Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

በዩኒቨርሲቲው ጥበቃ ከተደበደቡት ተማሪዎች መካከል የአንዱ ሕይወት አለፈ

$
0
0

በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አካባቢ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ፋኩልቲ፣ ሁለት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው የጥበቃ ሠራተኛ ድብደባ ተፈጽሞባቸው አንደኛው ሕይወቱ ማለፉ ተረጋገጠ፡፡
news
ጥር 23 ቀን 2007 ዓ.ም. የግማሽ ዓመት ፈተናቸውን ካጠናቀቁት የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች መካከል፣ ሙሉቀን ከበደና ታምራት አባተ የተባሉ ተማሪዎች በዕለቱ ድብደባ እንደተፈጸመባቸው ታውቋል፡፡ ተማሪዎቹ ፈተናቸውን እንዳጠናቀቁ ከግቢ ወጥተው ሲዝናኑ ካመሹ በኋላ ወደ ማደሪያ ክፍላቸው ሲመለሱ፣ ፀደቀ አድማሱ ከሚባለው ተጠርጣሪ የጥበቃ ሠራተኛ ጋር መጋጨታቸውን ከፖሊስ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

ተማሪዎቹ ወደ ዩኒቨርሲቲው ግቢ ሊገቡ ሲሉ ተጠርጣሪው እንዲቆሙ ሲያደርጋቸው ተማሪ መሆናቸውን የሚያረጋግጡበትን መታወቂያ ቢያሳዩም፣ ከተጠርጣሪው ጋር ሊግባቡ ባለመቻላቸው ድብድቡ መጀመሩ ታውቋል፡፡ ተጠርጣሪው በወቅቱ ይዞት በነበረው የእንጨት ዱላ ደጋግሞ ሲደበድባቸው የተመለከተ ሾፌር፣ ሌሎች የተኙ ጥበቃዎችን በማስነሳቱ የተፈጠረው ድብድብ የቆመ ቢሆንም፣ ተማሪዎቹ በደረሰባቸው ድብደባ ተጎድተው ስለነበር በአቅራቢያቸው በሚገኘው ጥሩነሽ ቤጂንግ ጠቅላላ ሆስፒታል መወሰዳቸውም ተጠቁሟል፡፡

ታምራት አባተ የተባለው ተማሪ በጥሩነሽ ቤጂንግ ጠቅላላ ሆስፒታል በተደረገለት ሕክምና የተረፈ ቢሆንም፣ የደረሰበት ድብደባ ከባድ በመሆኑ ለተጨማሪ ሕክምና ሪፈር የተደረገው ተማሪ ሙሉቀን፣ በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል በሕክምና ላይ እያለ ጥር 25 ቀን 2007 ዓ.ም. ሕይወቱ ማለፉ ታውቋል፡፡ ፖሊስ በድብደባው ተሳትፈዋል በማለት በቁጥጥር ሥር ያዋላቸውን ተጠርጣሪ የዩኒቨርሲቲውን የጥበቃ ሠራተኞችን ፍርድ ቤት አቅርቦ ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ በመጠየቅ በምርምራ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡

ምንጭ – ሪፖርተር ጋዜጣ

The post በዩኒቨርሲቲው ጥበቃ ከተደበደቡት ተማሪዎች መካከል የአንዱ ሕይወት አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.


የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት አቤቱታ አቀረቡ

$
0
0
temesgen1

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ

‹‹መርማሪ ተመድቦ ጉዳዩ እየተጣራ ነው›› የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን

የፍትሕ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ሆኖ ሲሠራ በጋዜጣው የተለያዩ ዕትሞች ላይ በወጡ በራሱና ከአንባብያን በተላኩ መጣጥፎች ምክንያት የወንጀል ክስ ተመሥርቶበት፣ የሦስት ዓመታት እስር የተወሰነበት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት፣ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አቤቱታ አቀረቡ፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ጥፋተኛ በተባለበት የወንጀል ክስ በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 16ኛ ወንጀል ችሎት የሦስት ዓመት የእስር ቅጣት ውሳኔ ከተላለፈበት በኋላ፣ በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ዝዋይ ማረሚያ ቤት በእስር ላይ ይገኛል፡፡ በመሆኑም እናቱን ጨምሮ ወንድሙ፣ ጓደኞቹና ወዳጆቹ እየጠየቁት የነበረ ቢሆንም፣ ካለፉት 30 ቀናት ወዲህ ግን ማንም እንዳይጠይቀው መከልከሉንና በምን ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ማወቅ እንዳልቻሉ፣ እናቱ ወ/ሮ ፋናዬ እርዳቸው ለኮሚሽኑ፣ በግልባጭም ለሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማትና ለውጭ ኤምባሲዎች በጻፉት ደብዳቤ አሳውቀዋል፡፡

ወ/ሮ ፋናዬ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ዋናውን ለሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ በግልባጭ ለጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት፣ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ለሕግና ፍትሕ አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ለአፈ ጉባዔ ጽሕፈት ቤት፣ ለእንባ ጠባቂ ተቋም፣ ለአሜሪካና ለእንግሊዝ ኤምባሲዎች በጻፉት ደብዳቤ እንደገለጹት፣ ልጃቸውን ጋዜጠኛ ተመስገንን ካዩት (ድምፁን ከሰሙ) አንድ ወር አልፏቸዋል፡፡ ታናሽ ወንድሙ ታሪኩ ደሳለኝ ምግብ ይዞለት ዝዋይ ማረሚያ ቤት የሄደ ቢሆንም፣ በማረሚያ ቤቱ ጠባቂዎች ድብደባ ደርሶበትና ምግቡም ሜዳ ላይ ተደፍቶ ተመልሷል ብለዋል፡፡ ልጃቸው በቤተሰቦቹ፣ በጓደኞቹና በወዳጆቹ እንዳይጎበኝ ለምን እንደተከለከለ እንዲነገራቸውና ሰብዓዊ መብቱ ተጠብቆ እንደማንኛውም ታራሚ በነፃነት እንዲጎበኝ እንዲያደርጉላቸው፣ የሚመለከታቸውን የመንግሥት ተቋማትና የሁለቱን አገሮች አምባሳደሮች በደብዳቤያቸው ተማፅነዋል፡፡

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ለምን እንዳይጠየቅ (እንዳይጎበኝ) ክልከላ እንደተደረገበት ማብራሪያ ለማግኘት የፌዴራል ማረሚያ ቤቶች አስተዳደር ኃላፊዎችን ለማግኘት ተደጋጋሚ ጥረት ቢደረግም፣ አመራሮች በሥልጠና ላይ መሆናቸውን ከመግለጽ ባለፈ ማብራሪያ የሚሰጡ ማግኘት አልተቻለም፡፡

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ስለአቤቱታው ተጠይቆ፣ የጋዜጠኛ ተመስገን እናት የጻፉት የመማፀኛ ደብዳቤ እንደደደረሰው አረጋግጧል፡፡ መርማሪ መድቦ ጉዳዩን ማጣራት እንደጀመረም የኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ አባዲ አስረድተዋል፡፡

Source:: Ethiopian Reporter

The post የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ወላጅ እናት አቤቱታ አቀረቡ appeared first on Zehabesha Amharic.

በኦሮምያ ክልል የፌደራል ፖሊሶች ሁለት የቤተሰብ አባላትን በጥይት መትተው አመለጡ

$
0
0

(ፎቶ ከፋይል)

(ፎቶ ከፋይል)


በምእራብ ሸዋ ዞን በባኮ ወረዳ በቴቢ ከተማ ከሩሰንጎት ቀበሌ ገበሬ ማህበር ነዋሪ የሆኑት አቶ ተሙሻ በርጫ እና የ13 አመት ታዳጊ ልጃቸው ፋንቱ ተሙሻ የካቲት 2 ቀን 2007 ዓም በፌደራል ፖሊሶች በጥይት ተመትተው አምቦ ሆስፒታል መግባታቸውን ኢሳት ዘገበ::

እንደ ኢሳት ዘገባ ከሆነ ታዳጊዋ ወጣት አንገቷ አካባቢ በጥይት ስትመታ፣ አባቷ ደግሞ እግራቸውን በሁለት ጥይቶች ተመተው ሆስፒታል የገቡ ሲሆን በታዳጊዋ ላይ የደረሰው ጉዳት ከፍተኛ መሆኑም ታውቋል።

ማንነታቸው ያልታወቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት ወደ ቀበሌው በመሄድ፣ አቶ ተሙሻን አሸባሪዎችን አስጠግተህ ትቀልባለህ ብለው በጥይት እንደመቱዋቸውና የአካባቢው ነዋሪዎች ሆ ብለው ሲወጡ፣ በመጡበት መኪና ማምለጣቸውን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።
አሸባሪ የተባሉት ሃይሎች እንማን እንደሆኑ ባይታወቅም፣ ነዋሪዎች ግን ምናልባትም ለምርጫ ቅስቀሳ የመጡ የተቃዋሚ አባላትን ሊሆን ይችላል ይላሉ። ኢሳት በጉዳዩ ዙሪያ የወረዳውን ባለስልጣናት ለማናገር ያደረገው ሙከራ አልተሳካም።

The post በኦሮምያ ክልል የፌደራል ፖሊሶች ሁለት የቤተሰብ አባላትን በጥይት መትተው አመለጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

የእሥር ማዘዣ በመዉጣቱ አቶ ጸጋዬ አላምረው አገር ለቀው ተሰደዱ

$
0
0

20526_774706749280928_86029102619422382_n

የአንድነት ፓርቲ ምክትል አፈጉባኤ የሆኑትና በቅርቡ ሰማያዊ ፓርቲ የተቀላቀሉት አቶ ጸጋዬ አላምረው፣ ከወያኔ የፀረ-ሽብር ግብረ ኅይል እንዲታሰሩ የማዘዣ ወረቀት በመዉጣቱ፣ ለተወሰነ ቀናት አገር ቤት ራሳቸውን ሰዉረውከቆዩ በኋላ፣ በአሁኑ ጊዜ ከኢትዮጵያ ዉጭ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

አቶ ጸጋዬ የአንድነት ፓርቲ የፋይናንስ ሃላፊ ሆነው የሰሩ ሲሆን፣ አቶ ሃብታሙ አያሌው ከታሰሩ በኋላ የመኢአድ አመቻች ኮሚቴ ዋሃ ሰብሳቢ ሆነው ሰርተዋል።፣ ሕወሃቶች መሰናክል ፈጠርበት እንጂ በመኢአድ እና በአንድነት መካከል ዉህደቱ ጫፍፍ እንዲደርስ፣ ቁልፍ ሚና ከተጫወቱ የአመራር አባላት መካከል አንዱ ነበሩ። የአንድነት ፓርቲ ያደርግ በነበረው የምርጫ ዘመቻም፣ የምርጫ ኮሚቴ አባል በመሆን ትልቅድርጅታዊ ሥራ ይሰሩም ነበር።

የአንድነት ፓርቲ በአዲስ አበባ ጠርቶት በነበረው ሰልፍ ፣ የሕወሃት ታጥቂዎች በሰላማዊ ዜጎችን ላይ ኢሰባአዊ የሆነ ከፍተኛ ድብደባ በፈጸሙበት ወቅት፣ በአካል ከተጎዱት ወገኖች መካከል አንዱ አቶ ጸጋዬ ነበሩ። ከስድስት ወራት በፊትም በግንቦት ወር 2006 ዓ.ም፣ አንድነት እና መኢአድ የቅድመ ዉህደት ፊርማ በፈረሙበት ጊዜም፣ የአገዛዙ ካድሬዎች ስብሰባዉ ለመረበሽ በሞከሩበት ወቅት ተፈንክተው ትልቅ ጉዳት ደሮባቸውም ነበር።

ሕወሃቶች በአቶ ጸጋዬ ላይ ያነጣጠሩት፣ በርካታ የአንድነት አባላትን ይዘው አቶ ፀጋዬ ሰማያዊን ከተቀላቀሉ በኋላ ሲሆን፣ ዋና ክስ አድርገው የወሰዱትም “አንድነት ፓርቲ የገንዘብ እርዳታ ከሽብርተኞች ይቀበላል፣ የሚቀበለዉም በአቶ ጸጋዬ አላምረው በኩል ነበር” የሚል እንደሆነ ታውቋል። ሕወሃቶች በሚቆጣጠሩት ኢቲቪና ራዲዮ ፋና ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ በአንድነት ላአይ የጅመሩ ሲሆን፣ እነ ትግስቱ አወሉንም በሜዲያ፣ የአቶ ጸጋዬ አላምረዉን ስም እየጠሩ “ገንዘብ ተቀባይ እርሱ ነበር” እያሉም እንዲናገሩ እያደረጓቸው ነው።

የአንድነት ፓርቲ በዉጭ አገር ካሉ ኢትዮጵያዊያን ከፍተኛ የገንዘብ ድጋፍ ያገኝ እንደነበረ ይታወቃል። በዉጭ ያሉ የአንድነት ድጋፍ ድርጅቶችም፣ ከቅንጅት ጊዜ ጀምሮ በሰማዊ ትግል የሚያምኑ እንደመሆናቸው፣ በነርሱ በኩል ተሰብስቦ የሚላክን ገንዘብ ከሽብርተኞች እንደመጣ አድርጎ መቁጠር በሕግ፣ በሞራልም በአሰራር ተቀበያነት እንደሌላው የድጋፍ ድርጅቱ አባላት ይናገራሉ።

 

 

 

The post የእሥር ማዘዣ በመዉጣቱ አቶ ጸጋዬ አላምረው አገር ለቀው ተሰደዱ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤቱን እንዲለቅ ክስ ቀረበበት • በወር 40 ሺህ ብር ኪራይና 250,000 ብር ለ‹‹ኪሳራ›› እንዲከፍል ተጠይቋል

$
0
0

photo File

photo File


(ነገረ ኢትዮጵያ) ሰማያዊ ፓርቲ የካ ክ/ከተማ በቀድሞው መጠሪያው ቀበሌ 15 እንዲሁም በአዲሱ መጠሪያው ወረዳ 6 የቤት ቁጥር 460 የሆነውን ጽ/ቤቱን 25000 ሺህ ብር ቅጣት ከፍሎ እንዲለቅ በአከራዮቹ በኩል ክስ ቀረበበት፡፡ በከሳሽ እነ አቶ ሚስጥረ ሽበሽ የተመሰረተው ክስ ‹‹ቤቱን ለቀው ለማስረከብ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው …በወር ብር 40,000 (አርባ ሺህ ብር) ሒሳብ ከጥር 16 ቀን 2007 ጀምሮ ቤቱን ለቀው እስከሚያስረክቡ ድረስ ባልተነጣጠለ ኃላፊነት እንዲከፍሉን›› ያሉ ሲሆን ‹‹ከሳሽ ቤቱን ለማደስ ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በገባነው ውል መሰረት የደረሰብንን 250 ሺህ ብር ኪሳራ እንዲተኩልን›› ሲሉ ከሰዋል፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሚፈልግባቸው ጊዜያት የቀበሌ ካድሬዎች አከራዮቹና ደላሎቹ ለፓርቲው እንዳያከራዩ ሲያስጠነቅቁ የቆዩ ሲሆን በተለይ በጥር ወር 2007 ዓ.ም ይህ ጽ/ቤት እንዳይከራይ ግፊት የማድረጉ ተግባር ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡

The post ሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤቱን እንዲለቅ ክስ ቀረበበት • በወር 40 ሺህ ብር ኪራይና 250,000 ብር ለ‹‹ኪሳራ›› እንዲከፍል ተጠይቋል appeared first on Zehabesha Amharic.

የአዲስ አበባው ባቡር መንገድ ሁለተኛውን የመኪና አደጋ አስተናገደ

$
0
0

babur
babur 2

babur addis
(ዘ-ሐበሻ) የአዲስ አበባ ሕዝብ “ባቡሩን ሳንሄድበት አደጋ ጨረሰው” ማለት ጀምሯል:: ከሁለት ሳምንት በፊት የተመረቀውና ሥራ የጀመረው የአዲስ አበባ ባቡር ሃዲድ አጥር ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ የመኪና አደጋ ማስተናገዱን ዘ-ሐበሻ መዘግቧ አይዘነጋም::

ዛሬም ከአዲስ አበባ በፎቶ ግራፍ ተደግፎ ያገኘነው መረጃ “ባቡሩን ሳንሄድበት የመኪና አደጋ ጨረሰው” ያስብላል:: በፎቶ ግራፍ እንደምታዩት ይህ ገልባጭ መኪና የባቡሩን አጥር ሰብሮ ገብቶበታል:: ወደ ሳሪስ መሄጃ ጎተራ ማሳለጫው እንደተሻገረ ነው መኪናው አደጋውን ያደረሰው:: እንዴት እንዲህ ያሉ ትላልቅ መኪናዎች በጠባብ መንገድ እንዲያልፉ ይፈቀዳል? መልሱን ለሕወሓት/ኢሕአዴግ የመንገድ ባለስልጣን ትተነዋል::

The post የአዲስ አበባው ባቡር መንገድ ሁለተኛውን የመኪና አደጋ አስተናገደ appeared first on Zehabesha Amharic.

ከአራት ዓመት በፊት መጠናቀቅ የነበረበትና ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰበት የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለምተባለ፡፡

$
0
0

10431230_770386583022744_6091685951275320399_oየካቲት ፭(አምስት) ቀን፳፻፯ዓ/ምኢሳትዜና :-ከሕንድ መንግስት በተገኘ 640 ሚሊየን ዶላር በተገኘ ብድር እ.ኤ.አ በ2008 ሥራ የጀመረው ይህው ፋብሪካ ከሙስና ጋር በተያያዘ ጥራት ያለው ማሽነሪግ ባለመከናወኑና ሥራው በተገቢው ቁጥጥርና ክትትል ባለመታገዙ ተጠናቆ ወደ ስራ መግባት የነበረበት እ.ኤ.አ በ2010 መጨረሻ ቢሆንም ፋብሪካው እስካሁን ወደስራ መግባት እንዳል ቻለ ታውቋል፡፡

የስኳር ኮርፖሬሽን ከፍተኛ አመራሮች በዚህ ዓመትም ፋብሪካው ስራ ይጀምራልበሚልበ ተደጋጋሚ መግለጫ ከመስጠታቸው ባሻገር ፣ ጋዜጠኞችን ምረቃ እናካሂዳለን በሚል ወደ ስፍራው ቢወስዱም ከተተከሉት ማሽኖች አንደኛው ከጥቅም ውጪ በመሆኑ ሊሳካ እንዳልቻለ የፋብሪካው ምንጮች ገልጸዋል፡፡

ባለፈው ወር በአፋር ክልል ከተከበረው የአርብቶአደር በዓል ጋር ተያይዞ ፋብሪካውን ለማስመረቅ በስኳር ኮርፖሬሽን በኩል ታቅዶ የነበረ ቢሆንም አሁንም ፋብሪካውን ወደምርት ማስገባት ባለመቻሉ ምረቃው እንዲተላለፍ መደረጉም ተነግሮአል፡፡

ከተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ችግር ጋር በተያያዘ ስማቸው በሙስና ጉዳይ ከሚነሱት ባለስልጣናት መካከል ወ/ሮ ገነት ዘውዴ በህንድ የኢትዮጽያ አምባሳደር እና አቶ ግርማ ብሩ የቀድሞ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትርና በአሁኑ ወቅት በአሜሪካ ኢትዮጵያ አምባሳደር ይገኙበታል፡፡

በአሁኑ ሰዓት በገበያ ላይ ስኳር እጥረት በከፍተኛ ደረጃ ያለ ሲሆን ይህን ክፍተት ለመሸፈን ሀገሪቱ ከፍተኛ የውጪ ምንዛሪ በማውጣት ከውጪ ሀገር በመግዛት በማስገባት ላይ መሆኗ ይታወቃል፡፡

Source:: Ethsat

The post ከአራት ዓመት በፊት መጠናቀቅ የነበረበትና ከፍተኛ ገንዘብ የፈሰሰበት የተንዳሆ ስኳር ፋብሪካ ከሙስናና ብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ እስካሁን ስራ መጀመር አልቻለምተባለ፡፡ appeared first on Zehabesha Amharic.

