ ነዋሪ አላት። በዚያ ያሉ ገበሬዎች ከሚያርሱበት ቦታ በግድ እንዲፈናቀሉ ከመደረጉ በተጨማሪ፣ ብዙዎች ያታሰሩባት ወረዳ ናት። የቁጭ ወረዳ ትባላለች።

dire_kucha-1በአንድነት ፓርቲ አነሳሽነት ለሕዝብ የፋ የሆነው የሚሊዮኖች ድምጽ ለመሬት ባለቤትነት ትኩረት ከሰጠባቸው ወደ አሥራ የሚሆኑ አካባቢዎች አንዷ ቁጫ ናት። በቁጫ ሊደረግ የታሰበዉን ትእይነተ ሕዝብ በመደገፍ፣ በዚያም ለሚኖረው የተገፋዉ ሕዝብ ሶሊዳሪቲ በማሳየት የቃሌ ፓልቶክ ክፍል ፣ የቁጫን እንቅስቃሴ ሙሉ ለሙሉ እንደሚሸፍን እና ስፖንሰር እንደሚያደርግ ይፋ አደርጓል።
ሌላዋ የሚሊይን ድምጽ ዘመቻ የሚደረግባት ከተማ፣ የኢትዮዮጵያ ሁለተኛ ከተማ የሆነችዋ አንጋፋዉ ድሬዳዋ ናት። የደብተራዉ ፓል ቶክ ክፍል ፣ ድረደዋን ስፖንሰር እንደሚያደርግም ለማወቅ ተችሏል።

የቃሌ እና የደብተራዉ ፓል ቶክ ክፍሎች ከአለም ዙሪያ ሁሉ የተሰባሰቡ ፣ በኢንተርኔት ፓልቶክ አፕሊኬሽን ፣ በአገራቸው ጉዳይ ላይ ዘወተር የሚመካከሩ፣ የአገራቸው ጉዳይ የሚያስጨንቃቸው ኢትዮጵያዊያን የተሰባሰቡበት ክፍሎች ነው።

በኢትዮጵያ የሚደረገዉ ሰላማዊ ትግል፣ ስለተመኘንና ስላወራን ብቻ ዉጤት የሚያመጣ አይደለም። አገዛዙ ዘወትር ስለሚፈጽማቸው ግፎች ማዉራት አንድ ነገር ነው። እነዚህ ግፎች እንዲያቆሙና የስርዓት ለዉጥ እንዲመጣ ማድረግ ሌላ ነገር ነው።

የቃሌና የደብተራው ታዳሚዎች ፣ ከዉይይት አልፈው፣ አገር ወዳድነታቸውን በተግባር በማሳየት፣ በሜዳ ፊት ለፊት አምባገነንነትን እየተጋፈጡ ያሉ ጀግኖችን በቁጫና በድሬደዋ በመደገፍ የሚሊዮኖች አንዱ ነን እያሉ ነው።

የቃሌና የደብተራዉ ፓልቶክ ክፍሎች ለወሰዱት አኩሪና አገር ወዳድ አቋም ያለንን አድናቆት እየገለጽን፣ የተቀረነዉ በየአካባቢያችን እየተሰባሰብን ትግሉን እንድንቀላቀል፣ከሚሊዮኖች አንዱ እንሆን ዘንድ ጥሪ እናቀርባለን።

ትግሉን ለመርዳት፣ ለመደገፍ፣ ከሚሊዮኖች አንዱ ለመሆን የምንፈልግ ካለን በሚከተለው አድራሻ ሊያገኙን ይችላሉ።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

millionsforethiopia@gmail.com

ወደ እስራኤል ለመሄድ ቪዛ የጠየቁ ጉዟቸውን እንዲያራዝሙ ኢምባሲው አስታወቀ

$
0
0

Israel Flag
ለጉብኝትና ለሥራ ወደ እስራኤል የሚጓዙ ኢትዮጵያዊን አዲስ አበባ ከሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ የቪዛ አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ለሰንደቅ ጋዜጣ ገለፁ።

አዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ለሰንደቅ እንደገለፀው፤ ወደ እስራኤል ለጉብኝት የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን ላልተወሰነ ጊዜ ጉዟቸውን እንዲያራዝሙ አሳስቧል። የቪዛ አገልግሎት የሚያገኙት የቡሩንዲ እና የሩዋንዳ ዜጎችንም ጉዟቸውን እንደሚያስተጓጉል ለማወቅ ተችሏል።
ኤምባሲው አያይዞ እንደገለጸው፤ በእስራኤል መንግስት እና በእስራኤል ዲፕሎማቶች መካከል የደሞዝና የጥቅማጥቅም ጭማሪ አስመልክቶ የተነሳው ውዝግብ እልባት እስከሚያገኝ የዲፕሎማሲና የቪዛ አገልግሎት እንደማይሰጥ አስታውቋል።

