Quantcast
Channel: Zehabesha Amharic » News
Viewing all 2784 articles
Browse latest View live

ለቅሶ በራፍ ፍርድ ቤት ( የልጅና የአባት መተያየት) –ለገሰ ወልደሃና

$
0
0

 

zemeneዘመነ ምህረት እና መለሰ መንገሻ ከተያዙ አንድ ወር ከአንድ ቀን ሆናቸው በዛሬው እለት ፍርድ ቤት ይቀርባሉ ተብሎ የመኢአድ አባላት እና ይህ በፎቶ የምታዩት አንድነት ዘመነ ከእናቱ ጋር ከሰሜን ጎንደር ሌሎችም የዘመነ ቤተሰብም ተገኝተዋል ዘመነ የመኢአድን ጠቅላላ ጉባኤ ተካፍሎ ከተመለሰ በኋላ አላገኘነውም አይኑን ለማየት ጉጉተናል የተባለው ሰአት 8:00 ደረሰና ከእሱ ጋር የታሰረው መለሰ መንገሻም አብረው በጋቴና ሌሎች ወደ 25 የሚጠጉ ወጣቶች በፓሊስ ታጅበው ገቡ በእርቀት እጃችን በማወዛወዝ ሰላም አልናቸው እነሱ ባልታሰረው እጃቸው መለሱልን ። በጣም ተጎሳቁለዋል በተለይ መለሰ ግርጥት ብሏል፤ተአምረኛው አንድነት ።

አንድነት የዘመነ የበኩር ልጅ ነው። እድሜውም 3 አመት ከአራት ወር ነው። ሲበዛ ያሳዝናል ። አባቱ ዘመነ፣ ከበርካታ ታሳሪዎች ጋር ወደ ፍርድ ቤት ሲገባ አባቱን ያየው አንድነት፣ ከእጄ አምልጦ ወደ አባቱ ሮጠ። አባቱን ግን አላገኘም። አባቱን ለማቀፍ የሮጠው ልጅ፣ ከፓሊሱ አልፎ አባቱን ሊያቅፍ አልቻለም። ቀድሞም ይህ ህጻን አይኑ እያየ አባቱን እየደበደቡ የወሰዱት ፓሊሶች ነበሩና የማይጋፋው ጉልበተኛ እንደገጠመው አውቋል።

ያችን ቅጽበት ሁሌ የምረሳው አይደለም። አንድነት አራዳን በጩኸት አቀለጣት። ዘመነን ለማየት የጓጓው አይናችን ዘመነን እረሳ። ተሸነፍን። እንባችን ግድቡን ጥሶ ፈሰሰ። አንዳንድ የመኢአድ አባላት በህጻኑ አንድነት ልባቸው ተነክቶ ድምጻቸው ከፍ ብሎ እስኪሰማ አለቀሱ። በግቢው የነበሩ ባለጉዳዮችም ሲያለቅሱ ተመልክቻለሁ ። እንዴት ልብ ይነካል ።

ዘመነ ምን ተሰምቶት ይሆን ? በዚህ ክስተት መሀል ዘመነን ባይኔ ፈለኩት። ሌሎች ያለቅሳሉ ። ዘመነ ግን ከአይኑ የሚፈስ እንባ የለም የሆነውን አይቷል። እንዴት አንጀቱ ቻለው ? ዘመነ ልጁን እንዴት እንደሚወደው አውቃለሁ ። ዛሬ እንዴት ቻለው? ምን አልባት እንባን ያላየሁት ወደ ውስጥ እያለቀሰ ይሆን ?

The post ለቅሶ በራፍ ፍርድ ቤት ( የልጅና የአባት መተያየት) – ለገሰ ወልደሃና appeared first on Zehabesha Amharic.


ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ

$
0
0

• ‹‹ምርጫ ቦርድ ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ እንዲቆይ አይፈልግም›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

Yilkalሰማያዊ ፓርቲ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ በምርጫ ቦርድ ትዕዛዝ እንደተሰረዙበት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ለነገረ ኢትዮጵያ ገለጹ፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ በመላ አገሪቱ በተለይም በደቡብ ወሎ፣ በሰሜን ሸዋ፣ በወላይታ፣ በቤንች ማጅ፣ በምዕ/ጎጃም፣ በሲዳማ፣ በከምባታ፣ በጋሞጎፋ፣ አዲስ አበባ፣ በደቡብ ጎንደርና ጉጅን ጨምሮ በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከ200 በላይ ዕጩዎቹ አንድን ዕጩ ለመሰረዝ የሚያበቃ ምንም አይነት ህጋዊ ምክንያት ሳይኖር ‹‹ከብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በደብዳቤ ታዘናል›› በማለት ለህዝብ ተወካዮች ምክርቤትና ለክልል ምክር ቤቶች ያስመዘገብናቸው ዕጩ ተወዳዳሪዎቹን በመሰረዝ ከምርጫው ውድድር ውጪ እንዲሆኑ እየተደረገ እንደሆነ ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ገልጸዋል፡፡

በየክፍለ ሀገሩ የተሰረዙት ዕጩዎች ‹‹ፓርቲው ትብብር የሚባል ህገ ወጥ አደረጃጀት መስርቷል፣ የሌሎች ፓርቲዎች አባላት ናችሁ›› የመሳሰሉ ምክንያቶችና ደብዳቤ የተሰጣቸው ሲሆን በአንጻሩ በአዲስ አበባ የተሰረዙት ዕጩዎች ከምርጫ አስፈጻሚዎች ምንም አይነት ምክንያትና ደብዳቤ እንዳልተሰጣቸው ለማወቅ ተችሏል፡፡ ዕጩዎቹ ‹‹የተሰረዝንበትን ምክንያት ንገሩን፣ ደብዳቤ ልትሰጡን ይገባል›› ቢሉም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ‹‹እኛ እናንተን ለመመዝገብ ችግር የለብንም፡፡ ግን ከበላይ አካል እንዳንመዘግብ ተነግሮናል፡፡ ደብዳቤም ልንሰጣችሁ አንችልም፡፡›› የሚል መልስ እንደሰጧው ተግልጾአል፡፡

በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች መሰረዛቸውን ተከትሎ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች የቦርዱን ሰብሳቢ ፕ/ር መርጋ በቃናን ለማግኘት ቢጥሩም ‹‹ከከተማ ውጭ ናቸው፡፡ አሁን አታገኟቸውም›› የተባሉ ሲሆን ፕ/ር መርጋ የህወሓትን 40ኛ አመት ለማክበር መቀሌ መሆናቸው ታውቋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል ጌትነት በትናንትናው ዕለት በጉዳዩ ላይ ከቦርዱ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ነጋ ዱፌሳ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን አቶ ነጋ ‹‹ማመልከቻ አስገቡ›› ከማለት ውጭ ዕጩዎቹ ለመሰረዛቸው ተጨባጭ ምክንያት መስጠት እንዳልቻሉ ኢ/ር ይልቃል ገልጸውልናል፡፡

‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ያለ አግባብ የሚሰርዙት ሰማያዊ በምርጫ ሂደቱ ጫና መፍጠር ስለሚችል በሂደቱ እንዲቆ ስለማይፈልጉ ነው›› ያሉት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት፤ ሆኖም ይህ የምርጫ ቦርድ ውሳኔ ለነጻነት የሚያደርጉትን ትግል ትክክለኛ እንደሆነ እንዳስረገጠላቸው፣ ይህን የነጻነት ትግልም አጠናክረው እንደሚቀጥሉና የካቲት 22 ፓርቲያቸው ከትብብሩ ፓርቲዎች ጋር በ15 ከተሞች በተመሳሳይ ጊዜ በ15 ከተሞች የሚያደርገው ሰልፍ የዚሁ የነጻነት ትግል አካል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

The post ምርጫ ቦርድ ከ200 በላይ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎችን ሰረዘ appeared first on Zehabesha Amharic.

በምእራብ ኢትዮጵያ ቶንጎ አካባቢ ሌሊቱን ውጊያ ሲደረግ ማደሩ ተሰማ

$
0
0

(ምኒልክ ሳልሳዊ) በምእራብ ኢትዮጵያ በቤንሻንጉል ክልል ደቡባዊ አቅጣጫ ቶንጎ ተብሎ በሚጠራው አከባቢ በታጣቂ ሃይሎች እና በወያኔ ወታደሮች መካከል ለሊቱን ከባድ ውጊያ መደረጉን ለታጣቂ ሃይሎቹ ቅርብ ነን ያሉ ምንጮች ከማላካል አስታውቀዋል::
news
ከደቡብ ሱዳን ማላካል ተብሎ ከሚጠራው አከባቢ ተነስተው በምእራብ የኢትዮጵያ ድንበር ከሚገኙት የወያኔ ሰራዊት ጋር ውጊያ የገጠሙት ታጣቂ ሃይሎች በስርአቱ በደል ደርሶባቸው የሸፈቱ እንደሆነ ምንጮቹ ሲገልጹ ለሊቱን ከባድ ውጊያ ያካሄዱ ሲሆን ከታጣቂ ሃይሎቹ 26 ሰውች መሰዋቱን ምንጮቹ ተናግረዋል::

በጋምቤላ እና ቤንሻንጉል ጉምዝ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በስርአቱ ከባድ በደል እየደረሰባቸው ሲሆን ምንም አይነት የልማት መዋቅር ካለመዘርጋቱም በላይ ከየአከባቢያቸው እየተፈናቀሉ መሬታቸው ለውጪ ባለሃብት እንዲሁም ከትግራይ መጥተው ለሰፈሩ አልሚዎች ለተባሉ የትግራይ ተወላጆች እየተሰጣብቸው ለስደት ለስራ አጥነት እና ለድህነት ተዳርገዋል::እነዚህ የስርአቱ በደል አንገሽግሿቸው ደቡብ ሱዳን ጫካ በመግባት ራሳቸውን ያደራጁ ታጣቂ ሃይሎች የወያኔን ወታደሮች መዋጋታቸውን እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል::

የኢትዮጵያ ሕዝቦች ለነጻነቱ እና ለመብቱ በሚያደርገው ትግል በአንድነት መነሳት አለበት አለበት ያሉት ምንጮቹ ራሳችንን ከበደል እና ከብዝበዛ ለማዳን ጠንክረን ልንታገል ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጥተዋል::

The post በምእራብ ኢትዮጵያ ቶንጎ አካባቢ ሌሊቱን ውጊያ ሲደረግ ማደሩ ተሰማ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአሜሪካ የሶስት ሙስሊም ተማሪዎች መገደልና ከበስተጀርባዉ ያለዉ መንስኤ ሲቃኝ –ወቅታዊ ጥንቅር በሳዲቅ አህመድ (በድምጽ)

$
0
0

በአሜሪካ የሶስት ሙስሊም ተማሪዎች መገደልና ከበስተጀርባዉ ያለዉ ያለዉን መንስኤ ሲቃኝ
ወቅታዊ እና ጥናታዊ ፕሮግራም በሳዲቅ አህመድ
[jwplayer mediaid=”39159″]

(ሳዲቅ አህመድ)

(ሳዲቅ አህመድ)

The post በአሜሪካ የሶስት ሙስሊም ተማሪዎች መገደልና ከበስተጀርባዉ ያለዉ መንስኤ ሲቃኝ – ወቅታዊ ጥንቅር በሳዲቅ አህመድ (በድምጽ) appeared first on Zehabesha Amharic.

በቬጋስ የህብር ሬዲዮን 5ተኛ ዓመት ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባጎልድኮስት ሆቴል እንዲካሔድ ባለመፈቀዱ ወደ ሐምተን ኢን ሆቴል እንዲዛዋወር ተደረገ

$
0
0

unnamed (1)ዛሬ ከላስቬጋስ አልፎ በመላው አለም ተደማጭ የሆነው የህብር ሬዲዮ፤ 5ተኛ ዓመቱን ምክንያት በማድረግ በመጭው ረቡዕ ፊብርዋሪ 25ቀን2015 በቬጋስ ጎልድ ኮስት ሆቴል ያቀደውን ታላቅ ስብሰባ ሆቴሉ  ረቡዕ ማካሄድ አይቻልም ብሎ በመሰረዙ፤ በዚያው በቬጋስ ወደሚገኘውሐምፕተን ኢን ሆቴል በዕለቱ በተመሳሳይ ሰዓት እንደሚያካሂድ የህብር ሬዲዮ ዝግጅት ክፍል ለዘ-ሐበሻ በላከው መግለጫ ገለፀ።

የአድዋ ድል 119 ዓመት በሚዘከርበት፣ ወቅታዊ የአገር እና የጤና ጉዳይ ዋና መወያያ በሆነበት፣ በዚህ ታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ ላይ አቶ ኦባንግሜቶ ከካናዳ፣ የዘ-ሐበሻ ድህረ ገፅና ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ሄኖክ አለማየሁ ከሚኒሶታ፣ እውቁ ዩሮሎጂስት / ሙሉጌታ ካሳሁን ከቬጋስበሚገኙበት፤ አቶ ኪዳኔ አለማየሁ የዓለም አቀፍ ፍትህ የኢትዮጵያውያን ጉዳይ ዋና ስራ አስኪያጅ የሚሳተፉበትን ይህን ስብሰባ ሐሙስ እንጂረቡዕ ሊካሄድ አይችልም ሲል አስቀድሞ የተገባውን ውለታ አፍርሶ ዝግጅቱን ሰርዟል።በዚህ ከአቅማችን በላይ በሆነ ምክንያት የስብሰባውንቦታ በዕለቱ በሐምተን ኢን ሆቴል ለማድረግ ተገደናል።

ጎልድ ኮስት ሆቴል ባለፈው ሳምንት ሐሙስ ፌብርዋሪ 12/ 2015 በላከው የስልክ መልእክት የህብርን 5ተኛ ዓመት ዝግጅት የሰረዘ መሆኑንአሳውቀውናል። ከዚያ በኋላ በተደረገው ውይይት ረቡዕ ስብሰባው አለመደረጉ በህብር ላይ ጉዳት ያደርሳል ብለን ገልጸናል። በዚህ ሳቢያዝግጅቱን በመጭው ዕረቡ በቬጋስ ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘው ሐምፕተን ኢን ሆቴል የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንደሚካሄድ የህብርዝግጅት ክፍል ገልጿል።

የህብር ሬዲዮ 5ተኛ ዓመት በዋነኛነት የሚመጡ እንግዶች ባሉበት  ስብሰባውን በተሳካ መንገድ ማድረግ ነው የወቅቱ ትኩረታችን የሚለውየህብር ሬዲዮ መግለጫ ባለፈው ዓመት በጎልድ ኮስት ሆቴል 4ተኛ ዓመታችንን ፌብርዋሪ 26/2014 በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን አስታውሷል።

ህብር ሬዲዮ የወቅታዊ መረጃ ምንጭ በመሆን በወቅታዊ አገራዊ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ፣በኢኮኖሚ፣ በጤና እና በተለያዩ ማህበራዊ ችግሮች ላይሰፊ ትኩረት በመስጠት አቅም በቻለው መጠን የአማራጭ የሚዲያ ተግባሩን እያከናወነ መቆየቱን ይሔው መግለጫ ጠቅሶ /ሰቡ በቬጋስናበአካባቢው የሚኖሩ የኢትዮጵያ ወዳጆች በመጭው ረቡዕ ፌብርዋሪ 25 ቀን 2015 5 ፒኤም ትሮፒካናና ዲን ማርቲን ላይ በሚገኘውየሀምፕተን ኢን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ታላቅ ስብሰባ ላይ በመገኘት የተሳካ ዝግጅት እንዲደረግ  የህብር ሬዲዮ አጋር እንዲሆኑ መግለጫውጥሪውን አስተላልፏል።                              

The post በቬጋስ የህብር ሬዲዮን 5ተኛ ዓመት ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባጎልድኮስት ሆቴል እንዲካሔድ ባለመፈቀዱ ወደ ሐምተን ኢን ሆቴል እንዲዛዋወር ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

አረና ትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ያስመዘገባቸው እጩዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው ለማግለል እየተገደዱ መሆኑን አስታወቀ።

$
0
0

0,,1589020_4,00አረና ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ከ100 በላይ እጩዎቹ ቢመዘገቡም በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በርካቶች ከውድድር መውጣታቸውን ፓርቲው አመልክቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ሳይቀሩ ካርድ የለም ተብለው እንዲመለሱ መደረጉን የፓርቲው የሕዝብ ግኑኙነት ለዶቼቬለ ተናግረዋል።

አረና ትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ያስመዘገባቸው እጩዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው ለማግለል እየተገደዱ መሆኑን አስታወቀ። አረና ለፌደራል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ለክልል ከ100 በላይ እጩዎቹ ቢመዘገቡም በተለያዩ አካባቢዎች በደረሰባቸው ጫና ምክንያት በርካቶች ከውድድር መውጣታቸውን ፓርቲው አመልክቷል። የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ገብሩ አስራት ሳይቀሩ ካርድ የለም ተብለው እንዲመለሱ መደረጉን የፓርቲው የሕዝብ ግኑኙነት ለዶቼቬለ ተናግረዋል። የክልሉ የምርጫ ቦርድ ሃላፊ ግን የአረናን አቤቱታ መሠረተ ቢስ ሲሉ አጣጥለዋል። ዝርዝሩን ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሄር አዘጋጅቶታል ።

 
Source- m.dw.de/amharic/

The post አረና ትግራይ ኢትዮጵያ ውስጥ በመጪው ግንቦት ለሚካሄደው ምርጫ ያስመዘገባቸው እጩዎቹ ራሳቸውን ከምርጫው ለማግለል እየተገደዱ መሆኑን አስታወቀ። appeared first on Zehabesha Amharic.

የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ አብርሃን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና )

$
0
0

‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፣ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡
እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ››

ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ

ከዛሬ ከሰዓት በኋላ ከወዳጄ አቤል አለማየሁ ጋር ወደ ቂሊንጦ እስር ቤት አምርተን ነበር፡፡ አካሄዳችን በዞን ሁለት የሚገኙትን አብርሃ ደስታን፣ ጦማሪ እና ጋዜጠኛ በፍቃዱ ኃይሉንና ጦማሪ አጥናፍ ብርሃንን ለመጠየቅ ነው፡፡

የቃሊቲ እና የቂሊንጦ ጸሐይ ከረር ያለች ብትሆንም በቦታው ደርሰን ወደፖሊሶች ለምዝገባ ተጠጋን፡፡ ጠያቂና ተጠያቂ መዝጋቢ የሆነችው ሴት ፖሊስ ‹‹ማንን ነው የምትጠይቀው?›› ብላ አቤልን ጠየቀችው፡፡ በፍቃዱን እና አጥናፍን መሆንኑ ነገራት፡፡ መዘገበችውና ሂድ አለችው፡፡ ‹‹አንተስ ማንን ነው?›› ስትል ጠየቀችኝ፤ ‹‹አብርሃ ደስታን›› አልኳት፡፡ ቀና ብላ አየችኝና ‹‹ቆይ፣ ቁጭ በል›› የሚል መልስ መለሰች፡፡ ሌሎች ሰዎችን መመዝገቧን ቀጠለች፡፡ ‹‹ሰዓት እየሄደ ነው፣ ችግር አለ ወይ?›› አልኳት፡፡ ‹‹አይ ችግር የለም›› ካለች ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ ሌላ መዝገብ አምጥታ ፓስፖርቴን መዘገበችው፡፡ (መታወቂያዬ አልታደሰም) ከመዘገበች በኋላም ሌላ የፎርም መሙያ አውጥጣ በድጋሚ መዘገበች፡፡ ይሄንን ስትመዘግብ እኔ እንዳይባት ስላልፈለገች ስትደብቀው አስተውያታለሁ፡፡ …ከሌላ ወንድ ፖሊስ ጋር ከተነጋገረች በኋላ ግባ አለችኝ፡፡

የጸሐይ መነጽር ማውለቅ ግድ ነበር፡፡ ያው ፍተሻውን አልፌ ወደዞን ሁለት አመራሁ፡፡ ከኋላዬ አንድ ሲቪል የለበሰ ወንድ በቅርብ ርቀት እየተከተለኝ ነበር፡፡ አብርሃን አስጠራሁት፡፡ ከኋላዬ የሚከተለኝ ሰው ከጎኔ ሆኖ ሌሎች ጠያቂዎችን ለመጠየቅ ማስመሰል ሞከረ፡፡ በውስጤ ፈገግ መጣ፡፡

አስተናባሪዎቹ ‹‹አብርሃ እዚህ የለም፤ የዞን ሁለት መጠየቂያ ተቀይሯል›› አሉኝ፡፡ በእርግጥም ዞን አንድ ታስሬ በነበረበት ጊዜ የማውቃቸውን እስረኞች ተመለከትኳቸውና ሰላም ተባባልን፡፡ ልወጣ ስል ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በርቀት አይቶኝ ሰላም አለኝ፡፡ በደስታ ሰላም አልኩት፡፡ ነገር ግን ተመልሼ በእጄ ሰላም እንዳልለው ያ ከጀርባዬ ያለ ሰው ነበር፡፡ ከዚህ ቀደምም ‹‹አቡበከርን ለምን ጠየከው?›› ተብዬ የተፈጠረውን ግርግር አስታወስኩኝ፡፡ አብበከርም ይሄ ስለገባው በርቀት ሰላም ብሎኝ በእጁ ሂድ አለኝ፡፡

የዞን አንድ መጠየቂያ ለዞን ሁለት ታሳሪዎች፤ የዞን ሁለት ደግሞ ለዞን አንድ ታሳሪዎች መጠየቂያ ሆኗል፡፡ አቤል በፍቄንና አጥናፍን አስጠርቷል፡፡ እኔም አብርሃን አስጠራሁ፡፡ በፍቄና አጥናፍ ወዲያው መጡ፡፡
ያ ከጀርባዬ የነበረ ሲቪል ኮፍያ ለባሽ ከጎኔ ቆሟል፡፡ ለአጥነፍ ‹‹በቃ እናንተ ከአቤል ጋር አውሩ፡፡ እኔ አብርሃን ስላጠራሁ ልጠብቀው፡፡ ከአንድ ሰው በላይ መጠየቅ አይቻልም ብለዋል›› አልኩት፡፡ አጥናፍ ከዚህ ቀደም የደረሰብኝን አስታውሶ ‹‹አብርሃ አሁን ጠበቃ ተማንን ሊያገኝ ሄዷል፤ ከጎንህ የቆመው የግቢው ደህንነት ነው፡፡ ይሄን ንገረውና እስከዚያው ከእኛ ጋር ሁን›› አለኝ፡፡ ያን ሰውዬ ትከሻውን ስነካው ደንገጥ ብሎ ዞር አለ፡፡ ስለሁኔታው ነገርኩት፡፡ ‹‹እሱ (አብርሃ) እስኪመጣ ብቻህን ተቀምጠህ ጠብቅ›› አለኝ፡፡ ‹‹እስኪዚያ እነሱን ላናግራቸው›› አልኩት፡፡ ‹‹ብቻህን ብትቀመጥ ይሻልሃል አለኝ›› ተናድጄ ወደውጪ ወጥቼ ሌሎች ፖሊሶችን ስለሁኔታው አስረዳኋቸው፡፡ ኃላፊነት የሚወስድ ጠፋ፡፡ በመጨረሻም አንዱ ፖሊስ ‹‹እሱ አስኪመጣ ውስጥ ጠብቀው›› የሚል ምላሽ ሰጠኝ፡፡ የመጣው ይምጣ በሚል ገብቼ ከበፍቄ ጋር ማውራት ጀመርኩ፡፡

‹‹በፍቄ እንኳን ተወለድክ›› አልኩት፡፡ አሜን ካለኝ በኋላ ‹‹ዕድሜያችንን መቼ ሰራንበት፡፡ ልደት አክብሬ አላውቅም፡፡ ልደት ማክበርም ያስፈራኛል፡፡ ግን እንኳን ተወለድክ ላላችሁኝ በሙሉ ከልብ አመሰግናለሁ›› ሲል እየሳቀ መለሰልኝ፡፡

አቤል እና አጥናፍ ጋር የጦፈ ጨዋታ ይዘዋል፡፡ እኔም ከበፍቄ ጋር ባለችን አጭር ደቂቃ ስለሀገር ጉዳይ፣ ስለዘንድሮ ምርጫ፣ ስለአልጀዚራ ዘስትሪም የሰሞኑ ዘገባ፣ ስለ ክሳቸው እና እስራቸው ጉዳይ፣ ስለእኔ የክስ ሁኔታ፣ በአንድነት ፓርቲ ስለደረሰው ሁነትና አደጋ …በጥቂቱ አወጋን፡፡የመለያያ ደወል ተደወለ፡፡ አብርሃም ሳይመጣ ቀረ፡፡ ያው፣ ቻው ብሎ መለያየት ግድ ነበርና ተለያየን!!!