የህብር ራድዮ 5ኛ ዓመት በዓል በላስቬጋስ


ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን)

$
0
0

ሠዓሊአምሳሉ ገ/ኪዳንአርጋው

amsalugkidan@gmail.com

አበባን በስጦታ ማበርከት ከእኛ የተወሰደ ባሕል መሆኑን ያውቃሉ?

valentines-day-dinnerቫላንታይንስ ዴይ (ፍቅረኞች ቀን) ከወደ ምዕራቡ ከተዋስናቸው ወይም ከተጫናቸው በዓላት አንዱ ነው፡፡ ይህ በዓል በእኛ ዘንድ አሁን ያገኘውን ያህል ተቀባይነት እንዲያገኝ ከማድረግ አንጻር የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤፍ ኤም ሬዲዮዎች(ነጋሪተ ወጎች) ዐቢዩን ሚና ተጫውተዋል፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ የብሔራዊው የብዙኃን መገናኛውና ሌሎች የሬዲዮ (የነጋሪተ ወግ) ጣቢያዎችም እንደዚያው ቁምነገሬ ብለው ይዘውታል፡፡ የብዙኃን መገናኛዎች በተለይም የኤሌክትሮኒክሱ (በአየር ሞገድ የሚሠራጨው) በመልካም ጎንም ይሁን በመጥፎ ጎን ለሚመጣ ውጤት ታላቅ ጉልበት አላቸው፡፡ ከዚህ አንጻር ባጠቃላይ ለደረሰብን የባሕል ወረራና ጥቃት በዚህ የብዙኃን መገናኛ ከበጣም ጥቂቶቹ በስተቀር “የመዝናኛ ዝግጅት” በሚል ሥያሜ የአየር ሰዓት የወሰዱ እንደዜጋ የሀገርንና የሕዝብን እሴት ሀብት የመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ እንዳለባቸውና እንዴትም እንደሚጠበቅ ምንም የማያውቁ ወይም መጠበቅ የማይፈልጉ ከመናኛ የግል ጥቅማቸው ባለፈ ይሄንን ከባድ ኃላፊነት ለመረዳት የአቅም ውስንነት የገደባቸው አዘጋጆች ይሄንን ዕድል ለነሱ ከሰጧቸው አካላት ቀጥሎ ተጠያቂዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህ ግለሰቦች ጀርባም ደግሞ ጨርሶ ኃላፊነት የማይሰማቸው የተለያዩ ስግብግብ የንግድ ወይም የአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች አሉ፡፡

ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን) ከባሕላችን አንጻር እንዴት ይታያል?

ቫላንታይንስ ዴይ ይጠቅማል አይጠቅምም ወደ ሚለው ከመሔዴ በፊት ይሔንን ማየት አስፈላጊ ነው፡፡ ባሕላችን በነገራችን ላይ “ባሕላችን” ብየ ስል ንጥሩን(ኦሪጂናሉን) ማለቴ እንጅ ለምሳሌ አሁን አዲስ አበቤ ነን የምንለው እየኖርነው ያለውን በዘመናዊነት ሽፋን በባዕዳን ባሕል የተበከለውን ወጥነት ያጣውን ባሕል ማለቴ አይደለም፡፡ ከዚህ አንጻር ስናየው ሲጀመር ባሕላችን ፍቅረኝነትን ማለትም ከጋብቻ ውጪ ወይም በፊት የሚደረግን ፆታዊ ወዳጅነትን የሚያውቅና የሚፈቅድ አይደለም፡፡ በእኛ ባሕል የፍቅር ሕይዎት የሚኮመኮመው በትዳር ውስጥ ነው፡፡ በእርግጥ ባሕላችን እጮኝነትን ያውቃል፡፡ ይሁን እንጂ የእጮኝነት ወቅት እሷ የሱ እሱ የእሷ መሆናቸውን ከማረጋገጥ ባለፈ የፍቅር ሕይዎት ሊባል በሚችል ደረጃ ፍቅር የሚኮመኮምበት አይደለም፡፡ በመታቀብ ውስጥ ሆነው አንድ የሚሆኑበትን ቀን የሚጠብቁበት ወቅት ነው እንጂ፡፡

ይህ ቁጥብነት የተሞላበት ክቡር ባሕላችን ምን ያህል ክብርን፣ አካላዊና ሥነ-ልቡናዊ ንጽሕናን የጠበቀ እንደሆነ ከጋብቻ በፊት በሚደረጉ ፆታዊ ግንኙነቶች ከሚፈጠሩ ውስብስብ ችግሮች የጸዳ እንደሆነ መረዳት የሚሳነው ሰው ይኖራል ብየ መገመት እቸገራለሁ፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ከባሕላችን ጋር ተቃርኖና ተጻርሮ ያለውን ግላዊና ማኅበራዊ ሕይዎታችንን አደጋ ላይ የሚጥልን ምዕራባዊ ባሕል ለማዋሐድ መሞከር ምን ያህል የተሳሳተ ብቻ አይደለም ኃላፊነትና ማስተዋል የጎደለው እንደሆነ ግልጽ ይመስለኛል፡፡ ይህንን የምዕራባዊያን ድርጊት ወይም ባሕል መዋሱ ትክክል ይሆን የነበረው ከላይ የገለጽኩት ባሕላችን የተገለጸውን ዓይነት መሆኑ ከሞራል(ከግብረ-ገብ)፣ ከሥነ-ምግባር፣ ከላቀ ሰብእና እነፃ፣ ከሃይማኖታዊ አስተምህሮዎች ወዘተ. አንጻር ችግር ያለበትና ነውረኛ ቢሆን ነበር፡፡ እንደምናየው ግን ያለው እውነታ የሚያሳየው ይህንን አይደለም፡፡ ከጋብቻ ውጪ ፆታዊ መወዳጀትን መቀበላችን የሰውን ክቡርነት፣ የሕይዎትን ዋጋ ውድነትና ልዕልና ተቀብሎ ከተቀረጸው የጸዳና ኃላፊነት የተሞላበት ወይም የሚሰማው ባሕላችን መተዋችን የዚህን ተቃራኒ ውጤት ወደሚያመጣ መሔዳችን መውረዳችንን መዝቀጣችንን እንጂ ከፍ ማለታችንን መላቃችንን የሚያሳይ አይደለም፡፡ በመሆኑም ያለንን የነበረንን ባሕል ልንንቅ ልንለቅና ልንለውጥ የምንችልበት አንድም አመክንዮ የለም ማለት ነው፡፡ ይህ በሆነበት ሁኔታ ይሄንን የባዕድ ባሕል ወደ ባሕላችን ስንቀላቅል እጅግ መሳሳትና መውረድ መሆኑ እርግጥ ነው ማለት ነው፡፡ ምንጊዜም ቢሆን በአመክንዮ ያልደገፍነው ወይም ልንደግፈው ያቃተን አስተሳሰብ ሥራ ላይ ስናውል ችግር ማጋጠሙ ዋጋ ማስከፈሉ የማይቀር ይሆናል፡፡ ምናልባት ይህ የጸዳው ባሕላችን የኑሮ ዘይቤ ጊዜ ያለፈበትና በዚህ ዘመን የሚኖረውም የሌለ ተደርጎ ይታሰብ ይሆናል የሚል ሥጋት አለኝ፡፡ ነገር ግን ፍጹም የተሳሰተና ያሉ ነባራዊ ሁኔታዎችን ያላገናዘበ እንደሆነ አበክሬ ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ከኢትዮጵያ ሕዝብ 85% በገጠሪቱ ኢትዮጵያ የሚኖርና ይህ የእኛ ባሕል ነው ብየ የገለጽኩትን የኑሮ ዘይቤ የሚኖር ነው፡፡ በባሕል መበረዝ እየተበከለ ያለው ሕዝብ በተቀረው 15% ከተማ ነዋሪ ያለው ሕዝብ ነው፡፡ ያም ቢሆን ሁሉም የከተማ ነዋሪ ለባሕል መበረዝ እጁን የሰጠ ነው ለማለት አይቻልም፡፡ በመሆኑም ስለዚህ ባሕላዊ እሴታችን መጠበቅ መከበር ማንሰራራት ለማውራት መምሸት አይደለም ገናም አልረፈደም፡፡

አንድ ጊዜ ምን ገጠመኝ መሰላቹህ ከፌስ ቡክ (ከመጽሐፈ-ገጽ) ጓደኞቸ አንዱ አንድ ፎቶ(ምስለ አካል) ለጥፎ ዐየሁ፡፡ በምስለ አካሉ ላይ ላሊበላ ቤተ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ላይ የባሕል ልብስ የለበሱ ወንድና ሴት ሆነው ወንድየው ከሴቷ ፊት ተንበርክኮ የጋብቻ ቀለበቱን እያሳያት እሷ በድንገቱ በመገረም አፏን በእጇ ጭና ያሳያል፡፡ በዚህ ምስለ አካል በርካታ የመጽሐፈ ገጽ ተጠቃሚዎች ደስ በመሰኘት ምስለ አካሉን ተጋርተው በየራሳቸው መጽሐፈ ገጽ ለጥፈውት ነበር፡፡ እኔ ግን ነገሩ አልተመቸኝም ነበርና ከስሩ ይሄንን አስተያየት አሰፈርኩ፡፡

ወንድሜና እኅቴ በቅድሚያ ለዚህ ስላበቃቹህ እንኳን ደስ አላቹህ፡፡ ስቀጥል የተሰማኝን እንድገልጽ ከፈቀዳቹህልኝ እኔ በዚህ ምስለ አካል ላይ አልተደሰትኩም፡፡ ምናልባት የባህል ልብስ ባታደርጉና ቦታውም ሌላ ቦታ ቢሆን ትንሽም ቢሆን መከፋቴን በቀነሰልኝ ነበር፡፡ ነገር ግን የባሕል ልብሳችንን ግጥም አድርጋቹህ እንዲህ አምሮባቹህ በዚህ በተቀደሰውና የኢትዮጵያዊነትን ልዕልና በሚመሰክረው ቦታ ላይ ከምዕራቡ ዓለም የተወሰደን ድርጊት መፈጸምህ ምን ያህል እንዳመመኝ ለመግለጽ እቸገራለሁ፡፡ እንደምታውቀው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ኢትዮጵያዊ የሆኑ እሴቶችን ሁሉ በመቅረጽ በመጠበቅና በመንከባከብ ትታወቃለች፡፡ ይሄንን ተግባር ስትፈጽምም ሌላ ፈጻሚ አካል ኖሮ ሳይሆን እኛው ልጆቿ አባቶቻችንን ፊት አውራሪ አድርገን ነበር ይሄንን ከባድ ኃላፊነት ስንወጣ የኖርነው፡፡ ነገሩ እንዲህ ሆኖ ሳለ ታዲያ እንዳለፉት ትውልዶች ሁሉ ማንነቱን ይጠብቅ ዘንድ ይልቁንም አሁን ካለብን በሉላዊነት(globalization) ከተሸፈነ ጫናና የባሕል ወረራ አንጻር ካለፉትም ትውልዶች በተሻለ ብቃትና ጥንካሬ ማንነቱን ለመጠበቅ ከባድ የታሪክ ኃላፊነት ከተጣለበት ከዚህ ትውልድ አካል የሆናችሁት ከባሕላችን ውጭና ባዕድ የሆነን ድርጊት የኢትዮጵያዊነትን ልዕልናና ድል በሚመሰክረው ሥፍራ ላይ ስታደርጉት ሳይ በጦርነት ድል ተደርገን በግዛታችን ላይ የጠላት ሰንደቅ ቢውለበለብ ሊሰማህ የሚችለውን ዓይነት የሚተናነቅ ስሜት ነው የተሰማኝ፡፡

በእኛ ባሕል እንዲህ ዓይነቱ ድርጊት ቦታ የለውም ሲጀመርም አንተ እሷን እሷም አንተን ስትቀራረቡ በምን ዓይነት አቀራረብ ለምን ዓይነት ጉዳይ እንደሆነ ማለትም ለትዳር መሆኑን ተማምናቹህ አስቀድሞ የጨረሳቹህት ወይም እንደምትጨርሱት የሚጠበቅ የሚታሰብ በመሆኑ ይህ ድርጊትህ ከባሕላችን አንጻር በጣም የራቀና የተሳሳተ ነው፡፡

ወደ ምዕራቡ ዓለም ዜጎች ስትሔድ ግን አንድ ወንድና ሴት በፍቅር መጎዳኘት ሲያስቡ ሦስት አማራጮች ክፍት በሆኑበት ሁኔታ ነው፡፡ ምን ማለቴ መሰለህ ትዳር የሚለው ነገር ከፊት ለፊት ያለ አማራጭ ሳይሆን መጨረሻ ደረጃ ላይ ያለ አማራጭ ነው፡፡ በየደረጃው አንደኛውን አማራጭ እየኖሩ ግንኙነታችን ተመችቶናል ወደሚቀጥለው ደረጃ ይደግ እያሉ ነው መጨረሻ ላይ ትዳር ላይ የሚደርሱት፡፡ ትዳር ብለው የሚሉትም የእኛ ባሕል ለትዳር እንደሚሰጠው ትርጉምና ክብር ክብደት ዓይነት እንዳይመስልህ፡፡ በተመሠረተ በቀናት ልዩነት ሁሉ ሊፈርስ ይችላል፡፡ ትዳራቸው ጣጣውና ችግሩ ብዙ ነው ይሄን ለመዘርዘር ጊዜ የለኝም ዋነኛው ችግሩ የሚመነጨው ግን አስቀድሞ በነበረው ግንኙነት ወቅት ፍቅራቸውን አጣጥመው ጨርሰው አርጅቶ ስለሚገቡበት ትዳር ውስጥ አዲስ ነገር በማጣት በቀላሉና ወዲያው የመሰለቻቸት ችግር ከማጋጠሙ የተነሣ ነው፡፡

ከእነዚህ ሦስት አማራጮች የመጀመሪያው አማራጭ ላልተወሰነ ጊዜ በመሀከላቸው ጥል ተፈጥሮ እስኪራራቁ ጊዜ ድረስ ወሲብን ጨምሮ በፍቅር ውስጥ ልንፈጽማቸው ይገባናል የሚሏቸውን ነገሮች ሁሉ እየፈጸሙ የሚኖሩበት አማራጭ ነው፡፡ ግንኙነቱ የፍቅር ጓደኝነት(love friend ship) ይባላል፡፡ በዚህ ሕይዎታቸው ደስተኞች ከሆኑ ልክ አሁን አንተ እንዳደረከው ወንድየው ተዘጋጅቶበት ይቆይና በድንገት የጋብቻ ቀለበቱን በማውጣት ግርምት ወይም ድንቀት(surprise) በመፍጠር ጥያቄውን ያቀርባል፡፡ ሴቲቱ ያሳለፉት ሕይዎት ለሷም ከተመቻት ፈቃደኛነቷን በመግለጽ በእሽታ ትቀበለውና ለጋብቻ ይበቃሉ ማለት ነው፡፡ ከሁለቱ አማራጮች መሀል ደግሞ አንድ ሌላ አማራጭ አላቸው እድሜአቸው ገፋ ሲል ወይም ደግሞ ፍቺ የፈጸሙ የሚኖሩት ኑሮ ነው እሱም ልክ ትዳር እንደመሠረቱ ጥንዶች ሁሉ ወንዱና ሴቷ ትዳር ሳይመሠርቱ በአንድ ቤት የሚኖሩበት አማራጭ ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ሕይዎት ሲኖሩ ግንኙነቱን የወሲብ አጋርነት(sexual partner ship) ይሉታል ወንዱ ሴቷን አጋሬ ሲላት ሴቷም ወንዱን እንደዚያው፡፡ ሲበቃቸውም የሚቀደድ ሰማኒያ ሳይኖር በቅተሽኛል በቅተኸኛል ሳይባባሉ እንደወጡ የሚቀሩበት የግንኙነት ዓይነት ነው፡፡

ወንድሜ ከእነዚህ ደረጃዎች ጀርባ ከሃይማኖትና ከባሕል አንጻር የሚወገዙ ስንት አስተሳሰቦች አሉ መሰለህ፡፡ እንዱንና ዋነኛውን ብነግርህ “መጣጣምን” ለማወቅ ሲባል እንደሆነ ያወራሉ፡፡ እንግዲህ ከነዚህ ከነዚህ ጉዳዮች አንጻር ነው ይህ አሁን አንተ ያደረከው ድርጊት ያልተመቸኝ፡፡ ከጀርባው እንዲህ ያለ ከእኛ ባሕልና ሃይማኖት አንጻር የሚቃረን የሚወገዝ የማይበረታታ የሕይዎት ጉድ ያለበት በመሆኑ ይህ ያደረከው ነገር ትክክል አይደለም፡፡ ምናልባት ግን ይህ ያደረከው ነገር ምንም እንኳ የምዕራባዊያኑ እንጂ የእኛ ባይሆንም ቅሉ በገለጽኩት ዓይነት የምዕራባዊያን የፍቅር ሕይዎት ሳታልፉ ማለትም ከጋብቻ በፊት በግብር ሳትተዋወቁ (ወሲብ ሳትፈጽሙ) ቆይታቹህ በእግዚአብሔር ቤት እንዲህ ዓይነቱን ቃል የተቀደሰ ጥያቄ ባቀርብ ተገቢ ነው ብለህ አስበህ ጥያቄውን አቅርበህ ከሆነ ይቅርታህ ይድረሰኝ፡፡ ነገር ግን እሱም ቢሆን አሁንም በባሕላችን በሃይማኖታችንም ቀለበት የሚታሠረው በካህን ቡራኬ በመሆኑ ይህ የገለጽክበት መንገድ ትክክል አይደለም ማለት ነው፡፡ እናም ወንድሜ ግድ የለህም ይህ ምስለ አካል(ፎቶ) በተለይ ደግሞ በእግዚአብሔር ቤት የባሕል ልብሳችንን በለበሳቹህ ምእመናን መፈጸሙ ምን ያህል ለምዕራቡ ዓለም የባሕል ወረራ መንበርከካችንን መሸነፋችንን መማረካችንን እጅ መስጠታችንን ነውና የሚያሳየው እባክህን አንሣው? ብየ አስተያየቴን አሠፈርኩ፡፡ እሱም እግዚአብሔር ይስጠውና ጥፋት መሆኑን ተረዳ መሰለኝ ያንን ምስለ አካል ወዲውኑ አነሣው፡፡

እንግዲህ ቫላንታይንስ ዴይ ተብሎ እየተከበረ ያለው የምዕራባዊያኑ በዓል በእንዲህ ዓይነት “የፍቅር” ገጽታና ቅኝት ስለሆነና እዚህም እየተከለ ያለው ተመሳሳዩን ገጽታና ቅኝት በመሆኑ ሃይማኖታዊ አስተምህሮን መሠረቱ ካደረገው ባሕላችን ጋር ፍጹም የማይስማማና የማይጠቅምም ሆኖ እናገኘዋለን፡፡ ለነገሩ በምዕራቡም ዓለም ቢሆን ይህ በዓል ሙሉ ለሙሉ ተቀባይነት ያለው በዓል አይደለም፡፡ የዚህ በዓል ታሪካዊ ዳራ የካቶሊኮች ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ፕሮቴስታንቶች አይቀበሉትም፡፡ እነዚህ ሁለቱ እምነቶች “በሃይማኖት” ልዩነት ምክንያት በተለያየ ጊዜ እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ አውሮፓ ጦርነት ወይም ግጭት እስከማድረግ የደረሱ ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ አንደኛው ለሌላኛው እሴት አክብሮት የለውም፡፡ በመሆኑም ፕሮቴስታንት የሆኑ ሀገራት ቦታ የሚሰጡትና የሚያስቡት በዓል አይደለም፡፡ ጨርሶም የማያውቁት አሉ፡፡

የአበባ ስጦታና ባሕላችን ያላቸው ግንኙነትና ቁርኝት?