የእስራኤል ዲፕሎማቶች ከማርች 5 ቀን 2014 ጀምሮ የመቱትን የስራ ማቆም አድማ ተከትሎ በዓለም የሚገኙ የእስራኤል ኤምባሲዎች፣ ከእስራኤል መንግስት ባለስልጣናት፣ ተቋማት፣ ግብረ ሰናይ ደርጅቶች፣ አርቲስቶች እና ከሌሎቹም ጋር ምንም አይነት ግንኙነት አቋርጠዋል።

አዲስ አበባ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ ቃል አቀባይ የሆኑት ሊዮ ቪኖቨስኪ ስለተፈጠረው አለመግባባት አነጋግረናቸው በሰጡን ምላሽ ፣ “ለእስራኤል በተለያዩ የስራ መስኮች እየሰራን እንገኛለን። ስለዚህም በዓለም ዓቀፍ ተቀባይነት ባለው ደረጃ ደሞዛችን መስተካከል አለበት። በሌሎች ሀገሮች የዲፕሎማሲ ስራዎች የብሔራዊ ጥቅም ማስከበሪያ ማገሮች ተደርገው ነው የሚወሰዱት፣ ለእኛም በዚህ ደረጃ ሊስተካከልልን ይገባል። ዲፕሎማት በመሆናችን በድርድር እናምናለን። በሌላ ወገን ግን ለመነጋገር ፍቃደኛ ካልሆኑ ውጤቱ ግልፅ ይመስለኛል። ስለዚህም ሚኒስትር ላፒድ እና የስራ ባልደረቦቻቸው መንቃት አለባቸው። ምክንያቱም እኛ የወሰድነው እርምጃ፣ የማንቂያ ጥሪ ነው” ብለዋል።

በእስራኤል ውስጥ እና ውጪ የሚገኙ 1200 ዲፕሎማቶች ለድርድር መንግስታቸውን የጋበዙ ቢሆንም የእስራኤል የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር መስሪያቤት ድርድሩን አስመልክቶ የሰጠው መግለጫ የለም።

ከአምቦ ተፈናቅለው በአንድነት ፓርቲ ጽ/ቤት የተጠለሉ የአማራ ተወላጆችን አስመልክቶ በፍኖተ ነፃነት ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የተቀነባበረ ዘጋቢ ፊልም

ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶማስ አረፉ

$
0
0

የቀድሞ ስማቸው አባ መዘምር ተገኝ የአሁኑ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ጥር 14 ቀን 1932 ዓ.ም ጎጃም ደጋ ዳሞት ዝቋላ አርባዕቱ እንስሳ ተወለዱ፡፡ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርትን በሚገባ ከተማሩ በኋላ ጸዋትወ ዜማን ከመሪጌታ አንዱዓለምና መሪጌታ ካሣ ይልማ ፣ ቅኔ ከመሪጌታ ፈንቴ /ዋሸራ/፣ መጻሕፍተ ሐዲሳትን ከመሪጌታ ብርሃኑ ወልደ ሥላሴ ፣ መጻሕፍተ ሊቃውንትን ከመሪጌታ ቢረሳ ደስታ ተምረዋል፡፡ በዘመናዊ ትምህርትም እስከ 6ኛ ክፍል ፣ የእንግሊዝኛን ቋንቋ በግላቸው የተማሩና የመኪና ጽሕፈት /type writing/ የሚያውቁ ነበሩ፡፡ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ዲቁና ከአቡነ ማርቆስ፣ ቅስና ከአቡነ ባስልዮስ፣ ቁምስና ከብፁዕ አቡነ ተክለሃይማኖት ተቀብለዋል፡፡
abuna tomas

በደብረ ሊባኖስ ገዳም መጻሕፍተ ሊቃውንትን ረዘም ላለ ጊዜ አስተምረዋል፡፡ በገዳሙ የሠራተኞች ቅርንጫፍ ማኅበር ሲቋቋምም የመጀመሪያው ሊቀ መንበር በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ ተዛውረው በጎፋ መካነ ሕያዋን ቅዱስ ገብርኤል ካቴድራል በአስተዳዳሪነትና መጻሕፍተ ሓዲሳትንና ሊቃውንትን በማስተማር የሚጠበቅባቸውን ተልእኮ ተወጥተዋል፡፡ ጥር 14 ቀን 1972 ዓ.ም በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ አንብሮተ ዕድ ተሹመው ሰፊ አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተዋል፡፡ ከዚያም ወደ አዲስ አበባ በመመለስ የታእካ ነገሥት በዓታ ለማርያምና መንበረ መንግሥት ግቢ ገብርኤል ገዳም የበላይ ጠባቂ ሆነው አገልግለዋል፡፡
abuna tomas 2
ብፁዕነታቸው ከ2004 ዓ.ም ጀምሮ የምእራብ ጎጃም ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን ሲያገለግሉ ቆይተው፤ ባደረባቸው ሕመም በሕክምና ሲረዱ ቆይተው መጋቢት 16 ቀን 2006 ዓ.ም መንበረ ጵጵስናቸው በሚገኝበት በፍኖተ ሠላም ከተማ ዐርፈዋል፡፡ ሥርዓተ ቀብራቸውም በዚያው በፍኖተ ሰላም እንደሚፈጸም ይጠበቃል፡፡

