Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ”ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ”ያወጣው ጽሁፍ

$
0
0

ጋዜጣ (ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር) የዛሬ 96 አመት የፃፈው ፅሁፍ ለአሁኑ ትውልድ ታሪካዊ ማስረጃ ነው

minilikኢትዮጵያ በየዘመኗ በሕልውናዋ ላይ የተቃጣባት የመበታተን አደጋን ያለፈችበት መንገድ የጦርነት መንገድ ብቻ አይደለም።ሆኖም ግን ከነበሩን የግጭት ታሪኮች በዘለለ በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅ የነበሩ እና በሕዝብ ዘንድም የተወደዱ መሪዎች ነበሩን።ከእነኝህ ውስጥ ዳግማዊ ምንሊክ አንዱ ነበሩ። አፄ ምንሊክ ሀገር የማስተዳደር ጥበብን የተማሩት በአፄ ቴዎድሮስ እጅ ሆነው እድገታቸውን በንጉሡ ቤተመንግስት ማድረግ ከጀመሩበት ጊዜ ጀምሮ መሆኑን ብዙዎች ይስማማሉ።ንጉሡ የቀደሙ አባቶቻቸው አፄ ቴዎድሮስ እና አፄ ዮሐንስ ኢትዮጵያን አንድ የማድረግ አላማቸው እውን እንዲሆን ያደረጉ እድለኛ ንጉስም ናቸው።

አፄ ምንሊክ ኢትዮጵያን አንድ ከማድረግ አልፈው እስከ ኬንያ፣ሱዳን እና ሱማልያ ግዛት ድረስ ዘልቀው ገብተው በቅኝ ግዛት ይማቅቁ የነበሩ ህዝቦችን ነፃ ያወጣሉ የሚል ስጋት የነበረባቸው እና በወቅቱ በእነኚሁ የጎረቤት ሃገራት ላይ የጥቅም ፍላጎት የነበራቸው የአውሮፓ ሃገራት በብርቱ ተፈታትነዋቸው ነበር።በመሆኑም አዲስ የድንበር ውል ከኢትዮጵያ ጋር የመፈራረም ፍላጎት ከእንግሊዝ፣ፈረንሳይ እና ኢጣልያ በኩል ጥያቄ መነጻቱን የወቅቱ የታሪክ ድርሳናት ያወሳሉ።

ዛሬ ዛሬ በምንሊክ ላይ ታሪካዊ መሰረት የሌላቸው ቀድሞ አፄ ምንሊክ የቅኝ ግዛት ጥማታቸውን በገቱባቸው እና ቂም በያዙ ፀሐፊዎች የተፃፉ ናቸው ብለው ከሚነግሩን አስገራሚ ”የታሪክ” ፅሁፎች ውስጥ ”በምኒሊክ ዘመን እስከ አስር ሚልዮን ኦሮሞዎች አለቁ” የሚል ፅሁፍ በአንዳንድ የማህበራዊ ድህረ ገፆች ተለቀው ሲነበቡ መመልከት አስገራሚ የሰሞኑ ክስተት ነው።በፖለቲካው አለም በቂ ርዕዮተ አለምም ሆነ ፖለቲካዊ ፍልስፍና የጠፋባቸው አንዳንድ ወገኖች ”ትርፋማ” ብለው ያሰቡት የዘር ፖለቲካ በኢትዮጵያውያን መካከል መዝራት እና ከመቶ አመት በፊት የሆነውን የታሪክ ክስተት የአሁኑን ትውልድ በመውቀስ ትኩረት ለማግኘት ሲታትሩ መመልከት የዘመኑ አስቂኝ ተውኔት ነው።ዳግማዊ ምንሊክ ገና ብዙ የሚጠና ፖለቲካዊ፣ማኅበራዊ እና ወታደራዊ ክህሎት ባለቤት ለመሆናቸው በወቅቱ ከወጡት የዓለማችን ድንቅ ጋዜጦች አንዱ የ ኒውዮርክ ታይምስን እትም መመልከት ይበቃል።

ከእዚህ በታች በሚገኘው የኒውዮርክ ታይምስ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ የኢትዮጵያ ጠቅላላ ሕዝብ ብዛትን 7,000,000 (ሰባት ሚልዮን) መሆኑን ያስቀምጣል። እዚህ ላይ አንዳንድ እራሳቸውን የታሪክ ምሁራን ነን በሚል ባልተጨበጠ ይልቁንም በምኒሊክ የቅኝ ግዛት ህልማቸው ከተደናቀፈባቸው ቂመኛ ፀሐፊዎች አነበብን የሚሉት እና የኦሮምኛ ተናጋሪ ኢትዮጵያውያንን ያማለሉ መስሏቸው ”ምንሊክ 10 ሚልዮን ኦሮሞ ገደሉ” እያሉ ኢትዮጵያ ከነበራት የህዝብ ብዛት (7 ሚልዮን) በላይ ቁጥር ሲጠሩ እፍረት አልተሰማቸውም።

”ማን ያውራ የነበረ” እንዲሉ የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ላይ ጋዜጣው አዲስ አበባ በነበረ በልዩ ዘጋቢው አማካይነት ስለንጉሡ እና ኢትዮጵያ ፖለቲካዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ሁኔታ ፅፎ ነበር።ጋዜጣው አፄ ምንሊክ እና አስተዳደራቸውን ከገለፀበት አረፍተ ነገር ውስጥ እነኝህ ይጠቀሳሉ –

– ኢትዮጵያን ወደ ህገመንግስታዊ የንጉሥ አስተዳደር ለመቀየር ሂደት ላይ መሆኗን፣

– የኢትዮጵያ ህዝብ ብዛት 7 ሚልዮን መሆኑን፣

– አፄ ምንሊክ ንጉሰ ነገስት ሲሆኑ ጦርነት የነበረው የአፄ ዮሐንስ ተተኪ እሳቸው መሆናቸውን ካልተቀበሉት ጋር ብቻ እንደ ነበር፣

– የአውሮፓውያንን ስልጣኔ ወደሀገራቸው ለማምጣት የባርያ ንግድን ከመዋጋታቸውም በላይ ነፃ ትምህርት ዕድል ዜጎች እንዲያገኙ መሰረት መጣላቸውን፣

– ምንሊክ እራሱ ልዩ ችሎታ ያላቸው ሰው መሆናቸውን። ከችሎታዎቻቸው መካከል ዲፕሎማት፣የፋይናንስ ባለሙያ እና ወታደር የሚሉት እንደሚጠቀሱ እና

– እንደ ዲፕሎማት እና ወታደር የጣልያንን ወረራ ኢትዮጵያ እንድታሸንፍ ያደረጉበት ጥበብ መሆኑን፣

የሚሉ ይገኙበታል።የጋዜጣውን ሙሉ ፅሁፍ ከእዚህ በታች ያለውን ሊንክ ከፍተው ያንብቡ።

የኒውዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ኅዳር 7/1909 ዓም እ ኤ አቆጣጠር እትም ለማንበብ ይህንን ሊንክ ይክፈቱ።

Published: November 7, 1909 Copyright © The New York Times
http://query.nytimes.com/mem/archive-free/pdfres=F50A12F63A5A15738DDDAE0894D9415B898CF1D3

The post ስለ ዳግማዊ ምንሊክ የ” ኒዎርክ ታይምስ ጋዜጣ” ያወጣው ጽሁፍ appeared first on Zehabesha Amharic.


አባይ ጸሐዬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዛቱበት ድምጽ ተለቀቀ –“በአ.አ. ማስተር ፕላን ላይ ዳግም ጥያቄ ካነሱ ልክ እናስገባቸዋለን”አሉ

$
0
0

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን ም እመናንን ለሁለት በመክፈል የኢሕአዴግን የስልጣን ዘመን ያረዘሙት ሕወሓቱ አባይ ጸሃዬ ሰሞኑን በኦሮሞ ሕዝብ ላይ ዛቱ:: ድምጻቸው ተቀርጾም በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ በኩል ለሕዝብ ይፋ ሆነ:: አባይ ጸሓዬ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን ጉዳይ እንዲራዘም የተደረገው ሕዝቡ ባነሳው ተቃውሞ እንዳልሆነ ገልጸው በቅርቡ ተግባራዊ እንደሚሆን ገልጸዋል::

የአዲስ አበባ ማስተር ፕላን እንዳይሳካ የኦህዴድ ባለስልጣናትም ተባብረዋል ያሉት አባይ ጸሓዬ በአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ማስፋፊያ ዙሪያ ዳግመኛ ጥያቄ የሚያነሱትን ልክ እናስገባቸዋለን ብለዋል::

ከኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ የተገኘው ዜና የሚከተለው ነው::

አቶ አባይ ጸሐዬ

አቶ አባይ ጸሐዬ

The post አባይ ጸሐዬ በኦሮሞ ሕዝብ ላይ የዛቱበት ድምጽ ተለቀቀ – “በአ.አ. ማስተር ፕላን ላይ ዳግም ጥያቄ ካነሱ ልክ እናስገባቸዋለን” አሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

ኦብኮ በገዥው ፓርቲ ወከባ እየደረሰብኝ ነው አለ

$
0
0

‹‹በጋራ ምክር ቤቱ እየተጠቀምን አይደለም›› አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ የኦብኮ ሊቀመንበር