The post የዛሬ የቂሊንጦ አጭር ቆይታ አብርሃን መጠየቅ ከጀርባ ሰው ያስከትላል (ከኤልያስ ገብሩ ጎዳና ) appeared first on Zehabesha Amharic.

ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችለው ሰማያዊ ብቻ መሆኑ ተረጋገጠ

$
0
0

ነገረ ኢትዮጵያ

መድረክ 218 ኢዴፓ 127 መቀመጫዎች ብቻ ነው ያሰመዘገቡት

ethiopia-blue-party-300x164የምዝገባ ጊዜ ሳይጀምር፣ የአንድነት ፓርቲ ከሶማሌ ክልል በስተቀር በሁሉም የአገሪቷ ክፍሎች ለፓርላማና ለክልል ምክር ቤቶች ተወዳዳሪዎች አዘጋጅቶ እንደነበረ ይታወቃል። የአንድነት ጥንካሬ ከወዲሁ የተረዳሁ የሕወሃት ፖሊት ቢሮ ለምርጫ ቢርድ መመሪያ በመስጠት፣ ተለጣፊ ቡድን በማደራጀት አንድነት ላይ የኃይል እርምጃ ወስዷል።

የአንድነት አባላታ ለድርጅት ሳይሆን ለነጻነት የሚታገሉ እንደመሆናቸው ማሊያ ቀይረው በሰማያዊ ፓርቲ ሥር ለመንቀሳቀስ ተነሱ። የሰማያዊውች እና የአንድነቶች መያያዝ ትግሉን የበለጠ አጠናከረው። ሳምንታ ባልሞላ ጊዜ ዉስጥ አንድነቶ ተነቃነቁ። ወደ ሰማያዎ ጎረፉ። በፊትም ጠንካራ የሆነው የሰማያዊ ፓርቲ አንድነቶች ሲመጡ የበለጠ ተጠናክሮ ከአራት በላይ ለፓርላማ፣ ከሰባት መቶ በላይ ለክልልተወዳዳሪዎች አስመዘገበ። ከሁለት መቶ በላይ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎች በምርጫ ቦርድ የሌላ ፓርቲ አባል ናችሁ በሚል ተሰረዙ።

እንደዚያም ሆኖ ከኢሕአዴግ ቀጥሎ ብዙ ተወዳዳሪዎችን ሰማያዊ ፓርቲ እንዳሰለፈ ለማወቅ ተችሏል። ኢሕአዴግ ከ547 የፓርላማ መቀመጫዎች 457 ላይ ተወዳዳሪዎች ያስመዘገበ ሲሆን፣ ሰማያዊ የተሰረዙትን ሳይጨመር ለፓርላማ 345 (63%) ተወዳዳሪዎችን አስመዝግቧል። ኢሕአዴግ የሚወዳደረው በትግራይ፣ ደቡብ፣ አማራና ኦሮሚያ ክልልም በአዲስ አበባ ብቻ ነው። በአፋር፣ ሶማሌ፣ ቤኔሻንጉልና ጋምቤላ የሚወዳደሩ ኢሕአዴግ አጋር ድርጅቶች የሚላቸው ናቸው።፡

የብዙ ድርጅቶች ስብስብ የሆነ መድረክ 218 ( 39%) መቀመጫ ብቻ ሲሆን ለፓርላማ ያሰለፈው በትግራይ ከ38 መቀመጫዎች ከሰላሳ በላይ፣ በኦሮሚያ ከ175 መቀመጫዎች በ160ው ተወዳዳሪዎችን አሰልፏል። በደቡም ክልል ወደ ሃያ ብቻ የሚሆኑ ተወዳዳሪዎችን ያሰለፈ ሲሆን በአማራዉ ፣ በጋምቤላ፣ በአፋር፣ በቤኔሻንጉልና በሶማሌ ክልል ምንም ተወዳዳሪዎችን አላስመዘገበም።
ከመድረክ ቀጥሎ ብዙ ቁጥር ያስመዘገበው ኢዴፓ ሲሆንም ፣ ለ127 መቀመጫዎች (23%) ተወዳዳሪዎችን አስመዝግቧል።

በዚህ መሰረት ገዢው ፓርቲ ድምጽ መስረቁ አይቀርም እንጂ፣ ካሰመዘገባቸው 345 የፓርላማ አባላት 274 ቱን ( 80% ) ማሸነፍ ከቻለ ስልጠና የመያዝ እድል ይኖረዋል። እንድ እመድረክ፣ ኢዴፓና ሌሎች ያሰለፏቸውን በሙሉ መቶ በመቶ ቢያሸንፉም ስልጣን መያዝ አይችሉም።

The post ተወዳድሮ ማሸነፍ የሚችለው ሰማያዊ ብቻ መሆኑ ተረጋገጠ appeared first on Zehabesha Amharic.


የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ

$
0
0

• ‹‹ምርጫ በህዝብ ፍላጎት ሳይሆን በሎተሪ ሆኗል›› ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

አዲስ አበባ ከተማ ወረዳ 5 ለመጭው ምርጫ ለተወካዮች ምክር ቤት ሰማያዊ ፓርቲን ወክለው ሊቀርቡ የነበሩት የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ከቀረቡት 17 ዕጩዎች መካከል በተጣለ ዕጣ ወድቀዋል›› በመባላቸው ለመጭው ምርጫ በዕጩነት እንዳይቀርቡ መደረጋቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ኢ/ር ይልቃል በዕጩነት በቀረቡበት ወረዳ 5 የምርጫ ጣቢያ ኢህአዴግ፣ የትግስቱ አንድነት፣ ቅንጅትን ጨምሮ ሌሎች ስድስት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ያለ ምንም ዕጣ አልፈዋል የተባለ ሲሆን ‹‹የሚያልፉት በዕጣ ነው›› የተባሉት ሰማያዊን ጨምሮ 11 የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች መካከል ሰማያዊና ሌሎች አራት የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ‹‹ዕጣ አልወጣላቸውም፡፡›› ተብሏል፡፡
Hiber Radio Interview with Eng Yilkal Getnet
ስለ ጉዳዩ ያነጋገርናቸው የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹ሰማያዊ ህዝብ ውስጥ በሰፊው እየገባና እያንቀሳቀሰ ያለ ግንባር ቀደም ፓርቲ ነው፡፡ እንደ ኢህአዴግ ያሉን ጨምሮ ዕጣ ውስጥ አይገቡም፡፡ ሰማያዊ ደግሞ ይህ ነው የሚባል እንቅስቃሴ ከማያደርጉት ፓርቲዎች ጋር ዕጣ ውስጥ ገብቶ ወደቀ መባሉ ዴሞክራሲ ከጅምሩ ጀምሮ የህዝብ ድምጽ ሆኖ እያለ በእኛ አገር ሎተሪ ሆኗል ማለት ነው፡፡›› ብለዋል::

ሊቀመንበሩ አክለውም ‹‹ሂደቱ ምንም ይሁን ምን አንድን ፓርቲ ወይንም ተወካይን ህዝብ ነው መምረጥ ያለበት፡፡ ህዝብ የሚፈልገውና የሚመረጥ ፓርቲ ነው ለምርጫ መቅረብ ያለበት፡፡ አሁን ግን እየተባለ ያለው በአንድ በኩል ህዝብ የማይፈልገው ያለ ዕጣ ሲገባ፣ በሌላ በኩል ህዝብ የሚፈልገው ሰማያዊን የመሰለ ፓርቲ ዕጣ ውስጥ ገብቶ አላለፈም እየተባለ ነው፡፡ በአንድ በኩል ህዝብ የተማረረባቸው ያለ ቅድመ ሁኔታ ህዝብን እንደሚያንቀሳቅስ የሚታወቀው ሰማያዊ ደግሞ ህዝብ ስፈለገው አሊያም በጥንካሬው ሳይሆን በሎተሪ ወድቀሃል ተብሏል›› ሂደቱ የተሳሳተ ነው ሲሉ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

The post የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት በዕጩነት እንዳይቀርቡ ተደረገ appeared first on Zehabesha Amharic.

በስልጢ ለሳምንት የዘለቀው ቃጠሎ በደን ላይ ውድመት አደረሰ

$
0
0

አዲስ አድማስ ጋዜጣ እንደዘገበው
በደቡብ ክልል ስልጢ ዞን ስልጢ ወረዳ ውስጥ በተፈጥሮ ደን ላይ የእሳት ቃጠሎ ውድመት እየደረሰ መሆኑን ምንጮቻችን የጠቆሙ ሲሆን የወረዳው ግብርና ላይ በበኩሉ እሣቱ በቁጥጥር ስር መዋሉን ጠቅሶ የአደጋው መንስኤ በፖሊስ እየተጣራ ነው ብሏል፡፡
news
ከሳምንት በፊት የጀመረው የእሳት ቃጠሎ እስካለፈው ሐሙስ ድረስ አለመቆሙን የተናገሩት ምንጮች፤ ከወረዳው ዋና ከተማ ቂቢት በስተምዕራብ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በዘቢዳር ሰንሰለታማ ተራራ ላይ የሚገኘው ይሄው ደን፤ በአራት አቅጣጫዎች በእሳት እየወደመ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

እስካሁን እሳቱን ለማጥፋት ከአካባቢው መስተዳድር የተደረገ ጥረት አለመኖሩን የጠቆሙት ምንጮቻችን፤ በግምት ከ20 ሄክታር በላይ ደን ሳይቃጠል እንደማይቀር ተናግረዋል፡፡ ወሌ 26 እና ቦሌ በሚባሉ ቀበሌዎች ውስጥ የሚገኘው ደኑ፣ የአካባቢው የተፈጥሮ ሃብት መሆኑን የጠቀሱት ምንጮች፤ ከዚህ በፊትም በተደጋጋሚ ቃጠሎ እንደደረሰበትና ግለሰቦች ለማገዶ ፍጆታ ሲሉ እሳት ለቀውበት ሊሆን እንደሚችል ግምታቸውን ገልፀዋል፡፡

የወረዳው የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ መሃመድ ከድር ስለጉዳዩ ተጠይቀው ሲመልሱ፤ ከግብርና ቢሮና ከፖሊስ የተውጣጣ ግብረ ሃይል መሰማራቱንና እሳቱን በትናንትናው እለት መቆጣጠር መቻሉን ጠቅሰው ቃጠሎው በሰውና በንብረት ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖረውም በደኑ ላይ ያደረሰው ውድመት መጠን እንዲሁም ፖሊስ የእሳቱን መንስኤ ፖሊስ እየመረመረ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

The post በስልጢ ለሳምንት የዘለቀው ቃጠሎ በደን ላይ ውድመት አደረሰ appeared first on Zehabesha Amharic.

“ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ –ኤ”–ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ)

$
0
0

8100 A ethiopia
ወቅታዊው የቴሌቭዥናችን አዝማች፤
.. ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ- ኤ ብለሽ መላዕክት ከላልሽ፣
አባይን ገድበሽ ሽልማት በሽበሽ። …. 8100 …. 8100 …. 8100-A A A

የምትለው ዜማ በብዛት ትለቀቃለች። ኮሜዲያን ተሰብሰበው የሰሩዋት ዜማ ናት። ቀልደኞቹን ማኖ ለማስነካት ተብላ የተቀነባባረች ነገር ናት የሚሉም አሉ። የቴሌቭዥኑን ጣብያ ከፍቶ የሚመለከተው ሰው እጅግ ጥቂት ቢሆንም መልእክቱ በማህበራዊ ድረ-ገጾች መደመጡ አልቀረም። የዚህ ማስታወቅያ አላማ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የእጣው ዝርዝር ግን ለብዙዎች እንግዳ ሳይሆን አልቀረም።

አንዲት አዛውንት የልጃቸውን ተንቀሳቃሽ ስልክ እያነሱ ይቀጠቅጣሉ። በሳምንት ሶስቴ 8100 እየደወሉ ‘A’ ፊደልን ይጫናሉ። ከብዙ ግዜ በኋላ ታዲያ ልጃቸው አወቀባቸው። በመገረምም ለምን ይህንን ሁሉ ግዜ መደወል እንደፈለጉ ጠየቃቸው። እናት መለሱ “ሁሉም ነገር አለኝ። ዲግሪ ግን የለኝም። በዚህ እድሜየም በአቋራጭ ካልሆነ ላገኘው አልችልም።” ሲሉ የማስትሬት ዲግሪው እጣ እንዳጓጓቸው ነገሩት።

ሶስት ብር ከፍሎ ‘8100-A’ አጭር መልዕክት የላከ ሰው ሁሉ እጣ ይወጣለታል። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ እድሉ የቀናው ሰው የመኖርያ ቤት፣ መኪና፣… እንዲሁም ዶክትሬትና ማስትሬት ዲግሪ ይደርሰዋል።

ማስትሬት እና ዶክትሬት ዲግሪ በእጣ እንዴት ነው ለህዝብ ሊቀርብ የሚችለው? መሰረታዊ ትምህርት የሌለው አንድ አርሶ-አደር አልያም አንዲት የቤት እመቤት የዶክትሬት ዲግሪ እጣ ቢደርሳቸው ዩኒቨርሲቲ ገብተው ዲግሪያቸውን ሊጭኑ ነው? ብቻ ምን ችግር አለ? ለመዕተ-ዓመቱ እቅድ ማሟያ ተብለው የተሰሩት ፴ ዩኒቨርሲቲዎች አሉ። ምሁራንን ሳይሆን ‘ድንጋይ ማምረቻ’ እየተባሉ የሚተቹ ዩኒቨርሲቲዎች። የኮሌጅን መስፈርት በአምስት በመቶ እንኳን የማያሟሉ ባዶ ህንጻዎች። ከነዚህ ኮሌጆች እየተመረቁ የሚወጡት ተማሪዋች ስማቸውን እንኳን በቅጡ መጻፍ አይችሉም የሚባሉበት ኮሌጆች።

ለነገሩ በስልጣን ላይ ያሉትም ሁሉ ዛሬ የማስትሬት እና የዶክትሬት ዲግሪ ባለቤቶች ሆነዋል። ሴንቸሪ ዩኒቨርሲቲ ምስጋና ይግባውና እነ አባዱላ ገመዳም ማስትሬት ዲግሪ ገዝተዋል። ጀነራል ባጫ ደበሌም ሁለት ዲግሪ ጭነዋል።

ያልተጠና እና ግብታዊ በመሆኑ ይመስላል የ 8100-A ዘመቻ መቀለጃ እየሆነ መምጣቱ። ኢሳያስ አፈወርቂም የዚህ እጣ እድል ደርሷቸዋል አሉ። ባለፈው ሰሞን የኢትዮጵያ አየር ሃይል ባልደረባ የነበረው ካፒቴን የህወሃትን ስርዓት በመቃወም ይዞት የጠፋውን ሚግ 23 አውሮፕላን ለአስመራው መንግስት እንዳስረከበ ነበር ይህ ቀልድ የተነገረው።
የዚህ ጽሁፍ ዋናው ጉዳይ የትምህርት ማሽቆልቆል ነገር አይደለም። የ 8100-A ዜማ እንዳበቃ ባናቱ ላይ የሚነገር አንድ መልእክት ላይ እንጂ። የሰማንያ አንድ ዜሮ-ዜሮ ቁልፍ በእዚህ መልእክት ላይ ይገኛል።
“እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን?”
ምን ማለት ነው? ላይጨርሱት ኖሯል እንዴ የጀመሩት? አባባሉ የጀመሩትን የመጨረስ ጥርጣሬ ውስጥ እንዳሉ ፍንጭ ይሰጠናል። ፍጹም በግብታዊ በሆነ፣ በዕውቀት እና ዕቅድ ላይ ያልተመረኮዘ፣ የባለሙያ ክህሎት ያልነበረው ጅምር መሆኑን ፍንትው አድርጎ ያሳየናል።

“እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!” መፈክር ሆነ። እድገት የሚመጣው በመፈክር ሳይሆን በስራ ነው። ስራ ደግሞ በእውቀትና በእቅድ እንጂ በስሜት አይከወንም።

ሃይለማርያም ደሳለኝ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱ ስልጣን ላይ ጉብ ያሉ ሰሞን ደጋግመው የሚሉት ነገር ነበር። “እዚህ የተቀመጥቁት መለስ የጀመረውን እቅድ ሁሉ ለመጨረስ ነው።”

ይህን ካሉን ሶስት አመታት አለፉ። ሃይለማርያም ደሳለኝ የጨረሷቸውን ፕሮጀክቶች ስንፈትሽ አንድ ነገር ብቻ አገኘን። እሱም የጸረ-ሽብር አዋጁን ተግባራዊ በማድረግ የህሊና እስረኞችን ቁጥር መጨመር ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ በገዢው ፓርቲ ተጀምረው የተጨረሱ ነገሮች የሉም። ሌሎቹን ለግዜው ተወት አድርገን የመስኖ ልማት ፕሮጀክቶችን ብቻ እንቃኝ። አስራ አንድ ግድቦች ተጀምረዋል። ግን ሁሉም አላለቁም። ለምን? በዚህ ላይ ወደ ኋላ እመለስበታለሁ።

ባለፉት ሁለት አሥርት ዓመታት የተጀመሩት የመስኖ እርሻ እና የሃይድሮ-ኤሌክትሪክ ልማት ፕሮጀክቶች በርካታ ናቸው። የተንዳሆ ግድብ፣ የከሰም ግድብ፣ የርብ ግድብ፣ የጊዳቦ ግድብ፣ የአርጆ ደዴሣ ግድብ፣ የራያ አዘቦ ግድብ፣ የቆቦ ጌራ ግድብ፣ አድአ በቾጠ ግድብ፣ የቆጋ ግድብ፣ የመገጭ ግድብ፣ እንዲሁም የጉደር እና ዳቡስ ግድቦች ናቸው። በ፩፱፱፯ ዓ.ም በአፋር የተጀመረው የከሰምና የተንዳሆ ግድብና መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ግንባታ አመታት አለፉት። የታቀደለት ጊዜ ከ ፭ አመት በፊት ቢያልፍም ስራው ገና አልጀመረም። በ፪፻፪ ዓ.ም የተጀመረው የርብ ግድብ ግንባታ፣ የጊዳቦ ግድብ ግንባታ፣ የአርጆ ደዴሣ ግድብና መስኖ ልማት፣ የራያ አዘቦ መስኖ ልማት፣ የቆቦ ጊራ መስኖ ልማት፣ አድአ በቾጠ መስኖ ልማት ፕሮጀክቶች ሁሉ ግዚያቸውን በልተው የኤሊ ጉዞ ላይ ናቸው። ግንባታው በ፪፻፬ የተጀመረው የቆጋ መስኖ ልማት፣ የመገጭ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት፣ ላይኛው ጉደር መስኖ ልማት፣ ዳቡስ መስኖ ልማት … ተጀምረው ቆመዋል።…እነዚህ እንግዲህ “እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!” ያልተባሉ ፕሮጀክቶች ናችው። ምክንያቱም የፖለቲካ ጠቀሜታቸው ይህን ያህል ስላልሆነ።

እርግጥ ነው። በመጀመሪያው “የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ” ውስጥ የአባይ ግድብ ፕሮጀክት አልነበረም። ከበጀቱም ውጭ ነው። ስለሆነም አጀማመሩ ድንገት ነበር። ጥናት ሳይጠና፣ ሳይመከር፣ በጀት ሳይያዝ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው። አባይ በባዶ ተጀመረ። የቦንድ ሽያጭ ተሞከረ።…እንዲህ እያለ ሎተሪ ላይ ደረሰ… ይህ ብዙ እንዳላስኬደ በግልጽ ይታያል። በዛሬይቱ ኢትዮጵያ ሁሉም ነገር በስሜት እና በግብታዊነት ስለሚሰራ የአጭር ጊዜን እንጅ ረጅሙን አያዩትም። በመጨረሻ ግን ግዜው ደርሶ ማጠፊያው ሲያጥራቸው ይታያሉ። የዚህ ፕሮጀክት አጀማመር በእርግጠኝነት አባይን ገድቦ ልማት ላይ ለማዋል ተብሎ ሳይሆን ከወቅታዊው የስልጣን ችግር ለማምለጥ የተወጠነ እቅድ ነበር። ለግዚያዊ ጥቅም ተብሎ እንደቀልድ የተጀመረው ነገር አሁን የህዝብ እምሮ ውስጥ ስለገባ ይመስላል ቅኝቱን ያስተካከሉት። … እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!