ከቫላንታይንስ ዴይ ጋራ ተያይዘው ከሚከወኑ ኩነቶች ውስጥ የስጦታ ልውውጥ በተለይም የአበባ ስጦታ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች እኛ ኢትዮጵያዊያን የአበባ ስጦታ የማበርከት ባሕል እንደሌለን አድርገው ያስባሉ፡፡ እውነታው ግን ከዚህ በእጅጉ የተለየ ነው፡፡ እንዲያውም ሲመስለኝ ሲመስለኝ ፈረንጆቹ አበባን የማበርከት ባሕል የወሰዱት ከእኛ ነው፡፡ ምክንያቱም እኛ በባሕላችን ምድረ አውሮፓ ከነመፈጠሩ እንኳ በማይታወቅበት ዘመን ለተለያዩ ጉዳዮች አበባን የማበርከት ልማድ ወይም ባሕል ስንፈጽም እንደኖርን ታሪካችን ያስረዳናልና፡፡ በቤተክርስቲያናችን ማለትም በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበባ እጅግ የከበረ ስጦታ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ኢትዮጵያዊ ባሕል ወይም እሴት ነው ተብሎ የሚታወቀውን ባሕልና እሴት በመቅረጽ በኩል የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ሚና ጎልቶ ይታያል፡፡ ያሉንን ኢትዮጵያዊ መገለጫ ያላቸውን ባሕላዊ በዓላትና ኩነቶችን መለስ ብለን ብናጤን ሃይማኖታዊ አሻራ የሌለበት አንድም እንኳን አታገኙም፡፡ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አበባ ለየት ያለ ሥፍራና አግልግሎት አለው፡፡ ለአብነት ያህል ሦስቱን እጠቅሳለሁ፡-

  1. ቤተክርስቲያን ካሏት አጽዋማት ውስጥ ዋነኛ በሆነው በዐቢይ ፆም መጨረሻ በሕማማት ሳምንት የጌታችን የአምላካችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስቅለት በሚታሰብበት ቀን በመስቀሉ ስር ላይ ጽጌረጋ አበባ በመነስነስ ለክርስቶስ እንዲበረከት “ግብረ ሕማማት” የሚባለው መጽሐፍ በሚያዘው መሠረት በየዓመቱ ይህ ይፈጸማል፡፡
  2. “ጽጌ” ፆምን የተመለከተው ነው፡፡ የጌታንና የተወዳጅ እናቱን ወደ ግብጽ መሰደድ ለማሰብ የሚፆም ፆም ነው፡፡ የዚህች ፆም ሥያሜ “ጽጌ” የሚለው ቃል ሲተረጎም አበባ ማለት ነው፡፡ የዚህ ምክንያቱ ቅዱሳን አባቶቻችን በመጻሕፍቶቻቸው እመቤታችንን በአበባ ስለመሰሏት አንዱ ምክንያት ሲሆን ልላኛው ምክንያት ደግሞ ወቅቱ የአበባ ወቅት ስለሆነ በወቅቱ ሲጠራ ነው፡፡
  3. ሌላኛው ደግሞ በኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን አንድ ዓመታዊ በዓል አለ መስከረም 10 ይውላል፡፡ ሥያሜው “ተቀጸል ጽጌ” (አበባን ተቀዳጅ) ይባላል፡፡ ቤተክርስቲያን ንጉሡን እንኳን ለአዲሱ ዓመት አደረሰህ የምትልበት በዓል ነው፡፡ የጸሎቱና የቅዳሴው ሥርዓት ከተፈጸመ በኋላ ካህናት በደመቀ የዝማሜ፣ የማስረገጥ፣ የወረብ፣ የሽብሻቦ፣ መዝሙር ታጅቦ ንጉሡንና ንግሥቲቷን እንኳን አደረሳቹህ በማለት አበባ የሚያበረክቱበት በዓል ነበር፡፡

በተጨማሪም ሃይማኖታዊ ብቻ ሳይሆኑ ባሕላዊ ከሆኑትም በዓላቶቻችን ሁለቱን ስጠቅስ አንደኛው ድርጊቱ ከንግሥተ ሳባ ና ከእንቁጣጣሽ ታሪክ ጋራ ተያይዞ ይጠቀስ እንጂ ከዚያ አስቀድሞም ይፈጸም እንደነበረ ይገመታል፡፡ እሱም ልጃገረዶች የአበባየሁሽን ጭፈራ እየጨፈሩ የአበባ ስጦታን ለወላጅ ለጎረቤት ለዘመድ አዝማድ እንኳን አደረሳቹህ እያሉ የሚያበረክቱበት በዓል ነው፡፡ ሌላኛው ደግሞ የመስቀል በዓል ነው፡፡ የመስቀል በዓል ሲከበር ደመራው የእኛ ብቻ በሆነውና ሌላ ቦታ ጨርሶ በማይበቅለው ሁሌም አዲስ ዓመትን በሚያበስረን አደይ አበባችን አጊጦ የሚደመረው በዓል ነው፡፡ እናም እነኝህ እነኝህ መረጃዎች እንደሚያረጋግጡት የአበባና የሐበሻ ቁርኝት ቀደምቱና ጥንታዊው ታሪካችን ከሚጀምርበት አንሥቶ የነበረ በመሆኑ ከማንኛውም ሀገር የላቀና ለሌሎቹ አርአያ እንደሆነ በቀላሉ መታዘብ ይቻላል፡፡ የዚህ ዘመን ሰው ግን እንዲህ ዓይነት ታሪኮቻችንን ስለማያውቅ የአበባ ስጦታ ወይም አበባን ማበርከት የእኛ ባሕል ያልሆነ ከባእድ የመጣ ይመስለዋል፡፡ እውነቱ ግን ከላይ እንደተገለጸው ነው፡፡ እናም አበባ ስታበረክቱ የእኛን የራሳችንን ባሕል እየፈጸማቹህ እንደሆነ በማሰብ እንጅ ከፈረንጅ በተውሶ የመጣን ባሕል እየፈጸማቹህ እንደሆነ ተደርጎ እንዳይታሰብ መጠንቀቅ ያሻል፡፡

ይህ “ቫላንታይንስ ዴይ” ባዕዳዊ በዓል ከማኅበራዊ ሕይዎት አንጻር እንዴት ይታያል?

ይህንን በዓል ከማኅበራዊ ሕይዎትም አንጻር ስናየውም የምንጎዳበት ወይም የምናጎልበት እንጂ የምናተርፍበት ሆኖ አናገኘውም፡፡ ብዙዎቻችን እንደታዘብነው ሁሉ በዚህ በዓል ቀን ወላጅና ልጅ ግጭት ውስጥ የሚገቡበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ችግሩ ጎልቶ የሚታየው ለአቅመ ሔዋን ባልደረሱ ሴቶች እኅቶቻችን ላይ ነው፡፡ በዚህ የእድሜ ደረጃ ያሉ ልጆችን በዓሉ በዚያ ሳቢና አባባይ ድምቀት ሲከበር ሲያዩ በሚፈጥርባቸው መነሣሣትና ጉጉት ያለ ወንድ ጓደኛ መሆናቸው ባዶነትና ወደ ኋላ መቅረት ወይም ያለመሠልጠን ሆኖ እየታያቸው ያለ ዕድሜያቸው የወንድ ጓደኛ እንዲይዙ ከባድ ጫና እያሳደረባቸውና ችግር ላይ እየጣላቸው ይገኛል፡፡ ጓደኛ ከያዙም በኋላ በሌሎች ጊዜያትም ሆነ በበዓሉ ቀንም በዓሉን ለማክበር በሚል ከወንድ ጓደኞቻቸው ጋር በሚሔዱባቸው ቦታዎች ላልጠበቁትና ላልፈለጉት ችግር መዳረጋቸው የተለመደ ዜና ሆኗል፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኤድስን ጨምሮ በሚከሰቱ የተወሳሰቡ ተያያዥ ችግሮች ቅድመ ጋብቻ ምንም ዓይነት ግንኙነት አለመጀመር መፍትሔ መሆኑ በታመነበት ዘመን ይሄንን መግባባት አፍርሶ እንደገና ወደ ኋላ የሚመልስን አፍራሽ ተግባር መከወን እውነት ያለመብሰል ብቻ ሳይሆን የለየለት ጠላትነትም ነው፡፡

በመጨረሻም ይሄንን ጣጣ ላመጡብን ምን እየሠሩ እንደሆነ በውል ለይተው ለማያውቁት “የመዝናኛ ዝግጅት” አዘጋጆች ማስገንዘብ የምሻው ጉዳይ አለ፡፡ አንድን ነገር ከሌላ አምጥታቹህ ከመዘርገፋቹህ በፊት እባካቹህ ከተለያየ አቅጣጫ ለመመርመር ሞክሩ፡፡ ይህን በማድረጋቹህ የምትጠቀሙት ነገር ቢኖርም እንኳ በሀገርና በሕዝብ ላይ የሚፈጥረው ችግር የእናንተም መሆኑ አይቀርምና አስፍታቹህ ለማሰብ ሞክሩ፡፡ በአሁኑ ሰዓት ይሄንን ዕድል የሰጧቹህን አካላት ከመለመን ከማሳሰብ ከማስገንዘብ ይልቅ እናንተን መለመኑ ማሳሰቡ ሳይሻል አይቀርም፡፡ አነሱ እዛ ላይ ቁጭ ብለው ምን እንደሚሠሩ እንደሚውሉ አልገባ ብሎኝ በጣም ተቸግሬያለሁ፡፡ እናም ወደናንተው ልመለስና እንዲሁ ስታስቡት የቸገረን ነገር ይሄና መሰል ድርጊቶች ናቸውን? ከዚህ ይልቅ ምናለ በቸገረንና ሊኖረን በሚገባው ነገር ላይ ብታተኩሩ ብትተጉ ብትረባረቡ? እንዲህ እንደቀላል የሚወራ ወሬ ስታጡ የአየር ሠዓት ለመሙላት ብቻ ቀበጣጥራቹህት የምትወጡት ነገር ለእናንተ ቀላል መስሎ ቢታያቹህም ሀገርን ማፈራረስ የሚያስችል አቅም አለው እያፈራረሰንም ይገኛል፡፡ እንደዜጋና እንደሚያስብ ሰው ይሄንን ላትረዱ የምትችሉበት ምንም ዓይነት ምክንያት ይኖር አይመስለኝም፡፡ ከስሜታዊነት ይልቅ ዕውቀትን ከግል ጥቅም ይልቅ ሀገርንና ሕዝብን የማስቀደም የሐሳብ መሠረት ላለው ሰው ይህ ፈጽሞ የሚቸግር ጉዳይ አይሆንም፡፡

ልጆች በተለይም ሴቶች በትምህርት ላይ እያሉ ወደ እንደዚህ ዓይነት ግንኙነት እንዲገቡ የማይመከረው ያለወቅቱ ወሲብ በመጀመራቸው ምክንያት ከወሲብ ጋራ ተያይዘው ተግተልትለው ከሚመጡት ዓይነተ ብዙ ሕይዎትን ከሚያሰነካክሉ ከባባድ ችግሮች ባሻገር ትኩረታቸው ሙሉ በሙሉ ስለሚሰርቅ አቅጣጫውን ስለሚያስተው ነው፡፡ ትምህርት በራሱ የሙሉ ጊዜ ሥራ ነው ሙሉ ጊዜን ለትምህርት አትኩሮት ሰጥተውትም ከስኬት ለመድረስ ስንት ፈተናዎች አሉት በዚህ ላይ ያለጊዜው ያለ ቦታው ፍቅር ውስጥ ከተገባ ለትምህርት ልንሰጠው የሚገባው ትኩረት ከመሰረቁ ጋር በተያያዘ ምን ያህል የብቃት መውረድ መንሸራተት መጎዳት ሊያጋጥም እንደሚችል በሁሉም ሰው ግንዛቤ ውስጥ ያለጉዳይ ነው፡፡ ፍቅር ቀናተኛ ነው ሙሉ ትኩረት ስጡኝ ባይ ነው፡፡ እንቅልፍና ምግብ እስከመከልከል ከዚያም አልፎ እስከማሳበድም ይደርሳል፡፡ ታዲያ እንዲህ ዓይነት ነገር ውስጥ ተገብቶ ትምህርን ያህል ከባድ ሥራና ኃላፊነት ወይም ጥናት እንደምን በብቃት መወጣት ይቻላል? ይሄም በመሆኑ ነው በተለይ ሴቶቻችን በየከፍተኛው የትምህርት ተቋማቱ የገቡትን ያህል ሳይሆን ለመጥቀስ በሚያሳፍር እጅግ በጣም እጅ ብቻ ለመመረቅ የሚበቁት፡፡ ከዚህ ችግር አምልጦ በትምህር መስክ ለስኬት ለመብቃት ያለው ብቸኛ አማራጭ ይደረስበታል የራሱ ጊዜ አለው በሚል የበሰለና አርቆ ማሰብ የታከልበት ውሳኔ ፍቅርን ከትምህርት ወይም ከምረቃ በኋላ መቅጠሩ ብቻ ነው፡፡ እንደምናየውም ትምህርታቸውን በብቃት ተወጥተው በግሩም ነጥብ የሚመረቁት እራሳቸውን ከእንደዚህ ዓይነት ጉዳይ የቆጠቡት ናቸው፡፡

ወጣቱ ከዚህ የበሰለ ውሳኔ ደረጃ ላይ እየደረሰ በላቀ ብቃት ህልሙን እንዲያሳካ ለማስቻል የሁሉም ርብርቦሽ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ በተለይም የብዙኃን መገናኛው እጅግ ከባድ ኃላፊነት አለበት፡፡ እዚያ ላይ የተቀመጡ የየዝግጅቱ አዘጋጆች ባለሞያዎች ለመልካም ሰብእና ምሳሌና አርአያነት ያላቸው ሊሆኑ የግድ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ደረጃ የሚታዩ ካልሆኑም ሁለተኛው አማራጭ ካሳለፉት ከየግል የሕይዎት ተሞክሮዎቻቸውና ከውድቀት ጥንካሬዎቻቸው ወጣቱ እንዲማር የማድረግ ከባድ ኃላፊነት አለባቸው፡፡ ነገር ግን እኛንም የበላ ጅብ ይብላቹህ በሚል የደነቆረና እጅግ ኃላፊነት የጎደለው የምቀኝነት ፈሊጥ ምኑንም የማያውቀውን ወጣት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዲነጉድና እንዲጠፋ ማድረግ ቃል ሊገልጸው የማይችለው ድንቁርናና ከጠላትነት የከፋ ጠላትነት ነው፡፡

ከዚህ ሁሉ ነገር በኋላ የተገለጹት ቁም ነገሮች ለማይዋጡለትና መናኛ የግል ጥቅሙ የሚበልጥበት የጥፋት ዓላማ ላለው የመከነ ዜጋ ግን መድኃኔዓለም ክርስቶስ ልብ ይስጥልን ልብ የማይገዙና ሰይጣን ያገበራቸው ከሆኑ ግን ሳያጠፉን በፊት ይቅደምልን ጉልበታቸውን ቀጤማ ያድርግልን ከማለት ውጪ ምን ማለት ይቻላል ወገን?

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

 

 

The post ቫላንታይንስ ዴይ (የፍቅረኞች ቀን) appeared first on Zehabesha Amharic.

ላልቀረልን ሀገርንና ሕዝብን የመታደግ ትግል ተነሡ! –ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

$
0
0

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

amsalugkidan@gmail.com

ላልቀረልን ሀገርንና ሕዝብን የመታደግ ትግል ተነሡ!

Amsalu

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

ሥልጣንን ይዞ ሀገርንና ሕዝብን ለማሥተዳደር ሁለት የትግል አማራጮች አሉ፡፡ በሀገራችን ሁለቱም ዓይነቶች በሚገባ ይታወቃሉ ተሞክረዋልም፡፡  አንደኛው ሕዝብ በሚያደርገው ምርጫ የመንግሥትነት ሥልጣንን መያዝ መሠረቱ ያደረገው ሰላማዊ የትግል አማራጭ ሲሆን፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ይህ ሰላማዊ የትግል አማራጭ ዝግ ሲሆን ወይም ሊሠራ በማይችልበት ጊዜ በሕዝብ ላይ በኃይል የተጫነን አንባገነን አገዛዝን በኃይል ለማስወገድ የሚደረግ የኃይል እንቅስቃሴዎችን መሠረቱ ያደረገ የትጥቅ ወይም የዐመፅ የትግል አማራጭ ነው፡፡ እስኪ ሰላማዊው የትግል አማራጭ በዘመነ ወያኔ ምን እንደሚመስል በአጭሩ ዕንይ፡፡

ወያኔና ምርጫ፡-

በዘመነ ወያኔ ምርጫ እየተባለ ለአራት ጊዜያት ያህል በሕዝብና በሀገር ላይ ከባድ ቀልድና ሹፈት ሲቀለድና ሲሾፍ ሲፌዝ ተቆይቷል አሁን ደግሞ ለአምስተኛ ጊዜ እየተሾፈና እየተቀለደ ይገኛል፡፡ በዘመነ ወያኔ ምርጫ ተደርጎ አያውቅም፡፡ ይህ ሐቅ ከአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር (State department) እስከ የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ድረስ በሚሰጧቸው መግለጫዎች በተደጋጋሚ ያረጋገጡት ሀቅ ነው፡፡ ዐይኑን ጨፍኖ ለመሞኘት የፈቀደ ካልሆነ በስተቀር በሁሉም ዜጋም በሚገባ ይታወቃል፡፡ አገዛዙ ፍትሐዊና ትክክለኛ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል አቅም ፍላጎትና ተፈጥሮ ከቶውንም ኖሮት አያውቅም መቸምም ደግሞ አይኖረውም፡፡

ለዚህ በርካታ ምክንያቶችን ልንጠቅስ እንችላለን፡፡ አንዱና ዋነኛው ግን አገዛዙ እንደዚህ ዓይነቶችን የዲሞክራሲያዊ (የበይነ-ሕዝባዊ) መንግሥታት መርሆዎችን ለመቀበልና ለመተግበር የሚያስችለው ተፈጥሮና አስተሳሰብ የሌለው በመሆኑ ነው፡፡ ይሄንን ባሕርይውን ከትግል ዘመኑ ጀምሮ ባለው ታሪኩ ማንነቱና ሰብእናው ማረጋገጥ ይቻላል፡፡ ነገር ግን በዚህ በ21ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አሁን ድረስ ንጉሣዊ የመንግሥት ሥርዓት ካላቸው ጥቂት ሀገራት በስተቀር በመላው ዓለም ኅብረተሰብ ዘንድ “ሥልጣን የሚያዘው በሕዝብ ምርጫ ይሁንታ ነው” የሚለው አስተሳሰብ ገዥና ተቀባይነትን ያገኘ አስተሳሰብ በመሆኑ ምክንያት እንደ ወያኔ ያሉ አንባገነናዊ አገዛዝ ከእነሱ አስቀድመው የነበሩትን መንግሥታት በኃይል ካስወገዱ በኋላ በያዙት ሥልጣን ላይ ለመቆየት ያላቸው አማራጭ ምንም ዓይነት ፋይዳና ትርጉም የሌለው የይስሙላ ምርጫ አዘጋጅቶ በማኪያሔድና በሕዝብ ተመረጥን እያሉ በማጭበርበር ሥልጣንን ጨምድዶ ይዞ መቆየት ግዴታ ስለሆነባቸው በከፍተኛ ሸርና ጥንቃቄ ያንን የይስሞላ ምርጫ ወቅቱን እየጠበቁ ያደርጋሉ፡፡