OFC_2009ኦብኮ ኢህአዴግን ጨምሮ ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመሰረቱት የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባል ሆኖ እየተንቀሳቀሰ ቢሆንም የምክር ቤቱን ስምምነት በጣሰ መልኩ በአባላቱ ላይ ከፍተኛ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ እና የጋራ ምክር ቤቱም ህጎቹን ለማስከበር አቅም ማጣቱን የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ቶሎሳ ተስፋዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጸዋል፡፡ የኦህዴድ ካድሬዎች የኦብኮን አባላት በማስፈራራት፣ ቤተሰቦቻቸውን በማሸማቀቅና በማዋከብ ከምርጫ እጩነታቸው ራሳቸውን እንዲያገሉ፣ ራሳቸውን ከምርጫው አናገልም ያሉትን በማሰርና ከስራ በማባረር እንዲሁም ንብረታቸውን በመዝረፍ ላይ እንደሚገኙ የገለጹት አቶ ቶሎሳ በፓርቲው አባላት ላይ የሚደርሰውን ወከባ ለምርጫ ቦርድና ለጋራ ምክር ቤቱ ቢያቀርቡም ሁለቱ አካላት መፍታት እንዳልቻሉ ገልጸዋል፡፡

‹‹በኦህዴድ ካድሬዎች ወከባ የደረሰበት አባላትን ለምርጫ ቦርድ ሪፖርት በማድረጉ፣ ለምን በምርጫ ቦርድ ሪፖርት አደረክ በሚል የኦህዴድ ካድሬዎች ሌሊት ሰብረው ገብተው የሞባይል ሱቁን ዘርፈውታል፡፡›› ያሉት ሊቀመንበሩ ጫናው ከአቅማችን በላይ ሆኗል ብለዋል፡፡

አቶ ቶሎሳ አክለውም ‹‹ወደ ጋራ ምክር ቤቱ ስንገባ አባላቶቻችን ላይ የሚደርሰው ወከባና አፈና ይቀንሳል የሚል እምነት ነበረን፡፡ ሆኖም የጋራ ምክር ቤቱ ህጎቹን ለማስከበር አቅም የለውም፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ የተለያዩ ምክንያት እየተጠቀሰ ወርሃዊ ስብሰባውን ማድረግ አልቻለም፡፡ ለይስሙላህ ካልሆነ በስተቀር ጠንክሮ ውጤት ያስመዘግባል የሚል ግምት የለኝም፡፡ ምንም እንኳ እንዲጠናከር ግፊት ብናደርግም እንደተባለው እየተጠቀምንበት አይደለም›› ብለዋል፡፡

The post ኦብኮ በገዥው ፓርቲ ወከባ እየደረሰብኝ ነው አለ appeared first on Zehabesha Amharic.

ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ

$
0
0

• ‹‹ሰማያዊ ሳይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ምርጫ ቦርድ በየወረዳው ለሚገኙ የምርጫ ቦርድ አስፈፃሚዎች ‹‹ከቦርድ የሚጠበቅ ውሳኔ ስላለ፣ ሰኞ ተሰብስበን እስክንወስን ድረስ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎቹን ወደ ቅጽ 4 እንዳታዘዋውሩ›› የሚል መልዕክት ማስተላለፉን እና ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ከመቀነስ ጀምሮ ፓርቲውን ከምርጫው ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ከምርጫ አስፈጻሚዎች መረጃዎች ደርሰውናል ሲሉ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
ፓርቲው ከትግራይ፣ እስከ ሞያሌ ጫፍ ዕጩ ማቅረቡ ለገዥው ፓርቲ ያልተጠበቀና አስደንጋጭ ሆኖበታል ያሉት ኢ/ር ይልቃል በህጋዊ መንገድ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሰማያዊ ፓርቲ ላይ የሚደረጉት ጫናዎች ተጠናክረው መቀጠላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሰማያዊ ሰይጠብቁት በመላ አገሪቱ ዕጩ በማቅረቡ ደንግጠዋል፡፡ በአዲስ አበባ 23 ዕጩዎችን አቅርበናል፡፡ አዲስ አበባ ውስጥ አንድ ዕጩ ያቀረቡ ፓርቲዎች ሳይቀር በሚዲያ ሲነገርላቸው ሰማያዊ ፓርቲ ያቀረባቸውን ዕጩዎች ለመግለጽ ፈቃደኛ አልሆኑም፡፡ ዛሬ ጠዋት ደግሞ የምርጫ ቦርድ ባለስልጣናት በቴሊቪዥን ቀርበው ‹ሰማያዊ በተደጋጋሚ ብንነግረው አልሰማም፣ በመሆኑም ሰኞ ቦርዱ ተሰብስቦ ውሳኔ ያስተላልፋል› ብለዋል፡፡ ይህም የሚያሳየው ሰማያዊ በምርጫው እንዳይሳተፍ ችግር መፍጠር እንደሚፈልጉ ነው፡፡›› ሲሉ ፓርቲው ላይ እየተፈጠረበት ያለውን ጫና ገልጸዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ወንድሙ ጎላ በዛሬው ዕለት በኢቢሲ ቀርበው ሰማያዊ ይቅርታ ባለመጠየቁና ማስጠንቀቂያዎችን ባለመቀበሉ ነገ ሰኞ ጥር 9/2007 ዓ.ም ውሳኔ ያስተላልፋል ብለዋል፡፡
ከሌሎች ፓርቲዎች ሰማያዊን በመቀላቀል በፓርቲው ምልክት ለመወዳደር የወሰኑ ዕጩ ተወዳዳሪዎች እንዲሰረዙ መደረጉና በሌሎች ዕጩዎች ላይም ከፍተኛ ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝ ነገረ ኢትዮጵያ መዘገቧ ይታወሳል፡፡

The post ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ ፓርቲን ከምርጫ ለማገድ ፍላጎት እንዳለው ታወቀ appeared first on Zehabesha Amharic.

ማኅበረ ቅዱሳን በሚኒሶታ የቴሌቭዥን ስርጭት ጀመረ

$
0
0

mahibere-kidusan-logo(ዘ-ሐበሻ) በሚኒሶታ የማኅበረ ቅዱሳን የሚዲያ ክፍል ሃላፊ( ተጠሪ) የሆኑት አቶ መለሰ አበበ ለዘ-ሐበሻ እንዳስታወቁት ማኅበረ ቅዱሳን በሚኒያፖሊስ እና በሴንት ፖል ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የሚሆን የቴሌቭዥን ስርጭት ጀመረ::

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስትያን ማኅበረ ቅዱሳን የሚኒያፖሊስ ንዑስ ማዕከል በየሳምንቱ እሑድ በሚኒያፖሊስ እና በሴንት ፖል ከተሞች የቴሌቪዥን ፕሮግራሙን የሚያቀርብባቸው ቻናሎች:-

ሴንት ፖል SPNN Channel 14

እሑድ 12:30pm-1:30pm እንዲሁም እሑድ 7:30pm-8:30pm ሲሆን

በሚኒያፖሊስ MTN ደግሞ

Channel 75 እሑድ ከ9pm-10pm መሆናቸው ታውቋል::

እንደ አቶ መለሰ ገለፃ ከሚኒያፖሊስ እና ሴንት ፖል ከተማ ውጭ ወይም አገር የምትገኙ መርሐግብሩን በተመሳሳይ ስዓት በኢንተርኔት ድረ ገጽ በቀጥታ መከታተል ይቻላል ብለዋል:: የኢንተርኔት አድራሻው Channel 75: http://www.mtn.org/channel 75 ነው::

The post ማኅበረ ቅዱሳን በሚኒሶታ የቴሌቭዥን ስርጭት ጀመረ appeared first on Zehabesha Amharic.

የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ

$
0
0

በፌብርዋሪ 14, 2015

አጠቃላይ የአባላት ስብሰባ 

unnamed (3)

ፌብርዋሪ 14, 2015 በኖርዌይ የሚኖሩ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ መተዳደሪያ ደንቡ በሚያዘው መሰረት የአባላት ጠቅላላ 3ኛ  እና 4ኛ ሩብ ዓመት መደበኛ ስብሰባ የሥራ ክንውን ሪፖርት የቀረበበት የተሳካ አጠቃላይ ስብሰባ አድርገዋል። በስብሰባው ላይ በኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎና በተለያዩ የኖርዌይ ከተሞች የሚኖሩ የድርጅቱ አባላቶች የተገኙ ሲሆን የአባላት ስብሰባው አስቀድሞ በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት በኖርዌጂያን የሠዓት አቆጣጠር ከቀኑ 13፡30 ተጀምሮዋል።

 

ስብሰባውን የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ አቢ አማረ በ 24 ዓመት የወያኔ አረመኒያዊ አገዛዝ በግፍ ለተገደሉት እና በየእስር ቤቱ በግፍ ለሚስቃዮ ንጹሀን ዜጐች የአንድ ደቂቃ የህሊና ጹሎት በማድረግ ስብሰባውን ያስጀመሩ ሲሆን በመቀጠልም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ሊቀመበር አቶ ዮሐንስ አለሙ አባላቱን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ንግግር አቅርበው የዛሬው የአባላት ስብሰባ ከሌሎቹ ጊዜያት በሁለት ምክንያቶች የተለየ መሆኑን ለተሰብሳቢው ገልፀዋል ይሄውም፦

  • የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60 ኛ ዓመት የልደት በአል የሚከበር መሆኑና

 