የአባይ ጉዳይ ለገዥው ፓርቲ ህልውና ወሳኝ ነገር ተደርጎ ተወስዷል። ከኢኮኖሚው ይልቅ የፖለቲካ ጠቀሜታው ቀላል አይደለምና። የኢኮኖሚውን ጠቀሜታ ቢመለከቱ ኖሮ አባይን መገደብ እንደሚያወሩት ከባድ አልነበረም። ገዥው ፓርቲ ለሃገር ካሰበ ገንዘቡም ቅርብ ነው። የዜጎች ደሞዝ ሳይቆረጥ፣ ቦንድ ሳይሸጥ፣ ህዝብ ሳይቸገር፣ ቀረርቶ ሳይነፋ… አባይን መገደብ ይቻላል። የኤፈርት ገንዘብ ብቻ አንድ ሳይሆን ሃምሳ አባይን ይገድበዋል። በግል ከተዘረፈው 16ቱ ቢሊየን ዶላር ሳይነካ ማለት ነው።

አባይ ተገድቦ አገልግሎት ቢሰጥ መልካም ነገር ነው። ይህ ጎስቋላ ህዝባችንም ከድህነት አረንቆ ሲወጣ ብናይ ሁላችንም ደስታችን ነው።ዲያስፖራውም አባይ ተገድቦ ማየት ይፈልጋል። ችግሩ ያለው ግልጽነት እና ቅንነት በጎደለው በዚህ መልኩ ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል ብቻ በመከናወኑ ነው። ችግሩ ያለው በልማት ስም በሚደረገው የሰብአዊ መብት ጥሰት ላይ ነው። አባይን ከመገደቡ በፊት የመብት ረገጣው ቢገደብ ዲያስፖራውም በዚህ ላይ በተረባረበ ነበር።

“እድገትና ትራንስፎርሜሽን” የተባለው “ቅኝት” አምስቱን አመት እንደዋዛ ዘልቆታል። የተባለው ለውጥ ግን አልታየም። ሃይለማፘም ደሳለኝ ፓርላማ ላይ ጉብ ብለው በእቅዱ አፈፃፀም የነበሩ ተግዳሮቶችን ዘርዝረውልናል። አፈጻጸም አሉን እንጂ ነገሩ ሌላ ነው። ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው የአገሪቱ ህዝብ የሚተዳደርበትን የግብርናውን ዘርፍ ለማሻሻል የታቀዱ የመስኖ ፕሮጀክቶች ተግባራዊ አልሆኑም። የገጠር መንገዶች ሰባ በመቶ እንደሚሰሩ ቅኝቱ ላይ ነበር። ይህም ፈጽሞ ሊሆን አልቻለም። አሁን ያለውን አስር በመቶ የኤሌትርክ ሃይል ተጠቃሚ በሰማንያ አምስት በመቶ ለማሳደግ ቃል ገብተው ነበር። ወጤቱን ስናየው ግን የነበረው አስር በመቶም ወደ ፈረቃ አሽቆልቁሎ መሄዱን ነው።

በደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ታምቦ ምቤኪ የሚመራው የጥናት ቡድን ባለፈው ወር ከሂልተን ሆቴል የለቀቀው ዘገባ በኢትዮጵያ ስለሚካሄደው ስለዘረፋው አስደንጋጭም አስረጋጭም ነበር። ከኢትዮጵያ ተዘርፎ የወጣው ገንዘብ 16.5 ቢሊየን ዶላር መድረሱን አረጋግጦልናል። ይህ አስደንጋጭ ዘገባ ከዚህ ቀደም Global Financial Integrity (GFI) አለማቀፍ የገንዘብ ግልጸኝነት ተቋም ዘገባ ላይም ወጥቷል። የትራንስፓረንሲ ኢንተርናሽባል ዘገባ እንደሚለው ከሆነ ከተዘረፈው ገንዘብ ግማሽ ያህሉ ከሃገር የወጣው በእድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ ዘመን ነው።

ሌላም አስደንጋጭ ነገር አለ። ኢትዮጵያ በዘመነ ህወሃት በዋስትናም ሆነ ያለዋስትና የተበደረችው እዳ 40 ቢሊየን ዩ..ኤስ. ዶላር ደርሷል። ይህን የዘገበው ላሙዲ የተባለው አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም ነው። ይህ እዳ ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ሲሰላ እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የግማሽ ሚሊዮን ዶላር ባለ እዳ እንደሆነ ይጠቁመናል። ይህ ገንዘብ ለልማት መዋል ሲኖርበት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ ከሀገር እየወጣ መሆኑን ነው እንዚህ አለም አቀፍ ተቋማት እየነገሩን ያለው።

በዚህ በኩል የ”ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ” ዘመቻ፣ በዚያ በኩል ደግሞ ዘረፋው ሊጣጣሙ አልቻሉም። የሚወጣው ከገቢው አልተስተካከለም። ዘረፋው ግዙፍ ነው። በዚህ ሁኔታ ነው መፈክር እየተሰማ ያለው። “እንደጀመርነው እንጨርሰዋለን!”

በኢትዮጵያ የዓለም ባንክ ዳይሬክተር ከሆኑት ከኬን ኦሃሺ ስለ መፈክሩ ቅኝት የተናገሩት የሚያስደምም ነው።
“ኢትዮጵያ … ተዓምራዊ በሆነ መልኩ የነዳጅ ክምችት ጉድጓድ ካላገኘች ወይንም ያልተጠበቀ – ነፋስ አመጣሽ የሆነ ገንዘብ ከሰማይ እንደ መና ካልወረደ በስተቀር (እድገት እና ትራንስፎርሜሽኑ) በምንም ዓይነት መልኩ ቀጣይነት ያለው መሆኑ አይታየኝም… እንደዚህ ያለውን በኃይል እና በመፈክር የተሞላ እና የውስጥ ችግሩን በጥልቅ ያልተመለከተ ዕቅድ እንዴት ሊያስቀጥሉት እንደሚችሉ የሚታየኝ ነገር የለም። እንደ ሀገር በቂ የሆነ ጥሪት መቆጠብ እስካልተቻለ ድረስ ምንጊዜም ቢሆን ጥገኛ የሚሆነው በውጭ መዋዕለ ንዋይ፤ አልያም ደግሞ ጤናማ እና ቀጣይነት በሌለው የመዋዕለ ንዋይ መሰብሰቢያ መንገድ ነው… እንደዚህ ያለ ወጥመድ ውስጥ ነው ተወጥረው ያሉት…
“ዕዳ ካለ አደጋ አለ… ይህ የመንግስት-መራሹ ኢንቨስትመንት ዕድገት አንድ ቦታ ላይ ቢቆም ወይም ለጥቂት ጊዜ መንቀሳቀስ ባይችል እና ቢንገዳገድ እነዚህ ሁሉ የብድር ዕዳዎች ይመሰቃቀላሉ…የግል ዘርፉን ባላሳተፈ እና ጠንካራ ሆኖ ባልተስፋፋበት መልኩ የሚመጣ ፈጣን የምጣኔ ሀብት ዕድገት ዘለቄታ እንደማይኖረው እና፤ ይህ ከሆነ እነዚህ በጊዜ ሂደት የሚደረጉ የብድር ዕዳዎች ሁሉ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ የሚችሉ መሆናቸው እጅጉን ያሳስበኛል።”
ሲሉ ለገዥው ፓርቲ ዱብዳ የሆነ ይህን እውነታ አፍረጥርጠውታል። እውነታው ይህ ነው። ሳይጨመርና ሳይቀነስ የቀረበ የገለልተኛ አካል ምልከታ።

ሁላችንም በአንድነት እንዲህ እንበል። አባይ ይገደባል። ከአባይ በፊት ግን የመብት ረገጣው ይገደብ!
በሰሞኑ ቀልድ ልሰናበት። ጎተራ አካባቢ ነው። መብራት ፈረቃውን ተከትሎ ጠፍቷል። የሰፈሩ ማጅራት መቺ ምሽቱን ተገን በማድረግ ፍተሻ ጀምሯል። ጸዳ ያለ መኪና አቁሞ ወደ ቅምጥ ቤቱ እየነካ ያለውን ስውዬ አስቆመው።
“ቁም! ሳተበላሽ ገንዘብህን በሙሉ አስረክብ!”
“ምን ነካህ! እኔ’ኮ ባለስልጣን ነኝ። ምንስቴር!” ባለስልጣኑ መለሰ።
“አሃ! ክቡር ሚኒስቴር እንግዲያውስ ገንዘቤን ሃምጣ!”
***

ለዛሬ በዚህ እነሰነባበት። በሚቀጥለው ጽሁፌ ስለ ኢሳያስ አፈወርቂ የምለው አለኝ። የነገ ሰው ይበለን።

The post “ሰማንያ አንድ ዜሮዜሮ – ኤ” – ክንፉ አሰፋ (ጋዜጠኛ) appeared first on Zehabesha Amharic.

የሕወሓት አስተዳደር በአዲስ አበባ ዙሪያ በአዳማ እና ደብረዘይት ማስተር ፕላኑን በሚቃወም ቅስቀሳ ተረብሿል

$
0
0

መላው ኢትዮጵያውያን ለሚደረገው ህዝባዊ እንቅስቃሴ ከጎናችን እንዲቆሙ ሲሉ አስተባባሪዎች ጠይቀዋል::

(ምንሊክ ሳልሳዊ) ከመሃል ሃገር ከሚገኙ የኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የደረሱን መረጃዎች እንደሚጠቁሙት በወጣቶች ማህበር አስተባባሪነት በአዲስ አበባ ዙሪያ በናዝሬት/አዳማ እና ደብረዘይት የአዲስ አበባን ማስተር ፕላን በመቃወም እንዲሁም የወያኔው ጀሌ አባይ ጸሃዬ የሚባለው የተናገረውን ጸረ ሕዝብ አፍራሽ አነጋገር በመቃወም ከፍተኛ የሆነ ሕዝባዊ እንቅስቃሴ ለማድረግ ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑ ተጠቁሟል::ይህ ቅስቀሳ ወያኔን አስጨንቆ የያዘው ሲሆን ሊያስቆመው የማይችል ከፍተኛ የሆነ ህዝባዊ አመጽ ይቀሰቀሳል የሚል ስጋት አስከትሏል::
oromia land grap
ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ክልሎች ላይ በተደረገ ተቃውሞ የአዲስ አበባ ማስተር ፕላንን የተቹ የተቃወሙ እና ጥያቄዎችን ያቀረቡ ስለገበሬዎች መብት አቤት ያሉ ወጣቶች ተገለዋል ታስረዋል ተደብድበዋል በአፋኝ ሃይሎች ተሰውረዋል::ይህ ቁስል ሳይጠገን የሕወሓት ጀሌዎች በሃዋሳ በተደረገ ስብሰባ ላይ ባደረጉት እብሪት የተሞላ ንግግር ልክ እናስገባለን ብለው መዛታቸው በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ በአለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቁጣን ቀስቅሷል::ይህንን ቁጣ ተከትሎ በአዲስ አበባ ዙሪያ ከፍተኛ የሆነ የተቃውሞ እንቅስቃሴ ለማድረግ ህዝብን የማስተባበር ስራ እና የቅስቀሳ ስራ እየተሰራ በመሆኑ መላው ኢትዮጵያውያን ከአስተባባሪዎች ጎን እንዲቆም ጥሪዎች አስተባባሪዎቹ ጠይቀዋል::

The post የሕወሓት አስተዳደር በአዲስ አበባ ዙሪያ በአዳማ እና ደብረዘይት ማስተር ፕላኑን በሚቃወም ቅስቀሳ ተረብሿል appeared first on Zehabesha Amharic.

‹‹ዘጠነኛው ስቃይ›› – (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ)

$
0
0

U.S. Immigration And Customs Officials Deport Undocumented El Salvadorians
በቀድሞው የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የሰው መግደል ወንጀል ምርመራ ክፍል ህንፃ ውስጥ በሚገኝ አንድ ደብዘዝ ያለ ብርሃን ያለው ክፍል ውስጥ ተቀምጧል፡፡ አሮጌ ጠረጴዛና ወንበር እንዲሁም ጥቂት ፋይሎች የተደረደሩበት የመጽሐፍ መደርደሪያ መሰል ነገር ጠበብ ያለውን ክፍል ለብቻቸው ይዘውታል፡፡

በተሰበረው የመስኮት መስተዋት በኩል ቀዝቃዛ አየር ይገባል፡፡ ታገሰ እና መርማሪ ፖሊሱ ፊት ለፊት ተፋጥጠዋል፡፡ በእንጨት ጠረጴዛው ላይ የተዘረጋው አረንጓዴ ቀለም ያለው የተከሳሽ ቃል መቀበያ ፎርም ላይ አቀርቅሮ የሚጽፈው መርማሪ ፖሊስ ታገሰ የሚናገረውን ነገር በሙሉ ይመዘግባል፡፡ አልፎ አልፎ ቀና እያለ ጥያቄ ይቀርብለታል፡፡

የተረበሸ ስሜቱ እያስታወቀበት ነገር ግን የተረጋጋ ለመምሰል እየሞከረ ቃላቱን በቀስታ ከአፉ እየጎተተ የሚያወጣቸው ታገሰ እዚህ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘበትን ምክንያት ይተርካል፡፡ ይህ የ38 ዓመት ጎልማሳ በሰው መግደል ወንጀል ተጠርጥሮ ነው የተያዘው፡፡ የተጠረጠረበትን ወንጀል ደግሞ በራሱ የእምነት ቃል ትክክል መሆኑን አረጋግጧል፡፡ መርማሪ ፖሊሱ በወንጀል ሕግ ቁጥር 25 መሰረት የእምነት ክህደት ቃሉን በፍርድ ቤት ከማፅደቁ በፊት እዚህች ጠባብ ክፍል ውስጥ በተከሳሹ ስም በተከፈተ ፋይል ታሪኩን እያሰፈረ ነው፡፡

ግንቦት 22 ቀን 1997 ዓ.ም፡፡ ከተማዋ ከምርጫ ቀውሱ ወሬ ገና አላገገመችም፡፡ የአብዛኛው ህዝብ የወሬ ርዕስ ምርጫው በሆነበት የአብዛኛው ህዝብ የወሬ ርዕስ ምርጫ በሆነበት የአብዛኛው ፖሊስ ትኩረትም በዚህ ጉዳይ ላይ ባረፈበት በዚያ ወር ታገሰ በፖሊስ እጅ ወድቋል፡፡ የዚህ ምክንያቱ ደግሞ የዘጠኝ ዓመት ፍቅረኛውን በጩቤ ወግቶ ገድሏል መባሉ ነው፡፡

‹‹ዘጠኝ ዓመት ዘጠኝ ጊዜ ተሰቃይቻለሁ፡፡ ከዘጠነኛው ስቃይ በላይ የሚሸከም ልብ አልነበረኝም›› ይላል፡፡ ታሪኩን ለመርማሪው እየነገረው ነው፡፡ የተወለደው ከአዲስ አበባ ከተማ አዋሳኝ ቀበሌ አንዷ በሆነችው ዛሬ ግን በከተማው ውስጥ በተካተተችው ቂሊንጦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ውስጥ ነው፡፡ ወደ መሀል ከተማ የገባው ደግሞ በ1988 ዓ.ም ሐምሌ ወር ላይ ነው፡፡ ወደዚህ ያመጣው ምክንያት እንጀራ ፍለጋ እንደሆነ ይናገራል፡፡ በአጎቱ በኩል ተፈልጎ የተገኘለትን የጥበቃ ስራ ለመስራት የአባቱን ሞፈርና ቀንበር ለታናሽ ወንድሙ አስረክቦ ቂሊንጦን ለቀቀ፡፡ ከዚያ በኋላ ነው የከተማ ልጅ የሆነው፡፡

አማርኛ ለመግባባት ያህል ብቻ የሚናገረውና ከተማውን እምብዛም የማያውቀው ታገሰ ጅማ ከአካባቢው ለመላመድ አልተቸገረም፡፡ ቀጣሪዎቹ ሰዎ ኦሮሞዎች መሆናቸው በቀላሉ ለመግባባትና ቀስ እያለም የከተማውን ህይወት ለመልመድ አስችሎታል፡፡ ባይተዋርነቱ ሲቀንስና ቀለል ሲለው አገሩ ሳለ የሚታወቅበትን ዘፈን ማንጎራጎር ጀመረ፡፡ ‹‹ምናለ ጥምቀት በመጣና የታገሰን ድምፅ በሰማን›› ይሉኝ ነበር ይላል ስለ ጓደኞቹ ሲናገር፡፡ በእርግጥም አሳዛኝ ቅላፄ ባለው ድምፅ የኦሮምኛ ዜማውን ሲያንቆረቁረው ጆሮን ለመያዝ ኃይል ነበረው፡፡ ከቀናት በኋላ በራሱ ቴፕ እየዘፈነ የቀዳውን ድምፁን በካሴት ማጠራቀምም ጀምሮ ነበር፡፡ ብዙ ጊዜ አሰሪዎ ወጣ ሲሉ በር ላይ ተቀምጦ የሚያንጉራጉራትን ዜማ አጥብቃ የምትናፍቅ ሴት የተፈጠረችው ከሩቅ አልነበረም- ከዚያው ከግቢው እንጂ፡፡ የቤት ሠራተኛዋ፡፡ ታገስ ለአራት ዓመታት በዚያ ቤት ሲቆይ የዚህች ሴት ወዳጅ መሆኑን እንኳን ያወቀበት የገመተም አልነበረም፡፡ ልጁ ዘለግ ያለ ቁመናውና ፈርጠም ያለ ሰውነቱ ለጥበቃ ስራ ‹የሰጠ› ነው ያስብለው እንጂ ድምፁ ደግሞ በሌላ ወገን የማረካት ሴት አለች፡፡ ስራ በጀመረ በ6ኛው ወር ነበር መግባባት የቻሉት፡፡ እሱም ይህን ዘፈኑን እንደምትወድለት ስለሚያውቅ ባለቤቶቹ በሌሉት ወቅት ሲያንጎራጉርና የልጅቷን ልብ ሲያሸፍት ይውላል፡፡ የሚያዜመውን ነገር ቋንቋውን ሰምታ ረዳት ባትችልም የሆነ የሚያሳዝን ቅላፄ እንዳለው ግን ደጋግማ ትነግረዋለች፡፡ ታገሰ የጥበቃ ቤቱ ውስጥ በነበረችው ትንሽዬ ቴፕ ሁለቱ ቁጭ ብለው ሲያወሩ ደጋግሞ ቀርፆታል እንደምትወደው ነግራዋለች፡፡ እንደሚወዳት ነግሯታል፡፡ የሚዘፈነው ለእርሷ ብቻ እንደሆነም ጭምር፡፡ ይህ ድምፅ ለእርሷ ስጦታ ነው፡፡ የታገሰ ስጦታ፡፡

ትርጎን የወሎ ልጅ ናት፡፡ ሐይቅ አካባቢ ነው የተወለደችው፡፡ አዲስ አበባ ከመጣች ቆየት ብላለች፡፡ ከዚህ ቀደምም በሁለት ሶስት ሰዎች ቤት ተቀጠራ ሰርታለች፡፡ አሁን ከታገሰ ጋር ያገናኛት ቤት የገባችው ከአንድ ዓመት በፊት ቢሆንም ለቤቱ ግን የኖች የቤተሰቡ አባል ነው የምትመስለው፡፡ አየር ጤና አካባቢ በሚገኘው በዚህ መኖሪያ ቤት ብዙ ጊዜ እሷና ዘበኛው ታገሰ ብቻ የሚውሉባቸው ቀናት ብዙ ናቸው፡፡ ነጋዴው አባወራ ከባለቤታቸው ጋር ወደ ሱቃቸው ሲሄዱ ልጆቹ ደግሞ ወደ ትምህርት ቤታቸው ያዘግማሉ፡፡ ቤቱ አልፎ አልፎ ካልሆነ በቀር ቀን ላይ አይከፈትም፡፡ እንደተዘጋ በግቢው ውስጥ የሁለት ሰዎች ፍቅር እንደነገሰ ይውላል፡፡ ትርንጎና ታገሰ የሚለያያቸው ቅዳሜና እሁድ ነው፡፡ ያ እንደማይተዋወቁ እንደማይነጋገሩ እንደማይግባቡ ሆነው ሁለቱን የፈተና ቀን ከዓይንና ከጥርጣሬ ለመውጣት በመታገል ያሳልፉታል፡፡ ሁለት ቀን መታገሳቸው አምስት ቀን ያለስጋት ለመጫወታቸው መስዋዕት ናት፡፡ አንድም ሰው ሌላ ግንኙነት አላቸው ብሎ አስቦ አያውቅም፡፡