የሚገርመው ግን አሁንም ድረስ ዜጎች እውነት መስሏቸው የወያኔን ተፈጥሮና አቋም ካለማወቅ ይሁን ተስፋ ካለመቁረጥ አገዛዙ አካሂደዋለሁ በሚላቸው ምርጫዎች በመምረጥና በመመረጥ ለመሳተፍ ፓርቲ እያቋቋሙ መንቀሳቀቃቸው ነው፡፡ የሚያሳዝነው እነኝህ ፓርቲዎች የመድብለ ፓርቲ የመንግሥት ሥርዓት ደንብና ሕግ በሚፈቅድላቸውና በሰጣቸው መብት መሠረት ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት በነጻ መደራጀትና መታገል የሚችሉበትን ዕድል ለአንድም ጊዜ እንኳን አግኝተው አለማወቃቸው ነው፡፡ አገዛዙ ከመጀመሪያው ጀምሮ ሌላ ሥራ ትቶ ዲሞክራሲያዊ (በይነሕዝባዊ) ነኝ እያለ ግን ለሀገርም ለወገንም ለማንም በማይጠቅም ሁኔታ ሥራየ ብሎ መንገዳቸውን በመሰናክሎችና ሸር አጥሮ እንዳይፈናፈኑ እንዲኮሰምኑ ሲያደርጋቸው ቆይቷል፡፡ ይሄንን ሁሉ ተቋቁመው ለመውጣት ሲሞክሩም መከፋፈልና መሰነጣጠቅ አንድን ፓርቲ ምን ያህል እንደሚያሽመደምድ እንደሚዶዳ ከማንም በላይ ከበረሃ ጀምሮ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ በኋላም በራሱ ላይ በተደጋጋሚ ደርሶበት ያውቀዋልና ሰርጎ እየገባ ይከፋፍላቸዋል ይሰነጥቃቸዋል ከዚያም ይበትናቸዋል፡፡ እንዲህ ያደርግና ሲያበቃ ደግሞ ለባዕዳኑ “ጠንካራ ተፎካካሪ ፓርቲ አላደለንም ለዚህ ነው ሥልጣኑ በእኛ ብቻ የተያዘ ሊሆን የቻለው” እያለ ይሳለቃል፡፡ በዘመነ ወያኔ የፓርቲዎች ሕይዎት በእንዲህ ዓይነት ሁኔታ የተመሰቃቀለ እንደሆነ ዛሬም ድረስ አለ፡፡

አገዛዙም በተለያየ ጊዜ በሚያደርጋቸው የይስሙላ ምርጫዎች የበይነ ሕዝባዊ (የዴሞክራሲያዊ) ሥርዓት ያለ ለማስመሰል ብቻ በጣት የሚቆጠሩ ተወዳዳሪ ወገኖችን ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክርቤት እንዲገቡ ከሚያደርጋቸው ውጭ ሕዝብ በሰጠው ድምፅ መሠረት መንግሥት እንዲመሠረት ፈቅዶና ፈልጎ አስቦም አያውቅም፡፡ በእርግጥ ከምርጫው ሐሰተኝነት የተነሣ እነኝህ ዜጎች በተሳተፉባቸው የውሸት ምርጫዎች ውጤት አግኝተው ትርጉም ያለው የፖለቲካ (የእምነተ-አሥተዳደር) ሥርዓት ሽግግርና እድገት ማስመዝገብ ባይቻልም ምንም የተከሩት የፈየዱት ነገር የለም ማለት ግን አይቻልም፡፡ ቢያንስ የአገዛዙን የምርጫ ድግሶችን ሐሰተኝነት በሚገባ ማጋለጥ ችለዋልና ከዚህ አንጻር የነበራቸው ተሳትፎ ፋይዳ ነበረው ማለት ይቻላል፡፡

ወያኔ እነዚያን ሐሰተኛ ምርጫዎች ሲያስፈጽም መጨረሻ ላይ እሱ የሚፈልገው ውጤት እንዲገኝ የሚያደርግባቸው 3 ዋና ዋና ስልቶች ወይም መንገዶች ዘሉት፡-

  1. የምርጫውን ሒደት እሱ በፈለገው መንገድ የሚዘውር ለእሱ ታማኝ የሆነ ምንደኞች ርካሾችና ቆሻሾች የሞሉበት የይስሙላ የምርጫ ቦርድ ማቋቋም፡፡
  2. ወደ ፖለቲካ ፓርቲዎች (የእምነተ-አሥተዳደር ቡድኖች) አባሎቹን አስቀድሞ አስርጎ በማስገባት የተለያየ ሴራ እንዲሸርቡ በማድረግ ፓርቲዎቹ የሚጠበቅባቸውን የፖለቲካ ሥራዎች በአግባቡና በብቃት እንዳይከውኑ ማድረግ፣ ስምምነትና አንድነት ማሳጣት፣ አቅማቸው የተዳከመ እንዲሆን ማድረግ፣ በተፈለገ ጊዜ መሰንጠቅና ማፍረስ ወይም መበተን ወዘተ.
  3. ትክክለኛና ፍትሐዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችል ምቹ ሁኔታ እንዳይኖር ማድረግ፡፡ ለምሳሌ፡- ምርጫ በመጣ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከምርጫ ወቅት ውጭ ባሉ ወቅቶችም ጭምር የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ከሕዝብ ጋር ሊገናኙና አቅድ መርሆዎቻቸውን ለሕዝብ ማድረስ ማስተዋወቅ የሚችሉባቸውን ሕገ መንግሥታዊ የብዙኃን መገናኛዎችን ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታና ቅድመ ምርመራ የመጠቀምና በስብሰባ በሰላማዊ ሰልፎች ገጽ ለገጽ ከሕዝብ ጋር ሊገናኙ የሚችሉባቸውን ሕገ መንግሥታዊ መብቶችንና ዕድሎች እንዳያገኙ እንዳይጠቀሙ በመንፈግ በመከልከል፣ ሕዝቡ በሕገ መንግሥታቸው የተረጋገጠለትን መብት ተጠቅሞ ያለ ሥጋትና ፍርሐት ያመነባቸውንና የተቀበላቸውን ፖለቲካ ፓርቲዎችን እንዳይደግፍ በአባልነትም እንዳይሳተፍ ማድረግ፣ አድርጎት ሲገኝም የሥራ ዋስትናውን ከማሳጣት ጀምሮ በዜግነቱ ሊያገኛቸው የሚችላቸውን መብትና አገልግሎቶች እንዳያገኝ በማድረግ ከዛም አልፎ እስር እንግልትና ሰቆቃ በመፈጸም በተለያየ መንገድ ሌላው እንዲያውቀውና በመቀጣጫነት እንዲገነዘበው በማድረግ ሕዝብ እንዲርቃቸው እንዳይከተላቸው ማድረግ ወዘተ. ናቸው፡፡

እነኝህን የሚያካክሉ ግዙፍ ግዙፍ መሰናክሎች ባሉበት ሁኔታ በምንም ተአምር ቢሆን እንደየትም ተሁኖ ትክክለኛና ፍትሐዊ ምርጫ ማድረግ የሚታሰብ አይደለም፡፡ አገዛዙ በእነኝህ ሠርና ክፋትና ኢፍትሐዊ ተግባሮቹ ውጤቶች በመመካትና በተሳሳተ ግንዛቤ ለሕዝብ ከነበረው ንቀትና ዝቅጠኛ ግምት ተደፋፍሮ ለምዕራባዊያን አጋሮቹ የገባውን ቃል ለመጠበቅ ሲል በምርጫ 97ዓ.ም. ሰጥቶት በነበረው ሰፋ ያለ ዕድል ፈጽሞ ያልጠበቀውና ያላሰበውን ውጤት ስላስከተለበት “ኧረ! እኔ ውጤቱ እንደዚህ የሚሆን ስላልመሰለኝ ነው እንጅ እንደዚህማ በጭራሽ አይሆንም አይደረግም!” በማለት በአንጻራዊ መልኩ ሲታይ መልካም የነበረውን የምርጫ ሒደት ከምርጫው ማግስት ጀምሮ በመቀልበስ የሕዝብን ድምፅ በሕዝብ ደም አጥቦ ገደል በመክተት ሁለተኛ በእንደዚህ ዓይነት ተመሳሳይ ቅሌት ውስጥ እንደማይገባ ለራሱ ምሎ ወደ ነበረበት ቦታው ተመልሷል፡፡ በዚህም ምክንያት በ2002ዓ.ም. ላይ አስቂኝ በሆነ ሁኔታ ምርጫ አደረኩ ብሎ 99.6 በመቶውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫን አሸንፌ መንግሥት መሠረትኩ ብሎ እየገዛ ይገኛል፡፡

ወያኔ በምንም ተአምር ትክክለኛና ፍትሐዊ ምርጫ ሊያደርግ እንደማይችልና የማይችልበትን የማይፈልግበትን ምክንያት ከዓመታት በፊት ጀምሮ ስገልጽ እንደቆየሁ ይታወሳል፡-

  1. አገዛዙ ከማንነቱና የሚታወቅባቸው በግልጽም በስውርም የያዛቸው ፖለቲካዊ ዓላማና ጥቅሙ የተነሣ ለምሳሌ፡- ከገጠር እስከ ከተማ ሕዝቡ በትውልደ ትውልድ እየወረሰው የመጣውን የኖረበትን መሬቱን እየተነጠቀ ለባለ ሀብት እየተሰጠበት በገዛ ሀገሩ ሀገር አልባ መኖሪያ አልባ ስደተኛ የሚያደርገው ፖሊሲው (መመሪያው) እና በሌሎቹም የሀገርንና የሕዝብን ጥቅም የሚጎዱ ሥራዎቹ በኃይል ካልሆነ በስተቀር በትክክለኛና ፍትሐዊ በሆነ ምርጫ በሕዝብ ዘንድ ተመራጭ እንደማያደርገው ስለሚያውቅ፡፡
  2. አገዛዙ ከቅጥረኛነቱና አንባገነንነቱ የተነሣ በፈጸማቸው ኢፍትሐዊና ከባባድ የሀገር ክህደቶች፣ በርካታና እጅግ የገዛዘፉ የሙስና ወንጀሎች፣ በግፍ ባፈሰሰው የንጹሐን ዜጎች ደም በመሳሰሉት ወንጀሎቹ ምክንያቶች ሥልጣን በለቀቀ ማግስት እየታነቀ ለፍርድ እንደሚቀርብ ስለሚያውቅ፡፡
  3. ፀረ ኢትዮጵያና ሕዝቧ የሆኑ ከጠባብ ደንቆሮና ጎጠኛ ማንነቱ የተነሣ የፈጸማቸው እየፈጸማቸው ያሉትና ሊፈጽማቸው የሚፈልጋቸው የጥፋት ዓላማዎቹ በአስተማማኝ መልኩ ገና ከግብ ስላልደረሱለትና እነሱን ከግብ ለማድረስ ካለው ጽኑ ዓላማና ፍላጎት የተነሣ፡፡
  4. አገዛዙ ማንነቱ በሕዝቡ ዘንድ ከመቸውም ጊዜ በላይ በሚገባ ከመታወቁ ጋር በተያያዘ ከደረሰበት የሞራል ኪሳራ የተነሣ በራስ መተማመኑ ስለጠፋ፡፡

በእነዚህ ሦስት ዋና ዋና ምክንያቶች ወያኔ በኃይል ተገዶ ካልሆነ በስተቀር ምርጫን መሠረቱ ባደረገ ሰላማዊ የትግል አማራጭ መሸነፉን አምኖ ፈጽሞ ሥልጣንን እንኩ ብሎ ሊያስረክብ ስለማይችል በምርጫ ሥልጣን መረከብን ተስፋ አድርገው እየተሳተፉ ያሉ ወገኖችን ለወያኔ የሕዝብ ግንኙነት ፍጆታና የውጭ የፖለቲካ ግንኙነት ፍጆታ መጠቀሚያ ከመሆን በስተቀር የምታልሙትንና የምትመኙትን ያህል ምንም ልትፈይዱ የምትችሉት ነገር የለም ጊዜያቹህን በከንቱ እያጠፋቹህ ሕዝብንም ተስፋ የማይደረግ ነገርን ተስፋ አድርጎ ቶሎ ነቅቶ ማድረግ ያለበትን ነገር አድርጎ ሀገሩንና እራሱን እንዳይታደግ እንዲዘናጋ እያደረጋቹህትና ወያኔ ለጥፋት ዓላማው ተጨማሪ የማጥፊያ ጊዜ እንዲያገኝ እየረዳቹህት ነውና ኧረ እባካቹህ ንቁ? እያልኩ ሳሳስብ መቆየቴ የሚታወስ ነው፡፡

ዘንድሮ ግን ወያኔ ማንነቱን ሕዝቡ ጠንቅቆ ከማወቁና በሚፈጽማቸው በደሎችና ግፎች ከመንገሽገሹ የተነሣ በተፈጠረበት እጅግ በጣም ከባድ በራስ ያለመተማመን ችግር እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ለተቃዋሚ ወይም ለተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ከገዛ ሕገ መንግሥቱ ድንጋጌዎች በተጻራሪ ነጻነታቸውንና መብቶቻቸውን እየከለከለ በራሱ ፍላጎት ብቻ በጠባቡ ከልሎ የሚሰጣቸውን የመጫዎቻ ሜዳም እንኳን ሊሰጥ በፍጹም አልፈለገም፡፡ እንደወያኔ አስተሳሰብ ይሄ ስልቱ ጊዜው አልፎበታል ተበልቶበታል፡፡ ቢያደርገው “ልቆጣጠረው በማልችለውና ባልጠበኩት አቅጣጫ ሄዶ ያስበላኛል” ብሎ ያምናል፡፡ በመሆኑም ብቻውን ሮጦ አሸነፍኩ ብሎ በማስጨብጨብ አሁንም መንግሥት ነኝ ሊል ፈልጓል፡፡

በዚህም መሠረት መኢአድንና አንድነትን ሕገ ወጥነት ሸፍጥና ሸር በተሞላበት መልኩ ከምርጫ ፉክክር ውጪ አድርጎ ሲያበቃ ከፉክክር ውጪ ማድረጉን አውጇል፡፡ ባወጀ ማግስትም እንዲያው ለማስመሰል እንኳን ያህል የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ባልተያዘበት ወይም በሌለበት ሁኔታ ዐይን ባወጣ የውንብድና ተግባር ጽ/ቤቶቻቸውንና የየፓርቲዎቹን ንብረቶች ነጥቆ ለቅጥረኞቹ አስረክቧል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲንም ጥረት እያደረገባቸው እንዳለው ሁሉ አንድ ሰበብ ፈጥሮ መሸኘቱ የማይቀር ይመስላል፡፡ ፓርቲውን ባያስወጡትና በምርጫው ቢሳተፍም እንኳ ከዚህ ቀደም እንደነበሩት ምርጫዎች ሁሉ ይሄኛውም የይስሙላ ከመሆን አይድንምና ብቻ ለማስመሰል ያህል ሦስት አራት ለሚሆኑት የፓርቲው ተመራጮች ተመርጣቹሀል ብሎ ወንበር ከመስጠት ባለፈ ሕዝብ የሰጠው ድምፅ ቅቡል ሆኖ መንግሥት የሚመሠረትበት አሠራርና ዕድል ስለሌለ ከአጫፋሪነትና አዳማቂነት የተለየ ሊፈይደው የሚችለውና የሚመጣም ለውጥ አይኖርም፡፡ ሰላማዊ የትግል አማራጩ ፍጹም ዝግ ቢሆንም ሰማያዊ ፓርቲ እንደ መኢአድና አንድነት ሁሉ ወያኔ ካላስወጣው በስተቀር በምርጫው ሒደት ውስጥ የሚያጋጥሙትንና በወያኔ የሚፈጸሙትን ውንብድናና ማጭበርበሮች እያጋለጠ በምርጫው ሒደት ውስጥ ቢቆይ መቆየቱ የሆነ ሰዓት ላይ ለሕዝባዊ ትግሉ ሊጠቅም የሚችልባቸው ሁኔታዎች አሉና ከሒደቱ ባይወጣ መልካም ይመስለኛል፡፡

እንግዲህ እውነት ለሥልጣን ሳይሆን ለሀገርና ለሕዝብ ነጻነትና ደኅንነት በማሰብ በመቆጨት በመብከንከን በፖለቲካው መስክ የተሠማራ ወገን ካለ የሚለየው አሁን ነው፡፡ ይህ የሀገርና የወገን ፍቅርና ኃላፊነት እንዳለበት የተገነዘበ ዜጋ ቀድሞውንም ያልነበረውን ወያኔ ያልሰጠውን የሰላማዊ ትግል አማራጭ እንዳለ ቆጥሮ ከነበረ አሁን እንደማይቻል በተግባርና በይፋ መታወጁ መነገሩ ሀገርንና ሕዝብን ለመታደግ ያለበትንና ያመነበትን የዜግነት ግዴታና ኃላፊነት ለመወጣት የቀረውንና ብቸኛውን የትግልን አማራጭ እንዲጠቀም ያደርገዋልና በዚያ መንገድ ይሄንን አንባገነናዊ አገዛዝ ከስሩ ነቅሎ ለመጣል ከመታገል ወደ ኋላ ባለማለቱ የምናየው የምናውቀው የምንለየው ይሆናል፡፡ ሀገርናንና ሕዝብን ከወያኔ አንባገነናዊና ፀረ ሕዝብ ፀረ ሀገር አገዛዝ ነጻ ልናወጣ የምንችልበት ቀሪ ብቸኛው አማራጭ የኃይል አማራጭ ነው፡፡ መሬት አንቀጥቅጥ በሆነ ሕዝባዊ ዐመፅ ወይም የትጥቅ ትግል፡፡

የሀገርና የወገን ፍቅር አለኝ የሚል ወገን ከሁለቱ የኃይል አማራጭ መንገዶች አንደኛውን ወይም ሁለቱንም መንገዶች በመጠቀም ትግሉን ይቀጥላል እንጅ በቃ! ሰላማዊ የትግል አማራጭ አይቻልምና መንገዱ ተዘግቷልና ብሎ ሀገርና ሕዝብን ለጅብ አሳልፎ ሰጥቶ አርፌ ልቀመጥ አይልም፡፡ ይሄንን የሚያደርግ ካለ ይሄ ሰው ቀድሞውንም ቢሆን ሥልጣንን ይዞ በተራው ለመብላት ነበረ ዓላማው እንጅ ዋጋ ከፍሎ ሀገርንና ሕዝብን ከግፍ አገዛዝ ነጻ ለማውጣት ሲል ለትግሉ ነፍሱንም እስከመስጠት ድረስ ታማኝ አልነበረም ማለት ነው፡፡ ሀገርንና ሕዝብን እመራለሁ ብለው በፖለቲካው የሚሳተፉ ሰዎች ሊያውቁት የሚገባው ቁምነገር ቢኖር እንዲህ ዓይነት ሰው የሚያስፈልገው ምላስ ብቻ ሳይሆን ልብም ጭምር ዋነኛ አስፈላጊው ነገር መሆኑን ነው፡፡ በእንዲህ ዓይነት አጋጣሚ ላይ ቆራጥ አቋም ወስዶ ዋጋ ለመክፈል የማይደፍር ሰው ወይም ለዚህ የሚበቃ ልብ ወኔ የሌለው ፖለቲከኛ ነኝ ባይ ካለ በዚህ በፖለቲካው ትግል ሁለተኛ ዝር ላይል አርፎ እቤቱ ይቀመጥ፡፡ በዚህ መስክ ቢሠማራም እንደ መይሳው ካሳ (ዐፄ ቴዎድሮስ)  በቆራጥነትና ድፍረት ጀግንነት የሀገር ፍቅር የደረጀ የተሞላ ብልህነትና አርቆ አሳቢነትን ለሚጠይቀው ሀገርንና ሕዝብን ያህል ነገር ለመምራት የሚያበቃ ሰብእና የለውምና፡፡