  • የዲሞክራሲ ለውጥ በኢትዩጵያ ድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የተመሰረተበትን 10ኛ አመቱ ላይ መገኘቱ እንደሆነ በማስረዳት ድርጅቱ በእነኚህ አስር ዓመታት ውስጥ ብዙ አመርቂ ስራዎችን እንደሰራና ቅንጅት ይዞለት የተነሳው አላማ እስከ አሁን ድረስ ይዞ በመጓዝ ላይ ያለ ድርጅት በመሆኑ ኩራት የሚሰማቸው መሆኑን በመግለፅ ይህንንም አላማ ከግብ ለማድረስ በድርጅቱ ውስጥ ያሉ ወጣቶች እየሰሩ ያለውን በማድነቅ ወጣቶች ወያኔን ከስልጣን ለማስወገድ ትልቅ አስተዋፅኦ ያላቸው በመሆኑ ትግላቸውን አጠንክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተናግረዋል። ሊቀመንበሩ በንግግራቸው መጨረሻ አቶ አንድአርጋቸው ፅጌንና ሌሎችም በግፍ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞችን በትግላችን እናስፈታለን ብለዋል።

unnamed (2)በመቀጠል የተለያዩ የስራ ክፍል ኃላፊዎች የስድስት ወር የስራ ክንውን ረፖርት ለአባላቱ ያቀረቡ ሲሆን ከበርገን፣ ከስታቫንገር፣ እና ከትሮንዳይም የመጡ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት  በኖርዌይ የስራ ኃላፊዎች በስድስት ወር ውስጥ ስለሰሩት ስራዎች እና ወደፊትም ሊሰሩ ያቀዱትን ስራዎች ለአባላቱ በዝርዝር አስረድተዋል።

ከአባላቱ የተለያዩ ጥያቄዎች የቀረቡ ሲሆን በድርጀቱ ሊቀንበሩ አማካኝነት ማብራሪያ የተሰጠባቸው ሲሆን፣ በመቀጠል የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ የሚረዳቸው ድርጅቶችን በማስመልከት በድርጅቱ በተወከሉት ሠዎች አማካኝነት ስለድርጅቶቹ አላማ እና ድርጅቶች እየሰሩ ስላሉት ስራዎች ሰፋ ያለ ግምገማ አቅርበዋል።

ግንቦት ሰባትን በመወከል ዶ/ር ሙሉዓለም አዳም ንግግር ያደረጉ ሲሆን በቅርቡ ግንቦት 7 ከአርበኞች ጋር ውህደት እንደፈጠሩ በመግለፅ ውህደት ያስፈለገበትንና የውህደቱን ጠቀሜታ በመግለፅ ግንቦት 7 የፍትህ የነጻነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ የሚለው ስምም አርበኞች ግንቦት 7 የፍትህ የነፃነት የዲሞክራሲ ንቅናቄ በሚል መተካቱን በመናገር ድርጅቱን እየመሩ ያሉትን አመራሮች እነማን እንደሆኑ ለአባላቱ አስተዋውቀዋል ።

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ እየደገፈ ያለውን የሰማያዊ ፓርቲ አላማ እና እየሰራ ያለውን ስራ ሰፋ ያለ ማብራሪያ ያቀረቡት ደግሞ አቶ ተዘራ ሲሆኑ የሰማያዊ ፓርቲ ከአረመኔያዊው የወያኔ መንግስት የተለየ ወከባ እንደሚደርስበትና የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችም ሆነ አባላቶች በወያኔ እየደረሰባቸው ያለውን ጫና በመቋቋም ትግላቸውን  አጠናክረው በመቀጠል ላይ እንደሆኑ በማስረዳት ወደፊትም ዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ አባላቶች ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

unnamed (1)ስለ አንድነት ፓርቲ አጠር ያለ ንግግር ያደረጉ አቶ ዮሐንስ  ሲሆኑ እሳቸው በወያኔ መሰሪ ሴራ አንድነት ፓርቲ በመፍረሱ እንዳዘነኑና ነገር ግን ዘጠና ከመቶ የሚሆኑት የአንድነት አባላትም ሆነ አመራሮች ሠማያዊ ፓርቲን መቀላቀላቸውን ጠቅሰው ይሄም እንዳስደሰታቸውና ለጊዜው አንድነትን መደገፋቸውን በማቆም የዲሞክራሲያዊ ለውጥ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አላማ ጋር ተመሳሳይነት ያላቸው ድርጅቶች ሠማያዊ ፓርቲ እና አርበኞች ግንቦት 7 ድርጅቶችን በመደገፍ እንደሚቀጥሉ አባላቱ በአንድነት ድምፅ ወስነዋል። ከዚህ በፊት የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ አንድነት ፓርቲን፣ ሰማያዊ ፓርቲ እና ግንቦት ሰባትን ሲደግፉ መቆየታቸው ይታወቃል።

በመጨረሻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ምክትል ሊቀመንበር አቶ ዳንኤል አበበ የመዝጊያ ንግግር አድርገው የአባላት ስብሰባው 16፡30 ተጠናቋል።

በመቀጠልም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን 60ኛ አመት የልደት በአል አከባበር የዲሞክራሲያዊ ለውጥ ድጋፍ ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ዮሀንስ የመክፈቻ ንግግር አድርገው ስለአቶ አንዳርጋቸው አጭር ንግግር በማድረግ ዝግጅቱን አስጀምረዋል። የአንዳርጋቸውን ታሪክ የሚዳስስ አጭር ፊልም በወጣቶች ክፍል የቀረበ ሲሆን በመቀጠልም አቶ  አንዳርጋቸው ፅጌ ማን ነው? በሚልህይወትታሪኩ ዙሪያ እና ለሀገሩ ያደረጋቸውን የትግል ተሞክሮዎች በቅርበት ከሚያውቋቸው ሰው ሰፋ ያለ ማብራሪያ ቀርቧል። እንዲሁም አቶ አንዳርጋቸውን የሚያወድሱና ስለጀግንነቱ የሚያወሩ የተለያዩ ግጥሞችም ቀርበዋል።

በመጨረሻም የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌን ምስል የያዙ ኬኮች ከድርጅቱ ዋና ፅፈትቤት እና ትሮንድላንድ ቅርንጫፍ ፅፈትቤት አማካኝነት የተዘጋጀ ሲሆን በድርጅቱ ሊቀመንበር እንዲሁም በወጣቶችና ሴቶች ክፍል ተወካዮች የመልካም ልደት ኬኩ ተቆርሶ ስነስርአቱ በአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ በተደረሰው ላንቺ ነው ሀገሬ ላንቺ ነው ላንቺ ነው ኢትዮጵያ ላንቺ ነው በሚለው ዝማሬ ዝግጅቱ በተሳካ ሁኔታ በኖርዌጅያን የሰአት አቆጣጠር ከምሽቱ 22፡00 ተጠናቋል።

በመጨረሻ የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ ወጣቶች ፕሮግራሙን በመዘጋጀትና

በመምራት ላደረጉት  አስተዋጾ በድጅቱ ና በስራ አስፈጻሚኮሚቴ ስም ምስጋና እናቀባለን!1

 

ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ

የዲሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ የድጋፍ ድርጅት በኖርዌይ

The post የዲሞክራሲዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድጋፍ ድርጅት ኖርዌይ የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ 60ኛ አመት የልደት በአል በተሳካ ሁኔታ ተከናወነ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: የህወሓት አስተዳደር የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተጻረረ መሆኑ.. ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ…የኢ/ር ይልቃልና የዶ/ር መረራ ወቅታዊ ቃለምልልስ…አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚጠይቅ ከ70 ሺህ በላይ ፊርማ ተሰባስቦ ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር መሰጠቱ…የቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ያስከተለው ክፍፍልና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የካቲት 8 ቀን 2007 ፕሮግራም

እንኳን ለ78ኛው የየካቲት 12 የሰማእታት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ

<...ምርጫ ቦርድ ሆን ብሎ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ህገ ወጥ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ያለው ይመስላል … ትግላችንን ግን የበለጠ አጠናክረን እንቀጥላለን...> ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

በቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫና ተከትሎት የመጣው ክፍፍል ስለ ጉዱዩ ከሰበካው ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ከዶክተር አለባቸው ደሳለኝ የቤተክርስቲያኒቱ አስመራጭ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ አቶ መላኩ አምባቸው እና የሰበካው ጉባኤ ምርጫ ህጋዊ አይደለም ተቀባይነት የለውም ከሚሉ ወገኖች አቶ ዩሀንስ ዳኘው ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ

የየካቲት 12 መታሰቢያ (ልዩ ጥንቅር)

ቃለ መጠይቅ ከአቶ ኪዳኔ አለማየሁ ከአለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ ፋሺስት ጣሊያን በወገኖቻችን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ መድረክ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ የኢጣሊያ መንግስት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ

<..የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርቻ መስረቅ ነውር ነው ዘላለም ምርጫ እየሰረቅክ አትቀጥልም ይሄ እንዲያበቃ ለመብቱ ለድምጹ ዘብ መቆም አለበት...ምርጫውን ለመታገያ ነው የምንፈልገው..> ዶ/ር መረራ ጉዲና የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ጋር ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

* ዕውቁ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቁ ከ70 ሺህ በላይ የተማፅኖ ፊርማዎች ለእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሰጡ

* ጠበቃቸው አዲስ አበባ ሄደው እንዲጎበኟቸው ለም/ቤት አባላት ተጠይቋል

* የኢህአዲግ አገዛዝ የደህንነትና የመከላከያ ባለስልጣናት ከኦብነግ ባለስልጣናት ጋር ሰሞኑን ኬኒያ ውስጥ መነጋገራቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ ታወቀ