ትርንጎ ብዙ ጊዜ የምሽት ስራ ትወዳለች፡፡ ይህን የምታደርገው ሌሊቱ ገፋ ሲል ታገሰን ለመጎብኘት ምቹ ሁኔታ ስለሚፈጥርላት ነው፡፡ ይህን ሐሳብ ያመጣው ራሱ ቢሆንም የሌሊቱን ጨለማ ተግና ያቺን የዘበኛ ቤቱን በፍቅር አሟሙቃት የምትመለሰው ትርንጎ ግን ምን ማድረግ እንዳለባት ታውቃለች፡፡ አንዲት ከፉ ቀን መጥታ እስክታጋልጣቸው ድረስ ሁለቱ ጥንዶች ፍቅራቸውን ከብርድልብስ ከጣራና ግድግዳው ውጪ ለማንም ሹክ አላሉም ነበር፡፡

የቤቱ ወይዘሮ አንዲት ለነ ታገሰ የተረገመች በነበረችበት ዕለት ከምሽ 5፡30 ላይ አድርገውት በማያውቁት ሁኔታ ትርንጎን ፈለጓት፡፡ ተኝታ ይሆናል ብለው በማሰብ እንዳያስደነግጧት ብለው ወደምትተኛበት ሰርቪስ ክፍል ሄደው አንኳኩ፡፡ በሩ ክፍት በመሆኑ ውስጥ አለመኖሯን ለመመልከት አልተቸገሩም፡፡ በፍፁም ወደ ሌላ ቦታ ትሄዳለች ብለው ባለመጠርጠራቸው ሲያጧት ደንግጠው ነበር፡፡ የጥሪያቸውን ድምፅ ታገሰ ጥበቃ ቤት ውስጥ ተኝታ የሰማቸው ትርንጎ እየተንደፋደፈች በጨለማ ውስጥ ወደ ሰርቪስ ክፍሏ ስትጣደፍ ወይዘሮዋ ወደበረንዳው ሲመጡ እኩል ተገጣጠሙ፡፡ የምትሰጠው ምክንያትና በዚህ ሰዓት ከክፍሏ ወጥታ የነበረችበትን ቦታ ለመናገር የደረደረቻቸው ውሸቶች ወይዘሮዋን አላሳመኗቸውም፡፡ በዚህ ወቅት ነው ‹‹ከነገ ጀምሮ ጨርቅሽን ጠቅልለሽ ውጪ›› ብለው ያዘዟት፡፡

ያሉትን ተግባራዊ ለማድረግ አላመነቱም፡፡ ‹‹ነገ ተባብረሽ ቤቴን ታስፍሪዋለች እኔ በሌለሁበት እስከ ዛሬ ያደረግሽውን ነገርም አላውቅም›› በማለት ከቤት እንድትወጣ ጨከኑባት፡፡ ይህ ለታገሰ የማይጋፋው ጭንቀት ጣለበት፡፡ እሱም ተረኛ ተባራሪ እንደሆነ እየገመተ ባለበት ወቅት ወይዘሮዋ ስለድርጊቱ ሰብደውትና አስጠንቅቀውት እንዳይለመደው ነግረው ተዉት፡፡ እሱ ፍፁም ያሰቡት ነገር ልክ አይደለም ብሎ ቢናገርም ከማስጠንቀቂያ ያለፈ ቅጣት ሳይጣልበት ቀኗን ተሻገራት፡፡ ከዚያ ቀን ጀምሮ አካሉ ግቢ ውስጥ ቢሆንም ልቡ ግን ከትርንጎ ጋር ተሻግሮ ጠፋ፡፡

ከ2 ወራት በኋላ
ታገሰ ከዚህ በላይ መቆየት አልቻለም፡፡ ይህቺን ልጅ የወደደበት መንገድ ሌላ ማንንም መውደድ የሚችልበት መንገድ አይደለም፡፡ ዘወትር ስለርሷ እያሰበና እየተጨነቀ መኖሩ ፋይዳ እንደሌለው አውቋል፡፡ ስለዚህም ከዚህ ቤት ወጥቶ ትርንጎን መፈለግ እንዳለበት ወሰነ፡፡ ግን የት እና እንዴት እንደሚፈልጋት ማወቅ አልቻለም፡፡ ይህ በሆነበት አንድ ቀን ግን ያልጠበቀው ክስተት ተፈጠረ፡፡

እንደተለመደው የቤቱ ባለቤቶች ወደ ስራ ሄደዋል፡፡ ቤቱም ኦና ሆኗል፡፡ አዲስ የተቀጠረችው ሰራተኛ ከዚህ ዘበኛ ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንዳይኖት ቀድሞ ተነግሯት ስለነበር በምግብ ሰዓት ምሳ እና እራቱን ጣል አድርጋለት ትመለሳለች እንጂ ብዙም ንግግር የላቸውም፡፡

ታገሰም ቢሆን ቀና ብሎ አይቷት አያውቅም፡፡ ለዚህች አዲስ ሴት ቀርቶ በዓለም ላይ አሉ ለተባሉ ቆነጃጅት እንኳን ገፁ የሚበራ አይመስለውም፡፡ በዚህች ቤቱ ውስጥ ያለርሱና ያለሰራተኛዋ ማንም በሌለበት ሰዓት ስልክ ተደወለ፡፡ የባለቤቶቹ ስልክ፡፡ ሰራተኛዋ እንደወትሮ እመቤቷ የደወሉ መስሏት ነበር ያነሳችው፡፡ ከወዲያኛው ጫፍ አንዲት ሴት ታገሰን እንደምትፈልግ ተናገረች፡፡ ሰራተኛዋ አንዳች ጥያቄ ሳታበዛ ታገሰን ጠራችው፡፡ ግራ ተጋባ፡፡ ስልክ ይፈልግሃል ሲባል ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡ አንድ ሁለት ቀን የቤቱ ባለቤት ደውለው ትዕዛዝ ቢጤ ነግረውት ያውቃሉ፡፡ ከእሳቸው ሌላ የሚደውል አይኖርም ብሎ ፈጠን ፈጠን እያለ ወደ ሳሎኑ ገባ፡፡ ስልኩን ሲያነሳውና የደወለችው ሴት ትርንጎ ነኝ ስትለው ግን ማመን አልቻለም፡፡ ትርንጎ እዚህ ቤት በዚህ ሰዓት ማንም እንደማይኖር ታውቃለች፡፡ ለዚህ ነበር የደወለችበት አወሩ፡፡ በጣም ጠቂት ወሬ፡፡ በማግስቱ መምጣት ከቻለ ዑራኤል ቤተክርስቲያን በር ላይ እንደምትጠብቀው ገለፀችለት፡፡ ደስ አለው፡፡ ወትሮም ከዚህ ቤት ለመውጣትና እሷን ለመፈለግ የነበረው እቅድ አሁን ሳይለፋ ቤቱ ድረስ መጥቶለታል፡፡ እንደ ዕድል የቆጠረው ደግሞ የትም ሳይሄድ እሷ እራሷ ያለችበትን ማሳወቋ ነው፡፡ ቀድሞ ከስራ ባለመልቀቁ ተደሰተ፡፡
ምሽት ላይ ቆረጠ፡፡ ፈቃድ እንደሰጡት ሊጠይቅ ካልሆነም ደግሞ ጥሎ ሊሄድ፡፡ አሰሪው ሲመጡ በማግስቱ ወደ ቤተሰቡ ለራሱ ጉዳይ መሄድ እንደሚፈልግ ነገራቸው፡፡ አልተቀበሉትም፡፡ ቤቱን የሚጠብቅ ሰው ስለማይኖር ሰው በሚኖርበት ዕለት መሄድ እንደሚችል ነበር የነገሩት፡፡ እሱ ግን አልተስማማም፡፡ ሰውዬው ‹‹የተናገርኩትን ተናግሬያለሁ በቃ!›› በሚል አይት ጥለወት ገቡ፡፡

ነጋ፡፡ ታገሰ ሌሊቱ ግራ ገብቶት ነው ያለቀለት፡፡ ማለዳው አልመጣህ ብሎት ነው የነጋለት፡፡ ይህ ሁሉ ሆኖ ታዲያ ሊነጋጋ ሲል የቀሰቀሱት እኚያ ሰውዬ ናቸው፡፡ አሰሪው ወደ ስራ ሲሄዱ ለምን ይህ ያህል ሰዓት ተኝቶ እንደሚያረፍድ አስጠርተው በስድብና በቁጣ ገሰፁት፡፡ ይህቺ ቃል ‹ሆድ ለባሰው› ታገሰ የመጨረሻው ሆነች፡፡ እሳቸው ባላሰቡት መንገድ ቤቱ ውስጥ ያለችውን አነስተኛ ሻንጣ አንስቶ ልብሱን ከታተተ፡፡ በኋላ አሰናብቱኝ አላቸው፡፡ አባረሩት፡፡ ሄደ፡፡ በዚያ ማለዳ ዑራኤል ቤተክርስቲያን አካባቢ ሲደርስ ልቡ ፍርሃት ፍርሃት እያለው ነበር፡፡ በፊት ለፊት በር ላይ ቆሞ እሷን በዓይኑ ይማትር ጀመር፡፡ ሳያስበው ከኋላው መጥታ ያዝ አደረገችው፡፡ ከዚያ በኋላ የነበራቸው ጓዜ ለሁለቱም ምን ያህል እንደሚዋደዱ ያሳየ ነው፡፡ ‹‹በእግራችን መገናኛ እስክንደርስ ድረስ ነው ያወራነው፡፡ ምን ያህል መንገድ እንደተጓዝን እንኳን አላወቅንም›› ይላል ታገሰ ለፖሊስ ሲናገር፡፡

ተለያዩ፡፡ እሱም ወደዘመዱ ቤት እሷም ወዳረፈችበት የአክስቷ ቤት፡፡ ከዚሁ ቀን በኋላ ያለውን ጊዜ ግን ሁለቱን ጥንዶች የሚለያያቸው ነገር አልነበረም፡፡

ከዓመታት በኋላ

ሁልጊዜ እሁድ እሁድ ሳይገናኙ ቀርተው አያውቁም፡፡ ታገሰ ከዘበኝነት ወጥቶ የቀን ስራ መስራት ከጀመረ በኋላ በየዕለቱ ትርፍ ጊዜ አለው፡፡ ትርንጎ ግን ያው በሰው ቤት ስለምትሰራ ሁሌም ከእሁድ በቀር የዓመት ፈቃድ የላትም፡፡ ስለሆነም ከእሁድ በቀር ከታገሰ ጋር ለመገናኘት ዕድሉ የለም፡፡ ፍቅረኞቹ ላለፉት 6 ዓመታት ያሳለፉት በርቀት ፍቅር ነው፡፡ ተገናኝተው ለማውራት ያለቻቸው ቀን ይህቺ ብቻ በመሆኗ እሁድን እንደነፍሳቸው ነው የሚሰስቷት፡፡ አብረው ለመኖር ግን የትርንጎ ፈቃድ አልተገኘም፡፡ እስካሁን ድረስ ታገሰ ቤት ተከራይቶ አብረው እንዲኖሩ ቢለምናትም በጄ አላለችም፡፡ ይህ ደግሞ የታገሰን አዕምሮ ወደ ሌላ ሃሳብ መርቶታል፡፡ ይህቺ ሴት ሌላ በፍቅር የምታስበው ሰው አለ ማለት ነው ብሎ፡፡ ድምፀ መልካሙ ታገሰ በድምፁ ያሸነፈው ልብ በሌላ ሰው የተጠለፈበት ስለመሰለው ተናዷል፡፡ አብረው ለመኖር ደጋግሞ ሲጠይቅ የምትሰጥ ምላሻም እርሱ በሚፈልገው መልኩ ባለመሆኑ ደስታ ርቆታል፡፡ ወደፊትም አጋጣሚ ቢፈጠርላት ከእርሱ ለመለየት ቀን የምትጠብቅ አድርጎ ሳላት፡፡ ፈርዶበት ቅናት ላዩ ላይ ሰፈረ፡፡ ከዚህ ጊዜ በኋላም በመካከላቸው የነበረው ግንኙነት ሻከረ፡፡

በአጓጉል ፀባዩ የሚጨቀጭቃትን ይህንን ሰው ልትቋቋመው አልቻለችም፡፡ ብስጭቷ ገንኖ ወጥቷል፡፡ አልፎ አልፎ ትናገረዋለች፡፡ ያቺ ስንት ነገር የሚያሳልፉባት እሁድ በየሳምንቱ የጭቅጭቅ ሆኗል፡፡ ይህ ደግሞ ትርንጎን ቅር አሰኝቷታል፡፡ ታገሰ ያለመፈለግ ስሜት ከተሰማው ቆይቷል፡፡

‹‹ያለፉትን ዓመታት ሙሉ ለእርሷ ስል ብዙ መስዋዕትነት እንደከፈልኩ ታውቃለች፡፡ ከስራ ወጥቼ ተንከራትቻለሁ፡፡ ሰርቼ የማገኘውን ነገር ሁሉ ለእርሷ አስፈላጊ ነገር በመግዛት ገንዘቤን አጥፍቻለሁ፡፡ ቤት ተከራይ ብላኝ ተከራይቻለሁ፡፡ የቤት ዕቃ ግዛ ብላኝ በአቅሜ መጠን ገዝቻለሁ፡፡ ትርንጎ የተቀጠረችው ሀብታም ቤት ስለሆነ እዚያ ያየችው ነገር እንዲሟላላት የፈለገች መስላለች፡፡ ይህ ሁሉ የሆነው ግን እኔን ለማዘናጋት እንጂ እንደማታገባኝ ታውቃለች፡፡ በተለይ እኔን አጃጅላ ሌላ ሰው እንደፈለገች ገብቶኛል›› ብሏል ለፖሊስ ሲናገር፡፡

የዚህ ሰው ልብ በፍቅረኛው ላይ አምርሯል፡፡ አለችኝ የሚለው ነገር ዛሬ ፖሊስ ጣቢያ ለመጣው ጉዳይ መሰረት እንደሆነበት ይገልጻል፡፡ ላለፉት 8 ጊዜያት የቋጠርኳቸው ቂሞች በርሷ ታይተውኛል የሚለው ይህ ‹አፍቃሪ› የትርንጎ ሀጢያት ናቸው የሚላቸውን ነገሮች ዘርዝሮ ተናግሯቸው ነበር፡፡

‹‹ስልክ ደውይልኝ ስላትም- ያለሽበት ቤት ስልክ ልደውል ስላትም እሺ አትልም፡፡ ፍቅረኛ እንዳላት እንዲታወቅ አትፈልግም፡፡ እንደር ስላት ‹አዳር ፈቃድ ላንተ ብዬ ያለባህዬ አልወስድም› አለችኝ፡፡ እኔ ለእርሷ ብዬ ስንት ነገር ስሆን እሷ ለእኔ ብላ ማደር አልፈለገችም፡፡ አንድም ቀን እወድሃለሁ አላለችኝም፡፡ እኔ ስጠይቃት ብቻ ነው የምትመልስልኝ፡፡ ቤቴ ነይ ስላት ሁለት ቀን ብቻነው የመጣችው፡፡ ‹ያላገባሁት ወንድ ቤት ለምን እሄዳለሁ› አለችኝ፡፡ ይህም በእኔ ላይ አለመተማመኗን መሰከረልኝ፡፡ ዘመዷን እንድታስተዋውቀኝ ስጠይቃት እምቢ አለች፡፡ ታፍርብኛለች ማለት ነው፡፡ ከእኔ ሌላ ሰው ማፍቀር ትችያለሽ ወይ ብዬ ስጠይቃት ‹ሰው እኮ ነኝ› አለች፡፡ ከእኔ ስትለይ ግድ የላትም ብዬ አሰብኩ፡፡ የእኔን ቤተሰብ ላስተዋውቅሽ ስላት ‹ይቅርብኝ› ያለችኝ ስለምትንቀኝ ነው፡፡ ከዚህ ቀደም አገር ቤት እያለች ያገባችውንና አምልጣው የመጣችውን ባሏን ሁለት ቀን አነሳችብኝ፤ ትፈልገዋለች ማለት ነው፡፡ እነዚህ ስምንት ነገሮች ለዓመታት የቆየበትን ፍቅር ንደውብኝ ኪራ ደርሶብኛል፡፡ ያቃጠልኩት ጊዜ ቆጭቶኛል፡፡ ለመጨረሻ ጊዜ ላናግራት ወስኜ ቤቴ ይዣት ስሄድ ግን ያ ዕለት ያላሰብኩት ሆነብኝ›› ብሏል፡፡ እነሆ ዘጠነኛ ስቃይ ያለውን ታሪክም ተናገረ፡፡

ግንቦት 19 ቀን 1997

ታገሰና ትርንጎ ቤት ተቀምጠዋል፡፡ ዛሬ ይዟት የመጣው አንድ ጥያቄ ሊጠይቃት ነው፡፡ ‹‹ትፈልጊኛለሽ አትፈልጊኝም?›› የሚል፡፡ እፈልግሃለሁ ካለች እንድታገባው፤ አልፈልግህም ካለች ትታው እንድትሄድ ነበር ውሳኔው፡፡ ቀትር ላይ ነው በሰበብ ያስመጣት፡፡ ለቅሶ አለብኝ ብላ ፍቃድ ጠይቃ ነው የመጣችው፡፡ እዚያች ሳሳ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ብዙ ሳይቆዩ ወሲብ እንዲፈፅሙ ጠየቃት፡፡ ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ ምክንያቱም ደግሞ እሱ እንደሚናገረው ‹‹አረግዛለሁ›› የሚል ነው፡፡ እሱ ግን በሌላ ተርጎሞታል፡፡ አልፈልግህም ማለትሽ ነው ሲላት ‹‹እንዲያ ከመሰለህ አዎ›› አለችኝ ብሏል፡፡ ይህ ደግሞ ለታገሰ ‹‹ዘጠነኛው ስቃይ ነው›› ተናደድኩ ይላል፡፡ ለፖሊሱም የነገረው ይህንኑ ነው፡፡

‹‹ይህንን ቃል ስትናገረኝ ወረረኝ፤ ያቃጠልኩት ዕድሜ ቆጨኝ፡፡ በወጣትነቴ ስንት ዕድል ነበረኝ፡፡ ዛሬ ብቻዬን አልኖርም ነበር፡፡ በዓይኔ ባላይም የካደችኝ መሆኑን ሰውነቴ ነግሮኛል፡፡ ይህን ደግሞ ማረጋገጥ አያስፈልገኝም፡፡ ከዚህ በኋላ የማላውቀው ስሜት በውስጤ ገባ፡፡ ሰይጣን አሳሳተኝ፡፡ ስለዚህም ገደልኳት››

ታገሰ ይህቺን ወጣት የገደላት ፍራሹ ስር ደብቆት በነበረው ጩቤ ነው፡፡ ዘጠኝ ጊዜ የተለያዩ የሰውነቷ ክፍል ላይ ወግቷታል፡፡ ደሟ ያንን አልጋ ሙሉ በሙሉ ደም ሸፍኖታል፡፡ ታገሰ ‹‹የዘለዓለም ፍቅረኛዬ›› ያላትን ሴት ሲያብሰለስለው በነበረው ውሳኔ በጩቤ ከገደላት በኋላ ለፖሊስ እጁን ሰጠ፡፡ ያደረገው ነገር ትክክል ባይሆንም ሌላ ምርጫ አልነበረኝም ብሏል፡፡ ፍፁም የተሳሳተ ውሳኔ መሆኑን ግን ልቦናው ያውቃል፡፡ ታገሰ ወደ ወህኒ ቤት ሲወርድ ግን ፖሊስ ጋር የሰጠው ቃል በአፉ ውስጥ አልነበረም፡፡ ይልቅስ ለቅሶ ፀፀትና ናፍቆት እያንገላቱት ነበር፡፡ ‹‹እሷን ከምገድል ራሴን ገድዬ ቢሆን ምንኛ ጥሩ ነበር›› ብሏል፡፡

The post ‹‹ዘጠነኛው ስቃይ›› – (እውነተኛ የወንጀል ታሪክ) appeared first on Zehabesha Amharic.