ስለሆነም የሰላማዊ የትግል አማራጭ ዕድል የተነፈጋቸው ወገኖች እንደፍላጎታቸው ሁሉ ሕዝብንና ሀገርን የመምራት ብቃቱ አለን የሚሉ ከሆነ ወያኔን በሕዝባዊ ዐመፅ ወይም በትጥቅ ትግል በኃይል ከሥልጣን ለማስወገድ ወገባቸውን አስረው መንቀሳቀሳቸው ግዴታቸው ነው ማለት ነው፡፡ ይሄንንም ሲያደርጉ ትግሉ በሚጠይቀው የተቀናጀና የተጠና የበሰለ ስልታዊ መንገድ እንጅ የግድ በግልጽ አዋጅ እያወጁ ዘራፍ በማለት እንዳልሆነ ልብ ይሏል፡፡ ይህ የትግል ስልት እንደ ሰላማዊ ትግል ባለመሆኑና ከበድ ያለ በመሆኑ ወዳለፍነው ዘመን እንድንመለስ ተገደናልና እንደ የኢሕአፓ ዘመን ወጣቶች ላቅ ያለ ብስለት ቁርጠኝነት የዓላማ ጽናትና ጀግንነት የሚጠይቅ በመሆኑ ለዚህ ከባድ ትግል ከሥነልቡና ጀምሮ እራስን በበቂ ሁኔታ ማዘጋጀት ግድ ይላል፡፡ ኢሕአፓ ከነበረበት ደካማ ጎኖች ትምህርት በመውሰው ጠንካራ ጎኖቹን ደግሞ እንዳሉ መውሰድ አስፈላጊ ይሆናል፡፡ አማራጭ የለምና መቁረጥ ግድ ነው፡፡

ከሰው በታች ሆኖ ተንቆ ተረግጦ ተዋርዶ ለሀገር ምንም ሳይፈይዱ ከማለፍ እንቢ ለውርደት እንቢ ለጭቆና እንቢ ለባንዳ እንቢ ለሞት (ለወያኔ) በማለት እንደሰው የሰውነት ክብርን ለራስ አውጆ አስጠብቆ ለሀገርና ሕዝብ ክብር ማለፉ በእጅጉ ተመራጭ ነው፡፡ ይሄ ግዴታ የፖለቲካ መሪዎችና አባላቱ ብቻ ሳይሆን የሴቱም የወንዱም፣ የሽማግሌውም የወጣቱም፣ የተማሪውም የሠራተኛውም፣ የሀብታሙም የድሀውም፣ የምሁሩም የጨዋውም (ያልተማረውም)፣ የእስላሙም የአማራውም፣ የሃይማኖት መሪውም የሕዝባዊውም የሁሉም ኢትዮጵያዊያን የዜግነት ግዴታ ነው፡፡ ሁሉም እንደ አቅሙና ችሎታው ሊወጣው የሚገባው ተልእኮ ነው፡፡ ለሕዝብና ለሀገር ሲል መሥዋዕትነት የመክፈል ግዴታ ያለበት የተለየ ዜጋ ስለሌለ፡፡

ዋጋ ተከፍሎ በሚገኘው ነጻነት ተጠቃሚው ሁሉም ስለሆነ፡፡ አሁን ሀገራችን ተጋፍጣው ባለችበትና ከመከራ ከጥፋት ለመዳን የዜጎቿን ርብርብና ተሳትፎ በእጅጉ በምትሻበት የፈተና ወቅት ለመሀል ሰፋሪ ቦታ የለም፡፡ ወይ ከአጥፊዋ ከወያኔ ወገን መሆን ወይ ሊታደጓት ከቆረጡት ወገን እንጅ በመሀል ተንጠልጥለው የሚንሳፈፉበት በመሀል ያለ የመሀል ሰፋሪ ቦታ የለም፡፡ ጥቂቶች እራሳቸውን ለመሥዋዕትነት አሳልፈው ሰጥተው እየታገሉ እየተፋለሙ አብዛኛው ይሄንን ሁኔታ እንደተውኔት ዳር ሆኖ የሚመለከትበት ሁኔታ ሊኖር አይችልም፡፡ ሁሉም ዜጋ በትግሉ የመሳተፍ ግዴታ ይኖርበታል፡፡ በደርግ ዘመን የኢሕአፓ ወጣቶች በምን ያህል ብስለት የዓላማ ጽናትና ቁርጠኝነት ትግላቸውን ይከውኑ እንደነበር ይታወቃል፡፡ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ከደርግ ይልቅ ወያኔ ሩቅ ነው፣ ባዕድ ነው፡፡ በደርግ ዘመን የበሰለ የተቀናጀና የተደራጀ ኅቡዕ ወይም ሥውር ትግል ማድረግ ከተቻለ ሕዝቡ ባዕድ አድርጎ በሚመለከተው በወያኔ ዘመን ይሄንን ማድረግ ሊያቅት አይችልም፡፡ እስከታሰበበት ጊዜ ድረስ የማይቻል ነገር የለም ይቻላል!

ወያኔ ቅዘናም ነው አንድ ሁለቱ ባለሥልጣናት ላይ እርምጃ ቢወሰድ ፍርስርሱ የሚወጣ ድንብርብሩ የሚጠፋ ቡድን ነው፡፡ ወያኔ ሕዝቡን የዚህን ያህል የናቀውና መጫወቻ መቀለጃ ሊያደርገው የቻለው እንዲህ ዓይነቱ ቆራጥ እርምጃ በባለሥልጣናቱ ላይ ሊወሰድ ስላልቻለ ነው፡፡ በአንድ ሁለቱ ላይ እርምጃ ቢወሰድ ግን እመኑኝ ወያኔን ባለበት ቦታ ላይ አታገኙትም፡፡ በትውልደ ኢትዮጵያዊነታቸው እንዳዘንላቸው እንዳሰብንላቸው በፍጹም ሊረዱ ሊገባቸው አልቻለምና መጨከን ግድ ነው፡፡ እንዲህ ካልተጨከነባቸው በስተቀር ወያኔ ልክ ሊገባ የሚችል ዓይነት ቡድን አይደለም፡፡ እንዲህ ዓይነቱን ሥራ ለመሥራት የግድ በስፋት መደራጀት አያስፈልግም ሦስት አራት የሚተማመኑ ጓደኛሞች እየተሆነም ብዙ ሥራ መሥራት ይቻላል፡፡ መከላከያ ውስጥ ያሉ የወያኔ እርኩሰት የሚያንገሸግሻቸው ወገኖች ለዚህ ቅርብ ናቸው፡፡ በትጥቅ ትግል ያሉ የአርበኞች ግንቦት 7 ኃይልም በሚገባ የሠለጠኑ ኮማንዶዎችን ቢያሠማራ ግሩም ግሩም ሥራ መሥራት ይቻላል፡፡ እያንዳንዱ ዜጋም ቢሆን ወያኔን ከማዳከም አኳያ እንደየ አቅሙ ብዙ ሊሠራቸው የሚችላቸው ተግባራት አሉ፡፡ ረዘም ያለ ጊዜ ከሚጠይቀው ከትጥቅ ትግልና የተለየ አጋጣሚ ከሚያስፈልገው ከሕዝባዊ ዐመፅ ይልቅ በፍጥነት ለውጤት የሚያበቃው ይሄኛው በባለሥልጣናት ላይ የሚወሰድ እርምጃ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ወደዚህ ዓይነት ትግል ውስጥ ዳግም እንደገና እንዲገባ በመገደዱ እጅግ እጅግ እናዝናለን ሙሉ ኃላፊነቱንና ተጠያቂነቱንም የሚወስደው ወያኔና ደጋፊዎቹ ያሆናሉ፡፡ እንዲህ ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ደግመን እንዳንገባ ነበር የኢትዮጵያ ሕዝብ ይሄንን ያህል ዘመን ሊታገሱት የማይቻልን ነገር እየታገሰ የቆየው፡፡

የሕወሀት መሥራቾች (ወያኔዎች) በደርግ ላይ ተስፋ ቆርጠው ወደ ትጥቅ ትግል ሲያመሩ ከአንድ ዓመት በላይ ደርግን ታግሶ ማየት አልቻሉም ነበር፡፡ የኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ወያኔን ይሄንን ያህል ዘመን እጅግ በጣም በሰፋ ትዕግስት የማይቻል ነገር እየቻለ ታግሶ ቆይቷል፡፡ ወያኔ ዕለት ተዕለት እየባሰበት እንደመጣው ሁሉ ከዚህም በላይ ሌላ 23 ዓመታት ቢጨመርለት እያከፋ ይሄድ እንደሆነ ነው እንጅ ተምሮና ተጸጽቶ ሰው ይሆናል ብሎ ማሰብ ጨርሶ የሚቻልበት ሁኔታ የለም፡፡ እስከ አፍንጫው የተጋተው የተነከረበት የወንጀል ዓይነትና ድርጊትም ካለበት ተመልሶ ሰው ለመሆን ዕድል የሚሰጠው አይደለምና፡፡ ገና 40 እና 50 ዓመታት እንገዛለን በሥልጣን ላይ እንቆያለን እያሉ ሲደነፉ አልሰማንምን? ይታያቹህ! በዚህ መራር የአገዛዝ ሁኔታ ሌላ 40 እና 50 ዓመታት እየገዙ ከስርህ ተነቅለህ እስክትጠፋና እነሱ እንደዋርካ እስኪሰፉ ድረስ ለመቆየት ለመኖር ነው እየተመኙና ያንን ያህል ለመቆየትም እየጣሩ ያሉት፡፡ ያንን ያህል መቆየት ከቻሉማ ከዚያ በኋላ ማን ኖሮ ለማን ሲሉ ሥልጣን ያስረክባሉ? አንተ እንደሆንክ ያን ጊዜ አትኖር! መንጥረው ይጨርሱህ አይደል እንዴ? ስለሆነም ከዚህ በኋላ ለወያኔ ያለህ ትዕግሥት እርባናና ጥቅም አልባ እንደሆነ ተረድተህ ሁልህም ወገን ቆርጠህ ተነሥ፡፡ ከዚህ በኋላ የሚኖርህ ዝምታ የከፋ አደጋ በራስህና በሀገር ላይ ካለማምጣት ካለመጋበዝ በስተቀር የሚጠቅምህ የሚፈይድልህ ነገር የለምና፡፡

የምናደርገው ሕዝባዊ ትግል ፈተናዎች፡-

አሁንም ደግሜ ማሳሰብ የምሻው ነገር ቢኖር ይህ ተገደን የምንገባበት ትግል መራራና ከባድም ነው፡፡ ይሁን እንጅ ከዚህ ውጭ ሌላ አማራጭ ስለሌለን የፈለገውን ያህል መሥዋዕትነት ቢያስከፍልም ወደ ኋላ ልንል አንችልም፡፡ መታወቅ ያለበት የምንፋለመው ዝም ብንልም ከማይምረንና ቀረጣጥፎ ከሚበላን ጭራቅ ጋር መሆኑን ነው፡፡ ስለሆነም ካለ መቁረጥ መጨከን በቀር ሌላ አማራጭ የለንም፡፡ ቀጥሎ የምጠቅሳቸው የትግል ወቅት ፈተናዎቻችንን አውቀናቸው እንዘጋጅባቸውና እንጠነቀቅባቸው ዘንድ በጣም ያስፈልጋል፡፡ እነዚህን ፈተናዎች ትእግስት ጥበብና ቆራጥነት በተሞላበት መልኩ ለመቆጣጠር ለመፍታት ካልቻልን በስተቀር እጣ ፋንታችን ከድጡ ወደ ማጡ እንዳይሆን ያሰጋል፡፡ በተራ ቁጥር አራት ላይ ያለው አሳሳቢ ችግር ወያኔ በእድሜ ዘመኑ አወሳስቦ ሲተበትባቸው የቆዩ ዋና ዋና ችግሮች በመሆናቸው የአምላክ እርዳታም ሊጠየቅበት ይገባል፡፡

  1. በደርግ ዘመን የመጀመሪያዎቹ ዓመታት ወቅት የነበረው የቀይ ሽብርና የነጭ ሽብር ጠባሳዎች አሁንም ድረስ ያሉና ያልተረሱ በመሆናቸው በሕዝቡ ዘንድ ሊኖር የሚችል ፍርሐት፡፡
  2. የአገዛዙ የስለላ ሥራዎች፡፡
  3. አገዛዙ ትግሉን ለማጨናገፍ የሚወስዳቸው የጭካኔ እርምጃዎች፡፡
  4. አገዛዙን ታግሎ ለመገርሰስ የቆረጡ ኃይሎች በፖለቲካዊና ሃይማኖታዊ ምክንያቶች ጥቅምና ፍላጎቶቻቸው የተለያየ የማይጣጣምና የተቃረነ መሆን ናቸው፡፡

አራተኛውን ነጥብ ጥቂት ማብራራት የሚያስፈልግ ይመስለኛል፡፡ እንደሚታወቀው በሀገራችን ወያኔን የሚታገሉ የፖለቲካ ኃይሎች ዓላማና ግብ ሲታይ አንደኛው ከሌላኛው ተቃራኒ ነው፡፡ አንደኛው በወያኔ የሚራገብ እሱም ከኢትዮጵያ መገንጠልን ዓላማና ግብ ያደረጉ መኖራቸው ሲሆን ሌሎቹ ደግሞ መገንጠልን አጥብቀው በመቃወም የሀገርን ህልውናና አንድነትን ማስጠበቅ ዓላማና ግባቸው ያደረጉ መኖራቸው ነው፡፡ ዓላማቸው እንዳለመጣጣሙና እንደመቃረኑ ሁሉ እነኝህ ሁለቱን ማጣጣም ማስታረቅ የሚቻል አይሆንም፡፡ የሚለያቸው አንደኛው በሌላኛው ላይ የሚያገኘው የጦር ድል ነው፡፡ የተለያዩ የባዕዳን የጥፋት ኃይሎች እጅ በመሀል ስላለ ነው እንጅ ሁሉም ብሔረሰቦች በእኩልነት በነጻነት የሚኖሩባት ኢትዮጵያ የምትኖር ከሆነ እገነጠላለሁ የሚሉ ወገኖች የሚገነጠሉበት ምንም ዓይነት ምክንያት ሊኖር ባልተገባ ነበር፡፡

ሌላኛው እስካሁን በበቂ ያልተነገረለትና ያልታወቀ ነገር ግን ብዙ ሊያውከንና ከባድ አደጋ ሊያደርስብን የሚችል ሃይማኖትን ሽፋን ያደረገ ተጨባጭ ሥጋት ነው፡፡ እሱ ምንድን ነው? ሰሞኑን አንድ “የፈረንሳዩ ቻርሊ ሂብዶ ጋዜጣ አሸባሪዎችና ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት” የሚል ርእስ ያለው ጽሑፍ አስነብቤ ነበር፡፡ በዚህ ጽሑፍ ላይ እስልምናን የሚከተሉ ወገኖቻችንን በዘልማድ የሚያደርጓቸውን ነገር ግን ሃይማኖታዊ ትእዛዝ የሌለባቸውን ከኢትዮጵያዊነታችን ጋር የሚቃረኑ አንዳንድ ተግባራት በመጥቀስ ለሀገርና ለማንነት ቅድሚያና የበለጠ ትኩረት እንዲሰጡ አበክሬ ለማሳሰብ ሞክሬ ነበር፡፡ መጀመሪያ ጽሑፉ በተለጠፈበት የመጽሐፈ ገጽ (የፌስ ቡክ) ግድግዳ ላይ 180 ያህል አስተያየቶች ተሰጥተዋል፡፡ ከአምስቱ እስልምናን የማይከተሉ ወገኖች አስተያየቶች በስተቀር የተቀሩት አስተያየቶች እስልምናን ከሚከተሉ ወገኖቻችን የተሰጡና “ከሀገር ከማንነት ከነፍሳችንም በላይ ነቢያችንንና ሃይማኖታችን እንወዳለን ለእሱም ነፍሳችንን እስከመስጠት ድረስ ቁርጠኞች ነን በዚህ አንደራደርም” በሚል የአስተሳሰብ አስኳል ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ናቸው፡፡ ልብ በሉ እኔ ያልኩት ባልጠራ ግንዛቤና ከቁርአናቸው ትእዛዝ ውጭ ኢትዮጵያዊ ማንነታቹህን እየሸረሸራቹህና የራሳቹህን ማንነት ጥላቹህ ዓረባዊ እየሆናቹህ ነውና ይሄ ከእስልምና ጋር ምንም የሚያገናኘው ነገር ስለሌለ እስልምናቹህን መከተል ትችላላቹህ ሀገራቹህንና ማንነታቹህን ግን ጠብቁ አልኩ እንጅ እስልምናቹህን ጣሉ አለማለቴ እየታወቀ የተሰጡት አስተያየቶች ግን እነዚያ የጠቀስኳቸው ነገሮች ከሃይማኖት ጋር እንደማይገናኙ እያወቁ የሚገናኙ አድርገው በመቁጠር “ሀገር ማንነት አይገባንም ለኛ ነቢያችንና ሃይማኖታችን ይበልጡብናል” በማለት ኃይልና ቁጣ ስድብና ዘለፋ የተሞላበት አስተያየቶችን ነው የሰጡት፡፡

የእነዚህ ሰዎች ችግር እስልምናንና ዓረብነትን፣ እስልምናንና የዓረቦችን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ባሕላዊ ጥቅሞች መለየት አለመቻል ነው፡፡ ዓረቦች ጥቅማቸውን ለማስተበቅ ሲሉ ሁለቱንም ቀላቅለው ሲሰብኳቸው ስለኖሩ ይሄ ችግር ሊከሰትባቸው እንደቻለ እገምታለሁ፡፡ እስልምናን መቀበል ማለት የዓረብ ባሪያ ሎሌ ባንዳ መሆን ማለት አይደለም፡፡ ዓረቦች የራሳቸው ማንነት እንዳላቸው ሁሉ እኛም ሐበሾች ከነሱ የተሻለ ማንነት አለን፡፡ የራስን ጥሎ የዓረብን መያዝ ማለት የውዴታ ባርነት ነው፡፡ ችግሩ ይሄንን አለመረዳታቸው ብቻ ሳይሆን ለመረዳት አለመፈለጋቸው ነው፡፡ የዚህን ጉዳይ አደገኛነት የማይረዳ ሰው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ እነኝህ ወገኖች በደም ኢትዮጵያዊ መሆናቸውንና በኢትዮጵያዊነታቸውም ዜጋ በመሆናቸው ብቻ ሀገራቸውንና ማንነታቸውን የመጠበቅ ግዴታ እንዳለባቸው ጨርሶ መቀበል አይፈልጉም፡፡ ዓረቦች በሃይማኖት ሽፋን የዓረብን ጥቅሞች እንዲጠብቁ እንዳደረጓቸው አያውቁም ማወቅም አይፈልጉም፡፡ ዓረቦች ወገኖቻችንን እያሳቱ ያለበት ዘዴ ከቁርአን ውስጥ የሌለና ያልታዘዘ መሆኑ ነው የሚደንቀው፡፡