ዶ/ር መራራ ጉዲና ምርጫ ቦርድ በህገ ወጥ ምንገድ ዕጩዎቻቸውን እንዳይመዘገቡ እያደረገ መሆኑን ገለፁ

ህዝቡ ምርጫ እየሰረቅክ መግዛትህን አቁም ማለት አለበት ብለዋል

* ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ዕጩዎች እንዳይመዘገቡ መታገዱ ምርጫ ቦርድ በሰማያዊ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ያሳያል አሉ

ትግሉ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል

ቦርድ ሰማያዊን ዕጩዎችና ምልክቶች ሆነ ብሎ ይፋ አላደረገም እያገደም ነው ብለዋል

* የህውሃት ኢህዴግ አገዛዝ የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተፃረረ ነው አንድ የሀይማኖት ተቋም ወቀሳውን ገለፀ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: የህወሓት አስተዳደር የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተጻረረ መሆኑ.. ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ… የኢ/ር ይልቃልና የዶ/ር መረራ ወቅታዊ ቃለምልልስ… አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚጠይቅ ከ70 ሺህ በላይ ፊርማ ተሰባስቦ ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር መሰጠቱ… የቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ያስከተለው ክፍፍልና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

ለ11 ሰዎች ሰዎች መጥፋት ምክንያት የሆነው የሲኖ ትራክ እና የሚኒባሱ ግጭትና የተቃጠሉበት ፎቶዎች ይዘናል

$
0
0

ዘ-ሐበሻ ጠዋት ላይ በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ ቀርሳ በተባለ ስፈራ ትላንት ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት በሚል ዘግባ ነበር:: አደጋው የደረሰው ትላንት ምሽት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ሲሆን፥ ወደ አዲስ አበባ ይመጣ የነበረ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ አደጋው መድረሱን መዘገባችን ይታወሳል:: የታጋጩትና የተቃጠሉትን የሁለቱን መኪናዎች ሁኔታ የሚያሳይ ፎቲ ግራፎች ከአዳነ አረጋ አግኝተናል – ይመልከቱት:-
kataelo

katelo 2

katelo 3

The post ለ11 ሰዎች ሰዎች መጥፋት ምክንያት የሆነው የሲኖ ትራክ እና የሚኒባሱ ግጭትና የተቃጠሉበት ፎቶዎች ይዘናል appeared first on Zehabesha Amharic.


Hiber Radio: የህወሓት አስተዳደር የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተጻረረ መሆኑ.. ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ…የኢ/ር ይልቃልና የዶ/ር መረራ ወቅታዊ ቃለምልልስ…አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚጠይቅ ከ70 ሺህ በላይ ፊርማ ተሰባስቦ ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር መሰጠቱ…የቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ያስከተለው ክፍፍልና ሌሎችም

$
0
0

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የካቲት 8 ቀን 2007 ፕሮግራም

እንኳን ለ78ኛው የየካቲት 12 የሰማእታት መታሰቢያ በዓል አደረሳችሁ

<...ምርጫ ቦርድ ሆን ብሎ በሰማያዊ ፓርቲ ላይ ህገ ወጥ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጅት ያለው ይመስላል … ትግላችንን ግን የበለጠ አጠናክረን እንቀጥላለን...> ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

በቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫና ተከትሎት የመጣው ክፍፍል ስለ ጉዱዩ ከሰበካው ጉባኤ ዋና ፀሀፊ ከዶክተር አለባቸው ደሳለኝ የቤተክርስቲያኒቱ አስመራጭ ኮሚቴ ዋና ፀሀፊ አቶ መላኩ አምባቸው እና የሰበካው ጉባኤ ምርጫ ህጋዊ አይደለም ተቀባይነት የለውም ከሚሉ ወገኖች አቶ ዩሀንስ ዳኘው ጋር ያደረግነው ቃለ መጠይቅ

የየካቲት 12 መታሰቢያ (ልዩ ጥንቅር)

ቃለ መጠይቅ ከአቶ ኪዳኔ አለማየሁ ከአለም አቀፍ ሕብረት ለፍትሕ የኢትዮጵያ ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ ፋሺስት ጣሊያን በወገኖቻችን ላይ ያደረሰው ጭፍጨፋ በዓለም አቀፍ መድረክ ተገቢውን ትኩረት እንዲያገኝ የኢጣሊያ መንግስት ለኢትዮጵያ ተገቢውን ካሳ እንዲከፍል ስለሚያደርገው እንቅስቃሴ

<..የኢትዮጵያ ሕዝብ ምርቻ መስረቅ ነውር ነው ዘላለም ምርጫ እየሰረቅክ አትቀጥልም ይሄ እንዲያበቃ ለመብቱ ለድምጹ ዘብ መቆም አለበት...ምርጫውን ለመታገያ ነው የምንፈልገው..> ዶ/ር መረራ ጉዲና የመድረክ ም/ሊቀመንበርና የውጭ ግንኙነት ሀላፊ ጋር ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

* ዕውቁ የነፃነት ታጋይ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲፈቱ የሚጠይቁ ከ70 ሺህ በላይ የተማፅኖ ፊርማዎች ለእንግሊዙ ጠቅላይ ሚኒስትር ተሰጡ

* ጠበቃቸው አዲስ አበባ ሄደው እንዲጎበኟቸው ለም/ቤት አባላት ተጠይቋል

* የኢህአዲግ አገዛዝ የደህንነትና የመከላከያ ባለስልጣናት ከኦብነግ ባለስልጣናት ጋር ሰሞኑን ኬኒያ ውስጥ መነጋገራቸው ተሰማ

ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ ታወቀ

ዶ/ር መራራ ጉዲና ምርጫ ቦርድ በህገ ወጥ ምንገድ ዕጩዎቻቸውን እንዳይመዘገቡ እያደረገ መሆኑን ገለፁ

ህዝቡ ምርጫ እየሰረቅክ መግዛትህን አቁም ማለት አለበት ብለዋል

* ኢ/ር ይልቃል ጌትነት የሰማያዊ ዕጩዎች እንዳይመዘገቡ መታገዱ ምርጫ ቦርድ በሰማያዊ ላይ እርምጃ ለመውሰድ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን ያሳያል አሉ

ትግሉ በተጠናከረ መንገድ ይቀጥላል

ቦርድ ሰማያዊን ዕጩዎችና ምልክቶች ሆነ ብሎ ይፋ አላደረገም እያገደም ነው ብለዋል

* የህውሃት ኢህዴግ አገዛዝ የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተፃረረ ነው አንድ የሀይማኖት ተቋም ወቀሳውን ገለፀ

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: የህወሓት አስተዳደር የክርስትና ዕምነት ተከታዮችን ሀሳብን በነፃ የመግለፅ መብት እየተጻረረ መሆኑ.. ኢትዮጵያ የበርበራን ወደብ ለመጠቀም ማቀዷ… የኢ/ር ይልቃልና የዶ/ር መረራ ወቅታዊ ቃለምልልስ… አንዳርጋቸው እንዲፈቱ የሚጠይቅ ከ70 ሺህ በላይ ፊርማ ተሰባስቦ ለእንግሊዙ ጠ/ሚ/ር መሰጠቱ… የቬጋስ የደብረ ምህረት ቅዱስ ሚካኤል ቤ/ክ አወዛጋቢው የሰበካ ጉባኤ ምርጫ ያስከተለው ክፍፍልና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

ተመስገን ደሳለኝ ምልክታችን ነው! –ከበድሉ ዋቅጅራ

$
0
0

ተመስገን ደሳለኝ ምልክታችን ነው፤ ልንሸፍነው ያልቻልነው ምልክት፡፡ ተመስገን የተከሰሰውና የተፈረደበት ከአሸባሪዎች ጋር ግንኙነት አለው ወይም ደግሞ አሸባሪ ነው ተብሎ አይደለም፤ የተከሰሰውም የሶስት አመት እስር የተፈረደበትም በጻፈው ጽሁፍ ነው፡፡ በመሆኑም ተመስገን ሀሳብን በነጻነት የመግለጽ ህገመንግስታዊ መብታችን ያለመከበር ምልክት ነው፡፡
Temesgen Desalegn behindbar
ተመስገን ጠንካራ ግለሰባዊ ሰብእናውንና ህገመንግስታዊ መብቱን በመጠቀም፣ ለዚህች ሀገርና ለህዝቦቿ ይበጃል ያለውን ሀሳብ ለመግለገልጽና በሰላማዊ መንገድ ለመሟገት አፍላ የወጣትነት እድሜው ያላጓጓው ዜጋ ነው፡፡ በመሆኑም ተመስገን የ‹መሬት ላራሹንና የብሄረሰቦችን መብት ጥያቄ አንግበው በነሳት ላመኑበት እንደታገሉት አይነት ወጣቶች ዛሬም ለመኖራቸው ምልክት ነው፡፡