ምንጭ፡ ማህበረ ቅዱሳን

“ኢህአዴግ ከምሆን ሞቴን እመርጣለሁ” –ኢ/ር ዘለቀ ረዲ (ቃለምልልስ ከሎሚ መጽሔት ጋር)

$
0
0

Zeleke Redi
ኢ/ር ዘለቀ ረዲ ከወራት በፊት በተዋቀረውና አዲስ አመራሮችን በመረጠው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ ውስጥ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ሆነው መመረጣቸው ይታወቃል፡፡ የሎሚ መፅሔት እውነትን ለህዝብ ለማድረስ ካለባት የሞያ ግዴታ አንፃር በኢ/ር ዘለቀ ዙሪያ በሚነሱ ሀሳቦች ላይ ተንተርሶ የሎሚ ም/አዘጋጅ ቶማስ አያሌው ያደረገውን ቆይታ የመጀመሪያ ክፍል እንደሚከተለው ቀርቧል፡፡

ሎሚ፡- አዲሱ የአንድነት ካቢኔ ሥራዎች እንዴት እየተከናወኑ ነው?

ኢ/ር ዘለቀ፡- በጣም ጥሩ ነው፡፡ ኢ/ር ግዛቸው በተለያዩ የአመራር ቦታዎች ላይ አዳዲስ ሰዎችን ነው ያመጣው፡፡ ከዛ አኳያ ጠንካራ ወይም ለቦታው ይመጥናሉ የተባሉ ሠዎች ናቸው የተመረጡት፡፡ ከዚህ ቀደምም ጠንካራ ሠዎች ነበሩ፡፡ አሁን ደግሞ የበለጠ ጠንካራ ሆነው ሊሠሩ የሚችሉ ሠዎች ናቸው የተመረጡት፡፡ እንደሚታወቀው አንድነት መሬት የረገጠ ፓርቲ ነው፡፡ ዝም ብሎ አየር ላይ የተንጠለጠለ ፓርቲ አይደለም፡፡ ከዛ አንፃር ሥራዎች በጥሩ ሁኔታ እየተከናወኑ ነው፡፡ አሁን ያለው አሠራር በዚሁ ከቀጠለ ጥሩ ውጤት ይመጣል የሚል እምነት አለኝ፡፡
ሎሚ፡- በርካቶች ግን አዲሱን የአንድነት ካቢኔ አወቃቀር አልወደዱትም ይባላል፤

ኢ/ር ዘለቀ፡- ከምን አንፃር?…ግልፅ አድርግልኝ?

ሎሚ፡- አንተን ጨምሮ ሌሎች ሁለት ሶስት ሰዎችን ማካተቱ ትክክል አይደለም የሚሉ ሂሶች ተሰንዝረዋል፡፡ ለምሳሌ፡- አንተን ከፓርቲው ለረጅም ጊዜ ርቆ ነበር፤ ራሱንም ማግለሉንም ተናግሮ ነበር፡፡ ቀደም ሲል በአመራርነት በነበረበት ጊዜ ድክመት ታይቶበት ነበር፡፡ እንደዚህ ዓይነት ችግሮች ያሉበት ሠው እንዴት በአመራር ደረጃ ሊመረጥ ይችላል የሚሉ ወገኖች አሉ፤

ኢ/ር ዘለቀ፡- አንዳንድ ነገሮችን ግልፅ ላድርግልህ፡፡ በመጀመሪያ ከፓርቲው ርቆ ነበር የሚለው ስህተት ነው፡፡ የፓርቲው አባል ነኝ፤ ከፓርቲውም ራሴን አላገለልኩም፤ ከስራ አስፈፃሚነት ራሴን አግልዬ ነበር፤ ከፓርቲው ግን አላገለልኩም፡፡ በብሔራዊ ም/ቤት ውስጥ እሰራ ነበር፡፡ በአባልነትም ቢሆን እሰራ ነበር፡፡ ሁልጊዜ ከፓርቲው ጋር እሰራ እንደነበር ነው የማስበው፡፡ ከፓርቲው ርቆ ፓርቲውን ለቆ ተመልሶ ወደ አንድነት መመለስ ትንሽ ከባድ ነው፡፡ አንድነት እንደ ሌሎች ፓርቲዎች አይደለም፡፡ አንድነት በጣም በነፃነት የሚሰራበት ፓርቲ ነው፡፡ እውነት ነው የምነግርህ፤ እኔ አንድነትን ለማስተዋወቅ አይደለም፡፡ ለምሳሌ ኢ/ር ግዛቸው ዛሬ ተነስቶ እኔ መስራት አይችልም ቢል ለምን የሚል ጥያቄ እንኳን አይቀርብበትም፡፡ እሺ ነው የሚባለው፡፡ ከአንድነት ሥራ አስፈፃሚው እለቃለሁ ሲል ለምን ትለቃለህ ብሎ የሚጠይቅ አልነበረም፡፡ መብትህ ነው፡፡ ማንም ሰው ከአባልነት እለቃለሁ ካለ የመልቀቅ ሙሉ መብት አለው፡፡ እመለሳለሁ ካለም ደግሞ ትቀበለዋለህ፡፡ ከፓርቲው ርቆ የነበረ ሰው ድጋሚ ልመለስ ቢል ትንሽ ከባድ ነው፡፡ አባላቱ ከባድ ናቸው፡፡ ብሔራዊ ም/ቤቱም እንደዚህ እንደምንገምተው አይደለም፡፡