አቡነ ማትያስ የእሬቻ በዓል በዝቋላ ገዳም ሊከበር ነው የሚለውን ዜና ኢቢሲ እንዲያስተካክል ጠየቁ

$
0
0

abune-matyas
ማህበረ ቅዱሳን እንዘገበው: በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ላይ በመጋቢት ወር መጨረሻ የኢሬቻ በዓል እንደሚከበር መስከረም 15 ቀን 2007 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ብሮድ ካስቲንግ ኮርፖሬሽን በኦሮምኛና በአማርኛ ቋንቋ መተላለፉ ተገቢ እንዳልሆነና ችግር ሊፈጥር የሚችል መሆኑን በመግለጽ የተላለፈው መረጃ እርማት እንዲደረግበት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ለአቶ ሙክታር ከድር በጻፉት ደብዳቤ ጠየቁ፡፡

የሃይማኖቶች እኩልነት በታወጀበት የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕግ መንግሥት አንዱ ቤተ እምነት የሌላውን እምነት መንቀፍም ሆነ መንካት እንደሌለበት ተደንግጓል” ያሉት ፓትርያርኩ በሚዲያ ሽፋን የተሰጠው ጉዳይ ሕገ መንግሥቱን የሚተላለፍ፤ የገዳሙን መናንያን መነኮሳትና በአካባቢው የሚኖሩ ሕዝበ ክርስቲያኖችን የሚያስቆጣ በመሆኑ የክልሉ መንግሥት ለተዘገበው ጉዳይ እርማት እንዲሰጥበት ለኦሮምያ ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳደር ለአቶ ሙክታር ከድር በጻፉት ደብዳቤ አሳስበዋል፡፡

በሌላ በኩል ጉዳያችን የጡመራ መድረክ የሚከተለውን ዘገባ አሰራጭቷል:-
ባለፈው መስከረም 15/2007 ዓም በኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን (በቀድሞ ስሙ ኢቲቪ) በአማርኛ እና በኦሮምኛ እንደተለቀው ዜና ከሆነ ”በመጪው መጋቢት ወር መጨረሻ ላይ የእሬቻ በዓል በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ውስጥ ይከበራል ”ይላል።ዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ከተከበሩት እና ከታፈሩት ገዳማት ውስጥ አንዱ ነው።ገዳሙ ፃድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ከግብፅ ወደ ኢትዮጵያ መጥተው ለኢትዮጵያ እና ለመላው የሰው ዘር የፀለዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው።

ይህንን ከ800 ዓመታት በላይ ፀንቶ የኖረ ገዳም ”እሬቻ” እንዲከበርበት የተደረገበት ዋና ምክንያት እምነትን ከእምነት ለማጋጨት በስርዓቱ የተሸረበ ተንኮል ነው የሚሉ ብዙዎች ናቸው።ከእዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ መሰረተ እምነትን የጣሱ ተግባራት ሲፈፀሙ እና ሙስና የሚፈፅሙ የስርዓቱ አጎብዳጆች (በቤተ ክህነቱ ዙርያ ‘የጨለማው ቡድን አባላት’ በመባል የሚታወቁት) የቤተ ክርስቲያኒቱን ንብረት እና ገንዘብ መተዳደርያቸው ሲያደርጉት አመታት መቆጠራቸው ይታወሳል።

በቅርቡም በርዕሰ አድባራት እንጦጦ መንበረ ፀሐይ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ሙዚየም የወርቅ መስቀልን ጨምሮ ሌሎች በቅርስነት የተመዘገቡ ንብረቶች መጥፋታቸው ይታወሳል።ከእዚሁ ጋር ተያይዞ የደብሩ አስተዳዳሪ ቀደም ብለው ሰራተኞችን ሰብስበው ”በሙዚየሙ የሚገኙ ቅርሶች ተሸጠው ለአባይ ቦንድ መግዣ ይዋሉ” የሚል ሃሳብ አቅርበው በደብሩ አገልጋዮች እና ሰረተኞች ”ታሪክ አጥፍተን ታሪክ አንሰራም” የሚል ምላሽ እንደሰጧቸው የገለፀው የሪፖርተር ጋዜጣ ባለፈው ሮብ የካቲት11/2007 ዓም በዘገባው ”የቤተ ክርስቲያኗ ካህናት፣ ሠራተኞችና የአካባቢው ነዋሪዎች የደብሩን አስተዳዳሪና ሌሎች ኃላፊዎች ተባብረው ወርቆቹን ማጥፋታቸውን፣ በቤተ ክርስቲያኗ ሠራተኞች ላይ በደልና ብልሹ አሠራር እንዲደርስ ማድረጋቸውን በመግለጽ ተቃውሟቸውን በፊርማ በተደገፈ አቤቱታ ለሚመለከታቸው ሁሉ መላካቸውን” ይገልጣል።

The post አቡነ ማትያስ የእሬቻ በዓል በዝቋላ ገዳም ሊከበር ነው የሚለውን ዜና ኢቢሲ እንዲያስተካክል ጠየቁ appeared first on Zehabesha Amharic.

በአዲስ አበባ የታክሲ ሹፌሩ መኪናውን አቁሞ ራሱን ወደድልድዩ ወርውሮ ሕይወቱን አጠፋ (ፎቶዎች ይዘናል)

$
0
0

አዲስ አበባ ያሉ የዘ-ሐበሻ ተከታታዮች “እኔም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ” ካሉን ቆይተዋል:: በሶሻል ሚዲያ ለዘ-ሐበሻ መረጃዎችን በፎቶ አስደግፈው መላካቸውን ቀጥለዋል:: አሁንም ለሌሎች ኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ በሌሎች ሃገራት የሚገኙ የዘ-ሐበሻ ወዳጆች ‘እኔም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ነኝ’ በማለት መረጃዎችን በቶሎ በሶሻል ሚዲያዎቻችን በፌስቡክ, ዋትሳፕ, ቫይበር, ስካይፕ, ትዊተር እና ሌሎችም መንገዶች ሊያደርሱን ይችላሉ::

ዛሬ የአዲስ አበባ የዘ-ሐበሻ “ሪፖርተር” 6 ፎቶ ግራፎችን ከመረጃ ጋር አድርጎ ልኮልናል:: እንደመረጃ ምንጫችን ገለጻ ድርጊቱ የተፈጸመው በአዲስ አበባ በተለምዶ እስጢፋኖስ ቤተክርስቲያን አካባቢ ነው:: ትናንት ከቀኑ 8:45 አካባቢ እስጢፋኖስ ቤ/ክ አካባቢ የሚገኝ ድልድይ ጋር የሚነዳትን ታክሲ በማቆም ወደ ወንዙ ራሱን በመወርወር ራሱን አጥፍቷል:: በፎቶዎቹ እንደምታዩት ፖሊስ ጉዳዩን ሲከታትልና የወደቀውን ታክሲ ሾፌር ነው:: የታክሲ ሹፌሩ ለምን ራሱን እንዳጠፋ በምርመራ ላይ ሲሆን ለጊዜው የተገኘው መረጃ ራሱን ማጥፋቱ ብቻ ነው::

ፎቶዎችን ይመልከቱ:: እርስዎም የዘ-ሐበሻ ሪፖርተር ይሁኑ::
addis ababa suside

addis ababa suside1

addis ababa suside2

The post በአዲስ አበባ የታክሲ ሹፌሩ መኪናውን አቁሞ ራሱን ወደድልድዩ ወርውሮ ሕይወቱን አጠፋ (ፎቶዎች ይዘናል) appeared first on Zehabesha Amharic.


ታሪካዊ የአድዋን መታሰቢያ በአል ማስታወቂያ

119ኛው የአድዋ ድል በዓል ቀን በዳላስና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ

$
0
0

እንደሚታወቀው አሁን የያዝናት ወር ለኛ ለኢትዮጵያውያን ብሎም ለመላው ለጥቁር ህዝብ ትልቅ ድል የተከናወነበት ወር ነው። መላው አለም ነጭ የበላይ አድርጎ በሚቆጥርበትና ሁሉም የአፍሪካ አገሮች በቀኝ ግዛት በወደቁበት ወቅት ኢትዮጵያን ለመውረር የመጣውን የጣልያን ጦር በጀግናው በአፄ ምኒሊክ ብልህ መሪነት አይቀጡ ቅጣት በመቅጣት ኢትዮጵያን ከቀኝ ግዛት ያዳኑበት ወር ሲሆን በአለማችን የሚገኙ ጥቁሮችና በቅኝ ግዛት የነበሩት የአፍሪካ አገሮች ለነፃነታቸው እንዲታገሉ ተስፋ የሆናቸው ድል ነው። ይህ የሆነው March 1, 1896 ነበር። እነሆ ታሪክና ትውፊት መጠበቅ ለአንድ አገርና ሕዝብ ህልውና መሆኑን በመገንዘብ 119ኛው የአድዋ ድል በዓል ቀን በዳላስ በግራንድ ሆቴል (Grand Hotel) ለማክበር ተዘጋጅተናል። በዳላስና አካባቢ የምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያ March 1, 2015 በግራንድ ሆቴል (Grand Hotel) በመገኘት የበዓሉ ተካፋይ እንድትሆኑ ተጋብዛችኋል።

Guest Speakers:-
1. Mr. Obang Metho
Executive Director of SMNE
2. Prof. Solomon A. Getahun
Associate Proffesor of History Department at CMU
3. Journalist Kifle Mulat
Former President of EFJA

Place:- Grand Hotel Located @ 7815 LBJ Frwy, BLDG B Dallas, Tx 75251
Date:- March 1, 2015
Time:- 4 PM – 8 PM

For more info:- 1(214) 404 4737
#ኢትዮጵያውያን #አድዋ #ጥቁር

 

unnamed

The post 119ኛው የአድዋ ድል በዓል ቀን በዳላስና አካባቢዋ ለምትኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በሙሉ appeared first on Zehabesha Amharic.

Hiber Radio: ወይንሸት “ከምርጫው ተወዳዳሪ ዕጩነት እኔን እጣ አልደረሰሽም ብለው አስወጥተውኛል”ማለቷ…እቴጌ ጣይቱ በታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ ታላቅ ሴት (ልዩ ጥንቅር).. አበበ ገላው የሀሰት ዲግሪ የሰበሰቡ የስርዓቱ ሰዎችን የተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መረጃ እንደሚያቀርብ ገለፀ…አገዛዙ በኢትዮጵያ በሙስሊም ወጣቶች ላይ የከፈተው የእስር ዘመቻ የድል ዋዜማ ጠቋሚ ነው መባሉና ሌሎችም

$
0
0
ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ

ጋዜጠኛ ሃብታሙ አሰፋ


የህብር ሬዲዮ የካቲት 15ቀን 2007 ፕሮግራም

<...ምርጫ ውስጥ እስካሁን በመቆየታችን በሂደቱ የሚፈፀመውን ወንጀል ሁሉ እያጋለጥን ነው.... ለይስሙላ ብቻ አጃቢ ግን ሆነን አንቀጥልም...> አቶ ስለሺ ፈይሳ የሰማያዊ ፓርቲ ምክትል ሊቀመንበርና የምርጫ ጉዳይ ሃለፊ ለህብር ሬዲዮ ከሰጡት ማብራሪያ (ሙሉውን ያዳምጡ)

በቬጋስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን የተፈጠረውን አለመግባባት ተከትሎ ከተከራዩት ቤተክርስቲያን በሀሰት ክስ ሳቢያ በመናፈሻ መፀለያቸውና ተከትሎ የመጣው ቅሬታ ላይ የተሰጠ ቃለ መጠይቅ እና ውይይት (ሙሉውን ያዳምጡ)

እቴጌ ጣይቱ በታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ ታላቅ ሴት (ልዩ ጥንቅር)

<..ከምርጫው ተወዳዳሪ ዕጩነት እኔን እጣ አልደረሰሽም ብለው አስወጥተውኛል ...የኢሀዲግና ሌሎች ፓርቲ ተወካዮች ባለፈው ምርጫ ስለተወዳደሩ ቀድመው ሎተሪ ውስጥ አልገቡም ..> ወጣት ወይንሸት ሞላ የሰማያዊ ፓርቲ የምክር ቤት አባልና የሴቶች ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ አባል ጋር ካደረግነው ቃለ መጠይቅ የተወሰደ(ሙሉውን ያዳምጡት)ውይይት በህብር ሬዲዮ የአምስተኛ አመት ዝግጅት አስቀድሞ ከታሰበለት ቦታ ወደ ሀምተን ኢን የስብሰባ አዳራሽ መዘዋወሩ ላይ የህዝብ አስተያየት

ሌሎችም

ዜናዎቻችን

በአገዛዙ ምርጫ ቦርድ የተሾሙት የመኢአድ ፕሬዝዳንት ከዚህ ቀደም ኢህአዴግ ም/ሚኒስቴር ሊያደርጋቸው እንዳግባባቸው ገለፁ

የዞን 9 ጦማሪያን በእስር ቤት የተለያየ ሰቆቃ እንደሚፈፀምባቸው ለፍ/ቤት ገለፁ

ሱዳን በአባይ ጉዳይ የግብፅ ስጋት አልተወገደም አለች

ከኢትዮጵያና ከግብፅ ጋር ውይይት እንዲደረግ ጠየቀች::

ጋዜጠኛ አበበ ገላው የሀሰት ዲግሪ የሰበሰቡ የስርዓቱ ሰዎችን የተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መረጃ እንደሚያቀርብ ገለፀ

አገዛዙ በኢትዮጵያ በሙስሊም ወጣቶች ላይ የከፈተው የእስር ዘመቻ የድል ዋዜማ ጠቋሚ ነው ተባለ

የህብር ሬዲዮ የ5ኛ ዓመት በታላቅ ህዝባዊ ስብሰባ በሐምፕተን ኢን ሆቴል ይደረጋል

ሌሎችም ዜናዎች አሉ

The post Hiber Radio: ወይንሸት “ከምርጫው ተወዳዳሪ ዕጩነት እኔን እጣ አልደረሰሽም ብለው አስወጥተውኛል” ማለቷ… እቴጌ ጣይቱ በታሪክ ሲታወሱ የሚኖሩ ታላቅ ሴት (ልዩ ጥንቅር).. አበበ ገላው የሀሰት ዲግሪ የሰበሰቡ የስርዓቱ ሰዎችን የተመለከተ ሰሞኑን አዲስ መረጃ እንደሚያቀርብ ገለፀ… አገዛዙ በኢትዮጵያ በሙስሊም ወጣቶች ላይ የከፈተው የእስር ዘመቻ የድል ዋዜማ ጠቋሚ ነው መባሉና ሌሎችም appeared first on Zehabesha Amharic.

ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሙሉ -ከኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW)

$
0
0

ኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW)

CREWላለፉት ሦስት ተከታታይ ዓመታት የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ስለ ኢትዮጵያውያን ሴቶች ዘርፈ ብዙ ችግሮች ምንነት ማህበረሰቡን ግንዛቤ ለማስጨበጥ በየዓመቱ የአለም አቀፍ የሴቶችን ወር ምክንያት በማድረግ በመጋቢት ወር ላይ ጉባኤ በማዘጋጀት  ሴቶችን  በሚመለከቱ በተለያዩ  ርዕሰ ጉዳዮች  ላይ ምሁራን ጥናታዊ ጽሑፎችን እንዲያቀርቡና፣ ለችግሮቹ መፍትሔ እንዲጠቁሙ በማድረግ ማህበረሰባችንን ግንዛቤ ለማስጨበጥ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል። ሴቶች በማህበራዊ፣ በኤኮኖሚና በፖለቲካ የሚደርስባቸውን ችግሮች በተለይም የተሻለ ኑሮ ፍለጋ በአረብ አገራት ተሰደው ስላሉ ኢትዮጵያዊያን ሴቶች መብትን አስመልክቶ በየጉባኤዎቹ ሰፋ ያለ ትምህርታዊ ውይይቶች አካሂዷል።

ዘንድሮም የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል ለ፬ኛ ጊዜ የሚካሄድ ዓመታዊ ጉባኤ  አዘጋጅቷል፡፡ የዚህ  የ፬ኛው የኢትዮጵያ ሴቶች ጉባኤ መሪ ቃል የህዝባዊ ማህበራት ሚናና  የ2015 የኢትዮጵያ  ምርጫ  ነው።(THE ROLE OF CIVIL SOCIETY IN THE UPCOMING 2015 ETHIOPIAN ELECTION)

እንደሚታወቀው ሕዝባዊ ማህበራት ለአንድ ሀገር የዲሞክራቲክ ሥርዓት ምሥረታ ምሰሶ ናቸው፡፡ በሀገራችን ሰብአዊ መብት ለማስከበር በቆሙ ሕዝባዊ ድርጅቶች ላይ ማዕቀብ የጣለው በ2009 የወጣው ሕግ (The Charities and Societies Proclamation) ጸድቆ ተግባራዊ በመሆኑ ስለ ሰብአዊ መብቶችና የሴቶች መብት የማስከበር ስራ መስራት የማይቻልበት ሁኔታ ላይ እንገኛለን፡፡

ስለዚህም ጉባኤው ስለሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች መጠበቅና የመጻፍ፣ የመደራጀትና የመሰባሰብ መሠረታዊ  መብቶች በሌሉበት አገር ምን ዓይነት ምርጫ ይካሄዳል? በሚለው ጥያቄ ላይ የሚያጠነጥን ጥልቅ የሆነ ወቅታዊ ውይይት የሚካሄድበት ሲሆን፣ ምሁራን ጥናቶቻቸውን የሚያቀርቡበት በመሆኑ በዝግጅቱ ላይ የሁላችሁም መገኘትና ተሳትፎ ወሳኝ ነው። ስለዚህ ውድ ወገኖቻችን በዝግጅቱ ላይ በመገኘት የበኩላችሁን አስተዋፅኦ እንድታደርጉ በአክብሮት ተጋብዛችኋል።

ዝግጅቱ የሚካሄድበት ቦታ በSILVER SPRING SHARATON HOTEL ሲሆን

ቀኑ፦ ቅዳሜ MARCH 7, 2015 ነው፡፡

አድራሻው፦ 8777 GEORGIA AVENUE SILVER SPRING MD, 20910 ሲሆን ከመስብሰቢያ ሆቴሉ ጀርባ ነፃ የመኪና ማቆሚያ አለ፡፡

ሰዓቱ፦ ከጥዋቱ 9AM እስከ 5PM ነው፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል

The post ለዋሽንግተን ዲሲና አካባቢዋ ለምትገኙ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በሙሉ -ከኢትዮጵያ ሴቶች መብት ማዕከል (CREW) appeared first on Zehabesha Amharic.

ሀገራዊ የጸሎት ጥሪ -ሰሎሞን ንጉሡ (ከሱዳን)

$
0
0

ሰሎሞን ንጉሡ (ከሱዳን)  (የካቲት 11 ቀን 2007ዓ.ም ተጻፈ)
prayerእንዴትና በምን አኳኋን ይህን የጸሎት ጥሪ እንደምጀምር ጭንቅ ብሎኝ በጣም ግራ ተጋብቼ ነበር፡፡ ልጻፍ አልጻፍን ጨምሮ ከራሴ ጋር ብዙ ተሟገትኩ፤ “ጊዜው ገና ነው” በሚልም ጭምር፡፡ ለማንኛውም አፍ ወድቆ አይሰበርምና መጻፌ ካለመጻፌ እንደሚሻል ራሴን አሳመንኩ፡፡ ደግሞም ለማንኛውም ራሴን በትንሹ ማስተዋወቁ ለጸሎት ጥሪዬ መጠነኛ ትኩረት ያስገኝልኝ ይሆናል የሚል ተስፋ አሣደረብኝ፡፡ አንባቢያንም – ለማንኛውም – ይህን የጸሎት ጥሪ ችላ ሳትሉ ዐይንና ጆሮ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ሁሉ በምታገኙት አጋጣሚና ባላችሁ የመገናኛ አውታር አድርሱልኝ፡፡ በተረፈ ሊሆን ያለው ሁሉ ከመሆን እንደማይዘለል ብዙዎቻችን ስለምናምን በተለይ የሀገራችንን ነፃነት በሚመለከት በየበኩላችን የምንችለውን ከማድረግ ውጪ በህልም ዓለም ሩጫ በከንቱ ልንባዝን እንደማይጠበቅብንና እንደማይገባንም ባስታውስ ቅር የሚለው ሰው አይኖርም ብዬ እገምታለሁ፡፡

የደርግ መንግሥት ሊወድቅ ጫፍ ላይ ነበር፡፡ ያኔ በ82 እና በ83ዓ.ም ሀገር ልትፈራርስ አንድ ሐሙስ ቀርቷት በነበረበት የኤሎሄ ሰዓት ሕዝቡ በደርጎች ላይ በነበረው ከፍተኛ ጥላቻ ምክንያት የወያኔዎች ግስጋሴ ከቁብም አልተቆጠረም ነበር፡፡ የደርግ ጨፍጫፊነትና አረመኔያዊ አገዛዝ የወያኔዎችን የትግል እንቅስቃሴ አልጋ ባልጋ አደረገው፡፡ ብዙዎች “ከደርግ የማይሻል አይመጣም” ከሚል ተላላነት የተነሣ ለወያኔዎች መልካም ፊት ከማሣየት ጀምሮ ሁለንተናዊ እገዛም የሚያደርገው ገራገር ዜጋ ጥቂት አልነበረም፡፡ የነሴኩቱሮ የጫካ ፕሮፓጋንዳም ቀላል አልነበረም፡፡ ለብዙኃን የዋሆች በቀላል መሸነፍ ምክንያት የነበረው የወያኔዎች ሥልታዊ የቆረጣ ፕሮፓጋንዳና የደርግን ጦርና መንግሥት በልዩ ልዩ ዘዴ ከፋፍሎ የማሽመድመድ መሠሪ ተንኮል ነበር (ለትግሬው አድማጭ፣ ለአማርኛው አድማጭ፣ ለኦሮሞው አድማጭ፣… የተለያዬና እርስ በርስ የሚጋጭ ቅስቀሳ እንደነበራቸው ያስታውሷል)፡፡ ያኔ ነበር ታዲያ በወቅቱ የወያኔ ሤራ ከሚያንገበግባቸው ከነገብረ መድኅን አርአያና አብርሃም ያዬህ ያልተሣካ ሀገርን የማዳን ጥሪ ጩኸት ቀጥሎ እኔም የአቅሜን በዚህ ብዕር የተፍጨረጨርኩት፡፡ የታሪክ ሽሚያ ውስጥ መግባቴ እንዳልሆነ ይታወቅልኝ፤ በፍጹም፡፡ እዚያ ውስጥ የመግባት ዓላማም ሆነ ፍላጎት የለኝም፡፡ አንዳንዶች ይህን ስም ስታዩ የሚቀሰቀስባችሁን ትዝታ ብጋራ ግን አልጠላም፡፡

የወያኔን ጉድፍና ሀገርን የማጥፋት ዘመቻ ብቻ ሣይሆን የደርግ መንግስት ራሱና በውስጡ የተሰገሰጉ አፍራሽ ኃይሎች ያደርጉት የነበረውን በደል በቅን ልቦና በመነሣት በጽሑፎቼ ውስጥ አካትት ስለነበር የተወሰነ ተሰሚነት የነበረው ብዕር እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ በእውነቱ በዚያን ዘመን ለአቅመ-ፖለቲካ የደረሳችሁና ለሚዲያ ቅርበት የነበራችሁ እንደምታስታውሱት ስለወያኔዎች በጋዜጣም ይሁን በሬዲዮና በቲቪ ያልቀባጠርኩት አልነበረም፡፡ ብዙ ሥፍራዎችን እየተቆጣጠሩ ስለነበርና ከሚይዟቸው አካባቢዎች የመረጃ ምንጭ ስለነበረኝ እነዚህ ብልሹ ዜጎች ሀገራችንን ወዴት አቅጣጫ ሊወስዷት ይቋምጡ እንደነበር የበኩሌን ገልጫለሁ፡፡ የብዙዎቻችን ጩኸት ግን የቁራ ጩኸት ሆኖ ነው የቀረው፡፡

ከሁለት አሠርት ዓመታ ፀጥታ በኋላ ታዲያ ምን መለሰኝ?