ከሁሉም በላይ ተመስገን የዘመን ተሻጋሪው ኢትዮጵዊ አስተሳሰባችንና ስብእናችን አጋላጭ ምልክት ነው፡፡ በዘመነ ፊውዳሊዝም ለተገኘው ለውጥ (ትሩፋቱ በጎም ይሁን ክፉ) መስዋእትነት የከፈሉት ጥቂቶች ናቸው፡፡ በደርግ አብዮታዊ አገዛዝ ዘመንም የታሰሩት፣ ተገድለው የተጣሉት፣ ለትግል የወየኑት፣ የተሰደዱት ጥቂቶች ናቸው፡፡ አሁንም ከዚሁ የተለየ አይደለም፤ ስለህዝባችንና ሀገራችን፣ ስለፖለቲካዊው አስተዳደራችን ያገባናል ብለው በድፍረት መንግስትን የሚሞግቱት ጥቂቶች ናቸው፡፡ በሶስቱም ዘመን በአጋጣሚው ተጠቅመው ሀገራዊና ህዝባዊ ጥቅምን፣ በአንድ እንጀራ አፉን ለሚዘጋ ወስፋታቸው ጩኸትና በቃኝ ለማያውቅ ፍትወተ-ንዋይ ማርኪያ የተጠቀሙበት በርካቶች ናቸው፡፡ አብዛኛው ህዝብ ግን በገዢዎቹ የጭካኔ ድንኳን ውስጥ በፍርሀት ተደቅድቆ ‹‹በአያገባኝም›› እንዳላዘነ አለ፡፡ ይህ ህዝብ ስለልጁ መረሸን አልጠየቀም፤ አላለቀሰም፡፡ በገዢዎቹ የሚጣሉበትን አዋጆች ይቆጥራል እንጂ፣ በአዋጆቹ ስለሚያጣው መብቱ ወይም ስለሚያጎናጽፉት ትሩፋት አይጠይቅም፡፡ ይህ ህዝብ እያጨበጨበ የሚፈጥራቸውን ተሟጋቾቹን (ጀግኖቹን) እራሱን እየነቀነቀ ወደ እስር ቤት፣እያለቀሰ ወደ ቀብር ከመሸኘት በቀር ‹‹ለምን?›› ብሎ አይጠይቅም፡፡ በመሆኑም ተመስገንና ሌሎች ሀሳባቸውን በሰላማዊ መንገድ ሲገልጹ፣ ለእስርና ለስደት የተዳረጉ ዜጎች፣ የዚህ ከዘመን ጋር እየሰለጠነና እየዳበረ የመጣ ጸያፍ ኢትዮጵያዊ ስብእና አሉታዊ ምልክቶች ናቸው፡፡

The post ተመስገን ደሳለኝ ምልክታችን ነው! – ከበድሉ ዋቅጅራ appeared first on Zehabesha Amharic.

(ዜና ፎቶ) ታክሲዋ ባንክ ገባች

$
0
0

lada taxi
(ዘ-ሐበሻ) በኢትዮጵያ በተለይም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚሰሙት የመኪና አደጋዎች እጅጉን እየበዙ መጥተዋል:: በየቀኑ የሚደርሰው የመኪና አደጋም በሰውና በንብረት ላይ እያደረሰ ያለው ጉዳት ተጽፎ የሚያልቅ አይደለም:: ከአዲስ አበባ ወሬዎች ያገኘነው የፎቶ መረጃ እንደሚያመለክተው ዛሬ የካቲት 4 ቀን 2007 ዓ.ም. ከእኩለ ቀን በኋላ መንገዷን ስታ በካዛንቺስ መናኸርያ መንገድ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካዛንቺስ ቅርንጫፍ ጎራ ያለችው ላዳ ታክሲ በዚህ መልኩ ባንክ ገብታለች::

በንብረት ላይ የደረሰው አደጋ የታወቀ ሲሆን በሰዎች ላይ የደረሰው አደጋ በመጣራት ላይ ይገኛል::

The post (ዜና ፎቶ) ታክሲዋ ባንክ ገባች appeared first on Zehabesha Amharic.

(አሳዛኝ ዜና) ሲኖ ትራክ እና ሚኒባስ በመጋጨታቸው በተፈጠረ እሳት የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

$
0
0

ዘ-ሐበሻ በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚከሰቱ አሳዛኝ የመኪና አደጋዎችን ስትዘግብ ቆይታለች:: ዛሬ ያገኘነው ዜና ደግሞ እሽጅግ አሰቃቂ ነው:: በቡራዩ ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋና ተከትሎት በተነሳው የ እሳት ቃጠሎ የ11 ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተዘገበ:: በቡራዩ ከተማ አስተዳደር ወረዳ ሁለት ልዩ ስሙ ቀርሳ በተባለ ስፈራ ትላንት ማምሻውን በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰው ህይወት ሲያልፍ ሁለት ሰው ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል ሲሉ መንግስታዊው ሚዲያዎች ዘግበዋል::
kataelo

እንደ ዘገባዎቹ ከሆነ አደጋው የደረሰው ትላንት ምሽት 1 ሰዓት ከ20 ደቂቃ ላይ ሲሆን፥ ወደ አዲስ አበባ ይመጣ የነበረ ሲኖ ትራክ የጭነት ተሽከርካሪ ከሚኒባስ ጋር በመጋጨቱ ነው አደጋው የደረሰው። በዚህ አደጋ የተነሳም የ11ዱ ሰዎች ሕይወት ማለፍ ምክንያት ሲሆን ሲኖ ትራኩ ላይ የነበሩት ሹፌር እና ረዳት ከአደጋው መትረፍ ቢችሉም በሚኒባሱ ውስጥ የነበሩ ከ11 የሚበልጡ ሰዎች በተነሳው እሳት ተቃጥለው ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ ለመንግስት ሚዲያዎች አስታውቋል::

The post (አሳዛኝ ዜና) ሲኖ ትራክ እና ሚኒባስ በመጋጨታቸው በተፈጠረ እሳት የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግል ጥሪ አስተላለፈ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

10304784_666160690176259_2094795952727390569_nየ9ኙ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብር ‹‹ነጻነት ለፍትሃዊ ምርጫ›› በሚል መርህ የሁለተኛ ዙር የሠላማዊ ትግል ጥሪውን ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች አስተላለፈ፡፡ ትብብሩ የካቲት 15 ቀን 2007 ዓ.ም በተመሳሳይ ሰዓት በ15 ከተሞች ሊያደርገው አቅዶት የነበረውን ሰላማዊ ሰልፍ በሳምንት አራዝሞ ለየካቲት 22 ቀን 2007 ዓ.ም ማስተላለፉንም አስታውቋል፡፡

ትብብሩ ዛሬ የካቲት 10 ቀን 2007 ዓ.ም በሰማያዊ ፓርቲ ጽ/ቤት በሰጣው ጋዜጣዊ መግለጫ እንዳስታወቀው፣ ገዢው ፓርቲ የቱንም ያህል አሰቃቂና አረመኔያዊ የአፈና እርምጃዎች ቢወስድም የህዝብ ጥያቄዎች እስካልተመለሱ ድረስ ህዝባዊ ትግሉን ማዳፈን እንጂ ማስቆም እንደማይችል ይልቁንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ከተለያዩ የህዝብ እንቅስቃሴዎች መገንዘቡን ገልጹዋል፡፡ ትብብሩ ምርጫን በተመለከተ እንዳስታወቀው ኢህአዴግ ስለመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ከቃላት ያለፈ እምነትም ሆነ ቁርጠኝነት የሌለው መሆኑን በዚህ የምርጫ ወቅት በተፎካካሪ ፓርቲዎች ላይ እየወሰደ ያለው ህገ-ወጥ እርምጃ ማሳያ ነው ብሏል፡፡

‹‹ለውጡ የሚመጣባቸው አምባገነኖች ድንገተኛ ከፍተኛ ፍርኃትና ሥጋት በማሳደሩ ህገ-መንግሥቱን በመጨፍለቅ በግልጽና በአደባባይ ህገ-ወጥ ውሳኔዎችንና እርምጃዎችን ለመውሰድ መገደዳቸው፣ ይህም የህዝቡን የለውጥ ፍላጎትና የትግል ተነሳሽነት በማሳደግ ህዝባዊውን ትግል ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገሩ የበለጠ ግልጽ ሆኗል›› ብሏል ትብብሩ፡፡

ትብብሩ አሁን ባለንበት ተጨባጭ ሁኔታ የአገራችንና ዜጓቿ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ በሁለት አማራጮች ላይ የተንጠለጠለ ነው ያለው መግለጫው፣ አንድም ያለውን አምባገነናዊ ሥርዓት ተቀብሎ የጭቆና ቀንበር ተሸክሞ በከፋ ውርደት ሥር ሰጥ- ለጥ ብሎ መገዛት፣ አሊያም አምባገነንነትና ጭቆናን ‹‹በቃ›› በማለት በሕዝባዊ የተቀናጀ ሰላማዊ ትግል ለአገራችን ሉዓላዊነትና የዜግነት ክብራችንን ለማስመለስ በህገ መንግስታዊ መብታችን ተጠቅመን ትግላችንን እስከማይቀረው ለውጥ ድል ደጃፍ ድረስ በቆራጥነት መቀጠል ናቸው ብሏል፡፡

በዚህም ትብብሩ ህገ-መንግስታዊ መብትን በመጠቀም በህግና በሥርዓት ትግሉን ለመምራት መዘጋጀቱን በመግለጽ፣ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች የትግል ጥሪውን እንዲቀላቀሉት አሳስቧል፡፡ ስለሆነም ትብብሩ ‹‹ኢህአዴግነት ከዜግነት በላይ›› ለሆነባቸው የሥራ ዋስትናቸው፣ ዕድገትም ሆነ ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች በሙያቸው፣ በልምዳቸው፣ ክህሎታቸው፣ በመሳሰሉት ባልተመሰረተ መልኩ በደል እየደረሰባቸው ላሉ ሁሉ የትግል ጥሪውን አስተላልፏል፡፡