ሎሚ፡- ከዚህ ቀደም ለሰንደቅ ጋዜጣ በሰጠኸው ቃለ ምልልስ ከስራ አስፈፃሚነት በራስህ ፍቃድ መልቀቅህን ተናግረህ ነበር፡፡ የፓርቲው ሊ/መንበር የነበሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ደግሞ አንተን ከቦታው ያነሱት እርሳቸው መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡ ይሄን ነገር እንዴት ተመለከትከው?

ኢ/ር ዘለቀ፡- በዚህ ጉዳይ ምንም ባልል ደስ ይለኛል፡፡ ከዚህ ቀደም በእናንተ መፅሔት ላይ እርሳቸው ያሉትን አይቼዋለሁ፡፡ የመፅሔታችሁ ደንበኛ ነኝ፡፡ እርሳቸው እኔ ነኝ ያነሳሁት ብለዋል፡፡ ጥሩ፤ እርሳቸውም ያባሩኝ እኔም ልልቀቅ ችግር የለውም፡፡ አንድነት በነበሩበት ጊዜ ስለሰሩት በጎ ነገር አውርተዋል፡፡ ከበጎ ነገሮች አንዱ ደግሞ እኔን ማባረር ነው፡፡ ከዚህ ላይ ሊያገኙት የሚችሉት ትርፍ ምንድን ነው? እኔን የመሰለ ሠው፣ ራሱን ችሎ የሚንቀሳቀስ፣ የራሱ ሥራ ያለው፣ ፓርቲውን ሊደግፍ የሚችል ሰው ማባረራቸው ነው ውጤታማ ሥራቸው? በጣም በርካታ ሠዎችን አስገብተው እነገሌን አምጥቻቸዋለሁ ማለት ነው የሚሻለው ወይስ ኢ/ር ዘለቀን አባርሬዋለሁ?! እሺ እርሳቸው አባረሩኝ ብዬ ልውሰድ፤ ሰንደቅ ጋዜጣ በገዛ ፈቃዴ መልቀቄን ተከትሎ ጠይቋቸው ነበር፡፡ ያኔ “ኢ/ር ዘለቀ አለቀቀም፤ ሥራ እየሰራ እንደሆነ ነው የምናውቀው፡፡ አልሄደም አለቀቀም” ብለው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ በርሳቸው ዕድሜ ያለ ሰው ያንን ምስክርነት መካድ ይችላል?…ያኔ የተናገሩት ነገር መረጃ ነው፡፡ ወደኋላ ተመልሰው እኔን አባረውኝስ ቢሆን? መናገራቸው ምንድነው ትርፉ? እኔና እርሳቸው በዕድሜ በእጥፍ እንለያያለን፡፡ በዕድሜያቸው ብዙ ችሎታ አላቸው፤ ብዙ ለፍተዋል፡፡ ውጤት ማምጣት አለማምጣት የራሱ ጉዳይ ሆኖ ማለት ነው፡፡ እኚህ ሠው እኔ እንኳን በጣም መጥፎ ሠው ሆኜ ባስቸግር እንኳን መልሰው በጣም መጥፎ ሰው ነበር፤ እኔ ነኝ ያስተካከልኩት ቅርጽ ያስያዝኩት ቢሉ ነበር የሚሻለው፡፡ ኢ/ር ዘለቀን ያባረርኩት እኔ ነኝ ማለት ጀብደኝነትም አይደለም፡፡

አንድ ሰው ሊቀ-መንበር የሚሆነው ሰዎችን ለማባረር አይደለም፡፡ ደካማውን ማጠንከር ይጠበቅበታል፡፡ ማንም ሠው ደካማ ሊሆን ይችላል፡፡ እኔ በተፈጥሮዬ ደካማ አይደለሁም፡፡ ደካማ ብሆን ኖሮ አሁን ያለሁበት ቦታ ላይ አልገኝም ነበር፡፡ በትንሹ 150 ሠራተኞችን በስሬ አስተዳድራለሁ፡፡ ከ40 በላይ ቋሚ ሠራተኞች አሉኝ፡፡ ከ200 ሺህ ብር በላይ የወር ደመወዝ እከፍላለሁ፡፡ ይሔን ሁሉ የሚሰራ ሰው ደካማ ነው? ቤተሰቤንም ሆነ ሌሎች ሠዎችን ማስተዳደር የምችል ሠው ነኝ፡፡ ደካማ ብሆንም ከዶ/ር ነጋሶ የምጠብቀው “እንደዚህ ያለ ደካማ ነበር፤ እኔ ነኝ ጠንካራ ያደረግኩት” የሚል ምላሽ ነበር፡፡