እንደነገርኳችሁ ያኔ እኔን ጨምሮ የወደፊቱ እሳት አስቀድሞ የታያቸው ወገኖች ብዙ ጮኹ፡፡ እንደምናስታውሰው ያዳመጣቸው ግን አልነበረም፡፡ የሞኙ እረኛ ዓይነት ክስተት ተፈጠረና ቀድሞ የተነገረው ነገር ግን ማንም ከቁም ነገር ያልቆጠረው የወያኔዎች ሤራ ተግባር ላይ ሲውል ልቅሶውና ዋይታው በረታ፡፡ እንደተባለውም ሀገር ድምጥማጧ ጠፋ፡፡ አይሆንም የተባለው ሆነ፤ ይሆናል የተባለው ሣይሆን ቀረ፡፡ የዘረኝነት ክርፋቱ፣ የሞራል ዝቅጠቱ፣ የሃይማኖት መላላቱና ለአምልኮተ ንዋይ መንበርከኩ፣ የሙስና መንሠራፋቱ፣ ከሞላ ጎደል ሁሉም የሀገሪቱ ቋሚና ተንቀሣቃሽ አንጠራ ሀብት በሕወሓት ቁጥጥር ሥር መግባቱ፣ በማይማንና ደናቁርት ዘረኞች መገዛቱ፣ በኢትዮጵያዊነት ሰበብ ስቃይና እንግልቱ አለቅጥ መስፋፋቱ፣ በትምህርት ረገድ ከሞላ ጎደል በሁሉም የትምህርት መስክ ቁልቁል መንጎዱና የበታችነት ስሜት የሚያስከትለውን አእምሯዊ ምስቅልቅል ለመሸፈን የውሸት ዲግሪ በመንግሥት መሪዎች ዘንድ ሣይቀር እንደዘመናዊ ፋሽን መዘውተሩ፣ ውሸትና ቅጥፈት የመንግሥት መርህ ሆኖ ሥራ ላይ መዋሉ፣ አንድን የኅብረተሰብ ክፍል ለይቶ ከማንኛውም የሀገሪቱ የጥቅም ቦታዎች ማስወገድ ብቻ ሣይሆን ዘሩም እንዳይተርፍ በያለበት ማሳደዱና መቀጥቀጡ ወዘተ. በሀገራችን በግልጽ ታዬ፡፡ የሀገሬን ውድመት መጀመሪያውን ያሣየኝ የኢትዮጵያ አምላክ አሁን ደግሞ የጠላቶቿን የመጨረሻ አይወድቁ አወዳደቅ ሊያሣየኝ ዳር ዳር እያለ መሆኑን ስድስተኛው የስሜት ሕዋሴ ሹክ አለኝና ዛሬ ተመለስኩ፡፡ የሰቀልኩትን ብዕርም አቧራውን አራግፌ ይሄውና አሃዱ አልኩ፤ ጥፋት አይመስለኝም፡፡

“መካሪ የሌለው ንጉሥ ካለአንድ ዓመት አይነግሥ” የሚለው ብሂል ትርጉም ካጣ ሰነበተ፡፡ ይሄውና 24 ዓመትም ቢሆን መንገሥ ተችሏልና፡፡ 24 ብቻም አይደለም፡፡ በጥቅሉ 40 መሆኑ ነው፡፡ አሥራ አንድም ይሁኑ በመቶ ሺዎችም ይቆጠሩ ዋናው የመከራችን ድግስ ከተጠነሰሰባት ከዚያች ከቀኖች ሁሉ ተለይታ ልትረግም ከሚገባት የካቲት 11/67 ጀምረን በነሱ የቅዠት ዓላማ ሥር ወድቀናልና የሰቆቃ ዘመናችን 40 ዓመቱን ደፈነ፡፡ የዚህ ዘመን አበቅቴም ያለቀ ይመስለኛል – ልንገባባቸው ከማያስፈልጉን ብዙ ነገሮች አንጻርም ቢሆን፡፡

እንግዲህ የወያኔ ዘመን አልቋል የሚለውን በጋራ የምንስማማበት ሃሳብ እንዲሆን ምኞቴ መሆኑን ልግለጽና ወደ ጀመርኩት የጸሎት ጉዳይ ወደሚያመራኝ መንደርደሪያ ልግባ፡፡

አሁን በዓለም ዙሪያ እየሆነ ያለውን የአረመኔነት ተግባር ሁሉ ተመለከትኩ፡፡ በተለይም ሰሞነኛ ስለሆነው ዘግናኝ የአይሲሎች ጉዳይ ሲነሣ የማይደመም ከንፈሩንም የማይነክስ የለም፡፡ በበኩሌ የሰው ልጅ በሰው ልጅ ላይ የሚፈጽማቸው እነዚህን መሰል አሰቃቂ ግፎች ከዘመን መጨረሻ ትንቢቶች ጋር (endtime predictions) ይያያዙ እንደሆን በሚል ጥቂት ድረገፃዊ መዛግብትን ለማገላበጥ ሞክሬያለሁ፡፡ ዝርዝሩ በርካታ ስለሚሆን ወደዚያ መግባት አያስፈልግም፡፡ ኹነቶችን  መመርመርና የዘመን አሻራዎችን በማጤን የትኛው ከየትኛው በምን እንደሚለይ፣ የትኛው ድርጊት ለየትኛው ቀዳሚ ትንቢት ጠቋሚ ሊሆን እንደሚችል ማስተዋሉ ግን መጥፎ አይመስለኝም፡፡

የክፋት ድርጊቶች አፈጻጸማቸው ቢለያይም ዓላማና ግባቸው ግን ተመሣሣይ ነው፡፡ አንዱ ወገን ከሃይማታኖዊ ቀኖናው ተነስቶ ሊፈጽመው ይችላል፤ ሌላኛው ወገን ከአለማወቅ ተነስቶ ሊፈጽማቸው ይችላል፤ አንደኛው በጠባብነት የዘረኝነት መነጽር አጮልቆ እየተመለከተ ከራሱ ዘር ውጪ ያለውንም ሁሉ እንደጠላትና የደኅንነት ሥጋት እየቆጠረ ከዚያ አኳያ ተነስቶ ሊፈጽማቸው ይችላል፤ ሌላው ደግሞ ከፍርሀት ተነስቶ ሊያከናውናቸው ይችላል፤ አንዱ ከኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ኅልውና ሥጋት አንጻር በመነሣት ሊፈጽማቸው ይችላል፤ ሌላው ከበታችነት ስሜት ተነስቶ አገኘሁት ብሎ የሚያስበውን ጊዜ ወለድ ዕድል ላለማጣት ሲል ሊፈጽማቸው ይችላል፡፡ በ“የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው” ባላዊ ፍልስፍና ከተመለከትነው በምንም ምክንያት ይፈጽማቸው ክፋቱ ግን ያው ክፋት ነው፡፡ የኃጢኣት ትንሽና ትልቅ ደግሞ የለውም፡፡ የወንጀልም እንዲሁ ይመስለኛል፡፡ ቅጣቱ ይለያይ እንጂ ኃጢኣት ኃጢኣት ነው፤ ወንጀልም ወንጀል፡፡ ‹አነሳም አንጠለጠለም ያው ተሸከመ ነው›፡፡

ወደ አፈጻጸሙ ስንመጣ ለምሣሌ አይስሎች ከአምልኮታቸው አንጻርም ሊሆን ይችላል – የክፋት ድርጊታቸውን የሚፈጽሙት የሚገድሏቸውን ሰዎች ብርቱካናማ ልብስ አልብሰው በማንበርከክ ጥቁር ጭምብል በለበሰ አራጅ አንገታቸውን በመቅላት ነው፡፡ እነሱንና ፈጣሪያችን ነው የሚሉትን ኃይል የሚያስደስቱበት መንገድ ያ ነው ማለት ነው፡፡ ምክንታዊነት፣ ተጠየቃዊነት ቅብጥርስ እዚህ ላይ አይሠራም፡፡ እዚህ መታወስ ያለበት የሚመስለኝ ተገዳዮች ንጹሓን ዜጎች መሆን አለባቸው፤ ወንጀለኞች ከሆኑ ገዳዮች ትኩረትንና ተፈሪነትን አያገኙም፡፡ በአገዳደሉ ብንከፋም መገደሉ የሚያስደስተን እንኖራለንና፡፡

በተመሣሣይ ሁኔታ በሀገራችን የአይስሊዝምን የአረመኔነት እምነት አቀንቃኞችን – ወያኔዎችን ማለቴ ነው –  ብንመለከት ክፋቱና የክፋቱ የሩቅ ግብ አንድ ነው፡፡ አንድን ዓላማ ከግብ ለማድረስ የኃይል እርምጃን በመውሰድ መፈራትና ፍርሀትን የርዕዮተ ዓለም ማራመጃ ማድረግ ነው፡፡ ወያኔዎችም ሆኑ ቢጤዎቻቸው የሚያደርጉት ነገር መልካም እንዳልሆነ እነሱ ራሳቸውም ያውቁታል፡፡ ግን ሌላ መንገድ እንደማያዋጣቸው ደግሞ እነሱም እኛም እንረዳለን፡፡ አይስሎች በማስፈራራት ጭራቅ መስለው መታየትን የወደዱት ፈልገውት ሣይሆን የአስተሳሰብ ትንሽነት(ድውይነትም ቢባል ያስኬዳል) የሚፈጥረውን የበታችነት ስሜት ለማስወገድ ጭካኔን እንደሀሽሽ በመጠቀም ብዙኃንን ማርበድበድና ሥጋን ብቻ ሣይሆን ነፍስንም ጭምር በነሱ ሥር ለማንበርከክ መሞከር ነው፡፡ ሠላሣ ምናምን ሺህ የኢስላሚክ ካሊፌት ተብዬዎቹ ጦር በብዙ ሚሊዮን ለሚቆጠረው  የዓለም ሀገሮች ጦር ሠራዊት ቢከፋፈል ለቁርስነት እንኳን ፈጽሞ የሚታሰብ አይደለም፡፡ ምንም ያህል ቁጥር ይኑረው – ወያኔ ይተማመንበታል የሚባለው የሕወሓት ዘውድ ጠባቂ ጦር ሠራዊት ለጭቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቢከፋፈል – ለአያ ፍርሀት ምሥጋና ይግባው እንጂ – ለቁርስ ቀርቶ ለአፍ ማሟሻ መክሰስ ቢጤ እንኳን አይሆንም፡፡ ይህን የወያኔ ውስጣዊ የአመለካከት/የአስተሳሰብ ትንሽነትና የጥቂትነት ስሜት እስከተቻለ ድረስ በዘለቄታ ለማቆየት ፍርሀትን ከማንገሥ ውጪ ያለው አማራጭ እስከዚህም ነው፡፡ በፍቅር ሁሉን አስተሳስረው እንዳይገዙ ከጉልበትና ከእልህ ውጪ ዕውቀትና ጥበብ የላቸውም፡፡ ምርጫ ከተባለ ደግሞ መቼም ቢሆን ገዳይህን ይግዛኝ ብለህ አትመርጥምና አያስኬዳቸውም፡፡ ያላቸው ብቸኛ መንገድ ምርጫን በማጭበርበር “የዓለምን ማኅበረሰብ” ማታለል – የውስጥ ተቃውሞን ደግሞ በበረገጉና በባተቱ ቁጥር ንጹሓን ዜጎችን ቁምስቅላቸውን በማሣየት በእኔን ያዬህ ተቀጣ አፍን ማዘጋት ነው፡፡ ለነገሩ በነሱ አይፈረድም፡፡ አያድርስ ነው ማለት፡፡ በታሪክ ዕብደትና ቅብጠት የተነሣ እነዚህ ሰዎች ለዚህ ገነት መሣይ ሲዖል አንዴውኑ ተዳርገዋል፡፡ የማርያም በር ደግሞ አይፈልጉም፤ እንደመጽሐፉ ቃል ልባቸው ወደ ድንጋይነት ተለውጧልና ምናልባት ሲወድቁ እንጂ ከመውደቃቸው በፊት ጊዜና አስተዋይ ልቦና አግኝተው ቆም ብለው የሚያስቡ አይመስለኝም፡፡ ሁኔታው ያሳዝናል፤ እነሱም ያሳዝናሉ፡፡ ሰፊው የኢትዮጵያ ሕዝብም ለመሪነት ቀርቶ ለተመሪነትም በማይመጥኑ በነዚህ ድንጋዮች ከሁለት አሠርት ዓመታት በላይ እንደሰም ቀልጦ እንደብረትም ተቀጥቅጦ መገዛቱ የሚገርም ክስተት ነው፡፡ ሲያስቡት ውለው ሲያስቡት ቢያድሩ የዚህ ታሪካዊ ቀመር ለማንም የሚከሰትለት አይመስለኝም፡፡ ቧልታይ ድንቃይ የሚመስል ግን የሚመርና የሚዘገንን ኤዞፓዊ ቀልድ ነው፡፡ኢትዮጵያን የመሰለች የድንቅ ታሪክ ባለቤት በነዚህ “ልጆቿ” እጅ ስትወድቅ ይታያችሁ፡፡ እነአክሊሉ ሀ/ወልድና እነራስ አሉላ በወጡበት ማኅጸን እነልደቱ አያሌውና መለስ ዜናዊ ሲወጡበት ይታያችሁ፡፡  ለዚቅ ያህል “የቆዬ ሰው ከሚስቱ ይወልዳል” ማለት አሁን ነው፡፡ “ዘመነ ግርምቢጥ ውሻ ወደግጦሽ፣ አህያ ወደሊጥ” – ነፍስ ይማር ገሞራው፡፡

በገደምዳሜም ቢሆን ለማለት የፈለግሁትን ሳትረዱልኝ የምትቀሩ አይመስለኝም፡፡ ማለት የፈለግሁት ባጭሩ “ወያኔዎችና ኢስላሚክ ካሊፌቶች የሚባሉት የአንድ ሣንቲም ሁለት ገጽታዎች ናቸው” ነው፡፡ ቁጭ ብለው የሰቀሉት ቆሞ ማውረድ እያቃተ ኢትዮጵያም ሆነች የተቀረው ዓለም በጥቂት ሽፍቶችና ወሮበሎች እየታመሰ የመገኘቱ ዕንቆቅልሽ አስገራሚ ሆኗል፡፡ ወያኔዎች ከአሥራ አንድ ዘልለው ያልጠገቡ ጮርቃ ሕጻናትና ከአምስት ጥግንግን ጠበንጃዎች ተነስተው ይሄውና በሀገራችን ታሪክ ላይ መቼም ሊፋቅ የማይችል ጥቁር ጠባሳ አሣርፈው ወደማይቀርላቸው የታሪክ መዝገብ ሊሠተሩ ጫፍ ላይ ደርሰዋል – እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ፡፡ በዬዓለም ማዕዘናቱ የፕላኔታችን ራስ ምታት የሆኑ ቁጥር ሥፍር የሌላቸው አሸባሪ ቡድኖችም ለዚህ ወይ ለዚያ ድብቅ ዓላማ ማስፈጸሚያ ሲባል በተወሰኑ የዓለም ኃያላን መንግሥታት ወይም በኅቡዓን የመንግሥታት ተቆጣጣሪዎች (cabals) አማካይነት ይፈጠሩና በወርድና ቁመት – እንደዝንጀሮ ልጅ ማለት ነው – ጠንከር የማለት ስሜት ሲሰማቸው ከተሠሩበት ዓላማ ይወጡና ፈጣሪዎቻቸውን ሣይቀር ክፉኛ መገዳደር ይጀምራሉ፡፡ በዕንቁላሉ ያልተቀጣ ልጅ ደግሞ አንዴ መረን ከለቀቀ በኋላ መመለስ እንደማይቻል ከኛ በላይ አዋቂ ሊኖር አይችልም፤ በመጨረሻው ከባድ የሕይወት ዋጋ ክፍያ ተምረነዋል፡፡ ከህዋስ ደረጃቸው በመውጣት ከጎሬያቸው አፈትልከው በአሁኑ ወቅት ዓለምን እያመሱ ያሉት ወያኔን መሰል የሥውር ድርጅቶቹ ተላላኪዎች ጊዜያቸውን በደንብ እየተጠቀሙበት ይመስላል፡፡ ጊዜ ወሳኝ ነው፡፡ ነገ የነሱ እንደማትሆን ትናንት የነሱ ያልነበረ መሆኑን በማስታወስ የሚረዱት ሃቅ ነውና በጊዜያቸው ያሻቸውን ያደርጋሉ፡፡

የኞቹ በዘግናኝ ጭካኔያቸው ሀገራዊ ፍርሀትን አንግሠው 90 ሚሊዮን ሕዝብ ፀጥ ረጭ ሲያደርጉ እነዚያኞቹ ደግሞ የጋዜጠኞችንና የረድኤት ሠራተኞችን አንገት እየቀነጠሱ ዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ በፍርሀት ማራድ ነው – በፍርሀት የማራድ አዲስ ፖለቲካ፡፡ መድሓኒቱ እርግጥ ነው  አለመፍራት ነው፡፡ ግን እንዴት ይቻላል? ፍርሀትን ማስወገድ ትልቁ የሰው ልጅ ተግዳሮት ይመስለኛል፡፡ አለመፍራት ብቻም አይደለም የኞችን በተመለከተ ልዩነቶችን አስወግዶ እጅ ለእጅ በመያያዝ በኅብረት ታግሎ የነዚህን አይሲሊስት ወያኔዎች አደጋ ማስወገድም ቀላል ነበረ፡፡ አሁንም ቢሆን ዘዴያቸውን መረዳትና ከናካቴው ለይቶልን ሳንጠፋ መንቃት ይገባል ፡፡ ግን እንዴት እንንቃ? አስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ነው የምንገኘው፡፡ ንቃቃት በመፍጠር የተካኑ ናቸው፤ ሌላ ችሎታ የሌላቸው እስኪመስሉ ድረስ በተቃዋሚዎቻቸው መካከል ልዩነትን መፍጠርና እርስ በርስ ማባላት ልዩ ችሎታቸው ነው፡፡ ጤናማ ሰው ተኝቶ ያድራል፡፡ እነሱ ግን ተንኮል ሲጎነጉኑና ሸር ሲጠነስሱ ስለሚያድሩ በዐይናቸው እንቅልፍ የሚዞር አይመስልም፤ ካባሊስቶች በተፈጥሯቸው አደገኞች ናቸው፡፡ በቁጥር አናሳነታቸው በሚፈጥርባቸው ልዩ ሥነ ልቦናዊ ጫና ምክንያት በፍርሀት ተውጠው ስለሚኖሩ የገዛ ጥላቸውን ሣይቀር ይጠራጠሩታል፡፡ ፍርሀት መጥፎ በሽታ ነው፡፡ ከነተረቱ የፈሪ ዱላ ዘጠኝ ነው ይባላል፡፡ የጀግና ግን አንድ ነው – ያንንም አዘውትሮ አይጠቀምበትም – እውነተኛ ጀግና ታጋሽና ይቅር ባይ ሊሆን ይገባዋልና፡፡ የፈሪ ዱላ ግን አያድርስ ነው – መቆሚያ መቀመጫ ነው የሚያሣጣ – ልክ አንድን በሬ ያሸነፈች በለስ የቀናት ላም ዓይነት፡፡ ወያኔን መሰል ካባሊስቶች ሁል ጊዜ በፍርሀትና በድንጋጤ ውስጥ ተሸብበው ስለሚኖሩ ሁሉንም ነገር ወደሥጋት የመለወጥ ባሕርያቸው የጎላ ነው፡፡ በዚያም ምክንያት ዱላ ከእጃቸው አይለይም፤ ያገኙትንና ከነሱ የተለዬ የሚመስላቸውን አለርህራሄ ይዠልጡታል፡፡ ሕይወታቸው እንደዚህ የተመሰቃቀለ ነው፡፡ የዚህ ዓይነት የሰቀቀን ኑሮ ደግሞ ባፍንጫ ይውጣ የሚባል ነው፡፡ አሁን ወያኔዎች ከሥልጣን ሲወርዱ ሃያ አራት ዓመት እንደገዙ ሊነገርላቸው ይሆናል – ሀገር ተገዝቶ ተሙቶ፡፡ ድንቄም፡፡ ዜጎችን ማጋጨትና ማናጨት፣ ዕረፍት በሌለው ሁኔታ ሀገርን ሲሸጡና ሲለውጡ መባዠት፣ በማን መጣብኝ የሠርክ ድንጋጤ በመባነን ሌት ተቀን መቃዠት … ሀገርን እንደማስተዳደር የሚቆጠር ከሆነ – እውነት ነው – ወያኔ ኢትዮጵያን 24 ዓመታትን ገዝቷል፡፡ ያቆየንና ታሪክን ለማንበብ ያብቃን፡፡

ቦኮ ሃራም፣ አልቃኢዳ፣ ታሊባን፣ አልሻባብ፣ አይስል፣ ሎርድስ ሬዚስታንስ፣ ሕወሓት፣ ወዘተ. አንድ ናቸው ብለናል፡፡ አንድ ሰው በጥይትም ገደልከው በጩቤም አረድከው ውጤቱ ያው ነፍስን ከሥጋ መለየት እስከሆነ ድረስ ለኔ ብዙም ለውጥ የለውም፡፡ አፅንዖት ልሰጠው የሚገባኝ አንድ ነገር ደግሞ አለ፡- ሕወሓት እንዲያውም አይስልን በዋናነት ጨምሮ ከሌሎች አሸባሪዎች በተለዬ መልኩ የባሰ አረመኔ ነው – በዚያ ላይ መንግሥታዊ ዕውቅናና መንግሥታዊ ተቋምነት ተደርቦበት እንግዲህ የጭካኔው ልክ ይታያችሁ፡፡ የወያኔን ዓለም አቀፍ ምስልና የወዳጆቹን ቅባት(ሬቶሪክ) ተውት – የዐይጥ ምሥክር ድምቢጥ ነውና፡፡ እናም የጭካኔያቸውን ደረጃ ስናይ በግልጽ እንደሚስተዋለው ሌሎቹ በመግደል እንጂ በማሰቃየት የወያኔን ያህል አይደሰቱም ባይ ነኝ – የንጽጽር ጉዳይ ነው – የሎጂክም፡፡ ሕወሓት ግን የሚጠላውን መግደል ብቻ ሣይሆን ከመግደሉ በፊትና በኋላም ማሰቃየቱና ማንገላታቱ እጅግ ያስደስተዋል – ሬሣን በማንገላታት የምትደሰት እኔ እስከማውቀው ድረስ ድመት ብቻ ትመስለኝ ነበር፡፡ ይህ የወያኔ ‹ሳዲስት› ጠባይ ተብሎ ተብሎ ያለቀ ጉዳይ ነው፡፡ ሳስበው ከነሱ ጋር ተደምረን ዘጠና ሚሊዮን መባላችን በጣም ያንገበግበኛል፡፡ ከሰው ጋር ብቆጠር ያለ ነው፤ እንዴት ከዐውሬ ጋር እደመራለሁ?