‹‹የህወኃት/ኢህአዴግ ተራ አባላትና ካድሬዎች፤ የፖለቲካ ልዩነት የተለያየ አመለካከትና ሀሳብ ማራመድ ጤናማ የመድብለ ፓርቲ ፖለቲካ መገለጫ እንጂ እንደሚነገራችሁ ‹‹ጠላትነት›› ባለመሆኑ፣ ትግላችንም ለሠላማዊና ህጋዊ የሥልጣን ሽግግር እንጂ በናንተ ‹‹መቃብር›› ላይ አዲሱን ሥርዓት የማቆም፣ የነበረውን አጥፍቶ ከዜሮ የመጀመርና እናንተን የማጥፋት ዓላማ እንደሌለው ተረድታችሁ፣ ተቃዋሚዎች እንደናንተው ኢትዮጵያዊያንና ለኢትዮጵያና ህዝቧ የሚጨነቁ መሆናቸውን በመረዳት ተቃዋሚዎችን እንደ‹‹ ጠላት›› ከመመልከት አስተሳሰብ ራሳችሁን ነጻ እንድታወጡ›› ሲልም ትብብሩ መልዕክቱን አስተላልፏል፡፡

ወጣቶችና ሴቶች በተለይም የወጣቶችና ሴቶች አደረጃጀቶች፣ መምህራንና ተማሪዎች በተለይም የዩኒቨርስቲና የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች፣ የእምነት ነጻነት መብት ጠያቂ የማኅበረሰብ አባላት፣ የመገናኛ ብዙሃን አባላት፣ የፍትህ አካላት፣ የዴሞክራቲክ ፓርቲዎች አባላት፣ የነጻነትና የዴሞክራሲ ሰላማዊ ታጋዮች፣ በውጪ አገር የሚኖሩ ኢትዮጵዊያን/ዲያስፖራዎች እና ሌሎችም ጥሪው የተላለፈላቸው አካላት መሆናቸውን መግለጫው አትቷል፡፡

በመሆኑም፣ ‹‹በምናርገው አገራዊ፣ ሰላማዊና ሕዝባዊ ትግል በማይቀረው የሥርዓት ለውጥ ለሰላማዊ የሥልጣን ሽግግር በአንድነትና በቆራጥነት እንድትሰለፉ፤ የካቲት 22/07 በየከተሞቹ በቦታውና በሰዓቱ እንድትገኙ ጥሪያችንን አበክረን እናቀርባለን›› ብሏል የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር፡፡

The post የ9ኙ ፓርቲዎች ትብብር የትግል ጥሪ አስተላለፈ appeared first on Zehabesha Amharic.

ፍርድ ቤቱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አቤቱታ ላይ ቀጠሮ ሰጠ

$
0
0

በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር

10403649_666636843461977_4586775875862445773_nየልደታ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት በዘላለም ወርቃገኘው ክስ መዝገብ የተከሰሱት የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ ያቀረቡት አቤቱታ ላይ ውሳኔ ለመስጠት ለየካቲት 25/2007 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጠ፡፡ በዛሬው ችሎት የተከሳሾቹ ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ‹‹ህዳር 12 ለ 13/2007 ዓ.ም አጥቢያ ድንገተኛ ፍተሻ ተደርጎ የተጠርጣሪዎቹ ንብረት ተወስዶባቸዋል፣ የሰብአዊ ጥሰት ተፈጽሞባቸዋል፣ ድንገተኛ ፍተሻው ህገ ወጥ ነው›› በሚል በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት አስተዳደር ላይ ላቀረቡት አቤቱታዎች ማረሚያ ቤቱ የሰጠውን መልስ ሰምቷል፡፡

የማረሚያ ቤቱ መልስ በጽሁፍ ከቀረበ በኋላ በቃልም እንዲቀርብ በታዘዘው መሰረት የቂሊንጦ ማረሚያ ቤት የቀጠሮ ማረፊያ አስተዳደር አስተዳዳሪ ዋና ሱፐር ኢንተንደንት አምባዬ ክቡር ፍተሻው መካሄዱን አምነው ነገር ግን፤ ‹‹ፍተሻው የተከናወነው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ ከጠዋቱ 12 ሰዓት በኋላ ነው፡፡ ፍተሸውም በአቤቱታው ላይ እንደቀረበው ባልታወቁ ሰዎች ሳይሆን በቂሊንጦ ማረሚያ ቤት ጥበቃዎች ነው የተከናወነው›› ሲሉ መልስ ሰጥተዋል፡፡ የፍተሻውን አላማም ‹‹የታራሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ ሲባል የተከለከሉ ነገሮችን ፈትሾ ለማስወገድ ነው፡፡ በፍተሸውም ሚስማር፣ ስለት ነገሮች፣ እንዲሁም ብጥብጥ የሚቀሰቅሱ ጽሁፎች ተገኝተዋል፡፡›› ብለዋል፡፡

ባለፈው የአብዛኛዎቹ ተከሳሾች የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሲደረግ የ7ኛ ተከሳሽ አብርሃም ሰለሞን፣ እንዲሁም 8ኛ ተከሳሽ ሰለሞን ግርማ የተወሰኑ የክስ ማሻሻያዎች እንዲያደርግ ትዕዛዝ ሰጥቶ እንደነበር ይታወቃል፡፡ በዚህ መሰረት በዛሬው ዕለት በሁለቱ ተከሳሾች ላይ አሻሽየዋለሁ ያለውን ክስ አቃቤ ህግ ይዞ ቀርቦ በንባብ አሰምቷል፡፡

በመጨረሻም በፍተሻው ወቅት ተፈጽሟል በሚል በተከሳሾቹ ጠበቃ የቀረበውን አቤቱታና ማረሚያ ቤቱ የሰጠውን መልስ አገናዝቦ ውሳኔ ለመስጠት እንዲሁም፤ በሁለቱ ተከሳሾች ላይ የቀረበው ማሻሻያ ፍርድ ቤቱ በሰጠው ትዕዛዝ መሰረት ‹‹ተሸሽለዋል ወይንም አልተሸሻሉም›› የሚለውን ለመወሰን ለየካቲት 25/2007 ዓ.ም ጠዋት 3 ሰዓት ላይ ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡

The post ፍርድ ቤቱ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች አቤቱታ ላይ ቀጠሮ ሰጠ appeared first on Zehabesha Amharic.

በጆርጂያ አትላንታና አካባቢው ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን –የአድዋ ድል በዓል ጥሪ


የአድዋ ድል በዓል ጥሪ –በሚኒሶታና አካባቢው ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያን ወዳጆች

$
0
0

የኢትዮጵያ ኮምዩኒቲ በሚኒሶታ የአድዋ ድል በዓልን በማስመልከት ልዩ የሆነ ትምህርታዊ ዝግጅት አሰናድቷል:: በመሆኑም በሚኒሶታ እና አካባቢው የምትገኙ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በዝግጅቱ ላይ እንድትታደሙ ተጋብዛችኋል:: ፍላየሩን ይመልከቱ::
adwa Minnesota

The post የአድዋ ድል በዓል ጥሪ – በሚኒሶታና አካባቢው ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ኢትዮጵያን ወዳጆች appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት አስተዳደር ሙስሊሞችን ከየአካባቢው እያደነ ማሰሩን ቀጥሏል

$
0
0

ጋዜጠኛ የሱፍ ጌታቸው በፌስቡክ ገጹ እንዳስታወቀው በርካታ ንፁሃን ወንድሞቻችን ከመዲናችን አዲስ አበባ እየታደኑ ነው።

(ፎቶ ከፋይል)

(ፎቶ ከፋይል)


“ህወሃት መራሹ ወያኔ አሁንም ንፁሃን ሙስሊሞችን ከየአካባቢው ማደነኑን ቀጥሏል።” ሲል ዘገባውን የጀመረው ጋዜጠኛው በዛሬው እለት በብርጭቆ አካባቢ ኮንዶሚኒየም ይኖር የነበረው ወንድማችን የሆነው እና የቢላል ሬዲዬ ጋዜጠኛ የነበረው ፣ ከአመት በፊት በረመዳን ወር መግቢያ ላይ በ3ተኛ ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛ ካሊድ ሙሃመድ በዛሬው እለት የፈጅር ሰላቱን ሰግዶ ወደ ቤቱ በሚመለስበት ወቅት በደህንነት ሀይሎች ታፍኖ እየተደበደበ ወዳልታወቀ ቦታ ተወስዷል ብሏል::

እንደ ጋዜጠኛው ዘገባ ካሊድ መሃመድ ከቤቱ ውስጥም ላፕቶፖችን ጨምሮ በርካታ የሚገለገልባቸውን ንብረቶች ተወስዶበታል:: ካሊድ በአሁኑ ወቅት የ2 ወር ልጅ ያለው ሲሆን በዛሬው እለት የደህነነት ሃይሎች በአራስ ባለቤቱ ላይም ከፍተኛ ድብደባ እንደፈፀሙ ለማወቅ ተችሏል።

The post የሕወሓት አስተዳደር ሙስሊሞችን ከየአካባቢው እያደነ ማሰሩን ቀጥሏል appeared first on Zehabesha Amharic.

የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ

$
0
0

አርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሰላማዊ፣ ተዓማኒና ፍትሀዊ በሆነ ምርጫ የማይፈልጋቸውን መሪዎች መሻር፤ የሚፈልጋቸውን ደግሞ መሾም የሚያስችሉትን መሠረቶች ለመጣል የሚታገል ንቅናቄ ነው። እንደሚታወቀው የሕዝብ እውነተኛ ፍላጎት የሚገለጽበት እውነተኛ ምርጫ እንዲኖር ገለልተኛና ቀልጣፋ የፍትህ ሥርዓት፣ የጦርና የፓሊስ ሠራዊት ሊኖሩ ይገባል። ነፃ የሚዲያ ተቋማትና በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የሲቪክ ማኅበራት መኖርም መታለፍ የሌለባቸው አቢይ ጉዳዮች ናቸው። አማራጭ ፓሊሲዎችን ማቅረብ የሚችሉ በነፃነት የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች ከሌሉም አማራጮች የሉምና ምርጫ ትርጉም የለውም። ይህ ሁሉ ቢሟላ እንኳን ምርጫውን የሚያስፈጽመው አካል ገለልተኛ፣ ሀቀኛና ተዓማኒ ካልሆነ የሚደረገው ምርጫ የመራጩን ሕዝብ ፍላጎት የሚያንፀባርቅ ሊሆን አይችልም።

g 7ከላይ የተዘረዘሩትን የምርጫ እሴቶች ሙሉ በሙሉ ባይሆንም እንኳን የተወሰኑትን በመጠኑም ቢሆን ያካተተ ምርጫ እንዲኖር መጣርና በሂደት የምርጫውን አፈፃፀም ማሻሻል ይቻል ይሆናል በሚል እምነት የዲሞክራሲ ኃይሎች በህወሓት የሴራ ምርጫዎች ሲሳተፉ ቆይተዋል። ሆኖም በህወሓትና በእውነተኛ ምርጫ መካከል  ያለው ተቃርኖ እያደር እየሰፋ ሲሄድ እንጂ ሲጠብ አልታየም።  በህወሓት ሙሉ ቁጥጥር ስር በሚካሄድ ምርጫ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ለውጥ ሊመጣ ይችላል የሚለው እምነት ለአርበኞች ግንቦት 7 ፈጽሞ የተሟጠጠው ከምርጫ 97 ማግስት ጀምሮ  ነው። በግንቦት 7 ቀን 1997 ዓም የኢትዮጵያ ሕዝብ በታላቅ የለውጥ ተስፋ የሰጠው ድምጽ በህወሓት የተዘረፈው ከላይ የተዘረዘሩት ተቋማት ያልነበሩ በመሆናቸው፤ ስለዚህም ከምርጫ በፊት ተቋማቱን መገንባት፤ ተቋማቱን ለመገንባት ደግሞ ህወሓትን ከስልጣን ማስወገድ ይገባል ብሎ በማመኑ ነው አርበኞች ግንቦት 7 በሁለገብ የትግል ስልት በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኘው።

ያም ሆኖ ግን በምርጫ ላይ ያላቸው ተስፋ ፈጽሞ ያልተሟጠጠ ፓርቲዎችን በማክበርና ሥራቸውንም አስቸጋሪ ላለማድረግ ሲባል ከምርጫ 97 ወዲህ የነበሩ ብሄራዊም ሆነ ክልላዊ ምርጫዎችን አስመልክቶ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከምርጫ ዉጭ ያሉ ሌሎች አማራጮችን ብቻ እንዲመለከት አርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ አድርጎ አያውቅም ነበር። አሁን ግን የአገራችን ኢትዮጵያ የፓለቲካ ሁኔታዎች  ይህንን የቆየ አቋም በሚያስቀይር መንገድ፤ የአገራችንን የወደፊት ዕድል ብቻ ሳይሆን ባጠቃላይ ያካባቢውን ሰላም በሚጎዳ መልኩ ተቀይሯል። የሰሞኑ የወያኔ እርምጃዎች ትንሽ ተስፋ ያደርግ የነበረውን የዴሞክራሲ ወገንተኛ ተስፋም እምሽክ አድርጎ በልቶታል:: እየተቃረበ ያለው ዓይነት የፌዝ ምርጫ ወያኔ እንደ እንጄራ የራበውን የተቀባይነት እጦት ለአጭር ጊዜ ያስታግስለት ይሆናል እንጂ የሀገሪቱን እያደር እየተወሳሰበ የመጣ ችግር ለጊዜውም እንኳን የሚያስታግስ አይሆንም፤ ይልቁንም ጊዜው በገፋ ቁጥር ችግሩ መቋጠሪያ የጠፋው እየሆነ ይሄዳል::

የሁኔታውን አሳሳቢነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ለዲሞክራሲ ንቅናቄ አመራር የወቅቱን የአገራችን የፓለቲካ ሁኔታ በጥንቃቄ መርምሮ የሚከተሉት ግንዛቤዎች ላይ ደርሷል።

  1. ህወሓት ብዙዎች እትዮጵያዊያን የተሰውላቸውን አንድነት ፓርቲንና መኢአድን በመበተን የድርጅቶቹን ስምና ንብረት ለአገልጋዮቹ መስጠቱ፤ ከዚህ በፊት ሲያደርግ እንደነበረው የመራጭን ድምጽ መስረቅ ሳይበቃው የምርጫ ተወዳዳሪንም መዝረፍ መጀመሩን አመላካች ነው። ይህ ተግባር ህወሓት የምርጫ ውጤትን ብቻ ሳይሆን ተወዳዳሪዎችንም እሱ ራሱ ለመምረጥ መወሰኑን ያሳያል፤ ከዚህ በተጨማሪ የሴራ ምርጫውን ከጅምሩ ጀምሮ አስቀድሞ እስከተወሰነለት መዳረሻው ድረስ ለምንም ዓይነት ያልተጠበቀ አጋጣሚ (በምርጫው ወቅት የሚደረጉትን ክርክር ተብዬዎች ጨምሮ) እድል ላለመስጠት ወስኖ እየተንቀሳቀሰ መሆኑን በግልጽ ያሳያል፤
  2. ይህ እኩይ ውሳኔ በምርጫ ቦርድ ፊርማና አንደበት ቢነገርም ምንጩ የህወሓት ፓሊት ቢሮ  መሆኑን የሚከተሉት ተግባራት ይጠቁማሉ፤

2.1.         በምርጫ ቦርድ በኩል እንዲገለጽ የተወሰነው እርምጃ ለማስመሰል ያክልም ቢሆን የህጋዊነት ሽፋን እንዲኖረው አለመደረጉ ውሳኔው ፍጹም እብሪተኛ በሆነ አካል መወሰኑን ያመለክታል። እንዲህ                   ዓይነቱ እብሪተኛ አካል ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ነው። ውሳኔውን ለማስፈፀም የነበረው ጥድፊያም ይህንኑ ያጠናክራል።

2.2.        ለማስመሰያ ያክል እንኳን ምንም አይነት የፍርድ ቤት ትዕዛዝ ሳይኖር ፓሊስ የአንድነትና የመኢአድ ቢሮዎችን መውረሩ፤ ህወሓት አንድነትንና መኢአድን አጥፍቶ የድርጅቶቹን ስሞችና ንብረቶች                   ለሚፈልጋቸው ሰዎች ሰጥቶ በአስቸኳይ ለምርጫ ድራማው በፊት መስመር ሊያሰልፋቸው መወሰኑን አመላካች ነው። እንዲህ ዓይነት ከባድ ውሳኔ የሚሰጠው ደግሞ የህወሓት ፓሊት ቢሮ ብቻ                    ነው።

2.3.        ወደ ፈቃድ መንጠቅ ከመደረሱ በፊትም በሰማያዊ ፓርቲ፣ በአንድነትና በመኢአድ አባላት የደረሰው አረመኔያዊ ድብደባ፤ ንቁ የፓለቲካ ተሳትፎ የሚያደርጉ ዜጎች ላይ የሚደርሰው እስር፣ መሰወርና                 እና ባልታወቁ ሰዎች ተገድሎ መገኘት መብዛት እነዚህን አገራዊ ፓርቲዎች የመበተን የፓለቲካ ውሳኔ መሰጠቱን አመላካቾች ናቸው።