ሎሚ፡- የአንድነት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ሊቀጣህ የነበረበትና እንዲቀጣህ መመሪያ የተላለፈበት ሁኔታ ነበር?…

ኢ/ር ዘለቀ፡- ዶ/ር ነጋሶ ያላወቁት ነገር ሰው ወንጀለኛ ነው ጥፋተኛ ነው ተብሎ ሊከሰስ እንደሚችል ነው፡፡ አንድ ሌባ ፍርድ ቤት እስከሚፈርድበት ድረስ ተጠረርጣሪ እንጂ ወንጀለኛ አይባልም፡፡ ፍ/ቤቱ ትክክለኛ ውሳኔ እስከሚሰጠው ማለት ነው፡፡ የኔ ጉዳይም በዲሲፕሊን ያስቀጣል አያስቀጣም የሚለውን ማየት የነበረበት የዲሲፕሊን ኮሚቴ ነው አይደል? ያንን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ደግሞ ማጠናከር የነበረባቸው ዶ/ር ናጋሶ ናቸው፡፡ እርሳቸው ያዳከሙትንና እርሳቸው የሌላቸውን ዲሲፕሊን ዲሲፕሊን ኮሚቴ ሊሰራው አይችልም፡፡ መጥተው ማቋቋም ይችላሉ፤ በሩ ክፍት ነው፡፡ እመጣለሁ ሲሉ አንድነት ይቀበላል፤ እሄዳለሁ ሲሉ ደህና ሁኑ ይላል፡፡ ጥፋት ኖሮብኝ ቢሆን ኖሮ እቀጣ ነበር፡፡ እርሳቸው ግን ውጭ ሆነው ይቆጫቸዋል፡፡ የኔ አለመቀጣት ትርፉን አላውቀውም፡፡ ፍ/ቤትም አለ እኮ፤ ከዛ ባለፈም እኔን መክሰስ ይቻላል፡፡ እኔ በእውነቱ የዲሲፕሊን ግድፈት አልነበረብኝም፡፡ ም/ቤቱ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ይየው ብሏል አይደል? ይሄ ማለት ደግሞ ዘለቀ የዲሲፕሊን ግድፈት አለበት ማለት አይደለም፡፡ ዲሲፕሊን ኮሚቴውን አጠናክሮ እኔን ወደ ዲሲፕሊን ኮሚቴ ማቅረብ የነበረባቸው እርሳቸው ነበሩ፡፡ እውነት ለመናገር በእናንተ መፅሔት ላይ እንዳየሁት እኔ በፓርቲ መቀጠሌ ደስተኛ አላደረጋቸውም፡፡ እኔ ለቅቄ እወጣላቸዋለሁ፤ ችግር የለውም፡፡ ውጭ ሆኜ ፓርቲዬን መርዳት እችላለሁ፡፡ ዋናው ግን የሚያገኙት ትርፍ ምንድነው የሚለው ነው፡፡

ከመንግስት በኩል ብዙ ጫና አለብኝ፡፡ የኮንስትራክሽን ድርጅቴ ስምንት ዓመት ሆኖታል፡፡ እስካሁን ድረስ ግን ከመንግስት ሁለት ጊዜ ብቻ ነው የስራ ዕድል ያገኘሁት፡፡ ማንኛውም ኮንትራክተር የኮንደሚኒየም ሥራ የሚሰጠው ተጠርቶ ነው፡፡ የእኔ ድርጅት ግን ኮንዶሚኒየም ላይ አንድ ጠጠር አልጣለም፡፡ ለምን ቢባል ሊያዩኝ ስላልፈለጉ ነው፡፡ የኔ አንድነት ውስጥ መቀጠል ለምን ዶ/ር ነጋሶን ያበሳጫቸዋል? የሶስት ወር ጊዜ ነው የተሰጠን፡፡ አቅም ከሌለኝ የአንድነት ድርጅት አመንክም አላመንክም በሶተኛው ወር ዘለቀ አቅም የለውምና ይውጣ ይላል፡፡ ያንን ጊዜ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ከኢህአዴግ ጎራ የወጡ ሰዎችን የዲሞክራሲው ትግል አጋር ማድረግ ነበረባቸው፡፡ እንጂ እኔም ላግዝ ብሎ የመጣውን የኔ ዓይነት ሰው አባረርኩት ማለት አይጠበቅባቸውም ነበር፡፡

ሎሚ፡- የአንድነት ፓርቲ የውጪ ግንኙነት ኃላፊ ነህ፡፡ ቦታው ትልቅ ነው፤ ይህንን ትልቅ ቦታ ያገኘኸው ደግሞ ፓርቲያችሁ አንድነት የሚሊዮኖች ድምፅ ለነፃነት የሚለውን እንቅስቃሴ ባዘጋጀበት ወቅት የገንዘብ ልገሳ ስላደረገ ለውለታው የተሰጠው ነው እንጂ ለቦታው የሚመጥን ሆኖ አይደለም ሲባል ነበር፤