በመሠረቱ ጭካኔ ዱሮም ነበር፤ አሁንም አለ፡፡ ደረጃው ግን እስከዚህን ድረስ ሲለያይ የሰውን ልጅ የሰው ልጅነት እንድንጠራጠር ያስገድደናል፡፡ ልብ በል፣ አንድን በወንጀል የሚጠረጠርንም ይሁን ንጹሕን ዜጋ ብርሃን የማይታይበት ጉድጓድ ውስጥ ጥለህ በዘር ጥላቻ የተመረዘ አጸያፊ ስድብ እየሰደብከውና እየደበደብከው፣ እየረገጥከውና ምራቅህን እየተፋህበት – ድምጽ እንዳያሰማ፣ እንዳይገላበጥ፣ ሰውነቱን እንዳያክ፣ እንዲራብና እንዲጠማ … አድርገህ አበስብሰህ መግደል ምን ማለት ነው? የየትኛው ሰማይ ወይም የየትኛው ፕላኔትስ ህግ ነው? የየትኛውስ ሃይማኖት ቀኖናና ቃለ ዐዋዲ ይሆን? የእነዚህ ሕወሓቶች ጭካኔ ታዲያ ከማንኛውም ምድራዊ አረመኔ ተግባርም ሆነ ከጋራ አባታቸው ከሰይጣን ጭካኔ አይበልጥምን? ማሰርስ ቢፈልጉ ለምን በአግባቡ አያስሩም? መግደልስ ቢፈልጉ ለምን በአግባቡና በክብር አይገድሉም? እነሱስ ከሰው አልተፈጠሩምን? ሰብኣዊ  ኅሊናቸውን እስከዚህን አሳዛኝ ደረጃ ያሣወረውን የአረመኔነት ባሕርይ ከየት ወረሱት እንበል? ዘወትርና ከጥንት በረሃ ሳሉ ጀምሮ የሚያስጨንቀኝ ይህ ጥያቄ ነው፡፡ ጭካኔያቸው እዚህ ደረጃ ላይ የደረሰው ማንና እንዴትስ ቢበድላቸው ይሆን? ተበድለውስ ቢሆን በደል በይቅር ባይነትና በሆደ ሰፊነት እንጂ በሚከፋ በደል ይመለሳል ወይ? ዐመፅ ዐመፅን እንደሚወልድ እንዴት ዘነጉት? ተበድያለሁ ብሎ በረሃ የገባና የታገለ ሰው እንዴት መፈጠርን የሚያስረግም ግፍና በደል የገዛ ወገኑ መሆኑን አምኖ ሊቀበለውና ሊንከባከበውም በሚገባ ሰብኣዊ ፍጡር ላይ ይፈጽማል? ለዕርቅና ለግልግል በሚያስቸግር መልኩ ለምን ይህን ያህል ጨከኑ? ምሥጢሩን የምታውቁ አካፍሉን፡፡ ብርቱ ጸሎት ግን ያስፈልገናል! የገባ ገብቶብናል፡፡ አንዲትን ነፍሰ ጡር የፈለግኸውን ያህል ብትጠላት እንዴት ሆዷን ረግጠህ ለስቃይና ለውርጃ ትዳርጋታለህ? እነሱስ በዚያ ማኅጸን አይደለምን የወጡት? ሰይጣን ራሱም እንዲህ ያለ ነውር የሚፈጽም አይመስለኝም፡፡መጥፎ ድርጊት ዳር ድንበር ሊኖረው ይገባል፡፡ በወጣትነት ዘመኔ ያየሁት “The Evil that Men Do”የሚል ፊልም ነበር፡፡ የነዚህ ከዚያም የከፋ ነው፡፡ ወደር የሚገኝላቸው አይመስለኝም፡፡ እግዚአብሔር ምሕረቱን ይላክላቸው፡፡ በጽኑ ታመዋልና፡፡ …

 

ይታየኛል፡፡ ደግሞም በገሃድ የሚታየውን እውነት በግልጽ በመናገሬ አሟረትህ አትበሉኝ ወይም እንዳትሉኝ፡፡ እንደገና ደግሞም ዱሮ ብዙ ነገሮችን ለፍልፌ ሳበቃ ከሞላ ጎደል አንዱም ተግባራዊ ሣይሆን አለመቅረቱን አስታውሱልኝ – ምላሴ ጥቁር ነው ማለት አልፈልግም፤ ባይሆን በወደድኩ እንጂ ልበል፡፡

በስደት ከምኖርበት ሀገር ሆኜ ስለሀገሬ እንደምሰማው ከሆነ ኢትዮጵያ ውስጥ እየተንተከተከ ያለው ድፍድፍ መፈንጃው ተቃርቧል፡፡ ይህ ሕወሓት የዘለለው ጠላ ምርጊቱን ፈንቅሎ ወይም ጋኑን ሰብሮ ሊወጣ የቀረው ጊዜ በጣም ኢምንት ነው፡፡ ሰኞን አለመሆን እንጂ ከሆኑ በኋላ መቆጨት ትርፍ የለውም፡፡ ትልቅ ሰው በሀገር ውስጥ የለም፡፡ ሜሮን ጌትነት በግጥሟ እንደጠቆመችው ዋርካዎች ተቆራርጠዋል፤ ሰንሰልና ሣማ ብቻ ነው እዚያና እዚህ ጉች ጉች ብሎ አገር ምድሩን አጥለቅልቆት የሚገኝ፡፡ ምራቅ የዋጡ አስታራቂ ሽማግሌዎችንና ተደማጭ ሃይማኖታዊና ማኅበራዊ ስብዕናዎችን ወያኔዎች በሥልት ጨርሰዋቸዋል፤ ከየዘሩ እየለቀሙ በአነር አስበልተዋቸዋል፡፡ ጥቂት እርሾ ቢኖሩም እንኳን በፍርሀት ተሸማቀው – በዘራቸው ማንነት ወይም በሌላ ምክንያት አንገታቸውን ደፍተው – የዕለት ተለት ሕይወታቸውን እንደምንም ከመምራት ባሻገር የሚፈይዱት ነገር እንዳይኖር ተደርገው ተሸመድምደዋልና አንድ ነገር ቢነሣ የሚያስታርቅ ተሰሚ ሰው አለን ማለት ይቸግረኛል፡፡ ሀብትም ሆነ ዝናና ክብር የምታገኘው ከወያኔ ጋር ስትሞዳሞድና መስህ ስታጨበጭብ በመሆኑ ከነሱ ጋር ያልተጎናበሰ የኅሊናው ሰው ለማግኘት በቀላሉ አትችልም – ታዋቂ ስፖርተኛም ሁን ነጋዴ ወይም የአርት ሰው በቀጥታም ይሁን በተዛዋሪ መርፌያቸውን ይወጉህና ከራስህም ከሀገርህም ከሕዝብህም ሣትሆን ከሁሉም ጋር ዐይንና ናጫ እንድትሆንና እንትን የነካው እንጨት ሆነህ እንድትቀር ያደርጉሃል፡፡ ‹ሳዲስቶቹ›(ሀዘን አምላኪዎች?) የሚያነካኩህ  ብዙ ዘዴ አላቸው፡፡ ለአብነት ያህልም የሚዲያ ሽፋን ለማግኘት ስትል የነሱን ቱሪናፋ በመናጆነት የምታናፍስበት ሁኔታ አለ – ለጉዳይህ ኤፍ ኤም ሬዲዮ ብትከራያቸው፡፡ ወያኔ ብዙ ሰው አሳጥቶናል – ተፈጥሯዊ የተለዋዋጭነትና የአሽቃባጭነት ባሕርይ ሲጨመርበት ደግሞ ነገሩ ይከፋል – እንጂ ገነት ዘውዴና ሙሉጌታ አሥራተ ካሣ፣ ዳዊት ዮሐንስና አሰፋ ብሩ፣ ክፍሌ ወዳጆና ብርሃ ዳምጤ ጭንቅላት በሰም ካስት ይደረግ ይመስል በየጊዜው እየተለዋወጡ ከሰውነት ተራ ባልወጡ ነበር፡፡

ለማንኛውም የምንፈራው ነገር – ‹ቢቀሰቀስ› የሚል ባዶ ተስፋ እንኳን የለኝም – ለጊዜው ባለኝ ግንዛቤ  ‹ሲቀሰቀስ› ነው ማለት የምፈልገው – እናም የሚፈራው ማኅበራዊ ቀውስ ሲቀሰቀስ ለዘር የሚተርፍ ሰው የሚኖር አይመስለኝም፡፡ ከራስ በላይ ንፋስ ብሎ ሀገራችንን ለማፈራረስ ቆርጦ የተነሣው ሕወሓትና የውጭ ስፖንሰሮቹ የዘረጉት ወያኔዊ አጥፍቶ የመጥፋት ሤራ የያዘላቸው ይመስላል፡፡ በ40 ዓመታት ሊበርድላቸው ያልቻለው የቂምና የጥላቻ ቋጠሮ እየባሰባቸው ሄዶ አሁን አሁን ከናካቴው እንዳበደ ውሻ የሚሠሩትን አጥተው ዕልቂትን እየጋበዙ ይገኛሉ፡፡ ትዕቢትና ዕብሪታቸው ለከት አጥቶ ዜጎችን ከጉንዳንና ከዝምብ ባለፈ እንደሰው መቁጠር አልፈለጉም፡፡ እንደተወለዱ ያረጁት እነዚህ ወያኔዎች የሀገራዊ ማንነት ስሜትም ሆነ ሰብኣዊነት ስለሌላቸው ምንም ነገር ቢፈነዳ ጉዳያቸው አይመስልም፡፡ ዓላማቸውና የመጨረሻ ዕቅዳቸው ሀገሪቱን የደም አላባ ውስጥ ዘፍቆ ወደሚቃዡባት የተስፋዋ ምድር ትግራይ-ትግሪኝ ለመንጎድ ያቆበቆቡ ይመስላሉ – እዚህ የሚፈነዳው ሽንት ቤት ጎረቤት ድረስ ሽታው ተዛምቶ መላ አካባቢውን እንደማይበክል በምን እንዳረጋገጡ አላውቅም፡፡ የዕውቀት ድሆች ስለሆኑ ከየሚያስቡት ዕውር ድምብራዊ ቅዠት በስተኋላ ሊከሰት የሚችለውን መለኮታዊም በሉት ሰብኣዊ የአጸፋ ድርጊት ሊያስቡ አይችሉም ወይም አይፈልጉም፤ ምክንያቱም በድፍን ቅልነት ሊመሰል የሚችል ባዶ ጭንቅላታቸው በጥጋብና በዕብሪት ተወጥሯልና፡፡ ዕውቀታቸው – ዕውቀት ከተባለ – መብላት፣ መጠጣትና መራባት የሚያስችል እንስሳዊ የደመ ነፍስ ዕውቀት ነው – ከተንኮል በተጓዳኝ፡፡ ለነገሩ ከእረኝነት ተነስቶ ጄኔራል ከሆነ ሰው ብዙም የሚጠበቅ ነገር የለም – ብቻ አልታደልንም፡፡ ትዕቢትና ዕብሪት ደግሞ ወደ ውድቀት እንደሚመሩ በፍጹም አያውቁም፤ ከታሪክም መማር ዕርማቸው ነው – ለነሱ ታሪክ ማለት ጠግቦ ማደር ነው፡፡ ወያኔ ከእግዜሩም በላይ ነው – ይህንንም “እንኳንስ ከአመሪካ ከመንግሥተ ሰማይም እናስመጣሃለን!” ሲል አንዱ ጥጋበኛ ወያኔ ለሰሎሞን ክፍሌ በግልጽ ባስተላለፈው ዛቻ መረዳት ይቻላል – ድፍን ቅልነት ከዚህ በላይ የለም፡፡ መታወቅ ያለበት ነገር ታዲያ በትምክህት የታወረ ስብዕና መጨረሻው ዕልቂት ብቻ መሆኑ ነው፡፡ ችግሩ ደግሞ ሟች ይዞ ይሞታልና ለጠገበ የሚላክ መቅሰፍት የተራበንም መጨመሩ ነው፡፡

ስለዚህ ውድ ወገኖቼ!

ለሀገራችሁ ነፃነት ስትሉ በበረሃና በዱር በገደል የምትንከራተቱና የምትዋደቁ [ካላችሁ] እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን፡፡ በበርካታ ቡድኖች ተበጣጥቆ ይህን የኢትዮጵያ ኢስላሚክ ካሊፌት(አጠራሬ ሃይማኖታዊ አንድምታ እንዳይዝብኝ) አሸንፋለሁ ማለት ፍጹም ዘበት ነው፡፡ ስለዚህ ምንም ነገር ከመጀመራችሁ በፊት ኅብረትና ውህደት ፍጠሩ፤ በሌለች ሀገርና በሌለ ሥልጣን በባዶ መሬት አትወዛገቡ፣ አትጨራረሱም፡፡ ሥልጣኑን ከሕዝብ ለመቀበል በቀናነት ትጉ እንጂ መሠሪ ተንኮል በልባችሁ አሸምቃችሁ ወደ ትግል አትግቡ – መጨረሻው ኪሣራ ነውና፡፡ ከወያኔና ከደርግ ብዙ መማር ይቻላል፡፡ “የሞኝ እንትን ካለአንድ ቀን አይበልጥ” እያለ በሥነ ቃሉ በሚተርት ሕዝብ መሀል የልብን መሥራት በመጨረሻው ወደ ጥልቅ እንጦርጦስ እንዴት እንደሚከት ከዐፄው ጀምራችሁ በተከታታይ የመጡትን የበረከተ-እርግማን ተጋሪዎች ዕጣ ፋንታ በማጠየን መረዳት ይገባችኋል፡፡ ስለሆነም በአንድ የዕዝ ሰንሰለት ውስጥ ገብታችሁ በጋራ የጋራ ሀገር ባለቤት የምትሆኑበትን ሁኔታ አሁኑኑ አመቻቹ እንጂ በየጎጡ መሽጌ ዘመነ መሣፍንትን እደግማለሁ ብትሉ ሕዝ ነቅቷልና አንቅሮ ይተፋችኋል፤ የሕዝን የልብ ትርታ አድምጡ – ለምሣሌ ዴምሃት የሚባለው ድርጅት በኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማ መዋቡ ግሩም ሆኖ መሀሉ ላይ የአክሱምን ሀውልት ማኖሩ ተገቢ አይመስለኝም፤ እንደግል ተቋም ዓርማነት ከሆነ አላውቅም፡፡

አሁን ጊዜ የላችሁም፡፡ ተጨማሪ ደቂቃ ባጠፋችሁ ቁጥር አይስሎቹ በሤራ ጉንጎና ቀላል ስላልሆኑ እየጠነከሩ ይሄዳሉ – ከጎናቸው የተሠለፉ ኃይሎችም ቀላል አይደሉም – ፈጣሪ ለራሳቸው የቤት ሥራ ካልሰጠልን በቀላሉ የሚተውን አይደሉም፤ ኢትዮጵያዊነት ልዩ ብሔራዊ ኩራት የዓለምን ሰላም የሚያደፈርስ ይመስል እንደወገብ ቅማ ጠምደው ከያዙን ብዙ ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ለነሱ አደግዳጊ ያልሆነ መንግሥት አይፈልጉም – በየሀገራቱ ይህን የማስገበር ሥርዓት ይተክላሉ – እምቢ የሚልን ይገድላሉ/ያስገድላሉ፡፡ ስለሆነም ከዚህ ነጥብ አንጻር ተጠንቀቁ! ሕወሓቶች መቼም ቢሆን ብቻቸውን ሆነው ለድል በቅተው አያውቁም፡፡ የኢትዮጵያ እንደሀገር በራሷ እግር መሄድ እንደ እግር እሳት የሚያንገበግባቸው ከሩቅም ከቅርብም ብዙዎች አሉና ትግላችን መራራ መሆኑን ተገነዘቡ፡፡ ወያኔ ሞተ ሲባል እንደባብ አፈር እየላሰ የሚነሳበት ምክንያት ሌላ ሣይሆን ይኼው መርዘኛ ጭራውን ከነዚህ የሀገራችን መሠሪ ጠላቶች ጋር በማስተሳሰሩ ነው፤ የከንፈር ሽንገላውንና የዐዞ ዕንባውን ብዙም አትመኑት – የአዛኝ ቅቤ አንጓችነት ከጥንትም ነበርና እውን በማይሆን ከንቱ ተስፋ አትደለሉ፡፡ ፈጣሪያችን ትቶ አይተወንምና እናንተ ተስማምታችሁ ቀጥሉ፡፡ ስምምነት ከሌላችሁ ግን ፈጣሪ ከእናንተ ጋር አያብርም፤ ፈጣሪ ከሁለት ዕኩያን ለአንዱ አያዳላም፤ ንጹሕ ልብስን ለብሶ በቆሻሻ ቱቦ ውስጥ ማን ሊያልፍ ይሞክራል? ስለዚህ የርሱን ድጋፍ ለማግኘት ከወያኔ የተሻለ የጠራ ስብዕናና ሕዝባዊ ወገንተኝነት ሊኖራችሁ ይገባል እላለሁ፡፡ ደግሞም ለለውጥ መነሣታችሁን ከራሳችሁም በበለጠ ፈጣሪን ለማሳመን ሞክሩ፤ ያኔ በርግጠኝነት ይረዳችኋል፡፡ የፈጣሪ እገዛ የሌለበት የነፃነት ትግል ፍሬው ለሕዝብ አይደርስም – እጫፍ ይቀራል፡፡ እነመለስ ዜናዊ ትግላቸው ለራሳቸው እንጂ ለሕዝብ አልነበረም፡፡ ፈጣሪን የማያውቅ ሕዝብን አያውቅም፡፡ እንዴት ተድርጎ?