ስለ አለባበስ በዚያ ጽሑፍ ላይ የገለጽኩት በመሆኑ አልደግመውም፡፡ ቋንቋን በተመለከተ ግን “እስልምናን የተቀበለ ሁሉ የራሱን ቋንቋ ጥሎ ዓረብኛን ይያዝ” የሚት ትዕዛዝ በቁርአናቸው እንደሌለ እየታወቀ ዓረቦች የባሕል ወረራ ለማድረግ ሲሉ “ዓረብኛ ቁርአን የወረደበት ቅዱስ ቋንቋ ስለሆነ እስላም ለሆነ ሁሉ ዓረብኛን ማወቅ ግዴታው ነው” እያሉ እየሰበኩ ቋንቋቸውን ያስፋፋሉ፡፡ የሚያሳዝነው ይህ አባባላቸው ስድብ መሆኑን ከዓረብ ውጭ ያለው ሌላው እስልምናን ተቀባይ ዘር አለመረዳቱ ነው፡፡ ለመሆኑ የቋንቋ እርኩስ አለ እንዴ? ከእግዚአብሔር ውጪ ከዓረብኛ ውጪ ያሉ ቋንቋዎችን የፈጠረ ሌላ እርኩስ ፈጣሪ አለ እንዴ? በዓረብኛ ቋንቋ እርኩስ ነገር ሊወራ አይችልም እንዴ? ይሄንን እያሉ ከሚያታልሉት ዓረቦች ይልቅ ደግሞ ማን ይገርመኛል መሰላቹህ? ይሄንን የዓረቦችን አባባል እውነት አድርገው የተቀበሉ ከዓረብ ውጭ ያሉ ሌሎች እስልምናን የተቀበሉ ዘሮች፡፡ ዓረብኛ ብቻ ሳይሆን ሌሎች ቋንቋዎችንም ማወቁ ይጠቅማል እንጅ አይጎዳምና ቋንቋን ማወቅ መልካም ነው፡፡ ቋንቋውን ማምለኩና የራስን ርኩስ ሌላውን ቅዱስ ማለቱ ግን ችግር ያለበትና እጅግ ያልበሰለ አስተሳሰብ ነው፡፡ ሰውን የሚቀድሰውም የሚያረክሰውም ሥራው ነው እንጅ ቋንቋ አይደለም፡፡ ሰው ዓረብ ስለሆነ ቅዱስ አይሆንም ሌላ ዘር ስለሆነም እርኩስ አይሆንም፡፡ እናም ወገኖቸ ሆይ! የቱንም ያህል የኢትዮጵያዊነትን አሻራ እየጣላቹህ የዓረብን ማንነትና አሻራ ብትላበሱት ከጥቁርነታቹህ ከኢትዮጵያዊ ቀለማቹህ ከሐበሻነታቹህ ተቀይራቹህ ዓረብ ልትሆኑ አትችሉምና የማይቻል ነገርን በማድረግ ለመሆን በመጣር በማንነት ቀውስ በሽታ እራሳቹህን ባታውኩ ባታሰቃዩ እራሳቹህን ብታከብሩ ለራሳቹህ ዋጋ ብትሰጡ እራሳቹህን መሆን ብትችሉ ለጤናቹህ መልካምና ሰላምም ነው ለማለት እወዳለሁ፡፡

እኔ ይሄንን ነገር ለማመን ከመቸገሬ የተነሣ ሳስበው ሕልም ሕልም ሁሉ ይመስለኛል፡፡ እንዴት ሰው የራሱን ማንነት ጥሎ ለሌላው ምናልባትም ለጠላቱ ማንነት ነፍሴን እሰጣለሁ ይላል? እኔ ክርስቲያን ነኝ ክርስቲያን በመሆኔ ግን ሀገሬንና ከቋንቋየ ጀምሮ እስከ ባሕሌ ድረስ ማንነቴን እንድጠላ እንድንቅ አላደረገኝም፡፡ በእርግጥ ከአውሮፓ የመጣ ክርስትና ነው ብለው ፕሮቴስናንትና ካቶሊክ የሆኑ ወገኖች ለሀገራችንና ለማንነታችን ያላቸው ግምት እንደ ላይኞቹ ነው፡፡ የሚያስጠብቁት ጥቅም የሰበኳቸውንና የሚረዷቸውን ምዕራባዊያን ጥቅሞች ነው፡፡ ተግባሮቻቸውም ሁሉ ኢትዮጵያዊነትን በማጥፋት ላይ ያተኮረ በዚህም የተጠመዱ ናቸው፡፡ በእርግጥ የተለያዩ ሀገራት የሀገራችንን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅሞች በማጥፋት የየራሳቸውን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅም ለማስጠበቅ ሥራ እንደሚሠሩ እንደሚጥሩ ከድሮ ጀምሮ የሚታወቅ ጉዳይ ቢሆንም የዚህ ግብ ግብ ሰለባ የሆኑ ኢትዮጵያዊያን ወገኖችንና ተግባራቸውን ስናይ ግን እጅግ መገረማችን የሚቀር አይመስለኝም፡፡

ለማንኛውም ሀገርንና ማንነትን በተመለከተ የእኔ ሃይማኖት ግን ከምንም በላይ ሀገሬንና ማንነቴን እንድወድ እንድጠብቅ እንድኮራባት እንድሞትለትም አድርጋ ቀረጸችኝ እንጅ የራሴን አስጥላ ሃይማኖትህ መጣበት የምትለውን ሀገር ጥቅም እንድይዝና የራሴን ጥየ ለነዚያም ጥብቅና እንድቆም አላደረገችም፡፡ ለነገሩ የኔ ሃይማኖት ከየትም አልመጣም በዚህ ርእሰ ጉዳይ ሰፊና መረጃ ሰጪ ንባብ እንዳስነበብኳቹህ ይታወሳል፡፡ የኔ ሃይማኖት ለዚህች ሀገርና ማንነት ካላት የላቀ ቦታ የተነሣ እንዲያውም ይህች ሀገር የተቀደሰችና ልዑል እግዚአብሔርም ከእናቱ ጀምሮ ዋና ዋና ለሚላቸውና ከፍተኛውን ተጋድሎ ለፈጸሙ ቅዱሳን የዐሥራት በገራቸው እንድትሆን የሚሸልማት ብርቅ ድንቅ ቅድስት ሀገር እንደሆነችና ለዚህች ሀገር ነፍሴንም ጨምሮ ምንም የምሰስተው ነገር እንዳይኖር መክራና አስተምራ ነው ያሳደገችኝ፡፡ እንኳን እኔን ኢትዮጵያዊውን ሐዋርያዊ ተልእኮ ለመስጠት በሄደችባቸውና በምታገለግልባቸው ሀገራት ላሉ ባዕዳን ሁሉ ኢትዮጵያን በዚህ መልኩ እንዲያስቧት ነው የምትሰብከው፡፡ እኔ የማውቀው ይሄንን ነው፡፡ ከዚህም የተነሣ ሳይሆን አይቀርም እነዚህ ወገኖች በደም ኢትዮጵያዊያን ሆነው ሳለ የገዛ ሀገራቸውን በመክዳት ለባዕዳን ከዚያም ባለፈ ኢትዮጵያዊ በመሆናቸው እንደ ጠላት ለሚቆጥሯቸው ሀገራትና ሕዝቦች እሴቶችና ማንነት ጥብቅና ሲቆሙና ሲዋደቁ እጅግ እጅግ የሚገርመኝ የሆነው፡፡ አንድ የዓረቦች አባባል ትውስ አለኝ ዓረቦች ምን ይላሉ “በመንገድህ ላይ መርዘኛ እባብና ኢትዮጵያዊ ቢያጋጥሙህ ቀድመህ ኢትዮጵያዊውን ግደለው” የሚል አይገርሟቹህም? ይሄንን ያህል ከእባብም በከፋ መልኩ ለሚጠሏቸውና ለሚጠየፏቸው ሊያጠፏቸውም ሌት ተቀን ለሚያሴሩት እኩዮች እንዲህ እንደሚያስቧቸውና እንደሚጠሏቸው እያወቁ እንሞትላቹሀለን ሲሉ? ይሄ የጤና ነው ትላላቹህ?

እንደምታውቁት አሁን በዚህ ወቅት ሁሉም ባይሆኑም የሚበዙቱ በተሟሟቀ ሁኔታ ከዚህ ብዥታ ጋር ሆነው ለእስልምና እየታገሉ እየመሰላቸው ለዓረብ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ባሕላዊ ጥቅሞች እየታገሉ ያሉ እስልምናን የሚከተሉ ወገኖች አሉ ዋጋም እየከፈሉ ይገኛሉ፡፡ አደጋው ያለው እዚህ ላይ ነው፡፡ እንደሚታወቀው ዓረቦች ከረጅም ጊዜ ጀምሮ ይህችን ሀገርና ሕዝቧን በተመለከተ የተለየ ፍላጎት ይዘው በሀገራችን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ባሕላዊ ጥቅሞች ጉዳይ ላይ እጃቸውን እያስገቡ የራሳቸውን ጫና ሲፈጥሩ፤ ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅሞች ለማስጠበቅ አውዳሚ ጦርነቶችን ከማድረግ ጀምሮ ብዙ ነገር ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል፡፡ ዛሬም ላይ ዓረቦች እንደወትሮው ሁሉ በዚህች ሀገር ላይ ላላቸው ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ታሪካዊና ባሕላዊ ጥቅም በሚያደርጉት ጣልቃ ገብነት ጫናና ፍልሚያ አጋጣሚው ባመቻቸው ጊዜ ሁሉ እጃቸውን በሚያስገቡበት ወቅት እነኝህ ወገኖች መጠቀሚያ መሆናቸው የማይቀር ጉዳይ ነው፡፡ ይሄ ከባድ አደጋ ነው፡፡

በእርግጥ ፊት ለፊት ወጥተው ከወያኔ ጋር እየተጋፈጡ ያሉት ወገኖች ቁጥር ያን ያህል ላቅ ያለ ላይሆን ይችላል፡፡ ከጀርባ ግን በሚሊዮኖች (አእላፋት) የሚቆጠሩ የዓላማ ተጋሪ እንዳላቸው የሚጠረጠር አይመስለኝም፡፡ የሚያሳዝነው የእነሱ ትግል ግብ የሀገርንና የሕዝብን ክብር ሉዓላዊነት ታሪክ ባሕል ማንነት እሴቶችን ሁሉ በተመለለከተ ቢሳካላቸው ከወያኔ በከፋ መልኩ የከፋ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ብዙዎቹ የሚያውቁ አለመሆናቸው ነው፡፡ ይሄንን አብዛኞቻቸው በቅጡ ሳያውቁት የሚያደርጉትን ደግሞ ሌላው ኢትዮጵያዊ የማይፈልገው የማይፈቅደውም ከመሆኑ የተነሣ የጥቅምና የዓላማ ግጭት መነሣቱ የማይቀር ይሆናል በዚህ መሀል የጠላት እርስ በእርስ እያፋጀ ሀገሪቱን የማዳከም ሰትራቴጂ (ስልት) ተሳክቶላቸው እንደቆየው ሁሉ ወደፊትም ይሳካላቸው ይሆናል፡፡ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ሁሉ በሃይማኖትና በዘር ሳንለያይ ለጠላቶቻችን ሳይሆን ለእኛ የምትሆን ነጻ እኩልነት የሰፈነባትን ኢትዮጵያን ለማምጣት ስንል የማይቀርልንንና የሚገጥመንን ፈተና በብቃት ተወጥተን ዓላማና ግባችንን ለማሳካት ከወዲሁ መዘጋጀቱ ግድ መሆኑን ልንረዳ ያስፈልጋል፡፡ በዚህ ረገድ የገባቸውና ፈተናው ተግዳሮቱ አጋጣሚውን ለመጠቀም ጠላት ሃይማኖትንና ዘርን ሽፋን አድርጎ እንደሚመጣ በመረዳት በሀገራቸውና በሕዝባቸው ጥቅሞች ላይ ፈጽሞ ያለመደራደር ጠንካራ አቋም የያዙ የእስልምና ተከታይ ወገኖቻችን እነኝህን የሳቱና ያልገባቸውን የጠላት መጠቀሚያ ወገኖቻችንን ከያዙት የጥፋት ዓላማ እንዲመለሱና ለገዛ ሀገራቸውና ለሕዝባቸው ዋጋ መሥዋዕትነትን እንዲከፍሉ የመምከርና የማስተማር ተግባራቸውን ሳይደክሙና ሳይሰለቹ ጠንክረው እንዲወጡ በዚህ አጋጣሚ አበክሬ ማሳሰብ እወዳለሁ፡፡

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!!!

 

 

The post ላልቀረልን ሀገርንና ሕዝብን የመታደግ ትግል ተነሡ! – ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው appeared first on Zehabesha Amharic.

ድንገተኛና ደማቅ የፊኛ መልቀቅ ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ ተካሄደ

$
0
0

muslim 1

muslim addis 3
‹‹ሲፈልግ ሾማቸው ሲፈልግ ሻራቸው!!››
አርብ የካቲት 6/2007
ድምጻችን ይሰማ እንደዘገበው:-

የመንግስት እጆች ዛሬም በመጅሊስ ውስጥ እንደተዘፈቁ ያረጋገጠውን በቅርቡ የተካሄደውን ህገወጥ የመጅሊስ ሹማምንት ሹም ሽር በመቃወም ደማቅ ድንገተኛ ተቃውሞ በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ ተካሄደ፡፡ ተቃውሞው ‹‹ሲፈልግ ሾማቸው ሲፈልግ ሻራቸው!›› በሚል መሪ ቃል የተካሄደ ነበር፡፡ ህብረተሰቡ የተለያዩ ቀለማት ያላቸው ፊኛዎችን እና መፈክሮችን በመጠቀም መሪ ቃሉን በደማቅ ሁኔታ አንፀባርቋል፡፡ ተቃውሞው በወኪሎቻችን አማካኝነት ለመንግስት ያቀረብነው የ‹‹ነፃ መጅሊስ›› ጥያቄ ዛሬም ህያው የማታገያ አጀንዳ እንደሆነና ከወኪሎቻችን ጋርም እስከ ድል አብረን እንደምንቀጥል ትልቅ መልዕክት ያስተላለፈ ነው፡፡
muslim addis

በከፍተኛ መስዋእትነት በወታደራዊው ደርግ ዘመን ያገኘነው ተቋማዊ መብታችንን (መጅሊስን) በኢህአዴግ መንግስት ከተነጠቅን ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ በይበልጥም የሃይማኖት መሪዎችን ምርጫ ‹‹በቀበሌዬ ካልሆነ አይሞከርም›› በሚል አይን ያወጣ ጣልቃ ገብነት ካድሬዎችን የሾመበት አጋጣሚ ‹‹መንግስት በመጅሊስ ውስጥ ጣልቃ ገባ›› የሚያስብል ከመሆንም አልፎ ህዝብ ትንሽም ቢሆን በተቋሙ ጉዳይ ጣልቃ እንዳይገባ በሩን የዘጋበት ታሪካዊ ሁነት ነበር፡፡ በቅርቡ ደግሞ ሲፈልግ ከያሉበት ጠርቶ በፖለቲካዊ ስሌት የሾማቸውን የመጅሊስ ህገወጥ ሹማምንት አንድ የቀበሌ አስተዳዳሪ ከመቀየር ባልከበደ ሁኔታ ሲሽራቸው ከርሟል፡፡ የሹም ሽሩ ድራማ በደም የተገኘውን መጅሊሳችንን ክብር ያጎደፈ፣ መንግስት ዛሬም ከመጅሊስ ለመውጣት ትንሽም ፍላጎት እንደሌለው ያሳየ፣ በመንግስት ጉያ ተሸሽገው ከህዝብ ተቃራኒ የቆሙ ወገኖች የነገ እጣ ፈንታቸው ምን ሊሆን እንደሚችል በተግባር ያሳየ፣ እንዲሁም በመጅሊስ እና በሌሎች የመንግስት የፖለቲካ መዋቅሮች ውስጥ የሚካሄዱ ሹምሽሮች ከተመሳሳይ ቦታ በተመሳሳይ ‹‹ህግ›› የሚከናወኑ መሆኑን ከምንግዜውም በላይ በተግባር ያሳየ ነበር፡፡

ህዝበ ሙስሊሙ ተቋሙን ዛሬ ላይ እጁን ተጠምዝዞ ተቀምቶ ህገ ወጦች እንዲፈራረቁበት ቢደረግም በተቋሙ ላይ ያለው የባለቤትነት ስሜት ግን አሁንም ህያው ነው፡፡ የጀመረውን ሰላማዊ ትግል ዳር ሲያደርስ መጅሊስን እውነተኛ የህዝብ ተቋም እንዲሆን አድርጎ ነፃ ማውጣትም ትልቁ ግቡ ነው፡፡ መንግስት እያካሄደ ያለው ሹምሽር ህገ ወጦችን በህገ ወጦች መተካት በመሆኑ በራሱ ህገወጥነት ነው፡፡ ህዝቡም ተግባራዊ ምላሽ መስጠትን ጨምሮ ጉዳዩን በዝምታ እንደማያልፈው መግለፁ ይታወሳል፡፡ የዚህ ህዝባዊ ምላሽ አንድ አካል የሆነው የዛሬው የጁሙዓ መርሃ ግብር በተሳካ መልኩ ተከናውኗል፤ አልሐምዱሊላህ!!!

ትግላችን እስከድል ደጃፎች በአላህ ፈቃድ ይቀጥላል!
ድምጻችን ይሰማ!

The post ድንገተኛና ደማቅ የፊኛ መልቀቅ ተቃውሞ በአንዋር መስጊድ ተካሄደ appeared first on Zehabesha Amharic.