ኢ/ር ዘለቀ፡- በርግጠኝነት ይሄን የሚሉ አዕምሮ ያላቸው ሠዎች ይኖራሉ ብዬ አልገምትም፡፡ ይሄ አንድነትን መናቅ ነው፡፡ አንድነት የት ቦታም እንዳለም አለማወቅ ነው፡፡ እውነቴን ነው የምነግርህ አንድነት ለብር ብሎ በህልውናው ላይ የሚደራደር ፓርቲ አይደለም፡፡ ይሄ የአዕምሮ ማነስም ጭምር ነው፡፡ ይሄ ማለት ዘለቀ አንድነትን በብር ይገዛዋል ብሎ ማሰብ ነው፡፡ አንድነትንም ማናናቅና መወንጀልም ጭምር ነው፡፡ የአንድነት ም/ቤት በሃገር፣ በህዝብ፣ በህልውና ላይ የማይደራደር ም/ቤት ነው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ሊቀ-መንበር በነበሩበት ጊዜ በአብላጫ ድምፅ የሚወሰነውን ነገር የመስራት ግዴታ አለባቸው አይደል? የራሳቸውን ልዩነት ግን በጋዜጣ ሁሉ ያራግቡ ነበር፡፡ ስለመድረክ ጉዳይ ልዩነት አለኝ ብለው ይፅፋሉ፡፡ ልዩነታቸውን እየፃፉ በአብላጫ ድምፅ ለመገዛት ደግሞ ህጉ ያስገድዳቸው ነበር፡፡ ስለዚህ ዘለቀ ለሚሊዮኖች ድምፅ ገንዘብ ስላወጣ ነው የተመረጠው ብሎ አንድነትን መናገር አሳፋሪ ነው፡፡
ሎሚ፡- ኢ/ር ዘለቀ የኢህአዴግ መልዕክተኛ ነው የሚሉ ወገኖች አሉ፤ ለዚህ አባባላቸው ደግሞ ካሉት ሶስት ም/ጠ/ሚኒስትሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር የቅርብ ወዳጅና ከወዳጅነትም በላይ በአንድነት ውስጥ የማዳከምና የአንድነትን እቅስቃሴ ለመቅጨት ሰርጎ እንዲገባ የተደረገ መልዕክተኛ ነው ይባላል፡፡ አንተስ ሰምተሃል? ምንስ ትላለህ?

ኢ/ር ዘለቀ፡- በመሠረቱ እነዚህን ነገሮች በሁለት ከፍዬ ማየት ነው የምፈልገው፡፡ እኔ የሙክታር ከድር ወዳጅ ብሆን እፈልገው ነበር፡፡ ለምን መሰለህ ሙክታርን እያነጋገርኩኝ መንግስት ያለውን አቋም ማወቅ እችል ነበር፡፡ እውነት ለመናገር እንደዚህ ያሉ ሠዎችን አጥተን ነው እንጂ ከመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር ጓደኛ ብንሆን እኮ ብዙ ነገር ታወራለህ፡፡ ድክመቱንም የምታገኘውም በዛ ነው፡፡ ኢህአዴግ እኮ ደርግን ያሸነፈው በደህንነቱ በእነ ተስፋዬ ወ/ስላሴ አማካይነት ነው፡፡ ቁልፍ ሰዎችን መያዝ ያስፈልጋል፡፡ ብንይዛቸው ደግሞ ይህ የድክመት ምልክት አይደለም፡፡ ምናልባት እንግዲህ ሙክታርም የጅማ ልጅ ነው፤ እኔም የጅማ ልጅ ነኝ፤ ያው መላ ምት ነው፡፡

እንደ ዶ/ር ነጋሶ ያሉ በርካታ ሠዎች የሚጎነትሉህ ቦታ ቁጭ ብለህ የኢህአዴግ መልዕክተኛ ከምትሆን የኢህአዴግ ካድሬ አትሆንም? የአንድ ዞን አስተዳዳሪነት ቦታ ይሰጥሃል እኮ፡፡ አሁን ካሉት ሠዎች በአቅም ላልተናነስ እችላለሁ፡፡ ኦህዴድ ብሆን ደረጃዬን ጠብቄ መጥቼ ሙክታር ያለበት ደረጃ መድረስ እችል ነበር፡፡ በርግጠኝነት ዛሬ ሄጄ ብጠይቀው ኢህአዴግ ይሄን የሚነፍግ ንፉግ አይመስለኝም፡፡ እንደውም ጠላት መቀነስ ነው፡፡