ሀገርና ሕዝብ ሲባል ደግሞ በየዘፈኑ እንደምንሰማው ወንዝና ሸንተረሩ አይደለም፡፡ እሱ እሱ ነገር ለማሳመርና ተቀባይነትን ለማግኘት እንጂ ሀገር ማለት የመሬት ቅርጽና የውኃ አካላት ማለት ሣይሆን ሕዝቧ ማለት ነው፡፡ እናም ሕዝቡን ውደዱት፡፡ ይህን በተተካኪ መንግሥታዊ ዱላዎች እየተቀጠቀጠ ያለ ሕዝብ ከልብ አፍቅሩት፡፡ የእያንዳንዱ ዜጋ ዕንባና ሰቆቃ የእያንዳንዳችን እንደሆነ ያህል ካልተሰማን የነፃነት ታጋይ ልንሆን አንችልም፡፡ የክርስትና ሃይማኖት የማዕዘን ራስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ “የሚወደኝ ቢኖር መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ” እንዳለው የሕዝቡን መከራና ስቃይ እንደራሳችን ቆጥረን ጎንበስ ብለን ዕንባውን እናብስለት፡፡ ከማስመሰልና ከታይታ ተቆጥበን ቅድመ ሁኔታ በሌለው ፍቅር ሁላችን እንተሳሰር፤ የነፃነት ታጋዮች የሆናችሁ ሁሉ እርስ በርሳችሁም ተሳሰሩ፡፡ ያኔ ሕዝቡም ከአንጀት ይወዳችኋል፡፡ የምሬን ነው – አንዳችን ለአንዳችን ልባዊ ፍቅር ይኑረን፤ ለበጣና ማስመሰል ቅር፡፡ በሀብት፣ በገንዘብ፣ በትምህርት፣ በዕድሜ፣ በሃይማኖት፣ በዘውግ፣ በጤንነት ፣ በፆታ፣ በመልክና በቁመት … ልንለያይ እንችላለን፤ ተፈጥሯዊም ነው፡፡ ግን ሁላችንም ሰዎች ነን፡፡ ቢቻል በሰውነታችን ያ ቢከብደን ደግሞ ቢያንስ በአንዲት ሀገር የጋራ ባለቤትነታችን እርስ በርስ እንዋደድ፡፡ የማያውቀን ፈረንጅ ልብሱን ከገላው እያወለቀ፣ ምግቡን ከጉሮሮው እየነጠቀ እኛን በዘር በቀለም የማንገናኘውን የዓለም ዜጎች በሰብኣዊነት ሲረዳን እኛ የአንዲት ሀገር ዜጎች ካለበቂ ምክንያት የምንነካከስበትና ጀርባ የምንዟዟርበት ሁኔታ ሊኖር ፈጽሞ አይገባም፡፡ ቂምና ጥላቻን ከማስወገዱ በተጓዳኝ ያለን ለሌለን እንርዳ፡፡ ስንፋቀር አንዱ የሁሉም፣ ሁሉም የአንዱ ይሆናል፡፡ ስንፋቀር ተዝቆ የማያልቅ በረከት(ረድኤት ማለቴ ነው) ይኖረናል፡፡ ስንፋቀር አንጨካከንም፤ ፍቅር ሁሉንም የክፋት ምንጭ የሚያደርቅ ከእውነተኛው ፈጣሪ የምትገኝ መለኮታዊ ማርከሻ ናት፡፡ በምንፋቀር ጊዜ ለመገዳደል የሚሮጡ እግሮችና ለመቦጫጨቅ የሚያሰፈስፉ እጆች ለመረዳዳትና ለመጎራረስ ይሽቀዳደማሉ፡፡ ያኔ ሰይጣንን ቀንዱን መትተን  አሸነፍነው ማለት ነው፡፡ ሰይጣን መሸነፉን ሲያውቅ ተስፋ ቆርጦ ይተወናል፡፡ ያኔ ለኛ ቀርቶ ለሌላ የሚተርፍ ሀብት ወይም እርዚቅ ይኖረናል፤ ልብ ባንል ወይም ልብ  ብንልም ዕድሉን ስላጣነው እንጂ እኛ ኢትዮጵያውያን ከእግራችን ሥር ወርቅና አልማዝ ቀብረን እላዩ ላይ ቆመን የምንቧቀስና በማን አባት ገደል ገባ የጠላቶቻችን መስተፃልዓዊ ድግምት የምንገዳደል ምሥኪን ፍጡራን ነን፤ ስንቧቀስም እየተዋጋንና ዕየተራብን በሁለት መንገድ እናልቃለን – በጦርነቱና በርሀቡ፡፡ በማከያው ግን ለጥቂት መሠሪዎች የሀብት መቆናጠጫ እንደሆን እንኖራለን – እሞኝ ደጃፍ  ሁሌም ሞፈር እንደተቆረጠ የዓለም ፍጻሜ ተቃረበ! ጥያቄው “በዚሁ እንቀጥል ወይንስ ካለፈው ተምረን አስተሳሰባችንን በማዘመን እንሻሻል?” የሚል ነው፡፡ ልብ እንበል – ፍቅር በሌለበት የገበታ ማዕድ ባዶ ነው፡፡ ባዶ ማዕድ ይዘህ ደግሞ ስደትንና በተንኮል መጠማመድን፣ መመቀኛኘትንና መፋጀትንም አታቆምም፡፡ ስለሆነም ታጋዮች በአዲስ መንፈስ ታግላችሁ አታግሉን፡፡  ተመሳሳይ አረንቋ ውስጥ ደግመን እንዳንዘፈቅ ትታደጉን ዘንድ ኅሊናዊና መንፈሣዊ ዕድገታችሁ እንደወያኔዎቹ ቀጭጮ እንዳይቀር ተግታችሁ ሥሩ፡፡ ሁሉም ነገር አላፊ ነው – ሀብትም ሥልጣንም ዝናም … በአንዴም ባይሆን በሂደት ይንኮታኮትና ሁሉም ነገር ወደነበረበት ይመለሳል – ወደባዶ፡፡ የማያልፈው ግን መጥፎና ደግ ታሪክ ነው፡፡ ምርጫው የራሳችን ነው፡፡ ደግ ታሪክ ሠርቶ በትውልድ መወደስ ወይም እንደነመንግሥቱ ኃ/ማርያምና መለስ ዜናዊ ዘግናኝ ታሪክ ሠርቶ በትውልድ መወቀስ፡፡

በዓለም ዙሪያ የተበተንን ኢትዮጵያውያንም ሆን በሀገር ውስጥ የምትገኙ ሁሉ፤

ኢራቅን፣ ሶማሊያን፣ አፍጋኒስታንን፣ ዩጎዝላቪያን፣ ሩዋንዳን፣ ሊቢያን፣ ሦሪያን፣ የመንን፣… የሚያስመሰግን አስከፊ ገጽታ በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ኢትዮጵያ እየገሠገሠ ነው፡፡ ይህም የሆነው ጆሮ የሌለው የወያኔ ጉጅሌ ላለፉት ጥቂት የማይባሉ አሠርት ዓመታት ሕዝቡ ራሱና የኢትዮጵያን ታሪክ የሚያውቁ ጠበብት የሚነግሩትን  (በቂም በቀልና ጥላቻ በመለከፉ ሣቢያ) በማወቅም ይሁን ባለማወቅ መስማት ባለመፈለጉ ይልቁንም ይህ አስከፊ ገጽታ እንዲከሰት ጠንክሮ በመሥራቱ ነው፡፡ ወያኔዎች ሀገራዊ ፍቅርና ስሜት ይቅርና ቅንጣት ሰብኣዊ ስሜት ቢኖራቸው ኖሮ ይህችን ሀገር ለማዳን ዋናው ቁልፍ በእጃቸው ነበር፡፡ ግን ተፈጥሮን ተመክሮ ስለማይመልሰው የዚህች ሀገር ዕጣ ፋንታ በፈጣሪና በጥቂት ቅን ልጆቿ መዳፍ ሥር ነው፡፡ ለሥልጣን ያሰፈሰፈው(አራት ኪሎ ያለችው አንዲት ወንበር ብቻ መሆኗን የዘነጉ ይመስላሉ) የግሪሣ መንጋ ጥቂት ባልሆበት፣ የዘረኝነት አዶ ከብሬ በጦዘበትና ያዙኝ ልቀቁኝ በሚልበት፣ ድህነቱና የኑሮ ውድነቱ ሰማየ ሰማያትን አልፎ የትዬለሌ በተወነጨፈበት፣ ሙስናው እግር አውጥቶ ከታች እስከላይ በተንሠራፋበት፣ አላግባብ ብልጽናው መረን ለቅቆ  ከዜሮ ሣንቲም ተነስቶ በቅጽበት ሚሊዮኔር በሚኮንበት፣ የነጋዴው ስግብግብነትና አለልክ ማትረፍ ቅጥ ባጣበት፣ ኤቢሲዲን በቅጡ ያልለየው ምድረ ማይም ዘረኛና አሽቃባጭ ባንዳ ሁላ ቢሮክራሲውንና የጦርና የፀጥታ ተቋማትን ባጥለቀለቀበት፣ አእምሮ ወደሆድ ወርዶ ሆድ ወደራስ ወጥቶ በተሰቀለበትና እነሆድ አምላኩ በነገሡበት … እጅግ አስጨናቂ ሁኔታ ላይ እንገኛለንና ሁላችንም ጊዜ ሰጥተን በጥሞና እንጸልይ፡፡ ችግራችን በጦር ብቻ እንደማይፈታ እንረዳ፡፡ ችግራችን በጩኸትና በጦር ቢፈታ ኖሮ ከ66 እና ከ83 ዓመተ ምሕረቶች አንድኛቸው በቂያችን ነበሩ፡፡ ስለዚህ የጎደለን ቅመም አለ ማለት ነው፡፡ እንደኔ ያ ጉድለት ጸሎት ነው – በነገራችን ላይ በምንም ዓይነት ፈጣሪ አለማመንን ወይም የተለያዬ እምነት መከተልን እንደማልቃወም ይታወቅልኝ፤ ሊከበር የሚገባው መብት ነው፤ (ኢ-አማኒ/ኤቲይስት ማለት ግን በኅሊናዊ የዕውቀት ሀብቱ የሚመራና ማኅበራዊ የአብሮነት ዕሤቶችን የሚያከብር ጥንቁቅ እንጂ እንደልቡ ፈንጣዥ ሊሆን እንደማይገባው አምናለሁ) ፡፡

በሀገር ቤት ቤተ ክርስቲያንና መስጂድ ለወያኔ ስላደሩ ጸሎት ማድረግ የሚቻል አይመስለኝም፤ ለወያኔ ባደረ ቤተ አምልኮ ተጸልዮ ደግሞ ጸሎቱ እንኳንስ ጽርሃ አርያምና መንበረ ፀባዖት ሊደርስ ከአፀደ ቤተ ክርስቲያን ጣሪያና ኮርኒስም አያልፍም፤ እኛ ልንቀልድ እንችላለን፡፡ ፈጣሪ ግን ለቀልድ ጊዜና ፍላጎት ያለው አይመስለኝም፡፡ እየተዋወቅን መተናነቁ ልትዝብት ይዳርጋል እንጂ አይጠቅምምም፡፡ በየምንኖርባቸው የስደት ሀገሮችም ሆነ በሀገር ቤት ካሉ  የቤተ አምልኮት አገልጋዮች ጋር አብረን እንውላለን፤ እናመሻለን፡፡ ጳጳሣትንና ሼሆችንም መንፈሣዊ ወሥጋዊ ድርጊቶቻቸውን እንከታተላለን፡፡ ያውቁናል – እናውቃቸውማለን፡፡ ለሥጋው ምቾት አድሮ የግፍ አገዛዝን ባለመቃወም ከዚያም ባለፈ ለጸረ-ሃይማኖቱ ዲያብሎሣዊ ኃይል መሣሪያ በመሆን ናቡከደነፆራዊው አገዛዝ እንዲቀጥል ማድረግ የነቅዱስ ጳውሎስንና የመጥምቁ ዮሐንስን ሰማዕትነት ማርከስ ነው፡፡ ወደ ዝርዝር ሳንገባ በነዚህ ዓይነት የሃይማኖት መሪዎች የሚድን ሀገርም ሆነ ሕዝብ እንደሌለ በመጠቆም ብቻ የሀገራችንን መራር እውነት ማስገንዘብ እወዳለሁ፡፡ ስለዚህ በበኩሌ በዚያ በኩል ብዙም ተስፋ አላደርግም፡፡ እንደኔው በውጪ ያላችሁት ካህናትና ምዕመናን ይልቁናስ በርቱ – ከመሰል ሃሜታ ንጹሕ ከሆናችሁ፡፡(መጸለይ ያለበት ንጹሕ ሰው ብቻ ነው እያልኩ እንዳልሆነ ግን ይታወቅልኝ! በመሠረቱ ማንም ይሁን ማን ስህተትን መሳሳት ሰውኛ ነው – በስህተት ቆርቦ ስህተትን ባህል ማድረግ ግን እንኳንስ ከሃይማኖት መሪ ከተራ ምዕመንም አይጠበቅም… ኣ! ዝርዝር ኪስ ባይቀድ ኖሮ…፡፡)

በሀገር ቤት የቡድን ጸሎት በቤተ አምልኮዎች ካልተፈቀደ ሌላው አማራጭ በየግል በዓትና በቤትም ውስጥ ጸሎትን ማድረስ ነው፡፡ ያን የሚከለክል የለም፤ አይችሉምም፡፡ ግን ከልብ እንጸልይ፡፡ ስንጸልይ እንደልማዳዊው የአብዛኞቻችን ጸሎት “እመብርሃን፣ የእገሌን ነገር እስከዚህን ቀን ድረስ ካላሣየሽኝ ደጅሽን አልረግጥም!” ዓይነት ሣይሆን ከዚህ የተለዬ ሊሆን ይገባል፡፡ ከፍ ሲል በዘወርዋራ መንገድ ለመጠቆም እንደሞከርኩት ስንጸልይ ፈጣሪ እንዲሰማን የኛን ደጅ ቀድመን አጽድርተን መሆን አለበት፤ ፈጣሪ የሚሰማው ጸሎት ከንጹሕ ልብ፣ በንስሃ ከታጠበና ይቅርባይነትን ከተላበሰ ንጹሕ ሰውነት የሚወጣን እንጂ ከአስመሳይ አንደበት የሚንበለበልን ልፋፌ ጽድቅ እንዳልሆነ መረዳት ይገባል፤ ዋናው በጸሎቱ ውስጥ ያለው የቃላት ማማር ሣይሆን የልብ ንጽሕና ነው – የጸሎት ጎልዳፋ የለውም፡፡ ከእንስሳት ውስጥ እንኳን የሚጸልዩ እንዳሉ ይነገራል፡፡ ጸሎታችን ከልብ ከሆነና እንዴት እንደሚጸለይ ካወቅን፣ ምን መጠየቅ እንዳለብንና እንዴት መጠየቅ እንዳለብን ከተረዳን ፈጣሪ መልስ ለመስጠት ደቂቃ አይፈጅበትም፡፡ ጸሎትን ለማድረስም ሀገርን ከጫፍ እጫፍ ማካለል አይጠበቅብንም – መኝታ ቤትህ ሆነህ የሚሰማህ አምላክ ግሼንና አክሱም ጽዮን ተጉዘህ ባይሰማህ አትታዘበው( ሂድ/አትሂድ እያልኩ ሣይሆን ዋናውና ወሳኙ እግርህ ወይም አፍህ ሣይሆን ልብህ ነው እያልኩ ነው፤ ወንድሜ – የማታውቀውን እየነገርኩህ አይደለም – የተማርኩትን እያስታወስኩህ እንጂ)፡፡

በሌላም በኩል  ችግሩ የሚመስኝ የአጠያየቅ ጉዳይ  ነው፡፡ “ሄይ! ሰውዬ፣ አንድ ሺህ ብር የማትቦጭቅልኝ ምናባህ ቆርጦህ ነው!” ብለህ አንዱን ሀብታም ነጋዴ ብትለምነው – ይህ መለመን ነው እንዴ እሚባል ለነገሩ – ማለትም ብታፋጥጠው መስጠቱ ከባድ ላይንበት ቢችልም አጠያየቅህ ስለማያምር ግና ድምቡሎ የሚያቀምስህ አይመስለኝም፡፡ በዘበኛው ያባርርሃል ምናልባት፡፡ ስለጸሎት አደራረስም ብዙዎቻችን ጥቂት ማንበብ የሚኖርብን ይመስለኛል፡፡ ወይም አንዱ አንባቢ በራሱ ጊዜ ይመለስበትና ያስነብበን፡፡

ለማንኛውም ከሃያ ሦስት ዓመታት በኋላ – በደርግ መጨረሻ እንደመጣሁ – በወያኔም መጨረሻ ብቅ ብያለሁና በተለይ በዚያው የእሁድ ማለዳ የታምራት አሰፋ(ነ.ይ) ቆንጆ የንባብ አቀራረብ ትከታተሉኝ ለነበራችሁ ወገኖቼ  የናፍቆት ሰላምታየ በያላችሁበት ይድረሳችሁ(በተለይ የአዲስ ዘመኑ ወዳጄ እምሩ ወርቁ ባለህበት ሰላም ልበልህ)፡፡ እንደእግዚአብሔር ፈቃድ በስፋት የምንገናኝበት ዘመን መምጣቱ አይቀርም፡፡ ጸሎታችንን ሳናቋጥ ማድረሳችንን ግን አንርሣ፡፡ በየሃይማኖታችን እንጸልይ፡፡ ፍቅር ይኑረን እንጂ የሃይማኖት መለያየት በጭራሽ አያጣላንም – “አንቺም ባይማኖትሽ እኔም ባይማኖቴ” ብሏል ተወዳጁ አቀንቃኝ ቴዲ አፍሮ፡፡ የመተዛዘንና የመዋደድ በችግራችንም ጊዜ የመድረስ ቆንጆ ባህላችን እየደበዘዘ የመጣ ይመስለኛልና እንሰብበት፡፡ ከፍ ሲል ለማስታወስ እንደሞከርኩት ሀገርን ስናፈቅር መሬቱን [ብቻ] ሣይሆን ወገናችንን ዜጋውን መሆን አለበትና እንዲያው ለምሣሌ ሰው አንከላፍቶት ቢወድቅ “እኔን! ተጎዳህ? አይዞህ ወንድማለም/እህታለም” በማለት በሚያስፈልገውና አቅማችን በቻለ እንርዳው፤ እናጽናናውም – አየህ፣ አንተን እንደዚህ ቢሉህ ደስ አይልህም? አዎ፣ የቻይናውን ፈላስፋ የኮንፊሼስን ብሂል እንከተላት – “ሰዎች ባንተ ላይ እንዲያደርጉብህ የማትፈልገውን ነገር አንተም በነሱ ላይ አታደርግ”፡፡ ካልተረዳዳን፣ ካልተነፋፈቅን፣ እንደቀደመው ባህላችን በመዋደድና በመተሳሰብ አዳራሽ ካልተመላለስን የአንዲት ሀገር ዜጎች መሆናችን ጥቅሙ ታዲያ እምኑ ላይ ነው? የፈረንጆቹ ዘግቶ በላው “ባህል” ይቅርብን፡፡ ስንነግድም ተያይተን እንነግድ፡፡ ከአፍኣዊው ይልቅ ወደ ተግባራዊው የፍቅርና የመዋደድ መግለጫዎች በቶሎ እንዙር፡፡ እየጠፋን ስለሆነ ቆም ብለን እናስብ፡፡ የጥንቱን ፍቅርና መተሳሰብ እንዲመልስልን አላህን/እግዜርን በጸሎት እንጨቅጭቀው፡፡ እነዚህ የፍቅር መቀሶች ፈጣሪ እንዲገላግለንም ዘወትር በዱኣ እንነዝንዘው፡፡  የሰው እንጂ ሁለት የፈጣሪ ጆሮ ቁጥር ሥፍር የለውምና ይሰማናል – ከተለያየን ግን አይሰማንም፡፡ ደጋግሜ እንደምለው ሃይማኖትን የጠብ መንስኤ እንዳናደርግ እንጠንቀቅ፡፡ በማንም ሃይማኖት ማንም ጣልቃ አይግባ፡፡ የሚድነውንም ሆነ የሚጠፋውን የሚያውቅ አንድ ብቸኛ አካል ፈጣሪ ስለሆነ በመሰለን መንገድ ብናመልከው ተግባራችን መልካም እስከሆነ ድረስ በቀኖናና በመንገድ መለያየት ምክንያት ብንጣላ ግብዝነት ይመስለኛል፡፡ ጠበቃና ደም መላሽ የማያስፈልገው የፍጡራን ሁሉ ፈጣሪ ራሱ ስለራሱ ጥብቅና መቆም አያቅተውምና የማንም ሃይማኖት ተከታይ በማንም ሃይማኖት ጣልቃ ገብቶ ረቂቄን መንፈስና የሕይወት መፍለቂያ የሆነውን ኃያል ኑባሬ(Being) የሰውኛ ባሕርይ በማላበስ አቦካቶ ለመሆን አይዳዳ – በዚህን ዓይነቱ ቂልነት ፈጣሪ ራሱ ከትከት ብሎ ሣይስቅ የሚቀር አይመስለኝም፡፡ እሱ ስለራሱ ያውቅበታል፡፡ ይልቁንስ ስለራሳችን እንጨነቅ፤ ማንም እንሁን፣ ምንም ይኑረን ብዙ የሚያስጨንቁን ነገሮች ግን አሉ – የደስታና የሀዘን ምንጮች ደግሞ ገንዘብ ማግኘትና ማጣት ብቻ እንዳልሆኑ ሁሉም ያውቃል፡፡  መልካም የነፃነት ዘመን ያድርግልን፡፡እኔም ወደ ሀገሬ እንድገባ ጸልዩልኝ፡፡ ስደት ሰልችቶኛል፡፡ የሰው ሀገር ኑሮ ለተወሰነ ጊዜ እንጂ እስከወዲያኛው ሲሆን መፈጠርን ያስጠላል፡፡ ሰላም፡፡

 

ለማንኛውም ገምቢ አስተያየት፡- khartoum71@gmail.com

 

 

The post ሀገራዊ የጸሎት ጥሪ -ሰሎሞን ንጉሡ (ከሱዳን) appeared first on Zehabesha Amharic.

Viewing all 2784 articles
Browse latest View live


<script src="https://jsc.adskeeper.com/r/s/rssing.com.1596347.js" async> </script>