ስለታላቁ አንዋር መስጅድ ቅጽበታዊ ተቃውሞ የቢቢኤን የድምጽ ዘገባ ያድምጡ

$
0
0

በማህበራዊ ሚዲያዎች ሳይነገር; በሚዲያ ሳይይጠራ ውስጥ ለውስጥ በተደረገ ግንኙነት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ውስጥ ለውስጥ በህቡዕ በመነጋገር ዛሬ በአንዋር መስጊድ ደማቅ ተዋውሞ አካሂደዋል:: ቢቢኤን የተቃውሞውን ሁኔታ አስመልክቶ ሰበር ዘገባ አዘጋጅቷል – ዘ-ሐበሻ እንደሚከተለው አካፍላችኋለች::
[jwplayer mediaid=”38989″]
muslim addis 3

The post ስለታላቁ አንዋር መስጅድ ቅጽበታዊ ተቃውሞ የቢቢኤን የድምጽ ዘገባ ያድምጡ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሲሸልስ 4 የደደቢት ተጨዋቾች ሃገሯ እንዳይገቡ አገደች * ቅዱስ‬ ጊዮርጊስ እና ደደቢት በካፍ ክለቦች ጨዋታቸውን ነገ ቅዳሜ ያደርጋሉ

$
0
0

ለአፍሪካ የክለቦች ሻምፒዮንስ ሊግ የማጣሪያ ጨዋታን ለማድረግ የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ አባላት አልጄሪያ ይገኛሉ።

ቅ.ጊዮርጊስ የፊታችን ቅዳሜ ምሽት 12:00 ሰአት ከአልጄሪያው ኤም ሲ ኤል ኤልማ ክለብ የሚያደርገው ጨዋታ የቀጥታ ስርጭቶች በቲቭ እንደሚያገኝ የደረሱን መረጃዎች ያመላክታሉ::
st. George
ሌላኛው የኢትዮጵያ ተወካይ ደደቢት ከሲሸልሱ ኮት ዲ ሆር ጋር ቅዳሜ በ9 ሰአት ለሚያደርገው የካፍ ኮንፌዴሬሽን ጨዋታው ወደ ስፍራው በኬንያ አድርጎ ቢያመራም አራት የደደቢት ክለብ ተጨዋቾች በቪዛ ምክንያት ከሲሺየልስ ተመለሱ መመለሱን ኢትዮ ኪክ ኦፍ ዘገበ::

በየአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ካፕ የቅድመ ማጣሪያ የመጀመሪያ ጨዋታውን ለማካሄድ ትናንት ወደ ሲሺየልስ ካመራው የደደቢት እግር ኳስ ክለብ 29 የልኡካን ቡድን አባላት መካካል በቪዛ ምክንያት አራት የውጭ ሃገር ተጨዋቾች ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ ተደረገ፡፡
dedebit
የሲሺየልስ ኢሚግሬሽን ባላስልጣን እ.አ.አ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ ስራ ላይ ያዋለውንና በምእራብ አፍሪካ ሃገሮች ዜጎች ላይ ተፈጻሚ እንዲሆን የተደረገው ጥብቅ የጉዞ መመሪያ ባለመከበሩ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ የተገደዱት አዲሱን ጋናዊ ግብ ጠባቂ ጨምሮ የክለቡ ተጨዋቾች ሱሊማና አቡ፣ሞሃመድ አዳሙ፣ሳሙኤል ሳኑሚ እና ጋብርኤልአህመድ ሹኢብ ናቸው፡፡

ከደህንነት ስጋት ጋር ተያይዞ የሲሺየልስ ኢሚግሬሽን ባለስልጣን ባወጣው ጥብቅ መመሪያ መሰረት ከምእራብ አፍሪካ አገሮች ለማንኛውም ጉዳይና ተልእኮ ወደ ሲሺየልስ ለሚያመሩና አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ የመግቢያ ቪዛ የሚጠይቁ ተጓዦች በቅድሚያ ህጋዊ ፓስፖርታቸውን ወደ ሲሺየልስ በመላክ ፈቃድ መያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
አራቱ ተጨዋቾች ያጋጠማቸውን የመግቢያ ቪዛ ችግር ለመፍታት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አዲስ አበባ ከሚገኘው የሲሺየልስ ኤምባሲ ጋር በመነጋጋርና ተጨማሪ የጉዞ ሰነዶች በመላክ እንዲሁም ከኤምባሲው የትብብር ደበዳቤ እንዲጻፍና በተላያዩ የመገናኛ ዘዴዎች ተከታታይ መልእክቶች እንዲተላላፉ ቢያደርግም በመመሪያው ጥብቅነት የተነሳ ሊሳካ እንዳልቻለ ታውቋል፡፡ ከሲሺየልስ አውሮፕላን ማረፊያ እንዲመለሱ የተደረጉት አራት የደደቢት እግር ኳስ ክለብ ተጨዋቾች ነገ ከቀኑ 6፡00 ላይ አዲስ አበባ እንደሚገቡ ይጠበቃል፡

ክለቡ ቌሚ ግብ ጠባቂዎቹ በጉዳት ምክንያት ከቡድኑ ጋር ያልተጓዙ ሲሆን አዲሱ ጋናዊ ግብ ጠባቂ ለቡድኑ ቌሚ ተሰላፊ ይሆናል በሚል ተስፋ የተጣለበትም ቢሆን የሲሸልስ መንግት ህግ መሰረት ደደቢት ጋናዊውን ግብ ጠባቂ ጨምሮ የምህራብ አፍሪካ ተጨዋቾቹን ወደ አዲስ አበባ እንዲመለሱ እና ያለ ቌሚ ግብ ጠባቂ ከሜዳ ውጭ ጨዋታውን ያደርጋል::

ይህ በእንዲህ እንዳለ

“የመጀመሪያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታችንን ለማድረግ ተዘጋጅተናል”

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከምስረታው ጀምሮ በወጣቶች በማመን ከታች ቡድን በማሳግ እና እድል በመስጠት ያምናል፡፡ በዘንድሮው አመትም ይኸው አመኔታ ቀጥሎ በዛ ላሉ ወጣቶች ዕድል መስጠት ተችሏል፡፡
በተለይም አምና በተስፋ ቡድን ሲጫወት የምናውቀውና ዘንድሮ የዋናው ቡድን አባል የሆነው አንዳርጋቸው ይላቅ፤ ባለፈው አመት በቢጫ ቴሴራ አድጎ በዋናው ቡድን ሲጫወት የነበረው እና ዘንድሮ በፕሪምየር ሊጉ ብቻ በግራ መስመር በኩል በመሰለፍ ከአስር በላይ ጨዋታዎችን በቋሚነት መጀመር የቻለው ዘካርያስ ቱጂ ከዚህ በተጨማሪም ባለፈው አመት የከ17 አመት በታች ቡድናችን አምበል የነበረው እና ዘንድሮ ቡድናችን ከአርባ ምንጭ፤ ወልዲያ እና ደደቢት ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ መሳተፍ የቻለው አቡበከር ሳኒ ለዚህ ምሳሌያችን ተጠቃሾች ናቸው፡፡

እነዚህ ለምሳሌ ያህል የጠቀስናቸው ታዳጊ ተጨዋቾች በሀገር ውስጥ እድል ሲሰጣቸው የነበረ ሲሆን አሁን ደግሞ ቡድናችን በመጪው ቅዳሜ በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ከአልጄርያው ኤም ሲ ኤል ኡልማ ጋር በሚካሂደው ጨዋታ ላይ ቁጥራቸው በዛ ያሉ ወጣቶች እና ለአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ እንግዳ የሆኑ ተጨዋቾች ይሳተፋሉ፡፡
ሰልሃዲን ባርጌቾ፤አንዳርጋቸው ይላቅ፤ዘካርያስ ቱጂ፤ መሀሪ መና፤ዳዋ ሁጤሳን የመሳሰሉ ተጨዋቾች የመጀመርያ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡ይህንን ምክንያት በማድረግም ዘካርያስ ቱጂ እና አንዳርጋቸው ይላቅን በአፍሪካ ሻምፒየንስ ሊግ ላይ በመሳተፋቸው ምን እንደተሰማቸው ጠይቀናቸው ነበር፡፡

ዘካርያስ ቱጂ ” የአንድ ተጨዋች ትልቁ ህልሙ ክለቡን በሊግ እና በአህጉራዊ ውድድሮች ላይ ጥሩ ተሳታፊ አድርጎ ሻምፒዮን መሆን ነው ሁለተኛው ደግሞ ሀገርህን በአለም አቀፍ ውድድሮች መወከል ነው፡፡ እኔ እንደ አንድ ተጨዋች ዘንድሮ በሊጉ ላይ በአብዛኛው ጨዋታዎች ተሰልፌያለሁ፡፡ በዚህም ደስተኛ ነኝ ነገር ግን እንደነ ደጉ ፤ አዳነ እና አሉላ ያሉትን የቡድን ጓደኞቼን ስመለከት ገና ብዙ መስራት ያሉብኝ ነገሮች እንዳሉ ይሰማኛል፡፡ የመጀመሪያውን አሰልጣኞቼ እና የቡድን ጓደኞቼ የሚነግሩኝን እየሰማሁ አሁን የደረስኩበት ቦታ ደርሻለሁ፡፡አሁን ቀጣዩ የሻምፒየንስ ሊግ ጨዋታም እኔ የምፈተንበት ይሆናል ብዬ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን የመጀመርያ ጨዋታዬ እንደመሆኑ መጠን በጥሩ ጤንነት እና ጥሩ ስራን እየሰራሁ በትኩረት በመዘጋጀት ላይ እገኛለሁ፡፡”
አንዳርጋቸው ይላቅ አምና የአዲስ አበባ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሚያዘጋጀው የተስፋ ቡድኖች ጨዋታ ላይ ሲጫወት የነበረ ተጨዋች ነው፡፡እንደ ዘካርያስ ሁሉ አንዳርጋቸውም ታላላቅ ተጨዋቾች የደረሱበት ደረጃ ለመድረስ ጠንክሮ እየሰራ እንደሆነ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ድህረ ገፅ ተናግሯል፡፡

“ትልቅ ቡድን ውስጥ በወጣትነት መግባት ጥሩነቱ ከታላላቅ ተጫዋቾች ጋር እንድትጫወት እና ከእነሱም ብዙ ልምዶችን እንድትቀስም ያደርግሀል፡፡በተለይም ለእኛ ቡድን ውስጥ ለወጣቶች እድሎች በብዛት ስሚሰጡ ወጣቶች የመማርያ ቦታን ያገኛሉ፡፡ እኔም ያንኑ እያደረግኩ እገኛለሁ፡፡ለሚመጣው ጨዋታም ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ ልጫወት ነው፡፡ በዚህ ደግሞ እጅግ በጣም ደስተኛ ነኝ፡፡ መጪውን ጨዋታም አሸንፈን ወደ ቀጣዩ ዙር እንደምናልፍ እርግጠኛ ነኝ በማለት ሃሳቡን አካፍሏል፡፡
የቅዱስ ጊዮርጊስ እና የኤል ኡልማ ጨዋታ በመጪው ቅዳሜ በኢትዮጵያውያን ሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ ሁለት ሰአት ይከናወናል፡፡

The post ሲሸልስ 4 የደደቢት ተጨዋቾች ሃገሯ እንዳይገቡ አገደች * ቅዱስ‬ ጊዮርጊስ እና ደደቢት በካፍ ክለቦች ጨዋታቸውን ነገ ቅዳሜ ያደርጋሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ሰበር ዜና አቶ አስገደ ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ ነው

$
0
0
Asgede

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ

አቶ አስገደ ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ ነው
በዘንድሮው ምርጫ ሰማያዊን ወክለው በመቀሌ ለውድድር የቀረቡት አቶ አስገደ
ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ መሆኑን ገለጹ፡፡
አቶ አስገደ አሁን ላይ ከቤታቸው ውጭ ከተማ መውጣታቸውን ገልጸው፣ ቤታቸው
ሦስት ፖሊሶች ሄደው ‹‹አቶ አስገደ የት ናቸው? ይፈለጋሉ!›› በሚል አሁንም ድረስ
ቤታቸው አካባቢ እየፈለጓቸው መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

The post ሰበር ዜና አቶ አስገደ ገ/ስላሴ በፖሊስ እየታደኑ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ኣሸጎዳ የንፋስ መብራት ማመንጫ ሃይል ዲናሞ በመቃጠሉ ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆነ

$
0
0

ከአምዶም ገብረሥላሴ

በመቐለ ምስራቃዊ ክፍል የሚገኝ የኣሸጎዳ በንፋስ የሚሰራ ኤለክትሪክ ማመንጫ ሃይል በዲናሞ መቃጠል ምክንያት ከስራ ውጭ መሆኑ ታውቋል። የተቃጠለው ዲናሞ 150 ሜጋዋት የማመንጨት ኣቅም የነበረው ሲሆን ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት በመቃጠሉ ሃይል የማመንጨት ኣቅሙ ሙሉ በሙሉ ማቆሙ ታውቋል። የተቃጠለው ዲናሞ ቅያሪ በሃገር ውስጥ እንደሌለና ከፈረንሳይ ሃገር እንደሚመጣ ታውቋል። የህወሓት የ40 ዓመት የልደት በዓል እንደ ታላቅ ውጤትና ማጣፈጫ ተደርጎ ሊወሰደ ታስቦ የነበረ ሲሆን ባልታወቀ ምክንያት መቃጠሉ በክልሉ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከፍተኛ ቁጣና ድንጋጤ መፍጠሩ ታውቋል።
news
የትግራይ ባለስልጣናት እንደ ግዝያዊ መፍትሄ ኣድርገው የወሰዱት የየካቲት በዓል እስኪያልፍ ከፈርንሳይ በክራይ እንዲመጣና ብልሸት እንዳልደረሰው ኣስመስሎ በማሳለፍ በዓሉ ከተጠናቀቀ በሗላ ዲናሞው ወደ ፈረንሳይ እንዲመለስ የሚል ትእዛዝ ኣስተላልፈዋል። የህወሓት ባለስልጣና የየካቲት በዓል ታዳሚዎች ኣሳፋሪ በሆነ ድራማ ኣጭበርብረው ለመመልስ ከፈረንሳይ ዲናሞ ተከራይተው ካሳዩሗቹ በሗላ ተመልሰው ወደ መጣበት ይመልሱታል።

ህወሓት የዲናሞው መቃጠል ለየካቲት በዓል ማክበርያ ካወጣችው 1 ቢልዮን ብር ወጪ የምታወጣው ተጨማሪ ግዙፍ ብር ይሆናል።

The post ኣሸጎዳ የንፋስ መብራት ማመንጫ ሃይል ዲናሞ በመቃጠሉ ምክንያት ከጥቅም ውጭ ሆነ appeared first on Zehabesha Amharic.


ሰማያዊ ለአንድነት አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሊያደርግ ነው

$
0
0

blue partyሰማያዊ ፓርቲ ምርጫ ቦርድ በአንድነት ፓርቲ ላይ ውሳኔ ማስተላለፉን ተከትሎ ፓርቲን ለተቀላቀሉትን የቀድሞ የአንድነት አባላት እሁድ የካቲት 8/2007 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እንደሚያደርግ ሊቀመንበሩ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

ፕሮግራሙን ማዘጋጀት ያስፈለገው ምርጫ ቦርድ በአንድነት ላይ በወሰደው እርምጃ ተስፋ ሳይቆርጡ ሰማያዊ ፓርቲን የተቀላቅሉ አባላት ትግሉን ለማጠናከር ያሳዩትን ቆራትነት እና አብሮነት ለማጠናከር እንደሆነ ሊቀመንበሩ ገልጸዋል፡፡

ከጥር 26/2006 ዓ.ም ጀምሮ ፓርቲውን የተቀላቀሉትና አሁንም መቀላቀሉ የሚፈልጉት የቀድሞው የአንድነት አባላት በፕሮግራሙ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረቡት ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሁለቱ ፓርቲዎች አባላት በሰማያዊ ፓርቲ ጥላ ስር አብሮነታቸውን በማጠናከር የተሻለ ለውጥ እንደሚያመጡ ተስፋቸው እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

The post ሰማያዊ ለአንድነት አባላት የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ሊያደርግ ነው appeared first on Zehabesha Amharic.

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ”ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ”ያወጣው ጽሁፍ

$
0
0

ጋዜጣ (ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው

minilikኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ”የታሪክ” ፅሁፎች ውስጥ ”በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ” የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ”ትርፋማ” ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።

ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው ”ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ” እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።

”ማን ያውራ የነበረ” እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ –

– ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣

– የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣

– አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣

– የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣

– ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና

– እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣

የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።

የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

Published: November 7, 1909 Copyright © The New York Times
http://query.nytimes.com/mem/archive-free/pdfres=F50A12F63A5A15738DDDAE0894D9415B898CF1D3

The post ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ” ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ” ያወጣው ጽሁፍ appeared first on Zehabesha Amharic.

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለማህሙድ አህመድ ያላቸውን ክብር ገለጹ

$
0
0

(ዘ-ሐበሻ) “የትዝታው ንጉስ” በሚል በኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ላይ በትልቁ ስሙ የሚጠራው ድምፃዊ ማህሙድ አህመድ በሚኒሶታ ደማቅ የሙዚቃ ኮንሰርት አቀረበ::
Mahmud Ahemed – A day filled with tears
74ኛ ዓመቱን የያዘው አርቲስት ማህሙድ አህመድ ትናንት የቫለንታይን ደይን በማስመልከት በሚኒሶታ በተደረገው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ ያሳየው ብቃት ሙዚቃ ምን ያህል አብራው እንደተፈጠረች የሚያሳይ ነው ሲሉ በስፍራው የነበሩ ኢትዮጵያውያን አድናቆታቸውን ገልጸዋል::

ዛሬ በኮምፒውተር ድምጻቸውን እየሞረዱ የሚወጡት አርቲስቶች መድረክ ላይ ሲወጡ በሚሸማቀቁበት ዘመን ማህሙድ የሚታወቅበትን ከትዝታ እስከ ጉራጊኛ ዘፈኖች በማይቀየር ድምጹ ተጫውቶታል ያለን አንድ የሙዚቃ አዋቂ ይህ ዘመን የማይሽረውን ድምፃዊ በዓይኔ ዳግም ከረዥም ዓመታት በኋላ መድረክ ላይ በማየቴ ደስተኛ ነኝ ብሏል::

ማህሙድ ወደ መድረኩ ሲወጣ ሕዝቡ በከፍተኛ ጩኸትና ፉጨት የተቀበለው ሲሆን እርሱም ደረቱን በሁለት እጆቹ በመያዝ ለሕዝቡ ያለውን ፍቅር ገልጿል::

በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተለይ ለአንጋፋ አርቲስቶች የሚሰጡት ክብር በአረአያነት የሚጠቀስ ሲሆን ከዚህ ቀደምም በተመሳሳይ ቴዎድሮስ ታደሰ ሲመጣ ክብራቸውን ገልጸዋል::

በሙዚቃ ሕይወት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ የቆየው ማህሙድ አህመድ ባለፈው ሳምንት በኤድመንተን ካናዳም ተመሳሳይ የሆነ ክብር በሕዝብ ዘንድ ማግኘቱን የዘ-ሐበሻ ዘጋቢዎች ከስፍራው ጠቁመውን ነበር::

በትናንትናው ዕለት በሚኒሶታ በተደረገውና ናዲ ፕሮሞሽን እና ዲጂ ሶሎ ባቀረቡት በዚህ የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ በርካታ ሕዝብ ከመገኘቱም በላይ በመሃሙድ ሥራዎች በ እጅጉ ሲዝናና አምሽቷል::

በዚህ ኮንሰርት ላይ ወጣቱ ድምጻዊ ጃኪ ጎሲም ሥራዎቹን አቅርቧል::

ይህን ታላቅ ኮንሰርት ዘ-ሐበሻ በቭዲዮ አስቀርታዋለች – ሕዝቡ ለማህሙድ ያሳየውን ፍቅርም ይመልከቱበት:: ተከታታይ ቭዲዎችን ለማቅረብም እንሞክራለን::

ዘ-ሐበሻ በአንድ ወቅት ያቀረበችውን የማህሙድ አህመድን ታሪክ ለማንበብ እዚህ ይጫኑ

The post በሚኒሶታ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለማህሙድ አህመድ ያላቸውን ክብር ገለጹ appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል››

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት
• ‹‹ቃል ኪዳናችንን ማጥበቅ አለብን!››

(በዛሬው ዕለት ለቀድሞው የአንድነት አመራሮችና አባላት የተዘጋጀው የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል ላይ ከተናገሩት)

10994318_665307356928259_3852354460061459043_n

ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ፓርቲ ጣኦት አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ቅንጅትንም አፍርሶታል፡፡ አንድነትንም አልፈረሰም ብለው እንዳይከሱኝ እንጅ አፍርሰውታል ማለት እችላለሁ፡፡ በዚህ ሁኔታ ሰማያዊ ላይም አንድ ነገር ማምጣታቸው የማይቀር ነው፡፡ ያ ማለት ግን ሰላማዊ ትግሉ ምን ያህል እንዳስፈራቸው ነው የሚያሳየው፡፡ አገዛዙ በፓርቲዎች ላይ የሚወስደው እርምጃ የሚያሳየው ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን እንጅ ወደኋላ መመለሱን አይደለም፡፡ አንዳንዶቹ እንዲህ አይነት ችግር ሲከሰት ሰላማዊ ትግሉ አበቃለት ይላሉ፡፡ ሆኖም አገዛዙ ሰላማዊ ትግል አስፈርቶት አውሬ ሲሆን የሚያረጋግጥልን ሰላማዊ ትግሉ መጠናከሩን ነው፡፡

በመሳሪያ ትግል ውስጥ አንድ ጀኔራል ሲሞት አሊያም አንድ የጦሩ አካል ችግር ሲደርስበት ‹‹የትጥቅ ትግል አበቃለት›› እንደማይባለው ሁሉ ሰላማዊ ትግል ላይ አንድ ጫና ወይንም የስርዓቱ ደባ ሲከሰት ትግሉ አይሰራም ማለት አይደለም፡፡

ሰላማዊ ትግል መስዋዕትነት አያስከፍልም ማለት አይደለም፡፡ እንዲያውም ሰላማዊ ትግል ውጤት ማምጣት ሲጀምር፣ ዙሩም ሲካረር፣ የሚከፈለው ዋጋም ይበልጥ እየጨመረ ይሄዳል፡፡ የስርዓቱ አውሬነት በተገለጠ ቁጥር፣ እኛም በተሻለ አመራር ትግሉን ስንመራው መስዋዕትነቱ ይበልጡን እየበዛ እንደሚመጣ እንረዳለን፡፡