ለህሊናቸው ሳይሆን ለሆዳቸው ያደሩ ጋዚጠኞችም አሉ፡፡ አንድ ሁለት ሶስት ጋዜጠኞች ደውለውልኝ አንድ ጥያቄ ጠይቀውኝ ነበር፡፡ በጣም የወረደ ጥያቄ ማለት ነው፡፡ እኔ ብዙ አልፈራም፤ ሠዎች ይመጡና አንድ ነገር እንስራ ይሉሃል፡፡ በሁለተኛው ቀን ሌላ ነገር ይጠይቁሃል፡፡ ይሄማ ትክክል አይደለም ስትላቸው እንደዚህ ነህ እንልሃለን ይሉሃል፡፡ ምንም ይበሉህ ምን ጊዜውን ጠብቆ እውነት ያወጣዋል፡፡ እኔ ከአንድነት ስራ አስፈፃሚ እንደወጣሁ ኢህአዴግ ሊሆን ነው ምናምን ይሉ ነበር፡፡ ኢህአዴግ እኔ የማስበውን የሚያስብ ከሆነ እንደኔ አንድነት የሚያጠናክር ከሆነ ልናግዘውና ልናጠናክረው ነው የሚገባው፡፡ እንደኔ ዓይነት ኢህአዴጎች ካሉ ለምንድነው የማንሠበስባቸውና የማናመጣቸው? ዘለቀ የኢህአዴግ አባል ሲሆን መታወቂያ ይኖረዋል አይደል፡፡ ኢህአዴግ አንድነትን ለመሠለል ከበቃ አድገናል ማለት ነው፡፡ ይቺ አሉ የሚባሉትን ሠዎች ከስር ሆኖ መቀንጠሻ ናት ዘዴ ናት፡፡

ስለ አንድ ሰው ልንገርህ፤ የባንክ ሠራተኛ ነው፤ ስሙን አልገልፅልህም፤ መሃንዲስ ነው፡፡ አንድ ቀን በራሴ ፅሁፍ በይፋ እገልጸዋለሁ፡፡ አንዱን ጋዜጠኛ ምን ብሎ ያሳስተዋል መሠለህ? አርሲ ነገሌ “መንገድ ስራ” ወስደነው ነበር፡፡ መንገዱ ፈርሶ ተበላሻሽቶ ከፍተኛ ብጥብጥ ተነስቷል ብሎ ይነግረዋል፡፡ ይሄን የሰማው ልጅ ይደውልልኝና “ኢ/ር ዘለቀ ነህ አዎ…አርሲ ነገሌ የምትሠሩት መንገድ ተበላሽቷል ወይ? ምናምን ብሎ ይጠይቀኛል፡፡ ማን ነገረህ? አልኩት፡፡ ጥቆማ ደርሶን ነው አለ፡፡ ዓይተህ ማውጣት ትችላለህ፤ ይህን ካላደረግክ እኛ ህጉን ጠብቀን እንከስሃለን ብዬ መለስኩለት፡፡ ከ15 ቀን በኋላ መንገዱ ይመረቅ ነበር፡፡ ከመመረቁ በፊት ተዟዙሮ የተመለከተው የከተማው አስተዳደር “የመጀመሪያ ኮንትራክተር ነው” ብሎናል፡፡ ሞያውን ተጠቅሞ ስራውን በአግባቡ ሰርቶልናል ተብሎ የከተማ አስተዳደሩ “ቡልኮ” ሸልሞኛል፡፡ በኦሮሞ ባህል ቡልኮ የተሸለሙት እነ አባዱላ ናቸው፡፡ ጋዜጠኛው እዛ ነበርና በጣም ነው የደነገጠው፡፡ ስለዚህ እዚህ መጥተው የተለየ ጥቅም የሚያገኙ ሠዎች ሄደው ስም ያጠፋሉ፡፡ ኢ/ር ግዛቸውን ብዙ ነገር ይሉታል፡፡ ኢ/ር ግዛቸው በተፈጥሮው ጠንካራና እያጣራ ማለፍ የሚወድ ሠው ነው፡፡ ዶ/ር ነጋሶ ቢሆኑ በዚህ ፈተና ይወድቁ ነበር፡፡