  1. ለጊዜው የፈቃድ ነጠቃና የንብረት ዘረፋ የተፈፀመው በአንድነትና በመኢአድ ላይ ቢሆንም በሰማያዊ ፓርቲ ላይ በየእለቱ እየጠነከረ የመጣው የአፈና እርምጃም በተመሳሳይ ፓርቲውን ወደማገድ አለዚያም ፈጽሞ መንቀሳቀስ ወደማይችልበት ደረጃ ሊያደርሰው ይችላል የሚል እምነት አሳድሯል። ሌሎች ፓርቲዎችም ከዚህ ህወሓት ካሰመረው የውሸት ጫወታ መስመር የመውጣት ዝንባሌ ቢያሳዩ ተመሳሳይ እርምጃ አይቀርላቸውም።
  2. የህወሓት የወቅቱ የጥፋት ዒላማ ያነጣጠረው አንፃራዊ በሆነ መንገድ የተሻለ መዋቅርና ማኅበራዊ መሠረት ባላቸው እና በአገራዊ አጀንዳዎቻቸው በሚታወቁ ፓርቲዎች ላይ መሆኑ፤ የወቅቱ የጥፋት ዘመቻ የኢትዮጵያ አንድነትን የማዳከምና ከፋፍሎ የመግዛት የህወሓት ትልቁ አጀንዳ አካል መሆኑን ያሳያል።
  3. እራሱን በዘር ያደራጀዉና ኢትዮጰያ ዉስጥ ያለዉ ፖለቲካዊና ማኅበራዊ አደረጃጀት ከዚሁ እሱ ከተደራጀበት የዘር አደረጃጀት ዉጭ እንዲሆን በፍጹም የማይፈቅደዉ የወያኔ አገዛዝ፤ መጣፊያው ሲያጥረውና ወደ ማይቀረው ውድቀቱ ሲያመራ፤ እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለችው አህያ አገራችን ኢትዮጵያን በቀላሉ ወደማትወጣዉ የዘዉግ ግጭት ዉስጥ አስገብቶ ዘመናት ያስቆጠረዉ አንድነቷ እንዲፈረስ በትጋት እየሠራ መሆኑን ያሳያል።
  4. ከመለስ ዜናዊ ሞት ወዲህ ህወሓት ከሁሉን ጠቅላይ (totalitarian) አገዛዝ ወደ ፋሽስታዊ ቡድንነት ያሽቆለቆለ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ህወሓት ዘረኛ፣ ጠቅላይና ፈላጭ ቆራጭ ጨቌኝ በመሆኑ ፋሽስት ብለነዋል።  ሆኖም በታሪክ የሚታወቁ ፋሺስታዊ አገዛዞች ከፍተኛ ብሄራዊ ስሜት የነበራቸው ሲሆን የህወሓት ፋሽስታዊ አገዛዝ ግን ብሔራው ስሜት አልባ መሆኑ ልዩ እና የበለጠ አደገኛ ያደርገዋል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን የህወሓት መሪዎችንና ጥቂት ሌሎች አጫፋሪዎቻቸውን የያዘ ለጊዜው አስተባባሪ መሪ የሌለው ሆኖም ግን የጦር ሠራዊትን፣ የስለላ መዋቅሩንና ፓሊስን ተቆጣጥሮ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያን እየገዛ ያለው ይህ አስኳል የለሽ ፋሽስታዊ ቡድን መሆኑ እጅግ አሳሳቢ ጉዳይ መሆኑን አርበኞች ግንቦት 7 ተገንዝቧል። ይህ ፋሽስታዊ ቡድን ተደላድሎ መሪ እንዲፈጥር ከተፈቀደለት አገራችንን የከፋ መከራ ውስጥ ሊከታት እንደሚችል ግንዛቤ ተወስዷል።

 

ከላይ በአጭሩ ከተራ ቁጥ 1 እስከ 6 የተዘረዘሩትን በማገናዘብ በግንቦት 2007 ሊደረግ የታቀደውን አምስተኛው ዙር ሀገር አቀፍ የሴራ ምርጫን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ውሳኔዎችን አስተላልፎ ከዚህ የሚከተሉት ጥሪዎችን ለኢትዮጵያ ሕዝብ አቅርቧል።

  1. በምርጫ 2007 መሳተፍ ለዲሞክራሲያዊ ለውጥ ሁኔታዎችን ከማመቻቸት ይልቅ ፋሽስታዊውን ቡድን የሚያጠናክርና የኢትዮጵያን ሕዝብ የወደፊት ዕድል የሚገድል በመሆኑ፣ ለፍትህ፣ ለነፃነት፤ ለዲሞክራሲና ለአገር አንድነት ግድ ያላቸው ወገኖች ሁሉ ከአሁኑ ከዚህ የይስሙላ ምርጫ ዉጭ ዓይኖቻቸውንና ሙሉ ጉልበታቸዉን በሌሎች የኢትዮጵያን ሕዝብ ነፃነት በሚያፋጥኑ አማራጮች ላይ እንዲያሳርፉ ጥሪ ያደርጋል። አርበኞች ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ሕዝብ ከዚህ ዓይን ያወጣ የሴራ ምርጫ ይልቅ መብቱን፤ ነፃነቱንና እኩልነቱን በሚያፋጥኑለት በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመፅ የትግል አመራጮች ላይ እንዲሳትፍ ለመላው ያገሪቱ ሕዝብ ጥሪ ያስተላልፋል።  ህወሓት ማኅበረሰባችንን ለመከፋፈልና ለማባላት የሚያደርገውን እኩይ ሴራ በጋራ እንድናከሽፈው ወገናዊ ጥሪ ያስተላልፋል፤ “አንከፋፈልም፤ ተከፋፍለንም አንጠቃም“ እንበል ይላል::
  2. ህወሓትን ማስወገድ የሚቻለው በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ በመሆኑ፤  ከሁለቱ አንዱንም አለመያዝ ሌላ ሰው ታግሎ ነፃነቴን ያቀዳጀኝ እንደማለት የሚቆጠር በመሆኑ፤ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ በአፋጣኝ ከእነዚህ ሁለት የትግል ዘርፎች ዉስጥ የተሻለ አስተዋጽኦ አበረክታለሁ በሚለው የትግል ዘርፍ ውስጥ ተሳትፎ  እንዲያደርግ ጥሪ ያቀርባል።
  3. አርበኞች ግንቦት 7፣ በሁለቱም የትግል ዘርፎች ድርጅታዊ መዋቅሩን እያሰፋና ከሌሎች ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሕዝባዊ እምቢተኝነትና በሕዝባዊ አመጽ ህወሓትን ከስልጣን ለማስወገድ አቅዶ በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኝ በመሆኑ ኢትዮጵያዊያን በስፋት እንዲቀላቀሉት፤ በኅብረት እንድንቆም እና የህወሓትን ውድቀትና የኢትዮጵያን ትንሳኤ እንድናፋጥን ጥሪ ያደርጋል::
  4. ያለንን አቅም በሙሉ ህወሓትን በማስወገድ ላይ ካዋልነው አንድ ጠንክር ያለ ሕዝባዊ አመጽ አገዛዙን ሊያፍረክርክው የሚችል በመሆኑ፤ በአንድ ወይም በሌላ መንገድ ከምርጫ ጋር ለተያያዙ ሥራዎች ሊውል ታስቦ የነበረው የሰው ኃይል፣ ጊዜ፣ ገንዘብና እውቀት ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀሻነት እንዲውል ጥሪ ያደርጋል።
  5. በውጭ አገራት የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንም በ2007 ምርጫ ላይ ጊዜና ንብረት ከማባከን ይልቅ በአንድ ልብ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሕዝባዊ አብዮት መቀስቀስ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ ያደርጋል።   ከሁሉም ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች የተውጣጣ አካል የዚህን ጥሪ ተፈፃሚነት እንዲከታተል ቢደረግ ይበልጥ ውጤታማ ይሆናል ብሎ ያምናል።

The post የ2007ቱን ሀገራዊ ምርጫ ሂደት እና ከምርጫዉ ዉጭ ያሉ አዋጭ አማራጮችን በተመለከተ የአርበኞች ግንቦት 7: የአንድነትና ዲሞክራሲ ንቅናቄ የአቋም መግለጫ appeared first on Zehabesha Amharic.

“እንኩሃንም ከናንተ ጓሮ በቀልኩ!” –የጐንቻው

ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ

$
0
0

• ‹‹ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

blue partyሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

በየክፍለ ሀገሩ የተሰረዙት ዕጩዎች ‹‹ፓርቲው ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርቷል፣ የሌሎች ፓርቲዎች አባላት ናችሁ›› የመሳሰሉ ምክንያቶችና ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን በአንጻሩ በአዲስ አበባ የተሰረዙት ዕጩዎች ከምርጫ አስፈጻሚዎች ምንም አይነት ምክንያትና ደብዳቤ እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዕጩዎቹ ‹‹የተሰረዝንበትን ምክንያት ንገሩን፣ ደብዳቤ ልትሰጡን ይገባል›› ቢሉም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ‹‹እኛ እናንተን ለመመዝገብ ችግር የለብንም፡፡ ግን ከበላይ አካል እንዳንመዘግብ ተነግሮናል፡፡ ደብዳቤም ልንሰጣችሁ አንችልም፡፡›› የሚል መልስ እንደሰጧው ተግልጾአል፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች መሰረዛቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የቦርዱን ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃናን ለማግኘት ቢጥሩም ‹‹ከከተማ ውጭ ናቸው፡፡ አሁን አታገኟቸውም›› የተባሉ ሲሆን ፕ/ር መርጋ የህወሓትን 40ኛ አመት ለማክበር መቀሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በትናንትናው ዕለት በጉዳዩ ላይ ከቦርዱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፌሳ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን አቶ ነጋ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከማለት ውጭ ዕጩዎቹ ለመሰረዛቸው ተጨባጭ ምክንያት መስጠት እንዳልቻሉ ኢ/ር ይልቃል ገልጸውልናል፡፡

‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ያለ አግባብ የሚሰርዙት ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ ጫና መፍጠር ስለሚችል በሂደቱ እንዲቆ ስለማይፈልጉ ነው›› ያሉት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፤ ሆኖም ይህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለነጻነት የሚያደርጉትን ትግል ትክክለኛ እንደሆነ እንዳስረገጠላቸው፣ ይህን የነጻነት ትግልም አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የካቲት 22 ፓርቲያቸው ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ በ15 ከተሞች የሚያደርገው ሰልፍ የዚሁ የነጻነት ትግል አካል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

The post ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>