በአሁኑ ወቅት ስርዓቱ ሰላማዊ ትግሉ በመጠናከሩ ፍርሃት ውስጥ ይገኛል፡፡ ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል፡፡ እስካሁን በሰላማዊ ትግሉ፣ አሁንም በአንድነት ላይ የደረሰው ፈተና የሚያሳየው ሰላማዊ ትግሉ አሸናፊ እንደሆነ ነው፡፡

ዛሬ ያደረግነው ግንኙነት፣ አንድም ለመተዋወቅ፣ በሌላ መልዕክት ለማስተላለፍ፣ ከዚህም በተጨማሪ አንድነታችንን ለማጠናከርና ለትግሉም በቆራጥነት የተዘጋጀን መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ አሁን እዚህ ቦታ የተገናኘን ሰዎች ሰላማዊ ትግሉ ይበልጡን እየተጠናከረ ሲሄድ ምን አልባትም አንድ እስር ቤት የምንታጎር በመሆናችን ቃል ኪዳናችንን ማጥበቅ አለብን፡፡ አንድታችንም የቆየ የፓርቲ ድንበር ሳይገድበን ማጠናከር አለብን፡፡ ከአሁን በኋላ ለሚደርሱብን ችግሮችና እንቅፋቶች ፈጣን መልዕክት እየሰጠን እንቀጥላለን፡፡ ለዚህም የሰማያዊ ፓርቲ አመራር ትግሉን በተገቢው መንገድ እንደሚመራው ማረጋገጥ እፈልጋለሁ፡፡

ሰማያዊ ፓርቲ ውስጥ አንድ የተለመደ ባህል አለ፡፡ በሰማያዊ ቤት ሁሉም ሰው ጓደኛ ነው፡፡ ሁሉም ሰው እኩል ነው፡፡ ማን የማን ጓደኛ መሆኑ አይታወቅም፡፡ የምክር ቤት አባል፣ ኦዲት፣ ስራ አስፈጻሚ፣ ተራ አባል የሚባል ነገር የለም፡፡ በሰማያዊ ቤት ስልጣን ለግንኙነት ምንም አይነት ችግር አይፈጥርም፡፡ አብዛኛዎቹን የአንድነት አባላት አውቃቸዋለሁ፡፡ ይህ የሰማያዊ ፓርቲ ባህል ጋርም ተላምዳችሁ፣ ጥያቄና ሀሳብ ሲኖራችሁም በግልጽ ማቅረብ የምትችሉበት ቤት ነው፡፡ በዚህ መልክም ጠንክረንና ቃል ኪዳናችን አድሰን ትግላችን ማስቀጠል አለብን፡፡ ለምንጓዝበት የተራራ ጉዞም ወገባችን ጠበቅ፣ ልባችን ሞቅ አድርገን በቃል ኪዳናችን ፀንተን ለምንወዳት አገራችን ትግላችን አጠናክረን እንድንቀጥል ጥሪዬን አስተላልፋለሁ፡፡

‹‹አንድነትን ያሳጣኝ ኃይል ለእኔ ጠላቴ ነው››

ወጣት ስንታየሁ ቸኮል (የቀድሞው አንድነት ወጣቶች ጉዳይ)

አንድነት የኢትዮጵያን ፖለቲካ መቀየር የሚችሉ ምሁራንና ታጋዮች የያዘ ፓርቲ ነበር፡፡ አንድነት የኢትዮጵያን ያለባትን ችግር የሚገባ የሚረዱ ወጣትና ሴቶችም ስብሰብ ያለው ፓርቲ ነበር፡፡ አንድነት በነበረው ቁመና ምን አልባትም የመንግስትን ስልጣን መቀበል የሚያስችል አቅም የነበረው ፓረቲ ነው፡፡ አንድነትን ማፍረስ የተፈለገው አንድነት በነበረው አቅም ቢቀጥል ህወሓት/ኢህአዴግ ስልጣኑን እንደሚለቅ ስለሚያውቀው ነው፡፡ አንድነት ያፈረሱት ፓርቲው ውስጥ ምንም አይነት ችግር ኖሮ ሳይሆን ስርዓቱ ስለፈራው ነው፡፡ አንድነት ፕሬዝደንቱን የሰየመው በጠቅላላ ጉባኤው ነው፡፡ አሁን ግን ፕሬዝደንቱ ከኢህአዴግ ጽ/ቤት ነው የተመደበው፡፡ ይህን ከኢህአዴግ ጽ/ቤት የተመደበውን ፕሬዝደንት ነው በቀጥታ ተቀበሉት የተባልነው፡፡ እኛ ደግሞ አንቀበልም፡፡ ያልተቀበልነውና ወደሰማያዊ የመጣነው ሰላማዊ ትግሉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ለማሳየት ነው፡፡

የአንድነት አባላት ወደ ሰማያዊ ፓርቲ ሲመጡ ለፕሮግራምና ለመሳሰሉት ጥቃቅን ነገሮች እየተጨነቁ አይደሉም፡፡ እኛ ወደዚህ የመጣነው በቁጭት ነው፡፡ አንድነትን ያሳጣኝ ኃይል ለእኔ ጠላቴ ነው፡፡ ይህን ጠላት ለመታገል ነው የመጣሁት፡፡ ጥቃቅን የፕሮግራም ልዩነቶች ይህን ትግሌን አያደናቅፈውም፡፡ ስርዓቱ ሰላማዊ ትግል አይቻልም፣ ሲለን እኛ ደግሞ እንዴት እንደሚቻል እናሳየዋለን፡፡ ወደሰማያዊ የመጣንበት ዋነኛው አላማ ይህ ነው፡፡ እኔ በበኩሌ ከሰማያዊ ፓርቲ ወጣቶች ጋር መተዋወቅ አይጠበቅብኝም፡፡ አውቃቸዋለሁ፡፡ እንዲያውም ወደ ቤታችን እንደመጣን ነው የሚሰማኝ፡፡ የጊዜ ጉዳይ መልሶ አገናኝቶናል፡፡ የዚህ አገር ችግር ምን እንደሆነ እናውቀዋለን፡፡ ከዚህ በኋላ የምናደርገው ትግል የነጻነት ትግል ነው፡፡ ወደ ሰማያዊ በመጣንበት ወቅት ከሊቀመንበሩ ጀምሮ በጣም ደስ በሚል ሁኔታ ተቀብለውናል፡፡ ዛሬም በተመሳሳይ መልኩ በጣም ደስ የሚል አቀባበል አድርገውልናል፡፡ ወደፊትም ለምናደርገው ትግል በተመሳሳይ መንፈስ እንደምንቀጥል ተስፋ አለኝ፡፡

The post ‹‹ሰላማዊ ትግሉ ሲጠናከር ስርዓቱ ወደ አውሬነት ይቀየራል›› appeared first on Zehabesha Amharic.

እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ከፖለቲካ ፣ ሲቪክ ፣ የሃይማኖት ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች

$
0
0

«ለውጥ በማይቆም ተሽከርካሪ የሚጓዝ አይደለም፤ የተከታታይ ትግል ውጤት ነው። ነጻነት የምንፈልግ ሁሉ ጀርባችንን ቀና አድርገን መታገል አለብን። ራሳችን ካልፈቀድንለትና ካልተሸማቀቅን፤ ማንም ሰው እንደ ከብት ሊጋልበን ከቶ አይችልም” ነበር ያሉት ዶር ማርቲን ሉዘር ኪንግ ጁኔር ።

በማንኛውም አገር ቢሆን፣  ነጻ የሆነ የዜና አገልግሎት የማያገኝ፤ ተቆርቋሪ የፖለቲካ ወይንም የማህበረሰብ ወይንም የሲቪክ ድርጅት እና በነጻነት የሚንቀሳቀስ የመገናኛ ብዙሃን አገልግሎች የሌለው  ሕዝብ መብት የለውም። መብቱ በመንግሥት የተከለከለ ግለሰብ ሆነ ቡድን፤ ማህበረሰብ ሆነ ሕብረተሰብ ዘላቂነትና ፍትሃዊነት ያለው እድገት አይጎናፀፍም።

ሕወሃት/ኢሕአዴግ ለሃያ አራት ዓመታት በበላይነት ሲገዛት የቆየችዋ ኢትዮጵያችን  ፍትህ፤ ነጻነት፤ ሰብአዊ መብት፤ የሕግ የበላይነት  የማይታይባትና  አምባገነናዊ ስርዓት የሰፈነባት ሃገር ሆናለች። ምንም እንኳን ኢትዮጵያ የመድበል ፓርቲ ስርዓት የምትከተል መሆኗ በሕግ መንግስቱ ቢደነገግም፣ በተግባር የታየው ግን ከገዝው ሕወሃት/ኢሕአዴግ ነጻ የሆኑ ድርጅቶችን ሁሉ የማጥፋት ሂደት ነው። የአገሪቷን ሕግ ሆነ የምርጫ ቦርድን አሰራር  በጣሰ መልኩ፣ በቅርቡ በአገሪቷ ጠንካራ የሚባለውን የአንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ (አንድነት)  አመራርን በማገድ ራሱ ያቋቋማቸዉን ተለጣፊ መሪወች መሾሙ፣ ሕወሃት/ኢሕአዴግ  በምርጫ የማያምንና፣ ብቻውን ለሚቀጥሉት ሃያ፤ ሰላሳ አመታት በጉልበት ለመግዛት እንደወሰነ አመላካች ነው። የዜጎችን የመደራጅትና የመሰባሰብ ሰባአዊ መብትም የረገጠ ነው።

በአንድነት ፓርቲ ላይ ከታየው የሕወሃት/ኢሕአዴግ ያገጠጠ ኢፍትሃዊ እርምጃ በተጨማሪ፣ በሌሎች የፖለቲካና የሲቪክ ማሀብራት ላይ አፈናዉና የመብት ረገጣው ተባብሷል፡፡በህጋዊነት የሚንቀሳቀሱ ድርጀቶች ሁሉ ህልውናቸው አደጋ ላይ ነው። ዜጎችን ሕገ መንግሥቱ በሚፈቅደው መሰረት ሰላማዊ ሰልፍ ሲያደርጉ ይደበደባሉ። ጋዜጠኞች የሰባዊ መብት ተሟጋቾች፣ የሃይማኖት መሪዎች ይታሰራሉ።

ሕወሃት/ኢሕአዴግ  በሚያራምዳቸው የተሳሳቱ የኢኮኖሚ ፖሊሲዎች ዜጎች  ባስከፊ በድህነት እና የኑሮ ዉድነት ስቃይ ዉስጥ እንዲዘፌቁ አድርጓቸዋል። የስራ እድል ማጣት፤ የተፈጥሮ ሃብት ከኢትዮጵያዊያን ተነጥቆ ለጥቂቶች ሃብት ማካበቻ መሆን፤ የጎሳ አድልዎ፤ ጉቦ፤ ሙስና፤ በብዙ ቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ከሕግ ውጭ ማሸሽ፤ በኢትዮጵያዉያን መካከል ስርዓት ወለድ የሆነ የጎሳና የኃይማኖት መለያየት በአገራችን ትልቅ ቀዉስን እና ዉስጣዊ አለመረጋጋትን ፈጥሯል። ከመቼዉም ጊዜ በላይ አገራችን ትልቅ አደጋ ላይ ትገኛለች።

መንግስት የሕዝብ አገልጋይ ሊሆን ይገባዋል። ህወሃት/ኢሕአዴጎች ግን በመንግስት ወንበር ላይ ተቀምጠው ህዝብን ማገለገል ሳይሆን ህዝቡን እየከፋፈሉትእና  እያሰቃዩት ነው። ለሃያ አራት አመታት በህዝብ እና በሀገር ላይ እጅግ ብዙ በደል ፈጽመዋል።  ይህን ለማስቆም ኢትዮጵያዉያን ቆርጠንና  ደፍረን፣  አገር አቀፍ በሆነ ደረጃ መነሳት ይኖርብናል። በውጭና በውስጥ የምንገኘው ለውጥ እና ፍትህ ፈላጊ  ኃይላት፣ አብረን ተባብረን መስራት ግዴታችን ሆኗል። ሕወሃት የሚፈልገው በየተራ ለማጥቃት እንዲያመቸው በተናጥል የሚደረግን  ትግል ነው። ትግሉ የመኖር ያለመኖር፤  የህልውና ጉዳይ ስለሆነ አብሮ ተያይዞ መነሳት የወቅቱ መሪ ጥያቄ ነው።

እኛ ስማችን ከዚህ በታች የተዘረዘረው ስብስቦች እንደዚህ ያለ ተከታታይ ግፍ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ ሲካሄድ በአንድ ላይ ድምፃችን ማሰማት ግዴታችን ነው እንላለን። ስለሆነም፤

  1. በቅርቡ የአንድነት ፓርቲ አመራር አባላትን ህገወጥ በሆነ መንገድ የገዝው ቡድን መሳሪያ በሆነው የምርጫ ቦርድ አማካንነት ከሀላፊነታቸው በግዳጅ አባሮ በአባላት ያልተመረጠ ግለስብ በመሪነት መሾሙን አጥብቀን እናወግዛለን። ለዚህ በስርአቱ ለተሾመ ግለሰብም፣ እውቅና የማንሰጥ ሲሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ትብብር እንዲነፍገው እንጠይቃለን። የተለጣፊው ቡድንም፣ ሊወድቅ የተቃረበን የግፍ አገዛዝ ለማገለገል በወሰዳቸው አሳፋሪ ተግባራትም ተጠያቂ እንደሚሆን ለማሳሰብ እንወዳለን።
  2. ስርአቱ በመኢአድ የውስጥ ጉዳይ ጣልቃ በመግባትና በቀጣይ የከፋፋይነት ስራ ድርጅቱን ለማዳከም የሚያካሂደውን ሁሉ ተገንዝበናል። ይህ የገዥው እኩይ ተግባር እውን የሚሆነው በከፊል በድርጅቱ ውስጥ ያሉትን ችግሮች በመመካከር ማስወገድ ሳይቻል ሲቀርና ለገዥው ቡድንም ጣልቃ መግባት መንግድ ሲከፍት እንደሆነ በመገንዘብ፣ ሁሉም የድርጅቱ መሪወችና አባላት ውስጠ ድርጅት ቅራኔወችን በውስጥ አሰራር፣ በመቻቻል፣ በሆደሰፊነትና በተለመደ ሀገራዊ ጨዋነት በመፍታት ሁሉም የድርጅቱ አባላት እንዲሰባሰቡና ታሪካዊ ሀላፊነታቸውን በጋራ እንዲወጡ  እናበረታታለን።
  3. ገዥው ቡድን በአንድነት ፓርቲ ላይ የማፈራረስ እርምጃ ሲወስድ የድርጅቱ አባላት ፣ ተስፋ ቆርጠው፣ ትግሉን እርግፍ አድርገው እንዲያቆሙ ወይም ሀገር ጥለው እንዲሰደዱ ለማድረግ ነው። ይህን በማድረግም አላንዳች ተቀናቃኝ ሁሉንም ተቆጣጥሮ በህዝባችን እና በሀገራችን ላይ የጀመረውን የግፍ አገዛዝ ለመቀጠል ነው። ሆኖም ሁላችንም እንደተመለከትነው አፍራሹን ህወሀት/ኢህአዴግን በሚያሳፍር ለውጥ ፈላጊውን ደግሞ በሚያኮራ መልክ በአዲስ አበባም ሆነ በክልል ያሉ በዛ አሉ የአንድነት አባላት አሁንም ትግሉን ለመቀጠል ወደ ሰማያዊ ፓርቲ እየተቀላቀሉ መሆናቸውን እንገነዘባለን። በዚህ እጅግ ፈታኝ በሆነ ሰዓት ከድርጅት በላይ ሀገርንና ነጻነትን በማሰቀደም በወሰዱት ቆራጥ እርምጃ ያለንን አድናቆት እየገለጥን ወደ ሰማያዊ ያልተቀላቀሉ ጥቂት የአንድነት አባላትም የአንድነትና የዴሞክራሲ ሀይሎችን በመቀላቀል ትግላቻውን እንዲቀጥሉ እናበረታታለን።
  4. ሁሉም የአንድነትና የዴሞክራሲ ሀይሎች የህወሀት/ኢህአዴግን ቀጣይ አፈና መቋቋም የሚቻለው ተነታጥሎ ሳይሆን በጋራ በመቆም እንደሆነ በመገንዘብ አሁንም ትብብራቸውን አጠናክርው ትግላቸውን እንዲቀጥሉ እናሳስባለን። በአፋኙ የህወሀት/ኢህአዴግ ስርአት ስር ለሀገር አንድነት፣ለህዝብ መብት መከበርና ግፈኛውና ከፋፋይ ስርአት ተደምስሶ በምትኩ ለህዝብ ሙሉ መብት መከበር፣ ለሀገር እንድነትና፣ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስታዊ ስርአትን ለመመስረት ለሚደረገው ትግል ያለንን አጋርነት በጋራ እናረጋግጣለን።

ነጻነት ዋጋ ያስከፍላል። ነጻነት ስለተመኘናት አትመጣም። የኛ እጅ ለእጅ መያያዝና መተባበር የአምባገነኖች ፍጻሜ መጀመርያ ነው። በመሆኑም በተጨበጡ ሥራዎች ዙሪያ ትብብራችንን እያጠናከረን፣ አገር ቤት ለሚደረገው ትግል ሙሉ ድጋፍ እያሳየን፣ የኢትዮጵያ ህዝብ አካል እንደመሆናችን የህዝባችን ነጻነት እስኪያረጋግጥ ከመቼውም ጊዜ በላይ ሳንታክት በጽናት የምንታገል ስለመሆናችን ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን።

  1. የሴቶች  የሰብዓዊ መብት ድርጅት
  2. የኢትዮጵያ ሽግግር ምክር ቤት
  3. የሰማያዊ ድጋፍ ማሀበራት
  4. የአንድነት የስዊዱን ድጋፍ ማህበር
  5. የአንድነት የለንደን ድጋፍ ማሀብር
  6. የኢትዮጵያ ድንበር ጉዳይ ኮሚቴ
  7. ሞዓ አንበሳ
  8. የኢትዮጵያ ፖለቲካ እስረኞች አንድነት ድርጅት በካናዳ (ሶሴፕ ካናዳ)
  9. ጋሻ ለኢትዮጰያ የሲቪክ ድርጅት
  10. ኢትዮጰያዊነት የሲቪክ ድርጅት
  11. ኢትዮ ሶሊዳሪቲ ሚኔሶታ
  12. የአንድነት የሰሜን አሜሪክ የሚልዮኖች ድምጽ ለነጻና ፍትሀዊ ምርጫ ኮሚቴ
  13. የኢትዮጵያ ህዝብ የጋራ ትግል ሽንገፐ (በስሩ የሚገኙት አባል ድርጅቶች ሁሉ)
  • የኢትዮጵያሕዝባዊ አብዮታዊ ፓርቲ (ዴሞክራሲያዊ)
  • የኢትዮጵያመድህን ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (መድህን)
  • ትግራይዴሞክራሲያዊ ትብብር (ትዴት)
  • መላኢትዮጵያ ሶሻሊስት ንቅናቄ (መ.ኢ.ሶ.ን)
  • የኢትዮጵያሲቪክ ማህበራት ስብስብ በእንግሊዝ ሀገር
  • የኢትዮጵያየፖለቲካ እስረኞች አንድነት ኮሚቴ (ኢፓእአኮ)
  • ኢትዮጵያሲቪል ኅብረተሰብ ደጋፊዎች በለንደን ኦንታሪዮ

 

Ethiopia

The post እየከፋ በመጣው የሰብአዊ መብት ረገጣ ላይ የጋራ አቋም መግለጫ ከፖለቲካ ፣ ሲቪክ ፣ የሃይማኖት ድርጅቶችና ታዋቂ ግለሰቦች appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>