ዶ/ር ነጋሶ ጋር ቀድሞ ሄዶ የነገራቸው ሰው አሸናፊ ነው፡፡ እኔ አንተን ቀጥቅጬህ ቀድሜ ሄጄ ከነገርኳቸው ቁስልህን ብታሳይ አይሰሙህም፡፡ ኢ/ር ግዛቸው ግን ይህንን ሁሉ ነው የተቋቋመው፡፡ እነዚህ ሠዎች ካንተ ጥቅም ሲያጡ ፓርቲ ውስጥ ስትገባ የምትጠቀም ይመስላቸዋል፡፡ ለሃገርህ የሆነ አስተዋፅዖ ለማበርከት የሄድክ አይመስላቸውም፡፡ ከዚህ አንፃር ብዙ ነገር ሊወራብህ ይችላል፡፡ በመረጃ “ኢህአዴግ ነው ብሎ” የሚሞግተኝ ካለ ምንም ችግር የለብኝም፡፡ አሉባልታ ግን አሉባልታ ነው፡፡ የኔ ማረጋጋጫ ስራዬ፡፡ ኢህአዴግ ብሆን ኖሮ አንዲት ሴትዮ 400 ሺህ ብር በልታኝ አትቀርም ነበር፡፡ ኢህአዴግ ሆኜ ይሄ ነው የኮንዶሚኒየም ግንባታ ላይ እንዳልሳተፍ (እንዳልሰራ) አልደረግም ነበር፡፡ ኢህአዴግ የሆኑ ሰዎችን እናውቃቸዋለን፡፡ ቢጠሯቸው አይሰሙም፡፡ ገንዘባቸው የት ነው ያለው? እኛ እኮ NGO እየለመንን ነው የምንሰራው፡፡ ያውም ደግሞ ጠንካራ ጠንካራ NGOዎች ናቸው እንጂ አነስ አነስ ያሉት ዝም በሉ ሲባሉ ዝም ይላሉ፡፡ በርካታ NGOዎች ናቸው ጨረታ ካለፍን በኋላ የሰረዙብን፤ ደህንነቶች እያስፈራሯቸው ማለት ነው፡፡ ዘለቀ ኢህአዴግ ነው የሚባለው ከአንድነት ከፓርቲ አገልግሎት ለማስወጣት ሲባል ነው፡፡ ኢህአዴግ መሆን ብፈልግ በአንድነት በኩል መዞር የሚጠበቅብኝ አይመስለኝም፡፡ ለሰራተኞቼ ከ5 ሚሊዮን ብር በላይ ኢንሹራንስ የምገዛ ሰው ነኝ፡፡ አንድ ሚኒስትር የሚከፈለው ደመወዝ ስንት ነው? እኔ እኮ 38 ሺህ ብር ነው ለአንድ መሃንዲስ የምከፍለው፡፡ ምን አጥቼ ነው ኢህአዴግ ስር የምሸጎጠው? በህልሜም የኢህአዴግ አባል ሆኜ ማየት አልፈልግም፡፡ እስካሁን ባለኝ አቋም የኢህአዴግ አባል አይደለሁም፡፡ የአይዲዎሎጂ አስተሳሰብ ጊዜውን ጠብቆ የሚቀየር ነገር ነውና ወደፊት ምን እንደሚፈጠር አላውቅም፡፡ ምኒልክም “ሃገሬ ስትወረር ከማይ ሞቴን እመርጣለሁ” እንዳሉት እኔም ኢህአዴግ ከምሆን ሞቴን ነው የምመርጠው፡፡ የሚሊዮኖች ድምፅ ለነጻነት የሚለውን የአንድነት ዘመቻ ረዳህ ተባልኩ፡፡ ግድቡ ለኢትዮጵያ ጥቅም ሲሰራ እደግፋለሁ፡፡ ኢህአዴግ የፖለቲካ ቅስቀሳ ስለሚያደርግበት አንድም እርዳታ አድርጌበት አላውቅም፡፡ የአባይ ግድብ የኔ ገንዘብ የለበትም፡፡ ለምን? ለፖለቲካ ቅስቀሳ እያዋለው ስለሆነ፡፡ ለህዝብ አሳልፎ ስላልሠጠ፤ ለህዝብ ስጥ እያልኩ እየፃፍኩበት ነው፡፡ ለህዝብ ሲሰጥ ግን አንደኛ የምረዳው እኔ ነኝ፡፡ አሁን ግን ለአባይ ግድብ የአንድ ብር ቦንድ አልገዛሁም፡፡

ሎሚ፡- ከዚህ ቀደም የፓርቲያችሁ ልሳን የሆነው ፍኖተ ነፃነትን “አዲስ ዘመን” ብለህ ዘልፈኸዋል፤ አዲሱ ካቢኔ ሲዋቀርም በአንተ መመረጥ ዙሪያ ከተነሱ ቅሬታዎች አንዱ ይሄነው፤ እንዲህ ልትል የቻልክበት ምክንያት ምንድነው?

ኢ/ር ዘለቀ፡- ምን መሰለህ? በወቅቱ አንድ ዜና ሰርተው ነበር፡፡ እኔን የሚመለከት ዜና ም/ቤቱ ሲሰጣቸው ሚዛናዊ ለማድረግ ሀሳቤን አላካተቱም ነበር፡፡ ስላልጠየቁኝ “ፍኖተ ነፃነት” ትልቅ የህዝብ ሚዲያ ናት፤ ግን ምንድነው ከአዲስ ዘመን የተለየ የሚያደርገው?…አዲስ ዘመን ዜና ሲሰራ የጉዳዩን ባለቤት አይጠቅም አይደል?…ፍኖተ ነጻነትም እንደዚያ ስላደረገ አዲስ ዘመን ብዬው ነበር፡፡ እኔን መጠየቅ ነበረባቸው፡፡ በአንድነት ባህል አንድ ግለሰብ ከፕሬዚዳንቱ እኩል መብት አለው፡፡ ያንን መብቴን አልሰጣችሁኝም የሚል ቅሬታ ነው ያነሳሁት፡፡ ከጋዜጠኛው ጋርም ተነጋግረናል፡፡ ዜናውን ስትሰሩ ሚዛናዊ ማድረግ አለባችሁ በሚል ተወያይተናል፡፡ ችግሩም በሰላም ተፈትቷል፡፡

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>